Monday, March 26, 2012

አራት ሰው ሞተ 2


click here for pdf 
ነፍስ ኄር ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ 3ኛን ቀርቤ የማየት ዕድል ያገኘሁት የዛሬ ዓመት ነበር፡፡ ግብጽ ካይሮ በሚገኘው አባስያ መንበረ ፓትርያርክ ግቢ ውስጥ፡፡ በመንበረ ፓትርያርኩ ግቢ አራት አብያተ ክርስቲያናት ሲገኙ ትልቁ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል ነው፡፡ ያሠሩት ከአቡነ ሺኖዳ በፊት የግብጽ ፓትርያርክ የነበሩት አቡነ ቄርሎስ 6 ሲሆኑ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረውም 1968 ዓም ነው፡፡ እኛም ኢትዮጵያውያን በንጉሥ ኃይለ ሥላሴ በኩል አስተዋጽዖ ያደረግንበት ካቴድራል ነው፡፡
እኔ ግብጽ ስገባ በሀገሪቱ የተቀሰቀሰው አብዮት ሙባረክን አውርዶ ከፍተኛውን ወታደራዊ ምክር ቤት ተክቶ ነበር፡፡ ያም ቢሆን ግን የታሕሪር አደባባይ አሁንም ከአብዮቱ ውጥረት ነጻ አልነበረም፡፡ በተለየም ከዓርብ የጁምዐ ስግደት በኋላ ወደ ታሕሪር ማምራት የወቅቱ ልማድ ነበር፡፡
በየአካባቢው ከፍተኛ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡ ታላላቅ መሥሪያ ቤቶች በወታደሮች ጥበቃ ይደረግባቸዋል፡፡ አብያተ ክርስቲያናትም እንዲሁ፡፡ የገናን በዓል ለማክበር በተሰበሰቡ ክርስቲያኖች ላይ ፈንጅ ተጠምዶ ብዙዎቹን ከገደለ በኋላ በየአብያተ ክርስቲያናቱ የሚደረገው ጥበቃ እና ፍተሻ ጠበቅ ብሏል፡፡
በጠዋቱ ቁርስም አልቀመስን፡፡ በግብጽ ቤተ ክርስቲያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወኪል የሆኑት አባ ገብረ ሕይወት ወይንም ግብጻውያን እንደሚጠሯቸው አቡነ ሐያት ከፖፕ ሺኖዳ ጋር የተያዘው ቀጠሮ ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት መሆኑን ትናንት ማታ ነግረውናል፡፡
እኛ ያረፍነው መዲናት ናስር ከሚገኘው የቅድስት ድንግል ማርያም እና የቅዱስ አትናቴዎስ ቤተ ክርስቲያን አጠገብ ነው፡፡ ከቤተ ክርስቲያኑ አጠገብ የእንግዶች ማረፊያ ባለ አራት ፎቅ ሕንፃ አለ፡፡ እኛ ሁለተኛው ፎቅ ላይ ነው ያረፍነው፡፡
ከመዲናት ናስር ወደ መንበረ ፓትርያርኩ ወደ አባስያ ለመጓዝ የተጨናነቀውን የካይሮ ትራፊክ ማለፍ ይጠይቃል፡፡ እዚህ ሀገር መኪናው ከሰው ቁጥር ይበዛል፡፡ እስካሁን የትራፊክ መብራት ሲበራ እንጂ በመብራት መኪና ሲቆም አላየሁም፡፡ ጡሩንባ እየነፉ መጓዝ ብቻ ነው፡፡ መኪኖቹ ጡሩንባ እንጂ ፍሬን ያላቸው አይመስሉም፡፡
የመንበረ ፓትርያርኩ አካባቢ በወታደሮች እየተጠበቀ ነው፡፡ ወደ ግቢው የምትገቡት በደኅንነት መፈተሻ ሳጥኑ በኩል አልፋችሁ ነው፡፡ ከግቢው ሰፊውን ክፍል የያዘው ቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል ሲሆን የፓትርያርኩ መኖርያ በካቴድራሉ ፊት ለፊት፣ ከዋናው መግቢያ ጀርባ ይገኛል፡፡
