Thursday, April 5, 2012

ማንበር

click here for pdf

ተወዳጁ ፕሮፌሰር ሺፈራው በቀለ አስተጋብተው ባረቱት እና «ባሕል እና ልማት በኢትዮጵያ» በሚለው መጽሐፍ ላይ እርሳቸው ያዘጋጁት ጥናታዊ መግቢያ አለ፡፡ ይህንን ጥናታዊ መግቢያ ማንበብ አንድ የዕውቀት ባሕር ውስጥ ገብቶ ከመጠመቅ ይቆጠራል፡፡
ፕሮፌሰር ሺፈራው በገጽ 18 እና 19 ላይ እንዲህ ይላሉ፡፡ «የዛሬ አምስት ዓመት ገደማ በሀገራችን አድጎ የአማርኛ ቋንቋን አቀላጥፎ የሚናገረው የኖርዌዩ ዜጋ ዶክተር ሄላንድ ስለ ኢትዮጵያ የዕድገት ማነቆዎች በምንወያይበት ወቅት አንድ ትዝብቱን አነሳብኝ፡፡ በአማርኛ ቋንቋ ሜንቴናንስ (maintenance) ለሚለው የእንግሊዝኛ ቃል አቻ እንደሌለውና ጥገና ወይም እድሳት የሚሉት ቃላት አንድ እንደ ሕንፃ፣ አውራ ጎዳና ወይንም ተሽከርካሪ ያለ ቁሳዊ ነገር ወይንም ንብረት እስኪበላሽ ድረስ ቆይቶ ከዚያ በኋላ የሚደረግ ማስተካከልን ማለትም ጥገና ማድረግን እንጂ እየተገለገሉ በዚያውም እንደ ነበር ጠብቆ ማቆየትን እንደማያመለክቱ ታውቃለህ ወይ? ደግሞም የቃሉ አለመኖር እንደ ሚያመለክተው በኢትዮጵያ ሁሌ እንደሚደረገው አንድ ነገር ተበላሽቶ ወይንም አልቆ እስከሚያበቃለት ቆይቶ ከዚያ ወደ እድሳት መግባት እንደሆነ ልብ ብለሃል ወይ? ብሎ ጠየቀኝ» ይላሉ፡፡
ይህንን ሳነብ እጅግ በጣም ነበር የተገረምኩት፡፡ በሁለት ምክንያቶች፡፡ በአንድ በኩል በዶክተር ሄላንድ አስተውሎት፣ በሌላ በኩል ደግሞ የቋንቋ ጥናት ለሌሎች አያሌ የጥናት ዘርፎች የሚኖረውን ቁልፍ ቦታ በማየት፡፡
ፕሮፌሰር ሺፈራው ሜንቴናንስ (maintenance) የሚለውን «ማንበር» ብለው ተርጉመውታል፡፡ ሲፈቱትም «በጥቅም ላይ እያዋሉ እንደ ነበር ጠብቆ ማቆየት» ይሉታል፡፡ እኔም ይህንን ካየሁ በኋላ ለመሆኑ በባህላችን ማንበር አለ? ብዬ ጠየቅኩ፡፡ ከእምነት እስከ ባህል፣ ከፖለቲካ እስከ ኢኮኖሚ፣ ከሀገር እስከ ቤተሰብ፣ ከሕዝብ መገልገያዎች እስከ ግል ንብረቶች፣ ከአሠራር፣ እስከ ሕግጋት፣ ከሥነ መንግሥት እስከ ሥነ ሕዝብ "ማንበር" ፈተሽኩት፡፡ እኔም አላገኘሁትም፡፡
ለሦስት ዘመናት የሚያህልን የመንግሥት እና የሕዝብ ታሪክ የምንቆጥር ሕዝቦች የመንግሥታችን ታሪክ እየፈረሰ እንደገና ሲሠራ እንጂ ያለውን እየጠበቁ፣ አዳዲስ አሠራሮችንም እየጨመሩ የማንበር ሥርዓት አልነበረንም፡፡ ከኋላ የመጣው ሀገሪቱን እንደ አዲስ ሲጀምራት፡፡ እርሱ መንበር ላይ በተቀመጠ ቁጥር ነጻ ሲያወጣት፡፡ ከዚያ በፊት ለነበራት ህልውና ዕውቅና መስጠት ተስኖት ራሱ የፈጠራት አገር ሲያደርጋት፡፡ ደንቆሮ የሰማ ዕለት ያብዳል እንደሚባለው እርሱ ስለ ነጻነት የሰማበትን ቀን ሕዝብም ያን ቀን የሰማ እየመሰለው፣ እርሱ የነገሠበትን ቀን ሕዘብም ያን ቀን የነገሠ አድርጎ እየቆጠረው ሲያፈረስ ሲሠራ ነው የኖረው፡፡
አኩስምን የመሰለ ሥልጣኔ ርግፍ አድርገን ስንተወው እና ወደ ሮሐ ስንሻገር ምንም ያልተሰማን ሕዝቦች ነን፡፡ እነዚያን ሰው ደግሞ ሊሠራቸው የማይቻላቸውን የላሊበላ ድንቅ ሥራዎች 300 ዓመታት ባላይ እንደ ጠላት ገንዘብ ስንተዋቸው ቅንጣት ታህል ቅሬታ አላደረብንም፡፡ ከሦስት መቶ ዓመታት በላይ የተለፋባትን ጎንደርን የተውንበት ምክንያት ግልጽ አይደለም፡፡ ነገም አዲስ አበባን ትተን ወደ ሌላ ቦታ ላለመሄደችን ምንም ዋስትና የለንም፡፡ አፍርሶ ሠሪዎች ነና፡፡
እንዲህ ዛሬ የትምህርት ሥርዓታችን መከራውን እንዲያይ የፈረድንበትኮ አፍርሶ በመሥራት መንገድ ስለገነባነው ነው፡፡ ለሺ ዓመታት የዘለቀ ነባር የትምህርት ሥርዓታችንን ሳንፈትሸው፣ እንዴት እየተ ጠቀምን እንደምናዘምነው ሳናስብበት አፈረስነውና ከእንግሊዝ እና ከፈረንሳይ፣ ከግብጽ እና ከአሜሪካ በተወሰደ አዲስ የትምህርት ሥርዓት ተካነው፡፡ ታድያ ባህል ሆኖብን አሁንም የራሳችንን ፈትሸን እያነበርን ከመሄድ ይልቅ ችግር እስኪፈጠር እየጠበቅን የትምህርት ሥርዓታችንን ስናፈርስ ስንጠግን እየኖርን ነው፡፡
