click here for pdf
ደንበኛ ንጉሥ ነው፤ የት?
ጎንደር አንድ ሻሂ ቤት ተቀመጥን፡፡ አዘዝን፡፡ አልመጣም፡፡ ደግመን አዘዝን፡፡ አልመጣም፡፡ በኋላ ያዘዝናትን ልጅ ጠራንና «ተውሽንኮ» አልናት፡፡ አንገቷን ሰበቅ አደረገችና «ከቸኮልክ ማትሄድ» አለችን፡፡ ምን ይደረግ የፋሲልን እና የቴዎድሮስን ንግሥና እንጂ የደንበኛን ንግሥና ከማታውቅ ልጅ ብዙም መጠበቅ የለብንም ብለን ተውነው፡፡
አዲስ አበባ መገናኛ ካለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ሦስት ጊዜ ሄድኩ፡፡ ከድሬዳዋ የተላከ ገንዘብ ልወስድ፡፡ ሦስቴም አልደረሰም ተባልኩ፡፡ በተላከ በሦስተኛ ቀኑ፡፡ እዚያ ድሬዳዋ ስደውል ደግሞ ተልኳል ይሉኛል፡፡ ታድያ ምን ላድርግ? «በቃ የላከልህ ሰው ባንክ ሄዶ ይደውልልን» አሉኝ፡፡ ምን አደርጋለሁ ብዬ እንዳሉት አደረግኩ፡፡ በእኔው ስልክ ተደዋውለው ሰጡኝ፡፡ ለስልክ ግን የላከልኝ ሰው ከፍሏል፡፡ የባንኩ ደንበኛ መሆኔ ቀርቶ የባንኩ ሠራተኛ ሆኜ በስልኬ እየደወልኩ መረጃ ሳቀባብል ቆየሁ፡፡
እዚህም ደንበኛ ንጉሥ አይደለም፡፡ ንጉሥን ደርሶልሃል ብለው ይጠሩታል፤ ሲመጣም አረፍ በል ብለው ያስተናግዱታል እንጂ በራስህ ስልክ ደውለህ ገንዘብክን አስመጣ አይሉትማ፡፡
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገባሁ፡፡ እዚያ የመጻሕፍት መሸጫ መደብር አላቸው፡፡ ሁለት መጽሐፍ እገዛ ዘንድ ፈለግኩ፡፡ አንዱን ገዛሁ፡፡ ሁለተኛውን ግን «ሻጩ የለም» ተባልኩ፡፡
«የሥራ ሰዓት አይደለም ወይ?» አልኩ
«ሻሂ ሊጠጣ ሄዶ ነውና ጠብቀው» አሉኝ፡፡
ምን ያህል ሰዓት?» አልኩ፡፡ «አንድ ሃያ ደቂቃ፡፡»
«የሥራ ሰዓታችሁ ከስንት እስከ ስንት ነው?» አልኩ፡፡
«እስከ ስድስት ሰዓት ተኩል» ተባልኩ፡፡
«ታድያ ምነው ይህቺን ሰዓት እንደማታስተናግዱ ማስታወቂያችሁ ላይ አልጠቀሳችሁም? ወይም ሌላ መንገድ አልፈለጋችሁም» ብዬ ጠየቅኩ፡፡ (መ) መልሱ የለም፡፡ እዚህ ትልቁ የትምህርት ተቋም ውስጥም ደንበኛ ንጉሥ አይደለም፡፡ ንጉሥ ቢሆንማ ለሻሂ የሄደ አገልጋዩን ሃያ ደቂቃ እንዲጠብቅ አይደረግም ነበር፡፡ ያውም ሊከፍል እንጂ ሊከፈለው ያልመጣ ንጉሥ፡፡
እኔ እስካሁን ደንበኛ ንጉሥ ሆኖ በትክክል ያየሁት ቀብር አስፈጻሚዎች ጋ ነው፡፡ እዚያ በክብር ይሸከሟችኋል፡፡ ይገንዟችኋል፡፡ መኪና ውስጥ ያስገቧችኋል፡፡ በመኪናቸው ሲወስዷችሁም አያንቀዠ ቅዧችሁም፡፡ በወታደራዊ ተጠንቀቅ ያጅቧችኋል፡፡ በኋላም ተሸክመው መቃብር ያደርሷችኋል፡፡ ከዚህ በላይ ለንጉሥ ምን ይደረግለታል?
