Tuesday, October 30, 2012

118ኛው ፓትርያርክ መንገድ ላይ ናቸው

ዐቃቤ መንበር አቡነ ጳኩሚስ ድምጽ ሲሰጡ
የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን 118ኛውን ፓትርያርክ የመምረጡ ሂደት ወደ መጨረሻው ምዕራፍ ተሻግሯል፡፡  በቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግ መሠረት አዲስ ፓትርያርክ ለመምረጥ አራት ሂደቶችን ማለፍ ያስፈልጋል፡፡ የጥቆማና ማጣራት፣ የመጨረሻዎቹን አምስት ዕጩዎች የመወሰን፣ ለዕጣ የሚቀርቡትን ሦስት አባቶችን መምረጥና የመጨረሻውን አባት በዕጣ መምረጥ ናቸው፡፡
በዚሁ መሠረት ከተጠቆሙት ወደ አሥራ ሰባት አባቶች መካከል የማጣራቱና አምስቱን የመወሰኑ ሂደት እጅግ ረዥም ጊዜ የወሰደ መሆኑ ታውቋል፡፡ ይህ ሂደት ሁለት ከባባድ ችግሮች ተጋርጠውበት ነበር፡፡ የመጀመርያው ፈተና በቤተ ክርስቲያኒቱ ቀኖና ከተጻፈውና የግብጽ ቤተ ክርስቲያንም ሕግ ከሚደነግገው ውጭ ሀገረ ስብከት ያላቸው አባቶች ራሳቸውን ሳይቀር ለዕጩነት መምረጣቸው፣ ከዚህ በፊት አንዳንድ ችግሮች ተከስተውባቸው የነበሩ አባቶችም በዕጩዎች ዝርዝር ውስጥ መግባታቸው ነበር፡፡
ይህ ሁኔታ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ቀኖናና ሕግ ጋር የሚጋጭ በመሆኑ ራሳቸውን ከዕጩነት እንዲያገልሉ በአስመራጭ ኮሚቴውና በቤተ ክርስቲያኒቱ ታላላቅ አባቶችና ሽማግሌዎች የማግባባትና የማረም ሥራ ሲሠራ ነበር፡፡ ለሁለት ጊዜ ያህል ሱባኤ ታውጆ፣ ጳጳሳቱም ሁሉ ወደ አባ ብሶይ ገዳም ገብተው በጸሎትና በውይይት ችግሩን ለመፍታት ጥረት አድርገዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የተወሰኑት አባቶች ‹እኔ በሺኖዳ መንበር መቀመጥ የለብኝም› እያሉ ራሳቸውን ከዕጩነት አግልለዋል፡፡ 
ከዚያ በኋላም ቢሆን የዕጩዎቹ ቁጥር በመብዛቱና በምእመናኑም ዘንድ በአንዳንድ ዕጩዎች ላይ ቅሬታ በመፈጠሩ የምርጫ ኮሚቴው ጊዜ ወስዶ ችግሮቹን ለመፍታት ሞክሯል፡፡ እጅግ የባሰው ሁለተኛውም ፈተና የተጀመረው በዚህ ጊዜ ነበር፡፡
አንዳንድ ዕጩዎች በቴሌቭዥን ፕሮግራም ሳይቀር ልክ እንደ ፖለቲካ ተመራጮች የምረጡኝ ዘመቻ ጀመሩ፡፡ ሕዝቡ ግራ ተጋባ፡፡ ዐቃቤ መንበሩ አባ ጳኩሚስ አንዳንድ ክርስቲያን የቴሌቭዥን ጣቢያዎችን እስከ ማስጠንቀቅ ደረሱ፡፡ በዚህ ጊዜ ምእመናኑና አባቶች በወሰዱት ቆራጥ አቋምና ግፊት አንዳንድ እጩዎች ከዕጩነት እንዲወጡ ተደረገ፡፡ በመጨረሻም አምስት አባቶች ቀሩ፡፡ በዚህ ሂደትም አምስት ጳጳሳትና ሰባት መነኮሳት ከዕጩነት ወጡ፡፡ በሂደቱ ከዕጩነት ከወጡት መካከል የሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ አቡነ ቢሾይ፣ የቀድሞው ፓትርያርክ ረዳት የነበሩት አቡነ ቡትሮስና የመንበረ ፓትርያርኩ ዋና ጸሐፊ አቡነ ዮሐንስ ይገኙበታል፡፡ 

