Saturday, June 16, 2012

ቢደርስባችሁ ምን እርምጃ ትወስዳላችሁ

click here for pdf 
ዲ/ን ዳንኤል ሰላምና ጤና ከነቤተሰቦችህ እየተመኘሁ

ይህቺን አጭር ጽሁፍ ለአንባቢያን አስተያየት እንዲሰጡበት ታደርግልኝ ዘንድ በመተማመን ነው፡፡

እኔ በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ ሠራተኛ ስሆን ባለቤቴ የመንግሥት ሠራተኛ ነው፡፡ እኔና ባለቤቴ የ4 ልጆች የአብራካችን ክፋዬች አሉን ፡፡ ከጥቂት ዓመታት ጀምሮ  ቤታችን  ሰላም በማጣት ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንገኛለን፡፡  ቤቴንና ልጆቼን ጥዬ እንዳልወጣ በልጆቼ ላይ የሚደርሰው የሥነ ልቦና ቀውስ ከባድ መሆኑ ይታየኛል፡፡ ሁሉን ችዬ ልኑር ብዬ ሳስብ እስከመቼ ሰው በአንድ ጣሪያ ሥራ እየኖረ ቢያንስ ስለልጆች ጉዳይ እንኳን ሣይነጋገር ለዓመታት ይቻላል፡፡ 

ልጆቼ በእርግጥ አሁን በትምህርታቸው ዩኒቨርሲቲ ደረጃ የደረሱ ናቸው፡፡ ልጆቹ ትምህርታቸውን እስኪጨርሱ ድረስ ልቻልና ላስጨርስ  ብል የማየው ነገር ማለት በር ዘግቶ መቀመጥ፣ ምግብ መኝታ ቤት ድረስ እየተወሰደለት እኔ የሠራሁትን እየበላ እኔን ለዓይኑ እየጠላ የሚያደርገው ነገር እኔን በጣም እያበሳጨኝ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ዝምታ ወርቅ አይደለም በሚል ርዕስ በተጻፈው ሥር የኔን ቤት አስቀምጬ ስመለከተው እስከመቼ ድረስ ልቀጥል እችላለሁ የሚል መልስ የማላገኝለት ጥያቄ  ያስጨንቀኛል፡፡

ተነጋግሬ ያለብንን ችግር የመፍታትም ሆነ የመለያየት ነገር የሚኖረው የቤቱ ምሰሶዎች ሲነጋገሩ ብቻ መሆኑ በእርግጠኝነት ባምንበትም ከሱ በኩል ግን የማገኘው ምላሽ ምንም የለም ለመነጋገርም ፈቃደኝነት የለም፡፡ ይህ ሊሆን የቻለበት ምክንያት ምንድነው ብትሉኝ እባክህ ለቤታችን ሰላም የማትሰጥ ሴት ገብታለችና ከሷ ጋር ሌላ ግንኙነት ባይኖርህም ከሥራ ስትወጣና ስትገባ በሰፈር ውስጥ መታየት ለኔም ሆነ ለአንተ በአጠቃላይ ለቤተሰባችን  እዚህ ጋር ልብ እንድትሉልኝ የምፈልገው /ሴትየዋ ባል የሌላት በመሆኗ ነው/ ጥሩ ባለመሆኑ በአንድ ሠርቪስ ብትጠቀሙም አብረህ አትታይ አትውጣ አትግባ ብዬ በመናገሬ ይኸው ለ3 ተከታታይ ዓመታት ቤቴ ሰላም አጥቶ ልጆቼም ግራ እንደገባቸው ይገኛሉ፡፡

 ሶስቱ የተሳሳቱ ምዕራፎች የሚለውን ሰኔ 8/2012 የጻፍከውን አንብቤ እስኪ ይሄ የሚመልሰው ከሆነ ላድርገው ብዬ ከራሴ ጋር ብነጋገርም ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ጊዜ እባክህ ቤታችን አይበተን ልጆች ጐዳና አይውጡ ይሄንን ኩርፊያህን ትተህ ወደነበርንበት ሰላማዊ ኑሮ እንመለስ ብዬ ይቅርታ የጠየቅሁ በመሆኔ ድርጊቱን ለመፈጸም ጭራሽ ተሸናፊነት ሆኖ ነው የተሰማኝ፡፡ ከዚህ በሚተርፈው ግን ከሴትየዋ ጋር ያለህን መውጣትና መግባት ግን እንዲተው ያደረኩት ይሄው ኩርፊያው ምክንያት የሆነችው ከሷ ጋር ሲሄድና ሲመለስ ምንም ዓይነት የመናደድም ሆነ የማኩረፍ ጸባይ ስለማላይበትና እኔ ላይ ይሄንን ድርጊት በማድረጉ በመሆኑ  ነው እንጂ ያየሁትም ሆነ የሰማሁበት ሌላ ጸባይ ኖሮ አልነበረም፡፡

ይህ የመቀራረብ ነገር ምናልባትም አዝማሚያው ወደማልፈልገው አቅጣጫ ሄዶ ከዚህ በባሰ ሁኔታ ራሴን እንዳልጐዳ በሚል እንጂ አድርጓል ብዬ እርግጠኛ የምሆንበት ምንም ማስረጃ በሌለኝ እሱን ለመወንጀል ራሴን ንጹህ ለማድረግ ብዬ አይደለም፡፡ አሁን በቤት ውስጥ  ያለን ግንኙነት የጠላት ያህል እንጂ እውነት ልጆች አፍርተን ክፉ ደጉን ተነጋግረን ተሳስቀን ያሳለፍን ሰዎች አንመስልም፡፡  ልጆች ገብተው እንዲያወያዩን ባደረኩት ጥረት ጭራሽ ልጆቹ ላይ የጥላቻ ስሜት የወገናዊነት ስሜት ያሣዩ አድርጐ ስላሰበው በዚህ ጉዳይ ዳግመኛ እንዳይገቡ እኔም እነሱም ወሰኑ፡፡ በሃይማኖቴ የኦርቶዶክ ሃይማኖት ተከታይ ነኝ ጉዳዩን ወደ አባቶች ሊመክሩት ቢሞክሩም ስልኩን ለመመለስ ፈቃደኛ ባለመሆኑ እነርሱን ይቅርታ ጠይቄ ተውኩት፡፡ እስኪ እንዲህ ዓይነቱ ነገር ቢደርስባችሁ ምን እርምጃ ትወስዳላችሁ፡፡

ከአዳማ

66 comments:

 1. ይህ ሰው አንድ የሚያስጨንቀው ነገር እንዳለ ይገባኛል፡፡
  አራት ልጆች አሏቹህ ማለት በእድሜም በልምድና ተመክሮም ብዙ የሚያውቅ ሰው መሆን አለበት እላለሁ፡፡ ካንች ከሚስቱ እና የልጆቹ እናት ጋር ተዘጋግቶ ሶስት አመት መቁየት ማለት ውስጡ በብርቱ የተረበሸ ሰው መሆኑን እረዳለሁ፡፡ አንድም በብርቱ ሁኔታ አስቀይመሽዋል፡፡ ወይ ደግም ሊመለስ የማይችልበት ጥፋት ውስጥ ገብቷል ማለት ነው ብየ እንዳስብ ያደረገኛል፡፡ የህን አምኖ ለመቀበልም ዝግጁ ባመሆኑ ማለት አልታይህ ያለው ጉይ አለ፡፡ ሆኖም ግን አንች የሰራሽውን ምግብ መኝታ ክፍል እየበላ የምትኖሩ መሆኑን ገልጸሻል፡፡ ሊያይሽ የማይፈልግ መሆኑን ገልጸሻል፡፡ ምናልባት በጠረጠርሽው ጉዳይ ነዝንሽው ይሆን? አብሮ ምብላታችሁስ እምን ድረስ ነው ?ማለቴ በምትበሉት እና በምትተኙበት ጊዜ በተለይ የሚጠጣ ከሆነ ጠጥቶ ደስ በሚል ስሜት ውስጥ በሚገኝበት ጊዜ ነገሩን ቀለል አድርገሽ ስለጉዳዩ ቀጥታ ሳትገቢ ጥሩ ነገር ብታሳይው ወይም ድስ የሚል ስሜት እንዳለው እና ደስ ሲለው አንቸንም እንዳስደሰተሸ (የእውነት ባይሆንም) ገልጸሸለት ወሬ ብታስጀምሪው ብዙ ሊያወራሽ ይችላል፡፡ ያስቀየምሽው ካለም ሊነግርሽ ይችላል፡፡ ያንችን መጥፎነት ወይም ደግነት ጥሩነት ላውራት ይዳዳዋል፡፡ ስለአደረግሽው ነገር ሁሉ ሊነግርሽ ይችላል፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ ብቻችሁን መሆንን ይመርጣል፡፡
  ዋናው ጉዳይ ባንድም ሆነ በሌላ መንገድ ሁለታችሁ የምትነጋገሩበትን ስልት ማግኘት ነው፡፡ ማናገር ከጀመረም አንች በእሱ ላይ ያለሽን ጥርጣሬ ፈጽመሽ ማስወገድ አለብሽ፡፡ሲነግሽም መቶ በመቶ ስሚው፡፡አንች እራስሽ ከሴትዮዋ ጋር ስላለው ጉዳይ መረጃው እንደሌለሽ ገልጸሻል፡፡ በዚህ ሁኔታም ስለ እሷ ማንሳት የለብሽም፡፡ሲገባና ሲወጣ መልካም ፊት አሳይው፡፡ ሙሉ በሙሉ እምነት( በአሱ ላይም ሆነ በራስ መተማመን አሳይው) ያለሽ መሆኑን ይወቅ፡፡ እራስሽ ከሱ በማስበለጥ ተዋቢ ( ስልሽ ከነበረሽ ነገር አንጻራዊ ሆኖ አንሰሽ ግዴለሽ ሆነሽ አትታይው፡፡ በሌላ በኩል እሱ አንችን የማይጠራጠርም ይሁን፡፡ በጠቅላላው ፍቅር ለግሽው፤ ፍቅር መግቢው፤ ተንከባከቢው በጠረጠርሽው ጉዳይ ምክንያት የተለየ ፊት አታሳይው፤ የጠረጠርሽው መስሎ ከታየው አሁንም ከመዝጋት አይመለስም( አደረገውም አላደረገውም)፡፡ ለመሆኑ ከልጆቻችሁ የትኛውን ይወዳል ወይ ደግሞ በተሻለ ይቀርባል? በሚወደው ልጁ አማካኝነት ገመናው ሳይወጣበት ለምን እንደዘጋሽ ልጁ ማናገር ይችላል፡፡ ይህ እንድትነጋገሩ በር ከፋች ነው፡፡ ያሉሽን አማራጮች ሁሉ ተጠቀሚባቸው፡፡ ይህ ጉዳዩን ቀላል ያደርገዋል፡፡ ለማኝኛውም አንች ሁሉም ነገር( መጥፎውና የጠረጠርሽው) አንዳልሆነ ሁልጊዜ አስቢ፡፡ ማስረጃው ካለሽ ግን እሱን የሚቀርበውን ሰው በመያዝ ጉዳዩን እልባት መስጠት የመጨረሻ ውሳኔ ይሆናል፡፡ እንዲመለስ የሚደረገው ጥረት የሚጀምረው ጉዳዩ እውነት መሆኑ በቅድሚያ ሲታወቅ ነው፡፡ ጉዳዩም በሰውና በህግ ያልቃል፡፡
  እግዚአብሔር ይርዳሽ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. "tidar" malet yefelegutin menor aydelem yegara yehone hiywot memesret enji tidar degmo yand genber gojo aydelem behidet yemigeneba enji, hulum rasun endemewudedu lerasu yadelal misretawu lay kezih yeweta neger algetemachihum. atirshi tertireshiwal, kemiwedewu neger kelkileshiwal,... wedyawu bedesita laykebelewu yichilal manim bihon layikebelewu endemichil, meterter demo yamal leziyawu bemitiwedewu mistu, beza lay beset. ebakish teregagina hulun betigist adirgi e/r kenante gar yihun.

   Delete
 2. Subae Gibina Tidarachihun Asmermiri Beka Lela Minim Yelem!
  (Aemiro)

  ReplyDelete
 3. yenegerutn yemayresa yeteyekutn ymaynesa AMLAK yredashal. atbkesh lemgniw. teyiku yisetachihual........... teblualna. EMBETE trdash.

