አንድ በእርሻ ላይ የሚሠራ ዪኒቨርሲቲ መምህር በገበሬው ዙርያ ጥናት ለመሥራት ወደ
ገጠር ወጡ፡፡ የአካባቢው የገበሬዎች ማኅበርም በአካባቢው የሚኖሩትን ገበሬዎች ለጥናቱ እንዲተባበሩ ለማድረግ ስብሰባ ጠራ፡፡
ምሁሩም ከገበሬዎቹ ፊት ለፊት ተቀመጡና ስለመጡበት ሥራና ከገበሬዎቹ ስለሚጠበቁ ነገሮችም ማብራራት ጀመሩ፡፡
‹‹ጉድ አፍተርኑን፤ እዚህ የመጣነው ፍሮም ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ነው፡፡
ከእናንተ ጋር ሚት ማድረጋችን ጉድ ኦፖርቹኒቲ ነው፡፡ ኦፍ ኮርስ እዚህ ለመምጣት ያሰብነው ቢፎር ኤ
ይር ነበር፡፡ በት አንዳንድ ፕሮሲጀሮችን ለማሟላት ሃርድ ስለሆነብን ትንሽ ሌት
ሆነናል፡፡ ሶሪ፡፡
‹‹የኢትዮጵያ ሜይን ኢንካሟ አግሪካልቸር መሆኑን አንደርስታንድ
ታደርጋላችሁ ብዬ አስባለሁ፡፡ አግሪካልቸር ዋን ኦፍ ዘ ሜይን የሰው ልጆች አንሸንት አክቲቪቲዎች ነው፡፡ ኢን
ኢትዮጵያ ደግሞ ሎንግ ሂስትሪ አለው፡፡ በት አግሪካልቸራችን አንደር ደቨሎፕ ሆኗል፡፡ ፋርሚንጋችን
ፑር ነው፡፡ አክቲቪቴያችን ሌበረስ ነው፡፡ ገበሬው ሳይንቲፊክ ዌይ አይጠቀምም፡፡ ፋርሚንጋችን
ሜካናይዝድ አይደለም፡፡ ገበሬው ኢንፎርሜሽን እንደልቡ አያገኝም፡፡
እነዚህን ኢንፎርሜሽኖች ወሰደን ዳታዎቹን የእናንተን ላይፍ
ለማስተካከል እንጠቀምበታለን፡፡ ኢሪጌሽን ላይና አኒማል ሀዝባንደሪ ላይ ለመሥራት እየተዘጋጀን ነው፡፡ አፍተር
ዛት ደግሞ ሌሎች ላይ እንሄድባቸዋለን፡፡
ታንክ ዩ
ለትብብራችሁ፡፡
ገበሬዎቹ አላጨበጨቡም፤ ራሳቸውንም አልነቀነቁም፡፡
የገበሬ ማኅበሩ ሊቀ መንበር ‹‹እስኪ ጥያቄ ያላችሁ?›› አሉ፡፡
ገበሬዎቹ ዝም አሉ፡፡ ሊቀመንበሩ ደጋግመው ቢጎተጉቱም ገበሬዎቹ ጸጥ አሉ፡፡ በመካከል አንዲት እናት ተነሡና፡፡
‹‹እስኪ የመጡት ሰውዬ ይናገሩና እንጠይቃለን›› አሉ፡፡
ሊቀ መንበሩ ግራ ገባቸውና ‹‹እርሳቸውማኮ ተናገሩ›› አሉ፡፡
‹‹እኛ ግን አልሰማናቸውም›› አሉ እኒያ እናት፡፡
‹‹ታድያ እስካሁን ምን ያደረጉ ነው የመሰላችሁ›› አሉ ሊቀ መንበሩ፡፡
‹‹እኛማ በማናውቀው ቋንቋ የመክፈቻ ጸሎት እያደረሱ ነው የመሰለን›› አሉ፡፡
(መስከረም 17 ቀን በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ቀርቦ በነበረ ዝግጅት ከኢትዮጵያ የመጡ ምሁር
በአማርኛ ማስረዳት ሲያቅታቸው ጋዜጠኛውም በአማርኛ ሲተረጉም ለተሰማው ነገር መታሰቢያ ነው)
ቺካጎ፣ ኤሊኖይስ
Geberewochu be "amarariw" fit bihon ayishalim? I like it very much!!!
