Monday, April 9, 2012

ሰሙነ ሕማማት

 በጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት እጅግ ከሚወደዱ እና ከሚናፈቁ ወቅቶች አንዱ ሰሙነ ሕማማት ነው፡፡ በዕለተ ሆሳዕና ጀምሮ በዕለተ ትንሣኤ የሚጠናቀቀው እጅግ ላቅ ያለ መንፈሳዊ ሕይወት የሚታይበት ጊዜ ነው፡፡ በላቲን Hebdomas Sancta or Hebdomas Maior በግሪክ ደግሞ Ἁγία καὶ Μεγάλη Ἑβδομάς, Hagia kai Megale Hebdomas  ታላቁ ሳምንት ተብሎ ይጠራል፡፡ በኛ ደግሞ ሰሙነ ሕማማት፡፡
የሕማማትን ወቅት ከመጀመርያው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ክርስቲያኖች ያከብሩት እንደነበር የሚያሳዩ ጥንታውያን መዛግብት አሉ፡፡ በሕግ ደረጃ ክርስቲያኖች በሰሙነ ሕማማት ከማንኛውም ሥራ ነጻ ሆነው፣ ፍርድ ቤቶችም ተዘግተው እንዲከበሩ የወሰነው ደግሞ ታላቁ ቆስጠንጢኖስ ነው፡፡
 እስከ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አዳዲስ ክርስቲያኖች ለመጠመቅ ይመርጡት የነበረው ጊዜ የትንሣኤን ቀን ነበር፡፡ ለዚህም ሁለት ዓይነት ምክንያቶች ነበሯቸው፡፡ የመጀመርያው ሰሙነ ሕማማትን በልዩ ሁኔታ ጾመው በትንሣኤው ቀን መጠመቁ ልዩ የሆነ መንፈሳዊ ኃይል ስለሚሰጥ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እንደ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት መጠመቅ ከክርስቶስ ጋር ሞቶ ከክርስቶስ ጋር መነሳት ነውና ጥምቀቱን ከትንሣኤው ጋር አያይዘውት ነበር፡፡
የሕማማት ሰሞን የኦሪት ጊዜን የሚያስታውስ ሰሞን ነው፡፡ አዳዲስ ክርስቲያኖቸም ይህንን ሰሞን ያለፈ ሕይወታቸውን ለማስታወስ እና ለማልቀስ ብሎም ራሳቸውን ወደ ሐዲስ ዘመን ለመለወጥ ይጠቀሙበት ነበር፡፡
በመጀመርያው መቶ ክፍለ ዘመን ከዓርብ ጀምሮ ሰሙነ ሕማማትን ማክበር የተዘወተረ ነበር፡፡ በሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ግን ስድስቱንም ቀን ማክበር የክርስቲያኖች ሥርዓት እየሆነ መጣ፡፡ ለዚሀም መነሻ የሆነው የአባቶቻችን ቀኖና የተሰኘው ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ የተደነገጉ ቀኖናት መዝገብ  በቦታው መዳረስ ነው፡፡ በዚህ መዝገብ ዐንቀጽ 5 ቁጥር 19 ላይ «በሰሞነ ሕማማት ከሳምንቱ ሁለተኛ ቀን (ሰኞ) እስከ ቅዳሜ የሰንበት መዘጋጃ ቀን ድረስ ጹሙ፡፡ በእነዚህም ጊዜያት ከእንጀራ እና ከጨው፣ ከማባያም በቀር ሌላ ነገር አትብሉ፡፡ ለመጠጥም ውኃ ብቻ ይሁንላችሁ» ይላል፡፡
የኛም ግብረ ሕማማት ይህንኑ የሐዋርያት ቀኖና በመጥቀስ በክፍል አንድ ሠላሳ አንደኛ ትእዛዝ በሚለው ርእስ ሥር «በሕማማት ሰሞን ከእንጀራ፣ ከጨው እና ከውኃ በቀር ምንም ምንም አትብሉ» ይላል፡፡
260 ዓም ለባሲሊደስ በጻፈው ደብዳቤ እያንዳንዷን የሰሞነ ሕማማት ቀን እና ሰዓት ከክርስቶስ መከራ ጋር በማያያዝ ገልጾ ነበር፡፡ 2ኛው ወይንም 3ኛው መክዘ ተሰባስቦ መጠረዙ የሚነገርለት የሶርያው ዲድስቅልያም ሰሙነ ሕማማት እንዴት መጾም እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ አቡሊዲስ ዘሮም በጻፈው የሐዋርያት ትውፊት (215 ዓም) ስለ ሰሙነ ሕማማት ሥርዓት ይደነግጋል፡፡ እያንዳንዷንም ሰዓት ከክርስቶስ መከራ ጋር ያገናኛታል፡፡
ሰሙነ ሕማማት አሁን ያለውን መልክ የያዘው 4ኛው መክዘ በኢየሩሳሌሙ ፓትርያርክ በቄርሎስ ዘመን ነው፡፡ ፓትርያርክ ቄርሎስ በመጨረሻዎቹ ዓመታት በኢየሩሳሌም ከሚከበረው የጌታችን ትንሣኤ በፊት ያለውን ሰሙነ ሕማማት እያንዳንዱን ቀን በማሰብ የሚከበርበትን ሥርዓት ሠርቶ ነበር፡፡ 381 እስከ 385 ወደ ኢየሩሳሌም ለመሳለም የሄደችው ኤገርያ የተባለች ስፔናዊ በኢየሩሳሌም እንዴት ሰሙነ ሕማማት ይከበር እንደነበር የታሪክ መዝገብ ትታልናለች፡፡
