Monday, May 14, 2012

ምን? ወይስ እንዴት?

አንዲትን መንደር ኃይለኛ ሞገደኛ ነፋስ እየተነሣ ያስቸግራታል፡፡ የመንደርዋ ካቢኔ ተሰበሰበና ሦስት ባለሞያዎችን መድቦ ለችግሩ መፍትሔ እንዲሰጡ ለማድረግ ወሰነ፡፡ በዚህም መሠረት ሦስት ባለሞያዎች ተጠሩና ችግሩ ተነገራቸው፡፡ ከዚያም በችግሩ ላይ አሉን የሚሉትን መፍትሔ እንዲያቀርቡ የአንድ ሳምንት ጊዜ ተሰጣቸው፡፡

ከአንድ ሳምንት በኋላ ካቢኔው ተሰብስቦ ሃሳባቸውን መስማት ጀመረ፡፡ የሦስቱን ሰዎች ሃሳብ ለመስማት ከተቀመጠው ካቢኔ ጋር በጉዳዩ ላይ ላቅ ያለ ዕውቀት ያላቸው አንድ ሰው እንዲገኙ ተደርገው ነበር፡፡ የመጀመርያው ሰው «ሞገደኛው ነፋስ ለአካባቢው ነዋሪዎች ሕይወት አስጊ በመሆኑ ነዋሪዎቹን ሌላ ቦታ ማስፈር» እንደሚገባ ሃሳብ አቀረበ፡፡ ሁለተኛው ሰው ደግሞ «ነዋሪዎቹን ወደ ሌላ ቦታ መውሰዱ ከብዙ ማኅበራዊ ነገር ስለሚያፈናቅላቸው እዚያው ባለቡት ሆነው ነገር ግን ሞገደኛው ነፋስ ሲነሣ ሊጠለሉበት የሚችሉበት የመሬት ውስጥ የምሽግ ቤት እንዲሠራ» ሃሳብ ሰጠ፡፡


ሦስተኛው ሰው ደግሞ «ይህ ሞገደኛ ነፋስ ለነዋሪዎቹ የተሰጠ በረከት ነው» አለ፡፡ «ነዋሪዎቹ ነፋሱ በሚቀንስበት የአካባቢው መልክዐ ምድር ላይ ሄደው እንዲሠፍሩ ማድረግ ይቻላል፡፡ ነገር ግን ይህንን ነፋስ መጠቀም አለባቸው፡፡ ይህ ነፋስ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ሊያመነጭ የሚችል ነው፡፡ በዚህ አካባቢ መተከል ያለባቸው መሣርያዎች አሉ፡፡ ነዋሪዎቹ በአንድ ላይ ገንዘብ አዋጥተው እነዚህን መሣርያዎች ይትከሉ፡፡ በጋራም ለየአካባው የኤሌክትሪክ ኃይል በመሸጥ ተጠቃሚ ይሁኑ፡፡ ይህ ነፋስ ችግር አይደለም፤ በረከት ነው፡፡» አለ፡፡

የካቢኔው አባላት የትኛውን መቀበል እንዳለባቸው ለመወሰን ስለተቸገሩ እኒያን ተጋባዥ ባለሞያ አማከሯቸው፡፡ እርሳቸውም እንዲህ አሉ «ጉዳዩ ሰዎቻችን ምን አዩ? የሚለው አይደለም፡፡ እንዴት አዩ? የሚለው ነው፡፡ ኃይለኛና ሞገደኛውን ነፋስማ ማንም ያየዋል? ያውቀዋል፤ ይረዳዋል፡፡ ጥበብ እርሱን ማየት አይደለም፤ እንዴት ታየዋለህ? ነው፡፡ ሁለቱ ሰዎች በችግር ዓይን አዩት፤ ሦስተኛው ሰው ግን በበረከት ዓይን አየው፡፡ አሁንም እናንት መወሰን ያለባችሁ በነፋሱ ላይ አይደለም፡፡ በራሳችሁ ላይ ነው» አሏቸው፡፡

«እንዴት በራሳችን ላይ?» አሉ የካቢኔ አባላቱ፡፡

«ውሳኔውኮ ምን እንይ? አይደለም፡፡ እንዴት እንይ? ነው፡፡ ነፋሱን መርገም አድርገን እንየው ወይንስ በረከት? ጥቅም አድርገን እንየው ወይስ ጉዳት? እሴት አድርገን እንየው ወይስ ዕዳ? ነውኮ ጥያቄው፡፡» አሉ ባለሞያው፡፡

ለምሳሌ ለሁላችንም እውነት ተመሳሳይ ነው፡፡ እውነቱንም እናውቀዋለን፤ እንረዳዋለን፡፡ ውስጣችንም ይነግረናል፡፡ ግን አንዳንዶቻችን እውነትን ስንናገርና እውነት የሚያመጣውን ሰማዕትነት ስንቀበል ሌሎቻችን የምናውቀውን እውነት መናገር ለምን ይቸግረናል? ስለ እውነት ያለን ዕውቀት አይደለምኮ? ለእውነት ያለን አመለካከት ነው ልዩነቱ? ለአንዳንዶቹ እውነት ሊሸፍኗት የማይገባ፣ ልትገለጥ ግድ የምትል፤ በመገ ለጧም የምታስከትለውን ዋጋ ሊከፈልላት የሚገባ ነገር ናት፡፡ ለሌሎች ደግሞ እውነት እውነት ብትሆንም አደጋ የምታስከትል ከሆነ ውሸትም ልትሆን ትችላለች፡፡ 

ለመሆኑ ያገቡ ሰዎች ሁሉ በትዳር ላይ ነው እንዴ ልዩነታቸው? በትዳር ላይ ልዩነት ቢኖራቸውማ አይጋቡም ነበር፡፡ ትዳርን በሚያዩበት ዓይን ላይ ነውኮ ልዩነቱ? ሚስትህን በጣም ክፉ አድርገህ ማሰብም ትችላለህ፤ በጣም ደግ አድርገህ ማሰብም ትችላለህ፤ በጣም ቆንጆ አድርገህ ማየት ትችላለህ፤ በጣም አስቀያሚ አድርገህ ማየትም ትችላለህ፤ ትዳርህን ምቹ ማደረግም ትችላለህ፤ ጎርበጥባጣ ማድረግም ትችላለህ፡፡ 

ግን ብዙ ጊዜ ሚስት እርሷ አመለካከቷን ሳትለውጥ ባሏ እንዲለወጥ ትፈልጋለች፤ ባልም እርሱ አመለካከቱን ሳይለውጥ ሚስቱ እንድትለወጥ ይፈልጋል፡፡ የሚገርመው ደግሞ ሁለቱም አመለካከታቸውን ሳይለውጡ ትዳራቸው እንዲለወጥ ይፈልጋሉ፡፡ ችግሩ እዚያ ነው ብለው ስለሚያምኑ፡፡ ችግሩ ግን እዚያ አይደለም እዚህ ነው፡፡ ውጭ አይደለም ውስጥህ ነው፡፡ ከዚያኛው አካል አይደለም ካንተ ነው፡፡ ወዳጄ «ጨለማ በጸጥታ የምንሠራበት ጊዜ ነው» ያሉ ሰዎች መብራት ሠሩ፡፡ በጨለማ ለመሥራት፡፡ «ጨለማ የዕንቅልፍ ጊዜ ነው» ያሉ ሰዎች ይሄው እስካሁን እንደተኙ ናቸው፡፡