  ReplyDelete
 4. ፍስሐ -ሲያትልJune 16, 2012 at 10:23 AM

  ታሪክሽ በጣም ያሳዝናል ትዳርን የሚያክል ትልቅ ሀገር መሪ ሲያጣ ቤተሰቡ ሲታወክ በልጆች ባንዲራ የማንነት ቀለም ማንትን ከለዩ በዋላ ራስን ሲያስጎድፍ ምን የከፋ ውርጅብኝ በባልሽ ልብ ውስጥ ተሸንቁሮ ለውይይትም የማይጋብዝ ሰላምን ለምን ጠላ?ያቺ ያልሻት ሴት በድግምት ትብታብ አስራበት ይሆን?3 አመት አይደለም ሁለት ቀንስ ትዳርን ሳያወሩ እንዴት ከስራ ተውሎ ቤት ይገባል?ምንስ ሆድ አለና ተበልቶ ይታደራል።እግዚሃብሔር ስለ ልጅዎችስ ሲል ያንቺን መከራ በጥበቡ ይፍታልሽ ብቻ ነው የምለው።

  ReplyDelete
 5. በቅድሚያ ሰላመ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ይሁን ፤፤ በመቀጠል fire proof የሚለውን ሙሉ ፊልም ተመልከቺዉ፤፤you can get this movie on you tube....dont ever ever treat your marriage by divorce

  ReplyDelete
  Replies
  1. ...DONT EVER EVER TREAT YOUR MARRIAGE BY DIVORCE...

   Delete
 6. እኔ በበኩሌ ግራ የገባኝ የሱ የቤተ ክርስቲያን አያያዙ እንዴት ነው የሚለው ነው፡ ቤተክርስቲያን የሚከታተልና የትዳርን ክቡርነት የሚያውቅ ቢሆን መቼም አባቶች ላይ ስልክ ይዘጋል ብዬ አላስብም። በተረፈ ግን እስኪ ለጊዜው ዞር ብለኝ በጸሎት እየተጋሽ ቆዪ፡ ከመሄድሽ በፊት ግን የሚቀርበው ሰው አፈላልገሽ ያለው ሀሳብ ምን እንደሆነ፣ አንቺ ዞር በማለትሽ የተሰማውን ስሜተና መሰል ነገሮችን እንዲያጠናልሽ ማድረግ አለብሽ ባይ ነኝ። ከዛም በኋላ ያገኘሻቸውን እነኝህንና መሰል መረጃዎችሽ አዎንታዊ ከሆነ ለማስፈራራት ያደረገው ኩርፊያ ሜሆሆኑን ተገንዝበሽ ግንኙነታችሁን ማደስ በተቃራኒው አሉታዊ ከሆነ ግን አባቶችን አማክረሽ መውሰድ የሚገባሽን እርምጃ መውሰድ ነው። ባልና ሚስት ተብሎ ለዚህ ሁሉ ግዜ ተዘጋግቶ መኖር ከሸክም በላይ የሚከብድ እንደሆነ ይሰማኛል።
  በተረፈ ትዳርን ባርኮ የፈጠረ አምላክ ድካምሽን አይቶ ይጎብኝሽ።

  ReplyDelete
 7. yalshiw hulu ewnet kehone kanchi mitebekewun argeshal silezih yalesh amarach beselam meleyayet bicha new aliya yekefa dereja eskiders metebek yelebishim lijochunim bihonu lemasamen mokiri bewala anchina esu tetaltachu kemimetaw xexet ahun beselam teleyaytachu esum wedefelegebet yihid andiken yixexitew yihonal yeseraw sira anchi gin minim athongim egziabhare kanchi gar ale.

  ReplyDelete
 8. እርስዎም ሳይጸልዩ ቀርተው ባለቤትዎ በዝሙት ሀጢያት ቢወድቁ ተጠያቂ ከመሆን አያመልጡም፡፡
  እናት ለደረሰብዎ ችግር አዝናለሁ፤ ከራሴ ልምድ በመነሳት ለደረሰብዎ ችግር መፍትሄ ነው የምለውን እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡ እኔ በቂ የሆነ የገቢ ምንጭ አለኝ ፤ መልክና ቁመናዬም የተስተካከለ ነው ነገር ግን እንደ ዘመኑ ወጣቶች የሴት ጋደኛ ስለሌለኝ/ከሴት ጋር ለማመንዘር ዕድሉን ስላላገኘሁ/ ሁል ጊዜ እራሴን ጎዶሎ አድርጌ እቆጥር ነበረ ፤ ከረጅም አመታት በኃላ ታላቅ እህቴ እና አክስቴ ደብዳቤ ላኩልኝ መልዕክቱ በአጭሩ እንዲህ ይላል፤ ወንድማችን አንተ በዝሙት ሀጢያት እንዳትወድቅ ሁል ጊዜ ማታ ማታ ስለአንተ እንጸልያለን፡፡ እኔ ባለማወቅ ስመኘው የነበረን ክፉ ስራ እህቴ እና አክስቴ እኔን ለማዳን ተዋግተው ሲያሸንፉ አዩ አይደል፡፡ አዎ እርስዎም ሳይጸልዩ ቀርተው ባለቤትዎ በዝሙት ሀጢያት ቢወድቁ ተጠያቂ ከመሆን አያመልጡም፡፡
  እኛ የምናመልከው የሚሰማንን እምላክ መሆኑን በጸሎት ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡ ፈልጉ ታገኛላችሁ፤ ጠይቁ ይሰጣችኃል ይላል መጽሐፉ፡፡

  ReplyDelete
 9. the sources of conflict is diablos so you have to go one monastry and pray for 7 days inorder to bring the past peace then give for god he give appropriate remedy

  ReplyDelete
 10. yene ehete 3 amet mulu moteshale woy setasebiw balesh anchine biwodesh 3 amet mulu yakorefeshale woye bayehone ke 1 wey 3 wor behuwala tenegagerachehu gudaune mefetate neberebachehu ene yemeleshe lejochesh adegewale anechime sira aleshe baleshe yefelegesh weye ayfelegesh endehone bequme neger teyeqewi weye aseteyeqiwe enbie kale kemayewedeshe sew gare mine taderegiyalesh wesanewene anchi erasesh weseteshen adameteshe wesegni wey cheleshe nuri weye cheleshi wechi

  ReplyDelete
 11. ውድ ዳኒ
  መፍትሄ የሚያስፈልጋቸው ማኅበራዊ ችግሮቻችን እኮ ብዙ ናቸው:: በዚህ መንገድ ባትገባባቸው እመርጣለሁ ባይሆን እህታችን እንደጠቋቆመቻቸው ያሉ በረከቶችህን ብታወርድ:: በየቤቱ የምንሰማቸው ታሪኮች እኮ አሳዛኝ ናቸው:: ለነገሩ በ15 ደቂቃ ስብከት ከሚመሠረቱ ትዳሮች ምን እንጠብቃለን? እህታችን የደረሱ ልጆቿ እንኳን ሊፈቱት ያልቻሉት ችግር በጓዳዋ ይዛ በትእግስት እየኖረች ነው:: እንዲህ ያለው በማንም አይድረስ

  ኦርቶዶክሳዊነሽና እናቴን ገጥሟት የነበረውን ተመሳሳይ ችግር የፈታችበትን መንፈሳዊ መንገድ ልጠቁምሽ:: አንቺ የሄድሽበትን መንገድ ሁሉ ሂዳ መፍትሄ ባጣች ጊዜ ወዳጆቿ ዘመድ ጎረቤቱ ሁሉ ጠንቋይ እንድታማክር ይጎትታት እንደ ነበር አስታውሳለሁ::

  በወቅቱ በታላቅ ወንድማችን ይመራ የነበረ ሳምንታዊ የቤተሰብ የጽሎት መርሐ ግብር ነበረን:: አባታችን በዚያም ላይ መገኘቱን በማቆሙም ተከፍተን ነበር:: እናቴ ግን በጥንቃቄ የምታደርጋቸውን ነገሮች ዛሬ ሳስባቸው ልጆቿ ባለ ዲግሪዎች እንጂ ባለ መፍትሄዎች አልነበርንምና እደነቃለሁ::

  በሥርዓት ክልክል ሊሆን ይችላል ግን እናቴ ደጋግማ ስታደርገውና ለውጥ ሲያመጣ በዓይኔ አይቻለሁ:: እንደራትና ምሳው ሁሉ የአርብ ጽሎት ጸበል መኝታ ቤቱ ይጠብቀዋል:: አባቴ አንድ ቀን ጸበል እያላችሁ መርዝ ብትግቱኝስ ከዚህ በኋላ አልፈልግም ብሎ ሲናገር እናቴ መልስ አልሰጠችውም ነበርና በጣም ተቆጥቼ ተናገርኩት:: እናቴ የዚያን እለት የተናገረችን ነገር አለ:: አባትሽን እንዲህ መናገር አይገባሽም ደግሞም አትጠቅሚውም:: ወዶ ይመስልሻል ልጆቹን ያስጠላው? ምን ክፋት ነበረበት ከኛ መነጋገሩ? ጸሎት ማድረግ የከለከለው ጸበል እንዲቀምስ ይፈቅድለታል እንዴ? አሁን በሚያደርገው ነገር ልናዝንለት እንጂ ልናዝንበት አይገባም... ብዙ አለችኝ:: ይህንን ግን መቼም ልረሳው አልችልም:: ከዚያ በኋላ አርብ አርብ እራቱ ጋር የሚቀርበው ውኃና ማባያ ዳቦው ጸበል እንደነበር አውቃለሁ:: አንድ ምሽት አባዬ ለጸሎት ከኛ ጋር ቆሞ እንደነበር ያየሁት ጨርሰን ስንቀመጥ ነበር:: ጸበሉን ሳዞር ለርሱም እየፈራሁ ሰጠሁት ተቀበለኘና ቆመ:: ልጆቼ ይቅር በሉኝ ባለ ማወቅ በድያችኋላሁ:: እናታችሁ ይቅር እንድትለኝ እናንተ አማላጅ ሁኑኝ:: እያለ እግሯ ላይ ወደቀ::ሁላችንም ደስ እያለን አለቀስን::

  ጸሎታችን ለማን ነው? አንተ እንድትመለስ ወደከፋ ነገር እንዳትሄድ አደለም እንዴ? ይቅር ብለንሀል እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ:: አለችው እናቴ:: አግብቼ ከናቴ ቤት እስክወጣ የቤተሰባችንን የጽሎት ጊዜ በምንም አልለውጠውም ነበር:: ለዚህ እርቅ መታሰቢያም እናቴ በየዓመቱ ሕዳር 12 ቀን የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤልን ዝክር ታደርጋለች:: ጸሎታችንን ቸል ያላለ አምላክ ክብር ምስጋና ይግባው:: እህቴ እግዚአብሔር ያልፈታውን ችግር ሰው አይፈታውም:: እናቴን የረዳ ይስማሻ::
  ካንቺወዲያ /ክአዲስ አበባ/

  ReplyDelete
 12. Sele E/ber belesh tegtesh tseleyi

  ReplyDelete
 13. the husband, please forgive her i total agreed she is on the right track, simply you need to give her peace and love, she might be wrong to speak out however it is why she concerned the situation, please give her love. the more you approach her the more you are showing responsibilities to your family. please forgive !

  ReplyDelete
 14. it is good if u pray to God contentiously. may be it is the way u will be tested how much u love your husband. u see he may be in a big misunderstanding on u. and tell fathers to remember ur family in their daily prayer.
  and if there is something on u again see your self properly. let God help u and family.

  ReplyDelete
 15. Kedose Mekaiel yeredashe.
  eske egame batsalote eneredate.
  Egizeabehare yemarawe.
  amen

  ReplyDelete
 16. Here is my comment and suggestion:

  1. It's sad that you resort to a blog to find a solution for your marital problem. It's an indication that you're not very respectful of your marriage, your husband, your family, and your faith.

  2. Please use the power of prayer.

  3. As per our society's well known conflict resolution mechanisms, find an appropriate person (Shimagllae) to talk to your husband or, better still, to arrange a peace-making discussion between you and your husband.

  4. If your children are at least 18 years old, they could be of help in achieving peace and stability in the family.

  5. Please keep on trying to have a sober, calm and peaceful discussion with your husband.

  My very best wishes.

  ReplyDelete
  Replies
  1. HEllo,

   What do u mean u don't respect ur marriage? If u read what she has wrote,she is staying with her husband without peace for 3 years to give it a chance.This shows her respect and her commitment for her marriage.She has told u,how she tried Shimagiles,her kids but nothing worked.U need to put ur self in her shoes.I only agree with one of your thing which is PRAYER.Let Lord's will happen to her and the family.

   Delete
  2. Is this advise??

   Please think what you are writing. Put yourself on the person's foot before you judging.this women tried her best before she coming out with her problem. Please don't advice something like "besew qusil enchet sidedbet" thanks.

   By the way, I have similar problem, and I was trying to learn something from here.

   Delete
 17. Dear Sister!
  Please day and night pray to the Almighty God, He will give you a solution for your problems. He is the only one gives you a solution to your problem and pease on your marriage. You have to be fully committed to your prayer and keep asking His guidance to sort out all the problems you are facing in your marriage. My family and myself are promised to remember you during our prayer.
  May God be with you.

