click here for pdf
ሴትዮዋ እርሟን አንድ ቀን ወጥ ሠራች አሉ፡፡ ገና ወጡ ከድስቱ ሳይወጣ ጎረቤቱን ሁሉ
በነቂስ ጠራችና ወጥ ቅመሱ አለች አሉ፡፡ ሰውም ምን አዲስ ነገር ልታሳየን ይሆን? እያለ ግልብጥ
ብሎ ወደ ቤቷ መጣ፡፡ ሴትዮዋም እንጀራውን እያጠፈች ከድስቱ ወጥ እየጨለፈች አቀረበች፡፡
በላተኛውም ግምሹ እያዳነቀ፣ ግማሹም እየሳቀ፣ ግማሹም እየተሳቀቀ፣ ሌላውም በቸርነቷ
እያመሰገነ በላ፡፡ እርሷም ከምግቡ በኋላ ቡና አፍልታ የተጋባዦችን አስተያየት ትቀበል ጀመር፡፡ አንዳንዱ በወጡ አሠራር
መደነቁን፤ ሌላው በተጠቀመችው ቅመም መማረኩን፤ ሌላውም የጨመረችው ቅቤ ልዩ መሆኑን፤ የቀረውም ሰው በሠራችበት ድስት የተደነቀ
መሆኑን ነገራት፡፡ እርሷም ‹‹እርሟን ጠምቃ ሰጠች ጠልቃ›› ሳይሏት ይህ ሁሉ ጎረቤት ተገኝቶ ይህንን የርሷን ግብዣ ማድነቁ አስደስቷታል፡፡ ከዚህ በፊት በሠፈሩ ያልተደረገ፤
አዲስ ነገር መሆኑንም ጎረቤቶቿ አድንቀውላታል፡፡
እስከ ዛሬ ድረስ እኔ ነኝ ያሉ አያሌ የወጥ ባለሞያዎች በመንደርዋ ተሠርተዋል፤
እንዲህ እንደርሷ ሰው ግልብጥ ብሎ ወጥቶ ወጡን የቀመሰለት፤ እንዲህ እንደርሷም ወጡን ለሕዝብ ክፍት ያደረገ ባለሞያም ታይቶ
ተሰምቶ እንደማይታወቅ የተናገሩም ነበሩ፡፡
እናም በዚያ ዕለት ቀኑን ሙሉ ቤቷ ወጥ ለመቅመስና አድናቆታቸውን ለመግለጥ በመጡ
ሰዎች ተጨናንቆ ዋለ፡፡ አንዳንዱም፣ ሰው ወጥ ለመቅመስ የተሰለፈ መሆኑን አንኳን ሳይሰማ እንዴው ሰልፍ ሲያይ ጊዜ ወይ ቲ
ሸርት ወይም ስንዴ ይሰጣል ብሎ በመገመት እንዴው ተቀላቅሎ የገባም ነበረ፡፡
እናም ቀኑ በዚህ መንገድ አለፈ፡፡
ማታ ሴትዮዋ ቀኑን ገመገመችው፡፡ የሕዝቡ ተሳትፎ እንዴት ነበር? አለች፡፡
የመንደሩ ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ አስተያየቱን የገለጠበት ሁኔታ መኖሩንም ተገነዘበች፡፡ በሌላም በኩል የተሠራው ወጥ ማነሱን
ከሕዝቡም ቁጥር አንጻር ቅስቀሳ ቢደረግና በሚገባ ቢሠራ ኖሮ ከዚህ በላይ ሕዝብ ሊወጣ ይችል እንደነበረ ተረዳች፡፡
ከዚያም በመንደሩ እኔ ነኝ ያለ ትልቅ ጎላ ተከራየች፡፡ ይህ ድስት በአንድ ጊዜ
ከዐሥር በላይ በጎችን ውጦ ዝም ማለት የሚችል ዓይነት ነው፡፡ ምድጃውንም ናቡከደነፆር ሠለስቱ ደቂቅን ከጣለበት ምድጃ
እንዳይተናነስ አድርጋ አሠራችው፡፡ ማማሰያውንም ወጥ ለማማሰል ሳይሆን ነገር ለማማሰል በሚያስችለው መጠን አስቆረጠችው፡፡ ምንም
