Friday, May 25, 2012

118ኛው የግብጽ ፓትርያርክ

 

117ኛው የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ታላቁ አባት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ 3 ሲያርፉ ዓለም በሙሉ ነበር ኀዘኑን የገለጠው፡፡ ክርስቲያኑና ሙስሊሙ፣ ቡድሂስቱና ሺንቶይስቱ፣ የሚያምነውና የማያምነው፣ የቻይናና የአሜሪካ ፖለቲከኞች፣ አንድ ሆነው በአቡነ ሺኖዳ ዕረፍት አዝነው ነበር፡፡
Coptic patriarchs
የእርሳቸውን ዕረፍት ተከትሎም የግብጽ ቤተ ክርሰቲያን እንዲህ ዓለምን በፍቅር አንድ አድርገው የሚገዙ ሌላ አባት ታገኝ ይሆን? የሚለው ጥያቄ ግብጻውያን ምእመናንን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ያሳሰበ ነበር፡፡ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት ዝግጅቷን ጀምአመራረጥ ራለች፡፡ በቤተ ክርስቲያኒቱ የአዲስ ፓትርያርክ ሥርዓት እጅግ የሚያስደስት፣ ለክርክርና ለሐሜት በር የሚዘጋ፣ አባቶችንና ምእመ ናንን የሚያሳትፍ፤ መንፈሳዊነቱንም የተሞላ ነው፡፡
 እስካሁን ድረስ የአዲስ ፓትርያርክ አመራረጥን በተመለከተ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የተዘጋጀ ዝርዝር ሕግ አላየሁም፡፡ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ላይ ያለው እጅግ በጣም አጭር ነገር ነው፡፡ ሂደቱን፣ የአባቶችንና የምእመናንን ተሳትፎ፣ የእጩ አቀራረብና አመራረጥ፣ የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ሂደትን የሚያሳይ ራሱን የቻለ ሕግ ያለ አልመሰለኝም፡፡
በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ አንዱ አከራካሪ ሆኖ የሚታየው ነገር የፓትርያርክ አመራረጥና አሿሿም ጉዳይ ነው፡፡ ከመጀመርያው ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ ጀምሮ ከፖለቲካ ነጻ የሆነ፣ የሕዝቡን አመኔታ ያተረፈ፣ ሕዝቡም እግዚአብሔር አባት ሰጠን ብሎ እንዲያምን የሚያደርግ አሠራር ባለመኖሩ፣ ሐሜቱና ቅሬታው፣ ተቃውሞውና አለመግባባቱ እንዲቀጥል አድርጎታል፡፡
while the ballot for the late Pope shenouda was announced
በመሆኑም ቅዱስ ሲኖዶስም ሆነ ሌሎች አባቶች፣ አገልጋዮችም ሆኑ ምእመናን ሊያስቡባቸው ከሚገቡ ቤተ ክርስቲያናዊ ጉዳዮች አንዱ የፓትርያርክ አመራረጥና አሿሿም ሥርዓት ነው፡፡ ዛሬ በመንበሩ ላይ ያሉት አቡነ ጳውሎስም ሆኑ ተሰድደው በአሜሪካ ያሉት አቡነ መርቆሬዎስ ማረፋቸው አይቀርም፡፡
ያን ጊዜ አዲሱን አባት እንዴት ነው መምረጥ ያለብን? የእግዚአብሔርንስ ፈቃድ እንዴት እናገኛለን? ከፖለቲካዊና ሌሎች ተጽዕኖዎች ነጻ የሆነ፣ ሁሉንም የሚያግባባ ምርጫ እንዴት ማድረግ ይቻላል? ቅሬታዎችንና ነቀፌታዎቸን እንዴት ማስተናገድና መፍታት ይቻላል? መራጮች እነማን ናቸው? መራጮችስ እንዴት ይመረጣሉ? ለፕትርክና ዕጩ መሆን የሚችሉት እነማን ናቸው? ምን ምን መመዘኛ ያሟሉ ይወዳደራሉ? የሚሉትና ሌሎች በዝርዝር ተደንግገው የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች ሁሉ እንዲያውቁት መደረግ አለበት፡፡ አሠራራችን ሁሉ እንደ ሐበሻ መድኃኒት ተደብቆ የሚኖርበት አሠራር እየጎዳን ነው፡፡ ሌላ ጭቅጭቅ ደግሞ ለትውልድ እንዳናተርፍ፡፡
ግብጻውያን ጠንካራ የምእመናን ጉባኤ ለማግኘት ከ1874 ዓም ጀምረው ለሰባ ዓመታት ታግለዋል፡፡ እኛ ግን ስለ ቤተ ክርስቲያን ማሰብ የምንጀምረው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ሲጀምር ነው፡፡ ዘላቂ በሆነ መልኩ እንዴት ችግሮችን እንደምንፈታ አንወያይም፡፡
ለዛሬ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን የአዲሱን ፓትርያርክ አመራረጥ ሂደት ግልጽ ለማድረግ ያወጣችውን ጋዜጣዊ መግለጫና ሌሎችንም መዛግብት መሠረት አድርጌ በእነርሱ ዘንድ የአዲስ ፓትርያርክ አመራረጥ ሕግና ሂደት ምን እንደሚመስል ለምሳሌነት ላቅርብ፡፡ «መልክ ከፈጣሪ ሞያ ከጎረቤት» ይባላልና እኛም ለእኛ እንደሚሆን አድርገን ብንቀስመው አይጎዳንም፡፡ እንዴት ሁልጊዜ የሰው እያደነቅን እንደተመኘን ብቻ እንቅር፡፡
the Interim patriarch metropolitan phacoumis
 በግብጽ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ ፓትርያርክ አመራረጥን ሂደት በዝርዝር የሚያስረዳ ራሱን የቻለ ሕግ አለ፡፡ ይህ ሕግ በቅዱስ ሲኖዶሱ ተወስኖ በግብጽ ፓርላማ እኤአ 1957 ዓም የጸደቀ ነው፡፡ በዚህ ሕግ መሠረት አንድ ፓትርያርክ ባረፈ በሰባት ቀናት ውስጥ ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጳጳሳት መካከል ቀዳሚ የሆነው ሜትሮፖሊታን ዐቃቤ መንበር ለመምረጥ የቅዱስ ሲኖዶሱን አባላት ስብሰባ ይጠራል፡፡ በዚህም መሠረት የአሲዩቱ ሜትሮፖሊታን አቡነ ሚካኤል ይህንን ስብሰባ እንዲያካሂዱ ሜትሮፖሊታን ጳኩሚስን ወከሏቸው፡፡
