Tuesday, September 18, 2012

የደብረ ምጥማቅ መግባቢያ


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ውስጥ መንግሥታዊ ያልሆነች ትልቋ ተቋም ናት፡፡ በሕዝቡ ሃይማታኖዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ታሪካዊ ጉዞ ውስጥ የማይተካና ወሳኝ የሆነ ሚናም አላት፡፡ ዕድገቷ ለሀገሪቱ ዕድገት፣ ሥልጣኔዋ ለሀገሪቱ ሥልጣኔ፣ አሠራርዋ ለሀገሪቱ አሠራር፣ የችግር አፈታቷም ለሀገሪቱ የችግር አፈታት ወሳኝ ነው፡፡
በመሆኑም የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግሮች ለመፍታትና አንዲት፣ ጠንካራ፣ በአሠራርዋ ዘመናዊ፣ በእምነቷ ጥንታዊ፣ በሀገሪቱ ጉዞ ውስጥ ተደማጭና ወሳኝ የሆነ ሚና ያላት፣ ሌሎች ችግሮቻችንን በመፍታት ረገድ ሀገራዊ መንፈሳዊና ተልእኮዋን የምትወጣ ቤተ ክርስቲያን እንድትሆን በማድረጉ ጉዳይ ላይ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ ይመለከተናል፡፡
በዚህ ዘመን ቤተ ክርስቲያኒቱ ከገጠሟት ፈተናዎች አንዱ የመለያየት ዕጣ ፈንታ ነው፡፡ ይህ ዕጣ በተለይም በሀገር ቤትና በውጭ በሚባል ሲኖዶስ፣ በማይግባቡና በማይቀራረቡ አባቶች እነርሱም በተከተሉት ሁለት ዓይነት የችግር አፈታት ምክንያት የተከሰተ ነው፡፡ 
ይህንን ችግር እንፈታው ዘንድ ከተፈጠሩልን መልካም ዕድሎች መካከል አንዱ ላይ እንገኛለን፡፡ አባቶችም፣ ምእመናንም፣ ሀገር ወዳዶችም ይህንኑ እየጠየቁና እያሳሰቡ ይገኛሉ፡፡ ይህንን ሁላችንም ልናየው የምንመኘውን የቤተ ክርስቲያን አንድነት ሊያመጡ ከሚችሉት መንገዶች አንዱ የሆነው ‹‹ የደብረ ምጥማቅ መግባቢያ›› የተሰኘው መግባቢያ ነው›፡፡
ደብረ ምጥማቅ በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ተጉለት ውስጥ የምትገኝ ቦታ ናት፡፡ በ14 ኛው መክዘ በንጉሥ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት የመለያየት ፈተና ተጋርጦባት የነበረችውን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን አንድ ለማድረግ ሲባል ሁሉን አቀፍ ሀገራዊ ጉባኤ የተደረገባትና አንድነቱም የተገኘባት ቦታ ናት፡፡
ከ13ኛው መክዘ ጀምሮ የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን እንድነት የፈተነ አንድ ጥያቄ ነበር፡፡ የሰንበት አከባበር ጉዳይ፡፡ በአንድ በኩል መከበር ያለባት ሰንበተ ክርስቲያን ብቻ ናት በሚሉትና በደብረ ሊባኖስና በሐይቅ እስጢፋኖስ አባቶች በሚመሩት፤ በሌላ በኩል ደግሞ መከበር ያለባቸው ቀዳሚትም የክርስቲያን ሰንበትም ናቸው በሚሉት በአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ደቀ መዛሙርትና በደብረ ብሥራት ዜና ማርቆስ (ሰሜን ሸዋ) በሚመሩት አባቶች መካከል የሀሳብ ልዩነት ተፈጥሮ ነበር፡፡
ይህ የሃሳብ ልዩነት ወደ አለመግባባት አምርቶ የሁለት ሰንበት ሃሳብ አስተማሪ የነበሩት አቡነ ኤዎስጣቴዎስ መጀመርያ ወደ እስክንድርያ፣ በኋላም ወደ አርመን(ቆጵሮስ) ሄዱ፡፡ በዚያውም በስደት ዐረፉ፡፡ የእርሳቸው ደቀ መዛሙርት የሚገኙባቸው በኋላም ኤርትራ በሚገኘው ደብረ ቢዘን ይመሩ የነበሩት ገዳማትና አድባራትም በአብዛኛው በስተዳደር ጉዳዮች ከመሐል ሀገር አብያተ ክርስቲያናት እየተለዩ መጡ፡፡ በተለይም ደግሞ ዐፄ ዳዊት ችግሩን ለመፍታት በጠሩት የሐይቅ እስጢፋኖስ ጉባኤ ላይ የተገኙትን የደብረ ቢዘኑን አቡነ ፊልጶስን በዚያው በሐይቅ በግዞት እንዲቀመጡ ማድረጋቸው ችግሩን አባባሰው፡፡ በሰሜን ትግራይና በኤርትራ የነበሩ ገዳማትና አድባራትም ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ ከመካከለኛው ሕዝብና ቤተ ክህነት ተለያዩ፡፡
ችግሩ የተፈታው ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ወደ ሥልጣን ሲመጣ እና ሁለቱም አባቶች የተሳተፉበት ጉባኤ በደብረ ምጥማቅ በ1442 ዓም በተደረገ ጊዜ ነው፡፡ በዚህ የደብረ ምጥማቅ ጉባኤ ሁለቱም ወገኖች ተገኝተው በችግሩ መፍትሔ ላይ ተወያዩ፡፡ መለያየታቸውን ለማስወገድ ተስማሙ፡፡ ሁለቱም ሰንበቶች እንዲከበሩ፤ ነገር ግን የቀዳሚት ሰንበት አከባበር እንደ አይሁድ የሰንበት አከባበር እንዳይሆን ከመግባባት ላይ ደረሱ፡፡
ይህ መግባባት የመለያየት አደጋ ተፈጥሮባት የነበረችውን ቤተ ክርስቲያን ወደ አንድነት በማምጣትና መለያየቱም መልክዐ ምድራዊ አቅጣጫ እንዳይከተል በማድረግ ታላቅ ሚናን ተጫውቷል፡፡ ለዚህ ነው ይህ ለዛሬዋ ቤተ ክርስቲያናችን አንድነት የቀረበው መግባቢያ በዚሁ ስም የተሰየመው፡፡ ከራሳችን ልምድ እንድንማር ተብሎ፡፡
የደብረ ምጥማቅ መግባቢያ
1.      ባለፈው ላይ መነጋገር ማቆም፡- በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የሚደረገውን የአንድነት ውይይትም ሆነ፣ እኛ ሌሎች አካላት የምናደርገውን አስተዋጽዖ የሠመረ ለማድረግ ውይይቱ በቀጣይ የመፍትሔ ሃሳቦች ላይ እንጂ በትናንቱ ላይ እንዳይመሠረት ማድረግ፡፡ ትናነት ማን ነበር ጥፋተኛ? እገሌ ለምን እንደዚህ አደረገ? ለምን እንደዚህ አላደረገም? እያልን መከራከራችንን ብናቆየው፡፡ ምክንያቱም ትናነትን መቀየር አይቻልም፡፡ ሆኗል፡፡ ልንሰጠው የምንችለው ትርጉም ብቻ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ያከራክራል፤ ከዚያም አልፎ ያጨቃጭቃል እንጂ መፍትሔ አያመጣም፡፡ አንዱ ከሳሽ ሌላው ተከሳሽ፤ አንዱ ወቃሽ ሌላው ተወቃሽ፣ አንዱ አሸናፊ ሌላው ተሸናፊ እየሆነ ግብግብ ከመፍጠር ያለፈ ፋይዳ የለውም፡፡ ስለዚህ ነገ አንድነቱ ሲመሠረት ገለልተኛ የሆነ አካል አቋቁመው ሁለቱም አካላት ትምህርት እንዲወስዱበት የትናነቱ ወደፊት በባለሞያ ይጠና፡፡ አንድ ሆነንም ማን እንደነበርን ያኔ እናየዋለን፤ እንሰማዋለንም፡፡ አሁን ግን በምናደርጋቸው ውይይቶች የትናንቱን ትተን በነገው መፍትሔ ላይ እንመሥረት፤ ነገ በእጃችን ላይ ስለሆነ፤ ትናንት ግን አምልጦናል፡፡
2.    ሁሉን ዐቀፍ ይቅርታ፡- ለተፈጠረው ችግር የተወሰኑ ግለሰቦችን፣ አካላትን ወይም የታሪክ አጋጣሚዎችን ብቻ እየኮነንና እያወገዝን ከምንጨቃጨቅ፤ ሁሉም ራሱን ነጻ ለማድረግም ከሚረባረብ   ‹‹የበደልነው ሁላችንም ነን፤ የተበደለውም እግዚአብሔር ብቻ ነው›› ብለን አምነን ሁላችንም ሁላችንን እና ሁላችንም እግዚአብሔርን ይቅርታ ብንጠይቅ፡፡ ይህም ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በአንድ በታወቀ ዕለት ከሁለቱም ወገን በሚወከሉ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ መነኮሳት፣ ምእመናንና አገልጋዮች አማካይነት ለሕዝብ ግልጥ ሆኖ ቢከናወን፡፡ ይህ ሁኔታ በአንድ በኩል ክርስትናችን የሚያዘን ነውና የእግዚአብሔርን ረዳትነት ያስገኝልናል፤ በሌላም በኩል አንዱ በሌላው ላይ ጣት መጠቆሙን፣ የክስ ፋይልም መተንተኑን አቁሞ ነገሩን በጋራ ለመዝጋት ያስችለናል፡፡
3.    ውግዘቱን ማንሣት፡-  በሁለቱም አካላት የተላለፉትን ውግዘቶች ከይቅርታው በኋላ አከታትሎ በሁለቱም አካላት አማካይነት እንዲነሡ ማድረግ፡፡
4. ሁለቱም አካላት ችግሩን ከሚያባብሱ ተግባራትና አዝማሚያዎች መቆጠብ፡- እያንዳንዱ ወገን የሚያከናውነው ነገር ሰላሙንና አንድነቱን የሚያጠናክር እንጂ ችግሩን የሚያባብስ እንዳይሆን መጠንቀቅ፡፡ ሁለቱም አካላት ይህንን የሚከታተል የጋራ ኮሚቴ አቋቁመው እነዚህን ተግባራትና አዝማሚያዎች መከታተልና እንዲታረሙ ማድረግ፡፡ ግለሰቦችንና ቡድኖችንም መገሠጽ፤
5.    የጋራ የእርቅ ኮሚቴ መመሥረት፡- እስካሁን ውይይቶቹ በሦስተኛ አካል በኩል የሚደረጉ ናቸው፡፡ ዕርቁ ከተፈጸመና ውግዘቱ ከተነሣ በኋላ የጋራ የሊቃነ ጳጳሳትና የሊቃውንት ኮሚቴ ማቋቋምና ቀጣዩ ሂደት ምን እንዴት መደረግ እንዳለበት አንድ ሆኖ ሰነድ ማዘጋጀት፡፡ በዚህ ሰነድም
·     የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሁኔታ
·  በውጭ ሀገር ያሉ አባቶች ወደ ሀገር ለመግባት የሚችሉበት ሁኔታ
·  በልዩነቱ ዘመን የተፈጠሩ ሕጋዊ፣ ተቋማዊና አስተዳደራዊ ልዩነቶች ስለሚጣጣሙበት ሁኔታ
·   የሀገረ ስብከት ድልድል
·   አንድ የሚያደርግ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ
·   ከሰላሙና ከአንድነቱ ሂደት የሚያፈነግጡትን በተመለከተ
· ሌሎች ጉዳዮችን የሚመለከቱ ነገሮችን በዝርዘርና ከነ መፍትሔያቸው አንድ ሆኖ በድርድር መንፈስ ሳይሆን የጋራ መፍትሔ በመስጠት መንፈስ ማከናወንና በሁለቱም አካላት አስጸድቆ የጋራ ሰነድ ማድረግ
6.    የ2006ን የጥቅምት ሲኖዶስ በአዲስ አበባ ማድረግ፡- በ2005 ችግሮቹን ሁሉ ፈትቶ የ2006ን የጥቅምት ሲኖዶስ ጉባኤ ሁሉም አባቶች በሚገኙበት በአዲስ አበባ ማከናወን፡፡ በዚህ ቀን ሕዝብ የሚሳተፍበት የአንድነት በዓል ማዘጋጀትና ከሁለቱም ወገን በሚወከሉ አባቶች ለሕዝቡ የሰላምና የአንድነት ትምህርት እንዲሰጥ ማድረግ፡፡ በዚህ የጥቅምት ጉባኤም የመለያየቱን ዘመን በአንድነት ጉባኤ መዝጋት፡፡
ነገሩ እንደሚጻፈው ያህል ቀላል አይደለም፡፡ ነገር ግን ላመነ ሁሉም ይቻላል ለምንል ክርስቲያኖች ዓለም ከዚህ በላይ ይጠብቅብናል፡፡ ማየት ያለብን የየራሳችንን አመለካከት አይደለም፤ የየራሳችንንም ጥቅም አይደለም፤ የየራሳችንንም በጎ ሃሳብ አይደልም፡፡ ማየት ያለብን ታላቋን ሥዕል ቤተ ክርስቲያንን ነው፡፡ አንዳንዱን ነገር እየተውን፤ አንዳንዱን ነገር እያሳለፍን፤ አንዳንዱን ነገር እየተሸነፍን፤ አንዳንዱንም ነገር እየናቅን መሻገር አለብን፡፡ ወደሚያግባባን እንጂ ወደሚለየን፤ ወደሚያስታርቀን እንጂ ወደሚያኳርፈን አንጓዝ፡፡ አንድ ትውልድ በመለያየቱ ግንብ ውስጥ ተወልዶ አድጎ፣ ለወግ ለማዕረግ በቃ፡፡ አይበቃንም? ለመሆኑ ስንት ትውልድ ማለፍ አለበት?
አሁን ሁላችንም ከጸሎት ጋር ከዚህ የተሻሉ ሃሳቦችንም በማምጣት፤ ይህንንም በማዳበር ግፊትና ጥረት እናድርግ፡፡
የሰላም አምላክ ይርዳን፡፡ አሜን፡፡


ቺካጎ

85 comments:

