click here for pdf
ማክሰኞ ሐምሌ 3 ቀን 2004 ዓም የተዘጋውን የኢንተርኔት መሥመር ለማስከፈት እዚህ አያት መንገድ ጉርድ ሾላ ያለው የቴሌኮሙኒኬሽን ቅርንጫፍ ሄድኩላችሁ፡፡ በጠዋቱ ሠልፉ ለጉድ ነው፡፡ ምናለ የቀበሌ መስተዳድሮች ለአንዳንድ መሥሪያ ቤቶች ሥልጠና ቢሰጡ? ቀበሌ እንኳን የጠፋው ሰልፍ እዚህ ከነ ሙሉ ክብሩ ይንጎማለላል፡፡ አዛውንትና አሮጊቶች እግራቸው እየተንቀጠቀጠ ውጭ በብርድ ቆመዋል፡፡ ያውም ከሠላሳ ደቂቃ በላይ፡፡
እንደምንም ተራ ደርሶኝ ወደ ውስጥ ገባሁ፡፡ እዚያም ለካስ ሌላ ሰልፍ አለ፡፡ ደግነቱ እዚህ የምትሰ ለፉት ተቀምጣችሁ ነው፡፡ ፊት ለፊታችን የተገተሩት ኮምፒውተሮች ብዙዎች ናቸው፡፡ የሚሠሩት ሰዎች ግን ሦስት ኮምፒውተር ለአንድ ሠተራኛ እንዲደርሳቸው ሆነው ነው፡፡ አሁን እነዚህ ሁሉ ኮምፒውተሮች የሚሠራባቸው ከሌለ ለምን ተገዙ? ከተገዙስ ለምን አይሠሩም? ማን መልስ ይሰጣችኋል? ትሻልን ሰድጄ ትብስን አመጣሁ አለ ያገሬ ሰው፡፡
እኛ ካሁን ካሁን ደረሰን እያልን ማርያም ማርያም ስንል አንድ ሕንድ ቦርሳውን አንጠልጥሎ መጣ፡፡ የሚያስተናግዱን ሴትዮ ቀጥ አድርገው ወደ መስተንግዶው ወንበር ወሰዱት፡፡ ይታያችሁ ውጭ አያሌ አዛውንትና አሮጊቶች ቆመዋል፡፡ ውስጥ እኛ ተቀምጠናል፡፡ አላስቻለኝምና ሰውዬውን ተራ እንዲይዝ በሚያውቀው ቋንቋ ነገርኩት፡፡ ወዲያው አስተ ናጋጇ «ተወው» አሉኝ፡፡ ገርሞኝ ወደ እርሳቸው ሄድኩና «ለምን?» ስል ጠየቅኳቸው፡፡ «ፈረንጅኮ ነው» ብለውኝ እርፍ፡፡
ይሄኔ አዝኜም ተናድጄም «እና ፈረንጅ ቢሆንስ፤ ፈረንጅ አይሰለፍም? ተራ አይጠብቅም? መመሪያችሁ ያዝዛል?» ደረደርኩት ጥያቄዬን፡፡ ምንም አልመሰላቸውም፡፡ «አንድ ሰው ነው ቢገባ ምናለ» አሉኝ «እዚህኮ በቡድን የመጣ የለም፡፡ ሁላችንም አንዳንድ ሰዎች ነን፡፡ እንደዚህ ለሰው ካሰባችሁ ለምን እዚያ ወገባቸው የሚንቀጠቀጠውን አሮጊቶችና አዛውንት አታስቀድሟቸውም» አልኳቸው፡፡ «እነርሱማ የኛው ናቸው እርሱ ግን ፈረንጅ ነው»
ይኛን ጭቅጭቅ ሰምተው የቦታው ኃላፊ ይመስሉኛል ሌላ ሴትዮ መጡ፡፡ «ምን ሆናችሁ ነው?» አሉን፡፡ ነገርኳቸው፡፡ «አይዞህ ይደርስሃል፤ አትጨቃጨቅ፡፡ ምናለ አንድ ሰው ነው፡፡» ማለሳለሳቸው ነው፡፡ ሌላም ሰውዬ «አንድ ሰው ነው ማለት ምን ማለት ነው? እኛስ ስንት ሰው ነን?» ሲል ሁላ ችንም ሳቅን፡፡ ሌላ ተስተናጋጅም «ቅድም እኒያ አሮጊት በምርኩዝ መጥተው አላስገባም አላላችሁም? እኛ አይደለን ይግቡ ግዴለም ብለን ያስገባናቸው? እርሳቸው ለሀገራቸው ሠርተዋል፤ ልጆች አሳድገዋል፤ በእድሜም አርጅተዋል፤ ለእርሳቸው ሳታዝኑ እንዴት ለሕንዱ አዘናችሁለት?» ሴትዮዋ ነገሩ መክረሩን ሲያውቁ፡፡
«በቃ ተውት፤ ምናልባት ተራ ያዝ ለማለት ቋንቋውስ ከየት ይመጣል ብላችሁ ነው» ብለው ሁላችንንም አሳቁን፡፡
እኛም «ምናልባት ቴሌ ኮሙኒኬሽን ኢትዮ ቴሌኮም ተብሎ ፈረንጆቹ (ፈረንሳውያን) አስተዳደሩን ስለ ያዙት ለፈረንጅ ቅድሚያ እንዲሰጥ ታዝዞ ይሆናል እያልን ወረፋችንን ይዘን ትንታኔያችንን ቀጠልን፡፡
አንዳንድ ወረፋ ያዦች ብዙ ቦታ ሲሄዱ ፈረንጅ ሲፈተሽ እንደማያዩ ተናገሩ፡፡ ሌሎችም በቤተ ክርስ ቲያን ከፈረንጅ ጋር ለሚጋቡት የተለየ ክብር እንደሚሰጥ፣ ለሌላው የማይደረግ የቀኖና ማስተካከያ እንደ ሚደረግ ያጋጠማቸውን አወጉን፡፡ ሌሎችም በየፋብሪካውና በየግንባታ ኩባንያው በስመ ፈረንጅ የመጡ ነጮች ሠራተኛውን ሲደበድቡና ሲበዘብዙ ፈረንጅ በመሆናቸው ብቻ ሃይ የሚላቸው እንደሌለ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በአካባቢው ለሚገኙ የመስተዳድር አካላት ሲያመለክቱም ከአበሾቹ ይልቅ ፈረንጆቹን መስማት እንደ ሚመርጡ ይተርኩ ጀመር፡፡
ይሄኔ ነው የኦፕራ ገጠመኝ ትዝ ያለኝ፡፡ ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ታዋቂዋ የቴሌቭዥን መርሐ ግብር አዘጋጅ ኦፕራ ዊንፍሬ ኢትዮጵያ በመጣች ጊዜ ያጠማትን ነገር ኀዘን በተሞላበት ሁኔታ የገለጠችበትን ዝግጅት አቅርባ ነበር፡፡ እርሷ ወደ ኢትዮጵያ ስትመጣ አራት ጠባቂዎችን ቀጥራ ነበር፡፡ ችግሩ ቀጣሪዋ ኦፕራ ጥቁር፣ ተቀጣሪዎቹ ደግሞ ነጮች ሆኑ፡፡ ኢትዮጵያ ደርሳ ከአውሮፕላን ማረፊያው ጀምሮ ኦፕራ ያላገኘችውን ክብርና መስተንግዶ እርሷ የቀጠረቻቸው ነጭ ጠባቂዎቿ እንዴት ያገኙት እንደነበር በኀዘን ገልጣ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነጻነት አምባ ትባላለች እንጂ ራስዋን እንደ ጥቁር አፍሪካ አካል አድርጋ አትመለከትም የሚል ትችትም ሠንዝራ ነበር፡፡
አንዲት አፍሪካውያን በሚበዙበት ድርጅት የምትሠራ ወዳጄ አብራት ለምትሠራው አፍሪካዊት እኅቷ የቤት ሠራተኛ ታፈላልግላታለች፡፡ የቤት ሠራተኛዋ የቀጣሪዋን የሥራ ቦታ ስታውቅ ደሞዙን ሞቅ አደረገችው፡፡ ያችም የሰው ሀገር ሰው አማራጭ ስላልነበራት ተስማማች፡፡ ሥራ የምትጀምርበትን ቀን ቆረጠና የኔ ወዳጅ የቤት ሠራተኛዋን ይዛ ወደ ቀጣሪዋ ቤት ሄደች፡፡
እዚያ ስትደርስ የቤት ሠራተኛዋ ሃሳቧን ቀየረች፡፡ «ቤቱ ሩቅ ነው፤ ትልቅ ነው» የሚሉ የእናቴ መቀነት አደናቀፈኝ ዓይነት ምክንያት መደርደር ጀመረች፡፡ ብትባል ብትሠራ አልነካውም አለች፡፡ በነገሩ አዝ ነው ቀጣሪዋና አስቀጣሪዋ ተሰነባበቱና አስቀጣሪዋ ያችን የቤት ሠራተኛ በመኪናዋ ይዛት ወጣች፡፡