ይህ መንበረ ፕትርክና የተገነባበት ቦታ ጥንት የግብጻውያን ክርስቲያኖች መቃብር የነበረበት ቦታ ነው፡፡ ቦታው ለቤተ ክርስቲያኒቱ የተሰጠው 969 ዓም ለቤተ መንግሥቱ መሥሪያ ተብሎ በተወሰደባት ቦታ ምትክ ነው፡፡ በቦታው ላይ ጥንታዊው የአባ ሮዩስ ቤተ ክርስቲያን ነበረበት፡፡
12ኛው መክዘ በአካባቢው 12 አብያተ ክርስቲያናት ነበሩ፡፡ 1280 ዓም አብያተ ክርስቲያናቱ ተቃጠሉ፡፡ ከዚያም በቦታው ሁለት አብያተ ክርስቲያናት ተሠሩ፡፡
ወደ መንበረ ፕትርክናው ልትደርሱ ስትሉ ከግራ እና ከቀኝ ተራራ የሚያህሉ ሁለት ውሾች አሉ፡፡ በቅርብ ጊዜያት በግብፃውያን ክርስቲያኖች ላይ አደጋዎች እየበዙ ሲመጡ ለጥበቃ የገቡ የመንግሥት ፈታሾች ናቸው አሉን፡፡  
ወደ ውስጥ ስንዘልቅ አያሌ እንግዶች ተኮልኩለዋል፡፡ ወደ እንግዶች መጠበቂያ ቤት ወሰዱንና አንድ ሠላሳ ደቂቃ ተቀመጥን፡፡ ከዚያም ወደ ልዩ ጸሐፊያቸው ወደ አቡነ ኤርምያስ ቢሮ ገባን፡፡
ፖፕ ሺኖዳ ሦስት ልዩ ጸሐፊዎች አሏቸው፡፡ ሦስቱም ኤጲስ ቆጶሳት ናቸው፡፡ ሃያ ደቂቃ ያህል በልዩ ጽሕፈት ቤቱ ካረፍን በኋላ ተራችን ደርሶ ገባን፡፡
አቡነ ሺኖዳ አጭር ናቸው፡፡ መንበራቸውም እንደ እርሳቸው አጭር ነው፡፡ ጥቁሩን የጳጳሳት ልብስ ለብሰዋል፡፡ በእድሜ እና በአገልግሎት ብዛት መዳከማቸውን የፊታቸው ገጽታ ይመሰክራል፡፡ ይህም ሆኖ ግን ረቡዕ እና ዓርብ በካይሮ እና በእስክንድርያ ምእመናኑን ማስተማራቸውን አልተውም፡፡ እኤአ ኦገስት 3 1923 ዓም በላዕላይ ግብጽ አስዩት አብኑብ በተባለ ቦታ የተወለዱት ሺኖዳ ዛሬ በሰማንያ ስምንተኛው እድሜ ላይ ይገኛሉ፡፡ የጻፏቸው ከአንድ መቶ በላይ መጻሕፍት በመንበረ ፓትርያኩ ቤተ መጻሕፍት ልዩ ቦታ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ወላጆቻቸው የሰጧቸው ስም ናዚር ጋዪድ የሚል ነበር፡፡ ገና በተወለዱ በጥቂት ቀናት ውስጥ እናታቸውን ያጡት ሺኖዳ ከአምስት እኅቶቻቸው እና ከሁለት ወንድሞቻቸው ጋር ብቻቸውን ቀሩ፡፡ የመጀመርያውን ትምህርት በዳማንሁር ባንሐ ካይሮ የተከታተሉ ሲሆን ከካይሮ ዩኒቨርሲቲ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን በታሪክ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ ወሰዱ፡፡
ከዚያም ከኮፕቲክ ሴሚናሪ በነገረ መለኮት የመጀመረያ ዲግሪ አግኝተው በዚያው ሴሚናሪ የብሉይ እና የሐዲስ ኪዳን መምህር ሆኑ፡፡ የግብጽ ቤተ ክርስቲያንን ከድካም ያበረታት ሐቢብ ጊዮርጊስ የሰንበት /ቤቶችን እንቅስቃሴ ሲጀምር ዋናው የተልዕኮው አንቀሳቃሽ ሺኖዳ ነበሩ፡፡ እርሳቸው በዚያ ወቅት የኮፕቲክ ወጣቶች ኅብረትን መሠረቱ፡፡ ለሰንበት /ቤቶች መጽሔቶች የተለያዩ ጽሑፎችን በማበርከት ወጣቱን ያበረቱት ነበር፡፡ በኋላ ዘመን የመንፈስ አርነት (The release of the Sprit) ተብሎ የታተመው መጽሐፋቸው የእነዚህ መጣጥፎች ስብስብ ነው፡፡