ይህ ስብሰባ በሁለት አካላት መካከል የሚደረግ ስብሰባ ነው፡፡ በነገራችን ላይ የግብጽን ቤተ ክርስቲያን የሚመሯት ሁለት አካላት ናቸው፡፡ የመጀመርያው በሃይማኖታዊና ሌሎች ጉዳዮች የመጨረሻውን ውሳኔ የመስጠት ሥልጣን ያለው ቅዱስ ሲኖዶሱ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ላይ የሚሠራው የምእመናን ጉባኤ (Al-Maglis al-Milli) ነው፡፡ የምእመናን ጉባኤ 1874 ዓም ጀምሮ በልዩ ልዩ መንግሥታዊ፣ ማኅበራዊና ሃይማኖታዊ አገልግሎታቸው በታወቁ ምእመናን አማካኝነት በቤተ ክርስቲያኒቱ የምእመናንን መብት ለማስጠበቅ፣ ምእመናን በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደርና አገልግሎት ድርሻ እንዲኖራቸው ለማድረግ ሲታገል የቆየና በመጨረሻም መጀመርያ በአቡነ ቄርሎስ በኋላም በአቡነ ሺኖዳ ጊዜ ይበልጥ የተጠናከረ ጉባኤ ነው፡፡ ይህ የምእመናን ጉባኤ በማናቸውም የቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳዮች ከፍተኛ ተሰሚነት ያለው ጉባኤ ነው፡፡
ሜትሮፖሊታን ሚካኤል የእነዚህ ሁለቱን አካላት ጥምር ጉባኤ መጋቢት 14 ቀን 2004 ዓም በማካሄድ ራሳቸው ሜትሮፖሊታን አቡነ ሚካኤል በአንድ ድምጽ ዐቃቤ መንበር ሆነው ተመR-êLÝÝ በዚህም መሠረት ፓትርያርኩ ተመርጠው በመንበራቸው እስኪቀመጡ ድረስ ሲኖዶሱን ይሰበስባሉ፡፡ በዚሁ ጉባኤ ላይ በቅዱስ ሲኖዶሱ የምርጫ ኮሚሽን ተመርጧል፡፡ የዚህ ኮሚሽን ተግባራትም
 • ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላትና ከምእመናን ጉባኤ ዕጩዎችን መቀበል
 • ከቅበላ እስከ ምርጫ ያለውን ሂደት ማስፈጸም ናቸው፡፡
ይህ ኮሚሽን አሥራ ስምንት አባላት ያሉት ሲሆን አባላቱም ዘጠኙ ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ ዘጠኙ ደግሞ ከምእመናን ጉባኤ አባላት መካከል የሚሰየሙ ናቸው፡፡
ግብጽን ከአርባ ዓመታት በላይ አገልግለው ላረፉት ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ክብር ሲል ካረፉበት ቀን ጀምሮ እስከ ዓርባ ቀን ድረስ ዕጩዎችን ላለመቀበል ቅዱስ ሲኖዶሱ ወስኗል፡፡ ይህም ሚያዝያ 18 ቀን 2004 ዓም ይጠናቀቃል፡፡
ለፕትርክና ዕጩ መሆን የሚችሉት ቢያንስ የሚከተሉትን ያሟሉ ናቸው
 • ዕድሜያቸው ቢያንስ ዐርባ ዓመት የሞላቸው
 • በገዳም ውስጥ ቢያንስ አሥራ አምስት ዓመታት የኖሩ ደናግል መነኮሳት
 • ሀገረ ስብከት የሌላቸው
 • ነውር ወይንም ነቀፋ የሌለባቸው
 • የቤተ ክርስቲያኒቱን ትምህርት በሚገባ የተማሩ
አንድ ዕጩ ዕጩ ለመሆን ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት መካከል በስድስቱ ወይንም ደግሞ ከምእመናን ጉባኤ አባላት መካከል በአሥራ ሁለቱ መጠቆም አለበት፡፡ ይህም ጥቆማ ያረፉት አባት ካረፉበት ቀን ከአርባኛው ቀን በኋላ እስከ ስድሳኛው ቀን ሊከናወን ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ በቅዱስ ሲኖዶሱ አስቀድሞ በወጣው ሕግ መሠረት ለዕጩነት የሚያበቃቸውን መሥፈርት የሚያሟሉትን አባቶች ኮሚሽኑ ሲቀበል ይቆያል፡፡
በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ ሚደዲያው፣ ካህናትና መምህራን ታላቅ ሚና አላቸው፡፡ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ምን ዓይነት አባት እንደሚያስፈልጋት ሃሳብ በመስጠት፡፡ መራጮች ምን ላይ ማተኮር እንዳለባቸው በመምከር አስተዋጽዖ ያበረክታሉ፡፡ በአጥቢያዎችና በገዳማትም ጸሎት ይደረጋል፡፡ በሕዝቡም መካከል ማን የቤተ ክርስቲያኒቱ ፓትርያርክ ቢሆኑ መልካም እንደሆነ ውይይትና ክርከር ይካሄዳል፡፡
በነገራችን ላይ በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ፓትርያርክ ከጳጳሳት መካከልም ሆነ በገዳም ካሉ አባቶች መካከል ሊመረጥ ይችላል፡፡ ያረፉት ፓትርያርክ አቡነ ሺኖዳ ሀገረ ስብከት ከሌላቸው ጳጳሳት መካከል የተመረጡ ሲሆን፣ ከእርሳቸው በፊት የነበሩት አቡነ ቄርሎስ ደግሞ ከገዳማውያን መካከል የተመረጡ ነበሩ፡፡ እስካሁን ሀገረ ስብከት ያለው ጳጳስ ፓትርያርክ ሊሆን አይችልም፡፡
አስመራጭ ኮሚቴው ጥቆማዎችን ከተቀበለ በኋላ በስድሳኛው ቀን የዕጩ መቀበያ ጊዜ ማብቃቱን ያውጃል፡፡ ከአሥራ አምስት ቀን በኋላ ማለትም በሰባ አምስተኛው ቀን ሕጉን የሚያሟሉትን ዕጩዎች ለይቶ ስማቸውን ሕዝብ ሊያየው በሚችልበት ቦታና በሚዲያ ለሕዝብ ይፋ ያደርጋል፡፡ የዕጩዎች ስም ለአሥራ አምስት ቀናት ይፋ ሆኖ ሲቆይ ዕጩዎችን በተመለከተ ቅሬታ፣ የተለየ ሃሳብ፣ መረጃ ወይንም ሌላ ነገር ያለው ሰው ለዕጩዎች ቅሬታ ተቀባይ ኮሚቴ ያቀርባል፡፡