መንገድ ላይ «ከተስማማሽ በኋላ ሃሳብሽን እንዴት ትቀይሪያለሽ? ለምን መጀመርያ አልነገርሽኝም ነበር» አለቻት አስቀጣሪዋ፡፡ የቤት ሠራተኛዋም «እኔ ፈረንጅ መስላኝ ነበር እንጂ» ስትል አስቀጣሪዋ በንዴት መኪናዋን አቆመችና «አንቺ ከደመወዝሽና ከሥራው እንጂ ከሴትዮዋ ቅጣትና ጥቁረት ምን አለሽ?» አለቻት፡፡ «እንዴ እኔ ጥቁር ቤት እሠራለሁ ማለት አፍራለሁ» ብላት ዕርፍ፡፡ እንግዲህ እርሷ ነጭ መሆንዋ ነው፡፡
አንዱ ችግራችን ራሳችንን የጥቁር አፍሪካ አካል አድረገን አለማየታችን ይመስለኛል፡፡ ስለሌሎች አፍሪካ ውያን ስናወራ እንኳን «ጥቁሮች» እያልን ነው፡፡ የመንግሥቱ ለማ ባሻ አሸብር እንደሆኑት ማለት ነው፡፡ ጥቁርነታችንን አለመቀበላችን ለነጭ የተለየ ቦታ እንድንሰጥ አድርጎናል፡፡ በተለይ ደግሞ ኢትዮ ጵያውያን ወደ ውጭ ሀገር እየሄድን ለመኖር የተለየ ጉጉት ካደረብን ካለፉት ዐርባና ሠላሳ ዓመታት ወዲህ ከፈረንጅ ጋር መሥራት፣ ፈረንጅ ሀገር መሄድ፣ በፈረንጅ ቋንቋ መናገር፣ የፈረንጅ ልብስ መልበስ፣ የፈረንጅ ምግብ መብላት፣ ፈረንጅ ማግባት፣ ፈረንጅ መቅጠር፣ የፈረንጅ ፊልም ማየት፣ የፈረንጅ ስም ማውጣት፣ ፈረንጅ ማስተናገድ፣ የክብርና የደረጃ ማሳያዎች እየሆኑ መጥተዋል፡፡
ዛሬ ዛሬ ያ በሽታ አድጎ አድጎ ተቋሞቻችንና ዩኒቨርሲቲዎቻችን ፈረንጅ መቅጠር፣ በፈረንጅ መመራትና አስተዳደሩን ለፈረንጅ መስጠት የሥልጣኔና የደረጃ መሳያ አድርገውታል፡፡ ሌላው ቀርቶ ይቺ በመዳህ ላይ ያለቺው የፊልም ጥበባችን እንኳን በፈረንጅ ቻይናዎች እየተሞላች መጥታለች፡፡ በሙዚቃ ክሊፖቻችንም ፈረንጅ እስክስታ ሲመታና ሞሰብ ከብቦ እንጀራ ሲመገብ ማሳየት የተወዳጅነቱ ማሳያ ሆኗል፡፡
ስለ አድዋና ማይጨው፣ ስለ ሦስት ሺ ዘመን ነጻነትና ስለ ቅኝ አለመገዛት የምናወራው ሁሉ እንደ ላሜ ቦራ ተረት እየሆነ መጥቷል፡፡ በአሜሪካና በአውሮፓ የሚገኙ የኢትዮጵያውያን ምግብ ቤቶች እንኳን ሲፎካከሩ «እዚህ ቤት ነጮች ብቻ ናቸው የሚያዘወትሩት» መባልን የክብራቸው መለኪያ ሲያደርጉት ታያላችሁ፤ ትሰማላችሁም፡፡ ሌላው ቀርቶ ቤተ እምነቶቻችን እንኳን ለሀገሬው ሰዎች አይነኩም አይዳሰሱም የሚባሉትን ነገሮች ለፈረንጆች መፍቀድና ማሳየት ነውር አይመስላቸውም፡፡
ይሄው ለነጮች አልገዛም ብሎ የኖረው መሬት እንኳን ዛሬ ነጭ በነጭ እየሆነ አይደለ፡፡ መሬት ወሰዱ ሲባል የምሰማቸው ሁሉ «ፈረንጆቹ» ናቸው፡፡ መሬት ወሳጆቹም ነጮች፣የሚዘራውም ነጭ፣ የሚሸ ጠውም ለነጭ፡፡
እጅግ በጣም የሚገርመው ደግሞ በተለይ በምዕራብ ሀገሮች ቆይተው የሚመጡ ዳያስጶራ ኢትዮ ጵያውያን ከፈረንጅ ጋር መኖር ያረንጅ ይመስል ራሳቸውን እንደ ፈረንጅ መቁጠራቸው ነው፡፡ አንዳንድ መሥሪያ ቤት ስትሄዱ፣ ወይም አንዳንድ ጉዳይ የሚፈጸምባቸው ቢሮዎች ስትገቡ ዳያስጶራ በመሆናቸው ምክንያት ብቻ ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ይፈልጋሉ፡፡ አንዳንዴማ እነርሱ ከውጭ ስለሚመጡ ብቻ የሊዝ ዋጋ ለእነርሱ እንዲቀንስ፣ መሬት ቅድሚያ እንዲሰጣቸው፤ መኪናና የቤት ዕቃ ያለ ቀረጥ እንዲ ያስገቡ፣ በየቢሮው የተለየ አስተያየት እንዲደረግላቸው ይጠይቃሉ፡፡ ባለፈው እንኳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በፋሲካ ሰሞን ሰብስቧቸው ስለ ኢትዮጵያ ሕዝብ አንዳችም ነገር ሳያነሡ ለዲያስጶራ ይሄ ይደረግለት፣ ይሄ ይፈቀድለት፣ ይሄ ይሟላለት እያሉ ሲጠይቁ ነው የዋሉት፡፡ ፈረንጆች፡፡
እነርሱ ምን ያድርጉ በኢትዮጵያ ፓስፖርት ለሚገቡ ኢትዮጵያውያን የማይፈቀደው ላፕቶፕ እንኳን በውጭ ሀገር ፓስፖርት ለሚገቡ «ኢትዮጵያውያን» ሲፈቀድ ያያሉ፡፡ አበሻ ከመሆን ይልቅ ፈረንጅ መሆን ሲያስከብር አይተዋል፡፡ ታድያ ቢፈረንጁ ምን ይገርማል፡፡
ዝም ብለን በባዶ የምንጠራራ ጉረኞችና ዘረኞች ነን። አንድ ነጭ አምላኪ ጓደኛችን ለትምህርት አውሮፓ ሂዶ ያነገሳቸው ነጮች በዘረኝነት ሲጠዘጥዙት የሆነውን አልረሳውም። የጋምቤላና የቤኒሻንጉል ወገኖቻችን በንቀት የሚያይ ነበርና ሁኔታውን አይቼ አዘንኩለት።
ReplyDeleteዝም ብለን በባዶ የምንጠራራ ጉረኞችና ዘረኞች ነን። አንድ ነጭ አምላኪ ጓደኛችን ለትምህርት አውሮፓ ሂዶ ያነገሳቸው ነጮች በዘረኝነት ሲጠዘጥዙት የሆነውን አልረሳውም። የጋምቤላና የቤኒሻንጉል ወገኖቻችን በንቀት የሚያይ ነበርና ሁኔታውን አይቼ አዘንኩለት።
ReplyDeleteዝም ብለን በባዶ የምንጠራራ ጉረኞችና ዘረኞች ነን። አንድ ነጭ አምላኪ ጓደኛችን ለትምህርት አውሮፓ ሂዶ ያነገሳቸው ነጮች በዘረኝነት ሲጠዘጥዙት የሆነውን አልረሳውም። የጋምቤላና የቤኒሻንጉል ወገኖቻችን በንቀት የሚያይ ነበርና ሁኔታውን አይቼ አዘንኩለት።
ReplyDeleteዝም ብለን በባዶ የምንጠራራ ጉረኞችና ዘረኞች ነን። አንድ ነጭ አምላኪ ጓደኛችን ለትምህርት አውሮፓ ሂዶ ያነገሳቸው ነጮች በዘረኝነት ሲጠዘጥዙት የሆነውን አልረሳውም። የጋምቤላና የቤኒሻንጉል ወገኖቻችን በንቀት የሚያይ ነበርና ሁኔታውን አይቼ አዘንኩለት።
ReplyDeleteno pdf today?
