Thursday, September 13, 2012

4 ሚሊዮን


የጡመራችን ተከታታይ 4 ሚሊዮን መድረሱን መረጃችን ገልጦልናል፡፡ ይህ በሁለት ዓመት ከአምስት ወር የተገኘ ስኬት በብዙዎች ጸሎት፣ እገዛና አስተያየት የተገኘ መሆኑን እገነዘባለሁ፡፡ በጽሑፎቹ ሃሳቦች ተስማምተው የሚያነቡም ሆኑ ተቃውመው የሚያነቡ፤ የሚያመሰግኑም ሆኑ የሚሳደቡ፣ ለራሳቸው የሚያስቀሩም ሆኑ ለሌሎች የሚያዳርሱ ሁሉ አስተዋጽዖ አድርገዋል፡፡
ለጽሑፍ መነሻ የሚሆኑ ነገሮች የሚልኩ፣ ጊዜ ወስደው ከሀገርም ሆነ ከውጭ ደውለውና ጽፈው ሃሳብ የሚሰጡ፤ ያልጣማቸውን ነገር የሚተቹ፤ ለቀጣይ ሥራ ብርታት የሚሆን ድጋፍ የሚሠጡ ብዙዎች ናቸው፡፡ በዚህ የጡመራ መድረክ የሚወጡ ጽሑፎች በሀገር ውስጥ ከስድስት ከሀገር ውጭ ደግሞ ከአምስት በሚበልጡ ጋዜጦችና መጽሔቶች ላይ ይወጣሉ፡፡ በልዩ ልዩ ሬዲዮዎችም ይቀርባሉ፡፡ በተለይም አንዱ ዓለም በፋና ሬዲዮ የሚያቀርባቸውን ትረካዎች ብዙዎች እንደሚከታተሉት ነግረውኛል፡፡ 
በዚህ ጦማር የሚወጡትን አንዳንድ ጽሑፎች ለአዲስ ጉዳይ መጽሔት የተጻፉ ናቸው፡፡ እስካሁን ድረስ ተገቢውን ክፍያና የሥነ ምግባር ደንብ የሚፈጽመው እርሱ ብቻ ነው፡፡ አንዳንዶች ባይከፍሉም ያስፈቅዳሉ፤ ከዚህ የባሱት ደግሞ ምንም ዓይነት ፈቃድ ሳያገኙ እንዲሁ ያትማሉ፤ እጅግ የባሱትም ከየት እንዳገኙት ምንጭ ሳይጠቅሱ፣ የጸሐፊውንም ስም ሳያሰፍሩ ያወጣሉ፡፡ እጅግ በጣም የከፉት ደግሞ በራሳቸው ስም ያወጡታል፡፡
በተለይ ከኢትዮጵያ ውጭ የሚታተሙ አንዳንድ ጋዜጦችና ድረ ገፆች ስም እንኳን አለማውጣታቸው ካሉበት ሀገር ምንም አልተማሩም እንዴ? ያሰኛል፡፡
በዚያም ሆነ በዚህ ወንጌል ተሰበከ እንዳለው ጳውሎስ፣ በዚህም ተብሎ በዚያ ሃሳቦቹ ብዙ ቦታ እንዲደርሱ ተደርገዋል፡፡ በተለይ ደግሞ በኢሜይል የሚያሠራጩ፣ በወረቀት አትመው የሚበትኑ፣ በፌስ ቡክ ላይ የሚያወጡ፣ ማንበብ ለማይችሉ ወላጆቻቸውና ጎረቤቶቻቸው የሚያነቡ አያሌ መሆናቸውን ተረድቻለሁ፡፡ ከባንክ ዓመታዊ በዓል እስከ ሰንበት ትምህርት ቤቶች በዓል ድረስ ያነበቡም አልጠፉም፡፡ የሃይማትና የፖለቲካ መሪዎች እነዚህን ጽሑፎች እንደሚያገኙዋቸው ርግጠኛ ነኝ፡፡ መጠኘኛ ሃሳብ ያገኙባቸዋል ብዬም አምናለሁ፡፡
አልፎ አልፎ በተገቢው ጊዜ ጽሑፎቹን ለማውጣት ባለመቻሌ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ የክፍለ ሀገርና የውጭ ጉባኤያት ሱበዙ፤ የምሔድበት ቦታ የኔትወርክ ችግር ሲኖረው፤ መብራት ሲጠፋና ኃላፊነቶች ሲደራረቡ እንዲህ ይከሰታል፡፡ አልፎ አልፎ ደግሞ የፒዲኤፍ ቅርጹን ለማውጣት የኢንተርኔት መሥመር መጨናነቅ ያጋጥማል፡፡
በተቻለኝ መጠን ሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ለሆኑ አገልግሎቶች በቀን እስከ ሰባት ሰዓት መድቤ እንኳን ማጠናቀቅ አልተቻለም፡፡ በየቀኑ ቢያንስ ለሃ አምስት ሰዎች በኢሜይል ጥያቄዎቻቸውን እመልሳለሁ፤ ቢያንስ አምስት ሰው በቢሮ አማክራለሁ፣ ቢያንስ ሁለት ስብሰባ ላይ እገኛለሁ፤ በስልክ ደግሞ ከኢትዮጵያ ውጭ ካሉት ጋር እንነጋገራለን፤ በገዳማትና በስብከተ ወንጌል ላይ የሚሠሩ ሁለት ኮሚቴዎችን እሰበስባለሁ፤ እነዚህ እንግዲህ ከሌሎች ጋ ሲደመሩ ቀኑ ይጠባል፡፡ እንደዚህም ሆኖ ግን ላለማቋረጥ ጥረት አድርጌያለሁ፡፡
እንግዲህ አብረን ተባብረን እዚህ እንደደረስነው ሁሉ ለወደፊትም ጸንተን እንቀጥላለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ጸሎታችሁ፣ አስተያየታችሁና፣ ሃሳቦቻቸሁ አይለዩን፡፡ ምናልባት በታሪካችን ውስጥ አንድ በጎ አሻራ መተው ብንችል፡፡
በቀጣዩ ዓመት ሚያዝያ ወይም ግንቦት ላይ ዕድሜ ቢሰጠኝ የዚህን ጡመራ ሦስተኛ ዓመት ከአዲስ አበባ ውጭ በሚገኝ አንድ የክልል ከተማ እናከብራለን፡፡ ዋና ዓላማው ከአዲስ አበባ ውጭ ላለው ወገን ስለ ማኅበራዊ ሚዲያ በባለሞያዎችና በሚመለከታቸው አካላት የሚቀርቡትን ዝግጅቶች በቅርቡ እንዲያገኝ ማደረግ ነው፡፡ ከዚያም ወዲህ እንደዚሁ ከአዲስ አበባ ውጭ በሚገኝ አንድ ከተማ በዚህ ብሎግ ላይ የወጡ ጽሑፎች የተካተቱበት ሦስተኛው መድብል ምረቃ ይኖራል፡፡ ሁሉም ነገር ለምን አዲስ አበባ ብቻ፡፡
ለሁሉም እድሜና ጤና ይስጠን፡፡ አሜን፡፡
ዋሽንግተን፣ ዳላስ ዓለም ዐቀፍ ዐውሮፕላን ማረፊያ

