Wednesday, October 17, 2012

እስከ መቼ ?


ይህንን ስጽፍላችሁ እጅግ አዝኜ፣ እጅግም ተናድጃለሁ፤ ወንድ መሆኔን ከጠላሁባቸው ጥቂት አጋጣሚዎች አንዱ  የዛሬው ገጠመኝ ነው፡፡
ቢሮዬ ውስጥ ቁጭ ብዬ እየሠራሁ እያለ ድንገት የጫጫታ ድምጽ ከውጭ ሰማሁ፤ መጀመርያ የሰዎች የጨዋታ ድምፅ መስሎኝ ዝም አልኩ፡፡ እየቆየ ግን ‹ጩኸት በረከተ› እኔም ነገሩ ግራ ገብቶኝ ወጣሁ፡፡ ይህ አካባቢ የወፍ ድምጽ እንኳን የማይሰማበት ጸጥታ የሞላው አካባቢ ነበርና ነገሩ እንግዳ ነው የሆነብኝ፡፡
ከወጣሁ በኋላ ያየሁትንና የሰማሁትን ግን ለማመን አልቻልኩም፡፡
እኅትና ወንድም በአንድ ድርጅት ውስጥ ይሠራሉ፤ ብዙ ጊዜ በመግባባት መንፈስ መሥራታቸው ይደንቀኝ ነበር፡፡ ሲሳሳቁና ሲጫወቱ እንጂ ሲከራከሩ እንኳን ሰምቼ አላውቅም፡፡ አሁን ያየሁት ግን በእውኔ ነው፣ በሕልሜ፣ ወይስ በፊልም የሚያሰኝ ነው፡፡
አንዲት እኅት ስቅስቅ ብላ ታለቅሳለች፣ ወንድሟም አለፍ ብሎ ‹ልቀቋት ተዋት፤ ምን ታመጣለች› ይላል፡፡ የታመ መችም መሰለኝ፡፡ እኔ ግራ እንደተጋባሁ ምክንያቱን ጠየቅኩ፡፡ በመካከላቸው በሥራ አለመግባባት ይፈጠራል፤ ታላቅ ወንድም ይበሳጭና ታናሽ እኅቱን በጥፊ ይወለውላል፡፡ ቢሮ ውስጥ፣ በቢሮ ሰዓት፣ ሰው ሁሉ እያየና እየሰማ፣ በሥራ ግንኙነት፡፡ ማመን አልቻልኩም፡፡
የመማር ጥቅም ምንድን ነው?
መማር ሰርተፊኬታችንንና ደመወዛችንን ብቻ ነው እንዴ የሚቀይረው?
አሁንም ወንድ ማለት ለመማታት ሥልጣን ያለው ፍጡር ማለት ነው?
ታላላቆች ታናናሾችን ከታናሽነት በላይ ማየት የሚችሉት መቼ ነው?
የወንዶች ትምክህት የሚለቅቀው መቼና በምን ዓይነት የትምህርት ደረጃ ነው?
አንድ መዓት ጥያቄዎች ነበር የመጡብኝ፡፡ እኔ ወደ ክርክራቸው ፍሬ ነገር አልገባም፤ በጭቅጭቁ ውስጥ ማን ነበር ጥፋተኛው? የሚለው ውስጥም አልነከርም፡፡ በምንም መንገድ ግን ማንም ማንንም እኅት በተናደደና ባልተግባባ መጠን፣ ቱግ ባለና የተበለጠ በመሰለው ጊዜ፣ ስሜቱን መቆጣጠር ባቃተውና እሳት በላሰ ቁጥር መምታት ግን አይችልም፡፡ ፈጽሞም አይችልም፤ ከዚህ የበለጠ እንስሳነትም የለም፡፡ ሰው ማለት የሚያስብ እንስሳ ነው፡፡ ማሰብ ከሰው ሲጠፋ ግን ሰው እንስሳነቱ ብቻ ይቀራል፡፡
 እኅቶቻችን የጉልበታችን ማሳያዎች አይደሉም፤ እኅቶቻችን የጡንቻዎቻችን መፈተሻዎች አይደሉም፤ እኅቶቻችን የእልሃችን መወጫዎች ፈጽሞ አይደሉም፡፡ እኅቶቻችን ሃሳብ ባነሰን ቁጥር ዐቅማችንን የምናሳይባቸው የቦክስ መለማመጃዎች አይደሉም፡፡
ክርክር፣ ውይይት፣ ሽምግልና፣ ካልተቻለም ደግሞ ሕጋዊ አሠራር እያለ አንዲት እኅት በቢሮዋ፣ በገዛ ወንድሟ የምትደበደብ ከሆነ፤ በቤታቸው ላሉት እኅቶቻችንማ ዋስትናቸው ምንድን ነው? አንድ ወንድ በቢሮ ውስጥ ለመደባደብ ካላፈረ፣ በድብቅ ቦታ ወይም በመኝታው ውስጥማ የፈለገውን ለማድረግ ምን ይፈራል? አንድ ወንድ እኅቱን ታናሽ በመሆኗ ምክንያት ብቻ ጡጫ ከሰነዘረ ሚስቱ እጣ ፈንታዋ ምንድን ነው?
ይህች እኅት ባለ ትዳር፣ ለብዙ ዓመታት የሠራች፣ የተማረች ወይዘሮ ናት፡፡ የተማረና ለብዙ ዓመታት የሠራ ወንድምም አላት፡፡ ይህ ሁሉ ግን የወንዶችን ጡጫ ከመቀበል አላዳናትም? ታድያ አንዲት እኅት ለመከበርና ለመታፈር ከዚህ በላይ ምን ማድረግ ትችላለች?
ጡጫ መሰንዘር የአእምሮ ታናሽነት ማሳያ ነው፤ ጡጫ መሠንዘር የጥበብ መጉደል ምልክት ነው፤ ጡጫ መሠንዘር ሃሳብ አልባነት ነው፤ ጡጫ መሠንዘር በውይይትና ክርክር ለመርታት አልችልም ብሎ ቀድሞ መሸነፍ ነው፡፡ ስሜትን ለማሸነፍ የማይችሉ ሰዎች የመፍትሔ አቅጣጫ ነው -ጡጫ፡፡
ብዙዎቻችን የተማርነው ወጥተን ለመቀጠር የሚያገለግለንን ብቻ ነው፡፡ በተማሩት ትምህርት አመለካከታቸው የተለወጠ ሰዎች ዕድለኞች ናቸው፡፡ ‹ደመወዛቸው የዶክተር አመለካከታቸው ግን የኋላ ቀር› የሆኑ አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ሲቪያቸውና ማንነታቸው አብሮ የማይሄድላቸው ናቸው፡፡ የቤት ቀጋ የውጭ አልጋ የሚሏቸው ዓይነት፡፡ ገና አእምራቸው ወፍሮ ጡንቻቸው ያልረገበ ዓይነት፡፡ ደበበ ሰይፉ ‹ጥሬ ጨው ጥሬ ጨው ጥሬ ጨዋዎች፣ መሰለቅ፣ መደቆስ ገና ሚቀራቸው› የሚላቸው ዓይነት፡፡
‹የተማረ› ወንድም ለእኅቱ የውርደት መንሥኤ መሆን አልነበረበትም፤ የትንሣኤዋ ፋና ወጊ እንጂ፤ ኮሌጅ መበጠስና ሰውን በቡጢ መበጠስ አብረው ከተጓዙ ትምህርት የገንዘብ ኪሣራ እንጂ የእእምሮ ልማት መሆኑ ያበቃለታል፡፡
በተደፈሩ ሴቶች ላይ ጥናት ያደረጉ አካላት ኢትዮጵያ ውስጥ አብዛኞቹ ሴቶች በተላይ ሕፃናት ሴቶች የሚደፈሩት በቅርብ ቤተሰቦቻቸው ወይም ጎረቤቶቻቸው መሆኑን ይገልጣሉ፡፡ የዚህም አንዱና ዋናው ምክንያት ነገሩ ስለሚሸፋፈንና ከቤተሰብ ውርደትና ክብር ጋር ስለሚያያዝ ነው፡፡ ይኼም ነገር ነገ ‹ታድያ ወንድምሽ አይደል? የታላቅ ወንድም ደንቡ ነው› በሚሉ ቤተ ሰቦች ወይም ሽማግላች ቀልድ እንደሚኮላሽ አስባለሁ፡፡
ግን እኅቶቻችን ከቤት እስከ ቢሮ እየተጠቁ፣ ያውም በዘመዶቻቸውና በባሎቻቸው፣ በወዳጆቻቸውና በቀራቢዎቻቸው እየተዋረዱ እስከ መቼ? ያውም በ21ኛው መክዘ፡