ReplyDeleteለብ ያሉ ምሁራን ችግር !
ReplyDeleteአረ; ለብ ያላሉም:አሉ እንዲህ የሚጀመሩ::
Deleteha ha ha
ReplyDeleteGira yegebaw mihur, saymar bastemarew lay yemichemalek mihur negn bay. Libona yistachew enji min enlalen.
ReplyDeleteአንድ ምሁር በገበሬው ፊት
Deleteበጣም ሊታሰብበት የሚገባ በመሆኑ
መልሰን ብናነበው ከግርማይ ሀዋሳ
አንድ በእርሻ ላይ የሚሠራ ዪኒቨርሲቲ መምህር በገበሬው ዙርያ ጥናት ለመሥራት ወደ ገጠር ወጡ፡፡ የአካባቢው የገበሬዎች ማኅበርም በአካባቢው የሚኖሩትን ገበሬዎች ለጥናቱ እንዲተባበሩ ለማድረግ ስብሰባ ጠራ፡፡ ምሁሩም ከገበሬዎቹ ፊት ለፊት ተቀመጡና ስለመጡበት ሥራና ከገበሬዎቹ ስለሚጠበቁ ነገሮችም ማብራራት ጀመሩ፡፡
‹‹ ፤ እዚህ የመጣነው ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ነው፡፡ ከእናንተ ጋር ማድረጋችን ነው፡፡ እዚህ ለመምጣት ያሰብነው ነበር፡፡ አንዳንድ ለማሟላት ስለሆነብን ትንሽ ሆነናል፡፡
‹‹የኢትዮጵያ መሆኑን ታደርጋላችሁ ብዬ አስባለሁ፡፡ የሰው ልጆች ነው፡፡ ኢትዮጵያ ደግሞ አለው፡፡ ሆኗል፡፡ ነው፡፡ ነው፡፡ ገበሬው አይጠቀምም፡፡ አይደለም፡፡ ገበሬው እንደልቡ አያገኝም፡፡
እኛ የምንሠራበት ገበሬው በሚለው ዙርያ ነው፡፡ ከእናንተ እንፈልጋለን፡፡ ትሆናላችሁ፡፡ ያዘጋጀናቸው አሉ፡፡ ለእነዚህ ትሰጡናላችሁ፡፡ ከእናንተ መካከል እንወስዳለን፡፡ ሳትመረጡ ብትቀሩ እንዳትሆኑ፡፡ እናገኛችኋለን፡፡
እነዚህን ወሰደን የእናንተን ለማስተካከል እንጠቀምበታለን፡፡ ላይና ላይ ለመሥራት እየተዘጋጀን ነው፡፡ ደግሞ ሌሎች ላይ እንሄድባቸዋለን፡፡
ለትብብራችሁ፡፡
እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ የአነጋገር ልማድ አለው፡፡ አንዳንዱ ከሚናገረው ቃል ይልቅ አካላዊ እንቅስቃሴው ትኩረት ይስብና ታዳሚው የሚፈለገውን መልዕክት ላይረዳው ይችላል፡፡ አንዳንዱ ደግሞ ለአነጋገሩ የተለየ ዜማ በማውጣት የታዳሚውን ትኩረት የሚስብ አለ፡፡ ይህ ልማድ በተለይ በሴቶች ላይ ጎልቶ ይታያል፡፡ የጋዜጠኝነት ስነምግባሩን ረስታ ለፍቅረኛዋ በስልክ የምታናግር የምትመስል ጋዜጠኛ መስማትም ሆነ ማየት ያሳፍረኛል፡፡ ይህ ሲባል ንግግራቸው ቀልብ የሚስብና ብቃት ያላቸው ሴት ጋዜጠኞች የሉም ማለት አይደለም፡፡ በጣም የምኮራባቸው ሴት ጋዜጠኞች አሉ፡፡ ሌላው ደግሞ አውቀንም ይሁን ሳናውቅ ታዳሚው ቢረዳውም ባይረዳውም በአማርኛ ቋንቋ ውስጥ እንግሊዝኛ ቋንቋን መደባለቅ ነው፡፡ ይህ የአነጋገር ልማድ አሁን አሁን በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን በሚቀርቡ አንዳንድ ጋዜጠኞችም ጎልቶ እየታየ ነው፡፡ ጣልቃ የሚገባው አንዳንድ የእንጊዝኛ ቃል የሚፈለገውን የአማርኛ ቃል አለመተካቱ ደግሞ ያስገርማል፡፡ ይህ ልማድ ከስልጣኔ የመነጨ ወይስ ከማንነት ቀውስ? እንዲህ አይነት ንግግር አድራጊዎች ለታዳሚዎች ያላቸውን ንቀት የሚያሳይ ይመስለኛል፡፡ በስብሰባም ይሁን በተለያዩ መድረኮች ቢቻል የታዳሚውን አነጋገር ዘይቤ (ቀበሌኛ ቋንቋ) መጠቀም ካለተቻለም መደበኛውን የአማርኛ ቋንቋ መናገር እንዴት ይከብደናል? የእንግሊዝኛ ጉራማይሌውማ ለምደነዋል፡፡ አስፈላጊ ባልሆነ ቦታ የአማርኛ ቃላትን መደጋገም ለአድማጭ አሰልቺ ነው፡፡ “እንግዲህ” ካልተባለ ንግግር አይቀጥልም “ሁኔታ ነው ያለው” ካልተባለ ንግግር አይቋጭም የተባሉ እስኪመስልና ዋናውን መልዕክት እስክንዘነጋው ድረስ በሚያሰለች የቃላት ድግግሞሽ ጊዜ የሚያባክኑ ጋዜጠኞችና ንግግር አድራጊዎች ብዙዎች ናቸው፡፡ የቋንቋ ልሕቀት ቢኖር ምናለበት!