58 comments:

 1. በጣም ደስ ያሰኛል ብሎግህ ለድህረ ገጾች ሁሉ ቅመምና ጨው ሆኗል በዚሁ ቀጥል

  ReplyDelete
 2. ዳኒ ገና እንበዛለን በርታ ብርታቱን ያድልህ በጣም ደስ ይላል
  ዮናስ አበበ ከሮማ

  ReplyDelete
 3. may God be with u all the rest of your life

  ReplyDelete
 4. Thanks a million for your contribution. You said it right some people do not site reference when they want to share some articles to others. That is bad. Very bad! Yeah plagiarism is very disgusting. It discredits the writer's credibility. One brotherly comment, when you get articles from someone you know please ask them where they get it and who the author is. I am saying this because sometimes I read some articles on this blog without the originator’s name. Keep it up the good work.

  ReplyDelete
 5. ለሁሉም እድሜና ጤና ይስጠን

  ReplyDelete
 6. congratulation,Dani.It is our success.

  ReplyDelete
 7. Fetarie edemiawen tena yiseteh!!!kezihe kuter lake yale anbabie ena adenakie edaleh yebekulian mesekerente mesetete echelallehu.Yawe*ENAKUM?Benia bekule*Eneketel!
  Wondem ,Danie
  Dessalegn,Angola,Luanda

  ReplyDelete
 8. enkuan des alleh dn daniel. ene bebekule kezih tumera bizu timhirt agignchalehu. lewedefitu lelelochim endidares yebekulen astewatsi'o adergalehu. berta egziabher yirdah.

  ReplyDelete
 9. Endale Alemayehu - AtlantaSeptember 13, 2012 at 11:12 PM

  congratulation for your success. we are your big fans! .. keep it up brother !!

  ReplyDelete
 10. "በተቻለኝ መጠን ሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ለሆኑ አገልግሎቶች በቀን እስከ ሰባት ሰዓት መድቤ እንኳን ማጠናቀቅ አልተቻለም፡፡ በየቀኑ ቢያንስ ለሃ አምስት ሰዎች በኢሜይል ጥያቄዎቻቸውን እመልሳለሁ፤ ቢያንስ አምስት ሰው በቢሮ አማክራለሁ፣ ቢያንስ ሁለት ስብሰባ ላይ እገኛለሁ፤ በስልክ ደግሞ ከኢትዮጵያ ውጭ ካሉት ጋር እንነጋገራለን፤ በገዳማትና በስብከተ ወንጌል ላይ የሚሠሩ ሁለት ኮሚቴዎችን እሰበስባለሁ፤ እነዚህ እንግዲህ ከሌሎች ጋ ሲደመሩ ቀኑ ይጠባል፡፡ እንደዚህም ሆኖ ግን ላለማቋረጥ ጥረት አድርጌያለሁ፡፡" ዲ/ን ዳኒ የሚገባችሁን ሰርታችሁ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን በሉ የሚለውስ የት ሄደ? ራስን መስበክ ይመስላልና ይህንን አንቀጽ ብታስተካክለው ወይም ብታወጣው ደስ ይለኛል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Some times good to learn from it. But I argue he should have to take care not to be proud of it.
   Generally speaking I like the paragraph. It shows my failure to work things on time.