እንኳን ከዚያ በፊት እንጨት መቁረጥ ለአካባቢ ጥበቃና ለመሬት ለምነት ጎጂ መሆኑን፣ ኅብረተሰቡም ከዚህ ጎጂ ባሕል መውጣት
እንዳለበት በዕድርና በዕቁብ ቢከለከልም እርሷግን ያሳየችው ነገር ለየት ያለ በመሆኑ ተፈቀደላትና ስድሳ ሸክም እንጨት አስቆርጣ
ለማገዶ አዘጋጀች፡፡
በዚያ ሰሞንም የመንደሩ ወሬ ሁሉ ተቀየረ፡፡ በልቅሶም በገበያም፣ በሠርግ ቤትም፤
በሻሂ ቤትም፤ በቡና ቤትም ፤ በጠጅ ቤትም ወሬው ሁሉ ስለ ሴትዮዋ ወጥ ሆነ፡፡ እንዴውም ስለ እርሷ ወጥ የማያወራ ሰው ሁሉ
ወሬ የጠፋበትና አላዋቂ መስሎ እስከሚታይ ድረስ ወሬው ሁሉ ስለ ወጡ ብቻ ሆነ፡፡ የመንደሩ አዝማሪዎች እንኳን በየጠጅ ቤቱና
በየ አረቂ ቤቱ የሚዘፍኑት ዘፈን ሁሉ ስለ ወይዘሮዋ ወጥ ብቻ ሆነ፡፡ የአካባቢው ለማኞች እንኳን ከሕዝቡ ገንዘብ የምናገኘው
የሰሞኑን ወጥ ስናነሣ ነው ብለው ስላሰቡ፤ ‹‹ስለ ሰሞኑ ወጥ›› እያሉ ነበር የሚለምኑት፡፡ አንዳንድ የሠፈሩ ወይዛዝርትም በዚህ
ሰሞን የዚህ ወጥ ወሬ ካልቀዘቀዘ በቀር ሌላ ወጥ መሥራቱ ‹‹ሠርቶ እንዳልሠሩ መሆን ነው›› እያሉ ወጥ መሥራቱን ትተውታል
ይባላል፡፡
በየጉልት ገበያውና በየመንደሩ ሱቆች፣ በየመንደር መርፌ ወጊዎችና በየመንደር አዋላጆች
ዘንድ ወሬው ሁሉ ይህ ብቻ በመሆኑ ሠራተኞቹም ሥራ ፈትተው ወሬ ብቻ ሲያወሩ ይውላሉ ይባላል፡፡ ባለጉዳዮችም የሚያስተናግዳቸው
ጠፍቶ እነርሱም አዳዲስ የወጥ መረጃዎችን ብቻ ከየቦታው መሰብሰብ ሆኗል ሥራቸው ይባላል፡፡
‹‹ይህ በእንዲህ እንዳለ አለ ቴሌቭዥን››
‹‹ሴትዮዋ ወጡን ላቅ ባለና የሌሎች መንደሮችንም ተሳትፎ ሊጨምር በሚችል መልኩ
ለመሥራት ወስናለችና ዝግጅቱን አጠናቀቀች›› ሲል አንድ የመንደሩ የኮሙኒኬሽን ባለሞያ ገለጠ፡፡ በገለጠውም መሠረት ሕዝቡም
የተገለጠው ነገር ተግባራዊ እንዲሆን ከጎን ሆኖ ለመንቀሳቀስ የበኩሉን ጥረት እያደረገ ነው ይባላል፡፡
በትልቁ ጎላ የዐሥር በግ ሥጋ ተጨመረበት፡፡ ወደ ድስቱ የሚመጣው ውኃም እጥረት
እንዳያጋጥመው ሲባል በቦቴ ታዝዞ መጣ፡፡ የቅቤም እጥረት እንዳይኖር ቅቤ ሻጮች ሁሉ በየቅቤ ማኅበራት ተደራጅተው ቅቤ ወደ
ድስቱ እንዲያመጡ ተደረገ፡፡ ላሞች ራሳቸው ተሰብስበው ቅቤውን ለመስጠት በቁርጠኛነት መወሰናቸው ተነግሯል፡፡ እናም አሁን
ካለፈው የቅቤ ታሪክ ለየት ያለ ቅቤ ወደ ድስቱ በመግባት ላይ መሆኑንም ወይዘሮዋ ለዜና ሰዎች ገልጠዋል፡፡
ሽንኩርትና ቃርያም ቢሆን ካለፈው ለየት የሚያደርገው ሻጮቹ ራሳቸው ልጠው፣ ራሳቸው
