Wednesday, July 18, 2012

አትርፍ

click here for pdf 
ሰውዬው ምንም ነገር የማይጠግብ ነው ይባላል፡፡ ሁሉንም ነገር የርሱ ብቻ በማድረግ የሚረካ፡፡ መደመርና ማባዛት እንጂ ማካፈልና መቀነስ ያልተማረ፡፡ አንድን ነገር በመጠቀም ሳይሆን አንድን ነገር የራስ በማድረግ ብቻ የሚረካ፡፡ አንዳንድ ሰው ገጥሟችሁ አያውቅም፡፡ ኮሚቴ ከተቋቋመ እርሱ፤ ቢሮ ከተመሠረተ እርሱ፡፡ ሹመት ከመጣ እርሱ፤ ፊልድ የሚወጣ ከሆነ እርሱ፤ ስብሰባ ከተጠራ ራሱ፤ አበል ያለው ሴሚናር ካለ እርሱ፤ የውጭ ዕድል ከመጣ ራሱ፤ ልምድ ልውውጥ ከመጣ እርሱ፤ ድግስ የሚያ ዘጋጅ ኮሚቴ ከተቋቋመ እርሱ ጥልቅ የሚል ሰው አልገጠማችሁም? እንደዚያ ዓይነት ማለት ነው፡፡

