አንድ ጊዜ አንድ የሮም የጦር መሪ ወደ አንድ የአይሁድ ከተማ ይገባል፡፡ የከተማዋን ሕዝብም ወደ አንድ የማጎርያ ሥፍራ ይሰበስባቸዋል፡፡ የከተማዋ ቤቶች አንድ ሳይቀሩ እንዲቃጠሉ ለወታደሮቹ ትእዛዝ ይሰጣል፡፡ በዚያ ጊዜ ሕዝቡ በቤቶቹ ውስጥ ያለውን ሀብት ለማውጣት ለመነ፡፡ የሮም ወታደሮች ግን አልፈቀዱም፡፡ የሕዝቡ ልመና እየበዛ ሲሄድ የወታደሮቹ አለቃ አንድ ነገር ፈቀደ፡፡ ሕዝቡ ሁሉ ተስማምቶ አንድ እጅግ የሚፈልጉትን ነገር ብቻ እንዲያወጡ፡፡ ሕዝቡ ተተራመሰ፡፡ አንዱ አንድ ሌላውም ሌላ ይላል፡፡ ከዚያ ሁሉ ሀብት መካከል አጅግ አስፈላጊ የሆነውን ነገር መርጦ ማውጣት አስቸጋሪ ሆነ፡፡ ማንንም የሚያስማማ ሀሳብ ማግኘትም አልተቻለም፡፡
ረቢው ወደ ሕዝቡ ሲመለሱ አንዳች የሚታይ ነገር አልያዙም፡፡ ወደ ወታደሮቹ አለቃ ሄደው አንዲት ያረጀች በብራና የተጻፈች መጽሐፍ መሳይ ነገር አሳዩት፡፡ የወታደሮቹ አለቃ ስቆ አሰናበታቸው፡፡ እናም ከተማዋ ተቃጠለች፡፡
የከተማዋ ሕዝብ በጉዳዩ ላይ በጣም በመበሳጨቱ ረቢውን ሊገድላቸው ተነሣ፡፡ ስንት የወርቅ እና የብር ሀብት እያለ፡፡ ስንት በከበሩ ድንጋዮች ያጌጠ ሀብት እያለ አንዲት ያረጀች ብራና ይዘው በመምጣታቸው በምርጫችን ተሳስተናል አለ፡፡
ወታደሮቹ ከተማዋን አቃጥለው ሲሄዱ የከተማዋ ሰዎች ሜዳ ላይ ፈስሰው ረቢውን ጠየቋቸው፡፡ ለምን? ሲሉ፡፡
ረቢው እንዲህ አሉ፡፡ «አዎን በከተማዋ ለዓይን የሚያጓጓ ብዙ ሀብት አለ፡፡ ወርቅ አለ፡፡ ብር አለ፡፡ የከበሩ ድንጋዮችም አሉ፡፡ የሐር ልብሶች አሉ፡፡ ከተልባ እግር የተሠሩ ልብሶች አሉ፡፡ የጌጥ ዕቃዎች አሉ፡፡ ሁሉም አሉ፡፡ ይህ ግን ከሁሉ ይበልጣል፡፡
«እንዴት?» አለ ሕዝቡ፡፡
«እነዚያ ያለቁ ነገሮች ናቸው፡፡ አንድ ጊዜ ይሸጣሉ፤ ይበላሉ፡፡ ያልቃሉ፡፡ ለጊዜያዊ ችግር ይሆናሉ፡፡ እኛን ከረሃብ ያላቅቃሉ፡፡ ነገር ግን አያዘልቁንም፡፡ ሰው የሚበላ ብቻ አይደለም፡፡ የሚጠጣም ብቻ አይደለም፡፡ ሰው ማለት ሁለት ነገር ነው፡፡ መንፈስ እና ሥጋ፡፡ ሥጋ ማለት ምንድን ነው? ሥጋ ውሱን ነው፡፡ በቦታ፣ በጊዜ እና በዐቅም ይወሰናል፡፡ መንፈስስ? መንፈስ ግን አይወሰንም፡፡ መንፈስን በአንድ እሥር ቤት ልትወ ስነው አትችልም፡፡ ወደ ላይ ወደ ምጥቀቱ፤ ወደ ታችም ወደ ጥልቀቱ ይወርዳል፡፡ መንፈስ ሀገር የለውም፡፡ ይዋኛል፡፡ ይቀዝፋል፡፡ መንፈስን በጊዜ አትገድቡትም፡፡ ወደ ኋላ ወደ ትናንት፣ ወደ ፊት ወደ ነገ ይጓዛል፡፡ ሥጋን በአንድ ቅርጽ ብቻ ማኖር ይቻላል፡፡ በአንድ ሞላላ ቤት፤ በአንድ አራት መዓዝን ቤት፤ በአንድ ጉድጓድ ማር ይቻላል፡፡ መንፈስን ግን በአንድ ቅርጽ ማኖር አይቻልም፡፡
ለተወለደ ልጅ ስም ይወጣል እንጂ ለወጣ ስም እንዴት ልጅ ይወለዳል? ዳዊት የሚባል ስም አውጥቶ እንዴት እንደ ዳዊት ያለ ልጅ ለመውለድ ይቻላል? መንፈስን በቅርጽ መወሰን እንዲህ ነው፡፡ ማሰብ ያለብህ እንዲህ ያለ አስተሳሰብ ነው፤ አንተ የዚህ ወይንም የዚያ ቡድን አመለካከት አለህ፤ አንተ ይህንን ወይንም ያንን ብቻ ሁን ማለት አይቻልም፡፡ መንፈስ ነጻነትን ይፈልጋል፡፡ ዓይኑን ጨፍኖ ወደ ውስጥ፣ ዓይኑንም ገልጦ ወደ ውጭ መጓዝ ይሻል፡፡
«እዚህ ውስጥ ወርቅ ወይንም ብር የለም፡፡ እዚህ ውስጥ ሀሳብ አለ፡፡ ሰውን ሰው የሚያደርግ ሃሳብ አለ፡፡ ሰው ለሕልውናው ዓላማ እንዲኖረው፡፡ የሚኖርበት ምክንያት እንዲኖረው፤ ሰው ከመብላት እና ከመጠጣት በላይ ማሰብ እንዲችል፡፡ ሰው ከመኖር በላይ ማሰብ እንዲችል፡፡ ሰው ከችግሮቹ በላይ መኖር እንዲችል፡፡ ለነገ ሲል ዛሬን፣ ለጭንቅላቱ ሲል ሆዱን፣ ለነፍሱ ሲል ሥጋውን፣ ለሌላው ሲል ራሱን መሠዋት እንዲችል የሚያበቃ ሃሳብ አለ፡፡