  ReplyDelete
 18. nigusie dz
  ይህ ሰው አንድ የሚያስጨንቀው ነገር እንዳለ ይገባኛል፡፡
  አራት ልጆች አሏቹህ ማለት በእድሜም በልምድና ተመክሮም ብዙ የሚያውቅ ሰው መሆን አለበት እላለሁ፡፡ ካንች ከሚስቱ እና የልጆቹ እናት ጋር ተዘጋግቶ ሶስት አመት መቁየት ማለት ውስጡ በብርቱ የተረበሸ ሰው መሆኑን እረዳለሁ፡፡ አንድም በብርቱ ሁኔታ አስቀይመሽዋል፡፡ ወይ ደግም ሊመለስ የማይችልበት ጥፋት ውስጥ ገብቷል ማለት ነው ብየ እንዳስብ ያደረገኛል፡፡ የህን አምኖ ለመቀበልም ዝግጁ ባመሆኑ ማለት አልታይህ ያለው ጉይ አለ፡፡ ሆኖም ግን አንች የሰራሽውን ምግብ መኝታ ክፍል እየበላ የምትኖሩ መሆኑን ገልጸሻል፡፡ ሊያይሽ የማይፈልግ መሆኑን ገልጸሻል፡፡ ምናልባት በጠረጠርሽው ጉዳይ ነዝንሽው ይሆን? አብሮ ምብላታችሁስ እምን ድረስ ነው ?ማለቴ በምትበሉት እና በምትተኙበት ጊዜ በተለይ የሚጠጣ ከሆነ ጠጥቶ ደስ በሚል ስሜት ውስጥ በሚገኝበት ጊዜ ነገሩን ቀለል አድርገሽ ስለጉዳዩ ቀጥታ ሳትገቢ ጥሩ ነገር ብታሳይው ወይም ድስ የሚል ስሜት እንዳለው እና ደስ ሲለው አንቸንም እንዳስደሰተሸ (የእውነት ባይሆንም) ገልጸሸለት ወሬ ብታስጀምሪው ብዙ ሊያወራሽ ይችላል፡፡ ያስቀየምሽው ካለም ሊነግርሽ ይችላል፡፡ ያንችን መጥፎነት ወይም ደግነት ጥሩነት ላውራት ይዳዳዋል፡፡ ስለአደረግሽው ነገር ሁሉ ሊነግርሽ ይችላል፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ ብቻችሁን መሆንን ይመርጣል፡፡
  ዋናው ጉዳይ ባንድም ሆነ በሌላ መንገድ ሁለታችሁ የምትነጋገሩበትን ስልት ማግኘት ነው፡፡ ማናገር ከጀመረም አንች በእሱ ላይ ያለሽን ጥርጣሬ ፈጽመሽ ማስወገድ አለብሽ፡፡ሲነግሽም መቶ በመቶ ስሚው፡፡አንች እራስሽ ከሴትዮዋ ጋር ስላለው ጉዳይ መረጃው እንደሌለሽ ገልጸሻል፡፡ በዚህ ሁኔታም ስለ እሷ ማንሳት የለብሽም፡፡ሲገባና ሲወጣ መልካም ፊት አሳይው፡፡ ሙሉ በሙሉ እምነት( በአሱ ላይም ሆነ በራስ መተማመን አሳይው) ያለሽ መሆኑን ይወቅ፡፡ እራስሽ ከሱ በማስበለጥ ተዋቢ ( ስልሽ ከነበረሽ ነገር አንጻራዊ ሆኖ አንሰሽ ግዴለሽ ሆነሽ አትታይው፡፡ በሌላ በኩል እሱ አንችን የማይጠራጠርም ይሁን፡፡ በጠቅላላው ፍቅር ለግሽው፤ ፍቅር መግቢው፤ ተንከባከቢው በጠረጠርሽው ጉዳይ ምክንያት የተለየ ፊት አታሳይው፤ የጠረጠርሽው መስሎ ከታየው አሁንም ከመዝጋት አይመለስም( አደረገውም አላደረገውም)፡፡ ለመሆኑ ከልጆቻችሁ የትኛውን ይወዳል ወይ ደግሞ በተሻለ ይቀርባል? በሚወደው ልጁ አማካኝነት ገመናው ሳይወጣበት ለምን እንደዘጋሽ ልጁ ማናገር ይችላል፡፡ ይህ እንድትነጋገሩ በር ከፋች ነው፡፡ ያሉሽን አማራጮች ሁሉ ተጠቀሚባቸው፡፡ ይህ ጉዳዩን ቀላል ያደርገዋል፡፡ ለማኝኛውም አንች ሁሉም ነገር( መጥፎውና የጠረጠርሽው) አንዳልሆነ ሁልጊዜ አስቢ፡፡ ማስረጃው ካለሽ ግን እሱን የሚቀርበውን ሰው በመያዝ ጉዳዩን እልባት መስጠት የመጨረሻ ውሳኔ ይሆናል፡፡ እንዲመለስ የሚደረገው ጥረት የሚጀምረው ጉዳዩ እውነት መሆኑ በቅድሚያ ሲታወቅ ነው፡፡ ጉዳዩም በሰውና በህግ ያልቃል፡፡
  እግዚአብሔር ይርዳሽ፡፡
  mfatat gin bechirash ayifekedim

  ReplyDelete
 19. ዲን. ዳኒ ይህንን ነገር ሳነብ በጣም ገረመኝ!! ብሎግህን ከዳኒዬል አይታ ወደ እርስዎ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ እየቀየርከው ከሆነ አሳውቀን እና እኛም የጓዳችንን ችግሮች እንላክልህ፡፡
  ከዚሀ በተረፈ ከዚሀ በፊት አንድ እህታችን በሰጠችው አስተያየት ላይ የእናቷን ትዕግስት፡ ጽናትን ይቅር ባይነትነን ሳነብ አእያለቀስኩ ነበር ፡፡ አኔ ከዛ የተሻለ ምንም የለኝም ስለዚሀ እሷም ልክ እነደ ልጀጆቹ እናት ትዕግስት፡ ጽናትን ይቅር ባይነት ይኖራት ዘንድ እመኛለሁ፡፡

  ተስፋሁን አሪዞና

  ReplyDelete
 20. Egizabiher yirdash new yemilew....Tselot adrigi

  ReplyDelete
 21. bewntu kehon anche betam bertu site nishe meknyatum le3 amte hasbne ketdar gar saylwawtu meqoyt betam chay mehonshen yemyase nwe bemhonum lijochshen keasbshew alma madrse yegde nwe.gen anchen eygodashe aydlm mehon yalbte.selhonm mimlse kehon yemlse kalzya gen yemiftrwe ngre kebad selmihon lijochshem honu betsbhshe endtnorilachw yeflgalu bemhonum afatgn ermja wesje.

  ReplyDelete
 22. Akababyshe yale betekrestyan selemaryam fit lefet kuche beleshe lega yetsafeshewn like fitlefteshe endaleche adregeshe hulunem endeguadeg, ende kirbe sew, ende lebe guadega awryate erasua mefetehe tefelegeleshalehu yeswen lib kesua wechi mekeyere lemanem kebade new lesua gin egike kelake minalebatem yedekik sira new eregetaga hoge yemenegereshen binore leselua awereteshe setewechi tarikeshe yekeyeral ayzoshe emamelake tasebeshe terdashe

  ReplyDelete
 23. besmame des yelale wendmachen selbetsbu yakafelene ewente new egizabhre lhulme gizena mefetya alwe leswe kamakrute legzabhyre yamakrute chgre yekelale andande sewche gera legbune selmichlhue kedmene legizabhre engerewe

  ReplyDelete
 24. እኔ ሰውየው የሆነ ፀፀት ውስጥ ያለ ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ሰዎች ሽንፈታቸውን ለመሸፈን ሲሉ ቁጣን እንደ አንድ አማራጭ ይጠቀሙበታል፡፡ ሰውየው አንቺን የበደለ ስለመሰለው ነው እንጂ ባንቺ ጥፋት አይመስለኝም እንዲህ የዘጋችሁ፡፡ አሁን ይቅር ብሎ ከተስማማችሁ ያየሰራው ነገር ባለበቱን የሚጎዳ ከሆነ ፣ አረቆ በማጠር በደሉን ለመሸፈን እየሞከረ ይመስለኛል፡፡ ስለዚህ አንቺ ምንም በደል ቢሰራ ይቀርታ እንደምታደርጊለት መስተማመኛ ብትሰጪው፡፡ ለምሳሌ አያድርገውና ኤች.አይ.ቪ ቢኖረበት ምን ታደርጊያለሽ? አስቢበት
  አማረ ዘደብረ ዘይት

  ReplyDelete
  Replies
  1. Sewyew minim tsetset yelebetim, bitsetset yikirta yiteyikal aleyam kesbekes wedebetu yimeles neber. Yih sew yegemerew neger ale tidarunm meftat ayifeligim endihu eyamtata gizewn masalef feligo new.Yih sew eko tenegna aydelem 3 amet mulu eswam mechalwa? endene lemiwedew gwadegna weynim betshuf ltselot gize binorat ena Egzern bititeyik lebetesebu mefthe yihonal.

   Delete
 25. እህቴ እግዚአብሔር የቤትሽን ሰላም ይመልስልሽ፡፡

  እንዲህ አይነት ነገር እንዴት አስቸጋሪ እንደሆነ የደረሰበት ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡ ባሎች ለምን እሽሩሩ መባልን ከሚስት ብቻ እንደሚጠብቁ እኔ አይገባኝም፡ የቤተሰብ ሙሉ ኃላፊነት፣ የልጆች ነገር፣ ማህበራዊ ተሳትፎ፣ ስራ /ካለ/ ሚስቶች ከስንቱ ይሁኑ፤ ለምሳሌ የኔ ትልቁ ችግር ስለ ልጆች ማሰብ ፈጽሞ አይፈልግም ለምሳሌ ትምህርት ማስጠናት፣ ምግብ፣ ጤንነት ሁሉም ነገር እኔ ላይ ነው የተጣለው ቢታመሙ ከስራ ቀርቼ፣ ፈተና ቢደር ከስራ ቀርቼ፣ ስለሚበሉት ጠዋት ማታ ተጨንቄ ወይ ጉድ አንዳንድ ባሎች ግን እግዚአብሔር ልቦና ይስጣችሁ፡፡

