Tuesday, May 29, 2012

ስኳር

clik here for pdf 
አንድ መምህር ሁለት ትልልቅ የመስተዋት ገንቦዎች ይዞ ወደ ክፍል መጣ፡፡ ሦስት ተማሪዎች ደግሞ በካርቶን ሌሎች ሦስት ነገሮችን ተሸክመውለታል፡፡ ተማሪዎቹ ከመቀመጫ ተነሥተው ተቀበሉት፡፡
መምህሩ ትልልቁን የመስተዋት ገንቦዎች በተማሪዎቹ ፊት ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠው፡፡ ሦስቱን ካርቶኖቹን ደግሞ በጎን አደረጋቸው፡፡ መጀመርያ ትልልቅ ድንጋዮች አነሳና በአንደኛው የመስተዋት ገንቦ ውስጥ እስካፉ ድረስ ከተታቸው፡፡ ከዚያም ተማሪዎቹን አንድ ጥያቄ ጠየቃቸው፡፡
 «ይህ የመስተዋት ገንቦ ሙሉ ነውን?´
ተማሪዎቹም በአዎንታ ራሳቸውን ነቀነቁ፡፡
ከዚያም ቀጠለና ትንንሽ የከበሩ ድንጋዮችን አንሥቶ ወደ መስተዋቱ ገንቦ ውስጥ ከተታቸው፡፡ በድንጋዮችና በድንጋዮቹ መካከል በሚገኙ ባዶ ቦታዎች ወስጥ እየገቡ የከበሩት ድንጋዮች ገንቦውን ሞሉት፡፡ መምህሩም ተማሪዎቹን በድጋሚ ጠየቃቸው፡፡
«አሁንስ የመስተዋቱ ገንቦ ሙሉ ነውን?´
ተማሪዎቹም ሙሉ መሆኑን ተናገሩ፡፡
ቀጠለና መምህሩ ከሦስተኛው ካርቶን ስኳር እያፈሰ ወደ መስተዋቱ ገንቦ ውስጥ ከተተ፡፡ በቀሪው ባዶ ቦታ ውስጥ እየገባ ስኳሩ ሞላ፡፡ መምህሩም የተለመደ ጥያቄውን ጠየቀ፡፡ «የመስተዋቱ ገንቦ ሙሉ ነውን?´
ተማሪዎቹም በአዎንታ መለሱ፡፡
እንደገና መምህሩ ሁለተኛውን የመስተዋት ገንቦ አቀረበ፡፡ ከዚያም በተቃራኒው ስኳሩን በመስተዋቱ ገንቦ ውስጥ ሞላበት፡፡ ተማሪዎቹንም ገንቦው ሙሉ መሆንና አለመሆኑን ጠየቀ፡፡ ተማሪዎቹም ሙሉ መሆኑን መሰከሩ፡፡ በመቀጠል ድንጋዮቹን ለማስገባት ሞከረ፡፡ ነገር ግን ስኳሩ ሁሉንም ቦታ ስለያዘው ማስገባት አልቻለም፡፡ ለከበሩ ድንጋዮች የሚሆን ቦታም አላገኘም፡፡
መምህሩ ከሁለቱ የመስተዋት ገንቦዎች ፎት ቆመና ተማሪዎቹን ሃሳብ ጠየቃቸው፡፡ የመጀመርያው የመስተዋት ገንቦ ሦስቱንም ነገሮች ሲያስገባ ሁለተኛው ገንቦ ለምን አልቻለም? የመጀመርያው ገንቦ ድንጋዩን ሲያስገባ ሙሉ ነበረ፡፡ የከበሩ ድንጋዮች ሲጨመሩም ሙሉ ነበረ፡፡ ስኳሩም ሲጨመር ሙሉ ነበረ፡፡ ሁለተኛው ገንቦ ግን በስኳሩ ብቻ ሞላ፡፡ ለምን?
በሕይወታችሁ ውስጥ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ አለ መምህሩ፡፡ የመስተዋት ገንቦ ሕይወታችሁ ናት፡፡ ድንጋዩ፣ የከበሩት ድንጋዮችና ስኳሩ ደግሞ በሕይወታችሁ ውስጥ ቅድሚያ የምትሰጧቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡ ሰው በሕይወቱ ውስጥ የሚያስፈልጉትም ሆኑ የሚፈልጋቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ የሚያገኙትም ሆኑ የሚያገኛቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ የሚገጥማቸውም ሆኑ የሚያጋጥሙት ብዙ አማራጮች አሉ፡፡ ሁሉም ቦታ ይይዛሉ፡፡
