Thursday, October 25, 2012

በታሪክ መርካት

click here for pdf
(ፎቶ -በአሜሪካ የኢትዮጵያ  ኢምባሲ ድረ ገጽ)
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ የመመለሱ ፌሽታ ሕዝቡን አልለቀቀውም፡፡ ተጨዋቾቹና ፌዴሬሽኑም በዚሁ ደስታ ውስጥ ናቸው፡፡ ስለ እሑዱ ድል እንጂ ስለ ቀጣዩ ውድድር የሚያስብ ግን ያለ አይመስልም፡፡ ሌሎቹ ቡድኖች እስከ ጥር ወር ድረስ ምን እንደሚሠሩ በሚናገሩበት ጊዜ እንኳን የኛው ቡድን እስከ ጥር ወር ድረስ ምን እየሠራ እንደሚቆይ አይታወቅም፡፡
እንዴውም እንደምንሰማው ከሆነ አንዳንድ ተጫዋቾቻችን በየመጠጥ ቤቱ እየተጋበዙ በሸክም ሆኗል አሉ የሚወጡት፡፡ ምነው ሲባሉ ‹ድል አድርገናልኮ› ነው መልሱ፡፡
ይኼ በትናንት ድል እየረኩ ነገን የመርሳት አባዜ የቆየ በሽታችን ነው፡፡ በአድዋ ጦርነት ጣልያንን ወኔያችንን ተጠቅመን፣ ጀግንነታችንን ተኩሰን ፈጣሪም ረድቶን ድል አደረግናት፡፡ በጥቁር አፍሪካ ምድር ቅኝ ገዥዎችን ድል ያደረገ ጥቁር ሕዝብ መሆናችንን አስመሰከርን፡፡ ታሪክ ሠርተን ታሪክ አየን፡፡

ጣልያንን የአድዋው ውርደቷ ሲቆጫት ነው የኖረው፤ ያንን ውርደቷን እንዴት እንደምታራግፈው ስትመክር፣ ስትሠራና ስትፈጥር ኖረች፡፡ እኛ ደግሞ የአድዋን ድል ስናከብር፣ በድሉ ፌሽታ ስንጥለቀለቅ ከረምን፡፡ እኛ ዐርባ ዓመት ስለ አድዋ ስንዘፍን፣ እነርሱ ዐርባ ዓመት ውርደታቸውን ለማራገፍ ሲሠሩ ከረምን፡፡ ለኛ ጣልያንን ተወግዞ እንደወጣ ሰይጣን ተመልሳ የማትመጣ አድርገን ቆጠርናት፡፡

