Thursday, May 17, 2012

«ካህናተ ደብተራ»

«እናንተ ደብተራ ከምትባሉት በቀር ይህንን ሁሉ ያደረገ ማነው? ታመሰግኑታላችሁ፣ ታወድሱታላችሁ፣ እንዳንተ ያለ ኀያል ማነው? ትሉታላችሁ፤ እንዳንተ ያለ ድል አድራጊ፣ እንዳንተስ ያለ ለጋሥ በሁሉ ዘንድ ወዴት አለ? እንዳንተ ያለስ ምጽዋት ሰጭ የት አለ? ትሉታላችሁ፡፡ እንዲህ ስታመሰግኑትም በኀጢአት ላይ ኀጢአትን ይጨምራል፡፡»
ይህንን ቃል ከዛሬ ሰባት መቶ ዓመታት በፊት የተናገረው ታላቁ ተጋዳይ አባት አባ በጸሎተ ሚካኤል ዘደብረ ጎል ነው፡፡ ንጉሥ ዓምደ ጽዮን ከክርስትና ሕግ ውጭ የአባቱን ሚስት በማግባቱ እንደ ዮሐንስ መጥምቅና እንደ ዮሐንስ አፈወርቅ ሳይፈራና ሳያፍር ፊት ለፊት በመገሠፁ ብዙ መከራ ደረሰበት፡፡ ተገረፈ፤ ታሠረ፤ ተሰደደም፡፡
አስቀድማ የንጉሡ ሚስት የነበረች በኋላ ደግሞ ንጉሡ ለአንዱ ወታደሩ የሰጣት አንዲት ሴት ነበረች፡፡ ይህቺ ሴት ይህንን ሕይወት ንቃ ንስሐ ገባችና ሥጋወደሙ ተቀበለች፡፡ ንጉሥ ዓምደ ጽዮን «ሂዳችሁ አምጧት፤ እኔም በመኝታዬ አረክሳታለሁ» ብሎ በድፍረት ተናገረ፡፡ መልክተኛ ወደ ሴቲቱ ሲሄድ እርሷ ወደ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ዘንድ ላከች፡፡

አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ልጆቹን እንዲህ አላቸው «ተነሡ እግዚአብሔር ሥራ እንዲሠራ እንለምነው፡፡ ክውስጣዊ ልብሳችሁ በቀር ሌላውን አውልቁ፡፡ በፊቱም እያለቀስን እንለምነው»፡፡ ሌሊቱን ሙሉ በዕንባና በስግደት፣ በጸሎትና በማዕጠንት እግዚአብሔርን ሲለምኑት አደሩ፡፡ ሲያለቅስ መሬቱ የሚረጥብ አለ፡፡ ሲሰግድ መሬቱ የሚጎደጉድ አለ፡፡ ደረቱን ሲደቃ ውጭ ድረስ የሚሰማ አለ፡፡ ሲያጥን ዕንባው እሳቱን የሚያጠፋው አለ፡፡
ሌሊት ንጉሡ በከባድ ሕመም ታመመ፡፡ ነፍሱም ልትወጣ ደረሰች፡፡ ያን ጊዜ ባለሟሎቹ ቀረቡ፡፡ እርሱም «ይህ ሕመም በምን ምክንያት እንደ መጣ አውቄዋለሁ፤ ያቺን የበጸሎተ ሚካኤልን ልጅ ላረክሳት በመፈለጌ ነው፡፡ አሁንም ሂዱና ይቅር በለኝ በሉት» ብሎ በቤተ መንግሥቱ የሚያገለግሉትን ካህናት ላካቸው፡፡
ካህናቱ ወደ አባ በጸሎተ ሚካኤል ሲደርሱ «ልጆቼ ተነሡ እግዚአብሔር ሰምቶናል፡፡ ልብሶቻችሁን ልበሱ፤ መልክተኞችም መጥተዋል» አላቸው፡፡ እነርሱም ተነሥተው ከመቅደስ ሲወጡ የንጉሡን መልክተኞች አገኟቸው፡፡ መልክተኞቹም የንጉሡን መልክት ነገሩት፡፡ አባ በጸሎተ ሚካኤልም «እግዚአ ብሔር ይቅር ይበልህ በሉት» አላቸው፡፡ የንጉሡን አገልጋይ ካህናት ግን እጅግ ወቀሳቸው፡፡
አባ በጸሎተ ሚካኤል የወቀሳቸው ካህናት በዚያ ዘመን «ካህናተ ደብተራ» ይባሉ ነበር፡፡ ስማቸው የተወሰደው በንጉሡ ቤተ መንግሥት የምትገኘውንና በድንኳን ያለቺውን ቤተ ክርስቲያን ስለሚያገለግሉ ነው፡፡ ነገሥታቱ በየሀገሩ ስለሚዘዋወሩ የድንኳን ቤተ ክርስቲያን ነበራቸው፡፡ እዚያ ካህናት ይመደባሉ፡፡
የእነዚህ ካህናት ጠባይ በሌላው ቦታ ከነበሩት ካህናት ጠባይ ይለይ ነበር፡፡ ካህናተ ደብተራ የሚታወቁባቸው ጠባያት ነበሯቸው፡፡ የመጀመርያው ጠባያቸው በገዳም ከሚኖሩት ቅዱሳን አበው ጋር አለመስማማታቸው ነው፡፡ ለእነርሱ ገዳማዊ ሕይወት ጊዜ ማጥፋትና ራስን ማሞኘት ነው፡፡ በገዳም ያሉ አባቶቸንም በትኅትናቸው ምክንያት ይንቋቸው ነበር፡፡ እነርሱን ማሳጣትና መክሰስ ብሎም ከየገዳማቸው ማሳደድ የዘወትር ተግባራቸው ነበር፡፡ ገዳማቱ ሲፈቱና ማኅበረ መነኮሳቱ ሲበተኑ ምንም ዓይነት ቁብ አይሰጣቸውም ነበር፡፡ እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ የንጉሡ ወታደሮች የሚያዝኑላቸውን ያህል ካህናተ ደብተራ ለገዳማውያን አባቶች አያዝኑም፡፡ ወደ ንጉሡ ዘንድ ደርሰው ጉዳያቸውን እንዳያስፈጽሙ ከጠባቂዎቹ ይልቅ የሚያስቸግሯቸው ካህናተ ደብተራ ነበሩ፡፡
ሁለተኛው ጠባያቸው ደግሞ ማንኛውንም ነገር ከጥቅም ጋር ማገናኘታቸው ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና ሕግ፣ የእግዚአብሔር ቁጣና ቅጣት አይታያቸውም፡፡ ከንጉሡ ማዕድ እየበሉና ፍርፋሪ እየለቀሙ፣ በንጉሡም ካባና ላንቃ እየተሸለሙ ስለሚኖሩ የሚሠሩት የሚገባቸውን ሳይሆን የሚያበላቸውን ነው፡፡ በቤተ መንግሥቱ ያገኙትን ክብርና ማዕድ ዳያጡ ሲሉ ማንኛውንም ሃይማኖታዊ የሆነ ተግባር ከማድረግ አይመለሱም፡፡
