Thursday, October 11, 2012

አንድ ገመድ አለኝ

ሁለት ወንድማማቾች እናታቸው ስታርፍ በቤት ውስጥ ያገኙት አንድ ትልቅ ገመድ ብቻ ነበር፡፡ ታላቁ ልጅ እጅግ በመበሳጨቱ ገመዱን ጠቅልሎ ጣራ ላይ ወረወረውና ከቤት ወጥቶ ሄደ፡፡ ታናሹ ግን ምንም ቢሆን ገመዱ የእናቱ ቅርስ ነውና እንደምንም ብሎ ጣራ ላይ ወጥቶ አወረደው፡፡
ከባዱ ጥያቄ ግን ከዚህ በኋላ ያለውን ኑሮ እንዴት መግፋት ይችላል? የሚለው ነበር፡፡ ለብዙ ሰዓታት ተቀምጦ አሰበበት፡፡ ምንም ነገር ሊታየው ግን አልቻለም፡፡ መንገዱ ሁሉ በግንብ የታጠረ ነው፡፡ አስቦ አስቦ ወደ አንድ ጠቢብ ዘንድ ሄደ፡፡
ጠቢቡ ሰው እንዳገኘው የጠየቀው ጥያቄ ‹‹ምን አለህ›› የሚል ነበር፡፡
 መልሱም ቀላል ሆነ ‹‹ ምንም››
ጠቢቡ ሰውም ‹‹በዓለም ላይ ምንም የሌለው ሰው የለም፡፡ ምናልባት ግን ጥቂት ብቻ ያለው ሰው ሊኖር ይችላል፡፡ ከለምሳሌ አንተ ከወንድምህ በተለየ ጥበብ አለህ፤ ይህ ጥበብህም ነው ወደ ጠቢብ ያመጣህ›› አለው፡፡ ልጁ ግን በርግጠኛነት እየማለ ምንም እንደሌለው ተናገረ፡፡ 
ጠቢቡም ‹‹ይህ ፈጽሞ ሊሆን የማይችል ነው፡፡ ሰው ሆኖ ምንም የሌለው የለም፡፡ ረስተኸው ነው እንጂ አንዳች ነገር አለህ›› አለው፡፡ ልጁ ቢያወጣና ቢያወርድም ያለውን ነገር ሊያገኘው አልቻለም፡፡ የሚያውቀው ምንም እንደሌለው ብቻ ነው፡፡
ያን ጊዜ ጠቢቡ ልጁን ይዞት ወደ አንድ ክፍል ገባ፡፡ ክፍሉ ሊዳሰስ በሚችል ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ የተሞላ ነው፡፡ ጨለማው ዓይን ሊወጋ ይደርሳል፡፡ ከጠቢቡ ጋር በዚያ ክፍል ውስጥ እንደገቡ ‹‹ምን ይታይሃል?›› አለና ጠየቀው፡፡ ልጁም መለሱን ወዲያው ነበር ያገኘው ‹‹ጨለማ››
ጠቢቡ ግን እንደገና ጠየቀው፡፡ ‹‹ሌላ ነገር አለ፤ ፈልገው›› ዘወር ዘወር አለ፡፡ ግን ምንም፡፡
ጠቢቡ እንዲህ አለው ‹‹ና አብረን ቁጭ እንበልና ጊዜ ወስደህ ተመልከት››
ተቀመጡም፡፡
ልጁ በግራና በቀኝ፤ በፊትና በኋላ ማየት ጀመረ፡፡ ለብዙ ደቂቃዎችም አየ፡፡ በመካከል ላይም ‹አሃ›› የሚል ድምጽ ከልጁ ሲወጣ ተሰማ፡፡
 ጠቢቡም ‹‹እሺ ምን ተገኘ›› አለው፡፡
‹‹በዚያ በኩል ባለው ቀዳዳ ብርሃን ነገር ይታየኛል›› አለው፡፡
ጠቢቡ አቀፈው፡፡
‹‹አሁን አእምሮህን መጠቀም ጀመርክ፡፡ አእምሮን መጠቀም ማለት ከዓይነ ሥጋ ይልቅ በዓይነ ልቡና ማየት መቻል፣ ከእዝነ ሥጋ ይልቅ በእዝነ ልቡና መስማት መቻል ማለት ነው፡፡ ‹ልብ ካላየ ዓይን አያይም› ሲባል አልሰማህም፡፡ አእምሮውን የሚጠቀም፣ ሰው ሁሉ የሚያየውን ብቻ ሳይሆን የማያውንም ያያል፡፡ ለዚህ ነው አእምሮ ያለው ሰው ተስፋ የማይቆርጠው፡፡ አእምሮ ያለው ሰው በግንብ መካከል በር፣ በጨለማ መካከል ብርሃን፣ በተራራ መሐል መንገድ፣ በሞት መካከል ሕይወት ይታየዋል፡፡
