Wednesday, July 11, 2012

አንዳንድ ጊዜ እንኳን

click here for pdf
በዚህ ሰሞን ኢትዮጵያውያንን የተመለከቱ ሁለት መልካም ዜናዎችን ስሰማ በመክረሜ አምላኬን አመሰገንኩት፡፡ የመጀመርያው ባሳለፍነው የአውሮፓ ዋንጫ ላይ ለቼክ ሪፐብሊክ ቡድን ሲጫወት ስለ ነበረው «ገብረ ሥላሴ» ስለተባለው ወገናችን ሚዲያዎችና የእግር ኳስ ተንታኞች ይሰጡት የነበረው አኩሪ የሞያ ምስክርነት ነበር፡፡ ከዚያ ደግሞ እርሱን የራሳቸው ለማድረግ የአውሮፓ ቡድኖች ላይ ታች ሲሉ ማየት በራሱ ሌላ ኢትዮጵያዊ ኩራትን ይጭራል፡፡
 በነገራችን ላይ ይህንን ተጫዋች ሳስብ ይኼ ከስማቸው ወይም ከአባታቸው ስም ጋር «ሥላሴ» የሚል ነገር ያላቸው ሰዎች የተለየ ምትሐት አላቸው እንዴ? አሰኝቶኛል፡፡ በሩጫው አደባባይ ስማችንን የሚያስጠራው ኃይሌም የአባቱ ስም ገብረ ሥላሴ ነው፡፡ ከዚያ ወደኋላ ሄድኩና ዐፄ ኃይለ ሥላሴን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ፍቅረ ሥላሴ ወግ ደረስን፣ «ዕውቀት ይስፋ፣ ድንቁርና ይጥፋ፣ ይህ ነው ለኢትዮጵያ ተስፋ» እያሉ 75 ዓመታት በላይ ሲያትሙ የኖሩትን ተስፋ ገብረ ሥላሴን፣ የምኒሊክ ታሪክ ጸሐፊ ጸሐፌ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴን፣ የዐፄ ሱስንዮስ ታሪክ ጸሐፊ የሆኑትን አዛዥ ተክለ ሥላሴ ጢኖን፣ ታዋቂውን የቤተ ክህነት ባለ ቅኔ መጋቤ ብሉይ ሠይፈ ሥላሴን፣ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴን፣ ሣህለ ሥላሴ ብርሃነ ማርያምን፣ ማኅተመ ሥላሴ ወልደ መስቀልን እና ሌሎችንም አስታወስኩ፡፡
የመስቀል ወፍና የአደይ አበባ
ቀጠሮ እንዳላቸው መስከረም ሲጠባ
ማን ያውቃል? እንዳሉት መንግሥቱ ለማ፡፡
ቀጥሎ ደግሞ ወዳጃችን በዕውቀቱ ሥዩም በለንደን ኦሎምፒክ ከሚገኙ ገጣምያን መካከል አንዱ ሆኖ ሊሄድ ነው፤ እንዲያውም የመሸኛ ዝግጅት ተደርጎለትም ነበር የሚል ነገር አነበብኩ፤ ሰማሁም፡፡