በገድለ አቡነ ፊልጶስ ዘደብረ ሊባኖስ ላይ እንደ ተጻፈው ዓምደ ጽዮንንም ሆነ ልጁን ሰይፈ አርእድን ትክክል ያልሆነ ትምህርት አስተምረው ያሳሳቱት ካህናተ ደብተራ ናቸው፡፡ አቡነ ፊልጶስ ዘደብረ ሊባኖስ ወደ ዓምደ ጽዮን ገብተው ለምን ይህንን ጥፋት እንዳጠፋና የአባቱን ሚስት እንዳገባ ሲጠይቁት « ዐዋቂዎች የሆኑ ካህናት እርሷን ካላገባህ መንግሥትህ አይጸናም ብለውኝ ነው» ነበር ያላቸው፡፡ ከካህናተ ደብተራ አንዱ የነበረው እወደድ ባዩ ዘአማኑኤል የተባለ ሰው ከንጉሥ ዓምደ ጽዮን በኋላ የነገሠውን ሰይፈ አርእድን በተመሳሳይ ስሕተት አሳስቶት ነበር፡፡ «ከጥቂት ጊዜም በኋላ ዘአማኑኤል የሚባል አንድ ሰው ተነሣ፡፡ ይህም በግብር ሳይሆን በስም ነው፤ እርሱ ንጉሡን እንዲህ ሲል አሳስቶታልና፡ አንተ ንጉሥ ነህና በአንዲት ሚስት ልትኖር አይቻልህም፤ ንጉሥማ ሦስት ሚስት እንዲያገባ ታዝዞለታል ብሎም አስተማረው» (ገድለ አቡነ ፊልጶስ፣ ገጽ 225)
ካህናተ ደብተራ ንጉሡን የሚያስደስትና ጥቅማቸውን የሚያስከብር ከመሰላቸው ከንጉሡ በላይም ሄደው ግፍ ከመፈጸም አይመለሱም ነበር፡፡ በሰይፈ አርእድ ዘመነ መንግሥት ተመሳሳይ ስሕተት መሠራቱን አይተው አበው ከየአቅጣጫው መጥተው ሲገሥፁት አቡነ አኖሬዎስ ንጉሡን በኃይል ተናገረው፡፡ ይህንን ያየው የንጉሡ ማዕድ ባራኪ ካህን ወይም ቄስ ሐፄ ከወታደሮቹ ተሽቀዳደመና አቡነ አሮንን በጥፊ መታው፡፡ ለምን እንደ መታው ገድለ አቡነ አኖሬዎስ ሲናገር «በንጉሡ ዘንድ ሊመሰገን ሽቶ» ይለዋል፡፡ ያን ጊዜም አቡነ አኖሬዎስ «ለምን ትመታኛለህ? ለሰው ከማድላት ለእግዚአብሔር ማድላት አይሻልህም ነበር አለው ይላል፡፡ ቄስ ሐፄው ግን ያሰበውን ምስጋና አላገኘም፡፡ በአበው ኀዘን ምክንያት ወዲያውኑ ሞተ፡፡
የካህናተ ደብተራ ሌላው ጠባይ ደግሞ ወተቱን ማጥቆር ከሉን ማንጣት ነው፡፡ እውነትን የሚመዝኗት ከጥቅማቸው አንፃር ብቻ ስለነበረ ኃጢአት ሲሠራ እያዩ ጽድቅ ነው፤ ግፍ ሲፈጸም እያዩ ቅድስና ነው ማለት ይወዱ ነበር፡፡ ነገሥታቱና መኳንንቱ በበደል ላይ በደል እንዲጨምሩ ያደርጓቸው የነበሩትም እነርሱ ናቸው፡፡ ለዚህ ነው አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ወደ እርሱ ለማማለድ የመጡትን ካህናተ ደብተራ «እናንተ ደብተራ ከምትባሉት በቀር ይህንን ሁሉ ያደረገ ማነው? ታመሰግኑታላችሁ፣ ታወድሱታላችሁ፣ እንዳንተ ያለ ኀያል ማነው? ትሉታላችሁ፤ እንዳንተ ያለ ድል አድራጊ፣ እንዳንተስ ያለ ለጋሥ በሁሉ ዘንድ ወዴት አለ) እንዳንተ ያለስ ምጽዋት ሰጭ የት አለ? ትሉታላችሁ፡፡ እንዲህ ስታመሰግኑትም በኀጢአት ላይ ኀጢአትን ይጨምራል፡፡» ያላቸው በዚህ ምክንያት ነው፡፡
አንዳንዶቹ የካህናተ ደብተራ ወገኖች ሹመት እንጂ እምነት አልነበራቸውም፡፡ በገድለ አቡነ አኖሬዎስ ላይ እንደ ግብጦን በተባለ ቦታ ንቡረ እድነት የተሾመ አንድ የካህናተ ደብተራ ወገን ነበረ፡፡ ይህ ሰው ምንም ሳያደርገው በቅድስናው ብቻ አቡነ አኖሬዎስን ይጠላው ነበር፡፡
አንድ ቀን «ምን እንደምትሠራ ለማየት እመጣለሁ» ሲል ላከበት፡፡ ይህ ሰው ሹመት ሽልማት ፈልጎ ንቡረ እድ ሆነ እንጂ እግዚአብሔርን እንኳን የማያመልክ ሰው ነበረ፡፡ ገድለ አቡነ አኖሬዎስ እንዲህ ይላል «ቅዱሱም በዚያ በገዳሙ እያለ ስሙ ጳውሎስ የሚባል አንድ ሰው በትዕቢት «መጥቼ ሥራህን አያለሁ» ብሎ ወደ እርሱ ላከበት፡፡ ያም በስም መነኩሴና ንቡረ እድ የሆነ፣ ከንጉሡም ዘንድ የተሾመ ነበረ፡፡ እርሱም ቤተ ክርስቲያንን አጠፋት፡፡ ምእመናንንም አሳዘናቸው፡፡ የተላከውም መልክተኛ ለአባታችን ይህንን ነገረው፡፡ አባታችንም ይህንን ሰምቶ «ኃጥእን እንደ አርዘ ሊባኖስ ከፍ ከፍ ብሎ አየሁት፤» ብሎ ተናገረ፡፡ ወደ እግዚአብሔርም ስለ እርሱ ጮኸ፡፡ ያም በትዕቢቱ ሞትን አገኘ፡፡ ለቅዱሱም እንደ ሞተ ነገሩት፡፡ እርሱም «በተመለስኩ ጊዜ ግን አጣሁት» አለ፡፡ እርሱም «በምን ሞተ አላቸው፡፡ እነርሱም «ሌሎች አማልክትን ያመልክ ነበር» አሉት፡፡ ቅዱስ አባታችንም መራር ልቅሶን አለቀሰ፡፡ «ፈለግኩ ቦታውንም አላገኘሁትም» አለ፡፡
