Tuesday, June 19, 2012

የሰው ሀልወቱ

click here for pdf
የሰው ሀልወቱ ብዙ ነው ይባላል፡፡ ሰው በዚህ ምድር ይኖራል፡፡ በታሪክ ውስጥ ይኖራል፡፡ በሰዎች ኅሊና ውስጥ ይኖራል፡፡ በልጆቹ ውስጥ ይኖራል፡፡ በሥራው ውስጥ ይኖራል፡፡ በዐጸደ ነፍስም ይኖራል፡፡ አነዋወሩ ግን ይለያያል፡፡ በበጎ የሚኖር አለ፡፡ በተቃራኒውም፡፡ በሌሎቹ ሀልዎቶች ለሚኖረው አነዋወር ግን በምድር ላይ የሚኖረው ኑሮ ወሳኝ ነው፡፡
ሰው ከእንስሳት ከሚለይበት ነገሮች አንዱ ይኼው ነው፡፡ ለምድራዊ ህልውናው ብቻ ሳይሆን ለሌላውም ህልውናው ይጨነቃል፤ ያስባል፡፡ ሲኖርም ለእነዚያም ጭምር ይኖራል፡፡ እንስሳት በምድር ላይ ስላላቸው ኑሮ እንኳን አያስቡበትም፡፡ በደመ ነፍስ ይኖሩበታል እንጂ፡፡ ከዚያም አልፈው ሌላ ዓይነት አነዋወር የላቸውም፡፡ ትናንት የሚሉት ታሪክ፣ ነገ የሚሉት ተስፋ የላቸውም፡፡ ህልውናቸውን ሰው እንጂ ራሳቸው አይወስኑትም፡፡ ስለዚህም ብቻቸውን ሊመሰገኑም ሆነ ሊወቀሱ አይችሉም፡፡
 ሰው ግን እንዲህ አይደለም፡፡ በዚህ ምድር ያለው ህልውናው ቢያበቃ እንኳን በሰዎች ልቡና ውስጥ ያለው ህልውና ሊቀጥል ይችላል፡፡ እንዳይቀጥል አድርጎ ከኖረም ይረሳል፡፡ በታሪክ ውስጥ ያለው ህልውና ይቀጥላል፡፡ በአዎንታ ወይም በአሉታ ይነሣል፡፡ በሥራው ውስጥ ያለው ህልውና ይቀጥላል፡፡ ሥራው ያስመሰግነዋል ወይም ያስወቅሰዋል፡፡ በልጆቹ ውስጥ ያለው ህልውና ይቀጥላል፡፡ ልጆቹ ይኮሩበታል፣ ወይም ያፍሩበታል፡፡ በዐጸደ ነፍስም እንዲሁ፡፡ ይጸድቃል ወይም ይኮነናል፡፡ ሁሉም ግን እዚህ ይወሰናል፡፡