ይኼኔ ነው ታድያ የሴይንት ሉዊሱ ቀሲስ በለጠ ይረፉ የነገረኝ የአህያዋ ተረት ትዝ ያለኝ፡፡ አህያ ሆዬ ከባድ ሸክም ተጭና፣ ሰውነቷም ቆስሎ በዱላ እየተነረተች እያማረረች ስትሄድ አንዲት በቅሎ በልዩ የበቅሎ ዕቃ ተሸልማ፣ አምራና ተውባ በሁለት አሽከሮች ከጌታዋ ኋላ ኋላ ስትሳብ አየች አሉ፡፡ ታድያ አህይት ለአፍታ በቅሎዋን ተመለከተቻትና «እንዲህ ከመካከላችን አንዳንድ እንኳን ይውጣልን እንጂ፡፡ ትፍ ትፍ» ብላት ሄደች አሉ፡፡
እውነቷን ነው፤ እንዴው ሁልጊዜ በረሃብና በጦርነት፣ በምርጫ ግርግርና በድንበር ውዝግብ፣ በስደትና በልጆች ማደጎ ብቻ ስማችን ከሚጠራ እንዲህ ከመካከላችን እንኳን አንዳንዶች ብቅ ብለው ስማችንን ያስጠሩልን እንጂ፡፡
መቼም ይኼ ስም የማደስ ነገር ሲሰማ በአንዳንድ በዓላት በከተሞች እንደሚደረገው ያለ እንደ ማይመስላችሁ ትረዱልኛላችሁ ብዬ ተስፋ ላድርግ፡፡ የከተማውን ቆሻሻ ከማስወገድ፤ የከተማውን ድህነት ከመቅረፍ፣ የከተማውንም አሮጌ መንደሮች ከማዘመን ይልቅ በዓል ሲመጣና ስብሰባ ሲኖር በቀለምና በአጥር፣ በቢል ቦርድና በባንዴራ እንሸፍናቸዋለን፡፡ ምነው? ሲባል ስማችን እንዳይጠፋ ይባላል፡፡ ሃሳቡ መልካም ሆኖ መፍትሔው ግን ስሕተት ይመስላል፡፡
እኛን የሚጎዳን በሆንነው ነገር ምክንያት ስማችን መጥፋቱ አይደለም፡፡ ሥልጣኔ፣ ፍትሕ፣መኖርያ ቤት፣ ስኳር፣ የትምህርት ጥራት፣ አስተማማኝ የምግብ ዋስትና፣ የማይቋረጥ የኤሌክትሪክ ኃይል መጥፋቱ እንጂ፡፡ ገመናችንን ከማጥፋት ይልቅ ገመናችንን በመሸፈንና በመሠወር ማለፉ የምንኖረው ለራሳችን ሳይሆን ለሰዎች ይመስልብናል፡፡እንደምታውቁት ገመና የሚጠቅመው ፊልም ሲሠሩበት እንጂ ሲሸፍኑት አይደለም፡፡
ቻይና እንዲህ እንደዛሬው ስሟ በዓለም ሳይገንን በነ ማኦ ዘመን ስሟን በበጎ የሚያስባት አልነበረም፡፡ ረሃብና ችጋር መጠርያዋ ነበሩ፡፡ አሰቃቂው ኮሚኒስታዊ አገዛዟም መታወቂያዋ ነበር፡፡ ዛሬ ቻይናን በረሃብና በእርዛት፣ በችጋርና በድህነት የሚያማት የለም፡፡ ባይሆን ያንን ፎርጅዷን ትተወን እንጂ፡፡ ዛሬ ስሟ ተቀይሮ ከዓለም ኃያላን ጋር የምትወዳደር ብቻ ሳይሆን የምትፎካከርም ሆናለች፡፡ ቻይና ግን ችግሯን በራሷ ፈትታ የችግሯን መነሻ አስወገደች እንጂ ችግሯ እንዳይነገርና እንዳይታይ በማድረግ ብቻ የዓለምን ሁለተኛ ኢኮኖሚ አልገነባችም፡፡
