Tuesday, October 16, 2012

ገናዧ


ከላስ ቬጋስ ወደ ፊኒክስ አሪዞና በዩ. ኤስ. አየር መንገድ በመጓዝ ላይ ነበርኩ፡፡ የተቀመጥኩት በአውሮፕላኑ ወገብ ላይ ነው፡፡ ከእኔ ቀጥሎ አንዲት ወጣት ሴት፣ ከእርሷም ቀጥሎ አንድ ሽማግሌ በመስኮቱ በኩል ተቀምጧል፡፡ አውሮፕላኑ ተነሥቶ ጥቂት እንደተጓዘ የበረራ አስተናጋጇ ‹አሁን የኤሌክትሮኒክስ መሣርያዎቻችሁን መጠቀም ትችላላችሁ፣ ከስልክ በቀር› ስትል ሁሉም ኮምፒውተሩንና አይ ፓዱን መመዥለጥ ጀመረ፡፡
‹እኔስ የአበሻው ልጅ እንደ አባቶቼ ጎራዴ መመዥለጥ ቢያቅተኝ እንዴት አንድ አሮጌ ላፕ ቶፕ መመዥለጥ ያቅተኛል› ብዬ መዠለጥኩ፡፡ አንድ የማርመው ጽሑፍ ነበርና ያንን ከፍቼ ስሠራ ድንገት ከቀኝ ጎኔ ‹‹ይቅርታ›› የሚል ድምፅ ሰማሁና ዞር አልኩ፡፡ ልጅቱ ናት፡፡ ‹‹የምታነብበት ቋንቋ ምንድን ነው?›› ብላ ጠየቀችኝ፡፡ አማርኛ መሆኑንና የኢትዮጵያ ቋንቋ መሆኑን ነገርኳት፡ ያው እነርሱ ማድነቅ ልማዳቸው ነው ‹‹ዋ......ው›› ብላ አደነቀች፡፡ ከዚያ ደግሞ ስለምጽፈው ነገር ጠየቀችኝ፡፡ እርሱንም ነገርኳት፡፡ 
 ‹‹ደራሲ ነህ እንዴ?››አለችኝ፡፡ ምን እንደምሠራ ነገርኳት፡፡
‹‹የሚጽፉ ሰዎች ያስደስቱኛል›› አለች፡፡
‹‹ለምን?››
‹‹ዕውቀትና ሃሳብ ማካፈል በጣም ጥሩ ነዋ››
‹‹አየህ ስለዚህ አውሮፕላን ፍጥነት፣ ጽዳት፣ ውበትና ምቾት ለማሰብኮ አውሮፕላኑ መሥራት አለበት››
ራሴን ነቀነቅኩ፡፡
‹‹አንድ ሰው አእምሮው ካልሠራ በሌሎቹ ነገሮች ብቻ መኖር አይችልምኮ፡፡ አእምሮው እንዲሠራ ደግሞ ማሰብ አለበት፤ እንዲያስብ ደግሞ ዕውቀት የሚያካፍለው ያስፈልጋል፡፡ መብላትና መጠጣት እንድትቆይ እንጂ እንድትኖር አያደርጉህም››
ዛሬ ከፈላስፋ ጋር ነው የተቀመጥኩት አልኩኝና ምን ማለቷ እንደሆነ ጠየቅኳት፡፡
‹‹‹መኖር›ና ‹መቆየት› የሚለያዩ ይመስለኛል፤ መኖር የኅሊና፣ መቆየት ግን የአካል ነው፡፡ እየበላህና እየጠጣህ ሳትሞት ብዙ ዘመን መቆየት ትችል ይሆናል፡፡ በመብላትና በመጠጣት ብቻ ግን መኖር አትችልም፡፡ ለመኖር የኅሊና ምግብም ያስፈልግሃል፡፡ በነገራችን ላይ እኔ በተለያዩ ሀገሮች የሚገኙ ጸሐፊዎችን መብቶች ለመጠበቅ የሚሠሩ ተቋማትን በዐቅሜ በገንዘብ እረዳለሁ፡፡›› አለችኝ፡፡