አንዳንዶቹ ካህናተ ደብተራ ክህነትን ለእንጀራ ማግኛና ለክብር መሸመቻ እንጂ አምነውበት የሚያገለግሉበት አልነበረም፡፡ ርስት ጉልት ስላለ፣ በንጉሡ ማዕድ ለመቅረብ ስለሚያስችል፣ ልብስና መዓርግም ስለሚያሰጥ ነበር ወደ ክህነቱ የገቡት፡፡
ካህናተ ደብተራ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ለእንጀራና ክብር ማግኛ ብቻ እንጂ ለድኅነት ስለማይ ጠቀሙበት አንዳንድ ጊዜ ነገሥታቱን ከአምልኮ እግዚአብሔር ወደ ጥንቆላ ይከቷቸው የነበሩት እነርሱ ነበሩ፡፡ በዐፄ ዳዊት ዘመን አባ ጊዮርጊስ ሲከራከራቸው የነበሩትና በኋላም በንጽሕናው ምክንያት ተመቅ ኝተው ወደ ዳሞት እንዲጋዝ ያደረጉት በጥንቆላ ሥራ ተሠማርተው የነበሩት ካህናተ ደብተራ ነበሩ፡፡
ካህናተ ደብተራ በዕውቀትና በቅድስና የሚበልጧቸውን አባቶችና ሊቃውንት አይወዷቸውም፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ለማበልጸግ፤ ለማደራጀትና ስብከተ ወንጌልን ለማስፋፋት የሚጥር ሁሉ ጠላታቸው ነው፡፡ ግብጻዊው ጳጳስ አቡነ ያዕቆብ አቡነ ፊልጶስን ኤጲስ ቆጶስነት ሊሾመው ሲነሣ በዋናነት የተቃወሙት ካህናተ ደብተራ እንደነበሩ ገድለ አቡነ ፊልጶስ ይነግረናል «እንደዚህ አታድርግ፤ በአንድ ሀገር ሁለት ኤጲስ ቆጶስ ይሆናልን? ሕዝቡ ይከፋፈላል፤ የአንተም ክብርህ ይጠፋል፤ ምድረ ሼዋኮ ከፊል መንግሥት ናት፤ እንዴት እንደዚህ ትላለህ? ከኛ በኋላ የሚመጣ ትውልድም ይህንን አይፈቅድም፤ ከኛም አስቀድሞ እንዲሁ ነበረ፡፡ እኛስ ከኛ በፊት የነበሩ አበው ጳጳሳት ያላደረጉትምን አናደርግም፣ አንናገርምም» (ገድለ አቡነ ፊልጶስ፣ ገጽ 197)
በወቅቱ የነበረውን የደቡቡን ክፍል ከአሥራ ሁለት ከፍሎ አሥራ ሁለት ወንጌላውያንን የሾመውን በሰሜኑ ክፍልም ሐዋርያትን ያሠማራውን ግብፃዊውን አቡነ ያዕቆብን ካህናተ ደብተራ አልወደዱትም፡፡ የስብከተ ወንጌል መስፋፋትና የሕዝቡ ማወቅ ለእነርሱ የግብዝነትና የኃጢአት ሥራ ዕንቅፋት ይሆናል ብለው አሰቡ፡፡ በዚህም የተነሣ ይህንን የስብከተ ወንጌል አደረጃጀትና ሥምሪት ማጥፋት እንዳለባቸው ወሰኑ፡፡ በዚህም ምክንያት ዘአማኑኤል ንጉሡ አቡነ ያዕቆብን ወደ ግብጽ እንዲመልሰው መከረው፡፡ አቡነ ያዕቆብ ስላወገዘውም በለምጽ ተመትቶ ሞተ፡፡ አቡነ ያዕቆብም ወደ ግብጽ ተመለሰ፡፡
በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ የእውነተኞቹ አባው፣ ሊቃውንትና ካህናት አገልግሎትና ትሩፋት ለቤተ ክርስቲያን ብልጽግና እንዳይሰጥ ሲያሰናክሉና ለእውነት ዕንቅፋት ሲሆኑ የኖሩት ካህናተ ደብተራ ናቸው፡፡ እንክርዳዱ ከስንዴው ጋር አብሮ እስከ መከር ይኖራልና የካህናተ ደብተራ ጠባይና አሠራር ዛሬም ቤተ ክርስቲያንን ሲያውካት ይኖራል፡፡ እንደ አቡነ አሮን፣ እንደ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል እንደ አቡነ ፊልጶስና እንደ አቡነ አኖሬዎስ ያሉ ጀግኖችን እስክታገኝ ድረስ፡፡click here for pdf