‹‹መንገድ ያለው ከውጭ አይደለም፡፡ መንገድ ያለው ከውስጥ ነው፡፡ የውጭው መንገድ እግር ነው የሚሄድበት፡፡  የውስጡ መንገድ ግን ልቡና ነው የሚጓዝበት፡፡ በልቡናቸው የሄዱ ሰዎች ናቸው በእግራቸው ለመሄድ ፈልገው የእግሩን መንገድ የሠሩት፡፡ ከእነርሱ በኋላ ግን ብዙዎቹ በልቡናቸው ሳያዩ ይጓዙበታል፡፡ መጀመርያ በልቡናቸው የበረሩ ሰዎች ናቸው አውሮፕላንን የፈጠሩት፣ መጀመርያ በልቡናቸው የተገናኙ ሰዎች ናቸው ስልክን የሠሩት፡፡ እናም መንገድ ያለው ውስጥህ ነው፡፡ አንተ ውስጥ መንገድ አለ፡፡
‹‹ምን አልባት ያ መንገዱ አልተጠረገ ከሆነ ጥረገው፤ ተጎድቶ ከሆነ ጠግነው፤ አርጅቶ ከሆነ አድሰው፡፡ ከዚያ በኋላ ሁሉም ነገር ቀላል ነው፡፡ ጊዜ ውሰድ፡፡ ለማየት ጊዜ ውሰድ፡፡ ወሳኙ የጨለማው መጠን አይደለም፡፡ ወሳኙ አንተ የሰጠኸው ጊዜ መጠን ነው፡፡ ለማሰብ የምትወስደው ጊዜና የምታስብበት መንገድ፡፡ ጊዜ ወስደህ ባሰብህ ቁጥር ያለኸው ጨለማ ውስጥ አለመሆኑን ታውቀዋለህ፡፡ እስኪ ትንሽ ጊዜ እንውሰድ››
ሁለቱም ጥቂት ጊዜ ተቀመጡ፡፡
ያ ልጅም ማየት ጀመረ፡፡
‹‹እስከዚያ በዓለም ላይ ታዋቂ የሆነውን ‹የተጠማውን ቁራ ታሪክ› ልንገርህ፡፡ ቁራው ውኃ ጠማውና በአካባቢው ወዲያና ወዲህ እያለ መፈለግ ጀመረ፡፡ ግን አላገኘም፡፡ በመጨረሻም በውኃ ጥም ወደቀ፡፡ ነገር ግን ተስፋ ለመቁረጥ አልፈለገምና እንደምን ብሎ ተነሥቶ አካባቢውን ማማተር ጀመረ፡፡ በሩቁም አንድ ገንቦ አየ፡፡ ወድቆ እየተነሣ ገንቦው ጋ ደረሰ፡፡ ሲያይ ጥቂት ውኃ ውስጡ አለ፡፡ ምንቃሩንን አስገብቶ ሊጠጣ ሲሞክር የገንቦው አንገት ጠባብ ስለነበር አልቻለም፡፡ ገንቦውን ሊያዘነብለው ሲገፋውም ዐቅሙ ተዳክሞ ነበርና ያንን ከባድ ገንቦ መግፋት አልተቻለውም፡፡
‹‹ማሰብ ጀመረ፡፡ መንገድ ከውስጥ ነውና ውስጡ መንገድ ፈለገ፡፡ መንገዱንም አገኘው፡፡ በአካባቢው ያሉትን ጠጠሮች እየለቀመ ወደ ገንቦው ውስጥ መጣል ጀመረ፡፡ ለብዙ ጊዜ ሲጥል ገንቦው በጠጠር እየተሞላ ውኃውም ወደ ላይ እየወጣ መጣ፡፡ በመጨረሻም የገንቦውን ታችኛውን ክፍል ድንጋዩ ሞላውና ውኃው ወደ ገንቦው አፍ ደረሰ፡፡ ቁራውም ጠጣ፡፡››
በታሪኩ ትረካ መካከል ልጁ አንዳች ቅርጽ ያለው ነገር ተመለከተ፡፡ መሥመር ያለው ነገር፡፡ ከወለሉ ጀምሮ ወደ ጣራው የተሠመረ፡፡ ዓይኑን ከታች ወደ ላይ እያንከባለለ ተከተለው፡፡ አንዳች የብርሃን መሥመር፡፡ ቀጭን የብርሃን መሥመር፡፡ ከታች ወደ ላይ ሄደና እንደገና ወደ ግራ ዞረ፤ ተከተለው፡፡ ከግራ ደግሞ ወደ ታች ተጠመዘዘ፤ አብሮትም ሄደ፡፡ ከዚያም ተመልሶ ወለል ላይ ደረሰ፡፡