‹‹ለምን?››
‹‹እንደ እኔ ይህች ዓለም የሰዎች መኖርያ እንጂ መቆያ መሆን የለባትም ብዬ አምናለሁ፡፡ ሰዎች እንዲኖሩ ደግሞ የኅሊና ምግቦች ያስፈልጓቸዋል፡፡ የሚነበቡ፣ የሚታዩ፣ የሚጎበኙ፣ የሚሰሙ፣ ነገሮች፡፡ ምግብ ስንበላኮ ምግቡ በቀጥታ ደም ሥራችን ውስጥ አይገባም፡፡ የራሱ ሂደት አለው፡፡ በዚያ ሂደት ብዙ አካላት ይሳተፋሉ፡፡ አእምሮምኮ የሚያላምጠው፣ የሚፈጨው ነገር ይፈልጋል፡፡ ወዲያና ወዲህ የሚያመላልሰው፡፡ ይህንን ከሚሰጡን ሰዎች መካከል ናቸው ጸሐፍት፡፡ ለዚህ ነው የምደግፈው››
ወደ ሀገሬም፣ ወደራሴም እየሄድኩ እየመጣሁ እሰማታለሁ፡፡
‹‹አንቺ ይህንን አስተሳሰብ ከየት አገኘሽው?››
‹‹አጎቴ በጣም ጎበዝ ሰው ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲ ያስተምራል፡፡ ከጓደኞቹ ጋር የውይይት ክበብ አላቸው፡፡ ይከራከራሉ፡፡ እኔም አንዳንድ ጊዜ እንድሳተፍ ይጋብዘኛል፡፡ ከእነርሱ ብዙ ተምሬያለሁ፡፡ አንደኛው ጓደኛው ሰውን ‹ለማሰብ የሚበላና›፣ለመብላት የሚያስብ› ብሎ ሲከፍለው ሰምቼዋለሁ፡፡ ››
‹‹አንቺስ ምንድን ነው የምትሠሪው? አልነገርሽኝምኮ›› አልኳት፡፡
ከት ብላ ከልቧ ሳቀች፡፡
ሀገርሽ ወዴት ነው ብዬ ብጠይቃት
ከምከም ብላ ሳቀች ነገሩ ቢደንቃት
የሚለው ሀገራዊ ግጥም ትዝ አለኝ፡፡
‹‹ለምን ሳቅሽ?››
‹‹የኔ ሥራ ከበድ ያለ ነው›› ብላ በድጋሚ ሳቀች፡፡
‹‹እንዴት? ፈላስፋ ነሽ እንዴ?››
አሁን ጭራሽ ከልቧ ሳቀች፡፡
‹‹አጎቴ ያለኝ ትዝ ብሎኝ ነው፡፡ አሁን የምሠራበትን ሥራ ከብዙ ፍለጋ በኋላ አገኘሁና ኅሊናዬ መቀበል አቃተው፡፡ እንዳልገባ ቀፈፈኝ፤ እንዳልተወው በኢኮኖሚው ምክንያት ሥራ የለም፡፡ ለብዙ ጊዜ ሳወጣ ሳወርድ ቆየሁ፡፡ ኮሌጅ ትምህርቴን ደግሞ መጨረስ ነበረብኝ፡፡ ››
‹‹ሥራው ይህንን ያህል ምን ቢሆን ነው?››
‹‹ሬሳ መገነዝ››
