Tuesday, September 25, 2012

በመጥፋት ላይ ያለው ዝርያ


አደንን በመሰሉ ሰው ሠራሽ ችግሮችና በተፈጥሮ ላይ በሚደርሱ አደጋዎች የተነሣ በዓለማችን ላይ የነበሩ አያሌ እንስሳትና ዕጽዋት ጠፍተዋል፡፡
ለእነዚህ ዝርያዎች መጥፋት ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸው የሚባሉት አራት ናቸው፡፡ የመጀመርያው የሚኖሩበት የአየር ንብረት መለወጥ ነው፡፡ ለኑሯቸው ተስማሚ የሆነውና የሚያስፈልጋቸው የአየር ንብረት መለወጥ ሲጀምር እነርሱም ቀስ በቀስ ቁጥራቸው እየቀነሰ መጥፋት ይጀምራሉ፡፡ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ልቅ የሆነ አጠቃቀም ነው፡፡ የእነርሱን መብት ሊያስከብር፣ ዝርያቸውንም ከመጥፋት ሊያስጠብቅ የሚችል ኃላፊነት የተሞላው አጠቃቀም ከሌለ እነዚህን ዝርያዎች ማንም እንደፈለገ በማድረግ እስከመጥፋት ሊያደርሳቸው ይችላል፡፡ 
 ሦስተኛው ምክንያት ደግሞ የሰው ልጆች ያልተገባ ጣልቃ ገብነትና ጫና ነው፡፡ እያንዳንዱ ዝርያ በመኖርያ አካባቢው የራሱን የአኗኗር ዘይቤ ቀይሶና የኑሮ ልማድ መሥርቶ ይኖራል፡፡ የሁሉም የበላይ ነኝ ብሎ የሚያስበው የሰው ልጅ የራሱን ጥቅም ብቻ ለማስጠበቅ ሲል በሚያደርገው ሁሉንም የመነካካት በሽታው የተነሣ የእነዚህን ዝርያዎች አካባቢ ሲረብሸውና እነርሱም ይህንን የሰው ልጅ ረብሻ መቋቋም ሲያቅታቸው ወይ ቦታቸውን ለቅቀው ለአደጋ ይጋለጣሉ፤ ያለበለዚያም በአካባቢያቸው ሆነው ዝርያቸውን ያጣሉ፡፡ አራተኛው ደግሞ የመኖርያ አካባቢያቸውን ማጣታቸው ነው፡፡ በሕገ ወጥ ሠፈራ፣ በሚገነቡ ካምፖች፣ በጫካዎች መመንጠር፣ በጦርነትና በሌሎችም ምክንያቶች እነዚህ ዝርያዎች ለብዙ ዘመናት የለመዱት አካባቢ መልኩን ይቀይራል፡፡ በዚህ ጊዜ እነዚህ ዝርያዎችም አብረው ይጠፋሉ ወይም አካባቢውን ለቅቀው ለአደጋ ይጋለጣሉ፡፡
በእነዚህ አራት ምክንያቶች እየጠፉ ካሉት የዓለማችን ዝርያዎች መካከል የኢትዮጵያ ጋዜጦችና መጽሔቶች ሊካተቱ ይገባቸዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ እንደ ባለሞያዎቹ አገላለጥ አንድ ዝርያ በመጥፋት ላይ ያለ ዝርያ ነው (An endangered species) የሚያሰኘው የዚያ ዝርያ ቁጥሩ እየቀነሰ አለያም ደግሞ በአካባቢያዊ ለውጥ ምክንያት በዓለም ላይ የመቀጠል ዕድሉ እየተመናመነ ሲመጣ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ጋዜጦችና መጽሔቶችም ቁጥራቸው እየቀነሰና የመጥፋት አደጋም ከፊታቸው እየጠበቃቸው የሚገኙ ዝርያዎች ናቸው፡፡
ከሃያ ዓመታት በፊት ኢሕአዴግ አዲስ አበባ ከገባ በኋላ የተፈጠረውን ምቹ አጋጣሚ ተጠቅመው ጋዜጦችና መጽሔቶች ሀገሪቱን አጥለቅልቀዋት ነበር፡፡ መንገዱ ሁሉ ንባብ ንባብ ይሸት ነበር፡፡ ያን ጊዜ እስከ ሃምሳ ሳንቲም በሚጠጋ ዋጋ ይሸጡ የነበሩት እነዚህ ጋዜጦችና መጽሔቶች እረኛ ምናለ? የሚለውን ይትበሃል ቀይረው ጋዜጣ ምን አለ? አሰኝተውት ነበር፡፡ ከሰኞ እስከ እሑድ እየተደራረቡ እየወጡ መርጠንና አማርጠን እንድንገዛ አድርገውን ነበር፡፡