 
እኔ የምለው በውጭም ሆነ በውስጥ ፓርቲ፣ ድርጅት፣ ማኅበር፣ ሸንጎ፣ በተቋቋመ ቁጥር ብዙ ጊዜ የማያቸው ተመሳሳይ ሰዎችን ነው፡፡ እዚያኛው የነበሩት እዚህኛውም ይመጣሉ፤ ለዚህኛው ቡድን ቋሚ ተሰላፊ የነበሩት እንደገና ለዚያኛው ቡድን ይሰለፋሉ፡፡ ለዚያኛው ፓርቲ ላንቃቸው እስኪቀደድና ሆዳቸው እስኪደርቅ ሲሟገቱና እርሱን ያልደገፈ የማርያም ጠላት ሲሉ የነበሩት እንደገና እዚህኛው ገብተው እንደዚያው ይላሉ፡፡ እነዚህ የእግር ኳስ ተጫዋቾች እየተሸጡና እየተዛወሩ ለሌላ ቡድን እንደሚጫዎቱት እነዚህም ተሽጠውና ተዛውረው መጫወት ጀምረው ይሆን እንዴ? እንዴው ሁሉም ቦታ መግባት ያስፈልጋል ማለት ነው?
ምነው እዚህም እዚያም ድስት ጥልቅ ትያለሽ? ብለው ማማሰያን ቢጠይቋት «ባክህ እኔ ያልገባሁበት ወጥ አይጣፍጥም ብዬ ነው» አለች አሉ፡፡
የአንዳንድ ሰዎች የማዕረግ ስም ለምን የሚረዝም ይመስላችኋል? ያገኙትን ሁሉ ስለሚጠቀልሉኮ ነው፡፡ አንዳንዱስ ሕግ ወይም መመሪያ ወይም ደግሞ የመምረጫ መመዘኛ፤ አለያም ደግሞ የዕድገትና የደመወዝ ደረጃ ማሻሻያ እንዲያወጣ ሲመደብ ሕጉንና መመሪያውን ለርሱ በሚሆን ልክ የሚሰፋ ሰው አልገጠማችሁም? «3 ዓመት እንዲህ በተባለ የሥራ መደብ ላይ የሥራ ልምድ ያለው፤ ከአለቃው ጋር አራት አገር የተጓዘ፤ ቢያንስ በስድስት አገራዊ ስብሰባዎች የተካፈለ፤ ታላላቅ ባለ ሥልጣናትን የመቀበል ልምድ ያለው፤» እያለ የወጣውን መመዘኛ ስታዩት «እንዲህ ባለ የመኖርያ አድራሻ የሚኖር» የሚልና «የሸሚዝ ቁጥሩ ይህንን ያህል የሆነ» የሚል ብቻ ሲቀር ሌላው ሁሉ እርሱ ብቻ የሚያሟላው ይሆንላችኋል፡፡
ስኳሩንም፣ በርበሬውንም፣ ጤፉንም፣ ጨውንም፣ ዘይቱንም ካልሰበሰበና በመጋዝኑ ካላከማቸ የማይረካ ሰውስ አላያችሁም? አከማችቶ አከማችቶ ሕዝቡ ሲቸገር ሲያይ የሚደሰት? የሕዝቡን ችግር የገቢው ምንጭ አድርጎ በነፍስ ዋጋ እየቸረቸረ ገንዘብ ብቻ በመሰብሰብ የሚረካ? እንዲህ ያለው ስግብግብኮ እርሱ አይበላም፤ ሰውም አያበላም፤ ገንዘብ ብቻ እንደሰበሰበ ይሞትና የገዛ ልጆቹ ተካፍለው ሲበትኑት ታያላችሁ፡፡ ያደለው እንደ ቢልጌት ድርጅት አቋቁሞ ድኻውን ይረዳል፡፡ ያላደለው ደግሞ እንደዚህ ሰውዬ ሲያከማች ብቻ ይኖራል፡፡ የእርሱ ዓላማ ማከማቸት እንጂ መጠቀምና መጥቀም ስላልሆነ ከርሱ በላይ ችግረኛ የለም፡፡
ታድያ ይኼ ሰው ሰፊ የሆነ መሬት ነበረው፡፡ ነገር ግን በዚያ የመሬት ይዞታው ሊረካ አልቻለም፡፡ ዓለምን ጠቅልሎ የመያዝ ምኞት ነበረው፡፡ ልክ ቆንጆና ታዋቂ የሆነችን ሴት ሁሉ የራሱ ለማድረግ ሲኳትን እንደሚውል ቅንዝረኛ ስግብግብ፡፡
አንድ ቀን እርሱ መሬቱን ሲያሳርስ አንድ ጠቢብ ሰው በዚያ ሲያልፍ አገኘው፡፡ ብዙ ሰዎች ጠቢቡን ሰው ይከተሉት ነበር፡፡ ከተለያየ ችግራቸው ያላቅቃቸው ዘንድ፡፡ ይኼ ባለ መሬት ሰውዬ ሁኔታውን ሲያይ እርሱም ወደ ጠቢቡ ተጠጋ፡፡ ይኼኔ ጠቢቡ ተገረመ፡፡
«ደግሞ አንተ ምን ሆንክ? ይኼንን ሁሉ መሬት ታሳርሳለህ፤ እስኪ መሬትህን ተመልከተው? ለመሆኑ ልኩን ታውቀዋለህ? አንተም ከእነዚህ እኩል እኔ ምን አመጣህ አለው የዋሑ ጠቢብ፡፡ ለምን የዋሕ አልኩት መሰላችሁ፡፡ አባባ ታምራት ጋር ድንጋዩን ወርቅ አድርግልን እያሉ ይማልሉ የነበሩት እነማን እንደነበሩ ያልሰማ ጠቢብ በመሆኑ ነው፡፡ ዛሬም በየጠንቋዩ ቤት ሀብት ፍለጋ የሚጋፉት ችግረኞች እንዳልሆኑ ያላየ ጠቢብ ነው፡፡ ድኻው ድንጋይ እየጠረበ፤ መንገድ እያጸዳ፣ የሰው ልብስ እያጠበ፤ የጉልበት ሥራ እየሠራ፤ በሰው ቤት ተቀጥሮ፤ ዘበኛ ሆኖ ኑሮን ለማሸነፍ እየታገለ ነው ወዳጄ፡፡