የዕጩዎች ቅሬታ ተቀባይ ኮሚቴ አምስት አባላት ያሉት በቅዱስ ሲኖዶስ የሚቋቋም ኮሚቴ ነው፡፡ ሦስቱ የኮሚቴው አባላት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ሲሆኑ ሁለቱ ደግሞ የምእመናን ጉባኤ አባላት ናቸው፡፡
general Time table for election
ይህ ኮሚቴ በቀጣዮቹ ሠላሳ ቀናት ውስጥ በዕጩዎች ላይ አሉ የሚባሉትን ቅሬታዎችና ለቅሬታዎቹም የሚሰጡ መልሶችን ሲያጣራና ሲወስን ይቆያል፡፡ ይህ ቅሬታ ግን መቅረብ ያለበት ድምፅ ለመስጠት ሥልጣን ባላቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት በኩል ብቻ ነው፡፡ ሌላ አካል መረጃ ወይም ቅሬታ ቢኖረው በእነዚህ አካላት በኩል እንዲቀርብ ማድረግ ይችላል፡፡
ድምፅ የመስጠት መብት ያላቸው አባላት ማለት በቤተ ክርስቲያኒቱ የምርጫ ሕግ መሠረት ድምፅ ለመስጠት የተመረጡ አባላት ማለት ነው፡፡ እነዚህ ድምፅ የሚሰጡ አባላት የሚመረጡት በምርጫ ኮሚሽኑ በኩል ነው፡፡ ከእያንዳንዱ ሀገረ ስብከት በቤተ ክርስቲያኒቱ ይፋዊ አገልግሎት ያላቸው ካህናት(ማለትም ቦታ ይዘው ተመድበው የሚያገለግሉ ካህናት) ይወከላሉ፡፡ (በነገራችን ላይ በግብጽ ቤተ ክርስቲያን የካህናት ቁጥር ትንሽ ነው፡፡ እንደኛ 400,000 አድርገን አናስበው) እንዲሁም ከያንዳንዱ ሀገረ ስብከት አሥራ ሁለት የምእመናን ድምፅ ሰጭዎች ይመረጣሉ፡፡
በውጭ የሚገኙ አህጉረ ስብከትም እንደ ሀገር ቤቶቹ ሁሉ ካህናትንና ምእመናንን ይወክላሉ፡፡ ሀገረ ስብከት የሌላቸው አጥቢያዎችም አንድ ላይ ሆነው እንደ አንድ ሀገረ ስብከት ይታዩና ካህናትንና አሥራ ሁለት ምእመናንን ይወክላሉ፡፡
በፓትርያርኩ ምርጫ ድምፅ የመስጠት መብት የሚኖራቸው
 • የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት
 • የቀድሞዎችና የአሁኖቹ የምእመናን ጉባኤ አባላት በሙሉ
 • ከእያንዳንዱ ሀገረ ስብከት የሚመጡ ካህናት
 • ከእያንዳንዱ ሀገረ ስብከት የሚመረጡ አሥራ ሁለት፣ አሥራ ሁለት ምእመናን
 • አሁን ያሉና የቀድሞ ኦርቶዶክስ ሚኒስትሮች
 • አሁን ያሉና የቀድሞ ኦርቶዶክስ የፓርላማ አባላት
 • ኦርቶዶክስ የሆኑና በግብጽ የፕሬስ ማኅበር የተመዘገቡ ጋዜጠኞች ናቸው፡፡
ኮሚቴው የመራጮችን ዝርዝር ከተቀበለ በኋላ በትክክል መመረጣቸውንና በምርጫ ሕጉ መሠረት መመረጣቸውን እያረጋገጠ ይቀበላቸዋል፡፡ ይህም በስድሳኛው ቀን ይጠናቀቃል፡፡ ከስድሳኛው ቀን ጀምሮ እስከ ሰባ አምስተኛው ቀን ድረስ ለአሥራ አምስት ቀናት በመራጮች ላይ ቅሬታ አለኝ የሚል ቅሬታውን እንዲያቀርብ ዕድል ይሰጠዋል፡፡ ነገር ግን ይህም ቢሆን ለመራጭነት በተመረጠ አባል በኩል የሚቀርብ ቅሬታ መሆን አለበት፡፡ በሰባ አምስተኛው ቀን የመራጮች የመጨረሻ ዝም ዝርዝር ይፋ ይሆናል፡፡ የቅሬታ መቀበሉ ሂደትም ያቆማል፡፡
ለፕትርክና የተጠቆሙትን ዕጩዎች የማጣራቱ፣ የቀረበውን ቅሬታ አጣርቶ የመወሰኑ ሥራ እስከ አንድ መቶ ሃያኛው ቀን ድረስ ይከናወንና ያልቃል፡፡ በዚህ ቀንም ተጣርተው የቀረቡትን ከአምስት ያላነሱ ከሰባት ያልበለጡ ዕጩዎች ስም ዝርዝር የምርጫ ኮሚሽኑ ይፋ ያደርጋል፡፡ ከዚያ በኋላ በተመረጡት ዕጩዎች ላይ ድምፅ የመስጠት መብት ያላቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት በአንድ መቶ ሃምሳኛው ቀን ድምፅ ይሰጣሉ፡፡ የዚህም ውጤት በአንድ መቶ ሃምሳ አንደኛው ቀን ይፋ ይሆናል፡፡ በውጤቱም ከዕጩዎች መካከል ብዙ ድምፅ ያገኙት ሦስት አባላት ይፋ ይደረጋሉ፡፡
ሕዝቡም የሦስቱ አባቶች ስም ይፋ ከሆነ በኋላ በሚገኘው የመጀመርያው እሑድ  በመጨረሻዎቹ ሦስት አባቶች ስሞች ላይ ጸሎት ለማድረግ በቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል ይሰበሰባል፡፡ በዚያ ቀን የሦስቱም አባቶች ስሞች በወረቀት ተጠቅልለው በመንበሩ ላይ ይቀመጣሉ፡፡ ጳጳሳቱ፣ ካህናቱና ምእመናኑ በአንድነት በቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ጸሎት ያደርጋሉ፡፡ በየቤተ ክርስቲያኑም ጸሎት ይደረጋል፡፡
ጸሎቱ ሲፈጸም አንድ ሕፃን ከሕዝቡ መካከል ይጠራና ዓይኑን በጨርቅ ተሸፍኖ በመንበሩ ላይ ጸሎት ከሚደረግባቸው ስሞች አንዱን ያነሣል፡፡ እርሱ ያነሣውን ስም የምርጫው ኮሚሽን ሰብሳቢ አንድ መቶ አሥራ ስምንተኛው ፓትርያርክ መሆናቸውን ያውጃል፡፡
እያንዳንዱ ሥነ ሥርዓት የሚካሄድበት ቀን ከሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታና ከአስገዳጅ ነገሮች አንፃር ሊቀየር እንደሚችል መግለጫው ያመለክታል፡፡ ግብፃውያን ግን በመስከረም 2005 መጨረሻ አካባቢ አዲስ አባት እንደሚያገኙ ተስፋ አድርገዋል፡፡ ኢትዮጵያውያንስ?
 ሳክራሜንቶ፣ ካሊፎርንያ