ከትፈው ማቅረባቸው ነው፡፡ ይህም ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል የሚያሳየውን ርብርብ ያሳያል ያሉ አሉ፡፡ በተለይማ የቅመማ ቅመም
ነጋዴዎች ተሳትፎ ያልተጠበቀ መሆኑን ከአማሳዮች አካባቢ የተገኘውን መረጃ ጠቅሰው የዘገቡ አሉ፡፡ ቅመሙ እንደሌላው ወጥ
እየተመጠነ ሳይሆን፣ ስለ ምግብ አበሳሰል ከተጻፉት መጻሕፍት ድንጋጌ በተለየ መልኩ በኩን ታልም በቁናም እየተጨመረ መሆኑ
ታውቋል፡፡
የየአካባቢው ቅመማ ቅመም ሻጮችም እንዴው እንዳገኙት እያመጡ በድስቱ ውስጥ መጨመር
እንጂ ከእነርሱ በፊት ተመሳሳይ ቅመም ይግባ አይግባ አይጠይቁም ነበር፡፡ አሁን ስለ ወጡ አሠራር፣ ስለ ቅመሙና፣ ቅቤው፣ ስለ
ሽንኩርቱና ቃርያው፣ ስለ ጨውና በርበሬው አስተያየት የሚሰጥ፤ ‹‹ኧረ ይሄ ወጥ በኋላ ይገለምማል፣ ይጎረናል፣ ከልኩ ካለፈ እጅ
እጅ ይላል፣ ወጡ ልክና መልክ ይኑረው›› ብሎ የሚናገርም አልተገኘም፡፡ ቢገኝም የማርያም ጠላት ይሆናል፡፡
በተለይ የጨው ነጋዴዎች ድጋፍ ይሁን ተቃውሞ በማይታወቅ ሁኔታ ግማሽ ኩንታል ጨው
አምጥተው በድስቱ ውስጥ መጨመራቸውን በኩራት ሲያወሩ የሰሙ ሁሉ የነገሩ አዝማሚያ አላማራቸውም፡፡ በርበሬ ሻጮችስ ቢሆኑ፤ እስከ
ዛሬ ድረስ ሰውን ሁሉ አቃጣይ በርበሬ እየሸጡ ሲያስነጥሱትና ሲያስለቅሱት ከርመው አሁን ደግሞ ዋናው የድስቱ አማሳዮች ሆነው
መቅረባቸው አሳዛኝም አስተዛዛኝም ሆኗል፡፡ በሕዝቡ አስተያየት የበርበሬውን ቃጠሎ ያሻሽሉታል ሲባል ያንኑ በርበሬ በባሰ ሁኔታ አምጥተው
በድስቱ ውስጥ መጨመራቸው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡
በዚህም ተብሎ በዚያ ወጡ በትብብር ተሠራ፡፡
እንደተለመደው ሕዝቡ በነቂስ ወጣ፡፡
ይህንን በትብብር የተሠራ የወይዘሮዋ ወጥ ለመቅመስ ወጣ፡፡
እርሷም ከእንጀራው እያጠፈች ፣ ከወጡም እየጨለፈች ታቀርብ ጀመር፡፡
ውኃው ቧንቧ ውስጥ እንኳን እያለ እንዲህ ያለ ጣዕም አልነበረውም፡፡ ቅመማ ቅመሙ
ለሽያጭ የቀረበ እንጂ ሊበላ ድስት ውስጥ የገባ አይመስልም ነበር፡፡ ቅቤውማ ቃናው ብቻ ሳይሆን መልኩም ጭምር ይታያል፡፡
ሽንኩርቱ ለማራቶን የተዘጋጀ እንጂ ወጥ ውስጥ የገባ አይመስልም ነበር፡፡ የበጉ ሥጋማ እዚያው በስሎ በስሎ ሟሙቶ አልቋል፡፡
አሁን ለቀማሾቹ ችግር የሆነባቸው ወጡ የምን ወጥ እንደሆነ መለየት አለመቻላቸው