ReplyDeletereally that is good view however we all have this kind of problem. Me too
ReplyDeleteBy the way, why majority of Ethiopians scholars do not want to accept that they cannot properly speak English. I do not know the reason why. This is(the above message) one way which they use to show the other that they can speak and listen English. This kind of people usually cannot speak English properly in the environment where there are lots of foreigners and language scholars. We do not want to accept our reality. If some one openly speaks to others that he/she cannot speak English, it is alright, in some case, it has its own respection for being honest so that some one acceptance may be increase. People in our country still struggling to show for others that they are better from the person whom do they think that competitive for their way. If you want to break the psychology of Ethiopians, it has something to do with speaking English. Please!! We need to be what we really are!! Otherwise, we will end up in identity crises, either we can not properly speak Amharic or English. Finally, this condition leads us to some one who cannot express our ideas properly in front of others. This may predispose us to terrible consequences!! Thank you!!
ReplyDeleteyou can't write in english neither. so why don't u comment in Amharic???
DeleteThank you!! for your valuable comment!! With help of you, i will try to improve myself!!
DeleteDaniel; would you post us ur interview with Sendek newspaper? please.
ReplyDeleteሰላም ዳኒ እንኳን ለ ብርሃነ መስቀሉ አደረሰህ።
ReplyDeleteችግሩ በረጅም ጊዜ ያለው ተጽኖ ቀላል አይሆንም።እናም በ እጅ ያለ መፍትሄ ያለን ይመስለኛል። በ ኤፍ ኤም ራድዮኖች፣በ ፌስ ቡክ ወዘተ ዘመቻ መጀመር አለበት።በ ሆነ ባልሆነው የ ''ፈረንጁን አፍ'' ለሚለጥፉ ሁሉ (እራሴንም ጨምሮ)የሚኮሩበት አለመሆኑን ማስገንዘብያ ደረጃ ማድረስ ይገባል። እስኪ 'ፌስ ቡክ' እንክፈትለት እና አባል እንሁን የ እዚህ አይነት ችግር ያለባቸውን ገለጻዎች፣ንግግ ሮች ወዘተ ይለጠፉበት እና እየተዝናናንም እንማማርበት።
Gecho qedus hasab esmamalew behasabeh
DeleteI am so really conscious about this thing and let us struggle against this obstacle for the technology transfer.