ኤገርያ በጉዞ ማስታወሻዋ እንዲህ ትተርክልናለች
«በዓሉ የሚጀምረው በዕለተ እሑድ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ስለ ዓልዓዛር ትንሣኤ የሚገልጠው የወንጌል ክፍል ጠዋት ይነበባል፡፡ በሆሳዕና ዕለት ከሰዓት በኋላ ሁሉም ሰው ወደ ደብረ ዘይት ይወጣል፡፡ ከዚያም በጸጥታ የዘንባባ ዛፍ ተሸክሞ ወደ ኢየሩሳሌም ይመለሳል፡፡ ይህንንም በመጀመርያዎቹ ሦስት ቀናት ይፈጽማሉ፡፡ ይህም ጌታችን ማታ ማታ ከከተማዋ ወጥቶ በደብረ ዘይት ያደረገውን ጸሎት ለማስታወስ ነው፡፡
በጸሎተ ኀሙስ ጠዋት ቅዳሴ ይቀደሳል፡፡ (ይህም በዓመቱ ውስጥ በመስቀሉ መቅደስ ላይ የሚደረግ ቅዳሴ ነው)፡፡ ከሰዓት በኋላ ሌላ ቅዳሴ ተቀድሶ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ቆስጠንጢኖስ ባሠራው በኤሊዎና ቤተ ክርስቲያን ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት መብራት ያበራሉ፡፡ ከእኩለ ሌሊት በኋላ ደግሞ ወደ ጌቴ ሴማኒ ይጓዛሉ፡፡ በዚያም እስከ ንጋት ቆይተው የዓርብ ማለዳውን ወንጌል ለማንበብ ወደ ጎልጎታ ይመለሳሉ፡፡
ዓርብ ማለዳ ሁሉም መስቀሉን (በኢየሩሳሌም የነበረውን የጌታን መስቀል ነው) ቤተ ክርስቲያን አልባሳት ያስጌጡታል፡፡ ከስድስት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ጌታችን በጎልጎታ በተሰቀለበት ላይ ሁሉም ተሰብስቦ ጸሎት ያደርሳል፣ ያለቅሳል፣ ያዝናል፡፡ በሠርክ ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ወደ ስቅለቱ ቦታ በመጓዝ በዚያ ስለ ስቅለቱ እና መቃብሩ የሚገልጠው ወንጌል ይነበባል፡፡ ቅዳሜ ዕለት በየቤተ ክርስቲያኑ መብራት ይበራል፡፡»
ሰሙነ ሕማማትን ልዩ በሆነ ሁኔታ የማክበሩ ሥርዓት ከኢየሩሳሌም በተሳላሚዎች አማካይነት ወደ ልዩ ልዩ ሀገሮች መግባቱ ይታመናል፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አበው ከኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ዘመን አንሥቶ ወደ ኢየሩሳሌም የመጓዝ ሥርዓት ነበራቸውና ይህንን ሥርዓት ቀድመው ሳይወስዱት አይቀሩም፡፡ ቅዱስ ያሬድ ለዚህ ሰሙን የሚሆን ሥርዓት መሥራቱን ስናይም ይበልጥ ያጠናክርልናል፡፡
ለመጀመርያ ጊዜ አሁን በምናየው መልኩ የሰሙነ ሕማማት ምንባባትን ያዘጋጁት የገዳመ መቃርስ መነኮሳት መሆናቸውን ግብረ ሕማማት ይገልጥልናል፡፡ በእነዚህ የገዳመ መቃርስ አባቶች በመታገዝ የእስክንድርያው ፓትርያርክ አቡነ ገብርኤል 2 (1131-1145) (የኛ ግብረ ሕማማት "ጸሐፊ የነበረው የታሪክ ልጅ አባታችን አባ ቅብርያል" ይለዋል፡፡ ኢብን ቱርያክ የሚለውን ተርጉሞ ሳይሆን አይቀርም፡፡) በእርሱ አስተባባሪነት ሊቃውንቱ ለየቀኑ እና ለየሰዓቱ የሚሆኑትን ምንባባት ከብሉይ እና ከሐዲስ እያውጣጡ አዘጋጇቸው፡፡
ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ደግሞ የብሕንሳው ጳጳስ አቡነ ቡትሮስ ምንባባቱን ለየሰዓታቱ በተመጣጣኝ ሁኔታ በማካፈል ሁሉም ቀናት ተመጣኝ የሆኑ ሁሉም ዓይነት ምንባባት እንዲኖሯቸው አድርገዋል፡፡ ግብረ ሕማማታችንም «ከኦሪት እና ከነቢያት፣ ከነዌ ልጅ ከኢያሱ፣ ከንጉሥ ሰሎሞን መጽሐፍ ወስዶ ሁላቸው ትክክል እስከሆኑ ድረስ በየሰዓቱ ሁሉ የሚገባውን አደረገ፡፡ አባቶች ከተናገሩት ሁለት ሁለት ተግሣፅ እና ምክር አንዱ በነግህ አንዱም በማታ እንዲነበብ አደረገ» ይላል፡፡
ግብረ ሕማማት ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ የተተረጎመበትን ራሱ ግብረ ሕማማት ይነግረናል፡፡ በመጽሐፉ መጨረሻ በሰላማ መተርጉም ጊዜ (1340 ( 1380) ገብቶ መተርጎሙን ያሳያል፡፡ በግብረ ሕማማቱ ያለው ምንባብ አንዳንድ ጊዜ ከግብፁ ግብረ ሕማማት ይበልጣል፡፡ በግብፁ ግብረ ሕማማት የሌሉት ተአምረ ማርያም እና ተአምረ ኢየሱስም ተካተተዋል፡፡ ይህም የኢትዮጵያ ሊቃውንት እጅ በትርጉሙ እና በዝግጅቱ ሥራ ላይ መኖሩን ያመለክተናል፡፡
በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ ባዕድ ቃላት
በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡
ኪርያላይሶን
ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬ ኤሌይሶን» ነው፡፡ «ኪርያ» ማለት «እግዝእትነ» ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬ ኤሌይሶን» መባል አለበት፡፡ ትርጉሙም «አቤቱ ማረን» ማለት ነው፡፡ «ኪርያላይሶን» የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው «» ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ «» በመሳሳባቸው በአማርኛ «» ፈጥረው ነው፡፡
ናይናን
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡
እብኖዲ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡ «እብኖዲ ናይናን» ሲልም «አምላክ ሆይ ማረን» ማለቱ ነው
ታኦስ
የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡ «ታኦስ ናይናን» ማለትም «ጌታ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡
ማስያስ
የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡ «ማስያስ ናይናን» ሲልም «መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው
ትስቡጣ
«ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው
አምነስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ
Em-nees the-tee mo-ki-riey enti vasilia so
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ» ማለት ነው፡፡
አምንስቲቲ መዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ
Em-nees the-tee  mo-a-geh-e enti vasilia so
የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ - ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው
አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ
Em-nees the-tee mo-zess-pota enti vasilia so
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ- የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡
ሥርዓተ ሕማማት
በሐዋርያት ቀኖና እንዲህ ይላል «ይልቁንም በእነዚህ በስድስቱ ቀኖች መጾም የሚችል ቢኖር ሁለት ሁለት ቀን ይጹም፡፡ የማይችል ግን አንድ አንድ ቀን ይጹም፡፡ ሌሎችን ቀኖች እስከ ዘጠኝ ሰዓት ይጹሙ፤ እችላለሁ የሚል ግን ፀሐይ እስኪገባ ይጹም፡፡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተሰብስባችሁ መጻሕፍተ ኦሪትን እና መጻሕፍተ ነቢያትን፣ የዳዊትንም መዝሙር እያነበባችሁ በምስጋና በጸሎት ዶሮ እስከሚጮኽ ድረስ የሌሊቱን ሰዓት ጠብቁ፡፡
አንድ ምእመን የታመመ ቢሆን ወይም ክርስቲያን በሌለበት አገር ሆኖ ሳያውቅ የሕማማት ሰሞን ቢያልፍበት ወይንም በደዌ ውስጥ ሆኖ ቢቀርበት ከበዓለ ሃምሳ በኋላ ሰውነቱን በማድከምም ደስታን ያድርግ፡፡ ባለመፍራት እንዳይጠፋ ውስጣዊ ሰውነቱን ይመርምር፡፡
ጾምን ከመፍታታቸው በፊት ገላቸውን ይታጠቡ፤ ሁሉም መብራት የሚያበሩ ይሁኑ፡፡
የቻለ ዓርብ እና ቅዳሜ ሁለት ቀን ይጹም፤ ሁለት ቀን መጾም የማይችል በሽተኛ ቢሆን ግን ቀዳም ሥዑርን ይጹም፡፡ የኀዘን ቀን ስለሆነች፡፡ እንጀራ እና ጨውም አይቅመስ፡፡»

