Thursday, August 16, 2012

ከፊታችን ያለው መንገድ


click here for pdf
በትግራይ ክልል ዐድዋ ውስጥ ልዩ ስሙ እንዳ አቡነ ገሪማ በተባለው ቦታ ጥቅምት 25 ቀን 1928 ዓም የተወለዱት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አምስተኛው ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ማረፋቸውን ቤተ ክርስቲያኒቱ በይፋ ገልጣለች፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ከተሰየሙት ፓትርያርኮች መካከል በመንበራቸው ላይ ብዙ ጊዜ የቆዩት አቡነ ጳውሎስ ናቸው፡፡ ለሃያ ዓመታት፡፡
በቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪክ ውስጥ ካለፉት አምስት ፓትርያርኮች መካከል አንደኛው በደርግ ተገድለዋል፤ አንደኛው ተሰድደው ወጥተዋል፤ ሦስቱ ደግሞ በአገልግሎት እያሉ ዐርፈዋል፡፡ ምንጊዜም ቢሆን አንዲትን ቤተ ክርስቲያን ይመራ የነበረ አባት ሲያርፍ በቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች ዘንድ በአንድ በኩል ያረፉት አባት እንዴት ነበር ያገለገሉት የሚል ጥያቄ ሲነሣ በሌላ በኩል ደግሞ ቀጣዩስ ማን ይሆናሉ የሚል ጥያቄ ይፈጠራል፡፡
በኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ቀኖናና ትውፊት መሠረት አንድ ፓትርያርክ ሲያርፉ የሚከናወኑ ሥርዓቶች አሉ፡፡ እነዚህም በስድስት ይከፈላሉ፡፡

 1. ሁኔታውን ማወጅ
ቤተ ክርስቲያንን የሚመራ አባት ሲያርፍ ቤተ ክርስቲያኒቱ በይፋ ማወጅ አለባት፡፡ ይህ አባት በመንግሥት ወይም በአላውያን ተይዞ የደረሰበት ካልታወቀም ሲኖዶሱ የመጨረሻውን እስኪያውቅ ድረስ በቦታው ሰው ሳይተካ ሥራውን እየሠራ ይቆያል እንጂ በይፋ ሳያውጅ ሌላ አባት ወደ መምረጥ አይሄድም፡፡ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን በተመለከተ በታሪካችን የተሠራው ስሕተት ይህ ነበር፡፡ እርሳቸው ማረፋቸውን በይፋ ቤተ ክርስ ቲያኒቱ ሳታውጅ ወደ ሌላ ምርጫ ገባች፡፡ ይህም ከሌሎች እኅት አብያተ ክርስቲያናት ጋር በቀኖና ከማለያየቱም በላይ በቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪክም ላይ ጥቁር ነጥብ ጥሎ አልፏል፡፡
 1. የኀዘን ጊዜ መወሰን
የቅዱስ ሲኖዶስ ደንብ የአዲሱ ፓትርያርክ ምርጫ የሚከናወነው ነባሩ አባት ካረፈ ከዐርባ ቀን በኋላ መሆኑን ይገልጣል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ዐርባ የኀዘን ቀናት ስለሚታወጁ ነው፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ለዐረፉት አባት የፍትሐት ጸሎት ይደረጋል፡፡ ታሪካቸው በቤተ ክርስቲያን ደረጃ በይፋ ይወጣል፡፡ ስለነበሩበት የአገልግሎት ዘመን ይነገራል፡፡ በየቤተ ክርስቲያኑም ጸሎት ይደረግላቸዋል፡፡ እስካሁን ድረስ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ይፋዊ የኀዘን ጊዜ አላወጀም፡፡ ይህ ግን የሚያስፈልግ ይመስለኛል፡፡
 1. ዐቃቤ መንበር መሠየም
የቅዱስ ሲኖዶሳችን ደንብ በምእራፍ 3 በቁጥር አንድ ላይ ዐቃቤ መንበር ዕለቱኑ መሰየም እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ ይሄ ሁኔታ ግን የብጹዐን አባቶችን መሰብሰብ የሚጠይቅ በመሆኑ ብዙ ጊዜ ዕለቱን ለማከናወን ያስቸግራል፡፡ ዐቃቤ መንበሩ ቀጣ አባት ተመርጦ መንበሩን እስኪረከብ ድረስ መንበሩን በመጠበቅና የቤተ ክርስቲያኒቱን የዕለት ተዕለት ተግባር በማከናወን ይቆያል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶሱ ደንብ ‹‹በማዕረገ ጵጵስና ቅድሚያ ካላቸው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት መካከል›› እንደሚመረጥ ይደነግጋል፡፡ ዐቃቤ መንበሩ ‹‹ፓትርያርክ እስኪሾም ድረስ የነበረውን ጠብቆ ማቆየት እንጂ መሾም፣ መሻር፣ መጨመር፣ መቀነስ፤ አዲስ ሥርዓት እና ደንብ ማውጣት አይችልም፡፡››
 1. የቀብሩን ሥነ ሥርዓት ማከናወን
የአንድ ፓትርያርክ የቀብር ሥነ ሥርዓት የቤተ ክርስቲያኒቱን ታላቅነት፣ ቀኖና እና ጥንታዊ ትውፊት የሚያሳይ መሆን አለበት፡፡ ይህንንም ነገር ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ ለማከናወን ራሱን የቻለ መርሐ ግብር ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ምክንያት ነው የቅዱስ ፓትርያርኩ ቀብር በአስቸኳይ የማይከናወነው፡፡ የሚቀበሩበት ቀን፣ የሚቀበሩበት ቦታ እና የቀብሩም ሥነ ሥርዓት አስቀድሞ ደንብና ሥርዓት የወጣለት መሆን አለበት፡፡ ያረፉትን አባት ሕዝቡ የሚሰናበትበት ሥርዓት፣ በቀብሩ ቀን የሚነገሩትና የሚዝሙት ነገሮች፣ የአካሄድና የቀብር ሥርዓቱ ሁሉ ዝርዝር የሚያስፈልገው ነው፡፡
አሁን በቤተ ክርስቲያናችን በአስቸኳይ የሚያስፈልጉት ከላይ የተጠቀሱት አራት ነገሮች ናቸው፡፡ ስለ አቡነ ጳውሎስ የቱንም ዓይነት አመለካከት ቢኖረንም ለቤተ ክርስቲያኒቱ ክብርና እርሳቸውም በሕይወት ዘመናቸው በነበሩ ጊዜ ስለ ፈጸሟቸው በጎ ተግባራት ሲባል ነገሮች የቤተ ክርስቲያኒቱን ታሪካዊነት፣ ጥንታዊነትና ሰላማዊነት በሚያሟሉ ደረጃ መፈጸም አለባቸው፡፡
የአንድ ፓትርያርክ ዕረፍት የአንዲት ቤተ ክርስቲያን የአንደኛው የታሪክ ምዕራፏ ማጠናቀቂያ ነው፡፡ ሌላኛውን ምዕራፍ በተገቢው መንገድ ለመጀመር ያለፈውን ምዕራፍ በተገቢው መንገድ ማጠናቀቅ ያስፈልጋል፡፡ አሁን ይቅር ባይነትና ርኅራኄ፣ ለቤተ ክርስቲያን ሰላም ማሰብና ለምጣዱ ሲባል አይጧን ማለፍ የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ ነን፡፡
አሁን ከምንም ጊዜ በላይ ነገሮችን በሰከነና መንፈሳዊ በሆነ መልኩ ለማስኬድ ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ብዙ ይጠበቃል፡፡ ቢያንስ እነዚህ ዐርባ የኀዘን ቀናት ትውፊታችንን፣ ቀኖናችንን፣ ኢትዮጵያዊ ጨዋነታችንንም በጠበቀ መልኩ መከናወን አለባቸው፡፡ ስለ ሌላው ነገር ለማሰብ ጊዜ አለን፡፡
 1. የምርጫውን ሂደት ማከናወን
እኔ እስከማውቀው ድረስ በቅዱስ ሲኖዶሱ ደንብ ላይ ከተገለጠው በቀር የአዲስ ፓትርያርክን አመራረጥ በተመለከተ የተዘጋጀ ዝርዝር ደንብ የለንም፡፡ በግብፅ ቤተ ክርስቲያን እንዳየነው ከሆነ ራሱን የቻለ ዝርዝር ሕግ አለ፡፡ አስመራጩ ከየት ይዋቀራል? ምርጫው ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል? ጥቆማ ከየት ይመጣል? የጠቋሚና የተጠቋሚ መመዘኛ ? የምርጫው ሥነ ሥርዓት? የጸሎቱና የዕጣ ማውጣቱን ሂደት በተመለከተ ይደነግጋል፡፡ እያንዳንዱ ተግባር ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድም ያትታል፡፡
ቢቻል ቅዱስ ሲኖዶስ አስቀድሞ ቋሞ የሆነ ተመሳሳይ ሕግ ቢኖረው፡፡ ካልተቻለም ቢያንስ ለዚህኛው ምርጫ የሚያገለገል መመርያ ቢያወጣ፡፡ ቀጣ ምርጫ በተቻለው መጠን በቻል የሁሉንም ባይቻል ደግሞ የአብዛኛውን ምእመን ይሁንታ እንዲያገኝ፤ ምርጫው በድምጽና በቆጠራ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊነትና ትውፊታዊነትን በተላበሰ መልኩ በጸሎትና በዕጣም እንዲከናወን ቢደረግ፡፡ ዕጩዎቹ ቀድመው ታውቀው ሕዝቡ የሚጸልይበት የጸሎት ጊዜ ቢኖር፡፡ የምእመናን ተሳትፎ ተጠናክሮ የሚታይበትና አባቶችና ልጆች አንድ ሆነው የሚመሰክሩበት ጊዜ እንዲሆን ከወዲሁ ማሰብ ያስፈልጋል፡፡
 1. መምረጥ
ይህ ማለት ቀጣ ፓትርያርክ የሚታወቅበትና የመጨረሻው የምርጫው ዕለት ማለት ነው፡፡ በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ሕግ ከመጨረሻዎቹ ሦስት አበው መካከል ስማቸው በመንበሩ ላይ ተደርጎ ከጸሎት በኋላ ዕጣ የሚወጣበት ዕለት ማለት ነው፡፡ በኛ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ድምጹ ተቆጥሮ አብላጫውን ያገኘው በቅዱስ ሲኖዶሱ ጸድቆ ቃለ መሐላ የሚፈጽምበት ጊዜ ነው፡፡
በዚህ ጉዳይ ወደፊት በዝርዝር እንነጋገርበታለን፡፡

