Wednesday, August 29, 2012

ፓትርያርክና ፕትርክና


ከሰባት ዓመታት በፊት ነበር፤ ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ቃለ መጠይቅ ማድረግ በመንበረ ፓትርያርክ ግቢ በሚገኘው ቢሯቸው ወደ አሥር ሰዓት አካባቢ ከሌሎች ባልደረቦቼ ጋር ተገኝቼ ነበር፡፡ ያ ቃለ መጠይቅ ወደ አራት ሰዓታት ያህል የፈጀና በሐመር መጽሔት ላይ በተከታታይ የወጣ ነበር፡፡
በመካከል ላይ ቤተ ክርስቲያኒቱ በወቅቱ የነበረችበትን ሁኔታ የሚያነሣ አንድ ጥያቄ ተሰነዘረላቸው፡፡ መጀመርያ በመዳፋቸው አገጫቸውን ያዙና ወደ ጠረጲዛቸው አንገታቸውን ደፉ፡፡ በዚያም ለረጅም ሰዓት አቀርቅረው ቆዩ፡፡ ምን እያሰቡ ይሆን ብለን እናስብ ነበር፡፡ ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ቀና ሲሉ ዕንባዎቻቸው በሁለቱም ጉንጮቻቸው ላይ መንታ ሆነው ይፈሱ ነበር፡፡ ምንም አላሉንም፡፡ ዝም ብለው አዩን፡፡ ከዚያም ይቀረጹበት የነበረውን ቪዲዮ እንዲጠፋ አዘዙ፡፡ እኛንም ተቀመጡ አሉን፡፡ ግራ ገብቶን ተቀመጥን፡፡
ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ ያን ዕለት ሲናገሩት የነበረውን ነገር ከዚያ በፊትም ሆነ በኋላ ሲናገሩት ሰምቼ አላውቅም፡፡ ሲነግሩን ያለቅሱ ነበር፡፡ እኛም ብንሆን በኀዘን ድባብ ውስጥ ነበርን፡፡
ከዚያች ቀን ጀምሮ ስለ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ያለኝ አመለካከት የተዘበራረቀ ሆነ፡፡ የሚወስዷቸውን ርምጃዎች፣ የሚያሳዩዋቸውን ጠባያት፣ የሚፈጽሟቸውን ተግባራት ስመለከት ምን ዓይነት ሰው ናቸው? ያሰኘኛል፡፡ የዚያን ቀን ሁኔታቸውን ሳስበው ደግሞ እኒህ አባት ሁላችንም ያላወቅንላቸው የተደበቀ መልካም ሰብእና ይኖራቸው ይሆን? እላለሁ፡፡ ያ ዕንባ ዝም ብሎ የመጣ የተዋናይ ዕንባ እንዳልነበረ እኔ ራሴ በዓይኔ ያሁት ነው፡፡ በዚያች ሰዓት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከአጽራረ ቤተ ክርስቲያን እየደረሰባት ስላለው ፈተና የነገሩን ነገር በኋላ ይወስዷቸው ከነበሩት ርምጃዎች ጋር አልጣጣም እያሉኝ እቸገር ነበር፡፡
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አምስተኛ ፓትርያርክ ናቸው፡፡ ከአቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን እስከ መጨረሻው ግብጻዊ ጳጳስ እስከ አቡነ ቄርሎስ ድረስ አንድ መቶ አሥራ አንድ ጳጳሳት ከግብፅ መጥተዋል፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ የፓትርያርክ ሹመት ከፖለቲካ ተጽዕኖ ነጻ ሆኖ የሚያውቅ አይመስልም፡፡ የአቡነ ባስልዮስን የአቡነ ቴዎፍሎስ ሹመት ከዐፄ ኃይለ ሥላሴ ጋር፣ የአቡነ ተክለ ሃይማኖትና የአቡነ መርቆሬዎስም ሹመት ከደርግ ጋር፣ የአቡነ ጳውሎስም ሹመት ከኢሕአዴግ ጋር እየተያዘ ይነሣል፡፡ ቤተ ክህነቱንም አንድ ጊዜ ሸዋ አንድ ጊዜ ጎጃም፣ አንድ ጊዜ ጎንደር፣ አንድ ጊዜ ትግራይ ባለቤት ሲመስልበት ከዘረኛነት ወቀሳ ነጻ ሳይሆን እኛ ዘመን ደርሷል፡፡
ባስልዮስ ወቴዎፍሎስ ሊቃነ መላእክት እሙንቱ
ለሙሴ ቤተ ክህነት ቀበርዎ በሕይወቱ
የሚለው ቀኔ ቀድሞም ጀምሮ አባቶችን በአስተዳደራቸው የተነሣ መውቀስ የቤተ ክህነቱ ገንዘቡ እንደነበረ ያሳየናል፡፡
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለፓትርያርክነት ሹመት አዲስ በመሆንዋ የዳበረ ልምድና አሠራር የላትም፡፡ የመጀመርያው ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ እጨጌ ስለ ነበሩ በዚያው ነው ወደ ፕትርክናው የሄዱት፡፡ አቡነ ቴዎፍሎስም ከእንደራሴነት ወደ ፕትርክና ሲሻገሩ ያንን ያህል የምርጫና የአሠራር ሕግ አላስፈለገም፡፡ የእርሳቸው ሞት ሳይታወጅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሲሾሙም ቤተ ክርስቲያኒቱ በቀደምቱ ሁለት ፓትርያርኮች ምርጫ ያልተከተለችውን አዲስ አሠራር አምጥታ ከመነኮሳት መካከል ነው የመረጠችው፡፡ አቡነ መርቆሬዎስና የአቡነ ጳውሎስ አመራረጥም  አወዛጋቢና የሌሎች እጅ የነበረበት ነበር፡፡
ይህ ዓይነቱ ችግር በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አብያተ ክርስቲያናት ታሪክ ውስጥ የተከሰተና አያሌ ፈተናዎችንም ያመጣ ነው፡፡
በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ፓትርያርኮች በተለያዩ መንገድ ወደ መንበረ ማርቆስ መጥተዋል፡፡ በአንዳንድ ታሪኮች ነባሩ ፓትርያርክ ከእርሱ በኋላ በመንበሩ የሚቀመጠውን የሰየመበት ታሪክ አለ፡፡ ሁለተኛውን የእስክንድርያ ፓትርያርክ አንያኖስን የመረጠው የመጀመርያው ፓትርያርክ ቅዱስ ማርቆስ ነበር፡፡ በዘመን መለወጫ ዕለት አዘውትረን ስሙን የምንጠራው አባት ድሜጥሮስ ለመንበረ ማርቆስ የተመረጠው ከእርሱ በፊት በነበረው ልያኖስ በተባለው አባት ነበር፡፡ ታላቁን ሐዋርያዊ አባት አትናቴዎስንም ወደ መንበር ያመጣው እለ እስክንድሮስ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ምእመናኑና አባቶች በአንድነት የተስማሙበትን አባት በመንበረ ማርቆስ ያስቀ መጡበትም ጊዜ ነበር፡፡ በመሠዊያው ላይ ከጸሎት በኋላ በሚደረግ የዕጣ ሥነ ሥርዓት ፓትርያርኩ የተመረጡበት ጊዜም አለ፡፡ ብጹዕ አቡነ ሺኖዳ የተመረጡት አስቀድሞ ብዙ ድምጽ ካገኙ ሦስት አባቶች መካከል በተደረገ ዕጣ ነበር፡፡
በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደምናየው በፓትርያርኮች ምርጫ እና አገልግሎት ላይ በወቅቱ የነበሩ መሪዎች ጫና ያደረጉበት፤ ከዚያም አልፈው የራሳቸውን ሰው የሾሙበትም ጊዜ ነበር፡፡ ለምሳሌ ሐዋርያዊው አትናቴዎስ በግፍ ከመንበሩ ተሰድዶ በነበረ ጊዜ ባዛንታናውያን የራሳቸውን ፓትርያርክ መርጠው ጎርጎርዮስ ብለው ልከውት ነበር፡፡ እርሱም በመንበረ ማርቆስ ላይ 339–346 ዓም ተቀምጦ ነበር፡፡ የእስክንድርያ ክርስቲያኖች ግን አልተቀ በሉትም፡፡ በዚህም ምክንያት ከፓትርያርኮች ዝርዝር አያስገቡትም፡፡
በተለይም በኬልቄዶን ጉባኤ ዲዮስቆሮስ መከራ ከደረሰበት በኋላ መንበረ ማርቆስ የባዛንታይን መንግሥት በሚልካቸው ፓትርያርኮችና የእስክንድርያ ቅዱስ ሲኖዶስ በመረጣቸው አባቶች ሲፈራረቅ ነበር፡፡ በመንበሩ የተቀመጠውን ኦርቶዶክሳዊ ቀኖናዊ አባት በወታደር ኃይል እያሳደዱ የራሳቸውን ሰው መመደብን የባዛንታይን ነገሥታት ለመቶ ዓመታት ያህል ቀጥለውበት ነበር፡፡ ሕዝቡ ግን አልተቀበላቸውም፤ ከቁጥርም አያስገባቸውም፡፡
በስምንተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በመካከለኛው ምሥራቅ የዑምያድ ሥርወ መንግሥት አክትሞ የአባሲድ ሥርወ መንግሥት ሲተካ በግብጽ፣ በሶርያ እና በአካባቢው አለመረጋጋት ተፈጥሮ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት በአንጾኪያ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ለመሾም ከባድ ሆኖ ነበር፡፡ አስቀድመው የነበሩት ፓትርያርክ ዐርፈው በመንበሩ ያለ በዐለ መንበር ተቀመጦ ነበር፡፡
ሁኔታውን የተመለከተውና በወቅቱ ከነበረው የሶርያ ገዥ ጋር ቅርበት የነበረው በአንጾኪያ የካራን ሀገረ ስብከት ጳጳስ የነበረው አቡነ ይስሐቅ መንበሩን መረከብ ፈለገ፡፡ ለዚህ ሃሳቡም የካራንን አባሲድ ገዥ ከሊፋ አብዱላህ አቡ ጋፋርን ከጎኑ አሰለፈ፡፡ የአንጾኪያ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ‹‹የአባቶቻችን ቀኖና ሀገረ ስብከት ያለው ጳጳስ ፓትርያርክ እንዳይሆን ይከለክላል፤ በሌላም በኩል ማንም አባት ክህነትንም ሆነ ሥልጣንን ለማግኘት ብሎ የዓለማዊ መንግሥታትን የተማጸነ ይወገዝ ብለው አባቶቻችን ቀኖና ሠርተዋልና  አንቀበልህም›› አሉት፡፡
ከሊፋ አብዱላህ አቡ ጋፋር በሲኖዶሱ ውሳኔ ተበሳጭቶ ሁለት ጳጳሳትን አስገደላቸው፡፡ አቡነ ይስሐቅንም በኃይል በመንበረ ዮሐንስ ላይ አስቀመጠው፡፡ አቡነ ይስሐቅም የእርሱን ፓትርያርክነት የእስክንድርያው ፓትርያርክ አቡነ ሚካኤል አንደኛ (744-767) ያውቅለት ዘንድ ደብዳቤና ስጦታ ወደ እስክንድርያ ላከ፡፡
አቡነ ሚካኤል የአቡነ ይስሐቅን ደብዳቤ ከተመለከተ በኋላ ከቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ ሕግን በመጣስና ያለ ቅዱስ ሲኖዶሱ ፈቃድ የተሾመ በመሆኑ እንደማይቀበለው ለመልክተኞቹ ገለጠላቸው፡፡ መልክተኞቹም ጉዳዩን ወደ ግብጹ ገዥ አቀረቡት፡፡ የግብጹ ገዥ ከከሊፋ አብዱላህ ጋር መጋጨት ስላልፈለገ አቡነ ሚካኤል የአቡነ ይስሐቅን ሹመት እንዲቀበሉት አዘዘ፡፡
አቡነ ሚካኤልም ሲኖዶሱን ለመሰብሰብ የሦስት ቀን ጊዜ ጠየቁ፡፡ ነገር ግን የእስክንድርያ ሲኖዶስ ከቤተ ክርስቲያን ቀኖናና ታሪክ አንጻር ጉዳዩን በማየት አንድ ወር ወሰደ፡፡  በዚህ ጊዜም
 1. ሀገረ ስብከት ያለው አባት ሀገረ ስብከቱን መተው ወደ ሌላ ሹመትም መሄድ እንደሌለበት ቀደምት አበው መወሰናቸውን
 2. በዓለማዊ ባለ ሥልጣን ድጋፍ ወደ መንበር የሚመጣ ጳጳስ ቢኖር ከሹመቱ እንዲሻር የቤተ ክርስቲያን ቀኖና እንደሚያዝ
በመጨረሻም ዛሬ የአቡነ ሚካኤል ቀኖና የሚባለውን ውሳኔ በመወሰን የአቡነ ይስሐቅን ሹመት እንደማይቀበለው ገለጠ፡፡ መልክተኞቹም ለግብጹ ገዥ ጉዳዩን አቀረቡ፡፡ የግብጹ ገዥ በልመና ጭምር ለማግባባት ሞከረ፡፡ ግን አልሆነም፡፡ በመጨረሻም መልክተኞቹ አቡነ ሚካኤልን ከእነርሱ ጋር ከሊፋ አብዱላህ ወዳለበት ወደ ካራን እንዲሰድደው ጠየቁት፡፡
አቡነ ሚካኤል ወደ ካራን ሄዶ ስለ ቤተ ክርስቲያኒቱ ቀኖና የሚደርስበትን ሁሉ ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን ገለጸ፡፡ ሁለት ጳጳሳትም አብረውት ለመሄድ ተነሡ፡፡ መልክተኞቹና አቡነ ሚካኤል ወደ ካራን ለማምራት በዝግጅት ላይ እያሉ አቡነ ይስሐቅ በሕዝቡ ጸሎት ምክንያት ማረፉ ከአንጾኪያ ተሰማ፡፡ ነገሩም በዚሁ አበቃ፡፡
የግብጽ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ በተፈጠሩ ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ምክንያቶች ለዓመታት በዐቃቤ መንበር የተመራበት ዘመን ነበር፡፡ ይህ ሁኔታ ይፈጠር የነበረው በአንድ በኩል ነባሮቹ ፓትርያርኮች በገዥዎች ተግዘው ወይም ታሥረው መንበሩ ባዶ ሲሆን፤ ያለበለዚያም ደግሞ ነባሮቹ ፓትርያርኮች ዐርፈው በቀጣዩ አባት ምርጫ ላይ በምእመናኑና በአባቶች፣ በአባቶችና በአባቶች፣ እንደዚሁም በቤተ ክርስቲያኒቱና በገዥዎቹ መካከል ስምምነት ሲጠፋ ነው፡፡
ከአቡነ ዮሐንስ 19ኛ (1928–1942) በኋላ ለሁለት ዓመት፤ ከአቡነ መቃርዮስ 3ኛ (1944–1945) በኋላ ለአንድ ዓመት፤ ከአቡነ ዮሐንስ 2ኛ (1946–1956) በኋላ ዓመታት መንበረ ማርቆስ በዐቃቤ መንበር ብቻ ለመመራት ተገድዶ ነበር፡፡
አቡነ ሺኖዳ 3ኛ በመንበረ ማርቆስ ላይ ከተቀመጡ ከዐሥር ዓመት በኋላ ከአንዋር ሳዳት ጋር ስምምነት አልነበራቸውም፡፡ በተለይም ደግሞ በግብጽ አብያተ ክርስቲያናትና ምእመናን ላይ የሚደርሰውን ግፍ ለማስቆም መንግሥት ዝም በማለቱ አርሳቸው ፊት ለፊት የሳዳትን መንግሥት መተቸት ጀመሩ፡፡ ይህም አንዋር ሳዳትን ስላበሳጨው የግብጽ ሚዲያዎች በይፋ ፓትርያርኩን የሚያቃልሉ ፕሮግራሞችን ማቅረብ ጀመሩ፡፡ በመጨረሻም አንዋር ሳዳት አቡነ ሺኖዳን በ1981 ዓም ከመንበራቸው አንሥቶ በግዞት ወደ አባ ብሶይ ገዳም ላካቸው፡፡