እንዲህ እንደ ወንድሞቻችን ብቅ የሚሉ ኮከቦቻችን የሚጠቅሙን ገመናችንን በመሸፈን አይደለም፡፡ ነገር ግን ሀገርን አንዴ በወጣላት ስም ብቻ እስከዘላለሙ መጥራት ለሚወድዱ ለአንዳንዶች ሌላም ነገር እንዳለን ማሳያ ስለሚሆኑን ነው፡፡ «ይህም አለ ለካ» የሚል ፕሮግራም ለማዘጋጀት ይጠቅሙናል፡፡ ደግሞም እኛ ብዙ የጦርነት ጀግኖች ያሉንን ያህል የኢኮኖሚ፣ የሥነ ጽሑፍ፣ የታሪክ፣ የሳይንስ፣ የዲፕሎማሲ፣ የስፖርት፣ የጋዜጠኛነት፣ የመዝናኛ፣ የመምህርነት፣ የሹፍርና፣ የአመራር፣ ጀግኖች ስለሌሉን፡፡ ቢኖሩንም ስለማንፎክርባቸው ተጎድተናል፡፡
እኔ መቼም እስካሁን ሲዘፈንም ሲፎከርም የምሰማው፣ ቢያንስ በአብዛኛው ስለ ገዳይ እንጂ ስለ አስታራቂ፣ ስለ መድፍ ተኳሽ እንጂ ስለ መድፍ ሠሪ፣ ስለ ጥይት ተኳሽ እንጂ ስለ ቃላት ተኳሽ፣ ስለ ምሽግ ሰባሪ እንጂ ስለ ተራራ ሰባሪ፣ ስለ ሰያፊ እንጂ ስለ ፈልሳፊ ስላልሆነ ነው ብዬ ነው፡፡ እነዚያንም ቢሆን ከመፎከርያ ያለፈ በስማቸው እንኳን መታሰቢያ እምብዛም የላቸውም፡፡ [እንዴውም እዚህ ላይ ነገርን ነገር ያንሣውና መቼ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ወታደር የከበሬታ ሥፍራ ሲያገኝ የምናየው፡፡ አቤት እዚህ አሜሪካ ብናይ፤ የትም ስትገቡ ቅድሚያ ከነ ዩኒፎርሙ ላለ ወታደር ነው፡፡ እኔ ብዙ ጊዜ ከአው ሮፕላን ስወርድ «ዩኒፎርም የለበሰው ወታደር እስኪወርድ ጠብቁ» ተብዬ ቆሜ አሳልፌያለሁ፡፡ ወታደርነት እዚህ ሀገር በየሱቁ ቅናሽ ያስገኛል፡፡ የወታደር ቤተሰብ መሆን እዚህ ልዩ ክብርና ሞገስ አለው፡፡ ነገር ያነሳው ነገር እዚህ ላይ ያብቃ፡፡]
ትውልድ አርአያ ይፈልጋል፡፡ እንዲሁ ሰው አንድን ነገር አይመርጥም፡፡ እዚህ አሜሪካ፣ ታምፓ ፍሎሪዳ የሚኖሩት ቀሲስ ብርሃኑ የነገሩኝን ላጫውታችሁማ፡፡ ልጃቸው ሁል ጊዜ ሰዎችን ከአደጋ የሚያወጡ ሰዎችን ፊልም ያያል፡፡ እርሳቸውም የአደጋ መከላከያ መኪና ለመጫወቻ ለካ ገዝተውለት ኖሯል፡፡ አንዳንድ ጊዜም እዚያው የአደጋ መከላከያ ሠራተኞች ያሉበት ቦታ ወስደው አሳይተውታል፡፡ እነዚያ ሕይወታቸውን ሰውተው ሌላውን ሰው ለማዳን እሳት ውስጥ እንደ ቅዱስ ገብርኤል የሚገቡ ሰዎች ሲመሰገኑና ሲሸለሙ ያያል፡፡