ከዐርባ ዓመት በኋላ በ1928 ዓም ጣልያን ካለፈው ስሕተቷ ተምራ አውሮፕላንና መርዝ ሠርታ፣ ዘመናዊ ወታደር ትጥቅ አሟልታ፣ እስከ አፍንጫዋም ታጥቃ መጣች፡፡ እኛ ግን እነዚያኑ አድዋ የወሰድናቸውን መሣርያዎችና አጋሠሶች ይዘን ማይጨው ዘመትን፡፡ እናም በማይጨው የሆንነውን እናውቀዋለን፡፡
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ረሃብ፣ ወረርሽኝና ተስቦ እየደጋገመ ሀገሪቱን ሲመታና ሲያደቅቅ እናገኛለን፡፡ እያንዳንዱን የመከራ ጊዜ በጸሎትም፣ በእሳትም፣ በሞትም ስናሸንፈው ሌላ መከራ የማይመጣ ይመስል ያኛውንና ያለፈውን እንዴት እንደተወጣነው ብቻ በመተረክና በመዝፈን ጊዜውን እንጨርሰዋለን፡፡ ያም የመከራ ዘመን ጊዜውን ጠብቆ እንደገና ይመጣል፡፡
ጅርመኖች በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሀገራቸው እንዳልነበረች መሆንዋ፣ ከናዚ አስተሳሰብ ጋር በተያያዘ ስሟ መጥፋቱ፣ ጀርመናዊ ነኝ ማለት እስኪያሳፍር ድረስ መድረሱ አስቆጭቷቸው ለአርባ ዓመታት ሠሩ፡፡ በዐርባ ዓመት ጊዜ ውስጥ ጀርመን የዓለምን አራተኛ ኢኮኖሚ የምታስተዳድር ሀገር ሆና ወጣች፡፡ እኛ ግን የአፍሪካን ዋንጫ እንኳን ለመሳተፍ 31 ዓመታት ፈጀብን፤ ለምን? ቢባል በታክ የሚዝናና እንጂ በቁጭት የሚሠራ ስላላገኘን፡፡
አሁንም በእግር ኳስ ቡድኑ ላይ የምናየው ይኼንኑ ነው፡፡ ትናንት አሸነፍን፤ መልካም፡፡ ነገር ግን የኛ ደስታ እንደ ሄሊኮሜት በዘመናት አንድ ጊዜ ብቻ ነው እንዴ መምጣት ያለበት? ያለፈ ድል ለቀጣዩ መነሻ ይሆናል እንጂ ስንቅ ይሆናል እንዴ? አሁን መጠየቅ ያለብን ከነማን ጋር ደረሰን? የሚለውኮ አልነበረም፡፡ አሠልጣኝ ሰውነት እንዳሉት ‹ከማንም ጋር ይድረሰን፣ ከተዘጋጀንና ከሠራን እናሸንፋለን፤› ካልሠራን ግን ከራሳችንም ጋር ተጫውተን አናሸንፍም፡፡
ለምን እንረሳለን፤ እኛኮ በአፍሪካ ዋንጫ ከሁሉም ቡድኖች የበለጡ ጎሎችን ያስተናገድን ነን፤ በአፍሪካ ዋንጫ ከሚሳተፉ ቡድኖች በፊፋ ደረጃ ዝቅተኛ ደረጃ ካላቸው መካከል የምንመደብ ነን፤ ሌሎቹኮ ተጨዋቾቻቸውን  ከአውሮፓ እየጠሩ ነው፣ አራትና አምስት የወዳጅነት ጨዋታ ከአውሮፓ ቡድኖች ጋር ለማድረግ ዕቅዳቸውን ይፋ አድርገዋልኮ፡፡
     ሦስተኛውን የአፍሪካ ዋናጫ ያሸነፈው ቡድን
           ( ፎቶ -ከሪፖርትር)
እኛ ሱዳንን ስላሸነፍን ተዘጋጅቶ የሚጠብቀን እንጂ ፈርቶን የሚሸሽኮ የለም፡፡ እንዴት አሸነፉ? ምን ዓይነት ስልት አላቸው? ጠንካራና ደካማ ጎናቸው ምንድን ነው? እያለ ተንትኖ የሚጠብቀን እንጂ አርድ አንቀጥቅጥ የለበስን ይመስል ማንም አይደነግጥልንም፤ ያለፈው ድላችን ተጋጣሚዎቻችንን ይበልጥ ተዘጋጅተው እንዲጠብቁን ያደርጋቸዋል እንጂ ‹እንደ ሰም አቅልጦ፣ እንደ ገል ቀጥቅጦ› አይጥላቸውም፡፡
ባለፉት 31 ዓመታት የዛሬ ሠላሳ አንድ ዓመት ማን በጭንቅላት በገጫት ኳስ ለአፍሪካ ዋንጫ እንዳለፍን ስንተርክ ሰነበትን፡፡ ለመሆኑ ቀጣዩን የአፍሪካ ዋንጫስ? ‹ሳላዲን ሰይድና አዳነ ግርማ እንዲህና እንዲያ አድርገው ባገቡት ግብ ነበር ያለፍነው› እያልን ለምን ያህል ዓመት ይሆን የምንተርከው?
ይህ ሀገሩ ከፍ ስትል የሚወድ ሕዝብ ደስታው ምንያህል እንደነበረኮ አይተነዋል? ኢትዮጵያ ቡድን እንጂ ሕዝብ አላጣችም፤ ፌዴሬሽን እንጂ ሕዝብ አላጣችም፡፡ ይልቅስ አሁን መነጋገር ያለብን ይህንን ደስታ እንዴት ዘላቂ ማድረግ እንደምንችል ነው፤ እንዴት ነው የአፍሪካ ዋንጫ ብርቅ የምይሆንብን ደረጃ የምንደርሰው? እንዴት ነው የዓለም ዋንጫን በቴሌቭዥን ብቻ ከማየት የምንላቀቀው? እንዴት ነው በጠንካራ መሠረት ላይ የተመሠረተ እግር ኳስ የምናደራጀው? እንዴት ነው የባለሃብቶችን ድጋፍ ከሽልማት ወደ ቀድሞ መደገፍ የምንቀይረው?
ብዙ ሥራ አለብን፡፡ ደስታው ይብቃ፤ ፌሽታውም ልክ ይኑረው፤ እርሱ የኛ ሆኗልና ማንም አይነጥቅብንም፤ አሁን የኛ ስላልሆነው የአፍሪካ ዋንጫ እናስብ፡፡ ታሪክ ላይ መተኛት ብዙ ጊዜ ጎድቶናልና ይብቃን፡፡

