Tuesday, October 9, 2012

የአሸዋና የድንጋይ ጽሑፍ


አንድ ወዳጄ ከላከልኝ መጽሐፍ ላይ ይህንን አነበብኩ፡፡
ሁለት እጅግ የሚዋደዱ ጓደኛሞች ነበሩ፡፡ የትም ቦታ ሲሄዱ አይለያዩም ነበር፡፡ እንደለመዱትም አብረው ወደ አንድ ሀገር በእግራቸው ይጓዙ ነበር፡፡ መንገድ በዝምታ ይረዝማልና እየተጨዋወቱ ነበር የሚጓዙት፡፡ አንዳንድ ጨዋታ በድካም መንፈስ ከተጫወቱት ለጠብ ይዳርጋል፡፡ ድካም የትዕግሥትን ዐቅም ይፈታተናልና፡፡ ለዚህ ነው የሀገሬ ሰው የድካም ና የዕረፍት ጨዋታ ለየቅል ነው የሚለው፡፡
እነዚህም ወዳጆች የዕረፍቱን ጨዋታ ለድካም አምጥተውት ኖሮ አለመግባባት ተፈጠረ፡፡ አንደኛው ታድያ ብልጭ ሲልበት በቦክስ ድንፉጭ የማድረግ ልማድ ነበረበትና በጓደኛው ላይ ታይሰን የማይችለው ቡጢ ሠነዘረበት፡፡ ቡጢውን የቀመሰው ጓደኛም የፊቱን ደም ጠርጎ፣ እያበጠ የሄደውን ግንባሩን ዳሰሰው፡፡ እጅግም አዘነና መንገዱን አቋርጦ በበረሃው አሸዋ ላይ ተቀመጠ፡፡ አንገቱን ግራና ቀኝ እያወዛወዘ ኀዘኑን ገለጠ፡፡ ንዴቱ ከውስጥ እንደ ልቅሶ ቤት ሽሮ ቡልቅ ቡልቅ ይልበት ጀመር፡፡ መልሰህ ‹በለው፣ በለው› እያለ ወንድነቱ ያስቸግረው ነበር፡፡
 ያን ጊዜ ዓይኑን አማተረና አንዳች እንጨት ፈልጎ አገኘ፡፡ በአሸዋም ላይ ‹‹ዛሬ እጅግ የምወድደው ወዳጄ ግንባሬ ላይ በቡጢ መታኝ›› ብሎ ጻፈ፡፡ ቀና ብሎ ሲያይም ጓደኛው ጥሎት በመሄድ ላይ ነበር፡፡ እርሱም ያንን ጽሑፍ በአሸዋው ላይ ትቶት ጓደኛውን ተከትሎት ሄደ፡፡
ብልጭ ብሎበት የተማታው ጓደኛው እጅግ ተፀፀተ፡፡ በጓደኛው እግር ላይ ወድቆም ይቅርታ ጠየቀው፡፡ የተመ ታውም ይቅርታውን ተቀብሎ አብሮት ተጓዘ፡፡ የነበረውን ሁሉ ረስተው ደስ የሚል ጨዋታ እየተጫወቱ ተጓዙ፡፡ በዚህ መንገዳቸው ላይ አንድ ወንዝ ነበረ፡፡ በአሸዋውና በሙቀቱ የተነሣ ተዳክመውና በላብም ተጠምቀው ስለነበር ልብሶቻቸውን አውልቀው ወደ ወንዙ ገቡ፡፡ ወዲያና ወዲህ እየዋኙ ድካማቸውን በመርሳት ላይ ሳሉ ያ በቡጢ የተመታውን ጓደኛ ወንዙ ነጥቆ ይዞት ሄደ፡፡
ሁኔታውን ያየው ሌላው ጓደኛውም ያለ የሌለ ጉልበቱንና ብልሃቱን ተጠቅሞ እየዋኘ ጓደኛውን በወንዝ ከመወሰድ ታደገው፡፡ በአንድ እጁ እየሳበም ወደ ዳር አደረሰው፡፡ ያኛው ጓደኛም ከተወሰደበት ወንዝ ከወጣ በኋላ በዓይኑ ማተረ፡፡ እነሆም አንድ ድንጋይ አገኘ፡፡ ቀጥሎም አንድ ባልጩት አመጣ፡፡