ቀስ በቀስ ግን ዝርያቸው እየተመናመነ መጣ፡፡ በአንድ ቀን ሦስትና አራት ጋዜጦችና መጽሔቶች በአናት በአናቱ ይወጡ እንዳልነበር ጋዜጣና መጽሔት የማይወጣባቸው ቀናት እየበዙ ማንበብም ብርቅ እየሆነ መጣ፡፡ የተረፉትም  ቢሆኑ የወረቀትና የማሳተሚያ ዋጋ ጭማሬን ተከትለው ቁጥራቸው ወደታች ዋጋቸው ወደ ላይ ወጣ፡፡ አሁን ደግሞ የንባብ ርሃብ የምንቀምስበት ደረጃ ላይ እየደረስን ነው፡፡ ከሳምንት ወደ ሳምንት ከጥቂት ጋዜጦችና መጽሔቶች በቀር ዓይን ይዞ የሚነበብ ነገረ እይጠፋ ነው፡፡ ለዚህ ነው የኢትዮጵያ ጋዜጦችና መጽሔቶች በመጥፋት ላይ ያሉ ዝርያዎች ናቸው የምለው፡፡ ለዝርያዎች መጥፋት የመጀመርያው ምክንያት የሆነው የምድራችን የአየር ንብረት መለወጥ በጋዜጦቻችንና መጽሔቶቻችንም ላይ እየታየ ነው፡፡ ከ1984 እስከ አሁን ድረስ እጅግ ብዙ አሠራሮች፣ ሕጎችና ሥነ ሥርዓቶች ተለዋውጠዋል፡፡ እነዚህ ለጋዜጦችና መጽሔቶች መኖር አስፈላጊ የሆነውን የአየር ንብረት የሚያጨናንቁ ሕጎችና አሠራሮች መለዋወጥ የጋዜጦቻችንና መጽሔቶታችን ዝርያ እንዲመናመን እያደረገው ነው፡፡
በዓለም ላይ ብዙ ሀገሮች በመጥፋት ላይ የሚገኙ ዝርያዎችን የሚመለከት ሕግ አላቸው፡፡ እንደነዚህ ዓይነት ዝርያዎችንም እያጠና በየደረጃቸው ዝርዝር የሚያወጣና ሕጉንም የሚያስተገብር ተቋምም መሥርተዋል፡፡ ይህ የማይተገበርበት ሁኔታ ሲፈጠር ግን ለእነዚህ ዝርያዎች ሁለተኛው የመጥፋት ምክንያት ይሆናል፡፡ እነዚህ ዝርያዎች በሰው ሠራሽም ሆነ በተፈጥሮ ምክንያቶች እንዳይጠፉ የመከላከያና የመደገፊያ ሕግና አሠራር ካልወ ጣላቸውና ለዓለማችን ጤንነትና ደኅንነት የሚያስቡ ሁሉ ካልተባበሯቸው በቀር እነርሱ ብቻቸውን ራሳቸውን  ከመጥፋት ሊታደጉ አይችሉም፡፡
ጋዜጦቻችንና መጽሔቶቻችንም በዋጋ መናር፣ በአሠራር ዕንቅፋቶች መብዛት፣ በቀላጤና በሥጋት እየተመናመኑና እየጠፉ እንዳይሄዱ እንደ ዝርያዎቹ ሁሉ የሚከላከል ሕግና አሠራር ያስፈልጋቸዋል፡፡ የፕሬስ ጉዳይ የሁሉም ጉዳይ እንጂ የጋዜጣ አሳታሚዎችና የጋዜጠኞች ጉዳይ ብቻ አይደለም፡፡ በመጥፋት ላይ የሚገኙ ዝርያዎችን ለመታደግ የተሠማሩ ባለሞያዎች እነዚህን ዝርያዎች ከጥፋት ለምን መታደግ እንዳስፈለገ ሲገልጡ ‹‹ዓለማችን የተመጣጠነች የምትሆነው እነዚህ ሁሉ ዝርያዎች ሲኖሯት ነው፤ ያለበለዚያ የተዛባች ዓለም ትኖረናለች›› ይላሉ፡፡
እነዚህ የሀገራችን ጋዜጦችና መጽሔቶች እየተመናመኑና እየጠፉ በሄዱ ቁጥር አስተሳሰባችንና አመለካከታችን ያልተመዛዘነ (un balanced) ይሆናል፡፡ ወደ አንድ አቅጣጫ ብቻም ያመዝናል፡፡ የካንሰርን መድኃኒት ለመፈለግ የተሠማሩ ሳይንቲስቶች ‹‹ምናልባት ይህንን መድኃኒት ለመሥራት የሚያስፈልገው ነገር ከጠፉት ዝርያዎች ጋር አብሮ ጠፍቶ እንዳይሆን?›› ብለው ይሰጋሉ፡፡ ከእነዚህ ዝርያዎች መጥፋት ጋር ብዙ የኑሮ ብልሃቶችና የችግር መፍትሔዎች አብረው ይጠፋሉና፡፡