«እስኪ በመስኮት በኩል ተመልከቱ» አሉ፡፡ ሁሉም በመስኮት በኩል ተመለከቱ፡፡

«ይኼ በግቢው ውስጥ የተተከለው ዛፍ ይታያችኋል?» ሁሉም ራሱን ነቀነቀ፡፡ 

«ዛፉ ምንድን ነው ለናንተ?» ጠየቁ፡፡

የግቢው ውበት ነው
አየሩን ያቀዘቅዛል
የአፈሩን መሸርሸር ይጠብቃል
የአየር ንብረቱን ምቹ ያደርጋል
ሃሳብ ተሰነዘረ፡፡ 

«በጣም ጥሩ፡፡ ይኼ እንግዲህ በሰው ዓይን ሲታይ ነው፡፡ አንዲትን ዝንጀሮ አምጥተን ስለ ዛፉ ብንጠይቃት ደግሞ ምን የምትል ይመስላችኋል? ለርሷ ዛፉ መኖርያ ነው፡፡ ምግብ ነው፡፡ አያችሁ ዛፉ አልተቀየረም፡፡ የተቀየረው የተመለከትንበት ዓይን ነው፡፡ 
«ችግር እንኳን ችግር የሚሆነው በተመልካቹ ዓይን ነው፡፡ ለአንዳንዶች እሥር ቤት የመከራ፣ የስቃይ፣ ከዓለም የተገለሉበት፣ ራሳቸውን የጣሉበትና ተስፋ የቆረጡበት ቦታ ነው፡፡ ለሌሎች ደግሞ ነጥረው፣ እንደ ብረት ጠንክረው፣ ሌላ ሰው ሆነው የወጡበት ቦታ ነው፡፡ ልዩነቱ እሥር ቤቱ ሳይሆን ለእሥር ቤቱ የነበራቸው አመለካከት ነው፡፡

«ለአንዳንዶች መውደቅ የመነሣት መጀመርያ ሆኗቸዋል፡፡ ለሌሎቹ ደግሞ የመሞት መጀመርያ፡፡ ለአንዳንዶች ከሥራ መባረር የሌላ የላቀ ሥራ መጀመርያ ሆኗቸዋል፤ለሌሎቹ ደግሞ የቦዘኔነት መጀመርያ፡፡ ለአንዳንዶች ከትምህርት ገበታ መሰናበት የምርምር መነሻ ሆኗቸዋል፤ ለሌሎች ደግሞ የውንብድና መጀመርያ፡፡ ስለዚህ ምን ገጠመህ? አይደለም ዋናው ነገር እንዴት ገጠምከው? ነው፡፡ ምን ሆነብህ? አይደለም፤ እንዴት አገኘኸው? ነው፡፡ ምን ደረሰብህ? አይደለም፤ እንዴት ተቀበልከው? ነው፡፡ 

«እያለቀሱ የሚኖሩ አሉ፡፡ እየተደሰቱ የሚሞቱም አሉ፡፡ በክርስትና ታሪክ ብዙ ሰማዕታት እየዘመሩና እየተደሰቱ ነው የሞት ጽዋን የተቀበሉት፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በሕይወት እያሉ አንድም ቀን ሳይስቁ፣ እያማረሩና እያለቀሱ የሚኖሩ አሉ፡፡ ልዩነቱ ከምን የመነጨ ይመስላችኋል? ከአመለካከት ነው፡፡ እነዚያ ሞትን የኑሮ መጨረሻ አድርገው አላዩትም፡፡ እነዚያ ሞትን የመሸነፊያ መሣርያ አድርገው አላዩትም፡፡ እነዚያ ሞትን ቅጣት አድርገው አላዩትም፡፡ ለእነርሱ ሞት የሚሸሹት ሳይሆን የሚጋፈጡት ነው፡፡ ለእነርሱ ሞት ከአንድ ዓይነት የኑሮ ቅርጽ ወደ ሌላ ዓይነት የኑሮ ቅርጽ መሸጋገርያ ነው፡፡ ለእነርሱ ሞት ለእውነት የሚከፍሉት ዋጋ ነው፡፡ ለእነርሱ ሞት ለትውልድ የመልካም ሕይወት ድልድይ መሥሪያ ነው፡፡ ለእነርሱ ሞት ከመኖር ለሚበልጥ ዓላማ የሚከፈል ዋጋ ነው፡፡

«ታድያ እየሞቱ መሳቅና መደሰት ካለ፤ ለምንድን ነው እየኖሩ ማልቀስ የሚኖረው፡፡ አንዳንዶች በሞት ሲደሰቱ በኑሮ ለምን እናለቅሳለን? የአመለካከት ጉዳይ ነው፡፡ ለምን ሁል ጊዜ ችግሮችን በምሬትና፣ በሰቆቃ፣ በተስፋ መቁረጥና በኀዘን ስሜት ብቻ እንቀበላቸዋለን? ለምን በሽታን የመድኃኒት መፍጠርያ አናደርገውም? ለምን በሥራ ቦታህ ሁል ጊዜ ትማረራለህ? ለምን አካባቢህን አትቀይረውም፡፡ ለምን ያንን አጋጣሚ የጀግንነት መነሻ አታደርገውም? እንዴት ልቀይረው? ብለህ የምታነብበት፣ የምታስብበት፣ የምትወያይበት፣ አማራጭ የምትደረድርበት አጋጣሚ ለምን አታደርገውም? 

«ትልቁ ችግራችን ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ?»
ሁሉም በትኩረት ያዩዋቸው ነበር
«ሰው ሁሉ ዓለምን ስለ መለወጥ ስለሚጨነቅ ነው፡፡»

የግርታ ስሜት ተፈጠረ፡፡ ታድያ ዓለምን መለወጥ አይደል እንዴ ቁልፉ የሚል ዓይነት፡፡

«ዓለምን ለመለወጥ ከተነሣን ምንም አንለውጥም፡፡ መለወጥ ያለባት ዓለም አይደለችም፡፡ እኛ ነን፡፡ የሰው አመለካከት ነው መለወጥ ያለበት፡፡ ሰው ዓለምን የሚያይበት ርእዮት ነው መለወጥ ያለበት፡፡ ያን ጊዜ ዓለምን ስትቀይራት ትታይሃለች፡፡ ራሳቸው ሳይቀየሩ ዓለምን ለመቀየር የተነሡ ሰዎች ናቸው ዓለማችንን ያበላሿት፡፡ ዝም ብለው ዓለምን ለመቀየር የተነሡ ሰዎች ሁሉንም ነገር እንደ ችግር፣ ዕንቅፋት፣ የብልጽግና ጠላት እያደረጉ ያዩታል፡፡ ይህ የአመለካከት ችግር ነው፡፡ በዓለም ላይ ሰው ሊጠቀምበት የማይችል አንዳች ነገር የለም፡፡ መጥፎ ሆኖ የተፈጠረ ምንም ነገር የለም፡፡ አያስፈልግም ይወገድ የሚባል ምንም ፍጥረት የለም፡፡ ያ የኛ የአመለካከት ችግር ነው፡፡ ለዚህ ነው እኛ ነን እንጂ ዓለም አይደለችም መለወጥ ያለባት የሚባለው፡፡

