ሰኞ ሰኔ አሥራ አንድ ቀን 2004 ዓም ከቀኑ በሰባት ሰዓት ላይ ከካሊፎርኒያዋ ኦክላንድ ወደ ሳንታ ክሩዝ በመጓዝ ላይ እንገኛለን፡፡ አብረውኝ አስጎብኚዎቼ ኢሳይያስና ቅዱስ አሉ፡፡ ዓለማችን መቼም ዕንቆቅልሻቸው ያልተፈታ አስገራሚ ድንቅ ነገሮች አሏት፡፡ ልክ እንደ ቤርሙዳ ትሪያንግል ከመላምት በስተቀር እቅጩን ነገር ሊናገሩላቸው የማይቻሉ፡፡ ዛሬም የምንጓዘው አሜሪካኖቹ «ብታምኑም ባታምኑ ም» በሚለው የቴሌቭዥን ፕሮግራማቸው ከሚያቀርቧቸው የዓለማችን ድንቅ ነገሮችና ቦታዎች አንዱን ለማየት ነው፡፡
የሀገሬ ሰው ላሊበላ ሲሄድ
እንግዲህ ዲያብሎስ ምን ትበላ?
ትንሹም ትልቁም ሄደ ላሊበላ
የሚለው መዝሙር አሁን ነው ትዝ ያለኝ፡፡ እኔም በተራዬ
እንግዲህ ፊዚክስ ምን ትመልስ
ትንሹም ትልቁም ሄደ ሳንታ ክሩዝ

የሀገሬ መናኝ ዛፉ አልቆበታል፡፡ የአሜሪካ ደን ደግሞ መናኝ አላገኘም፡፡ የሀገሬ መናኝና የአሜሪካ ጫካ ቢገናኙ ኖሮ ምን ሊፈጠር እንደሚችል እያሰብኩ ሁለት መኪና ብቻ ግራና ቀኝ በምታስኬደው እንደ ግሼን መንገድ በቀጠነችው መንገድ ተፈተለክን፡፡ በጫካው ውስጥ ከአራት ኪሎ ሜትር በላይ እንደነዳን የሳንታ ክሩዝን ምሥጢራዊ ፓርክ ምልክት አገኘነው፡፡
የመንገዱ መንገጫገጭና ግራና ቀኙ አቧራ መሆን ወደ አንዳች ልዩ የሆነ ሥፍራ እየሄዳችሁ መሆኑን እንድትረዱት ያደርጋል፡፡ መንገዱ አንድ ይሆናል፣ እንደገና ደግሞ በሁለት ዛፎች ተከፍሎ መሄጃና መምጫ ይሆናል፡፡ መልሶ ደግሞ አንድ መንገድ ይሆናል፡፡ አንዳንድ ቦታ ደግሞ ከመንገዱ ጥበት የተነሣ ተያይቶ መተላለፍ የግድ ይላል፡፡ በጫካው ወስጥ ስታቋርጡ አስፓልቱ እንደ ዲሲ መንገድ ያንገጫግጫችኋል፡፡ መቼም እኔ ከሀገሬ የገጠር መንገድ የማይተናነስ ጎርበጥባጣ መንገድ በምዕራቡ ዓለም ያየሁት ዋሺንግተን ዲሲ ነው፡፡
ደረስን፡፡
የስጦታ መሸጫው ሱቅ ሄዳችሁ ነው ትኬት የምትቆርጡት፡፡ በየአሥራ አምስት ደቂቃው ጎብኚዎች ወደ ጉብኝት ሥፍራው ይገባሉ፡፡ እስከዚያው ትኬታችሁ ላይ ያለውን ሰዓት እያያችሁ መጠበቅ ነው፡፡ በሀገሩ አቆጣጠር አራት ሰዓት ተኩል፣ በኛ ደግሞ አሥር ሰዓት ተኩል ላይ ተራችን ደርሶ ገባን፡፡ «እንኳን ደኅና መጣችሁ» ብላ የተቀበለችን አስጎብኚ ጉብኚቱ 45 ደቂቃ እንደሚወስድ ነገረችን፡፡
«ከሰባ ዓመታት በፊት በ1939 ዓም እኤአ ሚስተር ፓራተር የተባለ ሰው በዚህ አካባቢ የበጋ ቤት የሚሠራበት መሬት ለመግዛት ይመጣል፡፡ ሚስተር ፓራተር በአካባቢው በሁለት ተራሮች መካከል ያለውን ረባዳ መሬት ለመግዛት የመሬቱን ባለቤት ይጠይቀዋል፡፡ ባለቤቱ ለመሸጥ ዝግጁ መሆኑን ለሚስተር ፓራተር ይገልጥለታል፡፡ ነገር ግን ረባዳውን መሬት ሲገዛ ሁለቱን ግራና ቀኝ የሚገኙ ተራሮችንም አብሮ መግዛት እንዳለበት ይነግረዋል፡፡