አሸዋው ላይ ተቀምጦ በዚያ ባልጩት ያንን ድንጋይ መቀጥቀጥ ጀመረ፡፡ ለብዙ ሰዓታት ከቀጠቀጠ በኋላ በድንጋዩ ላይ ‹‹ዛሬ እጅግ የምወደው ጓደኛዬ ሕይወቴን ከሞት ታደጋት›› ብሎ ጻፈ፡፡
አስቀድሞ የተማታው፣ በኋላም ጓደኛውን ያተረፈው ጓደኛም በሆነው ነገር ሁሉ ተገረመ፡፡ ጓደኛውንም እንዲህ ሲል ጠየቀው ‹‹ ቅድም ግንባርህን በቡጢ ስመታህ፡- የምወድደው ጓደኛዬ ግንባሬን በቡጢ መታኝ ብለህ በአሸዋ ላይ ጻፍክ፡፡ አሁን ግን በወንዙ ከመወሰድ ሳድንህ፡- የምወድደው ጓደኛዬ ሕይወቴን ከሞት ታደጋት ብለህ በድንጋይ ላይ ጻፍክ፡፡ ያኛውን በሚጠፋ አሸዋ ላይ፣ ይህንን ግን በማይጠፋ ድንጋይ ላይ ጻፍከው፡፡ ለምን?››
ጓደኛውም መለሰ፡፡ ‹‹ቅድም ጉዳት አደረስክብኝ፤ እኔም አዘንኩብህ፣ ተቀየምኩብህም፤ ተሰምቶኛል፤ ተናድጃለሁም፡፡ ነገር ግን የእኔና ያንተ ወዳጅነት እንዲቀጥል ከተፈለገ መርሳት መቻል አለብኝ፡፡ ስለዚህም በአሸዋ ላይ ጻፍኩት፡፡ አየህ ሰዎች በእኛ ላይ ክፉ ሲያደርሱብን የይቅርታ ነፋስ ጠርጎ ሊወስደው ይችል ዘንድ በአሸዋ ላይ ብንጽፈው መልካም ነው፡፡
‹‹በኋላ ሕይወቴን ከሞት ስትታደጋት ግን ዘወትር እንዳስታውሰው ስለምፈልግ በማይጠፋ ድንጋይ ላይ ጻፍኩት፡፡ ሰዎች የሚያደርጉልንን በጎ ነገር ሁሉ ማንም ሊያጠፋው በማይችል ልብ ላይ መጻፍ አለብን፡፡ ሰውን መውደድ የምትችለው በጎ ነገሩን አዘውትረህ ካስታወስክ ብቻ ነው፡፡››
ጓደኛው አቀፈው፡፡
‹የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳ› የሚል አባባል አለ፡፡ ልክ ነው፡፡ አንዱ በሌላው ላይ የሚያደርገውን ግፍና መከራ መርሳት ከባድ ይሆናል፡፡ አንዳንዱ ሰው ደግሞ የሚያደርሰው ጉዳት እንዳይረሳ አድርጎ የሚፈጽመው ነውና ለመርሳት አስቸጋሪ ይሆናል፡፡
ቢሆንም ግን ግፍንና በደልን እያስታወሱ መኖር ተበዳዩን ይበልጥ ይጎዳዋል፡፡ ምክንያቱም የደረሰብን በደልን ይበልጥ ባስታወስነው ቁጥር ጥላቻችን ይበልጥ እየጨመረ ይመጣልና፡፡ የደረሱብንን ነገሮች ብቻቸውን ልናስታ ውሳቸው አንችልም፡፡ ከዚያ በፊት ከነበሩትና ከዚያም በኋላ ከተፈጸሙት ነገሮች ጋር እናያይዛቸዋለን፡፡ እንተነትና ቸዋለን፣ የራሳችንንም ሥዕል እንሰጣቸዋለን፡፡ ‹እባብ ያየ በልጥ ይደነግጣል› የሚለው አባባል በአንድ ወቅት የተፈጸመ ነገር በተፈጸመበት ሰው ላይ ጥሎት የሚሄደውን ጠባሳ የሚያሳየ ነው፡፡