ታድያ ልጅ ሆዬ ለካስ የእሳት አደጋ ተከላካዮች ነገር ልቡ ዘልቆላችኋል፡፡ አሥራ ሁለተኛ ክፍል ሲፈተን ውጤቱ ዝቅተኛ ይሆናል፡፡ አባት ይገረማሉም፣ ያዝናሉም፡፡ በክፍሉ ውስጥ የሚጠበቅ ተማሪ ነበርና፡፡ ለምን? አሉት እርሳቸው ነገር ካለፈ በኋላ፡፡ እንዲህ አለ ልጃቸው፡፡ «አየህ አባዬ፣ እኔ የእሳት አደጋ ተከላካይ መሆን እፈልጋለሁ፡፡ አንተ ደግሞ አትስማማም፡፡ ከዚህ የተሻለ ውጤት ባመጣ ኖሮ እዚህ ኮሌጅ ካልገባህ ብለህ ታስቸግረኛለህ፡፡ ስለዚህ ይህንን ውጤት ያመጣሁት ዐውቄ ነው? አለላችሁ፡፡
«እንዴት አንተ ዓይንህ እያየ እዚህ እሳት ውስጥ ሰው አወጣለሁ ብለህ ትገባለህ ብሎ መጠየቅ፣ አባት፡፡
ልጅ ሆዬ ታድያ «አባዬ አንተ ቄስ ነህ፡፡ ጠዋትና ማታ የምትለፋው ሰዎችን ካላየኸው የገሃነም እሳት አወጣለሁ ብለህ ነው፡፡ ታድያ አንተ ካላየኸው የገሃነም እሳት ሰዎችን ለማውጣት ይህንን ያህል ካደረግክ እኔን ከሚታየው እሳት ሰዎችን እንዳላወጣ ለምን ትከለክለኛለህ» አይላቸው መሰላችሁ፡፡ «በዚህ ተሸንፌ ይኼው ዝም ብያለሁ» አሉን ታድያ እሳቸው፡፡
ትውልድ ጀግና ይፈልጋል የምላችሁ ለዚህ ነው፡፡ የሚያየው፣ የሚማረክበት፣ ከልቡ ጋር የሚስማማ፣ ፈለጉን የሚከተለው አርአያ ይፈልጋል፡፡ መቼም ሁሉንም ሰው ጀግና ማድረግ አይቻልም፡፡ «ሁሉ ከሆነ ቃልቻ፣ ማን ሊሸከም ነው ስልቻ» ተብሏል፡፡ ግን አህያዋ እንዳለችው እንዲህ ከመካከላችን አንዳንዶች ብቅ ሲሉ ልጆቻችን የሚከተሉት ሰው ያገኛሉ፡፡
«እናንተ በካሌብና በገብረ መስቀል፤ በዘርዐ ያዕቆብና በምኒሊክ፣ በቴዎድሮስና በዮሐንስ እየፎከራችሁ ጣልያንን ድል አደረጋችሁ፡፡ እኛ ከእንግሊዝ አገዛዝ ነጻ ለመውጣት ስንዋጋኮ መፎከርያ አልነበረንም፡፡ በትምህርት ቤት የተማርናቸው ጀግኖች ሁሉ እንግሊዛውያን ስለነበሩ»ብሎኛል አንድ የጃማይካ ተወላጅ፡፡ እውነቱን ነው፡፡
እንደ አቦ ሸማኔ የሚፈተለክ ስናገኝ ኃይሌ ገብረ ሥላሴን ትመስላለሀ እንለዋለን፡፡ አንቀርቅቦ የሚጫወት የእግር ኳስ ተጫዋች ስናይኮ ማንፀርያ አጥተን ነበር፡፡ እነዚያ የፈረደባቸውን ፔሌና ማራዶና፣ ሜሲና ሮናልዶን ነበር የምንጠራው፡፡ አሁንማ በቋንቋችን የምንጠራው አግኝተናል፡፡
ይኼው እንግሊዞች ድርቅና ረሃብ በመታን ቁጥር ካየር ላይ በሄሊኮፕተር ስንዴ ሲለቅቁብን ኖረው ዛሬ እኛም በተራችን ከለንደን አየር ላይ የበዕውቀቱን ግጥም በመልቀቅ ብድር ልንመልስ ነው፡፡ እንዲህ አንዳንድ ጊዜ እንኳን እንልቀቅባቸው እንጂ፡፡
ሚኒያፖሊስ፣ ሚነሶታ

© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ በመሆኑ በተመሳሳይ ኅትመት ላይ ባታውሉት ይመረጣል፡

33 comments:

 1. Geat view as usual dani! if you work hard with the will of GOD we hope you will be one ethiopian who will have his own media to report the truth !!work hard brother may GOD help you !i will try my best too!!!!!

  ReplyDelete
 2. «እናንተ በካሌብና በገብረ መስቀል፤ በዘርዐ ያዕቆብና በምኒሊክ፣ በቴዎድሮስና በዮሐንስ እየፎከራችሁ ጣልያንን ድል አደረጋችሁ፡፡ እኛ ከእንግሊዝ አገዛዝ ነጻ ለመውጣት ስንዋጋኮ መፎከርያ አልነበረንም፡፡ በትምህርት ቤት የተማርናቸው ጀግኖች ሁሉ እንግሊዛውያን ስለነበሩ»ብሎኛል አንድ የጃማይካ ተወላጅ፡፡ እውነቱን ነው፡፡

  ብዙ የምንፎክርባቸው ጀግኖች አሉን ለወደፊትም ይኖሩናል፡፡ በሁሉም መስክ፡፡ እግዚአብሔር ጥሩ ሥርዓተ መንግስት ያድለን እንጂ፡፡

  ReplyDelete
 3. Thanks Daniel. Bewuketu Seyoum, he deserves. A talened & straight forward writer.congra Bewukie, we expect more than this.

  ReplyDelete
 4. ገመና የሚጠቅመው ፊልም ሲሠሩበት እንጂ ሲሸፍኑት አይደለም፡፡

  ReplyDelete
 5. መሳጭ መጣጥፍህን ሳነብ-አንድ በሃሳብ ይዞኝ የሚነጉድ አረፍተ ነገር አገኘሁ! እኔም ስለ ደረሰብኝ ነገር በትንሹ ብናገር መማሪያ ይሆናል ብዬ-ሞጫጨርኩት። የወታደር ልጅ ነኝ። አባቴን በአካል አላውቀውም። አንድ አመት ሳይሞላኝ በደርግ ተገዶ ለውትድርና እንደ ሄደ አሁን በሕይወት የሌለችው እናቴ አጫውታኛለች። ያለ አባት ሁሉንም ሆና ያሳደገችኝ እናቴን ብዙ ነገር እጠይቃት ነበር። መልስ ለመስጠት የሚያስቸግር። ለምን እኔ አባት የለኝም የሚል የዘወትር ጭቅጨቃ! የስድስት አመት ህጻን እያለሁ አባቴ መሞቱን ለእናቴ አረዷት! የሕዝቡ ብዛት፤ልቅሶው አሁንም ውል ብሎ ይታዬኛል! የሰፈር ሰዎች ሲያዬኝ፤ የሚመጡት ከንፈር ድምጹ በሕሊናዬ ሲያቃጭል ይኖራል። አባት የሌለው ልጅ ሆኜ አደግሁ፤ በአምላክ ፍቃድ ዩኒቨርስቲ ገብቼም ተመረቅሁ። ምንም እንኳ ባለብዙ ውለታዋ እናቴ ለማዬት ባትታደልም፤ የመንግስት ስራ ተቀጥሬ እራሴን ቻልሁ። ያባት ፍቅር ሳላይ ማደግ አንሶኝ ለ 2005 ምርጫ ሌላ ውስጥን ሰባሪ ነገር ገጠመኝ። ወቅቱ መንግስት በእየ መስራቤቱ በሰገሰጋቸው አባላቱ አማካኝነት፤ ሰራተኞችን ለአባልነት ምዝገባ ማዋከብና መመልመል እንደ አንድ አቅጣቻ የተያዘበት ነበር። እኔ ሲጀመር እንዲህ አይነት ነገር ያመኛል። በማይረባ ፓለቲካ ቁማር ምንም የማያውቀው አባቴን አጥቻለሁ። በሌላ ነገር አገሬን አገልግዬ ማለፍን መርጫለሁ! ይህ የእኔ አቋም ነው። ሰው በመረጠው መኖር መብቱ ነው። እናም የማንም አይደለሁም! አንዱ የተላከልኝ ጀሮ ጠቢ ቁም ስቅሌን አሳዬኝ! እኔም እንደ አቅሜ መልሴን እየሰጠሁ ተከላከልሁኝ! በመጨረሻም-የዃላ ታሪኬ ተብሎ በመስሪያ ቤት ባልደርባዬ ተነገረኝ! አንተ አባል የማትሆነው የደርግ ወታደር ልጅ ስለሆንህ-ኢህአዴግን ስለምትጠላ ነው! በውነቱ ያን ቀን የተሰማኝ ስሜት አሁንም ያመኛል! በዚህ መጣጥፍህ-የወታደር ቤተሰቦች እንዴት እንደሚከበሩ የገለጥህባት አረፍተ ነገር፤ የኔን የስቃይ ኑሮ አስታወሰችኝ። ለአገሩ ዳር ድምበር መከበር ብሎ ውድ ሕይወቱን ለከፈለ ሰው ዋጋ የምንሰጥበትን ቀን እናፍቃለሁ። እኔን መሰሎች የተገፉ፤ በተለያዩ መስሪቤት የሚሰሩ ኢትዬጵያዊ ወገኖቼ-ኢህአዴግ የሚከተለው አጉል አካሄድ ወደ የትኛው ጠርዝ እየገፋን እንደ ሆነ በውሉ የተረዱት አይመስለኝም። የኢትዩጵያ አምላክ የሚያስተውል ህሊና ይስጣቸው! አመለካከትን አለመቀበል፤ ጠላት መሆን አይደለም!