እነዚህ የሀገራችን ጋዜጦችና መጽሔቶች ሲጠፉም አያሌ አስተሳሰቦች መውጫ አጥተው ይጨነግፋሉ፡፡ በአደባባይ ወጥተው ልናያቸው፣ ልንማርባቸው፣ አለያም ልንተቻቸው የሚገቡ ሃሳቦች መድረክ በማጣታቸው ብቻ ሆድ ውስጥ ይቀራሉ፡፡ ግብግባችን የሃሳብ ከመሆን ያልፍና የጉልበት ይሆናል፡፡
ቁሳዊ ዕድገት የሚመነጨው ከሃሳባዊ ዕድገት ነው፡፡ የማኅበረሰብ ንቃተ ኅሊና ሳያድግ የሚከወን ዕድገት ቀጣይነት አይኖረውም፡፡ ምክንያቱም ያልነቃ ኅብረተሰብ ዕድገትን የማስቀጠል ዐቅም አይኖረውምና፡፡ በተወሰኑ ኃይሎች ብርታት ለውጥ ወይም ዕድገት ይመጣ ይሆናል፡፡ ይህ ዕድገት እንደ አጥቢያ ኮከብ ታይቶ ብቻ እንዳይጠፋ በነቃ ኅብረተሰብ ኅሊና ላይ መመሥረት አለበት፡፡
ይህንን ኅብረተሰብ ከምንፈጥርባቸው መንገዶች አንዱ ደግሞ ሃሳብና መረጃ ነው፡፡ የመረጃና ሃሳብ ማስተላለፊያ መንገዶች የጥበቃና የክብካቤ ሕግና አሠራር ያስፈልጋቸዋል፡፡ ጋዜጦቻችንንና መጽሔቶቻችንን የሚንከባከቡ፣ ዝርያቸው እንዲጨምር፣ አመቺ ሁኔታዎች እንዲሟሉላቸው የሚወተውት ተቋም ያስፈልጋል፡፡ አንድ ፕሬስ ሲጠፋ አንድ አስተሳሰብ ይሠወራልና፡፡
ዝርያዎች ያልተገባ ጫናና ረብሻ የሰው ልጅ ሲያደርስባቸው ለመጥፋት እንደሚዳረጉ ሁሉ የፕሬስ ውጤቶችም ተገቢ ያልሆነ ጫናና ረብሻ ከተፈጠረባቸው በመጥፋት ላይ የሚገኙ ዝርያዎች ይሆናሉ፡፡ ከባለ ሥልጣናት፣ ከደጋፊና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች፣ ከፕሬስ ባለቤቶች፣ ያገባናል ከሚሉ አካላት፣ የራሳቸውን ጥቅም ብቻ ከሚያራምዱ ሀገራዊና ዓለም ዐቀፋዊ ተቋማት፣ የምንፈልገውን ብቻ ጻፉ ከሚሉ አንባብያን፣ ከባለ ገንዘቦችና ከሌሎችም አካላት እነዚህ ጫናዎችና ረብሻዎች ይፈጠራሉ፡፡ እነዚህ አካላት የየራሳቸውን ጥቅም ብቻ ፈልገው የሚጓዙ ከሆነ ይህንን በመጥፋት ላይ ያለ ዝርያ የሚኖርበትን አካባቢ ይረብሹታል፡፡ በምሬት ብዛትም እንዳይኖር ያደርጉታል፡፡
ማሰብና መጻፍ ዘና ያለ ስሜትና ነጻ የሆነ ሚዛናዊ ኅሊና ይፈልጋል፡፡ ደርሰትና ፈጠራ የኃላፊነት ስሜት እንጂ የጫና ስሜት አይስማማቸውም፡፡ ምን በጎ ነገር እንደሠሩ ማሰብን እንጂ ምን ኃጢአት ሠርቼ ይሆን? የሚልን ጭንቀት አይሹም፡፡ በሠራው ነገር ላይ የሚተማመንና ለሚመጣበት ተጠያቂነት የተዘጋጀ ሰውንም ይሻሉ፡፡ ነጻቱን የማያበላሽና በነጻነቱ ውስጥ በኃላፊነት ስሜት የሚሠራን ልቡና የግድ ይላሉ፡፡ ይህን መሰል የመኖርያ ቦታ ካላገኙ ድርሰትና ሃሳብ ሀገር ለቅቀው ይጠፋሉ፡፡ ለዚህ ነው ሁላችንም ለድርሰትና ለፕሬስ የሚሆን የመኖርያ አካባቢ እንፈጥር ዘንድ ግዴታችን የሚሆነው፡፡ ጋዜጦችና መጽሔቶች ብቻ ሳይሆኑ ሃሳብ ራሱ በመጥፋት ላይ የሚገኝ ዝርያ እንዳይሆን፡፡