80 comments:

 1. በተማሩት ትምህርት አመለካከታቸው የተለወጠ ሰዎች ዕድለኞች ናቸው፡፡
  thank you

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ehetochachen kebet eske biro eyeteketu yawem begeza zemedochachew bebalochachew bewedajochachew bemikerarebuwachew eyetewaredu eskemeche?yawem be 21 metok/z.Lebe yeseten.

   Delete
  2. ወንድሜ አመለካከት እኮ የሚቀየረዉ በተማሩት ትምህርት ሳይሆን በኖሩት ኑሮ እና ሚኖርበት ህብረተሰብ በፈጠሩበት ተጽዕኖ ምክንያት በሚማረዉ የህይዎት ተሞክሮ ነዉ፡፡

   Delete
 2. Dear Daniel,

  Regardless of socioeconomic status, this remains one of the deep rooted crimes on women and children. And eventually gives its wide way to domestic violence.
  And here we are facing this day in and day out. It starts addressing the arrogant egocentric alpha male who use any form of abuse as a notion of masculinity. And also the culture that encourages it.

  ReplyDelete
 3. (Some of the guys addicted to it.and they need psychoterapy.)
  Thankyou d/daniel

  ReplyDelete
 4. lik new yetafkew daniel.lene inzi sewoch btimhirt bet saihon yalefut timihirt betu new belayachew lay yalefew

  ReplyDelete
 5. አሁን የሰፈር ወሬ አቀባይ መሰልከኝ ጭራሽ::

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሰሚ ብቻ አንሁን እንማር እኛስ ብለን ራሳችንን እንጠይቅ ያንዱ ሰፈር ስህተት ለሌላው መማሪያ፣ ጥንካሬው ደግሞ አርአያ ሊሆን ይገባል፡፡
   እንድናስተውል ስለረዳኸን እናመሰግናለን

   Delete
  2. ምነው ሀሳቡ ላንተ ውሃ አላነሳም? እንደዛ ከሆነ ሃሳብህን ማስረዳት እንጂ እነደዚ ያለ አፍራሽ ቃል መሰንዘር ተገቢ አይደለም

   Delete
  3. Good comment, but I believe some times it helps for education.
   What I feel is that the article shouts a lot than the existing situation. There is a lot of progress in this regard that should be appreciated than condemned.
   Any way I believe this era is not an era of slapping or kicking any body.

   Delete
  4. የአንድ ሰው ማንነት አፉ ሲከፈት ይታወቃል የሚል አባባል አለ፡፡ ዲያቆን ዳንኤል ከፃፈው ቁምነገር መቅሰም እና ለለውጥ መነሳት ሲገባህ/ሽ እንዲህ ያለውን ቃል መሰንዘር የአስተሳሰብ ደረጃን ትዝብት ላይ ይጥላል፡፡ እንግዲህ እዚህ ላይም የመማር ትርጉሙ ምንድን ነው አያስብልም???

   Delete
  5. sasebewe yehen hasab yesetehewe antem bedula kemeyamenut weggene selehonk newe ....kaltesemamahebet eko hasabehen mestet enji terfe neger menager tegebi aydelem ....awo demo atersa hulu neger kesefer tenesto newe wede hager yemitelelefewe

   Delete
  6. I can't blame U. Because I guss you brought up with the family who encouraged vilence against women. That's why this issue seems easy for you. We all have the responsibility to end this violence and it needs comprehensive approach. Thanks Daniel.

   Delete
  7. ብዙዎቻችሁን ካዳመጥኩ በኋላ ተመልሼ መጣሁ፤

   "አሁን የሰፈር ወሬ አቀባይ መሰልከኝ ጭራሽ::" ብያለሁ! አሁንም እላለሁ::

   ሃሳብን መቃወም በጠላትነት አያስፈርጅም:: የአንዳንዶቻችሁ አስተያየት በአዎንታዊ መልኩ የምወስደው 'የሰጠሄውን አስተያየት አንስማማበትም፤ ተገቢም አይደለም፤ በመረጃ አስደግፈህ ሃሳብን በሃሳብ ተቃወም' የሚል እንደሆነ ተረድቻለሁ:: ይህንን ላላችሁ አዎ ተገቢ ነው ብዬ በሃሳብ ለመሞገት ሌላ ጊዜ እመለሳለሁ::አስተያየታችሁን ግን ተቀብያለሁ:: ከዚህ አንጻር ዳንኤል ራሱ ይህንን አስተያየት (ድጋፍም ይሁን ተቃዉም፤ ውዳሴም ይሁን ኩነኔ) ለእናንተ በማድረሱ አመሰግነዋለሁ:: በተረፈ ግን የግድ ለአንድ ግለሰብ ድጋፍ ለመስጠት አታሞ መምታት ያስፈልጋል ብዬ አላምንም:: የሌሎቻችሁ አቀራረብ ያንን ስላመላከተኝ ነው፤ ደፍሬ የምናገረው:: እንዲያው ዳንኤልን አይነኬ እንቁ የሆነ ሰው አድርጎ መሳል የተጠናወታችሁ ይመስለኛል::

   እስቲ መለስ ብላችሁ ከኣሁን በፊት "ኣጣልቶ የሚያፋቅር ትዳር ይስጣችሁ" ያለበትን የምክር ጽሑፍ ገምግሙና ከዚህኛው ጽሑፉ ጋር አናብቡ:: ተቃርኖን ፈጥሮብኛል እኔ:: የአንዳንዶቻችሁ ደግሞ ይገርማል እኔ የሰጠሁት አስተያየት በጥቅሉ 'ዳንኤል የጻፍከው አጻጻፍ የሠፈር ወሬ ሆነብኝ' ነው ያልኩት:: የዳንኤልን እናት: አባት: እህት: ወንድም ወይም ቤተሰብ የሚነቅፍ ነገር አላነሳሁም:: ላነሳም አልችልም አይገባምም፤ የእናንተ ደርሶ ጭራሽ የእኔን ቤተሰብ ለመንቀፍ መዳዳት ከእኔ (ራሴን ጥፋተኛ አድርጌ እንኳን ብቆጥር) የባሳችሁ መሆናችሁን ነው የሚያስገነዝበኝ::