ክው ነው ያልኩላችሁ፡፡ ክው፡፡ እኔን ራሴን እየገነዘችኝ ያለች መሰለኝ፡፡ ለካስ ከገናዧ ጎን ነው ያለሁት፡፡
‹‹ከመጀመርየው ሥራዬ አሰናበቱኝና ለትምህርቴ መደጎሚያ ሌላ ሥራ ስፈልግ በአንዲት ጓደኛዬ አማካኝነት ይህንን ሥራ አገኘሁ፡፡ እኔ በሕይወቴ እንዲህ ያለ ሥራ ይኖራል ብዬም ስላልገመትኩ ከበደኝ፡፡ የበፊቱን ሥራዬን በጣም እወደው ነበር፡፡ ይህንን ግን ለመቀበል ኅሊናዬ አልቻለም፡፡ በመጨረሻ አጎቴ ጋ ሄድኩና አማከርኩት፡፡››
‹‹ለምንድን ነው የከበደሽ›› አለኝ፡፡
‹‹ሥራውን አልወደድኩትም›› አልኩት፡፡
‹‹ለምን?››
‹‹በቃ አልወደድኩትም››
‹‹መልካም፡፡ አንቺ ወደፊት በሕክምና ሞያ ልትሠማሪ አይደለም እንዴ? ታድያ ለምን ጠላሽው? ይህኮ ምንም ማለት አይደለም፡፡ የምትወጅው ሥራ ባታገኚም ያገኘሽውን ሥራ መውደድ ግን ትችያለሽ፡፡ የምትወጅውን ሥራ ብታገኚ መልካም ነው፡፡ እርሱ ግን ባንቺ ብቻ አይወሰንም፡፡ የሚቀጥሩሽም ሰዎች ፈቃድ ያስፈልጋል፡፡ ሥራሽን እንድትወጅው ለማድረግ ግን አንቺ ራስሽ ብቻ በቂ ነሽ፡፡ የምትወጅውን ሥራ ለማግኘት ከብዙዎች ጋር መፎካከር አለብሽ፡፡ ያገኘሽውን ሥራ ለመውደድ ግን ከራስሽ ጋር ብቻ ትፎካከርያለሽ፡፡ የምትወጅውን ሥራ ለማግኘት ቀጣሪዎችሽን ማሳመን አለብሽ፤ ሥራሽን ለመውደድ ግን ራስሽን ብቻ ነው የምታሳምኚው፤ የምትወጅውን ሥራ አግኚተሽ  ነገ ልትጠይው ትችያለሽ፡፡ ያገኘሽውን ሥራ ከወደድሽው ግን መቼም አትጠዪውም፡፡ ››
‹‹ታድያ ምን ላድርግ?›› አልኩት፡፡
‹‹ ሥራሽን ለመውደድ ሞክሪ፡፡ ተመልከች ሥራሽ ማለት በቀን ቢያንስ ስምንት ሰዓት የምታሳልፊበት ቦታ ነው፡፡ ከቀኑ አንድ ሦስተኛውን፡፡ የሥራሽን ቦታ ከጠላሽው ከሕይወትሽ አንድ ሦስተኛውን ጊዜ ያለ ደስታ አሳለፍሽው ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከባድ ጉዳት ነው፡፡ ስለዚህ የግድ መውደድ መቻል አለብሽ›› አለኝ፡፡ እኔን የጨነቀኝ እንዴት አድርጌ? የሚለው ነበር፡፡