እስኪ በየቦታው ታዘቡ፡፡ የኢትዮጵያውያን የአሠራር፣ የአስተዳደር እና የሥልጣኔ ፍልስፍና የሚባል መልክ ያለው ነገር ታያላችሁ? ይህንን ያህል ዓመት ኖረን፣ ይህንን ያህል የተጻፈ ታሪክ ኖሮን፣ የተጻፈ ሕግ እና ጥንታዊ የዳኝነት ሥርዓት ኖሮን፣ ሦስቱ ዓለምን የለወጡ ታላላቅ እምነቶች ኖረውን፣ አፍሪካውያን ሚኒስትር የሚባል ከመሰየ ማቸው በፊት ከመቶ ዓመታት በፊት የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን ዘርግተን፡፡ ስልክ እና መኪና፣ የቧንቧ ውኃ እና መብራት፣ አውቶሞቢል እና ጋዜጣ ከመሰል ወንድሞ ቻችን በፊት የነበረን ሕዝቦች፤ እንዴት ነው የተዋጣለት የመገናኛ ሥርዓት፣ የዳበረ የፕሬስ ባህል፣የተሳለጠ የትራን ስፖርት አገልግሎት፣ አርአያ የሚሆን የፍትሕ ሥርዓት፣ ግልጽ እና ሥሉጥ የሆነ የመሥሪያ ቤቶች አደረጃጀት እና አሠራር፣ በምሳ ሌነት የሚጠቀስ ቤተ እምነት ሊኖረን ያልቻለው ለምን ይመስላችኋል?
ስናፈርስ ስንሠራ ነዋ የኖርነው፡፡ ማንበር የት እናውቅና፡፡
ያለንን አንብሮ የለለንን ጨምሮ፣ያለውን ከሌለው ጋር አስማምቶ እና አገናዝቦ የመሄዱ ባህል ቢያጥርብን ነው እንጂ በዚህ ሁሉ ዓመታት ጉዞ ዳኘው የሚባል ልጅ እንጂ ለዓለም የሚተርፍ ዳኛ፣ሃይማኖት የምትባል ልጅ እንጂ ሕዝቡን በሞራል እና በእምነት ልዕልና ላይ የሚያቆም የሃይማኖት ተቋም፤ መብራቱ የሚባል ልጅ እንጂ ከዓመት እስከ ዓመት የማይቋረጥ መብራት፣ ውኃ ልማት የሚባል ፌርማታ እንጂ የዓባይን ልጅ ውኃ እንዳይጠማው የሚያደርግ ዘላቂ የውኃ ልማት፣ በስልክ አነጋግሪኝ በቀጭኑ ሽቦ የሚል ዘፈን እንጂ የሚተማመኑበት የቴሌፎን አገልግሎት እንዴት እስካ ሁን ከኛ ሊርቁ ቻሉ?
ስንት የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን አፍርሰን ስንት ሌሎችን ሠርተናል፡፡ አፍርሶ ሌላ መሥራት ብቻ ሳይሆን አፍርሰን ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ መልሰን የሠራናቸውም አሉ፡፡ በአንዱ መሥሪያ ቤት የነበረ ታሪካዊ መዝገብ ወደ አንዱ ሄዶ፣ ከዚያም አንዱ ተረክቦት፣ በመጨረሻ ሙት ፋይል ያለበት ቦታ ተቆልፎበት የቀረ ስንት ታሪክ አለ?
መንገዱ ካልተሰባበረ፤ ሕንፃው ካልተሰነጣጠቀ፣ መኪናው አጓርቶ አጓርቶ በራሱ ጊዜ ካልቆመ፤ ወንበር እና ጠረጲዛው ተንቃቅቶ ተንቃቅቶ « - - » ብሎ ካልተጋደመ፡፡ የውኃ ቧንቧው አንጠባጥቦ አንጠባጥቦ ሲመረው ካልፈነዳ፤መስተዋቱ ተተርትሮ ተተር ተሮ ሲመረው «ምነው እቴ» ብሎ መሬት ላይ ካልተዘረገፈ፤ ፍራሹ ተቦጭቆ ተቦጭቆ ወደ ምንጣፍነት ካልተቀየረ፤ ምጣዱ እንኳን ተሰንጥቆ ተሰንጥቆ ሊጡን ማፍሰስ ካልጀመረ ማን ይደርስላቸዋል፡፡
ይገርማችኋል ይሄ ነገር በቁሳዊው ነገር ላይ ብቻ አይደለም የሚታየው፡፡ እስኪ የሕክምና ልማዳችንን ተመልከቱ፡፡ ለመሆኑ በየጊዜው የመታየት ልማድ አለን? በዓመት በተወሰኑ ጊዜያት ወደ ሐኪም ቀርበን ያለንበትን ሁኔታ የማወቅ ሥርዓት አለን? የሕመም ስሜት ሲሰማን እንኳን ወድቀን ካልተንከባለልን መቼ ወደ ሕክምና እንመጣለን፡፡ ካልፈረስን መሠራት አይሆንልንም ማለትኮ ነው፡፡ ልማዳችን ታምሞ የመዳን እንጂ ጤናን ጠብቆ የማቆየት አይደለማ፡፡
ታላላቅ የሀገሪቱ ሰዎች ደከሙ፣ ታመሙ፣ ተቸገሩ ይባላል፡፡ አብዛኛው ጸጥ ይላል፡፡ ከበደ ሚካኤል «ጽጌረዳ እና ደመና» በሚለው ግጥማቸው እንዳሉት
በችግሩ ብዛት ቆይቶ ሲጉላላ
ደክሞት እና ርቦት ከሞተ በኋላ
የመሞቱ ዜና ሲሰማ ሕዝብ ግልብጥ ብሎ ለቀብር ይወጣል፡፡ ጥቁር ይለብሳል፡፡ መታመማቸውን ያልገለጠው ሚዲያም ልማዱ ነውና ሞታቸውን ያስጌጠዋል፡፡ ከመሞታቸው በፊት ያልታተመው መጽሐፋቸው ከሞቱ በኋላ እየወጣ ይቸበቸባል፡፡ ታሪካቸውን እናቆይ፣ ሙት ዓመታቸውን እናስብ፣ ሐውልት እናሠራ፣ የምናምን ምሽት እናዘጋጅ ይባላል፡፡ ካለቀ ከደቀቀ በኋላ፡፡ ምን ይደረግ ማንበር አንችልበትማ፡፡