እነዚህ በየጠንቋዩ ቤት የምታያቸው አብዛኞቹ ምንም ሳይለፉ ሺውን መቶ ሺ፤ ሚሊዮኑን ቢሊዮን፤ ምድር ቤቱን ፎቅ፤ የጭልፋውን በአካፋ ማድረግ የሚፈልጉትኮ ናቸው፡፡
የባንኩን ቁልፍ ለኛ
ዘበኛው ይተኛ
ሊሉኮ ነው የሚያድሩት፡፡ የሌላውን አስዘግተው የራሳቸውን ብቻ ሊያስከፍቱ፤ ሌላውን አክስረው ራሳቸውን ብቻ ሊያስተርፉ ነውኮ የሚያደገድጉት፡፡ የዋሕ ጠቢብ፡፡
«ግንኮ የኔ ከሆነው የኔ ያልሆነው ይበልጣል» አለ ባለ መሬቱ፡፡
«ሕይወት እንደዚያ ነዋ፡፡ አንድ ሰው እርሱ ከያዘው ይልቅ ያልያዘው ካልበለጠ ሕይወት አትጣፍጥም፡፡ አታጓጓም፤ ሥራ ሥራ፣ ልፋ ልፋ የሚል ጉጉት አይኖርም፡፡ ሰው የደከመው፣ የተፈላሰፈውና የሠለጠነውኮ ከሚያውቀው የማያውቀው፣ ከደረሰበት ያልደረሰበት፣ ከቻለው ያልቻለው፣ ካገኘው ያላገኘው፣ የርሱ ከሆነው ያልሆነው በመብለጡ የተነሣ ነው፡፡ እንዳንተ ያሉ ሰዎች ዕድገትንና ሥልጣኔን ይገድሏቸዋል፡፡» አለው፡፡
ባለ መሬቱ ብዙም በመልሱ አልረካም፡፡ ትክክለኛ መልስ እንጂ የሚያረካውን መልስ አላገኘም፡፡ ለባለ ሀብቱ በትክክለኛ መልስና በሚያረካ መልስ መካከል ልዩነት አለ፡፡ ትክክለኛ መልስ ማለት «አምስት በጎች ለአምስት ሰዎች ሲካፈሉ ስንት ይደርሷቸዋል ሲባል «አንዳንድ» የሚለው ዓይነት ነው፡፡ ይህ ግን አርኪ መልስ አይደለም፡፡ አርኪ መልስ የሚሆነው «ለባለመሬቱ አራት በጎች ይደርሱትና ቀሪዎቹ አራት ሰዎች ግን አንዱን በግ አርደው ይካፈላሉ» የሚለው ዓይነት ነው፡፡
«ይሁን እሺ፤ ግን አሁን ካለኝ መሬት በተጨማሪ ብዙ መሬት እፈልጋለሁ፡፡ ይኼ እነ እገሌ እነ እገሌ እነ እገሌ የሚያርሱት መሬት፤ እዚያ ወንዙ ዳር፣ ተራራው ሥር፣ ከሸለቆው ማዶ ያለው ሁሉ መሬት የእኔ እንዲሆን እፈልጋለሁ» አለው፡፡
ጠቢቡ ተገረመ፡፡ «ይህንን ሁሉ መሬት ለምን የራስህ ታደርገዋለህ? ሌሎቹ ሰዎችስ? ሕይወትኮ መልካም የምትሆነው በመካፈል እንጂ በማከማቸት አይደለም፡፡ አንተ የምትዘራውን ሌሎች ካልገዙህ፣ ሌሎች የሚዘሩትን አንተ ካልገዛህ ምን ዋጋ አለው፡፡ እርሱን ተወው ቢያንስ የምትፎካከረው ሰው ካላገኘህ አንደኛ መውጣትህን በምን ታውቃለህ? አላየህም እንዴ ሯጮች እንኳን በደንብ ለመሮጥና ሪከርድ ለመስበር ሲሉ ሌላ አሯሯጭ ቀጥረው ከእርሱ ጋር ይፎካከራሉ፡፡ ያለ ተመጣጣኝ ፉክክር ሕይወት ደስታ አታገኝም፡፡? አለና መከረው፡፡ ይህ ግን ትክክለኛ መልስ እንጂ የሚያረካ መልስ አልነበረም፡፡
ለባለመሬቱ  «እገሌና አንተ ብትወዳደሩ ማን ያሸንፋል ለሚለው ጥያቄ ትክክለኛ መልስ «በሚገባ ሮጦ መሥመሩን ቀድሞ ያለፈ» የሚለው ነው፡፡ ይህ ግን አርኪ መልስ አይባልም፡፡ አርኪ መልስ የሚሆነው «ሮጦ አንደኛ ማን ወጣ የሚለው ሳይሆን እንዲያልፍ መደረግ ያለበት ማነው? በሚለው ላይ ቀድሞ በመወሰን በሚገኘው ውጤት አሸናፊው ይታወቃል» ከተባለ ነው፡፡ ይኼ ይህንን ሰውዬ ብቻ ሳይሆን ጨረታ የሚጫረቱ፣ ምርጫ የሚወዳደሩ ሰዎችንም ሊያረካ የሚችል ይሆናል፡፡
ጠቢቡ ሰው በጣም አዘነ፡፡ ለሌሎቹ ሰዎች ለሕይወታቸው የሚሆን የችግራቸውን መፍትሔ ሰጥቶ አሰናብቷቸዋል፡፡ የቀረው ይሄ ባለ መሬት ብቻ ነው፡፡ «የምትፈልገው ምን ያህል መሬት ነው አለና ጠቢቡ ጠየቀው፡፡ ባለ መሬቱ ልኩን መናገር ከበደው፡፡ ምናልባት በአካባቢው ያለው መሬት ከዚያ ከበለጠሳ? ረዥም ጊዜ ወሰደ፡፡ ጠቢቡ ረፈደበት፡፡
«ወዳጄ እኔ አንድ መፍትሔ ልስጥህ፡፡ ከዚህ እኔና አንተ ከቆምንበት ዛፍ ጠዋት ጀንበር ስትወጣ ተነሣና ብትፈልግ ሩጥ ብትፈልግ አዝግም፡፡ በእግርህ የረገጥከው መሬት ሁሉ ያንተ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ጀንበር ከመጥለቋ በፊት እዚህ ዛፍ ሥር መድረስ አለብህ፡፡ በል ቻው» አለውና ጠቢቡ ሄደ፡፡