አንዳንዶቹ ነገሮች እነርሱ በሕይወታችን ቀድመው ከገቡ ለሌሎቹ የሚሆን ቦታ የማይኖራቸው ናቸው፡፡ እነርሱ ብቻ ከሞሉ የሌሎችን ቦታ ይይዛሉ፡፡ ለሌሎች ቦታ እንተው ካልን ደግሞ እነርሱ ይጎድላሉ፡፡ በሌላም በኩል አንዳንዶች እነርሱ በሕይወታችን ቢሞሉም ለሌሎች ቦታ ያላቸው ናቸው፡፡
በመጀመርያው ገንቦ ውስጥ ድንጋዩን ስናስገባው ገንቦው ሙሉ ነበረ፡፡ ነገር ግን ለሌሎች መግቢያ የሚሆን ቦታ ነበረው፡፡ ድንጋዩ ምንድን ነው? በሕይወታችን የመጀመርያ ቦታ ልንሰጣቸው የሚገቡ ነገሮች አሉ፡፡ እምነታችን፤የሕይወት መመርያዎቻችን፤ ማንነታችን፣ ቤተሰባችን፣ ሀገራችን፣ ለእውነት የምናደርገው ተጋድሎ እነዚህ መጀመርያ በሕይወት ገንቧችን ውስጥ ከገቡ ሕይወታችን ሙሉ ትሆናለች፡፡
ተመልከቱ መጀመርያ ድንጋዩ ከገባ በኋላ ብንተወው እንኳን ገንቦው ግን ሙሉ ነበር የሚሆነው፡፡ ማለት ምን ማለት ነው፡፡ ገንቦው ሙሉም ጎዶሎም ነበር ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ጎዶሎነቱ ሙላቱን አልቀነሰውም፡፡በቃ ገንቦው ሊይዘው የሚችለው የድንጋይ መጠን ያንን ብቻ ነበረ፡፡ ስለዚህ ሙሉ ነበረ፡፡ ገንቦውን ሙሉ ለማድረግም እርሱ ብቻ በቂ ነበረ፡፡ ነገር ግን ቦታም ነበረው፡፡
ከላይ ያነሣናቸው ነገሮች በሕይወታችን ካሉ ሕይወታችን ሙሉ ትሆናለች፡፡ ነገር ግን ለሌሎችም ነገሮች ቦታ ይኖሯታል፡፡ ምናልባት ግን የከበሩ ድንጋዮችና ስኳሩ እንኳን ባይኖር ሙሉ እንደሆነች ትቀጥላለች፡፡ ሀብታም አንሆን ይሆናል፤ ታዋቂ አንሆን ይሆናል፤ ሁሉ ነገር የተሳካልን አንሆን ይሆናል፤ ከኛ ተርፎ ለሌለ የምንሰጥ አንሆን ይሆናል፤ ለመትረፍረፍና ለመዝናናት የሚበቃ ነገር አይኖረን ይሆናል፡፡ እንዲህም ሆኖ እንኳን ሕይወታችን ግን ሙሉ ትሆናለች፡፡
ሕይወትን የሚሞላት እንደ ድንጋዩ ጠንከርና ከፍ ያሉ ነገሮች ናቸው፡፡ እምነትና የሕይወት መመርያዎች ዋነኛ የሕይወት ሙላቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ካሉ የከበረው ድንጋይና ስኳሩ ባይኖሩ እንኳን ሕይወት ግን ሙሉ መሆንዋ አይቀርም፡፡ ሕይወትን በዋናነት የሚሞሏት እምነትና የሕይወት መመርያዎች ወይንም አቋሞች ናቸው፡፡ ችግር ችግር የሚሆነው በራሱ ችግር ስለሆነ አይደለም፡፡ ችግር ችግር የሚሆነው በችግር ዓይን ሲያዩት ነው፡፡
