ትናንት ማክሰኞ ማታ በእግር ኳስ ታሪክ አስገራሚ ከሚባሉት ጨዋታዎች አንዱን ተመለከትን፡፡ ስለ እግር ኳስ ልቡን ሞልቶ ማንም ቀድሞ መናገር አይችልም የተባለውን ብሂል ያረጋገጠ ነበር የባርሴሎናና የቼልሲ ጨዋታ፡፡
የዓለም ቁጥር አንድ ቡድን ከእንግሊዝ ስድስተኛ ቡድን ጋር ተጋጥሞ፣ ሰባ በመቶ የኳስ ቁጥጥር የነበረው ቡድን ሠላሳ በመቶ ኳስን በያዘ ቡድን ተሸንፎ፤ ከአራት በላይ አጥቂ ያሰለፈ ቡድን በአንድ አጥቂ ተበልጦ፤ ያጠቃ ቡድን በተከላከለ ቡድን ድል ተመትቶ ያየንበት ጨዋታ ነበር፡፡ የትናንቱ ጨዋታ፡፡
ከጨዋታው በፊት ባርሴሎና ቼልሲን በኑካምብ ሜዳ ላይ ድባቅ ሊመታው እንደሚችል የሚተነብዩ ነበሩ፡፡ ቼልሲ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ያለውን ቦታና ሰሞኑን ያስመዘገባቸውን ደካማ ውጤቶች ተንተርሰው፣ባርሴሎና ያሰለፋቸውን ምርጥ ተጨዋቾች ቆጥረው፣ የአሰልጣኝ ጋርዴዎላን ብቃት አሞካሽተው ለቼልሲ የፈሩለት ብዙዎች ነበሩ፡፡ ምንም እንኳን በስታምፎርድ ብሪጅ ቼልሲ በድሮግባ ጎል ባርሴሎናን አንድ ለባዶ ቢያሸንፍም፤ ያ ግን አጋጣሚን እንጂ የቼልሲን ብቃት፣ የባርሴሎናንም መውረድ እንደማያሳይ የተከራከሩ ነበሩ፡፡
«ደርሶ አይቼው» አለ አማራ ለልጁ ስም ሲያወጣ፡፡ ትናንት ደረሰና ሁሉንም አየነው፡፡ የተጠበቀው ቀርቶ ያልተጠበቀው ሆነ፡፡ እኔም ከጨዋታው በኋላ ነፍሴን እንዲህ አልኳት፡፡
ነፍሴ ሆይ በርቺ፡፡ ተስፋም አትቁረጭ፡፡ ምናልባት ከፊትሽ የምትጋጠሚው ፈተና በዓለም ላይ ወደር የሌለውና ለማሸነፍ ከባድ መስሎ የሚታይ ይሆን ይሆናል፡፡ ምናልባትም ብዙዎቹን የረፈረፈ፤ ታላቅ ስምም ያተረፈ ይሆን ይሆናል፡፡ ምናልባትም ደግሞ የዓለም ሻምፒዮናነትን ክብር የተቀዳጀ ታላላቅ የተባሉትን ሁሉ ድል እየመታ የመጣም ሊሆን ይችላል፡፡
ግን ነፍሴ ሆይ በርቺ፡፡
በኑሮ ትግል ውስጥ አይሸነፍም የሚባል ፈተና የለም፡፡ በሕይወት ፈተና ውስጥ እንዳሸነፈ ብቻ የሚኖር የለም፡፡ የጊዜ ጉዳይ ነው፡፡ እነ እገሌ የሚያሸንፉት እነ እገሌ ደግሞ የማያሸንፉት ፈተና የለም፡፡ ፈተናን የሚያሸንፉት በእምነት ተስፋ ሳይቆርጡ የታገሉ ብቻ ናቸው፡፡ ስለ ተናቅሽ ታናሽና ደካማ ነሽ ማለት አይደለም፡፡ ግንበኞች የናቁት ድንጋይ የማዕዘን ራስ መሆኑን አትርሺ፡፡ እነ እገሌን ያሸነፈ ሁሉ አንቺን ያሸንፋል ማለትም አይደለም፡፡ ዝሆን እንደ ትንኝ የሚፈራው እንደሌለ አትርሺ፡፡
ትናንት አንዱ የቼልሲ ተጨዋች የተናገረውን አልሰማሺምን? «ዓለም በሙሉ በባርሴሎና እንደምንሸነፍ ይነግረን ነበር፡፡ እኛ ግን እንደምናሸንፍ እናምን ነበር፡፡ የእነርሱን ያህል ስምና ዝና አልነበረንም፡፡ የእነርሱን ያህል ስብሰብና ጥምረትም አልነበረንም፡፡ አንድ ነገር ግን ነበረን አለ፡፡ እናምን ነበር፡፡ በማሸነፍ እናምን ነበር፡፡ሁላችንም በዚህ እምነት ውስጥ ነበርን፡፡የጥንካሬያችን መነሻውም ይህ እምነት ነበር አለ፡፡»
ነፍሴ ሆይ አንቺም እንደምታሸንፊ እመኚ፡፡ አታሸንፊም የሚሉሽን አትስሚ፡፡ ተፈታታኝሽን አግዝፈውና አልቀው፣ አክብደውና አምጥቀው የሚያስፈራሩሽን አትመልከቺ፡፡ አንቺም እመኚ፡፡ መጽሐፉም ላመነ ሁሉ ይቻላል ነው የሚለው፡፡ እነ አበበ ብቂላ ከገጠሪቱ ኢትዮጵያ መጥተው በሮም ኦሎምፒክ በባዶ እግራቸው ሲሮጡ ማን ያሸንፋሉ ብሎ ገምቷቸው ነበር? እንዲያውም ኢትዮጵያ ታሸንፋለች ተብሎ ስላልታሰበ ባንዲራ እንኳን በአካባቢው አልነበረም ይባላል፡፡ እነ አበበ ብቂላ በዓለም ሚዲያ አስቀድሞ አልተነገረላቸውም ነበር፤ በሌሎች ዓለም ያለውን ዓይነት የመወዳደሪያ ሜዳ፣ የመለማመጃ መሣርያም አላገኙም ነበር፡፡ አንድ ነገር ብቻ ነበራቸው፡፡ እምነት፡፡ እናሸንፋለን የሚል እምነት፡፡ እናም አሸነፈ፡፡
አይዞሽ ነፍሴ ሆይ በርቺ፡፡
በአንደኛው ውድድር ተሸነፍሽ ማለት በሁሉም ውድድር ተሸነፍሽ ማለት አይደለም፡፡አታይውም ቼልሲን፡፡ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ስድስተኛ ነው፡፡ በአምስት ቡድኖች ተበልጦ፤ አንዳንድ ጊዜ እስከ አምስት ጨዋታ በተከታታይ እየተሸነፈ፡፡ በሽንፈቱ ምክንያትም አሠልጣኙን እስከማጣት ደርሶ አልነበረምን? ነገር ግን ዓለም አንድ የመሮጫ መም ብቻ የላትም፡፡ መሮጫው ብዙ ነው፡፡ በአንዱ ስትሸነፊ በሌላው መንገድ ሞክሪ እንጂ ዓለም ሁሉ የተዘጋብሽ አይምሰልሽ፡፡ አንዱ በር ሲዘጋ ሌላውን አንኳኪ፡፡ አንደኛው ሲያቅትሽ ሌላውን ሞክሪ፤ ባንዱ ስትበለጭ በሌላው ብለጭ፡፡
ምንጊዜም ሌላም መንገድ አለ፡፡ ሌላም በር አለ፡፡ ሌላም አማራጭ አለ፡፡
እነዚህ አንድ ነገር ሞክረው ተስፋ የሚቆርጡ፣ ራሳቸውን የሚጥሉ፣ ዋጋ የለንም ብለው የሚያስቡ፣ ከዚያም አልፈው ራሳቸውን በራሳቸው የሚያጠፉ ሰዎች አያሳዝኑሽም?