«አንተም አካባቢህን ለመቀየር አይደለም መጀመርያ መነሣት ያለብህ፡፡ ለውጥን ከወዲያ አትጀምረው፡፡ ከጎረቤትህ አትጀምረው፤ ከጠላትህ አትጀምረው፤ ከራስህ ጀምረው፡፡ አንተ ተለወጥ፡፡ አንተ ስትለወጥ አካባቢህም መለወጥ ይጀምራል፡፡ እንደ ጠላት የምታያቸውን መውደድ ትጀምራለህ፤ እንደ ችግር የምታየውን ጥቅሙን ትረዳዋለህ፤ መሰናክል የመሰለህ ነገር ድልድይ ሆኖ ታገኘዋለህ፤ ጨለማ የመሰለህ ነገር በርቶ ታየዋለህ፤ ገደሉ ደልዳላ ሆኖ ይታይሃል፡፡ 

ችግሩ ሥልጣን አይደለም፤ ስለ ሥልጣን ያለው አመለካከት ነው፤ ችግሩ ሀብት አይደለም፣ ስለ ሀብት ያለው አመለካከት ነው፡፡ ችግሩ ዘር አይደለም ስለ ዘር ያለው አመለካከት ነው፡፡ ችግሩ ቀለም አይደለም፣ ስለ ቀለም ያለው አመለካከት ነው፡፡ ችግሩ ዴሞክራሲ አይደለም፣ ስለ ዴሞክራሲ ያለው አመለካከት ነው፤ ችግሩ ፓርቲ አይደለም፣ ስለ ፓርቲ ያለው አመለካከት ነው፡፡ ችግሩ ውበት አይደለም፣ ስለ ውበት ያለው አመለካከት ነው፡፡ ችግሩ የሌላ እምነት መኖር አይደለም፣ ሌላውን እምነት የምታይበት አመለካከት ነው፡፡

«አንዳንድ አካባቢ አላያችሁም፡፡ አካባቢያቸው ተራራማ በመሆኑ ሲያማርሩ ትሰማላችሁ፡፡ አንዳንድ አካባቢ ደግሞ ያመሰግናሉ፡፡ እነዚያ የሚያማረሩት ተራራውን እንደ ዕዳ ስለሚያዩት ችግር ችግሩ ነው የሚታያቸው፣ የሚሰማቸውም፡፡ እነዚያኞቹ ግን በተራራው ላይ መዝናኛ ገንብተው፤ ኬብል ዘርግተው፤ የተራራ መውጫ አዘጋጅተው፤ አካባቢውን አሳምረው የቱሪስት መናኸርያ አድርገውታል፡፡ ታድያ ተራራው ምን አጠፋ? ያጠፋውኮ ሰዎቹ ተራራውን ያዩበት መንገድ ነው፡፡

«እኛምጋ እንደዚህ ነው ወዳጆቼ፡፡ ነፋሱ ምን አጠፋ፡፡ ተውት ይንፈስ፡፡ ለእኛ ግን ነፋሱ ምንድን ነው? ችግር ነው ወይስ በረከት? ዕዳ ነው ወይስ እሴት? ይህንን ብቻ ነው መመለስ ያለብን፡፡ ችግር ነው፣ ዕዳ ነው ካልን ለቅቀን ከሰፈራችን እንሂድ፡፡ በረከት ነው፣ እሴት ነው ካልን ደግሞ እንጠቀምበት፡፡ መወሰን ያለብን በነፋሱ ላይ ሳይሆን በራሳችን አመለካከት ላይ ነው፡፡ 

ሁሉም ራሳቸውን ከላይ ወደ ታች ነቀነቁ፡፡

አሌክሳንድርያ፣ ቨርጂንያ፣ ዩ ኤስ ኤ

52 comments:

 1. 10Q Dani, I respect ur article selection & z way of discusion withrespct to our behaviour.
  God bless u ¦¦
  H/Eyasus from SWITZERLAND.

  ReplyDelete
 2. «ጉዳዩ ሰዎቻችን ምን አዩ? የሚለው አይደለም፡፡ እንዴት አዩ? የሚለው ነው፡፡

  ReplyDelete
 3. kala heiwatte yasamalen

  ReplyDelete
 4. When I read your articles assuming they are written by a good Ethiopian who is trying to see a well cultured society, they almost always are very meaningful. However, when I read them assuming they are written by a devoted Ethiopian Orthodox Christian, I most of the times feel many of the articles are mere diversions from more important current issues. I like to think of you as someone who has both qualities, a good Ethiopian devoted to the Orthodox Church. Nevertheless, by spending too much of your time on other issues, I am afraid you are going a little bit farther from the concerns of the church. The fact that you, most of the times, write about more general moral issues than church specifics creates a state of misunderstanding on most of your readers who feel the problems of the church are not as bad as they think. I believe letting the people know is the first step in solving our problems. The solutions can be prayers or other specific acts but the people need to daily hear about the problems to do their best towards solving them. Please know that I am in no way implying you should put yourself in any danger in trying to do so. I am saying all this just because sometimes I feel that you are slipping away into the vastness of the world. I feel that you can do a much better job and save many lives if you stay in your friendly territory, the territory about which you have been speaking since you were young. Please use the potential God has given you with wisdom and humility.

  ReplyDelete
  Replies
  1. did you see the way you see the article?
   it is not why? the problem but how ?

   Delete
  2. I think his writing is" wuste woyra" His message goes to the current situation of MK & the holly Syndos bad feeling about "Zena Betechristian" news.For me it is to mean don't be disturbed with what is said,don't take any complaint in bad way rather 1st assess your self.

   Delete
 5. It is really nice blog. God bless U!!!

  ReplyDelete
 6. ችግሩ ከተፈጥሮ አይደለም እኛ ተፈጠሮን ከምናይበት ዐይን እና ማሰብ ከሚችለው አዕምሮ ያለው አካል ውስጥ እንጂ፡፡

  " ችግሩ ሥልጣን አይደለም፤ ስለ ሥልጣን ያለው አመለካከት ነው፤ ችግሩ ሀብት አይደለም፣ ስለ ሀብት ያለው አመለካከት ነው፡፡ ችግሩ ዘር አይደለም ስለ ዘር ያለው አመለካከት ነው፡፡ ችግሩ ቀለም አይደለም፣ ስለ ቀለም ያለው አመለካከት ነው፡፡ ችግሩ ዴሞክራሲ አይደለም፣ ስለ ዴሞክራሲ ያለው አመለካከት ነው፤ ችግሩ ፓርቲ አይደለም፣ ስለ ፓርቲ ያለው አመለካከት ነው፡፡ ችግሩ ውበት አይደለም፣ ስለ ውበት ያለው አመለካከት ነው፡፡ ችግሩ የሌላ እምነት መኖር አይደለም፣ ሌላውን እምነት የምታይበት አመለካከት ነው፡፡ "

  KHY, Dani
  Tes, Phx,AZ

  ReplyDelete
 7. DEAR DANIEL,

  May the Grace and Blessings of Our Lord be with you.

