Wednesday, September 12, 2012

እናቁም?


አንዳንዴ የትግላችን፣የጥረታችን፣የልፋታችን ውጤት መና የቀረ የሚመስልበት ጊዜ አለ፡፡ ውኃ አልቋጥር፣ ጠብ አልል ሲልብን፤ መንገዱ ሁሉ ረዥም፣ በሮቹ ሁሉ ዝግ፣ ጩኸቱ ሁሉ ሰሚ አልባ ሲመስለን፣ በመጨረሻ የምንወሰደው መፍትሔ ነገር ዓለሙን ሁሉ መተውና መሸነፍ ይሆናል፡፡ ‹‹ከዚህ በኋላ አበቃ›› ማለት እንጀምራለን፡፡ እንኳን እኛ ቀርቶ ሌሎች እንኳን እንዳይበረቱ ‹‹ባክህ እኛም ብለነው ብለነው አቅቶን ነው›› እያልን ተስፋ እናስቆርጣቸዋለን፡፡
ግን ሰው መልፋት ያለበት፣ መትጋትስ ያለበት፣ መታገልስ ያለበት፣ መሮጥስ ያለበት እስከ የት ነው? ሰው ተስፋ መቁረጥ ያለበት የት ደረጃ ሲደርስ ነው? የመንገድ ማለቂያው የት ነው? ውጤቱን ዛሬ ያላየነው ነገር ሁሉ ውጤት አልባ ተደርጎ ሊቆጠር ይችላልን? በታሰበው ጊዜ ያልተደረሰበት ነገር ሁሉ ሊደረስበት የማይችል ነገር ነው ማለት ነው? መንገዱስ ይሄ እኛ የያዝነው መንገድ ብቻ ነውን? በሌላ መንገድስ ሊሞከር አይቻልምን?
መሆኑ ከማቆምና ከመቀጠል የትኛው ይመረጣል? ከማቆም ምን ይገኛል? ከተስፋ መቁረጥ በቀር፡፡ የሚጓዝ ሰው ጊዜው ይረዝም ይሆናል እንጂ አንድ ቀን የሚፈልገው ቦታ ይደርሳል፡፡ የቆመ ሰው ግን እንኳን ወደሚፈልግበት ለመሄድ  ወደ ተነሣበት ቦታም ተመልሶ አይደርስም፡፡ የሚታገል ሰው አንድ ቀን ያሸንፋል፤ ያቆመ ሰው ግን ሳይማረክ እጁን ሰጥቷል፡፡ ደጋግሞ የሚያንኳኳ ሰው ከተኙት ሰዎች አንዱን መቀስቀሱ አይቀርም፤ ማንኳኳት ያቆመው ግን እንኳን ሊቀሰቅስ ራሱም ይተኛል፡፡ የሚሄድ መኪና ጋራጅ ይደርሳል፤ የቆመ መኪና ግን ባለበት ይወላልቃል፡፡
ለማሸነፍ ትልቁ መፍትሔ አቋምን መቀየር ሳይሆን መንገድን መቀየር ነው፡፡ የተለያዩ ነገሮችን መሞካከር ሳይሆን አንድን ነገር በተለያዩ መንገዶች መሞከር ነው፡፡ የተለያዩ ነገሮችን ማየት ሳይሆን አንድን ነገር በተለየ መንገድ ለማየት መቻል ነው፡፡ ተስፋ መቁረጥ ሳይሆን፣ በውሳኔ ጊዜ መቁረጥ መቻል ነው፡፡ የምታገኘውን ሞት ከመመኘት የማታገኛትን ሕይወት በሚገባ ለመኖር ጣር፡፡
ሁለት ዕንቁራሪቶች እየተጓዙ ነበር፡፡ አንዷ ወፍራም ሌላዋም ቀጭን ነበሩ፡፡ እንዳጋጣሚ በገረወይና የተሞላ ወተት አገኙና ሰፍ ብለው ገቡበት፡፡ እዚያም አስኪበቃቸው ጠጡና ሲጠግቡ መውጣት ፈለጉ፡፡ ነገር ግን ውስጡ ያንዳልጥ ስለ ነበር ለመውጣት አልቻሉም፡፡ እግራቸውን ባንቀሳቀሱ ቁጥር ወተቱ እያንዳለጠ እዚያው ይጨምራቸዋል፡፡ ከጠዋት እስከ እኩለ ቀን ድረስ እጅግ ደከሙ፤ ነገር ግን ከድካም በቀር ያተረፉት ትርፍ አልነበረም፡፡