ReplyDeletekeep in touch too,
ዘ ትሩዝ ኢዝ እኛ የቋንቋ ችግር እንደሌለብን ዩ ሹድ አንደርስታንድ፡፡ ባይ ዘዌይ እኛ ቋንቋችንንና ባህላችንን ለመጠበቅ በጣም ትልቅ ስትረግል ላይ ነን፡፡ ቋንቋችንንና ካልቸራችንን እኛ ካልጠበቅነው ኖ ዋን የሚጠብቅልን ስለማይኖር በተቻለ መጠን ፕሮጀክቶችን ፕላን አድርገን ወደ ሥራ እየገባንበት የምንገኝበት ኹኔታ ላይ ነው ያለነው፡፡ ከአንዳንድ የሃይ ስኩል ተማሪዎችና በቅርቡ ስሙ (ስኩል ኦፍ ኮብልስቶን) ተብሎ ከተቀየረው ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር በጋራ እየተንቀሳቀስን የምንገኝበት ኹኔታ ነው ያለው፡፡ ኤፈርታችን ሬዘልት እንዲኖረውም ከብሪቲሽ ካውንስል ጋር በጋራ በመነጋገር ለመሥራት እየሞከርን ያለንበት ኹኔታ ላይ ነን፡፡ እርግጥ ነው አንዳንድ ክሪቲሲዝም የሚቀናቸው ፒፕል አማርኛን ለመጠበቅ እንግሊዘኛን የሚያስተምር ድርጅት ዘንድ ለምን ኼዳችሁ ብለውናል፡፡ ሀውኤቨር እኛ እስከምናውቀው ድረስ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ዘንድ ወይም ደስታ ተክለወልድ ጋር ለመኼድ ስለማንችል ነው ብለን ሪስፖንድ አድርገናል፡፡ ኢቭን የትምህርት ሚኒስቴርም ኾነ በሥሩ የሚያስዳድራቸው ሀየር ኢኒስቲቲዉሽንስ አማርኛ መጻፍ እንደማይችሉ ከሚጻጻፏቸው በእንግሊዘኛና ግራመሩ እጅግ ሜስድ አፕ በኾነ መልኩ በተሠሩ የአምሃሪክ ሴንቴንሶች የተዘጋጁ ግን ያልተዘጋጁ ደብዳቤዎች አንደርስታንድ አድርገናል፡፡ በመኾኑም ወደ ብሪቲሽ ካውንስል መኼዳችን አማራጭ አልነበረውም፡፡ እንዲያውም በቅርቡ ከስቴትስ የቀጠርናቸው ኮንሰልታንት አሊያንስ ፍራንሴዝንም እንድናማክር ሰጀስት አድርገውናል፡፡ በዚህ ላንጉዊጃችንንና ባህላችንን ለመጠበቅና ለሚቀጥለው ጄኔሬሽን ሳይበረዝና ሳይከለስ ለማስተላለፍ በምናደርገው ጥረት አንተም ከጎናችን እንደምትኾን ዊ ቢሊቭ፡፡ ሜሴጅህን እኛ አንደርስታንድ እንዳደረግንህ አዘርስ ደግሞ እንዲሁ አንደርስታንድ እንዲያደርጉህ ዊ ዊሽ ዩ ላክ፡፡
ReplyDeleteha ha ha... Thanks bro/sis. Dani, there are so many readers that understand what u want to say. u know how much I enjoyed by reading comments of ur readers. Even I feel happy that there are such number of people who are beside me as orthodox christian when I feel lonely in my working enviroment.
DeleteHelina from Hawassa
Very impressive defending.
Deletehaha, this is really funny. lol
Deletedes sil....arif new...hahaha.