እናም እንዲህ አሰብኩ፡፡ እዚህ ሀገር ደንበኛ ሆኖ ንጉሥ ለመሆን የግድ መሞት ያስፈልጋል ማለት ነው?
የሚሰራውን ያላየ አሰሪ የሚለጥፈው አባባል አይመስልህም?
ReplyDeleteD/N Daniel Kibret Tebalek
ReplyDeleteD/N Daniel Tebarek
ReplyDelete«ከቸኮልክ ማትሄድ»
ReplyDeleteእዚህ ሀገር ደንበኛ ሆኖ ንጉሥ ለመሆን የግድ መሞት ያስፈልጋል ማለት ነው? አዎ!!! በትክክል። የደንበኛ ንጉስነት የት እንደሆነ ልንገርህ? ወረቀት ላይ። አዲስ አበባ ዩንቨርስቲማ ....
ReplyDelete«በቃ የላከልህ ሰው ባንክ ሄዶ ይደውልልን» አሉኝ፡፡
ReplyDelete«ታድያ ምነው ይህቺን ሰዓት እንደማታስተናግዱ ማስታወቂያችሁ ላይ አልጠቀሳችሁም? ወይም ሌላ መንገድ አልፈለጋችሁም» ብዬ ጠየቅኩ፡፡ (መ) መልሱ የለም፡፡
እዚህ ትልቁ የትምህርት ተቋም ውስጥም ደንበኛ ንጉሥ አይደለም፡፡ ንጉሥ ቢሆንማ ለሻሂ የሄደ አገልጋዩን ሃያ ደቂቃ እንዲጠብቅ አይደረግም ነበር፡፡ ያውም ሊከፍል እንጂ ሊከፈለው ያልመጣ ንጉሥ፡፡
እዚህ ሀገር ደንበኛ ሆኖ ንጉሥ ለመሆን የግድ መሞት ያስፈልጋል ማለት ነው? wow, it is amazing view.
ReplyDeleteንግሥና ከቀረ እነሆ ሰላሳ ስንት ዓመት
ReplyDeleteእኞ….. የሚለውን የልጅነት ጨዋታ ረሳኸው ዳኒ… ስሙ ሲቪል ሰርቫንት ነው ለጊዜው ስማቸው ቢቀየር ምን ይመስልሃል፡፡ ስሙ ከብዷቸው ወገኖቻችንን ሞት እንዳይፈጅብን፡፡
ReplyDeleteሰው ሲሞት ይነግሳል ብለሃል ታዲያ ምነው አዲስ አደረከው ለሞት እንጂ ለሕመም ዕድር አለ?
Arif Tizibit new!!
ReplyDeleteye gondere sewe becha newe mastenagede yemichelewe?! Egege selete yekedale afote---! Astewele lije Daniel!
ReplyDeleteWhat kind of reader r u? please read appropriately. Hed didn't write like that.
DeleteI like your view. But what is the solution. Please write.
ReplyDeletemaki
Juba
ዲን ጥሩ ትዝብት ነው
ReplyDeleteይህ በየቦታው ያለ ትልቅ በሽታ ነው መድሃኒቱ ግን እያንዳንዱ ሰው ውስጥ ነው ማለቴ ደንበኛ ንጉስ ነው የሚለውን ከወሬ ባለፈ በተግባር ልንፈፅመው መቻል ነው
እነደው ዳኒ ሞቶ ንጉስ ከመሆንስ በህይወት ሳለን የምንችለውን ቢናደርግ አይበጅም ትላለህ የሞተው ንጉስ ከመባልስ የቀረው ይሻለል
dan,,,,,,,,,have you read reporter magazine at page 37 "some body said being Ethiopian is irrelevant because there is no Ethiopians rather oromo ,Tigre.......AND bleam AAU AS AN agent of AMHARIC LANGUAGE.........