በምን ቀን ነው እዚህ ወተት ውስጥ የገባነው? እያሉ ቀናቸውን የሚያማርሩበት ሰዓት ላይ ደረሱ፡፡ የሚያማክሩት ሽማግሌ የሚጠይቁት ባለሞያ በአካባቢያቸው አልነበረም፡፡ ወደ ኋላ ተጉዘው የሰሟቸውንና ያዩዋቸውን ነገሮች ሁሉ አስታወሱ፡፡ ነገር ግን ለዚህ ነገር መፍትሔ የሚሆን ነገር ማስታወስ አልቻሉም፡፡ ወደ ሰማይ ቢጸልዩ እንኳን ጸሎታቸው የተሰማ አልመሰላቸውም፡፡ አንዳች ፈጣን መልስ አላገኙምና፡፡ በአካባቢው የሚያልፉ ሰዎችም ሆኑ ሌሎች ዕንቁራሪቶች ድምፃቸውን ሰምተው ከማለፍ በቀር ዘወር ብለው ሊያዋቸው አልቻሉም፡፡ አንዳንዶቹም ከገረወይናው ውስጥ የሚሰማው ዕንቁራሪቶች ድምፅ ከተለመደው ውጭ ነው ብለው ለማሰብ አልቻሉም፡፡
ወፍራሟ ዕንቁራሪት ተስፋ ቆረጠች፡፡ ‹‹በቃን፤ ከድካም በቀር የተረፈን የለም፡፡ ለመውጣት መታገሉን ማቆም አለብን›› አለች፡፡ ቀጭኗ ግን ‹‹ የለም ከተስፋ መቁረጥ የምናገኘው ምንም ነገር የለም፡፡ ተቀምጦ ከመሞት እየታገሉ መሞት፤ ተሸንፎ ከመሞት እያሸነፉ መሞት፤ እጅ ሰጥቶ ከመሞት እጅን እያሠሩ መሞት፣ አልችልም ብሎ ከመሞት እችላለሁ ብሎ መሞት የተሻለ ነውና አታቁሚ›› አለቻት፡፡
‹‹እስኪ ተመልከቺ ከጠዋት ጀምረን ለፋን፡፡ የጠጣነው ወተት እንኳን እስኪያልቅ ድረስ ለፋን፡፡ ከሰማይም ሆነ ከምድር የደረሰልን የለም፡፡ የእኛም ድካም ውጤት አላመጣም፡፡ አንዳንድ ጊዜ የምናደርገው ሁሉ ቀልድ ይመስለኛል፡፡ ተንቦጫረቅን ተንቦጫረቅን፤ ወይ የሚንቦጫረቁ ልጆች የሚያገኙትን ደስታ አላገኘን፤ አለበለዚያም ደግሞ ከዚህ ቦታ መውጣት አልቻልንም፡፡ ታድያ የልፋታችን ዋጋው ምንድን ነው? እዚህ ቦታ መልፋታችንን እንኳን ያወቀልን የለም፡፡››
‹‹የሚረዳን ብናገኝ እንኳን የምንጠቀመው እኛ ለመውጣት የምንደርገውን ተጋድሎ ካላቋረጥን ብቻ ነው፡፡ ከልምድ መፍትሔውን የምናገኘው እኛ ጥረታችንን ካላቋረጥን ብቻ ነው፡፡ አንድ ቀን ይህንን ችግር ልናሸንፈው የምንችለው እኛ እየጣርን ከቀጠልን ብቻ ነው፡፡›› አለቻት ቀጭኗ ዕንቁራሪት፡፡ 
‹‹ባለፈው ጊዜ አታስታውሽም ቅቤ ውስጥ የገቡት ሦስት ዕንቁራሪቶች ምን ሆኑ?›› ወፍራሟ ይህንን ስትጠይቅ ለመውጣት የምታደርገውን ጥረት እያቆመችው ነበር፡፡
‹‹ለምን የተሸነፉትን ትጠቅሻቸዋለሽ? ከተሸነፉት መማር ያለብንኮ ለምን ተሸነፉ የሚለውን እንጂ የጥረት መጨረሻው መሸነፍ መሆኑን አይደለም፡፡ ሽንፈትኮ ትምህርት አያስፈልገውም፡፡ ሽንፈትኮ ልምድ አያስፈልገውም፡፡ ዕውቀት አያስፈልገውም፡፡ ሽንፈት እጅን አጣጥፎ መቀመጥ ብቻ ይበቃዋል፡፡ ለሽንፈት ምሳሌ መጥቀስ አያስፈል ግሽም፡፡ ሽንፈት ማለት በቀላሉ የሚደረስበት ነገር ነው፡፡ ሳትለፊ የምታገኚው ነገር ነው፡፡ ምሳሌ፣ አርአያ፣ ልምድ፣ ዕውቀት፣ ጥበብ፣ የሚያስፈልገው ድል ብቻ ነው፡፡ ስኬት ብቻ ነው፡፡ እርሱ በቀላሉ ስለማይገኝ ካገኙት ሰዎች ልምድና ጥበብ መቅሰም ያስፈልገዋል፡፡›› ቀጭኗ ዕንቁራሪት አሁንም በእግሮቿ ወተቱን መምታት አላቆመችም፡፡ እግሯ እየዛለ፤ ወገቧም እየከዳት ቢመጣም ግን ከወተቱ ላይ ተደግፋ ለመስፈንጠር በመታተር ላይ ነበረች፡፡
‹‹እሺ ይሄው አንቺ እስካሁን በመልፋት ላይ ነሽ፤ ግን ምን አመጣሽ?ያንስ ከድካሜ እፎይ ያልኩት እኔ አልሻልም››
