ይህንን ታሪክ የምትነግረን የአንድ ትልቅ ድርጅት መሪ ናት፡፡
«ልጅ እያለሁ እናቴ ከእኔ በአምስት ዓመት የምታንሰዋን ታናሿን እኅቴን ሁልጊዜ «እወድሻለሁ´ ስትላት እሰማ ነበር፡፡ እኔን ግን አልፎ አልፎ ካልሆነ በቀር እንደርሷ አዘውትራ «እወድሻለሁ» አትለኝም፡፡ እርሷ አልቃሻና ነጭናጫ ልጅ ነበረች፡፡ እኔም አልፎ አልፎ ታናሿን እኅቴን እንድከታተላትና እንድጠብቃት ትነግረኝ ነበር፡፡ ይህ ሁኔታ እናቴ እኔን አትወደኝም እንድል አደረገኝ፡፡ ስለዚህም «ቶሎ ቶሎ ተምሬ ወደ ኮሌጅ መግባት አለብኝ፡፡ ከማትወደኝ እናቴ ጋር ለምን እቀመጣለሁ» እል ነበር፡፡
«እንዳልኩትም ጠንክሬ ተምሬ ኮሌጅ ገባሁ፡፡ ኮሌጅ በመጀመርያ ሴሚስተር ላይ ቤቴ በጣም ይናፍቀኝ ነበር፡፡ በተለይ አባቴን ማግኘት እጅግ በጣም እፈልግ ነበር፡፡ እርሱ ለትምህርት ቤት የሚያስፈልገኝን ነገር ሁሉ ይልክልኝ ነበር፡፡ ናፍቆቱ ሲብስብኝ ግን «መምጣት እፈልጋለሁና የአውሮፕላን ትኬት ላክልኝ» አልኩት፡፡ እርሱም «አሁን ገንዘብ የለኝም፤ ሴሚስተሩ ሲያልቅ በዕረፍት ጊዜ ትመጫለሽ» አለኝ፡፡
«ከፋኝ፡፡ አባቴም እንደ እናቴ አይወደኝም ማለት ነው አልኩ፡፡ ቢወደኝ ኖሮማ እርሱ ሲናፍቀኝ ለምን ትኬት አይልክልኝም ነበር፡፡ በቃ በዚያ ቤት ውስጥ እኔን የሚወድ ስለሌለ ወደዚያ ቤት መሄድ የለብኝም ብዬ ወገቤን አሥሬ ተማርኩና ኮሌጅ ጨረስኩ፡፡ የመጀመርያ፣ ሁለተኛና የፒኤች ዲ ዲግሪዎቼን እያከታተልኩ በእልህ ተማርኩ፡፡
«አልፎ አልፎ ብቻ ወደ ወላጆቼ ዘንድ ስልክ እደውል ነበር፡፡ የማይወዱኝ ሰዎች ጋር ለገናም ሆነ ለመታሰቢያ ቀን ዝግ መሄድ አልፈልግም ነበር፡፡
«አንድ ቀን አንድ ጓደኛዬ «ላንድ ማርክ» የሚባል ኮርስ እየተሰጠ መሆኑን፣ እርሷም እየተማረች መሆኑን ነገረችኝ፡፡ ስለ ኮርሱ የሚያስረዱ ወረቀቶችንም አመጣችልኝ፡፡ ወረቀቶቹን ሳነባቸው ደስ የሚሉ ነጥቦች ስላገኘሁ ከፍዬ ተመዘገብኩ፡፡
«በኮርሱ ውስጥ «ሕይወትን መልካም ማድረግ» የሚል ክፍል ነበር፡፡ እንዴት አድርገን ነው ሕይወታችንን መልካም የምናደርገው? የትናንት ገጠመኛችንና ልምዳችን በዛሬውና በነገው ሕይወታችን ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ ያመጣል? ውሳኔዎቻችን ከየት ይመነጫሉ? ውሳኔዎቻችን ሁሉ ትክክል ናቸው ወይ? የተመሠረቱትስ በእውነታ ላይ ነው ወይ? እያለ ይተነትናል፡፡
«ክፍለ ትምህርቱ ሊጠናቀቅ ሲል መምህሩ በሕይወት ደስተኛ ለመሆን ከሚያስፈልጉን ነገሮች መካከል ሁለቱ ወሳኝ ናቸው አሉ፡፡ ይቅርታ መጠየቅና ይቅር ማለት፡፡ ይቅርታ የሚጠየቀውን ሰው ሳይሆን የሚጠይቀውን ሰው ይጠቅመዋል፡፡ በደል ሸክም ነው፤ ፀፀትም ሕመም ነው፡፡ ይቅርታ መጠየቅ ሸክምን ማራገፍና ሕመምን መፈወስ ነው፡፡ በደል ኅሊናን ያበላሻል፤ ውሳኔዎቻችንን ያበላሻል፡፡ አመለካከታችንን ያበላሻል፡፡ ስለ ሰው ያለንን እምነት ያበላሻል፡፡ ዘወትር የማይለቅ የቤት ሥራም ይሰጣል፡፡
«በደል ያለበት ሰው ሳይዘጋ መብራቱን ያጠፋ ኮምፒውተር ማለት ነው፡፡ ከላይ ሲያዩት ኮምፒውተሩ ሥራ ጨርሶ ያረፈ ይመስላል፡፡ በውስጡ ግን በሥራ የተጠመደ «ቢዚ» ነው፡፡ በደል ያለበት ሰው፣ የተቀየመም ሰው፣ በሰው ያዘነና ያኮረፈም ሰው ዕረፍት ያገኘ ይመስለው ይሆናል እንጂ ነፍሱ ግን «ቢዚ» ናት፡፡ በውስጧ የገባው ቫይረስ በማያስፈልጉ ሥራዎች ጠምዷታል፡፡ ለብዙ ነገር ልታውለው የነበረውን ችሎታና ጊዜ፤ ልብና አእምሮ፣ ነገር ለማብሰልሰልና ሁል ጊዜ ወደ ኋላ ለመጓዝ እንድታውለው አድርጓታል፡፡ በደል ያለበት ሰው ወደፊት ለመጓዝ ያዳግተዋል፡፡ አዘውትሮም ባሳለፈው ሕይወት ይጠመዳል፡፡ እያሉ መምህሩ አብራሩ፡፡
«ከዚያም አንድ የክፍል ሥራ ሰጡን፡፡ ቀጣዩን ክፍለ ጊዜ ከመጀመራችን በፊት አርባ ደቂቃ አለን፡፡ በዚህ አርባ ደቂቃ በሕይወታችሁ ያሳዘኑዋችሁ ሦስት ሰዎች ጋር ደውላችሁ እናንተ ይቅርታ ጠይቋቸው፡፡ ከዚያ ያጋጠማችሁን ነገር በቀጣዩ ክፍለ ጊዜ ከአርባ ደቂቃ በኋላ ትነግሩኛላችሁ፡፡ ክፍለ ጊዜው አበቃ፡፡