የግብጽ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ ሁኔታውን በተመለከተ በሁለት ሃሳብ ተከፈለ፡፡ በአቡነ ሳሙኤል የሚመራው አካል ሺኖዳን በኃይለኛነት በመውቀስ ቤተ ክርስቲያኒቱን ከመንግሥት ጋር እንድትጋጭ በማድረግ ችግር ውስጥ ከትተዋታል ብሎ አቋም ያዘ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ‹‹ለቤተ ክርስቲያናቸው ሲሉ የወሰዱት ትክክለኛ አቋም ነው›› ብለው አወደሷቸው፡፡ ከእርሳቸውም ጋር አብረው ተሰደዱ፡፡ ምንም እንኳን ሳዳት አቡነ ሺኖዳን ‹‹የቀድሞው ፓትርያርክ›› ቢላቸውም አብዛኞቹ ጳጳሳትና ምእመናን ይህንን አልተቀበሉትም ነበር፡፡
የቤተ ክርስቲያኒቱ ሲኖዶስም በአቡነ ሺኖዳ ምትክ ሌላ አባት መሰየሙን አልተቀበለውም፡፡ በምትኩ የጳጳሳት ኮሚቴ ተቋቁሞ ቤተ ክርስቲያኒቱን መምራት ጀመረ፡፡ በዚህ ጊዜ እጅግ የታወቁት የገዳማት አባቶች ሳይቀሩ የአቡነ ሺኖዳን ሃሳብ የተቃወሙበት ጊዜ ነበር፡፡ ታዋቂው የአባ መቃርዮስ ገዳም አበ ምኔት መታ አል ምስኪን አቡነ ሺኖዳ የተሾሙበትን  ጊዜ ‹‹ የቤተ ክርስቲያን የመከራ ዘመን መጀመርያ›› እስከ ማለት ደርሰው ነበር፡፡
በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የመካከለኛው ዘመን ታሪክም ‹‹የሦስት ፖፖች ታሪክ›› የሚባል ምዕራፍ አለ፡፡ ይህ ምዕራፍ በሮም ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከ1378 እስከ 1417 ዓም ድረስ በአንድ ወቅት ሁለት ፖፖች ራሳቸውን ሕጋዊ ፖፕ አድርገው ያቀረቡበት ጊዜ ነው፡፡ የሮም ቤተ ክርስቲያን መንበር ወደ ሮም ከተመለሰ በኋላ ፈረንሳይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ታደርግ ነበር፡፡ በወቅቱ የነበሩት ፖፕ ጎርጎርዮስ 11ኛ ሲያርፉ የሮም ሲኖዶስ የፈረንሳይን መንግሥት ተጽዕን በመፍራት ምንም ዓይነት ሮማዊ ዕጩ ሳይቀርብ ናፖሊታናዊውን ኡርባን 6ኛን በ1378 ሾሙ፡፡ ነገር ግን ከጥቂት ቀናት በኋላ የፖፕ ኡርባን ጠባይና አሠራር ተበላሸ፡፡ ሿሚዎቹም መፀፀት ጀመሩ፡፡ ብዙዎቹም በመካከለኛው ጣልያን ከሮም ምሥራቅ ደቡብ ምሥራቅ ወደ ምትገኘው አናኒ ከተማ ራሳቸውን አሸሹ፡፡
በአናኒ ከተማ የተሰበሰቡት የካቶሊክ ካርዲናሎችም ፖፕ ኡርባን በመንበራቸው ላይ እያሉ የጄኔቫውን ሮበርት  ፖፕ ቀሌምንጦስ 7ኛ ብለው በዚያው ዓመት መስከረም 9 ቀን ሾሙ፡፡ ይህም የብጥብጡ መነሻ ሆነ፡፡ ዮፖፑንም መቀመጫ ወደ በአቪግኖን አደረጉት፡፡ ፈረንሳይ፣ አራጎን፣ ቆጵሮስ፣ ቡርጉንዲ፣ ሳቮይ፣ ኔፕልስ፣ እና ስኮትላንድ የአቪግኖን ፖፕ ተቀበሉ፡፡ ዴንማርክ፣ እንግሊዝ፣ ፍላደርስ፣ የሮም መንግሥት፣ ሐንጋሪ፣ አየርላንድ፣ ኖርዌይ፣ ፖላንድ፣ ስዊዲንና የቬነስ ሪፐብሊክ ደግሞ ሮም ላይ የተቀመጠውን ፖፕ ደገፉ፡፡
ይህ የመንበርና የሕጋዊነት ጥያቄ ሁለቱም ፖፖች ካለፉም በኋላ ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ምክንያቶች እየተሰጠው ቀጠለ፡፡ ችግሩን ለመፍታት ለብዙ ዘመናት የተደረገው የዲፕሎማሲም ሆነ የኃይል ጥረት ውጤት አላመጣም፡፡ ሁለቱ ፖፖችን ይደግፉ የነበሩት ካርዲናሎች በ1409 ዓም ፒሳ በተባለች ከተማ ተሰብስበው ሁለቱንም ፖፖች በመተው ሌላ ፖፕ ለመምረጥ ተስማሙ፡፡ በዚህም መሠረት አሌክሳንደር 5ኛ የተባሉትን ፖፕ መረጡ፡፡ ነገር ግን በሊቃውንቱም ሆነ በምእመናኑ ዘንድ ድጋፍ አላገኘም፡፡ ከፖፕ አሌክሳንደር ቀጥሎም ተቃዋሚው ፖፕ ዮሐንስ 23ኛ (anti pope) በዚሁ መንገድ ተመረጡ፡፡ ጭቅጭቁ ግን ቀጠለ፡፡
አን ግሪሰን የተባሉ ሊቅ ባደረጉት ጥረት ቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶችና ምእመናን በመተባበር በ1414 ዓም የኮንስታንስ ጉባኤ የሚባለውን ጠሩ፡፡ በዚህ ጉባኤ ላይ ሦስተኛው ፖፕ አቡነ ዮሐንስ 23ኛ ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው ለመተው ተስማሙ፡፡ በሮም የነበሩት ፖፕ ጎርጎርዮስ 12ኛም ለቤተ ክርስቲያኒቱ ደኅንነት ሲሉ መንበራቸውን ለመተው  ተስማሙ፡፡ ጉባኤው ይህንን ካገኘ በኋላ በአቪግኖን የነበሩትን ፖፕ ቤነዲክት 13ኛን ተመሳሳይ ተግባር ያከናውኑ ዘንድ ጠየቀ፡፡ እርሳቸው ግን ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡
በዚህም የተነሣ ጉባኤው ፖፕ ቤነዲክት 13ኛን አወገዘ፡፡ በዚያው ጉባኤም ችግሩን ዘግቶ ከሦስቱም ውጭ የሆኑትን ፖፕ ማርቲን 5ኛን መረጠ፡፡ ነገር ግን የአቪግኖን ካርዲናሎችና አንዳንድ ወገኖች አዲሱን ፖፕ በመቃወም አቡነ ቤነዲክትን መደገፋቸውን ቀጠሉ፡፡ ከአቡነ ቤነዲክት 13ኛ በኋላም ሦስት ተከታታይ ፖፖችን መረጡ፡፡  በመጨረሻ ግን በአቪግኖን መንበር የተሾሙት አቡነ ቀሌምንጦስ 8ኛ ለቤተ ክርስቲያኒቱ በማሰብ በፈቃዳቸው ሹመታቸውን በመተው በ1429 ዓም በሮም ለተሰየሙት አቡነ ማርቲን 5ኛ ድጋፋቸውን ሰጡ፡፡
በግብጽም ሆነ በአንጾኪያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ስናይ በፓትርያርክ ምርጫ ጊዜ የሚፈጠሩት ችግሮች ከአራት ምክንያቶች የሚመነጩ ነበሩ፡፡ የመጀመርያው ቤተ ክርስቲያኒቱ በሌሎች ተጽዕኖ ሥር ስትወድቅ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች በሚፈጠሩ ክርክሮች የተነሣ ነው፡፡ ሦስተኛው ምክንያት አባቶች የሓሳብ አንድነት በሚያጡበት ጊዜ ሲሆን አራተኛው ደግሞ ሀገራዊ ጉዳዮች አስገዳጅ ሲሆኑ ነው፡፡
ዝርዝሩን ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሁኔታ አንጻር ሳምንት እናየዋለን፡፡