  ReplyDelete
 6. አንተም እኮ ዳንኤል ለየት ያልክ እኮነህ እግዚአብሄር ባለህበት ይጠብቅህ

  ReplyDelete
 7. Thanks man, I love it

  ይኼው እንግሊዞች ድርቅና ረሃብ በመታን ቁጥር ካየር ላይ በሄሊኮፕተር ስንዴ ሲለቅቁብን ኖረው ዛሬ እኛም በተራችን ከለንደን አየር ላይ የበዕውቀቱን ግጥም በመልቀቅ ብድር ልንመልስ ነው፡፡ እንዲህ አንዳንድ ጊዜ እንኳን እንልቀቅባቸው እንጂ፡፡

  ReplyDelete
 8. we shoot one ball however they ( western ) shoot one million ball!!!!!አንዳንድ ጊዜ እንኳን እንልቀቅባቸው እንጂ!!!!!"ዮሐንስ ራእይ "
  minnesota

  ReplyDelete
 9. እንዲህ አንዳንድ ጊዜ እንኳን እንልቀቅባቸው እንጂ፡፡...i like the way u summed it up. good article bro.

  ReplyDelete
 10. እንዲህ አንዳንድ ጊዜ እንኳን እንልቀቅባቸው እንጂ፡፡...i like the way u summed it up. good article!

  ReplyDelete
 11. ዳኒ እናመሰግናለን፡፡ ሰሞኑ በሀገራችን የተከናውነው በአንዲት የ17 ዓመት ወጣት ላይ ተጣብቀው የነበረው ነፍስ የሌለው መንትያ የመለየት የ 8 ሰዓት ቀዶ ጥገና ስምንቱ የህክምና ዶክተሮች ያደረጉት ጥበብ እጅግ የሚደነቅነው ይበል፡፡ እግዚአብሔር የተመስገነ ይሁን፡፡

  ReplyDelete
 12. ማየትም ማሳየትም የምንችላቸዉ ብዙ ነገሮች ነበሩን፡፡ ማየት ባለመቻላችን ማሳየትም አልቻልንም፡፡ እንድናይና እንድናሳይ የሚያደርገን ነዉ፡፡ እይታህ በጣም ጥሩ ነዉ አምላክ ያበርታህ . . .፡፡

  ReplyDelete
 13. Bewketu I am proud of you. You are special bro!

  ReplyDelete
 14. መቼ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ወታደር የከበሬታ ሥፍራ ሲያገኝ የምናየው፡፡ Because they are not serving the people they are working For TPLF and they are Killing their own People so how could we respect them??? Dero Deroma Bero woshebay teblo tezefnolachew neber yezaren ayargewena!!!