44 comments:

 1. ejihin degimo degagimo yibarkilih kemalet wuchi min elalehu ! yemisema yadmit!

  ReplyDelete
 2. This observation should be taken and used in our day to day life.

  ReplyDelete
 3. Yes! 'tarik lay metegnat yibkan' thanks Dn. Dani.

  ReplyDelete
 4. Great stuff,

  No we need to focus for the future game. Our team has to prepare to show good game to the tournament.

  According to yesterday's draw, we are grouped with Zambia, Nigeria and Burkina Faso.

  All the best

  ReplyDelete
 5. የተወደድክ ዲያቆን ዳኒ፡

  ተባረክ ብሩክ ሁን። ጽሁፎችህ ሁሉ ያንጻሉ። ባገኘነው ድል ስንኩራራ ሳናስበው እንነጠቅና ጉድ እንሆናለን ያልከው ትክክል ነው። እስማማለሁ። ስለዚህ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። እኔማ ሁልጊዜ ስጋት እየያዘኝ ተቸግሪያለሁ። ይህ ድል ቢጠፋስ? በአንድ ምክንያት ቢሄድስ እያልኩ፣ የወደፊቱን ሳስበው ድንጋጤ ይይዘኛል። የአሁኑን ደስታ ሳልኖረው የወደፊቱ ያስጋኛል። ድላችንን ቢነጥቁንስ? እነማን ያልከኝ እንደሁ -- እነሱ። ስማቸው አይጠቀሴው? ሁልጊዜ ፍርሃት ያዘኝ ዲያቆን ዳኒ። ምን ይሻለኛል? ንፋስ በበሩ ቁልፍ ቀዳዳ ሽው ብሎ ሲገባ እራሱ ጸጉሬን ከናላየ ነፍሰ ስጋየን ከስጋየ እያላቀቃት በስጋት እኖራለሁ። መቸም እምልህ ይገባሃል። የዚህ አለም ነገር ተቀያያሪ ነው። አይ መከራ። ኑሮ ካሉት መቃብር ይሞቃል አሉ። ዳኒየ ምን ትምከረኛለህ? ይህ የማይድን ይስጋት በሽታ ነፍሴን ተቆጣጥሯት በፍርሃት መኖር ከጀመርኩ ብዙ ሳምንታት አለፉ። አይ የኔ ነገር፣ ሳላስበው ሌላ እርዕስ ውስጥ ገባሁ። እና ምክርህን በትህትና እጠብቅለሁ። ያንተ ተከታታይ፣ ወለተ እግዚ (የክርስትና ስሜ ነው)። መልካም ቀን ዲያቆን ዳኒ።

  ReplyDelete
 6. Yes!! It is better to take time and think how can win Nigeria,Zambia and Burkinafaso and proceed to the next round.Thanks Dany.

  ReplyDelete
 7. ትክክል ነው ደስታው ይብቃ፤ ፌሽታውም ልክ ይኑረው፤ እርሱ የኛ ሆኗልና ማንም አይነጥቅብንም፤ ስላላገኘነው ነው ማሰብ ያለብን.

  ReplyDelete
 8. ohhhhhh dani !
  i agree with ur idea but its too much emotional and unbalanced. B/c to whom do u Write this blog to the people or to the federation or to the player or to the coach staff....... u hv to be specific, or u hv to let the critics 4 football professionals.