በሐምሌ 18 ቀን 1954 ዓም እኤአ በዋዲ ኤል ናትሩን ወደሚገኘው የሶርያውያን ገዳም ገብተው ምንኩስናን ተቀበሉ፡፡ የገዳሙ አበ ምኔት እንጦንስ የሚል ስም ሰጧቸው፡፡ በዚያ ገዳም ሺኖዳ አያሌ ቀደምት የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን ማንበባቸው ይነገራል፡፡ በመነኮሱ በዓመታቸው ክህነት ተቀብለው ቄስ ሆኑ፡፡
ሺኖዳ ከምንም በላይ ለምንኩስና እና ለምናኔ ሕይወት ልዩ ትኩረት አላቸው፡፡ በእርሳቸው ዘመን በግብጽ የነበሩት እና ለግብጻውያን ገዳማዊ ሕይወት እንደገና ማንሠራራት ታላቅ አስተዋጽዖ ያደረጉት የኢትዮጵያዊው አብዱል መሲሕ (ገብረ ክርስቶስ) ደቀ መዝሙር ነበሩ፡፡ የገብረ ክርስቶስን ፍጹማዊ መንገድም ለመከተል ይጥሩ ነበር፡፡ በዚህም የተነሣ ለብዙ ዓመታት የኖሩትም በተባሕትዎ ነበር፡፡ መጀመርያ ከገዳሙ ሦስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ አንድ ዋሻ ውስጥ ተቀመጡ፤ በመቀጠልም ከገዳሙ ዐሥር ኪሎ ሜትር ወደ ሚርቅ እና በባሕር አል ፋሪግ ወደሚገኝ ዋሻ ገብተው ተጋድሎዋቸውን ቀጠሉ፡፡
ባሕታዊው (The Hermit) የተሰኘውንና በኋላ እኤአ 1954 የታተመውን ቅኔያቸውን የጻፉት በዚህ ጊዜ ነበር፡፡
1959 እኤአ ቄርሎስ ስድስተኛ ልዩ ጸሐፊያቸው አድርገው ሾሟቸው፡፡ ሺኖዳ ግን ደስተኛ አልነበሩም፡፡ ከገዳማቸው መውጣት እና በኣታቸውን መልቀቅ አያስደስታቸውም ነበር፡፡ ብዙ ጊዜያቸውንም የሚያሳልፉት በዋሻቸው ውስጥ በጸሎት እና ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ ነበር፡፡ ለብዙ ጊዜያትም ወደ ኤጲስ ቆጶስነት እንዳይጠሩ ሲከላከሉ ኖረዋል፡፡
1962 እኤአ ሺኖዳ በነበሩበት ገዳም ውስጥ አንድ አስተዳደራዊ ችግር ተፈጠረ፡፡ ጉዳዩም ወደ ፓትርያርክ ቄርሎስ ስድስተኛ ዘንድ ቀረበ፡፡ በዚያ ጊዜ ሺኖዳ በገዳሙ አስተዳደር ውስጥ ነበሩበት፡፡ ገዳማውያኑ እንደ ጥንቱ አበው ሆነው እንዲኖሩ፣ ገዳማት የችግር ቦታዎች ሳይሆኑ የጸሎት ቦታዎች እንዲሆኑ፤ የግብጽ ገዳማት አዲሱን ትውልድ ለመቀበል በሚችሉበት መንገድ እንዲደራጁ፤ ገዳማውያኑ ሥራ፣ ጸሎት እና ትምህርትን አጣምረው እንዲይዙ ይታገሉ ነበር፡፡ ይህ የሺኖዳ ሃሳብ ያልተስማማቸው አንዳንድ ገዳማውያንም ሺኖዳን ከስሰው ወደ ቄርሎስ ዘንድ አቀረቧቸው፡፡
አቡነ ቄርሎስ ስድስተኛ ሺኖዳን አስጠሯቸው፡፡ ሺኖዳ በቄርሎስ እግር ሥር ተደፍተው «አጥፍቻለሁ፣ ድሮም ኃላፊነቱን የተቀበልኩት ያለ ዐቅሜ ነው፡፡ እባክዎ ከኃላፊነት ያንሱኝና በዋሻዬ ብቻ ተወስኜ ልኑር፡፡ እኔ ደካማ ሰው ነኝ» ሲሉ ለመኗቸው፡፡
ቄርሎስም «ዛሬ እንደርና ነገ ውሳኔዬን አሳውቃለሁ» አሉ፡፡
በማግሥቱ መስከረም 30 ቀን 1962 ዓም እኤአ ፓትርያርክ ቄርሎስ እና ሌሎች ጳጳሳት የሺኖዳን ጉዳይ ለማየት በመንበረ ፓትርያርኩ ተሰባሰቡ፡፡ ሺኖዳ ውሳኔውን በጉጉት ነበር የጠበቁት፡፡ ኃላፊነት ከሚባለው ነገር ተገላግለው የምናኔ ሕይወታቸውን ብቻ ለመያዝ ፈልገዋል፡፡
ሺኖዳ ተጠሩ፡፡ ጳጳሳቱ ቆሙ፡፡ ሁሉም ቄርሎስን ያይ ነበር፡፡ ሺኖዳ እንዲንበረከኩ ተነገራቸው፡፡ ተንበረከኩ፡፡ ቄርሎስ እጃቸውን በሺኖዳ ላይ ጫኑ፡፡ ሌሎች ጳጳሳትም ወደ እርሳቸው መጡ፡፡