ReplyDeleteእግዚአብሔር ማስተዋልህን ያብዛልህ፤
ReplyDeleteባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ባለዕዳ አይቀበለውም ይባል የለ፡፡
Hi Dn Daniel.
ReplyDeleteCould you release the pdf format please?.Because here in my work place computers i d't have Amharic fonts and i can't read any Amharic font written articles.
Thank you for understanding and let us to read your views.
May St. Raphael be with you
Getaneh
you can convert online using google chrome browser
DeleteWoy Anteneh! rasachene lemehon enmoker eyetebale be englizegna tetsefaleh? Woche Gud
Deleteወንድም ዳንኤል አንድ ሌላ የማህበረሰባችንን በሽታ ስልነካካሀው አመሰግናለሁ:: ድሮ አአዩ ሳስተምር በጣም የሚገርመን ነገር ነበር ማንኛውም ፈረንጅ ሳይፈተሽ አየገባ አኛ በተለይ በአድሜ ልጆቹ በፍተሻ ቁምስቅላችንን አናይ ነበር ይባስ ብሎ አንድ ጉአደኛችን ለሶስተኛ ዲግሪው ሊማር ውጭ ሀገር ሄዶ ለመስክ ሥራ ከአማካሪው ጋር ይመጣል የዩንቨርስቲው ባልደረባ የሆነው ጉአደኛችን ወዴት ነው አየተባለ ሲጠየቅ አማካሪው ግን ፈረንጅ በመሆኑ ሰተት ብሎ ሲገባ ነበር ይህን ያስተዋለው አማካሪው 'አኔ የዩንቨርስቲው ባልደረባ አንተ አንግዳ ትመስላለህ' ብሎ የታዘበውን ተናግሮ ነበር:: አንደው ለንጽጽር የካታር ገጠመኘን ላካፍል በቀደም በ ካታር አየር መንገድ ወደ ካናዳ ስናልፍ የታዘብነው የሀገሩ መንግስት ምን ያህል ዜጎቹን አንደምያከብር ነው የሀገሩ ዜጎች ፓስፖርት መቆጣጠሪያ መስኮት ላይ ወረፋ አይጠብቁም አንደመጡ ሰተት ብለው ያልፋሉ አኔ ብቻ ሳልሆን አብረውኝ የተሰለፉ ነጮች ሁሉ በጣም ሲገርማቸው ነበር አንግዲህ ከኛ ጋር ማወዳደር ነው
ReplyDeletewhat is the matter with u? there is no pdf eko!!
ReplyDeleteዳኒ ችግሩ ሶስት ምክንያቱች ያሉት ይመስሉኛል
ReplyDelete1/ ''ሚድያችን'' ላይ ነው። ሚድያው ሁሌ የሚያሳየን የፈረንጅን ስኬት፣የምርምር ውጤት፣አስገራሚነት ወዘተ ነው። ይህ በልጅነት አእምሮ ተቀርፆ ያድግና ችግር ይፈጥራል።
2/ወደ አፍሪቃ ፈረንጆች የሚመጡት ስለተመቻቸው እና የተሻለ ቦታ ሆኖላቸው መሆኑን እንረሳና የተለየ ምቹ ነገር ለእነርሱ ለመፍጠር ስንታትር ክብራችንን እናወርደዋለን።
3/የመጨረሻው ምክንያት የሚመስለኝ የልዩ ልዩ አለም ህዝቦች ጋር ተቀላቅለን ኣልኖርንም። ለምሳሌ ሰፈራችን በ እድር፣በ ጎረቤት ወዘተ የሚኖር የውጭ ዜጋ የለም። እንደዛ ቢሆን ድክመት እና ጥንካሬአቸውን በምን እኛ እንደምንሻል(በ ስነ ልቦና፣በመተባበር እና መከባበር)፣በምን እኛ መሻሻል እንዳለብን(ለምሳሌ በሰዓት አጠቃቀም) ወዘተ እንለይ እና በሃገራችን መኖርን ዋጋ መስጠት ብሎም ለተሻለ ስራ መትጋት ቀጥሎም የፈረንጅን ሪፖርት ለምሳሌ ባህሉንም ህዝቡንም ከሚያውቁት የሃገራችን አጥኚዎች አስበልጠን የ አለም ባንክ ወይንም ታይም መጽሔት ያወጣው ሪፖርት(ሪፖርቱ በምን መለኪያ ተጠቀመ ? ተብሎ ሳይተች) የ ፖሊሲ ማፍለቂያ ምንጭ እና የ ቴሌቭዥናችን ቀደምት የ ዜና ርዕስ ማድረግን ማቆም እንጀምራለን።
Getachew
lik neh. enem endantewu newu yasebkut
Deletereally it is wonderful view. I too think it before, but iam totally fed up for the identity Ethiopia in the future
ReplyDeleteዳኒ ምልከታህ ጥሩ ነገር ነው፡፡እኔም የገጠመኝን ልበል የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ ነው ፈረንጅ ሁሉ ሀገሬን ሲጎበኝ እኔስ አልኩና ተነስቼ ወደ አክሱም ጽዮን ሄድኩ፡፡መድረስ አይቀር ደረስኩና በሩን ተሳልሜ ወደውስጥ አቀናሁ ሰዓቱ 8፡30pm አካባቢ ነው አፀዱ ውስጥ ዞር ዞር እያልኩ ሳለሁ ወደ አራት ፈረንጆች ግቢው ውስጥ ሲገቡ ተመለከትሁ አንድ የኛ ሰው ከፊት ይመራል ስለቦታው እያስረዳ ይመስላል ቀጥ ብለው ወደ ቤተክርስቲያኑ በር ሲሄዱ ሳይ ተከተልኩ በበሩ ላይ ቆመው የነበሩት ጥበቃ በሩን ወለል አድርገው ሲከፍቱት እውነቴነው የምልህ የመንግስተ ሰማያት በር የተከፈተልኝ ያህል ነው የተሰማኝ በደስታ ተንደርድሬ እበሩ ላይ ደረስኩና ጫማዬን መፍታት ጀመርኩ ፈረንጆቹ ገቡ እኔም አምላኬን እያመሰገንኩ አንድ እግሬን ወደ ቤተመቅደሱ ላስገባ ስል እኮ ወዴት የሚል ድምፅ ከወደ ውስጥ ሰማሁ እኔም ለመሳለም ነው ብዬ መለስኩ በል ውጪ ተሳለም አይገባም ተቀድሶበታል ተባልኩ፡፡በጣም በመናደድ ፈረንጆቹ ለምን ገቡ በማለት ጠየኩ እነሱማ ጎብኚ ናቸው ተባልኩ፡፡እኔስ ብሆን ተሳላሚ ነኝ በማለት መለስኩ አይ ነገር እንዳታመጣ ብዬሀለው ተመለስ ተባልኩ ውስጤ በጣም እያዘነ እበሩ ላይ ቆሜ አይኔን ግን ከውስጥ መንቀል አልቻልኩም በገዛ ሀገሬ በራሴ ቤተክርስቲያን ምናይነት ክፉ ዘመን ነው እያልኩ አይኔን ሳማትር ይባስ ብለው ለሸክም ከባድ የሆነውን የብራና መፅሀፍ እያገላበጡ ፎቶ ሲያነሱት ሳይ ውስጤን የማላውቀው ሀይል ፈነቀለው ጥበቃውን ገፍትሬ ወደ ውስጥ በፍጥነት ተራመድኩ ሳላስበው ከፈረንጆቹ ጋር ተቀላቀልኩ በአትሮኖሱ ላይ ተቀምጦ የነበረውን የብራና መፅሀፍ ከተሳለምኩ በሁዋላ በጃቸው እያገላበጡ ፎቶ የሚያነሱትን እንደባለቤት ተቀብዬ በአትሮኖሱ ላይ ካስቀመጥኩ በሁዋላ ተሳልሜ ፊቴን ወደበሩ አቀናሁ ጥበቃው ባደረኩት ነገር ተገርሞ እዛው ከበሩ ጠበቀኝ በደረስኩም ጊዜ ጃኬቴን በመጎተት አብረን ከበሩ ወጣን፡፡ከግቢው ባፋጣኝ ካልወጣሁ አዳሬ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚሆን እያስረዳኝ ግቢውን ለቅቄ ወጣሁ፡፡ያቺን እለት ፈረንጅነት ያማረኝ ይሄው ሳልቀየር አለሁ፡፡፡፡፡
ReplyDeleteተክለወልድ ከላስቬጋስ
yeleben new yenegerkilege daniel betam tikikil neh meglte kemichlew belay geltehewal yehenen begazetana be tv yemiyakerbe wegen binoren sewu rasun yetazebibet neber.
