
ፊዚክስ ደኅና ሰንብች፣ የመሬት ስበት ደኅና ሁኚ ማለት እዚህ ነው፡፡
ቤቱ በ17 ዲግሪ ተጣምሞ ታዩታላችሁ፡፡ አስጎብኚዋም፡፡«ይሄ ቤት ተጣምሟል ወይስ አልተጣመመም» ብላ ጠየቀችን፡፡ «የሞኝ ጥያቄ፡፡ ፈረንጅ ደግሞ ተጃጅሎ ያጃጅላል» አልኩ በልቤ፡፡ ሁላችንም እያየሺው በሚል ስሜት መለስን፡፡ ከኪሷ የውኃ ልክ መለኪያውን አነሣችና ወለሉ ላይ አስቀመጠችው፡፡ መለኪያው ቤቱ በደልዳላ መሬት ላይ ማረፉን ያረጋግጣል፡፡ በዓይኔ ነው፣ በሕልሜ ወይስ በቴሌቭዥን አለ ያገሬ ሰው፡፡ «በዓይኔ በብረቱ» እያሉ መመስከር ሊቀር ነው ማለት ነው አልኩ፡፡ ጠጋ ብዬ አየሁት፡፡ ቤቱ አልተጣመመም፡፡ ግድግዳውም 90
ዲግሪ ነው፡፡
ታድያ ማነው የተጣመመው? አልኩና ጠየቅኩ፡፡ ለካስ ሁላችንም እንዲያ እንላለን መሰል አስጎብኚዋ ምሥጢሩን አፍረጠረጠችው፡፡ «እዚህ
150 ጫማ ዲያሜትር ክልል የገባ ሰው ሁሉ በ17 ዲግሪ ይጣመማል፡፡ ቅድምም ቁመታችሁ ያጠረው እናንተ ስለምትጣመሙ ነው» ብላን ዕርፍ፡፡ የሌሎቹን እንጃ እንጂ እኔ የሀገሬ ጠማማ ፎቅ ትዝ አለኝ፡፡ መሬቱ ትክክል ነው፡፡ ነገር ግን ወደታች የሚስባችሁ ነገር አለ፡፡ ከላይ ወደታች ዓይነት ይገፋችኋል፡፡
በመስኮቱ በኩል አንድ ጣውላ አወጣች፡፡ መስኮቱ ታችኛው ደፍ ላይ አኖረችው፡፡ ስናየው ከውጭ ያለው ከፍ፣ ከውስጥ ያለው ዝቅ ብሏል፡፡ ስትለካው ግን የውኃ ልኩ ትክክል ነው፡፡ ከፍም ዝቅም ያለ የለውም፡፡ በጣውላው የውጭው ጫፍ ላይ አንዲት የከረምቡላ ኳስ አስቀመጠችበትና ወደታች ገፋችው፡፡
ይቺ ናት የመሬት ስበት፤
እንዴ፤ ኳሷ ተመልሳ ማንም ሳይነካት ወደ ላይ መጣች፡፡ ደግማ በመከራ ወደታች ገፋቻት፡፡ አሁንም ተመልሳ ወደ ላይ መጣች፡፡ ይባስ ብላ ኳሷን ከታችኛው ቦታ አስቀመጠቻት፡፡ ማንም ሳይነካት እየተንከባለለች ወደ ላይ መጣች፡፡ እንዴት? ማንም አይመልሰውም፡፡ አንዷ ጎብኚ ቻፕስቲኳን አወጣችና ከጣውላው ሥር አደረገችው፡፡ እየተሽከረከረ ወደላይ ወጣላችሁ፡፡ ጉድ በል ጎንደር ማለት ይሄኔ ነው፡፡
ከጎኗ ከነበረው ኮዳ ውኃ አወጣችና አስጎብኚዋ ጠጣች፡፡ ከዚያ ውኃውን ከታችኛው የጣውላው ክፍል ላይ አፈሰሰችው፡፡ «ውኃውን የጠጣሁት ምንም ዓይነት ሌላ ኬሚካል እንደሌለው ላሳውቃችሁ ነው» አለችን፡፡ ይግረማችሁ ብሎ ማንም ሳይነካው ውኃ ሽቅብ ፈሰሰ፡፡ ማመን አልቻልኩምና ተጠግቼ እንደገና አየሁት፡፡ ውኃው ያለምንም መሳቢያ ከታች ወደላይ ኮለል ብሎ ይወርዳል፡፡ ብትሞቱ ውኃውን ወደታች እንዲፈስ ማድረግ አትችሉም፡፡
