ከጥቂት ዓመታት በፊት ኢየሩሳሌምን ለመጀመርያ ጊዜ ለማየት መጥቼ ነበር፡፡ ስመለስ አውሮፕላኑን የሞሉት ቤተ እሥራላውያን ነበሩ፡፡ በመካከሉ አንዱን ሽማግሌ «የት እየሄዳችሁ ነው?» ብዬ ጠየቅኳቸው፡፡
«ወደ አዲስ አበባ» አሉኝ፡፡
«ምነው አልቀበል አሏችሁ እንዴ» ስል መልሼ ጠየቅኳቸው፡፡
«ኧረ ከሄድን ስድስት ዓመታችን ነው» አሉኝ፡፡
«ታድያ ለምን ትመለሳላችሁ»
«ዋንዛዬ ጠበል ልንነከር
ነው»
ዋንዛዬ ጠበልን ዐውቀዋለሁ፡፡ ደቡብ ጎንደር የሚገኝ ፍል ጠበል ነው፡፡
«እናንተ ቤተ እሥራኤል አይደላችሁ እንዴ እንዴት ዋንዛዬ ጠበል ትሄዳላችሁ»
«ብንሆንስ የኖርንበት አይደል፤ የኖርንበትን ልንተወው ነው» ተገርመው ነበር የመለሱልኝ፡፡
እውነታቸውን ነበር፡፡ መልካቸው፣ጠባያቸው፣ ባህላቸው፣ አምሮታቸው፣ ሥነ ልቡናቸው ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ አንድ ሊቅ አንድ ጊዜ እንዲህ ብለው ጠይቀው ነበር፡፡
«ሰው ነው በሀገር ውስጥ የሚኖረው ወይንስ ሀገር ነው በሰው ውስጥ የሚኖረው?»
አንዳችን ይህንን ሌሎቻችን ደግሞ ያንን መለስን፡፡
እርሳቸው ግን እንዲህ አሉን «መጀመርያ ሰው በሀገር ውስጥ ይኖራል፡፡ ይህ ቀላሉ ነገር ነው፡፡ የመወለድ ጉዳይ ነው፡፡ የፈቃድ ጉዳይ ነው፡፡ የአሠራር ጉዳይ ነው፡፡ የመታወቂያ ጉዳይ ነው፡፡ ዋናው ከዚያ በኋላ የሚመጣው ነው፡፡»
«ከዚያ በኋላ ምን ይመጣል?»
«ከዚያ በኋላ ግን ሀገር በሰው ውስጥ ትኖራለች፡፡ ይህችን ሀገር በሰው ልብ ውስጥ የሚተክላት ፍቅር ነው፣ ባህል ነው፤ ቤተሰብ ነው፤ እምነት ነው፤ ታሪክ ነው፤ ከዚያም በላይ ደግሞ አንዳች ሁላችንም የማናውቀው ኃይል ነው፡፡ እውነተኛ ዜጎች በሀገራቸው ውስጥ የሚኖሩ አይደሉም፡፡ ሀገራቸው በእነርሱ ልብ ውስጥ የምትኖር ናቸው፡፡ እነዚህ ዜጎች የትም ይኖራሉ፡፡ ሀገራቸው ግን በልባቸው ውስጥ ናት፡፡
«ሰውን ከሀገር ማስወጣት ቀላል ነው፡፡ የኃይል ጉዳይ ነው፡፡ የጊዜ ጉዳይ ነው፡፡ የሥልጣን ጉዳይ ነው፡፡ የመሬት ጉዳይ ነው፡፡ የፍርድ ጉዳይ ነው፡፡ የዐቅም ጉዳይ ነው፡፡ ሀገርን ከሰው ልብ ውስጥ ማውጣት ግን በጣም ከባድ ነው፡፡ ማንም ባለ ሥልጣን፣ ማንም ባለ ጉልበት፣ ማንም ባለ ጊዜ፣ የሚችለው አይደለም፡፡
«አንዳንዴ ራሱ ሰውዬው እንኳን አይችልም፡፡ እነዚህ ዘፋኞች ሲዘፍኑ «ሕመሜ» የሚሉትን ነገር ታውቃላችሁ? የሚወዱትን ነገር «ሕመሜ» ይሉታል፡፡ ተመልከቱ ያንን ነገር ይወዱታል፡፡ ነገር ግን ደግሞ ሲያስቡት ያማቸዋል፡፡ ሊጠሉት አልቻሉም፡፡ ሊተውት አልቻሉም፡፡ የተውት እና የረሱት ይመስላቸዋል፡፡ ግን ደግሞ ሲያስቡት ያማቸዋል፡፡ ነገሩ ከደማቸው እና ከነፍሳቸው ጋር ተዋሕዷልና መንቀል ይከብዳቸዋል፡፡ ባላሰቡት እና ባልጠበቁት ሁኔታ እየወጣ ያስቸግራቸዋል፡፡ ስለዚህ «ሕመሜ» ይሉታል፡፡ ሰው ሲያምመው ያለቅሳል እንጂ እንዴት ይዘፍናል? የሚያስዘፍን ሕመም አለ ማለት ነው፡፡
«ሀገርም ለአንዳንዶች እንዲህ ናት፡፡ የሚዘፍኑላት ሕመም ናት፡፡ ነቅለው ሊያወጧት ወይንም ተክለው ሊያጸድቋት ያልተቻለቻቸው ሕመም፡፡»
እኒህ ሊቅ እውነታቸውን ነው፡፡ ሂዱ ግቡ ቴሌ አቪቭ፣ የእሥራኤል የፖለቲካ ከተማ፡፡ አያሌ ቤተ እሥራኤላውያን ሠፍረዋል፡፡ እነርሱ ራሳቸው ትንሿ ጎንደር ይሏታል፡፡ እንኮየ መስክን ጎንደር ላይ ታውቁታላችሁ? ዋናው የጠላው ሠፈር፡፡ አዝማሪ ሲያቀነቅን የሚያመሽበት ሠፈር፡፡ እዚህ ቴሌ አቪቭ አለላችሁ እንኮየ መስክ፡፡
እናንተ ይኼ ይገርማችኋል፡፡ ከጠላ ቤት አጠገብ ጣሳ ተተክሎ ብታዩ ምን ልትሉ ነው? ጎንደር እንኮየ መስክ እንዳይመስላችሁ፡፡ እዚህ በሰው ሀገር እሥራኤል ቴሌ አቪቭ ውስጥ ነው የምላችሁ፡፡ እነዚህ ቤተ እሥራኤላውያን ከኢትዮጵያ ወጥተው መጥተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ግን ከእነርሱ ልቡና ልትወጣ አልቻለቸም፡፡
በሠለጠነው የአዲሲቱ ኢየሩሳሌም አውራ ጎዳና ላይ በቆዳ በተሠራ አንቀልባ፤ ያውም በዛጎል በተጌጠ ልጇን አዝላ የምትጓዝ እናት ታያላችሁ፡፡ እርሷ እምነቷ ይሁዲ እንጂ ልቧ ኢትዮጵያዊ ነውኮ፡፡ ግቡ ወደ ቤተ እሥራኤላውያን መንደር፡፡ ቋ ቋ ቋ ቋ ቋ ቋ የሚል ድምጽ ወደ እኩለ ቀን ስድስት ሰዓት አካባቢ ትሰማላችሁ፡፡ ጠርጥሩ እስኪ ምን ይመስላችኋል? ቡና ተቆልቶ እየተወቀጠኮ ነው፡፡ ከመንገድ ላይ የሚገዛ ቡና ንክች የማያደርጉ አያሌ ቤተ እሥራኤላውያን አሉ፡፡
እንዲያውም ዛሬ በቤተ እሥራኤላውያን ሬዲዮ ጣቢያ በእሥራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ሕላዌ ዮሴፍ ቀርበው ነበር፡፡ ቤተ እሥራኤላውያንን እያስጨነቀ ያለውን ጥያቄ ሊመልሱ፡፡ የምን ጥያቄ ይመስላችኋል?