በኢንዱስትሪ አብዮት ዘመን ሁለት ሰዎች ከአንድ የጫማ ፋብሪካ ተልከው ወደ አፍሪካ መጡ፡፡ የጫማ ገበያን ጉዳይ ሊያጠኑ፡፡ ሁለቱም ሰዎች የተለያያ ሪፖርት ይዘው ተመለሱ፡፡ የመጀመርያው ሰው «እዚያ ለጫማ የሚሆን ገበያ የለም፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ሰዎች በባዶ እግራቸው ነው የሚሄዱት´ አለ፡፡ ሁለተኛው ሰውዬ ደግሞ «እዚያ ከፍተኛ የጫማ ገበያ አለ፤ ምክንያቱም አንድም ጫማ ያለው ሰው የለምና´ ብሎ ሪፖርት አቀረበ፡፡
አያችሁ ሁለቱም በአንድ እውነታ ላይ ተስማምተዋል፡፡ የሄዱበት ቦታ ጫማ ያደረገ ሰው የለም፡፡ በመርሐቸው ግን ተለየይተዋል፡፡ አንዱ እንደ ችግር የቆጠረውን ሌላው እንደ ዕድል ቆጥሮታል፡፡ ስለዚህ በሕይወታችሁ ውስጥ አምነትና መርሕ ካለ ሕይወትን ሙሉ ያደርጋታል፡፡
ማለት ግን ለሌሎች ነገሮች ቦታ አይኖራችሁም ማለት አይደለም፡፡ አሉ ሌሎች ነገሮች፡፡ ትምህርት፣ ሥራ፣ ዕድገት፣ ትዳር፣ ልጆች፣ ሌሎችም ነገሮች፡፡ በእምነትና በመርሕ አስቀድሞ ሕይወቱ የተሞላ ሰው ለእነዚህ ነገሮች በቂ ቦታ አለው፡፡ ሳይጎድ ልበት መሙላት የሚችል ቦታ አለው፡፡ የዚያኛውን ቦታ ሳያስለቅቅ ነገር ግን ለእነዚህም ቦታ ይኖረዋል፡፡
አለ ደግሞ ሦስተኛው ነገር፡፡ ስኳሩ፡፡ እንደምታውቁት ዛሬ ዛሬ ብዙ ሰዎች ስኳር እየተው ነው፡፡ ካልሆነም ደግሞ እየቀነሱ ነው፡፡ በሕይወታችንም እንደ ስኳር ያሉ ነገሮች አሉ፡፡ ለእነርሱም ቢሆን ግን ሕይወታችን ቦታ አላት፡፡ ግን መጀመርያ ድንጋዩና የከበሩት ድንጋዮች ከገቡ ነው፡፡
አስቀድማችሁ ስኳሩን ቦታ ካስያዛችሁት ለሌላ ነገር የሚሆን ቦታ አታገኙም፡፡እንዲህ ያደረጉ ሰዎች አሉ፡፡ መጀመርያ ሕይወታቸውን በትርኪ ምርኪ ነገር የሞሉ፡፡ በመዝናናት፤ በክብርና ዝና፤ በቧልትና ቀልድ፤ የሞሉ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች በኋላ ለሌሎች የሚሆኑ ቦታ አያገኙም፡፡ ካልሆነም የግድ የእነዚያን ቦታ ማስለቀቅ ይኖርባቸዋል፡፡ የገባን ማስወጣት ደግሞ ቀላል አይደለም፡፡
አንዳንዶች ከትዳር በፊት የለመዱትን ስኳር በትዳር ወቅት ማስለቀቅ አቅቷቸው መከራ ያያሉ፡፡ አንዳንዶች ከሥልጣን በፊት የለመዱትን ስኳር መላቀቅ አቅቷቸው ለመርሕና እምነት ቦታ አጥተዋል፡፡ አንዳንዶች ከትምህርት በፊት የለመዱትን ክፉ ስኳር በዕውቀት መተካት አቅቷቸው ይሰቃያሉ፡፡
ለመሆኑ በገንዘብ፣ በሥልጣን፣ በቆንጆ ወንዶችና ሴቶች፣ በግብዣና በስጦታ በቀላ የሚደለሉ ሰዎች አላያችሁም? ለምን ይመስላችኋል? እነዚህ ሰዎች ሕይወታቸው በስኳሩ ብቻ የተሞላ ስለሆነ ነው፡፡ በሕይወታቸው ውስጥ ምንም ዓይነት ጠንካራ ዐለት የለም፡፡ ምንም ዓይነት የከበረ ድንጋይ አልገባም፡፡ እነርሱ በስኳር ብቻ የተሞሉ ናቸው፡፡
