ወደ ዝቋላ አያሌ ወጣቶች ከአዲስ አበባ፣ ከደብረ ዘይት እና ከናዝሬት በመጉረፍ ላይ ናቸው፡፡ የእነዚህ ወጣቶች ወደ ቦታው መንቀሳቀስ ቢያንስ እሳቱን ወደ ገዳሙ ዘልቆ በመነኮሳቱ መኖርያ እና በአብያተ ክርስቲያናቱ ላይ አደጋ ከማድረስ ታድገውታል፡፡ ወደ ወንበር ማርያም ከተጓዙት የውኃ ቦቴዎች በወጣ ቶች ኃይል በማጓጓዝ፣ እሳቱ በመጣበት አቅጣጫ የሚገኙ የተወሰኑ ዛፎችን በመቁረጥ እና ሣሩን በማንሣት እሳቱ እንዳይተላለፍ አድርገውታል፡፡
ወደ አሥራ አንድ ሰዓት አካባቢ ተግ ካለ በኋላ በአሁኑ ሰዓት እሳቱ አጣብቂኝ እየተባለ ከሚጠራው ቦታ እስከ ዓርብ ረቡዕ ድረስ ባለው ቦታ ላይ ማምሻውን እንደገና የመጣ ሲሆን ወደ ገዳሙ እንዳ ይዘልቅ ለማድረግ በአካባቢው የደረሱት ወጣቶች ነቅተው በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡
በአካባቢው የሚገኙ የአደጋ ተከላካዮች እንደሚገልጹት እሳቱ አንድ ጊዜ እየቆመ ሌላ ጊዜ ካልታሰበበት አቅጣጫ ይመጣል፡፡ ይህም የመከላከሉን ሥራ ከባድ ያደረገው ሲሆን እሳቱ ጠፍቷል የሚል መረጃ እንዲሠራጭም አድርጓ፡
የገዳሙ መነኮሳት እንደገለጡልኝ አሁን ችግሩን ለመቋቋም ሁለት ዓይነት ተግባራት ያስፈልጋሉ፡፡ በአንድ በኩል ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡት በጎ ፈቃደኞች መጥ ረቢያ፣ አካፋ እና መቆፈርያ እየያዙ ቢመጡ የመከላከሉን ሥራ የተቃና ያደርገዋል፡፡ በተለይም አቅና የሚባለው የመቆፈርያ ዓይነት ለዚህ ሥራ አመቺ በመሆኑ ይህንን መሣርያ ይዘው እንዲመጡ ጥሪ አድርገዋል፡፡
የገዳሙ መነኮሳት እንደገለጡልኝ አሁን ችግሩን ለመቋቋም ሁለት ዓይነት ተግባራት ያስፈልጋሉ፡፡ በአንድ በኩል ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡት በጎ ፈቃደኞች መጥ ረቢያ፣ አካፋ እና መቆፈርያ እየያዙ ቢመጡ የመከላከሉን ሥራ የተቃና ያደርገዋል፡፡ በተለይም አቅና የሚባለው የመቆፈርያ ዓይነት ለዚህ ሥራ አመቺ በመሆኑ ይህንን መሣርያ ይዘው እንዲመጡ ጥሪ አድርገዋል፡፡
ሁለተኛው ደግሞ በሚቻለው ፍጥነት ሁሉ እሳት የማጥፋቱን ተግባር በአውሮፕላን ወይንም በሄሊኮፕተር ለማገዝ እንቅስቃሴ ማድረግ ነው፡፡ ለዚህ ተግባርም የመንግሥትን ድጋፍ ማፈላለግ ያለበለዚያም በግል ተነሣሽነት ወጭውን በመሸፈን የእሳት ማጥፊያ አውሮፕላን ወይንም ሄሊኮፕተር ወደ ቦታው እንዲሄድ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን በቦታው የሚገኙት የአደጋ ተከላካዮች ገልጠዋል፡፡
ከተለያዩ ከተሞች ወደ ገዳሙ የዘለቁት ምእመናን ሌሊት እና ቀን ያለ ዕረፍት የሚያደርጉትን ተጋድሎ ምግብ እና ውኃ በማቅረብ፣ በገንዘብ፣ በቁሳቁስ እና በጸሎት እንድናግዛቸው ጥሪ ቀርቧል፡፡
በእግዜአብሔር እርዳታ፣ በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስም አማላጅነት፣ በሁላችንም ትብብር አደጋውን መቀነስ ተችሏል፡፡ እሳቱ ግን ገና ፈጽሞ አልጠፋም፡፡ እናም ይበልጥ ተረባርበን ችግሩን እንዳይመለስ አድርገን መፍታት አለብን፡፡ እያንዳንዷ ሰዓት የራስዋ ዋጋ አላትና፡፡
egizabher yemasigan. tadiya ke'ena min yetabekal? how much does it cost to use the airplane? i can ask people here. can u let me know if "dkibretherhane@gmail.com" is ur email account so we can communicate.i will email u too plz check
ReplyDeleteዳኒ በጣም የሚያሰመሰግን ሥራ ሰርተሃል፡፡ አክብሮቴ ይድረስህ፡፡ ለብዙዎች አርዓያ መሆን የምትችልና ፍፁም ለቤተ-ክርስቲያናችን ተቆርቋሪ መሆንህን አሳይተካል፡፡ እግዚአብሄር ቤታችንንም አንተንም ይባርክ፡፡ ሥራህን አክብሬያለሁ፡፡
ReplyDeleteThanks, Dn Daniel. I was searching for an update after your last post but there was none over the net. I had to wait for your update and here it is. You are doing a good job and thank you. I would like to thank everyone participating in the effort to put the fire off. Let God be with men and women, the young and the old in their struggle with this temptation. Let His mercy be upon us. This is a time of awakening for those who are making our Church bleed. Please start to think and act like real fathers before God's wrath comes upon you. Let him hear who has hears.