ዐፄ ምኒሊክ ጥርሳቸው ወጣ ወጣ ያለ ነበርና አንድ ባለ ቅኔ
በሰማይ የሚጸድቅ በምድር ያስታውቃል
ከከንፈሩ ቀድሞ ጥርሱ ጣይ ይሞቃል
ብሎ ገጥሞላቸው ነበር፡፡ እውነቱን ነው በሰማይ የሚጸድቅ በምድር ያስታውቃል፡፡
ለመሆኑ እኛ እንዴት መታሰብ እንፈልጋለን? ነገ እናልፋለን፡፡ ከአካላዊ ህልውና ወደ ታሪካዊና ኅሊናዊ ህልውና እንሸጋገራለን፡፡ ያኔ በሌሎች ሰዎች ልቡና ውስጥ ምን ተብለን መታሰብ እንፈልጋለን? ጨቋኞች፣አረመኔዎች፣ አምባገነኖች፣ ዘረኞች፣ ሙሰኞች፣ ከፋፋዮች፤ ቅንዝረኞች፣ ስግብግቦች፣ አደራ በሎች፣ ገብጋቦች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ አገር አፍራሾች፣ የዕውቀት ጠላቶች፣ የሥልጣን ጥመኞች፣
ወይስ
ለጋሶች፣ ዴሞክራቶች፣ አገር አልሚዎች፣ የሰብአዊነት ተሟጋቾች፣ የሰላም አባቶች፣ የአንድነት ዋልታዎች፣ የፍቅር ተምሳሌቶች፣ የሕዝብ ጥቅም አስከባሪዎች፣ የድኾች ወዳጆች፣ በጎ አርአያዎች፣ የነጻነት አርበኞች፣ ትዳር አክባሪዎች፣ ታሪክ ጠባቂዎች፣ የመብት ተሟጋቾች፣ ለጋሶች፣ ለእውነት ሟቾች፣
ነገ የኛ የልጅ ልጆች በታሪክ ትምህርታቸው ምን ብለው እንዲማሩን እንፈልጋለን፡፡ ስለዚህ ዘመን ሲነሣ፣ ስለ ፓርቲዎቻችንና አብዮቶቻችን፤ ስለ ድርጅቶቻችንና ማኅበሮቻችን፣ ስለ ትውልዳችንና ምዕራፋችን፣ ስለ ሥልጣን ዘመናችንና የሥራ ጊዜያችን፣ ስለ ምርጫ ጊዜያችንና የሹመት ዘመናችን፣ ስለ ፊልሞቻችንና ድርሰቶቻችን፣ ስለ ሙዚቃ ዎቻችንና ሥዕሎቻችን፣ ስለ መንፈሳዊ አገልግሎታችንና ስብሰባዎቻችን ልጆቻችን ሲማሩ፣ ሲያስቡና ሲነጋገሩ ምን ብለው ስለኛ እንዲነጋገሩ እንፈልጋለን?
እንደ ሂትለርና ሞሶሎኒ እያንገሸገሽናቸው ወይስ እንደ ጋንዲና ማርቲን ሉተር ኪንግ እያስደሰትናቸው? እንደ ካሜር ሩዥና ኤዲ አሚን እየዘገነንናቸው ወይስ እንደ ማንዴላና ማዘር ቴሬዛ እያኮራናቸው?
አይቀርም መቼም፤ እኛ ሌሎችን ታሪክ ናቸው ብለን እንደተማርናቸው ሁሉ፤ እኛ ሌሎችን ለምን እንደዚህ አደረጉ? እንዳልናቸው ሁሉ፤ እኛ ሌሎችን እንዲህ ማድረግ ነበረባቸው እንዳልናቸው ሁሉ እኛም ታሪክ እንሆንና እንታሰባለን፡፡ ነገ የነበርነው ዛሬ እንደሆንነው ሁሉ፣ ዛሬ የነበርነው ደግሞ ትናንት እንሆናለን፡፡ ግን ሞቱልን እንባላለን ወይስ ሞቱብን?
ከመቶ ዓመታት በፊት አንድ ሰው በማለዳው የጠዋት ጋዜጣ ገዝቶ ሲያነብብ ባየው ነገር ደነገጠ፡፡ አንድ ሰው ማረፉን የሚገልጥ የኀዘን መግለጫ የሞቱ ሰዎች በሚወጡበት ዓምድ ላይ ሠፍሮ አገኘ፡፡ እጅግ ያስደነገጠውና የገረመው ደግሞ ሞተ ተብሎ የተዘገበው እርሱ ራሱ መሆኑ ነው፡፡
መጀመርያ ተጠራጠረ፡፡ «እኔ እዚህ ነኝ ወይስ እዚያ ብሎ ራሱን ጠየቀ፡፡ በኋላም ገረመው፡፡ በመጨረሻም እንዴት እንዲህ ሊሆን ቻለ? ብሎ አሰበ፡፡ ዘግይቶ ሲረጋጋ ግን ጋዜጣው በስሕተት ከሌላ ሰው ጋር ስሙን አምታትቶት እንደዘገበው ነገረው፡፡ ዝቅ ብሎ ግን ስለ እርሱ ሞት የተጻፈውን ነገር ለማወቅ ፈለገ፡፡ ለመሆኑ እርሱ ቢሞት ኖሮ ጋዜጦቹ እንዴት ብለው ነበር የሚዘግቡት? እርሱ ለዚች ዓለም እሴት ነው ወይስ ዕዳ? ጥቅም ነው ወይስ ጉዳት? የሚለውን ለማወቅ መልካም አጋጣሚ ተፈጠረለት፡፡ ይህንን አጋጣሚ ሲሞት አያገኘውምና፡፡
ይህ ሰው የኖቤል የሰላም ሽልማት መሥራችና የዲናሚት ፈጣሪ አልፍሬድ ኖቤል ነበረ፡፡ 1888 እኤአ የእርሱ ወንድም ሉድቪግ ዐረፈ፡፡ የፈረንሳዩ ጋዜጣም አልፍሬድ ኖቤል የሞተ ስለመሰለው ጋዜጣው ኖቤልን እያወገዘ ነበር የጻፈው፡፡