Deletekeep in touch too,
ReplyDeletefor me educated person means transfer his knowledge simply and clearly
ReplyDeleteyihe negere eco teleke ye ras mitate newu! gine manewu te teyakiwu? ye mefetehiew akals mannewu? betam ye migermew neger degmo aydelem be engelizegna be enat quanquawum hasabune be tekekele aygelitsem. yasazenal!!!!
ReplyDeleteteyekew eko yeweche zega newe. his name is peter. ena endet beneglzegna eyteyekew beamargna yemlselete.
ReplyDeleteNo, listen the program again. the interview was done for Amharic voa program by Amharic gazetegna/ the gazetegna mentioned that the interview was given for amharic program/ Peter works for voa english program and he interviewed the new prime minister, but this one which D.Daniel talking about is with Shimeles Kemal i think. don't worry Bereket Simon the boss has done it before/ bamarigna siteyeku be engliz memeles ????/
Deleteጥሩ እይታ ነው እነኳን ለአረሶ አደሩ በወጉና በባሕሉ ለሚኮራው ቀርቶ ለሙሁሩ በተመሳሳይ ደረጃ ላው ሊገባው ለሚችለው አካል እንኳ ተገቢ ነው ብሎ ማመን አይቻልም፡፡ በመሰረቱ ይህ እኮ የአዕምሮ የቅኝ ግዛት ውጤት እኮ ነው መማር ማለት የምዕራባውያኑን ቋንቋ እና እውቀት ነው በማለት የስንት አመት የስልጣኔ መገለጫ የሆኑ የእውቀት ሀውልት ያላትን አገር ታሪክና ምንነት ሳናውቅ በቅጡ ባልተረዳነውና ህይወታችንን ሙሉ ሲምታታው በሚኖረው መቋጫ አልባ ጥበባችን ስንመጻደቅ ይህው አርሶ አደራችን በበሬ እያረሰ ጤፍም በቁና እንዳለተሰፈረ በቆርኪ ሊሆን የበቃነው እንግዲያውማ የእወቅትና የልህቀት መዳረሻው ጽድቅማ ቢሆን እንደ ቀደምት የሀይማኖት አባቶቻችን በሆንን አለማዊው እውቀት ቢያንስ እንኳ ለከርሳችን በተረፈን ነበር፡፡ የልሂቃናት በረከት ለነዳይን ይትረፍ ነበር ቀሳውሰት በመደብ በበሉ ለነዳይ በሳጠራ ይነሳ ነበር ዛሬግን እንኳን ለነዳይ ከፊትም በሰቀቀን ያልቃል እሰቲ ይሁን የነገን ማን ያውቀል፡፡
ReplyDeleteymiyasqem! ymigermem! new emama degmo astway enat nachew.Dn.daniel berta!! MEDHANITE ALEM end abatochachen ewqetun degmo dgagmo yechmreleh. ETHIOPIA LZLEALEM TINUR::
ReplyDeleteEntertaining and very funny.Like it.
ReplyDeleteዳንኤል ታላቅ ትምህርት ነው ሁሌ የፈረንጅ አፍ መቀላቀል ዕውቀት ለሚመስለን መልእክት አለው ጌታ ይባርክህ፥
ReplyDeleteHi Dc Danniel! thank you for your great views.I mostly read yr blog and like it mostly.I just want to make one point about adding some english words in amharic languge.I know is not recommended or not very good way of communication for Amharic speakers,BUT it's very difficult to speak fluntly Amharic when u are working 10 hours with English speakers.I think every one wants speak their own languge clearly without mixing, but kind of hard.And I dont think it's for showing up or purpously ppl doing it.i think who do u spend yr time with has affect,bc the more u talk the perfect u become.So when u get some time with your friend or have kind of intervew,it very hard not to use english and remeber un used words.
ReplyDeleteHowever ppl must try not to mix english with Amharc languge. I think.
Thank you
from s.c
ቲፒካል የምሁር ንግግር ሆኖ አግኝቸዋለሁ እና አይ ላይክ ኢት ሶ ማች
ReplyDeleteNot only "በእርሻ ላይ የሚሠራ ዪኒቨርሲቲ መምህር " But also students in university spoken such kinds of language during their summer time in rural community.