ሳይታሰብ አቡነ ሺኖዳ ተብለው የግብጽ የመንፈሳውያን ኮሌጆች እና የትምህርት ተቋማት ጳጳስ ሆነው ተሾሙ፡፡ ሺኖዳ ደነገጡ፡፡ አለቀሱም፡፡
በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ላይ ጥናት በማድረግ የታወቀው የካይሮ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሩ ጀርመናዊው ኦቶአ ሜናድረስ የአቡነ ሺኖዳን መሾም ሲሰማ እንኳን ደስ ያለዎት የሚል ደብዳቤ ላከላቸው፡፡ ሺኖዳ ግን የመለሱለት የሚከተለውን ነበር
«የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እና ሰላም ካንተ ጋር ይሁን፡፡ እንኳን ደስ ያለዎት ብለህ በቅንነት ስለላክህልኝ መልእክት አመሰግንሃለሁ፡፡ ያንተን ወዳጅነት እና ፍቅር መቼም አልዘነጋውም፡፡ እውነቱን ለመናገር ግን ለእኔ መላክ ያለበት የኀዘን ደብዳቤ እንጂ የደስታ ደብዳቤ አይደለም፡፡ አንድ መነኩሴ ጸጥታ የተሞላበትን የጸሎት በረሃ ለቅቆ ጫጫታ እና ሁካታ በተሞላበት ከተማ እንዲኖር ሲደረግ እንዴት እንኳድ ደስ ያለህ ይባላል? ማርያምን ከክርስቶስ እግር ሥር ተነሥታ ማርታን ልታግዝ ወደ ጓዳ ስትገባ ማነው እንኳን ደስ ያለሽ የሚላት? ለእኔ ይህ ደስታ ሳይሆን ሀፍረት ነው፡፡ እኔ ኤጲስ ቆጶስ ሆኜ የተሾምኩበትን ቀን በደስታ ሳይሆን በኀዘን እና በለቅሶ ነው የማስታውሰው፡፡ ብሕትውና እና የተጋድሎ ጸሎት ከምንም በላይ የሚበልጥ ነገር ነው፡፡ ብሕትውና እና ምናኔ ከኤጲስ ቆጶስነት ቀርቶ ከፓትርያርክነት ጋር እንኳን የሚወዳደር አይደለም፡፡
«ወዳጄ ሆይ እውነተኛው ቅድስና ሲመት ሳይሆን ልብን ቤተ መቅደስ አድርጎ ለክርስቶስ መቀደስ ነው፡፡ ክርስቶስ በመጨረሻው ቀን የልባችንን ንጽሕና እንጂ የክህነታችንን መዓርግ አይጠይቀንም፡፡ ይህንን ደብዳቤ የምጽፍልህ በምወድዳት ዋሻዬ፣ በባሕር አል ፋሬግ፣ በዋዲ ኤል ናትሩን ውስጥ ሆኜ ነው፡፡ እዚህም እስከ ጥምቀት ድረስ ለመቆየት አስባለሁ፡፡ ከዚያም ወደ ካይሮ እመለሳለሁ፡፡»
አቡነ ሺኖዳ እያለቀሱ ያቺን የዋዲ ኤል ናትሩን ዋሻ ትተው ካይሮ ቢመጡም በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ወደ ዋሻቸው መሄድ ያዘወትሩ እንደ ነበር ታሪካቸውን የጻፈላቸው የቅርብ ወዳጃቸው እና በእምነቱ ፕሮቴስታንት የነበረው ኦቶአ ሜናድረስ ይናገራል፡፡
እስከ 1969 እኤአ ድረስ የቤተ ክርስቲያኒቱን የትምህርት ተቋማት በዘመናዊ መልኩ አደራጇቸው፡፡ በዚህ የተነሣም በሙሉ ጊዜያቸው የሚማሩ ተማሪዎች ቁጥር ከአንድ መቶ ወደ 207 አደገ፡፡ ሺኖዳም በየሳምንቱ ዓርብ ዓርብ ሕዝቡን የሚያስተምሩበት እና የሕዝቡን ጥያቄዎች የሚመልሱበት የትምህርት መርሐ ግብር ከፈቱ፡፡ እስከ አሥር የሚጠጋ ሕዝብም መርሐ ግብሩን ይከታተለው ነበር፡፡ ለሰንበት ትምህርት ቤቶች የሚሆኑ መጻሕፍትን፣ መዝሙሮችን እና ትምህርቶችን ያዘጋጁ ነበር፡፡ የሰንበት ትምህርት ቤት መምህራንንም ያሠለጥኑ ነበር፡፡ በዚህ የሥራ ብዛት ውስጥ እያሉ እንኳን የሳምንቱን ግማሽ በካይሮ ቀሪውን ደግሞ በገዳማቸው ዋሻ ውስጥ ያሳልፉ ነበር፡፡