 1. This is excellent idea. God bless you.

  ReplyDelete
 2. ስማማው አያሌው (ከአዋሽ)September 18, 2012 at 6:34 PM

  ጠቅለል ባለ መልኩ በእኛ ሃገር ተምሬአለሁ፤ ነÀ የብዙሃን መገናኛ ነኝ ወይንም ፈረንጅ ሃገር እኖራልሁ እያለ በተቃዋሚው ጎር
  የተሰገሰገው ሁሉም አዋቂ፤ ሁሉም ተንታኝ፤ ሁሉም ሃላፊ፤ ሁሉም መሪ፤ ሁሉም ሰብሳቢ፤ ሁሉም ተከተሉኝ ባይ፤ ሁሉም
  ተናጋሪ፤ ሁሉም ሰላምታ እንኳን ሳይለዋወጥ የአንድነት ተጠሪ፤ ሁሉም ፖለቲከኛ ነው። ዲሞክራት ሳይሆን እራሱን ዲሞክራሲ
  አድርጎ በህዝቡ ላይ እንደማዳበሪያ ሊበተንበትም ያዙኝ ልቀቁኝ ይላል። ሕብረተሰብ እሱን ማዳመጥ፤ መከተል፤ ትዕዛዙን
  መቀበል፤ ሽር ጉድ ማለት፤ መሽቆጥቆጥ ግድ ይለዋል። ሐቁ ግን ኢትዮጵያዊ በተፈጥሮ ዲሞክራት ነው፤ አልሚ ነው፤
  እንቬስተር ነው፤ ድርጅት ነው፤ መሪ ነው፤ ትህትና የተላበሰ ነው፤ ተግባቢም አግባቢም ነው፤ አዋቂ ነው፤ ለአንድነት ባንድነት
  የቆመ ነው፤ አስተዋይም ነው። ቢያንስ እነሱ ሳይሆኑ ሆነናል የሚሉትን መሆን አይገደውም። የምታውቀውን ሳይሆን
  የምነግርህን ባይ ስብስቦቹ እውቀታቸውም ሆነ ሙያቸው ስልጣን ኮርቻ ላይ እንዲያቆናጥጣቸው እንጅ በአግባቡ ከጥቅም ላይ
  ውሎ ከሚያደረስው ግብ መድረስ አንዳልሆነም ከተገነዘበው ውሎ አድሯል። ፖለቲካቸው የጨለማ ጉዞም መሆኑን
  ስለማይገነዘቡ ሃገሬና ወገን የሚል ሁሉ እነዚህን ማስወገድ ሌላ ሳይሆን ለሕዝብና ከህዝብ ጎን መቆም እንደሆነም ተረድቷል።
  ሕዝብም በጠ/ሚኒስቴር ሞት ቃል ሲገባ የጀመሩትን ዕቅድ ከዳር እናደርሳለን ሲል እኛ ደግሞ የጥፋት አረሞችን እንነቅላለን
  እንላለን። እነዚህን እሾሆችም ሙያ ካላችሁ ከባለሙያ መፎካከር፤ ከተማራችሁ ከምሁራን መወዳደር፤ አዋቂም ከሆናችሁ
  ጥበብ ሰርቶ ማሳየት እንጅ መንድር ለመንድር እኔ ሁሉንም ነኝ ማለት ወኔቢስነት ነው እንላቸዋለን። ሃገሬና ወገኔ ለሚል ሁሉ
  መልዕክቴ እስከ አሁን እነሱ ያሰናከሉት ሕይወትም፤ ንብረትም፤ በጎ ስራም፤ ሰፊ ራዕይም ተወዳድሮ ማሸነፍም በጣም ብዙ
  ነው እንâን ሌላ ተጨማሪ ጥፋት፤ ስድብ፤ ውርደት፤ ንቀተት፤ ተሸክምው ሊያሽክሙን።
  ለገነቡልን ያደገችና የተከበረች ኢትዮጵያ እኛም እናመሰግናለን እጅ እንነሳለን ይሏል!!!!
  አስማማው አያሌው (ከአዋሽ)

  ReplyDelete
  Replies
  1. True Ethiopian.........Asmamawe
   its for Daniel.... that's it!

   Delete
  2. የመልዕክትህ ይዘት አልገባኝም:: አየህ በአረም እንነቅላለን ሰበብ ይህች አገር ብዙ መከራ አየች:: ለመሆኑ ለዚች ሃገር ማን እንክርዳድ ማንስ ስንዴ? ወንድሜ እስኪ ማን ማንን ገፍቶ ባለሃገር ባለሃይማኖት ባለ ርዕስት ይሆናል:: ከውጭ ያለውን ኢትዮጵያዊ ከመውቀስና በኢትዮጵያ ጉዳይ አያገባችሁም ከማለት እዚሁ አፍንጫህ ስር የሚነፍሰውን ሽታ አሽት እዚሁ አይንህ ስር የሚታዬውን ትርምስምስ ተመልከት እዚሁ ከጎንህ የተገተረውን እሾሃማ ግንብ ዳስ:: መቼም እኔነቴ መገንዘብ የሚችለው ከርቀት የሚሰማን ድምጽ እንጂ ሌሎች ህዋሳቶቼ ከጥቅም ውጭ ናቸው እንደማትለኝ ተስፋ አደርጋለሁ:: ማንም ሰው በ አገሩ መኖርን አይጠላም ደግሞም ለአንድ ኢትዮጵያዊ ከ አገር ወጥቶ ከዘመድ አዝማድ እርቆ እንደመኖር ከባድ ነገር የለም:: ለ አንድ ኢትዮጵያዊ ህይዎት ማለት ኑሮ ማለት ከመብላት ከመጠጣት በላይ ነው:: እናም አንድ ኢትዮጵያዊ ከ አገር ስለወጣ አያገባህም መናገርም ሆነ መተቸት አይገባህም ልንለው አይገባም:: ይህኔ አንተም ቢሆ ቢያንስ አንዴ DV ሞልተህ ይሆናል:: እኛው እዚሁ የምንፈጥረው ችግር ያስበረገጋቸውን እና የሰው አገር ታድጓቸው ድምጻቸውን ስላሰሙ ወገኖቻችንን አይናችሁ ላፈር ማለት መፍትሄ አይመስለኝም:: ደግሞስ በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን ለ እኛ ተስማሚ የመሰለንን ነገር ሲያደርጉ አጀብ በርቱ ብለን ዜና ከሰራን እነዚሁ ሰዎች ለቤተሰቦቻቸው የሚልኩት የውጭ ምንዛሬ የአገሪቱ ዋነኛው የውጭ ምንዛሬ ምንጭ መሆኑን እያዎቅን ከነዚህ ሰዎች የሚሰማ የጩኸት ድምጽ የሚረብሸን ከሆነ በሽተኞቹ እነሱ ሳይሆን እኛ መሆናችንን አለመገንዘባችን ለምን ይሆን? ወንድሜ ዲ/ን ዳንዔል አለ ብሎ ስላመነበት ችግር የመፍትሄ ሃሳብ ይሆናል ብሎ ያሰበውን ተናግሯል አንተም ከቻልህ የራስህን ሃሳብ አካፍለን ካልቻልህ ደግሞ ዝም ይባላል እንጂ የጦርነት ነጋሪት ጎሳሚ ለምን ሆንህ? አልታዎቀህም አንጂ አንተም እኮ እንደዎቀስሃቸው ሰዎች ነህ:: አንተ እነሱን ታዎግዛለህ እነሱ አንተን ያዎግዛሉ! መረዳዳት መተባበር መግባባት ስንችል እየተወጋገዝን መኖር እስከመቸ?

   Delete
  3. afhn stkeft chinklathn ayehut asmesy weregna hod ader banda mehonkn ;;ye tshufu melkt enkua yalgebh neh lbona ena mastewal ysth.

   Delete
  4. betam tiru comment newe asmamaw.diaspora eko melefelefe becha newe tegbare laye zero nachew.

   Delete
  5. briliant comment asmamaw.especially for daniel kibret

   Delete
  6. የአቶ አስማማውን አስተያየት እንደተረዳሁት በፖለቲካ አመለካከታቸው ለተለያዩት ፣ ሥልጣንን ለመያዝ ጐራ ከፍለው የሚታገሉትን ተቀናቃኞች የሚመለከት ይመስላል ፡፡ የዲያቆን ዳንኤል መልዕክት ደግሞ የሚያትተው ቤተ ክርስቲያን እስከ መጨረሻው ወደ መከፋፈል እንዳትሄድ ፤ ችግራችንን መፍትሄ እናፈላልግለት የሚል ነው ፡፡ ባለፈው ላይ ርዕስ አድርጎ መከራከሩ ይብቃን ፤ ያለፈው ሥራችን ለታሪክ ተመራማሪዎች በይደር ይታለፍና መጪው ትውልድ እንዲማርበት ወደፊት በሂደት ይጠናም ይላል ፡፡

   ስለዚህም አቶ አስማማው ቤተ ክርስቲያን የምትሰብከው የክርስቶስ ወንጌልን እንጅ የፖለቲከኞችን ዲሞክራሲ አለመሆኑን ተረድተው ፣ የቤተ ክርስቲያንን ችግር ለመፍታት ያስኬደናል የሚሉትን መፍትሄ ቢያስንብቡ አማራጭዎትን እጠብቃለሁ ፡፡

   ስለ ቤተ ክርስቲያን ችግር የመፍትሄ ሃሳብ ሲቀርብ ያነሱዋቸው ነጥቦች ሙሉ ለሙሉ የፖለቲካ ይዘት እንደሚያንጸባርቁ ልብ እንዲሏቸው ያህል እኒሁት ፡-
   - በተቃዋሚው ጎር የተሰገሰገው ሁሉም አዋቂ፤ ሁሉም ተንታኝ፤ ሁሉም ሃላፊ፤ ሁሉም መሪ ….. ሁሉም ሰላምታ እንኳን ሳይለዋወጥ የአንድነት ተጠሪ፤ ሁሉም ፖለቲከኛ ነው
   - ዲሞክራት ሳይሆን እራሱን ዲሞክራሲ አድርጎ በህዝቡ ላይ እንደማዳበሪያ ሊበተንበትም
   - … ስብስቦቹ እውቀታቸውም ሆነ ሙያቸው ስልጣን ኮርቻ ላይ እንዲያቆናጥጣቸው እንጅ …
   - ፖለቲካቸው የጨለማ ጉዞም መሆኑን ስለማይገነዘቡ ሃገሬና ወገን የሚል ሁሉ እነዚህን ማስወገድ ….
   - ሕዝብም በጠ/ሚኒስቴር ሞት ቃል ሲገባ የጀመሩትን ዕቅድ ከዳር እናደርሳለን ሲል ….
   - እሾሆችም ሙያ ካላችሁ ከባለሙያ መፎካከር፤ ከተማራችሁ ከምሁራን መወዳደር፤ አዋቂም ከሆናችሁ ጥበብ ሰርቶ …..
   - ሃገሬና ወገኔ ለሚል ሁሉ መልዕክቴ እስከ አሁን እነሱ ያሰናከሉት ሕይወትም፤ ንብረትም፤ በጎ ስራም፤ ሰፊ ራዕይም ተወዳድሮ ማሸነፍም …..

   ልብ ይበሉ ዲያቆን ዳንኤል ያነሳው ስለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦታ ፣ ወይም የፖለቲከኞችን የጋራ ስምምነትና አንድነት ማፈላለጊያ ነጥቦች የተመለከተ አይደለም ፡፡ ከታሪክ ምሳሌው ጭምር የጠቀሰው ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነትና ስለአባቶች ስምምነት ነው ፡፡ የፖለቲከኞችም ስምምነት እግረ መንገዱን ቢገኝ እሰየው እንላለን ፤ ነገር ግን አሁን እኛን ያስጨነቀን የነፍሳችንና የሃይማኖታችን ጉዳይ ነው ፡፡ የታሪክ ተወቃሾችም ላለመሆን ፡፡
   ምነው ጽሁፍዎ ተደራራቢ ሃዘን የጎዳው ሰው ፣ ብሶቱን የሚገልጽ መሰለብኝሳ ?

   Delete
  7. Asmamawe ,anjeten newe yaraskewe... God bless you!!!!!!!!

   Delete
  8. የአቶ አስማማው አያሌው ጽሁፍ "የምታውቁትን ሳይሆን እኛ የምንነግራችሁን" በሚል ርዕስ በአይጋ ፎረም /http://www.aigaforum.com/articles/not-what-you-know.pdf/ ለፖለቲካ አቋማቸው መግለጫ ይሆን ዘንድና አሰላለፋቸውን ለማሳመር ካቀረቡት አምስት ገጽ ጽሁፍ ተቀንጭቦ ነው በዚህ ብሎግ የተለጠፈው ፡፡ ጸሃፊው ራሳቸው ወዲህ ለቤተ ክርስቲያንም አንድነት እንዲረዳን ያቅርቡት ወይም ሌላ ሰው በመልዕክታቸው ተደስቶ ለተቀረነው ወገኖች ለማስተላለፍ ያምጣው እግዜር ይወቀው ፡፡ ስለቤተ ክርስቲያን ችግርና መፍትሄ ሲቀርብ እንዴት የፖለቲካ አቋም እናነባለን ፣ በምንጻጻፈውም አልተግባባንም ማለት ነው በማለት ጭብጡን ወይም መስመሩን እንዲይዙልን ፣ በርዕሱም ላይ እንዲያተኩሩበት ያለዕውቀት ጫጭሬ ነበር ለማለት ነው ፡፡

   Delete
  9. አስማማው የሰጠው አስተያየት ሁሉንም ያቀፈ አስተያየት ነው፡፡ አስማማው በሳል ሰው ነህ፡፡ አመሰግንሃለው፡፡ ውጭ ያሉት ተቃዋሚ ነን ባዮቹ ሃሳባቸው ምን እንደሆነ አይታወቅም፡፡ ራዕይ የላቸውም እዚህ ጋ ፖለቲካ አጀንዳቸው ይሆንና ብዙም ሳይቆይ ደግሞ ሀይማኖት ይሆናል፡፡ መላቸው የማይታወቅ ቅዥቢዎች ናቸው፡፡ ይህን የሚሠሩት ደግሞ በሕይወታቸው ምንም የተረጋጋ ነገር የሌላቸው ሱሰኞች ናቸው፡፡ እዚህ ኢትዮጵያ ለሚኖሩት እናትና አባቶቻቸው እንኩዋን 100 ዶላር በወር የማይልኩ ብኩኖች ናቸው፡፡ ስለ ቤተክርስቲያናችን እንነጋገር፣ ይቅርታ እንጠያየቅ እንኳን ብንል መጨረሻቸው ውል የለውም ያለው መንግሥት ይውረድልን ነው የሚሉት፡፡ ሃይማኖት እና መንግሥት አንድ አለመሆናቸውን እንኳን ፈጽመው የማያውቁ በመላ ምት የሚኖሩ ምስኪኖች ናቸው፡፡ የጥፋት ወሬያቸውን ከማዝነብ የማይቦዝኑ፣ ኢትዮጵያኖች ከዳር እስከ ዳር በጠኔ አልቀዋል እራፊ ጨርቅም የላቸውም እያሉ የኢትዮጵያን መጥፎ ገጽታ ከመንገር እና ከማስነገር ውጭ ምንም ሥራ የሌላቸው፡፡ ወኔ የሌላቸው ባራክ ኦባማ የፈጣሪያቸው ያህል የሚያመልኩት “ እንምረጥህ፣ ግን የኢትዮጵያን መንግሥት አጥፋልን “ የሚሉ ውሾች፣ እንደ ውሻ ከመጮህ ውጭ ምንም እርባና የሌላቸው፡ በሱስ የተጠቁ ተስፋ ቢሶች፡፡ አላወቁም እንጂ ኢትዮጵያችን ድንጋይዋ ዳቦ የሆነበት ዘመን ከምንግዚው በላይ አሁን ነው፡፡ አለ ለኛ የተሻለ ነገር በአሁን ሰዓት፡፡ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገንና የጉልት ነጋዴዎች ሳይቀሩ የኮንዶሚኒየም ቤት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ከ13ዐዐ የአንድ ቀበሌ ነዋሪ ውስጥ 12ዐ ብቻ ናቸው የቀበሌ ቤት የመረጡት አቅማችን አይችልም ብለው ሌላው ግን የኮንዶሚንየም ቤት ነው የመረጡት ለምን ብትሉ ስለቆጠቡ ስላላቸው፡፡ ምስኪኖች እናንተ ናችሁ!! ሁልጊዜ ስድብ፣ የአገርን መሪ ማዋረድ፣ ለኢትዮጵያ ክፉ መመኘት፣ መራገም ሞያ መስሎአችሁ ነው ግን አላዋቂነት ነው፡፡ የጥቁር ራሱስ እሺ መቼም የአለም ሰው ነው በሱስም የተጠቃ ነው ነገር ግን አባቶቻችንስ ለምን አትመለሱም እስቲ የአብራካችሁ ክፋይ የሆነው፣ በደጀ ሰላም ያደገው ልጃችሁን ዳንኤልን እንኳን ስሙት እስኪ ምን ብትጣሉ ወደ ገዳማችሁ ትሄዱ ነበር እንጀ አሜሪካ ሄዳችሁ የእንቅልጥ ኑሮ እየኖራችሁ ቤተክርስቲያናችሁን ለምን ታውካላችሁ፡ እዚሁ ሆናችሁ ኢትዮጵያዬ ብረሳሽ ጉሮሮዬ ከምላሴ ጋር ይጣበቅ ምነው አለማለታችሁ፡ ስደት ወደ ገዳማት እንጂ ወደ አውሮፓና አሜሪካ ነው እንዴ ወይ አልተማራችሁ እስከ ፒኤችዲ አልደረሳችሁ ምንድነው ጥቅሙ ከውሾቹ ጋር አብሮ ሆይ ሆይ ማለቱ ኧረ ይብቃ ይብቃ ይብቃ፡፡