ReplyDeleteEg/zer Yesetelegne Dani.
ReplyDeleteBedenebe aderegehe tazebehewal. esekemeche Ferenge ameleken enedemenezelekewu ayegebagnem yemigeremewu degemo enesume betam newu yemigeremachewu le Ferenege yalen amelekaket. Wuche yalute zegochachen beminorubet agere enede huletegna ena kezam belaye zega metayetachewu sigeremen egnawu berasachen ager enede huletegna zega metayetachen Gebegeb Yaderegale. Ethiopia yetekurocha ager nate egnam tekuroch mehonachenen mamen aleben. God bless ethiopia!!!!!
Can you please post the PDF version
ReplyDeleteEwnet belehale ahunema beyemesiriyabetu yalewen neger eyelemedenew new. lelawe yekerena Ethiopiawit mist yageba ferenje enkuwane mistune debedebo police setameta ferenje selehone becha yesuwa chegere sayesema lesu ferdewe hedewale. Ferenje amelakinetachene keteluwale befekadegyenete kegye eyetegezane new yalenewe
ReplyDeleteYou can also read the book written by Michael Moore: STUPID WIHTE MEN. I am not against Ferng but you will get the opportunity to experience how being coloured can exactly make differences in Life.
ReplyDeleteU perceived well d.dani God bless u.
ReplyDeleteሃ ሃ ሃ ሃ... "እዚህኮ በቡድን የመጣ የለም፡፡ ሁላችንም አንዳንድ ሰዎች ነን፡..." I love you dear brother. መማርን "ከሙሉ ክብሩ፥ ጥቅሙና ግዴታዎቹ ጋር" አስትባብረህ የያዝህ ውድ ውንድሜ ዳንኤል You always quench my 'Amharic' thirst with your articles' grammatical beauty and the accompanying life changing lessons. May God richly bless you.
ReplyDeleteበቤታችን እንደ ባዳ እንቆጠር ?ወይኔ!
ReplyDeletetekekel
Deletegreat .................
ReplyDeleteአንዱ ችግራችን ራሳችንን የጥቁር አፍሪካ አካል አድረገን አለማየታችን ይመስለኛል፡፡
ReplyDeleteዳኒ ምናለ ቢገባ እንግዳ አክባሪነታችን ምኑ ላይ ነው?
ReplyDeleteእንግዳ ማክበር ጥሩ ነው ግን ራስንና የራስን እያቃለሉ መሆን የለበትም። ለዚያ ቤት እኮ ሁሉም እንግዶች ናቸው።
Deleteሰላም ላንተ ይሁን ዳንኤል በስራዎቸህ ዙሪያ አስተያየት ስሰጥ የመጀመሪያዬ ነው እውነቱን ለማናገር የተነሳው ሀሳብ በጣም አስፈላጊ ነው የሚል እምነት አለኝ ለፈረብጆች እያሳየናቸው ያለው መጠኑን ያለፍ አክብሮት አንዳንድ አፍሪካዊ ወንድሞቻችን እና ራሳቸውን ፈረንጆቹን ሳይቀር የሚያስገርም እኛን ደግሞ በጣም የሚሳፍር ነገር ነው አባቶችን ነጻ ሀገረ ያስረከቡን ሉላዊነታንን ለውጭ ወራሪ አሳልፈው ያልሰጡት እኮ ትውልዱ በነጻነት እንዲኖር ከማናቸውን ተፅእኖ ነፃ እንዲሆን እነጂ የተገላቢጦሽ እነዲሆን አልነበረም በመሆኑም በትውልዱ እየታየ ያለውን ክፍተት መሙላት የሚቻለው ታሪኩን በማሳወቅና የነፃነትን ትርጉም በማስረፅ በመሆኑ በዚህ ዙሪያ ተመሳሳይ ጽሁፎችን በመፅሁፍ መልክ ማዘጋጀት የምትችል ቢሆን ብዙሀኑን ከተጠናወተው ፈረንጅን አካብዶ የማየት አባዜ ልትገታው የሚያስችል ስራ በስራት ትችላለህ የሚል እምነት አለኝ እግዚአብሄር ይባርክህ
ReplyDeleteእዚህኮ በቡድን የመጣ የለም፡፡ ሁላችንም አንዳንድ ሰዎች ነን"
ReplyDeleteበጣም የሚገርም እይታ ነው። ብዙ ነገር ተምሬበታለሁ። እርግጥ ነው በከፊልም ቢሆን እንግዳ ከማክበር ጋ የተገናኘ ነገር እንዳለው እገምታለሁ።አስራ አንደኛ ክፍል ተማሪዎች እያለን አንድ የናይጀርያ አስተማሪ ነበርን፣ እርሱንም ቢሆን እንደፈረንጅ አንደ ብርቅ ነበር የምናየው። ዩንቨርሲትም ውስጥ እያለን ሌላ በጣም የምንወደው አፍረካዊ ወንድም መምህራችን ነበር። ጥቁር ላለማለት እየተጠነቀቅኩ ነው። እርሱንም ቢሆን በተለየ መንገድ ነበር የምናየው። ነገር ግን ብዙዎቻችን ማንም ሊክደው የማይችል ችግር አለብን። ከነጻነት ታሪካችን ያተረፍነው እና የተጎዳነው አንዱ ነገር ኔጮች ስለ እኛ ምን እንደሚያስቡ አለማወቃችን ነው። አሁን ባለፈው ያውሮፓ ዋንጫ አንድ የኢትዮጵያ ዝርያ ባለው የ ቼክ ረፐብሊክ ተጫዋች ላይ የዘረኝነት ጭሆት አንደተጮኸበት ሲነገር ምናለ ያገሬ ሰው በሰማ እያልኩ ነበር። እግዚያብሄር ይስጥልን ውድ ዳንኤል።
ReplyDeletethanks Dani
ReplyDeleteThis is a good topic to discus. Especially the view that we have to wards African American. No matter what, Ethiopians have no respect for them; they look them down(most of ethiopians). Most of African Americans have resentment towards us too. I don’t know about the rest of your readers but to me this is a big issue that we need to discus even deeper.
ReplyDeletefrom Charlotte.
yhe ager min nekaw ferengi mamleku
ReplyDeleteበውጭ አገር ትምህርት አእምሮው በመደንዘዙ ምክንያት ኢትዮጵያዊው ከእግዚአብሔር ጸጋ መለየት ብቻ ሳይሆን እስኪናቅ ድረስ፣ እስኪጠላ ድረስ፣ የሚበላው እስኪያጣ ድረስ፣ እግዚአብሔር የፈጠረለትን መሬት፣ ውኃ፣ የመሬቱን ፍሬዎች ሁሉ አሳልፎ እስኪሰጥ ድረስ፣ ከነዚህም ከውጭ አገር ሰዎች ተመጽዋች እስኪሆን ድረስ ተዋርዷል። የምእራባዊ ፍልስፍና ተማራኪ የሆነ ሰው እኔ እና ወገኖቼ እንዲህ አይነት የወደፊት ተስፋ አለን ብሎ መናገር እንኳን አይችልም። ይህ ሰው ሁልጊዜ የሚቀጥለው ቀን አዳሩ እንዴት እንደሚሆን ምእራባውያን እንዲነግሩት ይጠብቃል፣ እየጠበቀም ያንቀላፋል። ለራሱም ሆነ ለወገኖቹ ክብር የለውም። እራሱን እና ወገኖቹን ተስፋ የሌላቸው፣ በተፈጥሮ ስጦታ ማነስ ምክንያት በአስተሳሰብ የተበደሉ አድርጎ ይመለከታል። ኢትዮጵያዊ ደካማ ነውና ፍልስፍናና አስተሳሰብ፣ የመንገድንም አኪያሄድ ሁሉ መዋስ ያለበት ከምእራባውያን ነው ብሎ ያምናል። እንደዚህ አይነት ሰዎች ደግሞ በኢትዮጵያ ስለበዙ በስልጣን ኮሪቻ ላይ እስከመቀመጥ ደርሰዋል። እንደተማሩትም ዱቄታቸውን በአመድ ሲቀይሩ እናያለን።
ReplyDeleteBetekikel belehal!