‹‹ፈጽሞ አትሻይም›› አለቻት ቀጭኗ
‹‹እንዴት››
‹‹ቢያንስ እኔ ተስፋ አለኝ፤ አንቺ ግን የለሽም፡፡ እኔ በጥረት ውስጥ ደስታን አገኛለሁ፡፡ አንቺ ግን በኀዘን ውስጥ ነሽ፡፡ ጥረትኮ ባይሳካ እንኳን ደስታን ይሰጣል፡፡ ከቁዘማና ከድብርት ነፃ ያደርጋል፡፡ የሚጥር ስለነገ፤ ያቆመ ስለ ትናንት ያስባል፡፡ የሚጥር ስለ ኑሮ ያቆመ ግን ስለ ሞት ያስባል፡፡ በሩጫው ዓለም በመጀመርያዎቹ ዙሮች ቀዳሚውም መጨረሻውም እኩል ናቸው፡፡ አንዳንዴ እንዲያውም ተሸናፊው ከአሸናፊው የተሻለ መስሎ የሚታይበትም ጊዜ አለ፡፡ ግን ደወል ይደወላል፤ ያን ጊዜም አሸናፊውና ተሸናፊው ይለያል፡፡›› 
‹‹በይ አንቺ እቴ አይሰለችሽም ቀጥይ፤ እኔ ግን በቃኝ፡፡ አንዳች ነገር ጠብ ላይል ምን አደከመኝ፡፡›› አለቻት ወፍራሟ ዕንቁራሪት፡፡
‹‹ቢያንስ ቢያንስ ደክሞሽ ሳታስቢው መሞት እየቻልሽ እንዴት ዓይንሽ እያየ ሰጥመሽ ትሞቻለሽ›› አለቻት ቀጭኗ፡፡
ወፍራሟ ግን አቆመች፡፡ ቀስ በቀስም ወደ ታች መስጠም ጀመረች፡፡ ቀጭኗ ዕንቁራሪት ልትረዳት ሞክራ ነበር፡፡ ነገር ግን ወፍራሟ ምንም ጥረት ስላላደረገች የርሷ ርዳታ ውጤት ሊያመጣ አልቻለም፡፡ የሌላ እገዛ ውጤት የሚያመጣው የራስ ጥረት ካለ ብቻ ነው፡፡ አፉን ያልከፈተን ሰው ማጉረስ፣ ላልተፈተነም ሰው ቦነስ መስጠት አይቻልም፡፡
ወፍራሟ ዕንቁራሪት ቀስ በቀስ ወደ ወተቱ ዕቃ ሥር ገባችና ተሰናበተች፡፡
ቀጭኗ ግን አሁንም ጥረቷን አላቋረጠችም፡፡ በእግሯ አንዳች ለመቆንጠጥ እየሞከረች ትታገላለች፡፡ አንዳንድ ጊዜ የወፍራሟ ጓደኛዋ መፍትሔ ይሻላል? እያለች ታስባለች፡፡ ግን ደግሞ የዚያችን መሞትና ቢያንስ የርሷን መኖር ስታየው እንደዚህ ማሰቧንም ትቃወመዋለች፡፡ አንዳንድ ጊዜ ቆም ብላ ቀጥሎ ምን ሊመጣ እንደሚችል ታስባለች፡፡ ግን ምንም ነገር ታጣበታለች፡፡ ያን ጊዜ የምታደርገው ነገር ትክክል ይሁን ስሕተት ማረጋገጥ ትቸገራለች፡፡ በእርሷና በጓደኛዋ መካከል ያለውን ልዩነት የመሞቻ ጊዜ ልዩነት ይሆን? ብላም ታስባለች፡፡
እንዲህ እያሰበች እግርዋንም እያወናጨፈች ሌሊቱን በድካም አሳለፈችው፡፡ እናም ነጋ፡፡
ሲነጋም እንደዚሁ በእግሯ መወናጨፍን መስፈንጠርያ መፈለጉን ተያያዘችው፡፡ እኩለ ቀን ድረስ ግን ምንም አልነበረም፡፡
እኩለ ቀን ላይ እግሮቿን ስታወናጭፍ አንዳች ደረቅ ነገር ነካች፡፡ ልቧ በደስታ ቀጥ ሊል ነበር፡፡ ከየት ተገኘ? አለች፡፡ እንዴት እስከ ዛሬ አላገኘሁትም?
ለካስ ላለፉት ሰዓታት ወተቱን በእግሯ ስትመታው ወተቱ እይተናጠ፣ እየተናጠ፣ እየተናጠ ሄዷል፡፡ ከጊዜ በኋላም ወደ ቅቤነት ተቀይሯል፡፡ ያን ጊዜ እግሯ የሚረግጠው ነገር አገኘ፡፡ እርሱንም  ተደግፋ ከገረወይናው ውስጥ ዘልላ ወጣች፡፡
‹‹ይብላኝ ተስፋ ቆርጦ ለሚያቆም እንጂ፣ የጣረስ አንዳች መውጫ ነገር ያገኛል›› አለች ምድር ስትደርስ፡፡