‹‹ስለ ሥራሽ ዕወቂ፡፡ ብዙ ጊዜ የማናውቀውን ነገር እንጠላዋለን፣ ወይም እንፈራዋለን፡፡ የሥራውን ጠባይ፣ የሚያስገኘውን ጥቅም፣ በዚህ ሥራ ያሳለፉ ሰዎችን ተሞክሮ፣ ለሀገርና ለወገን የሚሰጠውን ጥቅም፣ በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ የሚያስገኘውን ፋይዳ፣ እንደ እምነትሽ ደግሞ ያለውን መንፈሳዊ ቦታ ዕወቂው፡፡ ከዚያም ከደመወዝ ያለፈ ዓላማ ለራስሽ ስጭው፡፡ ምን እያደረግሽ ነው? የአንቺ አስተዋጽዖ ምንድን ነው? ለሕይወትሽ ምን ልምድ ታገኚበታለሽ? ከዚህ ቦታ ብትወጭ እንኳን ምን ጊዜም ልጠቀሚበት የምትችይ ምን ትምህርት ማግኘት ትችያለሽ? ምን አዲስ ዕውቀትስ ትጨምሪያለሽ? እያልሽ ለራስሽ ተጨማሪ እሴት ፍጠሪ፡፡
‹‹የሥራ አካባቢሽን በቀን ለአንድ ሦስተኛ ጊዜ እንደተከራየሽው መኖርያ ቤትሽ ቁጠሪውና አሳምሪው፡፡ ለጽዳት ሠራተኞች ወይም ለሌሎች አትተይው፡፡ ያ ያንቺ ቤት ነው፡፡ ቢያምርና ቢስተካከል፣ ንጹሕና ሳቢ አካባቢ ቢሆን ከኃላፊዎቹም ሆነ ከባለቤቶቹ በላይ የሚጠቅምሽ አንቺን ነው፡፡ ሥራው የተቀላጠፈና የተስተካከለ ቢሆን የአንቺን ደስታ ነው የሚጨምረው፡፡ በነገርሽ ላይ በአንድ የሥራ ቦታ የሚፈጠሩ መልካምም ይሁን ክፉ ነገሮች የሕይወታችን አካል ሆነው ነው የሚቀጥሉት፡፡ ጠባያችንንና አሠራራችንን ይቀርጹታል፡፡ አንቺ ከሥራው ብትለቂም በዚያ ቦታ ያገኘሽው ነገር ግን አንቺን መቼም ቢሆን አይለቅሽም›› አለኝ፡፡
‹‹ለብዙ ቀን አሰብኩበትና ‹ልሞክረው› ብዬ ገባሁ፡፡ ይኼውልህ ሦስት ዓመት ከሰባት ወር ሠራሁ፡፡ አሁን ልለቅቀው አንድ አራት ወር ቀርቶኛል፡፡ ግን ቅር ቅር ይለኝ ጀምሯል፡፡ በሌላ ቦታ የማላገኛቸው ብዙ ነገሮች አግኝቼበታለሁ፡፡ ስለ ሕይወት ያለኝ አስተሳሰብ አሁን ተቀይሯል፡፡ ››
ፊኒክስ አውሮፕላን ማረፊያ ስንደርስ እርሷ ወደ ፍሎሪዳ ነበርና የምትጓዘው ተለያየን፡፡ እኔ ወደ ቺካጎ ለመሣፈር 45 ደቂቃ እዚህ እቆያለሁ፡፡ የነገርችኝ ነገር ግን መቼም ከኅሊናዬ አይጠፋም፡፡
ፊኒክስ፣ አሪዞና
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነውና በተመሳሳይ ኅትመት ባታወጡት ይመረጣል