«እንጀራ ካልበላሁ ምኑን በላሁት» የሚሉ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ወገኖች እዚህ አሉን፡፡ የሚያሳስባቸው የጤፍ ጉዳይ ነው፡፡ ጥያቄያቸው የእንጀራ ጥያቄ ነው፡፡ እዚህ ትንሿ ጎንደር ብቻ ሳይሆን በየቤቱ የዶሮ ዓይን የመሰለ ጠላ የሚጠምቁ ባለሞያዎች ሞልተዋል፡፡ እንዲያውም አንዷ ባለሞያ የጠመቁት ጠላ በጉዟችን መሐል ቀርቦ የአዲስ አበባ እናቶች ጉድ ጉድ ሲሉለት ነበር፡፡
አንዲት እናት እንዲያውም «እነዚህን የመሰሉ ወይዛዝርት እዚህ መጥተው ነዋ ሀገር ቤት ጠላው አልጥም ያለን» ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፡፡ ምን ጠላውን ብቻ፡፡ ብርሌ የሚያስም ጠጅ የሚጥሉም ሞልተዋል፡፡ ታድያ ምን ያደርጋል፡፡ ይሄ ሁሉ ሞያ ተሰልፎ ዶሮው በነጭ ጤፍ እንጀራ ካልቀረበ ነገር ተበላሸ፡፡
«ጋዜጠኞቹ እንዴው የጤፍ ጉዳይ ምን ይሻላል? እዚህ እንጀራ ሳይበሉ ውለው የማያድሩ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ዜጎች አሉ፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት አስተያየት ሊያደርግልን ይገባል» ሲሉ ነበር፡፡
እነዚህን ቤተ እሥራኤላውያን ከመቀመጫቸው አስፈንጥሮ የሚያስነሳቸው የእሥራኤልን ሀገር ዜማ ሲሰሙ እንዳይመስላችሁ፡፡
«እምየ ጎንደር ጎንደር ጎንደር
የፋሲል ከተማ የቴዎድሮስ ሀገር» የሚለውን የሰሙ ጊዜ ነው፡፡ ያን ጊዜ አንገት ይወልቃል፤ ትከሻ ተፈታትቶ ይቀመጣል፤ ወገብ በነጠላ ሸብ ይደረጋል፡፡ ሽልማት ይጎርፋል፡፡
ሀገርን ከልብ ማውጣት ከባድ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ከአንድ መቶ በላይ በሚሆኑ ሀገሮች ተበትነዋል፡፡ ከሀገራቸው ወጥተው የሚኖሩ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ዜ¯ች እንዳሉን የሚገምቱ አሉ፡፡ ከአብዛኞቹ ልብ ውስጥ ግን ሀገራቸው አልወጣችም፡፡
ታላቁ አባት አትናቴዎስ ከባዛንታይናውያን በደረሰበት ጥቃት በተደጋጋሚ የእስክንድርያን መንበር እየተወ ተሰድዶ ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ሮም ተገኝቶ በነበረ ጊዜ የሮሙ ሊቀ ጳጳስ ከእስክንድርያ በመባረሩ ማዘናቸውን ገለጡለት፡፡ እርሱም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው «እኔን ከእስክንድርያ ማስወጣት ቀላል ነው፡፡ ከባዱ እስክንድርያን ከእኔ ልብ ውስጥ ማስወጣት ነው፡፡ እስክንድርያ ሩቅ አይደለችም፡፡ እስክንድርያ እኔ ልብ ውስጥ ናት፡፡ እኔ የማዝነው ከእስክንድርያ ሲያስወጡኝ አይደለም፡፡ እስክንድርያ ከእኔ ልብ ውስጥ ከወጣች ነው» ነበር ያለው፡፡
በአሁኑ ጊዜ አራት ዓይነት ኢትዮጵያውያን አለን፡፡
- ኢትዮጵያ ውስጥ
ያሉ፤
ኢትዮጵያም
በእነርሱ
ውስጥ
ያለች
እነዚህ ኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ያለችው ኢትዮጵያ ልዩ ናት፡፡ በሀገራቸው ውስጥ ሆነው፣ ችግሯን እና መከራዋን ሁሉ አብረው ተቀብለው፤ ቢያዝኑም ሳይማረሩባት የሚኖሩ ናቸው፡፡ አቡነ ሺኖዳ «በአካል ካለችው ግብጽ በልባችን ውስጥ ያለችው ግብጽ ትበልጣለች» እንዳሉት በእነዚህ ኢትዮጵያውያን ውስጥ ያለችው ኢትዮጵያም ታላቅ ናት፡፡ በቀበሌው፣ በአስተዳደሩ፣ በአመራሩ፣ በአሠራሩ፣ በኢኮኖሚው፣ በኋላ ቀርነቱ ወዘተ ምክንያት በሚደርሰው ነገር አይለኳትም፡፡ እዚህ በዓይናቸው የሚያዩት ገጽታ በውስጣቸው ያለችውን ኢትዮጵያ ገጽታ አይቀይርባቸውም፡፡ የእነርሱ ኢትዮጵያ ታላቅ ናት፤ ኩሩ ናት፤ ጀግና ናት፤ ነጻ ናት፤ ውብ ናት፤ ፍቅር ናት፤ ሥልጡን ናት፡፡ ሲሠሩ፣ ሲደክሙ፣ ሲያለሙ፣ ሲሠው፣ ሲከፍሉ፣ በልባቸው ላለቺው ኢትዮጵያ ነው፡፡ በሚያዩዋት ኢትዮጵያ እንጂ በልባቸው ባለቺው ኢትዮጵያ አይማረሩም፡፡