60 comments:

 1. ምርጥ ፅሁፍ እግዚአብሄር ይባርክህ፡፡

  ReplyDelete
 2. ‹‹ይብላኝ ተስፋ ቆርጦ ለሚያቆም እንጂ፣ የጣረስ አንዳች መውጫ ነገር ያገኛል››

  ReplyDelete
 3. Dn Daniel....betam harief Eyta new ayzoh berta sira and ken frie yagengnal.

  ReplyDelete
 4. ቢያንስ እኔ ተስፋ አለኝ፤ አንቺ ግን የለሽም፡፡ እኔ በጥረት ውስጥ ደስታን አገኛለሁ፡፡ አንቺ ግን በኀዘን ውስጥ ነሽ፡፡ ጥረትኮ ባይሳካ እንኳን ደስታን ይሰጣል፡፡ ከቁዘማና ከድብርት ነፃ ያደርጋል፡፡ dani betam temechtognale!!!

  ReplyDelete
 5. ቀልቤን በጣምገዝቶታል፡፡ ተስፋ ያለው ቢያንስ ስለሚሆነው ነገር ስለሚያስብ ሕይወቱን ያቆያል፡፡ በዚህ ጥረት መካከልም ያላሰበው ስኬት ላይ ይደርሳል፡፡ የተቀመጠ ነገር ይዝጋል፤ይፈርሳል፤ይበላሻል፤ይጣመማል፤ ይፈርሳል… የሚሰራ፤ ሁሌም በሙከራ ሽክርክሪት ውስጥ ያለ ግን ጥቅም ይሰጣል፤ይሻሻላል…ለስኬት ይበቃል፡፡ በእውነት ይህ ስነ ልቡናዊ ምክር ነውና በጣም ደስ ይላል፡፡ አለመሞከርን እንደመሞከር የምንቆጥር ታካቾች ከዚህ ብዙ እንማራለን ብዬ አስባለሁ
  ዳኒ ለዚህች ሀገር ዜጋ በተለይም ለመማር ልቡ ቅርብ ለሆነ ሰው እየሰጠህ ያለው ምክር፤ተሞክሮ፤ ግሳጼ እና ትምህርት መልካም ነው፡፡ ግለሰባዊ ብቻ ሳይሆን ሀገራዊ ግዴታህንም እየተወጣህ ነው ቀጥልበት፡፡
  ገበታ

  ReplyDelete
 6. I used to be thew most optimistic person you could ever find. I hated to give up when things got rough people always counted on me to see the light at the end of the tunnel. until my husband got ill, I got scared to the point where I knew the outcome. My instinct told me it was over & to give up hoping for the better. But I kept on hoping..........trying. I did everything I could in my limited power. And when the unavoidable happened I felt let down by my GOD. But the funny part is I still find myself
  hoping.......I agree with u on not giving up but its a tough road to take. Believe me I've been there and still is.

  ReplyDelete
 7. እኩለ ቀን ላይ እግሮቿን ስታወናጭፍ አንዳች ደረቅ ነገር ነካች፡፡ ልቧ በደስታ ቀጥ ሊል ነበር፡፡ ከየት ተገኘ? አለች፡፡ እንዴት እስከ ዛሬ አላገኘሁትም?

  thank you heartily you do for generation; God bless you
  Almayehu from AA
  i read always your writings it heals.

  ReplyDelete
 8. ‹‹ይብላኝ ተስፋ ቆርጦ ለሚያቆም እንጂ፣ የጣረስ አንዳች መውጫ ነገር ያገኛል›› አለች ምድር ስትደርስ፡፡REALLY

  ReplyDelete
 9. betam melkam tsihuf new.

  ReplyDelete
 10. የምታገኘውን ሞት ከመመኘት የማታገኛትን ሕይወት በሚገባ ለመኖር ጣር፡፡andand geze be hiote endeze aenet neger yegtemal.This history is good for new year.

  ReplyDelete
 11. thanks, daniel. I love it man! Min ladirigih. Always your messages are touching. I don't know how to help you so that it can reach people (many). not just few diaspora and Ethiopians in Ethiopia having access to Internet.

  ReplyDelete
 12. ብላቴናዋ ከጀርመንSeptember 12, 2012 at 8:00 PM

  እእ ዳኒ አናቆምም እንዲህያለውን ነገር ማሰብብም አያሳፍልግ የመዝለፍለፍ ሁኔታ ለሚያሳዩት ጥሩ የማንቂያ ጹሁፍናት በጣም አናመሰግናለን ክርስቲያን ተስፋ አይቆርጥም የሚለው ነገር መፈክርብቻ መሆንየለበትም እንበርታ ያገራችንንና የቤተክርስቲያናችንን ትንሳኤ እስክናይ ድረስ አናቆምም!!!!!!

  ReplyDelete
 13. you forgot your pdf audiences.I can't read this article.

  ReplyDelete
 14. Diyakon Daniel, Eskezare des yelegn neber yemetitsifehu. yehe gin Betam yemiyanad tsihuf!!! Enen honek ende ene 35 amet beteleyaye meleku bizu negeroch mokirek alesaka bilok benebere yehen tsihuf befifum post ataregim neber! weye hulu neger endetsafkewu kelal behone.

  anduwa negn.

  ReplyDelete
 15. Betam Astemari Tsihuf new. May God Bless you.

