Thursday, September 27, 2012

የምታይበት መንገድ

click here for pdf
አንድን የናጠጠ ሀብታም ቤተሰብ የሚያስተዳድር አባት ልጁ ስለ ድኽነት እንዲያውቅ ስለፈለገ በከተማው ጥግ ወዳለው የድኾች መንደር ልጁን ይዞት ይሄዳል፡፡ እዚያም ወደ አንድ ድኻ ቤት ይገባና ለልጁ ሁሉንም ነገር ያሳየዋል፡፡
ከጥቂት ጊዜ በኋላ አባትና ልጅ ጉብኝታቸውን ፈጽመው ወደ ቤታቸው በመኪናቸው ይመለሳሉ፡፡ አባትም ልጁን ‹‹ጉዞው እንዴት ነበር?›› ይለዋል፡፡
ልጁም ‹በጣም ጥሩ ነበር›› ብሎ ይመልስለታል
አባትዬውም ‹‹ድኾች ምን ዓይነት እንደሆኑ አየህን?›› ይለዋል፡፡
ልጁም ‹‹በርግጠኛነት አይቻለሁ›› ሲል መለሰለት፡፡
‹‹ታድያ ምን ተማርክ?›› አለው አባት፡፡
‹እኛ አንድ ውሻ አለን፤ እነርሱ ግን አራት ውሻ አላቸው፡፡ እኛ እስከ ግቢያችን ግማሽ የሚደርስ መዋኛ አለን፤ እነርሱ ግን ማለቂያ የሌለው ሐይቅ አላቸው፡፡ እኛ በግቢያችን ውስጥ ከእንጨት የተሠሩ በጎች አሉን፤ እነርሱ ግን በሕይወት ያሉ ብዙ በጎች አሏቸው፡፡ እኛ የገዛናቸው ጥቂት አምፖሎች በቤታችን አሉን፤ እነርሱ ግን ቁጥር ሥፍር የሌላቸው ከዋክብት አሏቸው፡፡ የእኛ የፊት ለፊት ሜዳ ትንሽ ናት፤ እነርሱ ግን የማይጠገብ መስክ አላቸው፡፡ እኔ መጫወት የምችለው በግቢዬ ብቻ ነው፡፡ እነርሱ ግን እስከ ሐይቁ ድረስ ባለው ሜዳ ይንቧረቃሉ፡፡››
አባትዬው አፉን በመዳፉ ይዞ ነበር የሚሰማው፡፡
በመጨረሻም ልጁ ‹‹ አባዬ እኛ ምን ያህል ድኻ እንደሆንን ስላሳየኸኝ አመሰግንሃለሁ›› አለው፡፡
በማንኛውም ነገር ወሳኙ ነገሩን እንዴት ታየዋለህ? ነው፡፡ ለአንዱ የሞት ምክንያት የሚሆነው ለሌላው የመዳን ምክንያት ይሆናል፡፡ ለአንዱ ተስፋ የሚያስቆርጠው ለሌላው ተስፋ ይሰጠዋል፡፡ አንዱን የሚያተርፈው ሌላውን ያከስረዋል፡፡ አንዳንዶቹ የሚስማሙበት፣ ሌሎቹን ይለያያቸዋል፡፡ ለአንዱ ሀብት፣ ለሌላው ድኽነት ነው፡፡ ለአንዱ እጅግ ውብ የሆነው፣ ለሌላው መልከ ጥፉ ነው፡፡ ለአንዱ ጠባየ መልካም የሆነው፣ ለሌላው አብረውት ሊኖሩት የማይቻል ነው፡፡ አንዱ ለጋብቻ የሚመርጠውን ሌላው ለደቂቃ ቡና አብሮት ሊጠጣ አይፈልግም፡፡
የእነዚህ ነገሮች አንደኛው ምክንያት ነገሩን የምናይበት መንገድ ነው፡፡ አንድን ነገር በችግር ዓይንም ሆነ በመፍትሔ ዓይን ማየት ይቻላል፡፡
በ17ኛው መክዘ ከተነሡት እንስት ኢትዮጵያውያን ቅዱሳት መካከል አንዷ የሆነችው ወለተ ጴጥሮስ ከንጉሥ ሱስንዮስ ጋር ተጋጭታ ወደ ዋልድባ ገብታ ነበር፡፡ እዚያ እርስዋ በገባችበት የሴቶች ገዳም ውስጥ የነበረች አንዲት አሮጊት ነበረች፡፡ ይህች ሴት ጠባይዋ እጅግ አስቸጋሪ ነበር ይባላል፡፡ ምንም ዓይነት በጎ ነገር ቢደረግላት ትራገማለች እንጂ አታመሰግንም፡፡ የሚያገለግሏትንም ሁሉ ትነዛነዛለች፡፡ አንዳንዴም ትማታለች፡፡