ReplyDeleteድ/ን ዳንኤል
ReplyDeleteእነዚህ የጠቀስካቸው ሁሉም በሀገራችን ብተገበሩ ለሀገራችን እድገት ትልቅ ሚና ነበራቸው
ነገር ግን ሁሉም ሰራተኛ ባይባልም ብዙዎቹ የመውጫ ሰዓታቸውን እንጂ የመግቢያና የመስሪያ ሰዓታቸውን አያከብሩም
ስለዚህ ሁላችንም" ሥራ ክቡር ነው፣ ደንበኛ ንጉስ ነው" የሚባለውን አባባል በሥራ እንተርጉመው
i like this more.its so real and deep to its level
ReplyDeleteoooooo Dani there are a lot of things to say about this topic. It is very terrible the Ethiopian costumer services. Never mind the treatment as a king; at least we are not getting as ordinary people. Sometimes they curse for the costumer. In general there is no a basic respect for all mankind. Let us take the nice culture of western costumer services instead of taking their name.
ReplyDeleteግሩም እይታ ነው! በደንበኞች አያያዝ ላይ ብዙ ልናስተካክላቸው የሚገቡን ነገሮች አሉ!
ReplyDeleteyalkew hulu ewnet new beteley Yebanku (CBE) guday ejigun asazagn new. berasih silik dewuleh enkua tekebayu (wodiyagnaw kirinchaf silkun yemiyanesaw yangutithal) Bemestengdow kirieta alegn kalk semi yelem, yilik tsaf bilew yehone satin eyasayu yikeldubihal. Nigsinaw qerto baleguday enkua bikon yibeka neber, Egziabiher yibarkih Dani.
ReplyDeletekale hiwot yasemalin Dn. Daniel
ReplyDeleteYou're right that a dead person becomes a king on his funeral except that he doesn't put any cloth on. Atlanta.
why don't you go to Waldiba and tell us the truth?
ReplyDeletePlease do not trigger Dn Daniel to face this stuborn politics game the government and aba paulos are playing in Waldba Monastries case. I don't recommend!!! Being cruel and dull it is simple for the politicians to take arrogant actions against any opposing person. Dani has so many other roles & he shouldn't be victim.
DeleteTo me it is better to talk about our church at this critical time than blaming a waitress in Gondar. We know Daniel long before he became famous blogger as a dedicated preacher and a man of God.
Deletesew yatakabera feterate nawena.ENEKABABARE
ReplyDelete«ታድያ ምነው ይህቺን ሰዓት እንደማታስተናግዱ ማስታወቂያችሁ ላይ አልጠቀሳችሁም? ወይም ሌላ መንገድ አልፈለጋችሁም» ብዬ ጠየቅኩ፡፡ (መ) መልሱ የለም፡፡
ReplyDeletewell, if you GONDAR you can get good cafes like HABESHA CAFE near Piassa which give good service , i see them.
ReplyDeleteNot all Cafes there are like that there in GOndar, i know.
any ways good issue
Dear Daniel,
ReplyDeleteYour observation is so priceless. A week before I gave my clothes to the laundry. They told me to come back after a week to collect my clothes. I went there according to the time the gave me. I gave my receipt to them to find my clothes, one sweater is missing when they searched.I asked them what was wrong? they told me the sweater is in for the second wash and informed me to come back on the next day.
I went again on the next day and the sweater is not traced at all. I asked them where is my sweater and they told me that they are searching to got it. Still, I couldn't have my sweater and I don't know whether I will have find it or not.
Customer is king mind set up could not work here, it is rather owner of the business is the king.
"እኔ እስካሁን ደንበኛ ንጉሥ ሆኖ በትክክል ያየሁት ቀብር አስፈጻሚዎች ጋ ነው፡፡ እዚያ በክብር ይሸከሟችኋል፡፡ ይገንዟችኋል፡፡ መኪና ውስጥ ያስገቧችኋል፡፡ በመኪናቸው ሲወስዷችሁም አያንቀዠ ቅዧችሁም፡፡ በወታደራዊ ተጠንቀቅ ያጅቧችኋል፡፡ በኋላም ተሸክመው መቃብር ያደርሷችኋል፡፡ ከዚህ በላይ ለንጉሥ ምን ይደረግለታል?"
bewunu leshay khone birom metetal yichel neber neger gin Lemn Endemnesera Buzu Ethiopian yemiyawk aymeslegn.