«እኔ መጀመርያ የደወልኩት እናቴ ጋር ነው፡፡ «እናቴ ይቅርታ ላለፉት አሥራ አምስት ዓመታት ተቀይሜሽ ነበር» አልኳት፡፡ «ለምን?» አለችኝ፡፡ ተገርማም፤ ደንግጣም፡፡ «ስለማትወጅኝ» አልኳት፡፡ «በምን ዐወቅሽ?» አለችኝ፡፡ «ታናሿን እኅቴን እንጂ እኔን እወድሻለሁ ብለሽኝ አታውቂም» አልኳት፡፡ «ታናሽ እኅትሽኮ ሕመምተኛ ናት፡፡ የተለየ ጥንቃቄ ያስፈልጋት ነበር፡፡ ሕመሟ እያበሳጫት ትነጫነጭ ነበር፡፡ ስለዚህ ሁልጊዜ እንደምወዳት ማወቅ ነበረባት፡፡ እንቺንኮ አምስት ዓመት ለብቻሽ አሳድጌሻለሁ፡፡ ጤነኛ ነበርሽ፡፡ አንቺ በሰላም እንድትማሪ፣ አባትሸም በሰላም እንዲሠራ እኔ እኅትሽን መከባከብ ነበረብኝ፡፡ አንቺ እንደ እርሷ ዓይነት ልጅ ቢኖርሽ ኖሮ ምን ታደርጊ ነበር?» ይህ ለእኔ አስቤው የማላውቅ ታሪክና አስቤው የማላውቅ ጥያቄ ነበር፡፡
«እውነቷን ነው፤ ታናሿ እኅቴ ስትወለድ ጀምራ ሕመምተኛ ነበረች፡፡ ማልቀስና መነጫነጭ የዘወትር ተግባሯ ነበር፡፡ እናቴ ምንጊዜም እርሷን ይዛ ታችኛው ቤት ትወርድ ነበር፡፡ አባቴ ለረዥም ሰዓት ስለሚሠራ ቤት ሲመጣ ዕረፍት ይፈልግ ነበር፡፡ የታናሿ እኅቴ ልቅሶ ደግሞ ይረብሸዋል፡፡ የተወሰነ ጊዜ ከእርሷ ጋር ካሳለፈ በኋላ ለቀጣዩ ሥራ ዕረፍት ለማግኘት ይተኛ ነበር፡፡ እውነትም እናቴ እኅቴን ባትከታተላት ኖሮ እኔ አልማርም ነበር፡፡ እኔ እኅቴን የምከታተለው እናቴ ገበያ ስትሄድና ምግብ ስትሠራልን ብቻ ነበር፡፡ ሌሊት እንኳን ዕረፍት አልነበራትም፡፡ ለካ ይሄ ሁሉ ለእኔ በነበራት ፍቅር ነበር፡፡ ለምን ግን ቀደም ብዬ ይህንን ማሰብ አልቻልኩም? አለቀስኩ፡፡ በስልክ እየሰማችኝ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ፡፡ «እና እናቴ እኔን ትወጅኝ ነበር» አልኳት በድጋሚ፡፡ «በርግጥ፣ ምን ጥርጥር አለው፤ አንቺኮ የመጀመርያ ልጄ ነሽ» አለቀስኩ፡፡
«ቀጥዬ ወደ አባቴ ነበር የደወልኩት፡፡ «አባዬ ተቀይሜህ ነበርና ይቅርታ» አልኩት፡፡ ግራ ገብቶት «ለምን አለኝ?» «ስለማትወደኝ» አልኩት፡፡ እርሱም እንደናቴ «በምን ዐወቅሽ?» ነበር ያለኝ፡፡ «ያኔ ናፍቀህኝ ልመጣ ነውና ትኬት ላክልኝ ስልህ እምቢ አልክ፡፡ ብትወደኝ ኖሮ ትልክልኝ ነበር» አልኩት፡፡
«እኔ መላክ አቅቶኝ አልነበረም፡፡ ከዚያ በላይ የሆነ ገንዘብ ለትምህርት ቤትሽና ለትምህርት መሣርያሽ እየከፈልኩልሽ ነበርኮ፡፡ ባልወድሽ ለምን እንደሌሎቹ ሠርተሽ ተማሪ አላልኩሽም? ለረዥም ሰዓት የምሠራውኮ የአንቺን ትምህርት ቤት ለመክፈል ነበር፡፡ ያን ጊዜ ግን አንቺ በእኔ ናፍቆት ምክንያት ከመጣሽ አትመለሽም ብዬ አሰብኩ፡፡ ካልተመለሽ ደግሞ ከትምህርትሽ ትስተጓጎያለሽ፡፡ ከንቱ ልጅ ሆነሽም ትቀሪያለሽ፡፡ ናፍቆቱ ያልፍልሻል፡፡ በትምህርት ግን ቀልድ የለም፡፡ ስለዚህ አልላክሁልሽም፡፡ እኔ መቼም እወድሻለሁ፡፡» ስሰማው አለቅስ ነበር፡፡ ልቅሶዬንም ዕንባዬንም መቆጣጠር አቅቶኝ ነበር፡፡
«እነዚህ ሁለቱ ገጠመኞቼ አንድ ነገር አስተማሩኝ፡፡ ለስሕተት ስለሚዳርጉን ሦስት ምዕራፎች፡፡ በሕይወት ጉዟችን፡፡ ለስሕተት የሚዳርጉን ሦስት ምዕራች አሉ፡፡ የሚመስሉን ነገሮች፣ የምንፈጥራቸው ታሪኮችና በፈጠርናቸው ታሪኮች ላይ ተመሥርተን የምንወስናቸው ውሳኔዎች፡፡
«አንዳንዴ በኑሯችን የምናያቸው የምንሰማቸውና የምንገምታቸው ነገሮች አሉ፡፡ ለእኛ የሚመስሉን፡፡ ልክ እኔ እናቴ ለእኅቴ የምትላትን፣ አባቴም ትኬት አልልክም ያለውን አጋጣሚ እንደተጠቀምኩበት ማለት ነው፡፡ ያ ሰው ያንን ያለበት፣ ያደረገበት፣ ወይም ያላደረገበት ምክንያት እኛ ካሰብነው ውጭ ሊሆን ይችላል፡፡ እኛ መሰለን እንጂ ሰውዬው እንደዚያ ማለቱም ላይሆን ይችላል፡፡ የምናየው ነገር እኛ ተርጉመን ተረድተነው እንጂ እንደተረዳነው ላይሆንም ይችላል፡፡