  ReplyDelete
 9. Dani, inya bebizu gidayoch ayinachinin mekifet yitebekibinal. yihe igir kuwasun bicha sayihon ye mela hageritu chigir new. ibakachihu iyasitewalin!
  chemro chemro yisitih.

  ReplyDelete
 10. dani, yih yeigir kuwasum bicha sayihon yemela hageritu chigir new. ye astesaseb abiyotyasifeligal.
  ibakachihu iyasitewalin!
  dani, chemro chemro yistih.

  ReplyDelete
 11. “አሁን ገና በራልኝ አለች እብድ ቤትዋን አቃጥላ” ለ31 ዓመታት በጨለማ ተውጦ የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሁን ገና ብርኃኑ ፍንትው ብሎ በራለት። ሳልወለድ በፊት ማለትም የዛሬ 31 ዓመት በ1974 ዓ.ም ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ዋንጫ ተካፍላ ነበር። ይኸው ዛሬ ኢትዮጵያ ለአስረኛ ጊዜ ለአፍሪካ ዋንጫ አለፈች። ይህ ደስታ ልክ እንደ ብረት ምጣድ በአንዴ ግሎ ወዲያው የሚበርድ መሆን የለበትም። የሸክላ ምጣድ ለመጋል አመት ይፈጅበታል። ለመብረድም ጊዜ ይፈጃል። እንዲያውም እናቶቻችን እሳቱን አጥፍተው በጋለው የሸክላ ምጣድ እንጀራ ይጋግሩበታል። የኛ ኳስም ለመጋል የ 31 ዓመታት እንጨት ጨርሷል። ከዚህ ከጋለ ምጣድ ብዙ ያማረ እንጀራ ማውጣት አለብን። የሚጋገረው እንጀራ ሀገርን ያጠግባል። አንድም በጋለው ምጣድ የተጋገረው እንጀራ እንደነ ድሮግባ ለአውሮፓም መላክ ይቻላል። በዚህ በጋለው ደስታችን ስለወደፊቱ ብዙ መወያየት አለብን። ብዙ ፕሮፌሽናል ተጫዋቾችን ለማውጣት እነሆ ጊዜው ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው። ለአፍሪካ ዋንጫ ስናልፍ ለመሳተፍ ሳይሆን ተስፋ ለሚሰጥ ተሳትፎ መስራት ይጠበቅብናል። ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ በርትቶ መስራት የአባትነት ነው። ካለፍን ከአሁኑ ምን እንስራ ብሎ ማሰብም የእናትነት ነው። ሠርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ እንዳይሆንብን ከአሁኑ መዘጋጀት አለብን። በተለይ ጋዜጠኞች ብርቱ ስራ አለባችሁ። ብሔራዊ ቡድኑን በሙሉ ሰብስባችሁ ለየት ያለ ፕሮግራም ማዘጋጀት አለባችሁ። ስለ ኢትዮጵያ የኳስ እድገት ምን እንስራ? እንዴት እንደግፈው? ወፌ ቆመች ወፌ ቆመች የሚባልለት ብሔራዊ ቡድን ሳይሆን እንደ ሯጮቻችን ራሱን ችሎ በአስተማማኝ መሰረት ላይ የተገነባ ቡድን እንዴት እንስራ? ወዘተ ተረፈዎችን ዛሬ ያልተነሱ መቼ ሊነሱ ነው? እነዚህ ሁሉ ሕዝቡ በደስታ እንደጋለ መነሳት አለባቸው። ብረትን መቀጥቀጥ እንደጋለ ነው!


  =======================

  ይህችን አድራሻ በመጎብኘት የልጅ ዮናስ ብሎግ አባል መሆን ይቻላል!!

  http://yonas-zekarias.blogspot.com/

  ReplyDelete
  Replies
  1. አሁን ገና በራልኝ አለች እብድ ቤትዋን አቃጥላ!! KiKikiki

   Delete
 12. አበበ ሙ በየነOctober 25, 2012 at 5:48 PM

  ወንድሜ ዳንኤል ለመልካም እይታህ እግዚአብሔር ይስጥህ::