40 comments:

 1. "የካህናተ ደብተራ ጠባይና አሠራር ዛሬም ቤተ ክርስቲያንን ሲያውካት ይኖራል፡፡ እንደ አቡነ አሮን፣ እንደ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል እንደ አቡነ ፊልጶስና እንደ አቡነ አኖሬዎስ ያሉ ጀግኖችን እስክታገኝ ድረስ፡፡"

  ReplyDelete
 2. ግሩም ነው ወቅቱን የዋጀ ጽሁፍ! እ/ር የ አገልግሎት ዘመንህን ይባርክ

  ReplyDelete
 3. ለሰው ከማድላት ለእግዚአብሔር ማድላት አይሻልህም ነበር...? like

  ReplyDelete
 4. ውድ ወንድሜ፤
  በጣም በአዘንሁበት ስዓት ይሄን ጽሑፍ በመልቀቅህ በጣም ደስ ብሎኛል ብል እራሴን መሸወድ ነው። ግን አመሰግንሃለሁ። ያ ጀግና መቼ ይሆን የሚገኘው? እንዴት የእሳት ልጅ አመድ እንሆናለን? ደፍሮ አሁንስ በዛ ለማለት ጉሮሮአችንን ምን ዘጋው? በወናፍና በብረት መቀጥቀጫው መሃል እስከ መቼ ነው የምንኖረው? በውኑ ስርዓተ ቤተክርስቲያን ይጠበቅ፤ እግዚአብሔር የሚመለክበትን ቦታ አታርክሱ ማለት ከፓለቲካ ይቆጠር ይሆን? የአባቶቻችን እንቅልፍ ብቻ አይደለም የሚያሳስበኝ፤ እነሱ ባንቀላፉበት መደዴዎች ገብተው የሚያስጋቡት ተንኮል ነው እንጂ። በውኑ በአምላኬ ፊት ምን ይዤ እንደምቀርብ ግራ ይገባኛል። ቤተ ክርስቲያን ስትከፋፈል ጀሮ ዳባ ልበስ ያልሁ፤ ቀናኢ አባቶች ሲደበደቡ ዝም ያልሁ፤ መስቀሉን ሲያቃልሉ ያልሰማሁ፤ ቅዱሱ ቦታ ሲታረስ ያላዬሁ፤ ለጥቅማቸው ክህነት ለመቀበል የሚሯሯጡ ሰዎችን አሁንስ በዛ አቁሙ ያላልሁ፤ ጣኦት በአደባባይ ሲቆም አጎንብሼ ያለፍኩ፤ ቤተክርስቲያን ስትቃጠል ያልሰማሁ ብላቴና ልጅህ መጥቻለሁና ተቀበለኝ ነው የምለው? ወይስ እኒህ ግፋና መከራዎችን ለማስቆም መስዋዕትነት ከፍዬ ስለመጣህ ማረኝ ነው የምለው? እስኪ ልቦና ይስጠን። እንዳንተ ያሉ እውነተኛ ጸሐፊዎችን አያሳጣኝ። ቢያንስ አንድ ቀን ድርፈቱን አግኝቼ ከበረከቱ ተካፋይ እሆን ይሆናል። ካልሆነም ወዬልኝ።

  ReplyDelete
 5. God bless you D.Daniel.It is very important article.it is amazing how people live with this kind of
  cruel while they are acting part of God mission. Mastewalen yestachew & yisten .

  ReplyDelete
 6. Egziabher Be Tsegaw Yitebikih. Bezih Zemen Melkam eyeseru mekoyet kebad newuna.

  "kahinate debteran " bemenfesawuyan abatoche ayin sayachew asazenugn. Sew endet kibur hono sale behodu lehodu bicha yasibal ?

  Geta nisehan yemiwod, yemiyastemir hono sale shachochin ena lewachochin bejiraf yegerefebet ena yabarerebet mistir lezih yihon ? " ende ensisa silehonu be dula menedat yishalal bilo yihon ? "

  Kahinate debtera yihe yihon yemishalachewu weyis niseha ?


  Betam yemiyasazinew eko yihin tsihuf siyanebu enkuwan lene new bilew ayasibum.

  Hulgize egziabheren ameseginewalehu. Lebetu maseb mecheneq kesigana kedem aydelem. Yihinn tsega silalnefegegne getayen ameseginewalehu.

  EAD

  ReplyDelete
 7. Thank you Dn. Daniel. It is a timely article. Till the edict of Milan the Christian Church Fathers were so brave and strong to accept any persecution for the sake of their faith. But the edict of Milan, which gave freedom for the church has overshadowed its negative impact on the christian church. The so-called kahinate debtera has come to being since then. The Church lost her strength; the bishops and the priests have started to trust in the political leaders and have made flesh their strength. Even we are in need of blessings from these political leaders to fulfill our mission that has given us by God the Almighty. So let us pray to God that He may bring us back to the spirit and the strength of our holy fathers and mothers.

  ReplyDelete
 8. የሚያነበው ከተገኘ ቆንጆ የበቅሎ ልጓም ነው ፡፡ ትክክለኛውን መንገድ ለማሳየት ትንሽም ቢሆን ይጐሽማል ፡፡ ድሃነታችን ከሃይማኖት ይልቅ ገንዘብን የምናመልክ ይመስል የሰሞኑ ግርግር ትኩስ ርዕስ የተደረገና ለሲኖዶስ የቀረበው ከሃይማኖት ህጸጽ ይልቅ የመኪናና የቤት ጉዳይ ነው ፡፡

  ReplyDelete
 9. ቃለህይወት ያሰማልን ይህ ለኔ አዲስ እውቀት ነው የተሰማኝና በጣም ያዘንኩት ምን ያህል ቤተክርስቲያን በካህናተ ደብተራ መወረርዋ ሳስብ ነው። ለካ ይሄም ኑሯል ያሰያል።