  I have been hearing about you for the last two decades and also reading your blog for the last two years. You are so smart in the sense that you possess a great degree of caliber to emerge one of the known:

  Novelist,
  Social Critic
  Historian,
  Folklore expert and
  A good preacher

  Although you are bestowed with the aforesaid gifts and further you committed yourself to be a double-edge sword that shatters the wrong doings of the Spiritual and Political realms, signs of inconsistency, dare to say, I have been realizing that displacement is taking place that let us know that you are making a shit from your standpoint.

  I am gladly able to provide some proof of evidences that witness you 're displacing yourself from you standpoint :

  1. You shouted aloud criticizing the erection of the Patriarch's statue
  ሰው በቁሙ ሐውልት ለምን ያሠራል?
  We applauded and it is still the most visited article numbered 1 on
  your billboard

  2. You cried about Mahibere Kidusan that The Mahiber is getting out
  of the track that may lead to the total collapse of Gospel Service
  that spanned for nearly two decades.

  Not only the members but the laity including me who are not
  members of the Mahiber also strongly responded for what you
  produced on the blog. And soon, you confessed with letter of
  excuse. I personally sobbed that you have done great that may
  teach those who may commit mistakes.

  3. You boasted about (tell us how proud you are about Nile) Abay ,
  when you visited the Early Beloved Father Pop Shenouda III in
  Cairo, that you produced magnificent imaginary interview that
  would last in TWO PARTS. But because of some critics you lost your
  stand and ignored the SECOND PART? WHY?

  4. You made your blog a live broadcasting media when the Great
  Ziqualla Abo was set to fire. I had hour by hour, day by day report
  of the development and was able to contribute some bucks. Thank
  You for your wonderful deeds you have done so far.

  5. Now, Waldiba of Abba Samuel has got a lot of trouble and
  tribulation because of the Sugar development project. I am not
  against development nor a man of hatred politics. If you ask me
  what score would I give to EPRDF, I dare say not less than 60%.
  This is a good score that even the Cadres are not willing to give to
  their Party.

  WHERE ARE YOU RIGHT NOW? THIS IS THE TIME WE NEED YOU MOST.
  Are you sitting aside of you standpoint? Is it not your affair? Which one do you think more important Religion or Sugar Development?

  Have you ever read the recent commendation of President Dmitry Medvedev of Russia that he glorified the role of the Russian Orthodox Church for centuries old effort in keeping the values, cultures and spirituality of the Russian People.

  What is the thought inside you? Are you on the side of Tefera Walwa, who blatantly branded EOC "DEN OF NEFTEGNA"? Tell me what you are doing?

  I with utmost respect and courtesy beg you, DANIEL, to stop a moment from preaching and letting us read your article like

  የነፍሴ ጨዋታ
  ሃሳብ የሞተ ዕለት
  ለቤተ መጻሕፍትዎ
  ሦስቱ ማጣርያዎች
  ምን? ወይስ እንዴት?
  I wish if all my life is associated with reading folklore based articles and books. But this is not time. "Bo Gize Lekulu" endil. Let me finish with this powerful saying "THER IS NOTHING POWERFUL THAN AN IDEA WHOSE TIME REACH'' I read it from B600 Management course from Open Business School and He (The PM) is also well familiar with the saying.

  May God Bless You high, Amen

  Tesfaye

  ReplyDelete
  Replies
  1. i fully agreed with this idea

   Delete
  2. Selam Tesfaye,

   I agree with all your points. I always open this blog expecting to get something about the current EOC issues. I affirm agree "THER IS NOTHING POWERFUL THAN AN IDEA WHOSE TIME REACH.'' It is the reason why D/ Dani's recent articles can't get my interest as it was. However, I never attempt to balm him, because I don't know his reason(s).

   May God bless all,

   Netsi

   Delete
 8. ዳኒ አንድ አስተያየት አለኝ። ካለማስተዋል ይሁን ካለህ በቂ ምክንያት የተነሳ ምክንያቱን ባላውቅም ቀኖችን የምትጽፈው በፈረንጆቹ ነው። ምን አልባት አብዛኛው ተደራሲ ያለው በውጪ አገር ስለሆን ነገሩን ለማቅለል አስበህ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን አገራችን የምትጠቀምበት የራሷ የቀን መቁጠሪያ እያላት/በአሁኑ ሰዓት ብዙዎች እየተዉት ቢመጡም/ ይህንን መጠቀም አገራዊም መንፈሳዊም ግዴታ እንዳለብን ይሰማኛል። ከዛም ባሻገር በውጭ ያለው ህብረተሰብ ቀኑ እየተደበላለቀበት ያስለመደውን ጸሎትና ዝክር እያስተጓጎለ ስለሆነ የአንተ የኢትዮጵያን የቀን መቁጠርያ መጠቀም የህዝበ ክርስቲያኑን ቸግር በተወሰነ ለመቅረፍ ያስችላልና የአገራችንን የቀን መቁጠርያ ከፈረንጆቹ ጋር ለመጠቀም ቸል አትበል እላለሁ፡፡
  አዜብ ዘሚኒሶታ

  ReplyDelete
  Replies
  1. Good comment Azeb.

   Delete
  2. blog adel ende blog berasu yemikortew beferenjoche new

   Delete
 9. really true idea!!!

  ReplyDelete
 10. dn.daniel!! HAYALU AMLAKACHEN BRTATUN TEBEBUN YCHMRELEH. ETHIOPIA LEZLEALEM TINUR::

  ReplyDelete
 11. hasabu yetafital...geta yebarkih

  ReplyDelete
 12. Dani. i think it is the right time to talk about our church than any thing else.... i like it but please say some thing about it. we need you know than ever because you are influential person for us...... please say some thing for the current problem of our church.

  God bless you!!!!!!!!

  ReplyDelete
 13. i rely appreciate your point of view

  ReplyDelete
 14. ጆሮ ያለው ይስማMay 16, 2012 at 10:37 AM

  «ታድያ እየሞቱ መሳቅና መደሰት ካለ፤ ለምንድን ነው እየኖሩ ማልቀስ የሚኖረው፡፡ አንዳንዶች በሞት ሲደሰቱ በኑሮ ለምን እናለቅሳለን? የአመለካከት ጉዳይ ነው፡፡ ለምን ሁል ጊዜ ችግሮችን በምሬትና፣ በሰቆቃ፣ በተስፋ መቁረጥና በኀዘን ስሜት ብቻ እንቀበላቸዋለን? ለምን በሽታን የመድኃኒት መፍጠርያ አናደርገውም? ለምን በሥራ ቦታህ ሁል ጊዜ ትማረራለህ? ለምን አካባቢህን አትቀይረውም፡፡ ለምን ያንን አጋጣሚ የጀግንነት መነሻ አታደርገውም? እንዴት ልቀይረው? ብለህ የምታነብበት፣ የምታስብበት፣ የምትወያይበት፣ አማራጭ የምትደረድርበት አጋጣሚ ለምን አታደርገውም?

