Thursday, June 21, 2012

እሌኒ መሐመድ


የመጀመርያዋ ኢትዮጵያዊት ሴት ደራሲ
Queen Eleni Memorial Hospital Hosaena, Hadeya
በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን የሐድያ ገራድ የነበረው ማሒኮ ለንጉሡ ግብር ላለመገበር አሻፈረኝ አለ፡፡ ንጉሥ ዘርዐ ያዕቆብ ዓመታዊውን ግብር እንዲያመጣ ሲጠራው «ወደ ደጅህ አልደርስም፤ ሀገሬንም አልለቅም» ብሎ የንጉሡን መልክተኞች መለሳቸው፡፡ ይህ ከሆነ ከጥቂት ጊዜ በኋላ የጉዳይቶ ገራድ ወደ ንጉሡ በፍጥነት ገሥግሦ በመሄድ የሐድያ ገራድ ለጦርነት እየተዘጋጀ መሆኑን ደብረ ብርሃን ላይ አረዳው፡፡ ከአካባቢው የባሌና የደዋሮ ገዥዎችም ርዳታ ያገኝ ዘንድ ጠየቀው፡፡

ንጉሥ ዘርዐ ያዕቆብ ይህንን ሲሰማ የሐድያው ገራድ ዋና ዋና ተባባሪዎች እነማን እንደሆኑ፤ ዐመፁ ሕዝቡን ሁሉ ያስተባበረ ነው ወይስ የጥቂቶች ነው? አንተስ ምን ቢደረግ ይሻላል ትላለህ? ሲል ጠየቀው፡፡ የጉዳይቶው ገራድም ከማሒኮ ጋር የተባበሩ ዘጠኝ ገራዶች መኖራቸውን፤ ማሒኮ ወርዶ አጎቱ ገራድ ባሞ ቢተካ የተሻለ እንደሆነ ነገረው፡፡


ዘርዐ ያዕቆብ ምክሩን ተቀብሎ ባሞን ጠራውና ዋና ገራድ አደረገው፡፡ እርሱንና የጎዳይቶውን ገራድም ሸለማቸው፡፡ ሁለቱንም ሰዎች ከዳሞት ከተንቀሳቀሰ ከብዙ ወታደር ጋር ወደ ሀገራቸው ላካቸው፡፡ የደዋሮና የባሌ ሰዎችም ዐመፀኛው እንዳያመልጥ እንዲከብቡ ተነገራቸው፡፡ ጦሩ ወደ አካባቢው ሲደርስ የገራድ ማሒኮ ተባባሪዎች ድጋፋቸውን ለዘርዐ ያዕቆብ ሰጡ፡፡ ገራድ ማሒኮም ብቻውን ቀረ፡፡ 

ሁኔታውን የተረዳው ገራድ ማሒኮ በምሥራቅ በኩል ወደ አዳል ሸሸ፡፡ ነገር ግን የዳሞት ሰዎች ተከትለው ድል አደረጉትና ሞተ፡፡ ከዚህ በኋላ የሐድያ ገራዶች ለማዕከላዊው መንግሥት ታማኝ ሆነው ዘለቁ፡፡ በዚህ ሁኔታ ከቀጠሉት አንዱ ገራድ መሐመድ ነበረ፡፡
ገራድ መሐመድ በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብና በልጁ በበእደ ማርያም ዘመን የሐድያ ገራድ የነበረ ነው፡፡ 

ንጉሥ በእደ ማርያም ሥልጣን እንደያዘ ከሐድያ ጋር የነበረውን የክርስቲያኑ መንግሥት ግንኙነት በአንድ እርከን ከፍ አደረገው፡፡ የገራድ መሐመድን ልጅና የገራድ ማሒኮን እኅት «እቴ ዛን ዜላን´ እጅግ በታወቀችበት ስሟም እሌኒን አገባ፡፡ (R. Pankhurst, The Ethiopian Borderlands, 1997, pp.144-146 )