ነው፡፡ ቅመሙ፣ ቅቤውና ሽንኩርቱ በዛና ወጡ የሥጋ ወጥ መሆኑን ማንም እንዳያውቀው አደረገው፡፡ ያ በመጀመርያው ወጥ ከልቡ ያደ
ነቀው፣ ያጣጣመው፣ ያ መጀመርያ ጨምሩ ጨምሩ እያለ እጁን ጭምር ይልስ የነበረው፤ አሁን ቅመሙም ሲበዛ፤ ቅቤውም ሲበዛ፤
ሠሪዎቹም ከልባቸው ሳይሆን በመመርያ ብቻ ያሻቸውን ሲጨምሩ፤ የወጡን ጣዕም አጠፋው፡፡
አስቀድሞ ያደነቀውና ያመሰገነውም ማማረርና ማቅለሽለሽ ጀመረው፡፡
ሴትዮዋም መጀመርያ የሰዎችን ሁሉ አስተያየት በደስታ ትቀበል እንዳልነበረች አሁን ወደ
ድግሱ ቦታም ብቅ ለማለት አፈረች፡፡
ድሮም በአውጫጭኝና በመመርያ የተሠራ ወጥ መጨረሻው ይሄ ነው፡፡ እያሉ ተመጋቢዎች
በየጠረጲዛው ሥር ይተቹ ጀመር፡፡
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት የወጣ ነውና በተመሳሳይ መጽሔት
ባታወጡት ይመረጣል፡፡
አይ ዳኒ! በእርግጥ ጽሁፉ አስተማሪ ነዉ፡፡ አቀራረቡ ግን ቁርጥ የ’ETV’ ን ዘገባ ይመስላል!!!
ReplyDeletelool..that is the message he wants to convey. it is a critics on ETV. read it carefully.
Deleteእንግዲህ ውደደውም ጥላውም እኛ እንረባረባለን!!! እንደምታውቀው “የዘመቻና የመረባረብ” ፍቅር አለብን፡፡
Deleteፍሬንድ፣ ለምን ምናምን ብሎ መጠየቅ የፋራ ነው፡፡ እንደምታውቀው በዓለም ላይ ካሉ ሥራዎች ኹሉ እጅግ ከባዱ ማሰብ ነው፡፡ ስለኾነም ማን ዓይኑ እያየ በዚህ አድክም ሥራ ይጠመዳል! አለማሰብ ለዘላለም ትኑር! እኔ በበኩሌ ራሴን ችዬ ከማስብ ራሴ ላይ ሙቀጫ ቢወቀጥብኝ እመርጣለሁ፡፡ ያ ጸጋዬ ገብረ መድኅን የሚባል ሰውዬ
“ጭንቅላትህን ግዘፍበት፤ ውቀጥበት፤ ውገርበት፤
ዝግ ብሎማ ያሰበ እንደሁ ይነግርሃል አንዳች እውነት፡፡” ብሎ ያለውን አልሰማህም እንዴ!
እድሜ ለመረባረብ ዝም ብለህ ሰዎች የሚሠሩትን ተከትለህ ትሠራለህ፡፡ በቃ! ሰዎች የሚከተሉትን ትከተላለህ! ሰዎች የሚደግፉትን ትደግፋለህ! ሰዎች የሚነቅፉትን ትነቅፋለህ! በቃ በሰላም ትኖራለህ! በመጨረሻም አንጎል በማያዛቸው እጆች የተሠራው ኑሯችሁ ሲገለማ አብሮ መገልማትና ማማረር ነው፡፡ በቃ እንደሰዉ መኖር! የሐረር ሰው “ባድ ቤ ዘዲጃ በለቹንታ፡፡” ይላል፤ “በሀገር ኹሉ የመጣ ነገር ሠርግ ነው፡፡” ማለት ነው፡፡ ምናገባህ! አንተ ብቻህን ችጋር አይቆንድድህ እንጂ ሰዉ ኹሉ አብሮህ በችጋር የሚፈተፈት ከኾነ ምናለበት! የሚበልጥህ የለ!