ውኃ የሚያነሣ፣ ሃሳብን ያዝ የሚያደርግ፣ ኅሊናን የሚሟግት፣ የሚያመራምርና ያልተበላ ዕቁብ የሆነ አንዳች የሚነበብ ነገር እያነሰን የመጣ ይመስለኛል፡፡ በነ አዲስ ዘመንና በነ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ላይ እንኳን እነ አጋረደች ጀማነህ፣ እነ ዳንዴው ሰርቤሎ፣ ሀይለ ዘበቅሎ ቤት፣ እነ አሸናፊ ዘደቡብ አዲስ አበባ፣ እነ ጠንክር ዘካዛንቺስ፣ እነ እሸቴ ዘጃንሜዳ፣ ይጽፏቸው የነበሩትን በሁለት እጅ የማይነሡ ጽሑፎች ሳስብ፤ በእሑድ ጠዋት ፕሮግራም ይቀርቡ የነበሩትን የነ መጽሐፈ ሲራክ ትረካዎች ሳስታውስ፣ ዛሬ ዛሬ በርግጥም ድርሰትና ፕሬስ በመጥፋት ላይ ያሉ ዝርያዎች ናቸው ያሰኘኛል፡፡
በመጥፋት ላይ ያሉ ዝርያዎችን የሚያጠኑ፣ የሚመዘግቡና የሚከባከቡ ተቋማት እነዚህን ዝርያዎች በሰባት ይከፍሏቸዋል፡፡ እኔም ከቀድሞ ጀምረው ይታተሙ የነበሩትን ጋዜጦችና መጽሔቶች ሳስብ በእነዚህ ሰባት ምድቦች ውስጥ ገብተው ታዩኝ፡፡
 1. እልም ብለው የጠፉ(Extinct)፡- በምድራችን ላይ የነበሩ፤ አሁን ግን ከምድረ ገጽ የጠፉና ምናቸውም የማይገኝ፡፡
 2. በዋና መኖርያቸው ውስጥ የጠፉ(Extinct in the wild)፡- በሚኖሩበት ባሕር፣ ውቅያኖስ፣ ጫካና ምድረ በዳ ውስጥ የጠፉ፤ ነገር ግን ዝርያቸው በእንስሳት ማቆያዎች ወይም በምርምር ቦታዎች ብቻ የሚገኝ
 3. በአደገኛ የመጥፋት ሁኔታ ውስጥ ያሉ(critically endangered)፡- ቁጥራቸው ተመናምኖና አካባ ቢያቸው ተቃውሶ በመጥፋት ላይ ያሉ፡፡ ቁጥራቸው በጣት በመቆጠር ላይ የደረሰ፡፡ ድጋፍና ክብካቤ ካላገኙ ነገ ከነገ ወዲያ የሚሠወሩ፡፡
 4. በመጥፋት ላይ ያሉ(endangered)፡- እንደ ላይኞቹ አስጊ ደረጃ ባይደርሱም ነገር ግን ኑሮ ያልተ መቻቸው፡፡ አደን፣ የአካባቢ ጥፋትና የሰው ልጅ ወከባ የገጠማቸው፡፡ ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ በአደገኛ ሁኔታ ሊጠፉ ከተቃረቡት ወገን የሚደመሩ፡፡
 5. ለጥፋት የተጋለጡ(Vulnerable)፡- በመካከለኛ የጊዜ ለጥፋት ይጋለጣሉ ተብለው የሚፈረጁ፡፡ ቁጥራቸው አደገኛ በሆነ ሁኔታ እየቀነሰ ባይሆንም ከሚዋለዱት የሚጠፉት እየጨመሩ መሆናቸው የተረጋገጠ፡፡ በአዳኞች ወይም አካባቢያቸውን በሚፈልጉት አካላት ምክንያት አደጋ እየደረሰባቸው ያሉ፡፡
 6. በቅርቡ ጎራውን የሚቀላቀሉ(near threatened)፡- በአሁኑ ጊዜ የመጥፋት አደጋ ባይገጥማቸውም ይህ ችግር ከተወሰኑ ዓመታ በኋላ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል መረጃዎች የሚያሳዩ፡፡
 7. ብዙም ችግር የማይገጥማቸው(list concern)፡- የዚህን ዝርያ ሕልውና አደጋ ላይ የሚጥል ምንም ዓይነት ሥጋት የሌለባቸው ናቸው፡፡
እስኪ የኢትዮጵያን ጋዜጦችና መጽሔቶች የትናንቶቹን እያስታወሳችሁ የዛሬዎቹንም እየገመገማችሁ ከሰባቱ በአንዱ መድቧቸውና የት ደረጃ እንዳለን እወቅ?
‹‹የተለያዩ ዓይነት የሕይወት መልኮችና የኑሮ ሥርዓቶች ለሰው ልጅ ዕድገት እጅግ አስፈላጊ ናቸው፡፡››   Ishwaram & Erdelery, 2001, p. 179)
©ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ በመሆኑ በተመሳሳይ ኅትመት ላይ ባለማውጣት ተባበሩ

