Thursday, March 29, 2012

ሁለቴ መቸገር


      © ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው፡፡ በሌላ መሰል ኅትመት ባይወጣ ይመረጣል፡፡
«ከተራበ ይልቅ ለጠገበ አዝናለሁ» ይሉ ነበር አጎቴ፡፡ ለምን ብዬ ጠየቅኳቸው፡፡ «ሰው ተርቦ ከሚደርስበት ጉዳት ጠግቦ የሚደርስበት ጉዳት ይበልጣል» አሉኝ፡፡ «ሰው ጠግቦ ጉዳት ያደርሳል እንጂ ምን ጉዳት ይደርስበታል?» አልኳቸው፡፡ «እርሱኮ ነው ጉዳቱ፡፡ በሰው ላይ ጉዳት አደርሳለሁ ብሎ የሚመጣበት ጉዳት፡፡ ለተራበ ሰው ውድቀት ማለት ከመጀመርያው ደረጃ እንደ መውደቅ ነው፡፡ የጠገበ ሰው ውድቀት ማለት ግን ከመጨረሻው ደረጃ አጓጉል እንደ መውደቅ ነው» አሉ፡፡
ይህ የእርሳቸው አባባል የሕንዶችን ታሪክ ያስታውሰኛል፡፡ ሕንዶች ረሃብም ሆነ ጥጋብ ሁለቱም እኩል ይጎዳሉ ይላሉ፡፡ ረሃብ እና ጥጋብ ሁለቱም የጤንነት፣ የደኅንነት እና የሰላም ዕንቅፋቶች ናቸው ብለውም ይጨምሩበታል፡፡ ረሃብ እና ጥጋብ ሀገርን እኩል ነው የሚጎዷት ሲሉም የሚከተለውን ይተርካሉ፡፡
ሕንድ ውስጥ አንድ ትልቅ ሕንጻ የሚያሠራ ሰው ነበረ፡፡ ይህ ሰው ሕንፃውን ለማሠራት ቆሞ እያለ አንድ የኔ ቢጤ ወደርሱ ይመጣል፡፡ ያም የኔ ቢጤ የሳንቲም ድቃቂ የልብስ እላቂ ፈልጎ ሀብታሙን ሰውዬ ይለምነዋል፡፡ ሀብታሙም ሰውዬ «ተመልከት እኔ ሕንፃውን የሚሠሩልኝ ሰዎች ፈልጌ እዚህ ቆሜያለሁ፡፡ ታድያ አንተ ሠርተህ ለምን አትበላም?» አለው፡፡
የኔ ቢጤውም «መሥራት አልችልም» ሲል መለሰለት
«ለምን?» አለው ሰውዬውም
«ሆዴ ባዶ ነው፤ ጠኔ አሞኛል መሥራት አልችልም» አለው፡፡
ሕንፃ አሠሪ በሁኔታው አዘነና ባለሟሎቹን ጠርቶ ሰውዬውን እስኪበቃው ድረስ አብልተው እንዲያመጡት አዘዛቸው፡፡ እነርሱም ያንን የኔ ቢጤ ወደ ቤት ወስደው አይቶት የማያውቀውን ምግብ እና መጠጥ አቀረቡለት፡፡ እርሱም እምብርቱ እስኪለጠጥ የቻለውን ያህል አስገባ፡፡
ባለሟሎቹ መጥገቡን እንዳረጋገጡ ሕንፃው ወደሚሠራበት ቦታ ወሰዱት፡፡ የኔ ቢጤው ግን ወደ ሥራ መሠማራት አልቻለም፡፡ አንድ ዛፍ ሥር ተቀመጠ፡፡ ባለቤቱም ሲመጣ ዛፍ ሥር ተቀምጦ አገኘው፡፡
«እህ ጠገብክ» አለው
በዓይኑ ሰውዬውን በእጁም ሆዱን እያሸ በአንገቱ አረጋገጠለት፡፡
«መልካም በል አሁን ተነሣና ወደ ሥራ ተሠማራ፤ ከዚህ በኋላ ለምኖ መብላት የለም» አለው ሕንፃ አሠሪው፡፡
«አልችልም» አለ የኔ ቢጤው፡፡
«በልቼ ጠግቤያለሁ አላልክም»
«ልክ ነው ጌታዬ»
«ታድያ ቅድም ሥራ ስልህ ሆዴ ባዶ ስለሆነ በባዶ ሆዴ መሥራት አልችልም አልከኝ፡፡ አሁን ከጠገብክ ለምን አትሠራም»
«አሁን ደግሞ ሆዴ ከመጠን በላይ በመጥገቡ አሞኛልና ጎንበስ ቀና ብዬ መሥራት አልችልም» አለው፡፡
ርሃብም ያማል፤ ጥጋብም ያማል ያሉት ሕንዶች ለዚህ ነው፡፡
አለመማርም፣ መማርም፣ የሚያማቸው ሰዎች ገጥመዋችሁ አያውቁም፡፡ አንዳንዶቹ በሥልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ለምን ያጠፋሉ? ለምን ሀገር ይጎዳሉ? ለምን ሕዝብ ያስለቅሳሉ? ለምን ፍርድ ያዛባሉ? ለምን በሙስና ይዋጣሉ? ለምን የዘመድ አዝማድ አሠራር ይዘረጋሉ? ደረቴ ይቅላ፣ ሆዴ ይሙላ ብለው ብቻ ለምን ያስባሉ? እያልን እንጠይቅና ባይማሩ ይሆናል ብለን እናስተሠርይላቸዋለን፡፡
አንድ ኢትዮጵያዊ ደራሲ
ያላወቁ አለቁ ነበረ ተረቱ
እያወቁ ማለቅ መጣ በሰዓቱ
እንዳሉት ለቦታው እና ለሥራው፣ ለኃላፊነቱ እና ለወንበሩ የሚመጥን ዕውቀት ኖሯቸው፣ ዐወቁ፣ መጠቁ፣ ላቁ ያልናቸው ሰዎች ያልተማሩ ሰዎች የሚያጠፉትን ያህል ሲያጠፉ፣ ከዚያም በላይ ሲብሱ በምን እናስተሥርይላቸው?
መማርም አለመማርም እኩል ነው እንዴ የሚጎዳው?
ተለወጡ፣ አደጉ፣ ተመነደጉ፣ ኢንቨስተር ሆኑ፣ ሠለጠኑ፣ ተሾሙ፣ ተሸለሙ በሚባሉ ወገኖቻችን ላይ ዕድገት ነው የማየው ወይስ ጥጋብ? የሚለው ጥያቄ እስካሁን መልስ ላገኝለት አልቻልኩም፡፡ ዕድገት የአእምሮ ነው፣ የአመለካከት ነው፣ የልቡና ስፋት ነው፣ የኅሊና ምጥቀት ነው፣ የአስተሳሰብ አድማስ ንጥቀት ነው፣ የኃላፊነት መሰማት ነው፣ ለነገ ጭምር ማሰብ ነው፡፡
ጥጋብ ግን የሆድ ብቻ ነው፡፡ የቅሪላ መነፋት ነው፡፡ ከክብደት እና ከቅላት፣ ከወዝ እና ከስፋት ጋር የሚሄድ ነው፡፡ ዕድገት አገርን፣ ጥጋብ ሆድን ብቻ ያሳድጋሉ፡፡ መጥገብን ማንም ያውቀዋል፡፡ ይታያል ይዳሰሳል፡፡ ይጨበጣል፡፡ ጥጋብ ታይታ ይበዛዋል፡፡ የመኪና ጋጋታ፣ የግብዣ ቱማታ፣ የጌጣ ጌጥ ሻሻታ ነው ጥጋብ፡፡
አንዳንዱ ወገናችን ተራ ሰው ሆኖ አይሠራም፡፡ ምክንያት ሲሉት ችግሩን ያወራል፡፡ ባለ ሥልጣን ሆኖም አይሠራም፡፡ ምክንያት ሲሉ ጥጋብ አላሠራው ብሏል፡፡ አንዳንዱ ወገናችን ላጤ ሆኖም ያማርራል፡፡ ምክንያት ሲሉት የሞቀ ቤት፣ የሞላ ትዳር ናፈቀኝ ይላል፡፡ አግብቶ ጠግቦ ያማርራል፡፡ ምነው ሲሉት ትዳር ከውጭ ያሉ እንግባ እንግባ፣ ከውስጥ ያሉ እንውጣ እንውጣ የሚሉበት ነው ይላል፡፡