Deleteየምእራባውያን ፍልስፍናና ርእዮተ ዓለም መጀመሪያ ሲያዩት ማራኪ፣ ሲቀምሱት ጣፋጭ ሆኖ ነበር ለኢትዮጵያውያን የቀረበው። ፍልስፍናዎቹን ቀምሰው የፍልስፍናዎቹ ምርኮኛ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን በጣም ጥቂት ነበሩ። ፍልስፍናዎቹና ርእዮተ ዓለሞቹ ኢትዮጵያውያንን ሱሰኛ ማድረግ ብቻ ሳይሆን እንዲያውም ቅምሻው እየጨመረ ሲሄድ ሁሉንም ከሱሰኝነት ወደ እብድነት አሸጋገሩ። ድሮ አንድ ኢትዮጵያዊ በአስራ አምስት አመቱ በሬ ጠምዶ ያርስ ነበር። እህልም ዘርቶ ያጭድ ነበር። ወገኑንም ይመግብ ነበር። አቅሙ ገና ከሆነ ደግሞ ወይ ከብት ያግዳል፡ ወይም እግዚአብሔርን በማመስገን ሥራ ላይ ይሰማራል። ቁምነገር ክብር የሚሰጠው ስነምግባር ነበር። ይህን የማያደርግ ወጣት አልነበረም። አልፎ አልፎ ከነበረ ደግሞ እንደዚህ አይነቱ ዋልጌ ተብሎ ይጠራል። ምናልባትም ያን ጊዜ ዋልጌ ሊኖር የሚችለው ዋልጌው የአእምሮ ህመምተኛ ቢሆን ነው። አሁን ግን የምእራባውያን ትምህርት ኢትዮጵያውያንን በዋልጌነት ስላሰለጠነ ዘመን ተገላብጦ ዋልጌነት በቁምነገር ላይ የበላይነትን ተጎናጽፏል። በሬ አጥምዶ ማረስ ወይም ከብት መጠበቅ፣ ወይም እግዚአብሔርን በንጽህና ማገልገል ፈላጊ የሌላቸው የተናቁ ሙያወች ሲሆኑ፤ ወገንን በማጭበርበር እራስን ማድለብ የሚደነቅ ቅልጥፍና ተብሎ ተወድሷል። ጫት እየቃሙ ስለ ሊበራሊዝም መደስኮር ወይም ስለ ግሪክ ፋላስፎች ማላዘን ወይም ስለ እንግሊዝ ኳስ ተጫዋቾች ሲያወሩ ውሎ ሲያወሩ ማደር ክብር የሚሰጣቸው ምግባሮች ሆነዋል፣ ስልጣኔ እየተባለ የሚጠራው አዲሱ ባህልም ይሄው ነው።american tekemetew seleethiopia yeminegrun mehurochachinem yeh walgenet tetnawtoachewal
ReplyDeletehasabih moges alew!
DeleteTiru tazibehal Daniel. Enenim yagatemegne chiigir newu. Yawum, University wust. Bar lay egna habesha memihiran computer ke yazin enefeteshalen. Hindochin chemiro ye wuchi zega gin ayfeteshum. Le universitiwu astedader president be gile amelkiche nebere. Ye setegn melise gin "ebakihin memeriya newu zebegnochun tebaberuachewu" yemil neber. Ya president eskahun siltan lay ale. Bayehut kutir gin 'mulu sewu' aymeslegne.
ReplyDeleteያቃጥላል!!!
ReplyDeleteኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በአረብ ሀገር
ReplyDeleteክፍል አንድ
በግሩም ተ/ሀይማኖት
ሴቶቻችን ለሱዳን ወንዶች ይታገላሉ….
ኢትዮጵያዊያን እንደ ጉድ እየጎረፉበት ስላለው የአረብ ሀገር ስደት እና እየተፈጸመባቸው ስላለው ግፍ ሁሌም አስባለሁ፡፡ እጨነቃለሁም፡፡ ግን ምንም ማድረግ የምችል አይነት አይደለሁም፡፡ አቅም የሌለኝ ልክ ክንፍ እንደሌላት ወፍ የምፍጨረጨር እኔም አረብ ሀገር ገብቼ ገፈቱን፣ የሚደርሰውን አሰቃቂ ግፍ እያየሁ፣ እየቀመስኩም ያለሁ ስደተኛ ነኝ፡፡ ቢሆንም ወገናችን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ለወገኔ አድርሼ የሚረዳ እንዲረዳቸው ከማድረግ በተጨማሪ የሚሰደደውን ቁጥር በአምስትና አስር ሰው ቁጥር እንኳን ብቀንስ ብዬ እጫጭራለሁ፡፡
በዚህ ዙሪያ ሁለት መጽሀፍትን ባዘጋጅም የማሳተም አቅሜን እስካደራጅ እና አቅሜ ፈቅዶ አስካሳትም የስደተኛው ቁጥር በእጥፍ እየጨመረ መጣ፡፡ የሚደርስባቸውም ግፍ አሰቃቂነት አሳሳቢ እየሆነ፣ ሞት በየቦታው እየጠረጋቸው፣ የአካል መጉደል፣ መደፈር..የመሳሰሉት በእጥፍ እያደገ በመሆኑ ጊዜ ላለመስጠት በኢንተርኔት ጽሁፎቼን መልቀቁን አማራጭ አድረጌዋለሁ፡፡ እባካችሁ የሰማችሁ፣ ያነበባችሁ ለሌላው አሰሙ..አስነብቡ አንድም ቢሆን ወገን ይትረፍ፡፡ አረብ ሀገር ሆናችሁ የምታነቡም ለጥንቃቄም ሆነ ከአላማችሁ እንዳትዘናጉ ይሁናችሁ፡፡
በስደት ካሉ በጣም ከተለያዩ ሰዎች ጋር በደብዳቤ፣ በኢሜል፣ በስካይፒም የተለያየ ሀሳብ አካፍሉኝ እላለሁ፡፡ በርካቶች የማቀርብላቸውን ጥያቄ አቅም በፈቀደ ይመልሱልኛል፡፡ ከብዙዎቹ የምሰማው ግን አንገት የሚያስደፋ ነው፡፡ ሀገር እያለን እንደሌለን ሆነን የሚፈጸምብንን ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ችለን ያለንበት ህይወት ሰቅጣጭ ነው፡፡ ታንቀው የሚገደሉ፣ የሚደፈሩ ሴቶቻችን፣ ወንዶች እና ህጻናት ቁጥር የዋዛ አይደለም፡፡ ታንቀው፣ ተደብድበው፣ በእሳት ተቃጥለው፣ የሞቱ ወገኖቻችን በየአትክልቱ ስፍራ ተቀብረው በየቆሻሻ መጣያው ተጥለው ቀርተዋል፡፡ ቀባሪ አጥተው በየሆስፒታሉ ፍሪጅ ውስጥ በስብሰዋል፡፡ በህገ-ወጥ አጓጓዦች አጓጉል መንገድ ስንቶች ለሞት ተዳርገዋል? በየእስር ቤቱ ያሉ ወገኖች መጨረሻቸው ምንድን ነው? በየእስር ቤቱስ የሚደርስባቸው በደል ምንድን ነው? በዚህ ዙሪያ በተከታታይ እናወራለን፡፡ የስደት መንገዳችን እንዴት ነው? ተሰደንስ ምን አፈራን?