   Delete
  2. Ega benehone sente neger enkebateralen. Sefo seweta yalemenem weta werede yetesafe endaymeslen. wendemachen holonem neger selalzerezerew new enge ke Sematnate aytenanesem yemeseraw sera.
   Wondemachen Daniel Egzabher amlak regem edme yesteh Berta.

   Delete
 11. Daniel, I belived you will achieve your goal, but don't forget to give time for your family.

  ReplyDelete
 12. በጣም አስገራሚ...
  እስከ ታህሳስ 31 2011 እ.ኤ.አ. ድረስ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር 622,122 ሲሆን ይህም ማለት ከአጠቃላዩ የህዝብ ብዛት 0.7% አካባቢ የሚሆነው ብቻ ማለት ነው። እንዲሁም ፌስቡክን የሚጠቀሙት ኢትዮጵያዊያን እስከ መጋቢት 31 2012 እ.ኤ.አ. ድረስ 511,240 ብቻ ነው። ይህ ሆኖ ሳለ የዲያቆን ዳንኤል ክብረት ጡመራ (http://www.danielkibret.com) 4 ሚሊዮን ጊዜ መነበቡ በጣም ግራሞትን ይፈጥራል። 622,122 ተጠቃሚዎች 4 ሚሊዮን ጊዜ ከአነበቡት 4 ሚሊዮን ተጠቃሚ ቢኖር ምን ያክል ይነበብ እንደነበር መገመት አያዳግትም። ፌስቡክን እንኳን በኢትዮጵያ ውስጥ የእሱን አንድ ስምንተኛ አካባቢ ብቻ ነው የተጎበኘው። ምን አይነት ጠቃሚ ሐሳቦች ቢነሱበት ነው ይህን ያክል ሊነበብ የቻለው? በጣም አያሌ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን የሚዳስሱ መረጃዎች ይወጡበታል። መቼ ይህ ብቻ በጋዜጣ፣ በመጽሔቶች፣ በሬዲዮ እና በተለያዪ ብሎጎች ላይም ይሰራጫሉ። ስለዚህ በእነዚህ የመገናኛ ዘዴዎች ላይ የሚያነቡትን እና የሚሰሙት ቢቆጥሩ ደግሞ ቁጥሩ ከእልፍ ሚሊዮን በላይ እንደሚሆን መገመት ቀላል ነው።
  ስለዚህ የወጡትን ጽሁፎች አንበብን ጆሮ ያለው ይስማ፣ ልብ ያለው ልብ ይበል ነው ብንጠቀምባቸው፤ ጽሁፎቹ ደግሞ ያልሆነ ሀሳብ ያለባቸው ከመሰለን ብንተቻቸው ጸሀፊውም ወደ ፊት የበለጠውን ይጽፋል። ጽሑፎችም እኛ ተጠቅመንባቸው ለታሪክ ማስተላልፍም እንችላለን።
  ለነገሩማ ጦማር አደባባይም(http://www.adebabay.com) ከ“ዜግነታዊ ጋዜጠኝነት” አንዱ “ጡመራ” ነው ብሎን ነበር።

  ReplyDelete
  Replies
  1. 622,122 ተጠቃሚዎች 4 ሚሊዮን ጊዜ ከአነበቡት...4 ሚሊዮን አገር ውስጥ ነው እንዴ? አለም አቀፍ ነው:: Page views ይሁን total visitors አላወቅንም:: ጥሩ መለኪያው subscribers, (feed burner readers) ,percent new and return visitors and bounce rate ናቸው::

   Delete
 13. Dear Dani. You are my name sake, due to the few years of my childhood I spent in Ethiopia I am able to read geez fontes. In my adulthood i comeacross to your preachings and writings. Ewnet ewnet elhalew...Most of my vivde ideas are mostly from your teachings or your inspirations. I am not Ethiopian and I don't live in Ethiopia but I feel as a family through your teachings. You are making a difference Brother, and one thing I am among those who distribute your blog articles with print out and verbaly.
  God bless You more.I would love to read your articles till my old ages.