78 comments:

 1. Replies
  1. "አሁን በቤተ ክርስቲያናችን በአስቸኳይ የሚያስፈልጉት ከላይ የተጠቀሱት አራት ነገሮች ናቸው፡፡ ስለ አቡነ ጳውሎስ የቱንም ዓይነት አመለካከት ቢኖረንም ለቤተ ክርስቲያኒቱ ክብርና እርሳቸውም በሕይወት ዘመናቸው በነበሩ ጊዜ ስለ ፈጸሟቸው በጎ ተግባራት ሲባል ነገሮች የቤተ ክርስቲያኒቱን ታሪካዊነት፣ ጥንታዊነትና ሰላማዊነት በሚያሟሉ ደረጃ መፈጸም አለባቸው"
   kalhewet yasemalen dani
   egne astwayoche khonene gorebtochachen liy eyhone kalwo neger memare alben lhulm ሁሉም ከሱ ነውና መልካሙን ሁሉ እንዲያደርግ በጸሎት እግዚአብሔርን እንጠይቅ

   Delete
 2. this is what the church has to do, thank u dani

  ReplyDelete
 3. ዲ/ን ዳንኤል በ እውነት ደስ የሚል ገለጻ ነው::

  ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በ 2 ሲኖዶስ ተከፍላ የህገ ወጥ እና ህጋዊ እየተባለ ቆይቷል:: የውጩ ሲኖዶስ ጋር ያለው ግንኙነት እና ስምምነትን በተመለከተ ምን የምትለን አለ? ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ፓትሪያርክ ዘኢትዮጵያ በስደት እያሉ ሌላ እንዴት ሊመረጥ ይችላል ?
  የውጩን አባቶች ያላሳተፈ ምርጫ ለቤተ ክርስቲያናችን የባሰ ጉዳት አይሆንምን ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. That is correct. I strongly agree on it.
   First, peace then election. Conflict among spiritual fathers should be terminated soon.
   Then, based on the synod guide/church bylaw the next patriarch should be assigned.

   Delete
  2. enem temesasay amelekaket alegn.

   Delete
  3. I share your idea perfectly therefore dani I m expecting you so say something.dani,do believe that the talk b/n fathers is wright?

   Delete
 4. አንተ እኮ ተናግረህ ነበር ዲን. ዳንኤል። ይኸው ከዚህ ላይ
  ....
  ዛሬ በመንበሩ ላይ ያሉት አቡነ ጳውሎስም ሆኑ ተሰድደው በአሜሪካ ያሉት አቡነ መርቆሬዎስ ማረፋቸው አይቀርም፡፡
  ያን ጊዜ አዲሱን አባት እንዴት ነው መምረጥ ያለብን? የእግዚአብሔርንስ ፈቃድ እንዴት እናገኛለን? ከፖለቲካዊና ሌሎች ተጽዕኖዎች ነጻ የሆነ፣ ሁሉንም የሚያግባባ ምርጫ እንዴት ማድረግ ይቻላል? ቅሬታዎችንና ነቀፌታዎቸን እንዴት ማስተናገድና መፍታት ይቻላል? መራጮች እነማን ናቸው? መራጮችስ እንዴት ይመረጣሉ? ለፕትርክና ዕጩ መሆን የሚችሉት እነማን ናቸው? ምን ምን መመዘኛ ያሟሉ ይወዳደራሉ? የሚሉትና ሌሎች በዝርዝር ተደንግገው የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች ሁሉ እንዲያውቁት መደረግ አለበት፡፡ አሠራራችን ሁሉ እንደ ሐበሻ መድኃኒት ተደብቆ የሚኖርበት አሠራር እየጎዳን ነው፡፡ ሌላ ጭቅጭቅ ደግሞ ለትውልድ እንዳናተርፍ፡፡
  .....
  http://www.danielkibret.com/2012/05/118.html

  ReplyDelete
 5. egiziabeher le betecirestiyan yemebegewin yamitalen.

  ReplyDelete
 6. Egziabher amlak yehizbun enba yemiyabs,le amlaku, lemiemenuna lehilinaw yetamene, lebetekrstiyan tebaki yemihon, mengawin kemebeten yemiyadin cher tebaki yedilen zend bekan bilen entsely. Geta Medhanialemim yihin yifetsimilin zend enatu Dingil Maryam bemiljawa atleyen.

  ReplyDelete
 7. Ene Yedesta gize maweje new yalebin !!this is because he was distructing the church for the past 20 years together with TPLF !! lenegeru nisha sayigebu kehone yemotutue hazen yasfelegala leka!!!
  or the praying should be to look for blessed father in the future!!
  leka yeethiopia amelake aletewatem hageritunena netechrisianin ambagenenochina musegnochin(patriarich and prime minister ) berasu gize asewegedachew efoye new !!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. i can easily understand that you are not a member of the Ethiopian Orthodox Church.
   Please be a Christian and remember the words of Jesus Christ.

   Delete
  2. እግዚአብሄር አስተዋይ ልቡና ይስጥህ? ክርስቲያን እንደዚህ አያስብም፤አስቦም አያውቅም!!

   Delete
 8. you right brother this what we need for our church. Hopeofully our fathers they will do it. We need it badly to renew our church history. God is great i belive he will fixed. God be with us and with our church.
  Habtamu the GA

  ReplyDelete
 9. Hi Danni
  Really great work, always inspiring and I just want to tell you how much I enjoy reading your wisdom - and, of course, putting it to some good use
  Thank you so much ... and may His light continue to shine in your life!
  Please contact me direct through my Email address, I will be waiting to hear from you soon.

  Bereket

  Ps. I am getting error message 404 for this topic only


  ReplyDelete
 10. i am really sorry to read this from u Dn Daniel, i used to respect u and taught u r one of the most wise man in our church ,but now u did very unforgetabel mistake.You were expected to talk about bringing the two side fathers together, but u just start talking about electing new patriaric...u should be sorry for what u write...i used to like u ...
  but now...