የመረባረብ ኹለተኛው ጥቅሙ ማንም እጅህን እንጂ ልብህን ለማየት ጊዜ አለማግኘቱ ነው፡፡ ስለኾነም አንተ ምናገባህ! ፊትህን አስመትተህ ላሽ ትላለህ፡፡ በመረባረብ ግርግር ካልሽ በኋላ ሌላ ተረኛ ተረባራቢ ሲመጣ አያይዘሽ ላጥ ትያለሽ፡፡ አንቺ ወደ ቢዝነስሽ! ርብርቡ ቢሳካ ባይሳካ ምናገባሽ! ሰዐታትሽን ሆ! ብለሽ ትቆሚና! ማኅሌትሽን ግርግር ትዪውና፣ “ማይኩን” ይዘሽ “ዘምሩ፡፡ እልል በሉ!” ወይም ደግሞ “ምእመናን!” ምናምን… ትዪና ቦታው ላይ መኖርሽን ደሞዝ የሚመጸውቱሽ አለቆችሽ ወይም ከንቱ ውዳሴ የሚወረውሩልሽ አመስጋኞችሽ ካዩልሽ በኋላ አንቺም የምትፈልጊውን አገኘሽ! እነርሱም የሚፈልጉትን አዩ፡፡ ልብሽን ማን ያየዋል፡፡ ደግሞስ ማንስ ቢያየው ምናገባሽ!
አባቴ ቅዱስ ያሬድ “አርምሞ ወተዐግሦ ያጸንዕ ሃይማኖተ፡፡” ብሎ መዘመሩን ነግሮኛል፡፡ ሀይማኖት እንዲጸና የምታምኚው እንዲገባሽ ያስፈልጋል፡፡ እንዲገባሽ ማሰብ አለብሽሽ፡ እንድታስቢ ዝም ማለት ግዴታ ነው፡፡ ስለዚህ ፍሬንድዬ! ዝምታን እንዳትመርጪ አደራ! ለፍልፊ! ጩኺ! እልል በዪ! ዝምታ እርምሽ ይኹን! ለአፍታም እንኳ ዝም እንዳትዪ! ዝም ካልሽማ ዝግ ልትዪ ነው! ዝግ ካልሽማ
“ፈላስፋው ሲመክር አደራ ብሏል፤
በምትሠራው ሥራ ቀስ ብለህ ቸኩል፡፡”
ያሉት የከበደ ሚካኤል “እርግማን” ሊደርስብሽ ነው! አረ ምን በወጣሽ! ግርግር ለዘለዓም ትኑር!
Shame on you for saying shame on Dani. You should know Dani is an individual. He is a preacher, a writer, a father, and a husband. As a preacher he is accomplishing so many things. He has written so many books and articles. If I am not mistaken he has more religious books. As a writer he can write whatever he feels, and this is one if them. It's his view. He didn't force u to read it if u don't like it. On the other hand you expect him to write about what you want. You can suggest it would be good to write about the church but you cannot be ashamed of him. I bet you he is praying for the church more than you and I are.
DeleteAnd for those of you who don't understand this article, it's either because you don't watch ETV at all or because you just want Dani to tell you wet=wet.
God bless Dani!
ምን ነካህ ዳኒ!? አስደነገጥከኝ(ምንም አንጀት አርስ ጽሑፍ ቢሆንም ማለት ነው!) አሁን ባለንበት ወቅታዊ ሁኔታ እንዲህ ያለ ጽሑፍ?
ReplyDeleteአምላክ ከክፉ ይጠብቅህ!
You wate my time man. Ketsafk bedenb Tsaf endigeban adirgeh...
ReplyDeleteYou guys need to read. What he has to do is write at his level.
DeleteAdir Bay Bite neh. We can suggest what ever we can and you should not stand fr him. We love Dani as you love him.
DeleteKetafi
Dani tawkibetalh mechem chewatana kumnegerun!!!!
ReplyDeleteWhat can i say ? i am in need of your articles so please add more and more ......and finally " i am tired of wot"
GOD BLESS ETHIOPIA AND ETHIOPIAN!!
Best. Endih likachewun nigerilin ene "betedereja melkun"
ReplyDeleteDani, ye Aleka Zenebn 'Metshafe chewata...' astawoskegn. I think I've understood what is represented in the heart of the story. I liked it.
ReplyDeleteመልካም እይታ!
ReplyDeleteአይ ወጥ...
ReplyDeleteይሄ © ሠምና ወርቅ ነው፡፡
ReplyDeleteለቀማሾቹ ችግር የሆነባቸው ወጡ የምን ወጥ እንደሆነ መለየት አለመቻላቸው ነው፡፡
ReplyDeletehahahahah!!!!!!!!!! yigerimal melikitu minidinew ante sew? lemanis new? ene anid guday bewusitih endale gin begilit lemenager endalideferik bitinagerewum ahun gizew endalihon yemisemah betekaraniw degmo yehon eyetebelashe yale melikam yenebere neger eyetemeleketih zim yalik yisemagnal. Ebakih Tiliku gereweyna mulu wot sayibelash begilit tenagerina yestekakel.