አሁን በተማረው ወገናችን ያለው ዘንድ ጥጋብ ነው ወይስ እድገት ነው? የተለወጠው ማዕረጉ ነው ወይስ አመለካከቱ፣ የተሻሻለው ደመወዙ ነው ወይስ ዕውቀቱ? የሠለጠነው በምርምር ነው ወይስ በማጭበርበር ስልት? ጊዜውን የሚያሳልፈው ሥጋ ላይ ነው ወይስ ንባብ ላይ? ያጠናው ትንተና ነው ወይስ ቅንቀና?
ሕፃን ሆኜ የሰማሁት አንድ ተረት እዚህ ላይ ኖር ሊባል ይገባዋል፡፡ ያኔ ትርጉሙ አይገባኝም ነበር፡፡ ትርጉሙ የገባኝ አሁን ነው፡፡ አሞራ እና አይጥ ተጋብተው ለኑሮ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ፍለጋ ሲዞሩ አንድ በእህል የተሞላ ስልቻ ያገኛሉ፡፡ ስልቻውን አሞራ አንጠልጥሎ፣ አይጥም በጥርሷ እየጎተተች ወደ ማደርያቸው ይወስዱታል፡፡
እዚያ ደርሰው ሲፈቱት ለካስ የባቄላ ገለባ የተሞላ ኖሯል፡፡ መቼም በውስጡ አንዳች አይጠፋውም ብለው ፈተሹት፡፡ በመጨረሻም አንድ ፍሬ ባቄላ አገኙ፡፡ ባቄላውን እንዳገኙ ሁለቱም ክርክር ገጠሙ፡፡ አይጥ «ይህቺ በቄላ ተበልታ ምንም አትጠቅምም፤ ስለዚህ እንዝራት» አለች፡፡ አሞራ ደግሞ በጣም ርቦት ስለነበር እንደ ጓያ ነቃይ የዕለቱን አሰበና «የለም ለነገ ነገ ያውቃል፣ ዋናው ዛሬ ነው፣ እንብላት» አለ፡፡
በዚህ ክርክር እስካሁን አይጥ እና አሞራ እንዳልተስማሙ ይነገራል፡፡
ምን አይጥ እና አሞራ ብቻ እኛም አልተስማማንም፡፡ የሀገሪቱም ጥያቄ ይኼው ይመስለኛል፡፡ እንብላት እንዝራት? በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ «እንብላት» የሚለው ከበዛ በሀገሪቱ ውስጥ ዕብጠት እንጂ ዕድገት ሊኖር አይችልም፡፡ ሆዳቸው፣ ኪሳቸው፣ ሀብታቸው፣ ጡንቻቸው፣ ጉንጫቸው፣ አንጎላቸው ያበጠ ብዙ ዜጎችን እናፈራለን እንጂ አእምሮአቸው እና ኅሊናቸው፣ ልቡናቸው እና ሰብእናቸው ያደገ ዜጎችን በሥዕ ለትም አና ይም፡፡ ዕድገት የአእምሮ፣ ዕብጠትም የጥጋብ ውጤቶች ናቸው፡፡
ሰው ሲርበው በቁጭት እና በእልክ፣ በአልሸነፍ ባይነት እና በአልሞት ባይ ተጋዳይነት መሥራት አለበት፡፡ የሚታገለው ስለበላ፣ ስለሞላለት እና ለትግል የሚሆን ነገር ስላለው አይደለም፡፡ እንዲበላ፣ እንዲሞላለት እና ለተሻለ ትግል የሚሆን ነገር እንዲያገኝ እንጂ፡፡ ሰው ሲበላም በምስጋና እና የተሻለ ነገርን በማለም፣ ርካታው በጥማት፣ ሙላቱም በጉ ድለት እንዳይተካ ነገን ለማስተማመን መሥራት መታገል አለበት፡፡
ሲያጣ ራበኝ ብሎ፣ ሲያገኝ ጠግቦ መሥመር የሚስተውን ግን ምን ማድረግ ይቻላል፡፡ እነዚህን ሁለቱንም የያዘች ሀገር ጉዞዋቸውን በቁሳዊ ርካታ እና በቁሳዊ ድል በሚለኩ ዜጎች ትሞላለች፡፡ ድህነት እና ውርደትን፣ ዕድገት እና ጥጋብን መለየት በማይችሉ ዜጎች ትሞላለች፡፡ ሀገርን እነዚህ ሲሞሏት ደግሞ ዕውቀት ርካሽ ይሆናል፡፡ ዕውቀት እና ዐዋቂም ዋጋ ያጣሉ፡፡ ማጭበርበር እና መቀላጠፍ ከመማር እና ከማወቅ በላይ፣ ፖለቲካዊ ጥገኛነት እና መንጠላጠል ከምርምር እና ልሂቅነት በላይ ዋጋ ያወጣሉ፡፡ ፊደል ቆጣሪ እንጂ የተማረ ብርቅ ይሆንባታል፡፡
እንዲህ ያለች ሀገር የወጣቶቿ አመለካከት «ከሦስት ዲግሪ አንድ ግሮሠሪ» ወደሚለው ያዘነብልባታል፡፡ ዕውቀት አደሮች አልቀው ሆድ አደሮች ይበዙባታል፡፡
በአንዲት ሀገር ውስጥ እንዝራት የሚሉ ዜጎች ከበዙ ግን ያቺ ሀገር ተስፋ ያላት ሀገር ትሆናለች፡፡ ከዕለቱ የዓመቱን፣ ከዛሬው የነገውን ማየት የሚችሉ ዜጎች ታፈራለች፡፡ ጥቅምን ከራሳቸው፣ ገንዘብን ከኪሳቸው፣ ዕድገትን ከቤታቸው፣ በላይ አድርገው ማሰብ የሚችሉ ልጆች አግኝታለች ማለት ነው፡፡
እነዚህን ባገኘች ሀገር ድህነት ቁጭትን እና ንዴትን ይፈጥራል፡፡ ከድህነት ጋር ተስማምተው የሚኖሩ ሳይሆን ከድህነት ተመራምረው የሚያመልጡ ዜጎች ሻምፒዮና ይሆኑባታል፡፡ እንዲህ ባለች ሀገር ወይ ዕውቀት ከሀብት ይቀድማል፣ አለያም ዕውቀት ከሀብት እኩል ይመጣል፣ቢያንስ ደግሞ ዕውቀት ከሀብት ይከተላል፡፡
እንዲህ ባለች ሀገር ዕድገት እንጂ ዕብጠት ስለማይኖር ኃላፊነት የሚሰማቸው፣ ሆዳቸው ኅሊናቸውን ያልተ ጫነባቸው፣ በአመክንዮ እሺ ብለው በአመክንዮ እምቢ የሚሉ፣ ራሳቸውን በየጊዜው ለአዲስ ዘመን የሚወ ልዱ፣ በልተው የሚጠግቡትን ሳይሆን ዘርተው የሚያፍሱትን የሚያስቡ ልጆች በደስታ ይኖሩባታል፡፡
ሰው ሲያገኝም ሲያጣም ሆዱ የሚያስቸግረው ከሆነ፡፡ ሲያገኝም ሲያጣም ጥያቄው የሆድ ብቻ ጥያቄ ከሆነ፤ በማይምነት እና በምሁርነት፣ በሸማችነት እና በነጋዴነት፣ በተራነት እና በባለ ሥልጣንነት፣ በወጋነት እና በታዋቂነት ጊዜም ሆዱ ካስቸገረው፣ ከሆድ ወደ አእምሮ ለማደግ ካልቻለ ዕብጠት እንጂ ዕድገት ሲያልፍም አልነካካው ማለት ይኼም አይደል፡፡