አንቺ ግን እንደዚህ አታድርጊ በፕሪሚየር ሊግ ባይሳካልሽ በኤፍ ኤ ዋንጫ፣ በኤፍ ኤ ዋንጫ ባይሳካልሽ በካርሊንግ ዋንጫ፣ በካርሊንግ ዋንጫ ባይሳካልሽ በአውሮፓ ዋንጫ ሞክሪ እንጂ አለቀልኝ፣ አበቃልኝ አትበይ፡፡
አታይም በሀገሩ በትንንሽ ቡድኖች የተሸነፈው ቼልሲ የዓለም አንደኛውን ቡድን ሲረታው፡፡ አንቺም በትንንሽ ችግሮች በትረቺም፣ እዚህ ግባ በማይባሉ ፈተናዎች ብትሸነፊም፤ ደካማ ነሽ፣ ጥቅም የሌለሽ ነሽ ማለት ግን አይደለም፡፡በሌላኛው ጨዋታ ዓለም ሁሉ ሊያሸንፈው ያቃተውን ቡድን ታሸንፊው ይሆናልና፡፡
አየሽ አይደል ትናንት ባርሴሎና ሰባ በመቶ የኳስ ቁጥጥር ነበረው፡፡ ግን ተሸነፈ፡፡ አብዛኛውን ሜዳና ኳስ የያዙብሽ ሁሉ ያሸንፉሻል ማለት አይደለም፡፡ በኃይልም፣ በሥልጣንም፣ በዕድልም፣ በችሎታም ምክንያት በንግዱም፣ በፖለቲካውም፣ በኢኮኖሚውም፣ በግንባታውም፣ በውድድሩም ሜዳ ሰባ በመቶውን ከያዙ ቡድኖች ጋር ይሆናል ውድድርሽ፡፡ ግን ተስፋ አትቁረጭ፡፡ ሰባ በመቶ የያዘውን ቡድን በሠላሳ በመቶ የኳስ ቁጥጥር ማሸነፍ እንደሚቻል አየንኮ፡፡
ነፍሴ ሆይ «አንዱን ስትታገል ሌላው ሲተካብህ» እንደሚለው መዝሙር “በብሆር ላይ ቆረቆር”፣ “በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” ይገጥምሽ ይሆናል፡፡ አንቺ ኃይለኛ ቡድን ገጥሞሽ እርሱን ለማሸነፍ ስትሯሯጭ እንኳን ተጨማሪ ነገር ልታገኚ ያለሽም ይቀነስብሽ ይሆናል፡፡ ግን ተስፋ አትቁረጭ፡፡
አላየሽም ትናንት ባርሴሎና የቼልሲን የግብ ክልል መፈናፈኛ አሳጥቶ እንደ መድፈኛ ሲቀጠቅጠው፣ ቼልሲ ውጭ ነፍስ ግቢ ነፍስ ሲራወጥ፣ ቢቻል አሥራ ሁለተኛና አሥራ ሦስተኛ ተጨዋች የሚገኝበትን ዕድል ሲመኙ ጭራሽ “የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች” የሚለውን ለባርሴሎናዎች እንተወውና በአሥራ ሁለተኛው ደቂቃ ላይ ዋናው ተከላካያቸው ተጎድቶ ተቀየረ፡፡ አምበላቸው ጆን ቴሪ በሰላሣ ሰባተኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ወጣ፡፡
አሁን አንቺ ብትሆኚ ምን ትይ ነበር? ተስፋ ትቆርጫለሽ? አለቀ በቃ ትያለሽ? አየሽ የሽንፈት መጀመርያው ውስጥሽ ሲሸነፍ ነው፡፡ ልብሽ ተስፋ ሲቆርጥ፤ ራስሽ ለራስሽ መርዶ መንገር ስትጀምሪ፤ ከዚህ በኋላ የኔ ነገር አበቃ ስትይ፡፡ መታገል ያለብሽ እስክትሸነፊ ድረስ አይደለም፡፡ መኖር እስክታቆሚ ድረስ ነው፡፡ ሽንፈት የትግል መጨረሻ ሳይሆን የትግል መማርያ ነው፡፡
ከቼልሲ ተማሪ፡፡
ያ ሁሉ በኑካምብ ሜዳ ዙርያ የሠፈረ ዘጠና ሺ የባርሴሎና ደጋፊ በማያውቁት ቋንቋ የማያውቁትን ዜማ እያዜመ አውራውን ተከትሎ የመጣ የንብ መንጋ ሲያስመስለው፡፡ ከተከላካይ ያመለጠች ኳስ የቼልሲን መረብ ሁለት ጊዜ ስትደፍረው፤ አሁን ከዚያ በኋላ ቼልሲ ነፍስ ይዘራል ብሎ ማን ይጠብቅ ነበር? “እንኳንም ዘንቦብሽ እንዲያውም ጤዛ ነሽ” የሚለው በእንግሊዝኛ የለም እንዴ፡፡
አየሽ የሕይወት መመርያው ሁለት ነው፡፡ ማመንና መታገል፡፡ በቃ ባገኘሺው ትንሽ ዕድል፣ በተፈጠረልሽ ጠባብ ቀዳዳ ተስፋ ሳትቆርጭ በእምነት ታገዪ፡፡ ሞክሪ፣ ሞክሪ፣ ደጋግመሽ ሞክሪ፡፡ ያለችሽ የማለፊያ መንገድ እንደ እሳት ባሕር መንገድ የቀጠነች ብትሆን እንኳን በእርሷ መሄድ ከባድ ነው አትበዪ፡፡ ሞክሪ፣ ሞክሪ፡፡
ነፍሴ ሆይ
ተስፋ ሳይቆርጡ የመታገልን ጥቅም አየሽ አይደል፡፡ ከላምፓርድ እግር የተገኘችዋን ኳስ ያ ብራዚላዊ ራሜሬስ ወደላይ አንሥቶ ወደ ጎል ዶላትና እንደ ሶቪየት ጦር ቀይ መስሎ የተሰለፈውን የባርሴሎና ደጋፊ፣ በኣት እንዳጸና መናኝ ጽሞና ውስጥ ከተተው፡፡ አየሽ ያለቀ ሲመስል እንደገና ይጀመራል፤ የተቆረጠ ሲመስል እንደገና ይቀጠላል፡፡
መቼም ሰው ጭንቀት ውስጥ ሲገባ ብዙ ስሕተት ይሠራል፡፡ አንቺም እንደ ትናንቱ ቼልሲ ትግሉና ፈተናው ሲያስጨንቅሽ ትሳሳች ይሆናል፡፡ ቢጫም ቀይም ካርድ ታገኚ ይሆናል፡፡ ግን አታቁሚ ቀጥይ፡፡ ደግሞ በወዲያኛው የተሰለፉትን አትይ፡፡ ስለ ተፈታታኝሽ ዐቅም ትተሽ ስላለሽ ዐቅም አስቢ፣ ስለ ተፈታታኝሽ ችሎታ ትተሽ ስላለቺሽ አነስተኛ ችሎታ አስቢ፡፡ ሰው የሚሸነፈው ስለ ተፈታታኙ ብቻ ማሰብ ሲጀምር ነው፡፡ ሰው ስለ ተፈታታኙ እያሰበ ሲመጣ መጀመርያ እየፈራ፣ ከዚያም እየተጨነቀ፣ በመጨረሻም እጅ እየሰጠ ይሄዳል፡፡ አንቺ ግን እንደዚያ አታድርጊ፡፡
ፈተናው እየተደራረበ ቢመጣ እንኳን፤ ጨዋታው በአንቺ የግብ ክልል ዙርያ ቢሆን እንኳን፡፤ ከግራ ከቀኝ ቢወጥሩሽ እንኳን አትፍሪ፣ አትጨነቂም፡፡ እንደ ቼልሲ ግብ ከሃያ ሦስት ጊዜ በላይ ብትደበደቢ እንኳን አትጨነቂ፤ ተከላከይ፣ ወጥረሽ ተከላከይ፡፡ ከቻልሽ ደግሞ አጥቂ፡፡ ጊዜው እንደሁ ያልፋል፡፡ የጊዜ ጥቅሙ እርሱ አይደል፡፡ ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ አይሄድ፡፡ ጊዜ ወደፊት ባይሄድ ኑሮ ስንቱ ፈተና ሳያልፍ ባለበት ተገትሮ ይቀር ነበር፡፡
አይዞሽ ቀን የጣለው ዕለት፣ አንቺም የታገልሽ ዕለት ሜሲም ቅጣት ምት ይስታል፡፡ አይዞሽ ለታገለ ዕድል ከእርሱ ጋር ትሆናለች፡፡ አላየሽም እንዴ አንድ ጆን ቴሪ በቀይ ካርድ ቢወጣ የግቡ ቋሚና አግዳሚ ተከላካይ ሆኖ ሲያመሽ፡፡ ማዳን ከየት እንደሚመጣ ምን ታውቂያለሽ? ረድኤትስ ከየት እንደሚገኝ ማን ሊገምት ይችላል? የምንተማመንባቸውን ሰዎች ስናጣ ያልተጠበቀ አግዳሚና ቋሚ ከእኛ ጋር ይሰለፋል፡፡ ብቻ አንቺ ታገዪ፡፡
ተስፋ ቆርጦ ከሕይወት ትግል የሸሸ ሰው እድሉን መጠቀም አይችልም፡፡ መልካም ውጤት ማለት እድልና ትግል በሚገናኙባት የማቋረጫ ነጥብ ላይ የምትገኚ ናት፡፡ እድል ከሰሜን ወደ ደቡብ፣ ትግል ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ ሲጓዙ አንድ ቀን ይገናኛሉ፡፡ አንቺ ትግልሽን ካቆምሺው ግን ሳይገናኙ ይቀራሉ፡፡ ስለዚህ ተስፋ አትቁረጭ፡፡ ታገዪ ታገዪ ታገዪ፡፡
“በለሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል” ሲባል አልሰማሽም፡፡ አየሽ አይደል በዘጠናኛው ደቂቃ የተገኘው የቶሬዝ ጎል በባርሳ እድል ላይ እንዴት አድርጎ ሚስማር እንደመታበት፡፡ እስከ መጨረሻው የጸና ማለትም ይሄ አይደል፡፡
ቀን ጥሎኛል ብለሽ ራስሽን አትጣይ፡፡ ቀን ሲጥልሽ አንቺ ተነሺ እንጂ፡፡ ቀን እኮ አንቺን ብቻ ሳይሆን ሜሲንም ይጥለዋል፡፡ ቀን አንቺን ብቻ ሳይሆን ባርሴሎናንም ይጥለዋል፡፡ ለምን ሁሉንም ነገር ባንቺ ብቻ የመጣ አድርገሽ ትማረሪያለሽ? ለምን መከራ ባንቺ ላይ ብቻ የመጣ ይመስልሻል?
ነፍሴ ሆይ በርቺ፡፡
Great article Dani, in fact you remind me two sayings that i like & which has similar message with your article
ReplyDelete"Luck favours the better prepared” (Louis Pasteur)