  ReplyDelete
 16. Oh, it kindles my hope again. I am one of those who are desperate, who tried a lot, but not yet successful. I always try but no change. It takes me so long. I couldn't arrive to my destination. I don't know where and when the end will be. I hope, it might take too long, one day-may be at the end of my life, I will be the one I am supposed to be. Life is a long journey, boring,and sometimes overwhelming. but the end will come if you keep on hoping.

  ReplyDelete
 17. ይየሚጓዝ ሰው ጊዜው ይረዝም ይሆናል እንጂ አንድ ቀን የሚፈልገው ቦታ ይደርሳል፡፡
  I do no how to thank you danie, nice man!!!

  ReplyDelete
 18. so interesting . betemesito new yanebebkut.betam astemari new.

  ReplyDelete
 19. u change my mind for real thanks!!!

  ReplyDelete
 20. i heard this story on the movie called" Catch me if you can" nice movie if you like dani's story please also watch this movie

  ReplyDelete
 21. አበበ ሙ በየነSeptember 13, 2012 at 9:15 AM

  ወንድም ዳንኤል እግዚአብሔር ይባርክህ::
  ተስፋ ያለመቁረጥን አንዱ በር የተዘጋ ሲመስል ሌላ በር መሻት እንደሚያስፈለግ አስተምረሕናል :: ህይዎት አልጋ በ አልጋ ሊሆን ከቶዉንም አይችልም:: ችግር በተፈጠረ ቁጥር ተስፋ ከመቁረጥ አማራጭ እየፈለጉ መራመድ እንጂ ተኝቶ መጠበቅ አያስፈልግም:: መሸሽም ሆነ ማፈግፈግ ሁለቱም ለዉድቀት ይጋብዛሉ:: ስለዚህ ሕይዎትን ተጋፍጦ ለማሸነፍ መጣር እንጂ ተስፋ አይቆረጥም :: አንድ የሃገሬ ገበሬ ወላጅ እናቱ ወደ ዘመድ ጋር ሄዶ መልዕክት እንዲያደርስ ያዙታል:: ሂድ የተባልበት ስፍራ የሁለት ቀን መንገድ ነው:: የአናቱን ትዕዛዝ ለማክበር ሰንቁን ሰነቆ ለመጉዋዝ የወጣው ብላቴና አመሻሽ ላይ ወደቤቱ ተመለሰ:: እናቱም በአግራሞት እያዩት እንዴት የሁለቱን ቀን መንገድ በአንድ ቀን ጨርሶ እንደተመለሰ ይጠይቁታል:: እናቴ ሆዴ የሁለቱን ቀን መንገድ ለመሄድ አሰብኩ አሰብኩና ደክሞኝ ሳልሄድ ቀረሁ ብሎአቸዉ አረፈ። ቻይናዎች እንደሚሉት አንድ ሺህ ኪሎሜትር ለመጉዋዝ በአንድ እርምጃ እንደሚጀመረው ሁሉ ተስፋን መሰነቅ ደግ ነው::

  ReplyDelete
 22. Thank you Dani,

  This article has a direct and timely message for me personally. It has come at a time when I am in a dilemma of quitting everything including my ten years of marriage. I am still struggling to internalize the following poem of Mother Teresa that I wish to share here as it might help others also.

  Here it goes:

  "People are often unreasonable,
  illogical and self-centered;
  Forgive them anyway.

  If you are kind,
  people may accuse you of selfish ulterior motives;
  Be kind anyway.

  If you are successful,
  you will win some false friends and true enemies;
  Succeed anyway.

  If you are honest and frank,
  people may cheat you;
  Be honest anyway.

  What you spend years building,
  someone could destroy overnight;
  Build anyway.

  If you find serenity and happiness,
  they may be jealous;
  Be happy anyway.

  The good you do today,
  people will often forget tomorrow;
  Do good anyway.

  Give the world the best you have,
  and it may never be enough;
  Give the world the best you’ve got anyway.

  You see, in the final analysis,
  it is between you and God;
  It was never between you and them anyway."


  Huh!

  I am not sure if I will overcome the serious contemplation of quitting I am currently harboring.

  Please pray for me.
  Help me God!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Surprising, I am facing the same problem brother. I did decide ,when I read this message of yours to depart from her.And I laughed and said what a coincidence!I actually decided to move on,my heart always tells me to move on.But I don't know what my decision bring to my children. Anyway It is better to test the other way than crying and fighting with them.Actually thinking to depart from my sweet children makes me to feel as if moving my body without a soul. My soul will always cherish with them, it is my body which is creating a problem, so I will move it far from them,but I won't quit on them.Transition and transformation is always tough.

   Delete
 23. Dani PDF yelem ende?