እሌኒ በኢትዮጵያ ታሪክ በአስተዳደር፣ በእምነትና በፖለቲካ ኃያላን ከሆኑ ጥቂት መሪዎች የምትመደብ ናት፡፡ ምናልባትም ከንግሥተ ሳባና ከሕንደኬ ቀጥላ ልትጠቀስ የምትችል ኃያል ሴት ትመስለኛለች፡፡ ማዕከላዊው መንግሥት እንዲጠናከር፣ በሙስሊሙና ክርስቲያኑ መካከል የነበረው ግንኙነትም የተሻለ እንዲሆን ጥረት አድረጋለች፡፡ ምንም እንኳን የአብራኳ ክፋይ ልጅ ባይኖራት በነገሥታቱና በሕዝቡ ዘንድ እንደ እናት ትታይ ነበር፡፡ 

ባሏ በእደ ማርያም እሌኒን ከመውደዱ የተነሣ እንደ እናቱ ይሳሳላት እንደነበረ ዜና መዋዕሉ ይነግረናል፡፡ በበእደ ማርያም፣ በናዖድና በልብነ ድንግል ቤተ መንግሥት የእሌኒን ያህል የሚፈራና የሚከበር አልነበረም፡፡ በመፈራቷና በመከበሯም የተነሣ የመንግሥቱ ሽግግር እጅግ አንፃራዊ በሆነ መልኩ ሰላማዊ እንዲሆን አስችላዋለች፡፡ ዐፄ ናዖድ አርፎ ሕፃኑ ልብነ ድንግል በ12 ዓመቱ ሲነገሥ (1501ዓም) ቤተ መንግሥቱን ትመራው የነበረችው እሌኒ ነበረች፡፡ ዜና መዋዕሉ «የመንግሥቱን ሕግ በደንብ ጠንቅቃ የምታውቅ፣ በሦስት ታላላቅ ነገሥታት ቤተ መንግሥትም የነበረች» ይላታል፡፡ (ሕገ ወሥርዓተ መንግሥት፣ Bodeleian, MS Bruce 88, fol 39r)

በ15ኛው መክዘ አጋማሽ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ፖርቹጋላዊው አልቫሬዝ ይህቺን የሐድያ ልጅ «ብርቱና ታዋቂ ገዥ ነበረች» ይላታል (The Prester John of The Indies, Vol. I, p. 307) ፡፡ እንዲያውም በወቅቱ ጳጳስ የነበሩት አቡነ ማርቆስ ሕፃኑን ልብነ ድንግልን ወደ ዙፋን ያወጡት እርሳቸውና ንግሥት እሌኒ መሆናቸውን ገልጠውለት ነበር፡፡ «ምክንያቱም ሁሉም ታላላቅ ሰዎችና ሀብት  በእኛ አጅ ነበሩና» ነው ያሉት፡፡ (The Prester John of The Indies. Vol. II, p. 243) የቱርኮችንና የግራኝን ጦር ሁኔታ በማየት ወደ ፖርቱጋል ማቲዎስ የተባለውን መልክተኛ የላከችውም እርሷ ነበረች፡፡ (The Prester John of The Indies, vol. I, p. 39)

ንግሥት እሌኒ ከፖለቲካውና አስተዳደሩ በተጨማሪ በሃይማኖት በኩል ብርቱ ምእመን ነበረች፡፡ አልቫሬዝ እንደሚለው እሌኒ ዓመቱን ሙሉ የምትጾም ሰው ነበረች፡፡ ምግብ የምትመገበውም በሳምንት ሦስት ቀን ማክሰኞ፣ ኀሙስና ቅዳሜ ብቻ ነበር፡፡ (The Prester John of The Indies, vol. II, p. 395) 

ከሁሉም የሚገርመውና ምናልባትም እስከዛሬ በማንም የቤተ መንግሥት ሴት ያልተሞከረው የእሌኒ ችሎታ የነገረ መለኮት ዕውቀቷ ነው፡፡ አልቫሬዝ እንደሚለው እሌኒ በነገረ መለኮት የበሰለችና ከዚያም አልፋ ሁለት የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን የጻፈች ሴት ናት፡፡ የመጀመርያው ስለ ምሥጢረ ሥላሴና ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ንጽሕና የተጻፈ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ስለ ሕገ እግዚአብሔር የጻፈችው ነው፡፡

እጀግ ብዙው ርስቷ በነበረበት በጎጃም በኋላ ላይ ግራኝ አሕመድ ያፈረሰውን ታላቁን የመርጡለ ማርያም ቤተ ክርስቲያን አሠርታ ነበር፡፡ የቤተ ክርስቲያኑ መንበር ከእንጨት ተሠርቶ በወርቅ የተለበጠ ሲሆን፣ ጽላቱ ከንጹሕ ወርቅ የቀረፀ ነበር፡፡ ይህንን ቤተ ክርስቲያን ለማሠራትም ባለሞያዎቹን ከግብጽ አስመጥታ ነበር፡፡ 