“Our lives are not determined by what happens to us, but how we react to what happens”
What a great article i got to read this afternoon.Dear Deacon Daniel,it is so great to read your insprational,timelly,and couragiouse blogs all time,specailly it is so worthy to have this type of moral support on this time of,,,, .pls keep sharing us your all time great thoughts,,,God bless Ethiopia and you ,,,,Fasika(Sweden)
Deletethank you
ReplyDeleteWell written as usual Dani.
ReplyDeletewow nice perspective
ReplyDeleteyou are great, you wrote such an astonishing article in less than one day!!!
ReplyDeleteGod bless Ethiopia, EOTC, MK and you.
TG: may God bless you all.
ReplyDelete"የምንተማመንባቸውን ሰዎች ስናጣ ያልተጠበቀ አግዳሚና ቋሚ ከእኛ ጋር ይሰለፋል፡፡"
betam des yemil milketa new.
ReplyDeleteTesfa alemekuret
Beminet hulu endemichal
...
Egziabher yirdan
Txs
Best ever! KHY.
ReplyDelete“Our lives are not determined by what happens to us, but how we react to what happens”
ReplyDeletereally.....
ReplyDeleteYou are really a very good writer specially in addressing such article for this new generation who become hopeless by swimming in the river of addiction! Please make it to reach to the Eth. youth through TV and Radio as well! God bless your pen and keep you from EPRDF press slaugters!!
ReplyDeleteIncredible is your article but I have noticed one error. There is no identity as Amhara. It is used by some elites and politicians and the people in the south to describe people who speak Amharic as a mother tong. But the people do not call themselves Amharas, though there is an increasing adaptation of the name in cities after its political introduction by EPRDF. They call themselves Gojjame, Gondere, Welloye, etc. If you ask one Gojjame what he/she meant when he/she says that he/she is Amhara, he/she would say that he/she was talking about his/her religion. They would ask you "are you Amhara or Islam" when they want to know what your religion is not your ethnic identity.
ReplyDeleteምነው ኢትዮጲያዊነትን እንዲህ ጠላኸው? በማይገባበት ሁሉ እያስገባህ ጎሳ ትዘረዝራለህ:: የተለያዩ የጎሳ ስሞችን መጥራት ያኮራናል አያሳፍረንም ነገር ግን እንዳንተ አይነት ጠባብ ሰዎች ከሳጥኑ ውጭ ማሰብ የተሳናቸው በሌላ ስለሚተረጉሙት ስሙን እራሱ ደግሜ መጻፍ በጣም ከበደኝ:: ዳንኤል የጻፈው ነገር ፍጹም አንተ ስለጠቀስከው ነገር አያወራም አንተ ግን ከየትም የጎሳን ስም ብቻ ፈልገህ ጠባብነትህን አሳየኸን:: እስኪ ዳንኤል የጻፈው ምን እንደሆነ እንደገና በደንብ አንብበው ከዛም አንተ የጻፍከው አስተያየት ምን እንደሆነ በደንብ አስተውልና እራስህን ታዘበው:: የፈጠረህ አምላክ ልብ ይስጥህ:: ኢትዮጲያዊነትን ግን እንዲህ አትፍራው አትጥላው:: ኢትዮጲያዊነት አንድነት ነው: ፍቅር ነው: ያኮራል, ጀግንነት ነው, የመተሳሰብ ስሜት ያለበት ነው, የመከባበር ስሜት ያለበት ነው, እንግዳ ተቀባይነት ነው, ጠላት ወዳድነት ነው, ኢትዮጲያዊነት እዚህ ጋ ዘርዝሬ መጨረስ የማልችላቸው እጅግ በርካታ ጥሩ ነገሮችን በውስጡ የያዘ ነው:: የዘረዘርኳቸው ነገሮች ላይገቡህ ይችላሉ:: ሊገቡህ የሚችሉት ትክክለኛውን ኢትዮጵያዊነት ካወቅህና ቢያንስ ለሁለት አመታት ምእራባውያን አገር ውስጥ ኖረህ በትክክለኛው ኢትዮጵያዊነትና በምእራባውያኑ መካከል ያለውን ልዩነት ከተረዳህ ብቻ ነው:: ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ጎሳዎች ማለት በቃ ስያሜ ነው:: መሰረታቸው ግን ዘመዳሞች የነበሩ ሰዎችን በቡድን በቡድን ተደርገው ስያሜ የተሰጣቸው ናቸው:: በመጽሓፍ ቅዱስ የምታምን ከሆነ ደግሞ እንኳን በጣም የቅርብ ዝምድና ያለን ኢትዮጵያውያን ቀርቶ የአለም ሁሉ ህዝብ አንድ ነው:: የአዳምና የሔዋን ልጆች ነን:: እባክህ ወንድሜ ከትንሿ ሳጥን ወስጥ ወጥተህ ለማሰብ ሞክር:: በ1000,000 ሰዎች መካከል አንድን ብቸኛ አይነ ስውር እንደመፈለግ አይነት በማይመለከተው ቦታ ሁሉ በስንት መከራ አንድ ቃል ፈልገህ አትሰንጥቀው:: በቃ ውጣ ከሳጥኑ ወስጥ ሁሉም የአለም ህዝብ አንድ እንደሆነ አስብ, በተለይ እኛ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ሁላችንም የአንድ ቤተሰብ ልጆች እንደሆንና ፍጹም እህትና ወንድም እንደሆንን አስብ::
Deleteጎጠኝነትን በእጅጉ ከጠሉትና ትክክለኝውን ኢትዮጵያዊነትን ከሚናፍቁት ወንድምህ
ሐይለማርያም