- ኢትዮጵያ ውስጥ
ያሉ፣
ኢትዮጵያ
ግን
በእነርሱ
ውስጥ
የሌለች
እነዚህ በኢትዮጵያ ውስጥ አሉ፡፡ አንዳችም የኢትዮጵያ ጠባይ፣ ባህል፣ ፍቅር፣ ክብር፣ አመል፣ ስሜት፣ ወኔ፣ ቅንዐት በልባቸው ውስጥ የለም፡፡ ለእነርሱ ኢትዮጵያ መልክዐ ምድር ብቻ ናት፡፡ ቦታ ብቻ ናት፡፡ በሰሜን ኤርትራ፣ በደቡብ ኬንያ፣ በምዕራብ ሱዳን፣ በምሥራቅ ሶማልያ እና ጂቡቲ የሚያዋስኗት ሀገር ብቻ ናት፡፡ አለቀ በቃ፡፡ ኢትዮጵያ ብትወድቅ ብትነሣ፣ ብትሞት ብትድን፤ ቢያልፍላት ባያልፍላት፣ ብታድግ ብትደኸይ አይገዳቸውም፡፡ ሊጠቅሟት ሳይሆን ሊጠቀሙባት ብቻ ይፈልጓታል፡፡ ስለ እነርሱ እንድትኖር እንጂ ስለ እርሷ እንዲኖሩ አይፈልጉም፡፡ ለእርሷ አይሠውም፤ ለእነርሱ ግን ይሠውዋታል፡፡
- ከኢትዮጵያ የወጡ፣
ኢትዮጵያ
ግን
ከእነርሱ
ልብ
ያልወጣች፣
እነዚህ ደግሞ ወደውም ሆነ ሳይወዱ ከሀገር የወጡ ናቸው፡፡ በአካል ከሀገር ርቀዋል፡፡ በልባቸው ግን ኢትዮጵያን ፀንሰዋል፡፡ ደማቸው፣ ጠባያቸው፣ እምነታቸው፣ ዐመላቸው፣ ባህላቸው፣ ስሜታቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ ስሟን ሲሰሙ አንዳች ነገር እንደ ኤሌክትሪክ ይነዝራቸዋል፡፡ ልጆቻቸውን፣ ቤታቸውን፣ አቆጣጠ ራቸውን፣ ሃሳባቸውን፣ ምኞታቸውን፣ ጸሎታቸውን ሁሉ ኢትዮጵያኛ አድርገውታል፡፡ ለእነርሱ የጊዜ ጉዳይ ነው፡፡ አንድ ቀን ነፍሳቸውም ሥጋቸውም እዚያው ኢትዮጵያ ትኖራለች፡፡ ቢሞቱ እንኳን ሥጋቸው እንዲመለስ ይፈልጋሉ፡፡
- ከኢትዮጵያ የወጡ፤
ኢትዮጵያም
ከእነርሱ
ልብ
የወጣች
እነዚህ ደግሞ የሚኖሩትም ውጭ ነው፤ ኢትዮጵያም ከእነርሱ ወጥታለች፡፡ ምናልባትም መልካቸው ብቻ ካልሆነ በቀር አንዳችም ከሀገራቸው ጋር የሚያመሳስላቸው ነገር በዲኤን ኤ እንኳን ላይገኝ ይችላል፡፡ ለእነርሱ ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ የምትገኝ አንዲት ሀገር ናት፡፡ በቃ፡፡ ብትኖር ብትሞት ስሜት አይሰጣቸውም፡፡ አይኖሩባትም፤ አትኖርባቸውም፡፡ «ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ፣ ባላስብሽ ምላሴ ከትናጋዬ ትጣበቅ» የሚል ምሕላ የላቸውም፡፡ ኢትዮጵያን ከልባቸው ማውጣት ብቻ ሳይሆን ከልጆቻቸው ልብ አንዳትገባም አድርገዋታል፡፡
በዓለም ባሉ ቋንቋዎች ሁሉ ሁለት ቃላትን መተርጎም ከባድ ነው ይባላል፡፡ «ፍቅር እና ሀገር»፡፡ ልብ እንጂ ቃል አይተረጉማቸውምና፡፡
እኛስ ከየትኞቹ ወገን ነን?```
በዳላስ ያለነውን የተዋህዶ ልጆች በኢትዮጵያ ሲኖዶስ ስር እያመለከ ያለውን ህዝብ የማህበረ ቅዱሳን አባል የሆኑት አንድ ቄስ አንዳንድ የማህበሩን አባላትን ይዘው የራሳቸውን ርካሽ ጥም ለማርካት ለመሳሪያነት ዘርና ፖለቲካ እያራገቡ ቤተክርስቲያናችንን ሊከፍሉ ህዝቡን ሊለያዩ ነው።
ReplyDeleteከየትኛው ወገን እንደሆኑ ያስታውቅበወታል
DeleteThe person you post above is crazy.You post unrelated issue.የኢትዮጵያ ሲኖዶስ ይመለካል እንዴችግሩ ያለው ካንተ እንጅ ከማህበሩ ቄስ አይመስለኝም።ዘርና ፖለቲካ ያለው በአንተ ቤት ውስጥ ነው...ልብህ ያውቀዋል...በተ.ቁ.፬ ያለህ መሰለኝ.....
Deleteእባክህ ወንድሜ ዘር ለዱባና ለድንች ነው መጀመሪያ ማንነትን እወቅ ዝም ብሎ ነቀፋ ማን ይሉታል ደግሞ የሚመለከውን ሳታውቅ ነው እንደ የምታወራው ብዙ ቢያወሩ ሆድ ባዶ ይቀራልና መጀመሪያ መለያየትን ከራሳችን እናውጣው ደግሞ ሃሳብህ ፍየል ወዳ ቅዝምዝም ወድህ ነው ሲበሉ የላኩት እንደሚባለው ኣንተም ለመንቀፍ ስለቸኮልክ ሃሳቡን ኣልተረዳህም እግዚኣብሔር ወደ ኣንድነት ያምታህ
DeleteWhy don't you take it as the expansion of the Ethiopian Orthodox Church even if your "comment"/idea is not compatible with the topic of the article.