ReplyDeleteዲያቆን ዳኒ እግዚአብሄር አብዝቶ ይባርክህ, ገዳሙን ለመርዳት ስልክ ቁጥር ወይም አድራሻ ካለ ብታሳዉቀን
ReplyDeleteአምላከ ቅዱሳን በቸርነቱ በገዳሙ ከመጣዉ አደጋ ይታደገን
Amelak gebere menfes kedus yerdachihu.
ReplyDeleteDani ebakhn pdf option binorew bizu sew ke phone manbeb ychilal!!!!!
ReplyDeleteThank you
D/n Daniel thanks a lot for the updating, please coordinate the way to contribute money from those whom can't be there
ReplyDeleteBemen enagegnachu yegenzeb erdata lemadereg???eruk ager yalen endet enderess?
ReplyDeleteLet God of our early fathers' help us.
ReplyDeleteይህች ሀገር ግን መንግስት አላት?....የተጎዱ ቱሪስቶችን ለመታደግ ምን እንደተደረገ እናውቃለን!...የቤት ቀጋ የውጭ አልጋ ይሉሀል ይሄ ነው
ReplyDeleteMay God help us .
ReplyDeleteእኔ እስከ ምረዳው ድረስ መንግስት በሃይማኖት፣ ሃይማኖት በመንግስት ጣልቃ አይገባም የሚባው በመሰረታዊ የሃይማኖት ዶግማ ስራአት ላይ መንግስት ጣልቃ መግባት እንደማይችል እንጂ ሀይማኖት ያቆየውን ቅርስ እና ሀብት እየወደመ መንግስት ቅርሱን ና ሀብትን ለመታደግ በሚደረገው ርብርብ ጣልቃ አይገባም የሚባል አንድምታ ካለ ታሪካዊ ስህተት መፍጠራችን ነውና ይህን ንባብ የምታነቡ የተለያየ እምነት ተከታይ ወንድሞች እና እህቶች ከሀይሞኖት ይዞታነቱ ባሻገር ሀገራዊ የሆነውን የዝቃላ ገዳምን ለመታደግ በሚደረገው ርብርብ ለሚመለከታቸው የክልል እና የፌደራል ባለስልጣናት የተለያዩ መገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም መልእክቱ እንዲደርሳቸው የተቻለንን ርብርብ በማድረግ ገዳሙ ከተጋረጠበት የእሳት ቃጠሎ በመታደግ ታሪካዊ የዜግነት ሃላፊነታችንን እንወጣ፡፡
ReplyDeleteአቤቱ የማርያም ልጅ ሆይ ቤተክርስትያናችንን ታደግ
ሁለተኛው ደግሞ በሚቻለው ፍጥነት ሁሉ እሳት የማጥፋቱን ተግባር በአውሮፕላን ወይንም በሄሊኮፕተር ለማገዝ እንቅስቃሴ ማድረግ ነው፡፡ ለዚህ ተግባርም የመንግሥትን ድጋፍ ማፈላለግ ያለበለዚያም በግል ተነሣሽነት ወጭውን በመሸፈን የእሳት ማጥፊያ አውሮፕላን ወይንም ሄሊኮፕተር ወደ ቦታው እንዲሄድ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን በቦታው የሚገኙት የአደጋ ተከላካዮች ገልጠዋል፡:
ReplyDeleteይህች ሀገር ግን መንግስት አላት?....የተጎዱ ቱሪስቶችን ለመታደግ ምን እንደተደረገ እናውቃለን!...የቤት ቀጋ የውጭ አልጋ ይሉሀል ይሄ ነው
if they are true Government why they help us at this time for this fire, Rent the Helicopter for this work meaning this government is not Ethiopians,yigermal
thank you
Egziabhair yirdachehu
ReplyDeleteare fetari anete enkuan tadegen menegestes atan !!
ReplyDeleteዲ.ዳንኤል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይባርክህ፤
ReplyDeleteየስልክ ፡ ወይንም ፡ የባንክ ፡ ቁጥር ፡ ካለ ፡ ይነገረንና ፡ እንርዳ፡፡ ካለንበት ፡ ቦታ ፡ ከመጨነቅ ፡ በቀር : ምንም ፡ ማድግ ፡ አልቻልኩም፡፡
ሰማዕቱ ፡ ጊዮርጊስ ፡ ለአባቶቻችን ፡ በጠላት ፡ በተወረሩ ፡ ግዜ ፡ አንደደረስክላቸው ፡ አሁንመም ፡ ለኛ ፡ ድረስልን፡፡
አሜን!!!
Selistu dekiken kesat yawetah egziabiher iridan
ReplyDeleteእግዚአብሔር ይርዳችሁ
ReplyDeleteእግዚአብሔር ይርዳችሁ
ReplyDelete