ያለፈን በደል አዘውትሮ ማሰብ ፈጻሚውን ለመበቀል ያለንን ፍላጎት ይጨምረዋል፡፡ ያንን ሰው ወይም አካል እንከታተለዋለን፡፡ ዐውቀንም ይሁን ሳናውቀው ስለዚያ ሰው ወይም አካል መስማት እንፈልጋለን፡፡ ያ ሰው ወይም አካል የሚያደርገው ክፉ ነገር ብቻ ሳይሆን በጎ ነገሩ ራሱ ያበሳጨናል፡፡ ወድቆና ተንኮታኩቶ፣ ደኽይቶና ተጎሳቁሎ የማየት ፍላጎት ያድርብናል፡፡ የኛን ትክክለኛነት በዚያ ሰው ውድቀት ለማረጋገጥ እንመኛለን፡፡ የሰውየው ውድቀት  ተፈጥሯዊውን መንገድ ተከትሎ የማይመጣ ከሆነ እኛው ራሳችን ወደ መፈጸሙ እናመራለን፡፡
በአንድ ወቅት የተፈጸመ ነገር ረዥሙን የሕይወታችን ጉዞ የሚያበላሽበት ጊዜም አለ፡፡ ጉዳዩ የተፈጸመው አንድ ጊዜ ሆኖ ሳለ እንደ ወር በዓል በኅሊናችን ተደጋግሞ እየመጣ ዘላቂውን ሕይወታችንን ይበጠብጠዋል፡፡ ሌላው ቀርቶ ሌሎችን ሰዎችም በእነዚያ ክፉ አድራጊ ሰዎች ዓይን ማየትም እንቀጥላለን፡፡ ‹‹አይ ወንዶች፣ አይ ሴቶች›› የሚሉ አባባሎች ያለፉ ግንኙነቶቻቸው በተበላሹ ሰዎች የተፈጠሩ ሳይሆኑ አይቀርም፡፡ አንዳንዶችም ያኛው ጠባሳ እንዳይጠፋ አድርገው በዐለት ላይ ስለጻፉት ከዚያ ጋር የሚመሳሰሉ ገጠመኞች ሲያጋጥሟቸው ያ ነገር ተመልሶ እንዳይመጣ በመፍራት የጀመሩትን ያቆሙታል፡፡
ያለፈን ክፉ ነገር ማስታወስ ውሳጣዊ ሰላማችንንም ያናጋዋል፡፡ ሰላም ከውስጥ ወደ ውጭ እንጂ ከውጭ ወደ ውስጥ አይገባም፡፡ ሰላማዊ ልቡና በሌለበት ሰላም ተዘርቶ አይበቅልም፡፡ ድስቱ ውስጥ ጥቂትም ብትሆን መርዝ እስካለች ድረስ የሚገባበት ማንኛውም ዓይነት የወጥ እህል መበላሸቱ የማይቀር ነው፡፡ ከውጭ የሚገባው የወጥ እህል ንጹሕ ቢሆን እንኳን የድስቱ ውስጥ ንጹሕ እስካልሆነ ድረስ እርሾ እየሆነ ይበክለዋል፡፡ አንድ መቶ ኩንታል ዱቄትን እፍኝ የምትሞላ እርሾ ታቦካዋለች፡፡ በልብ ውስጥ የተቀመጠች የቂም ቁርሾም የሚመጡትን በጎ ነገሮች ሁሉ ስታቦካቸው ትኖራለች፡፡ ይህ ደግሞ ውሳጣዊ ሰላማችንን ያናጋዋል፡፡ ያ ደግሞ ተናዳጅ፣ ነጭናጫና ማንም ሳይረብሸን የምንረብሽ ያደርገናል፡፡
የደረሱብንን ነገሮች በአሸዋ ላይ መጻፍ ያለብን ያደረሱት ሰዎች ትክክል ስለሆኑ አይደለም፡፡ በደልን ለማበረታ ታትም አይደለም፡፡ ለዘብተኛ ለመሆንም አይደለም፡፡ ለይቅርታና ለዕርቅ ዕድል ለመስጠት እንጂ፡፡  ለሌላም ሲባል አይደለም ለራስ ሲባል እንጂ፡፡