47 comments:

 1. Thanks Dani .what about We?

  ReplyDelete
 2. ግብፃውያን ግን በመስከረም 2005 መጨረሻ አካባቢ አዲስ አባት እንደሚያገኙ ተስፋ አድርገዋል፡፡ ኢትዮጵያውያንስ?
  ይህ የሁሉም ህዝበ ክርስቲያን ጥያቄ ነዉ፡፡ ለግብፃዉያንም መልካም አባት ልክ እንደ አባት ሽኖዳ ለመላዉ አለም ምልክት የሚሆኑ ለሁሉ የሚተርፉ አባት ይስጣቸዉ፡፡ ኢትዮጵያዊያንም መልካም እረኛን ያምጣልን እኛም እግዚአብሄርን እንዲያስበን እንዲራራልን በምህረቱም እንዲጎበኘን እለምነዉ፡፡ አንተንም አምላከ እስራኤል ፀጋዉን ያብዛልህ፡፡

  ReplyDelete
 3. thank's Dani i hope one day we will see in Ethiopia...... God bless you ....

  ReplyDelete
 4. thank's Dani i hope one day we will see in Ethiopia ...God bless you ....

  ReplyDelete
 5. ግብፃውያን ግን በመስከረም 2005 መጨረሻ አካባቢ አዲስ አባት እንደሚያገኙ ተስፋ አድርገዋል፡፡ ኢትዮጵያውያንስ?

  ReplyDelete
 6. በአንድ ወቅት ደጀ ሰላም ተቀምጨ የሰማሁትን ልንገርህ:: ፍትሐት ያዘወትር የነበረን ዲያቆን በነገር ሊወጉት የፈለጉ አንድ ሰው መቼም የኔን ፍትሐት ታሳምረዋለህ አይደል? ብለው ይጠይቁታል ልጁም የዋዛ አልነበረምና እርሶ ይሙቱ እንጂ እንቀሽረዋለን ብሎ መለሰላቸው:: ዳኒ እነዚህን በቃችሁ ይበላቸው እንጂ መንግሥትም ምእመናኑም ማኅበራቱም ፍትሐቱን የናፈቁት ይመስለኛል:: መፍትሄው ግን አንተ እንዳልከው ሥርዓቱን በወጉ ማበጀቱ ነው:: የምእመናን ጉባኤ (Al-Maglis al-Milli) ያልከው እኮ መልኩን ቀይሮ እኛም ጋር አለ:: የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓላማና አስፈላጊነት እኮ ይህ ነበር:: እኛ ደግሞ በየዓመቱ ህልም አይሉት ቅዥት የእቅድ ሪፖርት በሚል ርእስ ተመካችን አሳታፊ ትረካ እየሰማን ደግሰን በልተን ቢራ ተራጭተን የምንለያይበት የሙት ዓመት ማውጫ አደረግነው:: የተደከመበት ድካምና ያመጣው ለውጥ ግን አይደራረሱም:: ይልቁንም መክኖ የቀረ አስመስሎታል::
  ካለንበት ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር የቤተ ክርስቲያን ልጆች ሦስት አማራጮች አሉን:: አንደኛ ያለ መታከት ለብጹአን አበው ጉዳዩን ማሳሰብ ከተቻለ የተሻሉ የምንላቸውን አማራጭ አሳቦች በማቅረብ መሞገት:: ሁለት በጉዳዩ ላይ መንፈሳዊ ሐዘን /ሱባኤ/ መያዝና የመጣውን ፈቃደ አምላክ ነው ብሎ ለመቀበል መዘጋጀት:: ሦስተኛው ግን በያለንበት የድርሻችንን መወጣት ነው:: ለውጥ ፈላጊው ብዙ ነው ለውጥ አምጭዎቹ ግን ጥቂቶች ናቸውና ከለውጥ ፈላጊነት ወደ ለውጥ አራማጅነት እንሻገር:: ያለዚያ ሌላ ተጨማሪ የሐዘን የመለያየት የመከፋፈል የጸብና የክርክር ጊዜ መግዛት ነው::
  ቃለ ሕይወት ያሰማልን ዲያቆን ዳንኤል ::

  ReplyDelete
 7. Thank you for sharing this timely info. I believe that we will also have a new Patriarc soon. It would be good to share this idea to members of the Holy Synod to draft a clear and detailed selection procedure.
  I know that you were researching how the transition between Abune Merkorios and Abune Paulos took place. You posted one of the papers written to Abune Merkorios about His retirement and asking him the Monastery where he chooses to stay. Although this is a sensitive issue why didnt you go further in informing us about the transition process during those black days. In a recent Wikleak info, Tamrat Layne informed the US ambassador that he was the one who ordered the removal of Abune Merkorios, and that he feels guilty for the current division in the church and that wants to mediate between the two.