  እመብርሃን ለገጠመሽ ፈተና ፈጥና ትድረስልሽ

  ReplyDelete
 26. ጥንተ ጠላት ሰይጣን በእያንዳንዱ ጓዳ እየገባ የሚያደርሰዉ ጥፋት ለሁላችን ግልጽ ነዉ፡፡የእህታችን/የእናታችን ታሪክም ከዚሁ የሚለይ አይደለም፡፡እኔ በጉዳዩ በጣም አዝኛለሁ፡፡ መቸም ሁላችን ጎደሎ እንዳለብን ብናዉቅም እርስዎ ምን ላድርግ ብለዉ በመጠየቅዎ የመፍትሄ አቅጣጫ ቢሆንዎ ብየ እንደሚከተለዉ ሀሳቤን ሰነዘርኩ፤
  • ይኸን የመሰለ ጠንካራ ዉሳኔ እንዴት ሊዎስን ቻለ የሚለዉን ጥያቄ እራስዎን በመጀመሪያ ሊጠይቁ ይገባል፤ መቸም አራት ልጅ እስክታፈሩ ድረስ አንዳችሁ የአንዳችሁን ጠባይ ሳትተዋወቁ ፤ሳትላመዱ አትቀሩም፡፡እናም እንዴት ስለ ላጤዋ ሴትዮ እንወያይ ሲሉት ሊያኮርፍ ይችላል?ያን ያህል ዘመን ስትኖሩ ተወያይታችሁ አታዉቁም እንዴ?ዉይይት ብለዉ እርስዎ ያነሱት አጀንዳ ያን ቀን ብቻ ነዉ ወይስ የጠየቁበት መንገድ አግባብነት አልነበረዉም፡፡እንወያይ ብለዉ ከማንሳትዎ በፊት ስለ ላጤዋ ምን አይነት መረጃ ነበረዎት፤ ባልዎን እስከምን ድረስ ያምኑትስ ነበር?ከእንወያይ ጥያቄዎ በፊት ከሌሎች ሰዎች ጋር ስለ ባልዎ መሳሳት ሃሜት አልነበረም?በቤት ዉስጥ ሌላ ችግር የለም ነበር?ብዙ ጊዜ በቤታችሁ ስለ ሴትዮዋ እያነሱ አልዘበዘቡት ይሆን---- ሌሎችንም ጉዳዮች አንስተዉ እራስዎን ይመርምሩ፤ ይጠይቁ፡፡በመካከላችሁ የገባ ነገረኛ መኖሩን አለመኖሩን አረጋግጠዋል?ነገረኛ ሰዉ እኮ የሰይጣን መልዕክተኛ፤የዲያብሎስ ፈረስ መሆኑን ይረዱ፡፡
  • ይች ቃሪያ ካደረች አትቆረጠምም የሚባለዉን አባባል ተረድተዉ ወደ መፍትሄ ለመግባት የፈጁት ጊዜ በራሱ የረዘመ ይመስለኛል፡፡እንዴት መኝታ ቤት ለሰራተኛ ምግብ ብቻ እየላኩ ኖሩ?ለልጆችዎ ብለዉ እንደሆነ ጽፈዋል ግን ምን ያመጣል ብለዉ አድርገዉት ቢሆንስ?እርስዎ እንደሚያስቡት ሁሉ እርሱም ለልጆቹ ብሎ ብቻ ምግብ እየተመገበ ትዳሩ እንዳይበተን እየኖረ ሊሆን እንደሚችል እራስዎን ጠይቀዉ ያዉቃሉ?የመፍትሄ አባቶች የተባሉት እንደት ያንን የመሰለ ችግር መኖሩን እርስዎ ሲነግሯቸዉ በስልክ ለማናገር ከመሞከር ለምን በአካል አልጠየቁትም?ቤት እንዲመጡ ለምን አልጋበዟቸዉም?ጎረቤት፤ዘመድ አዝማድ፤የንስሐ አባት---- ሌሎችም እንደት በአካል ሊጠይቁት አልቻሉም፡፡ባለቤትዎ ሰዉ ቤታችሁ ድረስ እንዳይመጣ ከልክሏል እንዴ?እናም ሶስተኛ ወገን መስማቱን ስለነገሩን ሶስተኛ ወገን በነገሩ ገብቶበት በአካል ከእርሱ ጋር ይወያዩ፤ተወያዩ፡፡
  • ታላቁን የጦር እቃ-ጸሎት ይታጠቁ፤ይጸልዩ፤ሱባኤ ይያዙ፡፡በዚህ ዙሪያ እርስዎ ብቻ ሳይሆኑ ቤተሰብዎ በሙሉ ይህንን ብታደርጉት፡፡እረ እንደዉም እኛ ሁላችን የእርስዎን ችግር ያነበብን እና የሰማን በሙሉ፡፡እባክዎን የእርስዎን እና የባለቤትዎን ስመ-ክርስትና ይጻፉልን፡፡

  wubshet(bd)

  ReplyDelete
 27. Egizhabiher Yirdash; think deeply, listen ur inner and decide your own decistion.

  ReplyDelete
 28. እህታችን በትዳሯ ውስጥ የገጠማትን አስቸጋሪ ሁናቴ አስመልክታ ጭንቀቷን አንባቢያን ይካፈሏትና መፍትሄ ያመላክቷት ዘንድ የልቧን ምስጢር እንካችሁ ብላለች፡፡ ወንድማችን ዳኒም ለእህታችን መፍትሄ የሚሆን አሳቦች ይንሸራሸሩ ዘንድ ይህን የእህታችንን ታሪክ በጦማሩ አስተናግዶ አንባቢዎችን ጋብዟል፡፡ ምንም እንኳ ርእሰ ጉዳዩ እንዲህ በዚህች በወንድማችን መጦመሪያ መድረክ ላይ እንዲህና እንዲህ ብታደርጊስ፣ እንዲህ ዓይነት ውሳኔ ብትወስጂ፣ እነ እከሌንና እከሌንስ ብታማክሪ፣ ነገሩን በጸሎትና በሱባኤ ብትይዥው ወዘተ ሌላም ሌላም ምክሮች፣ አስተያየቶችና መጽናኛ የሚሆኑ መልእክቶች ወደተፈለገው መፍትሄ ያደረሳል ባይባልም በብዙ ወንድሞችና እህቶች የሚገለጹ አሳቦች እህታችንን ወሳኔዋንና ወደፊትም በምን መልኩ ከዚህ አጣብቂኝ ልትወጣበት የምትችልበትን መንገዶች የሚያመላክቱ ቁምነገሮች አይጠፉበትምና መነጋገሩ ደግ ነው እላለሁ፡፡
  እንዲህ ዓይነቱ በትዳር ውስጥ ያለ አለመግባባትን ለመፍታት ከመንፈሳዊና አባቶችና የጋብቻ አማካሪዎች ጋር ቁጭ ብሎ በደንብ መወያየትና መነጋገር ያስፈልገዋል፣ ቢሆንም ግን እህታችን ምን ትሉኛላችሁ በማለት ላካፈለችን ችግሯ ቢያንስ መፍትሄ አመላካች ይሆናሉ ብለን የምንላቸውን ነገሮች ወርወር ማድረጉ ደግ ነው በሚል እሳቤ ነው እኔም የበኩሌን ለማለት እጄን ከብዕሬ ያዋደድሁት፡፡
  የእህታችን ችግር ጥቂት ዓመታትን ያስቆጠረ መሆኑና ደግሞ ከችግሩ ስር መስደድና እህታችንም እንደገለጸችው ችግሩን ለመፍታት የተወሰዱት እርምጃዎች ሁሉ እንደውም በጊዜ ሂደት ችግሩን አባብሶት ዓመታት መቆጠራቸውንና ዛሬም ቤታቸው በዝምታ ድባብ ተውጦ እንደ ባለትዳር ሳይሆን እንደ ጣውንት ተፈራርተው እየኖሩ ያሉበትን እጅግ የሚያስቀይምና ደስታ የራቀው ሕይወት ውስጥ መግባቷን እህታችን ጥልቅ በሆነ ምሬት ውስጥ በደብዳቤዋ ውስጥ ገልጻለች፡፡
  ያለመታደል ይሁን ከእኛ ይቅር ባይ፣ ልበ ሰፊነትና ቻይ ያለመሆን ጣጣ በዘመናችን ከባለትዳሮች ዘንድ ብዙም ደስ የሚል ዜና አይሰማም፤ እርስ በርስ መቀናናቱ፣ ጭቅጭቁ፣ አለመግባባቱ፣ ንትርኩና በአሳብ አለመጣጣሙ፣ ኢኮኖሚያዊ ቀውሱና የቤተሰብ ጣልቃ ገብነት፣ የልጆች አስተዳደግና ምጣኔ… ወዘተ ለባለትዳሮች ተግዳሮቶች ሆነው ብዙዎችን ትዳራቸውን ለማፈረስ የሚገደዱባቸው ሁኔታዎች በእጅጉ እየተከሰቱ ናቸው፡፡ ባሎች ስለሚስቶቻቸው በተገላቢጦሽም ሚስቶች ስለባሎቻው ቅንና መልካም የሆነን ነገር ማውራትና መስማት በዚህ ዘመን በእጅጉ የሚናፈቅ እየሆነ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ መራር የሆነ ስሜትና ጥላቻ ደግሞ ብዙ ትዳሮች የቆሙበትን የተሳሳተ መሠረት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡
  እንደ መጽሐፍ ቅዱስና አባቶቻችን አስተምህሮ ከሆነ ‹‹ባል ሚስቱን እንደ ራሱ አድርጎ ይወደዳት ይላል፡፡›› አደራችሁን ይህ ጥቅስ ‹‹ሚስትም ባሏን እንደ ራሷ አድርጋ ትወደደው›› ተብሎም ጭምር ይነበብልኝ፡፡ ታዲያ ቅዱስ ጳውሎስ ይህን ምክር በጻፈበት መልእክቱ በትዳር ውስጥ ያለውን ጥልቅ ምስጢርና እውነት ከሙሽራይቱና በክቡር ደሙ ከተዋጀችው ከቅድስትና ንጽህት ቤተ ክርስቲያንና ከኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል ላይ ታላቅ ፍቅር ጋር በማነጻጸር አቅርቦታል፡፡ ልክ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን ነፍሱን አሳልፎ እንደሰጠና ነፍሱንም አሳልፎ እስከመስጠት እንደወደዳት ሁሉ በሁለት ባለትዳሮች መካከል ያለው ሕይወትም እንዲህ እንዲሆን ቅዱስ መጽሐፍ ያዛል፡፡ ‹‹ነፍስን እስከመስጠት›› ይህ እውነት እንኳን በፍቅር ቃልኪዳን ተጣምረው በአንድ ጣር ስር ያሉትን ባለትዳሮች ብቻ ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱሳዊው ትዕዛዝ ባልንጀሮቻችንም እንደራሳችን መውደድ ብቻ ሳይሆን ነፍሳችንን እስከመስጠትም መውደድ እንዳለብን አበክሮ ይነግረናል፡፡
  ይቆየን!