Deleteይሄው እንግዲህ "ማኅበሩ ተነካ ብላችሁ አካኪ ዘራፍ ብላችሁ አቧራ ስታነሱ" ገለሰቡ/ቧ የሰጡት አስተያየት በምንም መልኩ ከዚህ ጽሑፍ ጋር አይገናኝም:: አንባቢም አድማጭም ይዳኘዋል:: ዳንኤልም እኮ አስተያየቱን ሲያወጣው ይህንን ሳይገነዘብ ቀርቶ አይመስለኝም:: ችግራችሁ (በፊት እናንተ ጋር ለ15 ዓመታት በአባልነት ስሠራ ስለነበረ ችግራችን ልበልና) አንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ እንደዚህ ዓይነት የተለየ ሀሳብ ሲያነሳ ወይም አባላችሁ ብያዝንባችሁ ቁጭ ብላችሁ የአባላቶቻችሁን ሕይወት በፍጹም ክርስቲያናዊ ፍቅር የመረዳትና አዝናችሁ የመርዳት አንዳች ነገር አልፈጠረባችሁም:: ልክ እንደ ዱር ቀበሮ ተቀባብሎ መንከስ ለምን???? እንደዚህ ዓይነት ተቃራኒ ሃሳብ ሲፈጠርበት እኮ አንድ ሰው ይጸለይለታል እንጂ አይሰደብም:: ከተሳደባችሁማ የቱ ጋ ነው ፍቅራችሁ? የቱ ጋ ነው አስተማሪነታችሁ? የቱ ጋ ነው የማኅበር አንድነት?
Deleteበሉ እንግዲህ ዳንኤል ይህንን አስተያየት ከለጠፈ ናዳችሁን አውርዱብኝ:: ካላወጣ ደግሞ "አንተ ራስህ እንደ አንድ ታላቅ (በዕድሜም በመንፈሳዊ ሕይወትህም) ታዘበኝ የጥያቄዬን መልስ ላንተው እተወዋለሁ::"
እንኳን አደረሰህ ዲ.ዳንኤል፡፡...ወደ ኢትዮጵያ የምንመለስበት ጊዜ ሩቅ አይደለም፡፡..."በዓለም ባሉ ቋንቋዎች ሁሉ ሁለት ቃላትን መተርጎም ከባድ ነው ይባላል፡፡ «ፍቅር እና ሀገር»፡፡ ልብ እንጂ ቃል አይተረጉማቸውምና፡፡"
ReplyDeleteThank You Dani! Ewedihalehu!
ReplyDeleteእንጀራ ካልበላሁ ምኑን በላሁት» የሚሉ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ወገኖች እዚህ አሉን፡፡ የሚያሳስባቸው የጤፍ ጉዳይ ነው፡፡ ጥያቄያቸው የእንጀራ ጥያቄ ነው፡፡ እዚህ ትንሿ ጎንደር ብቻ ሳይሆን በየቤቱ የዶሮ ዓይን የመሰለ ጠላ የሚጠምቁ ባለሞያዎች ሞልተዋል፡፡ እንዲያውም አንዷ ባለሞያ የጠመቁት ጠላ በጉዟችን መሐል ቀርቦ የአዲስ አበባ እናቶች ጉድ ጉድ ሲሉለት ነበር፡፡
ReplyDeletefor example my mother can do it very well but now due to poor life she leave to make Tella, in Ethiopia due to this racist Woyane Dihentu bezitual
thank you bro
እጅግ ጣፋጭ ምግበ ህሊና ነው ያቀረብክልን በጣም እናመሰግናለን
ReplyDeleteEne wondimeh ke Ethiopia yewetaw gen Ethiopia "setamegn setasamemegn" yemenor negn!!! endew men yeshalegnal? Yehe "besheta" medehanit yenorew yehon?
ReplyDeleteDn.Daniel,that is really deep observation!!!.
ReplyDeleteKeep in touch.
Dani betam ameseginalehu. wuste min endemiyalim lingerih.. " Ethiopia bewustachew yalech enesum be-Ethiopia wust yalu" yemiyametuat "Ethiopia" mayetna memot...beka!( plz, lets watch out the people catagorized in No.2 & 4 which are now trying to shape the present Ethiopia for only their interest.They are trying to ruin all our good culture,faith,love,religion....LIFE,COUNTRY) May God Bless Ethiopia.
ReplyDeleteዲ ን ዳንኤል በርታ !!!!!!!!!!!!!
ReplyDelete«ሰውን ከሀገር ማስወጣት ቀላል ነው፡፡ የኃይል ጉዳይ ነው፡፡ የጊዜ ጉዳይ ነው፡፡ የሥልጣን ጉዳይ ነው፡፡ የመሬት ጉዳይ ነው፡፡ የፍርድ ጉዳይ ነው፡፡ የዐቅም ጉዳይ ነው፡፡ ሀገርን ከሰው ልብ ውስጥ ማውጣት ግን በጣም ከባድ ነው፡፡ ማንም ባለ ሥልጣን፣ ማንም ባለ ጉልበት፣ ማንም ባለ ጊዜ፣ የሚችለው አይደለም፡፡
Dn. Daniel Egizeabher yistilin. yeante tsihuf eko ende wudase mariam yemidegagem new. Ene yihewilih ahun ahunima Ethiopian basebkuat gize enbaye yifesal. Ene sostegnaw negn Ethiopiaye mechem, beminim, endetim hona yematiwota. Hagere Egizeabher Ethiopia. Ahunim lezelalem tinurilin mesebsebiya enatachinin. yegize guday hono enji man ende enat man ende hager ayidel?
ReplyDeleteQale Hiywet yasemalin Dani,
ReplyDeleteMelkam Dagmai Tensae. Girum milketa new.Sint Gazetegnoch Eyerusalem hedewal andachwm endih neqsew altsafum. Bemereja zemen honen mereja yeteman nen eko. Ahun degmo liragem new. Yiqir yibelih belugn. ETV ....YIYILIH! Eneho Ye ETV propaganda le merejanet albeqa alen. Ahun le hizbu ye Areb hagerun miret,ye felashawn Ethiopian mewdedun,etc binegrut lehizbu minalebet.Malet Bereketoch barkew bifeqdulachew endiazegaju.
Thanks a lot Dani. Long live to Ethiopia, hope we believe God will restore all. Ay Ethiopia I love my country very much. It is a wonderful article. Thank you again Dani, may God Bless you more .
ReplyDeletewow,i like this issue.Dn.Daniel Kibret thank you
ReplyDeletereaky it is a good reflection about the current status of ETHIOPIA ,I think the isuue tha you share as is related to the idea of a genious men Mr Tewdros (Tedy Afro song's) .i did not mean that you are copy the idea, i know u are very hard
ReplyDeletethank D/n Dani
Dear I was on the first group but now am trying to be part of the second group or third group.Let me ask you one question . is human being created for nature/earth/land/country or did nature/land/country is created for him ? did Ethiopia is created for me or am born to her ? i think it is like the question of sun day for human being or human being for sun day ?