16 comments:

 1. እስኪ የኢትዮጵያን ጋዜጦችና መጽሔቶች የትናንቶቹን እያስታወሳችሁ የዛሬዎቹንም እየገመገማችሁ ከሰባቱ በአንዱ መድቧቸውና የት ደረጃ እንዳለን እወቅ?

  ReplyDelete
 2. This is the best idiomatic expression of the current oppression of free press in Ethiopia. Things are getting worst from time to time. It requires constant struggle to ensure what we need to achieve about freedom of expression. The above message may not be suffice to express what is really happening in Ethiopia. But, it serves us the stepping ladder for others to think, oppose and perhaps to fight for their freedom which is openly put in their constitutional right!!

  ReplyDelete
 3. በቅደሚያ ወንድማችን ዲን. ዳንኤል ክብረት ፀጋዉን ያብዛልህ::
  የሰዉ ልጅ ሰዉ በመሆኑ ብቻ ሊያገኛቸዉ ከሚገቡት መብቶች ዉስጥ አንዱ ሀሳብን የመግለጥ መብት ነዉ፡ፀሀፍት በማያገባችሁ አትግቡ ይሄ የኛ ጉዳይ ነዉ እየተባሉ ከስር ከስር አናት አናታቸዉን ከተባሉ ምንጊዜም ቢሆን በምክንያት የሚደግፍና በምክንያት የሚቃወም ህዝብ እንደናፈቀን እንኖራለን፡፡በየትኛዉም መልኩ ተወዳዳሪና ተፎካካሪ ከሌለ የተሻለ ስራና ለዉጥ ሊመጣ አይችልም፡፡ፀሀፍት ሁሌ ስለኢትዬጵያ የምድር ገነትነት(እንደ ኢቲቪ) እነዲፅፉ ብቻ ከሆነ የሚፈለገዉ ስህተታችንን ማን ያሳየን፡፡ዲን.ዳንኤል እንደምሳሌ ጋዜጦችና መፅሔቶችን አነሳህ እንጅ በተለያዩ የህብረተሰብ (social) Mediaዎች እያየን እኮ ነዉ Block የተደረጉት መብዛታቸዉ Facebook እና Diretubeን እነደምሳሌ መዉሰድ እንችላለን፡፡ለነገሩ የሚገርመዉ ከዚህ በተቃራኒዉ ብታደርጉ ነበር፡፡አልሰማንም አላየንም እንዳትሉ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ሆይ ከስህተታችሁ ተምራችሁ፡ ያልሆነ ስምና ታርጋ እየለጠፋችሁ ያሰራችሗቸዉን፡ልታስሩ ያሰባችሗቸዉን፡የዘጋችሗቸዉንና ልትዘጉ ያሰባችሗቸዉን ፀሀፍትና ጋዜጦችን ጉዳይ ብታስቡበት መልካም ነዉ፡፡ የተሻለ ሀሳብ የሚያመነጭ ህዝብ እንዲኖር የተለያዩ ነገሮችን እንድናነብ ይጠበቃል፡የተለያዩ ነገሮችን ለማንበብ የተለያዩ መጽሄቶች፡ጋዜጦች፡የግል ሚዲያዎች መስፋፋት አለባቸዉ፡፡ደግሞ ከሰለጠነ መንግስት ለምን ተናገርህ;ፃፍህ ብሎ ማሰር ;መፍታት አይጠበቅም፡፡ ቅን ልቦና ይስጠን፡፡

  ReplyDelete
 4. Avo temechitehignal

  "ምክንያቱም ያልነቃ ኅብረተሰብ ዕድገትን የማስቀጠል ዐቅም አይኖረውምና፡፡ በተወሰኑ ኃይሎች ብርታት ለውጥ ወይም ዕድገት ይመጣ ይሆናል፡፡ ይህ ዕድገት እንደ አጥቢያ ኮከብ ታይቶ ብቻ እንዳይጠፋ በነቃ ኅብረተሰብ ኅሊና ላይ መመሥረት አለበት፡፡ "

  Berta

  ReplyDelete
 5. መጀመርያውኑ እነዚህ ዝርያዎች ጤናማ ሳይሆኑ በሽተኞች ነበሩ
  በተገቢ ህክምናቸውን ተከታትለው የመድኀኒቱ ኣጠቃቀም መመርያ ተከትለው ስላልሄዱ ጤናቸው እየተጎዳ ዕድሜኣቸው እያጠረ ሄደና የሞቱም ኣሉ ለሞት የተቃረቡም ኣሉ! ታድያ ኣሁን እኛ ምን እናድርግ ከተባለ በሕክምና የተሰጣቸውን መድኃኒት በኣግባቡና መመርያው በሚፈቅደው የመድኃኒት ኣጠቃቀም መሰረት መድኃኒቱን እንዲወስዱ መምከር ነው ከዛ በመቀጠል ደግሞ ጤናማ የሆኑ በሽታ የሌላቸው ዝርያዎችን ማምጣትና መዝራትም ጠቃሚ ነው!