አነበበው፡፡
የጋዜጣው ርእስ Le marchand de la mort est mort  «የዲናሚቱ ንጉሥ ሞተ» ይላል፡፡ ቀጥሎም «ብዙ ሰዎችን ከበፊቱ በተሻለ ፍጥነት ለመግደል የሚያስችል መንገድ በመፈልሰፍ ሀብታም ለመሆን የቻለው ዶክተር አልፍሬድ ኖቤል ትናንት ሞተ፡፡» ይላል፡፡ ከዚያም «እርሱ የሞት ነጋዴ ነበረ»ይለዋል፡፡
ጥቅምት 21 ቀን 1833 ዓም እኤአ በስዊዲን ስቶክሆልም የተወለደው አልፍሬድ ኖቤል መሐንዲስ ነበረ፡፡ በመንገድ ግንባታ ወቅት ያጋጥም የነበረውን ታላላቅ ቋጥኞችን የማፍረስ ሥራ ለማቀላጠፍ እኤአ 1866 ዓም ዲናሚት የተባለውን የማፍረሻ ቴክኖሎጂ ፈለሰፈ፡፡ ከዚያም የራሱን ኩባንያ አቋቁሞ ቴክኖሎጂውን በማሻሻል ከፍተኛ ገቢ አገኘ፡፡
በዚህ ሁኔታ እያለ ነበር ያንን በፈረንሳይኛ የተጻፈ ጋዜጣ ገዝቶ ያነበበው፡፡ አልፍሬድ ኖቤል ወዲያውኑ አንድ ነገር አሰበ፡፡ «ለመሆኑ ስሞት ሰዎች እንደዚህ ነው ማለት ነው የሚያስታውሱኝ አለ፡፡ ኖቬምበር 27 ቀን 1895 እኤአ በራሱ ፈቃድ በፈረመው ፊርማ ከድርጅቱ አስፈላጊ ወጭዎች ከተቀነሱ በኋላ ለእርሱ የሚደርሰው ገንዘብ ለሰላም ሕይወታቸውን ላበረከቱ የዓለም ሰዎች እንዲሰጥ ወሰነ፡፡ የኖቤል የሰላም የሽልማት ድርጅትንም መሠረተ፡፡ የሰጠውም ገንዘብ በአሁኑ ጊዜ ወደ 300 ሚሊዮን ሊጠጋ የሚችል ነበር፡፡
እንዳሰበው አልቀረም፡፡ አልፍሬድ ኖቤል የጋዜጦቹን ርእሶች ቀይሯል፡፡ ዛሬ እርሱን ለሰላም ባበረከተው አስተዋጽዖ ዓለም በየዓመቱ ያስበዋል፡፡ ኖቤል የሚለው ስምም ከሰላም ጋር የተያያዘ ስም ሆኗል፡፡
ትናንት የዕለት ኑሯቸውን ብቻ አስበው እጅግ ክፉ የሆነ ተግባር የሠሩ ሰዎች ዛሬ እንደገና ከመቃብር ቢነሡ የመጀመርያ ተግባራቸው የሚሆነው ስማቸውን የሚያድስ ሥራ መሥራት ነው፡፡ በየጋዜጣውና በየመጽሔቱ፣ በየኢንሳይክሎፒዲያውና በየመዝገበ ቃላቱ፣ በየፊልሙና በየሥዕሉ፣ በየፖስተሩና በየፎቶ ግራፉ ስለ እነርሱ ምን እንደ ተባለ ቢያዩ ኖሮ መፈጠራቸውን በጠሉት ነበረ፡፡
የሚዘገንን ሥራ ሠርተው የሚያስደስት ሐውልት የተከሉ ነበሩ፣ በሕዝቡ ላይ መከራ አዝንበው በመሬት ላይ ወርቅ ያነጠፉ ነበሩ፡፡ ነገር ግን እነርሱ ሲያልፉ ክፉ ስማቸው ደጉን ሥራቸውን እንኳን ሊያቆየው አልቻለም፡፡ እነርሱ በምድር ላይ እንጂ በሰው ልቡና ውስጥ የተከሉት ሐውልት አልነበራቸውምና፡፡
አንዳንዶቹ ለእውነት፣ በእውነት ታግለው ስንዝር መሬት አጥተው በበረሃ ሞተዋል፡፡ በሰው ሀገር ተቀብረዋል፡፡ ነገር ግን ካረፉ ከመቶ ዓመታት በኋላ እንደ አቡነ ፊልጶስና እንደ ዮሐንስ አፈወርቅ ዐፅማቸው በክብር ተመልሷል፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ በሕይወታቸው በክብር ነግሠውና ተከብረው ሲያርፉ ግን ዐጽማቸው ወጥቶ ተቃጥሏል፡፡
ሰውን ሰው ከሚያሰኙት ነገሮች አንዱ ለዝክረ ሀልወቱ (legacy) ማሰቡ ነው፡፡ የኔ፣ ያንተ፣ ቺ፣ የእኛ፣ የእናንተ፣ የእናንቺ ዝክረ ሀልወታችሁ ምን ይሁን? ነገን ነገ መወሰን እንችልም፡፡ ስለማንኖር፡፡ ነገን ግን ዛሬ መወሰን እንችላለን፡፡ በሰው ልብ የሚቆም የበጎ ሥራ ሐውልት በመ፡፡
የትናንቶቹ ለዛሬ አልቻሉም፤ የዛሬዎቻችንስ ለነገ፡፡
ሳንሆዜ፣ ካሊፎርንያ
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ በመሆኑ በተመሳሳይ ኅትመት ላይ ባታውሉትይመረጣል፡