64 comments:

 1. Dear DN Daniel,

  May God Bless you it is timely and important clarifications.

  Remain blessed.

  >>

  ReplyDelete
 2. You don't know me,I am the one that gave u agenda of ommercial Bank of Ethiopia by your agent Habtamu.

  I really appriciate you

  ReplyDelete
 3. ቃለህይወት ያሰማልን! ዲ/ን
  ኪርዬ ኤሌይሶን/ አቤቱ ማረን!!!

  ReplyDelete
 4. ቃለህይወት ያሰማልን! ዲ/ን
  ኪርዬ ኤሌይሶን/ አቤቱ ማረን!!!

  ReplyDelete
 5. ዲያቆን ዳንኤል በጣም አመሰግናለሁ ምክንያቱም እስከዛሬ ድረስ የእነዚህን ቃላት ትርጉም ለማግኘት በጣም ስጓጓ ስለነበረና አሁን አንተ ባጋጣሚ በብሎግህ ላይ ስትገልጣቸው በጣም ደስ ስላለኝ ነው፡፡ እግዚአብሔር ጸጋውን አብዝቶ ጨምሮ ይስጥህ፡፡ ለእኛም አንብበን የምንጠቀምበት አስተዋይ አእምሮ ያድለን ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን አሜን!

  ReplyDelete
 6. እግዚአብሔር ይስጥህ እንደፈለግን ስንጠራው የነበረውን ዘንድሮ በትክክልና ገብቶን ልንጠራው ነው፡፡ ቃለ ሕይወት ያሰማልኝ፡፡

  ReplyDelete
 7. bezih semon sew bimot fitihat yelem yemibalew kemin ena endet endehone bibrara?
  egzer yistilin

  ReplyDelete
 8. ቃለህይወት ያሰማልን ,,,,,,,,,,,

  ReplyDelete
 9. አመግናለሁ ዲ/ን፡፡ ለምን ቀሲስ አየሆንም እያለኩ አስባለሁ፡፡ ስላማይፈልግ፣ለጥናትና ምርምሩ ስለማይመቸው፣ንሰሃ ልጆች ስለሚበዙበት፣ወይስ ፀጋው ይበቃኛል ብሎ ; መልሱን አላውቀውም፡፡ ለማንኛውም ስለአስተዋጽሆህ አመሰግናለው፡፡አመግናለሁ ዲ/ን፡፡ ለምን ቀሲስ አሆንም እያለኩ አስባለሁ፡፡ ስላማይፈልግ፣ለጥናትና ምርምሩ ስለማይመቸው፣ንሰሃ ልጆች ስለሚበዙበት፣ወይስ ፀጋው ይበቃኛል ብሎ ; መልሱን አላውቀውም፡፡ ለማንኛውም ስለአስተዋጽሆህ አመሰግናለው፡፡

  ReplyDelete
 10. Kale Hiwot Yasemalin. Betam Grum New.

  ReplyDelete
 11. ዲያቆን ዳንኤል በጣም አመሰግናለሁ: እግዚአብሔር ይስጥህ እንደፈለግን ስንጠራው የነበረውን ዘንድሮ በትክክልና ገብቶን ልንጠራው ነው፡፡ ቃለ ሕይወት ያሰማልኝ፡፡

  ReplyDelete
 12. "በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ ባዕድ ቃላት"
  ባዕድ የምትለዋ ቃል በሌላ ቃል ብትተካት የኛ አይደለም የሚል አንድምታ እንዳያመጣ::እርግጥ የዕብራይስጥ ቋንቛ ሊሆን ይችላል እኛ ምዕመናን ግን የኛ ብለን ተቀብለናቸዋል ስለዚህ ባዕድ ባትላቸው በግሌ ደስ ይለኛል::

  ትንሽ ውንድምህ HG

  ReplyDelete
 13. ፍስሐ -ሲያትልApril 10, 2012 at 7:25 AM

  የልብን ዋጋ የሚከፍል አምላክ የልብህን መሻት ሳይሞላ እንዳይቀር የሚሰጥህን አይጉደልብህ።በህይወት ቃል የተሞላች ነፍስ የፍፃሜዋን ዋጋ በፍሬዎችህ አግኝ።የማወቅ ፍላጎቴን ከጦማርህ ተሳክቶልኛልና...።

  ReplyDelete
 14. Holy Pascha Daniel
  CLICK HERE to see My Gallery
  www.bereketdecor.blogspot.com

  ReplyDelete
 15. I hope that you will have a blessed Holy Week.
  come and vist me @ www.bereketdecor.blogspot.com

  ReplyDelete
 16. thank you. it is timely information. Information is power if it is reliable and timely available. So God gave us a power for the holly week. God bless you, your family and your service

  ReplyDelete
 17. Kalehiwot yasemalen!

  ReplyDelete
 18. d/n danel betam mitidenk sew neh e/r wagan yikifelih,bezih manim legenzeb sewch yebiate chirstianin sim beminegidubet sihat endante aynet sew megegnetu tesfachin abizitehilinan

  G/mariam negn
  Adama univeristy

  ReplyDelete
 19. ቃለህይወት ያሰማልን!

  ReplyDelete
 20. Replies
  1. ዲ/ን ዳንኤል እግዚሀብሔር አምላክ እውቀትህን ያስፋልህ በህይወት ይጠብቅህ ከምትፅፋቸው ጹሁፎች ብዙ ተምሬያለሁ አሁንም የነዚህን ቃላት ትርጓሜዎች አላውቅም ነበር ነገር ግን እንዳውቅ አድርገኸኛልና አመሰግናለሁ

   Delete
 21. ዛሬ በጣም ደስ ብሎኛል ምክንያቱም ጥሩ የሆነ ትምህርት ከጦማርህ ስላገኘዉ ነዉ ዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሔር ፀጋዉን ያብዛልህ፡፡እስካሁን ስለ ሰሙነ ህማማት አመጣጥና ታሪክ ብዙም እዉቀቱ አልነበረኝም አሁን ግን አንተ ገከፅክልኝ በነካ እጅህ በሀገራችን ከሰሙነ ህማማት ጋር ተያይዘዉ ያሉ ትዉፊቶች አመጣጥንም ብትዘረዝርልን ደስ ይለኛል፡፡ምክንያቱም እንደዚህ አይነቶቹ ትምህርቶች በቤተ ክርስቲያናችን የሚከናወኑ ማናቸዉ ተግባራት ምክንያታዊ እንደሆኑ ማሳያ ስለሆኑና ለማንኛዉ ጥያቄ ላለዉ ወገን ምላሽ ስለ ሚሆኑ ነዉ ፡፡ በተጨማሪም መሰል ትምህርቶችን አሰባስበህ ለህትምት ብታበቃቸዉ ብዙ ህዝብን መድረስ ይቻላልና አስብበት