  ReplyDelete
  Replies
  1. There is no any restrictions on right of speech or write.There is no rule or law on right of speech.God give us this right for us equally without any restriction.Any goverment
   can not control or judge someone thought but only the people who read and heard can judge them.Dont use this right for political purpose.
   Demissie

   Delete
 6. Thanks Dn. Daniel
  There are also some news papers which undergo mutation with the change in environment(eg. Addis Admas).

  ReplyDelete
 7. 5(almost all are volunarable to be blocked)>4(the writers are in prison)>1(those we don't know &are distinct) >2(bocked in ethiopia)

  ReplyDelete
 8. ወዳጃችን ጥሩ ብለሀል::
  በየትኛውም ደረጃ ይገኙ ላለፉት 20 ዓመታት እየመጡ የሄዱትን የፕሬስ ውጤቶች እንደ እኔ ተመልሰው እንዲመጡም አልመኝም:: ሀሳብ የላቸውም የአመጽ ደወል ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩ የተቃውሞ ፖለቲካ ቅርጫቶች ነበሩ:: አልፎ አልፎ በየዋሀት የገቡትም ቢሆኑ በራሳቸው መተማመን የማይችሉ ፈሪዎች የመሩዋቸው ነበሩ:: ዘጠና ስም ይዘው ይወጡ የነበሩት እኮ የአንድ ቤተሰብ ሥራዎች ናቸው:: ሰዎቹ ደግሞ እንደ ሱቅ ነበር ያዩዋቸው እንጂ እንደ ማኅበረሰብ ጥቅም አልነበረም:: ስለዚህ ብቅ እያሉ ጠፉ::
  ቀልዱንማ ከባለ ተሰጥዎዎቹ መችአጣነው? ከማስታውሳቸው ጥቂት ልበል:: ፕሬዚዳንቱ ወረዱ ተብሎ በቦልድ የተጻፈ ርእስ ዝርዝር ዜናው እኮ የቻድ ሆኖ አግኝቻለሁ:: ቤተ መንግሥት ተተኮሰ በሚል እርስ ጽፎም ልብስ መሆኑን አንብበናልኮ:: እረ ብዙነገር:: መረጃ አልባ ማስረጃ የተራቡ ሥራዎች ቀልድ ቢሆኑ አይደንቅም:: የፕሬዝዳንቱ አሮጌ ልብሶች በአዲስ ሻንጣ ቤተ መንግሥት ገቡ:: መረጃስ ነው? ትዳር አደል የመሰረቱት ሰውየው . . . ስለዚ ቢቀሩም አይቆጭ::
  ካልተቃወሙ ካልተሳደቡ የጻፉ የማይመስላቸው ጋዜጣ ጽፈው ሀሳብ ተኮረጅን የሚሉ አቀበልን ማለት የሚያሳፍራቸው:: መሆን ካለበት ይልቅ የተገደፈውን መግለጥን ጀብዱ የሚመስላቸው:: ካልተሳደብን የሚሸጥ የማይመስላቸው በአንድ ጀንበር ለውጥ የሚጠብቁ:: በሰበከ በነጋታው ሁሉ ካልቆረበ/ካልጸደቀ እንደሚል ባሕታዊ የሚያስቡ “ጋዜጦች” ቢመጡ ቢሄዱ::
  እስኪ እነሱን እንተውና ተቋማት የሚያትሟቸው የሙያ የካውንስል የማእከላት ልሳናት የት አሉን? የስፓርት የማኅበራት የነጋዴዎች የሴቶች የጥናትና ምርምር ተቋማት የትምህርት ማእከላት ድርጅቶች የፓርቲዎች የሉም? ለግንዛቤ መስጫ አያዘጋጁም? የሚያዘጋጁዋቸውስ የት እየደረሱነው? ዳንኤል እንዳለው ቤተ መጻሕፍት ውስጥ እየተቆለፈባቸውነው?
  በይዘት ለየት ያሉ ልሳናት የት ገቡ? ለሕጻናት ማዘጋጀት አይቻልም ወይስ ገበያ የለውም? ዘፋኞቻችን ደጋግመው ስለፍቅር እንደሚዘፍኑት የተቃውሞ ፖለቲካ ካልሆነ አያዋጣም? ዘፋኞቻችን ስለ ቡና ስለ ቀይ ቀበሮ ስለ ትዳር ክብር ባይዘፍኑ ላይገርም ይችላል:: አያዋጣማ:: ጋዜጣስ መጽሔትስ? ለወጣቶች ለከፍተኛ ት/ተቋማት ተማሪዎች የቤተ እምነቶች የሳይንስ የጤና ወዘተ የኛዎቱ ግን ካልተሳደቡ የጽሑፍ ውቃቢያቸው ይርቃል መሰል:: ማንም ስድብን መሸከም የሚሻ የለም:: በቅርቡ ታሰረ ተፈነጨረ የሚባልለት አንድ ሰው አለ:: የፖለቲካውን እንተውና በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊ የትምህርት ሥርዓትን ሳይጠይቅ ሳይመረምርና ሳይረዳ በጻፈው ጽሑፍ ስንት ትውልድ ልምሾ እያደረገ እንደሆነ ታውቃላችሁ? እሱፊደል ቆጥሮ እንዲያድግ የእኔ የሚለውን ፊደልቀርጻ የሰጠችን እናት ምን እንደሚላት “ነጻነትን የማያውቅ ነጻ አውጭ” በተሰኘ ሥራው ያሰፈረውን ተመልከቱ:: ፈጣሪ ግን ሚዛናዊ ነው:: ለቤተ ክርስቲያን የሚቆም ቢጠፋ ተፋርዶላታል::
  ሥራው ከልምድ አዋላጆች ወጥቶ በባለሙያዎች ካልተያዘ የሀላፊነት ስሜት ከቶ ሊመጣ አይችልም:: የሀሳብ ሥራ የሚሰራው ትርፍ ለማግበስበስ አይደለም:: ከልብ በሚመነጭ ሕዝባዊ ወገንተኝነትነው:: የምንፈልገውን ለውጥ የጀንበር እድል ከሰጠነው ዳንኤል እንደሚለው የማን ሐዋርያ እርሻ ነበር ያልከው እንደሱ ተዓምር ብቻ ነው:: በጀንበር ለውጥ ለማምጣት ከሚሰሩ የሕትመት ውጤቶች ይጠብቀን:: ስለዚህ እነ ክብሪት እሳቶ ሳተናው በለው ተነሳ ፍለጠው ቁረጠው ቢቀሩም አይቆጭም ባይ ነኝ:: የሚያስፈልጉንን የሚሰሩ የሚመጡበት ጊዜ ይመጣል:: እርሱም አሁን ነው::