ያንን ስኳር ደግሞ ማሟሟት ቀላል ነው፡፡ ዐለቱ ግን አይሟሟም፡፡ የለመዱትን ስኳር እያላሱ እንደፈለጉ እምነታቸውንም ሆነ አመለካከታቸውን መቀያየር ቀላል ነው፡፡ አያችሁ በዐለት የተሞሉ ሰዎች ውስጥ የተወሰነ ስኳር መክተት የምትችሉትን ያህል በስኳር የተሞሉ ሰዎች ውስጥ ግን የተወሰነ ዐለት መክተት አትችሉም፡፡
እናም እነዚህ ሰዎች ለሕይወት ርባና ያለው ምንም ዓይነት ፋይዳ የላቸውም፡፡ እነርሱ ገንዘብ እስከተከፈላቸው ድረስ ለየትኛውም ቡድን ይጫወታሉ፡፡ ዛሬ ገጥመውት ከእጁ ዋንጫ የነጠቁትን ቡድን ነገ ደግሞ አብረውት ሆነው ዋንጫውን ለማንሳት ዝግጁ ናቸው፡፡ ሥልጣንና ክብር እስካገኙ ድረስ ከመላእክት ወገን ወርደው ከሰይጣን ጋር ለመሰለፍ አይዳግታቸውም፡፡
ለእነዚህ ሰዎች በሕይወታቸው ሜዳ ላይ ምንም ዐይነት መሥመር የላቸውም፡፡ አረንጓዴም፤ ቢጫም ሆነ ቀይ መሥመር የላቸውም፡፡ ሁሉንም ይሻገሩታል፡፡ «ከዚህ በመለስ ከመጣማ ሕይወቴ ያልፋል እንጂ፤´ የሚሉት ነገር የለም፡፡ አካባቢያቸውን ለመለወጥ ሳይሆን እንደ እስስት ከአካባቢያቸው ጋር ለመለወጥ ዝግጁ ናቸው፡፡ እንደ ስኳር ለመድረቅም፤ ለመሟሟትም ይችላሉና፡፡
ሰው ሲፈጠር ለሁለቱ ነገሮች የተፈጠረ መሆኑን ተፈጥሮው ይነግረናል፡፡ አእምሮ፣ ልቡናና ኅሊና እንዲኖረን የተደረገው ለምን ይመስላችኋል? አእምሮ ለማወቂያ ነው፡፡ ዓለምን የምናውቅበት፡፡ በአምስቱ የስሜት ሕዋሳት በኩል በሚገባው ዕውቀት የምንረዳበት፡፡ ኅሊናስ? ኅሊናማ የሕይወት የምትባለው መርከብ ካፒቴኗ ነው፡፡ ሕይወት በዚህ ካፒቴን ካልተመራች በማዕበል መካከል እንደተተወች የነጋዴዎች መርከብ ትሆናለች፡፡ ኅሊና የተቀመጠው ሕይወት በመርሕ እንድትመራ ነው፡፡ አንድ ሰው እሺም እምቢም የሚላቸው፤ የሚያከብራቸውና የሚሞትላቸው፤ የሚታገልላቸውና፤ መሥዋዕትነት የሚከፍልላቸው መርሖች ከሌሉት እርሱ ሰው ሳይሆን ካልዕ ፍጥረት ነው ማለት ነው፡፡
ልቡናስ ምንድን ነው? ልቡና የእምነት ቦታ ነው፡፡ ምንም እንመን ምን፣ ግን እምነት ያስፈልጋል፡፡ የሚያበረታና የሚያጠነክር፤ ኃይልና ብርታት የሚሆን፤ የማይታዩትን ነገሮች ልናይበት የምንችል፤ ከሞት ወዲያ ዓላማ እንዲኖረን የሚያደርግ፤ ሞትን ሊያሸንፍ የሚችል እምነት፡፡ እነዚህ ናቸው ዐለቶቹ፡፡ እነዚህም ናቸው የከበሩት ድንጋዮቹ፡፡ ከእነዚህ በመለስ ያለው ቢመጣ የማይጨምር፤ ቢቀርም የማያጎድል ስኳር ነው፡፡ ችግሩ አስቀድሞ ስኳሩ ከሞላ ለሌሎች ነገሮች ቦታ የለውም፡፡
አሌክሳንድርያ፣ ቨርጆንያ፣ ዩኤስ
 © ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ በመሆኑ በተመሳሳይ ኅትመት ላይ ባታውሉትይመረጣል፡