ReplyDeleteStarbucks Kuch Biye ategebe yetekemetu Sewoch Abede ende eskemilugn Asakegn... Rasenim Besewuyew Mestawet Ayehut... Abune Paulosm eko and Gize Ersewo Englizgna Yikelklalu lemndin new tebilew Siteyeku... Ene... never never bilewal alueko...
ReplyDeleteEgni mihur kebizuwochu andu endayihonu.
ReplyDeleteEndene mignot getsebehari bihonu neber.
ሰላም ዲ,ዳንኤል
ReplyDeleteእኔም ብዙ የታዘብኩት ጉዳይ ነው ። በአንዳንድ ፖለቲከኞች ምሁራን በሓይማኖት መምህራን በመሳሰሉት የሚታይ ነገር እየሆነ ነው ። ቪኦኤዎች ሊመሰገኑ ይገባቸዋል።
ጥሩ እይታ ነዉ።
ReplyDeleteእንግሊዝኛ መናገር የሰለጠና የተማረ ሰዉ መገለጫ ተደርጎ መታዬት የቆየና ሥር የሰደደ ችግራችን ነዉ።
እንዳዉም በአንድ ወቅት የሰማሁት አንድ ታሪክ እዚህ ላይ ትዝ አለኝ። በንጉሱ ዘመን ነዉ ይባላል አንድ ወገኔ እንግሊዝ አገር ይሄዱና ይመጣሉ፥ ስላዩትና ስላስደነቃቸዉ ነገር ሲናገሩ “እንግሊዝ አገር በጣም የሚገርመዉ ትንሹ ‘ሙጭቃቅላ’ ልጅ ሳይቀር እንግሊዝኛ ይችላል” ነበር ያሉት። የሚገርመዉ ከዚህ አይነት አስተሳሰብ አሁንም ያልወጣን መኖራችንና በቀላል አማርኛ ሊገለጥ ለሚችለዉን ነገር የእንግሊዝኛ ቃላት ፍለጋ መሄዳችን ነዉ።
እይታዎችህ ጥሩና አስተማሪ ስለሆኑ በርታ፥ እኛም በፍቅር እያነበብናቸዉ ነዉ። ያልከዉን ቃለ መጠይቅ እኔም አዳምጬዋለሁ፥ ጥሩ ታዝበሃል።
መልካም የመስቀል በዓል ለሁላችን!
wey dani hulem eyitahin atatmewalehu....berta !!
ReplyDeleteyasekale dese yelal lebalinjerocha negera betamm asakachew
ReplyDeleteወንድም ዳንኤል::
ReplyDeleteእጅግ ድንቅ ነገር ነው ያቀረብከው:: በማናቸዉም ስፍራ ንግግር ሲደረግ አድማጭን መለየት ተገቢ ነው:: በአንድ የአርሶ አደሮች ሰብሰባ ላይ አንድ ባለስልጣን ንግግር ያደርጋሉ:: በአካባቢያችሁ ዉሃ ለማስገባት ከፍተኛ ሥራ እየሰራን ነው:: በቅርቡ ፈንዱ ሲለቀቅልን የዉሃ ማስገባቱን ሥራ እንቀጥላለን:: ዋናው ነገር ፈንዱ በመሆኑ ፈንዱ እስኪለቀቅ ደረስ እንድትታገሱ በመጠየቅ ፈንዱ ሲደርስን ዉሃዉን በየጎጆአችሁ እናደርሳልን በማለት ያስረዳሉ:: ከዚያም በመቀጠል ተሰብሳቢዉን አስተያየት አንዳለው ይጠይቃሉ::
አንድ የተከበሩ አበው እጃቸዉን አዉጥተው በለዘብ አንደበት እንዲህ አሉ: ጌታው መቼም ዉሃ ሊያስገቡለን ማስብዎን እናደንቃልን:: የሆነስ ሆነና እኛ ሳንፈንዳ ዉሃዉን ልታስገቡልን የማትችሉ ሆኖ ነው ዎይ ፈንዱ ፈንዱ የምትሉን ብለው ተናጋሪዉን ሹመኛ ኩም አደረጉት:: ቀጠል አድርገዉም እኛስ ከምንፈነዳ ዉሃችንን አንደወትሮው ደክመን በትከሻችን ቤታችን እናደርሰዋለን ብለዉት አረፉ::
ስለዚህ ጥራዝ እየነጠቁ አድማጭን ከማደናገር እና እትዝበት ላይ ከመዉደቅ በብርቱ መጠንቀቅ ያስፈልጋል:: የሌሎች ሃገራትን አፍ ካልተዋስን ሃሳብ አይገለፅ ይመስል ግራ ተጋብተን ግራ ባናጋብ መልካም ነው እላለሁ:: ቸር እንሰንብት::
This is due to lack of basic knowledge about the use of own language.Dani u do have an amazing talent. May GOD bless what u hv.