ReplyDeleteTheme of message is not clear for me, probably, i did not read it properly!!
ReplyDeletethanks, arif ashimur new yahununu huneta lemegilets
ReplyDeletewhat do u want to tell us?????????Is it about the church or the government???????
ReplyDeletei was thinking of the same sort on a similar issue. I like the way you've told it. Good one.
ReplyDeleteድሮም በአውጫጭኝና በመመርያ የተሠራ ወጥ መጨረሻው ይሄ ነው፡፡ እያሉ ተመጋቢዎች በየጠረጲዛው ሥር ይተቹ ጀመር፡፡
ReplyDeleteአስቀድሞ ያደነቀውና ያመሰገነውም ማማረርና ማቅለሽለሽ ጀመረው፡፡ ድሮም በአውጫጭኝና በመመርያ የተሠራ ወጥ መጨረሻው ይሄ ነው፡፡ እያሉ ተመጋቢዎች በየጠረጲዛው ሥር ይተቹ ጀመር፡፡
ReplyDeleteyesmonun tederajto malkes yehew neber.
ReplyDeleteandendu begid enba lemawat yetayebet huneta neber.
lelaw yemiasznew yebtesbun hazen enkaun ende melese mote yalasazenchew ayente negegir betam
woreda aynet new. Yehe bewntu yehzibun zik yale astesasebin endew bicha adro megegneten
endehiwote fisfina yezo yemiguaz sebisib bicha
endhone aynetegna miskir new.
Daneil kezih befet bizum alwkihim. Eski yethiopian mahberseb astesaseb, wog, bahil
kalew yepolitica kewse ayayizeh ande bitlen
mikniatum tru yemtsaf endihum yemastewal enam
nikatehilnawem yaleh yimeslegnal.
Ene bebkule egna ager yalew yedemocracy chiger
yetiket sewoch tebmenga meyaz aymeslegnem tilku hibretesbu nekate hilnaw manse, woge, limad ena bahilachin lalenibet dinkurna, yedimocracy matat wona mikniat new baynegn.
enam eyandandachin zimbilen endew sleteweldnibet bicha yeraschinin bahil wog eyadnken lemanfelgew hiwot esrgna banaderg tiru new bay negn.
melkam ken
eree akuAm yinuren!!!!!!!!!!!
ReplyDeleteyeboi wuha eko honin!!!!!
አዎ! 'ሲበዛ ማርም ይመራል' አይደል ተረቱ
ReplyDeleteድሮም በአውጫጭኝና በመመርያ የተሠራ ወጥ መጨረሻው ይሄ ነው፡፡
ReplyDeletebemisale meneger yetejemerebet mikniat sineger sew silemimata new teblowal! endiya new!!!
ReplyDeleteaye Dani eski yehun semina worku yegermal zirzir kis yekedal new yemibalew aydel
ReplyDeleteinteresting and amazing please add more
ReplyDeleteTiru shemute nwe berta wedaje
ReplyDeleteእቺ ሰምና ወርቅ ትፈታና ዋ! እኔ ፈራሁ፡፡
ReplyDeleteLet's say ur wife or ur kid is deceased,how long will u murn? When will you forget them?
ReplyDeleteMay be u will loss ur concious and run bare over the road. That is what happened to our beloved Ethiopia. She lost her visionary leader. A brillient ever man it had. Every piece of its part is murning except the non- Ethiopian diasporas( those who changed their citizen for comfort or because they are criminals and have no chance to live in Ehiopia at all). U r not feeling that? U know how Ethiopia is changed in his leadership. At least everybody is trying his/her best to run aganist poverity. Everybody's mind is changed. No one is willing to listen to teretterets like ur article. That is the reason. Open ur mind and be confident. If u r a story teller, tell the truth.
soul is above material level of our life and it does not compromise any false issue like your saying; yeah you and your friends may get and accumulate materials and money in the regim of Woyane but Woyane was the layer and leave Eritrea due to its selfishness. i thought woyane may regret finally duet to their evil and selfish act on the country act on Ethiopia.
DeleteThis is the truth.History never lay.