   ነገርን ከምንጩ ሳይገነዘብ አጣርዞ ጽፏል:: የተማረ ሁሉ ካልተማረው የተሻለ ያስባል የሚል ጭብጥ ይዞ ነው ሊሞግተን የተነሳው ዳንኤል:: የተማረ የምንለው መጻፍና ማንበብ ስለቻለ ነው ወይ? ከዚህም በላይ የጉዳዩን ምንጭ ሊያጣራ አልፈለገም፤ ልክ ፊት ለፊት ላይ ያያትን ይዞ ነው ወደ ጽሑፍ የገባው/የሮጠው ዳንኤል:: 'ምንስ ቢሆን እንዴት በጡጫ ይታሰባል የሚል' መከራከሪያ እንደምትይዙ እረዳለሁ:: ያንን ጥፋት የሚደግፍ አካሄድም የለኝም፤ ከሥር ሳላጠራ ግን እንዲያው የማይቀለበስ ጉድ ተፈጠረ ብዬ ግን አልጽፍም:: ምንም ይሁን ምን አለመስማማት መብት እንጂ ግዴታ አይደለም:: እናም ዳንኤል 'ዝምታ አንዳንድ ጊዜ ጥሩ አይደለም' እንዳልከው ሁሉ እኔ ደግሞ "ሁሉም ነገር ታየ/ ተገኘ ተብሎ አይጻፍም" እልሃለሁ ለዚህም ይህንን ጽሑፍህን አልተስማማሁበትም:: በድጋፍ ሊጥሉህ ለሚዳዱት ግን ምክርህን ለግሳቸው:: ራሴ ብሰደድም "የተሰደዱ ስድቦች"ን ይዤ አልመጣሁም::

   Delete
  8. ወንድሜ ሆይ!!! እያንዳንዱን ማህበራዊ ክስተት ካስተዋልከው አስተማሪ ሆኖ ነው የሚያልፈው፡፡ ዳኒም ያስተዋለው ይህንኑ ነው፡፡ ዘመኑ የውይይት እንጂ የርግጫ አይደለም፡፡ ወንድም ዳንኤል ባገኘው አጋጣሚ አስታኮ የሚያቀርባቸው ጽሑፎች ልብ ይነካሉ፡፡ ይህንን ብሎግ ከእድሜ፣ ከትምህርት እና ከጾታ አኳያ ስንት ሰው ይጐበኘዋል? በዚህ ጽሑፍ የነበረበትን አስተሳሰብ (በጡጫና በስድብ ንዴትን መወጣት) ሊለውጥ የሚችል ሰው ይኖራል እና ነጋቲቭ አትሁን፡፡ ነገሮችን በበጎ ጐናቸው ተመልከት፡፡ ስደተኛነትህ እንዲህ ሊያደርግህ አይገባም፡፡ አይዞህ፡፡

   Delete
  9. ወንድሜ አንድ ነገር በትልቁ የተሳሳትክ ይመስለኛል፡፡ ”አጣልቶ የሚያፋቅር…” የሚለውን ጽሑፍ ስታነብ “ግጭት እስከምን ድረስ?” የሚለውን አላስተዋልከውም፡፡ ላንተ የገባህ (እኔ እንደተረዳሁት)“ ግጭቱ ምንም መልክ ይኑረው ያው መጋጨት ያለ ስለሆነ ዳንኤል በዚህኛው ጽሑፉ አትጋጩ እያለ ከመጀመሪያ ሐሳቡ ጋር ተቃርኗል” በሚል መልኩ ነው፡፡
   እውነታው ግን ይህ አይደለም፡፡ በፍቅር ውስጥ ያለ ግጭት ገደብ አለው፡፡ መከራከር፣ መጨቃጨቅ፣ መኳረፍ፡፡ ከዚያ ቆይቶ ሰላም ይወርዳል፣ ፍቅር ይመለሳል፡፡ ከዚህ ሲያልፍ ግን አደጋ ነው፡፡ ግጭት እስከዱላ፣ ግጭት እስከ አሲድ መድፋት፣ ግጭት አካል እስከማጉደል፣ ግጭት ነፍስ እስከማጥፋት ከሆነ ጠላትነት ይሆናል፡፡ ያ ጽሑፍ በዚህ መንፈስ የተጻፈ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ስለዚህ ከአክብሮት ጋር ያንተኑ አባባል ልዋስና ፡- ፊት ለፊት ያየሃትን ብቻ ይዘህ ወደ አስተያየት ከመግባትህ/ከመሮጥህ በፊት ፈረንጆቹ እንደሚሉት “በመሥመሮቹ መሐል አንብብ፡፡” የያዝነው ተራ ጉዳይ አይደለም፡፡ ትናንት እንደቀላል አይተነው ዛሬ ብዙ ዘግናኝ ታሪኮችን እየሰማንበት እና እያየንበት ያለ ጉዳይ ነውና፡፡

   Delete
  10. Lesson starts from your house, village and from your env't wherever you were born or raised or living dude. Don't get wrong. I know you want to see in his article or blog only about biblical lessons and I would say you are wrong. You may be one of the guy or lady beating some of your relatives. God bless you anyway and watch out you fingures.

   Delete
  11. አሁንም ለዳንኤል ድጋፍ ከመስጠት ያለፈና ቆይ እንደዚህ ላላት ነገር እንዲህ ልብለው ከሚል የቃላት ተኩስ ውጪ ቁምነገር አላገኘሁባችሁም አንዳንዶቻችሁ ላይ:: እናም የሁሉንም በዚህ ልደምድምና ሚዛን ይደፋል ልንከራከር እንችላለን ብዬ ካሰብኩት ከአቶ አስናቀ(ማዕረግ ከተሳሳትኩ ይቅርታ ይደረግልኝ)ላይ መልስ ልስጥ::

   "የያዝነው ተራ ጉዳይ አይደለም፡፡" ያልከው አቶ አስናቀ አዎ ተራ ጉዳይ አይደለም ግን ከጉዳዩ ይልቅ እኔን ሳትረዳ መከራከር ያዝክ:: እውነት ያየናቸውና የምንሰማቸው የዘግናኞቹ ጉዳዮች አሳስበውን ከሆነ ክርክራችን በዚህ መልኩ መሆን አልነበረበትም:: የዘግናኞቹ ጉዳዮች መነሻ ይታወቅ፣ ከላይ እሳቱ ሲንቦገቦግ አቃጠለኝ ብሎ ከመጮህ 'ፍሙ የቱ ጋ ነው ታዳፍኖ የተቀመጠው?' ብሎ መጠየቅ ይገባል ነው የእኔ ነጥብ የነበረው:: ዳንኤል የተዳፈነውን ፍም ትተህ ከላይ የሚንቀለቀለውን እሳቱን ያዝክ ነው ያልኩት:: ስለሚበራው አምፖል/ሻማ ሳይሆን ከታች "ጀነሬተሩን" ስለሚለኩሰው እና ነዳጅ ስለሚያቀብለው ነው መነጋገር ያለብን:: ለዚህ እንደፈረንጅ መሥመሮቹ መሐል አንብብ አልልህም:: ባይሆን እዚያው ላይ ጌትነት እንየው በግጥሙ እንደገለጸው "ቅኔ ስደተኛ" አትሁን እልሃለሁ:: ባላነብማ ባልተቸሁህ ነበር:: ጉዳዩ ቀላል ቢሆንማ ከመነሻ ይታይ ባላልኩህ ነበር:: አንተም ጉዳዩ ቢሰማህና እንደ ቀላል ባትቆጥረው ሐረግ እና ቃላትን መዝዘህ ይህችን ቃል ስለ ተናገረ እንደዚህ ብዬ 'ወጋ ላድርገው ቆይ' ዓይነት አጻጻፍ ባልጻፍክ ነበር::ለስድብ ወይም ለዘለፋ አንደበት እያሰሉ "ከአክብሮት ጋር ያንተኑ አባባል ልዋስና ፡-" ብሎ መቀጠል ምን አስፈለገ? ትህትናም አይደለም እኮ ይሄ! ጥያቄህ ጉዳዩ ጋ ከሆነ ጉዳዩን አስረድቶ ለመፍትሔ መጋበዝ ይሻል ነበር:: "ወንድሜ" ብሎ ጀምሮ በስድብ መደምደም የ"መንፈሳይ" እንጂ የ"መንፈሳዊ" ሰው ንግግርም አይደለም::