  ReplyDelete
 24. it keeps the current situation indicator for that matter.where as hoping is life by itself.for thinking my, hope is not always succeeded rather on the way.
  your reader simachew
  from A.A

  ReplyDelete
 25. ‹‹ለምን የተሸነፉትን ትጠቅሻቸዋለሽ? ከተሸነፉት መማር ያለብንኮ ለምን ተሸነፉ የሚለውን እንጂ የጥረት መጨረሻው መሸነፍ መሆኑን አይደለም፡፡ ሽንፈትኮ ትምህርት አያስፈልገውም፡፡ ሽንፈትኮ ልምድ አያስፈልገውም፡፡ ዕውቀት አያስፈልገውም፡፡ ሽንፈት እጅን አጣጥፎ መቀመጥ ብቻ ይበቃዋል፡፡ ለሽንፈት ምሳሌ መጥቀስ አያስፈል ግሽም፡፡ ሽንፈት ማለት በቀላሉ የሚደረስበት ነገር ነው፡፡ ሳትለፊ የምታገኚው ነገር ነው፡፡ ምሳሌ፣ አርአያ፣ ልምድ፣ ዕውቀት፣ ጥበብ፣ የሚያስፈልገው ድል ብቻ ነው፡፡ ስኬት ብቻ ነው፡፡ እርሱ በቀላሉ ስለማይገኝ ካገኙት ሰዎች ልምድና ጥበብ መቅሰም ያስፈልገዋል፡፡›

  ReplyDelete
 26. It tells me to continu my effort to get what i want.Never stop.
  May GOD give u more!!!

  ReplyDelete
 27. This remind me the history of St Yared.

  ReplyDelete
 28. ዲያቢሎስን እጅግ የሚያስደስቱት ሁለት ነገሮች አሉ።

  አንደኛው “ተስፋ” ማስቆረጥ ነው።

  ሁለተኛው አሁንም “ተስፋ” ማስቆረጥ ነው!

  የአምናውን የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ያየ ገጣም እንዲህ አለ።

  ተስፋ
  ለለፋ
  ትመጣለች ፊሽካ ሳትነፋ!


  ወንድም ዓለም ዲያቆን ዳንኤል እርስዎ የሚያነቡት መጽሐፍት የት እንደሚታተሙ ማወቅ የዘወትር ጉጉቴ ነው!! ብሩህ አእምሮ ግሩም ተሰጥዎ አልዎት። ስለሀገርና ስለቤተክርስቲያን ስለሰው ልጅ ያልዎት አመለካከት ደስ ያሰኘኛል!

  “ክፉ ዘመን አይምጣ ዘመድ እንዳላጣ” አሉ እቴጌ ጣይቱ። አዲሱ ዘመን ለእርዎ እና ለውድ ቤተሰብዎ ዘመነ ፍስሃ ዘመነ ሠላም ይሁንልዎ። አዲሱ ዓመት ለእናት ቤተክርስቲያን ለእናት ሀገራችን ለሁላችንም ዘመነ ሠላም ዘመነ ፍስሃ ይሁን፤ አሜን።

  ReplyDelete
 29. እግዚአብሔር ዋጋህን ይክፈልህ…..ቢያንስ እኔ ተስፋ አለኝ፤ አንቺ ግን የለሽም፡፡ እኔ በጥረት ውስጥ ደስታን አገኛለሁ፡፡ አንቺ ግን በኀዘን ውስጥ ነሽ፡፡ ጥረትኮ ባይሳካ እንኳን ደስታን ይሰጣል፡፡ ከቁዘማና ከድብርት ነፃ ያደርጋል፡፡
  ተስፋ የቀረጥኩበትን ነገር ይህንን አስተያየት ጽፌ እነዳበቃሁ ለመጀመር ወሰንኩ………….በጥረት ውስጥ ደስታ አለና፡፡
  ረጅም ዕድሜ ከጤና ጋር ያድልልኝ፡፡
  ዘሪሁን ከሀላባ ቁሊቶ

  ReplyDelete
 30. ለማሸነፍ ትልቁ መፍትሔ አቋምን መቀየር ሳይሆን መንገድን መቀየር ነው፡፡ የተለያዩ ነገሮችን መሞካከር ሳይሆን አንድን ነገር በተለያዩ መንገዶች መሞከር ነው፡፡ የተለያዩ ነገሮችን ማየት ሳይሆን አንድን ነገር በተለየ መንገድ ለማየት መቻል ነው፡፡ ተስፋ መቁረጥ ሳይሆን፣ በውሳኔ ጊዜ መቁረጥ መቻል ነው፡፡ የምታገኘውን ሞት ከመመኘት የማታገኛትን ሕይወት በሚገባ ለመኖር ጣር፡፡
  Egziabher Yibarkih, Hulem Tsinatun Yistih,Ante ewnetegna memhir neh

  ReplyDelete
 31. የምታገኘውን ሞት ከመመኘት የማታገኛትን ሕይወት በሚገባ ለመኖር ጣር!!! በጣም የወደድኩት አባባል
  የምትጽፋቸው ጽሁፎች እንደ አንዳች ነገር ውስጥን ይነካሉ በርታ ለእንደኔ አይነት አውቀተ ላነሳቸው ሰውች ዕውቀትን መጨመር ነው።

  ReplyDelete
 32. Good View Dani God Bless YOU!!!!!