‹‹ያ የብርሃን መሥመር ምንድን ነው›› አለው ጠቢቡን፡፡
‹‹ጠጋ ብለህ እየው››
ፈራ፡፡
‹‹አትፍራ ጨለማውን ሳትፈራ እንዴት ብርሃኑን ትፈራለህ፡፡ ምንጊዜም የማያውቁት ነገር ያስፈራል፡፡ ሂድ ተጠጋ፡፡
ሄደና ተጠጋ፡፡ የጣውላ በር በሚመስለው ነገር ዙርያ የሚገባ ብርሃን ነው፡፡
‹‹እስኪ ንካው›› አለው ጠቢቡ፡፡ እየፈራ እየደፈረ ነካ አደረገው፡፡ ጣውላ ነገር ነው፡፡
‹‹በምትችለው ዐቅም ሁሉ ግፋው›› አለው፡፡ ላቡ ጠብ እስኪል ገፋው፡፡ ሲጢጢጥ እያለ፤ በመጨረሻ ያ ጣውላ የመሰለ በር ነገር ወደ ኋላው ወደቀ፡፡ ያን ጊዜ በውጭ ያለው ብርሃን ፏ ብሎ ገባ፡፡ ዓይኑን ጨፈን አድርጎ ሲገልጠው በበሩ ፊት ለፊት ሰፊ መንገድ አለ፡፡
‹‹በሕይወትህ ለመለወጥ ከፈለግህ ሦስቱን መሠረታዊ ነገሮች አሁን ተምረሃለል›› አለው፡፡
‹‹ምንድን ናቸው?››
‹‹መጀመርያ እምነት ነው፡፡ ምንጊዜም መንገድ አለ፡፡ ሊዘጋ የማይችል፤ ሊታጠር የማይችል፤ መንገድ አለ፡፡ እርሱም አንተ ውስጥ ነው፡፡ ሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡ ጊዜ ስጥ፡፡ ለማሰብ ጊዜ ይኑርህ፣ ለመፈለግ ጊዜ ይኑርህ፣ ምንጊዜም በፍለጋ ላይ ሁን፡፡ አሁን ያልታየህ ቆይቶ ይታይሃል፡፡ ነገር ለመቁረጥ እንጂ ተስፋ ለመቁረጥ አትቸኩል፡፡ ‹ገና አላገኘሁትም› በል እንጂ ‹የለም› አትበል፡፡ አለ፤ ግን አልደረስክበትም፡፡ መድረስ ጊዜና ጥረት ይጠይቃል፡፡ ሦስተኛው ነገር ያገኘኸውን አጋጣሚ ንካው፡፡ ያገኘኸውን ብርሃን ንካው፡፡ ካልነካኸው በሩ ግድግዳ እንደሆነ ይቀራል፡፡ ከነካኸው ግን በሩ መንገድ ይሆናል፡፡ ብርሃን ማየትህ ብቻ ዋጋ የለውም፤ ብርሃኑ በሚገባ እንዳይገባ ያደረገውን ነገር መንካት አለብህ፡፡ እስኪወድቅና ብርሃኑ በሚገባ እስኪገባ፣ መንገዱም ወለል እስኪል መግፋት፡፡
‹‹ሳይነኩት በምኞት ብቻ የሚወገድ ችግር የለም፤ የሚከፈትም በር የለም፡፡ አየህ ማሰብ የብርሃን ጭላንጭልን አሳየህ፤ ጊዜ ሰጥቶ ማስተዋል ይህንን በር ገለጠልህ፤ መንካት ደግሞ መንገዱን አሳየህ፡፡ አሁን አይበቃህም››
‹‹ይበቃኛል››
‹‹ታድያስ አሁን ምን አለህ››
‹‹ገመድ አለኝ››
‹‹ሂድ ጊዜ ሰጥተህ፣ መጣፍ አገላብጠህ፣ ዐዋቂ ጠይቀህ፣ ግራ ቀኙን አስብ፡፡ ይህች ገመድ ሕይወትህን የመለወጫ ምክንያት ትሆንሃለች፡፡ የባለጸግነት መጀመርያ፣ የሥልጣን እርከን፣ የሊቅነት ፋና፣ የጀግንነት መንሥኤ ትሆንሃለች፡፡ ያለበለዚያ ደግሞ የመታነቂያ መሣርያ ትሆንሃለች፡፡ ሁለቱም በእጅህ ነው፡፡››
አሰናበተውና ሄደ፡፡
ሚልዋኪ፣ ዊስኮንሲን

