Tuesday, April 17, 2012

የዴር ሡልጣን ጥሪ

በኢየሩሳሌም የጥንቷ ከተማ ኢየሱስ ክርስቶስ ከጲላጦስ አደባባይ እስከ ጎልጎታ የተጓዘበት መንገድ አለ፡፡ ፍኖተ መስቀል ይባላል፡፡ ይህ መንገድ ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበላቸውን አሥራ አራቱን ሕማማት የምናስታውስበት መንገድ ነው፡፡ ኢየሩሳሌምን ለመጎብኘት የሚመጡ መንገደኞች ሁሉ በእያንዳንዱ ምእራፍ እየቆሙ ጸሎት በማድረስና በቦታው ላይ ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለውን መከራ በማሰብ እስከ ጎልጎታ የትሣኤው ቤተ ክርስቲያን ይደርሳሉ፡፡

በዚህ መንገድ የሚጓዝ ተሳላሚ ዘጠነኛው ምእራፍ ላይ ሲደርስ አንድ አስደናቂ ነገር ያያል፡፡ በጎልጎታ የሚገኙ ታሪካዊ እና ሃይማኖታዊ ቦታዎች ሁሉ በነጮች የተያዙ ናቸው፡፡ በቦታው የሚታዩት መነኮሳትም ነጮች ብቻ ናቸው፡፡ የኢየሩሳሌም ተሳላሚ ጥቁር አፍሪካውያንን የሚያየው ዘጠነኛው ምእራፍ ላይ ሲደርስ ነው፡፡ በዴር ሡልጣን የኢትዮጵያ ገዳም፡፡
ኢትዮጵያውያን ወደ ኢየሩሳሌም መጓዝ የጀመሩት ገና ክርስትና ሳይሰበክ መሆኑን የሐዋርያት ሥራን የጻፈልን ቅዱስ ሊቃስ በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ጉዞ አረጋግጦልናል፡፡ ከዚያም በኋላ በተለይም ክርስትና የሀገሪቱ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ በአራተኛው መክዘ ሲታወጅ አያሌ ክርስቲያኖች ወደ ኢየሩሳሌም ለተሳላሚነት ይሄዱ ነበር፡፡ እነዚህ ክርስቲያኖች በተሳላሚነት መጓዝ ብቻ ሳይሆን በዚያ በሚገኙ ቅዱሳን መካናት ገብተው በምናኔ ይኖሩ እንደነበር በቤተልሔም ለብዙ ዓመታት የኖረውን አባ ሄሮኒመስን  (ጄሮም) (347-420) ጨምሮ ብዙ የታሪክ ጸሐፍት መስክረዋል፡፡
የዐፄ ገብረ መስቀል ወንድም (አንዳንዶች ልጅ ይላሉ) ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው በዚያው ከመነኑት ኢትዮጵያውያን አንዱ ነበር፡፡ ይህ «ሙሴ አል ሐበሽ» ተብሎ የሚጠራው ኢትዮጵያዊ በተለይም በሶርያ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት ውስጥ ታላላቅ ሥራዎች ከሠሩ አበው አንዱ መሆኑን የሶርያ ቤተ ክርስቲያን መዛግብት ያስረዳሉ፡፡ በእርሱ ስም የተቋቋመው የመናንያን ገዳም ከደማስቆ 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከናብክ ከተማ አጠገብ ይገኛል፡፡
ከዐፄ ገብረ መስቀል በፊት ነግሠው በሀገረ ናግራን ዘመቻ ዝናቸው በመላው ዓለም የናኘው ዐፄ ካሌብም ከዘመቻው መልስ ዘውዳቸውን ወደ ኢየሩሳሌም የጌታ መቃብር ልከው ነበር፡፡ ይኼው ዘውዳቸው ከጎልጎታ ተሰርቆ ቤተ ልሔም በሩሲያውያን እጅ እንዳለ ይሰማል፡፡
«ሙሴ አል ሐበሽ» ገዳም