   Delete
  10. seriously arif yehone asteyayet newe asmamaw ena wendeme yesetehewe asteyayet.ager wedade malet yehe newe

   Delete
  11. Dear Dn. Daniel, thanks for your nice advice and opinion regarding the peace and unity of our church. God bless your effort aboundantly!!!!!!!!! May God bless you with long longgggggg life and talent!
   Mr. Asmamw and his supporters 'Fiyel wedih kizimzim wediya.' Ale Yagere sew.
   For God sake, is there a single word or line about politics here? Please try to come back to a healthy thinking. What we read here and bothering us currently is the situation of our church. If your sorrow is beyond crazyness about the death of our PM, it is a will of God, accept it and I think we all do. God has a reason for doing so. Please leave Daniel alone, at least try to read and comment related issue than rushing emotionally.

   Delete
  12. በ AnonymousSeptember 20, 2012 11:08 AM ለተጻፈው ጽሁፍ መልስ::
   የጦማሩ መልዕክት ሌላ ሁኖ ሳለ ወደፕኦለቲካ ለምን እንደገባህ አይገባኝም:: ለመሆኑ ይህን የጡመራ መድረክ የምታየው ነገር ለማሽተት ነው ወይስ ለመማማር?

   ወንድሜ ያያሉ አያስተውሉም ይሰማሉ ግን አያዳምጡም ከሚባሉት ሰዎች አንዱ መሰልኸኝ:: ከ1300 የአንድ ቀበሌ ሰዎች ውስጥ 120 ዎቹ የኮንዶሚኒዬም ቤት መምረጣቸው በ ኢትዮጵያ የአቅመ ቅንጦት ኑሮ መኖር መጀመሩን እንደማሳያ የተጠቀምኸው ወዳጄ:: ለመሆኑ ከነዚህ ሰዎች ውስጥ ሩቡ እንኳ የቀበሌ ቤት እፈልጋለሁ ብሉ ቢያመለክት ማግኘት ይችላል? የቀበሌ ቤት የመረጡትስ ያመረጡትን አገኙ? ኮንዶሚኒየም ቤት የደረሳቸው ሰዎችስ የሚከፍሉትን ከፍያ እነዴት እንደሚያገኙት ታውቃለህ? አዎ አንድም አከራይተው አለያም ሸጠው እንደሚያተርፉበት ሳታውቅ የቀረህ አይመስለኝም:: በ አ.አ. ስንት ነዋሪ ነው በኪራይ ቤት ብቻ በርካታ ቤተሰብ እያስተዳደረ ያለው? አመንህም አላመንህም ይህች ከተማ ያከራዮች ከተማ እየሆነች ነው:: ቤት እና ህንጻ ሰርተው በማከራየት ብቻ የሚኖሩ ዜጎች እየተበራከተ በሄደ ቁጥር ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት ያልቻልህ ሰው ሌሎችን ለመውቀስ ከመሮጥ ለቀረበው ጦማር የሚበጅ አስተያየት ብትሰጥ መልካም ነበር:: ለችግሮቻችን መፍትሄ አካል መሆን ለችግሮቻችን ምንጭ ከመሆን ለህሊናም ጥሩ ነውና::

   Delete
  13. asme betam tilk sewe akeberekuh.

   Delete
  14. ena betam yemgermegne andand swoch ye hezbune dhenet becha setaweru hezbu tlowachu eyalfe newe,mechersha laye rasachune Deha honachu tagegnutalachu.......yane akwamachu like endalneber lemerdat kelal newe......

   Delete
  15. Endihu sasibewu egna ethiopianoch berasachin lay chigirin, siqayin yeminabeza yimesilegnal. wana wusanewoch lay Emenetachinin anasqedimim. lela amarachochin ayinachin yifelgal. Lemin?

   Eris berasachin enimamar. Be-sewu lemfired anichekul. adera.

   Delete
  16. My dear and innocent brother Dn. Daniel Kibret, I would like to appreciate your effort to bring peace in the church. But are that innocent for knowing that the churches in diaspora are under the control of the toxic oppositions? How could our fathers living in U.S.A monastery have a courage to bring peace in the church? Because they are under the influence of these people.Actually these people have been contributing a lot for making their monastic life luxurious.So they won't say yes unless those people follow them where ever they go, but those people have no right to enter to Ethiopia. Though I don't have doubt that these people won't come to an agreement, I do believe that God could make the impossible ,possible.May God open their blind eyes.

   Oslo

   Delete
  17. Mr.Asmamaw Ayalew, what the hell with you? Can't you read? can't you understood ? You totally miss the over all concern of Dn. Daniel Kibrets' title. You totally merge politics with our church.It shows me how much you are hunger of politics. please before you wrote any thing you should have to understand what he wants to say. Period!

   Delete
  18. Great comment asme.God bless you

   Delete
 3. አንድ ትውልድ በመለያየቱ ግንብ ውስጥ ተወልዶ አድጎ፣ ለወግ ለማዕረግ በቃ፡፡ አይበቃንም? ለመሆኑ ስንት ትውልድ ማለፍ አለበት?
  ከንቱና አላፊ ምሆናችንን አስበን ስለመጭው ትውልድ ብለን እንሸነፍ እባካችሁ እባካችሁ እባካችሁ ... እስከመቼስ የአህዛብ መሳለቂያ ታደርጉናላችሁ?

  ReplyDelete
 4. አሁን ያለዉ የቤተ ክርስቲያን ችግር ያሳሰበህ አልመሰለኝም:: አስሜ

  ReplyDelete
  Replies
  1. አሁን ያለው የቤተክርስቲያን ችግር ምን ድነው መለያየት አይደለምን?
   እግዚአብሔር ማስተዋሉንና ጥበቡን ያድለን
   ዳኒ እግዚአብሔር ያበርታህ

   Delete
  2. My message was to Asmamaw

   Delete
 5. Girum selam amelakach mefetehe new Wgziabher yibarkih, yihin hasabihin degimo lelochu bebego endiyayut yadergachew.....Amen

  ReplyDelete
 6. These are marvellous points that lead to the ultimate solution. But it may be 'unthinkable' for those who manipulate the church for their own personal benefits, who are power thirsty, and who are closed minded, to benefit from them. Let's get ready to cut off them from our church if they don't change their mind. Tnx

  ReplyDelete
 7. ahun yelebene tenagerk

  ReplyDelete
 8. It is a nice idea! may God be with us!

  ReplyDelete
 9. Yihuna!!!አንዱን ወዳጄ ጀርመን ደርሶ መጥቶ እንዴት ነው በጀርመንና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ልዩነት ብዬ ብጠይቀው ተስፋ ያስቆርጣል ነው ያለኝ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ኸረ ከጀርመን ጋር መወዳደሩ ቀርቶብን እንደው ሰላም ያለበት፤ ማጭበርበር ያልበዛበት፤ ፍቅር ያለበት፤ በጣም ብዙም ባይሆን ትንሽ ስልጣኔ የገባው፤ (ምክንያቱም አወቀች አወቀች ስትባል እንዳይሆንብን ብዬ ነው) የየዋህነት ኑሮ መኖር በቻልን እኔ በበኩሌ ደስተኛ እሆን ነበረ

   Delete
 10. Thanks for your reaction on the Issue.On the paper it is ok.Well done so the next step is for our Fathers to progress and do their part for Unity.

  ReplyDelete
 11. አንድ ትውልድ በመለያየቱ ግንብ ውስጥ ተወልዶ አድጎ፣ ለወግ ለማዕረግ በቃ፡፡ አይበቃንም? ለመሆኑ ስንት ትውልድ ማለፍ አለበት?

  Thanks Daniel, hope the responsible church members will throughly think about all the issues mentioned above.

  Amilak yirdan,

  ReplyDelete
 12. egege betam tru amelekakete nwe yeselam amelake esu yerdan!!!

  ReplyDelete
 13. Egziabhare lehulachinim yemintazezebetn leb yesten kehulum belay metazez melkam newuna

  ReplyDelete
 14. በቅድሚያ ለዲ/ን ዳንኤል ቃለ ሕይወትን ያሰማልን። ምን ነካን? የተጻፈው ጽሑፍ ስለ ቤተክርስቲያን አንድነት እንጂ ሰለሌላ ነገር እንዳይደል በሚገባ እየተረዳነው ነገሩን ከፖለቲካ ጋር ማያያዙ ለምን አስፈለገ? የሚሰጡት አንዳንድ አስተያየቶች ከዚህ የጦማር ርዕስ ለቀው የወጡ ከመሆናቸውም በላይ ግላዊ ጥላቻን አጉልተው የሚያንጸባርቁ ናቸው። ቤተክርስቲያን ተከፍላለች፣ አንድ ትሆን ዘንድ ምን መደረግ እንዳለበት የመፍትሔ ሃሳብ ቀረበ እንጂ ሌላ ምን ተባለ? እግዚአብሔር ስለ ቤተክርስቲያን አንድነት የምናስብበት መልካም ልብን ለሁላችንም ይስጠን!

  ReplyDelete
 15. የሰላም አምላክ ይርዳን፡፡ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 16. ለተፈጠረው ችግር የተወሰኑ ግለሰቦችን፣ አካላትን ወይም የታሪክ አጋጣሚዎችን ብቻ እየኮነንና እያወገዝን ከምንጨቃጨቅ፤ ሁሉም ራሱን ነጻ ለማድረግም ከሚረባረብ ‹‹የበደልነው ሁላችንም ነን፤ የተበደለውም እግዚአብሔር ብቻ ነው›› ብለን አምነን ሁላችንም ሁላችንን እና ሁላችንም እግዚአብሔርን ይቅርታ ብንጠይቅ፡፡ እግዚአብሔር የሃሳብ መራራቃችንን ወደ አንድ መንገድ ይምራን

  ReplyDelete
 17. ከወ/ት መስከረም

  አማራጭ መፍትሄ ማሰብ ሳይሆን ሰው የሚያስበውን መየት ለማይፈልጉት፥ አምላክ ሆይ መልካሙን ያስተውሉ ዘንድ፣ ጥሩውን ይሹ ዘንድ፣ ወደ ልቦናቸው ተመልሰው ተስፋቸውን ባንተ ላይ ይጥሉ ዘንድ እንለምንሃለን።
  ወንድሜ ዳንኤል በርታ

  ReplyDelete
 18. "...ነገሩ እንደሚጻፈው ያህል ቀላል አይደለም፡፡ ነገር ግን ላመነ ሁሉም ይቻላል ለምንል ክርስቲያኖች ዓለም ከዚህ በላይ ይጠብቅብናል.."

  ለተፈጠረው ልዩነት ሁላችንም አስተዋጽዖ አድርገናል፥ ወደ እግዚ አብሔር ከመጮህ ይልቅ ከሁለቱ አንዱን ስንወቅስና ስናወግዝ ተገኝተናልና፡፡ ታዲያ ለዚህ ሁላችንም ንስሃ አያስፈልገንም ትላላችሁ?
  ከት.ም

  ReplyDelete
 19. Dani,

  If you really want/think this is good and you are a true chirstian, start first with you and your followers in north America. They are the main cuases for widening the gap. I will do my part too. By the way your writtings sprit from Ethiopia and abroad are different.

  ReplyDelete
 20. Dear Danny!
  This is blessing idea. Please forgive me for the last my harsh(hatred)comments.Because I was constantly being annoyed with ruling style of the late patriarch for the decades

  ReplyDelete
 21. በቅድሚያ ለዲ/ን ዳንኤል ቃለ ሕይወትን ያሰማልን። ምን ነካን? የተጻፈው ጽሑፍ ስለ ቤተክርስቲያን አንድነት እንጂ ሰለሌላ ነገር እንዳይደል በሚገባ እየተረዳነው ነገሩን ከፖለቲካ ጋር ማያያዙ ለምን አስፈለገ? የሚሰጡት አንዳንድ አስተያየቶች ከዚህ የጦማር ርዕስ ለቀው የወጡ ከመሆናቸውም በላይ ግላዊ ጥላቻን አጉልተው የሚያንጸባርቁ ናቸው። ቤተክርስቲያን ተከፍላለች፣ አንድ ትሆን ዘንድ ምን መደረግ እንዳለበት የመፍትሔ ሃሳብ ቀረበ እንጂ ሌላ ምን ተባለ? እግዚአብሔር ስለ ቤተክርስቲያን አንድነት የምናስብበት መልካም ልብን ለሁላችንም ይስጠን!

  ReplyDelete
 22. pleas give us the current situation (information) of waldeba monastery

  ReplyDelete
 23. በቅድሚያ ለዲ/ን ዳንኤል ቃለ ሕይወትን ያሰማልን። ምን ነካን? የተጻፈው ጽሑፍ ስለ ቤተክርስቲያን አንድነት እንጂ ሰለሌላ ነገር እንዳይደል በሚገባ እየተረዳነው ነገሩን ከፖለቲካ ጋር ማያያዙ ለምን አስፈለገ? የሚሰጡት አንዳንድ አስተያየቶች ከዚህ የጦማር ርዕስ ለቀው የወጡ ከመሆናቸውም በላይ ግላዊ ጥላቻን አጉልተው የሚያንጸባርቁ ናቸው። ቤተክርስቲያን ተከፍላለች፣ አንድ ትሆን ዘንድ ምን መደረግ እንዳለበት የመፍትሔ ሃሳብ ቀረበ እንጂ ሌላ ምን ተባለ? እግዚአብሔር ስለ ቤተክርስቲያን አንድነት የምናስብበት መልካም ልብን ለሁላችንም ይስጠን!