  ReplyDelete
 10. "በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ የእውነተኞቹ አባው፣ ሊቃውንትና ካህናት አገልግሎትና ትሩፋት ለቤተ ክርስቲያን ብልጽግና እንዳይሰጥ ሲያሰናክሉና ለእውነት ዕንቅፋት ሲሆኑ የኖሩት ካህናተ ደብተራ ናቸው፡፡ እንክርዳዱ ከስንዴው ጋር አብሮ እስከ መከር ይኖራልና የካህናተ ደብተራ ጠባይና አሠራር ዛሬም ቤተ ክርስቲያንን ሲያውካት ይኖራል፡፡ እንደ አቡነ አሮን፣ እንደ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል እንደ አቡነ ፊልጶስና እንደ አቡነ አኖሬዎስ ያሉ ጀግኖችን እስክታገኝ ድረስ፡፡"

  hmmmmmm, lebe kosele, ye ahunu ke derowe yebesale .
  The power of the Powerless!!

  ReplyDelete
 11. ዳኒ 10q
  መዳሰስ የነበረበት ነገር እና ወደፊት ባንተ እይታ የምታይልን የንጉሱን መውረድ ተከትሎ ደሞ እነዚ ሰዎች ጠቅለው ቤተ ክህነት ገቡ አደለም? የታየኝ እንዲ ነው:: የ1960ዎቹ ወጣቶች ይቅር ይበላችሁ:: ያልታሰበበት አብዮታችሁ የወለደውን እሳት ይኽው አሁንም እየሞቅን ነው::

  ReplyDelete
 12. BAEWENATE YEGA BATAKERESETAINE SELAM TAGAGE YEHONE?????????????????????????????????????

  ReplyDelete
 13. እውነት ነው ዲ/ን ዳንኤል ቅድስት የምትሆን ቤተክርስቲያን እውቀቱም መንፈሱም በሌላቸው ደብተራዎች ለአገልግሎት ሳይሆን ለእንጀራ ብቻ የሚሠሩ መሰሪዎች መፈንጫ ሆናለች፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ እያለ እንደሌለ እያወቀ እንዳላወቀ በመንፈስ ሳይሆን በደብተሮች አጫፋሪነት የሚመራ ሆኗል፡፡ ሌቦቹ እያሉ ጠባቂዎቿ የሚሰደዱባት ሆናለች ቤተክርስቲያን፡፡ እውነተኞች አባቶች ተነስተው ከድምፅ ማሳመር በቀር በሌላው ጨዋ የሆነው እንደቡችላ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ስር የማይጠፋው የድምጽ ማጉያ እነደጨበጠና እንደጎረሰ ያለው ስሙን የማልጠራው ሰንበት ትምህርት ቤቶችን ከደመራ በዓል ውጪ የማያውቃቸው ሰው ተሾመ፡፡ ሰንበት ትምህርት ቤቶች እንኳን ደስ ያላችሁ፡፡ ዳኒ እነኚህ ካህናተ ደብተራዎች መቼ ነው ከቤተክርስቲያን ራስ ላይ የሚወርዱት? እማምላክ ትለመነን፡፡

  ReplyDelete
 14. የዛሬዎች ካህናት ደብተራ የድሮዎቹ የግብር ልጆች አንብቡት!!!

  ReplyDelete
 15. ሌሊት ንጉሡ በከባድ ሕመም ታመመ፡፡ ነፍሱም ልትወጣ ደረሰች፡፡ ያን ጊዜ ባለሟሎቹ ቀረቡ፡፡ እርሱም «ይህ ሕመም በምን ምክንያት እንደ መጣ አውቄዋለሁ፤ ያቺን የበጸሎተ ሚካኤልን ልጅ ላረክሳት በመፈለጌ ነው፡፡ አሁንም ሂዱና ይቅር በለኝ በሉት» ብሎ በቤተ መንግሥቱ የሚያገለግሉትን ካህናት ላካቸው፡፡

  ReplyDelete
 16. That is true, Dn Daniel.
  There are some "fathers" who are knowingly or unknowingly conspiring with our traditional enemies to destroy the Church. There are others who are witnessing this mess but have kept their mouth shut for various reasons. There are also some fathers who are doing their best to fight these shameful happenings in our Church. There will come a time, be it near or far, when God decides to clean His house saying "It is written in the Scriptures, 'My house will be called a house for prayer for all people.' But you are changing God's house into a hiding place for thieves.'" (Mark 11:17)
  If we want this time to come faster, we must ask ourselves Which of the above groups we belong to. We have to know that not only our elders but we are also to blame for the current chaos. Have we made God pleased? Do we keep ourselves clean from sin? Do we pray? Do we try to get the hatred and the envy for our brothers and sisters out of our hearts? Do we try not to talk about our friends at their backs? Do we try to lead every minute of our lives by God's words? I don't think so. My friends, it is time to straighten ourselves and clean our hearts. It is time to start praying. When we do that, we will start fighting the Devil who is the father of all evil. We will then have the strength to call the dirt a dirt. We will also happily sacrifice ourselves and what we have so that our children will inherit the pure Tewahedo Church. This is God's wake-up call for us. Let's wake up from our sleep. Let's conquer sin. Let's conquer this world. We will then take our Church back.