  ReplyDelete
 14. Yetekedese hasab new D. danial enem ke addis ababa wuch hogn be mobile andim tsihuf amilitogni ayawukim berta
  from minjar

  ReplyDelete
 15. ወንድም ዳንኤል ይህን ያህል አንባቢ መታደሙ ጥሩ ነው፡፡ በቁጥሩ ብዛት ደስ የሚልህ ይመስለኛል ምክንያቱም ሰው የወለደውን ሲስሙለት የደገሰውን ሲበሉለት ይባላል፡፡ እኔ ግን በዚህ ጉዳይ ላይ ያለው አቋምህ ብዙም አልተመቸኝም፡፡ ምክንያቴም የሚከተለው ነው፡፡

  አንደኛ፣ ወደ ጡመራህ የሚገባውን ታዳሚ የሚከታተለው መረጃ አጠናካሪ ሶፍትዌር የሚያነበው በጥቆማ ወይም ክሊክ ስለሆነ ይህ ቁጥር 4 ሚሊዮን ሰዎች ታደሙ ማለት አይደለም፡፡ የዘወትር ተሳታፊዎች የሆኑና ቢያንስ በቀን ከአንድ ጊዜ አንስቶ እስከ 5 እና ከዚያ በላይ ክሊክ የሚያደርገውን ግምት ውስጥ ማስገባት አለብህ፡፡ ለምሳሌ እኔ ቢያንስ በቀን ከ5 ጊዜ ያላነሰ ክሊክ አደርጋለሁ፡፡ ስለሆነም በቁጥር ይህን ያህል ደረሰ ከምትል ይልቅ ይህን ያህል ጥቆማዎች ወይም ወደ ጡመራው ለመግባት የተደረጉ ክሊኮች ተመዘገቡ የሚለው ቀላል ይመስለኛል፡፡

  ሁለተኛ፣ ለአንተም ውዳሴ ከንቱ እንዳይሆንምህ እኛም አንጄክስ(አንጀበኛ) እንዳንልህ ቁጥሩ አስፈላጊ ነው ብለህ የምትገነዘብ ከሆነ ይህንኑ የሚመዘግበውን ሶፍት ዌር ከጡመራህ ጋር በማዋሃድ ማንኛውም የጡመራህ ጎብኚ እንዲመለከተው ብታደርግ እንደ መስቀል ወፍ ብቅ እያልክ ደስ ብሎኛል ደስ ይበላችሁ ከማለት እርፍ ትላለህ፡፡ ለምሳሌ እነ አቤ ቶክቻው ከአሽሟጣጮች ወጥመድ ለማምለጥ ቀድሞ ስላሰቡበት በቀደመው የወርድ ፕሬስ ገጹ ላይ መቁጠሪያውን በግራ ራስጌ በኩል አስቀምጦ በከፈትን ቁጥር ስንት ደረሰ እያልን እንደ ኢትዮጵያ የጤፍ ገበያ ዓይን ዓይን ሳናይ አንብበን አናውቅም፤ ቢያንስ እኔ፡፡

  ለማንኛውም 4 ሚሊዮን ብርቅ አይደለም፣ ኢሕአዴግም 5 ሚሊዮን ደጋፊ አለው፡፡ አገሪቱ የመረጃ ፍሰት ነጻነትና የተመን አገልግሎት ቅናሽ ስታደርግ፣ ሰው ላፕቶፕ መግዛት ሲችል የሚያነብልህ ቁጥር 4X80 ሚሊዮን አይደርስም ብለህ ተስፋ አትቁረጥ፡፡

  ያንተው አንባቢ ነኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. men tekebateralhe?

   Delete
  2. ቅናት ይመስላል:: ይህ ብሎግ በጣም ምርጥ ነው:: 4 ሚሊዮን ታዳሚ በበር ይምጣ በመስኮት አንዴም ይሁን 5 ግዜ ማንበብ የፈለገው የገረመው መደጋገም የፈለገው አለ ማለት ነው::በጣም commented ከሆኑ ብሎጎች ይህን የሚደርስበት ያለ አልመሰለኝም:: እኔን የሚያስቀናኝ በተደጋጋሚ የማይጠገቡ ጽሁፎችን ባለው ትንሽ ግዜ መጻፉ ምን ያህል አስተዋይ አንናቢ...መሆኑ ነው:: TV እና video ዘግተን ወደ መጽሃፋችን መመልስ አለበን!!

   Delete
 16. melkamun hlu emglealeu.

  ReplyDelete
 17. በቀጣዩ ዓመት ሚያዝያ ወይም ግንቦት ላይ ዕድሜ ቢሰጠኝ የዚህን ጡመራ ሦስተኛ ዓመት ከአዲስ አበባ ውጭ በሚገኝ አንድ የክልል ከተማ እናከብራለን፡፡

  ReplyDelete
 18. DANE CHERU EGZEABHER KANTE GAR YIHUN. ENIKETELIHALEN ,ENAGIZHALEN, ANTE BICHA BERTA!.
  DEREJE.T

  ReplyDelete
 19. God Bless You!!!!!!!!
  Your words are healing scare in life ...
  Many Thanks!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 20. Congratulations!!!