ወለተ ጴጥሮስ ምክንያቱን ስትጠይቅ የሴትዮዋን የጠባይ ክፋት ነገሯት፡፡ እርስዋም ይህንን ስትሰማ ‹‹እኔ አገለግላታለሁ›› ብላ ወደ ሴትዮዋ ሄደች፡፡ እጅግ የንትወዳትና የምታከብራት ጓደኛዋ እኅተ ክርስቶስ እንኳን በውሳኔዋ ተገርም ሃሳቧን እንድትለውጥ ስትነግራት ፈቃደኛ አልሆነችም ነበር፡፡
ለሴትዮዋ ትታዘዛለች፣ ምግብ ታበስላለች፣ ቤቷን ትጠርጋለች፣ ሰውነቷን ታጥባለች፣ ትላላካታለች፣ ወደ ቤተ ክርስቲያን ትወስዳታለች፡፡ ይህንን ሁሉ ብታደርግላትም ግን ሴትዮዋ አትደሰትም ነበር፡፡ ታማርራለች፤ ትራገማለች፤ ትሳደባለች፤ ትተቻለች፤ ታናቋሽሻለች፤ ከዚያ የባሰም ሲመጣ ትማታለች፡፡ አንድ ቀን እንዲያውም ወለተ ጴጥሮስ ለእርስዋ ምግብ እየሠራች እያለ ከምድጃው እሳት የያዘ እንጨት አውጥታ በፍሙ መትታት ነበር፡፡
ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ግን አንዲትም ቀን አማርራ አታውቅም ነበር፡፡ ነገሩንም ሁሉ በምስጋና ትቀበለው ነበር፡፡ ይህ ነገርዋም ስትሰድባትና ስታማርራት ለሚሰሙት ሌሎች እኅቶች ግራ ይገባቸው ነበር፡፡ ‹‹ለምን አትተያትም? ምን ትጠቅምሻለች? እንዲህ ከምትረግምሽ ሴት ምን በረከት ይገኛል›› ይሏት ነበር፡፡ እርስዋ ግን መልስ ሰጥታቸው አታውቅም፡፡
ለአንድ ዓመት ያህል ካገለገለቻት በኋላ ሴትዮዋ ሞተች፡፡ ወለተ ጴጥሮስም እጅግ አዝናና አልቅሳ ቀበረቻት፡፡ የደረሰባትን ሁሉ የሚያውቁት እኅቶችም እንደዚያ በማልቀስዋ ተገረሙ፡፡ አንድ ቀንም እንዲህ ብለው ጠየቁዋት ‹‹ለመሆኑ ምን አድርጋልሽ ነው አብረሻት የኖርሽው? ከእርስዋስ ምን አገኘሽ? ደግሞስ ምን ጎድሎብሽ ነው በመሞቷ ያለቀስሽው?››
ወለተ ጴጥሮስም እንዲህ አለቻቸው ‹‹ንብ ታውቃላችሁ? ንብ መልከ ጥፉና ክፉ ናት፡፡ መርዟም ሰው ከነደፈ ይጎዳል፡፡ ያምማል፡፡ አንዳንዴም ለመሞት ያደርሳል፡፡ ማንም የንብን ጠባይ አይወደውም፡፡ ከንብ ይልቅ ዝንብ ጠባይዋ መልካም ነው፡፡ አትናደፍም፤ መርዝ የላትም፤ አትጎዳም፤ በመርዟም ለሞት አታደርስም፡፡ ዝንብን የንብ ያህል ማንም አይፈራትም፡፡ ግን ዝንብ ማር አትሠራም፡፡ ለዝንብ ማንም ቀፎ አይሠራላትም፡፡ ምክንያቱም ማር የላትምና፡፡ ሰው ሁሉ የንብን ጠባይዋን ታግሦ፣ መርዟንም ተከላክሎ ለማርዋ ሲል አብሯት ይኖራል፡፡ ማንም ስለ ንብ ክፋትን መርዝ አያስብም፤ ስለ ማርዋ ነው እንጂ፡፡
‹‹እኔም እንደዚያው ነው፡፡ ይህች ባልቴት ጠባይዋ ክፉ ነው፡፡ ነገር ግን ከእርስዋ ዘንድ እንደ ማር የሚገኝ ብዙ በረከት አለ፡፡ ንብ ሌላውን የምትጠቅመውን ያህል ለራስዋ አትጠቀምም፤ ይህችም ሴት እኔን የጠቀመችኝን ያህል ራስዋን አልጠቀመችም፡፡ እዚያ ቤት ብዙ ነገር አጋኝቻለሁ፡፡ ጠባይዋን ታግሼ፣ መርዝዋንም ተከላክዬ ብዙ ማር ቆርጫለሁ፡፡ እናንተ መናደፏንና መርዟን ብቻ ነው የምታዩት፡፡ ማርዋ ሊታያችሁ አልቻለም፡፡ እኔ ደግሞ ማሩ እንጂ መናደፏ አልታየኝም፡፡›› አለቻቸው፡፡
የምታይበት መንገድ የምትደርስበትን ግብ፣ የምታገኘውን ነገር፣ የምታመጣውን ውጤት፣ የምታተርፈውን ትርፍ፣ የምታፈራውን ወዳጅ፣ ይወስነዋል፡፡
ቺካጎ፣ ኤሊኖይስ