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሹምት ከእግዚአብሔር እንጂ ከሰው አይደልም፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ለቤቱ ያውቅበታል፡፡
   እውነት የቀድሞው ፓትርያርክ ከሃገር ሲሰደዱ እግዚአብሔር መመለስ አቅቶ ይመስልሃል/ይመስልሻል?
   እግዚአብሔር ሁሉንም በምክንያት እንጂ አንዲቷንም ነገር ያለምክንያት አያደርግም፡፡ እግዚአብሔር ለቤቱ ጠባቂ የቀድሞውን ፓትርያርክ ከፍለገ ያመጣቸዋል ፣ አዲስ ከፈለገ ደግሞ አዲስ ይሾማል ፣ ለሱ ምንም የሚሳንው ነገር የለም ፡፡ ሁሉ እንደሱ ፍቃድ እንጂ እንደኛ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ለሁላችንም ልቦና ይስጠን፡፡
   ሁሉም ከሱ ነውና ምልካሙን ሁሉ እንዲያደርግ በጸሎት እግዚአብሔርን እንጠይቅ፡፡

   Delete
  2. Who you are to bring the former father. We don't want a father who escaped letting Ethiopian people. He was a strong follower of the dictator Derg. No need to be prophet to know what will happen if he come here and elected. We never and ever want him. You have top know this. We need a father from Ethiopia not from diaspora.

   Delete
  3. Hey dear,
   what u said above is part of the election. It is God's will besides,Dn.Daniel is not part of the election committee. If you really love your church, just pray. I guess it is not about who said what, it is a power of prayer and the will of God that will keep our church safe!!!

   Delete
  4. hulunim ande emiaderg erik yasfeligal...ye dani azmamia endeza meselenge....great dani...hulem leselam libachin kifte yihun.

   Delete
 11. hay Dn.dani u have said good but what was it seems the election after three patriarchal passed away before?? now we are in this world, our papasat will do by respecting the dogma and kenona of our church not by counting sounds of the people which have greater in number. i think it can't be manageable, brought dialogue among the people, conflict among the group or individuals etc...

  ReplyDelete
 12. ለቤተ ክርስቲያን ሰላም ማሰብና ለምጣዱ ሲባል አይጧን ማለፍ የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ ነን፡፡

  ReplyDelete
 13. ዲ/ን ዳንኤል፡በአባታችን ድንገተኛ እረፍት አዝኛለሁ፡፡ በረከታቸው ይደርብን! ለአባታችን በጎ አመለካከት ኖረንም አልኖረንም ለቤተ ክርስቲያን ክብርና ልዕልና ሲባል ሁላችንም የሚጠበቅብንን ማድረግ እንደሚገባን ያስተላለፍከው መልዕክት ጠቃሚና ልንተገብረው የሚገባ መልዕክት ነው፡፡ ወደፊት ያለው ሁኔታ ግን ከምንም በላይ አሳሳቢ ነው፡፡ ምን ዓይነት ትዕይንት እንመለከት ይሆን! በዓለም እንደምናየው በእኛም ቤት አልፎ አልፎ እንደምንመለከተው የምረጡኝና ለሥልጣን ሽኩቻ ወይስ እንደቀደሙት አበው አይገባኝም የሚል ልባዊ ትህትና? ወይስ ኢሕአዴግ እንደተለመደው ለራሱ ፖለቲካ የሚስማማውን አባት በደብዳቤ ይሾም ይሆን? አባት ሆይ እኛን ልጆችህን በቸርነትህ ጎብኘን!

  ReplyDelete
 14. Hello dear brother than you for valuable information and direction for all please in addition to your idea let us pray for our mother Church??

  ReplyDelete
 15. As an opinion of an ordinary person, your ideas look good. But don't try to impose them anymore.

  ReplyDelete
 16. Daniel

  It is time to be tested by God.How you ignore the real situation which our church has faced. There is 'Synod' in USA. Unless we solve the exile 'synod' problem at this time, still we will live in dark era. It is people like you responsibity to write about this issue. i surprised by your ignorance on exile 'synod'.

  ReplyDelete
 17. ዳኒ ጥቆማህ እጅግ ጠቃሚ ነው::
  ከዚህ ቀደም እንደምታደርገው ያለ እይታህን አቅርበሀል:: የሚጠቀም ይጠቀምበታል:: ያደረከውን ካደረክ በኋላ ዝም ማለት መልካም ነው:: ከዚህ በላይም በሕግ በሥርዓት ተጉዘን እግዚአብሔርን ደስ የምናሰኝበት ምግባር እንዲኖረን በምናውቀው ጉዳይ ላይ ሳይቀር ዘዳግም ያስፈልገናል:: ብዙ ይጠበቅብህ እንደሆነ እንጂ እንደኔ ያለፍከው ድንበር አልታየኝም:: ሸንበቆን ይመስል ነፋሱን ጠብቀው ወገናችን ወዲህ ነው ከሚሉ አስመሳዮች ይሰውርህ:: በደጅ እንደ ቲፎዞ የምትጮሁ ሰዎች ቤተሰብ ከሆናችሁ ነገ በሚሆነው ከማዘንም ከመለያየትም ከሀሜትም . . . ለመዳን አሳብ ከሌላችሁ ቢያንስ አቋም ይኑራችሁ:: ልምዳችንንማ አየነው እኮ አለያየን ከፋፈለን ቢያንስ በመረጃ አንድ እንሁን እንጅ:: እውነቱ አይጎዳም ይባል የለ::

  ReplyDelete
 18. Nice warnings, but would like to know the source, shall we find these points compiled in one doc? thanks.

  ReplyDelete
 19. How long we keep nursing past mistakes isn't practically unto plain definition, but I'm sure it won't exceed a generation. Sadly so our father (no matter what) departed with a lot of christianly legacy left behind. Now may we serve cleaning our house in a way we don't regret again. I'm pleased with Daniel Kibret's version of expected action, thank you sir.

  ReplyDelete
 20. Dany am a big fun (አክባሪህ) of u but I don’t think it is a time for u to write what should be done and how the papasat select the new patriarchal , u have said that before . I believe the papasat will now knew what to do and we should respect any decision they make(.what u should teach now is to respect any decision they make , but if u start saying they should do this and this …(even it was agreeable ) other will also start doing the same think like u, may be for some personal or other benefit which will make division among the people .
  So if u can p/s write about UNITY that we should stand together with our father ‘s and to pray that GOD will be with us in the coming event

  ReplyDelete
 21. Dear Dani, what you have suggested is logical & appropriate besides what the tradition and statute of the church says.

  ReplyDelete
 22. በእውነቱ ዳንኤል ምነው ሙሉ ስማቸው መጥራት ተሳነህ? ሙሉ ስማቸው የሳቸው ሳይሆን የቤተክርስትያኒቱና የአገሪቱ ክብርና መጠርያ ነበር. አንተ ባታከብራቸውም ዓለም በሙሉ አክብሮ የሰጣቸው ነውና አንተ አትቀይረውም. ላንተ የነበረኝ ግምትና ክብር ግን... አባቱን ያላከበረ... ነውና ነገሩ.

  ReplyDelete
  Replies
  1. do you think he should be called with a paragraph of his name !i dont think spritual fathers need fluttering in this world one name is enough !!!!

   Delete
  2. ሀብተ ማርያምAugust 18, 2012 at 9:50 AM

   ዳንኤል ያለው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አምስተኛው ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ነው፡፡ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሚለው በቂ ነው፡፡ የቤተክርስቲያን ሕግም የሚያዘው እስከዚህ ድረስ ብቻ ነው፡፡ ሌላው ሁሉ ከካባ ላይ ለምድ እንደመደረብ ነው፡፡

   Delete
  3. ወንድሜ/ አህቴ ከመናገራችን በፊት ስለማን ስለምን እንደምናወራ አናስብ! ለምን ሁል ጊዜ አሉታዊውን ነገር ብቻ እንመለከታልን..... ቅን እና መልካም ሰዎች ግን አውንታዊውን ነገር ነው ቀድመው የሚናገሩት፡፡ አሁን እንደው ለነገሩ የብፁ አባታችን ሙሉ ስም ዲን ዳንኤል ብቻ ነው ያልጠራው ምነው በኢቲቪ መሰለ፣ ተመስገን፣ አማረ ማሞ የሚባሉ ጋዜጠኞች ሙሉ ስማቸውን ጠርተው ያውቃሉ...... አን ግን አንዳንተ በዳኒ ምንም አላዝንም ምክንያቱም ዳኒ ስለመልካም ነገር ብቻ የሚያስብ ሰው እንዲያነበው ስለሚፅፍ፡፡ ወንድሜ/ አህቴ እባካችሁ ክርስቲያን ማለት የጎደለውን ሞልቶ የጠመመውን አቅንቶ የመግባት የለበትም የሚለውን አስወጠቶ በአውንታዊ አስተያየት የሚያይ ነው ምክንያቱም እኛ ሰዎች ነንና ሁሉንም ነገር ለሁሉም አንድስማማ አድርገን መፃፍ አንችልምና፡፡ ዳኒን ግን ሁል ጊዜም አከብረዋለሁ!!!