50 comments:

 1. Thank u for sharing... I cried when u told about HH Abune Paulus's reaction about our church... even if we have heard so many bad things it's nice to hear something heartfelt for a change...

  ReplyDelete
 2. why do u have to wait until his death to write this?

  ReplyDelete
 3. Ohh!thankyou Dani keep the good work !!this is what we need from you may GOD bless your knowledge !!cant wait to read the next

  ReplyDelete
 4. Thanks Dani, it is very nice piece. It is very nice to learn from history. We are now in the 21st century with "full" knowledge about the past. We should handle situations a lot better than in the past (11th c. ... 14th century or whatever).

  Keep writing Dani, hope our fathers will scarify for the best interest of the church.

  ReplyDelete
 5. ዲ/ን ዳንኤል
  ተባረክ!!! እንዲህ በእዉቀት ላይ የተመሰረተ ትንታኔህ በሌሎች ላይ እዉቀትን ስለሚጨምር ለመልካም ዉሳኔ ያራሱን በጎ አስተዋጽኦ ማድረጉ የማይታበል ስለሆነ በትጋትህ ያበርታህ እዉቀቱንም ያብዛልህ፡፡

  ReplyDelete
 6. 1. በመጽሐፍ ቅዱስ ንጉስ ሰለሞን በአባቱ በንጉስ ዳዊት ዘመን ሊቀ ካህን የነበረውን አብያታርን አባርሮ በእርሱ ምትክ ሌላ ሾሟል፡፡ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ካህኑ አብያታር የንጉስ ሰለሞን ተቃዋሚ የታላቅ ወንድሙ ደጋፊ ስለነበር ነው፡፡

  2. ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ክርስቲያኖች ሁሉ ለመንግስት ባለስልጣናት እንዲታዘዙ አጥብቆ ያስተምር ነበር ይህንን የሚያደርገው ለዓለማዊ መንግስታት ተጨንቆ ሳይሆን እነርሱን ቢቃወም የወንጌል ቃል እንዳይሰራጭ እንቅፋት ይሆናሉ ብሎ በመስጋት ነው፡፡

  ለሁላችንም ግልጽ ሊሆን ሚገባው ነገር የሰው ልጅ በባህሪው የሚቃወሙትን ይቃወማል፤ ስለዚህ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከመንግስት ጋር ተግባብቶ ሊሰራ የሚችል አባት ቢመርጡ መልካም ነው፡፡

  ReplyDelete
 7. ቤተ-ክርስቲያን እጅግ በጣም ዉስብስብ በሆነ ችግር ዉስጥ እያለፈች እንደመጣች ግልጽ አድርጎ የሚያሳይ ድንቅ ጥናት! የኛዋን ቤተ-ክርስቲያን በተመለከተም ሰፊ ዳሰሳ እንጠብቃለን፡፡

  ReplyDelete
 8. Hi Dani,

  Thank you for sharing this timely idea. God bless you.

  I also have similar prception on Abune Paulos behaviour. But, I think since He already passed, better not to look the detailed of Him.

  As you stated, due to the various reason worldwide Patriarich selction or nomination was facing so many challenges. But EOTC should learn from the others, and should done her best so as t create peace.

  So the first and the last thing should be praying to Almighty God so as to give Father that will lead us accordingly. The other things are simply for our satisifaction.

  keep in touch.

  kebede

  ReplyDelete
 9. Good Overview, especially the introduction. But for me, I can not wait to read the following article. Just to know what all this mean for our church. Hope we are ready to embrace the road ahead of us.

  ReplyDelete
 10. Thanks Dn. Daniel,

  በመጨረሻም አንዋር ሳዳት አቡነ ሺኖዳን በ1881 ዓም ከመንበራቸው አንሥቶ በግዞት ወደ አባ ብሶይ ገዳም ላካቸው፡፡
  I think the year is 1981. Isn't it?

  ReplyDelete
 11. Dn. Dani, could you edit the date of conflict between pope ShenodaIII and Sadat? It is not in 1881, but 1981.Thank you.

  ReplyDelete
 12. lmene ahune selalwe selwaldeba attsffeme. selwaldeba msemat aeneflegalne information kalh.please write about waldeba monastery

  ReplyDelete
 13. ወንድም ዳንኤል ላቀረብክልን ዝርዝር መረጃ አመሰግናልሁ-ሁኖም ስለ ፓትርያርኩ ባህርይ ግራ መጋባትህን ገለጽክ፡፡እኔ ደግሞ ያነተ ነገር ነው ግራ እየሆነብኝ የመጣው ምክንያቱም እኚህ አባት ዘመናቸውን ሁላ የቤተክርስትያን ጠላት ሆነው እንዳሳለፉ አስመስለህ መጻፍህ ነው ለዚህም "...እኒህ አባት ሁላችንም ያላወቅንላቸው የተደበቀ መልካም ሰብእና ይኖራቸው ይሆን? እላለሁ፡፡" የሚለው አገላለጽህ ምንም የሚታይ በጎ ሥራ እንዳልታየህ ለመግለጽ ይመስላል-ይሄ ግን በገሃድ ካየነው ጋር ይጋጫል፡፡በዚህ መሰረት አንተም እንዳልከው ቤተክህነት ብቻ ሳትሆን እንዳንተ ዓይነቱም ተራማጅ እና ቅን ሰዎችም ከፖለቲካ ጋር እየተቀላቀለባቸው ተስፋችን ሁላ ጨልሞ ይታየኛል፡፡

  ReplyDelete
 14. lamen alakaso kamaferade enedeneden negarane

  ReplyDelete
 15. betam asitemari, thanks dani
  ግን ለምን ነበር ያለቀሱት?
  dahlak

  ReplyDelete
 16. What impressive!! [interms of your ability to organize such piece - as usual very lucid & tasty piece]. And also very attractive to let us think of how to be acre full during Patriarch election.

  Many thanks!!!