«ይህ ሃሳብ ሲሞት ያን ጊዜ ከተማችን ፈጽማ ትጠፋለች፡፡ ይህ ሃሳብ ካልሞተ ግን ዘጠኝ ጊዜ ብትጠፋ እንኳን አሥር ጊዜ አብልጠን እንገነባታለን፡፡ ይህ ሃሳብ ከሞተ ሆዳችን አድጎ ጭንቅላታችን ይቀጭጫል፡፡ ይህ ሃሳብ ካልሞተ ግን ሆዳችን ቀጭጮ ጭንቅ ላታችን ያድጋል፡፡ ይህ ሃሳብ መቶ ሀገራችን ሀብታም ትሆን ይሆናል፡፡ ነገር ግን ሆዳሞች የሞሉባት ሀብታም ሀገር ትሆናለች፡፡ ሆዳሞች ደግሞ መጀመርያ የሀገራቸውን ሀብት ይበላሉ፡፡ ቀጥለው ሕዝባቸውን ይበላሉ፡፡ በመጨረሻም እርስ በርሳቸው ይበላላሉ፡
ያለ ሃሳብ ከመሠልጠን፣ ያለ ሥልጣኔ ማሰብ ይሻላል፡፡ ያለ ሃሳብ መሠልጠን ያለ ልክ የተሰፋን ልብስ መልበስ ነው፡፡ ሰውዬው እየወፈረ ይሄድና ልብሱን መቅደዱ አይቀርም፡፡ ልብሱ ለሰውዬው እንጂ ሰውዬው ለልብሱ ሊሰፋ አይችልምና፡፡ ያለ ሃሳብ መሠልጠን ሰውዬውን ለልብሱ እንደማዘጋጀት ያለ ነው፡፡ ሰውዬው ከልብሱ በላይ እንዳይሆን ወይ ታስርቡታላችሁ፣ ያለከበለዚያም በወፈረ እና በረዘመ ቁጥር ትቀንሱታላችሁ፣ ያለበለዚያም ውፍረቱን እና እድገቱን ለመቀነስ ሌላ ቅጣት ትቀጡታላችሁ፡፡
ሃሳብ የሌለበት ዕድገት እና ሥልጣኔ እንደዚህ ነው፡፡ ሰው ምንም ቢሆን ማሰቡን አይተውም፡፡ ያለ ሰው የሚኖር ሃሳብ፣ ያለ ሃሳብ የሚኖርም ሰው የለም፡፡ ስለዚህ ለኛ ሃሳብ ይበልጥብናል፡፡ ይህ መጽሐፍ ከኛ በፊት የነበሩ ሰዎች ያሰቡትን፤ በዘመናችን ያላችሁ ሰዎች ያሰባችሁትን ነገር ይዟል፡፡ ለሀገር ትልቁ ሀብቷ ሃሳቧ ነው፡፡ በሀገር ዋናዎቹ ሰዎች ቀድመው እና ልቀው ማሰብ የሚችሉ ዜጎቿ ናቸው፡፡ የበቁ አሳቢዎች የበቁ መሪ ዎችን መፍጠር ይችላሉ፤ የበቁ መሪዎች ግን የበቁ አሳቢዎችን መፍጠር አይችሉም፡፡
አሳብ እና አሳቢ የሞተባት ሀገር ወይ ሞታለች፣ ወይ ለመሞት ተዘጋጅታለች፡፡ እናም ወዳጆቼ አትዘኑ፡፡ ሃሳባችሁን የወሰደባችሁ የለም፡፡ ማሰብ ከቻላችሁ ዓለም ሁሉ የናንተ ናት፡፡ ከሀገር የሚበልጥ መቼም የለም፡፡ ሀገርንም ቢሆን እንኳን የሚፈጥራት ሀሳብ ነው፡፡ ያለ ሃሳብ በሀገር ከመኖር፣ ያለ ሀገር እያሰቡ መኖር ይበልጣል፡፡ ማሰብ ካልቻላችሁ ግን በጣታችሁ ያለው ቀለበት እንኳን የእናንተ አይደለም፡፡ ለዚህ ነው ይቺን መጽሐፍ የመረጥኳት፡፡
እንዳትበሉ የሚከለክሏችሁ፣እንዳትኖሩ የሚከለክሏችሁ፣ እንዳትሠሩ የሚከለክሏችሁ ብዙም አይጎዷችሁም፡፡ እነርሱ እንስሳነታችሁን ነው የከለከሏችሁ፡፡ እንዳታስቡ የሚከልክሏችሁ ግን አደገኞች ናቸው፡፡ ምክንያቱም የከለከሏችሁ ሰውነታችሁን ነውና፡፡»
ይህንን ታሪክ ሳነብ አንዲት የሮም ልዕልት ያለችው ትዝ አለኝ፡፡
ልዕልቲቱ በተንጣለለው የባዛንታይን ቤተ መንግሥት የምትኖር ሁሉ በእጇ ሁሉም በደጇ የሆነች ልዕልት ነበረች፡፡ እንኳን የተናገረችው የተመኘችው ሁሉ የሚደረላት፡፡ ቀን እና ሌሊት ዙርያዋን ከብበው ዓይን ዓይኗን የሚያዩ እልፍ ደንገጡሮች ያሏት፡፡
አንድ ጊዜ ከአንዲት የልብ ወዳጇ ከሆነች ደንገጡር ጋር ተማክራ ከቤተ መንግሥቱ ጠፋች፡፡ የት ሄደች ተብሎ ሀገሩ በሙሉ ታሰሰ፡፡ ልትገኝ ግን አልቻለች፡፡ በመጨረሻ በስንት ፍለጋ ፋርስ ውስጥ በሚገኝ አንድ ገዳም ውስጥ መኖርዋ ተሰማና አያሌ ወታደሮች ተላኩባት፡፡ የወታደሮቹን መምጣት ስትሰማ ራስዋን በራስዋ ለማጥፋት መርዝ አዘጋጀች፡፡
ይህንን የተረዱት ወታደሮች ግራ ተጋቡ፡፡ አባቷ በመሞቷ ያዝናል ብለው ስላሰቡ መልእክት ላኩበት፡፡ አባቷም ሊያግባቧት የሚችሉ ወይዛዝርትን ላከባት፡፡ እነዚያም ወይዛዝርት ወዳለችበት ቦታ ገብተው ጠየቋት፡፡
«በአባትሽ ቤት ሁሉም ሞልቷል፡፡ የጎደለሽ ነገር የለም፡፡ ያንን የመሰለ ቤተ መንግሥት ትተሽ እንዴት እዚህ የድኾች መንደር ውስጥ በችጋር ትኖሪያለሽ?»