የፖርቱጋል መልክተኞች ወደ ኢትዮጵያ በገቡ ጊዜ እሌኒ ስታርፍ በሕዝቡ ዘንድ ድንጋጤ ፈጥሮ ማየቱን አልቫሬዝ ይተርካል፡፡ በደግነቷ፣ በኃያልነቷ፣ በእምነቷና በፖለቲካዊ ጥበቧ የታወቀችው እሌኒ ያረፈችው በመጋቢት 1515 ዓም አካባቢ ነው፡፡ (The Prester John of The Indies, Vol. II, p. 425) እርሷ ማረፏ ሲሰማ ከመላዋ ኢትዮጵያ በመርጡለ ማርያም በሚገኘው መቃብሯ ላይ ለማልቀስ በየቀኑ ሕዝቡ ይጎርፍ ነበር፡፡ ሕዝቡም «እርሷ ስትኖር ሁላችንም እንኖር ነበር፤ እንጠበቅና እንታፈርም ነበር፡፡ እርሷ ከሞተች ግን ሁላችንም ሞትን ማለት ነው፡፡ እርሷ የታላቁም የታናሹም እናትና አባት ነበረችና» እያሉ ሲያለቅሱ ማየቱን አልቫሬዝ ይጽፋል፡፡ (The Prester John of The Indies, vol. II, p. 434) እንዲያውም ካረፈች ከስምንትና ዘጠኝ ወራት በኋላ እንኳን ሰዎች ከተለያየ ቦታ እየመጡ በመቃብሯ ያለቅሱ ነበር፡፡ (The Prester John of The Indies, vol. II,p. 425) 

ቨርጂንያ፣ አሌክሳንድርያ

26 comments:

 1. «እርሷ ስትኖር ሁላችንም እንኖር ነበር፤ እንጠበቅና እንታፈርም ነበር፡፡ እርሷ ከሞተች ግን ሁላችንም ሞትን ማለት ነው፡፡ እርሷ የታላቁም የታናሹም እናትና አባት ነበረችና»
  አዎ በኃላ ዘመን ላይ ለዳግማዊ አጤ ምኒልክ እምዩ መሞታቸው ቢደበቅም እጅግ መሪር ሃዘን አዝኖአል ይህ ነገር በዚህ በኛ ዘመን ይደገም ይሆን ማን ያውቃል ብለዋል ባለቅኔው ጋሽ መንግስቱ ዳኒ እባክህ በርታ ብዙ ሊነገሩ የሚገባቸው ታሪኮቻችንን በተቻለህ መጠን ጻፍልን ረጅም ዕድሜ፣ከጤና ጋር ያድልህ።
  ዘረያዕቆብ ይሁን

  ReplyDelete
 2. ይህች የመጀመሪያ የምትል ቃል ለአብዛኛዎቻችን ኢትዮጵያን የተወደደችና የተለመደች ትመስላለች፣ ይህን የታዘበው ወንድማችን በእውቀቱ ስዩም ኢትዮጵያውያን «የመጀመሪያ» የሚለውን ቃል በመጠቀም በዓለማችን ከሚገኙ ሕዝቦች ተወዳዳሪ የሌላቸው ሕዝብ ነን በማለት በቀልድ የተዋዛ ቁም ነገር ቢጤ መናገሩን አስታውሳለሁ፡፡ ይኸው አንተም የመጀመሪያዋ ሴት ደራሲ በማለት ስለ ንግሥት እሌኒ ገለጻህን አስቀደህምሳ፡፡