32 comments:

 1. dear d/ dani endew yehen masetalu yabezaleh meret senetsuhuf new Egezihabher yabertah.

  ReplyDelete
 2. አበበ ሙ በየነSeptember 27, 2012 at 11:03 AM

  ወንድም ዳንኤል::
  ድንቅ መጣጥፍ ነው:: ሰዎች አንድን ነገር በተመሳሳይ ሁኔታ ልንመለከተው አንችልም:: እይታችን እንደ ዉስጣዊ ማንነታችን ይለያያል ብዬ አስባለሁ:: ዋናው ቁምነገር ግን ከተናዳፊዋ ንብ ማሩ እንዴት ሊገኝ ይችላል የሚለው ነው:: ለእኔ ህይዎት እንደተመልካቹ ነው የሚል ዕይታና ግምት አለኝ:: በዉጭ ሃገራት ተሰደው የሚኖሩ ወንድሞች እና እህቶች ባሉበት ሀገር ለመኖር የሚሰሩትን ሥራ በሀገራቸው ለመኖር ቢሰሩት የስራ ባህላችን ምንኛ በተለወጠ ነበር ያሰኛል:: ምናልባት ከዚያኛው መንደር የሚገኘውን ያህል ክፍያ ላይገኝ ቢችልም እዚያኛው መንደር ለመኖር የሚያስፈልገዉን ያህል ወጭ በሀገር ቤት ለመኖር አያስወጣም ይሆናል:: እንዲያዉም በገንዘብ የማይለካ በርካታ ቱሩፋት ሀገር ዉስጥ ይገኛል ባይ ነኝ :: ይህንን ጉዳይ እንደምሳሌ ማንሳቴ የዕይታችን መለያየት በዓለም ላይ እንዴት እንደበተነን ማሳያ ይሆን እንደሆን ብዬ መሆኑን አንባቢዎች እንዲረዳልኝ እሻለሁ:: ሆኖም ግን ዕይታ ተመሳሳይ ሊሆን ስለማይችል የሌሎችንም ዕይታ አከብራለሁ:: በሀገር ዉስጥም ሆነ በ ዉጭ ሀገር ላላችሁ አባቶች እና እናቶች እህቶች እና ወንድሞች መልካም የመስቀል በዓል እንድሆንላችሁ እመኛለሁ::