Alex from Addis
አይ ዳኒ! በእርግጥ ጽሁፉ አስተማሪ ነዉ፡፡ አቀራረቡ ግን ቁርጥ የ’ETV’ ን ዘገባ ይመስላል!!!
ReplyDeleteEndehenew kene yetemare sew !!egizer yistehe yelebene new yetsafekelegne be ETV anegagere edege !!this is what i want from you !!!lesemonu yetenzaza hazene melese endihume yelekeso wote new!!
ReplyDeletekkkkkkkkkkkkkkkkkkk des mil ashmur new bakih dani geta yibarkih
ReplyDeletealgebagnim ene algebagnim ene
ReplyDeleteየጨው ነጋዴዎች ድጋፍ ይሁን ተቃውሞ በማይታወቅ ሁኔታ ግማሽ ኩንታል ጨው አምጥተው በድስቱ ውስጥ መጨመራቸውን በኩራት ሲያወሩ የሰሙ ሁሉ የነገሩ አዝማሚያ አላማራቸውም፡፡
ReplyDeleteውኃው ቧንቧ ውስጥ እንኳን እያለ እንዲህ ያለ ጣዕም አልነበረውም፡፡
Ere Dani yetsafkew eko ersbersu telateme. Yhe hulu chew techemirobetima wha wha lil aychilim. Biyans chew bezabet bitil yshalal. Kemeletefih befit edit arg. Ers bersu bemigach tsihuf lelan metechet, yemetechet abaze kalhone beker miyawata aymeslegnim.
tiru shemute nwe breta
ReplyDeleteBetam Debari Article new.
ReplyDeleteለቀማሾቹ ችግር የሆነባቸው ወጡ የምን ወጥ እንደሆነ መለየት አለመቻላቸው ነው፡፡
ReplyDeleteDaniel ewinetunina yetesemahin bechewa kuwankua silegelesk yasmeseginihal,EGZIABHER yibarkih. yemiyastewulm yastewul. "Zemenun waju" teblo yelem?
ReplyDeleteወንድሜ ሆይ በዚህም ሆነ በዜያ "አይቶ ማለፍን ሰምቶ መቻልን"ይስጥህ::ከማለት ምን ይባላል :: አንባብያን ሆይ ይህ ሰሞን የጾለት ግዜ ስለሆነ ይልቅስ አንገት ቀና ልብን ብርሃን አድርገን እንጸልይ:ጌታም ጾሎታችንን ይቀበል::አሜን!!
ReplyDeleteThank you Daniel for your wonderful view! I totally agree with you at least with this article. But I am a bit worried about your security. Will you not be threatened by writing such article? If so, our "democracy" is becoming democracy!!!Elilililili..., my country jumps up one unit on the ladder of democracy.
ReplyDeleteCheers man!!!!! see u next
Yemigerm eyita new!
ReplyDeleteaye ye zemen malek balefew lela zare degemo be lea maliya gebah awekesh awekesh biluwat metsehafun atebech alu. Degemos beketeta betetsef mene yemetabegnal beleh new. Be ewnet asekeyami tsehuf new
ReplyDeletemeles's death is the wot .... kikikik .... the extravagant activity is the mourning ...good way of experession
ReplyDeleteDaniel, ashmurun alewededekutem. Be ahunu se'at yeteleyayu sewech yeteleyaye agenda yizew yeminkesakesu sihon. Andandochu agatamiwen bemetekem lemekeber yemishu sihonu, andandu degemo hone belew be'belay akal endetederege bemasemesel hizebu wede meret endigeba yemadereg aketacha yeyaze new. Be lela bekul degemo weketu kebad kemehonu anetsar hunetawech eskistekakelu deres ye belay akalat gize lemegezat yetetekemubet yimeselal, yam hone yih gin be gelets ende balefew 'yetemarenebetem yetemarernebet semon' bemil endetsafekew bihon teregumu ashami balehone neber.Be'ereget yihe 'PM meles'n' mote mekeniyat yaderege mesaleyawi anegager kehone, balefew yaluten asemerari negeroch be gelets asekemetehew sale ahun be'ashemur metsaf lemen asefelege? weyes lela addis neger ale? be 'ETV' endayehut ye PM posterochin yemishetu sewech beyebotaw ayechalehu eneresu le' buisness yihonal, gin 'ETV' selezih zegebe? ene endemimeselegn yesemonun ye hizebun 'mane yihon ketayu tekelay minister?' yemil teyake ena yemeweyaya agenda wede lela agenda be mekeyer atadafi teyake ke hizebu endayemeta aketacha lemekeyer bihonese? yam hone yih yihegnaw yanetem tsehuf aselechi yimeselal. Yam hone yih semtehen yaleferehat selemetegelets des yilal.