   Delete
 23. yebalefew asafarina anget yasdefan shtet zare lay medegem yelebetm kemanachewm yepoletca tetsno yetseda menfesawinet yalew shigigir mekahed alebet besdet yalu abatoch bemulu ekul tesatfo endinorachew kemrchaw befit ye erku guday metenakek alebet hulachinm bemnchilew hulu tesatfo adrgen tiru tarik masmezgeb alebn

  ReplyDelete
 24. behulum bekul tnkake ydereg

  ReplyDelete
 25. በእውነቱ ዳንኤል ምነው ሙሉ ስማቸው መጥራት ተሳነህ? ሙሉ ስማቸው የሳቸው ሳይሆን የቤተክርስትያኒቱና የአገሪቱ ክብርና መጠርያ ነበር. አንተ ባታከብራቸውም ዓለም በሙሉ አክብሮ የሰጣቸው ነውና አንተ አትቀይረውም. ላንተ የነበረኝ ግምትና ክብር ግን... አባቱን ያላከበረ... ነውና ነገሩ.

  ReplyDelete
 26. እግዚአብሄር ነፍስ ይማር!!
  በቁጥር 5 ላይ ያለውን ወድጄዋለሁ መልካም ይመስለኛል /ዕጩዎቹ ቀድመው ታውቀው ሕዝቡ የሚጸልይበት የጸሎት ጊዜ ቢኖር፡፡ የምእመናን ተሳትፎ ተጠናክሮ የሚታይበትና አባቶችና ልጆች አንድ ሆነው የሚመሰክሩበት ጊዜ እንዲሆን ከወዲሁ ማሰብ ያስፈልጋል፡፡/
  ይህ ከመሆኑ በፊት ግን እንደሚታወቀው አገራችን ወይም ሀይማኖታችን በሁለት ጎራ ተከፈላ ነው ያለችው በሰሜን አሜሪካ እና እዚሁ አገራችን ላይ ባሉ በእርግጥ እንደሚገባኝ እዚህም የተከፋፈሉ ነገሮች አሉ ነገር ግን ያኛው የባሰ ይመስለኛል ስለዚህ አንዳድ ጊዜ ነገር ሁሉ ለበጎ ነው ይባል የለ የመጣው ሀዘን በጎ ነገርንም ይዞ ይሆናል እና ቆም ብልን እዚያም ካሉት አባቶች ጋር የምንነጋገርበት ሁኔታ ቢመቻች፡፡ ሁኔታውን ማመቻችት ብቻ ሳይሆን በቤተ ክርስቲያን የፆም ፤ የፀሎት እና የምህላ ጊዜ መጀመሪያ ታውጆ በዚሁ ጉዳይ ብቻ እዚህም አገር እዚያም አገር ያሉ አባቶች እናም ሁሉም ምእመን መሳተፍ ያለበት ይመስኛል ከዚያም የእግዚአብሄርን መልስ ማግኘት ተገቢ ይመስለኛለ፡፡
  አገራችን በየግዜው ድርቅ ፤ ጦርነት ፤ ችግር እናም አለመረጋጋት የሚገጥማት አንድ ሆነን ከእግዜር ጋር ስለማንገናኝ ይመስለኛል እና እንደኔ እምነት ይህ ነገር ከቤተ ክርስቲያን ሀላፊዎች ባይነገር እንኳን ሁሉም ስው በግሉ ይህን ማድረግ የሀይማኖቱ ግዴታ ያለበት ይመስለኛል፡፡ ካጠፋሁ ይቅርታ የተሰማኛን ለማለት ያህል ነው
  ሠላም ፤ በረከት እና እርቅ ለኢትዮጲያ ና ለ ዓለም አሜን!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. "Election" are you sure there will be fair election. Is there any mandate that the government will not get involved as they did to appoint the deceased one.
   And am quite sure they will pick up another Tigre.... Funny country, funny "religion"

   Delete
 27. ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ዐርፈዋል፡፡ እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማር።

  የግብጹ ፓትርያርክ አቡነ ሺኖዳ ካረፉ በኋላ እሳቸውን የመሰሉ ደገኛ አባት ፍለጋ ግብጽ በጸሎት ተጠምዳለች። ዳዊት በትንቢቱ “ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” እንዳለ ደገኛ አባት ስጠን ብለን እጃችንን ወደ እግዚአብሔር መዘርጋት ያለብን ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው። ስለ ቤተክርስቲያን የሚያለቅስና የሚጸልይ ቢኖር ጊዜው ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው። በአሜሪካና በሀገር ቤት የተራራቀችውን ቤተክርስቲያን በፍቅርና በብስለት አንድ የሚያደርጉ አባት ይሰጠን ዘንድ የጸሎት ጊዜው አሁን ነው። ሐዋርያው “እለት እለት የሚያስጨንቀኝ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ነው” እንዳለ እንደ ቅ/ጳውሎስ ያለ ለቤተክርስቲያን ቀናተኛ ለ
  መንጋው መልካም እረኛ እግዚአብሔር ያዘጋጅልን።  ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ “Apostolic Succession”

  ከሐዋርያት አለቃ ከቅ/ጴጥሮስ እስከ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ድረስ ኢትዮጵያ ያሳለፈችውን ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ እንዲህ እናገኘዋለን፦

  የሐዋርያት አለቃ ቅ/ጴጥሮስ ነው።

  ከቅዱስ ጴጥሮስ ቀጥሎ ቅ/ማርቆስ።

  ቅ/ማርቆስ ግብጽ ሄዶ መንበሩን በግብጽ አደረገ።

  ከቅ/ማርቆስ ቀጥሎ አንያኖስ ነው።

  ከአንያኖስ ቀጥሎ 20 ፓትርያርክ አሉ። 20ኛው አትናቴዎስ ነው።

  ከአትናቴዎስ ቀጥሎ ከሳቴ ብርኅን አባ ሰላማ /ፍሬምናጦስ/ ይህን ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ ወደ ሀገራችን አመጣልን።

  ፍሬምናጦስ ኢትዮጲያዊ አይደለም። አንድ ነጋዴ ሲድራኮስና ፍሬምናጦስ የሚባሉ ሁለት ልጆቹን ይዞ አንድ ነጋዴ ቤት ገብቶ መኖር ጀመረ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ነጋዴው ሞተ። ልጆቹም በገበሬው ቤት መኖር ጀመሩ። ፍሬምናጦስም የኢትዮጵያዊያንንn እምነትና ባህል አደንቃለሁ። ለምን ሥጋ ወደሙን አትቀበሉም? ብሎ ገበሬውን ጠየቀው። ገበሬውም ካህናት ስለሌሉን ነው አለው። ፍሬምናጦስም በኢዛና እና ሳይዛና ፈቃድ ግብጽ ሄዶ ፕትርክናን ከአትናቶዎስ ተቀበለ።


  የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ፍሬምናጦስ ነው።

  ከዚህ ጊዜ በኋላ ለብዙ ዘመናት ኢትዮጵያ በግብጽ ፓትርያርኮች ስትመራ ቆይታለች።

  የመጀመሪያው አራቱ ኢትዮጲያዊያን ጳጳሳት በ1921 ተሾሙ!