  ሃገራችን ኢትዮጵያ በታሪክ አልጋ ላይ ስታንቀላፋ ዘመናት ነጎዱ:: የአክሱም: የላሊበላ እና የጎንደር የስልጣኔ ትሩፋቶች አሁን ላይ ሆነን ስንመለከታቸው የቀደሙ አባቶቻችን የት ደርሰዉ እንደነበር ሲያመለክት እኛ የአሁኑ ትዉልዶች አሁን የአለንበት ስፍራ ላይ መገኘታችን ከማሳዘንም አልፎ አንገት ያስደፋል::

  በአፍሪካ ዉስጥ የእግር ኳስ ዉድድርን በቀዳሚነት ጀምረን ሶስት ግዜም ዉድድሩን አዘጋጅተን ለሰላሳ አንድ አመታት ያህል እኛዉ ከጀመርነዉ ዉድድር ርቀን መቆየታችን ያናድዳልም ያስተክዛልም::

  የሆነስ ሆነና ከአንድ ጅረት ዉሃ የምንጠጣዉን ጎረቤታችንን ሱዳንን በፀሎትም ሆነ በጨዋታ አሸንፈን ለአፍሪካ ዋንጫ ዉድድር ማለፋችን እሰየዉ ያስብላል:: ምድባችንም ከናይጄሪያ: ከዛምቢያ እና ከቡርኪናፋሶ ጋር እንደሆነም አዉቀናል::

  መቸም ለአፍሪካ ዋንጫ አለፍን ማለት ዉድደሩ አለቀ ማለት አይደለም:: ገና ጠንካራና ብርቱ ፉክክር ይጠበቀናል:: አይመጣምን ትቶ ይመጣልን መያዝ ተገቢ በመሆኑ ሊደርስበን ከሚችል የሞራልም ሆነ የክብር ዉድቀት ለመዳን ከወዲሁ በአካልም በመንፈስም መዘጋጀት ይጠበቅብናል::

  ተጨዋቾቻችንም የሀገር ክብር ለማስጠበቅ እና መልካም ገፅታዋን ለመገንባት በሚደረገዉ ጥረት ኃላፊነታችሁን ለመወጣት እንድትችሉ ከየመሸታ ቤቱ እንደ ህፃን ልጅ እየታዘሉ መዉጣትን ትታችሁ ቀበቶአችሁን ጠበቅ አደርጎ መዘጋጅት ያስፈልጋል::

  ማናቸዉንም ጦርነት ለማሸነፍ በሰላሙ ግዜ መዘጋጀት ያስፈልጋል:: ወንድሞቼ ላብ ደምን ያድናል እንዲሉ ሁሉ አሁን የምናፈሰዉ ላብ ደማችን እንዳይፈስ ልቦናችን እንዳይሰበር ያደርጋል::

  በዚህ አጋጣሚ ሼህ አል አሙዲን እና መሃንዲስ ተክለብርሃን አምባዬ ተጨዋቾቻችንን ለማበረታታት የአደረጉት ድጋፍ የሚያበረታታ መሆኑ አይካድም:: ምስጋናችንም ይደረሳቸዉ::

  ነገር ግን የአገሬ ወፍ እንደነገረኝ በተለይ ሼሁ የሰጡትን የማበረታቻ ድጋፍ ከተጨዋቾች: ከአሰልጣኞች: እና ከወጌሻዎች ዉጭ ለመቀራመት የአሰፈሰፉ ጆቢራዎች በርካታ በመሆናቸዉ ከዚህ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ ሃይ የሚል አካል ሊኖር ይገባል እላለሁ:: በሌሎች ድካምና ልፋት አኩፋድን እና ከርስን ለመሙላት መዳዳት ከማስተዛዘብም አልፎ እሰዉ ኪስ ጉድጉድ ማለት ነዉና የሚያስተዉል ልቦና የሚነዘነዝ ህሊና ይስጣችሁ እላለሁ:: ድብኝታችሁን ስትሞሉ ትዉልድ ትገድላላችሁ እና ሰርቃችሁ ከማሰብ እባካችሁ እጃችሁን ሰብስቡ ::

  ቸር ይግጠመን

  ReplyDelete
 13. @ዮናስ ዘካርያስ ket ametahew benatih eyhen teret አሁን ገና በራልኝ አለች እብድ ቤትዋን አቃጥላ!betam delagn lelam kale chemirilign.