46 comments:

 1. አስቀድማችሁ ስኳሩን ቦታ ካስያዛችሁት "sugar needs Dam"

  What are those pictures called when you can see two things at once????????? sugar sugar sugar sugar sugar sugar sugar sugar
  sugar!!!!!!!!!! sugar needs Dam!!!!!!sugar አስቀድማችሁ ስኳሩን ቦታ ካስያዛችሁት
  save Waldba

  ReplyDelete
  Replies
  1. what are you talking about???? esti satisekir lemanbeb mokir

   Delete
 2. egziabher yestlen ! kale hiwot yasemalen sateselech yehenen yemesaselu eyetawochehin selemetakafelen amlak wagahin yekfeleh, wedu wendimachin !!!

  ReplyDelete
 3. It is a good speculation Danie! Many thanks...
  PJ from DebreMarkos university

  ReplyDelete
 4. አንድ ሰው እሺም እምቢም የሚላቸው፤ የሚያከብራቸውና የሚሞትላቸው፤ የሚታገልላቸውና፤ መሥዋዕትነት የሚከፍልላቸው መርሖች ከሌሉት እርሱ ሰው ሳይሆን ካልዕ ፍጥረት ነው ማለት ነው፡፡

  ReplyDelete
 5. Awesome, long live bro

  ReplyDelete
 6. Save waldiba....werku yehe yehone?

  ReplyDelete
 7. TINA YESTLEN Dn.Daniel! berta EGZIABEHIR TEBEBUN, EDMIWENEM YECHMERLEH!!! yemiysazenew bSKWAR temolto yemyadeg sew Tebeta ertbet syagengew mqletun almasebu new endgena ende ALETU tetrbi lesera bil enkwan lihonlet yemychel haq new . BEALEMACHEN KEMTELUT YEHYWET TENQ ANDU NECHU SKWAR NEW. MEDHANITE ALEM KESKWARENWT YAWETAN. ETHOPIA LEZLEALEM TINUR AMEN::

  ReplyDelete
 8. U touched me. I wish u advise me how to get rid of "sugar". And abt sugar factory project of WALDIBA. . . govt should sometimes listen to other's opinion. . . . z govt becomes weaker and weaker as it assumes hardline approach is a symbol of strength. Where r u "govt"? plz listen to other voices. . . If not, when z silence is broken, govt will be ash!!!

  ReplyDelete
 9. what i understand from this article this ggeneration is" ሰው ሳይሆን ካልዕ ፍጥረት ነው ማለት ነው፡፡"

  ReplyDelete
 10. This is the best proverb for this article Dani
  "If you don't stand for something you will fall for everything." Malcolm X .I really appericate ur deeds thank uuuuuuu

  ReplyDelete
 11. This is the perfect match for your article Dani
  "IF You Don't Stand something You Will Fall For Anything"Malcolm X Thank youuuuuuuuuu.

  ReplyDelete
 12. አያችሁ ሁለቱም በአንድ እውነታ ላይ ተስማምተዋል፡፡ የሄዱበት ቦታ ጫማ ያደረገ ሰው የለም፡፡ በመርሐቸው ግን ተለየይተዋል፡፡ አንዱ እንደ ችግር የቆጠረውን ሌላው እንደ ዕድል ቆጥሮታል፡፡ In my opinion this idea directly related to the Consequence of "the sugar project on waldiba" report done by mahibere kidusa & እንደ ችግር betekinet እንደ ዕድል::

  ReplyDelete
 13. Dear Daniel,
  I am very touched by all the articles you wrote. It is a wonderful and God bless given. I want to put a comment on this article. This entry was posted by Stephen Convey on his book The 8th Habit of effective people, under the title "Big Rocks". This is a video that accompanies the book. you can refer to the film on http://www.the8thhabit.com/offer

  ReplyDelete
 14. Dani This is best example for this generation

  ReplyDelete
 15. I dont have words!! God Bless YOU!!

  ReplyDelete
 16. Thanks, D.D
  prioritizing is an essential event in our life. EPRDF,is unable to prioritize its development strategy, it gives priority for roads and dams while my family and Ethiopian are dying every second due to hunger and injustice!!

  Netsanet A.A.

  ReplyDelete
  Replies
  1. I can see how immature you are, this article is not for anybody else but you.So try to know and evaluat, your behavior and your adictions or bad habitys that are unnecessary to your life and get rid of it. Stop being negetive, negetive................, stay positive just so you can be healthy for yourself and the people around you.