«ይኼ የመጀመርያው ነገር ነው፡፡ ነገር ግን ብቻውን አይቀርም፡፡ በዚህ የተሳሳተ ገጠመኝ ላይ እንነሣና የየራሳችንን ታሪኮች እንፈጥራለን፡፡ እናቴ እኔን እንደ እኅቴ አዘውትራ «እወድሻለሁ» የማትለኝ ስለማትወደኝ ነው ያልኩት የራሴ ፈጠራ ነበር፡፡ እናንተም እንዲሁ ትፈጥሩ ይሆናል፡፡ እንዲህ ማለቱ ነው፣ እንዲያ ማለቷ ነው፡፡ የተወችኝ በዚህ ምክንያት ነው፤ ያልጋበዘኝ እንዲህ አስቦኝ ነው፡፡ ሰላም ያላለኝ ለዚህ ወይንም ለዚያ ምክንያት ነው፡፡ ሰሞኑን የጠፋው፣ ያልደወለልኝ፤ ያላስተዛዘነኝ በዚህና በዚያ ምክንያት ነው እያልን የየራሳችንን ታሪኮች እንሠራለን፡፡ ለእነዚያ ታሪኮች ደግሞ ካለፉት ልምዶቻችን እየተነሣን እጅና እግር፣ ዓይንና ጆሮ፣ ፀጉርና ምላስ እናበጅላቸዋለን፡፡ ለብዙ ጊዜ በታሪኮቹ ላይ ከማሰባችንና ከመገጣጠማችን የተነሣም እውነተኛ ታሪኮች መስለው ይወጣሉ፡፡ በደንብ የተዘጋጀ የፊልም ረቂቅ ወይንም ባለሞያ የደረሰው ድርሰት ይመስላሉ፡፡ ትረካ እናበጅላቸዋለን፡፡
«እነርሱም በራሳቸው አያቆሙም፡፡ በእነዚህ የተሳሳቱ ታሪኮች ላይ እንነሣና ውሳኔ እንወስናለን፡፡ በቃ ከዛሬ ጀምሮ እለየዋለሁ፣ አልደውልለትም፣ እፈታዋለሁ፣ ስልኩን አላነሣም፣ ወዳጅነቴን አቆማለሁ፣ ወደ እርሱ ዘንድ አልሄድም፤ እንዲህና እንዲያ ብዬ እመልስለታለሁ፤ እንዲህ ወይም እንዲያ ዓይነት ርምጃ እወስዳለሁ እንላለን፡፡ በዚያ ውሳኔ መሠረትም እንኖራለን፡፡
«ሰውዬው እኛ እዚህ ደረጃ መድረሳችንን አያውቅም፡፡ ለኛ እርሱ የተቀየረ መስሎናል፡፡ የሚገርማችሁ ግን የተቀየርነው እኛ ነን፡፡ በፈጠርነው መረጃ፣ በሠራነው ታሪክ፣ በመጨረሻም በወሰንነው ውሳኔ የተነሣ ሳናውቀው እኛ ራሳችን ተቀይረን ሰውዬው የተቀየረ ይመስለናል፡፡ ዓይናችን ስለተቀየረ የድሮውን አናየውም፤ ጆሯችንም ስለተቀየረ የድሮውን አንሰማውም፤ ልቡናችን ስለተቀየረም እንደ ድሮው አድርገን አንረዳውም፡፡ ስለዚህ እገሌ ተቀየረብን እንላለን፡፡ አንዳንዴም እጅግ ብዙዎች የተቀየሩብንም ይመስለናል፡፡
ዘጉኝ፣ አገለሉኝ፣ ናቁኝ፣ አሾፉብኝ፣ ተጠቃቀሱብኝ፣ አሙኝ፣ ተመካከሩብኝ፣ አደሙብኝ እያልን እኛው ራሳችን ራሳችንን አግልለን አግልለን ሌላ ደረጃ ላይ እንደርሳለን፡፡ እኛው እንሸሻለን፣ እኛው እንጠፋለን፣ እኛው እንለያለን፡፡ አሁንም ግን ሌሎች ያደረጉት ነው የሚመስለን፡፡
[እኔ
እዚህ ላይ ሰይጣን ትዝ አለኝ፤ ከሰማያት ሲወድቅ እርሱ ወደ እንጦሮጦስ ሲወርድ «ሥላሴ ፈርተውኝ ሸሹ» ይል ነበር ብለው አበው ነግረውናል፡፡ እርሱ መሸሹን አያውቀውም ነበር፡፡]
«ስለዚህ እስኪ ለይቅርታ በር እንክፈት፡፡ ሰዎችን ብቻ ሳይሆን ታሪክንም ይቅር እንበለው፡፡ ምናልባት አንዳንድ በሕይወታችን የወሰንናቸው ውሳኔዎች መጀመርያም በተሳሳቱ መረጃዎች፣ ከዚያም በተፈጠሩ ታሪኮች የወሰንናቸው ሊሆኑ ይችላሉና፡፡ ምናልባት እኛ ከፊሉን የብርጭቆ ውኃ ከማየት ይልቅ ባዶውን የብርጭቆውን ክፍል አይተን ይሆናል፡፡ ያን ጊዜ ውኃውን የቀዳው ሰው ውኃ ማድረጉን ያያል፤ ውኃውን የተቀበለው ሰው ደግሞ ከውኃው መወሰዱን ያያል፡፡ ይኼኛው ተደረገ ሲል፣ ያኛው ተወሰደ ይላል፡፡ ሁለቱም ለምን? ይሉና የየራሳቸውን ታሪክ ይፈጥራሉ፡፡ የየራሳቸውንም ውሳኔ ይወስናሉ፡፡
«አሁንም ይህንን ትምህርት ላስተምራችሁ የመጣሁት ከእኔ እንድትማሩ ነው፡፡ ይህንን ክፍለ ጊዜ ስንጨርስ ደውሉና በሕይወታችሁ ያሳዘኗችሁን፣ ያስቀየሟችሁን ወይም ያስኮረፏችሁን ሦስት ሰዎች ይቅርታ ጠይቁ፡፡ ወይንም በሕይወታችሁ ያዘናችሁበትንና የተጎዳችሁበትን ታሪክ ይቅር በሉት፡፡ ምናልባት እኔ ካገኘሁት ርካታ፣ ሰላምና ትምህርት የበለጠ ታገኙ ይሆናል፡፡ መቀበል የመስጠትን ያህል፣ መብላት የማብላትን ያህል፣ መጠጣት የማጠጣትን ያህል፣ መልበስ የማልበስን ያህል አያስደትስም፡፡ ይህንን ደግሞ ስትመለሱ ትነግሩኛላችሁ፡፡ ክፍለ ጊዜው ሲያልቅ ሁሉም ወደየ ስልኩ ሮጠ፡፡
ሳንሆዜ፣ ካሊፎርንያ