«አዎ በአባቴ ቤት ሁሉም ነገር አለ፡፡ ከአንድ ነገር በቀር» አለቻቸው፡፡
«ንገሪን ያንን ነገር በአስቸኳይ እናሟላልሻለን» አሏት፡፡
«እዚያ ማሰብ የለም» አለችና መለሰችላቸው፡፡
ወይዛዝርቱ እጅግ አዝነው «እዚያኮ ሁላችንም ላንቺ እናስባለን፡፡ አባትሽ፣ እናትሽ፣ አገልጋዮችሽ ሁሉ ስላንቺ ያስባሉ» እያሉ ማስረዳት ጀመሩ፡፡
«እኔ» አለች ልዕልቷ «እኔ የምፈልገው የሚያስብልኝ አይደለም» አለቻቸው፡፡
«ታድያ»
«እንዳስብ የሚፈቅድልኝ ነው» አለቻቸው ይባላል፡፡
ከረቢው ታሪክ በኋላ አንድ ግጥም አለ፡፡ እኔ ግን በሀገሬ ቋንቋ ስመልሰው እንዲህ ብዬዋለሁ
ሥልጣኔ ቢሞት በሃሳብ ይነሣል
ኢኮኖሚ ቢሞት በሀሳብ ይነሣል
ፖለቲካ ቢሞት በሀሳብ ይነሣል
ሃሳብ የሞተ ዕለት ወዴት ይደረሳል፡፡
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ በመሆኑ በተመሳሳይ ኅትመት ላይ ባታውሉት ይመረጣል፡
አዎን ሃሳብ የሞተ እለት ሰው ከሌሎች እንስሳት ይተካከላል
ReplyDeleteአዎን ሃሳብ የሞተ እለት ሰው ከሌሎች እንስሳት ይተካከላል
ReplyDeleteበዋልድባ ጉዳይ የጻፍከውን ጽሑፍ ያነበበ ሰው ጥሩ እንደነበረ ነግሮኛል፡፤ ነገር ግን እኔ ማግኘት አልቻልኩም፡፡
ReplyDelete"ዶሮን ሲያታልሏት፤ በመጫኛ ጣሏት።" አሉ ጋሽ ... ወንድማችን እኮ 'ገዳማዊ' ብቻ ሳይሆን 'ልማታዊ' ጦማሪ ነው። ምነው አኖኒመስ የዋልድባን ጉዳይ 'መነካካት' አይገባም ።(አራት ነጥብ)
Deleteወንድሜ ባክህ በማስተዋል ተናገር! ማለቴ ጻፍ!!! በመጀመሪያ ያንተንና የዲ/ዳንኤልን ድርሻ ተረዳ!!!!! ይህ መድረክ የዳንኤል እይታ ነው!!! አንተ ያለ ሃሳብ እየኖርክ ይሄ ምስኪን ሁሉን አስቦ ይዘልቀዋል እንዴ??? ስለ ሃገር ፖለቲካና ስለቤተክርስቲያን ጽፎ መታሰር እኮ የብሎገሮች ፍርጃ አይደለም!!! ዎንድ ማለት ባገኘኽው አጋጣሚ ሁሉ አንተ ራስህ እውነትን መመስክር እንጅ የትም ተወሽቀህ አሉን ያልናቸውን ሰዎች ሃሳብ በሌላቸው መሪዎች ልታስበላ ጃዝ ጃዝ አትበል!!! ለብቻህ አትሰብ !!! አንተ የዳኒን ሀሳብ እንደጠላሀው መጠን የምንወድለትም አለን!!!! ክርስቲያን ከሆንክ የቤተክርስቲያንን ድህነት ከሰማይ ጠብቅ! በዋልድባ ላይ የጻፈው ከበቂ በላይ ነው!!! ችግሩ ልክ እንዳንተ ሁሉ የዋልድባም ጠላቶች በተደፈነ አይምሮ ስለሚያነቡት መሆኑ ብቻ ነው!!!! ፖሊስ ባጠገብህ ባለፈ ቁጥር ልብ ድካምህ የሚነሳብህ ሰው ሁነህ ሳለህ ሰው እንዲታሰር ትሻለህ!! ውነት አሁን ዳኒ ቢታሰር ምን ልትፈይድለት ነው??? በሃዘን እንኩዋ የእንባ ስንቅ አትሰጠውም!!! እንዳንተ አይነቱ ኢትዮጵያዊ ምን እንደሚያስብ እናውቃለን!!! እንደ ጌታ ሃዋርያት ተበታትነህ ልትጠፋቅጥህ ዐይዞህ አይዞህ አትበል!!!! ዳኒየ ሃሳብ የለሽ ይሉሃል እንዲህ ነው!!! አቤቱ ስውነታችንን ከሚጠያፍኑ ሁሉ ይሰውረን!!!!!