ዋናው ደግሞ እኛስ በስደት ሀገር ምን እየሰራን ነው? ወገን ወገኑን አሳልፎ የሚሸጥበት፣ ለአደጋ የሚያጋልጥበት፣ ጥቂቶች በሚሰሩት መጥፎ ተግባር ሁሉም የሚወቀስበት፣ የሚታሰርበት ሁኔታ የለም? አለ፡፡ ይህንንም ለማየት እንሞክራለን፡፡ በተያያዥነት እንዲረዳይ ወይም መገለጽ አለበት የምትሉት ሀሳብ/መረጃ/ ካለ ላኩልኝ፡፡ መረጃ ልትሰጡኝ የምትፈልጉ ለአማራጭ ኢሜል መጠቀም ከፈለጋችሁ girum_tekl@yahoo.com ብላችሁ ተጠቀሙ፡፡
የምንሰራው መጥፎ ስራ ከእኛ አልፎ ሀገር ዜጋ የሚያስወቅስ፣ የሚያሰድብ የሚሆንበት ጊዜ የለም ወይ? የሚለውን ለማየት ስንነሳ ሴቶቻችን በሴተኛ አዳሪነት ተሰማርተው፤ ወንዶች በመጠጥና በሀሺሽ ንግድ በሌላም ህገ ወጥ ድርጊት ተሳትፈው የሚታዩበት ሁኔታ አለ፡፡ ሴቶቹ በሴትኛ አዳሪነት ተሰልፈው አሰደቡን፣ አዋረዱን የምንለውን ያህል ወንዶችም በዚሁ መስክ ተሰማርተው መገኘታቸው ያሳፈራል፡፡ ኩሉን ተኩሎ ሊፒስቲክ ተቀብቶ ታይት አድረጎ ለገበያ የሚቆም፣ ተደውሎለት ፒክ የሚደረግ ኢትዮጵያዊ አለ መባሉ ምን አይነት ስሜት ይጭርባችኋል? ዱባይ ካሉ ኢትዮጵያዊያኖች ጋር በዚህ ዙሪያም አውርቻለሁ፡፡ እመለስበታለሁ፡፡
ከዚህ ወጣ ብለን ተሰደን የሰራንበትን ቤተሰብ ለውጠናል ወይ? ለራሳችንስ ሆነናል፣ ጥሪት ቋጥረናል? የሚለውን ለማየት ስንሞክር ደስ የሚል እና የሚያሳዝን ነገር ልንሰማ እንችላለን፡፡ ጥቂቶች ደግሞ በሉብናን /ቤይሩት/፣ ዱባይ ሳዑዲ አረቢያ፣ ባህሬን.. ኩዌት ያሉ ሴቶቻችን የሱዳን ወንዶች ሲሻሙ እና የለፉበትን አባክነው ቤት ተከራይተውላቸው ማስቀመጣቸው እየተለመደ የመጣ ጉዳይ ነው፡፡
በዚህ ዙሪያ እንዲያውም አንድ ቤይሩት ያለች ጓደኛዬን ሳዋያት ሁሉን ነገር ነገረችኝ፡፡ አከለችናም ‹‹ በአጠቃለላይ የኢትዮጵያ ሴቶች ለሱዳን ወንዶች ይታገላሉ ማለት ያስችላል፡፡ ቤተሰቧ በርሃብ የሚቆላ ችግረኛ ሁሉ ስራ የጠላ በሴት ገንዘብ መቀመጥ የወደደ ሱዳናዊ ይዛ ቤት ኪራይ ከፍላ፣ አብልታ፣ አጠጥታ….አለችኝ ያሳፍራል፡፡ እዚህ የመንም ያለውን ሳይ በመውለድና በጋብቻ በኩል ሲታሰብ ከሀገር ያስወጣቸው የባል ችግር እስኪመስል ያገኙትን ሀገር ዜጋ አግብተው የሰሩበትን እያበሉ የሚኖሩ ያጋጥማሉ፡፡ አላማ መሳት ነው፡፡
ሰው ቤት፣ ድርጅት ውስጥ በጽዳት ተቀጥረው፣ አይገቡ ገብተው ገላቸውን ሸጠው ያገኙትን ለቁም ነገር ካላዋሉት ለምን መሰደድ አስፈለገ? ስትለፋበት የኖረችውን ገንዘብ ደግሳበት የሚበላው የሌለው ናይጄሪያዊ፣ ሶማሊያዊ..ህንድ፣ፓኪስታን…! ያገቡ እና ተያይዘው የእከክልኝ ልከክልህ ህይወት ሲመሩ ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡ ደግሞ የሚገርመው የፎቶ እና ቪዲዮ ትዝታ ለማስቀረረት ያላቸውን አንጠፍጥፈው ደግሰው ማግባታቸው፡፡ የተሻለ ሲያገኝ አመት ሳይሞላው ጥሏት የሄደ ሞልታለች፡፡ በዚህ ዙሪያ ብዙ እናወራልነአሁን የአፍሪካ ህብረትን አዲስ አበባ ላይ አድርገናል፡፡ ጎበዝ ከትንሽ አመት በኋላ ምን የአፍሪካ ህብረት ብቻ የተባበሩት መንግስታት ጽ/ቤትም ኢትዮጵያ እንዲሆን የምንጠይቅበት ሁኔታ እየተከሰተ ነው፡፡ ከአለም ያልወለድንለት ዜጋ ይኖር ይሆን? ቱቱ!!!...ቱቱ!.. ሴቶቻችን ማህፀናችሁ ይለምልም፡፡ አሜን በሉ!!
እግዚአብሔር ማስተዋልህን ያብዛልህ፤
ReplyDeleteባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ባለዕዳ አይቀበለውም ይባል የለ፡፡
ውድ ዳኒ ትዝብትህን ስላካፈልከን በጣም አመሰግናለሁ፡፡ የኔ አስተያየት ደግሞ ካንተ ለየት ይላል፡፡ ይኸውም ኢትዮጵያውያን የምንታወቀው በእንግዳ ተቀባይነታችን ነው፡፡ እነዛም ሴቶች ከአክብሮት አንጻር ሊሆን ይችላል እንጂ የፈረንጅ አምላኪነት ልክፍት ይዟቸዋል ብዬ አልገምትም፡፡ በተለያዩ ፈረንጅ አገር ያሉ ኢትዮጵያዊያን እዚህ ለነሱ የሚደረግላቸውን አክብሮት በነሱ አገር በተመሳሳዩ ይደረጋል ማለት ወተት ሲጠቁር ማለት ነው፣ ፈጽሞ አይታሰብም ግን በአቅማችን ብንጀምር፡፡ ያ ህንዳዊ በአገራችን አክብሮት ቢቸረው ምናልባት በአገሩ ኢትዮጵያውያንን ያከብር ይሆናል፣ ባያከብርም እግዚአብሔር ያክብረን እንጂ ምንም አይጎድልብንም እኛ ግን በየትኛውም ሥፍራ አክባሪዎች ሆነን እንገኝ፡፡ ስለዚህ ሴቶቹ አጠፉ ብዬ አልገምትም አንተም ወረፋ እንዲጠብቅ ስላዘዝከው ተሳስተካል፡፡ ግን ግን ይቅርታ
ReplyDeleteThis thing is happening because of stereotyping. Most of us associate all whites with success, goodness, wealth, kindness and other nice expressions where as we associate blacks with laziness, drugs, crimes, ponzi scheme and other bad situations. This blog has almost the same content as the other video you posted on your blog about stereoytyping problem presented by the famous Nigerian women writer at TED, entitled "The Danger of Single Story". In the same way, many of us associate ourselves with bad names. When we are degrading our own identity in a generalization form, we never think that we are not respecting ourselves. In my opinion, we have made ourselves victims of not appreciating our own identity and we lost our pride after the outside world started to associate us with famine and poverty.
ReplyDeleteLik new haimanot erasu eko yeferenji bemehonu bicha yemiketel sint ale !
ReplyDeleteያለ ነገር አይደለም እኮ የአፍሪካ ህብረት መዲና ኢትዮጵየ መሆን የለባትም ተብሎ ሲከራከሩ የነበሩት፤ምክንያቱም ገጻችን(ፊታችን) “ጥቁር አይደለም” ስለምንል እና ሊገርምህ አይገባም ፡፡ማንነታችንን(ስብዕናችንን) በፈቃዳችን ከሸጥን(ካጣን) ቆየንም አዶል!
ReplyDeleteyamal!!!
ReplyDeleteእውነት ለመናገር ሁሌም የሚያንገበግበኝ ጉዳይ ነው ከመጠን ያለፈ ፈረንጂ አምላኪነታችን፡፡ በተለይ በእኔ የደረሰ አንድ አጋጣሚ ላንሳ ምስሪያቤቴ የውጪ የትምህርት እድል ሰቶኝ የድጋፍ ደብዳቤ ላጽፍ ወደ ትምህርት ሚኒሰቴር በሄድኩ ወቅት የድጋፍ ደብዳቤውን ከኃላፊ አስፈረሜ መዝገብ ቤት ለማህተም ስሄድ ወረፋ እንድጠብቅ ተነግሮኝ እየጠበቅሁ እያለ አንድ ፈረንጂ ሲመጣ መዝገብ ቤት ሰራተኛዋ ከጁ ነጥቃ ማህተም አድረጋ ስትልከው እርር ድብን ነው ያልኩት፡፡ በተለይ በወቅቱ ለትምህርት ከመውጣቴ በፊት ብዙ ስመራቸው የነበሩ ከባድ የሚባሉ የመንግስት ጉዳዮች ማጠናቀቅ ስለነበረብኝ ለኔ ጊዜ ፈረነጂ ሆኖብኝ ነበር፡፡ ምነው እኔም እኮ ቡዙኃላፊነቶችን ነው ትቼ የመጣሁት ምናለ ቅድሚያ ለመታሁት ብታደረጊልኝ ስላት አታካብድ እሱ እኮ ፈረንጂ ነው ነበር መልሷ፡፡እሚገርመው ደግሞ ከማጠናቅቃቸው አስቸኳይ ስራዎች አንዱ ከራስዋ መስሪያቤት የበላይ ኃላፊዎች ጋር መሆኑ ነበር፡፡ እስኪ አሰቡት አሁን ፈረነጁ ነው ዎይ እኔ ነኝ መቅደም የነበረብኝ፡፡ ፈረንጁ ኮ የራሱን ጉዳይ ሊከውን የመጣው፡፡ ባለቀድም እንኳን ቅድሚያ እንደመምታቴ ቀድሜ መስተናግድ ነበረብኝ፡፡ ምራባውያን ስመጣ ደግሞ በተቃራኒው ሆነ ለጥቁር ያላቸው ግምት፡፡ እንዴ እኛ አገራችንም ተዋርደን በፈረንጂም ተዋርደን!