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ በመሆኑ በተመሳሳይ ኅትመት ላይ ባታውሉትይመረጣል፡
Ante sew ene emelew manew yehene hulu fetera yecherehe i swear you will creat stories for ever i know you are born for this.thanks it is so nice and timely!
ReplyDeleteመልካም ትምህርት፡፡ ይህ አይነቱ ደራሽ ውሃ ያልወሰደው ማን አለ? ራሳችን ራሳችንን እያገለልን በሌሎች እያመኻኘን ሳንጠላ ጠልተን ሳንገፋ ራሳችንን ገፍተን መኖር ትልቅ ህመም ነው እግዚአብሔር ይማረን፡፡
ReplyDeleteameeeeeeeeeennnnnnnnnnn!!!!!
Deleteግሩም ነዉ ዳን ዳንኤልዕ፤ ስራህ ይባረክ!!!
ReplyDeleteእጅግ ማራኪ ፁሁፍ መልዕክቱ የልብን የሚነግር።
ግሩም ነዉ
DeleteBerta ejig betam tiru memihir neh!!!!
Geta yibarkih!
"እርስ በርሳችሁ ትዕግሥትን አድርጉ፥ ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው፥ ይቅር ተባባሉ። ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ።" ቆላ.3:13
ReplyDelete"Forbearing one another, and forgiving one another, if any man have a quarrel against any: even as Christ forgave you, so also do ye." Colossians 3:13
እግዚአብሔር ይስጥሽ
ReplyDeleteOh dani you're very awesome!
ReplyDeleteit is not good story people always thing in both dimensions of brain so don't be blinded there are a lot issues to be concerned about...
ReplyDeletenot clear
Deletethank you
ReplyDeleteHi dani ante yemititsifachew bemulu lehiwot genbi silehinu ketilbet
ReplyDeleteDear Dn. Daniel,
ReplyDeleteThank you for the very interesting article. I think it touches most of us and we should try to do by each and everyone. In my case, I decide to call my parents, relatives, freinds and others whom by any means made them to be angry by my doing.
In addition to this christianity also teaches about that and in our daily prayer we are saying "ignam yebedelunin yikir indeminil".
kebede
Thank you Dn. Dani for your excellent article. Really it touched my hidden life. I was just a lady you mentioned here. My life is filled by sorrow. I am a person with good attitude towards people, but these days I do not know the reason all those received any good from, are rewarding me an evil. I do not mind about their reward, but I am developing bad attitude towards them, and even decide to be keep far from anybody. I could not cure the wounds of my heart. Please all you who read these comment remember in your prayer.