22 comments:

 1. Hi D.Dani
  You have a very inspiring way of exploring and sharing your thoughts.
  Thanks for sharing these great stories and your wisdom.
  I pray that Almighty God will give you more wisdom upon wisdom.
  ps. When are you planning to be in Los Angeles?

  www.bereketdecor.blogspot.com

  ReplyDelete
 2. አበበ ሙ በየነOctober 16, 2012 at 11:02 AM

  ወንድሜ ዳንኤል ለመልካም ዕይታህ እግዚአብሔር ይስጥሕ::

  በዚህ ፅሁፍህ የምትሰራዉን ሥራ ካልወደድከዉ የ ዕለቱን ኑሮህንና ዉሎህን ገደል ከተትከው ማለት እንደሆነ አሳይተህኛል:: ከሁሉም በላይ በሚከተለው ሁኔታ የአሰፈርከዉ ሃሳብ ለአስተማሪነቱ ወደር የለዉም::

  ሃሳብህንም በሚከተለዉ ሁኔታ እጠቅሳለሁ:-

  የምትወጅው ሥራ ባታገኚም ያገኘሽውን ሥራ መውደድ ግን ትችያለሽ፡፡ የምትወጅውን ሥራ ብታገኚ መልካም ነው፡፡ እርሱ ግን ባንቺ ብቻ አይወሰንም፡፡ የሚቀጥሩሽም ሰዎች ፈቃድ ያስፈልጋል፡፡ ሥራሽን እንድትወጅው ለማድረግ ግን አንቺ ራስሽ ብቻ በቂ ነሽ፡፡ የምትወጅውን ሥራ ለማግኘት ከብዙዎች ጋር መፎካከር አለብሽ፡፡ ያገኘሽውን ሥራ ለመውደድ ግን ከራስሽ ጋር ብቻ ትፎካከርያለሽ፡፡ የምትወጅውን ሥራ ለማግኘት ቀጣሪዎችሽን ማሳመን አለብሽ፤ ሥራሽን ለመውደድ ግን ራስሽን ብቻ ነው የምታሳምኚው፤ የምትወጅውን ሥራ አግኚተሽ ነገ ልትጠይው ትችያለሽ፡፡ ያገኘሽውን ሥራ ከወደድሽው ግን መቼም አትጠዪውም::

  የሥራ አካባቢሽን በቀን ለአንድ ሦስተኛ ጊዜ እንደተከራየሽው መኖርያ ቤትሽ ቁጠሪውና አሳምሪው፡፡ ለጽዳት ሠራተኞች ወይም ለሌሎች አትተይው፡፡ ያ ያንቺ ቤት ነው፡፡ ቢያምርና ቢስተካከል፣ ንጹሕና ሳቢ አካባቢ ቢሆን ከኃላፊዎቹም ሆነ ከባለቤቶቹ በላይ የሚጠቅምሽ አንቺን ነው፡፡ ሥራው የተቀላጠፈና የተስተካከለ ቢሆን የአንቺን ደስታ ነው የሚጨምረው፡፡

  በነገርሽ ላይ በአንድ የሥራ ቦታ የሚፈጠሩ መልካምም ይሁን ክፉ ነገሮች የሕይወታችን አካል ሆነው ነው የሚቀጥሉት፡፡ ጠባያችንንና አሠራራችንን ይቀርጹታል፡፡ አንቺ ከሥራው ብትለቂም በዚያ ቦታ ያገኘሽው ነገር ግን አንቺን መቼም ቢሆን አይለቅሽም አለኝ፡፡

  ቸር እንሰንብት


  ReplyDelete
 3. Dani arif eyeta new

  ReplyDelete
 4. Thanks alot D.Daniel please keep it up. we are learning more day to day from your articles. we pray to God to gives you long live.

  ReplyDelete
 5. Dani melkam eyita new.