43 comments:

 1. wooo bethma dease yelale

  ReplyDelete
  Replies
  1. ጊዜ ወስደህ ባሰብህ ቁጥር ያለኸው ጨለማ ውስጥ አለመሆኑን ታውቀዋለህ፡፡ እስኪ ትንሽ ጊዜ እንውሰድ››

   Delete
 2. Thank u dani.This was one of my problems.I had no chance to speak with my heart.For sure I am going to try it.I started to feel that I have at least something mine which may help me to lead my own life.
  Worku A

  ReplyDelete
 3. Replies
  1. awe awaki teykeh. yeteshale mengeb, bilhat, tibebin linegrut yichilalu.

   Delete
  2. awaki ante endemeseleh tenkuay ayidelem bilih, tibebegna, amakari malet new

   Delete
 4. Dani,
  Thank you for sharing the article as usual.Quick question for you.Is the above story your fiction? Or somthing else.Where is the source?

  ReplyDelete
 5. ሆ አንዳንዴ በዚህ ያል ገባንን በዚያ ከፍለን ያልደረስንበትን በነጻ የሚያሳየን ማን ነው? ብዬ እጠይቃለሁ:: ጌታ ሆይ እስኪገባኝ ድረስ ንገረኝ ትል ነበር እህቴ ታምርአየሁ:: ቃል ሕይወት ያሰማልን መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን! አሜን ጌታሆይ እስኪገባኝ ድረስ ንገረኝ!

  ReplyDelete
 6. Hohoho wondim Daniel tiru asetemarken, tiru negereken,tiru atsenanahen
  Tebarek tsegahen yabezaleh
  Enem ande gemed alegn

  ReplyDelete
 7. ዳኒ በጣም አስተማሪ ጹሁፍ ነው፡፡ እውቀቱን እግዚአብሔር ያብዛልህ፡፡ በሚቀጥለው ምን ታስነብበን ይሆን? በጉጉት እጠብቅሀለው፡፡

  ReplyDelete
 8. አበበ ሙ በየነOctober 12, 2012 at 9:51 AM

  ወንድም ዳንኤል ለተለመደዉ ድንቅ አስተምህሮትህ ልባዊ ምስጋናዬ ይድረስህ::