እስኪ በባህላችን የወለደ የሚያስጠይቅ፣ የታመመ የሚያሳክም፣ የቸገረውን የሚረዳ፣ ጀግናውን የሚሸልም፣ የደከመውን የሚያበረታ ዕድር ለምን አልፈጠርንም? ኢትዮጵያ ውስጥ ዕድር ተጀመረ የሚባለው 14ኛው መክዘ ነው፡፡ እንግዲህ ስድስት መቶ ዓመታትን ያህል አስቆጥሯል ማለት ነው፡፡ እንዴት በስድስት መቶ ዓመታት ውስጥ ሞትን ብቻ ስናስብ ኖርን፡፡ መኖር ጉዳያችን አይደለም ማለት ነው? ሲፈርስ መምጣት እንጂ እንዳይፈርስ የማድረግ ባህል የለንም ማለት ነው?
ለነገሩ ምን ይደረግ
ይብላኝ ለሟች እንጂ ልጅስ ያድጋል በእጁ
እንደ ጎታ ፍራሽ ወድቆ በየደጁ
እያልን አይደለ የምናለቅሰው? ከነዋሪው ይልቅ የምንጨነቀው ለሟቹኮ ነው፡፡ ለሟቹ ምርጥ መቃብር እያሠራን ልጆቹ ግን በቁማቸው በየደጁ እንዲወድቁ ተስማምተናል፡፡
ባለ ትዳሮች ሲጣሉ ለማስታረቅ የሚመጡ ሽማግሌዎች እና ቤተሰቦች እንጂ በትዳር ጸንተው እንዲኖሩ የሚያግዙ እና የሚመክሩ ሽማግሌዎች እና ቤተሰቦች መች በብዛት አሉን፡፡ ለመሆኑ ስንቶቻችሁን ሚዜዎቻችሁ እየመጡ ይጠይቋችኋል? ብትጣሉስ? ስንቱ ነው ሊመክራችሁ የሚመጣው፡፡ ለምን አትሉም? እንዳይሰበር የሚያነብር ሳይሆን ሲሰበር የሚጠግን ነዋ ያለን፡፡
እስኪ በየአካባቢያችን፣ በየድርጅታችን እና በየማኅበራችን የሚደረጉ ስብሰባዎችን ገምግሟቸው፡፡ አብዛኞቹ አንዳች ችግር ሲፈጠር ለችግሩ መልስ ለመስጠት ወይንም ችግሩን ለመፍታት የሚደረጉ ናቸው፡፡ ችግሩ እንዳይፈጠር፣ የተዘረጋው አሠራር ወይንም ሥርዓት ተጠናክሮ እንዲቀጥል፣ ሥራውን እያስቀጠሉ ችግሩን ለመፍታት የሚደረጉ አይደሉም፡፡ እንዲያውም አንዳንዶቹ ከዚህም ብሰው ሥራ አስቁመው፣ ቢሮ አስዘግተው የሚከናወኑ ናቸው፡፡ የማንበር ችግር፡፡
ማስታወቂያዎቻችንንስ አይታችኋል? ማስጠንቀቂያዎቻችንን ልበላችሁ እንጂ፡፡ እንዲህ ማድረግ ክልክል ነው፣ እንዲህ ማድረግ ያስቀጣል፡፡ የተሸጠ ዕቃ አይመለስም፤ ፎቶ ግራፍ ማንሳት ክልክል ነው፤ መቆም ክልክል ነው፣ መቀመጥ ክልክል ነው፤ መጸዳዳት ክልክል ነው፤ ስለ ማፍረስ ብቻ ነው የሚነግሯችሁ፡፡ ስለ ማንበር አይነግሯችሁም፡፡
የተሸጠ ዕቃ የማይመለስ ከሆነ አስቀድማችሁ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ የሚነግር አታገኙም፡፡ ፎቶ ማንሳት ክልክል ነው ይላል እንጂ የት ቦታ ደግሞ እንደተፈቀደ አይገለጥላችሁም፡፡ እዚህ መቆም ክልክል ከሆነ ታድያ የት እንቁም? ይህንንም ተውት መቆም ክልክል ነው ካለ ለምን መቀመጫ አያዘጋጁም፡፡ መቀመጥ ክልክል ነው ይሏችሁና ከጎኑ መቆምም ክልክል ነው ይሏችኋል፡፡ ታድያ መቆምም መቀመጥም ከተከለከለ ምነው አልጋ አያዘጋጁ? ሰው ሳይጸዳዳ መኖር አይችልም፡፡ መጸዳዳት ክልክል ነው ብሎ ቋንቋ ምንድን ነው? በአካባቢው የመጸዳጃ ቦታ ሳይኖርስ መጸዳዳት ክልክል ነው ብሎ ማስጠንቀቂያ ተፈጥሮን ከመቃወም ውጭ ምን ትርጉም ይኖረዋል፡፡
ሥርዓቱን፣ ንጽሕናውን፣ ጸጥታውን፣ ልማዱን፣ እንድንጠብቅ የሚያደርጉ የማንበር ሕጎች የሉንም፡፡ ስናፈርሳቸው እንዴት እንደምንቀጣ የሚነግሩን እና የሚያስጠነቅቁን ግን ሞልተዋል፡፡ እንዲያውም በአንዳንድ አካባቢዎች አፍራሾቹን የሚቀጡ እና የሚጠብቁ ሰዎች እንጂ ማክበር ለሚፈልጉ መረጃ የሚሰጡ እና የሚተባበሩ ባለሞያዎች አታገኙም፡፡ መጸዳዳት ክልክል ነው ከማለት ይልቅ የመጸዳጃ ቤቶችን መገንባት የተሻለ ጤናን እና አካባቢን ያነብር ነበር፡፡
እናመሰግናለን ፕሮፌሰር ሺፈራው፡፡ አሁን ስለ ማንበር እንድናስብ አድርገውናል፡፡ ይኼንን በየመሥሪያ ቤቱ «የጥገና ክፍል» የሚባለውን ሁሉ ከስሙ ጀምሮ የማንበር ክፍል ልንለው ነው፡፡ በየቤታችንም መጠገን እና ማስጠገንን ትተን ማንበር ልንጀምር ነው፡፡ እንጠግናለን እያሉ ንግድ የከፈቱ ሁሉ «እናነብራለን» ሊሉ ነው፡፡ 
         እኛም እናነብራለን፡፡