27 comments:

 1. ዛሬ ላይ ነገየን እንዳስብ ከተኛሁበትም እንድነቃ ስላደረከኝ እጅግ በጣም አመሰግንሃለሁ ።እግዚአብሔር ይስጥህ ።በጥዋት በትክክለኛው ሰዓት ከእንቅልፌ ነቃሁኝ ። እናንተስ?!

  ReplyDelete
 2. kala heiwate yasamalen

  ReplyDelete
 3. ዳኒ እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልህ። ይህን ጥበብ የገለጸልህን አምላክ ሳታሳዝነው ለሰማያዊው ክብር እንድትበቃ አምላክ ይርዳህ። በእርግጥ እኛ ተራዎቹ ምእመናን የምንመኘው ተርታ ኑሮ ኑረን ንሰሓ ገብተን ሰማያዊውን ርስት ለመውረስ ብቻ ነው። ነገር ግን አንተን የመሰሉ ለመጪው ትውልድ ሊተርፍ የሚችል ሥራ በመስራት ላይ ያላችሁ ወገኖች የምትችሉትን ሁሉ በማድረግ የህይወት ታሪካችሁን ገጾች ላለማበላሸት ብትጠነቀቁ መልካም ነው። እንደ ኖቤል ያለ ዕድል ሁሉችንም የለንምና። ሐዋርያው እንዳለው ''..ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ'' ና!
  እስቲ አንተም የጀመርከውን መንፈሳዊ ጎዞ ጠብቀህ ለሰማያዊውለክብር እንድትበቃ የቅዱሳን አምላክ ይርዳህ፤

  ReplyDelete
  Replies
  1. እግዛብሔር ይስጥልኝ፡ Mr. Anonymous

   Delete
 4. ቃለ:ሕይወትን:ያሰማልን:ዲ/ዳኒ:እግዚአብሔር:ጸጋውን:ያብዛልህ

  ReplyDelete
 5. Shalom!
  Thank you for presenting a balanced blend of the 19th cent. scientific legacy and the benefits of the good deeds of contemporary people(21st cent.) might lead to psychological boost up for future generation.
  But legacy, as you nicely put it,requires selfless, uncorrupted, unbiased,... mind set up.

  ReplyDelete
 6. DES YEMIL TSUHUF NEW. AND NEGER GN ALE... TARIK METAWES YEMIGEBAWN ENJI HULUNM AYASTAWSM....