ReplyDeleteሰውን ከሀገር ማስወጣት ቀላል ነው፡፡ ሀገርን ከሰው ልብ ውስጥ ማውጣት ግን በጣም ከባድ ነው፡፡
ReplyDelete«እኔን ከእስክንድርያ ማስወጣት ቀላል ነው፡፡ ከባዱ እስክንድርያን ከእኔ ልብ ውስጥ ማስወጣት ነው፡፡ እስክንድርያ ሩቅ አይደለችም፡፡ እስክንድርያ እኔ ልብ ውስጥ ናት፡፡ እኔ የማዝነው ከእስክንድርያ ሲያስወጡኝ አይደለም፡፡ እስክንድርያ ከእኔ ልብ ውስጥ ከወጣች ነው»
ግሩም መልዕከት ነው! ወንድሜ ብዙ እንድትጽፍ ብዙ እድሜ ይስጥህ!እኛኮ የእግዚአብሔር ሕዝብ ነን ደግሞም በታላቁ መጽሐፍ ስለ እኛ እንዲህ ተብሎ የተጻፈውን ማስተዋል መልካም ነው
‘በውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ወይስ ነብር ዝንጕርጕርነትን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን?’ ኤር 13:23
ቸር ያሰማን!
we,who live in Ethiopia,also could not eat "Engera" once per day and can not buy "Doro" even for holiday because of inflation. This racist gov't couldn't govern us well. I don't know why our heavenly father keep silent.
ReplyDeleteselam
Arbaminch
ዳኒ ጽሁፎችህ በጣም አስተማሪዎች ናቸው፡፡ እጅግ ብዙ ቁምነገሮችን አስተምረኸናልና በጣም እናመሰግናለን፡፡ እግዚአብሔር እጅህን ያበርታ፡፡
ReplyDeleteyeah we all wish a country inscribed in our heart but in my 23 years on this world i have never seen our senior citizens doing any significant work or achivements for the whole nation. we dont have any one to inspire us but to look some other country and their citizens achiving something so we r a nation with out a leader and i shall suggest a real,true leaders not a hypocrates...........thanks
ReplyDeleteመልካቸው፣ጠባያቸው፣ ባህላቸው፣ አምሮታቸው፣ ሥነ ልቡናቸው ኢትዮጵያዊ ነው፡፡
ReplyDelete10q Dn.Daniiiiiiiiiiiiiiiiiiiiiii
ዳኒ አሁን አሁን ጥሩውንና የድሮውን ዳኒ እየሆንክ መጣህ:: እጅግ አስተማሪ ነው:: ለካ ኢትዮጵያውያን በሃሳብ አልግባባ ያልነው ለዚህ ነው?
ReplyDeleteSo dani that means you are still listening music shame on you. If some one monk or any other Christian listen, you and your companion start accusation hardly. You are a real Snake.
ReplyDeletewhat are you talking about? did he speak about music? ነው በልብህ ስታሰላስል የነበረውን ነው ምታወራው? ተመልሼ ደግሜ አንብቤም ስለምታወራው ላገኝ አልቻልኩም:: በግምት ሰውን ለዛውም ታላቅህን የምትሳደብ ሙዚቃ ባታዳምጥ ልዩነት አለው? ምናልባት እንኩዋን አዳመጠ ብንል ከሱ ያንተ ጥፋት ይብሳል:: ከሰባቱ ጥብቅ ትዛዛት አንዱን ነው የተረማመድክበት:: አንተም ክርስቲያን ነኝ ትል ይሆን? ልቦና ይስጥህ ከቻልክ ደግመህ አንበበው::
Deletesewuyew weyim liku yaweruletn sayastekal endale makrebu new zefen yemisema yasmeseleh? amarigna timihrt altemarkm enji bitimar noro ye milikitochin tikim tireda neber. <<....>> yemiyamelekitih tsehafiw yelela sew tsihuf eyetetekeme endehone new. lemehonu metsaf kidus endet yihon mitanebew yenezihn milikitoch tikim satawuk? yikirta tiyake abezahubh.
DeletePlease don't post evil/unconstructive ideas.This is an idea which can demarginalze the curent tribal hatered in our country. Such distructive commoment is not not good and not usefull.
DeleteWhat kind of person are you to reach such kind of silly conclusion? A person who live in this world can hear a worldly music, not willingly but in different situations. For eg. A monk, priest or Deacon or any devoted christian can hear a music when he/she goes in taxi, bus or any where. Zim bileh tilachahin beketita atigelitsim?
Deleteስንት አይነት ገመድ ጎታችም አለ ለካ? ምኑ ነው እስቲ ዘፈን አዳመጠ ያስባለሁ? ይህን ጊዚ የምሽት ክለብ አድማቂ ትሆናለህ:: ይህ ክርስትና ከመሰለህ ድግመህ ሰንበት ት/ቤት ሀ ብለህ ተማር::ዳኒ እንዲህ አይነት መርዘኞችን አታዳምጥ:: ከየት እንደሆኑ ያስታውቃሉ
DeleteYigermal yekesash neger.
Deleteስንት አይነት ገመድ ጎታችም አለ ለካ?
Deleteኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ፣ ኢትዮጵያ ግን በእነርሱ ውስጥ የሌለች
ReplyDeleteእነዚህ በኢትዮጵያ ውስጥ አሉ፡፡ አንዳችም የኢትዮጵያ ጠባይ፣ ባህል፣ ፍቅር፣ ክብር፣ አመል፣ ስሜት፣ ወኔ፣ ቅንዐት በልባቸው ውስጥ የለም፡፡ ለእነርሱ ኢትዮጵያ መልክዐ ምድር ብቻ ናት፡፡ ቦታ ብቻ ናት፡፡ በሰሜን ኤርትራ፣ በደቡብ ኬንያ፣ በምዕራብ ሱዳን፣ በምሥራቅ ሶማልያ እና ጂቡቲ የሚያዋስኗት ሀገር ብቻ ናት፡፡ አለቀ በቃ፡፡ ኢትዮጵያ ብትወድቅ ብትነሣ፣ ብትሞት ብትድን፤ ቢያልፍላት ባያልፍላት፣ ብታድግ ብትደኸይ አይገዳቸውም፡፡ ሊጠቅሟት ሳይሆን ሊጠቀሙባት ብቻ ይፈልጓታል፡፡ ስለ እነርሱ እንድትኖር እንጂ ስለ እርሷ እንዲኖሩ አይፈልጉም፡፡ ለእርሷ አይሠውም፤ ለእነርሱ ግን ይሠውዋታል፡፡
ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆኑት የአሁን የኢትዮጲያ ገዢዎችና አባ ገብረመድህን/አባ ጳዉሎስ/ ናቸዉ
ስለምንድን ነው ዘፈኑ ነው እንጂ ዘፈን ሁሉ ሀጢያት አይደል ወገን። በዛ ላይ በየአውራጎዳናው ላይ፣ በየሬዲዮኑ፣ ቲቪው ሲጮህ እየዋለ ክርስቲያን ሁሉ ደንቆሮ አይደል ታዲያ ጆሮ ሲጠልፍ አይደል እንዴ ሚውል ጃል። ስለሃገር ፍቅር፣ ጋራው ሸንተረሩ፣ ስለጀግንነት፣ ስለባህል፣ ስለሃዘን ደስታው፣ ስላለፈው መጪው፣ ስለህብረት፣ አንድነቱ... ሲዘፈን ብትሰማ አንተም አደራ ጌታን ያሳዘንክ መስሎህ ምስኪን ነፍስህን በከንቱ አታስጨንቅ። ሁሌ ሃሳብህ ስለእግዚአብሔር መንግስት ሆኖ ህይወትህ ምስጋና፣ ፀሎት፣ መዝሙር ብቻ ከሆነልህ እሰየው። ነገር ግን እንደው ቢገጥምህ ግን ተስፋ አትቁረጥ ባለማወቅም በሰው አትፍረድ። ለወንድማችን ለመከላከል ሳይሆን መሰረቱን የሸሸ ሃሳብ መስሎ ስለተሰማኝ ነው።
ReplyDeleteI'm so SOOORY 4 U . Cose u just learn one word to attack D/N DANI yyyyyyyy??? (U R A REAL SNAKE ) that's u'rs word .
ReplyDeleteYou are ignorant or immature novice Christian, which I hate to see
ReplyDeleteDon't hate someone for no reason. If you do that, it is an evil deed. I advise you to comment only on the article posted here or related issues. Don't follow the path of Satan; otherwise, your desitination will be the hell.
DeleteYours,
Tewodros
My brother U did not get the point.Or U must be falt finder. I think the reverse is true 4 U(great shame on U).By the way snake is very carefull animal.Thanks D dani. keep it up.
ReplyDeleteDaniye Egziabhair yibarkih.Berta.
ReplyDeleteDani minlibelih? Beyeletu anebalehu.bizu temirialehu.kemanebachew leloch negeroch hulun ejig betam bizu kante temiryalehu. God bless you. nurilin...............
ReplyDeleteedage
ReplyDeleteከኢትዮጵያ የወጡ ኢትዮጵያም ከእነርሱ ልብ የወጣች ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ነገር ግን ኢትዮጵያዊነትን በውስጥቻዉ ካጡት በእጅጉ ይሻላሉ፡፡ አሳሳቢዉ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ እያሉ ኢትዮጵያዊነትን በውስጥቻዉ ያጡት መብዛታቸዉ ነዉ፡፡
ReplyDeleteEthiopia'ye is always in my Heart & Blood,
ReplyDeleteAnten yeseten Yabatochachin Amlak yikber yimesgen
Thanks Dani
ReplyDeleteGod Bless you
ReplyDeleteጽሑፉን ሳነብ ከመመሰጥ ወይም ከመማረክ ብዛት ልቤ ካለበት ቦታ ወደታች ይሁን ወደላይ ወደቀኝ ይሁን ወደግራ እንጃ ብቻ ቦታውን የሳተ መሰለኝ፡፡ የመልዕክቱ ጥልቀት ምጥቀት መሰለኝ እንዲህ እንዲሰማኝ የያደረገ፡፡ ለሚረዱ ሁሉ የሚፈጥረው ስሜት የተለየ ነው፡፡ ለመግለጽ ይከብዳል፡፡ ለማይገባቸው ግን ሞኝነት መሆኑን ከአንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች ተረዳሁ፡፡ ለሁሉም ግን ዳኒ ጌታ ይባርክህ፡፡ በልባችን ያለውን ነገር ግን የማናየውን እውነት ግልጥልጥ አድርጎ የሚጽፈውን ብዕርህንና ይህን መሳይ ጥበብ የሚያፈልቀውን ማስተዋልህን ወደድኩት፡፡
ReplyDeleteትዕግስት
WOW! Daniel..Very touching and powerful message. I live in CA, USA the opposite side of the world from where I was born, and where I still feel draws and connections. I do not believe the heart automatically adopts a home. I think we keep parts of our past with us always, and more, those we love are elements of what we feel is home.
ReplyDeletewww.bereketdecor.blogspot.com
Thank you.. God Bless You for following your heart and your calling
WOW! Daniel..Very touching and powerful message. I live in CA, USA the opposite side of the world from where I was born, and where I still feel draws and connections. I do not believe the heart automatically adopts a home. I think we keep parts of our past with us always, and more, those we love are elements of what we feel is home.
ReplyDeletewww.bereketdecor.blogspot.com
Thank you.. God Bless You for following your heart and your calling
ለነገሩ ውሱን እውቀትና አንባቢ አለመሆን ብዙ ስህተቶችን እንድንሠራ ያደርጉናል፡፡ ስለዚህ አስተያየት ሰጭው መሀይም ስለሆነ አትፍረዱበት፡፡
ReplyDeleteዲ/ን ዳኒ አንተን ግን እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡ ጽሑፎችህ ይመቹኛል “አንብቡኝ! አንብቡኝ” ይለናል፡፡
ለነገሩ ውሱን እውቀትና አንባቢ አለመሆን ብዙ ስህተቶችን እንድንሠራ ያደርጉናል፡፡ ስለዚህ አስተያየት ሰጭው መሀይም ስለሆነ አትፍረዱበት፡፡
ReplyDeleteዲ/ን ዳኒ አንተን ግን እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡ ጽሑፎችህ ይመቹኛል “አንብቡኝ! አንብቡኝ” ይለናል፡፡
ፍቅር እራስን ቤተሰብን ጎረቤትን ከመውደድ ይጀምራል …. በትልቁ ስንለጥጠው ደግሞ ወደ “ሀገር” ፍቅር እያለ ይቀጥላል፡፡ ወንድሜ በጽሁፉ ከዘረዘራቸው የኢትዮጵያዊያን አይነቶች መሀከል እጅግ ተራ፣እርካሽና ለሀረሬ ባይተዋር ዜጋ መሆኔ ተሰምቶኛል፡፡ እውነት ሀገርን ለመውደድ ያቺ ሀገር ከበርቴ መሆን አለባት ወይስ ደም እራሱ ዜጋው ሀብታምና የተሳካለት ሰው መሆን ይኖርበታል?