መጀመርያ ሚስተር ፓራተር ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ በኋላ ግን በአካባቢው በነበረው መልክዐ ምድር በመማረክ ሊገዛው ተስማማ፡፡ ከዚያም በስተግራ በሚገኘው ኮረብታ ላይ አነስተኛ ቤት ለመገንባት የመሬቱን አቀማመጥ የሚያጠናለት ሰው ቀጠረ፡፡ የተቀጠረው ሰው ወደ ኮረብታው ወገብ ላይ ወጥቶ በኮምፓስ አቀማመጡን ለማየት ሲሞክር ኮምፓሱ እየቀባዠረ ተቸገረ፡፡ ትንሽ ራቅ ሲል ግን ኮምፓሱ ይሠራል፡፡ ሚስተር ፓራተር የፈለገበት ቦታ ላይ ግን ኮምፓሱ ሊሠራ አልቻለም፡፡
ይህ ብቻ አይደለም፡፡ ወደዚያ ቦታ ለመሄድ ሲነሡ ከላይ የሚመጣ ኃይል ወደታች ይገፋቸው ነበር፡፡ ጫን ጫን እየተነፈሱ ነበር ወደዚያ ቦታ የሚደርሱት፡፡ በቦታው ላይ እንደምንም ሲደርሱ ያዞራቸዋል፣ ያጥወለውላቸዋል፣ የድካምና የመዛል ስሜት ይሰማቸዋል፣ አንዳንዴም ዕንቅዕፍ ዕንቅልፍ ይላቸዋል፡፡ ነገሩ ባለሞያውንና ሚስተር ፓራተርን ግራ አጋባቸው፡፡ በተለይ ደግሞ ነገሩ የተከሰተው በአንዲት ጠባብ ቦታ ላይ ብቻ መሆኑ ዕንቆቅልሽ ሆነባቸው፡፡
ይህንን ጉዳይ ለመሬቱ ባለቤት ሲነግሩት እርሱም ተመሳሳይ ነገር እንደገጠመው አወራላቸው፡፡ እንዲያውም ቤት ሲሠራ ቤቱ እንደሚንሸራተት ነገራቸው፡፡ አላመኑም፡፡ እነርሱም አንዲት ትንሽ ቤት በእንጨት ሠርተው ወደ ቤታቸው ሄዱ፡፡ በማግሥቱ ግን ቤቱ ተንሸራትቶና በአፍጢሙ ሊደፋ ደርሶ አገኙት፡፡ ቤቱ ወደ ተራራው ግርጌ እንዳይደርስ የሚያግደው ምንም ነገር አልነበረም፡፡ በአካባቢው የነበሩት ዛፎች ተቆርጠው ነበር፡፡ ነገር ግን አንድ ቦታ ላይ ቆሟል፡፡
እነ ሚስተር ፓራተር ሌሎች ባለሞያዎችን ይዘው ለአንድ ዓመት ያህል ጥናት ሲደረግ ያ ቦታ እጅግ በሚገርም ምሥጢር የተሞላ ልዩ ቦታ መሆኑ ተደረሰበት፡፡ ከ1940
ዓም እኤአ ጀምሮም ለሕዝብ ክፍት ሆነ፡፡
ይህ ነው እንግዲህ «የሳንታ ክሩዙ ሚስትሪ ፓርክ» እየተባለ የሚጠራው ሥፍራ፡፡ በተራራው ወገብ ላይ የሚገኝ አንድ መቶ ሃምሳ ጫማ ዲያሜትር ስፋት ያለው አስደናቂ ቦታ፡፡

እኛን ደግሞ እነርሱን እንድናይ ነገረችን፡፡ ሁለቱም ተመሳሳይ ቁመት አላቸው፡፡ እንጨቶቹ ላይ ወጥተው ስናያቸው ግን ከሚስትሪ ፓርኩ ውጭ ያለው ሰው ረዝሞ፣ ከሚስትሪ ፓርኩ ውስጥ ያለው ሰው ያጥራል፡፡ ተቀያየሩላችሁ፡፡ ያጠረው ረዝሞ፣ የረዘመው ደግሞ አጠረ፡፡ ግራ ተጋባንና ሁላችንም እየወጣን ሞከርነው፡፡ ከውስጠኛው ክፍል ስትሆኑ ታጥራላችሁ፣ ከውጨኛው ክፍል ስትሆኑ ደግሞ ትረዝማላችሁ፡፡ ለምንድን ነው? ብትሉ መልስ የለውም፡፡
ወደ ሚስትሪ ፕሎት ቤት ለመግባት ሠላሳ ሜትር የማይሞላ ዳገት አለው፡፡ ያንን ዳገት ከመውጣት በአንድ ፊት የግሼንን ዳገት መውጣት ይሻላል፡፡ አንዳች ነገር ወደ ኋላ ይገፋችኋል፡፡ ገባን እንደምንም፡፡