ReplyDeleteoh that's awesome dani, we better focus to develop our own local language instead of mixing it with English. i think this emanates from carelessness. of-course sometimes we becomes out of words but we can eliminate such problem by practicing or listening reading anything written in local language. let's give attention for it first then it will be very very easy!!
ReplyDelete‹‹...፤ እዚህ የመጣነው ... ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ነው፡፡ ከእናንተ ጋር ... ማድረጋችን ... ነው፡፡ ... እዚህ ለመምጣት ያሰብነው ... ነበር፡፡ ... አንዳንድ ... ለማሟላት ... ስለሆነብን ትንሽ ሌliት ሆነናል፡፡ ...፡፡
ReplyDelete‹‹የኢትዮጵያ ... መሆኑን ... ታደርጋላችሁ ብዬ አስባለሁ፡፡ ... የሰው ልጆች ... ነው፡፡ ኢን ኢትዮጵያ ደግሞ ... አለው፡፡ ... ሆኗል፡፡ ... ነው፡፡ ... ነው፡፡ ገበሬው ... አይጠቀምም፡፡ ... አይደለም፡፡ ገበሬው ... እንደልቡ አያገኝም፡፡
... እኛ ... የምንሠራበት ... ገበሬው ... በሚለው ዙርያ ነው፡፡ ከእናንተ ... እንፈልጋለን፡፡ ... ትሆናላችሁ፡፡ ያዘጋጀናቸው ... አሉ፡፡ ለእነዚህ ... ትሰጡናላችሁ፡፡ ከእናንተ መካከል ... እንወስዳለን፡፡ ... ሳትመረጡ ብትቀሩ ... እንዳትሆኑ፡፡ ... እናገኛችኋለን፡፡
እነዚህን ... ወሰደን ... የእናንተን ... ለማስተካከል እንጠቀምበታለን፡፡ ... ላይና ... ላይ ለመሥራት እየተዘጋጀን ነው፡፡ ... ደግሞ ሌሎች ላይ እንሄድባቸዋለን፡፡
Enat yetenagerut tikikil new
Kale Hiywot yasemalin Dn. Daniel
ታንክ ዩ ለትብብራችሁ፡፡
Dany ty yehn negre be 1weqet Tesfaye Kasa beqeldu tenagero nebr 1 ye NGO derejet geter lesera yehd ena gebrewochun sebesbo endeh yelachewal.."fendu yemeradchu ...fendu yemredachu.."belo yecheresal 1 enat tenstew ezeh ga tyqe alegn "Fendu " kalfendan ayredanem malet ?yalut hule yegremegnal ena yansahew neteb bezuhanen yasemaml GBU DANY
ReplyDeleteሰላም ዳኒ እንኳን ለ ብርሃነ መስቀሉ አደረሰህ።
ReplyDeleteችግሩ በረጅም ጊዜ ያለው ተጽኖ ቀላል አይሆንም።እናም በ እጅ ያለ መፍትሄ ያለን ይመስለኛል። በ ኤፍ ኤም ራድዮኖች፣በ ፌስ ቡክ ወዘተ ዘመቻ መጀመር አለበት።በ ሆነ ባልሆነው የ ''ፈረንጁን አፍ'' ለሚለጥፉ ሁሉ (እራሴንም ጨምሮ)የሚኮሩበት አለመሆኑን ማስገንዘብያ ደረጃ ማድረስ ይገባል። እስኪ 'ፌስ ቡክ' እንክፈትለት እና አባል እንሁን የ እዚህ አይነት ችግር ያለባቸውን ገለጻዎች፣ንግግ ሮች ወዘተ ይለጠፉበት እና እየተዝናናንም እንማማርበት።
ግሩም ሃሳብ ነው:: በርታ
tooo shame..........