ሰውዬው በደስታ ሰከረ፡፡ ማታ ራቱን በደንብ በላ፡፡ ሚስቱ ስንቁን አዘጋጀችለት፡፡ በእግሩ በአካባቢው ወዲህና ወዲያ በማለት ጥንካሬውን ፈተነ፡፡ ያስከነዳል፡፡ ዕንቅልፍ በዓይኑ አልዞረም፡፡ ልቡ ብቻ በአካባቢው ሲዞር አደረ፡፡ አሥር ጊዜ በግድግዳው ጭንቁር እያጮለቀ ጀንበር መውጣት አለመውጣቷን ሲያይ አደረ፡፡
አይነጋ የለም ነጋ፡፡
እኩል ነው ከጀንበሯ ጋር የወጣው፡፡ ሮጠ፤ ሮጠ፤ ሮጠ፤ ሮጠ፡፡ አስደሳችና አጓጊ ይሆነውን የመሬቱን መልክዐ ምድር እያየ ይህንንም ያንንም ለመጠቅለል ሮጠ፡፡ አንዱ ቦታ ሲደርስ ሌላ ይታየዋል፤ ያንን ሲያዳርስ ያላዳረሰው ይበልጥበታል፡፡ እርሱን አዳርሳለሁ ብሎ ሲሄድ ከዚያ የበለጠ ያገኛል፡፡ ይህንንማ መተው የለብኝም ብሎ ያንን በሩጫ ሲያዳርሰው ከርሱ ይበልጥ የተዋበ ያያል፡፡ ምን ያድርግ፡፡ ብቻ ሮጠ፤ ሮጠ፤ ሮጠ፤ ሮጠ፡፡
ጀንበር በስተ ምዕራብ ማቆልቆል ጀመረች፡፡ የሚገርመው ነገር እስካሁን ካየውና ከረገጠው መሬት ይልቅ ይህ አሁን የሚያየው በለጠበት፡፡ ተራራው፣ ከተራራው ሥር የሚፈልቀው ምንጭ፤ ጫካው፤ በጫካው ውስጥ የሚሰማው የወፎች ዝማሬ፡፡ እንዴት ይተወው፡፡ ሮጠ፤ ሮጠ፤ ሮጠ፤ ጀንበርም ወደ ምዕራብ ታሽቆለቁላለች፡፡ «ጥቂት ጊዜ አለኝ ቢያንስ ያንን ጫካ መጠቅለል አለብኝ አለ» የያዘውን ስንቅ እንኳን የሚበላበት ልብም ጊዜም አላገኘም፡፡ በከዳ ጉልበቱ ሮጠና እንደምንም ብሎ ጫካውን አዳረሰው፡፡ ጀንበሯ ግን ከቅድሙ በበለጠ ፍጥነት ወደ ምዕራብ መስኮቷ ልትገባ እየፈጠነች ነው፡፡
አሁን ሁሉንም ማዳረስ እንደማይችል ገባው፡፡ ከዚያ ይልቅ ትልቁ ፈተናው ጀንበሯ መስኮቷን ከፍታ ከመግባቷ በፊት ወደዚያች ዛፍ ለመመለስ መቻሉ ነው፡፡ ሩጫውን ወደ ዛፏ አደረገ፡፡ ከዛፏ እዚህ ለመድረስ ከዐሥር ሰዓት በላይ ወስዶበታል፡፡ አሁን በሁለት ሰዓታት ውስጥ እዚያች ዛፍ ላይ መድረስ ተመኘ፡፡
ጉልበቱ እየከዳው፤ አንጀቱም በረሃብ እየተሳበ፤ ጀንበሯም ከርሱ በበለጠ ፍጥነት እየተሽቆለቆለች ተጓዘ፡፡ ራሱን ማዞር፤ ሆዱን ማጥወልወል፤ ጉልበቱን ማሣሠር ጀመረው፡፡ እንዲያም ሆኖ ሮጠ፡፡ አሁን ፉክክሩ ከጀምበሯ ጋር ነው፡፡ «ምናለ እንደ ኢያሱ ፀሐይ ለማቆም በቻልኩ» አለ በልቡ፡፡ የቆሎ ተማሪ ትዝ አለው፡፡
የቆሎው ተማሪ የሚካኤል ዕለት አሥራ ሁለት ቦታ ድግስ ተጠራ፡፡ ግን አሥራ ሁለት ቦታ ማዳረስ አይችልም፡፡ የገጠር መንደር እዚህና እዚያ ማዶ ነውና፡፡ ወዴትኛው ድግስ መሄድ እንዳለበት መወሰን አቅቶት መሐል መንገድ ላይ ቆሞ ሂሳብ መሥራት ጀመረ፡፡ እዚህ ብሄድ እዚያ ይሄና ይቀርብኛል፡፡ እዚያ ብሄድ እዚህ ይሄና ይቀርብኛል፡፡ እያለ እያሰበ መወሰን ቢያቅተው «ምናለ ለዛሬ ሚካኤል ከአሥራ ሁለት በበታተነኝ» አለ ይባላል፡፡
ሰውዬው እየተንገዳገደ ይሮጣል፡፡ ጀንበር ግን በኩራት ወደ ቤቷ ትገሠግሣለች፡፡ እርሱ የተነሣባትን ዛፍ በዓይኑ እንኳን ለማየት ገና አልደረሰም፡፡ እጅግ ርቆ መሄዱን ያወቀው አሁን ነው፡፡
ደከመውና ወደቀ፡፡ የማይደከማት ጀንበር ግን ሄደች፡፡
ወድቆ እየተሳበ ለመጓዝ ሞከረ፡፡ ግን አቃተው፡፡ ልቡ እንደ ገጠር ወፍጮ ዷዷዷ እያለች ትመታለች፡፡ እንደምንም ኃይል ሰብስቦ ተነሣና አንድ ሁለት ርምጃ ተራምዶ ለመጨረሻ ጊዜ ወደቀ፡፡ ትንፋሹ ለመጨረሻ ጊዜ ወጣች፡፡ ልቡ ቆመ፡፡ ጀንበርም ጠለቀች፡፡
ሠፈር ጎረቤቱ ተጯጩኾ በስንት ፍለጋ ጅብ ሳይበላው አገኘው፡፡
በማግሥቱ እየተለቀሰ በሦስት ክንድ ከስንዝር መሬት ውስጥ ተቀበረ፡፡ ያንን ሁሉ መሬት ያካተተው ሰውዬ ይህቺ ቁራጭ መሬት ብቻ የርሱ ሆነች፡፡ ማካፈል አቅቶት ሁሉንም አስረከበ፡፡
ሐራሬ፣ ዚምባቡዌ፡፡