  ReplyDelete
 14. Abo Fenda , zim bile tichit , Daniel Kibret esti zim bel , endante bemaurat sayihon bemesrat yemeta dil silehone bertu belachew enji zim bilehe merzhin atirch, Daniel bebetehi gudayi yesew mikir endemayashahi hulu enesum lebelete dil tegetew eyeseru neww . Silezhi please shut your mouth and give us peace, "awekish awekish siluat.." alu ...beteret....Please Do me big favour .."PLEASE SEE YOUR SELF, LESEW YIMESEL BICHA SAYIHON KELIBHI SEWW MEHON ESTI ZARE JEMIR

  ReplyDelete
  Replies
  1. I do not think you have also started to be a human being. Better think how to be a human being!!!

   Delete
  2. entenkek malet merzinet kehone, dikmetin mawok sew alemehon kehone, sew ke ensisa bemin yileyal? le antes sew malet min malet new dani miker tekebay newuna lesu sitnegrew le egnam yidersenal. pls be positive!!!!

   Delete
  3. ከዚህ በላይ በአኖኒመስ-(ያልታወቀ ሰው) አስተያየት ለመስጠት የሞከርከው ሰው ባንተ አመለካከት ዲ.ዳንኤል ኢትዮጵያዊ እንዳልሆነ የተቆጠረ ይመስላል፡፡...በመሰረቱ አንድ ኢትዮጵያዊ በአገሪቱ ስም በሚካሄድ ማንኛውም ነገር ላይ አስተያየት ለመስጠትም ሆነ ሃሳቡን ለማንጸባረቅ አያገባህም ሊባል አይገባም፤ ይሔ ሰዎችን በማሸማቀቅ የዜግነት ግዴታቸውን እንዳይወጡ የሚደረግ ትንኮሳም ሊቆም ይገባል፡፡ በመሆኑም ዲ.ዳንኤልም ሆነ ማንኛውም ሰው ከመንፈሳዊነቱ ጎን ለጎን ማህበራዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ወይም ስፖርት የመሳሰሉት ነገሮች የሚያስደስቱት ሰው ከሆነ ይሄ የራሱ ምርጫ ነው፡፡ በዚያ ላይ 'ሰው ሁን' ብሎ ሌላውን የሚመክር ሰው 'እባክህ አፍህን ዝጋ' ብሎ አስተያየት ከመስጠት ይልቅ 'ከልብ ሰው ስለመሆን' ጠቃሚ ምክረ ሃሳቦችን በማንነቱ ሳያፍር መስጠት ቢችል የተሻለ ነበር፡፡ ልቦና ይስጠን፡፡

   Delete
  4. አካለል (ከ 5ኪሎ)October 31, 2012 at 12:24 PM

   Andande yesewu lij hulu tikikilegna neger Yaweral (yasibal) bilo metebeku tinish Yaschegiral mikniyatu (Fetariwunim Yesekelewu irasu silohone).Ahun kelay coment Yaderegewu sewuye (Anonymous) ijig askeftognal..." wodajih telatih indayhon andim idil atistewu, telatih wodajih indihon 1000... idil sitewu" andu guadegnaye indalkewu, tastemrewaleh biye igemtalehu...Ayzoh dani እግዚአብሔር የይርዳህ በርታ...

   Delete
 15. Honer the past and prepared for the better tomorrow.

  ReplyDelete
 16. it is good view

  ReplyDelete
 17. hi dani i really appreciate and follow ur vision keep it up but i didnt agree with this comment post cos when they won after 31 yrs you did not encourage our players or even u said nothing about it so why u start them blaming.............i dont remember when post it but you told us that everything should begin from positive things and now u started completely reverse so for me it doesnt make sense even if u r right what they did they need a bit rest and enjoy even the profesional players did it,there is a time for work,enjoy etc they r human like us it doesnt matter the way of their enjoy thats up to them.
  we have to praise them all the staff they remember us happiness of soccer and now we should encourage them as well not only always we talk about their weak part.
  tnx