አንድ ሊቅ ‹‹ይቅርታ መጠየቅ ሁልጊዜም ጥፋተኛነትን አያመለክትም፣ ለወዳጅነት ስንል መሥዋዕትነት መክፈልን እንጂ፤ እኔ ትክክል ሆኜ ወዳጅነታችን ከሚጠፋ፣ ይቅርታ ጠይቄ ወዳጅነታችን ይቀጥል ብሎ ማሰብን እንጂ›› ብሎ ነበር፡፡
ክፉ አጋጣሚዎችን መርሳት ለመርሳት ስለተፈለገ ብቻ የሚመጣ አይደለም፡፡ የመርሳት ችሎታንም ይጠይቃል፡፡ ይህንን ለማድረግ ደግሞ የመጀመርያው ርምጃ ለመርሳት መወሰን ነው፡፡ ለመርሳት መወሰን ለመርሳት ለመቻል በር ይከፍታል እንጂ ለመርሳት አያስችልም፡፡ ለመርሳት ለመቻል ቀጣዩ ምእራፍ የልብ ሕመምን ማውጣት ነው፡፡ በመጻፍ፣ በመናዘዝ፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር በማውራት፣ ለፈጣሪ በመስጠት፣ አልቅሶ በማውጣት ያለፈውን ክፉ ገጠመኝ የመሻርያ መንገድ መተለም ያስፈልጋል፡፡
ሦስተኛው ምዕራፍ ደግሞ ያንን ነገር ከሚያስታውሱ ነገሮች መራቅና መቆጠብ ነው፡፡ የሚያስታውሱ ፎቶዎች፣ ዕቃዎች፣ ግንኙነቶች፣ ዜማዎች፣ ቦታዎችና ሌሎችንም ለተወሰነ ጊዜ ማራቅ ይገባል፡፡ እነዚህ ነገሮች ለመርሳት እንድንችል መንገዱን ያመቻቹልናል፡፡ የልቡናችን ቁስልም ከንክኪ ነጻ ሆኖ እንዲሽር ዕድል ይሰጠዋል፡፡
አንዳንዴ ያለፈውን ጠባሳ የሚያስታውሱ ገጠመኞችና ትውስታዎች ሲመጡ ወዲያውኑ ከዚያ የሚያላቅቁ ርምጃዎችን መውሰድ ያስፈልጋል፡፡ ለእነዚህ ክስተቶች ረዘም ያለ ጊዜ መስጠት ነገሩ ወደ ውስጣችን ጠልቆ እንዲገባና ለመርሳት የምንፈልገውንም ነገር እንዳንረሳው ያደርጋል፡፡
ከትናንት ወጥቶ ነገ ላይ ማተኮር ክፉ ገጠመኝን እንድንረሳውና ከተቀየድንበት የትናንት አዙሪት እንድንወጣ ያደርገናል፡፡ የክፉ ገጠመኝ አንዱ ችግር ሕይወታችን ወደ ትናንት ብቻ እንድትሄድ ማድረጉ ነው፡፡ ትናንትን መቀየር አይቻልም፡፡ በትናንቱ ላይም ምንም መድረግ አይቻልም፡፡ በነገ ላይ ግን ብዙ ነገር ማድረግ ይቻላል፡፡ ትናንትን ተምረንበት እንተወው፣ በእጃችን ላይ ባለው ነገም እንሥራ፡፡ ስለትናንት ብቻ ማሰብ ግን ትናንትንም ነገንም ማጣት ይሆናል፡፡
ለዚህ ሁሉ አንድ ነገር አስቀድሞ ወሳኝ ነው፡፡ በሕይወታችን ምዕራፎች ሁሉ ክፉ ገጠመኞችንን በአሸዋ ላይ፣ በጎዎችንም በዐለት ላይ እየጻፍን መቀጠል፡፡
ላስቬጋስ፣ ኔቫዳ
 © ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነውና በተመሳሳይ ኅትመት ባታወጡት ይመረጣል