  ReplyDelete
 24. ውድ ወንድማችን የሚፃፍ ሁሉ ገሀድ ቢሆን እንዴት አይነት አለም ውስጥ ነበር የሚኖረው።በዚህች ጥንታዊት ቤተክርስትያን ውስጥ ያለውን እሰጣ ገባ ከብዙው በጥቂቱ በይቅርታ ጠቅልለህ የተሰማህን ብለሃል ደግ ነው፡ከይቅርታ ባይነት በላይ ምን አለ?ለፍቅር ቋንቋ አቻ አለው እንዴ ብቻ ምን ይሆናል ማንበብ እንጂ መነበብ የማናውቅ ሆነን በዘመነ ምህረት ባቢሎናዊያን ሆንን፤ብዙ ቀመር አይሻም የተማረም ያነበበም ያረቀቀም የረቀቀ ባለፀጋውም ባለጤናውም ወደ ይቅታ ሲመጣ ያኔ የሚፃፍ ይኖረናል፤....እስከዚያው ግን “የአህዛብ መተረቻ የአጋንንት መዘበቻ አታድርገን፤”በሚለው የቆየ ቢሂል እናዚም።ምኞቴ ብዙነህ ከፍሎሪዳ ጫካ

  ReplyDelete
 25. May God give us Love!!! I like the way u closed it...የሰላም አምላክ ይርዳን፡፡ አሜን፡፡ and the picture too. When u write spritual articles you have to close it like this, unlike ገለልተኞች ሆይ የት ናችሁ? of the previous. የሰላም አምላክ ይርዳን፡፡ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 26. Dani thank you for your second thought and paying attention on the big picture.In the past you were one of them trying to blame our fathers in exile for all the divisions in chifin tilacha. Many of your writings in your blog and personal chat to us well documented the fact about it. You should work hard to make it up. I give you credit for this article. Keep it up! In the end hulu kentu new. Le tewled yemitekem sera serto malf gin teleq tsega new. Some leaders wasted their time on the wrong way. You should be accountable and resposible to yourself for what you write and say.Always remember God!True justice is from Him.
  Thank you for posting my opinion.

  ReplyDelete
 27. Bemejemeria egna Saniwodewu Qedimo Lewodeden Amlakachin Misgana Ydiresewu.

  Diacon Daniel, hasabhin Silakafelken ameseginalehu. asteyayete endemiketelewu newu. Ene yalehut be wuch ager new. Ezih silalut kirstian wogenoche metenegna ginizabe binoregnim, gin sile-rase bicha newu ergitegna hogne menager yemichilewu. Wuch ager Eminetin yaqorequzal. fetena newu. Fez yibezal . Kentu alemin yishetalina des ayilim. ezih blog metiche astemari tsihufochin, bego asteyayetochin saneb- enkuanis endih aynet wogen noregn, ewunetin tenagro ewunetin yemiasasib, elalehu. Edilegnam endehonk yisemagnal mikniyatum Egziabherin enanite bafeleqachihut hasab wust ayewalehuna. Min albat agre bihon noro Endezih bidereg melkam newu , enideza degmo ayderg biye be-mulu lib sile-ewunet betenagerku des balegn.
  Chigirum meftihewum egnawu ga newu.
  Esu Yirdan.

  ReplyDelete
 28. ዘሪሁን ጎሳዬSeptember 22, 2012 at 4:36 PM

  የሀገራችን ተቃዋሚ ኃይሎች እጅግ በጣም የተበጣጠሳችሁ፣ እርስ በእርስ የማትተማመኑ፣
  በአጭር ጊዜ ተሰባስባችሁ ደግሞም በሣምንታችሁ መበታተናችሁ፣ የፖለቲካ ሥልጣን የጥቅም ምንጭ
  አድርጋችሁ መቁጠራችሁ (ሁላችሁንም ማለቴ አይደለም)፣ የተቃዋሚው ፓርቲ አመራር መሆንን እንደ ዝና
  የምትቆጥሩ፣ በየአደባባዩ እርስ በእርስ የምትዘላለፉና አለፍ ሲልም በቆመጥ ስትናረቱ የምትታዩ፣
  በተናገራችሁበት የማትፀኑ መሆናችሁ የአደባባይ ሚስጥር ነውና፡፡ ይህ የሥነ ምግባር ጉድለታችሁ
  ስብዕናችሁን ክከፉኛ የሸረሸረው በመሆኑ ሕዝቡ በእናንተ ላይ አመኔታ እንዲያጣ አድርጎታል።
  እናንተም ይህን ከጋራ የገዘፈ ችግራችሁን በመገንዘባችሁ ይመስለኛል ሥልጣንን ከምርጫ ከኮሮጆ ከመጠበቅ
  ይልቅ አቋራጭ መንገዶችን(like danielkibret & negative diaspora)ማማተርን ሥራዬ ብላችሁ የተያያዛችሁት፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ጠቢባን ሆይ ስትጽፉ ለምን ዲያቆኑ የተነሳበትን ጭብጥ ትለቃላችሁ ? ብሶትና ብስጭት እንደተሸከማችሁ ከአገላለጻችሁ ይታወቃል ፡፡ ነገር ግን የዲያቆኑ ጽሁፍ ከነምሳሌውና ፖስተሩ ሁሉ የሚያሳየው ስለ ቤተ ክርስቲያን ነው ፡፡ በግሉ ሊያስኬዱ ይችላሉ ፣ የቤተ ክርስቲያንንም አንድነት ለመፍጠር ያግዛሉ ያላቸውን አስተያየቶች አስነብቧል ፡፡ ታድያ የአቶ ዘሪሁን የተለየ አማራጭ መንገድ የትኛው መሥመር ላይ ተገለጸ ፡፡ ወይስ የክረምት ዝናም ስለዘነመ ፣ ሰማዩም አለቀሰ ፤ ማለትም እግዜር ጭምርም ስለሞታቸው አለቀሰላቸው የሚል የደናቁርት ልፈፋን ሊያስተምሩን እየዞሩን ነው የተጭበረበረ የምርጫ ኮሮጆን ታሪክ ያነሱብን ? ወይንስ ቤተ ክርስቲያንም ሳናውቃት የፖለቲካ መድረክ ሆና እያገለገለች እንደ ነበር እያረዱን ነው ?

   Delete
  2. i never see Dedeb like Betsue kkkkkkk

   Delete
  3. Please change your name: It doesn't describe you.

   Delete
  4. Anonymous September 24, 2012 11:35 AM
   i never see Dedeb like Betsue kkkkkkk

   መልስ፡- ለእኔ ደደብ የሚባለው በድንቁርና ያለ የጨለማ ሰው ፣ የተጻፈ የማይገባውና ርዕስ ስለምን እንደሚናገር እንኳን የማይረዳው ፣ ሲበሳጭና ሃቁ ሲነገረው ደግሞ እንደ ባህር ማሽላ የሚፈካና ወይም የሚስቅ ፣ ሰማያዊውን ሲያወሩት ከምድራዊው ጭቃ አስተሳሰብ ላለመውጣትና ላለመላቀቅ የተለያዩ ማሰናከያ ምክንያቶችን የሚደረድረው ደካማ ነው ፡፡

   Anonymous September 24, 2012 11:54 AM
   Please change your name: It doesn't describe you.

   መልስ፡- የጨለማው ሰው ፣ የአንተ ስም ነው መጥፎ መንፈስ መሆንክንና የተንኰል ሥራህን የሚገልጸው ፡፡ ራስክን ሸሽገህ ሰላም እንዳይፈጠር ፣ በስውር ጥላቻን ፣ ከተጻፈው የማይስማማ ሃሳብ የምትዘራው ፡፡ ለብጹዕነታችን ተስማሚ የሚሆነውማ ለቤተ ክርስቲያናችን አንድነትና ሰላም እንዲፈጠር ሸራችሁን መግለጣችንና አንድነትንና ስምምነትን መደገፋችን ነው ፡፡ በተረፈ ስም ያለው ከመቀየሩ በፊት ስም የሌለው ቢያንስ አንድ ስም ያግኝ እላለሁ ፤ እኔ የራሴን ጥቅም ብቻ የማስብ ስግብግብ አይደለሁም ፡፡ ስም ከሌለህ ለመለጠፍ ችግር የለብኝም ፡፡ ክርስትና ባላነሳህም ጠይቀኝ ለምግባርህ የሚስማማ ይሰጥሃል ፡፡

   Delete
  5. It is obvious, unquestionable, Bitsue is dedeb, addicted and homeless diaspora who is living on the street of USA. I understand all these from your comments.

   Delete
  6. ለባለዚህ አስተያየት Anonymous September 26, 2012 9:10 AM
   "It is obvious, unquestionable, Bitsue is dedeb, addicted and homeless diaspora who is living on the street of USA. I understand all these from your comments."

   አየህ አያ ጣፊ በአእምሮህ የማትጠቀም ፣ የማትረባ ደካማ መሆንህን ራስህ እየመሰከርክልኝ ነው ፡፡ ሰዎች የሚሉትንና የሚጽፉትን ቃላት ስለ ሰማህና ስላወቅህ ብቻ ቃላቶችን ማንነቱንና ምንነቱን በማታውቀው በአርአያ ሥላሴ በተፈጠረው በብጹዕነታችን ሰውነት ላይ ሠነዘርካቸው ፡፡ የራስክን ሥራና ፍርድ መለስ ብለህ መመልከት ብትችል ደደብ ማን እንደሆነ ሰው ሳይነግርህ ራስህ ትለየው ነበር ፡፡ የሰው ደካማነቱ ውስጡን ለማየት አለመቻሉ ነውና አልፈርድብህም ፡፡

   አንድም ቀን ያልተቆነጠጠና ያልተገራ ፣ ጐዳና ላይ ተወልዶ ጐዳና ላይ ያደገ የሰው እረኛ ይምስል ፣ ባህልና ወግ የለሌለው ስድ ፣ ያደገበትን ባህርይ በየሥፍራውና በየምክንያቱ እንደሚያስተዋውቅ ምናምንቴ ዓይነት ቃላቶችህ ሁሉ ክብረ ነክ ሆነውብኛልና ትንሽ ቀነስ አድርጋቸው ፡፡ ታውቃቸው ቢሆን እኒህ ምናምንቴዎች የሚሏቸው ብዙ መገለጫዎች አሏቸው ሲሉ ሰምቻለሁና ፤ እንዲያው ለምናልባቱ ማለቴ ?

   ትንሽ ከንፍጥ የተረፈች የምታስብ ነገር በጭንቅላትህ ውስጥ ካለችህ ፣ ሱሰኛና በኑሮው የተጐሳቆለ ፣ የጐዳና ተዳዳሪ የሆነ ሰው ስለ ሃይማኖትና ቤተ ክርስቲያን አንድነት ምን አግብቶት ሃሳብ ይሰጣል ብለህ ትገምታለህ ? ከኑሮው ይባስ በድራግ ደንዝዞ ሳለ መችና እንዴት የሚያስብ ሆኖ አገኝተኸው ነው የያሳድግልኝ ምርቃትህን የደረደርከልኝ ? ስለዚህም ግምትህ ሁሉ ስህተት ይሆናል ማለት ነው ፡፡

   በተረፈ እንዲያው እንዳልከው በሰው አገር ጐዳና ላይ የምንገላታ ደደብ ፣ ሱሰኛና ሌላም ፣ ሌላም ሆኜ ብገኝ እንኳን ጥፋተኛው እኔ ሳልሆን ለዚህ ያበቃኝ የተበላሸው ሥርዓትና አመራሩ እንደሆነ መገመትና ማሰብ ነበረብህ ፡፡ ምክንያቱሳ ብትለኝ ሃገሬ ላይ የተመቻቸ ዕድልና ነጻነት ቢኖረኝ ስደትን አልመርጠውም ነበርና ነው ፡፡ ለመሰደድ ያበቁኝ ደግሞ የእነ ስም አይጠሩ ምክንያት ብዙ ስለሚሆኑ ፣ ይኸው ዛሬ እንደምታነብልኝ እኔ ነጻ ሆኜ ፣ ጐምላላው የልቤንና ያሰብኩትን ያለ ይሉኝታ ፣ ከመጣልኝ ሰለእነርሱም እጽፋለሁ ፡፡ አንተ ግን የተቀየድህ የውሽማ ያህል እሥረኛቸው ስለሆንህ አንድ መስመር እንኳን እነርሱ ከሚሉት ውጭ ዝንፍ ማለት አትችልምና ችግርህ ገብቶኛል ፡፡ እግዚአብሔር እንደእኔው ለነጻነት ቢያብቃህ አምላኬን እለምንልሃለሁ ፡፡
   በተረፈ እግዜር ይርዳህ

   Delete
  7. ብፁዕ ለተሰጠህ አንድ መስመር ኮሜንት ይህንን ሁሉ መልስ የምትጽፈው የሚያሳየን እውቀትህን ወይም የሥነ ጽሑፍ ችሎታህን ሳይሆን ሥራ ፈት መሆንክን ነው፡፡ ደግሞስ ጎምላላው ነው ያልከኝ ? ቂ ቂ ቂ ቂ ቂ ምነው ጃል ከልቤ አሳቅከኝ፣ የአንተ አይነቱ ቤት አልባው አይደለም እንዴ በሰልፍ አንድ ትልቅ በርገርና የቆርቆሮ ኮካኮላ በቀን ሶስቴ የሚመገበው፡፡ በርግጥ እነዚህ ጃንክ ምግቦች ሰውነት ያዳብሩና ያጎማልሉ ይሆናሉ (ብዙ በሽታዎች ታሳቢ ሆነው ማለት ነው)፡፡ ምስኪን ወንድሜ ወደ አገርህ ግባና በኮብል ስቶኑም፣ በጥቃቅንና አነስተኛም ቢሆን ተደራጅተህ የሰው አገር ውሻ ከመሆን የእናት አገርህ ኩሩ ደሀ ብትሆን ይሻልሀል፡፡ የሰው ወርቅ አያደምቅ አሉ እማማ ጥሩ አይነት፡፡ ከዚያም አልፎ የቀኑን ሱስ ለማርገብ በአበሻውም በፈረንጁም መንደር መለመን ነው፡፡ ለምን ንገሩኝ ባይ ትሆናለህ፡፡ ይልቅ ዛሬም አልመሸም አገርህ ግባና በነጻነት ከትናንሽ እስከ ትላልቅ ሥራዎችን ሠርተህ የጤፍ እንጀራ በሽሮ በልተህ ተመስገን ብለህ በሰላም ብትኖር ይሻልሀል፡፡ የሠላም አየር ተንፍሰህ በአገርህ ኑር ማንም አይከለክልህም፡፡

   Delete
  8. ወንድም እንደ ወንድወሰን ከፎቅ ልትወረውረኝና የፍቅርህን መግለጫ ልታወጣ ወይስ በጠርሙስ አናቴን ብለህ ልትገላግለኝ አገር ግባ ብለህ የምትወተውተኝ ? በል ስለ ሃይማኖትና ቤተ ክርስቲያን አንድነት መወያየቱን ትተን ሌላ ርዕስ ካመጣህ ምን እየተመኘህልኝ እንደሁ ካላስተዋልከው ልቁጠርልህ