ReplyDeleteow dear 'anonymus z june 8, 2012 3:43 Pm' let GOD be with you and help you.Because i know person like you.but i want to say one thing that if you don't mind about the response for your good did then you will not face any problem.The point is don't expect a reward for ur good did from any one except from GOD. All what you should do should be for GOD and you should expect the result from him.unless you are going to be crazy .sorry if i miss ur point but it was must to share my view.
Deleteegziyabiher yibarkih edmem yisteh!
ReplyDeleteአረ እንደዉ እግዚብሄር ይባርክህ ዲን ዳንኤል! በዚህ የቃል መዶሻ አለት ልቤን ሰበርከዉ"መቀበል የመስጠትን ያህል፣ መብላት የማብላትን ያህል፣ መጠጣት የማጠጣትን ያህል፣ መልበስ የማልበስን ያህል አያስደትስም"፡፡ እንግዲህ እኔም ስልኬን ይዤ ልሩጣ!
ReplyDeleteዛሬም ሌላ ት/ት… እግዜር ይስጥልኝ
ReplyDeleteThanks! Dan!
ReplyDeleteግሩም ነው! በርታ::
ReplyDeleteGod bless you more and more
ReplyDeleteዳኒ ጽሁፎችህን ይህን ጡመራ ከጀመርክ ጀምሮ ማለት እችላለሁ እከታተላለሁ፡፡ አስተያየት ስሰጥ ግን የመጀመሪያየ ነው፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ሰሞኑን እጂግ በጣም ያስጨንቀኝ የነበረን ከጽሁፍህ ጋር እጂግ ተመሳሳይ የሆነ በኔው በተፈጠረና በኔው በዳበረ ታሪክ ምክንያት በህይወቴ ውስጥ ከፍተኛውን ቦታ የሚይዝ ሰው አስከፍቼ ፤ በእርሱ መከፋት ደግሞ እኔው ራሴ እጂግ በመጨነቅ ላይ ሳለሁ ይሄንን ድንቅ አስተማሪ ጽሁፍ ሳነብ የተሰማኝ ስሜት በቃላት ለመግለጽ ከምችለው በላይ በመሆኑ ነው፡፡ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፡፡ እኔም ወደ ስልኬ ልሩጥ፡፡ዳኒ ጽሁፎችህን ይህን ጡመራ ከጀመርክ ጀምሮ ማለት እችላለሁ እከታተላለሁ፡፡ አስተያየት ስሰጥ ግን የመጀመሪያየ ነው፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ሰሞኑን እጂግ በጣም ያስጨንቀኝ የነበረን ከጽሁፍህ ጋር እጂግ ተመሳሳይ የሆነ በኔው በተፈጠረና በኔው በዳበረ ታሪክ ምክንያት በህይወቴ ውስጥ ከፍተኛውን ቦታ የሚይዝ ሰው አስከፍቼ ፤ በእርሱ መከፋት ደግሞ እኔው ራሴ እጂግ በመጨነቅ ላይ ሳለሁ ይሄንን ድንቅ አስተማሪ ጽሁፍ ሳነብ የተሰማኝ ስሜት በቃላት ለመግለጽ ከምችለው በላይ በመሆኑ ነው፡፡ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፡፡ እኔም ወደ ስልኬ ልሩጥ፡፡
ReplyDeleteወንድምየ ተባረክ!!!! ልጽፍ የተዘጋጀሁትን ነው በሙሉ የጻፍክልኝ! እዚህ ላይ የምረዳው ነገር ቢኖር በዳኒ ሁኖ የሚናገረን የጌታ መንፈስ የብዙ ሰዎች ችግርን መሰረት ያደረገ መሆኑን ነው!!!! ዳኒ እባክህ ወንድምየ ባንተ ያለውን የጸጋ ስጦታ ችላ እንዳትል!!!!!!!!!!!! እኔ ግን ወደ ስልኬ ሮጥ ዘንድ ተሳነኝ..ጸጸት ብቻ....ጸጸት ብቻ....ጸጸት ብቻ......ጸጸት ብቻ....አቤቱ ባሪያህ ይሰማልና በብዙ እድሜ በዳንኤል ተናገረኝ!!!!! ዳኒ ከሰማይ ያገኘኸውን ሁሉ ሰጥተኸኛል ባክህ ወደስልክ የሚያስሮጥ ድፍረትን ይሰጠኝ ዘንድ ጸልይልኝ!!!! ወይ ጉዴ ከዚህ በላይ እግዚአብሄርን ማይት ከይት ይምጣ....ውድ መምህሬ ቃለ ህይዎትን ያሰማልኝ!!!
Deletethank you Dn.Dani...
ReplyDeleteit really touching history.
it reminds me to do something for a person...which i never thought before.
ውድ ወንድማችን ዲያቆን ዳንኤል ቃለ ኅይወት ያሰማልን! ጽሁፎችህን ሁልጊዚም ነው የምናነበው የብዙዎችንም ኑሮ የሚታደግ እንደሆነ እናስባለን እግዚአብሔር እረጅም እድሜ እና ጤና ከበለጠ ማስተዋል ጋር ይስጥልን! ሰሙኑንን ወደቤተ ክርስቲያናችን እንደምትመጣ ሰምተን ደስ ብሎናል የዛ ሰው ይበለን! አሜን!