ReplyDeleteDani.....betam harif new...enem wotu betam eyemereregne new. BEKAGNEEEEEEEEEEEEEEEEEEEE
ReplyDeleteአይመችም! ጥቃቅን ስህተቶችን የማጉያ ወቅት አይመስለኝም፡፡ በመተባበር ስሜት የተፈጠሩ ሥህተቶች እንዲስተካከሉ እንጂ ልክ በባለፈው ጹሑፍህ እንደጠቆምከው አይነት፡፡ እነደዚህ ግን አይገባም፡፡ እኔ ከይቅርታ ጋር አልተመቸኝም፡፡
ReplyDeleteመልካም በዓል
"Ashmur is coward's weapon" Lenin has siad so, eree akuAm yinuren!!!!!!!!!!!Akwamachinin degmo yale firhat ininager, yeboi wuha eko hone hizbu!!!!! Fidel ke kemesew wegen bizu yiTebekal. Sew yetesemawn Lemetsaf yihen yahil yiferal ?
ReplyDeleteአስቀድሞ ያደነቀውና ያመሰገነውም ማማረርና ማቅለሽለሽ ጀመረው፡፡ ድሮም በአውጫጭኝና በመመርያ የተሠራ ወጥ መጨረሻው ይሄ ነው፡፡ እያሉ ተመጋቢዎች በየጠረጲዛው ሥር ይተቹ ጀመር፡፡I like it !!
ReplyDelete‹‹ስለ ሰሞኑ ወጥ›› እያሉ ነበር የሚለምኑት??....ምነው ዳኒ ምነው?? "በእንተ ስለማርያም" የሚለውን ቃል እንዲህ በቀላሉ ታቀለዋለህ??? እባክህን የጻፍከውን ቃል አጥፋው አልያም ቀይረው ....pleassssssssssssss!!!!!!..thankyou ;)
ReplyDeleteIf i understand you try to talk about ETV thats good. however as orthodox Cristian you should talk about what this days going on our church to promote and initiate every body. i am afraid may be you are against if you are really shame before you try to talk about that stupid PM you should give priority for your religion
ReplyDeleteonce again if you will not say anything about this before its over really SHAME ON YOU !!!!!!!!!
I think this article is 'crystal clear' for someone who have been following the situation in Ethiopia in the past month &...
ReplyDeleteDani your view is great as usual... Wetu Gornetowal...
Melkam Addis Amet Yehunelen
U r kind of I know all person.
ReplyDeleteETV... channel kutir sint enbelew, Dani?
ReplyDeleteyesemonum lekso lik endezih neber yetegemerew.
ReplyDeleteDaniel Daniel yeteret abat honeh kereh eko! If you remember Ababa Tesfaye used to tell us what his teret was all about , but you are translating the meaning of your teret somewhere ... bet or cafe or 'be ye guranguru' You are becoming nowadays ... Please try to see the constructive side of things . Donot write for the sake of writing.
ReplyDeleteI think the problem here is somebody should have coordinated and led the people on how and how much to put into the ''WOT". Leadership is crucial.
ReplyDeleteI shame on Mare Tibebu because he & his follower intention is killing our country please Mare don't look your todays stomach only.Think for ur future child
ReplyDeleteO Mr. whom can I call you politician or religious one? any ways may God give us the heart of David
ReplyDeleteI am surprised Dani what an intellectual U r.U wrote every thing I seen for the last 30 days, thanks.God Bless U
ReplyDeletesimply amazing!!!!!!!!!!!!!!!!
ReplyDeleteDn.Daniel! Thank you for the greatest outlook.specially talking and writing about the truth this days has been hard and difficult.Thank you for reading my mind, and faced the reaility.writhing the truth doesn't make you unreligious person.I mostly admire your written article.
ReplyDeleteGod bless you .
ዝም ብለው ሆ!ለሚሉ አጨብጫቦዎች መልካም መልእክት ነው መጀመሪያ ዘሎ ገብቶ ከማማሰል ምን እየተሰራ መሆኑን ማወቅ ይቅደም.ዳኒ ተባረክ
ReplyDelete