በግንቦት ወር የተጀመረው 118ኛውን ፓትርያርክ የመምረጡ ሂደት ባለፈው ሰኞ ወደ መጨረሻው ደረጃ ተሸጋግሯል፡፡ ሰኞ ዕለት በካይሮ አባስያ በሚገኘው የቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል ከአምስቱ አባቶች ሦስቱን በድምጽ የመለየት ሂደት ተከናውኗል፡፡
የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ሕግ እንደሚፈቅደው ብቃት ያላቸው የሚባሉት ድምጽ ሰጭዎች ቁጥራቸው 2411 ነው፡፡ እነዚህ ድምጽ ሰጭዎች በቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ሥር ያሉ ካህናት፣ የገዳማት ተወካዮች፣ የምእመናን ተወካዮች፣ በግብጽ ፓርላማ ወንበር ያላቸው የኮፕት ማኅበረሰብ ተወካዮች፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ተወካዮችና ክርስቲያና ጋዜጠኞችን ያካተተ ነው፡፡
እንደ ዐቃቤ መንበር  ጳኩሚስ መግለጫ ከሆነ ከጠቅላላው የበቁ ድምጽ ሰጭዎች መካከል 93% ያህሉ በሰኞ ዕለት ድምጽ ሰጥተዋል፡፡ ምርጫው ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት የተጀመረ ሲሆን ከቀኑ 11 ሰዓት ተጠናቅቋል፡፡ ይህንን ሂደት እንዲታዘቡ ጋዜጠኞች ከመላው ዓለም የተጋበዙ ሲሆን የምርጫ ሳጥኑ በመስተዋት ተሠርቶ በግልጥ ቦታ እንዲታይ ተደርጓል፡፡ ሂደቱን ምእመናንና ጋዜጠኞች በግልጥ ሲከታተሉት የነበሩ ሲሆን ለዚሁ ርዳታ ለመስጠትና እንግዶችን ለመርዳት 300 የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት በቦታው በማገልገል ላይ ነበሩ፡፡
የድምጹ ቆጠራ በዚያው ዕለት ተከናውኗል፡፡ በዚህም መሠረት አቡነ ራፋኤልና አቡነ ታዋድሮስ የተባሉ ሁለት ጳጳሳትና አባ ራፋኤል አቫ ሚና የተባሉ መነኮስ ለመጨረሻው የዕጣ ሥነ ሥርዓት ተመርጠዋል፡፡ አቡነ ራፋኤል በሚዲያዎች የቅድሚያ ግምት የተሰጣቸው የ54 ዓመት አባት ናቸው፡፡ እኤአ በ1981 ዓም ከአይን ሻምስ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ፋኩልቲ የተመረቁት እኒህ አባት ከዚያ በኋላ ወደ ነገረ መለኮት ኮሌጅ ገብተው ተመርቀዋል፡፡ ክህነት የተቀበሉትም እኤአ በ1984 ዓም ነው፡፡
አቡነ ራፋኤል በመካከለኛው ካይሮ የፓትርያርኩ ረዳት ጳጳስ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን የወጣቶችን ጉዳይ ጉዳያቸው በማድረግና ከወጣቶች ጋር በመሥራትም ይታወቃሉ፡፡ አቡነ ራፋኤል ብዙ ጊዜ በከተማ ከሚገኙ ድኾች ጋር በመሥራታቸውና ችግራቸውንም ለመፍታት በመጣራቸው ‹የድኾች አባት› እስከመባል ደርሰው ነበር፡፡
አቡነ ራፋኤል ሥራ አጥነትና ድኽነትን በሚመስሉ ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ በሚያቀርቧቸው ሃሳቦች ይታወቃሉ፡፡ በሃይማኖቶች መካከል የሚደረገው ሽኩቻና ጥላቻ ‹ለእግዜር የለሽነት› መንገድ ከመክፈት ያለፈ ጥቅም የለውም በሚለው አቋማቸው ብዙዎች ያውቋቸዋል፡፡
አቡነ ታዋድሮስ በበህይራ ሜትሮፖሊስ የፓትርያርኩ ረዳት ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በዝምተኛነታቸውና ነገሮችን በማግባባትና በዕርቅ ለመጨረስ ባላቸው አቀራረብ ይታወቃሉ፡፡ በሚዲያ ላይ ወጥቶ በማንኛውም ጉዳይ ላይ መናገርን የማይወዱት አቡነ ታዋድሮስ ከሌሎች እምነቶች ጋር በመግባባትና በመተጋገዝ መኖርን የሚሰብኩ፣ ወጣቶች ራሳቸውን ከሌላው ማኅበረሰብ ማግለል እንደሌለባቸው የሚያስተምሩ ናቸው፡፡
የስድሳ ዓመቱ አባት አቡነ ታዋድሮስ ከእስክንድርያ ዩኒቨርስቲ በፋርማሲስትነት የተመረቁ ሲሆን ከዚያም በኋላ በፋርማሲ ኢንጅነሪንግና በማኅበራዊ ጤና ከሲንጋፖርና ከእንግሊዝ ዩኒቨርሲቲዎች ተመርቀዋል፡፡ ከመመን ኮሳቸውም በፊት በግብጽ የተለያዩ መድኃኒት ካምፓኒዎች ውስጥ ሠርተው ነበር፡፡ አቡነ ታዋድሮስ የሕዝብ በዛት በተጨናነቀበት የካይሮ አካባቢ ያገለገሉና የሕዝቡን ችግሮች በመካፈል የሚታወቁ አባት ናቸው፡፡
አባ ራፋኤል አቫ ሚና ከ1964 ዓም እኤአ ጀምረው በማር ሚና ገዳም የሚኖሩ አባት ናቸው፡፡ አባ ራፋኤል እድሜያቸው 70 ሲሆን ከሦስቱም እጩዎች በዕድሜ አንጋፋው ናቸው፡፡ ከሦስቱም እጩዎች ከተፈጥሮ ሳይንስ ውጭ የሆነ ፊልድ ያጠኑት እርሳቸው ሲሆኑ የተመረቁት በሕግ ዲግሪ ነው፡፡ አባ ራፋኤል የአቡነ ሺኖዳ መምህር የሆኑት የአቡነ ቄርሎስ ስድስተኛ አንዱ ደቀ መዝሙር ሲሆኑ ዛሬ በጵጵስና ያሉ ብዙዎቹ አባቶች አብረዋቸው የተማሩ ናቸው፡፡ አባ ራፋኤል በሕዝቡ ዘንድ ‹ብጹዕ ራፋኤል› በመባል ይታወቃሉ፡፡ 