  Ayenachew

  ReplyDelete
 17. ወንድማችን ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
  እግዚአብሔር ይስጥልን።
  ቃለ ህይወት ያሰማልን።
  እንደዚህ ታሪክን ዘካሪ አባቶች እግዚአብሔር አያሳጣን።
  አሜን።

  ReplyDelete
 18. ወንድም ዳንኤል በእድሜ ልጄ ትሆን ይሆናል:: ማድረግ ባትችል እንኳ ልምድህን አካፍለን:: መጠየቅ የሚቻለው መገደፉና መንቀፉ ሚዛናዊ የሚሆነው ሲታወቅ ይመስለኛ:: እኛ መሆን ያለበትን መሆን ከሌለበት ለይተን የምናውቀው በናንተ ተመርኩዘን ነው:: ሁሌም ጻፍ ባትመሰገን ብትነቀፍም ጻፍ ያመንክበትን የመሰለህን ጻፍ ጻፍ ጻፍ ጻፍ :: ብሎ ነበር መባል ቀላል አይደለም:: ነገ ልብ ያለው ከተገኘ እሱን አማክሩትም ይመጣል:: ወንድሜ የጻፍክ እንደሆነ አንተም ታርፋለህ:: ነገ ጸጸትን የሚወልድ ምንም አጋጣሚ የለህምና:: ምናልባትም ቀጣዩ ትውልድ መልእክቶችህን ምዕራፍና ቁጥር ሰጥቶ ይጠቅሳቸው ይሆናል:: ስለዚህ ጻፍ

  አንዳንድ ችግሮቻችን የመነጩት ከልምድ እጥረት ነው:: የራስን እየናቁ የሌላን በመከተልና ነባሩን ይዞ ለማቆየት በሚታገል ሕዝብ መካከል የትውልድ ክፍተት እንዳይፈጠር እንዲህ ዓይነት ገዥ አሳቦችም ክፍተቱን ለመሙላት የራሳቸው ሚና አላቸው:: የመጽሐፍ ሥራዎችህን ይዘት ጭምር ሳያቸው ችግር ፈቺ እንጂ ገበያ ተኮር አይደሉም:: ይበል ልጄ በርታ:: የሚዲያ ውበቱ የመሪነት ሚና መጣወቱ ነው::

  ReplyDelete
 19. Hi Dn. Daniel. could you make your recent articles becomes readable in pdf please? we are interested to read your blog. but i d't have an amharic font in my PC. it is not permitted to load any program in our computer.

  May Almighty God bless you.

  Getaneh

  ReplyDelete
 20. Someone who has gone looking for peaceAugust 29, 2012 at 6:10 PM

  This comment has been removed by a blog administrator.

  ReplyDelete
 21. ወንድም ዓለም ዳንኤል እንደ ወትሮው በሚገባ አነበብኩት። ሁል ጊዜ ከማንበብ ይህችን ጥሑፍ ብመርቅ መልካም መስሎ ታየኝና ጻፍኩት።

  የግብጹ ፓትርያርክ አቡነ ሺኖዳ ካረፉ በኋላ እሳቸውን የመሰሉ ደገኛ አባት ፍለጋ ግብጽ በጸሎት ተጠምዳለች። ዳዊት በትንቢቱ “ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” እንዳለ ደገኛ አባት ስጠን ብለን እጃችንን ወደ እግዚአብሔር መዘርጋት ያለብን ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው። ስለ ቤተክርስቲያን የሚያለቅስና የሚጸልይ ቢኖር ጊዜው ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው። በአሜሪካና በሀገር ቤት የተራራቀችውን ቤተክርስቲያን በፍቅርና በብስለት አንድ የሚያደርጉ አባት ይሰጠን ዘንድ የጸሎት ጊዜው አሁን ነው። ሐዋርያው “እለት እለት የሚያስጨንቀኝ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ነው” እንዳለ እንደ ቅ/ጳውሎስ ያለ ለቤተክርስቲያን ቀናተኛ ለመንጋው መልካም እረኛ እግዚአብሔር ያዘጋጅልን።  ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ “Apostolic Succession”

  ከሐዋርያት አለቃ ከቅ/ጴጥሮስ እስከ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ድረስ ኢትዮጵያ ያሳለፈችውን ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ እንዲህ እናገኘዋለን፦

  የሐዋርያት አለቃ ቅ/ጴጥሮስ ነው።

  ከቅዱስ ጴጥሮስ ቀጥሎ ቅ/ማርቆስ።

  ቅ/ማርቆስ ግብጽ ሄዶ መንበሩን በግብጽ አደረገ።

  ከቅ/ማርቆስ ቀጥሎ አንያኖስ ነው።

  ከአንያኖስ ቀጥሎ 20 ፓትርያርክ አሉ። 20ኛው አትናቴዎስ ነው።

  ከአትናቴዎስ ቀጥሎ ከሳቴ ብርኅን አባ ሰላማ /ፍሬምናጦስ/ ይህን ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ ወደ ሀገራችን አመጣልን።

  ፍሬምናጦስ ኢትዮጲያዊ አይደለም። አንድ ነጋዴ ሲድራኮስና ፍሬምናጦስ የሚባሉ ሁለት ልጆቹን ይዞ አንድ ነጋዴ ቤት ገብቶ መኖር ጀመረ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ነጋዴው ሞተ። ልጆቹም በገበሬው ቤት መኖር ጀመሩ። ፍሬምናጦስም የኢትዮጵያዊያንንn እምነትና ባህል አደንቃለሁ። ለምን ሥጋ ወደሙን አትቀበሉም? ብሎ ገበሬውን ጠየቀው። ገበሬውም ካህናት ስለሌሉን ነው አለው። ፍሬምናጦስም በኢዛና እና ሳይዛና ፈቃድ ግብጽ ሄዶ ፕትርክናን ከአትናቶዎስ ተቀበለ።


  የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ፍሬምናጦስ ነው።

  ከዚህ ጊዜ በኋላ ለብዙ ዘመናት ኢትዮጵያ በግብጽ ፓትርያርኮች ስትመራ ቆይታለች።

  የመጀመሪያው አራቱ ኢትዮጲያዊያን ጳጳሳት በ1921 ተሾሙ!

  አቡነ ሚካኤል
  አቡነ ጴጥሮስ
  አቡነ አብርሐም
  አቡነ ይሥሐቅ ናቸው።

  ከዚህ ጊዜ በኋላ በግብጽና በኢትዮጲያ መካከል ለሃያ አመታት ያክል ሀገራችን ኢትዮጵያዊ ጳጳስ ያስፈልጋታል አያስፈልጋትም በሚል ሽኩቻ ውስጥ ነበሩ።

  ይህ እልህ አስጨራሽ ሽኩቻ አለፈና በ1940 ሌሎች አራት ጳጳሳት በግብጻዊው ፓትርያርክ በአቡነ ዮሳብ ተሾሙ።

  አቡነ ሚካኤል
  አቡነ ያዕቆብ
  አቡነ ባስልዮስ
  አቡነ ጢሞቴዎስ ናቸው።

  ከእነዚህ ጳጳሳት አቡነ ባስልዮስ የመጀመሪያው ኢትዮጲያዊ ሊቀ ጳጳስ ኾነው ተሾሙ!! በዚህች እለት 21 ጊዜ መድፍ ተተኮሰ! ታላቅ ደስታ ነበርና! ጊዜውም በ1943 ዓ.ም ሲኾን ለአቡነ ባስልዮስ ሊቀ ጵጵስናውን የሰጡት የግብጹ ፓትርያርክ አቡነ ዮሳብ ነበሩ።

  ከ1951-1963 ዓም ድረስ የመጀመሪያው ኢትዮጲያዊ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ባስልዮስ የመጀመሪያው ኢትዮጲያዊ ፓትርያር ኾኑ!!


  በርግጥ ከአቡነ ባስልዮስ በፊት አቡነ አብርሐምና አቡነ ዮሐንስ የሚባሉ ሌሎች ሁለት ፓትርያርክ ነበሩ። ነገር ግን የኢጣልያው መንግስት ስለሾማቸው ቤተክርስቲያናችን ሕጋዊ ፓትርያርክ አድርጋ አትቀበላቸውም። የመጀመሪያው ሕጋዊ ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ ናቸው።  ከአቡነ ባስልዮስ ቀጥሎ ፓትርያር አቡነ ቴዎፍሎስ ናቸው።

  ከአቡነ ቴዎፍሎስ ቀጥሎ አቡነ ተክለሐይማኖት ናቸው።

  ከአቡነ ተክለሐይማኖት ቀጥሎ አቡነ መርቆርዮስ ናቸው።

  ከአቡነ መርቆርዮስ ቀጥሎ አቡነ ጳውሎስ ናቸው።


  ከአቡነ ጳውሎስ ቀጥሎ ማን ይሆን?