  ReplyDelete
 18. ሃቅ ነው፣ ዳኒ፣ የትናንት እራት ለዛሬ ምንም ሊሆን አይችልም ፣ቢሆንም ዕድሜ ለአባቶቻችን ታሪክ ባይሰሩልን ኖሮ ምን እናወራ ነበር ፣ የሚያሳዝነው፣ እንኳን ሌላ ታሪክ ልንጨምር እነሱ የሰሩትንም በአግባቡ መጠበቅ አልቻልንም፣ ሲሸነፍ የኖረ ህዝብ አንዴ ሲያሸንፍ ሊቦርቅ ይችላል፣ የሚያሳዝነኝ አሸንፎ ሳይጨርስ መሆኑ፣ ጀርመኖች በለንደኑ የኦሎምቲክ ጨዋታ በጣልያኖች ሲሸነፉ በጣም ተበሳጭተው ነበር፣ በኋላ እስፔኖች ጣልያኖችን ሲያስጨንቁ ፣ ጋዜጠኛው ከሜዳ ጠረጓቸው አለና እንኳን በጊዜ ተባረርን እኛ ብንሆን ደግሞ የባሰ እንዋረድ ነበር ነው ያለው፣ የአሁኑ ፌስታ በኋላ ደብቁኝ እንዳይሆን፣ ከሰይጣን ጋራ ማዕድ የሚጋራ ረጅም ማንኪያ ሊኖረው ይገባል ይባላል ፣ማሰብ ይጠቅማል ጎበዝ፣ ለጥያቄዎቻችን መልስ ስናገኝ መሻሻል፣ መልሶቻችንን መልሰን ስንጠይቅ ደግሞ አዲስ ግኝት ላይ እንደርሳለን፣ ዳኒ በርታ፣፣
  በረከተ እስጢፋኖስ ይህድር በላዕሌከ፣

  ReplyDelete
 19. እህቴ ወለተ እግዚእ ፣ ስምሽን እንደዚህ ነው መጻፍ ያለብሽ፣ በመቀጠል፣ ሞት ደጃፍ ላይ የቆመ እየመሰለሽ ነፋስ በነፈሰ ቁጥር አትጨነቂ፣ በማይድን በሽታ መያዝ ማለት የሞት በራፍ ላይ መቆም አይደለም፣ እስቲ አስቢው አንቺ ከተያዝሽ ወዲህ ስንት ያልተያዙ ሰዎች አለቁ፣ ደግሞስ የማይድን ያልሽው ዓንቺ ነሽ እንጂ እግዚአብሄር አይደለም፣ ያልታመመው በታመሙት የታመመው በሞቱት መጽናናት አለበትኮ፣ ካንቺ የባሱትን እያሰብሽ መጽናናት አለብሽ፣ ጌታ ተአምር ሊያናግርሽ ሊሆን ስለሚችል በትዕግስት ጠብቂው፣ እግዚአብሄር በምህረት እጁ ይዳብስሽ፣

  ReplyDelete
 20. nice to meet and read ur saying.
  keep in touch too,

  ReplyDelete
 21. Dear Daicon Daniel,
  You're one of my best teachers. A teacher who always gives a homework, an advice even though a student scores 100,today. A teacher who has something insightful to students to keep their mind working. A teacher who doesn't stop working hard to assist students to maximize and utilize their knowledge. A teacher who sees beyond the horizon that students don't see. A good teacher-a role model. Thank God for giving us a good teachers.

  ReplyDelete
 22. SELE ETHIOPIA EGRKAS EDGET YEMIGEDH ETHIOPIYAWI BEMULU AHUN YETBALEWN HULU BEDMB LB MALET ALBK...31 AMET YENBEREW...62 AMET ENDYHON ...ENSRA ...NGEM ENSRA ...ENSRA....

  ReplyDelete
 23. you said a perfect sayings.Hope we ethiopians have a noumber of past lessons that help us to leran our both bad good deeds.But in giving a great due to these events,we should to be blamed cos our history mainily remembers postive achivements by providing a zero space to wrong actions.For me it is impossible to walke having only a time of victory, what about a periods of failure? so it is too important to walke with both periods by not wasting a time on past appreciable activities. Let we dancing on futur achievements!