   - ሃያ እና ዓመት የተማረውን የኰሌጅ ጥበብ ወደ ጎን አድርጎ ድንጋይ መኰልኰልን ነው ፡፡ ይኸ አካሄድ በአገር ኢኰኖሚ ላይ ምን ያህል መቀለድ መሆኑ ጠፍቶህ ከሆነ አንድ ህጻን ልጅ ማንበብና መጻፍ እስኪችል ድረስ ስድስት ዓመት ለማስተማር የሚፈጀውን ወጭ ብቻ አስበው /መደመር ከቻልክ/ ፡፡ የተማረውን ማኀበረሰብ ሞራል አላሽቆ ትናንሽ ነጋዴና ወዝ አደር እንዲሆን በእጅ አዙር ማስገደድ ፣ በእርግማን ካልሆነ በስተቀር በቀናነት የሚመጣ የዕድገት አቅጣጫ ስላልሆነ አልቀበለውም ፡፡
   - እንግሊዝኛ ተናጋሪ የጐዳና ኮረዳ ማፍራት ፤ ይኸም በዘመናችን ከዕድገት እንደ አንዱ ስለተመዘገበ ጻፍኩት እንጅ አልተነተንኩትም
   - ባለጊዜ ሰዎች የሚመገቡትን የጤፍ እንጀራ /ኩንታል 14ዐዐ - 18ዐዐ ብር መግዛት የሚችሉ ሃብታሞች/ ፣ ጮማና ውስኪ በቴሌቪዥን መስኮት እየተመለከትክ ፣ አንተ የበላኸው ያህል እየተደሰትክ መቀመጥ ፤ እነሱ የለበሱትን ፣ የሚያሽከረክሩትን መኪና የገነቡትን ህንጻ እያየህ አደግሁ ብለህ አንተ መለመኛ ዘንቢልህን ይዘህ በየአደባባዩ መጉላላት
   - በተረፈ የኢንተርኔት ችግርህንና የዕውቀት ጥበትህን ለመደበቅ ሠራተኛ ነኝ አትበለኝ ፤ ጫት ቤት መደብ ፈልገህ ተጐልተህ መክረም ፣ ማምረት እንዲመስልህ ተደርገህ ደንዝዘሃልና መሥራት ምን እንደሆነ ገና አልገባህም ፡፡ የእኔ ሥራ ፈት መሆንና ለአንተ ምስኪን ወገኔ አጥጋቢ መልስ መስጠት ፣ ቢያንስ የኩረጃ ቃላትንና ጉራህን እንድቃቆምና በአማርኛችን እንድትጽፍ ማድረግ አስችሏል ፡፡

   ስለዚህም ሁሉ እንኳንስ የፈረንጁ ሃምበርገርና ኮካ ፣ የአበሻውም ኮቸሮና ቂጣ ቅራሪውም ሁሉ አሮብሃልና ያለንበትን ምድራዊ ገነት አታናንቅ ፡፡ በአሜሪካ በሙሉ ነጻነቱና መብቱ የሚንጎራደደውን ጐምላላ ፣ እንደ እኔ ሳይሠራ ተኝቶ የሚበላውን ባለበረከትና ጸጋ ፈልሳሳ ፣ የሰው ፍጥረትን ሳይሆን ፣ የተጣለው ውሻቸው ያለው ዕድል ቢገጥምህ እንኳን ፣ አንተን ለመሰለ መንገደኛ ትል ቅ መሻሻል ፣ እድገትና እመርታ ፣ ቤተ መንግሥትም የገባ ያህል እንደሚጨፍር እርግጠኛ ነኝ ፡፡ እንደ ዕቃ ሆነህ ለጌቶችህ እንዳሉህ እያጎበደድክ ፣ ከየሆቴል ቤት የእጅ ጥራጊና ትርፍራፊ እንጀራ ተሰልፎ በጉርሻ ከመለቃቀም ፣ ሰው መሆናችንን ተገንዝበን ፣ ነጻነትን ለተጠማን ምሩቃንና ቆራጦች ንጹህ ውሃና በረንዳውም ቢገኝ ስለ ሰብዓዊ መብትና የሰው ልጅ ክብር ሲባል ይመረጣል ፡፡

   የያዘህ ውቃቤ ያስጓራህ እንደሁ ለማየት ደግሞ ፣ እስከ አሁን አንተ ባለቀኑንና ተጠቃሚውን ወንድሜን ለማስታመምና ላለመጉዳት ስል በመጨነቅ ፣ ለቃላት አጠቃቀሜም ጥንቃቄ ለማድረግ ስል እንትን ይመስል ፣ እንትን ዓይነት ፣ እንትን የሚሏቸው ፣ የእንትን ያህል ብዬ ያስቀመጥኳቸው ሽፍን ቃሎች በሙሉ ከአሁን ጀምሮ አንተው እራስህ መሆንክን ተረዳው ፤ እስከ ዛሬ ይኸን የመሰለ ተናግሮ አናጋሪ አጋጥሞኝ አያውቅምና ቢጤህንና አምሳያህን አላገኘሁልህም ፡፡ የኛ አገር ወዳድ ሽማግሌ ፣ ምን ምን እንደጻፍኩ አልገባህ ከሆነ ወጣ ብለህ ድገመው ለጸሎት ጭምር ይሆንሃል ፡፡

   ኡህ ፣ ወንድም አሁንም ያረፈና የተደላደለ ስሜቴን ቀስቅሰህብኝ ሳላውቅ አበዛሁብህ ፣ ቀስ እያልክ ፣ እያረፍክ አንብበው ፡፡ ማንበብ ካቃተህም እንደ ፊደል መማሪያ ይሁንልህ ፤ ኋላ ትረዳዋለህ ፡፡

   ብልሆችና ጨዋዎች ለሁሉም ነገር ለከት እና ገደብ ያበጁለታል ፡፡ አህያ ይመስል ሁሌ ሲራገጡ አይኖሩም ፡፡ የያዘውን የማይለቅ ጅል ብቻ ነው ፡፡ ከነተረቱ ቁም ነገር ላይ ስለማይገኝ ጨዋዎቹ ጅል አይሙት እንዲያጫውት እንላለን ፡፡ ምክንያቱም እማዬ ብሎ ማልቀስ ከጀመረ መቋጫና ማቋረጫ የለውም ፡፡ በምታምነው መቀጠል ትችላለህ ፤ ብታስከፋኝም ጸሎቴን ግን አልተውብህም ፤ እስከወዲያኛው ሰላም ሁንልኝ ፤ ጊዜ ያስጐነበሰህና የጣለህ ወገኔ በመሆንህ ክፉህን አልመኝም ፡፡

   Delete
  9. አይ ወንድማለም ደጉ፡፡ ውስጥህን መጉዳቴ ታውቆኛል፡፡ በስደት ያለን ሰው እንዲህ መሳደቡ ትክክል እንዳልሆነ ተሰምቶኛል፡፡ በቁስል ላይ እንጨት ስደድበት ወይ ኮምጣጤ ድፋበት ሆነብኝ፡፡ ስለዚህ ለሺህ ፍልጥ ማሰሪያው ልጥ እንዲሉ ይቅርታ መጠየቅ ፈለግሁ፡፡ ይቅርታ አድርግልሀኝ፡፡

   Delete
  10. እግዚአብሔርን ስላደረገውና ስላሳየኝ መለወጥ ሁሉ ለማመስገን ተመልሼ መጥቼአለሁ ፡፡ ስለምን ብትለኝ ጸሎቴን በቶሎ ሰምቶ ወደ ሰውነትህ መልሶ እንደሰው እንድታስብና እንድትጽፍ ስላስቻለህ ነው ፡፡

   የእኔ መጣጥፍ መነሻ የሆነው ፣ አንተ ምናልባት በፍርሃት መግለጽ ያልደፈርከውን ብሶት ፣ እንዳወጣልህና እንዳስነብብልህ በመፈለግ የቆሰቆስከኝ ስለመሰለኝ ጠቋቆምኩት እንጅ ፣ ወንድሞቼና እህቶቼ ፣ ወላጆቼና ልጆቼ የሚሆኑት ወገኖቼ /የቀይ ባህርን ዓሣ ፈርተው የተቀመጡ ዘመዶችም ስላሉኝ ጭምር/ በሚያሳልፉት የዕለት ተዕለት የኑሮ ትግል ለመሳለቅ ፈልጌ አይደለም ፡፡

   ወንድሜ / እህቴ መረዳት ያለብህ ይኸ ይቅርታ የመጠያየቅና ይቅር መባባል በክርስትናችን እንዲያ ስልም ደግሞ እኛ በምንኖርበት በሰለጠነውና የአዳም የጥረህ ግረህ ብላ እርግማን በሌለበት ተኝተው በሚንፈላለሱበት አሜሪካ ባህላችን ስለሆነ ፤ ዲያቆን ዳንኤልም ያነሳው ፣ እኔም ተደርቤ ያጋፈርኩት ፣ አሁን አንተ እንደጠየከው ቃል ዓይነት ከአባቶቻችንም ይደመጥና አርዓያነታቸውን እንይላቸው ፣ ቤተ ክርስቲያናችንም በአንድ አመራርና አስተዳደር ሥር ትሁን (ገለልተኛው ሸዋ ፣ ስደተኛው ጎንደሬ ፣ የአገር ቤቱ ትግሬ መባባልም ይወገድ) ለማለት ነበር ፡፡ እኔና አንተ ዋልጌ ዓለማውያን ይህን ያህል ይቅር የመባባል ወግ ሲኖረን በመንፈስ ከሚመሩን አባቶች ደግሞ እጅግ ብዙ እጠብቃለሁና ያለሃፍረት ይህን አድርጉ ለማለት እደፍራለሁ ፡፡

   መጽሐፍም ደግሞ የሚያስተራርቁ ብጹዓን ናቸው ብሏልና ሃሳቡ ከስማችን ስለገጠመ ድጋፋችንን በመስጠት ፣ መንገድ የሳቱትን ቢቻል ለማሰባሰብና ርዕስ ለማስጨበጥ ብቅ አልን ፡፡ ያላሰብኩትና ያልጠበኩት ገጠመኝ ስለነበር ፣ ተሰድጄ በመኖሬ ሳይሆን ሰው መልካሙን እንኳን መረዳት እንዳይችልና ፣ አንደኛውን ከከብቶች እንዲዛመድ ፣ እንደ እንስሳም እንዲያስብ ፣ እንዲናገርና እንዲጽፍ በመደረጉ በጣም በማዘኔ ጫጫርኩልህ ፡፡ ውጤቱም ያው አሁን ማውረድ የማልችለው ወንበር ነቅናቂ የሚያሳዝነኝ ጽሁፍ ሆነ ፡፡

   በተረፈ እግዚአብሔር ሁላችንንም ይቅር ይበለን ፤ ሰላሙንም ያብዛልህ
   ግጭታችንን ወደፍቅርና መተሳሰብ ቋንቋ የለወጠና በይቅርታ ዓላማ ያስተሳሰረን አምላክ ይመስገን ፡፡

   Delete
  11. very funy, you are playing nice Drama,AnonymousOctober 1, 2012 1:07 PM
   አይ ወንድማለም ደጉ፡፡ ውስጥህን መጉዳቴ ታውቆኛል፡፡ በስደት ያለን ሰው እንዲህ መሳደቡ ትክክል እንዳልሆነ ተሰምቶኛል፡፡ በቁስል ላይ እንጨት ስደድበት ወይ ኮምጣጤ ድፋበት ሆነብኝ፡፡ ስለዚህ ለሺህ ፍልጥ ማሰሪያው ልጥ እንዲሉ ይቅርታ መጠየቅ ፈለግሁ፡፡ ይቅርታ አድርግልሀኝ፡፡ is written by you ብጹዕ...kkkkkkkkk......Yededeb kuncho......you think everybody is fool like you? kkkkkk Punk

   Delete
  12. Thanks,AnonymousOctober 1, 2012 10:36 PM, i feel the same. ብጹዕ(Daniel) thinks we all are jerk like him....nice acting....ha ha ha..... sham-full

   Delete
  13. መጀመሪያ የምጠቀምበትን የአማርኛችንን ቃላት ጥርት አድርጌ አውቃለሁ ፡፡ በጹሁፉ ውስጥ የመሰለ የሆሄያት ግድፈት አልፈጽምም ፡፡ ሰውን ሊያታልል የሚሻ ሰውም አስቀድሞ ራሱን ማታለል አለበት ፡፡ እኔ ይኸን የሰነፎች ሥራ ብሠራ ራሴን ክጄዋለሁ ፣ ስብዕናዬንም አጥቻለሁ ፣ እንደ አንተው ቀልያለሁ ማለት ነው ፡፡ አንደኛውን የታወርክ ሰው በመሆንህ እርግጠኛ ነኝ ሃቁን ብጽፍልህ አታምንም ፡፡

   ይኸን የጻፈው እኔ አለመሆኔን ለማረጋገጥ ደግሞ በግሌ ከቃሌ ውጭ ምንም መንገድ የለኝም ፡፡ ሌባ ደግሞ እንደራሱ እየመሰለው ሌላውን አያምንም ፤ ብጹዑን ሁሉ ይጠራጠራል ፡፡ ምናልባት የብሎጉ ኃላፊ ከየትኛው ኮምፒዩተርና አገር እንደተላከለት መመስከር ቢችል ፣ እውነት ያለችው የት እንደሆነ ያስረዳናልና ጥያቄዬ ወደርሱም ቀርቧል ፡፡

   እንደ እኛ እንደ ሰዎቹ ይቅርታ ለመጠየቅ ካልበቃህም ፣ ባዝንብህም እኔን ቅር አይለኝም ፤ አምላኬ ወደ ሰውነትህ እስከሚመልስህ ግን በጸሎቴ እገፋለሁ ፡፡ እንዲሁም ከቂምና በቀል ጋር ሆነው ሥጋወ ደሙን የሚፈትቱትን ፣ ምእመን የሚባርኩትን አባቶች መጀመሪያ ራሳችሁን ፈትሹ ማለቴንም አላቆምም ፡፡

   በል እንግዲህ ያው እንዳመጣብህ ከኮበሌዎችህ ጋር ኮበል ድንጋይ ደራድረህ ቂጣህን ወይም የሆቴል ቤት ትርፍራፊ ጉርሻህን ተሰልፈህ ገዝተህ ብላ ፡፡ እኔም ትላልቅ ሃምበርገሬን እየገመጥኩ ፣ የቆርቆሮ ኮካዬን እየጨለጥቁ ልተኛበት ፡፡ እንቁልጭልጭ