በመስቀል ጦርነት ጊዜ ብዙ ዓረቦች እየተሰደዱ ወደ ኢትዮጵያ በመግባታቸው ንጉሥ ላሊበላ እና ቅድስት መስቀል ክብራ እየተቀበሉ አስተናግደዋቸው ነበር፡፡ ሳላሕ ዲን የተባለው የዓረቦች ጦር መሪ ሮማውያን ድል አድርጎ ኢየሩሳሌምን በያዘ ጊዜ ለዚህ ውለታቸው ብሎ የጎልጎታን የጌታ መቃብር፣ የቤተ ልሔምን ቤተ ክርስቲያን እና እሌኒ መስቀል ያወጣችበትን የመስቀሉን ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያውያን ሰጥቷቸው ነበር፡፡
እነ ቅዱስ ላሊበላ፣ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ፣ አቡነ እዝራ፣ እና ሌሎችም ቅዱሳን ኢየሩሳሌም መጓዛቸውን ገድሎቻቸው ይተርኩልናል፡፡ በገድለ ዜና ማርቆስ ደግሞ ወደ ኢየሩሳሌም በተጓዙ የኢትዮጵያ መነኮሳት እና በመለካውያን መካከል ተደርጎ የነበረውን የሃይማኖት ክርክር በዝርዝር ይተርከዋል፡፡ በገድለ አቡነ እዝራም የኢየሩሳሌም መንገደኞች ይደርስባቸው የነበረውን መከራ እና እንግልት እናነባለን፡፡
1614 እኤአ ኢየሩሳሌምን ተሳልሞ የጻፈው ጣልያናዊ ተሳላሚ «በጎልጎታ ያለው የቅድስት ድንግል ማርያም እና የቅዱስ ጳውሎስ አብያተ ክርስቲያናት፣ በደብረ ጽዮን የሚገኘው የዳዊት ዋሻ፣ በቤተ ልሔም የሚገኘውም መቅደስ በኢትዮጵያውያን እጅ ነው» ብሎ ጽፎ ነበር፡፡
ሌላው ፈረንሳዊ ተሳላሚ ቻርለስ ፊሊፕ እንደሚለው «በጎልጎታ የሚገኙት የማርያም መግደላዊት፣ የቅዱስ ሚካኤል፣ የቅድስት ድንግል ማርያም፣ የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ እና የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ መቅደሶች የኢትዮጵያውያን ነበሩ፡፡»
የኢትዮጵያውያን ኃይል በኢየሩሳሌም እየተዳከመ የሄደው ቱርኮች ኢየሩሳሌምን ከያዙ በኋላ ነው፡፡ በአንድ በኩል የቱርክ ሁለተኛ ዜጎች ሆነው የመጡት ግሪኮች እና አር መኖች የኢትዮጵያውያንን ርስት ወሰዱ፡፡ በሌላ በኩል በቱርኮች እና በኢትዮጵያ መካከል ተደጋጋሚ ጦርነቶች በመደረጋቸው ኢትዮጵያውያን ወደ ቅድስት ሀገር ለመግባት አዳጋች ሆነባቸው፡፡ ከዚያም በላይ ደግሞ የዘመነ መሳፍንት የርስ በርስ ጦርነት ነገሥታቱ ለቅዱሳን ከማናት ይሰጡት የነበረውን ድጋፍ አስቆመው፡፡
የዴር ሡልጣን ገዳም
እነዚህ ሁሉ ሲደማመሩ እና የኢትዮጵያውያን ተሳላሚዎች እና መነኮሳት ቁጥር ሲቀንስ ቦታዎቻችንን ሌሎች እየወሰዱት ሄዱ፡፡ የመጨረሻውን የዴር ሡልጣን ርስት ደግሞ ግብጾች አብዛኛውን ሥፍራ ነጠቁን፡፡ በተለይም 1838 እኤአ በኢየሩሳሌም ገብቶ በነበረው ወረርሽኝ ብዙ ኢትዮጵያውያን መነኮሳት አለቁ፡፡ በዚህ ወቅት የኢየሩሳሌምን ከተማ በቱርኮች ሥር ሆነው የሚያስተዳድት ግብጾች ነበሩ፡፡ ይህንን አጋጣሚ ያገኙት ግብጻውያን መነኮሳትም እኛ የኢትዮያ ቤተ ክርስቲያን ጠባቂ ነን ብለው ቦታውን ተረከቡት፡፡ በገዳሙ የነበሩ መዛግብትንም አቃጠሏቸው፡፡
ከወረርሽኙ በኋላ የመጡት አበው ዋናው የዴር ሡልጣን ቦታቸው በግብጾች ተነጥቆ፣ ሌላውንም ሌሎች ተቀራምተውት ደረሱ፡፡ መጠጊያ ሲያጡም በእሌኒ የመስቀል ቤተ ክርስቲያን ጣራ ላይ ከጭቃ መጠለያ እየሠሩ ተቀመጡ፡፡ ኢትዮጵያውያን አበው ሰሚ እያጡ፣ እየተደበደቡ እና እየተባረሩ፤ እየታሠሩ እና እየተገደሉ አብዛኛውን ርስታቸውን ቢነጠቁም የቀረችውን ለማትረፍ ግን ባለ በሌለ ኃይላቸው ተጋድለዋል፡፡