  ReplyDelete
 29. መቼም ይህ እውነት በዚህ ዘመን የተዘነጋ ብቻ ሳይሆን ብዙዎቻችን ለማድመጥ የማንፈልገውና ብንሰማውም ይህ በአባቶቻችን ዘመን ቀረ ብለን የምናልፈው ወደመሆን መድረሳችን ልብን የሚያሳምም፣ ኅሊናን የሚያቆስለል ነው፡፡ ቢሆንም እኛ አልኖረንበትም ተብሎ እውነት መሆኑ አይቅርምና ቢያንስ በሥራ/በተግባር ልናደርገው ባንችል እውነትነቱን በብዕራችን እንኳን እንመስክር በማለት ነው ልጽፈው የደፈርኩት እንጂ… የተጻፈውና እየኖርን ያለውማ አራምባና ቆቦ መሆኑን ብዙም እማኝ መጥራት የሚያስፈልግ አይመስለኝም፡፡ እናም የክቡር ትዳርም ሆነ የባልንጀርነት የፍጻሜ ድንበሩ ሌላውን እንደ ራስ መዋደድና እስከ ነፍስ መስጠትም ድረስ በሆነ ዘላለማዊ መዝለቅ ነው፤ ብንቀበለውም ባንቀበለውም…!!!
  እስቲ እህታችን ስላጋጠማትና ስለገባችበት አጣብቂኝ ጥቂት ነገሮችን ልበል፡፡ እንደ እህታችን ገለጻ በእህታችን ትዳር ውስጥ የጋብቻ አማካሪዎችና መንፈሳዊ አባቶች ከፍቅር ቀጥሎ ለትዳር ቁልፍ ነው የሚሉት አሳብ መለዋወጥ/መነጋገር (communication) ከቤታቸው ጓዙን ጠቅልሎ ከተሰደደ ጥቂት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በዚህም ግራ የተጋባችና ነፍሷ የተጨነቀች እህታችን ይህን ጉዳይ እልባት ለመስጠት የሄደችባቸው መንገዶች ሁሉ መፍትሄ አልሰጣት ቢል ጉዳይዋን ለአደባባይ ለእኛ ለአንባቢያን አበቃችው፡፡ ለትዳር አሳብ መለዋወጥ/መነጋገር እጅግ ወሳኝ የሆነ ጉዳይ እንደሆነ ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡ በእህታችን ትዳር ውስጥ ደግሞ ይህ የትዳር ዋና ቀመም የሆነ መነጋገር/መወያየት ከቤታቸው ከጠፋ ከወራትም ዓመታትን እያስቆጠረ ነው፡፡ ባለቤቷ ከአንዲት ሴት ጋር አብዝቶ መታየቱ ደግ እንዳልሆነና ይህን ጉዳይ ቢተው መልካም እንደሆነ በተነሳ ግሳጼ ይባል ምክር ባል አኩራፊና ሚስቱንም ለማናገር ፈቃደኛ ያልሆነበት ሁኔታ ተከስቶአል፡፡
  መቼም በትዳር ውስጥ በአንድ ጣር ስር እየኖሩ ሊከሰቱ የሚችሉ ከዚህም በላይ የሆኑ አንዳንድ ጉዳዮች ይኖራሉ፤ ሚስት ደስ ያላሰኛትን ነገር መናገሯ ስህተት ነው አይባልም፤ ምናልባት የሚስት ንግግር በባለቤቷ ላይ እንዴት በዚህ ጠረጠረችኝ፣ ትቀናለች ማለት ነው ወይስ … ወዘተ በማለት በመሰል ቅሬታዎች ደስተኛ ላይሆን ይችል ይሆናል ግን ባል በሚስቱ ላይ ሊያነሳው የሚችለው ምክንያት ምንም ይሁን ምንም እንደ ባለትዳር እንደ ቤተሰብ ኃላፊ ተነጋግሮ፣ ተወያይቶና ተግባብቶ አንድ መፍትሄ ላይ መድረስ ሲቻል እንዴት ስም የሌለው ኩርፊያ የቤታችውን ምሰሶ ሊያናጋ፣ የሕይወታችውን ደስታ ሊዘርፋቸው፣ ቤታቸው እንዲበተን እንዲህ ዓይነቱ የዝምታ ጋግርት ምክንያት ይሆን ዘንድ ሊፈቀድለት ይገባል፡፡ እንደ እህታችን ገለጻ ከሆነ እነዚህ ባትዳሮች ጣፋጭ የሆኑ የፍቅር ጊዜያትን አሳልፈው እስከ ዩኒቨርስቲ ደረጃ የደረሱ ልጆችን አድርሰዋል፡፡ እናም…
  በዚህ ሁሉ ጊዜ ውስጥ ክፉውንም መልካሙንም በመመካከርና በመወያየት ለዛሬ ደርሰዋል፣ ከዚህ ሁሉ ጊዜ በኋላ ፈታኙንና አስቸጋሪውን ጊዜ አሳልፈው ዛሬ በልጆቻቸው ስኬት ለመደሰትና የትዳራቸውን መልካም እና ጣፋጭ ፍሬ ለማጣጣም በሰከነና በተረጋጋ አእምሮ ችግሮችን ሁሉ በጋራ ለመፍታት ብልህነትና ጥበብን በሚታደሉበት ጊዜ እንደ ገና ወደኋላ እንዲደረደሩ ያደረጋቸውንና ቤታቸውን የዝምታ ጋግርት እንዲነገሥበት የፈቀዱበትን ምክንያት በጨዋ መንፈስ ተነጋግረው ሊፈቱበት አቅሙንና ድፍረቱን ያጡበት ምክንያቶች በሚገባ ሊተነቱና ባልም በሚስቱ ዘንድ ሊያነሳቸው የሚችሉ ቅሬታዎች በቅጡ ሊታዩ ይገባል ባይ ነኝ፤ ምናልባትም ፍራቻዬ የአንድ ወገን ብቻ አሳብ በሚንሸራሸርበት መልኩ ማለትም ሚስት በባሏ ላይ ያጋጠማትን ችግሮች ብቻ በገለጸችበትና ባል አሳቡ ባልተስተናገደበት ሁኔታ ለችግሩ ትክክለኛ መፍትሄ ማመላከት ይቻላል ብሎ ማሰብ ትንሽ ይከብድ ይመስለኛል፡፡
  ቢሆንም ግን እህታችን ካለችበትና ከገባችበት ውጥረት አንጻር ቢያንስ በእርስዋ በኩል ምን ማድረግ ይገባታል በሚለው አቅጣጫ የጀመርኩትን እሳቤዬን ልቀጥል፡፡ በእርግጥ ተግባራዊው መፍትሄው የመጻፉን ያህል ይቀላል ባይባልም እህታችን ለገባችበት አጣብቂኝ ግን መፍትሄው ከመነጋገር ውጪ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል፡፡ መነጋገሩ የፍቅርን፣ የይቅርታን እና የትህትናን መንፈስ የተላበሰ እንዲሆን ግን በእጅጉ ያስፈልገዋል፡፡ ይህ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን በየትኛውም የሕይወታችን አቅጣጫ ልንተገብረው የሚገባ የሕይወት መርህ ነው፡፡ እህታችን፡- አንዳንዴ በትዳር ውስጥ የሚፈጠሩ ግጭቶችና አለመግባባቶች ወደሚበልጥ ብስለት፣ መፍትሄ፣ መግባባት፣ ግብረገብነትና ወደተሻለ እይታ የሚወስደንን ዕድል ስለሚፈጥሩ አንቺ ያለሽበት ችግር በሌላም መንገድ ሌሎችም ያለፉበት ነውና ከሰዎች ምክርንና የጸሎት እርዳታን መሻትም መልካምና ሌላው የሚበልጠው አማራጭ ይመስለኛል፡፡ በተጨማሪም የባለቤትሽን ልብ ለማራራትና ወደ ቅን መንገድ ለመመለስ የአንበሳውን ድርሻ በመውሰድ ፍቅርን፣ ይቅር ባይነትንና ትህትናን በማሳየት ከሳተበት ለመመለስ ሳታክቺ መሞከር አለብሽ፡፡
  ስላለሽበት ችግር ብዙም ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ልትገቢ አይገባም፡፡ በፍቅር ሁሉን ድል ማድረግ ትችያለሽና በሚበልጥ እውነተኛ ፍቅር በባለቤትሽ ልብ ውስጥ ያለውን የትኛውንም የዝምታ፣ የክፋት፣ የበቀል…ወዘተ ተራራ መናድ አንደምትችይና ትዳርሽንም ከመፍረስ መታደግ እንደምትችይ በእግዚአብሔር ኃይልና ጸጋ አምነሽና ተማምነሽ በጸሎት ፍሬው ጣፋጭ የሆነውን የፍቅርን የቤት ስራሽን በትጋት ለመወጣት ሞክሪ፡፡ በዚህ ጥረትሽ ውስጥም የአባቶች ጸሎት፣ የወንድሞችና የእህቶች ምክርና ድጋፍ እንዳይለይሽም በርቺ፡፡ ከባለቤትሽ ጋር በግልጽ ለመወያየት የሚያስችሉ ዕድሎች እንዲፈጠሩ ጥረትሽን አታቋርጪ፣ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ባለቤትሽን በፍቅር እና በትህትና ልታናግሪው ሞክሪ፡፡ በፍቅርና በፍቅር ብቻ ነው ማሸነፍ የሚቻልሽ፡፡
  በፍቅር ለይኩን ነኝ፡፡
  የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይርዳሽ!

  ReplyDelete
  Replies
  1. tiru tsuhif newu; fikr you can be writer try please
   thank you

   Delete
 30. ውድ ዳኒ
  መፍትሄ የሚያስፈልጋቸው ማኅበራዊ ችግሮቻችን እኮ ብዙ ናቸው:: በዚህ መንገድ ባትገባባቸው እመርጣለሁ ባይሆን እህታችን እንደጠቋቆመቻቸው ያሉ በረከቶችህን ብታወርድ:: በየቤቱ የምንሰማቸው ታሪኮች እኮ አሳዛኝ ናቸው:: ለነገሩ በ15 ደቂቃ ስብከት ከሚመሠረቱ ትዳሮች ምን እንጠብቃለን? እህታችን የደረሱ ልጆቿ እንኳን ሊፈቱት ያልቻሉት ችግር በጓዳዋ ይዛ በትእግስት እየኖረች ነው:: እንዲህ ያለው በማንም አይድረስ

  ኦርቶዶክሳዊነሽና እናቴን ገጥሟት የነበረውን ተመሳሳይ ችግር የፈታችበትን መንፈሳዊ መንገድ ልጠቁምሽ:: አንቺ የሄድሽበትን መንገድ ሁሉ ሂዳ መፍትሄ ባጣች ጊዜ ወዳጆቿ ዘመድ ጎረቤቱ ሁሉ ጠንቋይ እንድታማክር ይጎትታት እንደ ነበር አስታውሳለሁ::

  በወቅቱ በታላቅ ወንድማችን ይመራ የነበረ ሳምንታዊ የቤተሰብ የጽሎት መርሐ ግብር ነበረን:: አባታችን በዚያም ላይ መገኘቱን በማቆሙም ተከፍተን ነበር:: እናቴ ግን በጥንቃቄ የምታደርጋቸውን ነገሮች ዛሬ ሳስባቸው ልጆቿ ባለ ዲግሪዎች እንጂ ባለ መፍትሄዎች አልነበርንምና እደነቃለሁ::

  በሥርዓት ክልክል ሊሆን ይችላል ግን እናቴ ደጋግማ ስታደርገውና ለውጥ ሲያመጣ በዓይኔ አይቻለሁ:: እንደራትና ምሳው ሁሉ የአርብ ጽሎት ጸበል መኝታ ቤቱ ይጠብቀዋል:: አባቴ አንድ ቀን ጸበል እያላችሁ መርዝ ብትግቱኝስ ከዚህ በኋላ አልፈልግም ብሎ ሲናገር እናቴ መልስ አልሰጠችውም ነበርና በጣም ተቆጥቼ ተናገርኩት:: እናቴ የዚያን እለት የተናገረችን ነገር አለ:: አባትሽን እንዲህ መናገር አይገባሽም ደግሞም አትጠቅሚውም:: ወዶ ይመስልሻል ልጆቹን ያስጠላው? ምን ክፋት ነበረበት ከኛ መነጋገሩ? ጸሎት ማድረግ የከለከለው ጸበል እንዲቀምስ ይፈቅድለታል እንዴ? አሁን በሚያደርገው ነገር ልናዝንለት እንጂ ልናዝንበት አይገባም... ብዙ አለችኝ:: ይህንን ግን መቼም ልረሳው አልችልም:: ከዚያ በኋላ አርብ አርብ እራቱ ጋር የሚቀርበው ውኃና ማባያ ዳቦው ጸበል እንደነበር አውቃለሁ:: አንድ ምሽት አባዬ ለጸሎት ከኛ ጋር ቆሞ እንደነበር ያየሁት ጨርሰን ስንቀመጥ ነበር:: ጸበሉን ሳዞር ለርሱም እየፈራሁ ሰጠሁት ተቀበለኘና ቆመ:: ልጆቼ ይቅር በሉኝ ባለ ማወቅ በድያችኋላሁ:: እናታችሁ ይቅር እንድትለኝ እናንተ አማላጅ ሁኑኝ:: እያለ እግሯ ላይ ወደቀ::ሁላችንም ደስ እያለን አለቀስን::

  ጸሎታችን ለማን ነው? አንተ እንድትመለስ ወደከፋ ነገር እንዳትሄድ አደለም እንዴ? ይቅር ብለንሀል እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ:: አለችው እናቴ:: አግብቼ ከናቴ ቤት እስክወጣ የቤተሰባችንን የጽሎት ጊዜ በምንም አልለውጠውም ነበር:: ለዚህ እርቅ መታሰቢያም እናቴ በየዓመቱ ሕዳር 12 ቀን የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤልን ዝክር ታደርጋለች:: ጸሎታችንን ቸል ያላለ አምላክ ክብር ምስጋና ይግባው:: እህቴ እግዚአብሔር ያልፈታውን ችግር ሰው አይፈታውም:: እናቴን የረዳ ይስማሻ::
  ካንቺወዲያ /ክአዲስ አበባ/

  ReplyDelete
 31. my advice is

  1. pray for your mirage,
  2. try to make that women a friend, she may tell you some secret. don't worry for what he did with that women in public. i also have a friend which i like more and if my wife told me not to be with her i don't know what to do but i will be very angry. i don't have an affair with her or any thing but i like her. and i want her to be just a friend.
  so you have to give a chance to your husband to decide what is good or bad.
  3. forget him and do what you think good to you and all the families.

  i really admire your patience and at the same time try to see your self this time.

  the first and the last powerful thing is the prayer. pray pray pray

  little bro

  ReplyDelete
 32. እህታችን ካንቺወዲያ ላካፈልሽን ምሳሌያዊ ሕይወት ልትመሰገኚ ይገባል:: እባክሽ የምትችይ ከሆነና ይህንን መልእክት ካየሽ አባትሽ ምን ሆኜነው አሉ? ወይም እናንተ የደረሳችሁበት ነገር ካለ? ብታካፍይን:: ክንያቱም እህታችን ለገጠማት ችግር መፍቻ እንኳን ባይሆን ጠቋሚ ሊሆን ይችላል ብዬ አስባለሁ:: ወንድማችን ዳኒ ካንተ ደግሞ ማጠቃለያውንም እንሻለን አደራ:: እኔ እንዲ ዓይነት ነገር አልወድም:: በጣም ከልቤ ነው የምጨነቀው:: በማንበቤ ተጸጽቻለሁ:: ባለቤቷ እውነት ያሳዝናል ምን ገጥሞት ይሆን? ወንድሜን:: እህታችን ሕመምሽን ታመናል ከጽናትሽ ተምረናል ስለ አንችም አምላክን ተማጽነናል:: ይፈታዋል አይዞሽ::
  አባ ምህረቱ /ከአውሮፓ/

  ReplyDelete
 33. " Le sew yemayichal le egziabher yichalal " pray... pray.. pray.