በዚሁ ዓመት ሺኖዳ የመካከለኛው ምሥራቅ የነገረ መለኮት ተቋማት ማኅበር ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ፡፡ቤተ ክርስቲያኒቱን ከሌሎቹ ጋር የማቀራረቡን ሥራ የጀመሩት ገና በጳጳስነታቸው ዘመን ነው፡፡ በእርሳቸው መሪነት ቤተ ክርስቲያኒቱ በአያሌ የነገረ መለኮት ውይይቶች ላይ ተሳትፋለች፡፡
ፓርትያርክ ቄርሎስ በመጋቢት 9 ቀን 1971 ዓም ዐረፉ፡፡ በመጋቢት 22 የተሰበሰበው የግብጽ ሲኖዶስም ተተኪውን ለመምረጥ ዝግጅት ጀመረ፡፡ አምስት እጩዎችንም መረጠ፡፡ ነገር ግን በመካከሉ ቤተ ክርስቲያኒቱ አያሌ ፈተናዎች ገጠሟት፡፡ በዚህም ምክንያት ፓትርያርክ ሳይመረጠ ረዥም ጊዜ ቆየ፡፡ በጥቅምት 29 ቀን የተሰበሰበው ቅዱስ ሲኖዶስ የእጩዎችን ቁጥር ወደ ሦስት ዝቅ አደረገው፡፡ የሦስቱም እጩዎች ስም በመንበረ ማርቆስ ካቴድራል መንበር ላይ ተቀመጠ፡፡ ሕዝቡ እና ገዳማውያኑም ለሦስት ቀን ሱባኤ ያዙ፡፡
ጥቅምት 31 ቀን 1971 እኤአ በሰንበት ዕለት ሕዝቡ፣ ካህናቱ፣ ገዳማውያኑ እና ጳጳሳቱ በተገኙበት ጸሎት ከተደረሰ በኋላ አንድ ዓይኑን በሻሽ ለተሸፈነ አይማን ሙኒር ካሊል የተባለ ሕፃን በመንበሩ ላይ የተጸለየባቸው ስሞች ቀረቡለት፡፡ እጁን ዘርግቶ አንዱን ዕጣ አወጣው፡፡ በወቅቱ ቤተ ክርስቲያኒቱን በጊዜያዊነት ይመራ የነበረው ኮሚቴ ሊቀ መንበር ለሆኑት ለሜትሮጶሊጣን አንቶኒዮስም ሰጣቸው፡፡
ወረቀቱን ዘረጉት፡፡ «እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያናችን አባት ይሆኑ ዘንድ አቡነ ሺኖዳን መርጧል» ሲሉ አካባቢው በጭብጨባ እና በእልልታ ተናጋ፡፡ ከሁለት ሳምንት በኋላ የዛሬ ዐርባ ዓመት ኅዳር 14 ቀን 1971 እኤአ በቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል፣ ሺኖዳ 3 117ኛው የግብጽ ፓትርያርክ ተብለው ተሾሙ፡፡
በእራሳቸው ዘመን ቤተ ክርስቲያኒቱ እንደገና ኃይል አገኘች፡፡ አሁንም በነገረ መለኮት ኮሌጅ ያስተምራሉ፡፡ የኮሌጁ ዲንም ነበሩ፡፡ የኤልኬራዛ መጽሔት አዘጋጅ ናቸው፡፡ ዓርብ ዓርብ ያስተምራሉ፡፡ ገዳማትን እና ትምህርት ቤቶችን አስፋፉ፡፡ ወጣቱን ወደ አገልግሎት ጠሩ፡፡
አሁንም በፓትርያርክነታቸው ዘመን በአባ ቢሾይ ገዳም የሳምንቱን ግማሽ በገዳማዊ ሕይወት ማሳለፋቸውን አልተውም፡፡ መጻሕፍትን ይጽፋሉ፡፡ በውጭ እና በሀገር ውስጥ ያለውን ሕዝብ ይጎበኛሉ፡፡ እርሳቸው ሲሾሙ በውጭ ያሉት አጥቢያዎች ሰባት ብቻ ነበሩ፡፡ አሁን ግን በአሜሪካ እና ካናዳ የሚገኙትን አብያተ ክርስቲያናት እንኳ ከሰማንያ በላይ አድርሰዋቸዋል፡፡ በአውስትራልያ 26 በአውሮፓ 30 አጥቢያዎች ይገኛሉ፡፡
ሺኖዳ ለአቋማቸው እና ለእምነታቸው ሲሉ ስደትን የቀመሱ ፓትርያርክ ነበሩ፡፡ አንዋር ሳዳት የግብጽ መሪ በነበረ ጊዜ በቤተ ክርስቲያኒቱ እና በምእመናኗ ላይ የሚደርሰውን መከራ በመቃወም ሺኖዳ ደጋግመው ይናገሩ ነበር፡፡ በዚህ ያልተደሰተው ሳዳት መስከረም 3 ቀን 1981 እኤአ ባወጣው ዐዋጅ ሲኖዳን ከመንበራቸው አሳደዳቸው፡፡ በግዞትም ወደ አባ ብሶይ ገዳም ተላኩ፡፡