  ለቤተክርስቲያን ቀናተኛ ለመንጋው መልካም እረኛ እግዚአብሔር ያዘጋጅልን።

  Visit this Blog! http://yonas-zekarias.blogspot.com

  ReplyDelete
 22. Dn betam girum tarikawi timeret new esti degemo yegan enayewalen????

  ReplyDelete
 23. ለኔ ግዜ ያለፈበት ፅሑፍ ነዉ የፃፍከዉ አባ ጳዉሎስን በተመለከተ ማለቴ ነዉ
  እኔ በሩቅ ያዉም አንዳንድ ቀን ያዉም ተገድጄ ከምሰማዉ ንግግራቸዉና ከማየዉ ድርጊታቸዉ ለታላቁ ኃላፊነት ላይ ሊያስቀምጣቸዉ የሚያበቃ ስነምግባርም ሆነ ርቱዓ ሐይማኖት የላችዉም ሰዉየዉ ግን እንኳን የሚያዉቁትን የማያዉቁትንና የማያመኑበትን አስመስለዉ የመናገር ብቃት የተካኑ በዚህ ዓለም እዉቀት እጂግ የረቀቁ ሰዉ የነበሩ ይመስለኛል እንጂ እንዳልከዉ የመልካም ስብዕና ያዉም እስከ ማንባት የሚደርስ ብቃት ቢኖራቸዉ ምእመኑ እንዲህ እርሳቸዉን በመጥላት ክርስትናዉ ሲፈተንበት ለምን ዝም ማለትን መረጡ ለምንስ እንዲያ ከፓትሪያርክ ቀርቶ ከኔ ቢጤ ጎረምሳ ክርስትያን የማይጠበቁ ተግባራትን ለመንጋዉ አንዳች ሳያስቡ ፈፀሙ መጠራጠር ላልፈለግ እርሳቸዉ ነፍሳቸዉን ይማራቸዉና ያለቦታቸዉ ተደንጉረዉ የኖሩ ሰዉ ይመስሉኛል
  ያ እንባ የተዋናይ እንባ አይደለም ያልከንስ ምንድን ነበር ማስረጃህ የተዋናይ እንባ ቀይ ነዉ ቢጫ እንዲያዉ አይመስልም ብትል እንኳ አንድም ያንተ የመለየት አቅም ወርዶ አልያም እርሳቸዉ የማስመሰል ጥበቡን ተክነዉት ባልኩ ነበር ያ ዕንባ ዝም ብሎ የመጣ የተዋናይ ዕንባ እንዳልነበረ እኔ ራሴ በዓይኔ ያሁት ነው ማለት ግን እንደኔ ላለ አንባቢህ ቤት አይመታ ሚዛንም አይደፋም ከሁሉም በላይ ግን አባ ጳዉሎስን የትኛዉንም አይነት ሰዉ ቢሆኑም እንደ መንፈሳዊ ሳየዉ ስለርሳቸዉ ይህን የመሰለ ፅሁፍ መፃፍ የነበረብህ ዛሬ ሳየሆን በቁም ሳሉ ቤተ ክርስትያንን አባቶችን ቁም ስቅል ሲያሳዩ ግራ ሲያጋቡ ነበር ለኛም በጣሙን ደግሞ ለርሳቸዉ የሚጠቅማቸዉ አሁን ግን እኛም ያመጣ ወሰደ ብለን ነፍስ ይማር ብለናል እርሳቸዉም ካወዛጋቢዉ ማንነታቸዉ ጋር ወደ ፍርድ ሄደዋል በምህረቱ እንዲያያቸዉ ለቤተክርስትያንም ለመንጋዉ የሚራራ የሚረዳን የቀና ሃይማኖት ያለዉ አባት እንዲስጣት ላንተም ተናጋሪ አንደበት ድንቅ ድንቅ ቃላትንም የሚያፈልቅ ልብ ብቻ ሳይሆን አስተዋይ ክርስትያናዊ ህሊና እንዲሰጥህ እመኛለሁ
  በተቀረዉ ሃሳብ ግን እስማማለሁ

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተ ማን ነህና ነው ትልቁን ሰው የምትገመግም፡፡ ሥራ ፈት የመንደር ሃውልት፡፡

   Delete
 24. ዲ/ን ዳንኤል በጣም ጥሩ እና ወቅታዊ ጽሑፍ ነው። የእኛ ችግር አዲስ ያለመሆኑን ማወቃችን በራሱ ትልቅ ነገር ነው። ከጠቀስካቸው ታሪኮች እንደምንረዳው ለቤተክርስቲያን ችግሮች መፈታት የአባቶች/የግለሰቦች መንፈሳዊነት ወሳኝ ሚና አለው። በዚህ መንፈሳዊነት እንደሞኝነት በተቆጠረበት ዘመን ለችግሮቻችን መንፈሳዊ መፍትሄ መፈለግ በጣም ከባድ ቢሆንም ሊያስገርመን አይገባም። በእኔ አስተያየት የመጀመሪያው ተግባር መሆን ያለበት የዕርቀ ሰላም ጉዳይ ነው። ከዚያ በኋላ የሚደረግ ምርጫ (ካስፈለገ)በተቻለ መጠን የግል ሰሜታችንና ፍላጎቻችንን ለእግዚአብሔር አደራ የምንሰጥበት ይሆን ዘንድ እንደ ሐዋርያት ትውፊት ዕጣ በማውጣት የሚፈጸም ቢሆን ጥሩ ነው።ከሌሎች አብያተክርስቲያናትም ሆነ ከራሳችን ታሪክ ተምረን የተሻለ የመፍትሔ እርምጃ ለመውሰድ አባቶቻችንን እግዚአብሔር ይርዳቸው። የቤተክርስቲያን አምላክ ለቤተክርስቲያን ቅን መሪን እንዲሰጥ የምንማጸንበት ወቅት ላይ ስለምንገኝ እስቲ በጸሎት እንትጋ። ብዙዎቻችን ከምናስበው የተሻለ መፍትሔ ያለው እግዚአብሔር መሆኑን በተግባር እያየን ነውና።

  ReplyDelete
 25. tnks dani i am exited.i cant wait until next weak.

  ReplyDelete
 26. ዳንኤል፦ ነገር ቢበዛ ባህያ አይጫንም። አኹን አቡነ መርቆርዮስ ተመልሰው የቤተ ክርስቲያን አንድነት ስለሚገኝበት መንገድ ማሰብ ያሻል። ዝባዝንኬ አናብዛ!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. How can we be sure Abune Merkorios is appropriate? The previous records show us the reverse

   Delete
  2. Anonymous: How can we be sure about ANY THING WHATSOEVER, including, that is, about that which Daniel et al seem to be suggesting should be done?

   Delete
 27. ያ ዕንባ ዝም ብሎ የመጣ የተዋናይ ዕንባ እንዳልነበረ እኔ ራሴ በዓይኔ ያሁት ነው፡፡ ፓ ግሩም አገላለፅ ያልተረዳናቸዉ አባት የሚል ሐዉልት ብናሰራላቸዉ ወይ ከነጂጂ ጋር በመተባበር ጳዉሎስ ፋዉንዴሽንን ብናፋጥነዉ ከተቻለመ ታቦት ቢቀረፅላቸዉ ምን ይመስልሃል ግራ የገባችሁ አበሾች ለማዉራት እንጂ ለምን እንደምታወሩ የማታዉቁ

  ReplyDelete
 28. Good views and timely important!!!