  As always, may GOD be with you Daniel. You are real hero dani. Berta berta berta berta ..............................
  .......................

  I have to say this I am Dani Blog Addict (DBA, I did not want to use DA-drug addict). I always read your blog.

  I want to suggest one thing, for well organized continuality can we create some organization. The organization can work for publishing, teaching and supporting young writers, poeters.

  ReplyDelete
 21. such blog.is never erasing b/c it preaches a lot.even-though some of the readers are out of normal you & good idea raisers keep it up!!
  NO PAIN NO GAIN!!
  UR SIMACHEW FR. A.A

  ReplyDelete
 22. ውድ ወንድሜ ዲ/ን ዳንኤል፡- እየሰጠኸው ያለው አገልግሎት የብዙ ሰዎችን የችግር ቋጠሮ የሚፈታ፣ እንደ ሃገር ለሃገር እድገት ግባዓት ሊሆኑ የሚችሉ በጣም ወሳኝና በሌላ ሊተኩ የማይችሉ ወርቅ ወርቅ ሃሳቦች የያዘ በአጠቃላይ ለቤተ ክህነትም ለቤተ መንግሥትም በእጅጉ የሚበጁ ቁምነገሮች የሚገኙበት ስለሆነ ከዚህ የበለጠ እንድታገለግል እግዚአብሔር በጸጋ ላይ ጸጋ (ጸጋ በዲበ ጸጋ) እንዲጨምርልህ የዘወትር ጸሎቴ ነው፡፡

  አባቶቻችንን በነገር ሁሉ የረዳ የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር በቸርነቱ ይጠብቅህ፤ ረዥም እድሜ ከሙሉ ጤና ጋር ያድልህ፡፡ በርታ!!

  ReplyDelete
 23. I have no word to express my felling...

  God Bless you and your family. May St. Raphael be with you.

  ReplyDelete
 24. Congradulations Dani for your great job!!!

  ReplyDelete
 25. ዲ/ን ዳንኤል መልካሙን ነገር ሁሉ አደረክልን፤አሁንም በርታ፡፡በጽሁፎችህ እነዚህን ተጠቀምኩኝ፤
  1. ተቀድተዉ ሊያልቁ የማይችሉ ሃማኖታዊ እና አለማዊ ቁም ነገሮችን አግኝቻሉ
  2. ጽሁፍህ ላይ አስተያየት(በጥሩም በነቀፋም) በመሰንዘር የመጻፍ አድማሴን በመጠኑም ቢሆን እንዳሻሽል እረድቶኛል
  3. የመጀመሪያዉ መድብልህን ከአዲስ አበባ ወደ ክፍለ ሀገር በርከት አድርጌ በማስመጣት እና በመሸጥ መጠነኛ የሆነች ገቢ አገኝቻለሁ
  4. በጽሁፍችህ ላይ በስራ፤በአምልኮ፤በሰፈር እና በሌሎችም ቦታዎች ከተለያዩ አካላት ጋር ዉይይት ስለማደርግ የማሳመን፤የማስረዳት አቅሜን አሻሽሎልኛል
  5. የጡመራ ብሎግህን ስከፍት እግር መንገዴን የሌሎችንም የጡመራ ብሎጎችን በመክፈት ተጨማሪ እዉቀቶችን እያገኘሁ ነዉ
  6. መድብሎችህን አነባለሁ፤ለትዉልድም አስተላልፋለሁ ብየ ስለማስብ እያሰባሰብኩኝ ነዉ፡፡ሀርድ ኮፒዉን ያንተን መድብል ከሚያከፋፍሉ ሰዎች በመግዛት ሶፍቱን ዳዉንሎድ በማድረግ፡፡በዚህም ተጠቃሚ ነኝ፡፡
  7. አይነኬ የሆኑ ቁም ነገሮችን የምትጽፍበት ስልትስ እንዴት ይረሳል?ከሰዎች ጋር ፊት ለፊት ስፋጠጥ የነበርኩበት ዘመን አሁን አሁን ያበቃለት ይመስላል፤ሰዎችን በተለይም እነእንቶየን ለመናገር፤ለማደነጋገር ከፈለኩኝ የአንተን የአጻጻፍ ስልት በንግግሬ ተጠቅሜ ቁም መልዕክቴን ማስተላለፍ ነዉ፡፡
  8. ሌላም ሌላም
  በቀጣይ መሻሻል/መጨመር ያለባቸዉ ነገሮች
  • በመረጃ የተደገፉ ጽሁፎችህ እጅግ አነስተኛ ናቸዉ በተለይም አሁን አሁን የተዉካቸዉ ይመስላል፤በተረት መሰል እያዋዛህ የምታቀርባቸዉ ቁም ነገሮች የጡመራ ቦታዉን ሞልተዉታል፡፡
  • አንዳንድ ጊዜ አንገብጋቢ ወቅታዊ ነገር እያለ አንተ ሌላ ታስነብበናለህ፤እናም ይህ ሰዉ አቋሙ በዚህ ጉዳይ ላይ ምንድነዉ ብለን እስከመጠየቅ እንደርሳለን፡፡
  • በጡመራህ ዙሪያ ለመወያየት ግድ መድብል እስከማስመረቅ ለምን ይጠበቃል?ጡመራህ መቸም በርካታ አላማዎች ይኖሩታል ብየ አስባለሁ፣እናም ያንን ግቡን በበለጠ እንዲመታ ለማስቻል ይረዳህ ዘንድ በዋና ዋና ከተሞች ስለጡመራህ የዉይይት መድረክ ለምን አታዘጋጅም?ዛሬ 4 ሚሊዮን ተከታታይ ያለዉ የጡመራ ብሎግህ ከአንድ ወይም ከሁለት አመት በኋላ በአገራችን ታላቁ የማስታወቂያ ስራ የማይሰራበት መንገድ አይኖርም አንተ ትንሽ ጥረት ከጨመርክበት፡፡እናም በዚህ በኩል በርታ፤እኛ በጽሁፍህ እዉቀት እንዳገኘን አንተ ደግሞ ለስራህ ዋጋ ማግኘት አለብህ ከሚል እሳቤ ነዉ፡፡
  4 ሚሊዮን ተከታታይስ ምን ተረዳ፤ምን ተማረ፤ምን ድክመት አገኘ?
  በመጨረሻም 3ኛዉ የመድብል ምረቃ ፕሮግራምህ ጎጃም እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
  ዉብሸት/ዘጎጃም/