ReplyDeleteከሳንፍራንሲስኮ
ከሁሉም የሚደቀው የሰው ልጅ ለዘመናት የገነባው የተሳሳት መረጃ ለአምሮው ሲያስታጥቀው ኖሮ በሂሊናውም የሚታሰበውም አሉታዊ ህሳብ ለዘመናት ሲጎዱት ይኖራል በዚሕ አይነት ድንቅ አስተምሮ እራሳችንን መፈተሽ አለብን ማናችንም የግምት ተጠቂዎች ነን በዚሕ አጋጣሚ የፈረሳዮች አባባል ገልጨ ጽሁፊን ላጠናቅ "ከሩቅ ትልቅ መስሎኽ የተምለክትከው ስትቀርበውየገመትከውን ስይሆን ሌላ ሆኖ ታገኘዋለኽ " ምናባችን ከሚፈጥረው ስኽተት ከምናልባታዊ ግድፈት እራሳችን እጠብቅ ከዚሕ በፊት ለተሰሩ ስተቶች ይቅርት...ይቅርታ...ይቅርታ ብለን እንልመድ ከልብ !!
ReplyDeleteጠቅሞኛል አመሰግናለሁ።
ReplyDeleteGreat! Great! Thanks our brother D/n Daniel. God bless you!
ReplyDeleteከአመታት በፊት ጥላቻን በልብ ይዞ መኖር ፍም እሳት በእጅ ጨብጦ እንደመዞር ነዉ የሚል ሃሳብ ያላት ፅሁፍ አንብቤ ነበር እዉነት ነዉ እሳቱን እንዲቃጠል የፈለግነዉ ሰዉ ላይ እስክንጥለዉ እንደሚያቃጥለን ጥላቻን ማርገዝም እንዲሁ ነዉ ጥላቻችን በቀልን ወልዶ ያ ያቀድነዉን በቀልም እድልና አቅም ተገጣጥመዉ እስክንፈፅመዉ ራሳችንን ስናቃጥል እንቅፋት ሳይኖር እየዘለልን ራሳችን ደርሰን ራሳችን ፕሮዲዩስ ባደረግነዉ ሆረር ፊልም እየደነበርን ምናልባትም እነርሱ ከበደሉን በላይ ራሳችንን እየበደልን እንኖራለን አስቸጋሪዉ ነገር ግን ይህን ሁሉ አዉቀህም ልታጠፋዉ አለመቻል ነዉ እኔም ለልብ እንጂ ለጀሮም ዳገት የለዉምና ደስ ብሎኝ ስማሁት ግን እንዴት ብሎ ይተግበር
ReplyDeleteእንዲያዉም አንዳንዴ ይላመደንና በለት ተለት ዉሏችን ላይ ሁሉ መንፀባረቅ ይጀምራል ከዚህ ሲበረታ ደግሞ የአእምሮ ህመም ይሆናል
i guess we the majority of us miss this cream part of life YEKERTA !
DeleteGO ! DANIEL,SAY MORE.
H
Memhir sele ewente elehalew yih hunyta bene lay agatemogn yemiwedew sew yehenenu miker setogn lemasetekakel bemokerim bedneb amgne letewew gin alechalekum neber yihnene saneb gin aselekesegn Egziyabher b ndem belela yinageral sew gin ayastewelm yemilewn asebeku Betam amesegnalehu yihe lene yetesafe esekemeselegn dires new yetesemagn.Egziyabher beneger hulu kante gar yihun melekam yehonewn hulu eweket inedeseth emegnalew.Amen.
ReplyDeleteአሁንም ይህንን ትምህርት ላስተምራችሁ የመጣሁት ከእኔ እንድትማሩ ነው፡፡ ይህንን ክፍለ ጊዜ ስንጨርስ ደውሉና በሕይወታችሁ ያሳዘኗችሁን፣ ያስቀየሟችሁን ወይም ያስኮረፏችሁን ሦስት ሰዎች ይቅርታ ጠይቁ፡፡ ወይንም በሕይወታችሁ ያዘናችሁበትንና የተጎዳችሁበትን ታሪክ ይቅር በሉ
ReplyDeleteእኔም ደውዩ ተሳክቶልኛ እግዚአብሔር እድሜና ጤናውን ያብዛልህ
ሊገጥም ይችላል
ReplyDeleteዳኒ ያንተን ምክር ተጋባራዊ ለማድረግ ወዳጆቼ ፈረንጅ መሆን ነበረባቸው:: ምክንያቱንም ለቤት መሥሪያ እያልኩ የላኩለትን ገንዘብ የበላኝን የቀድሞ ወዳጄን የምልክልህ ገንዘብ አጥሮህ ይሆናል ከቤት መሥሪያው ላይ የወሰድከው ይቅርታ አድርግልኝ ገንዘቡ በመጥፋቱ ተናድጄ ስለተናገርኩ አልኩት:: የልብሽን ተናግረሽ ይቅርታ ብሎ ስልኩን ጆሮዬ ላይ ጠረቀመው:: እኔም ጽሁፍህን በኢሜሉ ላኩለት:: ሊገጥም ይችላል ወዳጆች ለምሕረቱም የሚገባ ወግ ይህ ነው አበዳሪ ሁሉ ለባልንጀራው ያበደረውን ይተዋል የእግዚአብሔር ይቅርታ ታውጆአልና ያበደረውን ከባልንጀራው ወይም ከወንድሙ አይሻ።/ዘዳ.15:2/ ተብሎአልና የሚገጥመን ምላሽ ወደ ኋላ እንዳይጎትተን::
Obviously give me constructive comment and Kale Hiwotin Yasemalin
ReplyDeleteበጣም ግሩም ይህ ለሁላችን የምጠቅም አንተም ክሁሉም የጸዳ ስራ ስራ ልብህን ንጹህ አድርግ አንተም ቅመኛ አትሁን የይቅርታ ሰው ሁን እድሜያችን በጣም አጭር ነው
ReplyDeleteplease dani why don't u give me your hand for my question that i have sent u in gkibret@gmail.com or if u can't tell me clearly since i am expecting u till now for your response....