32 comments:

 1. Thanks for ur post.But difficult for me. Could I able to forgive & forget all his deeds? I don't know. why God is patient on such kind of males who destroy famale morals repeatedly? A person who claim as if he is christian.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ms. Anonymous october 9 9:56 p.m, what if you hurted the feeling of your partner the same way he hurted your feeling. Honesty is the best policy to get the real reason why your partner is acting bad.What I mean is that you should stop keeping secrets, you should have courage to tell him the truth then you two will at least be good friends. If you lied to him twice, you should tell him that you lied him before he discovered it by himself.If so ,he will treat you as a liar and he could treat you as a useless creature,because this feeling is sown by you first and you shouldn't be surprised in ripping the same thing.If you cheated him ,tell him that you did so, you two will at least be friends.So better to see oneself before judging others,then we will have the strength to forgive.

   Delete
  2. Dear Anony
   Thanks for ur advice.But it is not as u described. Being innocent is not always a guarantee to be safe. There are some persons who hurt others without any reason.This person first initiate & then cancelled the promise ring ceremony after my families prepared for that.We wait in friendship for two years, with peace. He didn't mention nothing wrong I did. But he said" deberegn", better to stop.Is there any thing that touches persons'moral than this? Still I love him but I wish him suffering, death. I don't know, this is confusion.

   Delete
  3. እግዚአብሄርን የበደለኝን ቅር የምልበት ጸጋ ስጠኝ ብሎ በመጠየቅ ይቅር ማለት ይቻላል፡፡አለበለዚያ ህይወታችንን ቂም እንደነቀዝ ቦርቡሮ ይጨርሰውና ከአምላካችን ጋር ያለንን ግኑኝነት ያበላሸዋል፡፡

   Delete
  4. If you still love him ,forgive him.That is the meaning of love after all. 'while we are enemy of God ,he reconciled with us through the death his son'. 'wesobe emzetseru le'egziabeher lesehalene egziabeher be mote woledu' Means 'egna ye egzaibeher telatochu hunen salen beleju mote bekul tareken' Why do hate him because he changed his mind during your engagement time? Ask him why he did so.If he doesn't want to give a clear explanation then he can at least be a good friend for you .Because you still love him. Otherwise while you are wishing him death, if you say that you still love him.It is ridiculous .If you can't live together as husband and wife , you can be good friends.if you don't forgive him, you lose everything even his friendship.Be strong and don't dare to wish death for anyone let alone for your lover.

   Oslo

   Delete
  5. @ anonymous October 9
   I think both of you are saved because of departure. Your affection is very blind. It pushes you to wish death and suffering for the one that you said 'beloved'. This is not love, this is not the characteristic of love. Love does not push to wish death or suffering, it is only blind felling that have such power for wrong wish.
   I believe you better read bible of 'Korontos' part of st. Paul and take advice from elders.
   And do not forget that this type of felling that you felt is only experienced when departure happens. Even though departing is a bad habit, give thanks to God for experiencing such feeling.
   Last but not least is your partner at this time of relationship have the right to depart.