  ReplyDelete
 7. የሰው ዝክረ ሃውልቱ መልካም ሥራው ነው፡፡ በመጥፎ መነሳቱ ደግሞ ለቤተሰቡና በዙሪያው ላሉት ሁሉ ሃፍረት ነው፡፡ ስለዚህ ስምን ለትውልድ በመልካም ለማስነሳት ክፉነትን ወርውሮ ጥሩ ሰው መሆን ይጠቅማል፡፡ እንደ አልፍሬድ ሳንሞት ምልክት ላናገኝ እንችላለንና «የዲናሚቱ ንጉሥ ሞተ»፡፡
  ዲ/ን ዳንኤል መልካሙን ሁሉ ያሰማህ

  ReplyDelete
 8. ትናንት የዕለት ኑሯቸውን ብቻ አስበው እጅግ ክፉ የሆነ ተግባር የሠሩ ሰዎች ዛሬ እንደገና ከመቃብር ቢነሡ የመጀመርያ ተግባራቸው የሚሆነው ስማቸውን የሚያድስ ሥራ መሥራት ነው፡፡
  Mamush,MN

  ReplyDelete
 9. weyne dn.danial endet lebe yemineka neger new ene ahununu ermja lewsed eytenesahu new belu leften

  ReplyDelete
 10. የትናንቶቹ ለዛሬ አልቻሉም፤ የዛሬዎቻችንስ ለነገ፡፡

  ReplyDelete
 11. እግዚአሔር ይስጥልኝ መምህር. . እድምህን ያርዝመው

  ReplyDelete
 12. THIS IS EXCELLENT ARTICLE! WE ALWAYS EXPECT FROM YOU THIS KIND OF WRITING, NOT LIKE SOME OF .....YOU KNOW IT.

  ReplyDelete
 13. ሳሚ (ወ/ሚካኤል)June 23, 2012 at 3:12 PM

  ጆሮ ያለው ይስማ!!!!!!!!!!!!!!! ዲ/ዳኒ እግዚአብሄር አምላክ በትውልድ ሁሉ መልካም ሃውልትን በስምህ ይትከልልህ!!!

  ReplyDelete
 14. ሳሚ (ወ/ሚካኤል)June 23, 2012 at 3:14 PM

  ጆሮ ያለው ይስማ!!!!!!!!!!!!!!! ዲ/ዳኒ እግዚአብሄር አምላክ በትውልድ ሁሉ መልካም ሃውልትን በስምህ ይትከልልህ!!!

  ReplyDelete
 15. thank you ,dani for all your progress till now,thank you!

  ReplyDelete
 16. "Strength, rest, guidance, grace, help, sympathy, love - all from God to u!! What a list of blessings!"

  ReplyDelete
 17. ዳኒ እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልህ። ይህን ጥበብ የገለጸልህን አምላክ ሳታሳዝነው ለሰማያዊው ክብር እንድትበቃ አምላክ ይርዳህ።

  ReplyDelete
 18. It is really very nice article.you are adding something valuable on every other day,so please don't give up.

  ReplyDelete
 19. d/n daniel tebarek egzeabher yibarkh

  ReplyDelete
 20. ዳኒ እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልህ። ይህን ጥበብ የገለጸልህን አምላክ ሳታሳዝነው ለሰማያዊው ክብር እንድትበቃ አምላክ ይርዳህ። በእርግጥ እኛ ተራዎቹ ምእመናን የምንመኘው ተርታ ኑሮ ኑረን ንሰሓ ገብተን ሰማያዊውን ርስት ለመውረስ ብቻ ነው። ነገር ግን አንተን የመሰሉ ለመጪው ትውልድ ሊተርፍ የሚችል ሥራ በመስራት ላይ ያላችሁ ወገኖች የምትችሉትን ሁሉ በማድረግ የህይወት ታሪካችሁን ገጾች ላለማበላሸት ብትጠነቀቁ መልካም ነው። እንደ ኖቤል ያለ ዕድል ሁሉችንም የለንምና። ሐዋርያው እንዳለው ''..ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ'' ና!
  እስቲ አንተም የጀመርከውን መንፈሳዊ ጎዞ ጠብቀህ ለሰማያዊውለክብር እንድትበቃ የቅዱሳን አምላክ ይርዳህ፤

  ReplyDelete
 21. We need to be careful for not registering our name in earth,rather we need strive to hard for putting our name in heaven archive! Please God helps us!

  ReplyDelete
 22. thank you for the pearl of wisdom you have shared with us.

  ReplyDelete
 23. kale hiwoten yasemalin

  ReplyDelete