ባሕረ ሐሳብ
የቀመርና የሥነ ፈለክ ምሥጢር
አዘጋጅ፡- አለቃ ያሬድ ፈንታ ወልደ ዮሐንስ
የገጽ ብዛት፡- 214
ዋጋ፡- 50 ብር
ኅትመት፡- ፋርኢስት ትሬዲንግ
ዘመን፡- 2004 ዓመተ ሥጋዌ
ጥቂት ስለ ደራሲው፡- በ1915 ዓም የተወለዱት አለቃ ያሬድ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት የአቡሻክር ሊቃውንት ዋናውና አንጋፋው ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሚሰጡ ዋና ዋና ትምህርቶችን በሚገባ የተማሩት አለቃ ያሬድ ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅም ለአራት ዓመታት ተምረው ተመርቀዋል፡፡ አለቃ ያሬድ በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ኮሌጅ ለ24 ዓመታት ባሕረ ሐሳብን አስተምረዋል፡፡አለቃ ያሬድ ከማስተማር በተጨማሪ ልዩ ልዩ ጥናታዊ ጽሑፎችን በማቅረብም ይታወቃሉ፡፡ ይኼኛው አራተኛው መጽሐፋቸው ነው፡፡
መጽሐፉ
መጽሐፉ ከቃላት መፍቻ ይጀምራል፡፡ ይኼም ስለ ባሕረ ሐሳብ ማወቅ ለሚፈልግ ሰው ከትምህርቱ ጋር የተያያዙትን ሥያሜ ቃላት (Terminologies) እንዲረዳና ንባቡና ምርምሩ ቀና እንዲሆንለት ይረዳዋል፡፡
ወደ መጽሐፉ ሲገቡ እውነትም ይህ ትምህርት ባሕር ነው የሚያሰኝ ነገር ይገጥማችኋል፡፡ እያንዳንዱን በዓልና ጾም ለመወሰን የተጠቀሙበት ቀመር (Formula) አንድን ዘመን ወደፊትና ወደ ኋላ ተጉዞ ለማግኘት የሄዱበት የስሌት መንገድ እጅግ አስደናቂ ነው፡፡ በቀደምቶቻችን ዘንድ ስሌት የነበረውን ታላቅ ቦታ ያሳያችኋል፡፡
አበው ይጠቀሙባቸው የነበሩትን ሐሳበ ሳቤላን፣ ሐሳበ ጉንዳ ጉንዲን፣ የሐሳበ ግብፃውያንና ሐሳበ ቢዘንን እየተነተነ የእያንዳንዱን መነሻና ልዩነት ያትታል፡፡ ከዚህም አልፎ በጎንደር ዘመን በዐፄ ኢያሱ ጊዜ የተነሡ ሊቃውንት አራቱን ሐሳባት መርምረው ልዩነቶቻቸውን አንጥረው ያወጡበትን ምርምርም ይዟል፡፡
አለቃ ያሬድ የበዓላትና የአጽዋማት ማውጫ ቀመሮቹን ካስቀመጡ በኋላ ከ1984 ዓም ዕድሜ ከሰጠን እስከ 2480 ዓም ያለውን የበዓላትና የአጽዋማት ማውጫ ሠንጠረዥ አዘጋጅተውልናል፡፡
የየኔታ ያሬድን መጽሐፍ እስካሁን ከተጻፉት የባሕረ ሐሳብ መጻሕፍት ልዩ የሚያደርገው ስለ ጨረቃ፣ ፀሐይና ከዋክብት መንገዶች የጻፉት ሐተታ ነው፡፡ በዚህ ሐተታቸው ላይ ጨረቃ በየት ወጥታ በየት እንደምትገባ፣ በእያንዳንዱ ጉዞዋ የሚኖራትን መጠን፤ ከፀሐይ ጋር ያላትን ማነስና መብለጥ እየተነተኑ አቅርበዋል፡፡ እንዲያውም ለጨረቃና ለፀሐይ ብርሃንን የሚያወጡበት እንደ ወንፊት ያለ ነገር አላቸው ይህም ምዕዛር ወይንም ስቁረት ይባላል ይሉና ለፀሐይ 595 ለጨረቃ ደግሞ 105 አላቸው፡፡ የፀሐይ ብርሃን ከጨረቃ የሚበልጠው በዚህ ምክንያት ነው ይሉናል፡፡ ይህንን ብለውም አያበቁም፡፡ እያንዳንዱ ምዕዛር በስንት ሰዓት እንደሚከፈት ያትታሉ፡፡
በ1 ሰዓት 98
በ2 ሰዓት 196
በ3 ሰዓት 294
በ4 ሰዓት 392
በ5 ሰዓት 490
በ6 ሰዓት 588 ይከፈታሉ ይላሉ፡፡ በቀትር ሰዓት ፀሐይ የሚያይለውም ብዙ ምዕዛራት በዚያ ጊዜ ስለሚከፈቱ ነው ማለት ነው፡፡ ከስድስት ሰዓት በኋላ ደግሞ የመዘጊያቸው ጊዜ ነው ይሉናል፡፡ መጀመርያ የተከፈተው በሰባት ሰዓት ይዘጋል፡፡ ከዚያ እንዲያ እያለ እስከ አሥራ ሁለት ሰዓት ይቀጥላል፡፡