  መቼም ተራሮቹ ወደ መሐመድ ካልመጡ መሐመድ ወደተራሮቹ መሄድ አለበት:: የሰዉ ልጅ ወደአሰበዉ ግብ ለመድረስ በቅድሚያ ግቡን ሊያሳካዉ እንደሚችል ማማን አለበት:: ይህንን እምነት ይዞ መቼ እና እንዴት ሊተገብረዉ እንደሚችል የጊዜ ሰሌዳም ማስቀመጥ ይኖርበታል:: ቀጥሎም ወደግቡ ለመድረስ የጊዜ ሰሌዳዉን መሰረት አድርጎ መንቀሳቀስ ይጠበቅበታል:: እዚህ ላይ ዋናዉ ቁምነገር ይቻላል የሚለዉ ምኞት አይቻልም ከሚለዉ ስንፍና የሚሻል እና የሚበልጥ መሆኑን ማመን እና መቀበል ነዉ::

  ለማንኛችንም ግልፅ በሆነው መልኩ በሕይወት መስመር ያለዉ በር አንድ ብቻ አይደለም:: በርካታ የሕይወት በሮች እና መስመሮች ያሉ መሆኑን ማወቅና ማመን ያስፈልጋል:: ከፊት ለፊታችን ያለዉ አንዱ በር የተዘጋ ሲመሰል ተስፋ ቆርጦ ከመቀመጥ ይልቅ ሌላ ሊከፈት የሚችል በር እንደአለ አምኖ ያንን በር ለማግኘት መትጋት ያስፈለጋል::

  እንደ እኔ እንደ እኔ ማሰብ: እምነት: ጊዜ: ትጋት: እና ተስፋ ያለመቁረጥ የበሩ መክፈቻ የወርቅ ቁልፎች ናቸው እላለሁ::

  ቸር እንሰንበት

  ReplyDelete
 9. እህት ወንድሞቼ ዘመድ ወዳጆቼ
  በሃዘኔ ያዘናችሁ እናንት ወገኖቼ
  ዕንባችሁ ይታበስ አመሰግናለሁ
  ልባቹህ ይጽናና ቀልቤን አግኝቻለሁ
  ዓይን ይገለጥ እንጂ ብርሃን መቼም አለ
  ቀልብ ይሰብሰብ እንጂ መንገድ መቼም አለ
  እናም በእዉነት አልኩኝ ይቅር አትዘኑ
  ተቀሰቀሰ እንጂ ተሰበረ አትበሉ
  ከአምላክ ያይደል ከራስ ተለይቶ
  ከአምላክ ያይደል ከራስም ተጣልቶ
  የደመ ነፍስ ኑሮን መጋፈጡ ቀርቶ
  መከራ የመጣ ቀን ማን ነኝ ማለት መጣ
  ቀላሉ ልባችን
  በእዉነት ችሎት ቆሞ
  በፍቅር ተቀጣ
  ችግሬ ወዳጄ ዉድቀቴ መልካሙ
  የጣልኩ የረሳሁት
  የረገጥኩት ዉዴን
  ገላልጦ አሳየኝ
  ከሁካታዉ መሃል
  ነጥሎ ካለሙ

  ReplyDelete
 10. ejig melkam new dani, gin yegemeduan neger mechereshawan entebkalen!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 11. በእውነት ዳንኤል ምስጢሩ ረቂቅ ነው፡፡

  ReplyDelete
 12. Thanks for helping us to see first the rod in our mind.

  ReplyDelete
 13. that is owsome dani

  ReplyDelete
 14. dear dani,this is what makes world so different beacause those who have a dream can build a better world but other who lives without a dream spend their life not doing meaningful things.these thing proves that the real difference between the developed world and the third world

  ReplyDelete
 15. Hmmmm. Although i totally believe in the importance of positive thinking, I think it is an over simplified story. Especially for those who try to bring a societal change sometimes it is better to save their lives first. Otherwise the society will kill u via an often used method called isolation or excommunication or condemnation, depending on the societal change u r wishing to bring on.

  ReplyDelete
 16. really love it danisha...God bless u

  ReplyDelete
 17. God bless u big bro!!