  ReplyDelete
 22. ቃለ ሕይወት ያሰማልኝ.....የማንበብህ ፀጋ በሁላችን ላይ ይደር! አሜን
  አትፍረዱብኝ የማንበብ ችግር ስላለብኝ ነው....

  ReplyDelete
 23. May God Bless you!i like your explanation. It is important and timely.

  ReplyDelete
 24. ቃለ ሕይወት ያሰማልን ወንድማችን ። አንድ ጥያቄ ደግሞ አለኝ፡
  የቻለ ሁለት ቀን ይጹም ያልክው ላይ አንዳንድ ሰዎች ሦስት ቀን ይጾማሉ ማለትም ከሐሙስ ጀምረው እህል መቅመስ ያቆማሉ።
  እና ይህስ እንዴት ታየዋለህ?

  ReplyDelete
 25. Kale hiywot Yasemalin

  ReplyDelete
 26. kalehiywot Yasemalin!

  ReplyDelete
 27. ሳሚ(ወ/ሚካኤል)April 10, 2012 at 7:15 PM

  ለሃይማኖቱ አስተምህሮት የንስር ዓይን ከተሰጠው አስተዋይ የጌታ አገልጋይ የጡመራ ሰሌዳ ይህን ማንበብ የሁሉም ርካታ ነው!!!! መ/ዳኒ የሰሙነ-ህማማት የስርዓቱን ሆድእቃ ስላሳየኸን ሰው የሆነው ቅ/አምላክ የሰማያዊት መንግስቱን ሚሰጢር ያሳይህ!!!!...መልካም የህማም ጊዜ!!!! አሁን ያለነው በቀራነዮ ነውና በፍጹም ሀዘን ወደተሰቀለው እናንጋጥ!!! ያኔ እነሁዋት እናትህ የሚለውን የድህነት ኑዛዜ ተረክበን በትንሳኤው እንደምቃለን!!!ያለስርዓት ከሚሄዱት ፈቀቅ ትሉ ዘንድ በተሰቀለው ነጉስ ስለክርስቶስ እለምናችሁዋለሁ!!! ቃለ ህይወት ያሰማልን መምህር!!!!!!

  ReplyDelete
 28. Great! God bless you. I remember a servant of the church called Liquegubaie Tiguhe Bogale tried to collect the hymns of the church used during this Passion Week in an audio casset. He was saying the 'kirarison' part as you put it right. I appreciated him. This was issued some years back. I rememer also in one of the churches of Addis, an administrator of the chrch applying the same thing during the Good Friday's day, some years back. This shows that there is some understanding about the 'problem'in using the word as it is now.

  But sometimes I feel that Ethiopians tried to coin (including slight change in the tonation of the word)their own words instead of taking directly the word from other language. this word could be one example. the reason I said this is that the word 'kiraraison'is widely used in our Liturgy as well. Any how this is my reflection.

  The other point that I would like to make is about citing proper source for the information. For example, I would like to see the source for the information about Egaria (a woman from Spain), in what kind of language and the credibility of the source etc

  Keep this great work (educating and informing others)up!

  ReplyDelete
 29. mene beya lemarekeh?BABATEKERESTANE AGALEGELOTE TADASATE.

  ReplyDelete
 30. ma man betam arif new

  ReplyDelete
 31. ቃለ ሕይወት ያሰማልኝ..

  ReplyDelete
 32. በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የትንሳኤ በዓል ሊመጣ ሳምንት የማይሞላ ግዜ ቀርቶታል። እስቲ በሰላም ያምጣውና ሌላው ቢቀር እንኳን አደረሳችሁ ለመባባል ያብቃን።

  አሁን ህማማት ላይ እንገኛለን። በሀይማኖቱ የበቁ ወዳጆቻችን እንደሚነግሩን በዚህ ሰሞነ ህማማት ውስጥ ያሉ እያንዳንዱ ቀናት ክርስቶስ ስለ ሰው ልጅ የደረሰበት ስቃይ የሚታሰብባቸው ናቸው። በተለይም ኢየሱስ በአደባባይ ቆሞ ባስተማረ እና በተናገረ ግዜ የደረሰበት ስቃይ፤ ከአጓጉል ውንጀላ አንስቶ ግርፋት፣ እስራት፣ በመጨረሻም ስቅላትን ያካተተ ነበር።

  ነገር ግን ከዚህ ሁሉ በኋላ እሁድ ትንሳኤ ይሆናል። ደስታም ይበዛል።

  ከመንፈሳዊው ጉዳይ ፊታችንን ዘወር ስናደርግ የሚከተለውን እናገኛለን፤

  ኢህአዴግ አዲሳባን እና መላውን አገሪቷን “ለሰፊው ህዝብ ጥቅም” ብሎ ከተቆጣጠረ ስንት አመት ሆነው? ግንቦት ሲመጣ ሃያ አንድ አመት ይሞላዋል። (ደህና ጎርምሶ የለም እንዴ!?) አሁንማ ሚስት አምጡ ብሏል! አይሉኝም?