አለቃ ያሬድ የጨረቃን ብርሃን በየሰዓቱ ለክተው የብርሃንዋን መጠን በሠንጠረዥ አቅርበዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሊቃውንት እንዲህ የብርሃንን መጠን እስከ መለካት ደርሰው ነበር ማለት ነው፡፡
የአለቃ ያሬድ መጽሐፍ በፀሐይና በጨረቃ ብቻ አያቆምም፡፡ ወደ ከዋክብትም አልፎ የከዋክብትን ዓይነትና የአወጣጣቸውን ሁኔታ ከነ ስማቸው ይተነትናል፡፡ በየአንዳንዱ ወር የሚወጡ አሥራ ሁለት ከዋክብት መኖራቸውን፣ በእነርሱ ሥር የሚወጡ 28 ንኡሳን ከዋክብት መኖራቸውን ያትታሉ፡፡
አለቃ ከከዋክብት ወደ ነፋሳትም ይወርዳሉ፡፡ እንደ ሔኖክ አሥራ ሁለት ነፋሳት የሚነፍሱባቸው አሥራ ሁለት መስኮቶች መኖራቸውን ያትቱና እያንዳንዱ ነፋስ መቼ እንደሚወጣና ምን ይዞ እንደሚወጣም ይነግሩናል፡፡ ያንንም በሥዕል አሳይተዋል፡፡
የአለቃ ያሬድ መጽሐፍ እጅግ ጥልቅ ከሆነው ዕውቀታቸው የተቀዳ በመሆኑ ለእርሳቸው ትንሽ ለእኛ ግን ብዙ ነው፡፡ በተለይም ሐሳቡን በካርታ፣ በሥዕልና በሠንጠረዥ ለማስረዳት ያደረጉት ጥረት የሚመሰገን ነው፡፡
የዘጠና ዓመቱ አረጋዊ ሊቅ ወደ እግዚአብሔር ሳይሄዱ ቀድመን በተለይም በዚህ በዘመን አቆጣጠር ጉዳይ የሚነሡ ጥያቄዎችን በቀጥታ የሚመልሱበት፣ ሕዝቡም ጥያቄ የሚያቀርብበት መድረክ ቢፈጠር፤ ያም መድረክ በቪዲዮ ተቀርፆ አለቃን ከነ ሁለመናቸው እንድናስቀራቸው ቢደረግ መልካም ነው፡፡
እንዲህ ያሉ ሊቃውንትን ማጣት አንድ ቤተ መጻሕፍት እንደ ማጣት ነውና በተለይም ልጃቸው ሔኖክ ያሬድ አለቃ ነገ ተጠርተው ሲሄዱ ነፍሳቸው ከእግዚአብሔር ጋር እንደምትሆን ሁሉ ዕውቀታቸው ከኛ ጋር እንዲቀር የሚችለውን ሁሉ እንዲያደርግ አደራ እንላለን፡፡
መጽሐፉ ባለፈው ረቡዕ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም በመኰንን አዳራሽ፣ ትናንትና ደግሞ ራሳቸው አለቃ ለሃያ ስድስት ዓመታት ባስተማሩበትና አሁንም በማስተማር ላይ በሚገኙበት የካፑቺን ፍራንሲስካን የፍልስፍናና የነገረ መለኰት ተቋም ተመርቋል፡፡ እግረ መንገዳችንንም በተቋሙ ያገለገሉበትን የብር ኢዮቤልዩ አክብረናል፡፡
ReplyDeleteአለቃ ያሬድ ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ይክበር ይመስገንና ዛሬም በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ፡፡ ከእኔ ከወጣቱ በላይ እጅግ ጠንካራ ሁነውም ይታያሉ፡፡ ነገር ግን ትንሽ የመስማት ችግር እየገጠማቸው ይመስላል፡፡ ምንም እንኳ እኛ አንድ ሺህ ጥያቄዎች ጥያቄዎች ቢኖሩንና እርሳቸውም አንድ ሚሊየን መልሶች ቢኖሯቸውም እንኳ ይህ የመደማመጥ ችግር ዕንቅፋት እንዳይሆንብን እሰጋለሁ፡፡ በመሆኑም ችግሩ ሳይባባስ ገንዘብ አሰባስበን "hearing aid" እንዲያገኙ የምናደርግበት መንገድ ቢመቻች ተገቢ ይመስለኛል፡፡
ዳኒ 'ለቤተመጳሀፎ' ስትል እባክህ የምንገዛበትንም ዌብ ብትነግረን በጣም አመስግናለሁ።
ReplyDeleteThanks Dani, it is amazing. We really need to do something to help this. Can you please organise something so that also of can contribute something.