Deleteወንድሜ ባክህ በማስተዋል ተናገር! ማለቴ ጻፍ!!! በመጀመሪያ ያንተንና የዲ/ዳንኤልን ድርሻ ተረዳ!!!!! ይህ መድረክ የዳንኤል እይታ ነው!!! አንተ ያለ ሃሳብ እየኖርክ ይሄ ምስኪን ሁሉን አስቦ ይዘልቀዋል እንዴ??? ስለ ሃገር ፖለቲካና ስለቤተክርስቲያን ጽፎ መታሰር እኮ የብሎገሮች ፍርጃ አይደለም!!! ዎንድ ማለት ባገኘኽው አጋጣሚ ሁሉ አንተ ራስህ እውነትን መመስክር እንጅ የትም ተወሽቀህ አሉን ያልናቸውን ሰዎች ሃሳብ በሌላቸው መሪዎች ልታስበላ ጃዝ ጃዝ አትበል!!! ለብቻህ አትሰብ !!! አንተ የዳኒን ሀሳብ እንደጠላሀው መጠን የምንወድለትም አለን!!!! ክርስቲያን ከሆንክ የቤተክርስቲያንን ድህነት ከሰማይ ጠብቅ! በዋልድባ ላይ የጻፈው ከበቂ በላይ ነው!!! ችግሩ ልክ እንዳንተ ሁሉ የዋልድባም ጠላቶች በተደፈነ አይምሮ ስለሚያነቡት መሆኑ ብቻ ነው!!!! ፖሊስ ባጠገብህ ባለፈ ቁጥር ልብ ድካምህ የሚነሳብህ ሰው ሁነህ ሳለህ ሰው እንዲታሰር ትሻለህ!! ውነት አሁን ዳኒ ቢታሰር ምን ልትፈይድለት ነው??? በሃዘን እንኩዋ የእንባ ስንቅ አትሰጠውም!!! እንዳንተ አይነቱ ኢትዮጵያዊ ምን እንደሚያስብ እናውቃለን!!! እንደ ጌታ ሃዋርያት ተበታትነህ ልትጠፋቅጥህ ዐይዞህ አይዞህ አትበል!!!! ዳኒየ ሃሳብ የለሽ ይሉሃል እንዲህ ነው!!! አቤቱ ስውነታችንን ከሚጠያፍኑ ሁሉ ይሰውረን!!!!!
Deletetks dani intresting article e/r yagelgilot zemenhen yabzalih
ReplyDeleteእንዳትበሉ የሚከለክሏችሁ፣እንዳትኖሩ የሚከለክሏችሁ፣ እንዳትሠሩ የሚከለክሏችሁ ብዙም አይጎዷችሁም፡፡ እነርሱ እንስሳነታችሁን ነው የከለከሏችሁ፡፡ እንዳታስቡ የሚከልክሏችሁ ግን አደገኞች ናቸው፡፡ ምክንያቱም የከለከሏችሁ ሰውነታችሁን ነውና፡፡
ReplyDelete«እንዳስብ የሚፈቅድልኝ ነው» አለቻቸው ይባላል፡፡
thank you Dn.Daniel
God bless you Dn. Daniel. It is right. Where there is no thought or mind there is no humanity. We lose our personality.
ReplyDeleteእግዚአብሔር ይስጥልን:: አዎ እኛም በሃገራችን እንዳናስብ ነው እየተከለከልን ያለነው:: ማሰብ መናገር ማንበብ መስማት ወንጀል ከሆነ ቆየ በሃገራችን:: አሁን ደሞ ባሰና የሚበሉትን እንድንመለከትና እንድናድር ከተፈረደብን ከራረመ:: ተስፋ የምናደርገው የኢትዮጵያ አምላክ ፍርዱን ይስጠን እንጂ ሌላ ምን እንላለን?
ReplyDeleteይቺን አዲስ ጉዳይ መጽሄት ግን ባጠራቅማት ብዬ አሰብኩ ያንተን ጽሁፎች ለመሰብሰባና ለልጄ ባቆይለት::
ewenate nawe
ReplyDeletekala heiwate yasamalen
So touching dani, this what i call FREEDOM.
ReplyDeleteእንዳትበሉ የሚከለክሏችሁ፣እንዳትኖሩ የሚከለክሏችሁ፣ እንዳትሠሩ የሚከለክሏችሁ ብዙም አይጎዷችሁም፡፡ እነርሱ እንስሳነታችሁን ነው የከለከሏችሁ፡፡ እንዳታስቡ የሚከልክሏችሁ ግን አደገኞች ናቸው፡፡ ምክንያቱም የከለከሏችሁ ሰውነታችሁን ነውና፡፡»መልካም እይታ! ከማሰብ ነጻነት የሚበልጥ ነገር የለም፡፡ ፀጋዉ ይብዛልህ ዲ/ን፡፡
ReplyDeleteNIce article!EgziAbHer Yistilin!!.
ReplyDeleteግሩም ብለሃል ወንድም ዳንኤል! በኔ እይታ በሀገራችን ሀሳብ የተናቀች አሳቢዎችም ጥቂት እና የተረሱ ይመስለኛል:: ብዙው ለአዲስ ዕቃ እንጂ ዕቃውን ላበጀው ሀሳብ ደንታ የለውም:: (my reference is common sense) ዳሩ ነፃነት የማይሠማው ሕዝብ እንዴት ይፈረድበታል?