52 comments:

 1. great article! God bless u brother!!
  maryland

  ReplyDelete
 2. "ሥርዓቱን፣ ንጽሕናውን፣ ጸጥታውን፣ ልማዱን፣ እንድንጠብቅ የሚያደርጉ የማንበር ሕጎች የሉንም፡፡ ስናፈርሳቸው እንዴት እንደምንቀጣ የሚነግሩን እና የሚያስጠነቅቁን ግን ሞልተዋል፡፡ እንዲያውም በአንዳንድ አካባቢዎች አፍራሾቹን የሚቀጡ እና የሚጠብቁ ሰዎች እንጂ ማክበር ለሚፈልጉ መረጃ የሚሰጡ እና የሚተባበሩ ባለሞያዎች አታገኙም፡፡ መጸዳዳት ክልክል ነው ከማለት ይልቅ የመጸዳጃ ቤቶችን መገንባት የተሻለ ጤናን እና አካባቢን ያነብር ነበር፡፡"

  Liyu Agelaletse new. Egziabiher Yistilin Dn. Daniel. Egnam endinastewul Egziabiher Yirdan.

  ReplyDelete
 3. ንብረትን ከማንበሩ በተጨማሪ አስተሳሰቡ ለብዙዎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል፡፡

  ReplyDelete
 4. very good perception thanks

  ReplyDelete
 5. ALWAYS WRITING IS ENOUGH BY ITSELF,U HAVE TO FIGHT THE DECISION MAKERS,AT THAT TIME U WILL HAVE AFOLLOWER.fINALLY WE WILL HAVE MANY "ANBARIWACH"
  GOD BLESS U D.DANIEL

  ReplyDelete
 6. እጅግ በጣም አሪፍ ጽሑፍ ነው ዳንኤል:: ማንበር የእለት ተለት ተግባራችን ቢሆን መልካም እንደሆነ አሳይተህናል::

  አንድ ጊዜ በአውሮፕላን ውስጥ ሆኜ የበረራ አስተናጋጅ ምግብ ካቀረበችልኝ በኋላ ሌላም ነገሮችን በአማርኛ ጠየቅሁዋት (የኢት/ አየር መንገድ ነበር የተሳፈርኩበት):: የምፈልገውን ስላብራራችልኝ በቃላት ላመሰግናት ፈለግኩና : በእንግሊዘኛ ቴንኪው አልኩዋት:: ከአፌ የመጣው እሱ ነበራ:: ከጎኔ የተቀመጠው አውስትራላዊ ዜግነት ፈገግ ብሎ የሚከተለውን አለኝ:: "It is funny the whole time you talked with her in your language and at the end you say Thank You. እኔም ከአፌ የመጣው የምስጋና ቋንቋ እንግሊዘኛ ነው አሉኩት:: ምናልባትም እዚህ አገር ብዙ ስለቆየሁ ይመስለኛል:: I replied to him saying, it may be because I have spent a lot of time abroad and Thank You is the one which came to mind quickly. ነገር ግን መላልሼ አስበው ነበር እውነታው ብዙ ውጭ አገር ስለቆየሁ ነው? አይደለም:: በይበልጥ ዛሬ ደግሞ ያንን እንዳስታውስ አደረገኝ:: እኛ እንደ ምስጋና ያሉ ነገሮች ቋንቋው ቢኖረንም ባህላችን ስላልሆነ አንጠቀምበትም:: አልያም እንደ "ማንበር" ያሉ ቃላት በመዝገበ ቃላታችን ውስጥ የሉም::

  ዳኒ አድናቂህ ነኝ:: ጥሩ እይታ አለህ:: እውነትም የዳንኤል እይታ::

  ReplyDelete
 7. exactly!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 8. Dear Daniel,

  We are not blessed for maintaining our self. For centuries, we destroyed whatever we had first and then try to built again.

  Given the fact that we exhibited termination of knowledge rather that knowledge transformation.

  You argument is correct that we don't have incremental changing (maintenance) mind set up. In stead of gradual change, we are always working for dismantling the heritage and attempt to establish something new even without assessing the past.

  ያለንን አንብሮ የለለንን ጨምሮ፣ያለውን ከሌለው ጋር አስማምቶ እና አገናዝቦ የመሄዱ ባህል ቢያጥርብን ነው እንጂ በዚህ ሁሉ ሺ ዓመታት ጉዞ ዳኘው የሚባል ልጅ እንጂ ለዓለም የሚተርፍ ዳኛ፣ሃይማኖት የምትባል ልጅ እንጂ ሕዝቡን በሞራል እና በእምነት ልዕልና ላይ የሚያቆም የሃይማኖት ተቋም፤ መብራቱ የሚባል ልጅ እንጂ ከዓመት እስከ ዓመት የማይቋረጥ መብራት፣ ውኃ ልማት የሚባል ፌርማታ እንጂ የዓባይን ልጅ ውኃ እንዳይጠማው የሚያደርግ ዘላቂ የውኃ ልማት፣ በስልክ አነጋግሪኝ በቀጭኑ ሽቦ የሚል ዘፈን እንጂ የሚተማመኑበት የቴሌፎን አገልግሎት እንዴት እስካ ሁን ከኛ ሊርቁ ቻሉ?

  ReplyDelete
 9. this is what i like about you, you look things in a new perspective, out of the box!
  Keeps going.

  ReplyDelete
 10. this is what i like about you, you look things in a new perspective, out of the box!
  keeps going.

  ReplyDelete
 11. this is what i like about you, you look things in a new perspective, out of the box!
  keeps going

  ReplyDelete
 12. 'እስኪ በባህላችን የወለደ የሚያስጠይቅ፣ የታመመ የሚያሳክም፣ የቸገረውን የሚረዳ፣ ጀግናውን የሚሸልም፣ የደከመውን የሚያበረታ ዕድር ለምን አልፈጠርንም? ኢትዮጵያ ውስጥ ዕድር ተጀመረ የሚባለው በ14ኛው መክዘ ነው፡፡' አንተን ያቆይልን! Dani
  Mamush,MN

  ReplyDelete
 13. Excellent Daniel…good explanation Thank you.

  ReplyDelete
 14. Nice article ...Bless u

  ReplyDelete
 15. መጀመሪያ ራስን ማንበር አይቀድምም ወይ ከያ በኋላ ነው ታሪክ፣ሀገር…..የምናነብረው፡፡ አይደለም እንዴ?

  ReplyDelete
 16. ............ ከኋላ የመጣው ሀገሪቱን እንደ አዲስ ሲጀምራት፡፡ እርሱ መንበር ላይ በተቀመጠ ቁጥር ነጻ ሲያወጣት፡፡ ከዚያ በፊት ለነበራት ህልውና ዕውቅና መስጠት ተስኖት ራሱ የፈጠራት አገር ሲያደርጋት፡፡ ደንቆሮ የሰማ ዕለት ያብዳል እንደሚባለው እርሱ ስለ ነጻነት የሰማበትን ቀን ሕዝብም ያን ቀን የሰማ እየመሰለው፣ እርሱ የነገሠበትን ቀን ሕዘብም ያን ቀን የነገሠ አድርጎ እየቆጠረው ሲያፈረስ ሲሠራ ነው የኖረው..............