  አቡነ ሚካኤል
  አቡነ ጴጥሮስ
  አቡነ አብርሐም
  አቡነ ይሥሐቅ ናቸው።

  ከዚህ ጊዜ በኋላ በግብጽና በኢትዮጲያ መካከል ለሃያ አመታት ያክል ሀገራችን ኢትዮጵያዊ ጳጳስ ያስፈልጋታል አያስፈልጋትም በሚል ሽኩቻ ውስጥ ነበሩ።

  ይህ እልህ አስጨራሽ ሽኩቻ አለፈና በ1940 ሌሎች አራት ጳጳሳት በግብጻዊው ፓትርያርክ በአቡነ ዮሳብ ተሾሙ።

  አቡነ ሚካኤል
  አቡነ ያዕቆብ
  አቡነ ባስልዮስ
  አቡነ ጢሞቴዎስ ናቸው።

  ከእነዚህ ጳጳሳት አቡነ ባስልዮስ የመጀመሪያው ኢትዮጲያዊ ሊቀ ጳጳስ ኾነው ተሾሙ!! በዚህች እለት 21 ጊዜ መድፍ ተተኮሰ! ታላቅ ደስታ ነበርና! ጊዜውም በ1943 ዓ.ም ሲኾን ለአቡነ ባስልዮስ ሊቀ ጵጵስናውን የሰጡት የግብጹ ፓትርያርክ አቡነ ዮሳብ ነበሩ።

  ከ1951-1963 ዓም ድረስ የመጀመሪያው ኢትዮጲያዊ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ባስልዮስ የመጀመሪያው ኢትዮጲያዊ ፓትርያር ኾኑ!!


  በርግጥ ከአቡነ ባስልዮስ በፊት አቡነ አብርሐምና አቡነ ዮሐንስ የሚባሉ ሌሎች ሁለት ፓትርያርክ ነበሩ። ነገር ግን የኢጣልያው መንግስት ስለሾማቸው ቤተክርስቲያናችን ሕጋዊ ፓትርያርክ አድርጋ አትቀበላቸውም። የመጀመሪያው ሕጋዊ ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ ናቸው።  ከአቡነ ባስልዮስ ቀጥሎ ፓትርያር አቡነ ቴዎፍሎስ ናቸው።

  ከአቡነ ቴዎፍሎስ ቀጥሎ አቡነ ተክለሐይማኖት ናቸው።

  ከአቡነ ተክለሐይማኖት ቀጥሎ አቡነ መርቆርዮስ ናቸው።

  ከአቡነ መርቆርዮስ ቀጥሎ አቡነ ጳውሎስ ናቸው።


  ከአቡነ ጳውሎስ ቀጥሎ ማን ይሆን?

  ለቤተክርስቲያን ቀናተኛ ለመንጋው መልካም እረኛ እግዚአብሔር ያዘጋጅልን።

  Visit this Blog! http://yonas-zekarias.blogspot.com/

  ReplyDelete
 28. Dani arife negere new Yansakewe this is the time that we wait a lot from u regarding to the process of election pls share us your idea as usual and at this time all Cristian should pray God to keep our church and to bring a good day

  ReplyDelete
 29. ዲያቆን ዳኔል በ እውነት እግዚአብሔር ይስጥልን።
  እግዚአብሔር በ እውነት ሀገራችንን ይጠብቅልን።
  የ አባታችንን ነፍስም በ አብርሀም፣ በ ይስሐቅ በ ያዕቆብ አጠገብ ያኑርልን።
  አሜን።
  ስለሁሉም ንገር አግዚአብሔር በጥበቡ የማያልፍ ስራ የሚሰሩ አባትን ይስጠን።
  እላለሁ።

  ReplyDelete
 30. መጀመሪያ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ሰላም እና ፍቅር ይውረድ፡፡ በሁለት ሲኖዶስ መከፋፈሉ ያቁም፡፡ ቤተክርስቲያን አንድ ትሁን፡፡ ሕዝቡ / ምዕመኑ የሚፈልገው ይህንን ነው፡፡ ስለዚህ የዐቃቤ መንበሩ የመጀመሪያ ተግባር ይህ ይሁን፡፡ ከውጭ ያሉት አባቶች/ጳጳሳት አብረው መሳተፍ አለባቸው፡፡
  ቀጥሎ የመምረጫ መስፈርቶች በሕገ ቤ/ያን ወይም በሲኖዶስ መመሪያ መሰረት ይዘጋጅ፡፡ መልካም ተሞክሮንም ሆነ መመሪያው ከግብጽ ቤተ/ያን መውሰድ ይቻላል፡፡ ለቀጣይ ቋሚ የሆነ የመምረጫ መስፈርት ሆኖ ማገልገል አለበት፡፡
  ሌላውና በጣም ትኩረት ሊሰጥበት የሚገባው ጉዳይ የመንግስት ጣልቃ ገብነት እንዳይኖር መጠንቀቅ ነው፡፡ ይህ የሃይማኖት ጉዳይ ነው፡፡ ምናልባት አለመግባባት ከተፈጠረ እና መዳልሆነ መካረር ከተገባ ጣልቃ መግባቱ አይቀርም፡፡ ስለዚህ በሰላማዊ መንገድ ምርጫው በሕገ ቤ/ያን ብቻ እንዲካሄድ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

  ReplyDelete
 31. ቤተ ክርስቲያንን የሚመራ አባት ሲያርፍ ቤተ ክርስቲያኒቱ በይፋ ማወጅ አለባት፡፡ይህ አባት በመንግሥት ወይም በአላውያን ተይዞ የደረሰበት ካልታወቀም ሲኖዶሱ የመጨረሻውን እስኪያውቅ ድረስ በቦታው ሰው ሳይተካ ሥራውን እየሠራ ይቆያል እንጂ በይፋ ሳያውጅ ሌላ አባት ወደ መምረጥ አይሄድም፡፡ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን ደርግ አንቆ ሲገድላቸውና የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ንብረት ሲወ
  ረስ በታሪካችን የተሠራው ስሕተት ይህ ነበር፡፡ እርሳቸው ማረፋቸውን በይፋ ቤተ ክርስቲያኒቱ ሳታውጅ ወደ ሌላ ምርጫ ገባች፡፡የቅዱስ ሲኖዶስ ደንብ የአዲሱ ፓትርያርክ ምርጫ የሚከናወነው ነባሩ አባት ካረፈ ከዐርባ ቀን በኋላ መሆኑን ይገልጣል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ዐርባ የኀዘን ቀናት ስለሚታወጁ ነው፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ለዐረፉት አባት የፍትሐት ጸሎት ይደረጋል፡፡ ታሪካቸው በቤተ ክርስቲያን ደረጃ በይፋ ይወጣል፡፡ ስለነበሩበት የአገልግሎት ዘመን ይነገራል፡፡ በየቤተ ክርስቲያኑም ጸሎት ይደረግላቸዋል፡፡ያ ሁሉ ሳይደረግ ነበር ወደ ምርጫ የተገባው ፡፡ ይህም ከሌሎች እኅት አብያተ ክርስቲያናት ጋር በቀኖና ከማለያየቱም በላይ በቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪክም ላይ ጥቁር ነጥብ ጥሎ አልፏል፡፡

  ReplyDelete
 32. Abune Merkoryos is not a legitimate patriarch for our church, not accepted by Egypt Orthodox Church too.
  So with what legal ground could he be the next?
  Remember fellow Ethiopians, this is not about political power but it’s about serving our lord Jesus Christ and its people.

  ReplyDelete
 33. it is good that you share the knowledge and let Gods will be working .

  But what i --- dont be to judgmental who are we to judg
  Biyans yetelemedewin Nefis yimar gin malet lealemawiyan sewoch enqu sibal minew andem alsemahu Yih fitsum ethiopiawi aydelem

  ReplyDelete
 34. Menfesawi /haymanotawi/ ende alemawi /political/ endanaderigew sigat alegn beka betekrsitiyanachin yerasa yehone tifut silalat bezaw biketil melkam new elalehu

  ReplyDelete
 35. አንተ ዞረህ ስለ አየኸው ጉድ ጻፍ እንጂ ስለ ፓትርያርክ ደግሞ ትጽፋለህ?
  ደግሞ ስለሰሩት ልማትና ደግ ነገር ታሪካዊ ስራ ትላለህ?
  አባ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ለ 20 ዓመታት ያወደሙትን ሐውልት የተከሉትንስ የት ቀብረኸው ነው? አዲስ ታሪክ የምታስጠናን?
  እረሳኸው እንዴ ሰው ለምን ሐውልት ይሰራል ብለህ ያወጣኸው ጽሑፍ? ጠፋብህ እንዴ?
  በብሎግህ ላይ ፈልገህም ታገኘዋለህ?
  ስታስተምርስ የተናገርከው ይጠፋሃል እንዴ? የ20 ዓመት ልጅ ያስጠኑትን ነው የሚያውቀው ያልከው ረሳኸው? ለምሳሌ አቡነ መርቆሪዎስስ እኔ ብትጠይቀኝ አላውቅም ምክንያቱም 20 ዓመት ልጅ ያለከው ታሪክ ሁኔታ ነው?