ReplyDeleteIt is a normal phenomenon. Such a thing can happen in any bilingual/multilingual person. It is even impossible to speak with no mix. Only a monolingual person can speak with no mix. But the question is- is there monolingual person in Ethiopia?
ReplyDeleteHow nice is the text!!
I can not even stop laughing. [Yemir yemigerim tarik new. Hule Ethiopia wist yemigerimegn tarik yemir.] hahahhahahhhahhaa.
ReplyDeleteTHANK YOU SO MACH Dn.DANIEL IT IS SO NICE I LEARN FROM THAT!!!
ReplyDeleteHi Dani how are you doing ? I really like your article.It is funny,amazing & touching.You showed us that we are losing our identity.I can say that every one of us are held responsible for the problem.It would be better speaking pure Amharic in Amharic and pure English in English without mixing. DANI just keep on writing on the same issue. Ethiopians let's be hand and glove to eliminate the problem. Let's have a dignity to our identity.GOD BLESS ETHIOPIA!!!
ReplyDelete‹‹እኛማ በማናውቀው ቋንቋ የመክፈቻ ጸሎት እያደረሱ ነው የመሰለን›› አሉ፡፡
ReplyDeleteDani thank you a lot!
ReplyDeleteI was afraid about him, just you say my words. Hope he will gate lesson from, thank you dani, thank you the VOA journalist!
a nice view
ReplyDeleteጥሩ እይታ ነው
ReplyDeleteTsuhufochihin ewodachewalehu,yihie gin tinsh teganual.
ReplyDeleteSile-university ena Mihuran tiru neger atitsfim, minew betam tashitehal ende sitimar? Woyis University astemari lemhone yemiabeka wutiet yelehim?(netib bicha silemitay maletie neew.) Esum kehone litbesach ayigebam (dihinet neber yemiterfih)
tiru new,tinsh teganaul
ReplyDeleteIt is very true, I remember once, I was invited to train farmers on soil and water conservation and I couldn't make it without mixing with English, I don't even know some terms in Amaharic, was a shamed of myself!.
ReplyDeleteThanks Dani!
ዳንኤል ይህንን ሳነብ ትዝ ያለኝ ነገር ቢኖር ግእዝ ሳያውቁ እንደmiywk sew eyachemaleku yemiteksu sebakyan nachew ezih lay lemenager yemfelgew weg atbaki lemehon sayhon biyans yemiteksutn geez askedmew nibabun biyatenut kelalko new meteyek hatiat new ende? ande bus wust hogne slaf andu siteks mechem edme ledmsmaguya semche bedingate kiw alkugn geez awaki new lemebal kalhone beker kemabelashet bamargna bitekes min chigir alew? bergit geez tinikarena wubet yalew kuankua silehone amargna yasamral mengistm tetekmobet yele? hiddase,musnna....bihonm geez berasu kuankua silehone nibabu ketebelashe tirgumim layset yichlal woym tirgum yazabal.aree sintu mezmur beyekasetu yetebelashe geez ale? Bewnetu lemalet memokeru berasu yibel yasegnal. sibelash gin yasaznal. manm aysemawm blo endefekedu machemalekm lik aymeslegnm bekelalu teyko meredat yemichalewn neger mabelashet sinfna silehone sebakyan biyasbubet.endewm yemiyask getemegn alegn lezare yikrbgn. yikrta amargnaw fidel legizew embi blogn new fidelun yekeyerkut.
ReplyDelete