   Delete
  12. It seems complex የሚውደድ ሰው የሚያስቀናህ ትመስላለ

   Delete
  13. ምላሽህን ደግሜ፣ ደጋግሜ አነበብኩት፡፡ ጊዜ ሰጥተህ በማንበብህና መልስ በመስጠትህ አመሰግናለሁ፡፡ ነገር ግን ምላሽህ ከተነሳንበት ርዕሰ-ጉዳይ እየራቀ፣ ወደቃላት ስንጠቃ እና የመልስ “ምክቶሽ” ማምራቱን ተመልክቻለሁ፡፡
   እኔን አስመልክቶ ካነሳኻቸው ነጥቦች ልነሳ፡፡ “ለስድብ ወይም ለዘለፋ አንደበት እያሰሉ "ከአክብሮት ጋር ያንተኑ አባባል ልዋስና ፡-" ብሎ መቀጠል ምን አስፈለገ? ትህትናም አይደለም እኮ ይሄ! ጥያቄህ ጉዳዩ ጋ ከሆነ ጉዳዩን አስረድቶ ለመፍትሔ መጋበዝ ይሻል ነበር:: "ወንድሜ" ብሎ ጀምሮ በስድብ መደምደም የ"መንፈሳይ" እንጂ የ"መንፈሳዊ" ሰው ንግግርም አይደለም::” ብለሃል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ያንተን አባባል የተዋስኩት ክርክራችንን በአንድ ገጽ ላይ ሆነን እያደረግን እስከሆነ ድረስ ለአስተያየቱ እኩል የሆነ ምላሽ መስጠት ተገቢ ነው ብሎ በማሰብና ያንተ አባባል ለነገራችን ጥሩ ማሠሪያ ነው ብዬ በማመን እንጂ ምንም ዓይነት የስድብና የዘለፋ፣ የአሽሙርና የአግቦ ንግግር አስቤ አልነበረም፡፡ ሁለተኛ፡- እኔ አስተያየቴን የሰጠሁት እንደ “መንፈሳዊም” ሆነ እንደ “መንፈሳይ” ሰው ሳይሆን እንደ “ሰው” ብቻ ነበር፡፡ መነሻዬም የሰለጠነ ክርክር ማድረግ እንጂ ዘለፋና ስድብ ፍላጎቴ አይደለም፣ ጊዜውም የለኝም፡፡ አንተ ግን ከፍሬ-ሐሳቡ ይልቅ “እንዲህ ሲል እንዲህ ለማለት ፈልጎ ነው” ወደሚል የሴራ ንድፈ-ሐሳብ (Conspiracy Theory) ወሰድከው፡፡ ለማንኛውም የቃላት አጠቃቀሜ “ስድብ” ሆኖ ከተሰማህ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡
   ወደ ቀሪው የመልስህ ክፍል ስመለስ፣ ከጉዳዩ ይልቅ አንተን ሳልረዳ መከራከሬን ገልጸሃል፡፡ እውነታው ግን የተገላቢጦሽ ነው፡፡ አንተ ለእኔ ምላሽ ለመስጠት ስትነሳ እኔ ለየትኛው አስተያየትህ መልስ እንደሰጠሁ እንኳን ልብ አላልከውም፡፡ የእኔ አስተያየት ከዚህ ቀደም ዳንኤል “የሚያሸንፍ ፍቅር” በሚል ርዕስ በጻፈው ጽሑፍ እና “እስከመቼ” በሚለው ጽሑፍ መካከል “ተፈጥሮብኛል” ያልከውን ተቃርኖ አስመልክቶ “አልተረዳኸውም” ያልኩትን ክፍል ማጥራትን ግብ ያደረገ ነበር፡፡ ያንተ ምላሽ ግን በሁለተኛው ጽሑፍ ላይ ብቻ አተኮረ፡፡ ስለዚህ አንተ የኔን መነሻ ሳትረዳ ጻፍክ እንጂ እኔ ፍሬ-ነገሩን አልለቀቅኩም፣ ያንተን ሐሳብ መነሻም ሳልገነዘብ አልጻፍኩም፡፡
   እሺ ይሁን፡፡ በአሁኑ አስተያየትህም ላይ ቢሆን መከራከር እንችላለን፡፡ ስለ አንድ ነገር አስተያየት ከመስጠት በፊት የነገሩን መነሻ ማወቅ እንደሚገባ እኔም እስማማለሁ፡፡ “ነገርን ከሥሩ፣ ውሃን ከጥሩ” ይባል የለ በአገራችን? ነገር ግን “ከላይ እሳቱ ሲንቦገቦግ አቃጠለኝ ብሎ ከመጮህ 'ፍሙ የቱ ጋ ነው ተዳፍኖ የተቀመጠው?' ብሎ መጠየቅ ይገባል” የሚለው ምሳሌ “ከፈረሱ ጋሪው” የቀደመበት ዓይነት መስሎ ታይቶኛል፡፡ ከታች ያለውን የፍሙን አድራሻ ከመፈለግ በፊት ከላይ የሚንቦገቦገውን እሳት ማጥፋት ይቀድማል፡፡ አለበለዚያ ግን በእሳት መካከል ፍሙን ስናስስ መቃጠላችን የማይቀር ነው፡፡ በዚሁ አቅጣጫ ስናየው በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን መነሻ ከመመርመራችን በፊት ለጥቃት የተዘረጉ እጆችን መሰብሰብ ወይም መመከት ቀዳሚ ሥራችን ሊሆን ይገባል፡፡ እህቱን፣ ፍቅረኛውን፣ እጮኛውን ፣ ወይም ሚስቱን ለመምታት የተነሳን ወንድ በመጀመሪያ “ተው!” ብለን ማስቆም፣ ሴቷንም ማረጋጋት፣ ከዚያም “ምን አጋጫችሁ?” ብለን መጠየቅ፡፡ ይህ ነው ትክክለኛው መንገድ፡፡ ሴቷ በጥፊ እየተመታች፣ በዱላ እየተዠለጠች፣ በአሲድ እየተቃጠለች፣ በቦንብ እየጋየች፣ በጥይት ወንፊት እየሆነች፣… ያንን ሳናስቆም መንስኤውን መፈለግ ግን የማይቻል፣ ቢቻልም ዘላቂ መፍትሄ የማያመጣ የ“ውሃ-ቅዳ፣ ውሃ መልስ” ጉዞ ይሆናል፡፡

   Delete
  14. “አሁን የሰፈር ወሬ አቀባይ መሰልከኝ ጭራሽ::” ከመቼ ጀምሮ ነው ይህ አባባል ነገሩን በጥልቀት እንየው ማለት የሆነው?

   Delete
 6. የኔም ህይወት ከዚህ አይሻልም ባለ አንድ ዲግሪእና የተለያዩ ዲፕሎማወች ያሉት የትዳር አጋሬ መወያየት ብሎ ነገር አይገባውም አንድ መሳደብ ወይመማታት ብቻ ነው ያሚቀናው በዚህም የተነሳ ትዳሩን በገዛ እጁ ለያፈረሰው ተዘጋሽቷል የተማረ ግን ያልሰለጠነ ስንት አለ መሰለህ በየቤታችን

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dear ወለተ ሀና,
   Please be wise in protecting your marriage by treating your husband systematically. Be better than your husband, a man having "degree".