  ReplyDelete
 36. ሴትየዋ አሁንም ቤተክርስትያንን ከማመስ አልተቆጠበችም አባቶቻችንም መንግስትን በቃህ ወግድ አያገባህም አንዲሉ አግዚአብሔር ብርታቱን ይስጣቸው:: በቤተክርስትያን ሕግ ማንም የአንድን ጳጳስ አስከሬን መግነዝ መፍታት ማሰር አይችልም ለዚህም ነበር ብፁዓን አባቶች ሄደው የገነዙት:: ሴትየዋ ስለጮሀችና የደህንነት ኃላፊ ስለአዘዘ ዛሬ ሃይማኖቱ የማይፈቅደውን ነገር ለማድረግ ከተንበረከኩ ነገ አገሌን ነው የምትመርጡት ሲሏቸው ወግድ ለማለት ወኔው ከወዴት ይመጣል? ስለዚህ ከአሁኑ አያገባህም ወግድ ለማለት አግዚአብሔር ድፍረቱንና ኅይሉን ይስጣቸው አሜን !

  ReplyDelete
 37. Thanks Dn. Daniel for putting the right procedure how the election gonna be undertaken. But, what i want to remind you is work wisely on how things gonna be settled by keeping our differences internal. Our surrounding area is full of threat, we all have to work together to resolve this situation as a human even if it's determined by God.

  ReplyDelete
 38. that is realy great idea please let use it.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድሜ ዲያቆን ዳኒ ቅዱስ አባታችንን እረፍት ተከተሎ የሰነዘርካቸው ሃሳቦች ምሉዕ ባይሆኑም መፍትሄ አመላካች ናቸው፡፡
   በእኔ አመለካከት በተለይ ለዘመናት በተንከባለሉ ዘርፈ ብዙ ምስጣዊ እና ውጫዊ ችግሮች ለተተበተበች ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ ባይሆንልን በከፊል መፍትሔ የምናበጅበት አጋጣሚ ይመስለኛል፡፡
   1) ቤተክርስቲያኒቱ በሁለት ሺህ ዘመን ጉዞዋ ሲኖዶስዋ ለሁለት ተሰንጠቆ ‹‹የውጪ እና የውስጥ›› መባባሉ ማክተሚያው እድል አሁን ይመስለኛል፡፡ ለምሳሌ የተሰደዱትን አባት ወደ መንበራቸው መመለስ ተገቢ ይሆናል፡፡ እርሳቸው ቢመለሱ ከአሁን በኋላ በጉልበት በርትተው፤ በእድሜ ሰንብተው የምንቸገር አይመስለኝም፡፡ ህም ቢሆን ቀላል ሥራ እንደማይሆን እረዳለሁ፡፡ በቤተክርስቲያኒቱ ችግር ‹‹የሚማረሩ›› እንዳሉ ሁሉ ‹‹የሚኖሩም›› አሉ እና !
   2) ቤተክርስቲያኒቱ ከቄሳሮች ጣልቃ ገብነት ተላቃ በራስዋ ጉዳ ላይ በቀኖናዋ ብቻ ተመርታ ለመወሰን ጊዜው አሁን ነው፡፡ ሁሉም ፓትርረኮቻችን ወደ መንብር እንዴት እንደመጡ ለሚያውቅ ከፊታችን የሚጠብቀንን የባለሥልጣናት ተግዳሮት ይገነዘበዋል፡፡
   3) ቀድሞ በነበረው የአቡኑ አስተዳደር ከዕውቀትም ከመንፈሳዊነትም ርቀው (ንጽሕ ጠብቀው) በተለያዩ የሥልጣን እርከኖች ላይ የተደላደሉ ተመጋቢዎች ተቅማቸውን በዋዛ አሳልፈው ይለቃሉ ብሎ ማሰብ የዋህነት ስለሆነ ሁሉን አቀፍ የመፍትሔ አቅጣጫ ማመላከት ተገቢ ይሆናል፡፡ (ታሳቢ ማድረግ አለብን)
   የቤተክርስቲያን አምላክ የቀደመ በደለችንን ሳይቆጥር በከበሩ ደሙ መፍሰስ ዋጃትን ቅድሰት ቤተክርስቲናችንን በውስጥ በአፍኣ ከሚመጣ ፈተና ይጠብቅልን፡፡

   Delete
 39. መልካም ሃሳብ ዳኒ እግዚአብሂር የአባታችን ነፍስ ይማር

  ReplyDelete
 40. Egziabher yimiretilin!

  ReplyDelete
 41. It is great idea Dn. daniel, but one thing all E.O.Christian have to work hard to unite all these divided synodos and church leaders in Ethiopia and outside Ethiopia. Then they need to discuss according to the doctrine of Orthodox Christianity to Elect the new patriarch. Unless these huge problem solved and they will consider all church leaders, the problem will continue forever.

  ReplyDelete
 42. Dn Daniel thank you for your contribution at this critical historical turn point. At this time, We should talk the restoration of the Holy Chair of the old Patriarch, he is in exile instead of talking about election. We are sick and tired about worshiping separately in three name with a name of a church, I think it is better to be unify. You also know the reality well, otherwise it will bring other additional problems again. It is better to clean the dust once and for ever instead of blowing it!
  God Help Our Fathers sheepherders to Guard from wild and Restore the Grace of the Our Church! Amen

  ReplyDelete
 43. ዲያቆን ዳኔል በ እውነት እግዚአብሔር ይስጥልን።
  እግዚአብሔር በ እውነት ሀገራችንን ይጠብቅልን።
  የ አባታችንን ነፍስም በ አብርሀም፣ በ ይስሐቅ በ ያዕቆብ አጠገብ ያኑርልን።
  አሜን።
  ስለሁሉም ንገር አግዚአብሔር በጥበቡ የማያልፍ ስራ የሚሰሩ አባትን ይስጠን።
  እላለሁ። አንተም በርታ!

  ReplyDelete
 44. Abatachinin Egziabhear Nefsachewn Yeshelmiln.. D.Dani Geta Tsegawn Yabzalh Melkam Tiqoma Neaw Endetelemedew:: Hassab Aqirabi wegenochem YeTsehafiwn Teqilala ena Weqitawi Hassabun Enji KeGizew Antsar BeWanegn Lyastelalf Yalfelegew Lay Metegnatachn Melkam Aydelm:: Ahun Betelayaye Melku Yetebetatenewn Menfesachinin Sebsiben KeSimet Yetseda Eytachinin Zeleqetawi LeHonech Betekrstean Maseb Yenorbinal:: Yeqir Baynet,Qoratinetin, LeEgziabhear Ena LeRas Tamagninetin,....KeAbatoch Bicha Eyetebeqin Wedelay Eyangatetin Bicha Tamir Endiseru ena Selam Endisefin Menafeq Yebqan...Chigiru Yalew Egna Gar Neaw YeEgnan Nuro, Qurtegninet,Menedat... BeHasab ena Wsanewochachew Lay Tilq Wesagninet Alew:: BeAlem Zuria Balech Betekirstean Yalew Gud Weyem YeTelat Diabilos Tigadilo Mesakat BeWanegninet YeEgna Simetawinet, Menedat,Degafinetna Weregninet Neaw... Enastewl..BeDigaf Gora Bemewerawer Hiwotchinin Agosaqulen, Tedegafiwnm Asenaklen Ezih Lay Dersenal LeLaw Biqer LeMENFES QIDUS Sirawn Endisera Enqifat Anihun:: EGZIABHEAR ABATACHIN Adis Zemenin Yadilen Amen

  ReplyDelete
 45. i couldn't read the article b/c the PDF format won't let me,

  ReplyDelete
 46. Thank you dani,esti eghnem embete terdan.

  ReplyDelete
 47. that is good... the most important thing is that the pseudo-patriarich has departed! A new window is now opened for the church to restore its order and dignity!

  ReplyDelete
  Replies
  1. I pray for my God. Because I afraid how the way people and the members of The church are thinking very dangerous.But I can understand that we the people are full of complains. Even we complain on the Almighty God. We are trying to correct the bible, kenona and words of God even.

   For example I don't know about another synod. Because I live in Ethiopia. This is an Ethiopian Orthodox church. Because when I read the histories of our fore fathers including Egyptians, when there is a problem created they are not exiled to Other countries. They will go to monasteries to have more time for pray.