  የረጅም ዘመን ታሪክ፣ ስልጣኔና ስነ ጹሑፍ ሀብት ላላት ኢትዪጵያና ኢትዮጵያውያን ዓለምን ያሰደነቀና በወቅቱ ከነበሩት ከፋርስ፣ ከግብጽና ከቻይና ሥልጣኔዎች እኩል ክብርና ዝና በነበራት አክሱም ምንም እስከአሁን ድረስ በታሪክ ጥናትና በአርኪዮሎጂ ቁፋሮ የተደረሰበት መረጃ ባይኖርም ቢያንስ በጣት የሚቆጠሩ ሴት ባለ ቅኔዎችና ጸሐፍት/ደራሲያን ይጠፋሉ ብዬ አልገምትም፡፡ ምክንያቱም ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ በገባበት አካባቢ አክሱማውያን ቤተ መንግሥት በሞግዚነት በማስተዳደርና ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ የንግድና የውጭ ግንኙነትን በተመለከተ ምክርና ውሳኔ በመስጠት የሴቶች ተሳትፎ እንደነበረ የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ፡፡ ዳኒ፡- የእኛይቱ እንዲያ በጥበብ ፍቅር ነፍስ ያልቀረላት አክሱማይቷ ንግሥተ ሳባ/አዜብስ ብትሆን ጥቂት የፍልስፍና እና የጥበብ መጽሐፍ አይኖራትም ብለህ ትገምታለህ…ማን ያውቃል…

  ስለዚህም በመንግስት ደረጃ ይሄን ያህል ሚና የነበራቸው ሴቶች በማንበብና በመጻፍ ረገድም ያልተናነሰ ሚና ይኖራቸዋል ብዬ አላስብም፡፡ ስለዚህም ከታሪካችን ዘመን ርዝመትና ርቀት እንዲሁም ታሪካችን ገና በቅጡ ያልተጠና ከመሆኑ በላይ አውሮፓውያኑ በተለያየ አጋጣሚ የተውሉንን የጉዞ ማስታወሻዎችና የታሪክ ሰነዶች ብቻ ተመርኩዘን ንግስት እሌኒ የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ሴት ደራሲ ናት ብሎ መጥራት ብዙም የሚያስኬድ አይመስለኝም፡፡ እንዲያም ሲል ረጅሙን ታሪካችንን ማኮሰስና ማሳጠር ይመስለኛል፡፡ ከዛ ይልቅ በታሪክ ጸሐፊዎች ዘንድ እውቅናና ስፍራ የተሰጣት የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ሴት ደራሲ ቢባል የሚያስኬድ ይመስለኛል፡፡

  አስተያየቴ እንዳለ ሆኖ ቢሆንም ግን ስለዚህች ታላቅ ሴት የጠለቀ ስነ መለኮት እውቀቷና የድርሰት ስራዋ ለአንባቢያንህ በማስተዋወቅህ ሳላመሰግንህ አላልፍም፡፡
  በፍቅር ለይኩን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. የእኛይቱ እንዲያ በጥበብ ፍቅር ነፍስ ያልቀረላት አክሱማይቷ ንግሥተ ሳባ/አዜብስ ብትሆን ጥቂት የፍልስፍና እና የጥበብ መጽሐፍ አይኖራትም ብለህ ትገምታለህ…ማን ያውቃል…
   የሀድያ ንግስት የእናንተ አይደለችም ማለት ነው ??? ንግስት ሳባ ደራሲ ለመሆኗ ማስረጃ ካልተገኘ ምን ይደረግ ??? ታሪክ በግምት የጻፋል እንዴ ??? በዕውነት ተገቢ ያልሆነ አስተያየት ነው የጻፉት፡፡

   Delete
  2. 1ኛ/ እኛይቱ እንዲያ በጥበብ ፍቅር ነፍስ ያልቀረላት አክሱማይቷ ንግሥተ ሳባ/አዜብስ ብትሆን ጥቂት የፍልስፍና እና የጥበብ መጽሐፍ አይኖራትም ብለህ ትገምታለህ…ማን ያውቃል
   2ኛ/ የሀድያ ንግስት የእናንተ አይደለችም ማለት ነው ??? ንግስት ሳባ ደራሲ ለመሆኗ ማስረጃ ካልተገኘ ምን ይደረግ ??? ታሪክ በግምት የጻፋል እንዴ ??? በዕውነት ተገቢ ያልሆነ አስተያየት ነው የጻፉት፡፡
   በተራ ቁ 1ኛ እና 2ኛ ላይ ጠባብነታችሁን የገለጻችሁልን ጎጠኞች ብላችሁ ብላቸሁ በየሰፈሩ ፣ በየትምህርትቤቱ ፣ በየመ/ቤቱ የሰለቸንን ጠባብነት አምጥታችሁ ቁምነገር አምድ ላይ ስታራገግፉብን ህሊና የሚባለው ነገር አይቆነጥታችሁም፣፣ እግዚአብሔር ነገርን በመልካም የምትመነዝሩበት ልቦና ይስጣችሁ ሌላ ምን ይባላል፡፡

   Delete
 3. taricachenen mawek tiru new Dani alfo alfo endezi betetsef teru new.