በዚህ ዘመን ቅዱሳን ቦታዎችን ይዘው የነበሩት ግብጾች እና አርመኖች በኢትዮጵያውያን ላይ ያደርሱት የነበረውን ግፍ እና መከራ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚሲዮናዊነት ያገለገለው እንግሊዛዊው ሳሙኤል ጎባት ሲገልጠው «ኢትዮጵያውያን አስተዋዮች እና የተከበሩ ናቸው፤ ይሁን እንጂ በኢየሩሳሌም እንደ ባሮች ነበር የሚታዩት፡፡ በተለይም አርመናውያን እና ግብጾች እንደ አራዊት ይቆጥሯቸው ነበር፡፡ ኢትዮጵያውያን አርመኖች ደስ ካላላቸው በቀር ወደ ራሳቸው መቅደስ እንኳን ለመገባት መብት አልነበራቸውም፡፡ አንድ ጊዜ እንዲያውም ላረፈ ለአንድ አባላቸው ፍትሐት እንዳያደርጉ መቅደሳቸው በአርመኖች ተዘግቶባቸው ነበር፡፡ የበሮቻቸው ቁልፎች በጨቋኞቻቸው እጆች ነበሩ፡፡ ሲመሽ ይዘጉባቸውና አንዱ ደስ ያለው ግብጻዊ መጥቶ ጠዋት እስኪ ከፍትላቸው ይጠበቁ ነበር፡፡ በዚህም የተነሣ አንዳች የጤና እክል ቢደርስባቸው እንኳን ከመኖርያቸው ወጥተው ወደ ሕክምና ለመሄድ እድል አልነበራቸውም»
1850 አካባቢ በኢየሩሳሌም የእንግሊዝ ቆንስላ የነበረው ጄምስ ፊን ስለ ኢትዮጵያውያን አባቶች መከራ ሲገልጥ «የአርመኑ ሊቀ ጳጳስ ድኾቹን ኢትዮጵያውያን ያሰቃያቸው ነበር፡፡ ይገርፋቸዋል፤ በሠንሠለት ያሥራቸዋል፤አልፎ አልፎ ካልሆነም በቀር ወደ ቤተ መቅደሳቸው መግባትን ይከለክላቸዋል» ብሎ ነበር፡፡
ይህንን የመሰለው የመነኮሳቱ መከራ ነበር ዐፄ ቴዎድሮስን ኢየሩሳሌም ተጉዘው የኢትዮጵያውያንን መብት ለማስከበር እንዲመኙ ያደረጋቸው፡፡
ታጠቅ ብሎ ፈረስ ካሣ ብሎ ስም
ዓርብ ዓርብ ይሸበራል ኢየሩሳሌም ያስባሉትም ለዚህ ነበር፡፡ ራሳቸውም ሲፎክሩ «የኢትዮጵያ ባል የኢየሩሳሌም እጮኛ» ይሉ ነበር፡፡ ዐፄ ቴዎድሮስ ያሰቡት ሳይሳካ መቅደላ ላይ ዐረፉ፡፡ ዐፄ ዮሐንስ ከቱርክ በማረኩት አራት ብር የደብረ ገነት ኪዳነ ምሕረትን ሥራ አስጀመሩ፡፡ ንጉሥ ምኒሊክም አስፈጸሙ፡፡ ንግሥት ዘውዲቱ እና እቴጌ ጣይቱ ሕንፃ ገዙ፡፡ እቴጌ መነን የቅድስት ሥላሴን ቤተ ክርስቲያን አሠሩ፡፡ እነ አፈ ንጉሥ ነሲቡ፣ እነ ደጃዝማች ባልቻ፣ እነ ወይዘሮ አማረች ዋለሉ እነ ወይዘሮ በየነች ገብሩ፣ እነ ወይዘሮ አታየ ወርቅ የየራሳቸውን ሕንፃ እና ቦታ እየገዙ ገዳማቱን አጠናከሩ፡፡
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል መንገድ ተጉዘው ዘጠነኛው ምእራፍ ሲደርሱ እነዚህን ሁሉ እንዲያስታውስዎት የሚያድርግ አንዳች አሳዛኝ ነገር ያያሉ፡፡ ያሉበት ሀገር እሥራኤል መሆኑንም ይጠራጠራሉ፡፡ የቀሞሙበት ዘመን ሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን መሆኑን ለማረጋገጥም የዘመን መቁጠርያ ያስፈልግዎታል፡፡ ቁመታቸው አንድ ሜትር ተኩል እንኳን የማይሞላ፣ ስፋታቸው ከሁለት ካሬ ሜትር ያነሱ፣ ከጭቃ የተሠሩ ታናናሽ ቤቶችን ያያሉና፡፡ ከሁለት መቶ ዓመታት በላይ ያስቆጠሩት እነዚህ የጭቃ ቤቶች ቁጥራቸው ሃያ ስድስት ሲሆን ሁለት መቅደሶችንም ይጨምራሉ፡፡ መስኮቶቻው አየር እንጂ ሰው አያሳልፉም፡፡ አንዳንዶች ተሰነጣጥቀዋል፡፡ አንዳንዶች ጠቋቁረዋል፡፡ ሌሎች ተፈነቃቅለዋል፡፡ በተለይም ሁለቱ መቅደሶች ለመፍረስ የሚጠብቁት ቀናትን ብቻ ነው፡፡ በዚህ ዓመት በእሥራኤል የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሞያዎች የተደረገ ጥናት «ገዳሙ እና በመስቀሉ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያለው አደባባይ የመደርመስ አደጋ ተጋርጦበታል»፡፡