   I always fixed my ears to one synod that is working in Ethiopia. What ever the decision is made by one synod I will follow that only.

   I love if all are decided to come and work in Ethiopia.

   Beterefe Dn Dani endezih annd ewneta sitneka yesewun tikikilegna amelekaket tagegnalehina ketil. Lewedefit yemitsfachewun sihufoch liwedachewum litelachewim echilalehu. Mikniyatum hullem yemadamitew yerasen newina. Yemigeltewim bedmiye yetsafikutin yerasen metsehaf newina. Ante tsaf egna ennanebalen. Ante be ETV yetayeh, kezih befit endih yaderek maletu sew ayqerim. Gin tsaf. Yemimar yimaral yemidenequerim yidenequral.

   Abatachinin egziabher nefsachewin yimarelin. Tiruna menfesawi abat yisten. Ezih sihon mengistin degafi American sihed mengistin neqafi kemihon abat yisewuren. Ezih nore, amerika nore, Talian hede behaymanotu yeminor, Yemengisit degafim, teqawamim yehaymanot lije neew bilo yemiyamin abat yisten. Hulum ortodoxawi ye woyane degafi, woyim teqawami neew bilo mamen ayachalim.

   Teqawamiwim degafiwuim wedebetekirstian simetu ende betekiristian menor enji ende poletikachew enna endebiherachew eninur bilew biyasibu chirash annd mehon aychalimina chigir yinoral. Silezih enne bebekule yemitseliyew yihenin enkoklish yemifeta abat endagegne neew. Mnegistin endee mengistinetu yemiyakebir enji yemengist guday atsfetsami ehonalehu kale aschegari neew. Ye Haimanot meri hono yeteqawami ajenda angibe atsefetsmalehu kalem aschegari neww. Betekiristian bekononawa enna siratuwa endituguaz yemiyaderg bihon emertalehu.

   Ende Nabute eriste bete kirsitiyanachinin ketebeqin ersu degmo ke Elzabel zacha enna tenkol yadinenal. demachinin bitafes demuan afso bewisha yaslisatal.Silezih be Egiabher enna be Emebetachin amalajinet enaminalen, silezihim silekidusanu bilo melkamun Abat yitsetenal.

   Delete
 48. Dear Dn Daniel,

  Oh! NO! We must not repeat the same mistake again. We don't need any election for the sake of uniting our church.


  I used to think that you are a wise man who worries about the church's most serious problem. I am now surprised that you are talking about another election.


  Another fake election against the canon law of our church will guarantee the perpetuation of the grave mistake that shook our church to the core for the past 20 years.


  I am sure that you agree with me in saying the division of our church is a shameful history. The division of the church happened due to the assignment of a second "patriarch" while Patriarch Merkoriwos is still well and alive.

  Ending this division and uniting our beloved church must be the most important thing to do.


  Now Aba Paulos is called by his creator, may God bless his soul. Patriarch Merkoriwos is still well and alive.

  The courageous thing to do is to restore Patriarch Merkoriwos and heal the wound of our church once and for all.

  Dani, this is the only best way we should advocate for the sake of our church. I am sure there are opposing views and emotions, but we must think beyond our emotions do the right thing to unite our church.

  May God bless our Orthodox Church. May God give our fathers the wisdom to put our church before their personal wishes. May God help us, Orthodox Christians, to do our part to unite our church. Amen.

  ReplyDelete
 49. Dn you did ur best pls those of u dont blaim him . who did like Dani ....? no one . so do ur best.

  ReplyDelete
 50. please please please do not forget pdf

  ReplyDelete
 51. ዘና ብላችሁ ተቀመጡና አንድ ታሪክ ላጫውታችሁ!

  ==> “የዛሬ አበባዎች የነገ ጥሬዎች”<==

  ከራሴ ጋር አጠር ያለች ስብሰባ አደረኩና አንድ ታሪክ ትዝ አለኝ። ሰው በሞተ ቁጥር የሰፈሩ ሰው እትዬ ጣይቱን እድር ይግቡ እንጂ ብለው ሲመክሯቸው “እዲያ በሕይወት እያሉ ሳይረዳዱ ቀባሪን ለሚያበላ እድር ምን አስጨነቀኝ” ይሉ ነበር። የእድሩ ዳኛም “ጉድ መጣ ገንፎ ዛፍ ላይ ወጣ! የኛ ፈረንጅ!!” ብለው ሰዎች እንዲያግዟቸው በረጅሙ ሳቁ። እትዬ ጣይቱም ፈረንጅ እድር አለው እንዴ? ብለው ጠየቁ። የሚመልስ ሰው ግን አልተገኘም። “እናንተን ማስረዳት ቀባሪን ማርዳት እንዳይሆንብኝ እፈራለሁ” አሉ እትዬ ጣይቱ የእድር ዳኛውን በቆረጣ እያዩ። በአባባላቸው ሰው ሁሉ ሳቀ። “ማረኝ እንጂ አትመመኝ አይባልም” ይሉ ነበር እትዬ ጣይቱ። እውነታቸውን ነውኮ። “ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ ነው መጨነቅ” አሉ እትዬ ጣይቱ!

  መቼስ የእትዬ ጣይቱ ጨዋታ አይጠገብም። በጨዋታቸውና በሙያቸው የተመሰከረላቸው ናቸው። እንዲያውም የእትዬ ጣይቱን ምግብ በልቶ ማን እጁን ይታጠባል ይባልላቸዋል። ዛሬም ምርጥ ምርጡ በየዓይነቱ ጠረጴዛው ላይ ተደርድሯል። እትዬ ጣይቱ አንድያ ልጃቸውን ኤፍራታን ጠሩና እኔ በልቻለው አቅርቡና አብራችሁ ብሉ አሏት። ኤፍራታም ኧረ አልራበንም በኋላ እንበላለን አለች። ጉድ እኮ ነው የሱን ሆድ መች አየሽው? አሉ እትዬ ጣይቱ። አባባላቸው አሳቀኝ። “ከአንድ ብርቱ ሁለት ገልቱ” እስኪ አንድ ላይ ብሉ ብለው በየዓይነቱን አቀረቡልን። እትዬ ጣይቱ ምሳሌያዊ ንግግራቸውን አገለባብጠውት እያዝናኑ ስለሚያስተምሩ እወዳቸዋለሁ። “ነገር በብርሌ ጠጅ በምሳሌ” አሉ እትዬ ጣይቱ! ዛሬ እትዬ ጣይቱ የነገሩኝ ታሪክ ይህ ነው፦

  በአንድ ወቅት የእትዬ ጣይቱ ባለቤት አቶ ይድነቃቸው ገበሬዎች ከሚዘሩት ከአፈር ጋር የተቀላቀሉትን ጤፍ ሰበሰቡና ወቀጡት። ይህን ጊዜ ንጹህ ጤፍ ከአፈሩ ተለየ። አቶ ይድነቃቸው ይህን ጤፍ በሁለት ብር ሸጡና ዶሮ ገዙ። ዶሮውን አስታቅፈው ብዙ ጫጩቶችን አገኙ። ሲቀጥልም ዶሮውን በአምስት ብር ሸጡና በግ ገዙ። አቶ ይድነቃቸው ሰው ሁሉ እስኪደንቀው ድረስ በጉን አደለቡት አሰቡት። የሰባውን በግ ሸጡና አነስተኛ የእርሻ መሬት ገዙ። ሰው ሁሉ በአቶ ይድነቃቸው ተደነቀ። ከዛማ የእርሻ ምርቱ እንደ ጉድ ተስፋፋ። አቶ ይድነቃቸው የብዙ በጎች የብዙ ዶሮዎች የብዙ እንስሳት ባለቤት ባለሀብት ሆኑ! ሰው ሁሉ ስለተደነቀባቸው “አቶ ይድነቃቸው” የሚል ስም ወጣላቸው። ከጤፍ ፍርፋሪ የተከበሩ ባለሀብትም ሆኑ። አቶ ይድነቃቸው ድል ያለ ሠርግ ደግሠው እትዬ ጣይቱን አገቡ። አንድያ ልጃቸውን ኤፍራታንም ወለዱ።