   Delete
  2. @October 17
   I do not agree about your conclusion. If your husband had an intention for divorce he will not kick you. But I believe the kick is pushing you to think about divorce. Your on the Verge to give up for nothing.
   Instead of giving up better to work on why that happens. Breaking does not need much effort, because it does not have any good return. Therefore before quiting you should see different alternatives. The best alternative I believe and that I see in my life is change internally. You better to think what change in your self can change the situation. It is a solution for the case , not divorce or anybody. Your change should not be cosmetics, but real to have power and continuity.
   Last but not least is that change in many circumstance is occurred through time. It is only breaking that happens in few time/hour/month/year.Be brave to show that women can make a difference, not only to kick back but to eliminate kicking /harder than kicking back/.

   Delete
 7. እማዋይሽ ከ DCOctober 17, 2012 at 11:14 PM

  ዳኒ እግዚአብሄር አብዝቶ ይባርክህ ባለቤቴ በፍጹም ችግርን በውይይት መፍታት አይሞክርም በሚያስቆጣውም በማያስቆጣውም መቆጣት ይወዳል አሁን አሁን እየሰላቸኝ ነው

  ReplyDelete
  Replies
  1. @ October 17
   You are exhausted for good as you said, but he is not for bad. I do not think he is good for nothing. I think you better think and read why that behavior happens on beloved once. In my opinion, it happens when some one feels belongingness. But I believe also it is not a wise way to show belongingness.
   When such things happen in my experience it is better to show how belongingness could be expressed through personal change, readings,movies ETC. The best way is change. What I read from your article is that you believe the only way to put solution is through discussion. But there are does-en of solution. The best one to bring peace and show belongingness is giving the decision to your partner. This may be a bit difficult, especially for women, but I believe we should strive beyond our feelings to protect our beloved once, marriage and relationship. If have a problem to be out of your feelings better to ask weather you feel married or not. Marriage is a decision to leave beyond feeling. It is a life lead through mind not feelings from our kidney /kulalit yatesewen/.
   It is a life of honor
   It is a life of race that needs ego
   It is a life of education, you learn every time from it
   It is a life of miracles, not only lead by rules and regulation
   It is our arena to be what we are.

   Delete
 8. "የወንዶች ትምክህት የሚለቅቀው መቼና በምን ዓይነት የትምህርት ደረጃ ነው?" ጥሩ ጥያቄ ነው ዳኒ ፡፡ እኔ ግን እንዲህ አይነቱን ወንድ ብዬ ከቁጥርም አላስገባው ፤ የማይረባ ነው፡፡

  ReplyDelete
 9. "ጥሬ ጨው ጥሬ ጨው ጥሬ ጨዋዎች፣
  መሰለቅ፣ መደቆስ ገና ሚቀራቸው"
  ደበበ ሰይፉ

  ReplyDelete
 10. Not only women but also those men who is physically small and unfit including me have no guarantee in the Ethiopian set up.Everybody goes and tries to kick them.

  ReplyDelete
 11. ደበበ ሰይፉ ‹ጥሬ ጨው ጥሬ ጨው ጥሬ ጨዋዎች፣ መሰለቅ፣ መደቆስ ገና ሚቀራቸው› የሚላቸው ዓይነት
  Very thoughtful insight
  Thank you

  ReplyDelete
 12. ehhhhhhhhhhhhhh, endih new engdih. Sorry

  ReplyDelete
 13. sew temiro aimitow kaltelewote yetemare mehayim eyaferan new malet new. "digree chino yemayilewot sew ke mehayimnet yebikat dereja lay dersual malt new" (diaakon Birhanu Admas) endetenagerut.

  ReplyDelete
 14. አበበ ሙ በየነOctober 18, 2012 at 10:13 AM

  ወንድሜ ዳንኤል

  ሴቶች እናቶቻችን: እህቶቻችን እና ምሽቶችን ሆነው እያለ የስነተፈጥሮ ልዩነታችንን ተጠቅመን ለምን እንደበድባቸዋለን? በማናቸዉም ሁኔታ ማንንም መማታት በተለይም ሴቶችን መማታት ከሰዉነት ተራ ወጥቶ ከአዉሬዎች ጋር መሰለፍ ነው::

  በአደባባይ እህቱን እንደደቆሰዉ የሰዉ ከንቱ በግድግዳ ተከልሎ የአዉሬነት ባህሪዉን የሚወጣዉን አጉራ ዘለል ሁሉ ቤቱ ይቁጠረዉ:: ስለዚህ ከተጣባን ከንቱ የባህል ቁርኝት እንድንወጣ የአስከመጥከው ትዝብትና ቁጭት አስተማሪነቱ አያጠያይቀም:: የአንዲት ሴት እንባ ልታበስ እንጂ ሊፈስ አይገባዉም:: እናቱን ለመማታት የማይነሳ ሁሉ እህቱን ወይንም ምሽቱን ለማማታት መነሳት የለበትም::

  ቸር እንሰንበት

  ReplyDelete
 15. "YAWRA DORO DEGREE" YESEWREN KEMALET BEKER LELA MIN YBALAL....BE'WNET YASAZINAL,TIMHIRT BET ,YIBASBILO DEGMO COLLEGE /UNIVESITY "BETSO"ALEMEMARS MOT NEW,YAWM AGERNM RASNM MEGDEL.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Temiro ykir alemalets min ybal yhon? Leziyawm bedlewt? Eyerasachinin bnay tiru ymeslegnal.

   Delete
 16. ye setochenes kebabad sidib astewelewal ke dula yemibelt ye sidib aynet wordobachehu atakum?

  ReplyDelete
 17. D.Daniel, conflict is part of our life. sometimes disagreements can arise. the problem is not why we disagree, argue and sometimes fight. Rather how we solve them afterwards. I don't believe you are perfectly out of such a havoc through out your life. Even your funs who liked your posts. But I don't mean I'm in favor of humiliating women and children...I do hate any personal attack. But we can never avoid such things totally as they are part of our life and that's how we grow up... part of our sociological make up. It stars from our home(parents), the environment we grew up, and the social make up.

  Sometimes women are the source of the problem. I know the there are a lot of mischievous women who always torment their brothers, husbands and colleagues. they provoke you to kick them, slap them across the face...and what ever attack. they say , " let's your manhood, touch me, I'll show you, who do you think I'm?" etc. Most men are intolerant to such things that put their men-hood under question mark. so they fight or flight to justify who they are. I think women should know this fact and must stop using phrases and words. Because eventually they are the victims.

  Anyways thanks for the uplifting post!

  ReplyDelete
  Replies
  1. D.Daniel, conflict is part of our life.Matured!

   Delete
  2. Pls, do not focus on silly and trash issues, while we are engulfed with enormous country wide problems, try to mature like your prefix.

   Delete
  3. Let me guess. One of these "countrywide" problems you're talking about may be the issue of human rights. Don't you think this is one of the major human right abuses in the country? If you're "mature enough," you would have not ignored such incidents that you called "trash," for the accumilation of the "trash" issues makes an "iceberg" of problems.