የመጸዳጃ ቤቱ ለአንድ ደቂቃ በአካባቢው አያስቆማችሁም፡፡ ኢትዮጵያውያን መነኮሳት ግን ዓመቱን ሙሉ በአካባው ይኖራሉ፡፡ በገዳሙ የውኃ ችግር አለ፡፡ ሁሉም ነገር አርጅቶ መውደቁን ብቻ ይጠብቃል፡፡ በበጋው ማቀዝቀዣ በክረምቱም ማሞቂያ የላቸውም፡፡ የመብራቱ ገመድ እዚህም እዚያም ተቆራርጧል፡፡ ለምን?
ግብጻውያን የወሰዱት የዴር ሡልጣን ቦታ አልበቃቸውም፡፡ የዴር ሡልጣንን ይዞታ በሙሉ መጠቅለል ይፈልጋሉ፡፡ በዚህም የተነሣ የይገባኛል ጥያቄ በየጊዜው ያነሣሉ፡፡ ኢትዮጵያውያን ራሳቸው ገዳሙን እንዳይጠግኑ የእሥራኤል መንግሥት ይከለክላል፡፡ የእሥራኤል መንግሥት እንዲጠግነው ሲጠየቅ ደግሞ ኢትዮጵያውያን እና ግብጻውያን መጀመርያ ይስማሙ ይላል፡፡ በመካከሉ የዴር ሡልጣን ገዳም ሕልውና እያከተመ ይመስላል፡፡
እዚያ ያሉ አባቶች በየጊዜው ይደበደባሉ፡፡ ግብጻውያን የበሮቹን ቁልፎች ሊቀይሯቸው ይችላሉ ብለው በመሥጋት ሌት ተቀን ዕንቅልፍ የላቸውም፡፡ የሚያዩትን ሁሉ በንቃት እና በጥርጣሬ ይከታተላሉ፡፡ የተነጠፈን ምንጣፍ ማንሣት፣የተሰበረን ወንበር መቀየር፣ የተበላሸን ዕቃ መጠገን ያስከስሳቸዋል፡፡
ቤተ ክህነቱ ለዴር ሡልጣን ተገቢውን ቦታ አልሰጠውም፡፡ ግብጻውያን በሲኖዶስ ደረጃ ጉዳዩን የሚከታተል ኮሚቴ ሲኖራቸው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ግን ጉዳዩን በቦታው ላሉ አባቶች ብቻ ትታዋለች፡፡ በፓትርያርኮች ደረጃ ግንኙነት ሲጀመርም የዴር ሡልጣን ጉዳይ አይነሣም፡፡ ችግሩን ለመፍታት የሚደረግ ጥረትም የለም፡፡ የእሥራኤል መንግሥትን የመግፋት እና ጫና የማሳደርም እንቅስቃሴ አይታይም፡፡ ቤተ ክህነቱ ቢያንስ የባለቤትነት ውይይቱ ቀርቶ እድሳቱን የተመለከተ ውይይት እንኳን ማድረግ አልቻለም፡፡
ይህ ሁኔታ ለግብጻውያን የልብ ልብ ሰጥቷቸዋል፡፡ ቦታውን ባለቤት አልባ አድርገው እንዲቆጥሩትም አድርጓቸዋል፡፡ በቅርቡ ዴር ሡልጣን እንዲታደስ ለመወትወት የተቋቋመው ኮሚቴም ከመንግሥት ያገኘውን ድጋፍ ያህል ከቤተ ክህነቱ አላገኘም ይባላል፡፡ 
እነዚህ ሁሉ ተደማምረው ብቸኛውን የጥቁር አፍሪካውያን የጎልጎታ ርስት ዴር ሡልጣንን ወደ ፍርስራሽነት ሊቀይሩት ቀናት ቀርቷቸዋል፡፡ እነሆ ይህንን በምጽፍበት ሰዓት እንኳን የተወሰነው የሕንፃው ክፍል በመሰንጠቅ ላይ ይገኛል፡፡ ግብጾች በጥንቱ ቦታችን ከከፍታ ላይ ሆነው «እስኪ ምን እንደ ምታm እናያለን በሚል ስሜት ያዩታል፡፡ ቤተ ክህነቱ አዲስ አበባ ሆኖ ረስቶታል፡፡ ኢትዮጵ ያውያንም ለትንሣኤ መጥተው ተሳልመውት ይሄዳሉ፡፡ ዴር ሡልጣን ግን በውስጡ ያለፉትን ቆራጥ አባቶች ብቻ እያስታወሰ «ነበር» ለመሆን እየተቃረበ ነው፡፡
ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ
ዴር ሡልጣን፣ ኢየሩሳሌም