  ReplyDelete
 17. Dear Dn.Daniel,

  Why you did not say any thing about Waldiba monastery area under construction for Sugar Industry and Park?. Do u ever imagine in Ethi, historical and spiritual heritages are destroyed for Park and Industry?

  Are you running away from Truth like those who do not believe in Bible and Jesus?
  Please Do Not say any thing about Commitment/Trush and also Do not mension about reveling the truth here after in your preaching.

  If the Media is wrong say it is wrong and do the same again for Gov and the father there as well.

  Please Say the Truth, Sorry for that saying that but Our Father may not protect the Church from any danger unlike Abune Petros, The Church has been left alone with any responsible leader..

  Please reveal the fact Truth as much as you can!! You usually say Do not in cooperate with false! in you speech/preaching.

  NASH,

  USA

  ReplyDelete
  Replies
  1. Hello man,

   It may take to time to solve. Just wait, he might disclose it like Ziquala. It may require him a time to do that.

   Your Brother,

   South Africa

   Delete
 18. Dani very great article, God bless u

  ReplyDelete
 19. «ውልድብና» እና «ኢውልድብና»

  የሚለውን ርዕስ ተመልከቱ ስለ ዋልድባ ጹሁፍ ዳኒ የጸፈውን ጽፏል ልብ የሚል ካለ

  ከጀርመን

  ReplyDelete
 20. its nice view and keep going!

  ReplyDelete
 21. daniel,i like your article as usual but now i have a quition for you. where is the truth about waldeba?i scared your silence.i hope you are not part of....!?we are waiting you!
  from USA,las vegas.God bless you.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ebakachu lemin tichekechikutalachu seel waldiba metsaf yalabetin tsifowale ke engdhe menegager kaleben egna min enseera neew? «ውልድብና» እና «ኢውልድብና» yemileewun temelketu

   Delete
 22. ስሜ ሃይማኖት ሆኖ እንኳን በሃይማኖት ጠንካራ በአለመሆኔ እራሴን እታዘብ ነበር በእይታህ እራሴን አገኘሁት፡፡ ምልከታህን አከብራለሁ፡፡

  ReplyDelete
 23. ይችን መጣጥፍ እያነበብኩ አንዱን የአገራችን አባባል አስታወስኩ "ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስጥ ጥዶ ማለቀስ" እያልን የምንተርተውን። እኛ ኢትዮጵያውያን አስር ድስት መጣድ እንጂ አንዱን በደንብ ማብሰል(ማንበር) ተስኖን አንዱንም ሳናበስል ሳናነብር እዚህ ደርሰናል። ሁሉም በተነሳ ባለፈ ባገደመ ቁጥር የራሱን ኢትዮጵያ የምትባል አዲስ ድስት የሚጥድ እንጂ ቀድማ የተጣደችውን ኢትዮጵያ
  የሚያነብር፣ ቀድሞ የተጣደውን የአሰራር ድስት ከማበሰል (ከማንበር) ይልቅ አዲስ የመዋቅር ድስት ለመጣድ አለሙን ሁሉ ማካለል በሚቀልበት ሀገር እየኖርን የውጭ ሚዲያዎች ኢትዮጵያ ተራበች፣ ተጠማች፣ ታረዘች... እያሉ ቢለፍፉ አግባብ እንጂ ስተቱ አይታኝም። ምክንያቱም የተጣደች አስር ኢትዮጵያ እንጂ ለማዕድ የደረሰች አንድ ኢትዮጵያ የት አለን? አንድ ታሪክ ትዝ አለኝ በአንድ ወቅት አንድ ህፃን ልጂ ፊኛ ነፍቶ በገመድ አንጠልጥሎ ከአባቱ ጎን ሆኖ ይጫወታል፣ በመሀል አባቱን አባቴ ይቺ ፊኛ ለምንድን ነው አየር ላይ የምትንሳፈፈው? ብሎ ይጠይቀዋል አባትም ልጁን የምትንሳፈፈው በገመድ አስረህ ስለያዝካት ነው ይለዋል ልጁም መልሶ ገመዱማ ወደታች እየጎተተብኝ ነው ሲለው አባትም እንግዲያው ቆይ ላሳይህ ብሎ ገመዱን ሲቆርጠው ፊኛዋ ወደቀች። አንድ አንዴ ወደታች እየጎተቱን የሚመስሉን ነገሮች ወደላይ ደግፈው ይዘውናል። ለእድገት ማነቆ የሚመስሉን ወደታች እየሳቡን ያሉ የሚመስሉን የቀድሞ አሰራሮች፣ መዋቅሮች፣ ባህሎች፣ ህግና ደንቦች፣ የሃይማኖት ስርአቶች... ወደላይ ለመንሳፈፋችን አይነተኛ ሚና አየተጫወቱ እንደሆነና ወደፊትም እንደሚጫወቱ መገንዘብ ተስኖን ልክ እንደ ፊኛው ገመድ ቆርጠን መጣልና ከቻልን አዲስ ፊኛ መንፍትና ለማንጠልጠል መሞከር ይቀለናል። በዚህ አካሄድ ደግሞ ውሃ ቢወቅጡ እምቦጭ ነው ነገሩ! የኖሮዌያዊው ግን እኔንም ገርሞኛል።

  ዳኒ እግዚአብሄር ከነቤተሰብህ ይጠብቅህ በጣም እናመሰግናለን!

  ReplyDelete
 24. I started following your blog recently. I appreciate your considered points of view concerning our society's diverse, multiple and invariable ills. This is a very important undertaking to bring to light new ways of thinking and doing things. I feel we have been comfortable for too long with our way of life. It is about time that we take stock of our dirty laundry and take concrete steps to clean up our mess. If we want to keep the best of what we have and introduce changes, we must start to think and act differently. It is evident that we cannot remain stuck with only what we know. Change requires stopping to stare at what lies beyond mountains of seemingly intractable problems. We rather need to shift our line of thought to address our problems.

  ReplyDelete
 25. አንድም ስለ ዋልድባ ገዳም አለመዘገብ ምን ያህል እምነት እንደለለ ያሳያል::
  እኜ ድሮም ቢሆን ያንተን ነገሮች አልከታተልም:: ምክንያቱም ብዙ ልታይ ልታይ ታበዛለህ አሁን ደግሞ ውስጥህ በእምነት የለለው መሆንክን አርጋገጥኩ:: አንዲት መስመር እንካን ስለ ዋልድባ ገዳም አለመዘገብህ::

  ReplyDelete
  Replies
  1. Please dear check the "«ውልድብና» እና «ኢውልድብና» " article in the following url

   http://www.danielkibret.com/2012/03/blog-post_18.html

   Do not hurry to roar before you check what is there inside here.