ReplyDeletethanks.....
Dn, Egziyabher yistlin.
ReplyDelete-|-
Dani Egziabehaire Yibarkehe! Dikemetene kuleche adergo yemiasaye tsehufe new yasenebebekene.
ReplyDeleteEgziabhere Yestellen! qalehiwotenem yasemalen!Amlak endenetegeberew birtatun yesten! Amen!
ReplyDeleteA very difficult assignment. I usually give 3 chances before I decided to stay away from anyone. It is very diffuclt to read human minds. But one thing for sure most of us are fakes. I forgive the ppl who really hurted me in my life 10 years ago. I was pure and guss what God made me suffer more.... Sometimes I envey ppl who has it all - ppl who act like angel and does all the evils---- I am not saying I am with out weakness but to forgive ppl who are fake---- i can not do it. ( i just retrned from church)
ReplyDeleteበጣም ትክክልና አስተማሪ መሆኑን አምኜበታለሁ ተግባራዊ ለማድረግም እጥራለሁ::ሆኖም ግን ሰዎቹ ይቅርታህን ባይቀበሉትስ ይባስ ብለው ለመሳቅያና ለመሳለቅያ ቢያደርጉትስ ምን ታደርጋለህ? መፍትሔው ጠቆም ቢደረግ::
ReplyDeleteSara
ReplyDeleteDiakon Daniel Kibret
Egziabiher Yibarkih!
EmeAmlak Titebikih!!!
it is nice eukation forevery one i learn mentings god beles u very good work i like it
ReplyDeletehmhmhmhmhmhm well it is critical point and it is must as a christian to accept it but it is difficult but i have to do it.what if i don't ask them 'apologize'in person or via telephone but i use to apologize within my heart and for my self ?
ReplyDeleteTHANK YOU
DeleteGETA YIBARIKEH DANIYE!! BIRUK HUN.
ReplyDeleteDani yeteret abat, sint teret negerken. Mine anid ken enkua wongel sebkehen bitmot
ReplyDeleteበክርስትና ውስጥ ሁለት ዓይነት አብይ አማኞች (ቤተ-እምነቶች) እንዳሉ ማስተዋል ችያለሁ:: ሰዎች ወደ ወንጌል ሂደው ወንጌሉ ባዘጋጀላቸው ቦታ ራሳቸውን ለማስገባት የሚጥሩ እና በዎንጌሉ ውስን ቦታ መኖራችን ዘላለማዊ ህይዎት ያስገኘናል ብለው የሚያምኑ እና ወንጌሉን ወደራሳቸው አምጥተው ወንጌሉ እነሱነታቸውን እንዲሸፍንላቸው የሚጥሩ እና በዚህም ወንጌሉ ሸፍኖናል እና ህይዎትን ዘላለማዊ ህይዎትን እናገኛለን ብለው የሚያምኑ::
Deleteበ እኔ ትዝብት የመጀመሪያዎቹ አማኞች ከዎንጌሉ ጋር ተጣጥመው መኖር ግድ ሲላቸው በሁለተኛዎቹ አማኞች ዘንድ ደግሞ ወንጌሉ ከ እነሱ ህይዎት ጋር ይጣጣም ዘንድ ግድ ይለዋል::
ስለዚህ ውድ ዎንድሜ/እህቴ ይህ የዲያቆን ዳንዔል ጡመራ በተለይ ለመጀምሪያዎቹ አይነት አማኞች የዎንጌሉን ህይዎት መኖር ይችሉ ዘንድ የሚያግዛቸው እና ህይዎታቸውን ለ ዎንጌሉ ቃል እና ህይዎት የበለጠ የቀረበ ይሆን ዘንድ ያግዛቸዋል የሚል ስሜት አለኝ:: እናም ይህን የመሰለ አስተማሪ ጽሁፍ ምንም እንደማይፈይድ መተቸት ተገቢ አይመስለኝም:: ጽሁፉ ካልተስማማህ/ሽ አለማንበብን የመሰለ መልካም አማራጭ እያለ የግል ጸሃፊህ/ሽ እንደሆነ ሁሉ ይህን አስተማሪ እና በብዙዎች ዘንድ ተፈላጊ የሆነን ጽሁፍ ስለጻፈ ዲያቆን ዳንዔልን መዝለፍ ተገቢነቱ አልታየኝም::
Egziabher yebelete andebet yhunih...Kale hiwot yasemalin !
ReplyDeleteshe was mistaken to think that her family hates her.but i can tell u my chapters which i understood clearly.my family hates me 4 real.and am not mistaken about that.in fact just like the story teller i really hated to go home not only during the break between semesters,but even during summer time at the end of the year.she is lucky her family sends her enough money to let her live through the year.u hv no idea hw angry i am feeling right now when am writing this.but believe me when i tell u that i forgive them,because that is what i learned to do very well since childhood.forgiveness is the key to make it through the day,when the day is showing u hate and rejection.so if there is any body out there who is hated 4 real i wana say to them "just forgive them" and if u cant do that dont think about them to much.and dani tnx r sharing this
ReplyDeleteሆኖም ግን ሰዎቹ ይቅርታህን ባይቀበሉትስ ይባስ ብለው ለመሳቅያና ለመሳለቅያ ቢያደርጉትስ ምን ታደርጋለህ? ላልከው ወንድሜ - ይቅርታህን ባይቀበሉት አንተ ግን ነጻ ነህ ከልብህ ብቻ ይቅርታ ጠይቅ ከእግዚአብሔር ታገኘዋልህ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ይቅርታን እንደ ፍርሃት እንደ ሞኝነት÷ ........ አስመስለው የሚተረጉሙ አይጠፉምና በዚህ ነገር ወደኋላ እንዳትል፡፡
ReplyDeleteGod bless u please Dani rather than simply teaching tell us how can do such like your activity ,the way how can develop our mind
ReplyDeleteበርታ.... ብዕርህ ዋዘኛ አይደለችም፡ መሰረት ቁፋሮ ለጉራማይሌው ትውልድም ጭምር ይደርስ ዘንድ አስብበት፤ ይገርማል ከዘመኑ የቀደመ ሾተል ወይስ ብእር?