ምነው ኢትዮጲያዊነትን እንዲህ ጠላኸው? በማይገባበት ሁሉ እያስገባህ ጎሳ ትዘረዝራለህ:: የተለያዩ የጎሳ ስሞችን መጥራት ያኮራናል አያሳፍረንም ነገር ግን እንዳንተ አይነት ጠባብ ሰዎች ከሳጥኑ ውጭ ማሰብ የተሳናቸው በሌላ ስለሚተረጉሙት ስሙን እራሱ ደግሜ መጻፍ በጣም ከበደኝ:: ዳንኤል የጻፈው ነገር ፍጹም አንተ ስለጠቀስከው ነገር አያወራም አንተ ግን ከየትም የጎሳን ስም ብቻ ፈልገህ ጠባብነትህን አሳየኸን:: እስኪ ዳንኤል የጻፈው ምን እንደሆነ እንደገና በደንብ አንብበው ከዛም አንተ የጻፍከው አስተያየት ምን እንደሆነ በደንብ አስተውልና እራስህን ታዘበው:: የፈጠረህ አምላክ ልብ ይስጥህ:: ኢትዮጲያዊነትን ግን እንዲህ አትፍራው አትጥላው:: ኢትዮጲያዊነት አንድነት ነው: ፍቅር ነው: ያኮራል, ጀግንነት ነው, የመተሳሰብ ስሜት ያለበት ነው, የመከባበር ስሜት ያለበት ነው, እንግዳ ተቀባይነት ነው, ጠላት ወዳድነት ነው, ኢትዮጲያዊነት እዚህ ጋ ዘርዝሬ መጨረስ የማልችላቸው እጅግ በርካታ ጥሩ ነገሮችን በውስጡ የያዘ ነው:: የዘረዘርኳቸው ነገሮች ላይገቡህ ይችላሉ:: ሊገቡህ የሚችሉት ትክክለኛውን ኢትዮጵያዊነት ካወቅህና ቢያንስ ለሁለት አመታት ምእራባውያን አገር ውስጥ ኖረህ በትክክለኛው ኢትዮጵያዊነትና በምእራባውያኑ መካከል ያለውን ልዩነት ከተረዳህ ብቻ ነው:: ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ጎሳዎች ማለት በቃ ስያሜ ነው:: መሰረታቸው ግን ዘመዳሞች የነበሩ ሰዎችን በቡድን በቡድን ተደርገው ስያሜ የተሰጣቸው ናቸው:: በመጽሓፍ ቅዱስ የምታምን ከሆነ ደግሞ እንኳን በጣም የቅርብ ዝምድና ያለን ኢትዮጵያውያን ቀርቶ የአለም ሁሉ ህዝብ አንድ ነው:: የአዳምና የሔዋን ልጆች ነን:: እባክህ ወንድሜ ከትንሿ ሳጥን ወስጥ ወጥተህ ለማሰብ ሞክር:: በ1000,000 ሰዎች መካከል አንድን ብቸኛ አይነ ስውር እንደመፈለግ አይነት በማይመለከተው ቦታ ሁሉ በስንት መከራ አንድ ቃል ፈልገህ አትሰንጥቀው:: በቃ ውጣ ከሳጥኑ ወስጥ ሁሉም የአለም ህዝብ አንድ እንደሆነ አስብ, በተለይ እኛ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ሁላችንም የአንድ ቤተሰብ ልጆች እንደሆንና ፍጹም እህትና ወንድም እንደሆንን አስብ::
Deleteጎጠኝነትን በእጅጉ ከጠሉትና ትክክለኝውን ኢትዮጵያዊነትን ከሚናፍቁት ወንድምህ
ሐይለማርያም
why dont u concentrate on the central theme of the article rather than focusing on such very sillyyyyy things; u stone headed!!!!!
Deleteyegna historian!
Deletehey H/Mariam, why r u crying ? ha so funny.He wrote something good. it has nothing to do with ethnicity.It is an example why do not u cry loud @EPDRF ,with their "lematawi Gazetegnoche" dont try to defame someone ! u must be EPDRF member heheh so funny. Dani keep up the good work.
DeleteDear Anonymous on April 26, 2012 at 10:15,
DeleteI am not crying...read it again and what I have written is not for a reply to Dani rather to 'Unknown'. Daniel's view is perfect as usual. If you considered me as crying, I am crying for the statements written by "Unknown". Bofore writing replying to a wtitten article, please try understand the article and read it well to know exactly what is written for.
H/Mariam
please reade more and more.now you thinks as animal.
DeleteMaleqaqesih endet anjet yibelal jal:: mnaw mn tefetere (diyakon?) daniel kibret?
ReplyDeleteBetam anjeten belahew:: mndn new enedezih yamarereh?
Derso Ayichew: don't be pessimistic please.
DeleteI read almost all of your articles but not impressed by your perspective like now. You see things from a totally new and different perspective. This is something that will stay with me for a long time and help me to move forward. You right, believing that we can be the winner and the most high God make a difference. We will get where we intended to if we keep going. God bless you more and more. You are the best!!!
ReplyDeleteFerework
tabarake
ReplyDeleteEgizabehare yesetehe
ReplyDeleteነፍሴ ሆይ በርቺ
ReplyDelete"የምንተማመንባቸውን ሰዎች ስናጣ ያልተጠበቀ አግዳሚና ቋሚ ከእኛ ጋር ይሰለፋል፡፡"
ReplyDeleteGod Bless You Daniel
AET from Norway
በኃይልም፣ በሥልጣንም፣ በዕድልም፣ በችሎታም ምክንያት በንግዱም፣ በፖለቲካውም፣ በኢኮኖሚውም፣ በግንባታውም፣ በውድድሩም ሜዳ ሰባ በመቶውን ከያዙ ቡድኖች ጋር ይሆናል ውድድራችን፡፡
ReplyDeleteseems like our system here in Ethiopia
ግን ተስፋ አንቁረጥ፡፡
ፈተናን የሚያሸንፉት በእምነት ተስፋ ሳይቆርጡ የታገሉ ብቻ ናቸው፡፡
ReplyDeleteዲያ. ዳንዔል እግዚአብሄር ያሳድግህ። የጻፍከው ለኔ እስኪመስለኝ ድረስ ነው የገረመኝ።
ReplyDeleteመታገል ያለብሽ እስክትሸነፊ ድረስ አይደለም፡፡ መኖር እስክታቆሚ ድረስ ነው፡፡ ሽንፈት የትግል መጨረሻ ሳይሆን የትግል መማርያ ነው፡፡
wow
ReplyDeleteD Daneil betsam melkam melekt mew mechem yetadelk sew neh yihonalhal balemoya neh Andand Gize yalebotah tigebaleh yiluhal Ahun Mahibere Kidusann & Bete Kihinetin tetsenkek wede Poletikam Atigiba Ahun Yih melikit lakas weyim lenefis bile ayidelem tekawamim berta- Mahiberum Berta- Aba Serekem Bertu-lemalet yimeslal beterefe endat sewn eyastemare yetegege awki memihir yelem egiziabher yitsebkih Le Deje Selam -Ahat tewahedo-Gebir Her-Azegagochi lemin atnegirachewm Wedajochihi -gadegochihi nachew mile Aba Ekele Bezihi werede -Aba Ekele Bezih Aetsa-Abune Ekele-Diyakon ekele eyalu yesewn neger kememezigeb Astemar yehone neger beimezegibu Hulum yetemaru wendimoch nache ebakih keante endimaru nigerachew Berta
ReplyDeletesplendid!!