  በአቶ ይድነቃቸው የእርሻ ካምፓኒ ብዙ ገበሬዎች ተቀጠሩ። ከገበሬዎቹ መካከል አንዱ በጎቹን እየተንከባከበ ያደልባቸው ነበር። በጎቹ ቢታዩ ለዓይን የሚማርኩ ቢበሉ ለምላስ የሚጣፍጡ ሆኑ። አቶ ይድነቃቸው እጅግ ተደነቁና ይህን ገበሬ አስጠሩት። ገበሬውም ለጥ ብሎ እጅ ነሳና “መጥቻለሁ ጌታዬ” አለ። አቶ ይድነቃቸውም ታታሪው ገበሬ ሆይ ስራህ ድንቅ ነው! በጎቹን በሚገባ ተንከባክበሃልና! በጣም የሚገርመኝ ግን በጎቹን ትቀልባቸዋለህ ታደልባቸዋለህ እንጂ ምን አወቁ? ሃይማኖታቸው ምንድን ነው? አትልም። ዛሬም ወላጆች ለልጆቻቸው ወተት ብቻ ምግብ ብቻ መግበው ስለ ሃይማኖታቸው ስለ አስተሳሰባቸው ካልተጨነቁ በግ አደለብን እንጂ ልጅ አሳደግን ማለት ከቶ አይችሉም! ልጆች ምን አወቁ? ምን ያስባሉ? ብለው ካልጠየቁ እውነትም በግ እያደለቡ ነው! አሉ እትዬ ጣይቱ ገና በጠዋቱ። እኔና ኤፍራታም በአባባላቸው ሳቅን።

  እትዬ ጣይቱ አያችሁት ያን ልጅ? አሉ ድንገት ወደ ጓሯቸው እየተመለከቱ። በግ ለልጅዋ ወተት ስትመግብ አንድ ትንሽ ልጅ በጉልበቱ ተንበርክኮ ጎንበስ ብሎ አተኩሮ ይመለከት ነበር። ለሚያየው ሰው “እኔም ወተቱን ባገኘሁት” የሚል ይመስል ነበር። ኤፍራታ ቶሎ ብላ በያዘችው ሞባይል ፎቶ አነሳችው። ኤፍራታ በሳይንስ የተማረችውን አስታወሰችና “እናት ለልጅዋ በመጀመሪያ የምታጠባው ወተት ማለትም እንገር /colostrums/ የሚባለው ለሕጻኑ ጤንነትና እድገት እጅግ ወሳኝ ነው” አለችን። ልጆች የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች ሳይሆን “የዛሬ አበባዎች የነገ ጥሬዎች” እንዳይሆኑ ማሰብ ያስፈልጋል አሉ እትዬ ጣይቱ አንድያ ልጃቸውን ኤፍራታን በስስት እያዩ።

  © Visit this Blog! http://yonas-zekarias.blogspot.com/

  ReplyDelete
 52. +++ KHY

  Awon melketu bemulu ewenta alew beant hasab laye awendmachn ዮናስ ዘካርያስAugust 17, 2012 12:51 PM Hasab sedemer nefse terkalech esti wegnoce entelye ere tenseyu letselote

  ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ዐርፈዋል፡፡ እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማር።

  የግብጹ ፓትርያርክ አቡነ ሺኖዳ ካረፉ በኋላ እሳቸውን የመሰሉ ደገኛ አባት ፍለጋ ግብጽ በጸሎት ተጠምዳለች። ዳዊት በትንቢቱ “ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” እንዳለ ደገኛ አባት ስጠን ብለን እጃችንን ወደ እግዚአብሔር መዘርጋት ያለብን ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው። ስለ ቤተክርስቲያን የሚያለቅስና የሚጸልይ ቢኖር ጊዜው ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው። በአሜሪካና በሀገር ቤት የተራራቀችውን ቤተክርስቲያን በፍቅርና በብስለት አንድ የሚያደርጉ አባት ይሰጠን ዘንድ የጸሎት ጊዜው አሁን ነው። ሐዋርያው “እለት እለት የሚያስጨንቀኝ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ነው” እንዳለ እንደ ቅ/ጳውሎስ ያለ ለቤተክርስቲያን ቀናተኛ ለ
  መንጋው መልካም እረኛ እግዚአብሔር ያዘጋጅልን።

  ReplyDelete
 53. የሚገርም እኮ ነው:: ማኅበረ ቅዱሳን የቅዱስነታቸውን እረፍት ያልዘገበው እውነት በቴክኒክ ችግር ነው? ወይስ ከቀበሮ ተሞክሮ ወስዶ ካልቀበርኩ ብሎ ነው? የማይመስል ነገር መናገር ጥሩ አደለም:: እንደኔ ነገም የሚከሰተውን ለመናገር ሲፈዝ እንደ በግ እንዳይታረድ እፈራለሁ::

  ReplyDelete
 54. ሹምት ከእግዚአብሔር እንጂ ከሰው አይደልም፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ለቤቱ ያውቅበታል፡፡
  እውነት የቀድሞው ፓትርያርክ ከሃገር ሲሰደዱ እግዚአብሔር መመለስ አቅቶ ይመስልሃል/ይመስልሻል?
  እግዚአብሔር ሁሉንም በምክንያት እንጂ አንዲቷንም ነገር ያለምክንያት አያደርግም፡፡ እግዚአብሔር ለቤቱ ጠባቂ የቀድሞውን ፓትርያርክ ከፍለገ ያመጣቸዋል ፣ አዲስ ከፈለገ ደግሞ አዲስ ይሾማል ፣ ለሱ ምንም የሚሳንው ነገር የለም ፡፡ ሁሉ እንደሱ ፍቃድ እንጂ እንደኛ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ለሁላችንም ልቦና ይስጠን፡፡
  ሁሉም ከሱ ነውና ምልካሙን ሁሉ እንዲያደርግ በጸሎት እግዚአብሔርን እንጠይቅ፡፡

  ReplyDelete
 55. Aba Gebere Medihinin "Bitsuh" malet lebetekirstianachin sidib new...

  ReplyDelete
 56. ከእጩዎቹ መካከል በእጣ መለየት ቢቻል፤እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የይሁዳን ሹመት በእጣ አማካኝነት ቶማስ እንዲወስድ እንዳደረገ፡፡ እግዚአብሔር መልካም እረኛ ይስጠን!

  ReplyDelete
 57. thanks to God. every thing is in the hand of the God.every thing will be corrected by him through truth son's.
  deacon thanks.i love you .i always pray to you.
  i afraid of by the next process of election of patriarec.

  ReplyDelete
 58. Nebs ymar. Legnam endesachew yale biruh aymro yalew meri ysten. Amen.
  Endew endasteyayet Dani, sidib yalebachewn asteyayetoch bataweta.Kekirstinam antsar, leblogihm kibr mimetin aymeslegnm.

  ReplyDelete
 59. amin nebs yimar.neger gin kesachew yeteshale lebetu tekorkuwari abat yishumilin.lemanignawim ene yalkut bicha yemilewin gitirnet titen entseliye,enalikis.silehedew mawirat enichil yihonal silemimetaw gin fetsimo anawikim.dn. daniel hulem eyitahin asayen.minarimewin arimen likmnew yalinew tekeblen weyinim alemekebelim yegna fenta naw.lanite gin ahunim tibebunina tigistun yadilih.

  ReplyDelete
 60. ኢትዮጲያ ኦ ተ ቤተክርስቲያንን መከራ ላይ ጥለው የሄዱ ኢትዮጲያ ኦ ተ ቤ በታሪኩዋ በዲቃላ የእመራችበት ዘመን ይሄ የኛ ዘመን ነው ዲቃላ ማለት የሚመስል ግን ያልሆነ አባ ጳውሎስን አንድ የበቁ አባት ከጫካ ወጥተው ይህን ዲቃላ አስወግዱ ብለው ተናግረው ነበር ሰሚ አጥተው አባ ጳውሎስም ቤተክርስቲኑአን አዋርደው አለፉ ዋልድባ መነኮሳትም ጮሁ ሰሚ ጠፋ ዛሬም በሚዲያ እርቅ የለም የቀድሞው 4 ፓትሪየሚገቡ ከሆነ አክሱም ላይ ሲኖዶስ እናቁአቁማለን ይሚሉ ያልሆኑ የሚመስሉ ሊሎች ዲቃሎች ተነሱ እንደተመኘነው ሳይሆን እንደተምኙት ሆነላቸው እግዚአብሄር የቤተክርስቲያናችንን ሆነ የሀገራችን ኢትዮጲያን ዘላምና አንድነት ለማምጣት የተዋህዶን ልጆች ድፍረቱን እና ሀይሉን ይስጠን

  ReplyDelete