አቡነ ሺኖዳ ካህናትን ለመሾም ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ማር ሚና ገዳም ሲመጡ የመሰየሚያ በትራቸውን በመንበሩ ጀርባ ትተውት ሄዱ፡፡ ረዳቶቻቸውም ለምን እንደተውት ሲጠይቋቸው ‹በሚቀጥለው ስመጣ እወስደዋለሁ› አሏቸው፡፡ ይህም በሕዝቡ ዘንድ ‹ቀጣዩ ፖፕ ከዚህ ገዳም ይሆናል› የሚል ትንቢታዊ ንግግር ተደርጎ ተወሰደ፡፡ ሕዝቡም ምናልባት አባ ራፋኤል ሳይሆኑ አይቀሩም ይላል፡፡
የመጨረሻው የፖፕ ምርጫ የሚከናወነው ጥቅምት ሃያ አምስት ቀን 2005 ዓም እሑድ ነው፡፡ እስከዚያው የሦስቱ ዕጩዎች ስም መንበሩ ላይ ሆኖ ሲጸለይበት ይሰነብታል፡፡ በዕለተ እሑድ ቅዳሴው በመንበሩ ላይ የሦስቱም አባቶች ስም እያለ ይከናወናል፡፡ ከዚያም አባቶች፣ምእመናንና ተጋባዦች በተገኙበት ከቅዳሴ በኋላ በመንበሩ ላይ የተቀመጡት ስሞች ወርደው አንድ ዓይኑን በጨርቅ የተሸፈነ ሕፃን ልጅ በሚያወጣው ዕጣ 118ኛው ፓትርያርክ ይታወቃል፡፡
እግዚአብሔር ለሁላችንም የሚሆን አባት ያምጣልን፡፡ 

27 comments:

 1. አሜን እግዚአብሔር መልካም እረኛ ይስጠን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. እንዲያው ልፋት ነው ወንድሜ። እንደ ቤ/ክርስቲያኒቱ ህግማ በፓትሪያርክ ላይ ፓትሪያርክ አይሾምም ነበር። የኢትዮጵያ ቤ.ክ. እኮ አልቆለታል። ዝም ብለን ነው እምንጨነቀው። ዓይን ያወጣ የፖለቲካ ስራ በቤ.ክ. እየተሰራ እያየን ከዚህ የተሻለ ይመጣል ማለት ሞኝነት ነው። እነ ዲያቆን ዳኒም እኮ .... እንዲያው ዝም ይሻላል ወንድሜ! ዝም አይነቅዝም ነው ነገሩ። ጉድ በል ጎንደር ይላል ያገሬ ሰው.... ጉድ ጉድ ማለት ይሻላል።

   Delete
 2. our COPTIC CHRISTIANS father is our father too and im very much interested to see a holy father as SAINT FATHER SHOUNUDA III.

  ReplyDelete
 3. why our Ethiopian orthodox tewahido church follows this type of vote . this vote is very frank and including the God . please our church working together with followers and free from politics

  ReplyDelete
 4. OMG it is so descriptive.