ውኃ ሺቅብ ላይወጣ
ልጅነቴ ናፈቀኝ ተመልሶ ላይመጣየሚለው የሀገሬ ዘፈን ትዝ አለኝ፡፡ አልሰሜን ግባ በሉት ማለት አሁን ነው፡፡
ገባን ወደ ቤቱ፡፡ ቤቱ እያንደረደረ ወደ አንድ በኩል ስለሚወስድ መደገፊያ ተሠርቶለታል፡፡
ከቤቱ አንድ ማዕዘን ፔንዱለም ተሰቅሏል፡፡ ለካችው የፔንዱለሙን አለመጣመም፡፡ ውኃ ልክ ዜሮ ላይ ነው፡፡ እኛ ስንማር ፔንዱለምን በአንድ በኩል ስትገፉት በተመሳሳይ ርቀት ወደ ተቃራኒው አቅጣጫ ይወረወራል፡፡ አስጎብኚዋ ወረወረችው፡፡ ወይ ፍንክች የአባ ቢላ ልጅ፡፡ ተመልሶ የነበረበት ሄዶ ቀጥ፡፡ አሁንም ስትገፋው፣ ተመልሶ የነበረበት ቀጥ፡፡ ወደ ተቃራኒው አቅጣጫ ቢሞት አይጓዝም፡፡ መልሶ በወዲያኛው አቅጣጫ ለመውሰድ እርሱን ከመግፋት ግሬደር መግፋት ይቀላል፡፡ ለምን? አይታወቅም፡፡
በዚህ ስንገረም እዚያው ፔንዱለሙ አጠገብ የተሠራ ጠረጲዛ ላይ እንጣጥ ብላ ወጣች፡፡ እኛ ሀገር ብትሆኚ እንደ ዛፍ ቆራጩ «ጦጢት ትባይ ነበር» አልኩ በልቤ፡፡ ፊቷን ወደኛ ዞራ በአርባ አምስት ዲግሪ ዘንበል አለች፡፡ የምትወድቅ መስሏት አንዷ ጎብኚ ልትደግፋት ነበር፡፡ ግን ምንም ዓይነት የመሬት ስበት የለም፡፡ ሌሎችም እየወጡ ሞከሩት፡፡ በአርባ አምስት ዲግሪ አዘንብለው ምንም ሊወድቁ አልቻሉም፡፡ እጃቸውን ለቅቀው፤ ግራና ቀኝ ዘርግተው እንደሚበርሩ መስለው ተጋደሙ፡፡ መውደቅ ግን የለም፡፡
ለምን? አትሉም፡፡ መልሱ መ/ መልስ የለም ብቻ ነው፡፡
በቤቱ አንድ ግድግዳ ተጠግቶ የተሠራ መሰላል ጋ ወሰደችን፡፡ መሰላሉ መያዣ የለውም፡፡ ከግድግዳው ጋር ተያይዞ የተገነባ ነው፡፡ ግድግዳውም መያዣ ቦታ የለውም፡፡ እርሷ ቂብ ቂብ እያለች መሰላሉ ላይ ምንም ግድግዳ ሳትደገፍ ወጣችና ቆመች፡፡ ወደ መሬት አዘንብላለች ግን አትወድቅም፡፡ አንዲት ከነፍሷ የተጣላች የፈረንጅ ልጅ እርሷም እንዳስጎብኚዋ ወጣች፡፡ በአፍጢሟ ተደፋች ስንል በአየር ላይ የተንሳፈፈች መስላ ተጋደመች፡፡ ሌሎቹም ምንም ሳይዙ ግድግዳውን በተጣበቀው መሰላል እየወጡ የተንሳፈፉ መስለው ተጋድመው ቆሙ፡፡ እኔ ግን አሁን አዞረኝ፡፡ ሁላችንምኮ ተጣመናል፡፡ አጠገባችሁ ያለውን ሰው ስታዩት ተጣምሞ ነው የምታዩት፡፡ አንዱ እግሩ ይረዝማል፣ ሌላኛው ያጥራል፡፡ በተለይ ረዥም ሰውን አለማየት ነው ተቀንጥሶ የሚወድቅ ይመስልላችኋል፡፡ እዚህ የመሬት ስበት ብሎ ነገር የለም፡፡