  ReplyDelete
 8. ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡ የቅዱስ ማርቆስ መንበር ለአምስቱም ኦሪየንታል አኀት አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ አብነት ነው፡፡ 117ኛው የግብጽ ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ 3ኛ በስራቸውም በሕይወታቸውም አስተማሩን፡፡ የኛው ቤ/ን ቅዱስ ሲኖዶስ የሚመራው መንፈስ ቅዱስ ነገሩን በወቅቱ ውብ አድርጎ ይሰራዋል፡፡ እ/ር ሰው ያስነሳል፡፡ ልዩ እና ድንቅ የሆኑ አባቶችም አሉን፡፡አቡነ ሺኖዳም ለግብጻውያን ገዳማዊ ሕይወት እንደገና ማንሠራራት ታላቅ አስተዋጽዖ ያደረጉት የኢትዮጵያዊው አብዱል መሲሕ (ገብረ ክርስቶስ) ደቀ መዝሙር ነበሩ፡ የገብረ ክርስቶስን መንገድም ለመከተል ይጥሩ ነበር ፡፡118ኛው የግብጽ ፓትርያርክ የቅዱስ ማርቆስ አምላክ የመረጠው ይቀመጣል፡፡ የኛንም፤ ግልፅ በሆነ ሕግ እና አሰራር በአምላክ ስነጥበብ በእድሜያችን እንደምናይ ምኞት እና ተስፋ አለኝ፡፡

  ReplyDelete
 9. ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡ የቅዱስ ማርቆስ መንበር ለአምስቱም ኦሪየንታል አኀት አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ አብነት ነው፡፡ 117ኛው የግብጽ ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ 3ኛ በስራቸውም በሕይወታቸውም አስተማሩን፡፡ የኛው ቤ/ን ቅዱስ ሲኖዶስ የሚመራው መንፈስ ቅዱስ ነገሩን በወቅቱ ውብ አድርጎ ይሰራዋል፡፡ እ/ር ሰው ያስነሳል፡፡ ልዩ እና ድንቅ የሆኑ አባቶችም አሉን፡፡አቡነ ሺኖዳም ለግብጻውያን ገዳማዊ ሕይወት እንደገና ማንሠራራት ታላቅ አስተዋጽዖ ያደረጉት የኢትዮጵያዊው አብዱል መሲሕ (ገብረ ክርስቶስ) ደቀ መዝሙር ነበሩ፡ የገብረ ክርስቶስን መንገድም ለመከተል ይጥሩ ነበር ፡፡118ኛው የግብጽ ፓትርያርክ የቅዱስ ማርቆስ አምላክ የመረጠው ይቀመጣል፡፡ የኛንም፤ ግልፅ በሆነ ሕግ እና አሰራር በአምላክ ስነጥበብ በእድሜያችን እንደምናይ ምኞት እና ተስፋ አለኝ፡፡

  ReplyDelete
 10. ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡ የቅዱስ ማርቆስ መንበር ለአምስቱም ኦሪየንታል አኀት አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ አብነት ነው፡፡117ኛው የግብጽ ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ 3ኛ በስራቸውም በሕይወታቸውም አስተማሩን፡፡ የኛው ቤ/ን ቅዱስ ሲኖዶስ የሚመራው መንፈስ ቅዱስ ነገሩን በወቅቱ ውብ አድርጎ ይሰራዋል፡፡ እ/ር ሰው ያስነሳል፡፡ ልዩ እና ድንቅ የሆኑ አባቶችም አሉን፡፡አቡነ ሺኖዳም ለግብጻውያን ገዳማዊ ሕይወት እንደገና ማንሠራራት ታላቅ አስተዋጽዖ ያደረጉት የኢትዮጵያዊው አብዱል መሲሕ (ገብረ ክርስቶስ) ደቀ መዝሙር ነበሩ፡ የገብረ ክርስቶስን መንገድም ለመከተል ይጥሩ ነበር ፡፡118ኛው የግብጽ ፓትርያርክ የቅዱስ ማርቆስ አምላክ የመረጠው ይቀመጣል፡፡ የኛንም፤ ግልፅ በሆነ ሕግ እና አሰራር በአምላክ ስነጥበብ በእድሜያችን እንደምናይ ምኞት እና ተስፋ አለኝ፡፡

  ReplyDelete
 11. ኢትዮጵያውያንስ???? God knows!!!let us all prey to Him about this main issue.let our brothers in Christ, the copts prey for us! can you facilitate that!

  ReplyDelete
 12. ለኢትዮጵያውያንስ?አይ ዲ/ን ዳንኤል ለኛማ እንደ አቡነ ተክለሃይማኖት ያሉት እግዚአብሔር እንደ አባ ጳውሎስ ያሉት ደግሞ መንግስት ይመርጥልናል፡፡ እስኪ እግዚአብሔር እንድረዳን አንተ እርሱ በሰጠህ እውቀት የተቻለህን አድርግ; ሌሎቻችን ደግሞ በጸሎት እንትጋ፡፡
  አምላከ ቅዱሳን ሁላችንም ይርዳን ላንተም ረጅም የአገልግሎት ዘመን ከሙሉ ጤና ጋር ያድልልን፡፡

  ReplyDelete
 13. ለኢትዮጵያውያንስ?አይ ዲ/ን ዳንኤል ለኛማ እንደ አቡነ ተክለሃይማኖት ያሉት እግዚአብሔር እንደ አባ ጳውሎስ ያሉት ደግሞ መንግስት ይመርጥልናል፡፡ እስኪ እግዚአብሔር እንድረዳን አንተ እርሱ በሰጠህ እውቀት የተቻለህን አድርግ; ሌሎቻችን ደግሞ በጸሎት እንትጋ፡፡
  አምላከ ቅዱሳን ሁላችንም ይርዳን ላንተም ረጅም የአገልግሎት ዘመን ከሙሉ ጤና ጋር ያድልልን፡፡

  ReplyDelete
 14. this is very Good thing if we use it!

  ReplyDelete
 15. Betm Yidenk Srat/Hig New. Egnam Yihen Meketel Yigebanal.