46 comments:

 1. dn mene enedamel alakem.ename ka7 amatte bafate ayechawalaho.gene meneme alaragekome.ahone gene yakemane enedarage yaasare cometa tell no tayekahe
  negaragne.selam enedesamage.tabarake

  ReplyDelete
 2. Deacon Daniel,

  Yemakber selamta aqerballehu.

  Your piece on our historic monastery in Jerusalem: "Deir Sultan" is simply magnificent! You deserve the highest accolade for drawing attention to the urgent need for its repair.

  Kindly note that our World Association of Parishioners of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church has been struggling to get an approval by the Israeli government for us to repair the building. Please see our international petition addressed to the Israeli Government requesting his kind consent for the repair of the monastery buildings at our website: www.eotcipc.org.

  We would appreciate it greatly if you would link your website to that of ours and encourage your visitors to sign the petition and join us in the struggle to save our renowned, historic monastery.

  With thanks for your support,

  WAPEOTC (www.eotcipc.org)

  ReplyDelete
 3. This is extremely sad news. It just breaks someones's heart into pieces. I feel it is a responsibility for each of Ethiopian Orthodox Christian to save this monastery. It is not just a monastery, rather it is the "finger-print" of who we are and what our religion is. May God help the fathers who are living there and struggling to save it.

  ReplyDelete
 4. ibakih amlak hoy ethiopiawiyaninina ethiopian indihum yeethiopian neger lemin chila alk?

  ReplyDelete
 5. How about 'YWALDIBA TIRI???'

  ReplyDelete
 6. Dear Dani;

  The ownership controversy over the dare Sultan monastery has always remains unsettled & mysterious for a long time now. It is painful and at the same time embarrassing to witness the sufferings of Ethiopian monks living there.

  Since the carelessness& unpatriotic manners of the current leaders of the Ethiopian Orthodox Church is well documented, we don’t expect any positive interventions from them.

  But I was hoping the recently deceased patriarch of the Egypt Copts’ church (his holiness Shinoda) to solve the issue. Taking in to account his best services for God & influences, it is a pity not to address such important issue in his life. I suppose.

  God blesses historic Ethiopia!

  ReplyDelete
 7. ahune new ende uuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuu yemetele wendeme koyetewale eko yehe guday.

  ReplyDelete
 8. This is a time to talk about Waldba, Waldba, Waldba.......

  ReplyDelete
 9. It's a pity! Our beloved Ethiopian Saints should have not been tested this much by their fellow Armenian and Egypt Christians. Whatsoever their reward is great for they have stood firm and proved pious for the sake of the love of God. Woe to those who inflicted all those pains for they will be judged. But we shouldn't rather judge them for it's not our power, we pray for them in stead.

  ReplyDelete
 10. ምነዉ አቡነ ጳዉሎስ የቤተክርስቲያን ነገር አይገዳቸዉም? የዓለም አብያተክርስቲያናት ፕሬዘደንት ሲባሉ ስሙ አይከብዳቸዉም? ለማን አቤት እንበል? ኡኡኡኡ አቤቱ ክርስቶስ ሆይ በደምህ የመሰረትካት ቤተክርስቲያን ታደጋት

  ReplyDelete
 11. Is there anything which we can do as an Ethiopian orthodox church follower?
  pls. make it part of your discussions!!!

  ReplyDelete
 12. ዋልድባ ሲደፈር ዝም! ዝቋላ በእሳት ሲጋይ ዝም! አብያተ ክርስትያናት በአህዛብ በእሳት ሲቃጠሉ ዝም! ደብራት በአስተዳደር ብልሹነት ሲተራመሱ ጆሮ ዳባ ልበስ! ዴር ሱልጣን በቁሙ ሲፈርስ አሁንም ዝም! ቤተክህነት ሆይ ወዴት አለህ!!!!!!??????

  ReplyDelete
 13. ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ

  ReplyDelete
 14. Immediately, Yekirse Enkibekabe Hager Akef Mahiber Mequaquam alebet!Lesatume lehulum Yihonal.

  ReplyDelete
 15. Hager Tedeferech!

  ReplyDelete
 16. እስኪ ሁላችንም ስለ ዴር ሱልጣን ጉዳይ ወደ እግዚአብሔር እንጸልይ ።እግዚአብሔር የሰውን ልመና አይንቅም።ጸሎታችንን ይሰማናል።

  ReplyDelete
 17. Daniel is not wrong talking about Der Sultan because the issue of Waldba is not solved.NO! Neither Waldba nor Der Sultan are dispensible. If we have to work we have to work on both in a modern and civilized way. Not in violence. No!