ReplyDeleteI don't know if Aleka has a good contact with The Ethiopian Astronomical Association. Thi might be one opportunity. http://www.physics.ncat.edu/~michael/vses/eth4000/henok/
I have forwarded your blog for a friend who is part of this organisation so that he can find out some more information with Aleka Yared.
We should all do something and support his son Henok if he comes with some idea.
Thanks.
i am always committed to know about our calendar(abushaker)and i think this is a good material to explore the magnificent of the abushker.thanks dani to inform us this precious thing.but there is a constraint.I am in mekelle and I don't know how I get this book.if there are legal distributors assigned in the regions please inform us.or mahibere kidusan mekelle branch can bring it to us so please do something dani in mahibee kidusan to distribute this historical book.I also recommend them to post the soft copy in mereb.com the on line seller of books,so the Diaspora will able to read this book.thanks.yohannes hagos from mekelle
ReplyDelete"የአለቃ ያሬድ መጽሐፍ እጅግ ጥልቅ ከሆነው ዕውቀታቸው የተቀዳ በመሆኑ ለእርሳቸው ትንሽ ለእኛ ግን ብዙ ነው፡፡" አገላለጽህን ወድጀዋለሁ፡፡ ዳኒ አንተ ሁሌም ታላቃችን ነህ፡፡
ReplyDeleteዳኒ አንተ ሁሌም ታላቃችን ነህ፡፡ yes daniel is our great brother .he is the best son of ethiopia
Deleteዲ/ን ዳንኤል አለቃ ያሬድን በ አካል እንደምታገኛቸዉ አስባለሁ እባክህ ባገኘሀቸዉ ጊዜ ‹‹ ለእርስዎ ምስጋና ይድረስዎትና የሀገራችንን አቆጣጠር በየቤታችን ለመማር በቃን እጅግ ጥልቅ ከሆነዉ የአባቶቻችን እዉቀትም ለመቋደስ አስቻሉን›› በልልኝ
ReplyDeleteዳኒ ቢያንስ በየጊዜያቱ የሚከወኑትን ሥራዎች በዚህ መድረክህ እያወጣህ እንድናውቅ ስላደረከን በጣም እናመሰግናለን፡፡ በኢትዮጵያችን ከአምስተኛው እና ስድስተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ መፀኀፍት ይጻፋሉ፣ ምስጋና ይድረሳቸውና፣ አባቶቻችንና እናቶቻችን እውቀታቸውን በተለያዩ መጻኀፍት ይጽፋሉ አንተን ጨምሮ ማለት ነው፡፡ እኛም ያቅማችንን እናነብ ነበር፡፡ ነገር ግን አሁን አሁን መጽኀፍትን ጎንበስ ብሎ ከማንበብ ይልቅ እይታን እየመረጥን ከኢንተርኔት የሚገኙ ጽሑፎች በተለይም እጅግ የበዙ ጡመራዎች ባለችን ጊዜ እናነባለን የሚጠቅመውንም የሚጎዳውንም አይናችን እስኪቀላ ማፍጠጥ ምርጫችን ሆኗል፡፡ ስለዚህ የታተሙትን ጽኁፎች ለማንበብ ወኔውን ከየት እናምጣው ? እርግጠኛ ነኝ ይህ የኔ ብቻ ችግር አይደለም፡፡
ReplyDeleteDn Daniel, Thanks
ReplyDeletePlease advertise for the Abel Gashe as well
http://www.amazon.com/The-Wisdom-Compass-Eternal-Life/dp/146533808X/ref=sr_1_1?s=books&ie=UTF8&qid=1336054395&sr=1-1.