  ReplyDelete
 29. Dn. Daniel, I have read the comment written by "someone who has gone looking for peace". It is really amazing. The person, as I Perceived him,has three misunderstandings. He expressed us the Ethiopians as peoples who resist any kind of new ideas and may lable those pioneers. Again he presented us as we are so difficult ones to be served by someone, and Thirdly he agitates you not to leave the church, but to stay in. What does it mean? We are not peoples as the writer labled us. In fact we have not any room to hide in any wrong ideas or thoughts to be planted in our church. Look when the nine Saints came to Ethiopia with pure Orthodoxy our forefathers accepted them with open heart, but they refused when the Roman missionaries came and tried to substitute our faith by their ones. The writer to support his ideas he has mentioned about two of our church fathers and a church scholar that were labled by the congregations to be not an Orthodoxy. My dear to support or to denay the idea of the people we have to examine the real cause of the refusal of the people. All the three that he mentioned were known to the people by all what they taught while alive here in flesh. We know who is who and what. The real sense of ecumenism is not smuggling new ideas to the church of christ, but it is helping each other in propagating the goodtides. Nobody lables me as fantic for refusing any new idea which never sound orthodoxy. Secondly he has presented us peoples who are so difficult to serve them. I do not want to say more, but just a word. the whole world witness as we are a hospitable people. To be sure let any of us participate in the service with pure teaching of Orthodoxy and good behaviour.In fact there might be some labling will happen to some extent till the people taste our goodness. Finally the writer wants to advise Dn. Daniel as if Daniel is a stranger to his mother church. I have good relation with Dn. Daniel for more than 20 years. I know him as much as somebody could know the other. I know his failur and strength.Nobody defend his orthodoxy. So, while Daniel is a man who we know through all his services, why this guy/lady wanted to give him a "special" advice? As I read the comment in his introduction the person told him as this comment has written not to be posted officially, but to be read privately. What does it mean? If the person wants to advise Dn. Daniel why not he meet him in person? I do not want to say in black and white the person is intending this and that, but what I want is that please do not lable the Ethiopians as if we are block of the Gospel. We know from history the region that called as Asia Minor which was once a region where christianity was flourished.Even most of our church fathers are from that region. Today, where are those countries? They were converted to Islam or any other religion. Our Ethiopian Orthodox Tewahido Church and the Protestant Churches of Ethiopia have accepted the concept of ecumenism, and even some of them are members of the WWC. Does the writer believe that these protestant churches are serving according to the spirit of the ecumenism? Let us stay in our church, let us co-operate with others without leaving our forefathers faith, order and rites. Let us love the others who are not our members. Let us care the whole nations in Jesus Christ. Let us admire our innocent fathers and mothers. Let us hold fast that we have.

  ReplyDelete
 30. የቤተክርስቲያን አንድነቷን የመመለስ ጉዳይስ እንዴት ቢኾን የሚሻል ይመስልሃል? አሁን ያለውን አጋጣሚ በመጠቀም እስከአሁን የነበረውን ክፍተት ማስተካከል የሚቻልባቸው ነጥቦች የትኞቹ ይመስሉሃል? በዚህ ረገድ ጳጳሳት ምን ማድረግ ይገባቸዋል? ሀገርቤትና ውጪ ያሉ ምእመናንስ ምን ቢያደርጉ የተሻለ ነው? ቤተክርስቲያን ከፖለቲካው ተጽዕኖ እንድትላቀቅ ማድረግ ባይቻል እንኳ ተጽዕኖውን ለመቀነስ ካህናትን በማሠልጠን ረገድ፣ ምእመናንን በማንቃት በኩል የቤተክርስቲያን መዋቅራዊ ህላዌ እውን እንዲኾን (አሁን ባለው ሁኔታ ትንሽ አዛዥና ታዛዡ የተደበላለቀ ስለሚመስለኝ) በየት መንገድ ብትኼድ የሚበጃት ይመስልሃል? ምንም እንኳ እዚህ የምንወያያቸው ነገሮች ቤተክርስቲያን ውስጥ ዛሬውኑ ይተገበራሉ ባንልም ምናልባት አንድ ቀን መንቃት ኾኖልን እንሠራ ይኾናልና እስኪ ከንባብህ፣ ከትዝብትህና ከምልከታህ ጥቂት ተናገረን፡፡

  ReplyDelete
 31. Dani Egzer ybarkih. kezeregnanetina ketilacha yetseda tsihufih ejig betam asdestognal. Kale hiwot yasemalign.Bloghin bizu sew silemiyanebew endi aynet tsihofochihin bakih tolo tolo awtalin.Sintochachin yerasachinin mekiseft yemigebaw gudachinin chila bilen, betilachana bezeregninet menfes tenesasten, beagerachin yetekesetewn yemeriwoch mot keEgzer mekiseft ga ayayazinew? Abet alemawek! Endalemawekina besew liyawm benegative menged endemenedat yale kifu neger min ale?
  Alfen terfen Fetarin yetilachachin tebabari linaderg enmokiralen. Abet mot, egna bekum yemotinew min enbal? Betilacha leewnet mutoch lehaset tebekawoch. Geta edimena tena ystih Anjeten new yaraskew. Hilinayenm atsedahilign.Egzer ymesgen.

  ReplyDelete
 32. ሙት ወቃሽ !!! በሕይወት እያሉ ስለሳቸው አትነግረንም ነበር? ኃጢአት ውስጥ ገብተህ፣ እኛንም ኃጢአት ውስጥ አታስገባን፡፡ በሆነ ወቅት ፓትርያሪኩን ቀርበህ ማናገር ችለህ ከነበረ፣ ከዛስ ያለውን ጉድለት ለማስተካከል በአካል ተገናኝተህ ወይ በጽሑፍ አትገልጥላቸውም ነበር፡፡ አሁን ከአረፉ በኋላ መለፍለፉ፣ አንተነትህን ይቀንስብኛል፡፡ እባክህ የምትጽፈውን እየተጠነቀቅክ ቢሆን፡፡

  ReplyDelete
 33. አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፤ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ፤ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዚደንት ፤ የዓለም ሃይማኖቶች ምክር ቤት ለሰላም የክብር ፕሬዚደንትና የዓለም ለሰላም አምባሳደር ናቸው ቅድሥት ቤተክርስቲያናችንን በዓለም አብርታ እንድትታይ ያደረጉልን፡፡ የምርጦች ምርጥ ኢትዮጵያዊ ፓትርያሪክ በሕይወተ ሥጋ ቢለዩንም በረከታቸው ለዘላለሙ አድሮብን ይኖርል የሚል በህይወት የተሞላ ተስፋ አለኝ፡፡ ይሁን እንጂ ግዙፉን ሥራቸውን በማድነቅ ሳይሆን ጥቃቅኑን የጉድፍን ያህል ጉድለታቸውን እያገዘፉ፣ እያወጡ መልካሙን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁትን ሥራዎቻቸውን ጥላሽት ለመቀባት የሚጣጣሩት አዲስ አማኝ ከጳጳስ ይበልጣል እንዲሉ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው የ2ዐ ዓመት ጐረምሶች፣ ጥቃቅኑን እንጂ ግዙፉን ሥራዎቻቸውን ለማየት አይኖቻቸው የታወሩ የዘመኑ የብሎግ ወይም ፌስ ቡክ ጀግኖች ናቸው፡፡ የጻድቅ ሰው ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው፡፡ የአባታችን ስማቸው ዘመንን ተሻጋሪ መሆኑን አንዘንጋ ፣ ስድቡም፣ ዘለፋውም የአንድ ሰሞን ሆይሆይታ ነው፡፡ ታሪክ ግን ለዘለዓለም ምስክር ነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. አጨብጫቢ!

   Delete
  2. እ/ር የባርክሽ /የባርክህ ስው 99 አስደስተህው 1ኢ ብታስክይመው ያ 99 ትቶ የ አንዳን ጥፋት ነው የሚቆጥርብህ: እ/ር ዶሞ በተቃራኒው ማለት ነው :: በስፍሩት ኩና መስፍር አይክርም ! የራሳችንን ሃጥያት በቀን እናስታውስው አለን ዏይ ? ቤ/ክ ማንም አይ ጠብቃትም ክ እ/ር በስተክር ::

   Delete
 34. beDerg gize yetemeretut abatoch derg mertowachew new yemitilew abatochu eko ke derg gar bezerim behaymanotim ayimesaselum eko lemin yen aba paulosin ena Melesin sira tidebabisewaleh. asimesileh kemebilat winet tenagireh memot yishalihal

  ReplyDelete
 35. It is a good article.