ፊዚክስ ደኅና ሰንብች፣ የመሬት ስበት ደኅና ሁኚ ማለት እዚህ ነው፡፡
ኦክላንድ፣ ካሊፎርንያ
wow, thank you
ReplyDeleteOh may God really very interesting
ReplyDeletePlease go head!!
This comment has been removed by a blog administrator.
ReplyDeleteAntebalege yalteketahe yekeserehes ante neh side adege!!yemetanebewun yematereda asafari!!!!!!!kinat new ende
DeleteAmazing.... good job bro thanks alot
ReplyDeleteእግዚአብሔር ይስጥልን ዳኒ . . .ረጅም እድሜ ሰፊ ጤና!!!!
ReplyDeleteእረይገርማል ባየሁት
ReplyDeletewow!D/n Daniel it is amazing story! Is there any place alike this which do you know in Ethiopia? please say something. Thanks!
ReplyDeleteAmazing, I am waiting for the next part. Thanks Dn Daniel 4 sharing it with us
ReplyDeletewacha gode
ReplyDeleteedage
dat is amazing i will visit one day inshallah
ReplyDeleteLEKA ADEGU TEMENDEGU YEMINELACHE AGEROCH LEKA TIRE NACHW
ReplyDeleteEndiyaw Tebel binorbet ageru gudu yiweta neber. "Qitam endehon yiwetal shilim kehone yigefal" yilal yeagere sew.
ReplyDeleteDani Egziabiher tsgawun yabizalih:: Qale hiywot yasemalin.
Dani Ahun Eski Yihin Mengerih, Yanin Ager Endegobegneh, Eneman Endeteketelhu, minamin mezegebih leEgna min Yirebanal. Sint neger Memker, Sint neger Metsaf Eyechalik. Waldiba Sikuwar Litekelibet Sil Betekirstyan Bemusina Sititames, Angetihn Defteh, Wey Mengist Endayikotah Alebelezia Degmo Mengistin Wedeh...Zeim Eyalk... Sanhoze Hije... Yihin Ayehu Yihin teredahu tilenaleh. Kante Befit eko BeTV Ayitenewl
ReplyDeleteDear Anonymous, what about we who have not the chance to see it in TV? Endene gin makafelu kifat yelewum.