ReplyDeleteሰው ማለት ሁለት ነገር ነው፡፡ መንፈስ እና ሥጋ፡፡ ሥጋ ማለት ምንድን ነው? ሥጋ ውሱን ነው፡፡ በቦታ፣ በጊዜ እና በዐቅም ይወሰናል፡፡ መንፈስስ? መንፈስ ግን አይወሰንም፡፡ መንፈስን በአንድ እሥር ቤት ልትወ ስነው አትችልም፡፡ ወደ ላይ ወደ ምጥቀቱ፤ ወደ ታችም ወደ ጥልቀቱ ይወርዳል፡፡ መንፈስ ሀገር የለውም፡፡ ይዋኛል፡፡ ይቀዝፋል፡፡ መንፈስን በጊዜ አትገድቡትም፡፡ ወደ ኋላ ወደ ትናንት፣ ወደ ፊት ወደ ነገ ይጓዛል፡፡ ሥጋን በአንድ ቅርጽ ብቻ ማኖር ይቻላል፡፡ በአንድ ሞላላ ቤት፤ በአንድ አራት መዓዝን ቤት፤ በአንድ ጉድጓድ ማር ይቻላል፡፡ መንፈስን ግን በአንድ ቅርጽ ማኖር አይቻልም፡፡
ReplyDeleteሥጋ ማለት ምንድን ነው? ሥጋ ውሱን ነው፡፡ በቦታ፣ በጊዜ እና በዐቅም ይወሰናል፡፡ መንፈስስ? መንፈስ ግን አይወሰንም፡፡ መንፈስን በአንድ እሥር ቤት ልትወ ስነው አትችልም፡፡ ወደ ላይ ወደ ምጥቀቱ፤ ወደ ታችም ወደ ጥልቀቱ ይወርዳል፡፡ መንፈስ ሀገር የለውም፡፡ ይዋኛል፡፡ ይቀዝፋል፡፡ መንፈስን በጊዜ አትገድቡትም፡፡ ወደ ኋላ ወደ ትናንት፣ ወደ ፊት ወደ ነገ ይጓዛል፡፡ ሥጋን በአንድ ቅርጽ ብቻ ማኖር ይቻላል፡፡ በአንድ ሞላላ ቤት፤ በአንድ አራት መዓዝን ቤት፤ በአንድ ጉድጓድ ማር ይቻላል፡፡ መንፈስን ግን በአንድ ቅርጽ ማኖር አይቻልም፡፡
ReplyDeleteWow,fantastic!egziyabher yesetlen,serahen yebarekew tweld endilewetna endiyasseb yemetadergachewn zerfe bezu serawochehen ejeg wedejiyalew,dani egzyabeher yebarkeh!
ReplyDeleteልክ ብለዋል…መምህር
ReplyDeleteTsegawun Yabizalih...Amen
ReplyDelete“አስቡ! አስቡ!” የምትለን ልታስበላን ነው? ያሰቡት የት ደረሱ? ሀገራችሁ ኢትዮጵያ ማሰብ የሚፈቀድባት ሀገር ናት? ንባቤና ኑሮዬ በጋራ እንደሚመሰክሩልኝ ኢትዮጵያ አሳቢዎቿን ሲቻል በጥይት፣ ጥይት ከጠፋ በደንጊያ፣ እርሱም ካልተቻለ በሽሙጥና በሳቅ ስላቅ፣ ይህ ከተከለከለ ደግሞ በሐሜት የምትገድል፤ በመግደሏም ብርሃን እንደወረደላት፣ አብዮቷ እንደተራመደላት፣ ዴሞክራሲዋ እንደተስፋፋላት የሚታተትባት ሀገር አይደለችምን? ነገሮች ጥቁር ወይም ነጭ ካልሆኑ በስተቀር ሌላ ቀለም እንዲይዙ የማይፈቀድባት፣ “ከእኛ ጋር ካልሆንህ ከጠላቶቻችን ጋር ነህ!” ተብሎ ፍርድ የሚገመደልባት ሀገር ውስጥ እየኖርን መሆኑን ረሳኸው? እውነት ተናግረን በእውነት ነጻ ከምንወጣና አዲስ ከማናውቀው ዓለም ጋር ከምንጋፈጥ እንዲሁ በውሸት ውስጥ እየተጨማለቅን ብንኖር የምንመርጥ አይደለንምን? የምናውቀው ሰይጣን ከማናውቀው መልአክ የሚበልጥብንስ እኛ አይደለንምን? ቀን እስኪያልፍ የአባቴ ባሪያ እንዲገዛኝ አንገቴን አቀርቅሬ መኖር የምመርጥ እኔ ኢትዮጵያዊው አይደለሁም? ቀንና ቅዝምዝምን ቀና ብዬ አይቼ ከመመከት ይልቅ ጎንበስ ብዬ ራሱ ጊዜ እንዲያሳልፈው የምተወውስ እኔ አይደለሁ እንዴ? ጊዜ ያመጣውን ጊዜ እንዲመልሰው የምወድ ጊዜ ሲያልፍ ከዕድሜዬ ላይ እየሸራረፈ ይዞ እንደሚኼድ የማላስተውል እኔ አይደለሁ? ቀና ብሎ ከመኖር ጎንበስ ብሎ መሞትን የሚመርጠውስ ማን ሆነና? ሉሲ ዘመዴ ቀጥ ብላ በመኼዷ ምን አገኘች? ይኸው አጥንቷ እንኳ ዕረፍት አጥቶ ሀገር ለሀገር ይዞር የለ? እንዴት እኔን ኢትዮጵያዊውን አስብ ትለኛለህ? አትወድደኝም ማለት ነው? እኔ የሐሳብ ነጻነት አልራበኝም፡፡ እርሱን ለመራብማ ሰው መሆኔን ማመነን ያሻኛል፡፡
ReplyDeleteተወኝ አቦ! እየየም ሲዳላ ነው አለ ያገሬ ሰው! ሰው መሆን ቅንጦት ነው፡፡ የነጻነት ጠኔ የጨካኝ ሰው ጫማ ላይ እንጂ በረኀብ አንደፋድፎ መቃብር ላይ ሲደፋ አላየነውም፡፡ ስለዚህ ተው! አስብ አትበለኝ! ሳልኖር ልሙትበት!