  ReplyDelete
 9. Thank you Dani for the analogy. It would have been more valuable information if you list those papers.Also blocked cyber media should be included in your list.Yes, we all should be responsible for librating and protecting PRESS from supression in Ethiopia!!!Who can deny or grant free expression ideas? No one can't. I would rather die being free than live without freedom.Free Eskinder Nega and thousands of others!!!Respect their opinons.

  WE ARE NOT FREE UNTILL WE ALL ARE FREE! SB.

  ReplyDelete
 10. አንዳንድ ጊዜ ትናንትን መርሳት የጥፋቶች ሁሉ ቁንጮ የሚሆንበት አጋጣሚ አለ:: በነጻው ፕሬስ የገጠሙን ችግሮችም ይህን ዓይነት ሳይሆኑ አይቀሩም:: አገሪቱ በአዋጅ ንባብ የተከለከለባት አገር ፣ የግል የሚባል ፕሬስ የማይታሰብባትና ሌላው ሁሉ ቀርቶም ሀሳብን የመግለጥ መብት የማይወሳባት ዘመን ነበር:: በጥላሁን ገሰሰ ዜማ ልበለው? "እንዴት ይረሳል እንዴት ይረሳል . . . " ይህንን ረስተን ከጀመርን ነው አደጋው:: ነጻው ፕሬስ በብዙ ዓለማት ከልምድ አልፎ ባሕል መሆን ሲጀምር ነው እኛ ሀ ሁ ማለት የጀመርነው:: በእንቅርት ላይ ምን እንዲሉ ገና ፊሽካው ሲነፋ ደሞ አንዳንዶቹ የሀሳብ ሜዳ መሆናቸው ቀርቶ የጦር አውድማ ሆኑ::