65 comments:

 1. ሲያጣ ራበኝ ብሎ፣ ሲያገኝ ጠግቦ መሥመር የሚስተውን ግን ምን ማድረግ ይቻላል፡፡ እነዚህን ሁለቱንም የያዘች ሀገር ጉዞዋቸውን በቁሳዊ ርካታ እና በቁሳዊ ድል በሚለኩ ዜጎች ትሞላለች፡፡ ድህነት እና ውርደትን፣ ዕድገት እና ጥጋብን መለየት በማይችሉ ዜጎች ትሞላለች፡፡ ሀገርን እነዚህ ሲሞሏት ደግሞ ዕውቀት ርካሽ ይሆናል፡፡ ዕውቀት እና ዐዋቂም ዋጋ ያጣሉ፡፡ ማጭበርበር እና መቀላጠፍ ከመማር እና ከማወቅ በላይ፣ ፖለቲካዊ ጥገኛነት እና መንጠላጠል ከምርምር እና ልሂቅነት በላይ ዋጋ ያወጣሉ፡፡ ፊደል ቆጣሪ እንጂ የተማረ ብርቅ ይሆንባታል፡፡ እንዲህ ያለች ሀገር የወጣቶቿ አመለካከት «ከሦስት ዲግሪ አንድ ግሮሠሪ» ወደሚለው ያዘነብልባታል፡፡ ዕውቀት አደሮች አልቀው ሆድ አደሮች ይበዙባታል፡፡
  TESFA,PHX, AZ

  ReplyDelete
 2. ግልፅ ኣይደለም

  ReplyDelete
  Replies
  1. the message is very clear. "jero yalew yisma lib yalew lib yibel"

   Delete
  2. KE Zehe Belay Geltse Neger engdeh Min Lehone Endemechel Bemesale Betasredan Teru New.

   Delete
  3. if u want more than this clear leave your bad job! i think this work seems to be you! other wise very clear and clear!

   Delete
  4. menalbach....Yabete ayimro kale ..gilits layhone Yichilal!!! see your mind man!! ke 10 amet betach yehone sew yihin bilog bayigobeGnu Yimekeral!! gilits silemayihonlachew

   Delete
 3. "ሰው ሲያገኝም ሲያጣም ሆዱ የሚያስቸግረው ከሆነ፡፡ ሲያገኝም ሲያጣም ጥያቄው የሆድ ብቻ ጥያቄ ከሆነ፤ በማይምነት እና በምሁርነት፣ በሸማችነት እና በነጋዴነት፣ በተራነት እና በባለ ሥልጣንነት፣ በወጋነት እና በታዋቂነት ጊዜም ሆዱ ካስቸገረው፣ ከሆድ ወደ አእምሮ ለማደግ ካልቻለ ዕብጠት እንጂ ዕድገት ሲያልፍም አልነካካው ማለት ይኼም አይደል፡፡" it is a true profile E/r yibarkih Dn.Dani

  ReplyDelete
 4. it is a very nice written

  ReplyDelete
 5. nice article,God Bless You

  ReplyDelete
 6. የቤተክርስቲያን ሚና ወዴት አለ፡፡ ምንኩስናው አስተዳዳሪነቱ ጸሐፊነቱ ቁጥጥርነቱ ሁሉም የሚፈለጉት ያለአግባብ ለመጠቀም ነው ከዚህ ያልተገኘ ታማኝነትና ትህትና ከየት ይፈለግ?