  ReplyDelete
 16. ዳኒ ያስነበብከን እንደኔ ትልቅ ትምህርት ነው:: ለጥያቄህ ግን የፈጠረን የድንግል ማርያም ልጅ እንዴረዳን አምናለሁ ከመቸውም በተጠናከረ ሁኔታ ምእመን እየፀለየ ስለሆነ ሌላም በዜህ ድህረ ገጽ ልገልጽልህ የማልችል በፍጡር ሳይሆን በታላቁ ንጉሥ ለዝች ለኣርተዶክስ ቤተክርስትያን የተያዘላት ግሩም ድንቅ እንዳለ በእርግጠኝነት ሰለማምን የኛም ቀን ይኸው አይነት ይሆናል ብየ ተሰፋ አደርጋለሁ::ተስፋ ማድረግ ብቻ ሳይሆን አምናለሁ:: ለሁሉም ጌታ መድኋኔዓለም አገራችንና ምእመኑን ይጠብቅ እናንተንም አንድነታችሁን:እምነታችሁን ያጠንክር :: አሜን

  ReplyDelete
 17. Thank you Dn. Daniel addressing this basic information to our church.
  Our Church has very short and full of trouble historical path to get the Holy Patriarch. Specially within 21 years, we saw six Patriarchs of the single church. The four from Eritrea ( two passed and two alive) and two from Ethiopia one in exile the other with bloody hand in the Holy palace of Arat kilo. It is fact the church is now completely losing the truck of independent to exercises her rules and regulations in both "countries".
  I strongly support your idea our church should have this law soon. Otherwise, it will feuling a lot of mess again and drag the church a century back instead of preaching the truth to the world.
  God and his Holy Virgin St. Marry bless Our Church and you too.

  ReplyDelete
 18. thank you dani one day ! it will ethiopia too when god's will any way let us keep on pray

  ReplyDelete
 19. ኢትዮጵያውያንስ?.....ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ከአሁን አሁን መግለጫውን በንባብ ማሰማት ይጀምራሉ ተብሎ ሲጠበቅ እንዲያው ወረቀቱን አተኩረው እየተመለከቱ ጫ÷ እርጭ÷ ድምቡጭ አሉ፤ ገረገሩ፡
  Long Man the Minneosta!!!!!!

  ReplyDelete
 20. ‎'' በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ አንዱ አከራካሪ ሆኖ የሚታየው ነገር የፓትርያርክ አመራረጥና አሿሿም ጉዳይ ነው፡፡ ከመጀመርያው ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ ጀምሮ ከፖለቲካ ነጻ የሆነ፣ የሕዝቡን አመኔታ ያተረፈ፣ ሕዝቡም እግዚአብሔር አባት ሰጠን ብሎ እንዲያምን የሚያደርግ አሠራር ባለመኖሩ፣ ሐሜቱና ቅሬታው፣ ተቃውሞውና አለመግባባቱ እንዲቀጥል አድርጎታል፡፡'' ይህ በርግጥ የዳንኤል እይታ እንጂ ከእውነት የራቀ ነው። ዲ. ዳንኤል አሁን ያለውን ሥርዓት አልበኝነት ደፍሮ ለመተቸት ቢያስፈራው ቤተክርስቲያናቸውንና ሃገራቸውን በቅንነትና በአውነት ሲያገለግሉ ኖርው ያረፉትንና ሰማዕትነትን የተቀነሉትን አባቶች አደባልቆ መተቸቱ ያሳዝናል። በኢትዮጵያ ታሪክ ያለፉት ነገሥታት የሃገሪቱ ብቻ ሳይሆን የቤተክርስቲያኗም የበላይ ጠባቂዎች ስለነበሩ ቤተክርስቲያን የመረጠችውን ማጽደቃቸው የወቅቱ ሥርዓት ነበር። በሁሉም ዘንድ ደግሞ ተወዳጆችና ተቀባይነት የነበራቸው ነበሩ እንጂ እንደዘመናችን ያለ አሳፋሪ የስልጣን ጠብ አልነበረም። እንደ ግብጾች ያለ አሰራር ይኑረን ማለቱ ባልከፋ ነገር ግን አጥፊውን ለይቶ መውቀስ እንጂ ከኑግ የተገኘሽ ሰሊጥ አብረሽ ተወቀጭ ማድረግ ግን ያስተዛዝባል። ከፖለቲካ ነፃ ማለት ለቤተክረስቲያን ከሚያደላ ከቤተክረስርቲያን የበላይ ጠባቂ ጋር አብሮ አለመስራት መሆን ነበረበት? ወይስ እንደዘመናችን ቤተክርስቲያን ስትጠቃ ስትደፈር ዝም ብሎ መመልከት ነው? ደ. ዳንኤል ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ አድርጎት እንጂ ነገሩ ጠፍቶት አይመስለኝም። ብቻ የቤተክርስቲያን አምላክ ለሁሉ ጊዜ አለው። በኛ ቤተክርስቲያን ያለው ችግር /የፕተርክናው/ ችግር የገጠመው ከመቼ ጀምሮ ነው? ለምን? የሚሉትን ጥያቆዋች ከመሰረቱ በመመርመር መልሱን ማግኘት አይከብድም። እንደኔ የቤተክርስቲያናችን የስልጣን ጠብ የሚስተካከለውም ሁሉም ስለሰው ሳይሆን ፣የሚያስረውንና የሚገለውን ፈርቶ ሳይሆን ስለእውነትና ስለ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን በእውነት ሲቆም ነው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. by the way have u understand the message and its purpose ?? please write what u know ,why u blem others for what u feel and know???if u can and have the truth tell us ? dani told us what is important for us.i have seen that all important and fit ideas have visited this site not only the idea of the bloger.