   Delete
  14. ምነው ብፁዕ እስካሁን ድረስ በትዕግስት የሁላችሁንም ስድብ ቀመስ ምልልስ አንብቤአለሁ፡፡ በሰው ሰውኛው ለመፍረድ ያህል፡- እኔም ነዋሪነቴ አሜሪካ ቢሆንም ብፁዕ የምትኖርባት አሜሪካ ግን ሌላ መሰለችኝ ማርስ ላይ ወይስ ጁፒተር ላይ የተመሠረተችው???፡፡ ምነው ይህች እኛ የምንኖርባት አሜሪካ ግን ክፉ፣ ጨካኝ፣ አንድ ሰጥታ ሁለት የምትቀበል፣ በዲፕሬሽን ብዛት የተነሳ በኪኒን የሚኖርባት፣ ቢሉ ከመብዛቱ የተነሳ ክንፍ አስወጥታ የምታሳብድ፣ እንኳን እኛ መጤዎቹ ዜጎቿ እንኳን እረፍት የማያገኙባት፣ እኛ ምስኪኖቹ ዶላር ለማትረፍ 3 እና 4 ሰዓት ተኝተን እንኳን የምኞታችንን የማናገኝባት ፣ ምግብ እንኳን አጣጥሞ ለመብላት ካለመቻላችን የተነሳ በቫይታሚን ብቻ የምንውልባት፣ የገሃነብ ደጆች የተከፈቱባት፣ አምልኮ የበዛባት፣ ጥላቻ የነገሰባት፣ ዝሙት የተጠናወታት፣ እንኳን ሊንፈላሰሱባትና ሊዝናኑባት ቀርቶ ጩህ ብረር ብረር የሚል መንፈስ የበዛባት፡፡ አስጠሊታ አገር ብትኖር አሜሪካ ብቻ ናት፡፡ ሌላው ምናልባት ሠርቶ በል ያልሆኑ ሰዎች ከአንዱ ቤት አንዱ ቤት በዙረት የሚፈጽሙትና ለማኞች ከሆኑ እውነት ነው ምንም ሳይሰሩ መኖር የሚቻልባት አገር ነች፡፡ ወጥሮ ለሠራባት ደግሞ ዶላር በዶላር የምታደርግ አገር ነች፡፡ ግን ገንዘብ ብቻ ምን ያደርጋል አገር ቤት ኢንቨስት አድርጎ አገርንም ቤተሰብንም ካልጠቀሙበት ፡፡ ኤድያ !!! ገንዘብ ገደል ይግባ፡፡ ዋናው አእምሮ ነው ደስ መሰኘት ያለበት፡፡ ግን ደግሞ ምን ይዜ አገሬ ልግባ? ኧረ ጉድ ነው እንደኔ ስንቱ ተጨንቋል??? እኔስ አገሬ ብሔድ እንዴት ደስ ባለኝ፡፡ ቤተሰቦቼን፣ ጓደኞቼን፣ ማየት በጣም ተመኘሁ፡፡ ግን ደግሞ ወንዝ የማያሻግር ካፒታል ነው ያለኝ፡፡ ይህች ብኩን አገር እኔንም ብኩን አደረገችኝ፡፡ ስለዚህ ለመቋጨት ያክል ብፁዕዬ የትኛው ስቴት ነው ያለከው እኔም መጥቼ እንደልቤ ፍልስስስስስስስስስ ልበልበት፡፡

   Delete
  15. ብጹዕ(Daniel)ሃምበርገሬን እየገመጥኩ ፣ የቆርቆሮ ኮካዬን እየጨለጥቁ ልተኛበት play with your junk food,we Ethiopians are marching forward but you and looser like you are living the degraded life, some day you will wake up but who cares about a single Moron.

   Delete
  16. ስምክን ላለማስደፈር ለደበቅከው ወዳጅ Anonymous October 3, 2012 12:32 PM

   አንተ ባትሄድም ይህች ጽሁፍህን አገር ቤት ለጋዜጠኞች ብትልካት ፣ ምናልባት በየኤምባሲው በር ላይና ለመሰደድ ኢሚግሬሽን ተኰልኩሎ የሚንገላታውን ህዝብ ትቀንስ ይሆናልና አስብባት ፡፡ በተረፈ ለጉብኝትም ቢሆን ስመለስ ከዚህ አባባልህ የተነሳ ሻንጣ የሚጐትት ልታሳጣኝ ያሰብክ ይመስላል ፡፡ ሙሉ በሙሉ ባልቀበለውም ቆንጆ መግለጫ ነው ፡፡

   ከልምድ ካካበትነው ጥቂት ምክርና አስተያየት ፡-
   - አንድ መኪና /የአበሻዋ ተወዳጅ ቶዮታ ካምሪ/ እያለህ በነጻ ይሰጡህ ይመስል ፣ ማስታወቂያ ከቤትህ ስለላኩልህ ብቻ ዘለህ ዕዳ ውስጥ አትግባ ፡፡ የሚሰራ ቴሌቪዥንና ማቀዝቀዣም ካለህ ዘመናዊ ላድርገው ፣ ከጓደኞቼም ወደ ኋላ አልቅር በማለት በውድድርና በግብዝነት ባህርይ አትቀይር ፤ ይኸ እስከ አልባሳት ወጭ ሁሉ ይደርሳል ፡፡ ሥርዓቱ የተገነባው በንግድ ላይ ስለሆነ እኛ ብልሃታቸውን የማናውቅ ሁሉም እውነት እየመሰለን ዘለን ከአቅማችን በላይ በዕዳ እንዘፈዘፋለን ፡፡ ይህን ማስወገድ ከቻልክና የራስክን ኑሮ እንደ አቅምህ ከኖርክ እምየ ትላታለህ ፤ የነጋዴዎች ፍልስፍናና ዓላማ በቃላት አጠቃቀም ይቀያየር እንደሁ እንጅ መድረሻና ግባቸው አንድና አንድ ብቻ ነውና ዘወትር ሞኛቸው አትሁን ፡፡

   - በቃኝ ማለትንም ልመድ ፡፡ ሽቅብ ብቻ ሳይሆን ከአንተም አንሰው ደስ ብሏቸው የሚታገሉትን ምስኪኖች ተመልከት ፤ ትናንት የነበርክበትንም ደግሞ አትዘንጋው ፡፡ አንዳንዱ በስደት መምጣቱን እስከሚጠፋው ድረስ እነሱን መሆን የሚመኝ አለ ፤ ካሰቡበትና ከለፉለት በአሜሪካ መሆን ይቻላል ፡፡ ትናንት የነበረበትን የተረት ያህል እንኳን የማያስታውሰው ጭንቅላቱ ውስጥ ያለቀ የባትሪ ድንጋይ የተከለ ሰው ፣ በአገር ቤት ሂሳብ ቢመነዘር የሚኒስትሩን ደሞዝ ያህል እያገኘም አይምሮው አይረካም ፡፡ ስለዚህ ረድቶህና አሳክቶልህ ለደረስክበት የኑሮ ሁኔታ ያበቃህን አምላክ ማመስገን አትርሳ ፡፡ ሌሎች ይህችን የምታማርራትን የቪታሚን ህይወት አጥተዋት በአንገታቸው ገመድ እያጠለቁ ፣ በላያቸው እሳት እየለቀቁ ፣ በማያውቁት በረሃና ባህርም ችግርን ሊሸሹ ሲሉ ጠልቀው አልቀዋል ፡፡ አስበው ሁላችን ምንም ሳንይዝ ራቁታችንን ወደዚህች ምድር መጥተናል ፤ አንዱ በረንዳ አዳሪ ሌላው ዲታ ከበርቴ ሊሆን አልተፈጠረም ፤ አጋጣሚዎች ግን ሰውን ከፍና ዝቅ ፤ ኋላና ፊት አድርገውት ያበላልጡታል ፡፡ ታድያ በአጋጣሚስ ቢሆን አሜሪካ መጥቶ መኖር ሳይሻል ይቀራል ደመ ከልብ ሆኖ በየሥርቻው ከመቅረት ? ስለዚህ ዛሬውኑ ፈጣሪህን አስብ ስለደረስክበትም አመስግነው ፤ ርካታውን ያጐናጽፍሃል ፡፡

   - ያልተማርክ ከሆንክ ፣ ጥርስህን ነክሰህ ተማር / እየሰሩ ቢልን እየከፈሉ መማር እጅግ ከባድ ነው ፤ የቤተሰብ ኃላፊነትን ካለበት ደግሞ ህልም ወይም ቅዠት ይመስላል / ፤ ሰው የደረሰበት ለመድረስና እንደ ሰዉ ለመሆን ዓላማ ካለህ ፣ ዕድሜም ከድቶ ወደ ጌታ መሰብሰቢያ ጊዜህ ካልመሰለህ (ሰባዎቹና በላይ) ተፈላጊና የማይጣሉ ሙያዎች የትኞቹ መሆናቸውን ለይተህ ተካናቸው ፡፡ በሰዓት ስምንት ብር ተከፋይ ከሆንክ ፣ አልፈርድብህም ልትማረር ይገባሃል ፡፡ ቢሆንም አሁንም ለዚህ ያበቃኸኝ ፣ ሰርቼ ለመብላት የደገፍከኝ አንተ ተመስገን ፣ ለነገውም ታውቅልኛለህ ብለህ ጸልይ ፤ ሁሉንም ጉዞህን ትደነቅበታለህ ፡፡ ከትናንት በስቲያ የት ፣ ትናንትስ የት ፣ ዛሬስ ነገስ ደግሞ አስላቸው ያረጋጉሃል ፡፡

   - መማርም አልፈልግም እንዲያው ብቻ በተገኘው ካልክ ዓሣ ማስገር ትልቅ ገቢ አለው ፤ ጉልበትህን አበርትተህ ፣ ጨለማና ብርዱን ከተቋቋምከው ወደ አላስካ ወጣ በል ፡፡ ግን ያው ከሞት መለስ ቢሆንም ሊያልፍልህ ይችላል በማለት ነው እንጅ አድርግ ብዬ አልመክርህም ፡፡

   ሰምተኸው ቢሆንም ለማስታወስና ዛሬ እንኳን ፈገግ ብትልልኝ - ሰውየው ከአገር ቤት አሜሪካ መጣ አሉ ፡፡ ከእነኚህ ባለጥቁር መነጽርና ቁምጣ ሱሪ ለባሾች በወሬ የሰማውና በአእምሮው የቀረጸው ፣ አሜሪካ ዶላሩን ዝም ብለህ ከወፍጮ ቋት ደቅነህ እንደምትሰበስበው አድርጎ ነው ፡፡ ታዲያ ገና ከአይሮኘላን ወረድ እንዳለ የመቶ ዶላር ኖት ወድቆ ያገኛል ፡፡ ዞር ሲል ሰው ሁሉ ወደየጉዳዩ ለመድረስ በችኰላ እየተርመሰመሰ ነው ፡፡ ገና ከአሁኑ የወደቀ ስለቃቅም ሰውስ ምን ይለኛል ብሎ ሻንጣውን እየጐተተ ፣ ያገኘውን የእንኳን ደህና መጣህ ሲሳይ ሳይጠቀም የቃየልን ርግማን እንደተሸከመ /ዘፍ 4፡12/ ሄደ ይሏል ፡፡

   በተረፈ የብዕር ስም እንኳን አለመጠቀም ፤ ማን ጽፎ ማን እንደቀጠለ እንኳን ማወቅ የማንችልበት ጊዜ ደርሰናል ፡፡ የአንተ ጽሁፍ የለየሁት እንደኔ በአማርኛ መጻፍ የምትችል ሊቅ በመሆንህ ሲሆን ፣ ሌሎች ዲቃሎችና ድኩማኖች ደግሞ አለቆቻቸው የሚሏቸውንና ያስተማሯቸውን ይዘው በእኔ ላይ ቋንቋ ለመለማመድ አሁንም ይንደፋደፋሉ ፡፡ አሁን ልለያቸው ችያለሁና ካስከፋሁህ ይቅርታዬ ይከተል ፡፡ በገለጻዬ የዋሸሁ መስሎህ ከሆነ ያሉኝን ማስተጋባቴ መሆኑን ፣ ስለእኔ ኑሮ ምን ብለው እንደጻፉልኝ ከፍ በልና አንብበው ፡፡ ከመከራከር ይልቅ ሁኑበት ብዬ ጐመን ያረረበት አንጀታቸው እንዲጐመጅ ቀጠልኩበት ፡፡

   እግዚአብሔር ይጠብቅህ ይርዳህም

   Delete
  17. oh my GOG,you are useless, you are right to hide yourself in USA slams, empty head that's all.

   Delete
  18. Most old Diasporas ( who went to America as point 4 during Emperor H/selassie or due to fear of red terrorism during are ignorant and they assume as they are the superior of any Ethiopians in Ethiopia as well as they always complain about Ethiopia at abroad while almost nothing contribute to Ethiopia till now except they send the dead body of their friend to Ethiopia to be buried through Ethiopian Airlines. Their Dead body is also important as it is a good fertilizer. Nothing else they have. So, the young Diasporas got a lesson from these old & rotten head Diasporas. Sorry to say this & it doesn't include those few innocent old Diasporas

   Delete
  19. Egzer yesthe ,matyas

   Delete
 29. kale hiwot yasemalin.Egziabher andinetachinen yimelesilen, Amen!

  ReplyDelete
 30. ዲ/ን ዳንኤል አንባቢና አስተዋይ ካገኘህ ጥሩ ኃሣብ ነው፡፡ ነገር ግን ሥር ነቀል የባህሪና የአስተሳሰብ ለውጥ ያስፈልጋል፡፡ አንድ ብሔርን ማዕከል ያደረገ ውንጀላ፣ ጥላቻ፣ ንቀት፣ አልበለጥም ባይነት፣ ምቀኝነት ቀደም ብሎም በታሪክ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ከምንጊዜውም በከፋ መልኩ በተለይም በውጭው አለም /ዲያስፖራው/ የተስፋፋ ይመስለኛል፡፡ ሆኖም ግን ጥንት አባቶቻችን የፈፀሙት የታሪክ ስህተት ኖሮ ተወቃሽ ቢያደርጋቸውም እኛ ግን ተማርን፣ አወቅን፣ የአገር ውስጥና የውጭ ትምህርት ቀሰምን በምንለው ትውልድ እጅጉን ተስፋፍቶ ይገኛል፡፡ አሁን የሚያስፈልገው እሱን መስበር ነው፡፡ ሰው አኧምሮ የተሰጠው እንዲያስብበት አንገት የተሰጠው አዙሮ እንዲያይበት ልቦና የተሰጠው እንዲያስተውልበት ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት ይህንን ኩፉ ደዌ ሊፈውሱት የሚችሉት ደግሞ አባቶቻችን /በውስጥም በውጭም/ ያሉት ናቸው ፡፡ እነሱ ከእግዚአብሔር የተሰጡን አገልጋዮቻችን የሥላሴ ታዛዥዎች፣ ኃጢአታችንን ለእነሱ በግልጽ ተናዘን ቀኖናችንን ተቀብለን ከአምላክ ጋር በፍቅር እንድንኖር የሚያደርጉን የምንወዳቸው አባቶቻችን ናቸው እንጂ እዚህ ግባ ለማይባል ምንም አላማ ለሌለው አለማዊ ሰው ተገዥ መሆን አይገባቸውም፡፡ መሪ ናቸው አንጂ ማንም እየተነሳ የሚመራቸው፣ የሚያሽከረክራቸው አይደሉም፡፡ ስለዚህ መጀመሪያ ምዕመኑን ለመለወጥ እነሱ ግንባር ቀደም መሆን አለባቸው፡፡ ሕዝቡ አንድ እንዲሆን እነሱ ቅድሚያ አንድ መሆን አለባቸው፡፡ ስለዚህ ዘመኑን የተቆጣጠረው ርኩስ መንፈስ በጌታችን በእየሱስ ክርስቶስ ስም ይወገድልን፡፡ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 31. ቃለ ህይወት ያሰማልን ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
  በእውነት ያነሳህው ምክር ለቤተክርስቲያናችን ወቅታዊ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ ለሚያምን
  ሁሉ ይቻላል፡ እኛ ከልባችን ከፈለግነው ፤ ፈጣሪን ከለመነው፤ እንኳን ስምምነት ማምጣት ቀርቶ
  አምላክ ከዚህም በላይ በኛ አዕምሮ የማይገመት ነገር ይሰራል ፡፡ ምን ተስኖት፤ ግን በተቻለ መጠን
  መልካሙን እናስብ ፤ይቻላል፤
  አንተም በርታ ፤ምክርህን ፤መፍትሄ ይሆናል የምትለውን ሁሉ ከመግለፅ አትቆጠብ፤ ፀሐይ የሚሞቀኝ የለም ብላ ከመውጣት
  እንደማትቆጠብ ማለት ነው፤
  አምላክ ጥበቡን ይጨምርልህ ዓሜን፡፡