  ReplyDelete
 4. Very Interesting history. Surprisingly the country of this Lady /Professor of Orthodox/, Hadiya, is now invaded with Protestants.

  ReplyDelete
  Replies
  1. " Surprisingly the country of this Lady /Professor of Orthodox/, Hadiya, is now invaded with Protestants."pls pray! for those people.

   Delete
 5. The first time when I hear this history.
  Thanks Danieal for sharing us what you know.

  ReplyDelete
 6. Yes! She was really wise. She had also predicted and was repeatedly remind the king Libnedingil that great Ethiopian banda (together with Turkish) and terrorist will rise from Eastern Ethiopia--Giragn Ahmed. for further read this book ("Ethiopian History in the 16th century" Addis Ababa University.1954. pp.... by Yilma Deresa)

  ReplyDelete
 7. interesting part of our mothers history. In deed, It is yet to be re discovered. Thank you Dani.

  ReplyDelete
 8. Thanks dani. we have to wake up to know and research our history with this ringing bell and. thanks again!

  ReplyDelete
 9. ዲያቆን ዳንኤል ከሁሉ አስቀድሜ ላመሰግንህ እወዳለሁ
  ዛሬ ከሀድያ ብሄረሰብ ስለተገኘችው ንግስት እሌኒ የስነበብከን ታሪክ በጣም ደስ አሰኝቶኛል ነገር ግን ታሪኩ አንዳንድ ማስተካከያዎች ስለሚያስፈልጉት እንደሚከተለው አቀርባለው፡፡
  1. አንተ ያስነበብከን ታሪክ ሙሉ በሙሉ የሀዲያ ሳይሆን የጠንባሮ ህዝቦች ታሪክ ነው፡፡ የጠንባሮ ህዝብ ማለት በደቡብ ክልል በከንባታ ጠንባሮ ዞን ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የአንድ አባት ልጆች በሆኑ 7 ወንድማማቾች (ጎሳ መሪዎች) የተመሰረተ ህዝብ ነው ከነዚህ ጎሳዎች ውስጥ የ ባሞ ጎሳ ደርግ ስልጣን እስከያዘበት ጊዜ ድረስ ህዝቡን ሲመራ ነበር፡፡

  2. በጠንባሮ ህዝብ ቋንቋ ወማ ማለት ንጉስ ማለት ሲሆን አንድ ንጉስ ሲሞት ቀጣዩ ንጉስ የሚመረጠው ከባሞ ልጆች ወይም የልጅ ልጆች ብቻ ነው (የባሞ ዝርያዎች በሙሉ ባሙሼ በመባል ይታወቃሉ) ከባሞ ዝርያ ከተነሱት ነገስታት ውስጥ እኔ የማውቃቸው፡- ወማ ባሞ፤ ወማ ዋሪዩ፤ ወማ ላምቤቦ፤ ወማ ጨፎሬ ፤ ወማ አጢሶ፤ ወማ ቦኪሳ……. ቀኝአዝማች በየነ ባረና ሲሆኑ (ቀዳማዊ ኃ/ስላሴ ኢትየጵያ ውስጥ ሙሉ በሙሉ የጉልት ሥርዓትን ያስቀሩበት ጊዜ ላይ ሲደረስ ቀኝ አዝማች በየነ ወማ( ንጉስ) ተብለው መጠራታቸው ቀርቶ ቀኝ አዝማች የሚል ማዕረግ ተሰጥቶአቸው ህዙቡን በባላባትነት ሲመሩት ቆይተዋል)፡፡

  3. እኔ እራሴ የባሙሼ ጎሳ የወማ ዋሪዩ ቤተሰብ ስሆን የቀድሞ አባታችን የሆነው ባሞ የመቃብር ስፍራ ከእኛ ቤት በግምት በ 50 ሜትር ርቀት ላይ ነው የሚገኘው ፡፡ ( አሁን ግን እኔ የምኖረው ሀዋሳ ከተማ ውስጥ ነው)