  ReplyDelete
 36. ዳኒ አዋቂነትህን አውቃለሁ ግን ነፃ አደለህመ ተሸማቀቃለህ ግራ ይገባሃል ለምን መሰለህ ሰው ያንተን አስተሳሰብ እንዲኖረው ትፈልጋለህ አንደማይቻል እያወቅክ ደሞ አንዴ ከዘር አንዴ ከፖለቲካ እያያያዝክ ልትወነጅላቸው ትሞክራለህ ለመሆኑ ለምሳሌ ቅዱስ አባታችን ከኢህአዴግ ጋር እንዳይስማሙ የምትፈልግበት ነጥብ የቱ ላይ ነው ቤተ ክርስተያን ላይ በደል ደረሰ ህዝበ ክርስትያን ሆይ ተነስ በመንግስት ላይ እጅህን አንሳ ማለት ነበረባቸው? ይህ ብልህነት የጎደለውና ስሜታዊ ብለህ ለመዘገብ ነው አይደል፤ ደሞ የብሔርና የዘር ጉዳይ ለሁሉም አንስተሃል የቀረህ ጉዳይ ጌታችን ምድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም ሃዋርያት ከእስራኤል ብቻ መረጠ ብለህ ተችና እረፈው ቢያንስ ሰው ሞሆናቸውንና ሁሉም ቢሆኑ ሰውን ሲገመግሙ ከቅርበት ሊጀምሩ እንደሚችሉ አስብ እንጂ ዳሩ ምን ዋጋ አለው ሁላችንም በጎውን ጠቅሰን ማበረታታት አልታደልንም ለዚህም ነው ካለፉ በኋላ እንኳን ጠንካራ ስብእናቸውን እርግጠኛ ሁነህ መፃፍ ያቃተህ......
  እግዚአብሔር አምላክ ፅንፈኝነትን አስወጥቶ ይታደገን
  የንብስሔር መለሰ ዜናዊን ቅንነትና ሃቀኝነት ያድለን አሜን እንበል የግድ የቤ/ክርስተያን ሙሁር መሆን የለበት አይመስለኘም የአገዚአብሄርን ህግ የሚተገብር !!

  ReplyDelete
  Replies
  1. I can’t comprehend how people can get so charged blinded as this writer. Not to mention all over before and after this post, which I haven’t got the chance to go through. Clearly, the writer “anonymous” demonstrated your level of biasedness by inserting “Meles’s” name; I could say…”for real?” but I am afraid that would put me in your category, so I won’t. I only pray that you understand what you have written, because it sounds like the message is for yourself. May God return you to your sense- that goes for everyone in the similar category.
   Minilik

   Delete
 37. ይህ መሰዳደብ በፖለቲካዊ ድረ ገጾች ላይ ብቻ የሚታይ ይመስለኝ ነበር። እዚህም ሳገኘው በጣም ነው ያዘንኩት። መቼ ይሆን በሃሳብ ብቻ የምንከራከረው? መቼ ይሆን ሰውየውን ትተን ሃሳቡን ለመምታት የምንሞክረው?

  ReplyDelete
 38. We must stop wining. Ouch church has been divided for the past 20 years because of Aba Paulos' coming by force. period. Please read wikileaks documet on what the then PM Tamirat Layne told the US embasy as to how they caused the division in our Orthodox church.

  Aba Paulos is now gone, God bless his soul.
  Patriarch Merkorios is alive and without any fault.

  For the sake of restoring the unity of our chuch we must not repeat the very mistake commited 20 years ago, i.e., assigning a fake 'patriarch' in contravention of the Church's canon law.

  Remember, Abune Merkorios assumed the 'menber' after Abune Teklehaimanot passed away.

  ReplyDelete
 39. we have to pray to have a good father.

  ReplyDelete
 40. The long held canon law of the Ethiopian Orthodox Church about the assignment of a patriarch has been that no other patriarch be appointed while an existing patriarch is still alive unless the incumbent is found guilty of betraying the church’s teaching, adultery or murder. In 1992 a grave mistake was committed by the forceful imposition of Aba Paulos as a “patriarch” unjustly displacing the existing Patriarch, Aba Merkoriwos for no good reason. The heavy hand of the TPLF government, the greedy nature of some church fathers and the complacency of us, the faithful, were the main reasons that made such a serious mistake possible. The consequence has been the division and weakening of our church.
  The damage the late Aba Paulos has caused is enumerable. However, the most glaring damage of all is the division he has brought to the Ethiopian Orthodox Church and most recently his complacence while the age old monastery, Waldiba, is being desecrated. Aba Paulos is gone now, may God bless his soul. It is a relief for the church that he is out of the scene. This brings an opportunity to fix the two decades old division in our church. This is a momentous time to correct the grave mistake that was committed some 20 years ago and left our beloved church splintered. Unless we do the right thing now, it will be saddening to see a divided and weakened Orthodox Church that we will pass to the generation to come. This will have a direct impact on the future of Ethiopia as well.

  We need to step back and think thoroughly before we start beating the drum of electing another “patriarch”. We must not repeat the very mistake that caused us so much trouble. Remember, how the deceased, came to power 20 years ago. It was orchestrated by TPLF to control and weaken the church. If there is anyone out there who still believes Patriarch Merkoriwos relinquished his position due to ill health, I would say he/she must not have been observing what the TPLF has been doing to justify every atrocity it committed against our church and Ethiopia in the past two decades. Read the diplomatic cable released by wikileaks on what the then TPLF Prime Minister Tamirat Layne, now a protestant preacher, told to the US Embassy in Addis about how they caused the division of our church.

  Now that Aba Paulos is gone, the most important question should be how we can restore unity, dignity, and holy leadership going forward. This is the time to think how to solve our Church's most pressing problem, the division. It is time for soul searching and praying to God for guidance, and not a time to simply vent our emotions. If we allow a second “patriarch” by election or government imposition, we will guarantee the perpetuation of the very problem that divided our church for the past 20 years.

  We pray to God to give the fathers of the church to seize this moment as an opportunity to heal the division in our church. They must start conversation for peace and unity. For the sake of mending the splinter in the church, restoring the Patriarch Abune Merkoriwos appears to be the only best option. Unless God does his divine intervention, such a wise idea to solve the church's most significant problem is likely to be ignored by some short sighted church fathers, complacent followers and the intervention of the oppressive TPLF government. TPLF would like to assign, or may already have picked, another cadre. This is what must not happen if the Orthodox Church is to be united. We believe that God's plan and work is supreme as we are witnessing it these days. However, our church may remain divided if we sit by and don’t do our part. It will at last be united if we pray and rise up for our rights in defense of our faith. We must learn from our Muslim brothers and reject any interference that may come from the TPLF.

  May God bless our Orthodox Church! May God bless Ethiopia!

  ReplyDelete
 41. Putting emotions aside, the Orthodox Church followers should work to free the church from the interference of the government.

  Especially now, with a protestant Prime Minister in the horizon, the church is prone to a systematic dismantlement with direct and indirect influence of government people who don't care about it but actually want to replace it with protestant ideology.

  Beware Orthodox Christians. Unite and stand up in defense of the church. End the division in the church otherwise as divided as you are now you will fail.

  ReplyDelete
 42. dani i appriciate you your all views are good specially (betekinet ena bete mengist bleh yetsafkew betam tiru information new)GOD BLESE YOU

  ReplyDelete
 43. @geeze online

  abune merkoriyos lemin yimetalu America enji debrelibanos yalu meseleh ende ezihu honew yemimetawin aykebelum neber sidet belew eko gedam algebum America newe yehedut. EGZIABEHER CERE ENA BEGOCHUN ketekula yemitadeg eregna yisten amen

  ReplyDelete