ከቤት ከመውጣታችን በፊት «አንድ ነገር ይቀራል» አለች አስጎብኚዋ፡፡ በመውጫው በር ጫፍ ላይ ሁለት የእጅ መያዣ ብረቶች አሉ፡፡ «እስኪ ፈቃደኛ ሰው እነርሱን ይዞ ይንጠልጠል» አለች፡፡ ቅዱስ ፈጠን ብሎ ተንጠለጠለ፡፡ ምን ሆነ? አትሉኝም፡፡ በዓይናችን እያየነው ወደ ግራው በኩል ተጣመመ፡፡ አስጎብኚዋ መጥታ እግሩን ወደ ታች ቀጥ አደረገችው፡፡ ስትለቀው ግን መልሶ ተጣመመ፡፡ እዚያ ተንጠልጥሎ ቀጥ ማለት የቻለ ሰው አልተገኘም፡፡ የሀገሬ ባሕታውያን ቢያዩት ኖሮ «ጠማማ ትውልድ» ይሉ ነበር፡፡
ከቤቱ ወጣን፡፡ ፊታችንን ወደ ቤቱ በር አዙረን ቆምን፡፡ ከፊት ለፊታችን አንድ በግንብ የተሠራ የአርማታ ወለል አለ፡፡ ረዥም ነው፡፡ እንደለመደችው ውኃ ልኩን አውጥታ ለካችው፡፡ ትክክል ቀጥ ያለ ወለል ነው፡፡ በየደረጃው ቁመት ያላቸው አራት ሰዎች መርጣ ደረደረቻቸው፡፡ ከቀኝ ወደ ግራ ከረዥም ወደ አጭር ተደርድረው ቆሙ፡፡ አየናቸው፡፡ እንደ አንደኛ ክፍል ሰልፍ በቁመት ተደርድረዋል፡፡ ተቀያየሩ አለች፡፡ አጭሩ በቀኝ፣ ረዥሙ በግራ ሆኑ፡፡ ቁመታቸው ግን እኩል ሆነ፡፡ ሌሎችም ሞከሩ፡፡ በስተቀኝ የሚቆመው ሰው ሁልጊዜ ቁመቱ ይረዝማል፡፡ ለምን? ማንም አያውቀውም፡፡
አሁን ልንጨርስ ነው፡፡
ሚስትሪ ፓርክ ውስጥ ወላድ እንስሳት መኖር አይችሉም፡፡ ወፎች አያርፉበትም፡፡ እዚያ ተሳስተው ካረፉ በሰከንዶች ተነሥተው ይፈተለካሉ፡፡ ማን እንደሚያባርራቸው መድኃኔ ዓለም ይወቀው፡፡ እዚያ ክልል የሚበቅሉት ዛፎች በሳይንቲስቶቹ ቋንቋ ሴቴ ዛፎች ብቻ ናቸው፡፡ ወንዴዎቹ አይበቅሉም፡፡ እንዲያውም አስጎብኚዋ «ሚስ ትሪስ» ናቸው ብላናለች፡፡ እዚያ ቦታ ኮምፓስ ሰሜንና ደቡብ መለየት አይችልም፡፡ እንደኔ ይዞርበታል፡፡ እጅግ የሚገርመው ደግሞ ዛፎቹ ሁሉ ቅርንጫፍ የሚያወጡት በአንድ በኩል ብቻ ነው፡፡ እዚያ ክልል ውስጥ እንጨት አያረጅም፡፡ የሚስትሪ ፕሎት ቤት ከተሠራ ሰባ ዓመት ሆኖታል፡፡ እንጨቱ ግን አሁንም አዲስ ነው፡፡ አጥሩ ከተሠራ 30
ዓመቱ ነው፡፡ እርሱ ግን አርጅቶ ሊወድቅ ደርሷል፡፡ ለምን? ማንም አይመልሰውም፡፡
ስወጣ እየገረመኝ ነበር፡፡ ዓለማችን እንዲህ ዕንቆቅልሻቸው ባልተፈታ ነገሮች ተሞልታለች፡፡ ሰው ብዙ የሠራ ግን የሚቀረው መሆኑን ዘወትር የሚነግሩት ነገሮች፡፡ ሰው ብዙ የሚያውቅ ግን ከእርሱ በላይ ነገሮችን ሁሉ የሚያውቅ ፈጣሪ እንዳለ የሚያሳዩት ነገሮች ሞልተዋል፡፡ ሰው በቁሙ ያውም በጤናው ሲጣመም ያየሁት እዚህ ነው፡፡ ያነሡትን ቪዲዮ ሲያሳዩኝማ እኔም ራሴ ተጣምሜ ነበር፡፡