   Delete
  6. Thanks all of you. I will try my best to forgive with the help of God.

   Delete
 2. arif eyeta newe dani thanks

  ReplyDelete
 3. Girum new Dani Kale hiywetn yasemaln tsegawun yabezalh.

  ReplyDelete
 4. Dn Daneil kale hiowt yasemah. Even i heard the story before today it helped me to write on the sand the situation which happened on me and to forget forever.

  ReplyDelete
 5. wow! this is great! Keep the momentum on...(from Au)

  ReplyDelete
 6. አበበ ሙ በየነOctober 10, 2012 at 8:10 AM

  ወንድም ዳንኤል ድንቅ እይታ ነው::
  ደቡብ አፍሪካ ለዘመናት በአፓርታይድ አስተዳዳር ለዘመናት ጥቁሮች የሰዉ ልጅ እንዳልሆኑ ተቆጥረዉ መከራን ሲያሳልፉ ኖረዋል::

  ይህ ሁኔታ ያበሳጫቸው እነ ኔልሰን ማንዴላ የአፓርታይድን አስተዳዳር ለመጣል ነፍጥ አንስተው የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስን ተቀላቅለው ሲታገሉ በአስከፈዉ አገዛዝ ተይዘዉ ሮቢን ደሴት ላይ ሃያ ሰባት አመታት ተከረቸመባቸው::

  ነገሮች ተለዉጠዉ እና ማንዴላ ከእስር ተፈተው መራሄ መንግሥት የመሆን ዕድል ሲያገኙ ይቅር ባይነትን እና በደልን መርሳትን ለዓለም አስተማሩ::

  ይህንን በማድረጋቸዉ ዛሬ በአለማችን ኤኮኖሚያቸዉ እጅግ በማደግ ላይ ከአሉት ሀገሮች ማለትም እንደ ብራዚል:ሩስያ: ህንድ እና ቻይና ተርታ ደቡብ አፍሪካ እንድትቆም አደረጉአት:: ይቅር ባይነት እና የአለፈን ቁርሾን ያለመያዝ መጪዉን ዘመን መልካም ያደርገዋል::

  ቸር እንሰንብት

  ReplyDelete
 7. እውነት እልሀለው ሁሌም ጹሁፎችህ አስተማሪ ናቸው፡፡ አንተም መጥፎ መጥፎ አስያየቶችን በመርሳት ጥሩ ጥሩ ምልከታህን አስነብበን፡፡ በጣም አመሰግናለሁ!!!

  ReplyDelete
 8. D.Dani
  Thank you for sharing your thoughts. This is the perfect post for anyone who wants to know about forget and forgive.
  Thank you very much for creating it.
  Are you coming to the Los Angeles area or Oc?
  please let us know or (email) at your earliest convenience. Endenasetenagedehe.
  May the LORD bless you and protect you...
  bereketdecor@yahoo.com

  ReplyDelete
  Replies
  1. EGZIABHER YSTLIN DaNI be ewnet ejig astemari tshuf new,selame egziabhear kante gar yhun.

   Delete
  2. EGZIABHEAR YSTLN SELAME EGZIABHEAR KE ante gar yhun.