ReplyDeleteጸሀፊውን አመሰግናለሁ!!! የፍቅር አምላክ ፍቅርን በልባችን ያኑርልን
ፍቅር እራስን ቤተሰብን ጎረቤትን ከመውደድ ይጀምራል …. በትልቁ ስንለጥጠው ደግሞ ወደ “ሀገር” ፍቅር እያለ ይቀጥላል፡፡ ወንድሜ በጽሁፉ ከዘረዘራቸው የኢትዮጵያዊያን አይነቶች መሀከል እጅግ ተራ፣እርካሽና ለሀረሬ ባይተዋር ዜጋ መሆኔ ተሰምቶኛል፡፡ እውነት ሀገርን ለመውደድ ያቺ ሀገር ከበርቴ መሆን አለባት ወይስ ደም እራሱ ዜጋው ሀብታምና የተሳካለት ሰው መሆን ይኖርበታል ይሆን?
ReplyDeleteጸሀፊውን አመሰግናለሁ!!! “…….የፍቅር አምላክ ሆይ ልባችንን በፍቅር ሙላው “
Why don’t you say something like Dn Ephrem on the issues of MK? AS a member as well as a followers of EOTC I personally expect you to say some logical and convincing things
ReplyDeletetelba binchacha bandi mukecha yemibalewins alsemahim??????????????
DeleteDani egiziabher yabertah.
ReplyDeleteEgziabher yesetelen melkamu hulu yadelelen
ReplyDeleteዋው!!! ምግብ ተመገብኩ እረካሁም፤ ስለሆነም እየታየን ለመግለጥ ወደድኩ፤ ዲ/ን ዳኒ እንዳልመርቅህ የተመረጥህ ነህ……. ኃጢያተኛ ቢመርቅ እርግማን ስለሚሆንብህ ትቸዋለሁ፤ ምርቃትህ ግን ይድረሰኝ እያልኩ አምላኬን ተማፀንሁ!!! ውድ ወንድሜ አንተ ተባርካሀል ሰዎችንም እንድታስተምር ተመረጠኃል………አናም ይህ የአዕምሮ ምግብህን ሳትሰለቸን ትመግበን ዘንድ በምትዎዳት በድንግል ስም አማፀነሁህ!!! ኢትዮጵያ ነፃ መሆንን ትፈልጋለች!!!!! ነፃ ለማውጣት ወጣት አዛውንቶች እንነሳ…….
ReplyDeleteዋው!!! ምግብ ተመገብኩ እረካሁም፤ ስለሆነም እይታየን ለመግለጥ ወደድኩ፤ እንዲህም ገለፅኩ….. ዲ/ን ዳኒ እንዳልመርቅህ የተመረጥህ ነህ……. ኃጢያተኛ ቢመርቅ እርግማን ስለሚሆንብህ ትቸዋለሁ፤ ምርቃትህ ግን ይድረሰኝ እያልኩ አምላኬን ተማፀንሁ!!! ውድ ወንድሜ አንተ ተባርካሀል ሰዎችንም እንድታስተምር ተመረጠኃል………አናም ይህ የአዕምሮ ምግብህን ሳትሰለቸን ትመግበን ዘንድ በምትዎዳት በድንግል ስም አማፀነሁህ!!! ኢትዮጵያ ነፃ መሆንን ትፈልጋለች!!!!! ነፃ ለማውጣት ወጣት አዛውንቶች እንነሳ…….
ReplyDeleteእኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለሁና ኢትዮጵያን የምወድ ነኝ ፡፡ያበርታህ ወዳጄ፡፡
ReplyDeleteDn Danel yaneser eyetahen mene yahel adenaki endahonku lenagerh alechelm.
ReplyDeleteEnae Ka andegnaw group negn.
አንባሳ አደር ዳንኤል:
ReplyDeleteበመላው አለም ያሉ የተዋህዶ ልጆች ኢትዮጵያውያን ስለ ዋልድባ እና ባጠቃላይ ስለሀገራቸው እየተወያዩ ነው አንተስ ወደ ሌላ ርእስ የሰውን አይምሮ ለማስቀየር ለምን ተሞክራለህ? ማንነትህ ግራ አጋባን
ኧረ ጐበዝ ምነው ፀብ ፀብ፣ ነገር ነገር፣ አለን እሳ፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ እኮ ልክ ሰለፊዎችን በግልጽ ቋንቋ አክራሪ እንዳሏቸው ሁሉ፣ ማህበረ ቅዱሳንንም የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ አክራሪዎች ማለት ይችሉ ነበር፡፡ እኔ ግን የተረዳሁት በፖዘቲቭ ጐኑ ነው፡፡ ክርስቲያን ትዕግሥተኛ እንጂ እንደ ችኩል ጅብ ቀንድ አይነክስም፡፡ በዚህ ጐኑ ከአስተያየት መቆጠብህ አስደስቶኛል፡፡ ገና ለገና እንዲህ ነው እንዲያ ነው ያለው እያሉ መላ ምት ከማስቀመጥ፣ እርግጡ ሲመጣ የመልስ ምት መስጠት ይሻላል ባይ ነኝ፡፡
ReplyDeletegood Idea
ReplyDeleteThank you Dn.Daniel,May God bless you and all yours! please remember us in your prayer to be strong in our faith! Our ambition is to pass the true and only one religion to the world. wherever we are,we wish to go to our heavenly father for everlasting love,peace and glory.please everyone let us be positive and do our part for better future and make histry for the next generation!May God help us, Amen.
ReplyDeleteI like the way you addressed and categorized us! We have so many things that remember our country Holy land Ethiopia. Eating culture and foods (particularly the lovely ENJERA),multi-languages with amazing letters and numbers, the topology, weather conditions, even colors of our face, way of living, respect of elders, holy days celebrations, and many more.
ReplyDeleteThank brother.
አቦ አገሬ ናፈቀኝ!!!
What a nice reflection ...Blessed!