  ReplyDelete
 7. ተማር ልጀ ወገን ዘመድ የለኝ ሀብትም የለኝ ከጀ!
  በዚህ ዘመን ስላልሰራ እኮ ነው!
  ወረቀት መያዙ ወይም መዝረፉ ሆኖል ቁም ነገሩ!

  ከአዋሳ

  ReplyDelete
 8. ከመቀበል ይልቅ በመስጠት የሚገኝ ደስታ ይበልጣል ያለው ማን ነበር . . . አዎ ካህሊል ጊብራን ነው፡፡

  ለሀገሩ ተሰጥቶ ስሙን የሚተክል ምሉዕ ትውልድ የሚመጣበት ቀን ይናፍቀኛል፡፡ የበላና የተማረ . . . ከራስ በላይ ንፋስ ተብሎ ሳይሆን የሰራና የተማረ . . . ካገር በላይ ንፋስ ተብሎ የሚያድግ ትውልድ . . .

  ReplyDelete
 9. THANK YOU.DN DANI

  ReplyDelete
 10. እኔ የቱ ጋር ነኝ? ለዚህ መልስ ከሌለን አብረን እናልቃለን፡፡ ስለሁሉም አምላካችን ማስተዋሉን ያድለን፡፡ ዳኒ አንተንም ያኑርልን አሜን! በዋልድባ ላይ ግን ዝምታህ አልገባንም እውነታው ናፍቆናል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Guys! I don't understand what you want Dn Daniel to do. It is already publicized in others blogs & newspapers. Do we need to know Dn Dani stand???

   Ayenachew

   Delete
  2. Please both of you read this. http://www.danielkibret.com/2012/03/blog-post_18.html

   Delete
  3. sewoch alrady he wrote!!! ok ??!! "wlidibina and e-wilidibina" alanebebachihutim???? kzih belay min yihunilachihu???? dingay gar tegachito endinataw tifeligalchihu?????adamea bemoke hager tkemitachihu Yalenen andun mekari litasatun atimokru! please you all know who our state is!!!!! bene tedy afro animarm????? chinikilatu yabete mnigis Yene dani kibir ayigebawm!!!!

   Delete
  4. zm belachew!!! ene yemigermegn neger enternet metekem yegemere sew endet ..endet lesdb ynesal ...andande aynachn ena ejachn bicha yetemare hulu ymeslegnal.

   Delete
 11. wow wow ------every body culp your hand ----
  it is realy very intersting
  i don't went today any food let God give you full of healthly age inorder to feed us such spritiual food.
  D.Abebayehu

  ReplyDelete
 12. Thanks Daniel, amazing.

  እንዲህ ያለች ሀገር የወጣቶቿ አመለካከት «ከሦስት ዲግሪ አንድ ግሮሠሪ» ወደሚለው ያዘነብልባታል፡፡ ዕውቀት አደሮች አልቀው ሆድ አደሮች ይበዙባታል፡፡

  ReplyDelete
 13. ዳኒ በጣም ጥሩ ዕይታ ነው ጥጋብም ረሃብም በሽታ ነው ምክንያቱም ሁለቱም ልክ አይደሉምና ማለቴ ጥጋብ ከልክ ማለፍ ነው ረሃብ ደግሞ ልኩ ላይ አለመድረስ ነው ልጅ ሆነን ሲርበን እነለቅሳለን ስንጠግብ ደግሞ ሆዴን አመመኝ ብለን ሌላ ለቅሶ ነው ታዲያ መፍትሄው በልክ መሆን ነው ልክን ማወቅ የዕውቀትም ልክ አለው በሌላ አነጋገር የሁሉ ነገር ልክ አለው ልካችንን ማወቅ ደግሞ የሰውነት ወይም ሰው የመሆን መለኪያ ነውና በልክ መሆንን መመኘት ነው

  ልብስም እኮ በልክ ሲሆን ነው የሚያምርብን

  ከበደ

  ReplyDelete
 14. Miracle advice and scholarly suggestion for the current upheavals in Ethiopia and the world at large, for those who are so greedy who posses a big stomach and a little mind.

  God bless U, deacon Daniel.

  ReplyDelete
 15. Thanks for sharing your thoughts. This article showed me where I am and where I should be the future. God bless you!!!

  ReplyDelete
 16. Dani, i don know, i think this is the best ever. Coz we are in z era of "enblat". And i loved z idiom zat we spend time on eatin meat than reading books and skilled in "kinkena" but not analysis and very much selfish, cant see beyond z tip of nose. Keep on writin zat is one of the ways we learn and change. I love ur critique very much, sew ayasatan!!!

  ReplyDelete
 17. ቃለ ህይወት ያሰማልን ዲን.ዳንኤል
  ያነሳከው ሃሳብ በጣም ትክክለኛና ወቅታዊ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ በዚህ ዘመን ቡዙዎቻችን ጥያቄያችን ሁሉ የምናብጥበትን እንጂ የምናድግበትን ነገር እንድናስብ የሚያደርገን ነገር የለም ማለት ይቻላል፡፡ ፖለቲከኛውም፤ የሀይማኖት መሪውም፤ ሀብታሙም ሁሉም የዕድገትን ሳይሆን የእብጠትን መንገድ ነው የሚከተለው፡፡ ዕውቀትና እድገት ሚናቸው እየተሸፈነብን መጥቷል፡፡

  ReplyDelete
 18. For Anonymous who said "በዋልድባ ላይ ግን ዝምታህ አልገባንም እውነታው ናፍቆናል፡፡";he express his point of view,you can read

  http://www.danielkibret.com/2012/03/blog-post_18.html

  ReplyDelete
 19. Thank you Dani,
  Ke woyane gar liyalitimuh yemikosekusihin sewoch atisimachew.
  you have many things to do for the church and country.