  ReplyDelete
 15. ወንድም ተስፋዬ አስተያየትህን ሳነብ ካንተ በፊትም መሰል አስተያየት የሰጡ ሰወችንም አስታወስኩ ግን የገረመኝ ምን እንደሆነ ታዉቃለህ ‹‹ ዉልድብና እና ኢዉልድብና ›› የሚለዉን ጽሁፍ ያነበብከዉ አልመሰለኝም ምክንያቱም በዋልድባ ጉዳይ አቋምህን አሳዉቀን አይነት መንፈስ ስላነበብኩ ነዉ፡፡ ለማንኛዉም አቋሙን ለማወቅ ይረዳህ ዘንድ ዉልድብና እና ኢዉልድብና የሚለዉን ጽሁፍ በድጋሚ አንብብ፡፡ አንተም ብትሆን ይህንን የተናገርከዉ ስለቤተክርስቲያንህ ተቆርቁረህ የቤቱ ቅንአት በልቶህ ነዉ ነገር ግን አንቸኩል በችኮላ የሚሆን ነገር የለም ሁሉን በትእግስትና በማስተዋል ማድረግ መልካም ነዉ ስሜት ምንም መስራት አይችልም የእስራኤል ልጆች አኮ ከግብጽ ይወጣሉ ነገር ግን በችኮላ አትወጡም ተብለዋል ስለዚህ ወንድሜ እግዚአብሄር ይቀድማል እርሱም ይከተላል እኛም እንወጣለን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dear Commentator,

   Thank you for you advice. When I wrote the comment I didn't have any sign of anger or emotionality; I did it in good mood. But I couldn't hide my complain that he is still so passive on the issue. That made me a little bizarre. I read what you said ‹‹ ዉልድብና እና ኢዉልድብና ›› but it was neither as sweet as cake nor as bitter as "Quarf".

   The reason I did comment was that I need to care about Dn. Daniel. What ever happens happen for reason. He doesn't have the authority to turnaround what is going on now but can refrain from collaborating the evil under the guise of development or service of God and the Society at large

   I reget for any misinterpretation or understanding that may happen because of the language; My intention was not disrespecting or defaming the big Picture - Dn. Daniel


   Thank You
   Tesfaye

   Delete
 16. ለምሳሌ ለሁላችንም እውነት ተመሳሳይ ነው፡፡ እውነቱንም እናውቀዋለን፤ እንረዳዋለን፡፡ ውስጣችንም ይነግረናል፡፡ ግን አንዳንዶቻችን እውነትን ስንናገርና እውነት የሚያመጣውን ሰማዕትነት ስንቀበል ሌሎቻችን የምናውቀውን እውነት መናገር ለምን ይቸግረናል? ስለ እውነት ያለን ዕውቀት አይደለምኮ? ለእውነት ያለን አመለካከት ነው ልዩነቱ? ለአንዳንዶቹ እውነት ሊሸፍኗት የማይገባ፣ ልትገለጥ ግድ የምትል፤ በመገ ለጧም የምታስከትለውን ዋጋ ሊከፈልላት የሚገባ ነገር ናት፡፡ ለሌሎች ደግሞ እውነት እውነት ብትሆንም አደጋ የምታስከትል ከሆነ ውሸትም ልትሆን ትችላለች፡፡
  Mamush,MN

  ReplyDelete
 17. ዳኒ የምታቀርብልን ጣፋጭና ትምህርታዊ ትረካዎች የመንፈስ ምግብ እየሆኑን ነው፡፡ እባክህን አታቋርጥብን - የመንፈስ ሙቶች እንዳንሆን !!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምሳሌ ለሁላችንም እውነት ተመሳሳይ ነው፡፡ እውነቱንም እናውቀዋለን፤ እንረዳዋለን፡፡ ውስጣችንም ይነግረናል፡፡ ግን አንዳንዶቻችን እውነትን ስንናገርና እውነት የሚያመጣውን ሰማዕትነት ስንቀበል ሌሎቻችን የምናውቀውን እውነት መናገር ለምን ይቸግረናል? ስለ እውነት ያለን ዕውቀት አይደለምኮ? ለእውነት ያለን አመለካከት ነው ልዩነቱ? ለአንዳንዶቹ እውነት ሊሸፍኗት የማይገባ፣ ልትገለጥ ግድ የምትል፤ በመገ ለጧም የምታስከትለውን ዋጋ ሊከፈልላት የሚገባ ነገር ናት፡፡ ለሌሎች ደግሞ እውነት እውነት ብትሆንም አደጋ የምታስከትል ከሆነ ውሸትም ልትሆን ትችላለች፡፡
   Mamush,MN

   Delete
  2. ዳኒ የምታቀርብልን ጣፋጭና ትምህርታዊ ትረካዎች የመንፈስ ምግብ እየሆኑን ነው፡፡ እባክህን አታቋርጥብን - የመንፈስ ሙቶች እንዳንሆን !!!

   Delete
 18. Dear Dani,

  As usual amazing piece, such a kind of food for thought is very needed for a person like me. Apart from this please take comments as individual opinions, because always we are pushing enlightened persons to the edge, while we are sitting idle and waiting miracles. Thanks bro.

  ReplyDelete
  Replies
  1. I like your comment on behavior of some individuals, yes we don't have soft heart to those enlightened persons, but we push them to the cliff. Thank you my brother.

   Delete
 19. "To One who is idle, the sky is nearby him" is an Amharic Proverb. Don't discourage the blogger. Give him constructive comments and corrections. Dn Daniel is one of the genuine sons of Tewahdo. This is enough! But he is a human being that can commit error; he has his own stand; living style, philosophy, etc. To me his mistakes are like small white dots on a blackboard. When I see his works, I forget his weaknesses. I don't expect him to be a party affiliated, or supporter of individuals. As a religious man, he should be at the side of truth! so far, I have seen this.

  ReplyDelete
 20. Dear, Brother Dani

  I love most of your articles. This one is also a great message as usual. Please, pray as much as you can because when most christian build you with a good comment so you won't boast and fall. As you know, history tell us that we had many great people but most of them fail with pride. I love and pray for you so God help you to stay in the path of our true faith.