  ReplyDelete
 18. ‹ሳይነኩት በምኞት ብቻ የሚወገድ ችግር የለም፤ የሚከፈትም በር የለም፡፡ አየህ ማሰብ የብርሃን ጭላንጭልን አሳየህ፤ ጊዜ ሰጥቶ ማስተዋል ይህንን በር ገለጠልህ፤ መንካት ደግሞ መንገዱን አሳየህ፡፡ ››Dn.Daniel

  ReplyDelete
 19. ጠቢቡ ሰው እንዳገኘው የጠየቀው ጥያቄ ‹‹ምን አለህ›› የሚል ነበር፡፡
  መልሱም ቀላል ሆነ ‹‹ ምንም››
  keep it up,

  ReplyDelete
 20. It is great job to direct people when they are in darker state of life, when they are desperate, by the wisdom that the Almighty God has given us. Like D/n Daneal, all of you with different gift of wisdom try to light the road to salivate from our ignorance. So, I strongly appreciate this author and also encourage others to follow his foot steps.

  ReplyDelete
 21. ይህች ገመድ ሕይወትህን የመለወጫ ምክንያት ትሆንሃለች፡፡

  ReplyDelete
 22. you make me speachless!

  ReplyDelete
 23. ''emenet, gezie seteto masebe ena menekat'' what a wonderful article thanks bro

  ReplyDelete
 24. ቁራው ውኃ ጠማውና በአካባቢው ወዲያና ወዲህ እያለ መፈለግ ጀመረ፡፡ ግን አላገኘም፡፡ በመጨረሻም በውኃ ጥም ወደቀ፡፡ ነገር ግን ተስፋ ለመቁረጥ አልፈለገምና እንደምን ብሎ ተነሥቶ አካባቢውን ማማተር ጀመረ፡፡ በሩቁም አንድ ገንቦ አየ፡፡ ወድቆ እየተነሣ ገንቦው ጋ ደረሰ፡፡ ሲያይ ጥቂት ውኃ ውስጡ አለ፡፡ ምንቃሩንን አስገብቶ ሊጠጣ ሲሞክር የገንቦው አንገት ጠባብ ስለነበር አልቻለም፡፡ ገንቦውን ሊያዘነብለው ሲገፋውም ዐቅሙ ተዳክሞ ነበርና ያንን ከባድ ገንቦ መግፋት አልተቻለውም፡፡
  ‹‹ማሰብ ጀመረ፡፡ መንገድ ከውስጥ ነውና ውስጡ መንገድ ፈለገ፡፡ መንገዱንም አገኘው፡፡ በአካባቢው ያሉትን ጠጠሮች እየለቀመ ወደ ገንቦው ውስጥ መጣል ጀመረ፡፡ ለብዙ ጊዜ ሲጥል ገንቦው በጠጠር እየተሞላ ውኃውም ወደ ላይ እየወጣ መጣ፡፡ በመጨረሻም የገንቦውን ታችኛውን ክፍል ድንጋዩ ሞላውና ውኃው ወደ ገንቦው አፍ ደረሰ፡፡ ቁራውም ጠጣ፡፡››
  ነገር ግን ድንጋዮች ወይም ጠጠሮች ጥቂት ውሃ ወዳለበት እንስራ ሲገቡ ድንጋዮቹ ሙሉ ለሙሉ ስለማይገጥሙ በሚፈጠረው ክፍተት ውሃው ይኖራል እንጂ ድንጋዩ ከውስጥ ሁኖ ውሃው ወደ ላይ ሊወጣ አይችልም፡፡ ይህ ለኔ በጨለማ ውስጥ ያለ እይታ ነው፡፡ የቄስ ሚስትአወቅሽ አወቅሽ ሲሏት መፅሃፍ አጠበች አሉ!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ያልተገለጠልህ ነገር እንዳለ ግልጽ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ማስተዋል ያስፈልግኀሐል፣ነገሮችን በግልብ ሐሳብ አትመልከታቸው፡፡እርግጥ ችግርህ ይኸ ብቻ አይመስልም የእውቀት ማነስ ጭምር እንጅ፡፡ ይኸም ቢሆን ቅናት በመሰለ ጥርስ ማፋጨት ባይሆን መልካም ነው፡፡

   ቸር ሰንብት!!