  ReplyDelete
 20. Thank you Dani,
  Ke woyane gar liyalitimuh yemikosekusihin sewoch atisimachew.
  you have many things to do for the church and country.

  ReplyDelete
 21. በርግጥም የዚህች አገር ህልውና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም, የትውልዱም ማንነት ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ከመሄዱም በተጨማሪ የምእራብያውያኑ ዘመናዊ ቅኝ ግዛት ታክሎበት ትውፊት,ባህላችንና,ሐይማኖታዊ ስርአታችን በሙሉ እንዳይደመሰስ ስጋቴ ነው ብቻ እግዚአብሔር ይታረቀን የተሻለ ዘመን ያቅርብልን:: ዳኒ ሀሳቦቹ በጣም ጥሩ ናቸው በዚሁ ይቀጥሉ:: እ\ር ከሁላችን ጋር ይሁን:: አሜን
  Desalegn, Haramaya university

  ReplyDelete
 22. Ejig Betam esmamalehu...tsihufum betam astemarognal....Lerasachin Bicha sayhon leleloch yeminasbibetin sefa yale yemastewal bikat Egziabher yisten Amen!...Engdih yih aynetu sefi aymiro kalegn...lebizu wegenoch yemterfibetin sira yemisera yimeslegnal.

  DN.DANIEL EGZIABHER YISTILIN!

  ReplyDelete
 23. it's nice article...*be 3 digree 1 grosery*it's so funy...God bless u

  ReplyDelete
 24. D.n Daniel, God bless u with his love that make a joy forever ... I've no word to say about ze article ... -Huletie Mecheger-

  ReplyDelete
 25. D.n Daniel, God bless u with his love that make a joy forever ... I've no word to say about ze article ... -Huletie Mecheger-

  ReplyDelete
 26. I cant deny that all what you comment on got a saying in regrades to WALDEBA in one or the other way BUT .BUT SAY IT in clear cut word ON WHAT IS GOING ON WALDEBA !....WALDEBA IS THE ENBA THAT I AM CRYING WITH
  H

  ReplyDelete
 27. ዲን ዳንኤል ልታስተላልፍ የፈለከው መልህክት ሊገባኝ አልቻለም

  ReplyDelete
 28. ምን አይጥ እና አሞራ ብቻ እኛም አልተስማማንም፡፡ የሀገሪቱም ጥያቄ ይኼው ይመስለኛል፡፡ እንብላት እንዝራት? በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ «እንብላት» የሚለው ከበዛ በሀገሪቱ ውስጥ ዕብጠት እንጂ ዕድገት ሊኖር አይችልም፡፡ ሆዳቸው፣ ኪሳቸው፣ ሀብታቸው፣ ጡንቻቸው፣ ጉንጫቸው፣ አንጎላቸው ያበጠ ብዙ ዜጎችን እናፈራለን እንጂ አእምሮአቸው እና ኅሊናቸው፣ ልቡናቸው እና ሰብእናቸው ያደገ ዜጎችን በሥዕ ለትም አና ይም፡፡ ዕድገት የአእምሮ፣ ዕብጠትም የጥጋብ ውጤቶች ናቸው፡፡

  ReplyDelete
 29. መማር ማለት ትምህርት ቤት ገብተን የተማርነው ብቻ አይደለም እሱንማ አብዛኞቻችን ለፈተና ነው የምንማረው፡፡ መማር ማለት ነገሮችን ማመዛዘን መቻል እና አይምሮአችን ማሰብ ሲችል ማለት ነው፡፡

  ReplyDelete
 30. እንዲህ ባለች ሀገር ዕድገት እንጂ ዕብጠት ስለማይኖር ኃላፊነት የሚሰማቸው፣ ሆዳቸው ኅሊናቸውን ያልተ ጫነባቸው፣ በአመክንዮ እሺ ብለው በአመክንዮ እምቢ የሚሉ፣ ራሳቸውን በየጊዜው ለአዲስ ዘመን የሚወ ልዱ፣ በልተው የሚጠግቡትን ሳይሆን ዘርተው የሚያፍሱትን የሚያስቡ ልጆች በደስታ ይኖሩባታል፡

  ReplyDelete
 31. meriwochachinis be-ediget wois be-ebitet newu yemimerun memrat endih kehone.

  ReplyDelete
 32. ከሀብት ዕውቀት ሲቀድም እውነት ነው በጣም የተሻለ ይሆናል ባይሆን እንኳን ከሀብት እውቀት በቅርብ ርቀት ይከተል!
  አብነት ከሆሳዕና

  ReplyDelete
 33. ዳኒ የፓትርያሪኩን ሐውልት ስትቃወም ለእውነት አዳሪ ብየህ ነበር፣የዋልድባን ነገር ግን የመንግስት እጅ አለበት እና ዝም አልክን፡፡ ለነገሩ እንደ "ቤተ ክህነት" መነኮሳት አሣ ማስገር ይችላሉ ከምትለን ....ከስጋዊ ጉዳት የቤተክርስቲያን ጉዳት የሚበልጥበት ሰው እግዚአብሄር ያድለን፡:ለሁላችንም እግዚአብሄር ማስተዋሉን ያድለን::

  ReplyDelete
  Replies
  1. hay wendem nbeb mejemeria waldeba 2.5 km wedegedamo tegebto lemenged tarsual alek kezi belai min endiele new yemitebek, antes min eyaderegek new?

   Delete
  2. I don't know what to say to such people who triggers others to take extra-risks. Do you take such risks yourself?? I don't think. Why don't we leave Dani to decide by himself?? And Dani:- you are not publishing this kind of comments I forwarded so far.