31 comments:

 1. I forgot the title but Tolstoy also wrote an interesting short story almost the same like this. Thanks for sharing.

  ReplyDelete
 2. like Woyane; (the banda of Ethiopia)who is very greeey who take away money from poor people and collect as EFFORT in the means of company to take money and the same in the case of politics

  ReplyDelete
  Replies
  1. no like u man

   Delete
  2. The purpose of the story is to know yourself and clear your mind so first just check yourself, don't see others mistake...

   Delete
  3. stop poletics please,If you want talk about poleticsthis is not the place to be

   Delete
 3. QALE HIWOT YASEMALIN. It is very interesting story.10Q Dn. Dani

  ReplyDelete
 4. ውድ ዳኒ

  የሽሮ ሜዳ መዞሪያ ላይ የተለጠፈውን ቢል ቦርድ አስታወስከኝ ሕፃናት የተሽከሙት አንድ ትልቅ ሰው በትልቁ ተሰቅሏል:: በነርሱ ድካም ይንፈላሰሳል: በነርሱ ጉልበት ተኮፍሷል: በነርሱ ስም ፈቃድ አውጥቷል . . . እንዲህ የተሽከምናቸው ስንት ሰዎች አሉ መሰለ:: ዳኒ አንተ እንዳልከው በየሰልፋችን እነዚህ ሰዎችን ማጣት ዘበት ነው:: እረ አሁንማ ሳይደራጁ አይቀሩም:: ያም ሆኖ ግን እነዚ ሰዎች አያርፉም ኮ የንግድ ፈቃዳቸው ሌላ የተሰማሩት በሌላ: የሚያስፈልገን ሌላ የሚሰሩት ሌላ: . . . ስንቱን ተሸክመን እንችለዋለን? በቅርቡ በኢቲቪ አንድ ዜና አይተን ይሆናል:: ፈቃድ ያወጡትና በሕጋዊ መንገድ የሰው ኃይል ወደ ዱባይ እንልካልን ያሉት ድርጅቶች ጥቂት ናቸው:: ካለፈው ሳምንት በፊት ግን በቀን እስከ 1000 የሚጠጉ ሰዎቻችን ወደ ዱባይ ይላኩ ነበር:: ብር ከተገኘ ወገኑን የሚሸጥ ነጋዴ እናፍራ እስኪ? እነዚ ሰዎች ይሄኔ ለግድብ ግንባታ አዋጥተው ይሆናል:: ወገን እንወዳለንም ብለው ይለፍፉ ይሆናል:: እረ ያማል? በቅጡ መዝግበን ሳንይዝ ያላንዳች ስልጠና የላክናቸው ወገኖቻችን የአረብ አገራትን እስር ቤት መሙላታቸውን ታውቃላችሁ? ከፎቅ የተወረወሩ አሰሪዎቻቸውን የገደሉ መንገድ ጠፍቷቸው ወጥተው የቀሩ በሕመም የሚሰቃዩ እንዳሉ አልሰማችሁም? አሁን ዘመቱብን እነርሱ ወይስ በወገናችን ላይ ዘመትን? የባሪያ ንግድ እንዲቆም የታገለችና የፈረመች ግንባር ቀደም አገር አለችን:: እኛ ግን በሌሎች እንባ: በሌሎች ላብ: ሌሎች መቃብር ላይ ቆመን ማከማቸት ይዘናል::