  Nice view Dane Egziabeher kant gar yihun!!!!

  ReplyDelete
 15. የስነ ግጥም አስተማሪያችን በሳድስ የሚጻፉ ግጥሞች ፍዝ ናቸው ይሉ ነበር፡፡ እናስ!!! ሌሎች ፊደሎች ቤት አንደፋ፣ ቤት አንመታ፣ ቤት አንገጥም ያሉ እንደሆን ይሞታል እንዴ ? ዋናው ስሜት መግለጹ ነው፡፡ የግጥሜ ርዕስ “ት” ሲሆን መታሰቢያነቱ ላንተ ለራስህ ነው፡፡
  “ት”
  ዳንኤል ክብረት፣ ዳንኤል ክብረት፣
  የጦማሩ ጌታ፣ የዕውቀት ባለሀብት፣
  የምሳሌ ባህር፣ የተረት አባት፣
  የታሪክ መምህር፣ ሰባኪ ሃይማኖት፣
  በቀዳው ቢቀዳው፣ የማያልቅበት፣
  የጫረው የጻፈው፣ የሚጥምለት፡፡
  2 ነው ወይ አይኑ የሚቃኝበት፣
  5 ነው ጣቱ? የሚጽፍበት፣
  2 ነው እግሩ? የሚዞርበት፣
  አክናፉ ስንት ይሆን፣ ከአገር ወዳገር የሚበርበት፡፡
  አንድ ቀን ያዙና ቃሊቲ ወስዳችሁ እስኪ መርምሩት፡፡

  የግጥሙ ፈጣሪ፣ “ ገጣሚ” ትዕግስት፣
  በሐምሌ ጨለማ፣ በጠናው ክረምት፣
  እትት! እትት ፣ እትትት ትት፡፡

  ምነው እቴ!! በቃ!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. እንዲህ ነው እንጂ ግጥም
   በእውነት የሚጥም

   Delete
  2. thank you the man it is good poem to describe dani.

   Delete
  3. እንዲህ ነን እኛ ኢትዮጵያውያን፤ ሁላችን ባለጥበብ፡፡ የጥበባችን መሰረትም እግዚአብሔርን መፍራታችን ነው፤ ፈፅሞ ሌላ አይደለም፡፡ ወንድሜ ፍዝ የሚመስል ጠንካራ፣ ለዛ ያለውና ባለቁምነገር መወድስ አቅርበሃል ብዬ አምናለሁ፤ መቼ እንዲህ ሆነና መፍዘዝ፡፡ ሚገርመው ለዳኒ አንድ ግጥም ጽፌ ነበር፣ ቅኔ መሳይ፤ አንድ ቀን ትነበባለች፣ እግዚአብሔር ሲፈቅድልኝ፡፡ እሱ ቅን አመስጋኝ ስለሆነ ምስጋና ይገባዋል፡፡

   Delete
  4. ለትዕግስት፡ ዳኒ ቃሊቲ ኪዳነምህረት ከሆነ እንዲመረመር የፈለግሽው እሱም እምቢ ሊል አይችል፤ ሌላው ግን አይመለከተውም፡፡ ምን አስበሽ እንደጻፍሽ ግልፅ ግልጽ ስላልሆነልኝ ነው፣ ይቅርታ፣ በዚች ምክኒያት፡- ግጥሙ ፈዘዘ፣ ደነዘዘ፣ ብሎም ደነገዘ፡፡

   Delete
 16. ዳኒ የመዳን መንገድ አንድ ነዉ እርሱም እየሱስ ክርስቶስ ነዉ ስለዚህ ልብህን ለእየሱስ ስጥ ያለበለዚያ የዘላለም ሞት ይጠብቃል
  ትክክለኛሁ ቦታ በትክክለኛሁ ሳዓት ተገኝ የመዳን ቀን ዛሬ ነዉ እርሱም አሁን ነዉ ይሄን እድል አታሳልፍ

  ReplyDelete
 17. MeNe Ayente B EgizeAbehir MbarkI Newe?!!