  ReplyDelete
 33. እንዲህ እያሰበች እግርዋንም እያወናጨፈች ሌሊቱን በድካም አሳለፈችው፡፡ እናም ነጋ፡ እስከሚነጋ ድረስ መድከም ይኖርብናል እንጂ በምሽት መድከም የለብንም::

  ReplyDelete
 34. እንዲህ እያሰበች እግርዋንም እያወናጨፈች ሌሊቱን በድካም አሳለፈችው፡፡ እናም ነጋ፡ ዋናው መንጋቱ ነው ሲነጋ መላ
  አይጠፋም::

  ReplyDelete
 35. pleas rember us about waldeba monastery

  ReplyDelete
 36. the right thing to do is the reason why you are created to do,no one can tale you what to do but only GOD!BECAUSE GOD IS THE CREATOR OF YOU ,HE KNOWS WHAT POTENTIALS,QUALITY,AND SKILLS YOU HAVE BECAUSE HE IS THE CREATOR OF YOU,HE MADE YOU FOR A SPECIFIC PURPOSE,YOU MUST ASK LORD GOD BEFORE ATTEMPTING TO DO ANY THING IN YOUR LIFE,WAKE UP DO YOU KNOW WHY YOU ARE FRUSTRATION,DISAPPOINTED,HARDWORKING WITH OUT SATISFACTION? IT IS BECAUSE YOU ARE DOING THE WRONG THING!YOU MUST VALUE SUCCESS IN TERMS OF WHETHER YOU ARE DOING THE GOD GIVEN PURPOSE FOR YOUR LIFE OR NOT.....

  ReplyDelete
 37. Diyakon Daniel i really like your message it is so interesthing!!!!! I do not have any word about you i am just saying God bless u&your family too!!!

  ReplyDelete
 38. First of all ,I would like to thank you for your good and timely script of yours.This script could be interprated in many ways,but I would ike to interprate it positively.
  Transformation has cost.like those frogs which were trying to feed on the milk in the bowl and hard to go out from it. As the Deputy PM said'' we can't stand up in the middle of the mountain due to fattig, we have to use all the strength we have to reach to the top which will be safe for us.''

  Right now Ethiopia has started to establish 11 fertilizer factories with out which Ethiopia will be susceptible to foreign influence.Because most of our farmers are now using fertilizer without which the land won't be productive. The other factories which have equal importance with that of the fertilizer factories are the 10 sugar factories which are under construction now. These sugar factories will provide us ethanol which could be used as fuel, sugar,electric power,animal feed and so on. The other most important thing for Ethiopia is the hydro electric power dams under construction,and rail way construction. All these constructions can't be implimented without the full understanding of the people and what opportunity cost would the people pay. The first opportunity cost is inflation, we have two choices :
  one to stop those mega projects,and die like the frog which gave up to come out of the bowl and sink.

  The other choice is to persevere and finish those mega projects.When we say to persevere, we shouldn't forget that we could face hard times even worse than we are facing now,but not for very long time. Those problems could make us to lose hope,but we have to be encouraged by the light we are looking at the end of the tunnel. The political atmospher could even be challenging to pursue our goal,but we should move on in a positive direction atleast in finishing those mega projects. After all if we give up, we will die, so better to fight,fight and fight until death, this fight of ours is on poverty and ignorance.
  Is there any shame worse than begging for food for more than half a century? Is there any shame worse than fighting each other for power while there is enough assignment for everyone to do? We have to not give up,but we should strive relentlessly to come out of this.Let us share the burden and do what we can do, to see a better future. May God be with us!

  ReplyDelete
 39. I don't give Up in life cause I am always hoping the "Butter" it leads to the light...thanks Dani

  ReplyDelete
 40. ዳኒ እግዚሃብሄር ረጅም እድሜ ይስጥክ. ከሁለቱ ዕንቁራሪቶች ትልቅ ትምህርት አግኘቻልወ መቻም ቢሆን ተስፋ መቁረጥ እንደሌለብኝ የያዝኩትን ነገር አጥብቄ በመያዝ ወደ ፊት መጎዝ እንዳለብኝ ያስተማረኝ ርዕስ ነው ፡፡እግዚሃብሄር ካንተጋር ይሁን!!!

  ReplyDelete
 41. Very very intereseting idea

  ReplyDelete
 42. ሰላም ና ረጅም ዕድሜ እንዲሰጥህ እየተመኘው እነሆ የማስበውን ልንገርህ፡፡ተስፋ መቁረጥ ከብዙ ነገሮች ሊመነጭ ይችላል፡፡ ለምሳሌ እኔ ሰራተኛ ነኝ ግን ማታ መማር እፈልጋለው የምሰራው ከ ጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 3፡00 ነው እሚያሰሩኝም ሰዎች እኔ ብቻ ልብላ የሚሉ ናቸው ይህንን ስል ግን ስሜታዊ ሆኜ አይደለም ውስጤ በጣም ስለደማ ነው፡፡ ይገርምሃል እነሱ የሚያኖሩን የሚመስላቸው ሰዎች አሉ፡፡ግን እስከ መቼ መተዛዘን መረዳዳት ጠፍቶ እኔ ልብላ እናንተ የበላንበትን እጅ አሽትቱ ግን ለምን እባክህን ብዙ ሰው ሊማርበት ይችላልና እስቲ ትንሽ ምክር ሰጠን
  ትህትና ነኝ ከ አ.አ