  ከደርግ ጋር ሲነፃፀር የኢህአዴግ በትረ ስልጣኑን መያዝ እንደ አዲስ ኪዳን የቆጠሩት ብዙዎች ነበሩ። በተለይ ለዲሞክራሲ ናፋቂዎች ትልቅ ተስፋ ፈንጥቆ ነበር። “የመናገር እና የመፃፍ ነፃነት ተከብሯል።” ተብሎ ታወጀ። እሰየው ተባለ። “ተቀናቃኝ የፖለቲካ ፓርቲ ማቋቋም ይቻላል ተብሎ ተነገረ።” እንዲህ ነው እንጂ ብለን አደነቅን! “የነፃ ገበያ ስርዓት ተግባራዊ ይሆናል” ተባለ። እልልል… ይህንን ሁሉ አለም የሚያሳዩን እነዚህ እነማን ናቸው? የሚል ውዳሴ ጎረፈ። ህዝቤም በየ መስኩ ተሳትፎውን አሳየ።

  ቀን ቀንን እየወለደ ሄደና ዛሬ ሀያ አንድ አመት ሞላን አዲስ ኪዳን ስንል ያሞካሸነውም ዘመነ ኢህአዴግም በመግቢያው ያበሰራቸውን በሙሉ ረሳቸው። ችግር ረሀብ እና እርዛትም በዙ። ነፃ ገበያም ሆነ ነፃ ንግግር ተግባር ላይ ጠፉ። ይልቁንም በአደባባይ ቆሞ መናገር ያስወነጅል ጀመር። እስራት እንግልት ምርመራውም በረከተ። በሁሉም ዘንድ ስቃዩ በዛ! በርካቶችም አሉ፤ “ህማማቱ ገባ”

  እውነትም ወዳጄ ኢህአዴግ አዲሳባ ሲገባ አዲስ ኪዳን ሆኗል ካልን አሁን ያለነው በርግጠኝነት ህማማቱ ላይ ነው። ከህማማቱ ቀጥሎ ምን የሚከሰት ይመስላችኋል? እኔ ግን እላለሁ ትንሳኤ እየመጣ ነው! እናም በህማማቱ ላይ ያላችሁ በሙሉ አይዟችሁ!

  ለማንኛውም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ወዳጆቼ መልካም ሰሙነ ህማማት ይሁንላችሁ! ተግታችሁ “አቤት” በሉ

  ReplyDelete
 33. kale hiwot yasemalen agelgilotihen egiziabher yibark, amen!!

  ReplyDelete
 34. wendimachin kalehiwot yasemalin.

  ReplyDelete
 35. please just write only spiritual scripts i like your spiritual lesson.

  ReplyDelete
 36. ዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሔር ፀጋዉን ያብዛልህ፡፡እስካሁን ስለ ሰሙነ ህማማት አመጣጥና ታሪክ ብዙም እዉቀቱ አልነበረኝም አሁን ግን አንተ ገከፅክልኝ በነካ እጅህ በሀገራችን ከሰሙነ ህማማት ጋር ተያይዘዉ ያሉ ትዉፊቶች አመጣጥንም ብትዘረዝርልን ደስ ይለኛል፡፡እግዚአብሔር ይስጥህ, ቃለ ሕይወት ያሰማልኝ፡፡

  ReplyDelete
 37. Andande kemesimerih yelekekih eyemeselegn wuste kusilll yilal, azinalehu...lante bicha sayihon enen ena meseloche tananashochin chimr yizeh yemtitefa yimesilegnal. Ende semonu degmo sayih hulgizem mulu eminet..tesfa....endet des yilal yerase yalkutn hulu sitasemagn!!!!!!!
  E/r Yibarikih..Tsegawn Yabizalih!


  Tesfahun Phx, AZ

  ReplyDelete
 38. God bless u
  kale hiwot yasemaln.

  ReplyDelete
 39. Egizabher yebarkh.

  ReplyDelete
 40. Really In our church when they said "kerialiso"
  I said with them Kerialiso but I was confused so many years because of don't know the meaning of kerialiso
  Now I know the meaning Oh!
  1st thanks to God
  2nd thanks to D/danial

  ReplyDelete
 41. May God Bless your service
  what a nice lesson
  GOD BE WITH YOU

  ReplyDelete
 42. የጠቢቡ ሰለሞን ጥበብ እና ማስተዋል ይስጥህ ልዑል እግዚአብሐር ይባርክህ

  ReplyDelete
 43. ዉድ ዲ/ን ዳንኤል፡

  የምትጽፋቸዉን በሙሉ እያነበብኩ ነዉ፤ የራስህን አስተሳሰብ የምትገልጽባቸዉ ጽሑፎች እንዳሉ ሁሉ ስለ ሰሙነ-ህማማትና መሰል ጽሁፎች ስትጽፍ ግን ቢያንስ መነሻቸዉ ሌሎች ጽሑፎች ወይም መጻህፍት ናቸዉ። አንባቢዉ የበለጠ ግንዛቤ መያዝ ካስፈለገዉ የግድ ዋቢ መጻህፍትን መጥቀስ የሚገባ ይመስለኛል። ስለዚህ በጽሑፎችህ የተጠቀምክባቸዉን ዋቢ (References) እንደአስፈላጊነታቸዉ ብትጠቁመን ደስ ይለኛል።