  ReplyDelete
 18. Dn. Dn pls pls say something about Waldiba, your silence scares me.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dn danielma malet yemichlewin bloal kezih yekerewin degmo eyandandu sew malet yigebawal. Agelgilot bereket enji wetmed aydelem.

   Delete
 19. Before we say uuuuuuuuu about dere sultan( I KNOW IT NEED UUUUUU)BUT URGENT NEEDED uuuuuuuu & eerrrrrrerreeeeeeeeerererereeeeeeTA about WALDIBA. WHY WE WILL TRY TO FIND OUT THE TRUTH ABOUT WALDIBA WHY WHY WHY DANIEL U HAVE ACCESS TO GET INFO

  ReplyDelete
  Replies
  1. U TOO... HAVE ACCESS TO GET INFO, IF U WANT TO DO SOMETHING REALLY REGARDING!!!

   Delete
 20. what about waldiba????????

  ReplyDelete
 21. Dear Browsers,

  Dn. Daniel deserves our fullest appreciation for having brought to light the desperate situation facing our historic monastery in Jerusalem.

  Exposing the tragic situation is good but what is needed is not mere expressions of anger or sadness. What is needed is to take a pragmatic and meaningful action to effectively persuade the Israeli Government to allow the repair of the monastery premises. This effort is currently proceeding: please check: www.eotcipc.org.

  All Ethiopians who are genuinely concerned about the monastery are invited to sign the international petition addressed to the Israeli Prime Minister.

  ReplyDelete
 22. D. Daniel, kale hiwot yasemalin
  It is a very sad news, and Deacon, don't be surprised about the Bete Kihenet. They have a mission to destroy the church completely. They get paid by the Arabs to do just that. so it wouldn't surprise me. What surprises me is that all those Armnians and Egyptians who call themselves Christians while abusing other Christianity followers. It is aginst the teachings of our lord Jesus Christ, we were suppose to love each other and share what we all have. No greed. Do they really think they get to haaven by chasing us out and settle as they wish? I don't think so. Dani, if anybody contacts you about helping in any way, I will participate. We have let the United Nations know how people are abused in that area. Let God help us. Amen. Atlanta

  ReplyDelete
 23. It is good that you brought this burning issue once again. Most of us see & know the situation @ Der Sultan but unable to change it. In my opinion it is the result of two facts:
  1. The spritual status of most of the fathers currently residing in Jerusalem is not good enough to let God bring a solution for the problem-most of them are not real monks.
  2.For more than 40 years there is no 'bete kihinet' in Ethiopia who should work diligently to bring a spritual & diplomatic solutions for the problem.

  ReplyDelete
 24. የህልውናችን ጫፍ፤የታሪካችን ስር፤የደምና የነፍስ በህይወት ዋጋ ሲከፈልበት፤የሃይማኖታችን ቅርስ ነውና ስለ ዱር ሱልጣን ጥሪ ያነበብነውን ታሪክ ምላሹ ለኛ የኢትዮጱያን የጣት ቀለበት ነው።

  ReplyDelete
 25. Before we say uuuuuuuuu about dere sultan( I KNOW IT NEED UUUUUU)BUT URGENT NEEDED uuuuuuuu & eerrrrrrerreeeeeeeeerererereeeeeeTA about WALDIBA. WHY WE WILL TRY TO FIND OUT THE TRUTH ABOUT WALDIBA WHY WHY WHY DANIEL U HAVE ACCESS TO GET INFO

  It is fact.
  Daniel, it seems that you are limitmit... Yhew Melse zenawi mKn ( ahun Yanten Akuam balawkim) ashebari new alut ayaidel. Bicha antem kotetihn sitawera Ende Sibehat G/Egziabher tguwazaleh... Talk real, OFFFFFAAAAA