  ReplyDelete
 34. የሰላም አምላክ እግዚአብሔር ቤትሽን ሰላም ያድርግልሽ፡፡ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 35. እህቴ ሆይ የገጠመሽ ነገር በጣም ያሳዝናል እንኳንስ 3 ዓመት 3 ቀን ባልና ሚስት ተዘጋግቶ መቆየት በጣም ይከብዳል ፡፡ ሆኖም ግን በባዶ ሜዳ የቀናሽ ይመስለኛል ሰውዬው ምናልባት የመ/ቤት ጓደኛው ልትሆን ትችላለች አገባችም አላገባችም አለማግባቷ ብቻ ጥርጣሬሽን አለቅጥ ሊያገዝፈው አይገባም ፡፡ እኔ ግን እንደ እህትነቴ የምመክርሽ ሴትዬዋን /ጓደኛውን / አግኝተሽ ለማነጋገር ሞክሪ እስኪ ስልኳም ካለሽ ደውይላትና ቅረቢያት፣ አነጋግሪያት ከተቻለም ጓደኛሽ አድርጊያት ከዛ ቀስ በቀስ በአንቺና በባልሽ መካከል የተፈጠረውን ነገር አስረጂያት ማን ያውቃል እሷ እራሷ መፍትሔ ልታመጣ ትችላለች ንፁህ የመ/ቤት ጓደኛዋ መሆኑንም ትነግርሻለች፡፡ ለማንኛውም የነበረው፣ ያለውና የሚኖር ቅድስት ሥላሴ ይርዱሽ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. መልካም አስተያየት ነው ተቀራርቦ እንደመነጋገር የመሰለ መፍትሔ የለም፡፡

   Delete
 36. The version presented about the tragic family situation is one sided. It's only the wife's side. We don't know why the husband has been behaving, if he did, the way he has been reported to do.

  Therefore, opinions and advices offered by getting a one-sided information is truly and completely unwise.

  It's also very sad that an otherwise respectable blog by Dn. Daniel has sunk to a cheap psychological drama which is normally used by trashy magazines and newspapers.

  Issues of marriage are usually complex. I feel sure that if we knew the husband's version, we might, MIGHT!, find that the wife would have to mend her ways. And all those who have condemned the husband would have to apologize to him!

  Therefore, please stop messing around with a case where you want to be a judge without knowing all the facts.

  Dn. Daniel: shame on you for wasting your blog on such unworthy and pseudo-intellectual diversions.

  ReplyDelete
 37. TSUHUFN ESKI DEGMESH ANBBIW!. AYASTELAM BEGZIEHR!! YH HULU LEMN YAGATEME YMESLSHAL? MKNYATU... ANCHIW RASSH NESH.BZU MKNYAT DERDRESH ESU NEW TDARACHNN ENDIH ENDIOHON YADEREGEW... ENIE ENDIHNA ENDIYA ADRGIEALEHU... BEMALET RASSHN LEMASAMEN TMOKRI YHON. AHUNM ANCHI ENDTTKEMI SLEMFELG MKNYATU..... "ANCHIW NESH" KANCHI LIELA MANM TETEYAKI YELEM.ENDIE... 'ENEIN BCHA ENDIET' TWEKSEGNALEH TYI THOGNALESH!! KETSUHUFU NEW LIELA MNM MENESHA YELEGNM. YENIE EHT 1 MSTIR LINEGRSH FELEKUGN GN BEMN AYNET KALOCH ENDEMGELTSEW GN TEFABGN!!GN.... ANCHI YEMTFELGIWN ENDIYADERG ATGEFAFIW!ENDESU ENDIHON BEMOKERSHBET METEN ENA HAYL ESUM KANCHI YRKAL. ABABALIE KEGEBASH YEMOKERSHACHEW NEGEROCH HULU WTIETUN KAYESHW KANCHI ENDIRK ENJI WEDANCHI ENDIKERB TERA ALNEBERACHEWM ENA ENIE ENDEMIMESLEGN ANCHI MEJEMERIA RASSHN YKRTA METEYEK ALEBSH!!! (LEMN KONJOWN ALASEBKUM? ESU ENDIH AYADERGM!KEFA BIBAL ENKAN LIJOCHUN YAYAL!!) YEMILU KONJOWOCH ENA DES YEMIYASEGNU KALTOCH YASFELGUSHAL .... ENAM BEMECHERSA....." SEW YASEBEWN YHONAL" YH LK ENDE 'LAW OF GRAVITY' NEW YEMISERAW. KONJO KONJOWN KASBSH..... KONJO NEGER YAGATMSHAL METFO NEGER KASBSH DEMO ESU YAGATMAL. "KE SOSTEGNA FOK YEWEDEKE SEW... TRU SEW YHUN METFO SEW KEMERIET MEGACHETU AYKERM..... BETERFE EGZIABHIER YRDASH.
  LETS MAKE TOGETHER THE WORLD A BETTER PLACE.

  ReplyDelete
 38. Ye selam Amlak Egziabhere selamun Yimeleselesh!!

  ReplyDelete
 39. yihe sew lemezigatu mikinyat alew! as you said , u told him to stop z relation ship with unknown women! but rather than doing that he silence on you for 3 years. There fore he may had storng bond with her!

  solution;
  told the women to awy from ur husband.or send to her z local elders.
  pray to god
  ..........

  ReplyDelete
 40. ውድ እናቴ "ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው" እንዲሉ እኛ ደካሞች ብዙ እጅግም የብዙ ብዙ መላምቶች ልናወራልሽ እንችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከሞላ ጎደል ሁሉንም መንገዶች ባለፉት 3 የጭንቀት አመታቶችሽ ሳትሞክሪያቸው የቀረሽ አይመስለኝም፡፡ ስለዚህ ምንም የምጨምርልሽ ሃሳብ የለኝም፡፡ ይሁንና አንድ እኔ ደካማና ሃጢያተኛ ልጅሽ ለፀሎት እግዚአብሔር አምላክ አበርትቶ ባቆመኝ ግዜ አንችንም አስብሽ ዘንድ መልካም ፈቃድሽ ከሆነ እባክሽ የአንችንና የባለቤትሽን የመፅሃፍ ስም በዚሁ በዳኒ ብሎግ ላይ ተይልኝ፡፡

  እኔንም ደካማውን ወልደአረጋዊን እንዲሁ በፀሎትሽ አስቢኝ

  የሰላም አምላክ ሰላምሽን ይመልስልሽ፡፡ አሜን!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ...ለፀሎት እግዚአብሔር አምላክ አበርትቶ ባቆመኝ ግዜ አንችንም አስብሽ ዘንድ...

   እንደዚህ አይነት ወንድሞችን አያሳጣን

   የሁሉም ነገር መፍትሄ ፀሎት ላይ ነው ያለው፡፡ በትዳር ከሚገኝ የአንድነት በረከት ተካፋይ እንዳትሆኝ ለሚተጋ ፀላየ ሰናይ እጂሽን እንዳትሰጪ፡፡ ፀልይ ፀልይ ፀልይ

   Delete
 41. BEGZABHERE FETI SHIGERHI ASEKEMTISHE TSELOT ADERGI EGZABHERE MENGDE ALEWI .. YA MENGDE BFIKER EGZABHERE BELSHE YMETIKFELIYON WEGA RESIWA FIKER MSEWET NTSEA TEDRGSHAL

  ReplyDelete
 42. ene yamasibew be agatami be hiv or belela beshita teyizo anchi lelijochu endititerf asibo yehonal.

  ReplyDelete
 43. Adugna ZeDebreGenetJune 22, 2012 at 8:33 PM

  ውድ እህቴ እግዚአብሔር ብርታቱን ይስጥሽ፡፡ እንደ እህቴ ስለማይሽ ‹‹አንቺ›› ብልሽ እንደማይከፋሽ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ምንም እንኳ ያለሽበትን ሁኔታ በትክክል መረዳት ቢከብድም በጽሁፍ ከገለጽሽው ሃሳብ በመነሳት በተወሰነ መልኩ ስሜትሽን መረዳት ይቻላል፡፡ ይህ የገጠመሽ ችግር ያንች ብቻ አይደለም፡፡ የብዙ እናቶቻችንና እህቶቻችን ችግር ነው፡፡ ከዚህም የከፋ ችግር ውስጥ የሚኖሩ ሚስቶች ወይም ባሎች በርካታ ናቸው፡፡ ብዙ አክብደሽ ባታይውና ልጅ ወልደሽ ፍሬ ያፈራሽበትን ትዳር ለማፍረስ የሚሯሯጠውን ጠላት ዲያብሎስን ብትነቂበት መልካም ነው፡፡ ትዳርን ለማፍረስ ቀላል ነው፡፡ ትዳር ከፈረሰ በኋላ ያለው ህይወት ግን አሁን ካለሽበት የባሰና ጸጸት ውስጥ ሊከትሽ ይችላል፡፡ እናም ረጋ ብሎ ማሰቡ ብልህነት ነው፡፡
  በትዳር ህይወት ውስጥ አለመግባባት ሊኖር ይችላል፡፡ የተለያየ ዳራ፣ የተለያየ አመለካከት፣ የተለያየ ጠባይ፣ የተለያየ የትምህርት ደረጃ፣ የተለያየ ስሜት፣የተለያየ አቋም ወዘተ ያላቸው ጥንዶች ወደ ትዳር ህይወት ገብተው በመካከላቸው አለመግባባት መኖሩ አይደንቅም፡፡ ትልቁ ፈተና አለመግባባት መኖሩ ሳይሆን አለመግባባቱን በተገቢው መንገድ ማስተናገዱ ላይ ነው፡፡ እነዚህን በትዳር ህይወት ዙሪያ ለሚከሰቱ አለመግባባቶች መፍትሄ ለመስጠት የመጀመሪያው ርምጃ የአለመግባባቱን ምንጭ ወይም ምክንያት በትክክል ማወቅና መረዳት ነው፡፡ አንዳንዴ ለአለመግባባታችን ምክንያት ነው ያልነው ነገር ትክክለኛው ምክንያት ሳይሆን ይቀርና እንደገና ቸግሩ ያገረሻል፡፡ የችግሩን መንስኤ የራሳችንን መላምት ልንገልጽ እንችላለን፡፡ ነገር ግን በእርግጠኝነት ‹‹ነው›› ብሎ መደምደም ይከብዳል፡፡ ለምሳሌ እንቺ እንደገለጽሽው አሁን ለተፈጠረው ችግር ምክንያቱ ‹‹እባክህ ለቤታችን ሰላም የማትሰጥ ሴት ገብታለችና ከሷ ጋር ሌላ ግንኙነት ባይኖርህም ከሥራ ስትወጣና ስትገባ በሰፈር ውስጥ መታየት ለኔም ሆነ ለአንተ በአጠቃላይ ለቤተሰባችን ጥሩ ባለመሆኑ በአንድ ሠርቪስ ብትጠቀሙም አብረህ አትታይ አትውጣ አትግባ›› ብለሽ በመናገርሽ እንደሆነ ገልጸሻል፡፡ ትክክለኛው የአለመግባባታችሁ ችግር ይህ አነጋገርሽ ስለመሆኑ ምን ያህል እርግጠኛ ነሽ? ይህንን ቅሬታሽን(ቅሬታ ላይሆን ይችላል) ስትነግሪው በእርሱ በኩል ምን ዓይነት ምላሽ ሰጠ? ይህንን ንግግር ከመናገርሽ በፊት ግንኙነታችሁ ምን ያህል ጤናማ ነበር? ባለቤትሽ የማኩረፉ ወይም ከአንች ጋር አለመግባባት የተፈጠረው ከአንች ጋር ብቻ የተያያዘ ስለመሆኑ ምን ያህል እርግጠኛ ነሽ? ወዘተ የሚሉትን ጥያቄዎች መፈተሽ ይኖርብሻል፡፡
  ሰላማዊ ትዳርን አንቺ ብቻ ሳትሆኝ ባለቤትሽም እንደሚፈልግው እርግጠኛ ነኝ፡፡ ነገር ግን ሰላም መፈለግ ብቻውን ሰላምን አይሰጥም፡፡ ለሰላም ቅርብ የሆነ ልቡና ሲኖር እንጅ፡፡ ይቅርታ ማለትን እንደሽንፈት መቁጠርሽ በራሱ አንች ላይም ክፍተት እንዳለና እልህ ውስጥ እንደገባሽ ያመለክታል፡፡ ለኃጢአት መሸነፍ የሽንፈት ሽንፈት ነው፡፡ ለፍቅርና ለሰላም መሸነፍ ግን ሽንፈት ሳይሆን ድል ነው፡፡ ከይቅርታ የራቀ ልብ ለጥላቻ ቅርብ ነው፡፡ ብዙዎቻችን ማለት ይቻላል እንኳንስ ያስቀየመንን ሰው ይቅርና ያስቀየምነውንም ሰው ይቅርታ ለመጠየቅ የሌላኛውን ወገን ግፊት እንፈልጋለን፡፡ እንዲህ አይነት ጠባይ ተላብሰን እነዴት ነው ሰላማዊ ህይወት የምንመኘው? እናም እህቴ የመፍትሄው ቁልፍ በእጅሽ ላይ ያለ ይመስለኛል፡፡ በአንቺ አቅም ልታደርጊው የሚገባሽን ልጠቁምሽ
  1. ከሁሉ አስቀድመሽ የደነደነውን ልብ ለሚያለዝበውና ዘላቂ ሰላምን ለሚሰጠው አምላክ ሳታቋርጪ ጸሎትሽን አቅርቢ፡፡
  2. በጎ አስተሳሰብን አዳብሪ፡፡ a life situation by itself is not a problem, but the way we interpret the situation makes it problem. ባለቤትሽ ከማትፈልጊያት ሴት ጋር መሄዱና መቀራረቡ በራሱ ምንም ችግር የለውም፡፡ አንች ግን ችግር አድርገሽ ተረዳሽው፡፡ እንኳንስ በትዳር ህይወት ይቅርና ከማንኛውም ሰው ጋር አብረን ስንኖር ለሰዎች በጎ አመለካከት ከሌለንና ክስተቶችን ሁሉ በአሉታዊ ጎን የምንተረጉማቸው ከሆነ ውስጣዊ ሰላማችን ይደፈርሳል፡፡ ከገሊት ጋር ሂድ ከገሊት ጋር አትሂድ እያልሽ የምታሸማቅቂው ከሆነና አብሯቸው ከሚሰሩ ሰዎች ጋር ባለው ግንኙነት አንቺ ውሳኔ ሰጭ ከሆንሽ ነጻነቱን እንደተጫንሽው ልትረጅ ይገባል፡፡ ባለቤትሽ ምንም በማታስቢው መንገድ ተርጉሞ ከአንቺ ጋር አብሮ ከሚሰራ ሰው ጋር አብረሽ ስትሄጅ እንዳላይሽ ቢልሽ ምን ይሰማሻል; ‹‹በእኛ ሊደረግብን የማንፈልገውን ነገር በሌሎች ላይ አለማድረግና፣ ለእኛ ሊደረግልን የምንፈልገውን ለሌሎችም ማድረግ›› እንደሚገባ ነው የእግዚአብሔር ቃል የሚያስተምረው፡፡ አንቺ ለእርሱ ታማኝ እንደሆንሽ ሁሉ እርሱም ለአንቺ ታማኝ እንደሆነ ለምን አታስቢም? ስለዚህ ለትዳር አጋርሽ ያለሽን እምነትና አመለካከት ብትመረምሪው መልካም ነው፡፡ በጥርጣሬ የተሞላና እምነት የማይጣልበት የትዳር ህይወት ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ የባልና የሚስት ግንኙነት መሻከር መዘዙ ወደልጆች ይሸጋገርና የልጆችንም ሰላማዊ ህይወት መፈታተኑ አይቀርም፡፡ ስለዚህ ከልብ የመነጨ ይቅርታ ለማድረግና ወደነበራችሁበት ሰላማዊ ህይወት ለመመለስ ልቡናሽን ልታዘጋጅውና ቀና የሆነ አመለካከት ሊኖርሽ ይገባል፡፡
  3. የግትርነትና እኔ ብቻ ትክክል ነኝ የሚል ስሜት ካለብሽ ራስሽን መርምሪ፡- ብዙ ጊዜ የአንደኛው ወገን ብቻ ሀሳብ የበላይነትን የሚይዝ ከሆነና መደማመጥ ከሌለ ለተሳሳቱ ውሳኔዎች ሊዳርግ ይችላል፡፡ ስለሆነም ባለቤቶ የሚናገረውን ብትስማሚበትም ባትስማሚበትም ከልብሽ አዳምጭው፡፡ ውሳኔውንም ትዳራችሁን እስካልጎዳ ድረስ አክብረሽ ተቀበይለት፡፡ አንቺ ትክክል፣ እርሱ ደግሞ የሚሳሳት አድርገሽ የምታስቢ ከሆነ በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡
  4. በውይይት ወቅት አንተ እያልሽ ከምታወሪ እኔ የሚለውን አስቀድሚ፡፡ ‹‹የችግሩ ምንጭ አንተ ነህ፣ አንተ እንደዚህ እንደዚያ ባታደርግ ኖሮ እኔ እንዲህና እንዲያ አልሆንም ነበር›› ከማለት ‹‹የችግሩ ምንጭ እኔ ነኝ፣ አንተንም ለዚህ ነገር የዳረኩህ እኔ ነኝ›› ብሎ መናገርና አስቀድሞ ራስን ተጠያቂ ማድረግ ለጤናማ ውይይት ጠቃሚ ነው፡፡
  5. በመጨረሻም የኃይማኖት አባቶችን ወይም የሥነ-ልቡና ባለሙያዎችን ማማከር ሌላው ጠቃሚ መፍትሄ ነው፡፡
  ወላዲተ አምላክ በአማላጅነቷ አተለይሽ