ReplyDeleteEgizer Legna lebona yisten
ምን ታደርገዋለህ ያለመታደለል
ReplyDeleteenie gin betekrstian mekera eyayech ahun bezih ries or agenda menegager alebin antem yihen yalewokitu metsaf neberebih biye alaminim yesewun simiet divert yadergal.
ReplyDeleteWOW! how many people miss your point. People... wake up!
ReplyDeleteI believe he is trying to tell you about the WALDEBA issue. The miss treatment of the people by the government and its agent Ethiopian embassy in Washington DC.
Apologis for the Amharic software.
it is a nice perspective...... i also share your views.
ReplyDeleteI recommend Dejeselam to discuss on Waldba Monastries rather than this page. It is dangerous for Dani. Pls do not push him. I guess he will do his best in any other way. That is my recommendation.
ReplyDeletesorry I DON'T BELIVE WHAT DEJESELAM SAYS ! SORRY! I CALL THEM DEJE WERA
Deletemelkam zezbet new!! D DANIEL PLEASE SELE WALDBA
ReplyDeleteYEMESEMAHEN NEGEREN ?I was waching etv they said
waldeba and the suger factry is far away !
usa
እንግዳ ተቀባይ ከዚህ ሀሳብ ጋር ይገናኝ እንደሆን ብታብራራልኝ ደስ ይለኛል ዳኒ መስተንግዶ በየትኛውም የስራ ዘርፍ ትልቁን ቦታ ይወስዳል ብዬ አስባለሁ እኛ ኢትዮጵያውያን እንግዳ ተቀባዮች አስተናጋጆች ትሁቶች የሚለው የኛነታችን መገለጫ የሁኑት የሆነ ቦታ የተዘለሉ አይመስልህም ያውም እየከፈልክ ካልተስተናገድክ
ReplyDeleteአብነት ከሆሳዕና
I am a banker to the same organization working at other branch you r truly right on that circumstance this will help us in improving our customer service. God bless you dani and i will sent the rest based on this views of yours to your email
ReplyDeleteመምህር ዳኒ....ቀን የጨለማና የመአልት ጥምረት እንደሆነ ሁሉ የደንበኛ ንጉስነትም የሁለት ባህሪያት ውህድ ነው! አንዱ አሁን አንተ ያልከው መበ’ደሉ(ጠብቆ ይነበብ) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ መበደሉ! (ይላላ):: አንዳንድ ድንበኞች በአገልግሎት ሠጭዎች አክብሮት ሲሰጣቸው ደርሰው እንደ ሂትለር የሚደርጋቸው አሉ! ለ አንድ ብር ሻይ ትእዛዙን የሚያከብዱ...እንደወረደ..ጠቆር ያለ...ስኩዋሩ ያልበዛ.... ከሎሚ ጋር የፈላ! ውይይይይ!!!! ለነገሩ ምን ያድርጉ በአንድ ብር ንግስና ሲገኝ??? የተሞላው ሂሳብ ሳያልቅ በጊዜያቸው መጠቀማቸው ነዋ!!! ደሞ ያች አጭር የንግስና ግዜ ደሞዝ በሚቀበሉበት ሰዓት የምትገኝ ትሆናለች! ስለዚህ ስው ባጭር ግዜ ሊሰራው የሚችልው ስራ ቢኖር ክፋትና ሽብርን በመሆኑ በብዙ የካፌ ደንበኞች (ንጉሶች) ይህ አንባገነንነት መፈጸሙ አይደንቅም!!!