  ReplyDelete
 6. ዳኒ፣ በጣም ላመሰግንህ እወዳለሁ፡፡ ብርታቱን እንዲሰጥህ እመኛለሁ፡፡
  እንውደደውም እንጥላውም ያለሥራ መኖር አንችልም፡፡ ሥራ ምንድነው ለሚለው የተለያዩ ምሁራን የተለያየ ትርጉም ሊሰጡት ይችላሉ፡፡ አለም አቀፉ የሥራ ቡድን(International Work Team) ሥራ ማለት በማኅበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያለው፣ ደመወዝ ያለው፣ ከሰዎች ጋር ሊያገናኝ የሚችል፣ ለማኅበረሰቡ ፋይዳ ያለው ተግባር ነው በማለት ሲተረጉመው አንዳንድ ምሁራን ደግሞ ማንኛውም ዓይነት ገቢ የሚያስገኝ ነገር (ስርቆትንም ማጭበርበርንም ጨምሮ ማለት ነው) ሥራ ነው ብለው ይተረጉሙታል፡፡ የትኛው ነው ትክክል ለሚለው ተወያዩበት፡፡
  ሁሉንም ሰው በእኩል እንደማንወድው ሁሉ እንዲሁ ሁሉንም ዓይነት ሥራ እኩል ላንወደው እንችላለን፡፡ ሰዎች ሥራቸውን የሚወዱበት ምክንያት እንዳለ ሁሉ የሚጠሉበትም ምክንያት ይኖራል፡፡ አንደኛው የሚጠላውን ሥራ አንደኛው ሊወደው ይችላል፡፡ አንደኛው የሚወደውን ሥራ ሌላኛው ሊጠላው ይችላል፡፡ አንድን ሥራ ለመውደድም ሆነ ለመጥላት በአብዛኛው(በአብዛኛው የሚለው ይሰመርበት) ማኅበረሰቡ ለሥራው የሚሰጠው ዋጋ ወይም አመለካከት ወሳኝነት አለው፡፡ በአንደኛው ማኅበረሰብ ዘንድ ተወዳጅ የሆነ ምግብ በሌላኛው ማኅበረሰብ ዘንድ የሚያስጠላ ሊሆን ይችላል፡፡ ሥራም እንዲሁ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ሞግዚትነት ሥራ የማይመስለው ወንድ ወደምዕራቡ ዓለም ሂዶ በሞግዚትነት ተቀጥሮ ይሰራል፡፡ ስለዚህ አንድን ሥራ ለመውደድም ሆነ ለመጥላል ሥራው የሚሰራበት ማኅበረሰብ የሥራ ባህል ወሳኝ ነው፡፡ ህጻናትን ወደፊት ምን መሆን(መሥራት) ነው የምትፈልጉት ብለን ስንጠይቃቸው የሚሰጡን ምላሽ ይኖራል፡፡ በአብዛኛው ከወላጆቻቸውና አብረውት ከሚውሉት ሰው የሚሰሙትን በማኅበረሰቡ ዘንድ አድናቆት(ዕውቅና) የተሰጠውን ሥለሥራው ባህርይ ያልተረዱትን ሙያ መሆን እንደሚፈልጉ እየተናገሩ ያድጋሉ፡፡ ከአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች እስከ ከፍተኛ ት/ ተቋም ድረስ ያሉ ተማሪዎች ፍላጎታቸውና ምኞታቸው በማኅበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ሊያሰገኝላቸው የሚችለውንና “ዋው!” ሊያስብል በሚችል ሙያ ላይ መሰማራት ይሆናል ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ለአንድ ሥራ ያለን አመለካከትና ግንዛቤ ከህጻንነት ይጀምራል ማለት ነው፡፡ ለዚህ ነው ብዙዎቻችን ህይወታችንን ሊለውጥ የሚችል ብዙ ዓይነት ሥራ በዙሪያችን ከቦን ሥራ የምናጣው፡፡