   Delete
  2. "ድንጋዩ ከውስጥ ሁኖ ውሃው ወደ ላይ ሊወጣ አይችልም" I agree with this idea but I understand Dn Daniel's message.

   Delete
  3. you guys, what about z size of stone. i understand that the stone is sand like it is there at the bank of river.
   so in this situation the idea works. the water level will rise.
   i appreciate Dani

   Delete
  4. First of all there are different types of stones such as porous, impermeable, etc. Here for the wise people it is so simple if the stone is impermeable and not water absorbent due to the volume repulsed by the solid the water definitely will rise. This is used to calculate the volume of solid in physics. Check it on a cup of coffee or tea; if you add sugar on the coffee the coffee level will rise. How you blame this idea? Please don't rush for bad comments. Thank you Dn Daniel. Peoples who don't like good ideas may always try to tackle you till fall. May God help you to rise always!

   Delete
 25. betam tekami hassab new.beteley legna lewetatoch, begize yalenen neger felegen endenagegn yitekumenal. edme yisteh Daniel.

  ReplyDelete
 26. የማላውቅህ ወንድሜ Anonymous October 15, 2012 11:06AM ስህተት ከመፈለግ ሊተላለፍ የተፈለገውን መልእክት ለመረዳት መሞከር አይቀልም ፡፡ ከአነጋገርህ እርግጠኛ ሁኜ ልንገርህ አንተ ኦርቶዶክሳዊ አይደለህም እንዴት ብትለኝ አነጋገርህ ይገልፅህአል፡፡ የፊዚክስ ግንዛቤ ከሌለህ ለማግኘት ጣር በተረፈ አንገቱ ጠባብ ከሆነ ማሰሮ ከግማሽ ያለፈም ውሃ ቢኖር ጠልቆ ማውጣት አይቻልም፡፡ ሌላው ‹‹የተጠማውን ቁራ ታሪክ›› የዲያቆን ዳንኤል ፈጠራ አይመስለኝም፡፡ ወንድማችንን ለቀቅ፡፡ ዳኒ አንተን ግን የድንግል ማርያም ልጅ ጥበብን ከትሁት መንፈስ ጋር ደርቦ ደርቦ የስጥህ፡፡

  ReplyDelete
 27. YMDHANITE ALEM yaleh!!!! dn.Daniel wey gud betam grum sehof new EGZIABHIR ystelen.

  ReplyDelete
 28. ወንድማችንን ለቀቅ፡፡ ዳኒ አንተን ግን የድንግል ማርያም ልጅ ጥበብን ከትሁት መንፈስ ጋር ደርቦ ደርቦ የስጥህ፡፡ በርታ

  ReplyDelete
 29. መንገድ ያለው ከውስጥ ነው፡፡ የውጭው መንገድ እግር ነው የሚሄድበት፡፡ የውስጡ መንገድ ግን ልቡና ነው የሚጓዝበት፡፡ በልቡናቸው የሄዱ ሰዎች ናቸው በእግራቸው ለመሄድ ፈልገው የእግሩን መንገድ የሠሩት፡፡ ከእነርሱ በኋላ ግን ብዙዎቹ በልቡናቸው ሳያዩ ይጓዙበታል፡፡

  ReplyDelete
 30. Dear Daniel
  I thank you very much for this article. To be honest i read it at the time i need it most. Many thanks
  Samuel

  ReplyDelete
 31. "ሳይነኩት በምኞት ብቻ የሚወገድ ችግር የለም፤ የሚከፈትም በር የለም"

  ReplyDelete
 32. እግዚአብሔር ሁላችንንም የምነጠቀምበት አእምሮ ስለጠወን መሞከር አለብን

  ReplyDelete
 33. በጨበጣ ብቻ ቸግር አይፈታም መድከም እግዚአብሔር በሰጠን አእምሮ መጠቀም ያስፈልጋል

  ReplyDelete