   Delete
 18. ዳንኤል እንዳለው እኔም ሳነበው ደንግጫለሁ፤ አንዲት እኅት በቢሮዋ ውስጥ ከተደበደበች በሰላም መኖር የምትችለው የት ነው? አንድስ ወንድም የገዛ እኅቱን በአደባባይ ለመደብደብ ምንም ካልመሰለው የእኅቶች ከለላ ማን ሊሆን ነው? አንዳንዶቻችሁ ሰድባው ሊሆን ይችላል ብላችኋል፡፡ ዓይን ስለ ዓይን የሚባልበት የነ ሐሞራቢ ዘመንኮ አልፏል፡፡ የችግሮች ሁሉ መፍትሔ እንዴት ዱላ ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡ እኔ እነዲህ ዓይነት ሰዎች በዝምድና ታጅለው ግፍ እንዲፈጽሙ ሊፈቀድላቸው የሚገባ አይመስለኝም፡፡ እኅቴ ጉዳዩን ወደ ሕግ ውሰጅው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ሰው ከዚህ የባሰ ከማድረግም አይመለስም››

  ReplyDelete
 19. Dn. Daniel,

  Thank you for nice article and observation. I think these kinds of very ugly things are exisitng in our country Ethiopia wether you are educated or not. The main reason for that is how our personality is build up, moral, spiritual and other environmental/surrounding things.
  If a person becomes matured enough with the above things he will not bit his sisters. So lets do from the grass route so as to completely remove these kinds of societal problems.

  God Bless You.

  kebede

  ReplyDelete
 20. Dear Dn. Daniel,

  It is a very nice message we have got. I have very miner points for you to think about it. It is "ሰው ማለት የሚያስብ እንስሳ ነው". I don't think that human belongs to animal to define human being. I think it is not appropriate to use it in this way. But I am always your fun :)

  With regards,

  ReplyDelete
 21. I strongly disagree with the above comment by "Anonymous October 18, 2012 12:21 PM". I assuming its a man, he mentioned that women are the source of the problem. Your comments are very typical of what a man locked up in prison for abuse would say. The man accused of rape would say its not my fault, the woman wore short dress. Or the man in jail for beating up his wife says its not his fault because his wif pushed him. It doesnt matter who is the source of the problem. As God-fearing Chrisitians no matter who is the source of the problem we have to point the finger right back at ourselves. We have to exhibt self control, and think twice before acting on emotions. Oh goodness...If only we all were tolerant of each other, if only we had patience towards one another, if only we were hard on ourselves as we are hard on others I can just imagine how peaceful our world would be...
  -windy city

  ReplyDelete
 22. ከወ/ት መስከረም
  ወንድሜ ዳንኤል ገጠመኝህን ስላካፈልከን እግዚያብሄር ይስጥህ። ችግሮችን መፍታት የሚቻለው እንደዚህ ለሰዎች በማሳወቅና በመመካከር ነው። እዚህ ጉዳይ ላይ የስነ አእምሮ ባለሙያተኞች በሰፊው ትንተና ሊያቀርቡበትና መፍትሄውንም ሊጠቁሙን ይችላሉ። እስከዚያው ድረስ ግን ስህተት መሆኑንና መወገዝ የሚገባው ድርጊት መሆኑ ላይ ግን ልዩነት ላላቸው ሰዎች በጣም ነው የማዝነው። ስሜትን አለመቆጣጠር ትልቅ በሽታ ነው። አንድ የወንጌል ስብከት ላይ የሰማሁትን ላካፍላችሁ ፦ አንዲት የልጆች እናት በተመሳሳይ ሁኔታ የሚያስቸግራት የልጆቿን አባት በየጊዜው የሚደርስባትን ድብደባ ተቋቁማ ከመተኛቷ በፊት ፀሎት ወደ ፈጣሪዋ ታቀርባለች። የዘወትር ፀሎቷም እግዚያብሄር እባክህን ከዚህ ሰውዬ ገላግለኝ ነበር። ምንም ለውጥ ብታጣ አንድ ቀን ፀሎቷን ቀየረችና እንዲህ አለች። እግዚያብሄር ሆይ ይህንን ደካማ ልጅህን የሚሸከምልህ ስላጣህ ለኔ ሰጠህ። ስለዚህ የምለምንህ ትከሻዬንና አስፋልኝ፣ ትግስቴ አጠንክርልኝ አለች አሉ። ፀሎታችን ለደካሞች፣ ማስተዋል ለተሳናቸው፣ ትግስት ላጡ፣ ህሊናቸውን መቆጣጠር ላቃታቸው…………….ሁሉ መሆን አለበት። በተጨማሪም የሕግና የማህበረሰብ ጥበቃ በተጠናከረ መልኩ በተገባር ላይ መዋል ይኖርበታል።

  ReplyDelete
 23. Tuncha yalew betunchaw birr yalew degmo bebru setin yemaychekun kale ygermegnal. Ehtim honech mist hule bebaliwana bewendimua endetewaredech new.Anid nen bilo sint besewna beEgzer fit kal gebto agbtowat, huwala sirash yawtash endi yalkush besihtet new, man esat wst ygebal, belefahubet birr aygebashm yemayl wend kale lene ya kidus new.

  ReplyDelete
 24. መማር የአመለካከት ለውጥ ለማምጣት እንጂ ስራን ሰርቶ ደሞዝ ለማግኘት ከሆን ጥቅሙ ምንድን ነው?

  ReplyDelete
  Replies
  1. Tikmuma gilts new. Sira meyaz newa!Ezyaw melsehew/shiwalko.

   Delete
 25. First and for most i hate any kind of abuse that happen in human being. but i dont agree with ur conclusion .b/c its not men only responsible for gender violence/ physical abuse / it is women too take responsibility for avoiding violence . u know what women verbal abuse motivate men physical abuse. Therfore whenever disagreement happen b/n men and women both should discuss on the issue responsibly .u know what words hurt than punch.therefore dani u should rewrite concerning this one too. dani i saw ur emotion too in this writing, u have to re write again in constructive way.

  ReplyDelete
 26. ሰውን መጥላት ተገቢ ባይሆንም፣ በሕይወቴ በጣም የምጠላው በሴት ላይ እጁን የሚያነሳን “ወንድ” ነው፡፡ ለእኔ ይህ ሰው “ወንድ” አይደለም፡፡ እንደወንድነቴ ይህ ሰው “ወንድ አሰዳቢ” ሊባል ይገባዋል ባይ ነኝ፡፡ ምክንያቱም ከወንድነት መገለጫዎች አንዱ ለሴት ልጅ ክብር መስጠት መቻል ነውና፡፡ በተጨማሪም እንደእኔ አመለካከት ወንድ ልጅ በሴትም ሆነ በሌላ ወንድ ቢበደል እንኳን በደሉን ዋጥ አድርጎ በብልሃት ማለፍ የሚችል ነው፡፡ ወንድነት በጡንቻ ብቻ የሚገለጽ እንደሆነ የሚያስቡ “ወንዶች” ፈረንጆች እንደሚሉት “በመጠን ከሚመስላቸው ጋር” ቢሞካከሩ ይሻላል፡፡ በአጠቃላይ ግን እኛ ወንዶች ሴቶችን አስመልክቶ ያለን አመለካከት ፈውስ ያስፈልገዋል ብዬ አስባለሁ፡፡ ማስተዋልን ይስጠን!