  የሥራው ዓይነት ምንም ይሁን ምን ሰራተኛ ለምን ሥራውን ይጠላል ለሚለው የተለያዩ ምክንያቶችን መስጠት እንችላለለን፡፡ አንድን ሥራ ለመውደድም ሆነ ለመጥላት እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ መመዘኛ ሊኖረው ቢችልም ሥራ መውደድ ሲባል ምን ማለት ነው ሥራ መጥላትስ ሲባል ምን ማለት ነው ለሚለው የተለያዩ ሙያዊ መለኪያዎች(Scales) አሉት፡፡
  ሰዎች ሥራቸውን የሚጠሉበትን ምክንያቶች ከብዙ በጥቂቱ ልጠቁማችሁ
  ሀ. ሥራውን ወደነው ከሥራው ጋር ተያይዘው በሚመጡ ነገሮች ምክንያት የምንጠላው ሥራ
  1. ሥራውን ወደነው ሥራውን ለመሥራት የሚያስችሉ ሁኔታዎች ካልተመቻቹ ቀስ በቀስ ሥራውን ወደመጥላት እንሸጋገራለን
  2. ሥራውን ወደነው አብረውን ከሚሰሩ ሰዎች ጋር (ከኃላፊ፣ ከሥራ ባልደረባ፣ ከምንመራቸው ሰራተኞች፣ ወዘተ ) ሰምምነት ከሌለና ጭቅጭቅ የሚዘወተርበት ከሆነ ቀስ በቀስ ሥራውን ወደመጥላት እናመራለን
  3. ሥራውን ወደነው የሥራው አካባቢ ለጤና፣ ለአካላዊና ስነልቡናዊ ጉዳት፣ ወይም ለህይወታችን አስጊ ሲሆን ሥራውን ወደመጥላት ልናመራ እንችላለን፡፡
  4. ሥራውን ወደነው ነገር ግን የሥራችንን ውጤት ማየት ሳንችል ስንቀርና እርካታ ስናጣ ሥራውን ልንጠላው እንችላለን
  ለ. ለሥራው ያለን አመለካከት የተዛባ በመሆኑ የምንጠላው ሥራ
  1. ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርኩት ከአስተዳደግ ጋር ተያይዞ በሚመጣ የሥራ አመለካከት ምክንያት ሥራውን ሳንፈልገው ለመኖር ስንል ብቻ የምንሰራው ሥራ ይኖራል፡፡
  2. ስለሥራው ከሌሎች ሰዎች የምንሰማው የተዛባ መረጃ ሥራውን እንድንጠላው ሊጋብዘን ይችላል
  ሐ. ከክፍያ(ከደመወዝ) ጋር በተያያዘ የምንጠላው ሥራ ፡- ከክፍያ ጋር የተያያዘ የሥራ አመለካከት በያዝነው ሥራ እንዳንረካ የሚያደርገን ሲሆን ይህ በአብዛኞቻችን ላይ የሚንጸባረቅ ነው፡፡ ለዚህ የሚዳርጉን ብዙ ችግሮች ቢኖሩም ዋናው ምክንያት የመሰረታዊ ፍላጎት አለመሟላት ነው፡፡
  መ. ከአቅም ውስንነት ጋር ተያይዞ የምንጠላው ሥራ፡- የዕውቀትና የክህሎት ማነስ ሲኖር የምንሰራውን ሥራ ልንጠላው እንችላለን
  ሠ. ከተለያዩ ማኅበራዊ፣ ሥነ-ልቡናዊና መንፈሳዊ ችግሮች ጋር ተያይዞ የምንጠላው ሥራ፡- አንድ ሰው በሥራው ደስተኛ እንዲሆን ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ በአካል፣ በሥነ-ልቡና፣ በማኅበራዊ ህይወት ጤነኛ መሆን ነው፡፡ አንድ ሰው በእነዚህ ነገሮች ችግር ከገጠመው ቀስ በቀስ ሥራውን ወደመጥላት ሊያመራ ይችላል፡፡
  በአጠቃላይ ሥራን መጥላት በሁለንተናዊ ዕድገታችን(አካላዊ፣ ሥነ-ልቡናዊ፣ በማኅበራዊ፣ ወዘተ) ላይ ቀላል የማይባል አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያስከትል ችግር መሆኑን የሥነ-ልቡና ምሁራን ይገልጻሉ፡፡