ReplyDeleteDear Daniel,
ReplyDeleteI am so glad to read your reflection on this particular issue. But, I have few reservations. First, who is an Ethiopian? Who are these people whom you refer to generalize about Ethiopians? Can someone who strives to survive on a daily basis (and perhaps doesn't care about his/her self-esteem)represent Ethiopians? What does this tell us about race relations? To what extent are your premises/observations strong to draw such a conclusion? I believe that we need to be careful when we use these amorphous identities like Ethiopians, Blacks, Indians, whites and the like.
Thanks!
I couldn't find any fault in Daniel's article. The guy is telling us the truth. For your surprise there are so many of us who think we are not BLACK. I and so many others here in the US try not to associate ourselves with any other Africans, especially African Americans. The reason is the media has been brain washing the world and we don't think nothing good comes out of a Black mind. Even the old generation say "Ferenj yeseraw, Ferenj agebach, Ferej.....". We, Ethiopians, think that success comes from abroad and that is an undeniable truth. It's just so pathetic. I don't know where u live but try to look around and observe. You will be amazed.
Deleteየኔ ወንድም በጣም ብቻ ሳይሆን እጅግ በጣም ተሳስተሀል አንድ 102.1 ላይ የሰማሁትን የአንድ ኢትዮጲያዊ ታሪክ ልንገርህ ሰውየው የሚኖረው ካናዳ ውስጥ ነበር የሚኖረው ስራውም ሲብል ፖሊሲ (በኛ አገር ነጭ ለባሽ እንደምንለው መሆኑ ነው) እናም የገበያ ማእከል ውስጥ ሌባ አይቶ አባሮ ሲይዘው ተያዘው ይወድቃሉ ከዚያም ሌሎች ፖሊሶች መጥተው ሁለቱንም ከወደቁበት ያነሱና በማን እጅ ላይ ካቴና ያስገቡ ይመስልሀል በራሱላይ ምክንያቱም ጥቁር ነዋ ጥቁር እንጂ ነጭ አይሰርቅም ከዚያ መታወቂያውን አሳይቶ ነው ካቴናው ወደ ሌባው የዞረው፡፡ ስለዚ ወዳጄ እኛ አገራችን ላይ አንከበር በሰው አገር አንከበር ምንም የተሻልን እንኳን ብንሆን ፡፡ በርግጥ ብዙ ጥሩ የሚኮረጁ ጥሩ ነገር እንዳላቸው አምናለሁ ነገር ግን ሳንናቅ መሆን ያለበት የመስለኛል ለነገሩ እኛም የምንኮረጀው የሚጠቅመንን ወይ የምንቀየርበትን ሳይሆን አለ አይደል ሱሪ ማንዘልዘሉን እና እነደዚ የመሳሰሉትን ይመስለኛል ምን ማለት እንደሆነ እንኳን ሳናውቀው አገራችን ላይ ስላለው ልዩነት ብዙ ማለት የቻላል ግን እንደው ባጥሩ ያልተገዛው አገራችን እና አካላችን ብቻ ይመስለኛል እንጂ አእምሮአችን እስካሁንም ግዛትላይ ይመስለኛል እንግዲህ ከተሳሳትኩ ይቅርታ የደረግልኝ ሰላም፡፡
ReplyDeleteማክሰኞ ሐምሌ 3 ቀን 2004 ዓም የተዘጋውን የኢንተርኔት መሥመር ለማስከፈት እዚህ አያት መንገድ ጉርድ ሾላ ያለው የቴሌኮሙኒኬሽን ቅርንጫፍ ሄድኩላችሁ ነው ያልከው? መከፈቱንስ አየን ግን በምን ምክንያት ተዘጋ አሉህ?
ReplyDelete«በቃ ተውት፤ ምናልባት ተራ ያዝ ለማለት ቋንቋውስ ከየት ይመጣል ብላችሁ ነው»
ReplyDeleteWho can save us....???.... Praise be to God who is our salveation through his only Son Jesus Christ and His Holoy Spirit and His Living Word.
ReplyDeleteThe World is in darkenss but the light of God is all around us.
Hold your faith in and keep your love for God.
God Bless you.
From Ethiopia Addis Abeba.
contempolation on book of songs,have you seen my beloved,yemibalu hulet mshafte bemahley lay pope shenoda 3 metsfachewn internet laay temelkeche be amharic balemetergomachew sikoch,yibas bilo,ye tadros malatyn commentaryon book of songs temeleketku ena kinat bete tefeterebgh,ena yane yihen kinat wede dani bashagerew yemil hassab metalegh...
ReplyDeletesilzih dani sele hassabe min telaleh,ene gin mulu emnet alegh 3rrd trguame mesthafh mehaleye hono bekerbu endemtawetw bizu waga endemiskafleh gen resche aydelem meghoten new enji yegeletkut
ReplyDeleteI like your coment.
DeleteThank you so so much Dn Daniel for speaking my mind. I used to get mad, irritated, what not... when our high school director, who was an Indian, manipulated our Habesha teachers. uuuhhhggg.. kuslen kesekeskew.
ReplyDeleteIn contrast to this, let me say sth that I observed and is not appropriate. I live in the U.S. and of course we sometimes invite our friends, co-workers etc to our homes, parties, church etc. However we make a big circle only with our Ethiopian friends, family and relatives and we talk in Amharic and ignore the people we invited over. Who know what goes in their mind? We laugh, we raise our voices, we argue...and everything but nobody gives them attention. Even the food we prepare doesn't take their presence into consideration. The music/ the song will also be in Amharic and no body tries to interpret it for them. My question is : Why do we invite them to make them feel un-welcomed? I do love and appreciate my culture, my language and my people. Just saying...