ReplyDeleteEVEN IF THE DARK IS VERY LONG, BE SURE THAT THE SUN WILL RISE.
ReplyDeleteMetaphoric!
ReplyDeleteSuch a nice article! You have made great harmoney of the foot ball game and struggle in life. A Warm message! Learnt a lot. Thank you Daniel, You have such a beautiful mind. Solomon K.
ReplyDeleteግሩም መልዕክት ነው ወንድሜ! እምነት ፣ተስፋ ፣ፍቅርና ውሳጣዊ ጥንካሬ የሌለው ሕይወት አደጋው የከፋ ነውና እነዚህን ይዞ መገኘት ይገባል !
ReplyDeleteይኽኛው ( ዛሬ የፃፍክበት) የአፃፃፍ ዘይቤ ግን ከቅድስት ቤተ ክርሰቲያን የተቀዳ መሆኑ አስፈራኝ ውዳሴ አምላክ ዘዘወትር ነፍሴ ሆይ ....... ነፍሴ ሆይ...... ይላልና ። የአባ ጊዮርጊሱ አርጋኖንም እንዲሁ ነፍሴ ሆይ ....... ነፍሴ ሆይ...... ይላልና። አንዳንድ ምሳሌዎችህም ለምሳሌ .....የባርሴሎናን ደጋፊ፣ በኣት እንዳጸና መናኝ ጽሞና ውስጥ ከተተው.... የሚለው አይነቶችም አስፈሩኝ ። እናም ከጊዜ ብዛት እነዚህ እየተለመዱ ከሄዱ የመቅደሱን ወደ ውጭ.... እንዳይሆን ስትጽፍልን አስብበት ። በተረፈ መልዕክቱ እጅግ እጅግ እጅግ ጣፋጭ ነው!
እድሜህን ያርዝመው!
ቸር ያሰማን
Dani may God protect you from any danger for our benefit
ReplyDeleteመልካም ውጤት ማለት እድልና ትግል በሚገናኙባት የማቋረጫ ነጥብ ላይ የምትገኚ ናት፡፡
ReplyDeleteትልቅ ምክር
ReplyDeletethank God blass you thank so mach
ReplyDeleteOur lord keep your life
kale hiwet yasemalen deacon daniy
ReplyDeletenefse hoy berchi
ReplyDeleteEGZEABEHERE AMLAKACHENE, mekari wendem & baraki abate aysatane, Amen ¦¦
ReplyDelete(H/Eyesus from SWITZERLAND)
Thanks! Dn. Danil It is astonishing article keep it up. However, when are you going to be a "kesise danil and Dr. and Prof. I wish that for you and EOTC + Ethiopia peoples too". Would you please make it very soon, if possible?
ReplyDeleteWhat is Ur point AFBZ, does it make any change? And pls don't represent others in Ur personal wish!
Delete10Q DANI
ReplyDeleteጥሩ ምክር እግዚአብሔር ጸጋዉን ያብዛልህ
ReplyDeleteI Like it.
ReplyDeleteDear Daniel,
ReplyDeleteYou are advising us with this nice article. In military science there is one principle that stated that "No retreat no surrender."
ዳኒ እንኳን የኢትዮጰያ ያገሬ ልጅ የሆንክ ውስጥ ሲረካ ለመግለፅ ያስቸግራል፡፡ ካየነው&ከሰማነው&ከአካባቢያችን& ከሰዎች ንግግር ከመሳሰሉት መማር እንዲት እንደምንችን አሳይህን ጌታ እግዚአብሔር የአብርሃምን ፍቅር ይስጥህ፡፡
ReplyDeleteከሰሜን ወደ ደቡብ፣ ትግል ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ ሲጓዙ አንድ ቀን ይገናኛሉ=The center of cross
ReplyDeleteDani,God bless you.
ReplyDeletewhen sometimes we Ethiopians Lost our hopes about our politics,economy and church leaders God send us an elite people who gives a new hope.God send his message to us through Teddy Afro(Tikur sew) and now through you Dani,this article. At this time i see that still God didnot forget Ethiopia.
Ejig Girum yehone Melikit new
ReplyDeleteDn Daniel Egiziabher Tsegawn ahunim yabizalih
OMG!!
ReplyDeleteብልህ ሰው ከሁሉም ነገርና አጋጣሚዎች ይማራል፡፡ ወንድማችን ዳንኤል የአውሮፓን ጨዋታ መሰረት አድርጎ ሊያስተላልፈው የፈለገው መልእክት ከጨዋታው ውጤት፣ ከደጋፊዎች ደስታና ፈንጠዚያ፣ በጨዋታው ከተከሰቱት አስገራሚና ያልተጠበቁ ኩነቶች እጅግ ልቆ የሚያልፍ ለነፍሳችን የሚሆን መልእክት ነው፡፡ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ እንሁን በማመንና ተስፋ ባለመቁረጥ በሚደረግ ትግል ነገሮችን/የሕይወትን/የኑሮአችንን ገጽታ ወደ በጎ መለወጥ እንደሚቻል በጥበብ ቃል ይነግረናል፡፡ እንዲህ ሲል፡-
ReplyDelete«አየሽ ነፍሴ ሆይ፡- የሕይወት መመርያው ሁለት ነው፡፡ ማመንና መታገል፡፡ በቃ ባገኘሺው ትንሽ ዕድል፣ በተፈጠረልሽ ጠባብ ቀዳዳ ተስፋ ሳትቆርጭ በእምነት ታገዪ፡፡ ሞክሪ፣ ሞክሪ፣ ደጋግመሽ ሞክሪ፡፡ ያለችሽ የማለፊያ መንገድ እንደ እሳት ባሕር መንገድ የቀጠነች ብትሆን እንኳን በእርሷ መሄድ ከባድ ነው አትበዪ፡፡ ሞክሪ፣ ሞክሪ…፡፡» ድንቅ ብለሃል ዲያቆን!