  ReplyDelete
 24. እንዴት ሰነበትክ ዲያቆን ያነሳኸው ርዕስ በጣም ጥሩ ነው ነገር ግን ይህ ችግር መች በእግር ኳሱ ብቻ በሁሉም የሞያ ዘርፍ ተሰማርተው የሚገኙ ወገኖቻችንን ያጠቃ ወረርሽኝ ነው እግዚአብሔር አምላክ ፈውሱን ይላክልን፡፡ አይነልቦናችንን አብርቶ የምንቆጭና የምንሰራ ያድርገን ነገር ግን በቀደሙ ኩራቶቻችን ስንኩራራ የኛን ድርሻ እረሳነው የቀደሙት የቀደመውን ድርሻቸውን ሰርተው ለኛም ኩራት ሆኑን የሚቀጥለው እንዳይወቅሰን ያለውን ጠብቀን የተቀበልነውን እናቀብለው የድርሻችንን ተወጥተን መስራትን እናስተምረው ቸር እንሰንብት፡

  ReplyDelete
 25. egziabehr ejehen yebarkew

  ReplyDelete
 26. 1000000% yes!!!! thanks Dn. Daniel! yemisema sinor ayidel?

  ReplyDelete
 27. "ፎቶ -በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ድረ ገጽ " የሚለውን ሳይ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ስለዋልድባ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተን ሳያናግሩን እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ እንኴን ሳይቀበሉን አሳዝነውን መለሱን እኛም ከበር ተራግመን ገዳማትን ያፈረሰ ይፍረስ ብለን የተመለስነውን አስታወሰኝ::ታዲያ ዳኒ ብንጮህ አልሰማ ቢሉ ርእሰ መንግስቱ አቶ መለስ ተቀሰፉ:: የኛው ካህን ነኝ ባይ በዚያው በጉደኛው በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኢምባሲ መለስ አለሞተም አይሞትም መለስ ማለት እውነት ማለት ነው ክርስቶስ ማለትም እውነት ማለት ነው እያሉ በሁለቱም አንድ ነን እያሉ ሲሰብኩ ያየሁትን አስታወሰኝ እና ዳኒ ስለስፖርተኞቹ የታየህን እይታ እኔን ከላይ የተጻፈው ነገር "ፎቶ -በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ድረ ገጽ " የሚለው ነገር ዘግንኖኝ ሳላነበው ቀረሁ ::
  የስፖርቱ ውጤት ከአቶ መለስ እቅድ ውስጥ አንዱነበር ነው ተባለ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ይሀኸው በቴዲ አአፍሮ ድግስ ላይ አስጠብቆ ምችው ያደሩት የ17አመት ወጣቶቻችን እና ሴቶች ሉሲዎቻችን 5 ፣ 5 ጎሎችን አሰተናገዱልን! ለተጨዋቾቻችን ግዴለም መሸነፍ ማሸነፍ ያለ ነው ይኖራል የሚያሳዝነው ቅጥ ያጣው ሽፈራው ነው ደግሞስ ስለምን በሳምንት ግዜ ውስጥ ገና ብዙ ጨዋታዎች የሚጠብቃቸውን ወጣቶች ልክ እንደ ራፐር አቀንቃኝ ወይም ወደ ካዚኖ ቁማር ቤት እንደሚሄድ ጀብደኛ ልጆቹን በሊሙዚና ጭኖ ወደ ጭፈራ መውሰድ ምን የሚሉት ሙገሳ ነው የሄ? አሁንም የጥር ላይ ተረኛ ተጨዋቾቻንን ይጠብቅልን ከ ግርግር ሌላ ምን ይባላል

   Delete
 28. yematigebabet gudayi yelehim besimeab kehayimanotenga wode sportegna wolayi neh be mejemeriya yenten akwam astekakil sportgna nehnin diyakon nehin mindin neh lemehonu lemetechet merot Yigermal ///

  ReplyDelete
 29. Very Nice!Keep in touch!
  Biosbiology@gmail.com

  ReplyDelete
 30. Yelib adris !!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 31. "ደስታው ይብቃ፤ ፌሽታውም ልክ ይኑረው፤ እርሱ የኛ ሆኗልና ማንም አይነጥቅብንም፤ አሁን የኛ ስላልሆነው የአፍሪካ ዋንጫ እናስብ፡፡ ታሪክ ላይ መተኛት ብዙ ጊዜ ጎድቶናልና ይብቃን፡፡"

  ReplyDelete