Meron
እዚህኮ በቡድን የመጣ የለም፡፡ ሁላችንም አንዳንድ ሰዎች ነን፡፡
ReplyDeleteይቅርታ ይደረግልኝ እና እኔ ለፈረንጅ ትልቅ ቦታ አለኝ ያ ማለት ግን አፍሪካዊ ወገኔን እጠላለሁ ማለቴ አይደለም፡፡ ፈረንጅ ዘረኛ ነው የሚለውን ነገር አነባለሁ በጭራሽ በዚህ ነገር አልስማማም፡፡ እኛስ ዘረኞች አይደለን እንዴ ከኛ የባሰ ዘረኛ አለ እንዴ ? ዘረኞች ቢሆኑ ነው እንዴ DV ሞልተን የኛንም የቤተሰቦቻችን ህይወት በጥቂት ወራት ውስጥ የምናሳካው እስቲ አስቡት ስንት ኢትዮጲያውያን ናቸው በ England, USA, Australia , Canada , Norway , Sweden , Finland France, Germany ……………… ያሉት እስቲ የነሱን ህይወት እና የቤተሰባቸውን ህይወት እዩት ፈረንጅ ሀገር ተቀምጠው ነው የነሱም የቤተሰባቸውም ህይወት የተሳካው ሀገራቸው ወይም አሀጉራቸው ያላደረገችላቸውን እኮ ነው ፈረንጅ ያደረገላቸው፡፡ ባጠቃላይ እያቀረባችሁ ያላችሁት ነገር Hasty Generalization ነው፡፡
ReplyDeleteእኔ ለምሳሌ ኢትዮጵያዊ ነኝ ጅማ ብሄድ ኦሮምኛ ስላልቻልኩ ወይም ኦሮምኛዬ ስለሚሰባበር ብቻ ሰርቼ ሀብት ማግኘት አልችልም ትግሬ ስላልሆንኩኝ ወይም ትግርኛ ስለማልናገር ብቻ መቀሌ ገብቼ ሀብት እና ቤተሰብ መመስረት አልችልም እስቲ ንገሩኝ በምን መመዘኛ ነው እኛ ፈረንጅን በተለይ ነጭን የምንተቸው ስንት ወጣት ነው በባህር በበርሃ በዱር ፈረንጅ ሀገር ለመግባት ሲል ብቻ ህይወቱን የሚያጣው ፈረንጅ ዘረኛ ስለሆነ ነው ወይ ይህን ሁሉ ችግር ህብረተሰባችን የሚጋፈጠው ? አድሎ የሌለበት ሀገር ፍትህ ያለበት ሀገር ሰው በሰውነቱ ብቻ የሚከበርበት ሀገር ቢኖር ፈረንጅ ሀገር ብቻ ነው፡፡ ስንራብ ስንጠማ ስንሰደድ ጨቋኞች ሲጨቁኑን የሚደርስልን ፈረንጅ አይደል ለራሱ ጥቅም ብቻ እንዳትሉኝ ስንት NGO በሀገራችን ውስጥ ያቋቋመው ለራሱ ሲል ነው እንዳትሉ፡፡ ስለዚህ አንድ ተራ ሰልፍ ላይ ፈረንጅ ተራ ሳይጠብቅ ቢገባ ባይገባ ምን ለውጥ ያመጣል እንዳውም ሲያንሰው ነው፡፡ እንደውም ፈረንጅ ወደ እኛ ሀገር ሲገባ ፊዛ ባይጠየቅ እንኳን እኔ ደስተኛ ነኝ ለዚህ ዓለም ያተረፈው ዕውቀት ብቻውን ለዘር ማንዘሩ ክብር ነው ፡፡ በተረፈ እግዚያብሔር እንደ ፈረንጅ ያድርገን፡፡ ስለዚህ እኛ ስለ እኛ ያለንን ነገር ድንበር እናበጅለት ባይ ነኝ ስለኛ የምንሰጠው ግምት ውይ ውይ ውይ ድንበር የለውም፡፡
hi
ReplyDeleteእንዳንተ ዓይነት ጸሐፊ የሆኑት ሁሉ እንዲህ ዓይነት ነገር ሲያጋጥማቸው ጥሩ ነው። ምክንያቱም እንደዚህ ጽፈው ችግሩ እንዲታወቅ ያደርጋሉ። ስለዳያስፖራ ያነሳኸውን ግን አልስማማበትም። የመንግሥት ፖሊሲ ካፒታል ላላቸውና በገንዘባቸው ሥራ ለሚያንቀሳቅሱ ቅድሚያ ይሰጣል። ካፒታሊዝም ማለት ይኸው ነው። ይህም በሚገባ ተግባር ላይ ከዋለ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ ገበያውን በማነቃቃትና የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ለአገር ትልቅ ጥቅም አለው። ዳያስፖራውም በዚህ መንፈስ በትምህርት፣ በጤናና በሌሎችም መሠረተ ልማቶች እንዲሳተፍ በመሬት፣ በቀረጥ በመሳሰለው ማበረታቻ ተደርጎለታል - እንዲያም ሆኖ ስንት ሰው በጥሪው እንደተጠቀመበት እግዚአብሔር ይወቅ። እንዲያው ይህ በሰፊው ምነው ሆኖ በሆነ የምንልበት ጊዜ ላይ ነን ያለነው አሁን። እና ለማንኛውም ዳያስፖራው ብቻ ሳይሆን አቶ አላሙዲንም እንዲሁ ዳያስፖራ ሆነው ነው ይህን ሁሉ እድል ያገኙት። እና ፖሊሲው ይህ ነው ለማለት ነው። ፖሊሲውን መቃወም መብት ይመስለኛል። ግን ዘግይተናል።
ReplyDeleteእይታህን በጣም ወድጀዋለሁ, ነጭ ለምኔ ሲል የነበረ, በአድዋ ድል አለምን ሲያስደም የነበረ ሕዝብ ዛሬ ምን ነካዉ? እንዲህ በአስተሳሰብ ባርነት (በፈረንጅ አምላኪነት) እራሱን የሚያረክሠዉ? እኔ ግርም የሚለኘ ነገር የ clinic ማስታወቂያወች ላይ የምሰማዉ ነገር ነዉ: ከዉጭ ሀገር በመጡ ሀኪሞች ምና ምን የሚል ቅብርጥረሴ..... የሀኪሙ ፈረንጅነት እንደ ትልቅ scale ተደርጎ ይወሰዳል እንዴ? ይገርማል!
ReplyDeleteእኔ በምማርበት በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ዉስጥ የታዘቡኩት ነገር ቢኖር በር ላይ ያለዉ ቢሮክራሲዉ የበዛ ጥበቃ እና ፍተሻ የቆዳ ቀለምን በእጅጉ ያማከለ ነዉ ነጫጮች አይፈተሹም አይዲም አያሳዩም, ጥቁር ግን ተማሪም ሆነ ሌክቸር ቁም ሰቅሉን አይቶ ነዉ የሚገባዉ ይህ ለምን ሆነ ብየ ጠይቄ ምላሽ የተሠጠኘ በምን መልኩ እንደሆነ እኔ ነኘ የማዉቀዉ::
ቆይ እኔምለዉ ሽብርተኝነትን, በሽታን,ሰዶማዊ ቅሌትን, ዘማዊነትን, ሱሰኘነትን, እረምኑ ቅጡ ሁሉን ያሥጀመሩን እነርሱ አይደሉም አንዴ? ታዲያ ሀበሻ ምን ነካዉ ክብርን ለሚገባቸዉ ለዋኖቻችን በመስጠት ሳይሆን ለባእዳን አጎብዳጅ ሆኖ ቀረ???
እይታህን በጣም ወድጀዋለሁ, ነጭ ለምኔ ሲል የነበረ, በአድዋ ድል አለምን ሲያስደም የነበረ ሕዝብ ዛሬ ምን ነካዉ? እንዲህ በአስተሳሰብ ባርነት (በፈረንጅ አምላኪነት) እራሱን የሚያረክሠዉ? እኔ ግርም የሚለኘ ነገር የ clinic ማስታወቂያወች ላይ የምሰማዉ ነገር ነዉ: ከዉጭ ሀገር በመጡ ሀኪሞች ምና ምን የሚል ቅብርጥረሴ..... የሀኪሙ ፈረንጅነት እንደ ትልቅ scale ተደርጎ ይወሰዳል እንዴ? ይገርማል!
ReplyDeleteእኔ በምማርበት በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ዉስጥ የታዘቡኩት ነገር ቢኖር በር ላይ ያለዉ ቢሮክራሲዉ የበዛ ጥበቃ እና ፍተሻ የቆዳ ቀለምን በእጅጉ ያማከለ ነዉ ነጫጮች አይፈተሹም አይዲም አያሳዩም, ጥቁር ግን ተማሪም ሆነ ሌክቸር ቁም ሰቅሉን አይቶ ነዉ የሚገባዉ ይህ ለምን ሆነ ብየ ጠይቄ ምላሽ የተሠጠኘ በምን መልኩ እንደሆነ እኔ ነኘ የማዉቀዉ::
ቆይ እኔምለዉ ሽብርተኝነትን, በሽታን,ሰዶማዊ ቅሌትን, ዘማዊነትን, ሱሰኘነትን, እረምኑ ቅጡ ሁሉን ያሥጀመሩን እነርሱ አይደሉም አንዴ? ታዲያ ሀበሻ ምን ነካዉ ክብርን ለሚገባቸዉ ለዋኖቻችን በመስጠት ሳይሆን ለባእዳን አጎብዳጅ ሆኖ ቀረ???
k
ReplyDeleteTherefore??????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????
ReplyDeletethanks!
ReplyDeleteIn my office anyone from abroad or who finished high-schools in one of the highly paid schools like Sanford, Lyce ...can be a team leader. Weku here is they can tell a simingly close to native english speakers language and accent. i am mad but this is how things are done. Yeyazenewen yezen menor newe.
ReplyDeleteThis is Ethiopia .......but change begin with us & me.Thank you for looking.
ReplyDeleteበእውነት ግን ቅኝ አልተገዛንም ?
ReplyDeleteGIN ESIKE MECHE?
ReplyDeleteGIN ESIKE MECHE?
ReplyDeleteGIN ESIKE MECHE?
ReplyDeleteይሄ ሁሉ ችግር የሚፈጠረው ህጎቹ እንደወረዱ ስለሚተረጎሙ ነው፡፡ አንድ ህግ ከተደነገገ በኋላ የተደነገገው ህግ ማያካትታቸው ነገር ግን አገልግሎት ማያገኙ ተገልጋዮች ብዙጊዜ አገልግሎት የሚያገኙት በሰላማዊ ሰልፍ ብቻ ነው፡፡
ReplyDeletetiwulidu megezat silemifelig new jerbaw sitebes yitewewal ante dirshahin tewetehal .
ReplyDeletedanie university gebiche yetemarkuh anten new .sile ewunet new yemileh. GOD FEKIDOLIGN 1 ken kuch biye bimar dess yilegnal.ethiopia yemilewn sim define adirgilign.enem balewubet linager.
ReplyDelete