በነገራችን ላይ ከላይ ሀይለ ልዑል የተባለው አስተያየት ሰጪ “ለአዲስ ዕቃ እንጂ ዕቃውን ላበጀው ሐሳብ ቦታ ደንታ የሌለው” ሲል የገለጠውን ትዝብቱን የዛሬ ሰማኒያ ዓመት ገደማ ራስ እምሩ ኃይለ ሥላሴም ታዝበውት ነበረ፡፡ የእርሳቸው ትዝብት ከንጉሥ ተፈሪ ጋር አብረው አውሮፓን የጎበኙት መኳንንት አውሮፓ ውስጥ ተሠርቶ ያዩትን ነገር ሁሉ የሰው ልጅ ሥራ ውጤት መሆኑን ትተው እንደተአምር ዕፁብ! ዕፁብ! ብለው እንዴት እንደተሠራ አንዳቸው እንኳ ሳይጠይቁ መቅረታቸውን ነው፡፡ የሕይወት ታሪካቸውን እንድታነብና እንድትቃጠል ጋብዤሃለሁ፡፡
Endih yemiasbna yemitsif ,tsifom letikitochachin bihonim yemiaderse yeseten Amilak yikiber yimesgen yewondimachinm yagelilot zemen yibarkiln ,wagawin yikfeliln.AMEN!
ReplyDeleteእግዚአብሄር የተመሰገነ ነው! ባንተ ምክኒያት እውቀትን በልባችን ዉሰጥ ሰወርን! የተጠራጠርነውን አረጋገጠን!
ReplyDeleteከእስላም ቀበሌ ወልድያ/ወሎ
የዋልድባ ነገር አለመነካካት ያልከዉ ወንድሜ ክርስቲያን ከሆንክ ትእግስትን ገንዘብ ማድረግ አለብህ፡፡ ለራስህ ትእግስተኛ መሆን ካቃተህ ደግሞ የሰዉን ትእግስት ለማደፍረስ አትሞክር፡፡ እግዚአብሔር ምንግዜም ቤቱን ይጠብቃል እርሱ ካልጠበቀ ዲ/ን ዳንኤል ጽፎ አያድናትም፡፡ ተረፈ ባሮክን አንብብና አስተዉል እግዚአብሄር የእየሩሳሌምን ቅጥር በመላእክት ከፍቶ ለመላቶቿ እንዴት ተላልፋ እንደተሰጠች የእንድ ኤርሚያስና የባሮክ ጩኸት ከህዝቡ ሀጢያት ብዛት የተነሳ እንዳላዳናት ታስተዉላለህ፡፡ ስለዚህ እኛ ሁላችን አምላካችን ይቅር ይለን ዘንድ መጸለይ ይገባናል እንጅ በአንድ ሰዉ ላይ ጣት መቀሰር አያዋጣንም ወንድም!
ReplyDelete"በሬ ሆይ በሬ ሆይ፤ ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ"
Deleteስለዚህ 'ነብዩ ባሮክ ወደእግዚአብሔር መጮህ አልነበረበትም፤ ከንቱ ድካም ነው' እያልከን ነው?
who are you??? Of course you express your self as you are an ox!
DeleteThank you Dani.
ReplyDeleteየነፍሴ ጨዋታ እጅግ ልዩ የሆነ ሰውን እያሰደሰተ የሚያስተምር
ReplyDeleteብዙ ነገር ተማርኩበት አመሰግናለሁ ሁል ጊዜም ምንጊዜም እመአምላክ ከአንተ ጋር ትሁን
በጣም አከብርሀለውህ.
ኢ.አ
ጠጅ በብርሌ
ReplyDeleteነገር በምሳሌ...ይላሉ አባቶቻችን። አምላካችን እየሱስ ክርስቶስ ደግሞ የቄሳርን ለቄሳር የእ/ርን ለእ/ር...ይለናል። እንግዲህ ለዳኒ ጹሁፍ የሚሆን ጆሮ ያለው ይስማ!!
መሃበረ ቅዱሳን ግን ምነው ስለ ዋልድባ ሪፖርቱን አዘገየው? ንጉሱ ላቆመው የስኳር ምስል....
ምን ማህበረ ቅዱሳን ብቻ። ለምን ዲ/ን ዳንኤልስ ዝም ማለትን መረጠ? ወይስ ያ ሁሉ ጀግንነቱ እንደመንግስቱ ወኔ ተነፈሰ? ከንጉሱ ሃይለ ስላሴና ከዋልድባ ገዳም ለኢትዮጵያም፤ ለቤተክርስቲያንም ማን ይበልጣል?
DeleteFor Anonymous, you said where is Mahibere Kidusan and also where is Daniel?? You express your idea in relation to King Haile silassie. Why You get into contrasting two different things??? Please Please ......let me ask you... is there any tangible thing you did for our church ???? Why you don't write ??? are you not christian???? You may think that you are doing, if so where is your impact????
DeleteMASTEWAL
ስለ ዋልድባ መልስ የሰጠኸው ወንድሜ ክርስቲያን ከሆንክ ትእግስትን ብቻ ሳይሆን ለእግዚአብሔር ቤት ቀናኢነትንም መያዝ አለብህ:: "እንደርግብ የዋህ: እንደ እባብ ልባም" መሆን እንዳለብን ጌታችን አስተምሮናል:: በክርስትና እየኖርን አንዱን ብቻ መሆን አንችልም፤ ለድኅነትም አያበቃንም:: ከሰለስቱ ደቂቅ ሃይማኖትና ተጋድሎ መማር አለብን:: ለጣኦት አምላኪው ንጉስ ሰጥ ለጥ ብለው ይገዙ ነበር:: እስከመቼ? 'ለጣኦት ስገዱ' እስከሚባሉ ድረስ:: ከዚያ በኋላ ግን ሃይማኖታቸውን መግለጥ ግድ ሆነባቸው::
ReplyDeleteአንድ ክርስቲያን ለምድራዊ ንጉስ (በስጋው ብቻ)መገዛት እንዳለበት መጽሐፍ ቅዱስ ያዘናል:: ነገር ግን አንዲት የቀረችን የነፍሳችን ህልውና (ሃይማኖታችን) እስክትጠፋ መሆን የለበትም:: ይህ ትእግስት ሳይሆን 'ጅልነት' ነው::
አለበለዚያ እንደ ፈሪው ሰውዬ እንሆናለን (ጅብ ሌሊት መጥቶ እግሩን መብላት ሲጀምር ሚስቱ ሰምታ 'ምንድነው የሚንኮሻኮሸው?' ብትለው በሹክሹክታ 'ዝም በይ ጅቡ እግሬን እየበላኝ ነው' እንዳለው)
ወንድማችን እንዳልከው ይህ ሁሉ የማይቀር:የእግዚአብሔር ፈቃድ እንኳን ቢሆን እኛ ክርስቲያኖች አሰላለፋችንን መምረጥና ማስተካከል አለብን (ከእግዚአብሔር ጋር ነን ወይንስ በተቃራኒው?) መሃል ሰፋሪ መሆን አይቻልም:: በክርስትና የምንሰራው ስራ ጽድቅና ኩነኔው የሚለካው በምናመጣው ለውጥ (ውጤት) ብቻ ሳይሆን በአሰላለፋችን ጭምር ነው::
እስከዛሬ ብዙ ነገሮችን ሰርቶ ተጋድሎ ለቤተክርስቲያን በክፉ ቀኗ ያልደረሰላት (እጅግ ከባድና አንገብጋቢ፥ የሞት የሽረት ችግሯን ጆሮ ዳባ ልበስ ያለ) አገልጋይ ምን ይባላል?