  ReplyDelete
 17. Thanks Dane geta mefeteha Yisetin let us pray

  ReplyDelete
 18. kale heiwot yasamalen

  ReplyDelete
 19. Endih Tsafilat Enji Leenatih yemin mefrat new Dani.

  ReplyDelete
 20. እንክርዳዱ ከስንዴው ጋር አብሮ እስከ መከር ይኖራልና የካህናተ ደብተራ ጠባይና አሠራር ዛሬም ቤተ ክርስቲያንን ሲያውካት ይኖራል፡፡ እንደ አቡነ አሮን፣ እንደ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል እንደ አቡነ ፊልጶስና እንደ አቡነ አኖሬዎስ ያሉ ጀግኖችን እስክታገኝ ድረስ፡፡እግዚአብሔር ይቅር ይበላቸዉ ልባቸዉንም ይመልስላቸዉ እንጅ እንደነዚህ አይነቶቹ ናቸዉ በንጋዉን ተኩላ ያስከበቡት፡፡

  ReplyDelete
 21. በአበው ኀዘን ምክንያት ወዲያውኑ ሞተ፡፡........"የካህናተ ደብተራ ጠባይና አሠራር ዛሬም ቤተ ክርስቲያንን ሲያውካት ይኖራል፡፡ እንደ አቡነ አሮን፣ እንደ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል እንደ አቡነ ፊልጶስና እንደ አቡነ አኖሬዎስ ያሉ ጀግኖችን እስክታገኝ ድረስ፡፡"

  ReplyDelete
 22. እድሜ ለካህናተ ደብተራ! እድሜ ለግብጻውያን የ1600 ዓመት ኢክርስቲያናዊ ዘረኛ ጭቆና (የዴር ሱልጣንን መከራ ሳልቆጥር)! እድሜ ለምንደኛ ነገሥታት! እድሜ ለሆዳም መነኰሳት! እድሜ ለ1960ዎቹ ያበዱ ማርክሲስቶች! እድሜ ሀገር በደም ስትታጠብ አፋቸውን በፍትፍት ለመለጎም “ለከርሥከ”ን ለሚደግሙ ጳጳሳት! እድሜ በዕውቀት፣ በትዕግሥትና አርቆ በማስተዋል ሳይሆን በስሜትና በቡድንተኛነት ለሚንቀሳቀሱ ወጣቶች! እድሜ “ለነጩ ካፒታሊዝም”! እድሜ አንሻፍፈን ለኮረጅነው ሴኪዩላሪዝም! እነሆ ኢትዮጵያ ክርስትና ተራ ባህል የሆነባት፣ ወንጌል ተራ ትራስ የሆነችባት ሀገር ሆነች!

  ትንቢት

  የእናንተ ልጆች ቤተክርስቲያን አይኼዱም፡፡ የእናንተ የልጅ ልጆች ቤተክርስቲያኖቹን “ባዶ ቤቶች” ብለው ይሸጧቸዋል፡፡ የልጅ ልጅ ልጆቻችሁ ደግሞ "ሐጅ" ካላደረግን ይሉ ይሆናል፡፡ ክርስትና ሕይወት ሳይሆን ተራ ባህል፣ “ተራ የማንነት መገለጫ” ሲሆን ምን እንደሚመስል ለማየት የዛሬዋን ግራ የገባት ኢትዮጵያንና በ6 ዓመታት ብቻ 50000 ዜጎቿን በአደንዛዥ ዕጽ ጦርነት ያጣችውን የዛሬዋን ሜክሲኮን ማየት ይበቃል፡፡ የዚህ ጉዞ ፍጻሜው የት እንደሆነ ለማየት ደግሞ የአውሮፓ ክርስትና እንዴት ዛሬ የደረሰበት እንደደረሰ ማስተዋል ነው፡፡ እውነትን ዕወቋት፡፡ እውነት ነጻ ታወጣችኋለች!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ግሩም ምልከታ ነው፡፡ ግሩም ማስተዋል ነው፡፡ ኦ ያሳዝናል መጪው ጊዜ

   Delete
 23. «ተነሡ እግዚአብሔር ሥራ እንዲሠራ እንለምነው፡፡ ክውስጣዊ ልብሳችሁ በቀር ሌላውን አውልቁ፡፡ በፊቱም እያለቀስን እንለምነው»፡፡

  ReplyDelete
 24. kahinate debtera bizu nachewe (ename sunday school and sebeka gubayachinene enetebeke atibiyawene yaletebeke kewere ayalefime)