ሕዝቡ ሌላ አባት አንመርጥም ብሎ ተከትሏቸው አባ ብሶይ ገዳም ገባ፡፡ እዚያም በሚወዱት ገዳም ተጋድሏቸውን እና ትምህርታቸውን ቀጠሉ፡፡ በገዳሙ በግዞት ለአራት ዓመት ተኩል ከቆዩ በኋላ ሳዳት ሞቶ ሙባረክ ሲተካ በጥር 2 ቀን 1985 እኤአ ወደ መንበራቸው ተመለሱ፡፡
ሺኖዳ ቀልድ ዐዋቂ ናቸው፡፡ በተለይ ሕፃናትን ማስተማር ይችሉበታል፡፡ ሕዝቡን ሲያስተምሩም ቀልድ እና ታሪክ ጣል ማድረግ ይወዳሉ፡፡ ሴቶች በቤተ ክርስቲያን የነበራቸውን የአገልግሎት ተሳትፎ በማሳደግም ሺኖዳ ከፍተኛ ለውጥ አምጥተዋል፡፡ ሺኖዳ ለሀገራቸው ያላቸው ፍቅር ልክ የለውም፡፡ «በልባችን ውስጥ ያለችው ግብጽ ከምናያት ግብጽ ትበልጣለች» የሚለው አባባላቸው በግብጻውያን ልብ ለዘለዓለም ታትሞ ቀርቷል፡፡ ክርስቲያን እና ሙስሊሙ ሕዝብ ተከባብሮ እና ተባብሮ እንዲኖር በብርቱ ጥረዋል፡፡
በዐርባ ዓመት አገልግሎታቸው ከአንድ መቶ በላይ መጻሕፍትን ጽፈዋል፡፡ ንግግር ዐዋቂ፣ ባለ ቅኔ፣ ሰባኪ እና ደራሲ ናቸው ሲኖዳ፡፡ እንደዚህ ያለ ታላቅ ሰው በሀገራችን ሲሞት «አራት ሰው ሞተ ይባላል፡፡ እኔም
አራት ሰው ሞተ ደረሰና ጥሪ
ደራሲ፣ ሰባኪ፣ ጳጳስ እና መሪ
ያልኩት ለዚህ ነበር፡፡
በሙስሊሞች፣ በፕሮቴስታንቶች እና በካቶሊኮች ዘንድ የሚወደዱ እና የሚከበሩ አባት ሆነዋል፡፡ የታላቁ የአልአዝሐር መስጊድ ኢማም የፖፕ ሺኖዳን ሞት ተከትሎ «ግብጽ እኒህን ጥበበኛ ሰው በምትፈልግበት ወሳኝ ጊዜ እርሳቸውን ማጣታችን የሚያንገበግብ ነው» ነበር ያሉት፡፡
ሞታቸው ለግብጽ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን መላውን ዓለም የጎዳ ነው፡፡ ተወዶ የሚኖርና ተለቅሶለት የሚቀበር የሃይማኖት መሪ በዓለም ላይ እየጠፋ ባለበት በዚህ ጊዜ ሺኖዳ በሕይወታቸውም በሞታቸውም ያስተማሩ አባት ሆነዋል፡፡
እነሆ ፊት ለፊታቸው ቆሜ ዝም ብዬ አያቸዋለሁ፡፡ የተቀመጡበት መንበር ይህንን ያህል የተብለጨለጨ አይደለም፡፡ አንዳች የሚስብ ነገር ግን አለው፡፡ የርሳቸውም ልብስ ከመደበኛው የመነኮሳት ልብስ የዘለለ ልዩ ጌጥ የለውም፡፡ አንዳች ነገር ግን ረቦበታል፡፡
ከእርሳቸው ጋር ፎቶ ለመነሣት አስፈቅጄ ስቀርብ የወጣቱን እንቅስቃሴ በተመለከተ ጠየቁኝ፡፡ እኔም በአጭሩ ነገርኳቸው፡፡ «እንደ አባቶቻችሁ ለእግዚአብሔር ብቻ ስትሉ አገልግሉ፡፡ የናንተ አባቶች ለእግዚአብሔር ብቻ ሲሉ የሚያገለግሉ ነበሩ» አሉ፡፡
ስንለያቸው ለእያንዳንዳችን ፊርማቸው ያረፈበት ስጦታ ሰጡን፤ ከዚያም
«አሁን ለሕክምና ወደ አሜሪካ በቅርብ እጓዛለሁ፡፡ እግዚአብሔር ጤና እንዲሰጠኝ እና በሚገባ እንዳገለግል ጸልዩልኝ» አሉ ሺኖዳ፡፡
ወይ አልጸለይንላቸውም፣ ወይም ጸሎታችን አልረዳቸውም መሰል ባገኘናቸው በዓመቱ መጋቢት 8 ቀን 2004 ዓም ዐረፉ፡፡ በሚወዱት በአባ ብሾይ ገዳምም ተቀበሩ፡፡
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው፡፡ በሌላ መሰል ኅትመት ባይወጣ ይመረጣል፡፡