በክርስትና ሕይወታችን በሙሉ ከእግዚአብሔርና ከቅዱሳኑ ጋር እንድንሆን እግዚአብሔር ይርዳን::
What about You ????? what are you doing??
Deleteሆዳሞች ደግሞ መጀመርያ የሀገራቸውን ሀብት ይበላሉ፡፡ ቀጥለው ሕዝባቸውን ይበላሉ፡፡ በመጨረሻም እርስ በርሳቸው ይበላላሉ፡
ReplyDeleteወንድሜ ለምን ያልተጻፈ ታነባለህ ነብዩ ባርክ መጮህ አልነበረበትም አላልኩም ደግሞም መራራ ጩኸትን ጩኋልም ነገር ግን ከባርክና ከኤርሚያስ እና ከ አቤሜልክ በቀር ሁሉ ግን አልጮሁም ስለዚህም ለመጥፋት በቅታለች ልክ ሰዶም 5 ጻድቃን አጥታ እንደጠፋችዉ፡፡ እግዚአብሄር ግን ወዳጆቹን ከጥፋት ሰዉሯል፡፡ ስለዚህ እኔም ያልኩት ሁላችን መጸለይ አለብን ሁሉን የሚሰራ እግዚብሄር ነዉ እንጂ የዲ/ን ዳንኤል ጡመራ ብቻ አይደለም ከሰዉ እራስ ላይ እንዉረድ ሁልጊዜ በየቤታችን ተቀምጠን የኛን ሃሳብ ሰዉ እንዲናገርልን አንጠብቅ እራሳችንንም አሳልፈን መስጠት ካለብን ከፊት ሁነን መናገር ነዉ እንጂ በሰዉ ጀርባ ተከልለን አይደለም ሰለስቱ ደቂቅም እኮ ‹‹ እግዚብሄር አምላካችን ነዉ ለጣኦት አንሰግድም ›› አሉ እንጂ ነብዩ ዳንኤልን ሂደዉ ምነዉ ዝም አልክ ለጣኦት እንደማንሰግድ አንተ ንገርልን አላሉትም ፡፡
ReplyDeleteልክ ብለሃል ወንድሜ። ሁላችንም የሚጠበቅብንን እናድርግ። እያደረግን ያለንም ሳናቋርጥ ወደእግዚአብሔርና ወደሚመለከተው ሁሉ ጩኸታችንን እናሰማ። ነገር ግን ከዚህ በፊት ለቤተክርስቲያናችን በክፉ ጊዜ መስዋዕት እስከ መሆን እንዳለብን ሲያስተምረንና በተግባርም ሲያሳየን የቆየው ወንድማችን ዛሬ የባሰ ከባድ ችግር ሲያጋጥም ሰምቶ እንዳልሰማ መሆኑ (ጆሮ ዳባ ልበስ ማለቱ) ያሳዝናል። ይባስ ብሎ ቤተክርስቲያንን ከሚያጠፋ መንግስት ጎን ተሰልፎ ሲያሞግስና ሲያወድስ ማየትና መስማት እጅግ በጣም ያሳምማል።
Deletewendemachen diyakon daiale kae hiowt yasemalen...kelay yetafekew megebar yale haymanot ...haymanot yale megebar ... be metaf bech hone wey?
ReplyDeleteማሰብ የታባቱ!
ReplyDelete“አስቡ! አስቡ!” የምትለን ልታስበላን ነው? ያሰቡት የት ደረሱ? ሀገራችሁ ኢትዮጵያ ማሰብ የሚፈቀድባት ሀገር ናት? ንባቤና ኑሮዬ በጋራ እንደሚመሰክሩልኝ ኢትዮጵያ አሳቢዎቿን ሲቻል በጥይት፣ ጥይት ከጠፋ በደንጊያ፣ እርሱም ካልተቻለ በሽሙጥና በሳቅ ስላቅ፣ ይህ ከተከለከለ ደግሞ በሐሜት የምትገድል፤ በመግደሏም ብርሃን እንደወረደላት፣ አብዮቷ እንደተራመደላት፣ ዴሞክራሲዋ እንደተስፋፋላት የሚታተትባት ሀገር አይደለችምን? ነገሮች ጥቁር ወይም ነጭ ካልሆኑ በስተቀር ሌላ ቀለም እንዲይዙ የማይፈቀድባት፣ “ከእኛ ጋር ካልሆንህ ከጠላቶቻችን ጋር ነህ!” ተብሎ ፍርድ የሚገመደልባት ሀገር ውስጥ እየኖርን መሆኑን ረሳኸው? እውነት ተናግረን በእውነት ነጻ ከምንወጣና አዲስ ከማናውቀው ዓለም ጋር ከምንጋፈጥ እንዲሁ በውሸት ውስጥ እየተጨማለቅን ብንኖር የምንመርጥ አይደለንምን? የምናውቀው ሰይጣን ከማናውቀው መልአክ የሚበልጥብንስ እኛ አይደለንምን? ቀን እስኪያልፍ የአባቴ ባሪያ እንዲገዛኝ አንገቴን አቀርቅሬ መኖር የምመርጥ እኔ ኢትዮጵያዊው አይደለሁም? ቀንና ቅዝምዝምን ቀና ብዬ አይቼ ከመመከት ይልቅ ጎንበስ ብዬ ራሱ ጊዜ እንዲያሳልፈው የምተወውስ እኔ አይደለሁ እንዴ? ጊዜ ያመጣውን ጊዜ እንዲመልሰው የምወድ ጊዜ ሲያልፍ ከዕድሜዬ ላይ እየሸራረፈ ይዞ እንደሚኼድ የማላስተውል እኔ አይደለሁ? ቀና ብሎ ከመኖር ጎንበስ ብሎ መሞትን የሚመርጠውስ ማን ሆነና? ሉሲ ዘመዴ ቀጥ ብላ በመኼዷ ምን አገኘች? ይኸው አጥንቷ እንኳ ዕረፍት አጥቶ ሀገር ለሀገር ይዞር የለ? እንዴት እኔን ኢትዮጵያዊውን አስብ ትለኛለህ? አትወድደኝም ማለት ነው? እኔ የሐሳብ ነጻነት አልራበኝም፡፡ እርሱን ለመራብማ ሰው መሆኔን ማመነን ያሻኛል፡፡
ተወኝ አቦ! እየየም ሲዳላ ነው አለ ያገሬ ሰው! ሰው መሆን ቅንጦት ነው፡፡ የነጻነት ጠኔ የጨካኝ ሰው ጫማ ላይ እንጂ በረኀብ አንደፋድፎ መቃብር ላይ ሲደፋ አላየነውም፡፡ ስለዚህ ተው! አስብ አትበለኝ! ሳልኖር ልሙትበት!