  ReplyDelete
 44. My advice for this problem, everything start form you. You try to change yourself, forget everything and love him for your heart. Change yourself first. You get peace. Leave everything for GOD, He take care of you. Believe Him, He can fix all your problem.
  God bless you

  ReplyDelete
 45. እህቴ አይዞሽ ፈተና ያለ ነው አንዳንዴ ሰው ሲያፍር
  ሰው ሰማብኝ ባላደረኩት የሚሉ ምከንያቶች አያጡም
  ስለዚህ ብዙም ለሰው አታውሪ ዝም ብለሽ ፀልይ
  በተረፈ ባገኝሽ ደስ ይለኛል ስልክሸን ላኪልኝ
  ክርስትና ስምሽን ላኪልኝ በዚሁ ብሎግ

  ReplyDelete
 46. በጣም ይገርማል! የእናቴን ታሪክ ሳነብ በቤተሰባችን በደረሰ ተመሳሳይ ችግር ውስጥ ሆኜ ነው፡፡ ሰዎች ስለችግራቸው ተወያይተው መፍትሔ እንዳያገኙ ችግርን በልብ ደፍኖ በሰውነት ስቃይ የሚጠዘጥዝ ፣ በቀረበልን ታሪክ አባቶችን የማያናግር ሰይጣን በየቤተታችን እያንኳኳ ነውና ለራሳችን ብቻ ሣይሆን ስለሁሉም ከምንግዜውም አሁን ተግተን ልንጸልይ እንደሚገባ እኔን ተሰምቶኛል፡፡ ለእናቴ ችግር መፍትሔ የምትሉትን የበኩላችሁን ለላላችሁ በእግዚአብሔር ስም ሳላመሰግናችሁ አላልፍም መፍትሔው ለኔም ታሪክ ጭምር ስለረዳኝ፡፡ ታሪክሽን ያካፈልሽን እናት ደግሞ ይህ በአንቺ ላይ ብቻ የመጣ ቁጣ አድርገሽ ሳታስቢ ትዕግስትን ተላብሠሽ አምላክ እንዲረዳሸ ጸልዪ፡፡ የሚረዳሽ ከሆነ የቤተሰቤን ታሪክ ልጻፍልሽ የወንድሜ ነው በትዳር ሲኖር 15 ዓመት ይሆነዋል በዚህ ጊዜ ውስጥ 2 ልጆች አፍርቷል፡፡ ለልጆቹና ለባለቤቱ መልካም የሚባል ነበር ነገር ግን ከ 4 ወር በፊት ጀምሮ እስካሁን ድረስ በቤት ውስጥ አይመገብም፤ ልጆቹን አያቀርብም፤ ልብሱን የሚያጥበውም ሆነ ለራሱ የሚያስፈልገውን ራሱ ብቻ ነው፤ የሚያደርገው ባለቤቱንም እያሳዘናት ይገኛል ምን ሆነህ ነው ብላ ችግሩን እንዲነግራትም ሆነ የቤትዋን ሰላም ለማምጣት ብቻዋን ለፍታለች በጭራሽ ሊያናግራት ፈቃደኛ አየይደለም፤ ብቻ ጠዋት ከቤት ይወጣል ማታ እቤት ይገባል፤ እኛ ቤተሰቦቹ እንኳን ጉዳዩን የሰማነው ነገሩ ከአቅሟ በላይ ሲሆን እና ልጆቻቸው ደስታ እና ሰላም ማጣታቸው እረፍት ቢነሳት ነው፡፡ ታዲያ እንደጉዳያችን ወንድማችንን ለማነጋገር ያልተፈነቀለ ድንጊያ አልነበረም መልሱ ግን ዝምታ ብቻ ነው፡፡ የሚገርመው በጣም የተማረ የሚባል አይነት ሰው ነው ግን ምን ያደርጋል በዝምታ ራሱን አጥሮ ሰው እንዳያገኘው ማልዶ ከቤት እየወጣ በውድቅት እየገባ እኛም ግራ እንደገባን አለን በእርግጥ ከራሷ አንደበት የሰማነው ታሪክ አለ ይህም ለጋብቻ የበቀቁበት መንገድ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሳይሆን ጠንቋይ ቤት በምትሄድበት ጊዜ (አሁን ንሰሃ ገብታ ትታለች) ባል የሚሆንሽ ቤታችሁ ተከራይቶ የሚኖር ከመሐል አገር የሚመጣ ሰው ነው በተባለችው መሰረት ይህ ወንድሜ ለስራ ወደ ክ/ሀገር በሄደበት ሰኣት የቤተሰቦችዋን ቤት ተከራይቶ በሚኖርበት ወቅት በጠንቅዋይ የተነገራትን በማሰብ ሳያስበው አጥምዳ እንዳገባችው ጊዜ አልፎ ተናግራለች፡፡ ወንድማችን ይሄን በሰማ ጊዜ ቢያዝንም በፍቅርዋ ተረቶዋልና ባለማወቅዋነው ብሎ ነገሩን አቅልሎ በማየት ኑሮውን ሲኖር ነበር ታዲያ ከአመታት በኋላ እንዲህ መሆኑ ጥያቄ ብቻ ሆኖብናል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ሁላችንንም ይርዳን ፡፡ አንቺ እናት እኛ በወራት ያልቻልነውን ጉድ አመታት መታገስሽን አደንቃለው ጽናቱን ሰጥቶሽ ታሪክሽ ተለውጦ እግዚአብሔር እረዳኝ ደስም ብሎኛል ብለሽ ደግሞ እንድታበስሪን የድንግል ማርያም ልጅ ይርዳሽ ፡፡ እማምላክ በምልጃ ጸሎትዋ ፈተናውን ትለፍልሽ፡፡ አበቃው

  ReplyDelete
 47. 1, Tedare yatekedese, barasu kebur mehonu karto laljochae sele malate ayekabedm,
  2, Menem mereja belaelew neger ka asere amet belaye aberot yanore balon meterterot betam yasamemawal bately tamagnena afekari bale kahone hullun be zero sibaza mayet bezu neger yaregal.
  Waye degemo endih ayenet meserate yata tertare tadegagemo yametaket endayhone.
  3,Abatochen lamelak selk alanesa ale malet Endaet new yawem aberachehu eyenorachehu ebaet minorbetn tebko badengat kalhone. manem saw ko yazenebetn neger lalemasebm ayefalg enkuan la yerkerta.
  Ya yekerta tergum kalegebaw.
  Ahunem ba kahenat asetayekash hasabune ewaki, aleza yananet sekaye endale hono lalejochu sekeken naw yametehonut anede tarya megaratachehu aydelem lalejoch sibal menor, yenanta feker na selam temehert eski yalke belachu ka sebachehu lije honachehu yalayachehu yahel yesemagnal.
  5,Egziabher leben yayal tatsetsetash yekertan tayeki weda kenaw menged yemerash zend yasunem yedenedena lebe yefeta zend, batedarsh yagetemeshen fetena talfiw zened abezetash wada Egziabher tselyi.

  E.B

  ReplyDelete
  Replies
  1. የሰላም አምላክ አግዚአብሄር የገጠመሽን ችግር እንዲያስወግድልሽ በፀሎት ጠይቂው፡፡ ለእናቱ ለድንግል ማርያምም ንገሪያት::

   Delete
 48. bemejemeria egziyabher selamishin yimelisew elalew , neger gin bizu gize wondoch tsebayachew ketekeyayere ena sebeb kefelegu lemakuref lela begon sishareku new ene alifebetalehu silezih rasishin bemigeba lemechal mokirina ( be genzeb malete new) tigegnaw atihugn tinish ayitesh lijochishin yizesh wilik beyilet. yechinkilat selam ena tena yibeltal lelijochishim anchim esum tena sitihonunew tiru hiwot yeminorachew silezih 3 amet bizu new keegziyabher gar tinish gize sichiw ena titeshiw hiji . Don't be his dependent. keyazat gar yichemalek tinish koyito siselechew ena sikochew marign yilal. Adultory mechereshaw ayamirimina. lela bayiz bibeza hulet samint biyakorif new. rasishin tebike tenashin tenkebakebi , atinadeji, hulum yalfal...tikeribetalesh enji ayikeribishim. ayzosh ehite yetigil agarish negn ye wondin bahiriy awikewalehu. astekina le Setan ej yemisetu nachew.