  Let the Grace of God and the prayer of St. Mary be with you

  ReplyDelete
 21. ሰላም ዳ/ን ዳንኤል ክብረት: እስካሁን በምትጽፈው ነገር ሁሉ ለመንፈሳዊ ትምህርት: ለማህበራዊ ኑሮ :ብሎም በስደት ላይ ሰለምኖር አእምሮየን ለማዝናኛ : በተለያየ መልኩ ስጠቀምበት ቆየሁ በጣም አመሰግን አለሁ:: አሁን ግን የአባቶች መደፈር: የገዳሞች መበርበር ብሎም በሣት መጋየት: የማህበረ ቅዱሳን ማህበር ከመመስገን አልፎ መደነቅ ሲገባው የጕሪጥ መታየት:ይባስ ተብሎ የኦርተዶክስ ሃይማኖታችን የወደፊት መጨው ግዜ ብሩህ መስሎ አልታይ ሲለኝ እውነት ነው የምለው ጽሑፍህ እንደድሮ ቃላት በቃላት ማንበብ ተሳነኝ::ምን ሁኘ ይሆን? መልሱ አጭርና መንገዶም ግልጽ ነው:: ምእመን ሆይ ምን እስክንሆን እንጠብቅ ትላላችሁ:: አባቶች ሰሞኑን በተካሄደው ስብሰባ እንደተከታተልነው የተቻላቸውን እየተንቀሳቀሱ ነው:: ከዚያም አልፈው በመስመር እየገቡ ነው:: እናስ ምእመን የኛ አንገት አቀርቅሮ ውስጡ ወደተቦረቦረ ቤተክርስቴያን መሄድ ምን የሜያስከትል ይመስላችሁአል??ቤተክርስቴያናችን ከአባቶች አልፎ እኛው ላይ ሌደረመስ እንደሜችል እውን አጥታችሁት ይሆን? አይመስለኝም:: ይልቅስ እንደስላሙ ወንድሞቻችን አንገታችን ቀና አርገን ባአንድ ማተብ በመነሳት የምንለውን እንበል::አይዞን መንግሥት ከሆነ ጥያቄያችን ግልጽ :ጉላችን ውሱን እስከሆነ ድረስ ለኔህ የኣርቶዶክስ ሃይማኖት አፍራሽ አባት ሲል "አግአዚን" ይጠራል ብየ አልጠራጠርም:: እስላሞች ወንድሞቻችን ጥሩ ምሳሌ ሌሆኑን ይገባል::ምንም እንኳን መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ አልገባም ባይ ቤሆንም ትንሽ ቀና ብንል ግን የሜረዳን ይመስለኛል::ምክንያቱም በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉት አብያተ በተክርስትያናት ተወደውና አስወድደው : አስማምተውና ተስማምተው : መክረውና አስመክረው ምእመኑን መምራት ያልቻሉ አባት ስለሆኑ ሆድ ይፍጀው በማለት ነው እንጅ ሳያፍርባቸው የቀረ አይመስለኝም::ያም ሆነ ይህ ምእመናን እባካችሁ ሌላውን ጽሑፎች ለግዜው ቆም እናርግና ይህን አንገብጋቢ የማተባችን ጉዳይ እንድናስቀድም በእግዜአብሄር ስም እጠይቃለሁ :: ሁሉ የማይሳነው አምላክ ይርዳን:: አሜን

  ReplyDelete
 22. ዳኒ አምላክ ዕድሜና ጤና አብዝቶ ይስጥክ ቃለ ህይወት ያሰማልን!!!

  ReplyDelete
 23. ዳኒ ስለማትፅፋቸው ማህበራዊ ጉዳዮ እጅግ በጣም እናመሰግናለን፡፡ እንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ግን ይህ ጦማር የጭፍን ስሜት መግለጫ ሳይሆን በማስተዋል የምንወያይበት ነው፡፡እንዲ ያለ የሃይማኖት ድረጅት ተነስቷልና ተነሱ የሚል ቅስቀሳ የክርስተና ህይወት አይደለም ሃይማኖታች የተገነባው በደም ነው ስለዘህም ልንፀልይ ይገባናል፡፡ አባቱ የማያውቅ የሰው አባት ይሰድባን አይደል ተረቱ፡፡

  ReplyDelete
 24. one of problem solving is Redirect it
  -deflect the Problem(simply be redefined as not a problem)

  ReplyDelete
 25. በጣም ደስ የሚል መልእክት ነው እግዚአብሔር ይስጥልን ዲ.ዳንኤል

  ReplyDelete
 26. አስተያየቶችን ሁሉ ለማንበብ ሞከርኩና አንድ ድምዳሜ ላይ ደረስኩ፡ “ልዩነቱ ያለው ሁላችንም ጽሁፉን የተረዳንበት መንገድ ወይም የተመለከትንበት ዓይን ላይ ነው” የሚል፡፡

  ReplyDelete
 27. Thank you D/n Daniel. it is a good article. it is a nice view! you said it all, its all about attitude! its all about positive attitude, if one is strong enough to hold positive attitude up to being at peace on the death of a beloved one..... «ታድያ እየሞቱ መሳቅና መደሰት ካለ፤ ለምንድን ነው እየኖሩ ማልቀስ የሚኖረው፡፡ አንዳንዶች በሞት ሲደሰቱ በኑሮ ለምን እናለቅሳለን? የአመለካከት ጉዳይ ነው፡፡ ለምን ሁል ጊዜ ችግሮችን በምሬትና፣ በሰቆቃ፣ በተስፋ መቁረጥና በኀዘን ስሜት ብቻ እንቀበላቸዋለን?
  but sometimes it is going to be so difficult and also impossible to do this! because we are just human being. but nothing is more than having and holding on a positive attitude in life, then after you will see your own life turning around and become upbeat!
  again thank you for your really nice article. kale hiwot yasemanil.

  ReplyDelete
 28. «እያለቀሱ የሚኖሩ አሉ፡፡ እየተደሰቱ የሚሞቱም አሉ፡፡ በክርስትና ታሪክ ብዙ ሰማዕታት እየዘመሩና እየተደሰቱ ነው የሞት ጽዋን የተቀበሉት፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በሕይወት እያሉ አንድም ቀን ሳይስቁ፣ እያማረሩና እያለቀሱ የሚኖሩ አሉ፡፡ ልዩነቱ ከምን የመነጨ ይመስላችኋል? ከአመለካከት ነው፡፡ እነዚያ ሞትን የኑሮ መጨረሻ አድርገው አላዩትም፡፡ እነዚያ ሞትን የመሸነፊያ መሣርያ አድርገው አላዩትም፡፡ እነዚያ ሞትን ቅጣት አድርገው አላዩትም፡፡ ለእነርሱ ሞት የሚሸሹት ሳይሆን የሚጋፈጡት ነው፡፡ ለእነርሱ ሞት ከአንድ ዓይነት የኑሮ ቅርጽ ወደ ሌላ ዓይነት የኑሮ ቅርጽ መሸጋገርያ ነው፡፡ ለእነርሱ ሞት ለእውነት የሚከፍሉት ዋጋ ነው፡፡ ለእነርሱ ሞት ለትውልድ የመልካም ሕይወት ድልድይ መሥሪያ ነው፡፡ ለእነርሱ ሞት ከመኖር ለሚበልጥ ዓላማ የሚከፈል ዋጋ ነው፡፡Egziabher yistlen.Solomon Dejene From Addis

  ReplyDelete
 29. “ዘመኑን እየዋጃችሁ ..፤” የሚለው ሕያው ቃል ነፍስ ዘርቶ ሲሄድ የምናየው ባንተ ነውና በርታ፤
  ጉዱ ካሳ ..ምናባዊው የማነኩሳ ልጅ ቁም ነገር አዘል መጣጥፍህ አይገታ..ምኞቴ ብዙነው ከፍሎሪዳ ጫካ

  ReplyDelete
 30. This very important for our country. We have good weather, beautiful landscope, very based religion. We have all but we are looking other country. It is okay the one who do not have work and opportunity, I am very sad the one who has all opportunity out of his country.