   Delete
  2. no!no! you brother i am not thinking in a negative way. i have broad spectrum of view.i am not living in a selfish manner, i am a pure Ethiopian, i love my country and people.you know i will be free and healthy if justice is respected fully. i tell you the truth EPRDF can not privatize the pan.while people are dying from hunger and injustice he makes ''roads'' and ''house building.before sending this reply please prioritize your reply.rather than insulting. so life and health can not apart from justice and freedom.
   Thank you very much.

   Delete
 17. ጽሑፉ ጥሩ ነው ሰዎች በቅን ህሊና ከተመለከቱት አንተም በቅን ህሊና ሆነህ ጽፈሐው ከሆነ ከአስተያየት ሰጪዎች እየተረዳሁት ያለው ነገር ግን አጉል ቅኔና ነው

  ReplyDelete
 18. Great post.

  We priortized for our marked spritualism, sugar never been superimposed ,but it will come next.

  ReplyDelete
 19. ጽጌ ማርያም

  ዳንኤል ጽሁፍህን ወድጄዋለሁ።
  አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች በሰው ላይ መንጠልጠል ትፈልጋላችሁ።ዳንኤል የሚያንበትን ዳንኤል እንደሆነ እያወቅን በግልጽ ጻፈ። እናንተ ዳንኤል ብሎግ ላይ እንክዋ መገለጽ ፈርታችሁ በስውር እየጻፋችሁ፣ዳንኤል የናንተን ሃሳብ በናንተ ተገብቶ እንዲያስተጋባ ትፈልጋላችሁ።ዳንኤል ዳንኤል ነው፤ሰው ምንያስጠብቃችል መምራት ካለባችሁ ምሩ፤ መጻፍ ካለባችሁ ጻፉ። በቃ።
  ስለዋልድባ ያንተን ሃሳብ ዳንኤል ዳንኤል እንዲናገርልህ የምትፈልገው አስተያየት ሰጪ ዳንኤል የራሱን ተናግሩል።ማሕበረ ቅዱሳንም የራሱን ተናግሩል። አለም አቀፍ የዋልድባ አስተባባሪ ኮሚቴ እየተናገረ ነው። ሰው ምን ያስጠብቅሃል እራስህ ምራ፤ ማገዝ ያለብህን አግዝ፤ መዋጋት ካለብህ ተዋጋ፤ ማደራጀት ካለብህ አደራጅ። ዳንኤል ወይ እንቶኔ ካልመራኝ ብሎ ድርቅ ማለት ምን ይባላል። አንተ የልብህን ሐሳብ ይዘህ መሪሁን።አትፍራ መሪ ስትፈልግ እንዳ ይረፍድብህ
  ጽጌ ማርያም

  ReplyDelete
  Replies
  1. Good comment!

   Delete
  2. I agree with tsegemariyam . thank u God blase u my sister.our brother Daniel kibret wrote many good things every day
   እናንተ ዳንኤል ብሎግ ላይ እንክዋ መገለጽ ፈርታችሁ በስውር እየጻፋችሁ፣ዳንኤል የናንተን ሃሳብ በናንተ ተገብቶ እንዲያስተጋባ ትፈልጋላችሁ።ዳንኤል ዳንኤል ነው፤ሰው ምንያስጠብቃችል መምራት ካለባችሁ ምሩ፤ መጻፍ ካለባችሁ ጻፉ። በቃ .thank u our sister again.

   Delete
  3. tsegemarim, thank you very much !.

   Delete
 20. thank you for sharing

  ReplyDelete
 21. በእውነቱ ድንቅ የሆነ እይታ ነው። ትልልቆቹን ድንጋዮች እና ትንንሾቹን የከበሩ ድንጋዮችን ቅድሚያ ካስገባን ለስኳሩም የሚሆን ቦታ አናጣም።

  ReplyDelete
 22. this is the first time i read your article and i am impresed !

  ReplyDelete
 23. Thank you so much!!!! I am very away from my life principles and now I am feeling very weak. Thank you for the woke up call. I hope I am not going to sleep again.

  ReplyDelete
 24. Thank you! Dani.. Great read! I loved the analogy you used in your point about Faith
  More blessing to you

  ReplyDelete
 25. Dear Daniel kibert

  Thank you for all your thoughtful and heart touching articles.Keep up!

  God bless you

  ReplyDelete
 26. Thank you for advising me when i needed it.