  ReplyDelete
 49. "ሰዎች ስለችግራቸው ተወያይተው መፍትሔ እንዳያገኙ ችግርን በልብ ደፍኖ በሰውነት ስቃይ የሚጠዘጥዝ ፣ በቀረበልን ታሪክ አባቶችን የማያናግር ሰይጣን በየቤተታችን እያንኳኳ ነውና ለራሳችን ብቻ ሣይሆን ስለሁሉም ከምንግዜውም አሁን ተግተን ልንጸልይ እንደሚገባ እኔን ተሰምቶኛል:፡"

  ReplyDelete
 50. lijochish eskimereku betselot bemetsenat tibikiw minalbat limeles yichilal.

  ReplyDelete
 51. ኸረ ልጅ ማሰሪያው ኸረ ልጅ ገመዱ፣
  ጎጆማ ምን ይላል ጥለውት ቢሄዱ፣

  ታሪኩ ይህ ግጥም ትዝ እንዲለኝ ስላደረገ እንጂ ቤት ማፍረስስ መፍትሔ አይደለም፡፡ ቢሆን እግዚአብሔር እንደፈቀደ በጾም በጸሎትና በፍቅር ችግርን ለማሸነፍ መሞከር ደግ ነው፡፡ እኔ ግን አንድ ችግር ይታየኛል፡፡ ማናችንም ብንሆን የሰው እንጂ የራሳችን ችግር አይታየንም፡፡ ቢታየንም መጠኑ አንሶ ሸክሙ ቀሎ ነው፡፡ ስለዚሀ የአንድ ወገን ቅሬታ ሰምቶ መፍረድ ይቸግራልና በእውነት ህሊና ራስን ማየት ጥሩ ነው፡፡ ካልሆነም ሌሎች አይተው እንዲያሳዩን እድሉን ለአስታራቂ ሽማግሌ ሰጥቶ ስህተትን መቀበልና ይቅር መባባል ይሻላል፡፡

  እህቴ እኔም ባለትዳርና የ4 ልጆች እናት ነኝ፡፡ ላለፉት 18 ዓመታት የትዳርን ቀንበር በአግባቡ ለመሸከም የሚያስችል የሕይወት ልምድና ስልጠና ስቀስም ኖሬአለሁ፡፡ የፍቅሩ ሙቀትና የጥላቻው ውርጭ፣ የደስታውን ብርሃንና የሀዘኑ ጨለማ እንደክረምትና በጋ እየተፈራረቁብኝ፡፣ ካለኝ ልምድ ተነስቼ ሃሳብ ባካፍልሽ ብዬ ነው፡፡ እግዚአብሔርን በኑሮሽ እንድታስቀድሚና በጸሎት እንድትበረቹ የተለገሰሽ ምክር እንዳለ ሆኖ
  1. የባለቤትሽን ብቻ ሳይሆን ያንቺንም ጉድለት በንጹህ ህሊና መርምሪ
  2. እንዲህ ያለውና ከዚሀም የባሰ ችግር በየቤቱ አለና በአንቹ ቤት ብቻ የደረሰ ተአምር አድርገሽ ለጭንቀትና ለተስፋ መቁረጥ ቦታ አትስጪ
  3. እሱ አኮረፈ ጠላኝ ብለሽ ራስሽን አትጣይ፣ ይልቁንም ጥሩ በልተሽ ጥሩ ለብሰሽ ጥሩ ስሜት በውስጥሽ ፈጥረሽ ኑሪ፣ በልቶ ከሚያይሽ በልተሽ ታይው ይሉ ነበር እናቶች ሲመክሩን፡፡ ስለዚህ የሚያስደስትሽን ነገር አድርጊ ለራስሽ ጊዜ ስጪ፣
  4. የችግሩ መንስዔ ስለሆነችው ሴት በተለይም ግንኙነቱ እስከአሁን ያለ ከሆነ የነገሩን ስር አጣሪና ተጨባጭ መረጃ ይኑርሽ በውስጥሽ ጥርጣሬ እረፍት ሊያሳጣሽ አይገባም እውነቱን ማወቅ ስትችይ በእውነት ልብ ይቅርታ ለመጠየቅም ሆነ ይቅርታ ለማድረግ ይቻልሻል፣

  ReplyDelete
 52. እኔ ብሆን ለመድሐኒአለም በሙሉ ጉልበቴ በሙሉ ልቤ አልቅሼ እነግረዋለሁ። ጸላኤ ሰናይ ልቡናውን ከአንች እንዲያዞር ያደረገው ይመስላል፣ ከጸሎት ውጭ ምንም መፍትሔ ያለ አይመስለኝም። አልቅሽ!!!! አንችም በበኩልሽ ንስሐ ግቢ፣ በፍጹም መመለስ ወደኢየሱስ ክርስቶስ አልቅሽ!!!! እግዚአብሔር የማይሰማ መስሎሽ ሕመምሽን በየጓዳው አታባክኝ። የፍቅር አምላክ ፍቅር ይስጥሽ። አኔም እጸልይልሻለሁ።

  ReplyDelete
 53. ውድ እህቴ ይንን መልክትሽን ዘግይቼ በማንበቤ አዝናለሁ ሆኖም የዚህ የባለቤትሽ ችግር አንቺ የተናገርሽው ጉዳይ ከሴት ጋር ታይቶ የነቀፍሽው ሁኔታ አይመስለኝም ይህንንማ ማንም ሴት ታደርገዋለች ባሏን የምትወድ ሁሉ ሆኖም እኔ የሚመስለኝ እንዲህ ያስጨከነው ቀደም ብሎ በአንቺና በእርሱ መሐል የነበረ ችግር ግን ያልተፈታ እየተንከባለለ እዚህ የደረሰ ነው ብዬ ነው የማምነው ምናልባትም ችግሩ እንዳይፈታ ያደረገው ልጆቻችሁ ክፉና ደጉን ስላልዩ እሱም ዛሬ አንቺ እንደምትይው ልጆቹን ላለመረበሽ ብሎ ያልሽውን ሁሉ እሺ እያለ የኖረ ሰው የተጨቆነ ባል ይሆን ይሆንን?ምናልባት ለዚህ ሁሉ መፍትሄው ስለጋብቻ የተጻፉ ማንኛቸውንም መጽሐፍ መርምሪ ዓለማዊም መንፈሳዊም ሆኖ የማንኛውም ሃይማኖት ድርጅት ቢሆን ስለጋብቻ የተጻፉትን ብታነቢ አንድ ነገር ታያለሽ ከአቀራረብሽ ባልሽን ከዚያች ሴትዮ ጋር ስላየሽው ስለተቆጣሽው መስሎሽ የተቀየመ አይመስለኝም አንቺም እንደምታምኚው እርሱም ልቦናው ያውቀዋል ስለዚህ ቀደም ብሎ ትዳራችሁ ከተመሰረተ ጀምሮ ያልተፈታ እየተንከባለለ ያለ ጉዳይ ወይም ABUSE አድርገሽው ከሆነ ተንከባክበሽው ካልሆነ እንደሚስት ሳይሆን እንደገዢ እያሰቃየሽው እንደነበረ ራስሽን መርምሪ ግን ይህ ሁሉ ቢሆንም ትዳሩን ከፈለገ እርሱም ዛሬም ቢሆን ለውይይት ልቡን መቆለፍ የለበትም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ክርስቶስ እንዳስተማረው በቀን ሰባ ጊዜ እንኳን ቢበድልህ ሰባ ጊዜ መጥቶ ይቅርታ ቢጠይቅህ ይቅር በለው ነው የሚለው መቼም ቅድስት ቤ/ክርስቲያናችን አባቶችም ሳያስተምሩ ቀርተው አይደም የሚሰማ ጠፋ እንጂ ምነው ታዲያ እንዲህ እያለለት ቤቱን ሲኦል አደረገው ከጎልማስነት ሚስቱ ጋር መደሰት በሚችልበት ዘመን ምን ሸፈነበት?ልጆች ድሮ የልጅ ልጅ በሚስምበት ጊዜ ሰይጣን የጋረደው ነገር እኮ አለና በተቀረው በርትተሽ ጸልይ ጹሚ ከተቻለም ሱባኤ ውስጂ እግዚአብሔር ያታደጋልና አይዞሽ!
  ዮሴፍ ከአርማትያስ

  ReplyDelete
 54. እኔ እንደምረዳዉ፤-

  ሰዉየዉ ፍጹም ለትዳሩ ታማኝና አንችንም የሚወድ ይመስለኛል፤ምክንያቱም ያንች የጥርጣሬ ወይም የፍርሐት ማስጠንቀቂያ እጅግ ያሳዘነዉ ይመስለኛል፤ከዚህ ንግግሬ በፊት ነዉ እሱ የተለወጠብኝ ካልሽ ደግሞ ምነዉ ምን ነካህ የሚል ንጹህ የዉይይት ጥያቄ ማንሳት ነበረብሽ እንጅ ቀጥታ ከእርሱዋ ጋር ለማያያዝ መሞከርሽ ስህተት ይመስለኛል፤፤
  ለማንኛዉም፤-
  • የያዘዉ እስኪለቀዉ አይን አይኑን እያያችሁ ራሳችሁ ላይ አታዉጡት፤
  • ከልጆች ጋር መልካም ግንኙነቱን ይበልጥ እነዲያጠናክር አድርጊ
  • ወንድ ሆዱን ይወዳልና ለሆዱ ተጨነቂ
  • ትጉ የጸሎትና የቃሉ ሰዉ ሁኝ
  • በአለባበስም ሆነ በንጽህና ራስሽን ጠብቂ
  • በአባቶች በኩል ያለዉን እስከመጨረሻዉ ሂጅበት፤ይቀርሻል
  • ልምምጥ አታብዠ ኮራም በይ
  • እጅግ የሚወደዉ ዘመድ ወይም ጉዋደኛ ካለ በዚያም ጥረት አድርጊ
  • ከተቻለ ሌላም ግንኙነት እንደሌላት እርግጠኛ ከሆንሽ ሴትዮዋን
  በሽምግልና ብትጠቀሚባት፤
  • ጊዜ የማይፈታዉ የለምና ለችግሩ ሳትቸኩይ ጊዜ ስጭ
  መስቀል መከራ ነዉና ክርስቲያን እንደመሆንሽ ትዳርሽ መስቀል ሆኖብሻልና ተሸከሚዉ፤እሳትም ሆኖብሻልና ሙቂዉ እንጅ አትሰቀቂዉ፤ችግሩን ተሰቅቀሽ ከድጡ ወደ ማጡ እንዳትገቢ ተጠንቀቂ፤

  በተረፈ ችግርሽን በጥልቀት የምታዉቂዉ አንችነሽና ከማንም ቁልጭ ያለ መልስ አትጠብቂ አስተያየቶችን ለአንች እንደሚመችሽ አድርገሸ ተጠቀሚባቸዉ፤

  ‹‹ባለ ትዳሩ ነኝ ከባህር ዳር››

  ReplyDelete
 55. ልምድ ያለው አማካሪ ያስፈልግሻል ፡፡ ስለዚህ ጋሽ ተሰማ ሲመጣ አግኚው፡፡ አሁን ለጊዜው ከኢትዮጵያ ውጭ ነው፡፡ ከእርሱ ጋር ለመገናኘት የምትቺይበት ስልክ 0913-27-00-70 በዚህ ደውይላት ፕሮግራም ታመቻችልሻለች፡፡ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ይሁን፡፡አሜን፡፡

  ReplyDelete
 56. WHAT IS THE CAUSE FOR THE SILENCE OF HER HUSBAND? ,FROM WHERE IT BEGINS? when was the last time she speaks to her love peacefully? how was it ?. she has to riase such a question for her ownself and she must find the answer from the bottom of her own heart. ohh what is silence may be in his context it is qiyaame yes qiyaame we know what it means we are human not the heavenly angeles so we fellit but what is the source? may be he thougt that he loved his wife , he respect his family , is committed to keep his faith since the union and now what is his sin ,what makes him guilty he answered nothing but the said so why for all this suspicion why all they come against me. he feels he is lonely coz no one is trusted him, his wife his family but still he and his soul is clean he did no do the suspected sin so he keep with his faithfuness and silence (qiyame)so if I ware her I will show him how much he is trustful FOR HER AND FOR HIS FAMILY as long as I have no evidence FOR HIS SIN

  ReplyDelete
 57. ሁሉም ነገር የሚፈታው በፆም ፣ በፀሎት ስለሆነ ይህንን ችግር ፈጣሪ እንዲያስወግድላቹህ ሳታቋርጡ ጸልዩ እመብርሐን ችግራችንን ሁሉ ትፍታልን፡፡

  ReplyDelete