  4. ባሞ ሰባት ልጆች ነበሩት ስለዚህ የባሙሼ ጎሳ በአሁኑ ጊዜ በሰባት ቤተሰብ ተከፋፍሎ ይገኛል፡፡ እነዚህ የጎሳ አባላት የሆኑ ሰባት ቤተሰቦች በየዓመቱ አንድ አንድ ኮርማ በድምሩ ሰባት ኮርማ አምጥተው በአባታቸው መቃብር ላይ አርደው በመብላትና በመጠጣት ተድላ ደስታ ያደርጉ ነበር፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ህብረተሰቡ ወደ ፕሮቴስታንት ሀይማኖት እየተቀየሩ ሲመጡ ጉዳዩን ከባዕድ አምልኮ ጋር ስላያያዙት እንደ ቀድሞው በአባታቸው መቃብር እያረዱ መብላቱንና መሰብሰቡን እየተውት መጥተዋል፡፡

  5. በአሁኑ ጊዜ የባሞ ዝርያ ያላቸው የባሙሼ ጎሳ አባላት በሙሉ በአባታቸው መቃብር ላይ ሀውልት ለማሰራት በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ፡፡

  6. የጠንባሮ ህዝብ ከአንድ አባት የተገኙ በመሆናቸው እስከዛሬ ድረስ በመካከላቸው የእርስ በእርስ ጋብቻ ክልክል ነው ስለዚህ በጋብቻ የሚዛመዱት በዙሪያቸው ከሚገኙት ከሀዲያ፤ ከንባታ፤ ወላይታ፤ ኦሮሞ፤ ከፋ….ወዘተ ሲሆን በተለይ ከሀዲያ ጋር በስፋት በጋብቻ ተዛምደዋል /ተቀላቅለዋል/፡፡ ታሪክ ጸሐፊው ተመሳሳይ ቋንቋ፤ ባህል…ሲሆንበት ሁለቱንም ሀድያ አላቸው፡፡

  7. ንግስት እሌኒ ደግ መሆናን ጠቅሰህ ነበር፤ ከደግነት ጋር በተያያዘ የምነግርህ የጠንባሮን ህዝብ የሚያውቅ ሰው አግኝተህ ስለ ባሞ (ባሙሼ) ጎሳ ብትጠይቀው አንዲት ነገር ብቻ ነው የሚነግሩህ እርሱም ደግነታቸውን ነው፡፡ አንድ የባሞ ጎሳ ልጅ አግኝተህ የሄ እርሻ ወይም አዝመራ የማን ነው ብለህ ብትጠይቀው የእኛ ነው የሚልህ ( የእኔ ማለት አያውቁም)፡፡

  8. ማህኮ(መኮ) የባሞ አጎት ሳይሆን ወንድሙ ነው፡፡ ማህኮ(መኮ) ዛሬ ከጠንባሮ ህዝብ ጎሳዎች እንደ አንዱ ይቆጠራል፡፡

  ዲያቆን ዳንኤል ከንግስት እሌኒ ጋር በማያያዝ ያቀረብከው ታሪክ የሀዲያ ህዝቦች ሳይሆን የጠንባሮ ህዝቦች ታሪክ ነው ፡፡ አሁን በችኮላ ስለጻፍኩ ነው እንጂ ሌሎች በርካታ ማስረጃዎችን ላቀርብልህ እችላለሁ፡፡ ከዚህ ዉጪ ንግስት እሌኒ ሀዲያ ስለመሆኗ እና ባሞ የሀዲያ ጋራድ ስለመሆኑ ምንም ተጨባጭ ማስረጃ ማግኘት አይቻልም፡፡
  በቅርብ የሚያውቁኝ ሰዎች አንተኮ የነገስታት ዘር አለብህ ፤ የባላባት ቤተሰብ ነበርክ ሲሉኝ ትንሽ ክብደት ቢጤ ይሰማኝ ነበር ፤ ዳኒ አንተ ደግሞ የንግስት እሌኒ ዘር መሆኔን ስትነግረኝ የተሰማኝን ስሜት ለመግለጽ ቃላት….፡፡
  ዳኒ ላቀረብከው ጽሁፍ በጣም አመሰግናለሁ ከላይ ላቀረብኩልህ ጥቂት ማስረጃዎች ተጨማሪ ልትጠይቀኝ ከፈለክ አድራሻዬ፡- temeache@yahoo.com

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thank you My Brother for your detail information. You can read about the Gerad bamo, from the chronicle of Zerea yaeqob.
   Daniel kibret.