DeleteSile betekristiyanuam bihon Dn. Daniel bicha be Blog enditsif alketernewum malete erswom limokrut yichilalu::
Anonymous hoy sibeza tebab neh!!! danim endih ayinetun aranbana kobo yehone asiteyayetihin lemin endawetaw germognal! feri anite tekerikireh dani yabat eda alebet endea??? wondime kirstiyan khonk betslot tiga!
Deletebetam yemigeremew kezihe belaye yalehew aseteyayet sechi qoy dani ye teqelaye miniseteru amakari new aluhe weyse balesseletane esu bemichelew menegede sele waledebame hone sele leloche negeroche yayewene yesemawene safe sele betekeresetiyanem bihone betame bizu negerochene yetazebewene bezihe be bebelogu legna akafele wondeme hone dahi endante aynet sew new teqelaye minseter woyeme papase ayedeleme yeyazeweme eskirebeto enji temenja ayedeleme esu yemisefew hageu yalechebetene cheger wegenochu endisemute ena hulume be heberete mefetehe endiyametu enji endihe anbebo be comment endinchachubet ayedeleme andanede degemo ke ager agere siguwaze yagatemeewene aseqigne qeyeme asazagne weyeme asgerami neger legna yesefelenale egname yalefanebetene ebetachene quche belene enkomekemalene
ReplyDeletebeterefe wondeme dani mekeruneme bihone alnetefebeneme selwaledebame bihone sefowale kezihe belaye masetaqeqiya sefo mehale addis abeba laye yeletefelehe woye ohoy gude new dani sinete nefes yalew meselehe yehe qenate yasemeselebehale kefeleke eske zare yesafewene kefetehe anebebewe
beterefe ere ebakachehu lebona yesetene
dehena hune wondeme
kesetane baye negn
ዲ.ዳንኤል እግዚያብሄር አገልግሎትህን ይባርከው መልካም የሆነ እውቀት ሰጥተህናል እናመሰግናለን፡፡
ReplyDeletetiru
ReplyDeleteYegebahu yahl new yetesemagn. GBU Dany!
ReplyDeleteOH REALLY???? DANIEL TO BE HONEST AM NOT AMAZED AS U ARE.IT'S DRAMMA OF SEYETAN!!I THINK I RATHER READ SOMETHNG ELES...SOMETHING ABOUT HISTORY OF ETHIOPIA..OR..THE LOVING PPL.
ReplyDeleteTHANK U ANY WAY.
SOME PEOPLE SAID "BECAUSE U CAN,CAN'T DO ALL".
I ALWAYS ADMIRE YR WRITING.
S.C
እግዚአብሔር ይስጥልን ዳኒ . . .ረጅም እድሜ ሰፊ ጤና!!!!የገረመኝ ግን በዚያ አካባቢ ኑዋሪ የሆኑ ወገኖቻችን ምንም ተጨማሪ መግለጫ ሊሰጡ አልሞከሩም::ምነው?
ReplyDeleteI want to say something for the above comment, God crate all parts of the world and all humankind on earth so Daniel did the right thing he share what he saw in one part of the world and this place also created by God not by “Seytan”. It is not necessary to talk always about Ethiopia we have to discover and know what God create in other parts of the world.
ReplyDeleteThank you Dani Keep it up !
እንግዲህ ያንተ ስራ እኛ እዚህ ባለንበት እግራችን ዘርግተን ቁጭ ብለን ዓለምንና አስደናቂ ጓዳዎቿን በአይነ ልቡናችን በምናባችን እያየን እንድንጎበኝ ማድረግንም ይጨምራል ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ይባርክህ አቦ!!!
ReplyDelete