  ReplyDelete
 27. ጥሩ መልእክት ነው፡፡ ግን

  ‹‹ ሰው ማለት የሚያስብ እንስሳ ነው፡፡››

  የሚለው አባባልህ ከሃይማኖት አስተምህሮ አንፃር ሲታይ ስህተት ይመስለኛል ወይ ሳይንሱ ተጽእኖ አድርጎብሃል ወይ ሳታስተውለው የጻፍከው ነው፡፡ እርማት ቢደረግበት ጥሩ ይመስለኛል፡፡

  ReplyDelete
 28. ባሌ ብዙ ዲግሪዎች ኣሉት። መሃንዲስ ነው። ዶክተር ነው። ዲያቆንም ነው። እኔም ዲግሪዎች አሉኝ። ዶክተር ባልሆንም። ሲያገባኝ ያልገባው ቃል አልነበረም። እና ወደሚኖርበት ወሰደኝ። አሁን ግን ኑሮ የተገላቢጦሽ ሆነ። አልሰራ ኣልማር። ቁጭ ብየ መዋል ነው ስራየ። እንድ ነገር ስሞክር እገልግሎት ምናምን እያለ ፈተና ያስመልጠኛል። በዛ ላይ ወንድሙን ካገር ቤት ኣምጥቶ እርሱንም ችዬ እንድኖር አስገደደኝ። ጥዬ እንዳልሄድ ልጃችን ኣሳዘነችኝ። እንዲሁም ክህነቱ በኔ ምክንያት አንዳይጠፋ ፈራሁ። ዕባኪህ ዳኒ ኣገልግሎት ማለት ሚን ማለት ነው። ትዳርስ የባልንና የባል ወንድምን ችሎ መኖር ነው? ቤተሰብህን ሳታገለግል በሰው ፊት መቅለስለስ ጽድቅ ነው። ብዙ ከን ራሰን ስለማጥፋት ኣሰብኩ። ያም ሃጥያት ነው። መፋታትም ሃጥያት ነው። ሊያውም ካህን መፍታት። ቀኑን ሙሉ የተጋባንበትን እለት ስረግም ነው ሚውለው። ብዙ ተስፋና ቲሩ ሞያና ሲራ የነበረኝ ሰው ነበርኩ። ብዙ ሰዎችንም እረዳ ነበር። ዓሁን ግን ክርስትናን ብዬ ሽባ ሆንኩ። መሮኛል አንዲ ብዬ ምቀጥል ኣልመሰለኝም። እና ዳኒ ባክህን ስለ ኣገልግሎት ምንነት ጻፍ ና ቲዳረንና ህይወቴን ታደግልኝ። ባሌ ብሎግህን ያነባል እና እርዳኝ። ሰዉ ችግርህን ስታወራው የኣገልግሎት መሰናክል የሆንክ ነው ሚመስለው። በዛ ላይ የቤትን ገበና አደባባይ ማውጣት ያስጠላል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. @ anonymous October 19
   From your piece I feel that you are very submissive. But I also understand that you demand more in your marriage. The paradox happens here, between submissiveness and demand. If you want to make your life enjoyable you better choose from the two and work it wisely. The first one needs to give your self only, but to hard. The second needs much work, but not that much hard in my opinion.Any way both chooses needs consideration of the present situation and planning for the future, but it needs praying and regular treatment.
   As much as possible work what is expected from you in the same at any time, but try to explain for your partner what he should have to do to make you enjoyable.
   Giving up is a sign of weakness, do not think this as a solution. I believe you have the capacity to try many alternatives. May God help you ....

   Delete
 29. ከኣሁን በፊት ኣጣልቶ የሚያፋቅር ... ያለከዉን ሳስብ ግራ ገባኝ የተናገርከዉ ደረቅ ሎጂክ እንጂ የሰዉ ጠባይን ኣየንፀባርቅም። ሰዉ ሲናደድ ወንድም ይሁን ሴት ለቅፅበት ያህል ራሱን ይስታል እና ለዚህ ተጠያቂዉ ለዚህ ያበቃቸዉን ጉዳይ ዘንጋት የሰዉን ደካማ ባህሪ ኣለማገናዘብ አይሆንም ወይ?
  ለማንኛዉም ሰላሙን ያብዛልን ኣሜን

  ReplyDelete
 30. Dear Daniel. I was kind of blind and bully and one day i decided to murder my wife because i found out she cheated on me. I bought a pistol and was ready to fire. However, i also wanted to know the whole story of the cheating because i was fuming with jealousy. She was, to make it worse, very economical in her admission. The next day i was arrested and charged with illegal posession of weapons because my wife later refused to testify that i wanted to kill her. I was found guilty of illegal weapon and penalised a mere 100 Birr. That was not justice but my wife forgave me. Although my wife still wanted to be with me, I divorced my wife because i could not get over the incident of her cheating on me and from then on i became religious devotee. Of all things now i hold the highest respect for women. I wish i could live my life never to have touched or insulted a woman.

  ReplyDelete
 31. Hello Dn Daniel this is a googd example to our society who far apart from sprituality and so many other hiden in everywhere including shooting pls wath more in police program at ETV. she is symbolic for our church to me and image and think about our church who kicked by her children not by brothers.
  our church Tewahedo now?
  every body who have muscular showing his arm on our holy fathers to influence the patriaric election for they needs like nation money and corruption and this is more than that girl and her brother to me.
  pls say some about the current issues of peace and unity to our church strenght and do not kill your time on socioeconomic and folklore pls this is solved if only if the source (our church teaching)is pure and clear.

  ReplyDelete
 32. This is just one fight between a brother and sister.I don't like the way her brother tried to solve their problem. As the result both will be affected. But what makes you so upset when you live in a country where arrogant leaders perscute,jail,kill journalists,political opponents,citizens just because they challenge them by speaking up?

  ReplyDelete
 33. bilih kemogn sihitet yimaral mogn gin.....
  memar berasu eko yetsebay, yasitesaseb lewit ne...

  ReplyDelete
 34. Egziabher Ethiopian yibark yasazinal yihe temelketu!
  http://www.tigraionline.com/articles/article120954.html

  ReplyDelete
 35. yasazinal yihe temelketu Egziabher Ethiopian yibark!
  http://www.tigraionline.com/articles/article120954.html

  ReplyDelete
 36. We are better than any creature in this world as human being. I am very surprised of men’s inappropriate approaches to deals on any issues in their advantage. Who give men power to insult our sister, wife, and our mother in front of people? Who give men power to disgust and kill our beloved sisters, mothers and daughters? As if he is eligible to go with girls, he proud of talking as if he is the hero of this world. He also drinks and entertains himself as law support him. But, when our mother, sister daughters try to confront him, he run for pistol and shout and start to behave and act as animals. Why is that all these deprived from our beloved women and why all miracles and opportunities given to men? Let us fight these animals that kill our mother, wife, sisters and daughters!

  ReplyDelete
 37. ebakachu wondimochina ehitochi andin hasab manim yakiribewu man linimezinewu yemigebawu hasabun enji yebalebetun maninet mehon yelebetim.elay kebizuhanu gar mugit yegetemewu wondimachinim yegetemewu yihewu newu .hasabun yejemerewu kewondimachin dn kibiret maninet lay newu(...yesefer worie akebay...!). minale feresu ke gariwu bikedim...hasabu kesidibu bikedim maletie newu. lemanignawum hulachihum melkam nachihu!