  አንድ የመንግስት ቢሮ ውስጥ ያየሁትን ልንገርህ:: ልጅቱ የክፍለ ሀገር ልጅ ሁና በቋንቋ መግባባት አልቻለችም:: ኃላፊው እያመናጨቀ ሲያስወጣት ሳይ አላስችል ብሎኝ ተናገርኩ:: ይህን ዓይነት ቋንቋ ትችላለ? አለኝ:: እንደማልችል መለስኩለት:: የሚችል ሰው ፈልጋ ታምጣ እኔ አልችልም:: ከየት ታምጣ ወደናንተ ቢሮ በቀላሉ ሰው አይገባም:: ብዙ የገጠር ልጆች ደሞ ወደናንተ የሚያስመጣ ሥራ እየሰራችሁ ነው:: ቢቻል አስተርጓሚ ማዘጋጀት የነበረባችሁ እኮ እናንተ ናችሁ አልኩት:: ይህን ጥቆማ ሰጥቼ ደሞ በራሴ ገመድ ላስገባ? ሲለኝ ደንግጨ የምን ገመድ? አልኩት:: መቼም በጀት መድበው እንዲ ዓይነት አሠራር ሊያጸድቁ አይችሉም:: ያ ካልሆነ ደሞ እዚ ቦታ ላይ የሚመደብ ሰው በብዝሀ ቋንቋ ተናጋሪነት ሊመለመል ነው:: ተመልከት ያኔ እኔ የት እገባለሁ? አንተ ቢሮ ማመልከቻ ላምጣ ቦታ አለ? እያለ አፌዘብኝ:: ይህ ሰው የአንድ ዩኒቨርሲቲ የማስተርስ ዲግሪ ምሩቅ <> ነው:: ለሱ ካልሆነ ግን ለማንም ማሰብ አይችልም:: አቤት ሸክማችን ከክብደቱ ያበዛዙ::

  99 ከፊንፊኔ

  ReplyDelete
 5. በሁለም መንገድ ጽሑፍህ ይገርማል:: ይህ እውነትም የተባረከ ቅዱስ ትልቅ ትንታኔ ያለው ጽሑፍ ነው:: ለኔ ከሜለው ለኛ ᎒ ነገ ነገ እያልን ከመሮጥ ዛሬን ባግባቡ᎒ አይቀሪ ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት ለበጐ ነገር እንድንደርስ ታላቁ ኋያሉ አምላክ ይምረጠን::አሜን!

  ReplyDelete
 6. nice one, which is related with the current Ethiopian situation !!!!

  ReplyDelete
 7. lets learn from God message via daniel's view.thanks dani

  ReplyDelete
 8. ታላቁ መጽሐፍ “ገንዘብን መውደድ የኃጢኣት ኹሉ ሥር ነው፡፡” ሲል ወይም “ዓለምን መውደድ ከእግዚአብሔር ጋር ጠላት መኾን እንደኾነ አታውቁምን” ብሎ ሲናገር ይህንኑ ቶልስቶይን ተመርኩዘህ የጻፍህልንን ጠቃሚ ታሪክ እንደሚነግረን አምናለሁ፡፡ አዳምና ሔዋን የበደሉት በደልም ዓለምን መውደድ እንደኾነ ይሰማኛል፡፡ የተሰጣቸው አልበቃቸው ብሎ ሰጪውን ራሱን እነርሱ ሊገዙት ፈለጉ (ደግነቱ እርሱም ይህንን ዐውቆ የእነርሱን ሥጋ ለብሶ መጣላቸውና ልጃቸው ይሁዳ በሠላሣ ብር ሸጠላቸው)፡፡ ማዕከለ ዓለም (the center of the whole universe) እግዚአብሔር መኾኑ ቀርቶ እነርሱ እንዲኾኑ ተመኙ፡፡ ካስተዋልነው ኦሪት ዘፍጥረት ይህንን የዓለም በሽታ በግልጥ ይጠቁመናል፡፡ እባብ ፍሬውን ለሔዋን ሲያሳያት “ሴቲቱም ፍሬው ለዓይን የሚያምር፣ ለመብላትም የሚያስጎመዥ እንደኾነ ዐየች፡፡” ይላል፡፡ በቃ! መጎምዠት በሚለው ቃል ውስጥ የምጣኔ ሀብት (ሥነ ስስት/ ኢኮኖሚክስ) መምህሮቻችን “human wants are unlimited.” ብለው ያስተማሩን ነገር በጥንታውያን አበው ብርዕ ዘፍጥረት ውስጥ ቁልጭ ብሎ የተጻፈልን ይመስለኛል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ከሚናገራቸው ዐበይት እውነቶች አንዱ (በእኔ እምነት ዋናው ሰብአዊ ጉዳይ) ይህ የሰው ልጅ የተጠመደበት “የላብዛ ልግዛ” የኑሮ ፍልስፍና እንዴት ከቀውስ ወደ ቀውስ እንደሚመራ ማሳየት ይመስለኛል፡፡