በእርግጥም እስከመጨረሻ የነፍሳችን ሕቅታ ድረስ ሙከራችንን ማቆም የለብንም፣ Try try until you die! የሚል ብዙ ዘመናትን ያስቆጠር ብሂል አላቸው ምዕራባውያኑ፡፡ «ሕይወት ሠልፍ፣ ሕይወት ብርቱ ትግል ናት፡፡» ይለናል ጤናውን፣ አካሉን፣ ሀብቱን፣ ንብረቱን፣ ልጆቹን፣ ክብሩን፣ ዝናውን፣ መፈራቱን፣ ዘመዶቹንና ወዳጆቹን እጅግ የከፋውና መከራው ቅጥ የለሽ እንዲሆን ያደረገበት ደግሞ በስተመጨረሻ የሕይወቱን አጋር በደስታዬም ሆነ በሐዘኔ ከጎኔ ትሆናለች ያላትን የነፍሱን ክፋይ አካሉ የሆነች ሚስቱን እንኳን ጭምር ሳይቀር ያጣው ኢዮብ፡፡
ቅን፣ ጻድቅ፣ ፍጹምና እግዚአብሔርን የሚፈራ እንደሆነ የተነገረለት ኢዮብ በዚህ ሁሉ የመከራ ዶፍና ውርጅብኝ ውስጥ ሆኖ ያለው ነገር ቢኖር፡- «ሥጋዬን በጥርሴ እይዛለሁ፣ ሕይወቴን በእጄ አኖራለሁ፡፡ እነሆ ቢገድለኝም ስንኳ እርሱን በትዕግስት እጠባበቃለሁ…፡፡» (ኢዮብ ፴፣፴፩)
ማንኛችን እንሆን በእንዲህ ዓይነት የመከራ ውርጅብኝና ዶፍ ውስጥ ያለፈን ወይም ያለን… እንግዲያውስ ሕይወት ትግል ሕይወት ሰልፍ ናትና ጉዞአችን ወደፊት እንጂ ወደኋላ ሊሆን አይገባውም፡፡ በግል ሕይወታችን፣ በቤተሰባችን፣ በኑሮአችን፣ በቤተ ክርስቲያናችን፣ በሀገራችን፣ በማኅበረሰባችን፣ በኢኮኖሚውና በፖለቲካው… በሁሉም መስክ ልንጋፈጠው የሚገባን ብርቱ ትግል… ብርቱ ሠልፍ አለ፡፡ ታምነን የምንዘምትበት፣ በእምነት፣ በትዕግስትና ተስፋ ባለመቁረጥ መንፈሳችንን አጠንክረን፣ የምንታገልበት… ብርቱ ሠልፍ፣ ብርቱ ትግል በፊታችን አለ...፡፡
መጽሐፍስ ከምድራዊ ሕይወታችን ባሻገር በተስፋ ስለምንጠብቃት መንግሥተ ሰማያት/መንግሥተ እግዚአብሔር ሲናገር፡- «ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መጋደል እንድንገባ እንዳለን ይነግረን የለ እንዴ፡፡» ስለዚህም ከሠልፉም፣ ከብርቱ ትግሉም በላይ ትልቅ መጋደል እንዳለም አለመዘንጋትም ደግ ይመስለኛል፡፡ የወንድማችን የዳኒ መልእክትም ይኸው ይመስለኛል፡፡
ሰላም! ሻሎም!
wow daniye your are just ETHIOPIAN!!!
ReplyDeleteGOD SAVE ETHIOPIA AND ETHIOPIAN!!!
ይህን ማስተዋልህን እስከመጨረሻው ይዘኸው እንድትዘልቅ እግዚአብሔር ይርዳህ፡፡
ReplyDelete"ፈተናን የሚያሸንፉት በእምነት ተስፋ ሳይቆርጡ የታገሉ ብቻ ናቸው፡፡ ስለ ተናቅሽ ታናሽና ደካማ ነሽ ማለት አይደለም፡፡ ግንበኞች የናቁት ድንጋይ የማዕዘን ራስ መሆኑን አትርሺ፡፡ እነ እገሌን ያሸነፈ ሁሉ አንቺን ያሸንፋል ማለትም አይደለም፡፡ ዝሆን እንደ ትንኝ የሚፈራው እንደሌለ አትርሺ፡፡"
ReplyDeleteነገሮችን የምታይባቸው መንገድ በጣም ይመቻሉ፤ሁሉም ሰው ነገሮችን በበጎ ጎናቸው ቢያያቸው መልካም ነበረ ::ግን?
"ትናንት አንዱ የቼልሲ ተጨዋች የተናገረውን አልሰማሺምን? «ዓለም በሙሉ በባርሴሎና እንደምንሸነፍ ይነግረን ነበር፡፡ እኛ ግን እንደምናሸንፍ እናምን ነበር፡፡ የእነርሱን ያህል ስምና ዝና አልነበረንም፡፡ የእነርሱን ያህል ስብሰብና ጥምረትም አልነበረንም፡፡ አንድ ነገር ግን ነበረን አለ፡፡ እናምን ነበር፡፡ በማሸነፍ እናምን ነበር፡፡ሁላችንም በዚህ እምነት ውስጥ ነበርን፡፡የጥንካሬያችን መነሻውም ይህ እምነት ነበር አለ፡፡»
ReplyDeleteነፍሴ ሆይ አንቺም እንደምታሸንፊ እመኚ፡፡ አታሸንፊም የሚሉሽን አትስሚ፡፡ ተፈታታኝሽን አግዝፈውና አልቀው፣ አክብደውና አምጥቀው የሚያስፈራሩሽን አትመልከቺ፡፡ አንቺም እመኚ፡፡ መጽሐፉም ላመነ ሁሉ ይቻላል ነው የሚለው፡፡ እነ አበበ ብቂላ ከገጠሪቱ ኢትዮጵያ መጥተው በሮም ኦሎምፒክ በባዶ እግራቸው ሲሮጡ ማን ያሸንፋሉ ብሎ ገምቷቸው ነበር? እንዲያውም ኢትዮጵያ ታሸንፋለች ተብሎ ስላልታሰበ ባንዲራ እንኳን በአካባቢው አልነበረም ይባላል፡፡ እነ አበበ ብቂላ በዓለም ሚዲያ አስቀድሞ አልተነገረላቸውም ነበር፤ በሌሎች ዓለም ያለውን ዓይነት የመወዳደሪያ ሜዳ፣ የመለማመጃ መሣርያም አላገኙም ነበር፡፡ አንድ ነገር ብቻ ነበራቸው፡፡ እምነት፡፡ እናሸንፋለን የሚል እምነት፡፡ እናም አሸነፈ፡፡"
ዲ/ን ዳንኤል፣ እጅግ በጣም የሚገርም ምልከታ ነው፤ አሁን ማን እንዲህ አስተውሎ ያውቃል? ራሳችንን እንድንመረምር ስላደረግኸን እናከብርሃለን፡፡ እግዚአብሔር ጸጋውን አብዝቶ አብዝቶ ያድልህ፡፡ በዕድሜ በጸጋ ይጠብቅህ፡፡
እንደሌላ ጊዜ እንኳን ጽሁፍህን አንብቤ ለመጨረስ አለፈለኩም ገና ርዕሱን ሳየው ዘጋኝ ለምን ብትል ወቅታዊ በሆነው በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ ምንም ለማለት አለፈለክም እኛ የታመመ ነው ራሳችንን አንተ አሁን እየሰጠህን ያለህ መድኃኒት የሚያዝናና ነው አየህ ላንተ መንገር ቀባሪን እንዲሉ ቢሆንብንም ለሁሉም ጊዜ ያለው ጨዋታን ለመጻፍ አሁን ደግሞ መጻፍ ያለበት ምን እንደሆነ መቼም ላንተ መነገር እናት ለልጆ አይደል የሚባለው ዳኒ
ReplyDeleteላስታዋለው ሰው ይህ ፁሁፍ ለወቅታዊ የቤ/ያን ጉዳይ ምላሽ ነው፡፡ ሳይታክቱ መፀለይ፣ተስፋ አለመቁረጥ፤እሰከመጨረሻው መፅናት……አይልም?
DeleteWhy do u need to have his article on the current church issue? He is not suppose to write what others want to hear rather what he want to write and what he believes in?I think we need to make our culture to give space for others.No body is obliged to clap together with the majority.I think as an Ethiopian,this is one of our problem.T
Deleteአይዞሽ ቀን የጣለው ዕለት፣ አንቺም የታገልሽ ዕለት ሜሲም ቅጣት ምት ይስታል፡፡ አይዞሽ ለታገለ ዕድል ከእርሱ ጋር ትሆናለች፡፡ አላየሽም እንዴ አንድ ጆን ቴሪ በቀይ ካርድ ቢወጣ የግቡ ቋሚና አግዳሚ ተከላካይ ሆኖ ሲያመሽ፡፡ ማዳን ከየት እንደሚመጣ ምን ታውቂያለሽ? ረድኤትስ ከየት እንደሚገኝ ማን ሊገምት ይችላል? የምንተማመንባቸውን ሰዎች ስናጣ ያልተጠበቀ አግዳሚና ቋሚ ከእኛ ጋር ይሰለፋል፡፡ ብቻ አንቺ ታገዪ፡፡
ReplyDeleteThanks Dani for the awesome article!!!