  ዝርያቸው እንዳይጠፋ ብቻ ሳይሆን እንዳያጠፉም መጠንቀቅ የሚያሻ ይመስለኛል:: ለማኅበረሰብ ንቃተ ኅሊና ከሚያበረክቱት አስተዋጽኦ በላይ የማጥቂያ ፣ የመራበሻ ፣ ማሳሳቻ ፣ . . . እየሆኑ ነበር:: የተቃውሞም እኮ አይነት አለው:: ዓመት ሙሉ ቡሄ ሲሉእኮ ነበር የሚከርሙት መች አበባየሆሽ ብለው ያውቃሉ? በግ ይመስሉን ይሆናል እንጂ በበግ ለምድ ከተማ የገቡ ተኩላዎች ነበሩ:: በጠባያቸው ከፍሬያቸው የተረዳነው ይህንን ነው:: ነከሱን እንጂ ርሀባችንን የሚያስታግሱ አልሆኑም:: የማትረባ ፍየል እየተረቱ አበሳጩን እንጂ መች መማሪያ ሆኑን? በጽሑፍህ ሚዛን የደፋልኝና የሚመጥን ሆኖ ያገኝሁት አንድ አዲስ ነገርን ብቻ ነው:: ሌሎቹን ግን ስማቸውንም ባታነሳ የተሻለ ነበር:: ወደፊት የሚመጣው ጉልበት በቋንቋም በዝቶ በክልል ከተሞች ላይም ማየት የምንችልበት እድል ይኖራል ብዬ አስባለሁ:: ካልሆነ ከ 10 ሺህ ለማይበልጥ እትማቸውና ለጠብ ያለሽ በዳቦ ብእራቸው የዝርያ ያህል ባያሳስበን እላለሁ:: ከመኖራቸው በላይ ይዘታቸውም ቢያሳስበን መልካም ነው:: የጅምሩ ታሪክ ይህን እንዲመስል ያደረግነው ራሳችን ነን በጥቂት ቁጥርም ይቀጥል:: አለ የምንለው እነ እከሌ ሲጽፉነው ካላልን በቀር ያሉትን ያቆ ይልን:: መልካም ሁኔታ ላይ አሉ ባይ ነኝ ወደፊትም ለውጡን የሚያግዝ ሥራ የሚሰሩ ሞግተው የሚያሸንፉ ሰላማዊ ጫና መፍጠር የሚችሉ ብእሮችን ተስፋ እናደርጋለን:: ነገ መልካም ይሆናል!

  ReplyDelete
 11. በጣም ወሳኝ ጉዳይ ነው ያነሳሀው የጋዜጦችና መጽሔቶች ጥራት ምንም ይሁን ምን እንዲጠፉ ማድረግ በሰው ልጅ የማሰብ ነጻነት ላይ መዝመት ነው የተገደበ ህሊና አይደለም ለእድገት ውሎ ለማደርም ብቃት የለውም በእውቀት ላይ የሚዘምት በትውልድ ላይ የፈረደ ነውና በተቻለን አቅም መቃወም አለብን

  ReplyDelete
 12. በነ አዲስ ዘመንና በነ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ላይ እንኳን እነ አጋረደች ጀማነህ፣ እነ ዳንዴው ሰርቤሎ፣ ሀይለ ዘበቅሎ ቤት፣ እነ አሸናፊ ዘደቡብ አዲስ አበባ፣ እነ ጠንክር ዘካዛንቺስ፣ እነ እሸቴ ዘጃንሜዳ፣ ይጽፏቸው የነበሩትን በሁለት እጅ የማይነሡ ጽሑፎች ሳስብ፤ በእሑድ ጠዋት ፕሮግራም ይቀርቡ የነበሩትን የነ መጽሐፈ ሲራክ ትረካዎች ሳስታውስ፣ ዛሬ ዛሬ በርግጥም ድርሰትና ፕሬስ በመጥፋት ላይ ያሉ ዝርያዎች ናቸው ያሰኘኛል፡፡
  thank you

  ReplyDelete
 13. አንዳንዶቻችሁ በጣም ታስገርማላችሁ እስቲ ትንሽ ከዘረኝነትና ከተራ ጭፍን ደጋፊነት ወጥታችሁ ለአምስት ደቂቃ በነጻ ህሊናችሁ ለማሰብ ሞክሩ፡፡ እንኳንም ቀሩ ስለነሱ ማሰብ አያስፈልግም ሳይሆን ህዝብ አታሰፈልጉም ብሎ ይጣላቸው ነው እንጂ በግዳጅ በእስር በማንገላታት መሆን የለበትም እኛ እንደናንተ ልማታዊ መንግስታችን በሚያስብልን ሳይሆን እኛ እግዚአብሔር በሰጠን ነጻ ህሊናችን መርምረንና መዝነን እንትፋቸው ነው እናንተ ደግሞ ሁላችሁም ማለት ይቻላል ከነባለስልጣናቱ ጭምር ሁሉ እንደናንተ አህያ ወይም ድንጋይ ይመስላችዃል መሰል እኛ ገና የዲሞክራሲ ሀ ሁ ላየ ነን ትላላችሁ ሀ ሁ እኮ ከዚህ ነው የሚጀምረው ይህ እኮ ነው መሰረቱ ይህን አይነት ነጻነት ተገፎ መኖር በራሱ ምን ኑሮ ነው ሆድ አደርነት ካልሆነ እና ህዝብ መዝኖ ይጣል እንጂ መንግስት አይሁን

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ewnet belehal wendeme. Ene lasebelachohe Enante atasebo malet yehezbone nesanet megfefe new!!!

   Delete