   Delete
 26. don't dare hasty generalization

  ReplyDelete
 27. yemigerm eyita. amlak ahunim yichemirleh abooo. . .

  ReplyDelete
 28. ሰላም ዲን ዳንኤል፣ በአንድ ቃል ላይ ተነስተህ ለሰጠኸው ዳሰሳ አመሰግናለሁ። አንዷን መዞ ከነባራዊ ሁኔታ ጋር፤ አያይዞ የማቅረብ ችሎታህን አደንቃለሁ። ይበል፤ግፋ፤በርታ ብያለሁ። በዚህ ዳሰሳህ ላይ ግን እኔ የማልስማማባቸው ነገሮች አሉ። እኛ ያለውን ነገር አፍርሰን ከዜሮ የመንጀምረው አባዜ የቃላቱ አለመኖር ጋር የተያያዘ አይመስለኝም። አንዱ በሰራው ሌላው ተደስቶ፤ ቢቻል አዲስ ነገር ታክሎበት አልያም በእንክብካቤ ይዞ መጠቀም አለመቻል ከቃሉ አለመኖር ጋር የመጣ ችግር አይመስለኝም። ከዜሮ የመጀመር አባዜው ከቃላት ችግር ቦሆን ኑሮ የሶስተኛ አለም አገራት ይህ ችግር ባልገጠማቸው ነበር። ከዜሮ ያልተነሳ ምሳሌ የሚሆነን ምንም አፍሪካዊ አገር የለም። እንዲያውም ምስጋና ይግባቸውና አባቶቻችን፤ ቅኝ ከተገዙ አገራት እኛ እንሻላለን። እነሱ ባህሉንም፤ ኑሮውንም፤ እነደ አዲስ ከሰው ቤት አምጠው እየኖሩት ነው። ለእኔ ከዜሮ መጀመሩ በአደጉ አገራት የተቀነባበረና ሴራ ነው። አቅጣጫው እስኪጠፋብን እያራወጡን የሚኖሩት እነሱ ናቸው። ማልያ እየቀያየሩ አይናችን እያየ፤ ሀገራችንን በድህነት መቀመቅ ውስጥ እየከተቷት ነው። አሁን ደግሞ፤ በመንፈስም ለመግደል ያለ የሌለ ሃይላቸውን ተክለውባታል። የተማሪ መሳይ ከራባት አድራጊ፤ ጳጳስ መሳይ ቆብ አጥላቂ፤ የኺ መሳይ ኬፕ አድራጊ፤ ፓስተር መሳይ ማያክራፎን ጨባጭ ልክው በልዩነት አረቋ ስር እየከተቱን ነው። እኒህ ሰዎች መድረክ ላይ ወጠው ውሸትን ሲነዱት ምንም የማይሰቀጥጣቸው ናቸው። እናም ያለውን አጥፍቶ የሚበላ ትውልድ ቢፈጠር አይገርመኝም። በጣም የሚያሳዝነኝ ግን ቢያንስ ፊደል ቆጠረ የሚባለው ኢትዮጵያዊ ነገሮችን ቆም ብሎ ማሰብ አለመቻሉ ነው። እንዲሁ እን ፔንዱለም ዥዋ ዥዌ ይላል። ካልተማረው ክፍል ብሶ አቅጣጫውንና አቅሉን ስቷል። በሌሎችአገር በተከሰተ ችግር ተመርኩዞ በወጣ መፍትሔ፤ ለአገሩ ይበጅ ይመስል እንደ ወረደ ገልብጦ ሲወራጭ ይታያል። አንዳንዱም ወንበሩ ላይ ስለተቀመጠ እየመራ የሚመስለውም አለ። ግን አይደለም። መርቶም አያውቅም። በመሪነት ቦታ ጉዳይ አስፈጻሚ ነው እንጂ። ጥሩ ተጨዋች መሆን ቢችል ጉዳይ እያስፈጸመም ቢሆን ታሪክ መስራት ይችል ነበር። ግን ፈሪ ነው። ወንበሩንም አያውቀውም። በፍርሃት ወገኑን ይጨርስበታል እንጂ። እንዲያስፈጽም ያስቀመጠው አካልም፤ ተጠቅሞ ከቸረሰ በዃላ እንዳልነበር ተደርጎ እንዲወርድ ይደረጋል። የጋዳፊ ወይም የሙባረክን መጨረሻ ማየት በቂ ነው። ከዚያ ሌላ ከዜሮ ጀማሪ ይመጣል። እየመረረንም ቢሆን ዜሮዎች ሁነን እንኖራለን!

  ReplyDelete
 29. egziabher mechereshahin yasamirilih lezich betekrstian endante ayinet she yiwold...

  ReplyDelete
 30. Base.worku@gmail.comApril 7, 2012 at 2:52 PM

  Hi!Dani beHager,be bete-xan sewoch Haymanotachewn ke keyeru behala,Zafuam znab flga tnkerata neger stchers ye Demena medresu,Lmat yemayawk ye Waldban Haymanotwinet,tarikawinet,Alemakfawinet...be Mesno sebeb mannetun matfat,denoch be est sigyu zm blew eyau be COPENHAGEN conference sle ayer nbret endi tebale...malet,H/Slassie ye aserutn Mengstu,ye Mengstun Meles manber kalchalu,ye wodft guzoachn bzum ezh gba yemibal aydelem. Any how ...

  ReplyDelete
 31. ኃ/ገብርኤል ከአራት ኪሎApril 7, 2012 at 3:30 PM

  ለ NASH,USA
  ስለ ዋልድባ ገዳም ዲ/ን ዳንኤልን ለምን ዝም አልክ ብለው ከውስጥ በመነጨ ስሜት ጠይቀዋል። ምናልባት በስራ ምክንያት ይህንን መጦመሪያ በየጊዜው ስለማይጎበኙት ካልሆነ በቀር ዲ/ን ዳንኤል አምልቶና አስፍቶ «ውልድብና» እና «ኢውልድብና» በሚል ርዕስ Sunday, March 18, 2012 አቅርቦታል። እሱስ ያቅሙን ጮዃል ሰሚ አጣ እንጂ። ብዙዎቻችን እንቅልፍ በጣለን ወቅት ብቻውን አልተኛም ነበርና ጩኸቱን የሰማው የለም። ዛሬም ድረስ ይጮኻል። የነቃን ጊዜ እንሰማው ይሆናል ጅብ ካለፈ ቢሆንም።

  ReplyDelete
 32. ዳንኤል
  "...«ማንበር» .... «በጥቅም ላይ እያዋሉ እንደ ነበር ጠብቆ ማቆየት» ይሉታል፡፡ እኔም ይህንን ካየሁ በኋላ ለመሆኑ በባህላችን ማንበር አለ? ብዬ ጠየቅኩ፡፡ ከእምነት እስከ ... ሥነ ሕዝብ "ማንበር"ን ፈተሽኩት፡፡ እኔም አላገኘሁትም፡፡" አልክ

  እኔ ግን ሃይማኖቴ ውስጥ አገኘሁት!