የዚህን ወርቅ የሆነ ብሎግ ክብር የሚቀንሱና የሚያወርዱ አስተያየቶች ባይጻፉ ተመኘሁ፡፡ የሕይወት ምግብ የሆነውን ማር ጽሑፍና ወለላ መልዕክት አጣጥመን ሳንጨርስ እዚህ ግባ የማይሉት እሰጥ አገባ ማየት ደስ አይልም፡፡ እኔ ግን አንድ ነገር እየገረመኝ መጥቷል፡፡ እኔ የምልህ ዳኒ ውልብድና እና ኢውልብድና በሚል ርዕስ ስለዋልድባ የጻፍከውን ሰፊና ትምህርታዊ ጽሑፍ ለተወሰኑ አንባቢዎች ብቻ ነው እንዴ የለጠፍከው? እንዲህ ካልሆነ ይህ ተደጋጋሚ ቅሬታ ከምን መጣ?
ReplyDeleteትዕግስት
…..መንፈስ ነጻነትን ይፈልጋል፡፡
ReplyDeleteያለሀሳብ ከመሰልጠን ያለስልጣኔ ማሰብ ይሻላል፡፡
(ያውም አማራጭ ሣያስፈልገው)
እግዚአብሔር ህሊናህን ይጠብቅልህ፡፡
የቀመርና የሥነ ፈለክ ምሥጢር
ReplyDeleteአዘጋጅ፡- አለቃ ያሬድ ፈንታ ወልደ ዮሐንስ
የገጽ ብዛት፡- 214
ዋጋ፡- 50 ብር
ኅትመት፡- ፋርኢስት ትሬዲንግ
ዘመን፡- 2004 ዓመተ ሥጋዌ
ጥቂት ስለ ደራሲው፡- በ1915 ዓም የተወለዱት አለቃ ያሬድ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት የአቡሻክር ሊቃውንት ዋናውና አንጋፋው ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሚሰጡ ዋና ዋና ትምህርቶችን በሚገባ የተማሩት አለቃ ያሬድ ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅም ለአራት ዓመታት ተምረው ተመርቀዋል፡፡ አለቃ ያሬድ በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ኮሌጅ ለ24 ዓመታት ባሕረ ሐሳብን አስተምረዋል፡፡አለቃ ያሬድ ከማስተማር በተጨማሪ ልዩ ልዩ ጥናታዊ ጽሑፎችን በማቅረብም ይታወቃሉ፡፡ ይኼኛው አራተኛው መጽሐፋቸው ነው፡፡
AnonymousMay 3, 2012 1:23 PM
ReplyDeleteየዚህን ወርቅ የሆነ ብሎግ ክብር የሚቀንሱና የሚያወርዱ አስተያየቶች ባይጻፉ ተመኘሁ፡፡ የሕይወት ምግብ የሆነውን ማር ጽሑፍና ወለላ መልዕክት አጣጥመን ሳንጨርስ እዚህ ግባ የማይሉት እሰጥ አገባ ማየት ደስ አይልም፡፡ እኔ ግን አንድ ነገር እየገረመኝ መጥቷል፡፡ እኔ የምልህ ዳኒ ውልብድና እና ኢውልብድና በሚል ርዕስ ስለዋልድባ የጻፍከውን ሰፊና ትምህርታዊ ጽሑፍ ለተወሰኑ አንባቢዎች ብቻ ነው እንዴ የለጠፍከው? እንዲህ ካልሆነ ይህ ተደጋጋሚ ቅሬታ ከምን መጣ?
ትዕግስት
Reply
AmanAbMay 3, 2012 10:05 PM
…..መንፈስ ነጻነትን ይፈልጋል፡፡
ያለሀሳብ ከመሰልጠን ያለስልጣኔ ማሰብ ይሻላል፡፡
(ያውም አማራጭ ሣያስፈልገው)
እግዚአብሔር ህሊናህን ይጠብቅልህ፡፡
Reply
Thanks dani for this inspiring article. The readers of this article PLEASE PLEASE Some of you wrote ' Kalehiwot Yasemalin'...This is not a religious writing...abo atasedibun Orthdoxoch lehulum neger KHY yilalu Atasibiliun.... I know Dani writes both on religious and secular matters. But use KHY only for spiritual articles...for the rest you can use thank you or what ever other word you want..but not 'Kalehiwot Yasemalin'
ReplyDeleteአስተምሮናል አይዞን በርታ
ReplyDelete