  ReplyDelete
 18. ለአንዳንድ አስተያየቶች ሲባል ምነው LIKE በተን እዚህ ላይ በኖረ::
  ዳኒ ለዚ ብቻ ሳይሆን በብዙ መልኩ እንዲያገለግል አንተም ብሎግህን አ ን ብ ረ ው እንጂ:: በዚሁ ገጽ ድምጽህንም ምስልህንም ለማየት ያግዘናል::
  ZEWENGAL FROM ADDIS

  ReplyDelete
 19. አይ ትዕግስት ለ 20 አመታት ለሀገር ለወገን ፍቅር ብለው በቃሊቲ እስር ቤት የተሰቃዩ የሚሰቃዩ በሰውነት በኢትዮጵያውነት ቀና ብሎ የመኖር፣ የማሰብ፣ የመናገር ሀሞታቸው የፈሰሰ ወገኖች ህመም ተሰምቶሽ የቃሊቲን ምርመራ እቦታው ለመጠቀም ያብቃሽ።

  ReplyDelete
 20. http://www.diretube.com/articles/read-ethiopian-airlines-finishes-a-disappointing-7th-best-airline-in-africa_1632.html

  ReplyDelete
 21. don't want to be a killjoy but...have you heard that Ethiopian ranked the 7th best airline in Africa?

  ReplyDelete
 22. i really admire this blog and it makes me diffrent like good good!!!

  ReplyDelete
 23. ዳንኤል ክብረት፣ ዳንኤል ክብረት፣
  የጦማሩ ጌታ፣ የዕውቀት ባለሀብት፣
  የምሳሌ ባህር፣ የተረት አባት፣
  የታሪክ መምህር፣ ሰባኪ ሃይማኖት፣
  በቀዳው ቢቀዳው፣ የማያልቅበት፣
  የጫረው የጻፈው፣ የሚጥምለት፡፡
  2 ነው ወይ አይኑ የሚቃኝበት፣
  5 ነው ጣቱ? የሚጽፍበት፣
  2 ነው እግሩ? የሚዞርበት፣
  አክናፉ ስንት ይሆን፣ ከአገር ወዳገር የሚበርበት፡፡
  የነገው አራት አይናን እስኪ ጠዩቅት፡፡

  የግጥሙ ፈጣሪ፣ “ ገጣሚ” ትዕግስት፣
  በሐምሌ ጨለማ፣ በጠናው ክረምት፣
  እትት! እትት ፣ እትትት ትት፡፡
  የድንግል ልጅ ከአጠገብህ አይራቅ::

  ReplyDelete
  Replies
  1. Bravo ትእግሰት፣ ግድፈቷ ታረመች፡፡

   Delete
 24. God be with you! It is so interesting history. I like your perspectives very much.

  ReplyDelete
 25. God bless you daniel kibret ,God bless our religion and our country , enegerachin lay yikrta adrgilignina bewketu siyoum minim yemadenkew tsehafi yenebere bihonim behaymanote sabia dagim laladenkew endewum kibrun zik adrge limeleketew yemigeba sew honual tadia dani antes ketsehafinetih belay diaconis aydeleh ende endet hono new yehaymanotihin abatoch yemiyakalil sew bante zend moges yagegnew ???????????

  ReplyDelete
 26. May God widen your wisdom like that of King Solomon.Daniel, I use to listened to you preaching and read most of you writings any time I am at rest, they build spiritually and morally more over let you self and moral test or evaluate yourself.it is constructing the nation and the genration.At this time Ethiopian missed few of such persons,that is why the our county Ethiopia is pushed to the edge of crumpling.Any nomatter that they pushed Ethiopian to end,they will vanish like somke but ethiopia will remain for ever.
  May God Bless Ethiopia and Blesses you D.Daniel

  ReplyDelete