  ReplyDelete
 33. pls we shall not wait for some one to perform all the task. lets all do what we are capable of doing.the article u wrote about maintenance is in our blood, we the Ethiopians and need to change. Kinfe Geberiel from Arada Giorgis.

  ReplyDelete
 34. Manber


  Tadey from Addis ababa

  ReplyDelete
 35. Daniel you are right! I fully agree with your Idea! But We have to Start Today You are writing and we are reading. Let's start to apply "Manber" in every aspect of our life.
  Don't be afraid for everything including politics,religious leaders, others... Let's Start New Ethiopianism by implimenting "Manber"!
  Let Our God Jesus Christ Be with us! Amen.

  ReplyDelete
 36. በጣም ደስ የሚል ሀሳብ ነው ልብ ላለው

  ReplyDelete
 37. Dani: Hulun neger gin fursh atarigibina. Andande gize andin neger ye metifom ye tirum misale arigo metenten yichalal. ena Yekalun alemenor ende yebahil woyim ye amelekaket chigir bicha arigeh atakiribewu. Lenegeru beagerachin ante yemitilew ayinet siram yiseral, yekalatochi tirgum ashami silemihon yimeslegna.

  But, I follow ur blog every day and like most of your views and critics. Just give constructive comments as well.
  thanks Dani, keep it up

  wassihun

  ReplyDelete
 38. r u ok Dani? tefah

  ReplyDelete
 39. **************************
  ከኋላ የመጣው ሀገሪቱን እንደ አዲስ ሲጀምራት፡፡ እርሱ መንበር ላይ በተቀመጠ ቁጥር ነጻ ሲያወጣት፡፡ ከዚያ በፊት ለነበራት ህልውና ዕውቅና መስጠት ተስኖት ራሱ የፈጠራት አገር ሲያደርጋት፡፡ ደንቆሮ የሰማ ዕለት ያብዳል እንደሚባለው እርሱ ስለ ነጻነት የሰማበትን ቀን ሕዝብም ያን ቀን የሰማ እየመሰለው፣ እርሱ የነገሠበትን ቀን ሕዘብም ያን ቀን የነገሠ አድርጎ እየቆጠረው ሲያፈረስ ሲሠራ ነው የኖረው፡፡
  ***********************************
  The above is a perfect match for delusional TPLF.TPLF is considering Ethiopia and its peoples as its own private trophy obtained by its 'sacrifice'.Is TPLF liberating us or enslaving us?TPLF does not know the essence of "MANBER" and what it only knows is denounce the previous regimes for every thing and also abolishing all good things done by them.TPLF knows how to build a monument like "SEMAETAT HAWLT" for us to remember the bad side of our history and the bad days only.But when it comes to remembering our good side of our history and then erecting a monument for our HIM Haileselasie besides that of Nikurumah of Ghana then it does not want to do so.Why?Because TPLF does not know "MANBER"
  How comes you dare to rule a certain nation and its peoples if you deny their very history that be it bad or good it may be.
  Meles and TPLF aspires and wants to create a new Ethiopia in its image and likeness(characterized by racism,insanity,hatred,betrayal,plundering) ,but eventually we ended up in tragedy and failure like this.There is no such a thing as "MANBER" in the ABC governance dictionary of TPLF.Yes TPLF has created new wrecked and impoverished Ethiopian peoples and Ethiopia which is totally disgraceful failure as a nation.Really the top most disgraceful shame in Ethiopian history.

  ReplyDelete
 40. Dear Danile,
  Thankyou for the article. It is a great job. A nice piece of analysis. But you should make some corrections. Professor Shiferaw is not the one who coined the word 'manber'. The word is coined by Dr. Yeraswork. Please, look at the source again. Hence, all the appreciation you provided should go to the appropraite person. Right? We have lots of other issues to appreciate Professor Shiferaw.

  Thankyou for considering the comment

  ReplyDelete
 41. ዳኒ ኘሮፊሰሩ የሚገርም እይታ አላቸው ሌሎች የታሪክ ሰዎች አሉ እያቸው

  ReplyDelete
 42. የአክሱምን ከተማ አጥፍተን፤ ላሊበላ ላይ ሮሃን የገነባን ጀግኖች፤ ይህም አልበቃ ብሎን ደግሞ ሮሃን አጥፍተን የጎንደር ከተማን መገንባት ጀመርን፤ ያንንም አልቆየንበት የከተማውን ቅሬተ አካል ብቻ ትተን ደግሞ አንኮበር ወረድን:: በየወንዙ በየተራራው ስንዞር ከርመን ነው አዲስ አበባን ከ125 ዓመት በፊት ያገኘነው:: ልደቷ ሲከበር ከተማችን በስንት ከተሞች ደም መፍሰስ መገንባቷን ልናስታውሳት ይገባ ነበር ::

  ከተማ ፍለጋ ይህን ያህል የዞርነው ግን ምን ሆነን ነው? የከተማ መስፈርታችን ምን ነበር? ይህ ሁሉ ዙረት ለግማደ መስቀሉ ማረፊያ መስቀለኛ ተራራ ፍለጋ አይደለም:: ለከብቶች ግጦሽ ለምለም መስክ ፍለጋም አልነበረም:: የአፍሪካ መዲና የምትሰራበትን ከተማ ፍለጋ ይሆን? ነገ ደግሞ የት እንከትም ይሆን?

  እያጠፋን ስንመሠርት አብረን የገደልናቸው ስንት ታሪኮች፣ቅርሶች፣ ሥነጥበባት፣ በጎ ልምዶች፣ . . . አጥፍተን ይሆን? ለስንቱ በድህነቱ ላይ ሌላ ድህነት ጨምረንበት ይሆን? የገነቡትን እያፈረስን የራሳችንን ገነባን የኛን የሚያፈርስ ለመምጣቱ ግን እርግጠኞች አልነበርንም:: ነገሥታቱና መኳንንቱ ያቆሙትን መሳፍንቱ አፈረሱትና ግንባታቸውን ቀጠሉ የነርሱም ዘመን አጠረና ሌሎች ዘውድ የጫኑ መጡ የነርሱም ፈረሰ ፤የትንንቱ የጀመረውን በጎ ጅምር እንኳ መቃብሩ ላይ ካልሆነ መሥራት አንችልበትም:: ደርግ በዘውዱ መቃብር ላይ ራሱን ገነባ በርሱ መቃብር ላይ የመጡትንም መቃብር ካላወረድኩ የሚል ሞልቷል:: አዲስ አበባ 125 . . . !