  የደጋጎቹ አባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሃገራችንን ይባርክ::

  ReplyDelete
 3. የምታይበት መንገድ የምትደርስበትን ግብ፣ የምታገኘውን ነገር፣ የምታመጣውን ውጤት፣ የምታተርፈውን ትርፍ፣ የምታፈራውን ወዳጅ፣ ይወስነዋል፡፡

  ReplyDelete
 4. ዝ ጥበበ ዳንኤል ከመ ወይን ጣዕሙ ድግሙ ድግሙ

  በላነው ጠጣነው ከእንጀራው ከወጡ
  እግዚአብሔር ይስጥልኝ ከመሶብ አይጡ!

  ይህን የመሰለ እጅ የሚያስቆረጥም የተመጣጠነ ምግብ በልቶ ቅኔ የማይዘርፍ ማን አለ? ኮምፕዩተር የሌላቸው ሰዎች አሉና ከልጅ እስከ ደቂቅ እንዲያነበው ይህች የዳንኤል እይታ የበኩር መፅሐፍዋን ብታሳትም ጥሩ ይመስለኛል። በዓመት ፩ድ መፅሐፍ ቢታተም ደግ ሐሳብ አይደለም ትላላችሁ? እስኪ ፀሐፌ ጥበብ ዳንኤል ያስብበት! የበኩር መጽሐፉ ርዕስ “የዳንኤል እይታዎች ክፍል ፩” ተብሎ ሲወጣ እስኪ በሕሊናችሁ ሳሉት። (ስዕል መሳል አልችልበትም እንዳትሉኝ ብቻ!!)

  “የዳንኤል እይታዎች ክፍል ፩”

  ከንብ ይልቅ ዝንብ ጠባይዋ መልካም ነው፡፡ አትናደፍም፤ መርዝ የላትም፤ አትጎዳም፤ በመርዟም ለሞት አታደርስም፡፡ ዝንብን የንብ ያህል ማንም አይፈራትም፡፡ ግን ዝንብ ማር አትሠራም፡፡ ለዝንብ ማንም ቀፎ አይሠራላትም፡፡ ምክንያቱም ማር የላትምና፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. he has already published two books(containing 'wogs'
   ) and the 3rd on the way.

   Delete
 5. .......ነገር ግን ከእርስዋ ዘንድ እንደ ማር የሚገኝ ብዙ በረከት አለ፡፡

  ReplyDelete
 6. ዳኒ በጣም አስተማሪ ጹሁፍ ነው፡፡ ለወደፊትም እንደዚህ አስተማሪ ጹሁፎችን ደግመህ ደጋግመህ አስነብበን፡፡

  ReplyDelete
 7. እውነት ብለሃል ዳኒ። አሪፍ ጽሑፍ ነው።

  ReplyDelete
 8. ‹የዳንኤል እይታ ቁጥር 1› እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ

  ReplyDelete
 9. great article...nice keeeeeeeeep it up, please.

  ReplyDelete
 10. ‹‹እኔም እንደዚያው ነው፡፡ ይህች ባልቴት ጠባይዋ ክፉ ነው፡፡ ነገር ግን ከእርስዋ ዘንድ እንደ ማር የሚገኝ ብዙ በረከት አለ፡፡ ንብ ሌላውን የምትጠቅመውን ያህል ለራስዋ አትጠቀምም፤ ይህችም ሴት እኔን የጠቀመችኝን ያህል ራስዋን አልጠቀመችም፡፡ እዚያ ቤት ብዙ ነገር አጋኝቻለሁ፡፡ ጠባይዋን ታግሼ፣ መርዝዋንም ተከላክዬ ብዙ ማር ቆርጫለሁ፡፡ እናንተ መናደፏንና መርዟን ብቻ ነው የምታዩት፡፡ ማርዋ ሊታያችሁ አልቻለም፡፡ እኔ ደግሞ ማሩ እንጂ መናደፏ አልታየኝም፡፡›› አለቻቸው፡፡ ድንቅ እይታ ነው::

  ReplyDelete
 11. እናንተ መናደፏንና መርዟን ብቻ ነው የምታዩት፡፡ ማርዋ ሊታያችሁ አልቻለም፡፡ እኔ ደግሞ ማሩ እንጂ መናደፏ አልታየኝም፡፡
  It is really goooooooooooooooooooood!