  ReplyDelete
 7. ይደረስ ለዲ/ን ዳንኤል ክብረት በብሎግህ ላይ የሚቀርቡት ጽሁፎችህ እጅግ አስተማሪ እና አስደሳች ነው። በህይወቴ ያለመድኩትን የማንበብ ልምድ እንድለምድ ረድተህኛልና ከልብ አመሰግናለሁ። ጽሁፎችህ ሀይማኖታዊ ምክሮችን ያቀፉ በመሆናቸው ደስ ይለኛል። እግዚአብሔር አምላክ እድሜ እና ጸጋን ይስጥህ። የድንግል ማርያም ረድኤቷ እና በረከቷ ከአንተ ጋር ይሁን።

  ReplyDelete
 8. መብላትና መጠጣት እንድትቆይ እንጂ እንድትኖር አያደርጉህም

  ReplyDelete
 9. ሶሎሞን ዮናስOctober 17, 2012 at 11:36 AM

  ዳኒ ዛሬ ደስ ብሎኛል::ምክንያቱም የልጅቱ ሃሳብ የኔ የሁልጊዜ ስሜት ነው:: " ‹‹‹መኖር›ና ‹መቆየት› የሚለያዩ ይመስለኛል፤ መኖር የኅሊና፣ መቆየት ግን የአካል ነው፡፡ እየበላህና እየጠጣህ ሳትሞት ብዙ ዘመን መቆየት ትችል ይሆናል፡፡ በመብላትና በመጠጣት ብቻ ግን መኖር አትችልም፡፡ ለመኖር የኅሊና ምግብም ያስፈልግሃል፡፡ " አሁን እኔ ያለሁበት ቦታ እየበላህና እየጠጣህ ሳትሞት ብዙ ዘመን መቆየት የሚቻልበት ቦታ ነው::ግን ምንም የህሊና ምግብ የለም!!ምንም::እግዚሓር ይስጥልን::

  ReplyDelete
 10. thanks for sharing this with us!I also believe that one need to develop respect and love for their means of livelihood. Conversely, it requires a huge energy to develop that for the job or whatever which is not one's choice. it also slows down efficiency. the thing is a serious case in developing countries like ours, take teachers, we have over half a million (sorry if i miss the figure)and almost none love that profession, and it goes like that. BTW D. Daniel has made a good point, and i personally have got good issue to debate with friends,thanks!

  ReplyDelete
 11. በሥራ ባህላችን ዙሪያ የውይይት መድረክ ብትከፍትና ብንወያይ ደስ ይለኛል

  ReplyDelete
 12. yihe lene mels new! Egzibher yibarkih!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. what? mels is racist and son of Banda but danie is An Ethiopian.

   Delete
  2. wendime mejemeriya min endetetsafe anbib

   Delete
 13. ye igziaher slm le ante yhun dani minew minew minew......................ye ethiopia wede african up malefu alsemahim inde?kalsemah lingerih looool zim alik biye eko new

  ReplyDelete
 14. Tebarek wendme kemkegna mlas ysewrh

  ReplyDelete
 15. This man is A great asset for Ethiopia, thank you DANI

  ReplyDelete
 16. ሥራን ለመውደድ መጀመሪያ ስለ ሥራው ያለን ግንዛቤ፣ ያለን ሙያ ፣ የምናሳየው ብቃት፣ ይወስነዋል የሚል አመለካከት አለኝ ዳኒ፣ አልያም በተለይ በደንብ ጥቅም ይገኝበታል ተብሎ የሚታሰበውን ሥራ የሚያስጠላም ቢሆን ይወደዳል፣ ሰውኮ ጥቅምን እንጂ ሥራን አይደለም የሚፈልገው፣ ወደ ውጭ ሃገር የሚጎርፈው ህዝባችን ጥቅምን ፍለጋ እንጅ ሥራ ፍለጋ አይመስለኝም ፣ ሃገራችን ውስጥ ጠረጋ በዶላር መከፈል ቢጀምር ዶክተሩ ምን ይውጠዋል ፣ ያሳዝናል፣ ቤተክርስቲያናችን ውስጥ የእገሌ ደብር ደህና ይበላበታል የምትባል በሙስና የነቀዙ ሰዎች አባባል ትዝ አለኝ፣ የሚበላበት ከሆነ ትንሽ ደብርም ብትሆን ሰው ሁሉ ወደዛ መቀየር ይፈልጋል፣ በተለይ በተቸገሩ አድባራት ስም በየደብሩ እየዞሩ የሚዘርፉ አላጋጮች ፣ አይ ሙስና ግእዝ ባትሆን ኖሮ ባስቸኳይ እናስወግድህ ነበር፣ ለነገሩ ምልክትም ስለ ሆነ እንጃ መጥፋቱን፣

  ReplyDelete
 17. This is the best ever view of yours thank you Dear Dani!!!

  ReplyDelete