ወጣን፡፡ እንዳዞረኝ፡፡ በሱቃቸው በኩል ስናልፍ ምን እንዳየሁ ታውቃላችሁ፡፡ «ወስፈንጠር» ይሸጣል፡፡ ይኼ እንኳን ልጅ ሆነን ወፍ ለመግደል ጠጠር የምናስፈነጥርበት ወስፈንጠር፡፡ ይሄ እንኳን በባላ እንጨት የምንሠራው፡፡ እርሱ፡፡ ስንት? አትሉም፡፡ አሥራ ሁለት ዶላር ይሸጣል፡፡ ምቱት እስኪ በአማርኛ፡፡ በብር ስንት ይሆናል፡፡
ጉድ አየሁ ዘንድሮ፡፡ ደኅና ክረሙ፡፡
ኦክላንድ፣ ካሊፎርንያ
Amazing!!!!! thanks dn daniel it is so nice of you to share to the rest of the world what you sow. I can see how generous and kind you are. So now i have one assignment for myself, some day i will have to visit it. Thank you for that, keep doing what you are doing.
ReplyDeleteDani abo tsafe ante girum new thanks.
ReplyDeleteThanks a lot Dani Sharing Us Such Amazing Mistry, May GOD bless u
ReplyDeleteሰው ብዙ የሚያውቅ ግን ከእርሱ በላይ ነገሮችን ሁሉ የሚያውቅ ፈጣሪ እንዳለ የሚያሳዩት ነገሮች ሞልተዋል፡፡ ሰው በቁሙ ያውም በጤናው ሲጣመም ያየሁት እዚህ ነው፡፡ ያነሡትን ቪዲዮ ሲያሳዩኝማ እኔም ራሴ ተጣምሜ ነበር፡፡
አሃ ዲያቆን ምን ጉድ ነው የምትነግረን?ወይ ያምላክ ስራ ዘይገርም ነው!!! መድሃኔዓለም ስራህን ይባርከው ,ሰላመ እግዚያብሄር ካንተ ጋር ይሁን::
ReplyDeleteDANY EGZIABHER FEKIDOLHE ANTE AYTHEW LEGENA ASYHEN GIRUM DINK YE EGZIABHER SIRA!!!!! KEMALET LELA MIN ELALEHU
ReplyDeletevery funny
ReplyDeleteፈረንጅ እንኳን እንደዚህ የሚታይ ጉልህ ነገር ቀርቶ እራሱ ፈጥሮ ይመራመራል። ታዲያ የዚህን ስፍራ ምንነት ለማጥናት ምንም አልተደረገም አይባልምና ምክንያቱ ምንድነው? በዚህ ዙሪያ የተባለ ነገር እንዳለ አልጠቆምከንም!! ይህ ስፍራ ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ ቢሆን ኖሮ ምን ተብሎ ሊታመንበት የሚችል ይመስልሃል?