  ReplyDelete
 12. you did very well, what expected from you! what ever the idea you raise is so attractive and has power to change the thought of our society. i always eager to read your interesting and teaching view because your idea is unusual which is deviate from the traditional thinking of our ppl and it pushes the society to go in the right path. this is better to say i have no words to express my appreciation!! simply i like to say God Bless you!!
  Ethiopia needs you and people that thinks the progressive of Great Ethiopia!!!

  ReplyDelete
 13. ዳኒ ጦሲ እሞ /እግዚአብሔር ይስጥህ /

  ReplyDelete
 14. Hi D/n Daniel K.
  Thank you God for giving us such wonderful writter.Dani God bless you.I find this article very educational for my life.

  ReplyDelete
 15. ይህን ምስጢር ቀደም ብሎ የተረዳው ኢህአዴግ ለዚህም አይደል ምልክቱን ንብ ያደረገው፡፡ ከኢህአዴግ ዘንድ እንደ ማር የሚገኝ ብዙ በረከት አለ፡፡ “ንብ ሌላውን የምትጠቅመውን ያህል ለራስዋ አትጠቀምም፤ እናንተ መናደፏንና መርዟን ብቻ ነው የምታዩት፡፡ ማርዋ ሊታያችሁ አልቻለም፡፡ እኔ ደግሞ ማሩ እንጂ መናደፏ አልታየኝም ”፡፡

  ReplyDelete
 16. endezih aynet articls it's really good to read it ,but it's very hard to do it!!lets try? God will help us !!

  THE GOLA USA

  ReplyDelete
 17. ዳኒ አንተን የሰጠን አምላከ ቅዱሳን ይመስገን፡፡ የላይኛው ወዳጄ ልክነህ ኢሕአዴግም ልክ እንደ ንብ ማርና መርዝ አለው ልዩነቱ የኢሕአዴግ ማር ለራሱ ሲሆን መርዙን ግን ያለስስት የሰጠዋል፡፡

  ReplyDelete
 18. ‹‹ አባዬ እኛ ምን ያህል ድኻ እንደሆንን ስላሳየኸኝ አመሰግንሃለሁ›› አለው፡፡

  ReplyDelete
 19. what honey did this woman get from the older lady? You wrote about attitude and you used a metaphor of bees to explain your ideas. Bees give honey even though they can harm you. The old lady was bad tempered and irritating ,but, you failed to mention what Welete Petros get from sticking with the woman patiently. WHAT WAS HER HONEY? THX

  ReplyDelete
  Replies
  1. እኔም የተሰማኝን ነጥብ በማንሳትህ/ሽ ደስ አለኝ። ነገር ግን ወለተ ጴጥሮስ መንፈሳዊት እናት በመሆኗና በገዳም ውስጥ ያደረገችው ተጋድሎም በመሆኑ ለራሴ ጥቅሟ በትእግስት የሚገኘው ሰማያዊ በረከት ነው ብዬ ወሰድኩኝ አንተም/ቺም ሌላም ሰው በተመሳሳይ መልኩ እንደዚህ እንደሚረዳ እረዳለሁ ነገር ግን ዳንኤል ሳይገልጸው በማለፉ ትረካውን ጎዶሎ አድርጎታል። ምነው ዳኒ ሃሳቡ ድንገት ሙልት ሲል ሳይፈስ ቶሎ ፅፈህ ያውላችሁ አልከን እና ነው እንዴ። በተረፈ ድንቅ ነው።