ReplyDeleteAnother wonderful piece from Danny, such a great mind ....i was forced to say 'seriously'' ' is there some one to see from such a dimension' ,proud of you Danny... we all face such 'Gollaids' and Barcelona's in our life's that make us loose hope yet....
ReplyDelete"አይዞሽ ቀን የጣለው ዕለት፣ አንቺም የታገልሽ ዕለት ሜሲም ቅጣት ምት ይስታል፡፡ አይዞሽ ለታገለ ዕድል ከእርሱ ጋር ትሆናለች፡፡ አላየሽም እንዴ አንድ ጆን ቴሪ በቀይ ካርድ ቢወጣ የግቡ ቋሚና አግዳሚ ተከላካይ ሆኖ ሲያመሽ፡፡ ማዳን ከየት እንደሚመጣ ምን ታውቂያለሽ? ረድኤትስ ከየት እንደሚገኝ ማን ሊገምት ይችላል? የምንተማመንባቸውን ሰዎች ስናጣ ያልተጠበቀ አግዳሚና ቋሚ ከእኛ ጋር ይሰለፋል፡፡ ብቻ አንቺ ታገዪ፡" says Danny!!!
"የምንተማመንባቸውን ሰዎች ስናጣ ያልተጠበቀ አግዳሚና ቋሚ ከእኛ ጋር ይሰለፋል፡፡"
ReplyDeleteawesome perspective. tnx
ReplyDeleteThank you Dani
ReplyDeletecant stop crying !!!!!i got my whole story here dani may GOD bless you to write more and more !!!!!!
ReplyDeleteGod bless Ethiopia, EOTC, MK and you.
ReplyDeleteችግርህ ያልገባቸው የፈለጉትን ይበሉ
ReplyDeleteከመግባት መውጣት ይሻላል ያለው አቤ ቶክቾ ወዶ አይደለም ሰውየውም የሰላም አምባሳደር ያስባለህ ለዘዴው አይደለ አንተ ብቻህን አይደለህም voaም እንዳንተው ጫና ተጥሎባቸው ስለጋና ስለ አፍሪካ መጠጥ ውሀ እያወሩ ይገኛሉ ::
Thank you Brother Dn.Danial this is a nice view as usual! keep doing this great job.I love this part. May God bless you and your fmaily and our country.
ReplyDeleteHabtamu the GA
አሁን አንቺ ብትሆኚ ምን ትይ ነበር? ተስፋ ትቆርጫለሽ? አለቀ በቃ ትያለሽ? አየሽ የሽንፈት መጀመርያው ውስጥሽ ሲሸነፍ ነው፡፡ ልብሽ ተስፋ ሲቆርጥ፤ ራስሽ ለራስሽ መርዶ መንገር ስትጀምሪ፤ ከዚህ በኋላ የኔ ነገር አበቃ ስትይ፡፡ መታገል ያለብሽ እስክትሸነፊ ድረስ አይደለም፡፡ መኖር እስክታቆሚ ድረስ ነው፡፡ ሽንፈት የትግል መጨረyሻ ሳይሆን የትግል መማርያ ነው፡፡
It is really an amazing blog. please keep it up. what i can say God bless u.
ReplyDelete«ደርሶ አይቼው» አለ አማራ ለልጁ ስም ሲያወጣ፡፡
ReplyDeleteBoA Gize Lekulu.
thank you Dn.Daniel , you wise
am not clear wz "ነፍሴ ሆይ በርች" do u remember z mistakes that u hv done before?
ReplyDeleteዳኒ በጣም ጥሩ ጽሁፍ ነው፡፡ በጣም ባዶነትና የተሸናፊነት ስሜት ውስጥ እያለሁ ነበር ጽሁፍህን ያነበብኩት ጥሩ ትምህርት አግኝቼበታለሁ፡፡ እግዚአብሄር ይባርክህ፡፡
ReplyDeleteመታገል ያለብሽ እስክትሸነፊ ድረስ አይደለም፡፡ መኖር እስክታቆሚ ድረስ ነው፡፡ ሽንፈት የትግል መጨረሻ ሳይሆን የትግል መማርያ ነው፡፡
ReplyDeleteWonderful article...keep it up.
ReplyDeleteke daniel tafach tsihufoch yezihn yahil yemarekegn yelem.Thanks a lot
ReplyDeleteDear Deacon Daniel what is your standing and the goal of your blog? to preach Gospel , to get fame , to count this as your job i really baffled
ReplyDelete..... if your goal and aim is to serve the ministry of God why you opt to use ungodly words . you may say to be adroit in attracting and tract the heart the contemporary youth in a way which seems plausible but with sincere apology i dare to say this way is a path of PILATE .....you should not be rude and unworthy to show others how the world is rude and unworthy ...the scripture of the saints say BRHANACHIHU BESEWFIT YIBRA .....your spritual kin N.
ዳኒ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ::
ReplyDeleteየነፍሴ ጨዋታ እጅግ ልዩ የሆነ ሰውን እያሰደሰተ የሚያስተምር
ReplyDeleteብዙ ነገር ተማርኩበት አመሰግናለሁ ሁል ጊዜም ምንጊዜም እመአምላክ ከአንተ ጋር ትሁን
በጣም አከብርሀለውህ.
ኢ.አ
it is amazing how you write those kind of articles ... we r so lucky to have you on our side...thank god..keep on brother!!!
ReplyDeleteDani sele Waldeba ye'Zemetah guday algeba belognal.......... i think its Hot issue
ReplyDeleteWhat a wonderful insight is it?
ReplyDeleteኦኦኦኦኦኦኦኦ ዳኒ!!!!!! በእውነት ከቸልሲ ደጋፊዎች የደስታ ሲቃ በላይ እኔ ባንተ እይታ በእንባ ታጠብኩ!!!!!!!!!!!!! ብዙ ጊዜ እያደንቅሁህ በውዳሴ ከንቱ ጦር አንተን መውጋቱ ይጸጽተኛል!!!! አሁን ግን የደማሃውን ድማ እንጅ ለስው ልጅ የተሰጠውን ያድናቆት ልኬት ይገባሃል እልሃለሁ!!!!!
ReplyDeleteመምህር ምን እንዳሰብኩ ታቃለህ....የብዙ ሐይማኖት ሰባኪዎች አለምን እንድንረሳ ካላቸው በጎ እሳቤ ተነስተው ማር ሲበዛ ይመራል እንዲሉ ህዝቡን ያለበቂ ግንዛቤ ከዓለምና የዓለም ነገሮች ያርቁታል!!! ግን እንዳንተ በዓለም መነጸር የህይወትን ትግል እና የእግዚአብሄርን ዳኝነት ቢሰብኩ ኑሮ በዓለም ሆነን ዓለምን ማሸነፍ እና ስለበለጠችው የእግዚአብሄር መንግስትም ስንል ዓለምን መርሳት በቻልን ነበር!!!! ቅ/ጳውሎስ የአርጤምስ ቤተጣኦት ካህናትን መስሎ ከወንድም ሃዋሪያቱ(ዮሃንስና ጴጥሮስ ጋርበመሆን ክርስቶስን እንደሰበከ ሁል አንተም የእንግሊዝ ኮሜታተር መስለህ ስለሰበክልን ተስፋ እግዚአብሄር በሃዋሪያቱ ዋጋ ያስብህ!!! እንወድሃለን!!!!!!!
Waw! I wish if I was the one who commented this. God Bless You brother you said the right thing. D/N Daneil deserve this even more if there is. God Bless you Dani
Deletetxs da i don't say nothing about ur article b/c u said every thing what i wish!!!!