   Delete
  2. የቀደሙ አባቶች ምርጫ እንከን የለሽ ነበር ብዬ አልከራከርም። ነገር ግን አቡነ ባስልዮስ፣ አቡነ ቴዎፍሎስ፣ አቡነ ተክለሃይማኖት ከአባ ጳውሎስ ጋር በምንም መመዘኛ አብረው ሊወቀሱ አይገባም፤ ለምን?
   1. ያለው የዘመን ልዩነትና ያን ተከትሎ የተፈጠረው የፐለቲካ፣ ማኅበራዊና የምዕመናን ንቃተ ህሊና ዕድገት ስንመለከት መሻሻል እንጂ እዬሞተ መሄድ አልነበረበትም ። በ1951 እና በ1984 የተመረጡ ሁለት ፓትርያርኮችን በዲሞክራሲያው ምርጫ መስፈርት እኩል በፍጹም ሊወቀሱ አይችሉም።
   2. ርዕሳችን ምርጫ ቢሆንም ቅሉ እንዲህ እንድናስብ ያደረገን ግን አሁን በእግዚአብሄር ቤት የሚሰራው ግፍ፣ ሸፍጥ ፣ከማያምኑት የከፋ ኢ-መንፈሳዊነት እንጂ የዲሞክራሲያዊ ምርጫ ጥማት አይመስለኝም፤ በነዚያ አባቶቻችንም እንዲህ አይነት ነውር እንደተፈጸመ አላነበብንም። ይልቁን አቡነ ባስልዮስ ሲያረጁ እንደራሲ ሾመው፣ አቡነ ቴዎፍሎስ በሰማዕትነት፣ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም በብህትውና እንዳረፉ ሰማን እንጂ። ይልቅ አምስት አባቶች ከኢትዮጵያ እንደሚሄዱ እዚህ ቪዲዮ( http://www.youtube.com/watch?v=4wxpPAxUwiw) ጋር ሰምቻለሁና አጋጣሚውን እንዲጠቅቀሙበት ማሳሰብ ቢቻል ጥሩ ነው። ዳኒ ቲፎዞዎችህን አንድ ብትልልን ጥሩ ነው

   Delete
 21. Dn. Daniel,

  You deserve the highest appreciation for this magnificent piece. I do hope that all who read your article will think of what we ourselves should do to improve the situation in our church instead of expecting others to do it for us.

  ReplyDelete
 22. ግብፃውያን ግን በመስከረም 2005 መጨረሻ አካባቢ አዲስ አባት እንደሚያገኙ ተስፋ አድርገዋል፡፡ ኢትዮጵያውያንስ?

  ReplyDelete
 23. ዳኒ ያነሳኸው ሃሳብ በጣም ጥሩ እና ወቅታዊ ነው፡ እኔ የሚከተለውን አስተያየት ልስጥህ - የኛ ምእመናን በእምነት በኩል የማይታሙ ከእውቀት ግን ተከፍሎ ያለባቸው ናቸው ስለዚህ ከተቻለህ ይህንን የእውቀት ክፍተት ለመሙላት በኛ በቤተክርስቲያን ስላለው የአመራረጥ ሂደትና ልምድ ብታካፍለን ፤ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ምንነትና ጥቅሙን ፡ ያሉበትን ተግዳሮት ፡ እነማን አባል እንደሚሆኑበት፡ በቤተክርስቲያን ያለውን የስራ ድርሻ በተጨማሪም ሌላው ተራ ምእመን በዚህ ጉባኤ ውስጥ ያለው ድርሻ (ዞሮ ዞሮ ጉባኤው ከምእመናን የወጣ ስለሚሆን) ምን ሊሆን እንደሚገባና ተጠያቂነቱ እስከምን ድረስ እንደሆነ ብትጽፍልን፤ . . . . .ማን ያውቃል እግዚአብሔር ብሎ ቤተክርስቲያን ስራዋን እንዳትሰራ የተጫኗት እጆች በተነሱ ጊዜ እና መስራት በሚቻልት ዘመን እውቀት አጠሮች ሆነን በድፍረት ያደቀቅናትን ቤት ያለዕውቀት በመሥራት ደግሞ ይበልጥ እንዳንጎዳት ፤

  ReplyDelete
 24. እንደ አቡነ ተክለሃይማኖት ያሉት ከእግዚአብሔር !!!
  እንደ አባ ጳውሎስ ያሉትን ደግሞ መንግስት ይመርጥልናል::

  "belehe sew ke gorebet yemarale "

  ReplyDelete
 25. Notice from the Ethiopian Electoral Board

  Due to the sudden death of AP and with the consent of the holy synod it is now agreed to under go the process to elect the new Patriarch.
  The exact date of election will be announced at the later date but this is just to remind all applicants to be ready with their Sign and submit application till the end of the month.The application should be supported by 500 signatures of the Respective administrative Zone. The Independent MK is not allowed to observe the election process.Others who are legally registered as Mahiber will continue and fully participate in the process.The election process will be fair and free.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Me like this comment BETammmmmmmmmmmmmmm !!!

   Delete
 26. ግብፃውያን ግን በመስከረም 2005 መጨረሻ አካባቢ አዲስ አባት እንደሚያገኙ ተስፋ አድርገዋል፡፡ ኢትዮጵያውያንስ?? why you worry? long live Meles he will assign a Patriarch as soon as he die. so simple. no law, jinijanka minamin

  ReplyDelete
 27. menealebate ega maserate yalabenen sanesara karetane yehone????????????????????????????????

  ReplyDelete
 28. edagelene...........

  ReplyDelete
 29. እጅግ በጣም የተጠና ውጤቱም አርኪ ነው. . . ታድለው! እኛ ግን . . . እኔ የምለው ለሀገሪቱ ለዋሳ አስተዳደር የቤተክርስቲያን ደካማ አስተዳደር አስተዋፅኦ ይኖረው ይሆን? ወይስ የመንግስት ድካም ነው ያደከማት? ግን ፕትርክና ምን ያህል ጥንቃቄ እንደሚያስፈልገው የግብፅ ቤተክርስቲያን ምሣሌ ስትሆን. . . እኛ ደግሞ የዝርክርክ አሠራር ውጤት ተምሣሌት! Anyway im optimist this crisis period will end, but in z meantime brothers and sisters like dn daniel continue to feed us wiz z proper knowledge.

  ReplyDelete
 30. እጅግ በጣም የተጠና ውጤቱም አርኪ ነው! ታድለው! እኛ ግን. . . እኔ የምለው ለሀገሪቱ ለዋሳ አስተዳደር የቤተክርስቲያን ደካማ አስተዳደር አስተዋፅኦ ይኖረው ይሆን? ወይስ የመንግስት ድካም ነው ያደከማት? ግን ፕትርክና ምን ያህል ጥንቃቄ እንደሚያስፈልገው የግብፅ ቤተክርስቲያን ምሣሌ ስትሆን. . . እኛ ደግሞ የዝርክርክ አሠራር ውጤት ተምሣሌት! Im always optimist we will get out of this crisis period. Meantime brothers and sisters like dn daniel plz continue to teach us. . . knowledgable christians will definately make a huge difference finally. Thanks a lot dani.

  ReplyDelete
 31. Dani, May God bless you in His abundant Grace and Mercy.