   Ayenachew

   Delete
  3. ስለ ዋልድባ ከበቂ በላይ መረጃ እኮ አለን:: ዳንኤል ምን ተጨማሪ ነገር እንዲነግረን ጠብቀህ/ሽ ነው ውንድሜ/ እህቴ? የዳንኤልን አቋም ለማውቅ ከሆነ ፍላጎትሽ/ብ ፍላጎትህ ዳንኤል እንደማንኛውም ጥሩ የሐገሪቱ ዜጎች ሀገር እንዲጠፋ ሳይሆን እንዲለማ ይፈልጋል:: ሐገር እንዲለማ ሲፈልግ ደግሞ እንደ ወያኔ የሀገርን ቅርስ ወይም ታሪክ እያጠፉ ሳይሆን ያለውን ታሪክ እየተንከባከቡ አዲስ ቴክኖሎጂ ማስፋፋትን እንደኔና እንዳነተው/እንዳንቺው የፈልገዋል:: ለዚህ ደግሞ ከዚህ በፊት የጻፋቸው በቂ መረጃዎች ናቸው:: ስለዚህ ለሐገር ጥሩ ነገር መስራት በምንፈልግበት ጊዜ ሁሉ ዳንኤል የመጀመሪያው ሰው ከጎናችን ተሰላፊ ነው:: ስለዋልድባ ገዳምም የዳንኤልን አቋም ከፈለክ/ከፈለግሽ በርግጠኝነት ዳንኤል ከኛ ጋር ነው (ከትክክለኛ ኢትዮጵያውያን ጋር) ለሀገር ከሚያስቡ ጋር, የሃገሪቱ እሴቶች እንዳይጠፉ ከሚፈልጉ ጋር, የዋልድባ ገዳም እንዳይጠፋ ከሚፈልጉ ጋር ነው:: ይልቅስ ለዳንኤል አደራ የዋልድባን ጉዳይ ጫፍ ሳናደርስ ያንን የሚያስረሳ ነገር እንዳትጽፍ አደራ እልሃለሁ:: ወያኔ እንደሚያደርገው በሌላ ነገር ሃሳባችንን ለመውድ ወይም አቴንሽን ለመስረቅ ሌላ ነገር አትጻፍ:: ስለዋልድባ ግን መንግስት በዚያ አካባቢ እየሰራ ያለውን የጥፋት ስራ እስኪያቆም ድረስ ሁላችንም አብረን እንስራ በቂ መረጃ አለንና:: ሁላችንም ከያለንበት የምንችለውን ሁሉ እናድርግ:: ሌላው ቢቀር እዚያ አካባቢ የሚሰሩ ስራዎችን ተደብቀን ማውደም አያቅተንምና መንግስት የጥፋት ስራውን ካላቆመ እዚያ አካባቢ የሚሰራ ማንኛውንም ስራ በድብቅ በማውደም እንተባበር::

   Delete
 34. Dear Daniel,

  You did great, May the Almighty God bless you. I quote some of your expressions, which has heavy impact to us.

  አሁን በተማረው ወገናችን ያለው ዘንድ ጥጋብ ነው ወይስ እድገት ነው? የተለወጠው ማዕረጉ ነው ወይስ አመለካከቱ፣ የተሻሻለው ደመወዙ ነው ወይስ ዕውቀቱ? የሠለጠነው በምርምር ነው ወይስ በማጭበርበር ስልት? ጊዜውን የሚያሳልፈው ሥጋ ላይ ነው ወይስ ንባብ ላይ? ያጠናው ትንተና ነው ወይስ ቅንቀና?

  በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ «እንብላት» የሚለው ከበዛ በሀገሪቱ ውስጥ ዕብጠት እንጂ ዕድገት ሊኖር አይችልም፡፡ ሆዳቸው፣ ኪሳቸው፣ ሀብታቸው፣ ጡንቻቸው፣ ጉንጫቸው፣ አንጎላቸው ያበጠ ብዙ ዜጎችን እናፈራለን እንጂ አእምሮአቸው እና ኅሊናቸው፣ ልቡናቸው እና ሰብእናቸው ያደገ ዜጎችን በሥዕ ለትም አና ይም፡፡ ዕድገት የአእምሮ፣ ዕብጠትም የጥጋብ ውጤቶች ናቸው፡፡

  በአንዲት ሀገር ውስጥ እንዝራት የሚሉ ዜጎች ከበዙ ግን ያቺ ሀገር ተስፋ ያላት ሀገር ትሆናለች፡፡ ከዕለቱ የዓመቱን፣ ከዛሬው የነገውን ማየት የሚችሉ ዜጎች ታፈራለች፡፡ ጥቅምን ከራሳቸው፣ ገንዘብን ከኪሳቸው፣ ዕድገትን ከቤታቸው፣ በላይ አድርገው ማሰብ የሚችሉ ልጆች አግኝታለች ማለት ነው፡፡
  እነዚህን ባገኘች ሀገር ድህነት ቁጭትን እና ንዴትን ይፈጥራል፡፡ ከድህነት ጋር ተስማምተው የሚኖሩ ሳይሆን ከድህነት ተመራምረው የሚያመልጡ ዜጎች ሻምፒዮና ይሆኑባታል፡፡ እንዲህ ባለች ሀገር ወይ ዕውቀት ከሀብት ይቀድማል፣ አለያም ዕውቀት ከሀብት እኩል ይመጣል፣ቢያንስ ደግሞ ዕውቀት ከሀብት ይከተላል፡፡
  እንዲህ ባለች ሀገር ዕድገት እንጂ ዕብጠት ስለማይኖር ኃላፊነት የሚሰማቸው፣ ሆዳቸው ኅሊናቸውን ያልተ ጫነባቸው፣ በአመክንዮ እሺ ብለው በአመክንዮ እምቢ የሚሉ፣ ራሳቸውን በየጊዜው ለአዲስ ዘመን የሚወ ልዱ፣ በልተው የሚጠግቡትን ሳይሆን ዘርተው የሚያፍሱትን የሚያስቡ ልጆች በደስታ ይኖሩባታል፡፡

  ሰው ሲያገኝም ሲያጣም ሆዱ የሚያስቸግረው ከሆነ፡፡ ሲያገኝም ሲያጣም ጥያቄው የሆድ ብቻ ጥያቄ ከሆነ፤ በማይምነት እና በምሁርነት፣ በሸማችነት እና በነጋዴነት፣ በተራነት እና በባለ ሥልጣንነት፣ በወጋነት እና በታዋቂነት ጊዜም ሆዱ ካስቸገረው፣ ከሆድ ወደ አእምሮ ለማደግ ካልቻለ ዕብጠት እንጂ ዕድገት ሲያልፍም አልነካካው ማለት ይኼም አይደል፡፡