62 comments:

 1. I used to read his books back in high school. I dont know why but I felt this sudden desire to have the opportunity to meet him. I guess it was not meant to be. Now my only hope is that we (Ethiopians), will oneday, be blessed enough to have a Father like him. May GOD have mercy on all of us.

  ReplyDelete
 2. «በልባችን ውስጥ ያለችው ግብጽ ከምናያት ግብጽ ትበልጣለች»

  «እንደ አባቶቻችሁ ለእግዚአብሔር ብቻ ስትሉ አገልግሉ፡፡ የናንተ አባቶች ለእግዚአብሔር ብቻ ሲሉ የሚያገለግሉ ነበሩ» አሉ፡፡

  ተወዶ የሚኖርና ተለቅሶለት የሚቀበር የሃይማኖት መሪ በዓለም ላይ እየጠፋ ባለበት በዚህ ጊዜ ሺኖዳ በሕይወታቸውም በሞታቸውም ያስተማሩ አባት ሆነዋል፡፡
  Thanks Dn. Dani!Bereketachew yidrbn!

  ReplyDelete
 3. hi , brother daniel. i read ur write. realy thank u.

  i have some fiture . how can u post my writting.

  ReplyDelete
 4. Dn. Daniel
  ABATACHIN 4 SEW BICHA AYDELUM LELAM MEBAL ALEBACHEW.
  Most of us feel that we lost one of our family. May God send his blessings to us.
  Dd

  ReplyDelete
 5. ዲያቆን ዳንኤል
  እግዚአብሔር ይባርክህ
  የብጹእ አባታችንን ነፍስ ይማርልን!
  "እንደ አባቶቻችሁ ለእግዚአብሔር ብቻ ስትሉ አገልግሉ፡፡
  የናንተ አባቶች ለእግዚአብሔር ብቻ ሲሉ የሚያገለግሉ ነበሩ"አሉ።

  ፈጣሪ ለሁላችንም ልቦና ይስጠን!!!