  ReplyDelete
 5. what if they sent one of them to us ethiopia

  ReplyDelete
 6. አሜን! እግዚአብሔር ለሁላችንም የሚሆን አባት ያምጣልን፡፡

  ReplyDelete
 7. አቡነ ሺኖዳ ካህናትን ለመሾም ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ማር ሚና ገዳም ሲመጡ የመሰየሚያ በትራቸውን በመንበሩ ጀርባ ትተውት ሄዱ፡፡ ረዳቶቻቸውም ለምን እንደተውት ሲጠይቋቸው ‹በሚቀጥለው ስመጣ እወስደዋለሁ› አሏቸው፡፡ ይህም በሕዝቡ ዘንድ ‹ቀጣዩ ፖፕ ከዚህ ገዳም ይሆናል› የሚል ትንቢታዊ ንግግር ተደርጎ ተወሰደ፡፡

  የሚገርም ነገር ነው፡፡ ይህ ትልቅ ምስጢር እንዳለው አምናለሁ፡፡

  በእኛም አገር እንደዚሁ የእሱ ፈቃድ ብቻ ይሁንልን፡፡ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 8. አሜን! ዳኒ ሙያ ከጎረቤት ይባል የለ፡፡ የኛም እንዲህ ይሆን ዘንድ ተመኘሁ፡፡ ለማንኛዉም ለቤተክርስቲያናችን ቅን መሪ ይስጥልን፡፡

  ReplyDelete
 9. Amen, amlake israel legnam endihu melkam abat yisten.

  ReplyDelete
 10. አሜን እግዚአብሔር ለኛም መልካም አባት ይስጠን፡፡

  ReplyDelete
 11. Amen! Yadirgilin!

  ReplyDelete
 12. በጣም ደስ የሚል ነገር ነው በተለይ የግብጽ የአባቶቻቸው አገልገሎት:: በእኛ አገር ደርጃ እንደዚህ ታች ደርስ ወርዶ የሚአገለግል በግልጽ አይታይም:: ወደዚህ ደረጃ ለመደርሰ በዙ መሰራት አለብን:: ቃለ ህይወትያስማለን::

  ReplyDelete
 13. አአሜን እግዚአብሔር የፈቀደው ይሁን!!

  ReplyDelete
 14. ይሄ ለኛ ሲኖዶስ ታላቅ ትምህርት ነው:: ለሃይማኖቱ ተቆርቅዋሪ
  አርቆ አሳቢ አባት እግዚአብሔር እንዲሰጠን ሁላችንም በፀሎት እንትጋ

  ReplyDelete
 15. አቤት እንዴት ደስ ይላል ስርአቱ!!!!! አምላኬ ሆይ የኛንም ሃገር ጰጰስ በአንተ እርዳታ እንዲመረጡ አግዘን፡፡

  ReplyDelete
 16. አሜን.
  እግዚአብሔር ለኢትዮጵያም እንዲ ባደረገላት

  ReplyDelete
 17. የምረጡኝ ቅስቀሳውን ነገር እንኳን የሰይጣን ጆሮ አይስማ፡፡ የኛ ጳጳሳት ይቺን ከሰሙ ጉድ ነው፡፡

  ReplyDelete
 18. What a choice! what a blessing! three of them are really fit for the job in human terms!..what I am worried about is that if we can even find one from the Pops..I do 100% sure there can be many Monks but they are not willing to come out..the real once are hiding in the dense alone with God! May we at least have their prayers heard that God will give us a real father, a father for all of US! Amen

  ReplyDelete
 19. አሜን.
  እግዚአብሔር ለኢትዮጵያም እንዲ ባደረገላት አሜን.አሜን

  ReplyDelete
 20. how long ours gone take based on this!

  ReplyDelete
 21. I really like the picture captured by Reuters. As they say a picture is worth a thousands words! I don't think it's a coincidence that two of the most ancient Orthodox's churches (in the world) lost both their Pope's in a matter of months. If we see the bigger picture I truly beleive God has intended it to be this way. The Copts preceded us in history with many things, and we have been there to learn and follow. And now in real time, the EOTC church can learn so much from their preceedings in electing a new pope.

  ReplyDelete
 22. አሜን! ዳኒ ሙያ ከጎረቤት ይባል የለ፡፡ የኛም እንዲህ ይሆን ዘንድ ተመኘሁ፡፡ ለማንኛዉም ለቤተክርስቲያናችን ቅን መሪ ይስጥልን፡፡

  ReplyDelete
 23. አሜን! እግዚአብሔር ለሁላችንም የሚሆን አባት ያምጣልን፡፡

  ReplyDelete