የጎንደሩዋም ምናልባች እንደዛ ማለት የሚገቡዋትን ንጉሶች አለማወቁዋ እንጅ በደንበኛ ንጉስነት ለተረገጡ እና በአሰሪያቸውም በንጉሱም በ2 ወገን ተበዳይ ለሆኑ ሚስኪን የካፌ አስተናጋጆች ነጻ አውጭ (መሲህ) ሁና ይሆን???!....ይህ ብቻ አይደለም፡፡ በባንክም ሆነ በሌሎች መስሪያ ቤቶች ጎንበስ ቀና ብለው ባስተናገዱ..... ተራ አስቀደማችሁን.....አለቃችሁ ፈቅዶ እናንተ ቢሮክራሲ አበዛችሁብን እያሉ አገልጋዮችን ሊያስሩ ሊደበድቡ የሚገለገሉ.እጆቻቸውም በአማላጅ ሲያዝባቸው .በገላጋዮች ትከሻ በኩል የአይምሮን ሞራል የሚደፈጥጥ የስድብ አለት የሚጥሉትም ብዙ ናቸው!!! ዳኒየ በነዚህስ ስንቱን ታዝበኸው ይሆን ሰፊ ጽኁፍ ካንተ እጠብቃለሁ!...ዲ/ዳኒ ይህን ያልኩት ጽሁፍህን ተቃውሜ እንዳልሆነ እንኩዋን ያንተ ልብ ነገርን ሁሉ ለጠብ የሚያመቻቸው ሠይጣንም ያቃል!!! ግን የደንበኛን ንጉስነት ለመፍጠር የአገልጋዮቹን ያለመታዘዝ ትእቢት ማጥፋት ብቻ ሳይሆን የንጉሱንም የተገልጋነት ድንበር መከለል ያለብን መስሎ ስለታየኝ ነው!!!! ማር ሲበዛ ይመራል ተብሎዋል ዕርግጥም ነው!!! ዳኒየ የምስጋናየ ብዛት እናዳይመርህ በምርቃን ጨው ላጣፍጥልህ...እግዚአብሄር በመቅደሱ በራድ በአህዛብም ፊት ትኩስ ትሆን ዘንድ በፊቱ የተለካህ ያድርግህ!!!!ስለሁለት ስብከቶችህ ምርቃኔ ላንተ ብቻ ግልጽ ነው!!!
ReplyDeleteአባባሎች በትትክክል ተስተውለው እስካልተነበቡ ድረስ ልዩ ልዩ ትርጉም እንደሚኖራቸው ወንጊል ብዙ ያስተምራል:: የዲ/ዳንኤል አባባልም ግልጽና መስፈርት ያለው አባባል ነው:: እንግዳ ተቀባይነታችን መልካም ᎓ የአባባል ዚይቢያችን ግን ይኸው ነው:: ይልቅስ በሆቴል የእንግዳ ማስተናገድ በተለይ የአነጋገር ዘይቢ ስልጠና ቢሰጥ ካለም ቢታከልበት መልካም እላለሁ::በዚህ ዙሪያ ብዙ በተባለ ነበር ዳሩ ጭንቅላቴን አዙረት ያለ ይኸው የዋልድባ ገዳም እና የበተክርስትያን ሰው ማጣት ስለሆነ ለግዚው እዚሁ ላብቃ::
ReplyDeletewhat an amazing saw you saw
ReplyDeleteNot only Gonderye but all Ethiopia
ReplyDeleteI think that but i know Gondereye is good for new camer to them to make him happy in all aspect
Teru eyeta new Dani
ReplyDeleteTru eyeta new Dani
ReplyDeleteAmesegnalehu Dani!! kezih weta yale teyaqe liteyiqehe felegie neber..
ReplyDelete1, 'Lalibela weqeren yeserut awropawyan templaroch nachew' yibalal.. bezih zuria tenesh betaweran qere yilehal?
2, 'Gemade meskelu Gishen mariam alee' yibalal.. lenie gen eregetgna mehon yichegeregnal.. silezih tinesh betabraralegn???
(Yelalibelan guday gen be'E-mail'adrashaye yemetawuqut hulachihu betetsefulegn des yilegnal...)
Thank you!!! Dani!!!!
ReplyDeleteThank you!!!
ReplyDelete