  ReplyDelete
 32. ከሰማሁት ገጠመኝ ላካፍል፡-
  አንድ ዕድሜ የጠገቡ ፣ የክርስትና እምነት ያላቸው አዛውንት ወዲህ ወደ አሜሪካ ልጃቸውን ለማየት መጥተዋል ፡፡ ልጅም ወላጅ አባቱን ብቸኝነት እንዳያጠቃቸው ወዲያውም ናፍቆቱን ለመቀነስ ዕረፍት ወስዶ ፣ ከተማው ውስጥ መታየት የሚገባቸውን ሥፍራ ፣ ወጣ ገባውን ሁሉ እያስጐበኛቸው ነው፡፡ በዕለተ እሁድ ቤተ ክርስቲያን የመሳለም ልማድ ነበራቸውና ፣ ቅዳሜ ከመኝታቸው በፊት በማለዳ እንዲወስዳቸው የእኛ ቤተ ክርስቲያን /የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን/ መኖሩን ጠየቁት

  ልጅም ፡- አዎን አለ ፤ ምነው ጠየቅከኝ ብሎ ለአባቱ መለሰ
  አባት ፡- ነገ እኮ እሁድ ነው ፤ ለማስቀደስ ነዋ አሉት ፡፡
  ልጅም ፡- በምድረ አሜሪካ ያሉን ቤተ ክርስቲያኖች በሦስት ወገን ሲኖዶስ ተከፍለው /በአገር ቤቱ ፣ በስደተኛው ፣ በገለልተኛው/ ኀብረተሰቡ በአቅራቢያው በሚገኘው ቤተ ክርስቲያን እንኳን መገልገል አይችልም ፡፡ አሁን ለምሳሌ በዚህ ከተማችን ሁለት ቤተ ክርስቲያኖች አሉን ፡፡ አንደኛው የአገር ቤት ፣ ሌላኛው ደግሞ የስደተኛው ነው ፤ ለእኔ የሚቀርበኝ የአገር ቤቱ ቢሆንም ፣ ስለምክንያት እዛ መሄድ አልችልም ፡፡ ከተመቸኝ አንድ ሰዓት ቢሆንም ነድቼ የምሄደው የስደተኛው ከሚያስተዳድረው ነው አላቸው ፡፡
  አባትም ፡- በል እኔንም ከምትሄድበት ውሰደኝ እንጅ ፤ መቸም በዕለተ ገብርኤል ሳላስቀድስ አልውልም አሉት ፡፡ ይባላል

  ስለዚህም የቤተ ክርስቲያን አንድ መሆን በነገድና በጎሣ ፣ በፖለቲካም ሆነ በጾታ መለያየታችንን ያጠፋልናልና ፣ ፍቅርን ከሚሰብኩ ፣ ስምምነትን ከሚፈልጉ ጋር ሁሉ የአንድነትን ሃሳብ እጋራለሁ ፡፡ ሁላችንም ለቤተ ክርስቲያን አንድነት መፈጠር የሚቻለንን ሃሳብ በቅንነት እናንሸራሽረው ፤ የየግል ጥቅምንና ምንዳን አንመልከት ፡፡ ይህን ዕድል አሁን ካልተጠቀምንበት ግን ቤተ ክርስቲያንም ለፖለቲከኞች የኳስ ሜዳ ትሆናለች ፤ ለእምነት ጠላቶቿም ቀላል ሆና ትመቻቻለች፡፡ ባልና ሚስት ሲፋቱ ፣ ከአባቱ የተቀያየመው ወደ እናቱ ፣ ከእናቱ የተኳረፈው ደግሞ ወደ አባቱ እየኰበለለ እንደሚያስቸግረው ሁኔታ የመሰለ አሁንም በቤተ እግዚአብሔር ውስጥ እያየን ነው ፡፡ ቤተ ክርስቲያን አንድ ከሆነች ግን ፣ ኀብረተሰቡ ለተለያዩ አማራጮች አይጋበዝምና ፣ ሃይማኖቱን አንድም መካድ ወይም ወደ አንድነት የመምጣት ዕድል ብቻ ይኖርለታል ለማለት ነው ፡፡

  በተረፈ ዲያቆን ዳንኤል ፣ ኢየሱስም ለድኀነታችን ሲመጣ ከጥቂቶች ከተጠሩ በስተቀር አሜን ብሎ ወዲያው የተቀበለው አልነበረምና ተስፋ አትቁረጥ ፡፡ መልዕክቱ ይተላለፍ ፤ ምን ማለት እንደሆነ የሚገባቸው ሰዎች እየጨመሩ እንጅ እያነሱ አይሄዱም ፡፡ ራሳቸውን ወደ ውስጥ መፈተሽ ተስኗቸው አንዳንዶች ቢሰድቡንም ፣ ውትወታችን ሲበዛ ሊገነዘቡና ሊመለሱ ይችሉ ይሆናልና መቀስቀስክን አትተው ፡፡
  እግዚአብሔር ይርዳህ

  ReplyDelete
 33. 6ኛውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ምርጫን በሚመለከት ጥቅምት በሚካሔደው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የሚወሰን መሆኑንና ሕዘበ ክርስቲያኑ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔና የቤተ ክርስቲኒቱን ድምጽ ብቻ መከታታል እንደሚገባው በመግለጫቸው አመልክተዋል፡፡ no more the 4th one 6ኛውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ finished.

  ReplyDelete
 34. ዳኒ ጽሑፍህንም አስተያየቶቹንም አነበብኋቸው፡፡ የተሰጡህ አስተያየቶች ገሚሶቹ ሐሰትን መሠረት አድርጎ የሚተወነው የዓለም ፖለቲካና እውነትን የማዕዘን ድንጋይ አድርጎ የሚነሣው ሃይማኖት እየተደብለቀለቁ ቀርበውባቸዋል፡፡
  የአንድምታ ትርጓሜ “ማኅቶቱ ለሥጋከ ዓይንከ ውእቱ ወእምከመ ዓይንከ ብሩህ ውእቱ ኵሉ ሥጋከ ብሩሃ ይከውን፡፡ ወእመሰ ዓይንከ ሐማሚ ውእቱ ኵለንታከ ጽልመተ ይከውን፡፡ ወሶበ ብርሃን ዘላዕሌከ ጽልመት ውእቱ ጽልመትከ እፎ ይከውነከ፡፡” (ሉቃ. 11፣ 34) የሚለውን ቃል ሲተነትን እንዲህ ይላል፡-
  የሥጋህ ፋና ዓይንህ ነው፡፡ ማለትም የሥራህ መከናወኛ ዓይንህ ነው፡፡ ዓይንህ ብሩህ የሆነ እንደሆነ አካልህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል፡፡ ዓይንህ የቀና እንደሆነ ሥራህ ሁሉ የቀና ይሆናል፡፡ ዓይንህ የሚታመም እንደሆነ አካልህ ሁሉ ጨለማ ጨለማ ይሆናል፡፡ ማለትም ዓይንህ ያልቀና እንደሆነ ሥራህ ሁሉ ያልቀና ይሆናል፡፡ ባንተ ያለ ብርሃን ጨለማ ከሆነ ጨለማህ እንደምን ይሆን፡፡ በተፈጥሮ የተሰጠህ ዓይንህ የታመመ ከሆነ ጨለማ እንደምን ይጸናብህ ይሆን፡፡
  አንድም የሥራህ መከናወኛ ኤጲስ ቆጶስህ ነው፡፡ ኤጲስ ቆጶስህ የቀና እንደሆነ ሥራህ ሁሉ የቀና ይሆናል፡፡ ኤጲስ ቆጶስህ ግን ያልቀና እንደሆነ ሥራህ ሁሉ ያልቀና ይሆናል፡፡ ባንተ የተሾመ ኤጲስ ቆጶስ ያልቀና ከሆነ ፍዳ እንደምን ይጸናብህ ይሆን፡፡ ባንተ የተሾመ ኤጲስ ቆጶስ ያልቀና እንደሆነ እንደምን መክበሪያ መጽደቂያ ይሆንሃል?
  እንደእኔ አስተሳሰብ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ክፍፍልና በውስጥ የሚታየው ንቅዘት ጉዳይ የቤተክርስቲያን ታሪክን ትንሽ ገፋ አድርጎ የመረመረ ሰው ሊያስተውለው እንደሚችለው አምስተኛውና አስራ አንደኛው ክፍለ ዘመን ላይ የተፈጠሩትን አሳፋሪ ፖለቲካዊ ጥቅምና እኔ ያልሁት ካልኾነ የሚል ትዕቢት የወለዳቸው ክፍፍሎች እንዲሁም በአውሮፓ ቤተክርስቲያን ታሪክ “የሦስት ፖፖች” ዘመን በመባል የሚታወቀውን የቤተክርስቲያን በኃጢኣት የመተዳደፍ ወቅት ሳይመስል አይቀርም፡፡
  ቤተክርስቲያንን የሚያስተዳድሩ ጳጳሳት ከፍቅርና ከትሕትና ይልቅ የራሳቸው ክብርና ዝና ሲበልጥባቸው የማያጨቃጭቅ ነገር ያጨቃጭቃቸዋል፡፡ የማያለያይ ነገር ያለያያቸዋል፡፡ በክርስቶስ ዓይን ካየነው እንኳን ለመወጋገዝ ጮኽ ብሎ ለመነጋገር እንኳ የማያበቃ ነገር እነርሱን ያወጋግዛቸዋል፡፡ በውግዘታቸው ውስጥ ግን “ይህን ውግዘት የማስተላልፈው ክብሬ እንዲነካ ስለማልፈቅድ ወይም እኔ ያልኩት ካልኾነ በስተቀር ሌሎች የሚሉትን ለመፈጸም፣ እንደጌታዬ የሌሎችን እግር ለማጠብ ፈቃደኛ ስላልኾንኹ ነው፡፡” አይሉም፡፡ ይልቁንም ለምእመናን የሌላኛውን ወገን “ሃይማኖታዊ ሕፀፅ” የሚሉትን ነገር በመዘርዘር ሌላኛው ወገን ምን ያህል ኃጢኣተኛ፣ ምን ያህል መናፍቅ፣ ምን ያህል የሥርዓተ ቤተክርስቲያን ጠላት እንደኾነ ያትታሉ፡፡ እውነታው ግን የመለያየታቸው መነሻ የእኔ አካኼድ ካልበለጠ ሞቼ እገኛለሁ የምትል የሊቅነት ትዝኅርት ወይም ደግሞ ከእኔ በላይ ማን አለ የምትል ፖለቲካዊ መታጀር አልያም ደግሞ “ሆዴ ይሙላ፤ ደረቴ ይቅላ፡፡” የምትል የምቾት ፍለጋ ፍልስፍና ናት፡፡ እነዚህ ምንያቶች በሌሉበት የሚፈጠር የነገረ መለኮት ትምህርት ክርክር ግፋ ቢል መማማርን ትወልድ ይኾናል እንጂ መወጋገዝን አታመጣም፡፡ ለዚህም አምስተኛው ክፍለ ዘመን ላይ የነበሩት የቅዱስ አውጉስጢኖስና የቅዱስ ጄሮም ታሪክ በቂ ማስረጃ ይኾናል፡፡ ኹለቱ ሊቃውንት በአንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ትርጓሜ ላይ ሳይጣጣሙ ቀርተው ተጋጭተው ነበር፡፡ ኋላ ላይ ግን አንድ ላይ እስከመቀደስ ደርሰው ፍቅራቸውን አድሰውታል- በነገረ መለኮት ክርክራቸው ውስጥ ከበስተጀርባ የሸሸጉት ጥቅመኝነት አልነበረምና፡፡