ReplyDelete2.ኢትዮጵያ ውስጥያሉ፣ኢትዮጵያግንበእነርሱውስጥየሌለች
ReplyDeleteእነዚህ በኢትዮጵያ ውስጥ አሉ፡፡ አንዳችም የኢትዮጵያ ጠባይ፣ ባህል፣ ፍቅር፣ ክብር፣ አመል፣ ስሜት፣ ወኔ፣ ቅንዐት በልባቸው ውስጥ የለም፡፡ ለእነርሱ ኢትዮጵያ መልክዐ ምድር ብቻ ናት፡፡ ቦታ ብቻ ናት፡፡ በሰሜን ኤርትራ፣ በደቡብ ኬንያ፣ በምዕራብ ሱዳን፣ በምሥራቅ ሶማልያ እና ጂቡቲ የሚያዋስኗት ሀገር ብቻ ናት፡፡ አለቀ በቃ፡፡ ኢትዮጵያ ብትወድቅ ብትነሣ፣ ብትሞት ብትድን፤ ቢያልፍላት ባያልፍላት፣ ብታድግ ብትደኸይ አይገዳቸውም፡፡ ሊጠቅሟት ሳይሆን ሊጠቀሙባት ብቻ ይፈልጓታል፡፡ ስለ እነርሱ እንድትኖር እንጂ ስለ እርሷ እንዲኖሩ አይፈልጉም፡፡ ለእርሷ አይሠውም፤ ለእነርሱ ግን ይሠውዋታል፡፡
ይሄ አሁን በስልጣን ላይ ያሉትን ሆዳሞችን ይገልፃል
በተለይ ኢሃዴግን
እኔ በአሁኑ ሰዓት የምኖረው ደቡብ ሱዳን ጁባ ውስጥ ነው፡፡ በስራ ምክንያት ከመጣው ገና አንድ ወር ከ20 ቀኔ ነው፡፡ ኢትዩጵያ ውስጥ እያለው ብዙ መልካም እሴቶች እንዳሉን ባውቅም ያን ያህል ትኩረት አልሰጣቸውም ነበር፡፡ ሰዎች ኢትዩጵያ ልዩ ናት ሲሉ ለማጋነን ይመስለኝ ነበር፡፡ አሁን ግን ለሀገሬ ያለኝ አመለካከት በምድር ላይ ያለ ኃይል ሁሉ ቢሰበሰብ ሊገልፀው የሚችል አይመስለኝም፡፡ በተለይ የህዝቡ ሰላማዊነት፣ ፊታችን ላይ ያለው እርግት ያለት ፀጥታ፣ ለውጭ ሰዎች ያለን ቀና አመለካከት፣ የቤተክርስቲያንን ጉዳይማ ማሰብ አልፈልግም አልጋዬ ላይ ተኝቼ ከየካ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የምሰማው ቅዳሴ፣እጣኑ፣ ካህናት ከቅዳሴ በኋላ እጃቸውን ስንስም የሚሸተው መልካም መአዛ፣ አሁዱ እሁድ ከቅዳሴ በኋላ የምንበላው አነባበሮ በቃ ምንም ትዝ የማይለኝ የማይናፍቀኝ ነገር የለም፡፡ፀሎት ሳደርግ ስለኢትዩጵያ አምላኬን የምለምነው ነገር ለራሴም ድንቅ ይለኛል ከራሴ የማፈልቀው እንኳን አይመስለኝ፡፡ በቀኝ አለመገዛት፣ ስመ እግዚአብሔር ጠዋት ማታ ስሙ ከሚጠራበት ሀገር መፍለቅ፣ አብሮ ከሚበላ ሕዝብ ውስጥ መገኘት፣ በክፍ በደግ መጠያየቅ በእውነት ኢትዩጵያ ከሁሉም ልዬ ነሽ እንጀራ ፍለጋ ከአንቺ ብለይም በልቤ ውስጥ ሁል ጊዜ አለሽ፡፡
ReplyDeleteማኪ
ጁባ
የነፍሴ ጨዋታ እጅግ ልዩ የሆነ ሰውን እያሰደሰተ የሚያስተምር
ReplyDeleteብዙ ነገር ተማርኩበት አመሰግናለሁ ሁል ጊዜም ምንጊዜም እመአምላክ ከአንተ ጋር ትሁን
በጣም አከብርሀለውህ.
ኢ.አ
Dan /Daniel May God bless you. Those of you who read this try to make ourselves in a better choose.
ReplyDeleteThank you Danie.
God bless Ethiopia
ውድ ዲያቆን ዳንኤል፤
ReplyDeleteመቸም ታላቅ ስጦታ ነው ያለህ። በሁሉም በምትጽፈው እኔም ባለቤቴም ድንቅ ይለንና ደስ ብሎን አስተያየት ለመስጠት እያሰብን ቆይ ነገ ስንል ወዲያው ደግሞ ተከታዩን ታወጣለህ። አንተን እንዲህ ለነፍስ ምግብ የሚሆን ሙሉ ጽሑፍ እያከታተልክ ለማውጣት ያበረታህን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን። እያነበበ ደስ እያለው፣ እየተደመመ፣ እየተጽናናበት፣ የደከመ እየበረታበት፣ እየተለወጠበት የሚጽፍልህ ብዙ እንዳለ የማይጽፈው ደግሞ አያሌ መሆኑ አይጠረጠርም። እና ምን ለማለት ነው? በርታ ብዙዎቻችን ትምህርትህን ስለምንጠቀምበት። ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
Egziabher yebelete ybarkh ...yehiwotin kal yasemalin !
ReplyDeletei don.t have any word to express what u understand about any activity of Ethiopia and related issue specially religion,i wish GOD give u the secret of every thing dani keep it u!!!
ReplyDeleteegabher yebarkh !!!
ReplyDeleteedmawen kena tsgaw yeseth
d/dany yabezh lala menm alelem
እስመ መንክር ይእቲ.....
ReplyDeletefirst of all i would like to appritate you daniel,it was amazing things you wrote. that is great to know our nation.some people they take it like fun,but it is real things, but i want to tell you my bro no matter our people critic you as bad write or some thing else and insulting you do not take it as sirouse.becouse it is as normal things,even try to advace them better.for sure you will be the best author for the futur, and God bless you.
ReplyDeletehaaa haa isrel yemechael ke gonder city but አሳሳቢዉ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ እያሉ ኢትዮጵያዊነትን በውስጥቻዉ ያጡት መብዛታቸዉ ነዉ come to help him bezue atweru eshe ena israel ney haymanota i am proud to from ethio but isral
ReplyDeleteNot missing anything to eat in Israel there is more food and faith and mutual respect for Jews from Ethiopia!
Let's not talk a lot of talk ........... let's do things will take care of Ethiopians who have lost hope in your country without gossip about the Jews on Israel
«ሰውን ከሀገር ማስወጣት ቀላል ነው፡፡ የኃይል ጉዳይ ነው፡፡ የጊዜ ጉዳይ ነው፡፡ የሥልጣን ጉዳይ ነው፡፡ የመሬት ጉዳይ ነው፡፡ የፍርድ ጉዳይ ነው፡፡ የዐቅም ጉዳይ ነው፡፡ ሀገርን ከሰው ልብ ውስጥ ማውጣት ግን በጣም ከባድ ነው፡፡ ማንም ባለ ሥልጣን፣ ማንም ባለ ጉልበት፣ ማንም ባለ ጊዜ፣ የሚችለው አይደለም፡፡
ReplyDelete