  ኢትዮጵያውያን አበውና እማት “ዓለም ዘጠኝ ናት! ጎዶሎ! ሞልታ የማታውቅ!” ሲሉም በዘጠኙ ቀዳዳዎቹ ሲያስገባ ሲያስወጣ የሚኖረውን ቀዳዳውን በርሜል የሰው ልጅን ማለቂያ አልባ ፍላጎት ሲያመለክቱ እንደኾነ አምናለሁ፡፡ ፍላጎትህን ለማሟላት ትሮጣለህ፤ እስክትይዘው የሚያረካ ይመስልሃል ስትይዘው ግን ውኃ የማይቋጥር ኾኖ ታየዋለህ፡፡ ሌላ ውኃ የሚቋጥርልህ የመሰለህን ደግሞ ታባርራለህ እዚያም ስትደርስ እንዲሁ እርካታ የለም፡፡ እድሜህን እንዲሁ ስትሮጥ ትፈጽመውና በሕይወትህ ምዕራፍ መዝጊያ ላይ ስትደርስ እንደ ሾፐንአወር የሚከተለው ምሬት ብቻ ይተርፍሃል፡፡

  In early youth, as we contemplate our coming life, we are like children in a theatre before the curtain is raised, sitting there in high spirits and eagerly waiting for the play to begin. It is a blessing that we do not know what is really going to happen. Could we foresee it, there are times when children might seem like innocent prisoners, condemned, not to death, but to life, and as yet all unconscious of what their sentence means.
  …If two men- who were friends in their youth- meet again when they are old, after being separated for a life-time, the chief feeling they will have at the sight of each other will be one of complete disappointment at life as a whole;

  ወንጌል “እውነት ነጻ ታወጣችኋለች፡፡” ስትል ስሰማት “ኢየሱስ ጌታ እንደኾነ በልብህ ብታምን በአፍህ ብትመሰክር” ብላ ስታስተምር ሳደምጣትም የምትነገረኝ እውነት ይህንኑ ነው፡፡ “ጌታ” (“κύριος”) የሚለው ቃል እኔ በወንጌል ውስጥ ሳየው እንደው የሩቅ ጌትነት ማለት ብቻ አለመኾኑ ይሰማኛል፡፡ ይልቁንም በአንድ ቤት ውስጥ የቤቱ ጌታ የቤቱ ማዕከል እንደኾነና በቤቱ ውስጥ ያለው ኹሉ ከልሒቅ እስከ ደቂቅ እንደሚታዘዙለት ኹሉ ኢየሱስ ጌታህ ከኾነ መጀመሪያ የምትማረው እውነት አንተ የራስህ ወይም የሌሎች ጌታ አለመኾንህን ይኾናል፡፡ ስለዚህም አንተ ወይም ሌሎች ልታሟሉት የሚገባችሁ ፈቃድ የአንተን ወይም የእነርሱን ሳይኾን የኢየሱስን ነው፡፡ የእርሱ ፈቃድ ደግሞ እርሱን እንድንወድደውና ፍጥረትን ኹሉ ደግሞ በእርሱ የፍቅር ዓይን እንድንመለከትለት ነው፡፡ ይህን ጊዜ ብቻም በሰማያት የኾነችው የሰማዩ አባትህ ፈቃድ በሰማይ እንደኾነ እንዲሁም ደግሞ በምድር ይኾናል- አዳም ማለት ምድር ማለት ነውና፡፡