  ReplyDelete
 27. መልካም ምክር እድሜ ይስጥህ ዲን ዳንኤል! እምነት ይቅደም! እምነት ይቅደም! እምነት ይቅደም! እምነት ያለው አንባቢ ያድልህ...ለእኛም እምነት ያለው መሪ ያድለን አሜን!

  ReplyDelete
 28. i aperciate ጽጌ ማርያም

  ReplyDelete
 29. እንዴት ይሆን ስኳሩን አውጥተን ድንጋዮን የምናስቀድመው..?ማንነትን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

  ReplyDelete
 30. ዳንኤል ጽሁፍህን ወድጄዋለሁ።
  አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች በሰው ላይ መንጠልጠል ትፈልጋላችሁ።ዳንኤል የሚያንበትን ዳንኤል እንደሆነ እያወቅን በግልጽ ጻፈ። እናንተ ዳንኤል ብሎግ ላይ እንክዋ መገለጽ ፈርታችሁ በስውር እየጻፋችሁ፣ዳንኤል የናንተን ሃሳብ በናንተ ተገብቶ እንዲያስተጋባ ትፈልጋላችሁ።ዳንኤል ዳንኤል ነው፤ሰው ምንያስጠብቃችል መምራት ካለባችሁ ምሩ፤ መጻፍ ካለባችሁ ጻፉ። በቃ።
  ስለዋልድባ ያንተን ሃሳብ ዳንኤል ዳንኤል እንዲናገርልህ የምትፈልገው አስተያየት ሰጪ ዳንኤል የራሱን ተናግሩል።ማሕበረ ቅዱሳንም የራሱን ተናግሩል። አለም አቀፍ የዋልድባ አስተባባሪ ኮሚቴ እየተናገረ ነው። ሰው ምን ያስጠብቅሃል እራስህ ምራ፤ ማገዝ ያለብህን አግዝ፤ መዋጋት ካለብህ ተዋጋ፤ ማደራጀት ካለብህ አደራጅ። ዳንኤል ወይ እንቶኔ ካልመራኝ ብሎ ድርቅ ማለት ምን ይባላል። አንተ የልብህን ሐሳብ ይዘህ መሪሁን።አትፍራ መሪ ስትፈልግ እንዳ ይረፍድብህ
  ጽጌ ማርያም. ልክ ነው:: እኔም ከሜመከሩት አንድዋ ነኝ:: አዎ ሁላችን ለማተባችን ስንል ሁሉን ትተን እንደሙስሌም ወንድሞቻችን እጅ ለእጅ ተያይዘን እንጭሁ (እንዘምር) የማሪያም ልጅ ካለምንም ጥርጥር ይሰማናል::
  ዳኔ እድሜና ጤና እንዲያድልህ ከጾለቴ አልረሳህም:: አሜን!

  ReplyDelete
 31. egziabher yabertah aemerown mastewalun tebebun chemamro yesteh.

  ReplyDelete
 32. egziabher yabertah aemerown mastewalun tebebun chemamro yesteh.

  ReplyDelete
 33. it is an excellent advice that every man should assess what his/her course is

  ReplyDelete
 34. Egziabher yistilin !Diacon ! Yante hilwina lehizibochuwa ena Ethiopia kimem newna regim edime ena tenna yistih!

  ReplyDelete
 35. ልቡና የእምነት ቦታ ነው፡፡ ምንም እንመን ምን፣ ግን እምነት ያስፈልጋል፡፡ የሚያበረታና የሚያጠነክር፤ ኃይልና ብርታት የሚሆን፤ የማይታዩትን ነገሮች ልናይበት የምንችል፤ ከሞት ወዲያ ዓላማ እንዲኖረን የሚያደርግ፤ ሞትን ሊያሸንፍ የሚችል እምነት፡፡ እነዚህ ናቸው ዐለቶቹ፡፡ እነዚህም ናቸው የከበሩት ድንጋዮቹ፡፡ ከእነዚህ በመለስ ያለው ቢመጣ የማይጨምር፤ ቢቀርም የማያጎድል ስኳር ነው፡፡ ችግሩ አስቀድሞ ስኳሩ ከሞላ ለሌሎች ነገሮች ቦታ የለውም፡፡

  ReplyDelete
 36. ሥልጣንና ክብር እስካገኙ ድረስ ከመላእክት ወገን ወርደው ከሰይጣን ጋር ለመሰለፍ አይዳግታቸውም፡፡

  ReplyDelete