   Delete
  2. ende, ende.Dani soft Cake,This is my 1st time to see you giving response for ur readers comment which is good.keep it up.

   Delete
 10. Danie; i am at the age of 20s and i am fro northen Ethiopia and we in this age have no good info about ethiopia due to this government segregation system they only preach us about foot ball and -------
  you bridge for us who make us aware about our true personality and our brothers history i.e Debub Ethiopia, -----
  long live to you , berta

  ReplyDelete
 11. Amazing history, i'm from hossana,i frequently hear about Ileni yet i don't know about her much you gave me a nice explanation. now i'm confident enough to answer questions regarding her.i thank you very much long live to you

  ReplyDelete
 12. Interesting piece of history! Thank you for the contribution.

  I am currently reading a book by Paul Henze, entitled, "Layers of Time: A Histroy of Ethiopia". According to this book Queen Eleni was, in fact, one of the four wives of King Zara Yakob. She was indeed the daughter of the King of Hadiya, and orginally a muslim.

  Tseyon Mogasa, mother of Baeda Maryam, the book continues, died of mistreatment about 1462. Baeda Maryam apparently blamed his father Zara Yakob for her death. But later the two – the father and the son – reconciled and Zara Yakob reportedly appointed Baed Maryam as his successor. Zara Yakob died in 1468 and Baeda Maryam took the throne. Having lost his mother at an early age, the book claims, Baeda Maryam conferred Eleni the title of Queen Mother. That means according to Paul Henze’s narration of this part of Ethiopian history, it is very hard to say that Queen Eleni was in fact the wife of Baeda Maryam. Instead she was Zara Yakob’s wife and she outlived Zara Yakob and got the title of Queen Mother from Zara Yakob’s son and successor, Baeda Maryam.

  It is stated in the book that Baeda Maryam himself died at the early age of 30 in 1478 and Eleni outlived both Zaera Yakob and Baeda Maryam. She outlived Zara Yakob by 50 years and became one of the most influential women of Ethiopian history. Of course, the book admits that Eleni was practically a co-monarch during the reign of Baeda Maryam.

  One of Zara Yakon’s chroniclers says the following about her:

  …she was accomplished in everything: in front of Go, by practicing righteousness and having strong faith; by praying and receiving Holy Communion; as regards worldly matters she was accomplished in the preparation of food, in her familiarity with books, in her knowledge of the law, and in her understanding of the affairs of state.

  The book contains an extensive coverage of Queen Eleni taken from different sources, including, “ The Prestor John of the Indies", by the Portugese Father Francisco Alvares.

  I just wanted to bring this fact and the book to the attention of Dean Daniel who otherwise is feeding us all from his infinite, thoughtful and educative fountain of wisdom.

  By the way, here is the full citation of the book I am referring to:
  Paul B. Henze, Layers of Time: A History of Ethiopia, Hurst & Company, London, 2000.

  ReplyDelete
  Replies
  1. some of the historians make a confusion between Zarea Yaeqob's and Beede Maryam's Eleni. Zarea Yaeqobis Eleni Died before Beede Maryam become A king with mis treatment of her Husband. But Beede Maryam's Eleni Lives long life up to the time of Libne dingil and buried in Mertule Maryam of Gojjam.
   Dr. Beyeberu H.

   Delete
 13. thank you for this information keep it up. god bless you.

  ReplyDelete
 14. Minew Diakon Daniel...Nigist Yoditin resahet.
  1.Nigist Saba
  2.Nigist Yodit
  3.and then might come Eleni

  ReplyDelete
 15. thank you for this information keep it up. god bless you

  ReplyDelete
 16. Dear Deacon Daniel,
  I appreciate your ceaseless effort to address various important issues on your blog. This article is also too good and a real story. If we have a keen mind, we can learn a lot from Queen Eleni's qualities (strength, dedication and leadership styles . . .) as she was one of the model mothers in our church history.

  Please also write some articles about the current disease (regionalism, nepotism & favoritism).

  Keep it up!

  ReplyDelete
 17. we wish to have a leader like her God help us thank you Daniel.

  ReplyDelete
 18. tedelana destan mashenef yechalech enat,bereketua yedereben.

  ReplyDelete