"የአለቃ ያሬድ መጽሐፍ እጅግ ጥልቅ ከሆነው ዕውቀታቸው የተቀዳ በመሆኑ ለእርሳቸው ትንሽ ለእኛ ግን ብዙ ነው፡፡"
ReplyDeleteይገርማል ዳኒ መታኸንኮ!፣ ከተሳለ አእምሮ በሰላ ብዕር!! የኔ ቢጤ አላዋቂ ቢሆን "ያለውን የወረወረ ፈሪ አይባልም" ባለ ነበር፡፡አንተ ሁሌም መምህር ነህ ዳኒ ፡፡
ለአለቃም ዕድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን፡፡
I AM CONFUSED.I SINCERELY LOVE AND HONER ETHIOPIAN ORTHODOX LIQAWENT,BUUUUUTTTTT THERE ARE SOME FACTS THAT CONFLICT WITH SCIENCE SPECIALLY THE ONE THAT TALKS ABOUT THE LIGHT INTENSITY OF THE SUN AND OF THE MOON.AND BAHIRE HASAB IS NOT A BELIEF IT IS IN FACT A MATHEMATICAL KNOWLEDGE AND TO THE EXTENT I COULDN'T CLEARLY STATE IT IS SCIENCE.SO IT WAS NOT SUPPOSE TO BE IN CONFLICT.SO I WANA READ AN ARTICLE THAT TACKLES THE BIG QUESTIONS.
ReplyDeleteDiakon Dani, Egziabhere yestellegn. @Yhones Hagos, Such a brilliant idea you have. I'll shortly be contacting the customer service @'mereb.com.et' if they can advertise it on their site. Ante zemed or guadegna kaleh enesu endilekuleh betaderges? yene bahir mado selehone be guadegna weyem zemed kebed yelal beye new!
ReplyDeletedani you made me confuse last time here in dallas,tx,you saied that the sun is not move.but now you try to suporet that sun has a window.which one is right?please let me know which one is true?you or..............
ReplyDeleteወደ እግዚአብሔር ሳይሄዱ ቀድመን በተለይም በዚህ በዘመን አቆጣጠር ጉዳይ የሚነሡ ጥያቄዎችን በቀጥታ የሚመልሱበት፣ ሕዝቡም ጥያቄ የሚያቀርብበት መድረክ ቢፈጠር፤ ያም መድረክ በቪዲዮ ተቀርፆ አለቃን ከነ ሁለመናቸው እንድናስቀራቸው ቢደረግ መልካም ነው፡፡
ReplyDeleteThank you Daniel for your info.
ReplyDeleteHow interesting. I knew that Gashe Yared was a walking encycopaedia of the history and practices of the Ethiopian Orthodox Tewahdo Church. And it pleases me to hear that he is sharing his immense knowledge with like-minded so that some members of the young generation can perhaps pick up the line after him. The history of the Church is such an important part of Ethiopian history in general.
ዲ ዳንኤል እግዚአብሔር ይባርክህ::
ReplyDeleteዳኒ መጽሐፉን ልናገኝ የምንችልበትን መንገድ ብትጠቁመን! እግዚአብሔር ሁላችሁንም ያቆያችሁ
ReplyDeleteአብነት ከሆሳዕና
Hi Dani! say some about'waledeba gedam'please! am waiting detail inf.
ReplyDeleteMamush,MN
mahberun ena anten gieta ytebq. berta
ReplyDeleteI am afraid very few people are aware of the importance of this book. This book deserves a much wider readership, especially those interested in history of the church and in a way also regarding Ethiopian identity, for those belonging to the Tewahdo Orthodox church. This is not a run-off-the-mill authorship. It is the outcome of a lifelong dedication. If we want to realize the place of Ethiopia on the global cultural shelf, then look no further. Congratulations Aleka Yared. The nation owes you gratitude.
ReplyDelete