  መልካም በዓል

  ReplyDelete
  Replies
  1. በኢትዮጵያ ሀሳብ እኔም እስማማለሁ፡፡ ለሽምደዳ ሳይሆን ለንባብ ዋቢ መጻህፍትን መጥቀስ ግድ ይላል፡፡

   Delete
 44. http://www.youtube.com/watch?v=4KPizez2E8E&feature=share

  ReplyDelete
 45. እግዚአብሄር ይስጥልኝ!

  ReplyDelete
 46. በሰሞነ ኅማማት ሊተውና ሊደረጉ የሚገባቸው ልምዶች
  1. ይሁዳ ጌታን በመሳም አሳልፎ በመስጠቱ ምክንያት መሳሳም መከልከል የለበትም። መሆን ያለበት ሰዎች የፍቅር /የእውነት ሰላምታ ቢለዋወጡ ነው። የይሁዳ ሰላምታ አሳልፎ የመስጠት ወይም የውሸት መሆኑ እንጂ ችግሩ ሰላምታ በራሱ ችግር የለውም እንደውም ያስፈልጋል ምክንያቱም ሰላምታ አለመለዋወጥ በራሱ የይዳን ግብር አይቃረንም። ተቃራኒው በፍቅር መሳሳም ነውና።
  2. ጌታ በዚህ ሳምት ይቅር እንዳለን ክርስቲያኖችም በዚህ ሳምንት ይቅር ብንባባልና እርሱ የሐዋርረያቱን እግር እንዳጠበና እናንተም እንዲሁ አድርጉ እንዳለ እርስበራሳችን እግራችንን ብንተጣጠብ /ካህናት ከሚያደርጉት ከጸሎተ ሐሙስ በተጨማሪ/
  3. ጌታ በዚህ ሳምንት ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ለዘለዓለም ሕይወተ ይሆነን ዘንድ እንደሰጠን ወደ ቁርባን ብንቀርብ
  በጣም ትኩረት የሚሰጠው መሳሳም እንደማይገባ እንጂ አለመቁረብ ብዙም ችግር እንደሌለው ነው ይህ ቢስተካከል
  4. በአንዳንድ አካባቢ በጎንደር ፣በትግራይና በወሎ አካባቢዎች በዚህ ሳምት ሊወገዝ የሚገባው ትውፊት/ባህል አለ። ዳቦ/ቂጣ ጋግሮ መናፍቃን የጌታ እራት እያሉ እንደሚዘብቱት በአመት አንዴ በዚህ በህማማት ብቻ እየተጋገረ የሚበላ ልምድ አለ የምሴተ ሐሙስ ራት ጌታ አማናዊ ሥጋውንና ደሙን ለሐዋርያት የሰጠበት እና ይህን ሚስጢርም ሊሰሩ የተሰጣቸው ካህናት ብቻ ሆነው ሳለ አጉል ልማድ አለና ሊታረም ይገባዋል። በትግራም እንዲሁ ሴቶች ዠዋዥዌ ሲጫወቱ የሚውሉበት ወንወዶች ፀጉራቸውን የሚላጩበት ልምድ አለ በሰሞነ ኅማማት
  5. ስለ ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደሙ ግን ብዙ የምለው አለኝ። አሳዛኙ የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ታሪክ ነው። ብዙው ምእመን 80% የሚሆነው እንደኔ ግምት የክርስትናው እለት የቆረበ ዳግም ሳይቆር ነው ወደ መቃብር የሚወርደው። ለምን ??? በቤተክርስቲያን ስርዐት ላለመቀበል የሚያበቁ ነገሮች የተገለጹ ናቸው ነገር ግን መምህራን ማስፈራራት እንጂ የሚያቀርብ ትምህርት ስለማይሰጡ ምእመናን በአሳዘኝ ሁኔታ ዳግም ሳይቀርቡ ያልፋሉ። ከሁሉም በላይ ትኩረት ሊሰጥበት የሚገባ ጉዳይ ነው። ግብጻውያን ከኢትዮጵያውያን የተሻሉ ቅዱሳን ሆነው ወይም እኛ የበለጠ ኃጥያተኞች ሆነን ነው ወይ እነርሱ 90%ቱ ምእመን ሲቆርብ እኛ 90%ቱ የማይቆርበው? እንደእኔ ብዙ ያልተጻፉ የይመስላል ህጎችም በምእመናን አዕምሮ ውስጥ ስላሉ ነውና በዘመቻ መልክ ትኩረት ተሰጥቶት ግልጽ ያለ ትምህርት እየተሰጠ ሰው ወደ ቁርባን መቅረብ አለበት። ሥጋዬን ያልበላ ደሜን ያልጠጣ የዘለዓለም ሕይወጥ የለውም ብሎናልና።