  ReplyDelete
 38. በ18 ጥይት የቀድሞ ባለቤቱን በመሀል አዲስ አበባ ገደላት


  ጓደኛችንን ለመቅበር በተዘጋጀንበት ወቅት ከበስተኋላ ከፍተኛ የመኪና ክላክስ ሰማን ፤ የመኪናው አካሄድ ፍሬን የበጠሰ መኪና ይመስል ነበር ፤ ብዙም ሳይቆይ የበርካታ ጥይቶች ድምጽን ሰማን ፤ ወደ ቦታውም አመራን ፤ የገዛ ባለቤቱ ላይ ጥይት ያርከፈከፈ ሰው በትራፊክ ፖሊስና በበርካታ ሰዎች ተከቧል ፤ ልጅቷንም ወንፊት
  አድርጓታል ፤ ሰውየው ለግድያ የተጠቀመበት መሳሪያ በግለሰብ እጅ መገኝቱ አስገርሞናል ፤ ብዙም መቆም አልቻልንም ከቦታው ዘወር አለን ፤ በስተመጨረሻ ሲጣራ የተኮሰባት የጥይት ብዛት 18 መሆናቸው ታወቀ ፤ ጆሯችን የሚሰማው አይናችን የሚያየው መልካም ነገርም ጠፋ ፤ከዚህ አይነት ነገር ይሰውረን
  በሟች ዙሪያ ሪፖርተር ጋዜጣ በረቡ እትሙ ዘርዘር ያለ መረጃ ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጠቀሙ
  http://www.ethiopianreporter.com/news/293-news/8220-2012-10-24-06-29-26.html

  ReplyDelete
 39. AnonymousOctober 19, 2012 6:12 PM
  Yetwededech ehete Balebetech wechi amtto mesrat endalchalch negerchen Ene gen And neger lemkerech: BEZU GEZE EGNA BEBETEKERSTIAN YADEGEN TEDAR SENEYEZ !!! YEMELAKT NURO YEMENENOR YEMESLENAL!!!!gen tedar malet
  1, TEGESTEN YEMITEYEK
  2; MASTEWALWEN YEMIASFELEGEW
  3;TEBEBEN YEMIFELEG
  TALAK YEFETENA EGNA YEWKET TEMHERT BET NEW ANCHI DEGMO YEGZIABHEREN MELKAMUN HULU EYETEMEGNECH BETEBEB BESELOT LEMEGNEW ERSU HULUN YADERGALENA GEN YEHENEN HULU SELECH ANDEN NEGER ASTEWYE !!!SETEGENAGNU yegetan fekad teyekechal weyes melkena tekemen aytech new eraschen mermeri?????? ene yehenen yemelech semetawi endatehognie beye new keza beterefe yemtasebiwen hulu teyew erasechen besera egna bemanbeb aschenekiw lela endatasbie egnem endeanchi neberku ye 15 amet tedar new yalegn
  EGZIABHER MELKAM MELKAMUN HULU YASASBECH
  YEWCHI AGER HYWET TALAK FETENA NEWENA
  EHTECH KE GERMEN!!!!

  ReplyDelete
 40. የ ሀበሻ ወንድ እኮ መቼም አይሰለጥንም ቢማር ባይማር፡፡ አስተ ስደተኛው ደግሞ ዳኒ እኮ የሚጽፈው ድርሰት አይደለም፡፡ አሁን እስኪ "ኣጣልቶ የሚያፋቅር ትዳር ይስጣችሁ" እና ይሄን ጽሁፍ ምን አገናኘው? ግድ እኮ መንቀፍ የለብህም. ዋናው ነገር እኮ ያስተላለፈው መልእክት ነው፡፡ እግዚያብሄር ልቦናህን ይክፈትልህ፡፡

  ReplyDelete
 41. even in zis comments i can see people still blaming women. she is z one who has been hit? how can u say women is pushing men to hit her. whatever she said, done, or do, she should not be HIT by anybody. pls try to mature.

  ReplyDelete
 42. መቼም የሰዉ ኑሮ ገጠመኝ ነዉና
  አጋጣሚ ሆኖ ከሰዉ ብትጣላ ዱላህን አታንሳ ዘመኑ አልፏልና
  ወይም አትሳደብ ያስነዉራልና
  ቴስታ ታዉቅ የለም የጭንቅላት ቴስታ
  በል በጭንቅላትህ ጭንቅላቱን ምታ::

  ካነበብኩት የተወሰደ

  ReplyDelete
 43. Morally and Politically correct article!!

  ReplyDelete
 44. Some people get famous by insulting honorable people. People respect Daniel not for the sake of Daniel but for the Lord God who has appointed him for us to get God's maessages.

  As for me I respect even the trees growing in Churches than any others ones let alone those who feed us the word of God.

  It is God and God's people that we respect not a person as an individual.

  Even if you are to raise a point against him(Daniel) I wish you used a better language.

  After all "Let us do just as we want others to do unto us".

  Christianity is a religion of Peace and Love not disputes and foul languages against your brother.

  ReplyDelete
 45. ware ware ware....mindinew zim bilo mechekachek?

  ReplyDelete
 46. ዳኒ የምትጽፋቸው ጽሑሁፎች ሁሉ አሰተማሪዎች ናቸው አያዋዙ ሉሉ ትምህርት ሰጪዎች ናቸው ከአስተያየት ሰጪዎችም ግማሹ ሲቀበልህ አንዳንዱ ያልሆነ አስተያየት ሲሰጡህ አያለሁ ሁሉንም በጸጋ እንደምትቀበለው ሁሉ ጥሩ አድርገሀል የሚሰጡህ ምላች ላንተም ቢጽሑ ትምህርት ሰጪና ለጽሑፍ ይረዱሃል የሰውን አመለካከትና አስተሳሰብ መረዳት ትችላለህ ላንተ ብቻ አይደለም ለብሎግ ተከታታዮች ሁሉ ይጠቅማል በተለይ መልሶቻቸውን ተቀብለህ ማውጣት ጥሩ ነው አንዳንድ ዌብሳይቶች አሉ አስተያየት ሲሰጧቸው ጆሮ ዳባ ልበስ የሚሉ ምናልባት ማንነተቸውን ስለተገለጠባቸው ሊሆን ይችላል ስለዚህ የነሱ ዌብ ሳይት መክፈት ደግሞ የሰዎችን ስም ለማጉደፍ ለመኮነን ብቻ ይሆናል ብዬ ነው የምገምተው ስለዚህ ካንተ እንዲማሮ በዚህ አጋጣሚ እገልጻለሁ ማንነታቸውን ስለሚያውቁት ሲያነቡት ማንን እንደተባለ ያውቃሉ ብቻ ዳኔ ሰው ሲባል የተወሰኑት ማለቴ ነው ከመጻፍና ከመናገር በስተቀር ስለራሳቸው ሕይወት እንኳን የማያስቡ ናቸው የቱ ብናገር እግዚአብሔር ደስ ይለዋል የትኛው ያስቀይመዋል አይሉም ምናልባት አሁን እንደፈለግሁ ሆኜ ጊዜ ሞተ ሲደርስ ንስሀ አገባለሁ ብለው ይሆን ያችን የቁርጥ ቀን ማን ያውቃታል ብቻ ፈጣሪ ያስበን ሁላችንንም አይነ ልቦናችንን ያብራልን ዳኒ አንተም አምላክ በሰጠህ ፀጋ ለሁሉም ትምህርት ሰጪ የሆነውን አገልግሎትህ ያብዛልህ

  ReplyDelete
 47. ሲጀመር የሴቶችን ነገር እንዲህ ብቻ ማሰብ ይከብደኛል፣ እና ብዞዎቻችን ምክንያቱን እንኳ አንጠይቅም ወንድን መውቀስ እንጅ ይህ መፍትሄ አያመጣም፣ ነገርን ከምንጩ እንጅ፣

  ReplyDelete
 48. lets ask what would the women do when they get the power ........... treat us like kings or .........

  ReplyDelete
 49. dani bergt tiru newu gin IHAVE ONE Quetion dani yanten yehiwot tarik letmihirt yhonen zend bettsefiln kelijinet eskewket malet newu b/c getemengochih hulu yesewoch bicha hone hamet ayhonim bergt ante yeset gif yelebihm?.........bizu malet ychalal.................sorry hod basegn

  ReplyDelete