  ReplyDelete
 35. የቤተክርስቲያን ታሪክ እንደሚመሰክረው የጳጳሳት ኃጢኣት ግን ኹልጊዜም የጌታ ኢየሱስ ምሥጢራዊ አካሉ የኾነች ቅድስት ቤተክርስቲያንን ሲያቆስል ይኖራል፡፡ ምእመናንን ይከፋፍላል፡፡ አንድ ሊያደርገን በመስቀል ላይ እጁን የዘረጋልንን ክርስቶስን ለእኛ ሲል የተቸነከረበት ችንካር አልበቃው ብሎ ክንድና ክንዱን ለመገነጣጠል ግራና ቀኝ እየጎተተ የጎን ላይ ቁስሉን ያሰፋዋል፡፡ ያሳምመዋል፡፡ ከሰቃዮቹ ጋር ተባብሮ ያደማዋል፡፡ ነገር ግን ታሪክ እንደሚመሰክርብን ከታሪክ የምንማረው ከታሪክ አለመማራችንን ብቻ ይመስላል፡፡
  ጀልባዋን የውጪ ማዕበል ሲያማታት በአንድነት ኾነን “ጌታ ሆይ አድነን!” ስንለው ብድግ ብሎ ማዕበሉን ይገሥጽልናል፡፡ ጀልባዋ ውስጥ ኾነን ከእኛ መመካከል ማን ይበልጣል እያልን ስንፎካከር ግን ልቡ እጅግ ያዝናል- “ከእናንተ ታላቅ ሊኾን የሚወድ ቢኖር የኹሉ አገልጋይ ይኹን፡፡” (ማቴ. 20፣ 26) ሲል ያስተማረንን ዘንግተናልና፡፡ በዚህ የእኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ፉክክር የተነሣ ሰላም እናጣለን፡፡ ዕረፍት ይለየናል፡፡ ልባችን በፈጠረን በእርሱ አላረፈምና ሕይወት መባከን፣ ኑሮም መባዘን ትኾንብናለች፡፡ የእግዚአብሔር ማደሪያው የኾነችውን የምእመናንን ጉባኤ ቅድስት ቤተክርስቲያንንም እናውካታለን- “ወሖኮ ኃጥእ ለእግዚአብሔር” (ኃጢኣተኛ እግዚአብሔርን አስቸገረው፡፡) እንዲል መዝሙረ ዳዊት፡፡
  የውጪ ማዕበል ቢኾን ፀጥ ያሰኝልን ነበር፡፡ ለውስጣችን ትርምስ ግን በፈቃዳችን ትምህርተ ትሕትናውን አንሰማ ብለን ያመጣነው ነውና መልሱ ዝምታ ነው፡፡ ልባችንን “እኔ” “እኛ” “እኛ” ከምትል ትዕቢት ወደ ትሕትና ስንመልሰው ያን ጊዜ ሰላም እናገኛለን፡፡ ክህነት መዓርግ ሳይኾን ምሥጢር ነው፡፡ ልዩ ጥዑም፣ ክቡር ዘይት ተቀብተን፣ ሻምላ ጨብጠን፣ ወርቅ ለብሰን፣ ዘውድ ደፍተን የበላይ የምንኾንበትና የምንነግሥበት ሳይኾን “እፍ፡፡ መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ፡፡” በምትል ትሑት መንገድ የሚሰጠን “ይቅር ላላችኋቸው ኃጢኣቸው ይቅር ይባልላቸዋል፤ ይቅር ላላችኋቸው ደግሞ ኃጢኣታቸው ይቅር አይባልላቸውም፡፡” የሚል የሰው ልጆች ምኞትን መሠረት አድርጎ እግዚአብሔር ወደሌለበት ሐሰት ከሚስባቸው ዲያብሎሳዊ አካኼድ ነጻ ለማውጣት ከጌታ ኢየሱስ ጋር የምንሠራበትና የምንለፋበት ከአእምሮ በላይ የኾነ ኃላፊነት ነው፡፡
  ለዚህ ነው የቤተክርስቲያን መምህራን “የሥጋህ መብራት ዓይንህ ነው፡፡” ሲል ያስተማረውን ሲተነትኑ የነፍስህ መብራት ኤጲስ ቆጶስህ ነው፡፡ “ኤጲስ ቆጶስህ የቀና እንደሆነ ሥራህ ሁሉ የቀና ይሆናል፡፡ ኤጲስ ቆጶስህ ግን ያልቀና እንደሆነ ሥራህ ሁሉ ያልቀና ይሆናል፡፡ ባንተ የተሾመ ኤጲስ ቆጶስ ያልቀና ከሆነ ፍዳ እንደምን ይጸናብህ ይሆን፡፡ ባንተ የተሾመ ኤጲስ ቆጶስ ያልቀና እንደሆነ እንደምን መክበሪያ መጽደቂያ ይሆንሃል?” ሲሉ ያስተማሩት፡፡ በነፍስ የታወረ ዕውር ሌላ ነፍሱ የታወረችበትን ሰው ቢመራው ፍጻሜያቸው ገደል ነውና፡፡
  መለያየትን በልቡ ያረገዘ ካህን ሊሰብክ ሲቆም በጎቹን አንድ ሊያደርግ “ከመ ይኵኑ አሐደ ብነ ከማነ” “አንድ ይኾኑ ዘንድ” ብሎ ከመጸለይ አልፎ በዕቅፉ አንድ ሊያደርገን በመስቀል ላይ ስለሞተልን መልካ እረኛችን ከመስበክ ይልቅ እኛ ከእነዚያ ወይም ከእነዚህ እንዴት የተሻልን እንደኾንን ይነግረናል፡፡ የእረኛችንን ፍቅር ሳይኾን በእርሱ ዓይን የተመዘኑትን የወንድሞቻችንን መቅለል በልባችን ሊዘራ ይጮኻል፡፡ በዚህም እግዚአብሔርን ያገለገለ ይመስለዋል፡፡ እግዚአብሔር እርሱ የሚወድዳቸውን እንዲወድለት እርሱ የሚጠላቸውን እንዲጠላለት ይመኛል፡፡ በዚህም እግዚአብሔርን እንደእግዚአብሔርነቱ ከማምለክ ይልቅ በራሱ አምሳል ጠፍጥፎ ለመሥራት ይሞክራል፡፡

  ReplyDelete
 36. ለእኔ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ዛሬ ሥር ሰድዶ የሚታየኝ ኃጢኣት ይህ ነው- ትዕቢት፡፡ C.S. Lewis የሚባሉ የሃያኛው ክፍለ ዘመን የቤተክርስቲያን ሊቅ “ትዕቢተኛ ሰው ከእነማን በላይ እንደኾነ ለማየት ቁልቁል ቁልቁል በመመልከት ስለሚጠመድ ቀና ብሎ እግዚአብሔርን ለማየት ጊዜ የለውም፡፡” ይላሉ፡፡ እውነታቸውን ነው፡፡
  በቤተክርስቲያን ጉዳዮች ውስጥ ሱታፌ እናደርጋለን የሚሉ ምእመናንም ኾኑ ጳጳሳት እውነት ክርስቶስ ብቻ ስለኾነ እውነቱ እኔ ያልኹት ብቻ ነው የምትልን በአጉል አርበኝነት ውስጥ የምትሸሸግ ትዝኅርት ከውስጣቸው ሊያወጧት ይገባቸዋል፡፡ አንድ አባቴ በአንድ ወቅት እንዳሉት “ሰይጣን IDIOT አይደለም፡፡” ከጌታችን የሚለየንን ኃጢኣት የሚያሠራን ከጌታ ጋር ያቀራረበን አስመስሎ ነው፡፡ ዘፍጥረት እንደሚተርከው እባቡ አዳምና ሔዋንን የጣላቸው “እንደእግዚአብሔር ትኾናላችሁ፡፡” በምትል መልካም በምትመስል ምክር አልነበረምን? ሐዋርያቱንስ እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ብለው እዲፎካከሩ ያደረጋቸው የጌታ የቅርብ ወዳጆች ለመኾን የነበራቸውን በጎ የምትመስል መሻት በመጠቀም አልነበረምን? ገጣሚና ሠዐሊው ገብረ ክርስቶስ ደስታ
  “የዓለም መራራነት ነው የሚጣፍጠን
  መቼ መጣፈጧ፤
  ኮሶውን በማሯ ጠቅልላ ስትሰጠን
  ስትሰጠን እሳቱን
  አመድ አስመስላ ሸፍና ረመጡን፡፡
  ስትሰጥ ማየ ሕይወት ስሰጠን መድኃኒት
  መርዟን ጨምራበት፡፡”
  እንዳለው ትክክል እየመሰሉን የምንሠራቸውን ነገሮች ኹሉ ከትክክለኛው ከእግዚአብሔር አንጻር ብቻ መመልከት መጀመር ያለብን ይመስለኛል፡፡ የምናደርገው ነገር ወይም የምናስተምረው ትምህርት ሰዎች “ትክክል ናችሁ!” ስላሉን ወይም ብዙ ደጋፊዎች ስላገኘን ወይም እኛ ትክክል እየሠራን ስለመሰለን ወይም “ትክክለኛ” የሚል ስም ስለለጠፍንበት ብቻ ትክክል ሊኾን አይችልም፡፡ ድርጊቶቻችን፣ ንግግሮቻችንና ሐሳቦቻችን ትክክል የሚኾኑት በፍቅር ላይ ሲመሠረቱ ብቻ ነው- እግዚአብሔር ፍቅር ነውና፡፡ ይህ ፍቅር ደግሞ እንኳን ቤተክርስቲያን ውስጥ ትዳር ላይ እንኳ በተግባር የሚገለጥ “የወንድሞችን እግር በማጠብ” ላይ የተመሠረተ ነው እንጂ በግላዊ ተጠቃሚነት ወይም በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረተ አይደለም፡፡ “እኔ” ሳልኾን ወንድሞቼ የሚከብሩበት፣ ወንድሞቼ የሚጠቀሙበት፣ ወንድሞቼ የሚገለገሉበት ነው፡፡ ድርጊቴ፣ ንግግሬ፣ ሐሳቤ በዚህ እግዚአብሔራዊ መንገድ ከተቃኘ ብቻ የምናገረውም የምሠራውም የማስበውም እውነት ብቻ ይኾናል፡፡ ከዚህ ውጪ ግን እውነት የለችም፡፡ እውነትም ፍቅርም እግዚአብሔር ብቻ ነውና፡፡ በቅርቡ በዚሁ በአንተ ብሎግ ላይ “ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ (በረከታቸው ይደርብንና) “ያለ ፍትሕ ሰላም ያለይቅርታ ደግሞ ፍትሕ የለም፡፡” ብለዋል፡፡” የሚሉ አስተያየት ሰጪ ነበሩ፡፡ እውነት ነው፡፡ ተበድለናል የሚሉ እንዲካሡና ፍትሕ እንዲያገኙ መጀመሪያ ይቅር ለማለት ዝግጁ መኾን አለባቸው፡፡ ምክንያቱም ትናንት የተደረገን ጥፋት ዛሬ ላይ ኾነን እንደኮምፒወተር አንዱ “Undo” ልናደርገው አንችልምና፡፡
  ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ችግሮች እንዲፈቱ የቤተክርስቲያን ቅን አሳቢዋ የኾንኸው አንተ ካነሣኻቸው ሐሳቦች በተጨማሪ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ሐሳቦች በመንፈሳዊ አቅጣጫ ጠቃሚ ይመስሉኛል- ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ምሥጢራዊ መንፈሳዊት አካሉ ናትና፡፡ አንድም የቤተክርስቲያን ታሪክ እንደሚመሰክርልን ቤተክርስቲያን መዋቅራዊ ችግሮች የሚገጥሟት የምእመናን መንፈሳዊ ሕይወት በኃጢኣት ሲነቅዝ ስለኾነ በቅድሚያ መንፈሳዊ አቋሟን ልታስተካክል ይገባታል፡፡ የሦስተኛው ክፍለ ዘመን ሊቅ ቅዱስ አምብሮስ ቤተክርስቲያንን “Casta Meretrix” (Chaste Prostitute) ይላታል፡፡ በአማርኛ “ንጽሕት ጋለሞታ” ማለት ነው፡፡ “ንጽሕት” አላት፤ ምክንያቱም የክርስቶስ ስለኾነች፤ እርሱ በደሙ ስለመሠረታት፤ ከአደፍና ከፊት መጨማደድ ኹሉ ያነጻት ዘንድ ስለተሰዋላት፡፡ “ጋለሞታ” አላት፤ ምክንያቱም በፈቃዳችን ኃጢኣት እየተመላለሰ የሚያረክሰን የእኛ የምእመናን ጉባኤ ስለኾነች፡፡ ስለዚህም ነው በየጊዜው ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖረንን ግንኙነት የምናድስበት የመንፈሳዊ ሕይወት ተሐድሶ የሚያስፈልገን፡፡ ግልሙትናችን ሲበዛ እታወካለን፡፡ ቅዱሳን አበው ያሳዩንን መንገድ ትተን በእግዚአብሔር ፈንታ ሌሎች ነገሮችን አምባ፣ መጠጊያ፣ መታመኛ ስናደርግ እግዚአብሔርንም የእነዚህ ጣዖቶቻችን ጠባቂ እንዲኾንልን ስንፈልግ ወይም ጠባቂ እንዲኾንልን ጠፍጥፈን ለመሥራት ስሞክር የተፈጠርንበትን ዓላማ ስተናልና እንታወካለን፤ እንሸበራለን፤ እንፈራለን፡፡ ልክ እንደአዳም ሊሸሽገን ይችላል ብለን በምናስበው ነገር ሥር በመደበቅ ከለላ ለማግኘት እንሞክራለን፡፡ መጽሐፍ ግን “በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚመለስ ሰው ርጉም ነው።” (ኤር. 17፣ 5) ይለናል፡፡ ስለዚህም፡-
   ኹሉም ወደ ውስጡ ተመልሶ ድርጊቶቹን ከእግዚአብሔር አንጻር ቢመለከትና ቢገመግም ለዚህም ቤተክርስቲያን ውስጥ ከቅዳሴ ውጪ ምንም ቃል የማይሰማበት የዝምታ ሱባኤ በምእመናኑ ኹሉ ቢያዝ
   ምሥጢረ ክህነት የተፈጸመለት ሰው በሙሉ ክህነቱ ለእርሱ ምን እንደኾነች (“መዓርግ” ወይስ ምሥጢር) ኹሉን በሚያይና በሚያውቅ በእግዚአብሔር ፊት በዝምታ እርሱና እግዚአብሑር ብቻ ወደሚያውቁት ወደውስጡ ራሱን ቢፈትሽ
   ጳጳሳቱ ኹሉ ከቻሉ እርስበርሳቸው ተነጋግረው እነርሱ ብቻቸውን ማንም ጣልቃ ሳይገባባቸው ከቻሉ አንድ ላይ፣ ካልቻሉ በያሉበት ለአንድ ሳምንት ሕዝብና አሕዛብን አንድ ያደርግ ዘንድ፣ ቤተክርስቲያንን ከልዩ ልዩ ወገን ይሰበስብ ዘንድ በመስቀል ላይ እጁን በምስማር የተቸነከረላትን የኢየሱስን ሕማማት በማሰብ፣ በማሰላሰልና በማስተንተን ቢጸልዩ
   ማንም አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቦ ዝም እንዲል ቢደረግና እንደእመቤታችን እግዚአብሔር የወደደው ብቻ እንዲኾልን “ነየ አመቱ ለእግዚኣ ኵሉ፤ ይኵነኒ በከመ ትቤለኒ” የሚለውን የቃሏን ምሥጢር ብናስተነትን
  እኛ ዝም ካላልን እግዚአብሔር አይናገርም፤ ቢናገርም አንሰማውም፡፡ እርሱ ላይ ካልተመሠረትን ደግሞ ብንረዝም እንኳ ሳንወድቅ አንቀርም፤ ብንበዛ እንኳ አናሸንፍም (1ኛ ነገ. 19፣ 12)፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ድንቅ ምክርና ከዕውቀትና እምነት የመነጨ አስተያየት ፤
   እግዚአብሔር ይስጥልን
   እንደምክርዎ ዝም ብያለሁ

   Delete
 37. ከወ/ት መስከረም
  ዝምታውን እደግፋለሁ። ዝም ማለት የሚገባን ምድራዊ አመለካከታችን መሆን አለበት። ወደ እግዚያብሔር ከልብ መፀለይና ማልቀስ ግን መቋረጥ የለበትም። ሊነጋጋ ሲል ይጨልማል።

  ReplyDelete
 38. I agree with you Dn. Daniel. May God give us his forgiveness for what we have done. Please let's unite and pray for our church.
  YeDingil Milja ayileyen amen!

  ReplyDelete
 39. መተማማት አያድነንም፣
  ወይም ቤት ሆኖ አይጠልለንም፡፡
  ቂምና ቁርሾ ምን አይጠቅመን፣
  እስኪ እንነሣ ተወት አድርገን፡፡

  ሊመጣ ቀርቧ ሙሽራው ኢየሱስ የምንጠብቀው ታላቁ እንግዳ፣
  ይብቃ ከእንግዲህ መዝረክረካችን ነቃ ነቃ እንበል እንሰናዳ፡፡

  ለነፍሳት መዳን ተግተን ልንሠራ፣
  ተጥሎብናል ታላቅ አደራ፡፡
  ቸል ብንለው ይጠይቀናል፤
  ብንፈጽመው ይሸልመናል፡፡

  ከአባቶቻችን የተጣለብን፣
  ያልተከፈለ ዕዳም አለብን፡፡
  ሳናገባድድ ጌታ እንዳይመጣ ፤
  ነቃ ነቃ እንበል ተነሡ እንውጣ፡፡

  የተደፋውን ቀና እናድርገው፤
  የቆሸሸውን እንጠራርገው፡፡
  ከተፍ ሳይል ታላቁ እንግዳ፤
  እንደሚገባ ቤቱ ይሰናዳ፡፡

  መከሩ ብዙ እጅግ ብዙ ነው፤
  ያልደረስንበት ገና ያላየነው፡፡
  ሰለቸን ሳንል መሥራት ያሻናል፤
  እኛ ስንጀምር ጌታ ያበዛናል፡፡

  ReplyDelete