  ReplyDelete
 35. ያላወቁ አለቁ ነበረ ተረቱ
  እያወቁ ማለቅ መጣ በሰዓቱ


  በምን እንስማማ መልሱ ግልጥ ነው ፡ፍሬዋን በመዝራት ፡ ፍሬዋን ለመዝራት ደግሞ ጥሩ ዘሪ ገበሬ ያስፈልጋታል ፡፡ ገበሬው እንዲዘራው ማሳው መለስለስ፤ መኮትኮት ያስፈልገዋል……….. ………፡፡ ነገሮች በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዳይሆን ደግሞ የሚመለከታቸው ማሳውን ማስተካከል ይጠበቃል፡ያስፈልጋልም፡፡ ታሪክ የሚያስታው ፤ የሚዘክረው ስራ የበኩልህን እየሰራህ ነውና በዚሁ ቀጥል፡፡ ለግፈኞች ግን ቦታና ጊዜ መስጠት አያስፈልግም. . . . . ፡፡ ምን ማለትህ ነው ሀገሬ እኮ ከሁለት ድግሪ አንድ ገሮሰሪ በሚሉ ወጣቶች ተሞልታለች ፡፡ እስቲ መምህር የኮተቤን ተማሪውችና የአምስት ኪሎ ተማሪዎችን ለምን; ምን; እከመቼ; በለህ ጠይቅ ግልጥ ማብራሪያ ይሰጡሃል፡፡‹‹ ከሁለት ድግሪ አንድ ግሮሰሪን የሚለወን አባባል ያረግግጡሃል›› በነገራቸረ ላይ አጅግ በጣም ዘግይቷል፡፡ ባለስልጣናቱማ ምን ያድርጉ ‹‹የምጣዱ እያለ የንቅቡ ተንጣጣ ›› ስለሆነ ባለቤቱ እያለ ባለስልጣናቱ ምን ያድርጉ……..

  ReplyDelete
 36. ዕድገት የአእምሮ ነው፣ የአመለካከት ነው፣ የልቡና ስፋት ነው፣ የኅሊና ምጥቀት ነው፣ የአስተሳሰብ አድማስ ንጥቀት ነው፣ የኃላፊነት መሰማት ነው፣ ለነገ ጭምር ማሰብ ነው፡፡
  ጥጋብ ግን የሆድ ብቻ ነው፡፡ የቅሪላ መነፋት ነው፡፡ ከክብደት እና ከቅላት፣ ከወዝ እና ከስፋት ጋር የሚሄድ ነው፡፡ ዕድገት አገርን፣ ጥጋብ ሆድን ብቻ ያሳድጋሉ፡፡ 'kemetemtem memar yekdem' naw teretu. Amesegnalehu betam des yelale
  Mamush,MN

  ReplyDelete
 37. ምነው ዲ/ን ዳኒ ለዝቋላ የተባው ብዕርህ ለዋልድባ ነጠፈ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. He is some times on and some times off (in favor and against woyane) he doesn't have consistency on the mad dog Woyane. Don't expect from him

   Delete
  2. I don't think Dani is the right person for political issues. It is good to visit www.dejeselam.org I don't recommend Dani for TPLF related issues. Otherwise he will be a victim.
   Ayehu

   Delete
  3. What do you mean? Please the title of his blog. The blog is his own view on Politics, History, Culture, religion and society....... .

   Please read the title of the blog before anything else

   Delete
 38. ዉስጠ ወይራ ቢጤ ነው:: ግን ከላይ ያሉትን አስተያየቶች ካነበብክ ብዙ ቅሬታዎች አሉ:: ብዥታዎችም:: ለነዚህ ያንተን አስተያየት እንጠብቃለን:: ሰምተህ እንዳልሰማ አትሁን:: ስንወያይ ነው የሚገባንና:: የኔን ልጨምርልህ:-ይህ ጽሁፍ የሰሞኑን እፍታ ጠቅ ለማድረግ የተጻፈ ነው:: ምልከታህ ጥሩ ነበር ግን 'ፍየልና ቅዝምዝም...'ሆነብህ:: አንድ የማልወደው ተረት አለ 'እኔ ለዚህች ሀገር ምን አረኩላት እንጂ ይህች ሃገር ለኔ ምን አረገችልኝ አትበል' የምትል:: ብዙ ግዚ አልወዳትም:: አባባሉ የሚሰራው መሰረታዊ ፍላጎታቸው ተሙዋልቶ ቅንጦት ለሚያስቡት እንጂ "ዛሬስ በላሁ ነገ ደሞ ምን አገኝ ይሆን?" እያለ ለሚጨነቅ ህዝብ አደለም:: እኔ በቀን አንዴ በልቼ እግሬን ማንሳት ስችል ነው ለዚች ሀገር ምን አረኩላት ማለት የምችለው:: እንደ ቻይናው ማኦ አስተሳሰብ ብንጉዋዝ ባልከፋኝ ነበር የጋራ ችግር ለጋራ እድገት ነዉና:: ነገር ግን የኛዋ ሃገር ላንዱ ገነት ሆና ለሌላው ከሲኦልም ባሰች:: አንዱ በሚሊዮን ዶላር መኪና ሲገዛ ሌላው ደሞ ዳቦ በምን ገዝቼ ለልጄ ልስጥ ይላል:: እኩል ተመርቀው አንዱ የዘመን ንፋስ ሲነፍስለት ለሌላው ይነፍስበታል:: እና ያንተም ጽሁፍ አላገናዘበም:: ድፍጥጥ አረከው:: "አንተ ጠግበህ እየበላህ እኔ ራበኝ" ማለት አንተ እንዳልከው ሆድን ማሰብ አይደለም:: ሆድህ እየራበው ምን አይነት አእምሮ የምትሰጠውን ይቀበላል? ዳኒ የምንወድህ ብዙ ነን:: ነገር ግን አንዳንዴ ጣል የምታረጋቸው ነገሮች "ዳኒ ማነው? ያ የማውቀው ዳኒ ጻፈው?" እንድል ያረገኛል:: ያንተ አመለካከት ያንተ እንደሆነ እቀበላለሁ ነገር ግን አንተ ያንተ ከመሆን አልፈሃል:: የኛ ነህና ዝም ማለት ይከብዳል:: የህዝብ ሲኮን ደግሞ ማገናዘብንና አሰተዉሎትን ሁሌም ገንዘብ ማድረግ ይገባል:: ለማንኛውም ምንም ጻፍ ያስተምረናል:: ብታጣምመውም አቃንተን ለኛ አድረገን እናነበዋለን:: ተባረክ!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. I would be happy if I were able to know what you people want to hear from the Author (Dn Daniel). As to me he is good enough to show as motivating issues!
   Ayenachew

   Delete
 39. Thank you, Daniel,

  It is not about the food, it is about our mind.