  ReplyDelete
 26. ከባንክ ዓመታዊ በዓል እስከ ሰንበት ትምህርት ቤቶች በዓል ድረስ ያነበቡም አልጠፉም፡፡

  Dani,

  My classes at AAU are also one of the domains of your writings. Yeah! I took you as an example in my classes and the students were very interested. When I read "Dngay Felaccoch" to them, they were listening as a sermon or homily.

  Definitely, I have acknowledged you for I want my students to read your works for themselves. :)

  Keep up the good work. Let your light shine!


  ReplyDelete
 27. ውድ ወንድማችን፡-እኔ ስለ ስራዎችህ ቃላት ያጥረኛል። እጅግ ብዙ የሚያስቀኑ ጠባዮች አለሁህ። ትጋትህ፡-ለእኔ ታላቅ መሰረት ነው። ሲከፋኝ፤ ነገሮቹ እንዳሰብዃቸው አልሄድ ሲሉ፤ ድንገት ያላሰብኩት ነገር ሲደርስብኝ፤ ሙከራዬ ከንቱ ሲሆን ወደ ፈጣሪየ ማመልከት ጎን ለጎን በፍጥነት ወደ አንተ ድረ-ገጽ ዘው ብዬ እገባለሁ። ከገጠመኝ ችግር ሊያወጣኝ የሚችለውን መጣጥፍ (አንዳንዴ በፊት ያነበብሁት ቢሆንም) ደግሚ አነበዋለሁ። አዲስ ጉልበት፤ አዲስ ተስፋ፤ አዲስ አቅም ይሰጠኛል። አንተን የሰጠኝን አምላኬን አመሰግነዋለሁ።
  ውድ ወንድሜ አራት ሚሊዮን አንባቢ ስትል ደንግጫለሁ። ከዚህ ውስጥ አብዛኛው እንደ ኢትዮጵያዊነታችን የእኔው አይነት ገጠመኝ ያለው ነው ብዬ አስባለሁ። እናም ምክር ፈላጊ፤ አቅጣጫው የጠፋው፤ ተስፋን የተራበ አንባቢ እንዳለህ አትዘንጋ። ይሄ በጣም ትልቅ ሃላፊነት ነው። እኔ አንዳንዴ ይሄ ነገር ቢቆም ምን ይውጠኝ ይሆን የሚል ሃሳብ ይመጣብኝኛ፤ ዘልቆ ላለማሰላሰል እተወዋለሁ። ትዝ ይለኛል፤ አንድ ሰሞን በሕመም ምክንያት የተወሰኑ ጊዜያት ጠፍተህብን ነበር። የተሰማኝን ስሜት ባደባባይ ማውጣቱ ምንም ዋጋ የለውም! በመጨረሻ አንድ ጽሑፍ እስከ ጠፋህበት ምክንያት ስታወጣልን ልቤ በሃሴት ነበር የተሞላው። እናም አንባቢ በበዛ ቁጥር፤ ሃላፊነቱም እንዲሁ ነው። ከወዲሁ አንድ መላ አብጅለት። ዘላቂ ሊሆን የሚችልበትን። ይሄን መዕድ አንተ በተለያዩ ነገሮች ስትወጠር፤ አንተን ሁነው ሊያቀርቡ የሚችሉ ተተኪዎችን ማፈራት የሚያስፈልግ ይመስለኛል። ያ ሲሆን ነው፤ ለእራሱ፤ለወገኑ፤ለአገሩ፤ለእምነቱ ግድ የሚለው መሕበረሰብ ሊፈጠር የሚችለው። ያኔ ነው ያንተ ግብ መታ የምለው። ለዚህም ወላዲተ አምላክ ትርዳህ። አምላከ ኢትዮጵያ በየሄድህበት ቦታ ሞገስ ይሁንህ።