ReplyDeleteWhat a nice expression!.....Just awesome! Keep up the good work dear!..... May God bless your talent!
ReplyDeleteZarem tenawun ena edmewun andiye abizito yisitih....ebakih gin letiyakeyachinim mels siten..dani...
ReplyDeleteTenaye Nafekegn(ITAly)
yamral!
ReplyDeleteእንዲህ እንዲህ በለን እንጂ!!! ተባረክ ወንድሜ፣ የጻፍክበት እጅህ ይባረክ፣ አብዝቶ አብዝቶ ይጻፍልን፣ ማስተማር እንደዚህ ነው፡፡ እያዋዙ፣ እያሳሳቁ፣፡፡ ለካስ እግር ኳስ እንዲህ የሕይወት ትምህርት ይሰጣል፡፡ ላስተዋለው ማለት ነው እንዳንተ በአራት አይን ላየው፡፡ ላልታደሉትማ ከመስታወት መስበሪያነትና ከድራፍት መራጫነት አያልፍም፡፡
ReplyDeleteትዕግስት
ፀጋው ይብዛልህ ዳኒ!!!
ReplyDeletei hope Ethiopia is so great by their brilliant and famous writers like dn dani. i am so exited to be read your paper and i am so glad to have your papers reader. God plesses Ethioppia forever.
ReplyDeletewell said.may God give you the wisdom and the strength to write more!
ReplyDeleteEgziabher keante gar yihun!
tsihufih ejig ejig mekari new berta"Amhara"yemilewun gin batitekem enem des yilegnal wode semen akababi bithed eslamina amara yehaimanot enji yegosa megelecha ayidelemina egnam yihin land"biher"yetesete siyame kesemanew ke EPRDF gar 20 ametachin akeberin biyanis ante atitekemewu Dani-eniwodihalen
ReplyDeleteOne thing that I don't understand here,do Tigray Christians call themselves Amhara to identify their religion from Islam?
DeleteGo Dani!..we thank God for giving you the wisdom and good will to write for us!
ReplyDeleteThose who try to comment if dani should write this and that...dani is just one person..why don't u get your own blog or what ever and write :)..other wise give us peace and get the hell out of here!...Go Dani go...God Bless U!
This is Good Guys,But it will be so nice if we translate the POSTS positively and in a BROAD mind....
ReplyDeleteThanks to all of you!
dane beka kalat yelegnim ........bertalign!!!!!!!!!
ReplyDeleteAnonymous May 10,2012 12:13,you are realy a surprizing purson are you protecting the readers to not give any comment,writers like Daniel Kibret needs different comments from different attitudes and views .Not a comment like yours,he knows what he is doing that is why he is accomodating any comments .Your peace is in your mind not in the comments given by others.One person can have ablog can commit a mistake and needs a comment.Wondim yihin complexam behaviourihin ezawu balhibet Daniel kibretin gin hulum yiwodewal .Betsihufum,yetelayeye comment bemastenagedum ya malet gin perfect new malet ayidelem
ReplyDeleteHi, poeple common ,let's learn more from Dani ,thankyou ,
ReplyDeletemarshet
MSC student at aau .
hi , everybody common don't be negativethinker , learn more from DANI
ReplyDeleteዳኒ እንደ ሐዋርያት በምቹ ጊዜ በቃል በማይመች ጊዜ በጽሑፍ አፅናንተኽናልና
ReplyDeleteእግዚሃብሄር ይስጥልን ቃለ ሕይወት ያሰማልን::
thank u.........thank u alot dani
ReplyDeleteሁሉንም ጽሑፍ አንብቤዋለሁ፡፡ አተያየቱም ሆነ ይዘቱ እጹብ ያሰኛል፡፡
ReplyDelete/ያልተጻፈ ለምታነቡ፣ ላልተነገረ መልስ ለምትሰጡ፣ እኔ የፈለኩትን ለምን አልጻፈም ለምትሉ፣ ዳንኤልን የሐገር ሳይሆን የቡድን ብቻ አድርጋችሁ ለምታስቡ በናታችሁ ገለል በሉልንና ስለሰው እና ስለሰው እንስማበት፡፡/
ይቴ
ዳኒ እንደ ሐዋርያት በምቹ ጊዜ በቃል በማይመች ጊዜ በጽሑፍ አፅናንተኽናልና
ReplyDeleteእግዚሃብሄር ይስጥልን ቃለ ሕይወት ያሰማልን::
Wonderful , It the gift of GOD to express you view and share among us , I understand you can say what you want to say.Every time when I read your article I always admired by the examples you use to elaborate the idea and relate it with the core point.
ReplyDeleteI have no more word to say except keep up your good work.
remain Blessed.
God bless you Daniel.
ReplyDeleteBizu serawit bezuriyaw bisefrum Egziabher tekitun hezbun yitebqal.
It is good but make it analyze before you post!!
ReplyDeleteGREAT!
ReplyDeleteIt is all about LIFE. - Mamen and Metagel.
Great.
Ababu
AnonymousApril 30, 2012 8:48 PM
ReplyDeleteስለ ዋልድባ መልስ የሰጠኸው ወንድሜ ክርስቲያን ከሆንክ ትእግስትን ብቻ ሳይሆን ለእግዚአብሔር ቤት ቀናኢነትንም መያዝ አለብህ:: "እንደርግብ የዋህ: እንደ እባብ ልባም" መሆን እንዳለብን ጌታችን አስተምሮናል:: በክርስትና እየኖርን አንዱን ብቻ መሆን አንችልም፤ ለድኅነትም አያበቃንም:: ከሰለስቱ ደቂቅ ሃይማኖትና ተጋድሎ መማር አለብን:: ለጣኦት አምላኪው ንጉስ ሰጥ ለጥ ብለው ይገዙ ነበር:: እስከመቼ? 'ለጣኦት ስገዱ' እስከሚባሉ ድረስ:: ከዚያ በኋላ ግን ሃይማኖታቸውን መግለጥ ግድ ሆነባቸው::
አንድ ክርስቲያን ለምድራዊ ንጉስ (በስጋው ብቻ)መገዛት እንዳለበት መጽሐፍ ቅዱስ ያዘናል:: ነገር ግን አንዲት የቀረችን የነፍሳችን ህልውና (ሃይማኖታችን) እስክትጠፋ መሆን የለበትም:: ይህ ትእግስት ሳይሆን 'ጅልነት' ነው::
አለበለዚያ እንደ ፈሪው ሰውዬ እንሆናለን (ጅብ ሌሊት መጥቶ እግሩን መብላት ሲጀምር ሚስቱ ሰምታ 'ምንድነው የሚንኮሻኮሸው?' ብትለው በሹክሹክታ 'ዝም በይ ጅቡ እግሬን እየበላኝ ነው' እንዳለው)
ወንድማችን እንዳልከው ይህ ሁሉ የማይቀር:የእግዚአብሔር ፈቃድ እንኳን ቢሆን እኛ ክርስቲያኖች አሰላለፋችንን መምረጥና ማስተካከል አለብን (ከእግዚአብሔር ጋር ነን ወይንስ በተቃራኒው?) መሃል ሰፋሪ መሆን አይቻልም:: በክርስትና የምንሰ
እድል ከሰሜን ወደ ደቡብ፣ ትግል ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ ሲጓዙ አንድ ቀን ይገናኛሉ፡፡
ReplyDeleteThen what?????
Deleteነፍሴ ሆይ እኔ ለመዳን ተስፋ ብቆርጥም እርሱ እኔን ለማዳን ተስፋ አይቆርጥምና አይዞሽ
ReplyDeleteGod bless you dani
ReplyDeleteGod bless you!
ReplyDeleteThanks a lot Dani. I don't surprised with some individual saying b/c it don't start now but there are talkative individual starting from birth of Jesus Christ!!! so it nothing!!!
ReplyDeletethanks a lot bro!
ReplyDeleteberta wondimachin
ReplyDelete