  ReplyDelete
 40. "ኃላፊነት የሚሰማቸው፣ ሆዳቸው ኅሊናቸውን ያልተ ጫነባቸው፣ በአመክንዮ እሺ ብለው በአመክንዮ እምቢ የሚሉ፣ ራሳቸውን በየጊዜው ለአዲስ ዘመን የሚወ ልዱ፣ በልተው የሚጠግቡትን ሳይሆን ዘርተው የሚያፍሱትን የሚያስቡ ልጆች" መቼ ይሆን?

  ReplyDelete
 41. ዳኔ "በዋልድባ ላይ ግን ዝምታህ አልገባንም እውነታው ናፍቆናል፡፡"ሌላው ቤቀር በተለመደው እውነታህ ለኛ ለምእመናን ማጽናኛ ለአንተም ለታሪክ የሜሆን እይታህ አስምርበት:: እንደዘንድሮ አባቶች ተስፋ እንዳንቆርጥብህ::አይገርምም ለምእመኖቻቸው ጸልዩ ለማለት የሚፈራበት ዘመን ይገርማል::

  ReplyDelete
 42. HI Dani can you write someting about walldeba please!. thankyou.

  mule

  ReplyDelete
 43. hi dane canyou write someting about walldeba please, tankyou!.
  mule

  ReplyDelete
 44. አንድ ፀሀፊ ሰው ፃፍ ስላለው አይደለም የሚፅፈው ውስጡ ገንፍሎ በሚወጣ ስሜት ነው የሚፅፈው ስለዚህም ይህ እንቁ የሆነ የዘመናችንን ጅራታም ኮከብ አናጨናንቀው፡፡
  እንደእኔ አመለካከት ስለ ዋልድባ እንደሆነ በውስጡ ያሉ መነኮሳት አንድ ወጥ አይደሉም፤ በተጨማሪ በጣም የሚገርመኝ እና የሚያሳዝነኝ ነገር በሚዲያ ማብራሪያ የሚሰጡት እንኳን ጥቁር ፀጉር ናቸው@ ሌላው መፍረድ አይሁንብኝ እንጂ በገዳሙ ውስጥ ያሉት መነኮሳት የፀሎታቸው ሁኔታ ነው፡፡ አሁንም ይችን አገር ልዑል እግዚአብሔር ይጠብቃት
  ዳኒ እናመሰግናለን፡፡

  ReplyDelete
 45. 10q dani this is four direction view. Dani i live in out of Ethiopia i am worried about walldeba please write some this about the situation how is going on the trues.
  maki
  juba

  ReplyDelete
 46. ቃለ ህይወት ያሰማልን

  ReplyDelete
 47. ለምን በፊት የፃፍኩትን አለጠፍከውም?ብሶቴ የሚሰማህ ከሆነ ይህንን ብቻ ከቻልክ ለጥፍልኝ፡፡ባትለጥፈውም አልቀየምህም አልፈርድብህም፡፡ጥጋብና ርሃብ እንዲሁም ማጣትና ማግኘት ምን እንደሚመስሉ በወያኔዎች በደንብ አድርገን እያየነው ያለ ነገር ነው፡፡ስለዚህ ለዚህ የህይወት ቅኔ ከዚህ በላይ ምን አስረጂ ነገር አለው?አዎ ስትራብ ስለሰዎች ችግርና ነፃነት ተቆርቋሪ መስለህ የበግ ለምድ ለብሰህና ጭንብል አጥልቀህ ስለጭቆናና ስለነፃነት ስለዲሞክራሲ ትሰብካለህ እንዲሁም ጫካ ገብተህ ትዋጋለህ፡፡ተሳክቶልህ ስልጣን ላይ ስትወጣና ሀይልና ገንዘብ አግኝተህ ስትጠግብ ደግሞ ያለፈ ርሃብህን ችግርህንና የመጣህበትን ታሪክ ትረሳና ምስኪን ንፁሃን ዜጎችን ሀገር እንደሌለው እንደ ባእድ መጤ አድርገህ በመቁጠር ከቤታቸው ከመሬታቸው ከግብርናቸው ታፈናቅላለህ ለነሱ የነፈግኸውን ደግሞ በተቃራኒው ለባእዳን ሰዎች መሬት በርካሽ ትቸበችባለህ፡፡አዎ ኢትዮጵያ ለገዛ ዜጎቿ የእንጀራ እናት ለባእዳን መጤዎች ደግሞ እናት የመሆኗ ምስጢር ምን ይሆን?ኢትዮጵያ ሀገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ የተባለው ምስጢሩ ገና አሁን ገባኝ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ብስቡጣ ቦክረቓሉ ¾ስፖታ ;- ትርጉሙ (ደግ ገዢ) አለቃ ጽጊ ገብረኪዳን ግብረ ህማማት ባጭር ስርùት በሚል ር˜R 1985 ባሳትሙት መÍህፋቸው በገÎ 45 ገልËውታል*

   Delete
 48. WHAT A GREAT WORK YOU HAVE DONE!!! REALLY LIKE READING YR WORKS,AND LEARN FROM IT.bESID YR WORK I ENJOY PPL'S COMMENT AND HAVE GOT KNOWLEGE FROM DIFFRENT ASPECT.BUT WHAT I DON'T UNDERSTAND IS, WHY DONT YOU POST ALL THE COMMENT YOU HAVE GETTEN????
  I THINK YOU ARE ONE OF THE PPL WHO BELIVE,AND SAY "PPL COULD WRITE WHAT THEY WANT,AND BELIVE" SO PLEASE TAKE IT AS A COMMENT AND POST ALL THE COMMENTS,SO WE COULD ABLE TO SEE PPL'S BELIVE FROM ANOTHER VIEW.
  I ALWAYS ADMIRE YOU.
  GOD AND HIS MOTHER KEEPS YOU SAFE.
  TIO
  FROM S.C

  ReplyDelete