  ReplyDelete
 43. ምርጥ ፅሁፍ

  ReplyDelete
 44. መሆኑ ከማቆምና ከመቀጠል የትኛው ይመረጣል? ከማቆም ምን ይገኛል? ከተስፋ መቁረጥ በቀር፡፡ የሚጓዝ ሰው ጊዜው ይረዝም ይሆናል እንጂ አንድ ቀን የሚፈልገው ቦታ ይደርሳል፡፡ የቆመ ሰው ግን እንኳን ወደሚፈልግበት ለመሄድ ወደ ተነሣበት ቦታም ተመልሶ አይደርስም፡፡ የሚታገል ሰው አንድ ቀን ያሸንፋል፤ ያቆመ ሰው ግን ሳይማረክ እጁን ሰጥቷል፡፡ ደጋግሞ የሚያንኳኳ ሰው ከተኙት ሰዎች አንዱን መቀስቀሱ አይቀርም፤ ማንኳኳት ያቆመው ግን እንኳን ሊቀሰቅስ ራሱም ይተኛል፡፡ የሚሄድ መኪና ጋራጅ ይደርሳል፤ የቆመ መኪና ግን ባለበት ይወላልቃል፡፡
  ለማሸነፍ ትልቁ መፍትሔ አቋምን መቀየር ሳይሆን መንገድን መቀየር ነው፡፡ የተለያዩ ነገሮችን መሞካከር ሳይሆን አንድን ነገር በተለያዩ መንገዶች መሞከር ነው፡፡ የተለያዩ ነገሮችን ማየት ሳይሆን አንድን ነገር በተለየ መንገድ ለማየት መቻል ነው፡፡ ተስፋ መቁረጥ ሳይሆን፣ በውሳኔ ጊዜ መቁረጥ መቻል ነው፡፡ የምታገኘውን ሞት ከመመኘት የማታገኛትን ሕይወት በሚገባ ለመኖር ጣር፡፡
  እነዚህ ሁለት ፓራግራፎች በጣም ነክተውኛል:: may God bless u

  ReplyDelete
 45. "የምታገኘውን ሞት ከመመኘት የማታገኛትን ሕይወት በሚገባ ለመኖር ጣር፡፡" እውነት ነው ህይወት ውድ ናት

  ReplyDelete
 46. በጣም የሚያምር እና አስተማሪ ነው፡፡ Long life 4 u

  ReplyDelete
 47. mikrihin tegbarawi endadergwu yadirgegn

  ReplyDelete
 48. እድሜህን ያርዝምልን::

  ReplyDelete
 49. Dn. Daniel Tebarke tesefa bekoretekubete seate yehen tsehufe selanbebeku ejege tedesechalhu መሆኑ ከማቆምና ከመቀጠል የትኛው ይመረጣል? ከማቆም ምን ይገኛል? ከተስፋ መቁረጥ በቀር፡፡ የሚጓዝ ሰው ጊዜው ይረዝም ይሆናል እንጂ አንድ ቀን የሚፈልገው ቦታ ይደርሳል፡፡ የቆመ ሰው ግን እንኳን ወደሚፈልግበት ለመሄድ ወደ ተነሣበት ቦታም ተመልሶ አይደርስም፡፡ የሚታገል ሰው አንድ ቀን ያሸንፋል፤ ያቆመ ሰው ግን ሳይማረክ እጁን ሰጥቷል፡፡ ደጋግሞ የሚያንኳኳ ሰው ከተኙት ሰዎች አንዱን መቀስቀሱ አይቀርም፤ ማንኳኳት ያቆመው ግን እንኳን ሊቀሰቅስ ራሱም ይተኛል፡፡ የሚሄድ መኪና ጋራጅ ይደርሳል፤ የቆመ መኪና ግን ባለበት ይወላልቃል፡፡
  ለማሸነፍ ትልቁ መፍትሔ አቋምን መቀየር ሳይሆን መንገድን መቀየር ነው፡፡ የተለያዩ ነገሮችን መሞካከር ሳይሆን አንድን ነገር በተለያዩ መንገዶች መሞከር ነው፡፡ የተለያዩ ነገሮችን ማየት ሳይሆን አንድን ነገር በተለየ መንገድ ለማየት መቻል ነው፡፡ ተስፋ መቁረጥ ሳይሆን፣ በውሳኔ ጊዜ መቁረጥ መቻል ነው፡፡ የምታገኘውን ሞት ከመመኘት የማታገኛትን ሕይወት በሚገባ ለመኖር ጣር፡፡

  ReplyDelete
 50. የሚጥር ስለነገ፤ ያቆመ ስለ ትናንት ያስባል፡፡ የሚጥር ስለ ኑሮ ያቆመ ግን ስለ ሞት ያስባል
  i like it

  ReplyDelete
 51. Wow Daniel Egziagheir yibarkeh.i am a 23 years old young man and you touched my life.i mean this is exactly what i think it should be.i mean i always feel the kind of desperation that the thin frog felt but i just keep going thinking that i will one day find something to depend on and say goodbye to all my desperation and start the kind of life and have the kind of success i dream. This was so inspiring.God Bless You. Edmena tena Yisteh.

  ReplyDelete
 52. let God bless you.we need the real ETHIOPIAN like you.

  ReplyDelete
 53. let God ble3ss you

  ReplyDelete
 54. ዳኒዬ እግዚያብሔስ ይጠብቅህ! ተባረክ 🙏🙏🙏

  ReplyDelete