   Delete
 9. It was wonderful article which provide advises for those who really need to forget the past and to live for future!! Thank you!! Please keep to write for vital social problems which requires remedy like above in terms of our's context

  ReplyDelete
 10. ዳኔ የዘወትር የዓምድህ ተከታታይ ከሆኑት አንድዋ ነኝ:: በበተክርስትያን ዙሪያም ሆነ በየግዜው ከምታሳትማቸው መጽሐፍትህም ጥረትህንና የድካምህን ፍሬ ከሜቃመሱት አንድዋ በመሆኔ ዘወትር ደስተኛ ነኝ:: የድንግል ማርያም ልጅም እንዳይለይህ ጾሎቴ ነው:: “በጥባጭ ካለ ማን ጡሩ ውሃ ይጠጣል ተብሎ የል”ምክንያቱም ግልጽ ባይሆን የበተክርስትያን ሰው የሆነ ወንድም ሲጠየቅ ባለመግባባት ምሳሌ ከሆኑት አንዱ የአንተን ሰም ሴጠቅስ ልቤ አዘኖ ነበር:: ሰው መሆንህን ዘንግቸ ሳይሆን ከጽሁፍህ እንዳሰፈርከው የሜያጋጥምህን ዳገት ሁሉ ሌላው ቤቀር ለሜወደህና ለሜያከብርህ ምእመን ስትል ነገር ሁሉ ከአሽዋ ላይ ጻፈው:: ይህ ጽሑፍ ለአንተም ትልቅ መካሬና አስተማሪ ይሆንሃል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ:: በርታ

  ReplyDelete
  Replies
  1. @asbet dngl you r right am felling the same thing like you but i expect he(dn daniel)will do soon and we may mention him as example of this history,unless writing only did not give sense.as bible says" non believers also do this"

   Delete
  2. He had done it before a year. I did not heard any thing new. If you did not have the information pls ask.