ReplyDeleteamazing
ReplyDeleteThis is a real mystery in the ultra 'exhibitionistic' land. This world and the universe in general are yet to be fully known, but by nobody. This mainly makes life worth living, I must assume.
ReplyDeleteThanks for sharing Daniel.
Best,
Teklu
http://tekluabate.blogspot.no/
Thank you Dani!
ReplyDeleteዳኒ በጣም ገርሞሃል . . . . ቀናሁ ታድለሃል ! ! ባንተ ውስጥ እኛም ተገርመን አናባራም! ረጅም እድሜ ሰፊ ጤና!!!!
ReplyDeleteIncredible!! however Would you please put you own picture if it is possible to be sure.
ReplyDeletethat's great
ReplyDeleteYigermal
ReplyDeleteበዚህ ዙሪያ የተባለ ነገር..
ReplyDeletehttp://www.sandlotscience.com/MysterySpots/Mystery_Spots_1.htm
Cher yakoyen
"የሀገሬ ባሕታውያን ቢያዩት ኖሮ «ጠማማ ትውልድ» ይሉ ነበር፡፡"
ReplyDeleteWhat an incredible place! I wish I could see it.
Thanx again Dn Daniel 4 sharing it wiz us.
impressiv, If you don't mind can you please write about the cities you are visiting for agelgilot and share them with us. If it was not you who could do this, share a vulueble information.Thanks to you everybody in the world who reads your blog has the same information. whether someone lives in asmara or hageremariam, or the rest or the world. Thanks thanks thans thanks a lot!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!.
ReplyDeletethank you brothers
ReplyDeletehttp://www.sandlotscience.com/MysterySpots/Mystery_Spots_1.htm
ReplyDeleteif it was not for him we wouldn't be able to pull this website, and that is for sure.
Deletehaving say this: SAY, THANK YOU DANI
Dani edmi yisth
ReplyDeleteሳነበው እንኳን አዞረኝ:: ስንት ምስጢር አለ በምድራችን::
ReplyDeleteeyewelachu befetretu lefetretu yemiglets amlak alen ,EGZIABEHAIR YEMESEGEN
DeleteH
ይህን ሳነብ ትዝ ያለኝ ነገር በዚህ በአሜሪካ ሀገር አንድ የሕዋ ሳይንቲስት በሕዋ ላይ ሰለነበረው ከ 6 ወር ባላይ ቆይታው በሬዲዮ በሰጠው ቃለ ምልልስ ወቅት ቆይታው በጣም ሊያሰለች እንደሚችል ሲያስረዳ "በጣም ሲሰለችህ ለመታነቅ ጭምር ታስባለህ፣ ክፋቱ ግን gravity ስለማይኖር ይህን እንኳ ለማድረግ አትችልም።" ነበር ያለው።
ReplyDeleteWhere is the pdf format?
ReplyDeletei am eager to read the next part please.
Egziabher yesetelen.
wechewu gude !!! endew merete batesebene noro beren berene enaleke nebere belegna !ho ho endiawume yimeche nebere atelegnenem wode semaye enekerebe nebere yihonene what do you think??