  ReplyDelete
 26. እኔ የምለው ሲጀመር ቤተ-ክህነት አለን እንዴ? እንዲህ ደፋር እንድሆን ያደለገኝ የእነርሱ ሁኔታ ነው፣ እንደመንፈሳዊ ተቋም ማገልገላቸው ቢቀር እንኳን እንዴት እንደ ዜጋ ማሰብ ያቅታቸዋል? ዋልድባ የማንነታችን መለያ፡የሀይማኖታችን መገለጫ፡የኢትዮጵዊነታችን ኩራት የሆነውን ቅዱስ ገዳም ሲታረስ ዝም አሉ እኮ! የዝቃላ ገዳምም እንደዛ ሲቃጠል እንደቀልድ አለፉት አይደል! በየአድባራቱ የሚቃጠሉት የአብነት ት/ቤቶችስ ምክንያታቸው ዝም ተብሎ የሚታለፍ ነበር? አይ ዲያቆን ቤተ-ክህነትን በደንብ የምታውቀው ይመስለኝ ነበር፤ ቤተ-ክህነት ምነው ዝም አለች ስትል ገረመኝ እነርሱማ እንደ ፈርኦን ደንዳና ልብ ኖሯቸዋል፣ የነርሱ ጥቅም አይነካ እንጂ ለምንም ነገር ግድ የላቸውም እኛም ከነሱ ምንም አንጠብቅም እንኳን እስራኤል ያለን ገዳም ሊታደጉ ይቅርና እዚሁ አፍንጫቸው ስር ላሉት ገዳማት መቼ አለን አሉ ለቤተክርስቲያን አምላክ ይሁናት እንጂ እኛ ከነሱ ምንም አንጠብቅም፡፡መንግስታችንም እንደምናውቀው ነው ብቻ ነገሮች አስቸጋሪ ናቸው--ኡፍፍፍፍ----------

  ReplyDelete
 27. Thank you Dn. Daniel,

  It will be good to update us about current efforts of the New Committee working on Der-Sultan. How can I reach the committee and contribute my part please? Did the committee discussed the issue with the new Israeli Ambassador in Addis Ababa? She is of Ethiopian origin and has detailed information about the ups and downs around Der-Sultan. I think working in collaboration with the committee is mandatory for urgent solutions on the issue. Lets pray and do our best to save Der-Sultan at the same time doing our best to save the Holiest Jerusalem of Ethiopia that is blessed by Medhanealem and Dingil Mariam, known as Waldba Gedam. Idme Yistih Dn. Daniel!

  ReplyDelete
 28. በቅርቡ ዴር ሡልጣን እንዲታደስ ለመወትወት የተቋቋመው ኮሚቴም ከመንግሥት ያገኘውን ድጋፍ ያህል ከቤተ ክህነቱ አላገኘም ይባላል፡፡
  AYe Paulos Egizer yiyilih

  thank you dani

  ReplyDelete
 29. አንድ፡የሚያሳዝነኝ፡ነገር፡ግብጾች፡ይህን፡ሁለ፡ግፍ፡ሲፈጽሙብን፡ማለት፡ክርስትያኖቹ፡ማለቴ፡ነው፡እኛ፡በየቦታው፡ስናወድሳቸው፡መዋላችን፡ነው፡፡መቼም፡ብዙዎቻችን፡የምናደንቃቸው፡እንዲያውም፡ሁሉም፡ማለት፡ይቻላል፡ይህን፡የሚሰራውን፡ግፍ፡እንደሚያውቁትና፡እንደሚደግፉት፡እርግጠኛ፡ነኝ፡፡ታድያ፡ይህ፡ሁሉ፡ሲሰራና፡እኛ፡የግብጽ፡ክርስትያኖች፡ቅዱሳን፡ናቸው፡እያልን፡የማይገባቸውን፡ስናሞካሻቸውና፡ስናደንቃቸው፡የሚሰሩትን፡ተንኮልና፡ግፍ፡እንዲቀጥሉበት፡ማበረታታት፡አይሆንም?ይሄ፡ማበረታታት፡ብቻ፡ሳይሆን፡መተባበርም፡ነው፡፡ይህ፡ክፋታቸው፡አሁን፡የተጀመረ፡አይደለም፡ቆይቷል፡፡ክርስትያን፡በወንድሙ፡ላይ፡እንደዚህ፡ያለ፡ተንኮል፡ይሰራልን?????????????

  ReplyDelete
 30. በእርግጥ በዋናነት ኃላፊነቱ ለቤተ ክህነት ነው በተለይ የማስተባበሩ ስራ
  ግን ኣሁን አሁን በአንዳንዶች ምክንያት ቤተ ክህነት መሆኑ እየቀረ ቤተ ክህደት
  ሊያደርጉት ይሞክራሉ ከተቻላቸው:: ነገር ግን ስላንዳንዶቹ እነዚህ ሁሉ
  እንደሚስተካከሉ ተስፋ አለን:: የእነርሱን ጩኸት እግዜአብሔር ይሰማልና

  ReplyDelete
 31. Every thing is so regretable regarding our church why God keep silent we have to pray and ask forgiveness

  ReplyDelete
  Replies
  1. ከኔ ጀምሮ የጸሎትን ለስሙ ማወቅ እንጂ በህይወት ስለማንተረጉመው ብቻ፡፡
   በአጭሩ፡-

   1. ቂም ይዞ ጸሎት እንደማይሰምር ብናውቅም ልባችንን ለይቅርታ ስለማናዘጋጀው፣

   2.ከተበቀልን በኋላ ለመጸለይ ስለምናቅድ፣

   3. ስሙን የምንጠራው የኛን ፈቃድ ለመፈጸም እንጂ "ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን!" የሚለውን የጸሎት ክፍል በልባችን ለሆሳስ ስለምንደግመው፡፡

   ከአባቶቻችን ከጸሎታቸው በረከት ይክፈለን፡፡

   Delete
 32. What a wonderful insight is that Daniel. Our church should react promptly. but, for curiosity, the JANDEREBA case is on Apostle of Saint Mark not on Saint Luke.