ReplyDeleteይቅርታ በረከት አልያም ስጦታ ፤
ይቅርታ መለኪያ ሚዛን ለሰብዕና፤
ይቅርታ ቁልፍ ብትሆን ለሕይወት መዝጊያ፤
ይቅርታ ላደርግልህ እችላለሁ ግን አልረሳሁም ዘወትር..የሚል ፍጡር አለና ምን ትላለህ? ታዳሚው ምኞቴ ይበቃል ከፍሎሪዳ ጫካ
ለስሕተት ስለሚዳርጉን ሦስት ምዕራፎች፡፡ በሕይወት ጉዟችን፡፡ ለስሕተት የሚዳርጉን ሦስት ምዕራች አሉ፡፡ የሚመስሉን ነገሮች፣ የምንፈጥራቸው ታሪኮችና በፈጠርናቸው ታሪኮች ላይ ተመሥርተን የምንወስናቸው ውሳኔዎች፡፡
ReplyDeleteIt's interesting. I got many many things! Thanks.
ReplyDeleteበጣም ትልቅ እና አስተማሪ ጽሁፍ የውስጥን የሚነካ ነው ዳኒ ምልክቱን ሰላስተላለፍክልን ቃለ ህይወትይ ያሰማህ!
ReplyDeleteዳኒዬ ኑርልን . አስተማሪ የሆነ ፅሁፍ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ነገሮችን በበጎ መጠርጠር መልካምና ለህይወታችንም ሰላም የሚሰጥ ነው፡፡ ዝም ብለን መጥፎ መጥፎውን ብቻ ከሆነ የምንጠረጥረው የመጀመሪያውና በከፍተኛ ደረጃ ተጎጂዎቹ እኛው ስለምንሆን በበጎ መጠርጠሩ ነው የሚያዋጣን፡፡ በተረፈ ትዕግስትን ገንዘብ ማድረግ በክፉ የጠረጠርነውን ነገር ወደ ድርጊት እንዳንቀይረውና የባሰ ችግር ውስጥ እንዳንገባ የሚያደርግ ጥሩ መሳሪያ ነው፡፡
ReplyDeleteits nice story i relay like it keep it up.
ReplyDeleteDANI MARIAMN TEAMIR SERAH YIH NEGER EYASCHENEKEGH BESEATU ANEBEBKUT EGZIABHER YIBARKH
ReplyDeleteDani its big message for my life and it helps a lot for leading easy life! GOD bless you!
ReplyDeleteDani it is big message it helps me to see my back life.
ReplyDelete«በደል ያለበት ሰው ሳይዘጋ መብራቱን ያጠፋ ኮምፒውተር ማለት ነው፡፡ ከላይ ሲያዩት ኮምፒውተሩ ሥራ ጨርሶ ያረፈ ይመስላል፡፡ በውስጡ ግን በሥራ የተጠመደ «ቢዚ» ነው፡፡
ReplyDeleteውድ ዲ/ዳንኤል፤ እጅግ ጣፋጭ ምክር ነው። በእውነት ሙሉ ምስጋና ይድረስህ! ይሁን እንጅ ይህን ጽሁፍ ከማንበቤ በፊት ያስቀየሙኝን ዘመዶቼን በስልክም በአካልም ይቅርታ ጠይቄ ነበር። የነፍሴ እርካታም ልዩ ነበር። የሰላም እንቅልፍ ተኛሁ፣ ሰው ሁሉ «ውብ ነው» የሚል ስሜት በውስጤ አንሰራራ። ይቅርታ ያልኳቸው ዘመዶቼ ግን በግልባጩ ምን ቢያስብ ነው ይቅርታ ያለው በሚል በጥርጣሬ ያዩኝ ጀመር። ኩርፊያቸውም ባሰባቸው። ውጤቱ ለእኔ ጥሩ ስሜት ቢፈጥርብኝም ሙሉ አልነበረም። በተደጋጋሚ በግልጽ ብንነጋገርም ችግሩን መፍታት አልተቻለም። ለማነኛውም እ/ብሄር ይባርክህ!
ReplyDeleteThank You Dn Daniel! God Bless your work!
ReplyDeleteዳኒዬ ኑርልን . አስተማሪ የሆነ ፅሁፍ ነው
ReplyDeleteዳን እንዴት ብዬ እንደምገልጽልህ አላውቅም በጣም ስቦኝ ነው ያነበብኩት ምክንያቱም ሰዎች ሁልጊዜ የምንወድቀው ሆነ የምንሳሳተው የሌላውን ሰው የሚየስበውን ለማሰብ ስንሞክር ነው ፡፡ ከዚህ ይልቅ ስለራሳችን ብናስብ መልካሙን ሁሉ ማግኘት እንችላለን፡፡ከውስጣችን መልካምን የምናወጣ ከሆነ መልካምን እንቀበላለንና፡፡ እግዚአብሔር ይባርክህ ከልቤ!!!
ReplyDeleteegziabhair yebarekeh
ReplyDeleteegz. yebarkelene
ReplyDeletegeta yebarkeh, Dany, just do it for future also, donot stop it, Thanks to GOD.
ReplyDelete