  ጌታ ኢየሱስ “ነፍሱን ስለእኔ ሊያጠፋት የሚወድድ ያድናታል፡፡” ያለንም “እኔ” የምትባለውን ብዙዎቻችን በማወቅም ባለማወቅም የምናመልካትንና ለምቾቷ የምንደክምላት፣ ለፍላጎቷ የምንገብርላት፣ ለግዛቷ የምንዋጋላትን ጣዖት እንድተዋት ነው፡፡ “እኔ”ን ስተዋትና ራሴን ጨምሮ ፍጥረትን ኹሉ በእግዚአብሔር በኩል መመልከት ስጀምር ሌሎችን “መግዛት”፣ “መንዳት”፣ “በቁጥጥር ሥር ማዋል”፣ “የግል ንብረት ማድረግ” ከሚባለው ፍጻሜ አልባ አድካሚ የቁልቁለት ሩጫ እገላገላለሁ፡፡ እፎይ! እላለሁ፡፡ ፍጥረትን ኹሉ ለፍላጎቴ መፈጸሚያ፣ “ለማንነቴ” እንዲንበረከኩ ሳይኾን ልክ እንደኔው እንዲኖሩ የተፈጠሩ መኾናቸውን አስተውላለሁ፡፡ በፍጡርነቴ ያለብኝ ኃላፊነትም ከእነዚህ ፍጡራን ዘመዶቼ ጋር በፍቅርና በደስታ መኖር ብቻ ይኾናል፡፡

  ይሄኔ ሕዝብና አሕዛብ፣ ተገዳይና ገዳይ፣ አባራሪና ተባራሪ፣ ባርያና ጌታ፣ አይሁዳዊና ግሪካዊ፣ ወንድና ሴት የሚባሉ ማለቂያ አልባ የዓለም ክፍፍሎች ይጠፋሉ፡፡ ለጥቂቶች የማይጠቅም የወርቅ ሐብል ለመሥራት ለኹሉ የሚኾነውን የውኃ ምንጭ መመረዝ ያበቃል፡፡ ፍሬውን ለመብላት ሲሉ የማፍሪያ ጊዜውን በትዕግስት መጠበቅ ሳይኾን ዛፉን መቁረጥ ከሰው ልጅ ዘንድ ይወገዳል፡፡ ሰይፉን ቀጥቅጦ ማረሻ ያደርገዋል እንጂ ትራክተሩን መድፍ አይጭነውም፡፡ የሰው ልጅ ልቡ ያርፋል፡፡ የቤተክርስቲያን ሊቅ ቅዱስ አውጉስጢኖስ “ጌታ ሆይ! አንተ ላንተነትህ ፈጥረኸናልና ባንተ እስኪያርፍ ድረስ ልባችን ዕረፍት አልባ ኾኖ ይኖራል፡፡” ያለው ይህን ተመልክቶ ሳይኾን አይቀርም፡፡

  ReplyDelete
 9. gena kezi belay tsaf

  ReplyDelete
 10. Interesting! We have to know what we want & wish. God will give us what is best for us.. Hulume erasune befetishe tiru new

  ReplyDelete
 11. ሁሉም እራሱን ዞሮ እንዲያይ የሚያደርግ ነው thank u 4 sharing.

  ReplyDelete
 12. mehariyetebalekew kezihe belaye asteyayet yesafkew sew yesafekew endet dess yelale meselehe geta ewqetune yechmerelehe
  hewan

  ReplyDelete
 13. የዚህ ጽሁፍ መግቢያ ሳነብ የቀደሞው አለቃየ እኩይ ምግባር አስታወስከኝ

  ReplyDelete
 14. Mamo Qilo BegebeyaJuly 22, 2012 at 5:04 PM

  Thank you danny. lik endante nachew:: tarik saymaru tarik enawuqalen, poletica saymaru politica enawqalen, wozete... eyalu bemayawuqut gebtew mifetefitu sintoch alu:: keamba genenu meles zenawi jemro::

  ReplyDelete
 15. hi dani yehen text zari bemayeti betam dese belogale keahune behula bedeneb eketatelalehu egezeaber yesetelegne!!!

  ReplyDelete
 16. Thank you daniel, selastemarken amesegnalehu.

  ReplyDelete
 17. To Mamo: I don't think u understand the story & think about that man, in the first place who the hell are u judges peoples mind, who is right and wrong, who knows history and don't....specially OUR LEADER PM, if u believe or not the leaders are chosen by GOD not by a person like us. God knows who & what is best for our country and people so, if u want to see better thing first try to change & help yourself then your country. And if u know about the history of Ethiopia u will teach us....

  ReplyDelete
 18. arif mikir new dani ...please keep it

  ReplyDelete
 19. dear Ato Mamo i feel that u don't understand Amharic please try to go to school

  ReplyDelete
 20. "The world has enough for everyone's needs but not for everyone's greeds."

  pls, enjoy the following books:

  H. Staffner, 1979, "what does it mean to be christian?"

  Gerard H. Hughes. "God of surprises"

  st. Augustine. Confessions.

  ReplyDelete
 21. My Brothers and Sisters, my fellow Ethiopians let us overthrow fear, anger, greediness, hater and live with the everlasting love of God the Father.
  God bless you.
  From Ethiopia, Addis Abeba.

  ReplyDelete
 22. D. Daniel it's very interesting GBU and thanks for sharing !!!

  ReplyDelete
 23. god bless u for us

  ReplyDelete