  ReplyDelete
 25. D/n Daniel,

  I am very sure u wrote this article about Amde Tsion with very good intention. However, I would like to point out to you that there are other scripts that say the story of Amde Tsion is distorted. Amde Tsion was a hero and a genuine Christian. He was accused of all this dirty things about marriage by the monks who were unhappy about his corrective reforms and unwavering decision to destroy foreign cultures (including in the church administration) that was breaking down the church and the country. Even our history courses say that Ethiopia was relatively stable, prosperous, and her boarders were bigger and wider as a result of Amde-tsion's continuous war against enemies (especially Muslim Sultanates) than it was during the previous kings. When the Muslims are touched... of course the Copts lament. They are the ones who created dirty stories about him..... I find this alternative story convincing because often those who unified and made Ethiopia prosperous and wider after she was divided or weakened(like Amde-Tsion, Tewodros II, and Minilik II) were people who truly walked with God.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dear anonymous,

   I strongly agree with your point which states that Amdetsion was a triumphant warrior king. However, the fact that he was polygamous was mentioned even by his own chroniclers. So, I don't think your point to exonerate him from all the charges of polygamy is based on historical evidences. However, he was indeed a great warrior king of Ethiopia. To be a great warrior king one doesn't necessarily need to be holy or righteous.

   Delete
  2. Dear Mehari,

   Amde-Tsion WAS a holy and righteous man. He was given vision by God to fetch a sword given by Jesus to one of His disciples, and it was by that sword he drove the countless Muslim invaders out and broadened the boundaries of the kingdom. Ofcourse whenever Eth is at war with Islam, Copts get irritated. That's why the chroniclers are against him.

   BuT, I believe the most important truth you need to realize is that in Ethiopia, for any person to do good things for Ethiopia, Ethiopians, and Ethiopiawinet, he/she MUST be holy/righteous (which simply means "ewnetegna"-- a seeker of God's Truth and a humble repentant). Ageritu yeteserachiw endeziya newu. So, what you said "To be a great warrior king one doesn't necessarily need to be holy or righteous" works everywhere except in Ethiopia.

   Delete
  3. What makes Ethiopians more love- able than any other creature in this world? This is the illusion of Ethiopians. They are no more different than any other nation or society in the world. After all we are in the New Testament era, aren't we? Ethiopia is a country of dictators as any other nation, but a nation where the dictators live longer as a result of the people's extremely submissive and unquestioning behavior. Both history and our lives tell us this and only this fact. Don't think that the Lord favors you because you are Ethiopian. The Lord has no nation and no religion.

   Delete
 26. Daneil-can you provide other secndary sources about the origin of "Kahinat Debtera"? other than the one source you mentioned again and again? That makes it only one sided outlook-the "kahinat debtera" can also say a different thing. Any ways-shallow understanding will bring a demise to the very institution you claim to safeguard.

  ReplyDelete
 27. "መንጋውን ለሚተው ለምናምንቴ እረኛ ወዮለት! ሰይፍ በክንዱና በቀኝ ዓይኑ ላይ ይሆናል፤ ክንዱም አጥብቃ ትደርቃለች፥ ቀኝ ዓይኑም ፈጽሞ ትጨልማለች።" ዘካ.11:17

  "Woe to the idol shepherd that leaveth the flock! the sword shall be upon his arm, and upon his right eye: his arm shall be clean dried up, and his right eye shall be utterly darkened." Zechariah 11:17

  ReplyDelete
 28. to Know better about ""kahinate debtera'' please read Getachew Hailes introductory note for Church and State in ethiopia.He give the same information as Daniel.

  ReplyDelete
 29. በለው በለው በለው አርጩሜ አይሻልህም!!!

  ReplyDelete
 30. I got a beutiful explanation; god bless you

  ReplyDelete
 31. Egizeabhier yebarh!!!!

  ReplyDelete
 32. Great Dani Egziabeher Yibarkih

  ReplyDelete
 33. «ተነሡ እግዚአብሔር ሥራ እንዲሠራ እንለምነው፡፡ ክውስጣዊ ልብሳችሁ በቀር ሌላውን አውልቁ፡፡ በፊቱም እያለቀስን እንለምነው»፡፡እውነት ነው:: የኛም ትንሽዋ ጾለት በጌታችን ፊት ደርሳለች::እባካችሁ በጾለት እንበርታ::ግዜው አሁን ነው::

  ReplyDelete
 34. ካህናተ ደብተራ በዕውቀትና በቅድስና የሚበልጧቸውን አባቶችና ሊቃውንት አይወዷቸውም፡፡
  le awakiwochna le kidusan አባቶች አይወዷቸውም:: tebilo yitsaf, aynetsatserumna. attractive and power full idea.

  ReplyDelete
 35. «ተነሡ እግዚአብሔር ሥራ እንዲሠራ እንለምነው፡፡ከውስጣዊ ልብሳችሁ በቀር ሌላውን አውልቁ፡፡ በፊቱም እያለቀስን እንለምነው»፡፡ እውነት ነው፡፡ እኛ ተግተን መጸለይን እንዳለብን ያጠይቃል፡፡ ትጉና ፀልዩ

  ReplyDelete