  If I am not mistaken, the number in the message (which I believe is a great lesson) needs two more zeros.. (በነገራችን ላይ በግብጽ ቤተ ክርስቲያን የካህናት ቁጥር ትንሽ ነው፡፡ እንደኛ 400,000 አድርገን አናስበው)(Instead of 400,000 it is +40,000,000). Please correct me if I did not understand.

  ReplyDelete
  Replies
  1. What are u saing? is all orthodox's are Kahen?

   Delete
 32. kale hiwet yasemaln D/Daniel.Legna abatoch E/Z segawn abzto endih aynetun menfesawi mricha endiyadergu yirdachew.

  ReplyDelete
 33. Dn Daniel kale hiwot yasemalin
  I just have a question for you. I'm not against Abune Shinoda what so ever, but wasn't he a patriarch of Egypt when the Egyptian fathers commit all those crimes against the poor Ethiopian fathers in Israel. Or Der Sultan Gedam? I just thought he should have said something about it or even prevent it from happening.Just saying. Atlanta.

  ReplyDelete
 34. ስለ ቤተክረስቲያን ጉዳይ እንኳን ያበላሹብን ግብፃዊያን ናቸው እነዚያ የዋህ ደጋግ አባቶቻችን አላፊነት ሰጥተዋቸው፡፡ ዳኒ በጣም እናመሰግናለን በልጅነትህ ቀንበር ተሸክመሃል፡፡ ጌታ እግዚአብሐር ይረዳህ፡፡

  ReplyDelete
 35. Egnam endedirow keza bishomilin endet edilegnoch nebern. Inquan be Gibtsawianu ayinet yikrina kezam banase egiziabher kalgebabet besteker legna yemichal ayimeslim.

  God bless Ethiopia!!!

  ReplyDelete
 36. Dani God bless you...one thing i always want to know..is there a "kenona" as to what color the patriarch should wear...I saw all the previous Ethiopian and Coptic Pops in Black but the guy in the Ethiopian church now is seen in white and late Abuna T/Haimanot in yellow...i think there should be a reason why all the fathers wear black...can you please let us know in one article about these if you can?...thanks!

  ReplyDelete
 37. ኢትዮጵያውያንስ? ምን ለማለት ፈልገህ ነው ህጋዊና እውቅና ያላቸው አባት አሉን በርግጥ ሲሞቱ ወይም ሲያርፉ ከሆነ እውነት ነው አንደንዶቻቹ አስተያየት ሰጪዎች ምነው በጣም አሳዛኝ አስተያየት ፃፋቹ ለመሆኑ አባ ጳውሎስ በመንግስት ሲመረጡ ነበራቹ ለምን የማታውቁት ትጽፋለቹ ነውር ነው እንደዚህ ከሆነ ፃድቁ አቡነ ተክለሃይማኖትም በደርግ ተመረጡ የሚባሉት አቡነ ተክለሃይማኖትም ሌሎችም በምትሉት አይነት ተመርጠው የተቀመጡ አይደሉም ማለት እንደ ግብፅ ኮፕቲክ ከጳጳሳት ከካህናትና ከህዝብ በተውጣ የተመረጡ አይደሉም ለምን በአቡነ ጳውሎስ ብቻ ይህ ትላላችሁ ከትግራይ ስለሆኑ ነው? በጣም ሚዘናዊ አይደላችሁም ታሰዝናለቹ ታሪክ ከሆነ ሁላችንም እናውቀዋለን ለእውነት እንኑር ኢክርስቱን አንሁን

  ReplyDelete
 38. The first and the second patriarch were not politically assumed like Aba Paulos is. Please call a spade a spade. Do not try to mix the problem of our day with that of the true servants of the Church who rested in peace. It is with the coming of Abune Paulos to the patriarchate after toppling down Abune Markorios that our Church has faced such ugly fight over power. And it is TPLF which should be responsible for this, not Emperor Hailesilassie.Instead, His Majesty deserves appreciation and respect for what he did to emancipate EOTC from Coptic Church dominance. As he was the church's protector, the first and the second patriarchs were close to the Emperor. That was absolutely right. However, nowadays, the so called 'government' publicly declared that it was not neither christian nor other religions oriented but secular. If so, it should not have linked itself with the Church's leadership. But the fact is that it appointed its interest protector as patriarch and defends him blatantly. This is the situation that need to be criticized, Dn. Daniel. And also, if we follow our own rules of electing patriarch, it is enough and works well, I believe.

  ReplyDelete
 39. Wow. I am happy that someone finally said it.. It is about time..
  Thank you for sharing
  More Blessing to you....Dani

  ReplyDelete
 40. እድሜ ይስጥህ ዲን ዳንኤል! የእኛ ጉዳይ አሳሳቢ ነው ወይ ፍጹም መንፈሳዊ አልሆንን ወይ የለየለት ሥጋዊ አልሆንን! እንዲያው ለብ ብለን ፈጣሪን እያሳዘንን ነው. ግን ለቤተ ክርስቲያን ጉዳይ መፍትሔ ሊፈልግ የሚገባው ማነው? ምዕመናንስ ቤተ ክርስቲያን የእኔ ናት በቤተ ክርሰቲያን ጉዳይ ድርሻዬን ልወጣ የምንለው መቼ ይሆን? አቤት ሲያስፈራ ወዮልን!

  ReplyDelete
 41. ኃየሎም ከበደJune 5, 2012 at 10:54 AM

  ለኢትዮጵያውያንስ?አይ ዲ/ን ዳንኤል ለኛማ እንደ አቡነ ተክለሃይማኖት ያሉት እግዚአብሔር እንደ አባ ጳውሎስ ያሉት ደግሞ መንግስት ይመርጥልናል፡፡ እስኪ እግዚአብሔር እንድረዳን አንተ እርሱ በሰጠህ እውቀት የተቻለህን አድርግ; ሌሎቻችን ደግሞ በጸሎት እንትጋ፡፡
  አምላከ ቅዱሳን ሁላችንም ይርዳን ላንተም ረጅም የአገልግሎት ዘመን ከሙሉ ጤና ጋር ያድልልን፡፡

  ReplyDelete
 42. danel mhcem egziabeher anede gize feredobenal htiatachen kmbezatu Ytnesa yetsedekun sera lmayet tchgernale anteme bereta edemewen yabezalhe

  ReplyDelete
 43. ethiopian e/r yasibat kekifum neger yitebikat.

  ReplyDelete