  ReplyDelete
 31. እኛምጋ እንደዚህ ነው ወዳጆቼ፡፡ ነፋሱ ምን አጠፋ፡፡ ተውት ይንፈስ፡፡ ለእኛ ግን ነፋሱ ምንድን ነው? ችግር ነው ወይስ በረከት? ዕዳ ነው ወይስ እሴት? ይህንን ብቻ ነው መመለስ ያለብን፡፡ ችግር ነው፣ ዕዳ ነው ካልን ለቅቀን ከሰፈራችን እንሂድ፡፡ በረከት ነው፣ እሴት ነው ካልን ደግሞ እንጠቀምበት፡፡ መወሰን ያለብን በነፋሱ ላይ ሳይሆን በራሳችን አመለካከት ላይ ነው፡፡

  ReplyDelete
 32. Thank you D/n Daniel. it is a good article. it is a nice view! you said it all, its all about attitude! its all about positive attitude, if one is strong enough to hold positive attitude up to being at peace on the death of a beloved one..... «ታድያ እየሞቱ መሳቅና መደሰት ካለ፤ ለምንድን ነው እየኖሩ ማልቀስ የሚኖረው፡፡ አንዳንዶች በሞት ሲደሰቱ በኑሮ ለምን እናለቅሳለን? የአመለካከት ጉዳይ ነው፡፡ ለምን ሁል ጊዜ ችግሮችን በምሬትና፣ በሰቆቃ፣ በተስፋ መቁረጥና በኀዘን ስሜት ብቻ እንቀበላቸዋለን?
  but sometimes it is going to be so difficult and also impossible to do this! because we are just human being. but nothing is more than having and holding on a positive attitude in life, then after you will see your own life turning around and become upbeat!
  again thank you for your really nice article. kale hiwot yasemanil.
  ReplyThis very important for our country. We have good weather, beautiful landscope, very based religion. We have all but we are looking other country. It is okay the one who do not have work and opportunity, I am very sad the one who has all opportunity out of his country.
  ReplyThis very important for our country. We have good weather, beautiful landscope, very based religion. We have all but we are looking other country. It is okay the one who do not have work and opportunity, I am very sad the one who has all opportunity out of his country.
  ReplyThis very important for our country. We have good weather, beautiful landscope, very based religion. We have all but we are looking other country. It is okay the one who do not have work and opportunity, I am very sad the one who has all opportunity out of his country.
  ReplyThis very important for our country. We have good weather, beautiful landscope, very based religion. We have all but we are looking other country. It is okay the one who do not have work and opportunity, I am very sad the one who has all opportunity out of his country.
  ReplyThis very important for our country. We have good weather, beautiful landscope, very based religion. We have all but we are looking other country. It is okay the one who do not have work and opportunity, I am very sad the one who has all opportunity out of his country.
  Reply

  ReplyDelete
 33. አንድ ወዳጄ እንዲህ የሚል የዕውቁን የግሪክ ፈላስፋ የሶቅራጥስን አባባል ላከልኝ፡፡

  ሶቅራጥስ አንድ ጓደኛ ነበረው አሉ፡፡ አንድ ቀን ይኼ ጓደኛው መጣና «ሶቅራጥስ እገሌ ስለሚባል አንድ ወዳጅህ የሰማሁትን ነገር ታውቃለህ?» አለው፡፡ ሶቅራጥስም ዝም ብሎ ተወው፡፡ ሰውዬው ግን በሰማው ነገር ሳይደነቅ አልቀረምና እየደጋገመ «በጣም የሚገርምኮ ነው፡፡ እንዲህ ይሆናል ብዬ የማልገምተው ነገር ነው» ይለው ነበር፡፡ በነገሩ የተሰላቸው ሶቅራጥስም
  «በጣም ጥሩ፡፡ የሰማኸውን ነገር ትነግረኛለህ፡፡ መጀመርያ ግን ሦስት ጥያቄዎችን መመለስ አለብህ፡፡ የምትነግረኝ ነገር የእነዚህን የሦስት ጥያቄዎች መልሶች የሚያሟላ ከሆነ ብቻ እሰማሃለሁ» አለው፡፡

  ReplyDelete
 34. ሦስተኛው ሰው ደግሞ «ይህ ሞገደኛ ነፋስ ለነዋሪዎቹ የተሰጠ በረከት ነው» አለ፡፡ «ነዋሪዎቹ ነፋሱ በሚቀንስበት የአካባቢው መልክዐ ምድር ላይ ሄደው እንዲሠፍሩ ማድረግ ይቻላል፡፡ ነገር ግን ይህንን ነፋስ መጠቀም አለባቸው፡፡ ይህ ነፋስ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ሊያመነጭ የሚችል ነው፡፡ በዚህ አካባቢ መተከል ያለባቸው መሣርያዎች አሉ፡፡ ነዋሪዎቹ በአንድ ላይ ገንዘብ አዋጥተው እነዚህን መሣርያዎች ይትከሉ፡፡ በጋራም ለየአካባው የኤሌክትሪክ ኃይል በመሸጥ ተጠቃሚ ይሁኑ፡፡ ይህ ነፋስ ችግር አይደለም፤ በረከት ነው፡፡» አለ፡፡

  ReplyDelete
 35. «ጨለማ በጸጥታ የምንሠራበት ጊዜ ነው» ያሉ ሰዎች መብራት ሠሩ፡፡ በጨለማ ለመሥራት፡፡ «ጨለማ የዕንቅልፍ ጊዜ ነው» ያሉ ሰዎች ይሄው እስካሁን እንደተኙ ናቸው፡፡ lol

  ReplyDelete
 36. I thought comment is open for everyone. Yesterday, I posted a comment but it is not displayed. afena mehonu new kikiki. You showed me that free speech is not our culture even in personal sites like this. Try to be open to accept any comment. You write , we read and appreciate as usual. no problem. one day, one day, I hope things will be changed.

  ReplyDelete
 37. እውን ዲ/ን ዳንኤል
  ከመንፈሳዊው አገልግሎት ርቋል?