  ReplyDelete
 28. thank you dani, E/r yitebikih
  Alex from Addis Ababa

  ReplyDelete
 29. ዲ/ን ዳንኤል
  መልካምና አርአያነት ያለዉ ሀገራዊም፣ ቤተክርስቲያናዊም፣ ክርስቲያናዊም ሃላፊነትን መወጣት ነዉ፡፡ በትጋትህ እና መክሊትህን በመጠበቅህ እጅግ የሚገርም ጽናት አድሎሃል ወደፊትም ይጨምርልህ ይጠብቅህም፡፡

  ከብሎጉ ቋሚ ተከታታዮች አንዱ ነኝ፡፡

  ReplyDelete
 30. 10 Q dani Pls Keep working hard bezu entebeqalen!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 31. Congrats Deacon Daniel. I can't tell you enough how much your sebket has changed my life. I have become stronger spiritually because of you. I listen to your sebket, and read your writings over and over again. Everytime I read it, its like reading it for the first time. It just helps me so much. May God continue to bless you. I wish the best for you and your family, and hope God gives you everything you pray and ask for.

  ReplyDelete
 32. Dani, Gondar must be the place for the inauguration.

  God Bless you!

  ReplyDelete
 33. ዲያቆን ዳንኤል በጣም ደስ ብሎናል፡፡ እንኳን ደስ ያለህ የአገልግሎት ዘመንህን ያርዝምልህ ጤናህን ይስጥህ ከዚህ የተሻለ የበለጠ ነገር እንደምታስነብበን ተስፋ እናደርጋለን ብርታቱን ዕውቀቱን ይስጥህ ድንግል ማርያም ሁልጊዜ ከአንተ ጋር ትሁን አሜን

  ReplyDelete
 34. I would like to say Thanks God!
  Dani please keep the good work God has started in you. There is always ups and downs on a journey- though needless to tell you, let me use the exact words you used to tell us "Yemirote sewe enkifate ayatawem- kuche yalema endate enkifate yagegnewale" . The same medicine that cure one person may be a poison for the other - don't try to satisfy 80 million, number doesn't matter - let alone some millions a single life will matter for God! Keep doing the work God wants you to do in the years to come!!
  May God keep giving you the wisdom and strength!

  Yours brother in Him from Seattle,WA

  ReplyDelete
 35. ዳኒ ማመስገን ያስፈራኛል ምስጋናዎችንም በአይነቁራኛ ነው የማጤናቸው ያካባቢ የማህበረሰባችን ያጋጣሚዎችም ተጽእኖ ሊሆን ይችላል ለማንኛውም ምስጋና ለተገቢው ሰው ከተገቢው ሰው በተገቢው ቦታ ና ሰአት ተገቢና ትክክል በሁለቱም ጎን ለከንቱ ውዳሴ ተብሎ ካልተደረገ ችግር የሌለውና ከንቱ ውዳሴም እንዳልሆነ እረዳለሁና ስላደረግከው እያደረግክ ላለኸው ወደፊት ስለምታደርገው ስለሁሉም አገልግሎቶችህ በተለይ ስለፅናትህ ከልቤ ምስጋናዬ ይድርሰህ። በዘመናችን በተለይ በነዚህ 20 አመታት ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ውስጥ ለምሳሌ በሃይማኖት በፖለቲካ በንግዱ በስፖርት በስነጽሁፍ...እዛም እዚም ቦግ ቦግ ካሉ መብራቶች የሃገር ሃብቶች ቢያንስ በኔ ግምት አንዱ ነህና በርታ ጸንተህ አብራ ሁሌም ለኢትዮጵያ ለህዝባችን የሚጠቅም ነገር ተናገር የአበሾች ችግራችን የዘመንና የንቃተ ህሊና መራራቅ እንጂ እኛስ ጥሩዎች ነበርን የንቃተ ህሊና ችግር ደግሞ በምንም አይስተካከልም በትምህርት በማሳወቅ ብቻ ነው እናም በርታና በሃብትህ እወቅበት እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛልህ ረዳቶችህንም ይባርካቸው። ወንድምህ ከቴክሳስ

  ReplyDelete
 36. wow dani

  ውድ ወንድሜ ዲ/ን ዳንኤል፡- እየሰጠኸው ያለው አገልግሎት የብዙ ሰዎችን የችግር ቋጠሮ የሚፈታ፣ እንደ ሃገር ለሃገር እድገት ግባዓት ሊሆኑ የሚችሉ በጣም ወሳኝና በሌላ ሊተኩ የማይችሉ ወርቅ ወርቅ ሃሳቦች የያዘ በአጠቃላይ ለቤተ ክህነትም ለቤተ መንግሥትም በእጅጉ የሚበጁ ቁምነገሮች የሚገኙበት ስለሆነ ከዚህ የበለጠ እንድታገለግል እግዚአብሔር በጸጋ ላይ ጸጋ (ጸጋ በዲበ ጸጋ) እንዲጨምርልህ የዘወትር ጸሎቴ ነው፡፡

  አባቶቻችንን በነገር ሁሉ የረዳ የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር በቸርነቱ ይጠብቅህ፤ ረዥም እድሜ ከሙሉ ጤና ጋር ያድልህ፡፡ በርታ!!