   Delete
  2. እንደውም ጥሩ ነው ያደረገው::መጀመርያ እኔም ገርሞኝ ነበር:: በጎደለ ሙላ የሚለው ጥያቄ ድሮም አይመቸኝም ነበር:: እንዲያው ሁሉ ነገር ፍትፍት ብሎ....ቂቂ. ወለተ ጴጥሮስ ተንከባካቢ የሌላትን እናት ገላዋን አጥባ ቤተ ክርስቲያን አድርሳ ምግብ ሰርታ ተንከባክባ አስታማ ቀብራ...ይሁ ሁሉ ክርስቲያናዊ ስነምግባር ማር አደለም??? ምን እሱ ብቻ ..የሚሰድቡአችሁን መርቁ..ይህን እንድታደርጉ ህይወትን እንድትወርሱ ተጠርታችሃል¨ ይል የለ ወንጌሉ ምን እርሱ ብቻ..ክርስቶስ ያስተማረን ምን ነበር??? ደም ሳይፈስ ሰማእትነት ይህ ነው!!የ እለት ተለት ኑሮአችን ውስጥ ያለ ሰማእትነት ይህ ነው የሚቆርጥ ለ ጣኦት ካልሰገድክ ብሎ እሳት ውስጥ የሚጥል የለም:: ወለተ ጴጥሮስ እኔ እንደወደድኩዋችሁ (ራሱን እስከሞት አሳልፎ በመስጠት) እርስ በርሳቹ ተዋደዱ ብሎ ያለውን በተግባር አደረገውታል::

   Delete
 20. ውድ ወንድማችን ዲያቆን ዳኒ

  ቃለ ሕይወት ያሰማልን!

  እንዴት ግሩም የሆነ መልዕክት ነው:: ይቺ ለኔ ናት ብያለሁ!

  ከሳንፍራንሲስኮ

  ReplyDelete
 21. dani 10q so mach i love him so mach your bloog

  ReplyDelete
 22. ኢህአዴግ መራራ ቢሆንም በንቡ ምልክት፤ ምርጫ በመጣ ቁጥር መናደፉንና 99% ማሸነፉን ብታውቅም ማር ስለሆነ ዝም ብለህ ተሸክመኸው ኑር እያልክና ሕዝቡን እያደነዘዝክ ያለህ አይመስልህም?

  ReplyDelete
 23. የእኔ አስተያየት ግን የተለየ ነው፡፡ በገዳም ውስጥ ዓለም የበቃቸውና የመነኑ አባቶችና እናቶች እንደሚኖሩ እናውቃለን፡፡ ዳንኤል ግን ይህንን እውነታ በሁለት ነጥቦቹ የተጻረራቸው መሰለኝ፡፡ አንደኛው ታሪኩ ገዳማት ‹‹ክፉ››እንደተባለችው አይነት መነኩሴ መሰባሰቢያ ነው የሚል አንድምታ ያሰጥብሃል፡፡ ሁለተኛው መነኩሴይቱ ‹‹ክፉ›› ብትሆንም ሌሎቹ እርሷን የማይረዱ የማይተባበሩ ‹‹ክፉዎች›› ተደርገው ቀርበዋል፡፡ ይሄም ሌላ ጥፋት ነው፡፡ ስለዚህ ዳንኤል ላንተ የምመክርበት አንዳችም የእውቀት እንጥፍጣፊ ባይኖረኝም የዚህ አይነት ታሪኮችን ስትከተብ መሰረታዊውን ነገር ቆም ብለህ መርመረው፡፡ ከዚያ ወጭ ጥበብን ለአንተ የገለጸ አምላክ እኛንም ይጎበኘን ዘንድ ምኞቴ ነው፡፡

  ReplyDelete
 24. የምታይበት መንገድ የምትደርስበትን ግብ፣ የምታገኘውን ነገር፣ የምታመጣውን ውጤት፣ የምታተርፈውን ትርፍ፣ የምታፈራውን ወዳጅ፣ ይወስነዋል፡፡

  ReplyDelete
 25. ልክ እንደ ዳንኤል አእምሮው የበራ
  እፀልያለሁኝ ሀገር እንዲመራ

  God bless you... Daniel

  ReplyDelete