  ReplyDelete
  Replies
  1. The Jandereba case is on Acts(Yehawariat Sera)that was written by Saint Luke not Saint Mark.

   Delete
  2. The case of the "Jandereba" is written in the book of "ACTS" (የሐዋርያት ሥራ) by Saint Luke not Saint Mark.

   Delete
 33. ምን ታረጊዋለሽ ከሌለህ የለህም ቢሳቅብህ እንጂ አይሳቅልህም

  ReplyDelete
 34. this us part of the miission u should know that as long as Abune Poulos in there chair the dawn fall to Tewahido will continue

  ReplyDelete
 35. ዳኒ በቅድሚያ እንኳን ከቅድስት ሀገር በሰላም ተመለሰክ:: ከዚያ አካባቢ ሳይህ በጣም ነው ደስ ያለኝ :: ያለውን ችግር በዚሁ ሁኒታ እንደምትዘግበው ጥርጥር አልነበረኝም :: ጥሩ ብለሃል :: እኒም በእንባየ ሰው ፍጠር ብየ ጸልየ ተመልሻለሁ :: መቸስ ያንን መሳይ መጸዳጃ ያየ ሰው በእንባ መጸለይ ይነሰው? እባካችሁ ማየት ማመን ነው ዘንድሮ ያልቻላችሁ ከርሞ ለመሄድ ከራሳችሁ ጋር ቃል ግቡ :: ማን ያውቃል መፍትሄ የሚያመጣ ሰውም በማህላችሁ ሊፈጠር ይችል ይሆናል:: በአንድ ወቅት ትምህርቱ ወንድማችን ዲ/ዳንኢል ክብረት ሰው የለም አትበሉ ጌታ ሰው አለው:: ሰው ያዘጋጃል ሲል አስተምሮአል:: በሃይማኖት አባቶች ያለውን ድክመት ለግዚው እንለፈው እና በወጣት ምሁሮች በኩል ሊሞከር የሚችል ነገር ካለ ሁላችንም ጭንቅላታችንን እንጭምቅ::የመለኩሳቱን ስቃይ የሚያይ ያለ የቀራንዩ ንጉሥም ይረዳናል::ዋናው ከልብ ማሰባችን ነው::
  ዳኒ ስለጥቆማህ ሳላመሰግንህ አላልፍም:: የድንግል ልጅ በሂወትህ ዘመን አይለይህ።

  ReplyDelete
 36. ሳሚ ወ/ሚካኤልApril 27, 2012 at 7:10 PM

  ይህ ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያነው!!!! ጊዜው ደርሶዋልና በቤተክርስቲያናችን ትንሳኤ ተስፋ ውስጥ ሁነን ለፊታችን ለቅሶን ብቻ እናስተምረው!!!! አሁን የምንፈተንበት...አሁን የምንገደልበት....አሁን የምንረሳበት ..አሁን የምንረገጥበት ....ጊዜ ላይ እንደሆንን ይገባኛል!!!...ነገር ግን አባቶቸም ይህን ሁሉ አይተውና ታግሰው የሰጡኝን ቤተክርስቲያን ምስክር አድርጌ የሃገሬን ትንሳኤ ያሳየኝ ዘንድ በሃይለ ክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ!!!!! ዳኒየ ይገ'ባሃል!!! ኡኡ በል!!!! ዋጋህ በሰማይ ነውና በትኩስነት የቤተክርስቲያንህን ክብር ስበክ!!!! አትፍራ!!!! በዚህ አካሄድህ የምታገኘው ወይም የሚገጥምህ ሁሉ አባቶችህን የገጠማቸውና ላምላካቸው ርስት ተመራጭ ያደረጋቸውን የነበረና የሚኖር ነገር ነው1!!!!!!! ይባርክሀ!!!!! እግዚኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦ ማሃረነ ክርስቶስ!!!!!!!!!! በእእእእእእእንተማሪያያያያም ማሃረነ ክርስቶስ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 37. betam yasazinal!!!!!!!

  ReplyDelete
 38. first ,i like to thank dn.daniel for his effor to expose this issue which for me and probable for most of ethiopians orthodox belivers is new.The situation is really heartbreaking ,and i hope the concerned body will give prompote action becase it is not an issue of second priorit .may God spare this place for ethiopia and bless those who suffered.

  ReplyDelete
 39. ምን ይሻላል ከእኔስ ምን ይጠበቃል

  ReplyDelete