ReplyDeleteዳኒ ሁለት ነገር አየሁ አንዱ የእግዚአብሔርን ረቂቅ ምስጥር፡፡
ReplyDeleteሁለተኛው እንደ አባት ያለውን ጌታ በሰጠህ ጥበብ ሳትሳሳ ነገር ሁሉ በፅሁፍ እንድናይ አድረገህ አዝናናህን፡፡ ረጅም እድሜ ይስጥህ፡፡ አንድ ነገር ግን ይቀራል ያንተን ፎቶ ለምን አላሳይህንም ፀበል ፈርተህ ነው?
check out this site. http://www.mysteryspot.com/view/photo-gallery
ReplyDeleteD Daneil Seam Leante Yihun Yetewawekinew Filorida Tampa New Degimo Batam Endiwedih yaderegug Abirewh yetegabezut Kahin & Zemari Nachew Yeanten biloog Adirasha yesetsugim eirshachew nachew Beziyan elet besetsachihut timihirit betsam tedesche neber Kahinu yezemerutim mezimur melekitu tesmamtogal Ahun Degimo yanten biloog simeleket yameletseg hulu neger nafekeg Berta Astemren
ReplyDeleteDaniel EGZIABHER yakbirh.Berta
ReplyDeleteDiakon daniel EGZIABHER yakbirh,berta.
ReplyDeleteAye Dany ! Gud Teserah, AtsaTsafeken wodedikut,
ReplyDeleteSew Sychenekew Yageru teretoch(Enqoqilech) ena YeEnate Guwada Goleto Yetayewual Yemibalewun Ahun Aregagetehu,
Best greeting
wub
Daniel EGZIABHER yakbirh.Berta
ReplyDeleteDani, next time please try to do some researching before you rush to post anything u get along the way...we have overlooked this one now ;) Peace..
ReplyDeleteየሰይጣን ስራ የሰይጣን ሀገር
ReplyDeleteno is not it is real nature how could u said ye seyetan sera hee???????
DeleteAtichkule tisasatalehe Dn Dani...this is fake..they trick u in to thinking this way..dont be full do ur homework before you post
ReplyDeleteየሀገሬ ባሕታውያን ቢያዩት ኖሮ «ጠማማ ትውልድ» ይሉ ነበር፡፡???? all in all surprising place, i feel as if i where there 10q
ReplyDeleteMy dear friends this is not a miracle. It simply is an optical illusion. About 50 similar sites are found throughout the world. 25 sites around the world, and 22 different sites in the U.S alone. The illusion experienced by visitors results from the oddly tilted environment as well as standing on a tilted floor. Inside the tilted room of the Mystery Spot, misperceptions of the height and orientation of objects occur. Even when people are standing outside on a level ground, the slant of the building in the background causes misperceptions as we judge the height of people using the slant of the roof rather than the true horizon.
ReplyDeleteዓለማችን እንዲህ ዕንቆቅልሻቸው ባልተፈታ ነገሮች ተሞልታለች፡፡ ሰው ብዙ የሠራ ግን የሚቀረው መሆኑን ዘወትር የሚነግሩት ነገሮች፡፡ ሰው ብዙ የሚያውቅ ግን ከእርሱ በላይ ነገሮችን ሁሉ የሚያውቅ ፈጣሪ እንዳለ የሚያሳዩት ነገሮች ሞልተዋል፡፡ ሰው በቁሙ ያውም በጤናው ሲጣመም ያየሁት እዚህ ነው፡፡ ያነሡትን ቪዲዮ ሲያሳዩኝማ እኔም ራሴ ተጣምሜ ነበር፡፡
ReplyDeletenice funny topic and i wish i could see it .
ReplyDeleteyegramal dani
ReplyDeleteyegrmal dani
ReplyDeletetesfaye said
yegrmal dani
ReplyDeleteI wish if i can get a chance to see this wow really amazing
ReplyDeleteho hooooooooooooooooooooo! unbelievable ale ferenig!!!! Thanks d.dani!!!!
ReplyDeleteማን ያውቃል ይሄኔ አንዱ ጻድቅ እዚያ ኖሮ ይሆናል እንደኢትዮጵያው መልከጸዴቅ
ReplyDeletekefel anden post adergelen
ReplyDelete