   Delete
 11. ይቅርታ ምንድነው ለሚለው ሰዎች የተለያየ ትርጉም ሊሰጡት ይችላሉ፡፡ ከስሙ መረዳት እንደሚቻለው ይቅርታ ማለት ይቅር ማለት ፣ የደረሰብንን በደል መርሳት፣ የበደለንን ሰው ከመጥላት ይልቅ መውደድ ማለት ነው፡፡ የግጭቱ ምክንያት እንደሚለያይ ሁሉ የይቅርታው ዓይነትም እንዲሁ ሊለያይ ይችላል፡፡ ሰዎች ለአንድ ጉዳይ የሚሰጡት ትኩረትና አረዳድ እንደሚለያይ ሁሉ ለይቅርታ ያላቸው ዝግጁነትም እንዲሁ ይለያያል፡፡ ጤነኛ የሆነ ሰው በይቅርታ አስፈላጊነት ላይ ተቃውሞ ይኖረዋል ብየ አላምንም፡፡ ይቅር የማለት ባህርይ በመርፌ የሚወጋ ወይም የሚዋጥ መድኃኒት አይደለም፡፡ ወይም እንዲሁ በምክርና በተግጻጽ በአጭር ጊዜ የሚመጣ ጠባይ አይደለም፡፡ አብሮን ማደግ ያለበትና ሊዋሐደን የሚገባው ጠባይ እንጅ፡፡ ለዚህ ነው ስለይቅርታ የሚሰብከው ራሱ በቂም በቀል ተተብትቦ የሚሰቃየው፡፡ በሰፈር የሚጫወቱትን ህጻናት ተመልከቷቸው፡፡ እርስ በእርሳቸው እንዲጣሉ ከሚያደርጋቸው ነገር በአብዛኛው ከወላጆቻቸው የሚመጣ ችግር ነው፡፡ ተሸንፈህ እዚች ቤት እንዳትገባ እየተባለ ያደገ ልጅ እንዴት ነው ልቡናው ለይቅርታ የሚዘጋጀው? ፈንክቶ የገባው ልጅ ጀግና፣ የሮጠውና ግጭቱን የሸሸው ደግሞ ፈሪ ተደርጎ በሚወሰድበት ማኅበረሰብ ያደገ ህፃን ሲያድግ ምንም ሳያጠፋ ከሥራ ያባረረውን ሰው እንዴት ነው ይቅር የሚለው? ፈንክቶ ከተቻለም ገድሎ በማኅበረሱ የሚሰጠውን የጀግንነት ማዕረግ መቀበል ነው እንጂ! ይቅር ለመባባል በይቅርታ ሰፈር ማደግ ተመራጭነት አለው፡፡
  ብዙ ዓይነት ይቅርታ ዓይነቶች ቢኖሩም ትቂቶችን ላካፍላችሁ፡፡
  ሀ. የዝምታ ይቅርታ(መርሃ-ግብር ያልተያዘለት፤ ሁለቱም ወገን በያሉበት ትቼዋለሁ ብለው ለራሳቸው የሚወስኑበት )
  ለ. ፊት ለፊት በመነጋገር የሚደረግ ይቅርታ
  በግለሰቦች በኩል የሚደረጉ የይቅርታ ዓይነቶች
  1. ከበደልነው ወይም ከበደለን ሰው የምናገኘው ጥቅም እንዳይቀርብን ስንል የምናደርገው ይቅርታ
  2. ወደፊት ያቀድናቸው ሥራዎች የሚደናቀፉብን ሲመስለን የምናደርገው ይቅርታ
  3. የበደልነው ወይም የበደለን ሰው ይቅርታ ስለጠየቀ የአሸናፊነት ስሜት ተሰምቶን የምናደርገው ይቅርታ
  4. በውስጣችን ያለውን የስሜት መረበሽ ወደነበረበት ለመመለስና ጤናማ ስሜት ለመፍጠር ስንል የምናደርገው ይቅርታ
  5. በሰዎች ላይ ቂም በመያዛችን ወይም ጥላቻ በመያዛችን ፈጣሪ እንዳያዝንብንና በፈጣሪ ዘንድ ያለንን ተቀባይነት እንዳናጣ የምናደርገው ይቅርታ
  6. ከበደለን ወይም ከበደልነው ሰው ጋር ያለን ግንኙነት ለመራቅ አስቸጋሪና ሲሆን፣ ግንኙነቱ ለረጅም ጊዜ የሚቀጥል ከሆነና ከይቅርታ ውጭ ሌላ አማራጭ ስናጣ ይምናደርገው ይቅርታ
  7. ይቅር ባለማለታችን አብረውን በሚኖሩ ሌሎች ሰዎች(ቤተ ሰብ፣ የቅርብ ጓደኛ፣ ወዘተ) ላይ ጉዳት የሚደርስ መስሎ ሲታየን የምናደርገው ይቅርታ
  8. የፍቅርን ጣዕም ስንቀምሰውና የጥላቻን ጉዳት ስንረዳ የምናደርገው ይቅርታ
  በሁለት ወገኖች መካከል የሚደረጉ የይቅርታ ዓይነቶች
  1. በአንደኛው ወገን ግፊት ብቻ የሚደረግ ይቅርታ
  2. ባለጉዳዮቹ ሳያምኑበት በሌሎች ሰዎች ግፊት የሚደረግ ይቅርታ
  3. በሁለቱም ባለጋራዎች ግፊት የሚደረግ ከልብ የመነጨ ይቅርታ
  እኛ ትኛውን የይቅርታ ዓይነት ነው ብዙ ጊዜ የምንተገብረው?

  ReplyDelete
  Replies
  1. በጣም ጥሩ ጽሁፍ ነው! it is Good,

   Delete
 12. btame asetmari nwe dani tsegawen yabezalehe wnwdemachene

  ReplyDelete
 13. The value for forgiveness and love described well.!

  ReplyDelete
 14. yikrta mebabalin egziabher le-alem hizb hulu yadil, It is really a nice view. May God bless you.

  ReplyDelete
 15. GOD Bless You! 10Q

  ReplyDelete
 16. i say only tank u
  GOD bless u
  keep it up!

  ReplyDelete
 17. Forgivens is the key to enternity. Thank you Dani it was a great view. ergiem edem.

  ReplyDelete
 18. ጌታ አብዝቶ ይባርክህ!

  ReplyDelete