  ዲ/ን ዳንኤል በቅርብ አውቀዋለሁ ትርፍ ጊዜ የሚባል የለውም:: ሥራዎቹ ሁሉ አገልግሎት ናቸው:: በቅርቡ ለንባብ የበቃዉን ራእየ ዮሐንስ የዓለም መጨረሻን ጨምሮ ከ20 የማያንሱ መንፈሳዊ መጻሕፍትን ለንባብ አብቅቶልናል:: በቢሮው ሙሉ ጊዜውን የሚሰጠውም ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ነው:: በሚውልባቸው ጉባኤያት ተገኝተ ከምንማረው በላይ በየወቅቱ በየኤሌክትሮኒክ ሚዲያው የምናገኛቸው ትምህርቶቹ ተደራሽነቱን ከፍ አድርገውለታል:: የበለጠ ደግሞ እይታዎቹን የሚያካፍልበት የጡመራ ገጹ ከዲ/ን አባይነህ ቃሉን ልዋስና የማኅበራዊ ወንጌል //አገልግሎት እየስጠን ነው:: ወንድማችንን በእድሜ በጸጋ ይጠብቅልን እንጂ በራሱ መነሳሳት ለሀገር ለወገን ለቤተ ክርስቲያን እየከፈለ ያለው አስተዋጽኦ ቀላል አይደለም:: ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቃልም በጽሑፍም የሚስጡትን አስተያየቶችን ስመለከት ዲ/ን ዳንኤልን በቅርበት ካለማወቅ የመነጨ የግንዛቤ ችግር አይባቸዋለሁ:: ዲ/ን ዳንኤል ከመንፈሳዊው አገልግሎት የራቀ አስመስለው ይስሉታል:: የክርክር አሳቤን ማቅረብ እፈልጋለሁ:: ወዳሴ ከንቱ ወዳድ አይደለምና በዚህ ጽሑፍ ሊያኮራው ፈልጎ ነው እንዳትሉኝና እንዳትሰናከሉ:: እርሱን እንደማይደንቀው አውቃለሁና:: ወደ ነጥቤ ልለፍ

  ወንድማችን ይህን አገልግሎት እየሰጠን ያለው ባለፉት ዘመናት ይሰጣቸው የነበሩ አገልግሎቶችቹን ፈጽሞ በመተው አይደለም:: ወርኃዊ ጋዜጣና መጽሔት ይልቅ በፈጠነ መንገድ ነው የመጣው:: እኛም ተጨማሪ መድረክ ነው ያገኘነው:: ስለዚህ ዲ/ን ዳንኤል ተደራሽነቱን እያሰፋ መጣ እንጂ አገልግሎቱ አልተዳከመም:: ይልቁንም ምሳሌውን የሚከተሉ በርካታ ሰዎችን ፈጥሯል:: አገልግሎቱን በጀመረ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ነበር ብዙ ወንድሞች መንገዱን ተከትለው ምልከታቸውን ትምህርቶቻቸውን ጠቃሚ የሚሏቸውን መረጃዎች ... የሚሰጡባቸው የጡመራ መድረኮችን የከፈቱት:: በመሆኑም የጎደለውን የሚሞሉ አማራጮች እያሉን ንስሐ ግቡ ቁረቡ የሚል ጽሑፍ አልጻፈምና ከመንፈሳዊ አገልግሎት ርቋል አያሰኝም:: መልእክቶቹ ምን ጊዜም ከበደል እንድንርቅ ከስህተት እንድንመለስ አስተሳሰባችንን እንድናርቅ የሚጎተጉቱ ናቸው:: ለመንግሥት መልእክት ማስተላለፍ ፖለቲከኛነት ሊሆን አይችልም:: እንደውም ወንድማችን ምንቸገረኝ ሳይል ከድርሻውም በላይ እየሠራ እንደሆነ የሚያመላክት ነው:: ነጥቤ ካላይ ለማሳየት እንደሞከርኩት የብሎጉ በረከት /የእይታዎቹ ተቋዳሾች/ የአንድ ቤተ እምነት ተከታዮች ብቻ አይደሉም:: ለመላው የአማርኛ አንባቢዎች በሥነ ምግባር መበልጸግ አስተዋጽኦ ያደርጋል:: በብዙዎች ላይም በጎ ተጽእኖ እያሳደረ ይገኛል:: ይህ ማለት በተዘዋዋሪ መንገድ የቤተ ክርስቲያኒቱ ተጽእኖ ነው:: ወንድማችን የሚሠራቸው ሥራዎች ሁሉ ምንም አይነት ይዘት ይኑራቸው ከአጠቃላዩ የቤተ ክርስቲያን መርህ የወጣ አይደለም:: በመሆኑም እያገለገለን ነው::

  አንዳንዶቻችን ደግሞ አቋምህን ግለጽ አይነት ነገር ስለ እንትን ምን ትላለህ? ጥያቄ እናቀርባለን በጻፈበት ጉዳይ ላይም ጭምር አልጻፍክም ዘራፍ የምንል አለን:: እኔ የሚገርመኝ እንደውም አሳባችሁን ማስተናገዱ ነው:: ለአገልግሎቱ ስኬታማነት አስተዋጽኦ የሚያደርጉ አስተያየቶች ቢኖሩን:: ዲ/ን ዳንኤል በሰነዘራቸው ምልከታዎች ላይ የራሳችንን እይታና ተሞክሮ ብናቀርብ ምንኛ በተማማርን ነበር:: የብሎጉን መርሖዎች ነግሮናል ምልከታዎቹ እያጣጣምን ሁለት ዓመት ዘልቀናል /ምንም እንኳን ሁለተኛ ልደቷን በታስቦ ይውላል ቢዘጋንም/ ብዙ የጡመራ ዘመናት ለዳኒ እለምናለሁ:: አምላካችን ዋጋ ከፋይ ነውና ዋጋውን ያብዛለት:: ለአገልግሎቱ መፋጠን የሚያግዙትን ሁሉ በረከቱ ይድረሳቸው::

  ReplyDelete
 38. ዲ/ን ዳንኤል በቅርብ አውቀዋለሁ ትርፍ ጊዜ የሚባል የለውም:: ሥራዎቹ ሁሉ አገልግሎት ናቸው:: በቅርቡ ለንባብ የበቃዉን ራእየ ዮሐንስ የዓለም መጨረሻን ጨምሮ ከ20 የማያንሱ መንፈሳዊ መጻሕፍትን ለንባብ አብቅቶልናል:: በቢሮው ሙሉ ጊዜውን የሚሰጠውም ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ነው:: በሚውልባቸው ጉባኤያት ተገኝተ ከምንማረው በላይ በየወቅቱ በየኤሌክትሮኒክ ሚዲያው የምናገኛቸው ትምህርቶቹ ተደራሽነቱን ከፍ አድርገውለታል:: የበለጠ ደግሞ እይታዎቹን የሚያካፍልበት የጡመራ ገጹ ከዲ/ን አባይነህ ቃሉን ልዋስና የማኅበራዊ ወንጌል //አገልግሎት እየስጠን ነው:: ወንድማችንን በእድሜ በጸጋ ይጠብቅልን እንጂ በራሱ መነሳሳት ለሀገር ለወገን ለቤተ ክርስቲያን እየከፈለ ያለው አስተዋጽኦ ቀላል አይደለም:: ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቃልም በጽሑፍም የሚስጡትን አስተያየቶችን ስመለከት ዲ/ን ዳንኤልን በቅርበት ካለማወቅ የመነጨ የግንዛቤ ችግር አይባቸዋለሁ:: ዲ/ን ዳንኤል ከመንፈሳዊው አገልግሎት የራቀ አስመስለው ይስሉታል:: የክርክር አሳቤን ማቅረብ እፈልጋለሁ:: ወዳሴ ከንቱ ወዳድ አይደለምና በዚህ ጽሑፍ ሊያኮራው ፈልጎ ነው እንዳትሉኝና እንዳትሰናከሉ:: እርሱን እንደማይደንቀው አውቃለሁና:: ወደ ነጥቤ ልለፍ

  ReplyDelete
 39. 5t is really nice blog. God bless U!!!.

  ReplyDelete