  Congrats Deacon Daniel. I can't tell you enough how much your sebket has changed my life. I have become stronger spiritually because of you. I listen to your sebket, and read your writings over and over again. Everytime I read it, its like reading it for the first time. It just helps me so much. May God continue to bless you. I wish the best for you and your family, and hope God gives you everything you pray and ask for.

  ReplyDelete
 37. My question to you- How do measure your success in terms of changing or influencing your country's political, economical or social changes? I have been reading your blog since you started posting on.

  ReplyDelete
 38. ዲያቆን ዳንኤል በጣም ደስ ብሎናል፡፡ እንኳን ደስ ያለህ የአገልግሎት ዘመንህን ያርዝምልህ ጤናህን ይስጥህ ከዚህ የተሻለ የበለጠ ነገር እንደምታስነብበን ተስፋ እናደርጋለን ብርታቱን ዕውቀቱን ይስጥህ ድንግል ማርያም ሁልጊዜ ከአንተ ጋር ትሁን አሜን ::

  ReplyDelete
 39. Dn. Daniel,
  Thank God, you are here! Thank God, we are here! 4 Million. May God bless you with eternal wisdom and peace!!!

  ReplyDelete
 40. Dear D/daniel it was such happy moment for me to read ur blog and post it to my friends on fb, and to know knowledge and skill possesing brother in this years thankyou very much.at last witing ur 3rd one. God bless u and ur family.

  ReplyDelete
 41. I love you my brother, keep on writing keep on informing keep on inspiring so many lives!!!

  ReplyDelete
 42. Thank you so much for your effort. God bless you and your family.God be with you!

  Demissie

  ReplyDelete
 43. great dani, that is what we need from u. keep it up, i promise to read and post it my fb wall as i have been doing.
  GOD BLESS U DEAR BROTHER.

  ReplyDelete
 44. አዎ ለምን አዲስ አበባ ብቻ የመጽሀፉ መታተም ቴክኖሎጂና የቴሌ መስመር ባልተስፋፋባቸው የክልል ከተሞች ጽሁፍህን እንዲያነቡና እንዲማሩበት ጥሩ መፍትሄ ነው እግዚአብሄር ይርዳህ

  ReplyDelete
 45. እውነቱን ለመናገር የአንተን ጽሑፍ ጀምሬ ትቸው አላውቅም፡፡ ይጥማል፡፡ አይጎመዝዝም፡፡ ሁሉንም ያማከለ ነው፡፡ ፍትሐዊ ነው፡፡ ወገንተኛ አይደለም፡፡ ከሌሎቹ ጦማሪዎች የሚለይህ ይህ ነው፡፡ በአጠቃላይ ሳየው ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ሃይማኖታዊ ይዞታዎች ስላሉዋቸው አይሰለቹም፡፡ በርታ! Thank you very much. ግን ካለህ የተጣበቡ ጊዜያቶች ውስጥ ለቤተሰብህ ምን ያህል ጊዜ ትሰጣለህ? በተለይም ለሚስትህ፡፡ ምክንያቱም ማጀቱ ፍሪጁ ምን ቢሞላ የሚያስፈልግ በጣም የሚያስፈልግ ነገር አለ እሱን ለማሟላት ደግሞ በጣም ያልተጨናነቀ ሰውነት ያስፈልጋል፡፡ እና ብታስብበት፡፡

  ReplyDelete
 46. egzabher ybarkh yasebkehun hulu lemakenawen amlakachen yrdah

  ReplyDelete
 47. ይውጋህ ብሎ ይማርህ አልሆነብህም:: ይልቅስ ምን አለ በርታ አይዞህ የሜል መንፈሳዌና አበራታች ጽሑፍ ብታሰፍር::አልያም ለማህበረ ሰቡ ትልቅ ነገር አስቀምጠው ያለፉና ያሉት ይኽው ነው እረፍት ይናፍቀኛል እያሉ ማለፍ ነው::ብለህ ብትመክር:: ያም ሆነ ይህ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ሥራውንና መንገዱን ለፈጠረው ጌታው ያሰረከበ ሰለሆነ ዛሬ በ4ቁጥር የተገረምን ሁሉ እድሜውን ይስጠን የላቀውን እናያለን :: ዳኒ የድንግል ልጅ አይለይህ:: በርታ ::

  ReplyDelete