  ReplyDelete
  Replies
  1. (ሚስጢረ ተዋህዶ)??? "ይሁዳ ጌታን በመሳም አሳልፎ በመስጠቱ ምክንያት መሳሳም መከልከል የለበትም።"...ይህን ከምን አንጻር እንዳልክ ባይገባኝም ሰርዓቱ አንተ ከምታስበው በላይ ትርጉምና አንድምታ ያለው በመሆኑ ጠይቆ መረዳት ይገባል፡፡ "መሆን ያለበት ሰዎች የፍቅር /የእውነት ሰላምታ ቢለዋወጡ ነው።" ትክክል!! ይህን ለማድረግ ግን ሰዎች ራሳቸውን እንዲመረምሩ ይህን በመሰለ ደገኛ ስርዓት ማስተማር እንጂ ስርዓቱን መለወጥ አይደለም የክርስቲያኖች ምኞታችን፡፡ ..."የይሁዳ ሰላምታ አሳልፎ የመስጠት ወይም የውሸት መሆኑ እንጂ ችግሩ ሰላምታ በራሱ ችግር የለውም እንደውም ያስፈልጋል ምክንያቱም ሰላምታ አለመለዋወጥ በራሱ የይዳን ግብር አይቃረንም። ተቃራኒው በፍቅር መሳሳም ነውና"...ስለ እውነት እንነጋገር ከተባለ ሁሉም ወንድሙን አሳልፎ ለሚሰጥበት ለዛሬ ሰላምታ አንድ ሳምንት ቢያንስ እንጂ አይበዛበትም፡፡ እውነተኛና በወንድማማች ፍቅር የተሞላ መሳሳምን ሊያደርግ የሚወድ የጌታችንን ህማማት ከልቡ እያሰበ፣ እራሱን እየመረመረ ቢሰነብትና የብሉይ ኪዳንን የጨለማ ዘመን ምሳሌ አሳልፎ በትንሳኤው ብርሃን አማናዊውን መስዋዕት ስጋ ወደሙን በልብ ትህትና ተቀብሎ በመንፈስ ቅዱስ በተቃኘ መንፈሳዊ ሰላምታ ደስታና ፋሲካ ቢያደርግ ተገቢ ነው፡፡ ከዚህ በተረፈ ግን እኛ መማር፣መለወጥ ሲያቅተን ስርአቱን መቃወም ትክክል አይደለም፡፡ ትህትናን እንማር፡፡ ምህረትን እንለምን፡፡ ወደ ልባችን እንመለስ፡፡ የኛን ህይወት መለወጥ የሚችል የአባቶቻችን አምላክ ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም ያድርሰን፡፡

   Delete
 47. ምነው ኃየሎም የዘጉ፣ አልፎ አልፎ የሚበሉ፣ የሚበሉትን የማይመርጡ፣ ጨርሶ እህል የማይበሉ ቅዱሳን ባሉባት ሀገርና ቤተክርስቲያን እየኖርክ ባመት ሶስት ቀን ስለማይበሉ ሰዎች ገረመህሳ? ህጉ ሁለት ቀን ቢልም እነሱ ችለው 5 ቀንም ቢጾሙ እሰየው ነው። እንደዚህ አይነቶቹ አትራፊ ነጋዴዎች ይባላሉ/ትሩፋት/። እንሂን ያብዛልን ነው የሚባለው ጃል መፍራት ጾም አያስፈልግም የሚሉትን ነው። ይልቅ እንደዚኞቹ ለመሆን እንቅና/አብዝተው እንደሚጾሙቱ/።

  ReplyDelete
 48. please tell me about this is geez

  ReplyDelete
 49. አናመሰግናለን ዲ/ን ዳንኤል ክብረት (ታኦስ)የሚለው የግሪክ ቃል ቴኦስ በሚለው
  ቢስተካከል መልካም ነው

  ReplyDelete
 50. ቃለ ህይወት ያሰማልን ወንድማችን ብሎግህ ልእኛ ጥሩ የትምህርት ምንጭ ነው

  ReplyDelete
 51. Kale heyweten yasemalen bedema besega yetbkelen

  ReplyDelete
 52. let the sprite of God be with you, but i do like to say stay away from political activity you are created to teach Christianity.

  ReplyDelete
 53. እመቤቴ አብዝታ አብዝታ ትባርክህ ወንድማአለም ኑርልን አንጣህ ቃለህይወት ያሰማልን! ዲ/ን ኪርዬ ኤሌይሶን/ አቤቱ ማረን!!!

  ReplyDelete
 54. Egiziabher edmena tena yistlign! Kale hiwot yasemalign!

  ReplyDelete
 55. ዲ/ን ዳነኤል ቃለ ህይወት ያሰማልን በሰሞ ህማማት ሊተውና ሊደረጉ የሚገባቸው ብለህ ያስቀመጥካቸው ጥሩ አስተማሪ ናቸው እድሜውንና ጸጋውን ይስጥህ

  ReplyDelete
 56. የእድሜና የፀጋ የጤና ጌታ ከሞላው ቤተሰቦችህ ጋር አይለይህ ።በርታ!

  ReplyDelete
 57. ቃለ ሕይወት ያሰማልን ።

  ReplyDelete