  ReplyDelete
 43. You should right about Waldiba monastery in a very clear way and I hope you do it. Thanks!

  ReplyDelete
 44. thank you Dani, what about BPR(Business process Re-engineering in Ethiopia?

  ReplyDelete
 45. ሳሚ (ወ/ሚካኤል)April 11, 2012 at 9:53 AM

  ህህህህህህ....ይመስጣል!!!!ልብንም ይመልጣል!!!! ዳኒ አንድ ሰሞን ጉዋደኞቸ የአክሱምና የላሊበላ ትውልድ ለምን ላሁን ዘመን ትውልድ ተገላቢጦሽ ሆነ መሃል ላይ የሞተ(የጠፋ ) ትውልድ አለ! ብለው ለሞገቱኝ ሙግት ግምታዊ መልስ መስጠት ተስኖኝ ሳይሆን ማሰቡ አታክቶኝ እራሤን ላለማጨናነቅ ከጥያቄያቸው ተደብቄ እኖር ነበር!!!! አሁን ግን ግምትም ሳይሆን ተክክለኛውን መልስ አግኝቻለሁ!!! አፍርሶ የመስራት ልምዳችን እነደዚህ አይነት ወኔ ቢሰ ትውልድ እንዳበቀለ ገባኝ!!!!!!የባለፈው የዝቁዋላ ገዳም ቃጠሎ እና የዋልድባ ቅዱስ ምድር መደፈር የመጣውም ከዚሁ ልማዳችን ነው ብየ አሰብኩ !!! ሲቃጠል መሮጥ እንጅ እንዳይቃጠል መጠበቅ አለመደብንም!!! ሲቃጠል የወጣውን የገንዘብና የሰው ሃይልን አስተባብረን ከመቃጠሉ በፊት ለገዳማችን አውለነው ቢሆን ኑሮ የገዳሙ አሰተዳደርን ከመገንባት አልፈን ዙሪያ ጥጉን በከፍተኛ ጥበቃና ክትትል መጠበቅ የሚችል ከፍተኛ ሃይማኖታዊ ተቁዋም የሚሆንበትን አቅም በፈጠርንለት ነበር!!!! ጊዜው ህማመት ነውና ጌታችን እና አምላካችን ክርስቶስን ለ "ማንበር" አይነተኛ ምሳሌ አርገን መጥቀስ እንችላለን!!!
  ክርስቶስ የሰውን ልጅ መበላሸት (መውደቅ) ለመጠገን አፍርሶ መስራትን አልወደደም!! እንደዛው እነደቆሸሸ በደሙ አጥቦ አነጻው እንጅ!!! ረክሱዋልና ይህን ስጋ ላጥፋው ማለት ሲችል ጭራሽ የሱን ስጋ ተዋህዶ ሙቶለትም ሳያጠፋው በገነት በነበረው ክብር አደሰው!!!! ይህ ነው ማንበር!!! ሳይንዱ መካብ ለሚለው ከክርስቶስ መምጣት በላይ ምሳሌ የሚሆን አይገኝም!!!!! አሜን ኪሪዬ ኤሌይሶን!!!!!!
  መምህር ዳኒ የቃሉን ፍች እያበራ በመንፈሱም ልሳንህን እያበረታ በብዙ ቁዋንቁዋ (በጡመራ..በስብከት ወዘተ..) ህዝቡን ሁሉ ወደ ተዋህዶ እውነት መላሽ ወልደ ሐዋርያት ያድርግህ!!!! መልካም የትንሳኤ በአል ከወዲሁ ተመኘውልህ!!!

  ReplyDelete
 46. ዳኒ ሰላም ላንተ ይሁን!
  በምልከታህ በከፊል ስማማ በከፊል አልስማማም፡፡ ዳሩ አንተም ብትሆን ‹‹ ሁላቸሁም ተቀበሉ ፍልስፍናው ይኸው ነው አለቀ ደቀቀ›› አላልከንም!
  የተዘረዘሩት ሁሉን አቀፍ ችግሮቻችን ያንሱ ካልሆነ ዕውነታው ይኸው ነው፡፡ ሁላችንም እንደምንረዳው የአፍሪካውያን (ኢትዮጵያን ጨምሮ) ችግር በአንድ ጀንበር የተፈጠረ አይደለም፡፡ በአንድ ወቅት የዩጋንዳው ዩወሪ ሙሴቪኒ ስለዚህ ጉዳይ ሲናገሩ ‹‹የችግሮቻችንን መንስዔ ለመመልከት 500 ዓመታት ወደኋላ መመልከት ይኖርብናል›› ብለው ነበር፡፡ (ስጋ ቁጠር ቢሉት…ካላልከኝ!) ምክንያታቸው በዚያ ወቅት አፍሪካ ወጣቶቿን፤ መሪዎቿን፣ ፈላስፎችዋን… በግፍ እና በገፍ በመዘረፉዋ ነው፡፡
  ምሳሌ ቢስፈልግ! ተመልከት እስኪ! በዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ ብቻ የሚገኙ ሀገር ቤት የተማሩ ኢትዮጵውን ሜዲካል ዶክተሮች እዚህ ሃገር ቤት ካሉት በብዙ ይበልጣሉ፡፡ ራሳችን እንደ ጧፍ እየነደድን ለሌሎች ምቾት እየኖርን ነው፡፡ የሃሳብ አመንጪዎቻችን እና አሳላጮቻችን እንዲሰደዱ ለምን ሆነ? የስልጣኔ ፋና የሚያበሩ፣ ማኅበረሰባችንን ለማዘመን የሚተጉ…አብነቶቻችን (አይከኖቻችን) ወዴት ሄዱ?... ሁሉን ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራል !

  ReplyDelete
 47. i have been learning from your great thinking and philosophy.thank you Diakon Daniel Kibret. i wish you were more than many/more.
  long live Ethiopia
  AYCHEW.

  ReplyDelete
 48. yared
  I respect your view.To maintain our wealth we have to know it.When we know it we start to appreciate. Appreciation is a sprig board to maintain.

  ReplyDelete
 49. yes, We don't have this and we suffer a lot because we miss it. Please every one let us use "Manber" from now onwards.

  ReplyDelete