  ReplyDelete
 6. "...ፖፕ ሺኖዳ ሦስት ልዩ ጸሐፊዎች አሏቸው፡፡ ሦስቱም ኤጲስ ቆጶሳት ናቸው፡፡"
  በእኛ መንበርስ ልዩ ጸሐፊዎች ኤጲስ ቆጶሳት ሆነው ያውቁ ይሆን...

  ReplyDelete
 7. "ተወዶ የሚኖርና ተለቅሶለት የሚቀበር የሃይማኖት መሪ በዓለም ላይ እየጠፋ ባለበት በዚህ ጊዜ ሺኖዳ በሕይወታቸው
  ም በሞታቸውም ያስተማሩ አባት ሆነዋል፡፡"

  ጥልቅ፡አባባል፡ነው!መድኃኔ፡ዓለም፡ክርስቶስ፡ነፍስዎን፡ከቀደም
  ት፡አባቶቻችን፡ጋር፡ያሳርፍልን።የግብጽ፡ተዋሕዶዎችን፡እግዚአ
  ብሔር፡ያጽናችሁ፣ያጽናናችሁ።
  ለተዋሕዶ-ኢትዮጵያም፡እንደ፡እርሳቸው፡ያለ፡አባት፡ይስጠን።
  አሜን

  ሳሙኤል፡ዘአሰቦት።

  ReplyDelete
 8. ሳሚ (ወ/ሚካኤል)March 26, 2012 at 7:51 PM

  ዳኒ...ማለቀስ በሚገባን እንዲሁም የክርስቶስንና የክርሰቶስ መኖሪዎችን ሞት ልናስብ በተገባበት ሰሞን (ሰሞነ ሁዳዴ) ይህን ታሪክ በመጻፍህ በሃጥያት መሸጎሪያ ለተከረቸመው የእንባችን መስኮት መስበሪያ ሁኖናል!!! ከዚህ ያባታችን ታሪክ ልቤን የነካው አስደናቂውና ሆድ የሚያስብሰው ክርስቲያናዊ የቅድስና ህይወታቸው ብቻ ሣይሆን የሳቸው ቅዱስ ታሪክ ግልባጭ (ተቃራኒ) ሁኖ የሚተረከው የኛ አባቶችም ዝርክርክ ህይወት ነው!!! ውነት ይህ ህዝብ እንደሳቸው አይነት አባት ቢያገኝ ምን ሊሆን ነበር;;;!! መንግስትን ደግፎ ከመንግስት የባሰ ደንዳና ልብ ይዞ የቅ/ገዳሞቻችንን ቅጥር አርክሶ መራራ ክርስትና እንዲመነጭ የታቀደውን የጣፈጭ አፈር (ስኩዋር) እቅድ በመደገፍ ቅ/ገዳማውያኑን የሚዘልፍ ሲዶስና ቤተ ክህነት ያለው ህዝብ ከገዳም ወጥቸ ስለተሸምኩ እንኩዋን ደስ አለህ አትበሉኝ ክርስቶስ ልብን እንጅ ሲምትን አይመለከትም የሚሉትን ቅ/አባት ሲያይ ከማልቀስ ሌላ ምን ይተርፈዋል!!!! ለትውልዳቸው በ 100 መጻህፍት ውስጥ ክርስቶስን አኑረው መሄድ(ማረፍ) እያለ ክ 100 ኩንታለ በላይ የሆነ የድንጋይ ትክል(ደረቅ ሃውልት) እንካችሁ የሚል ትምክህተኛ እረኛ ያለው ህዝብ ለምን እርር አይል!! ለምን ስቅስቅ አይል!!! ዳኒ እንባየ ኮምፒውተሬን ጋርዶ በገላጋይ እያለኝ ስለሆነ ባለችኝ ሰዓት የቅዱሱን አባት ስም ላመስግንባት!!!!!! አቤቱ አባታችን ሆይ በጸሎትህ ታደገን በረከትህም የቲሞቹን እኛን ታጽናናን!!!!!ክርስቶስን ባንተ ሁኖ አይተናልና በማይጠፋው መሰረት ላይ የቆመውን ሃውልትህን ዞትር እንሳለመዋለን ዞትርም እንባርከዋለን!!!!ይትባረክ እግዚአብሄር አምላከ ሽኖዳ!!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Sami, may God bless you for your kind words. This is a wakeup call for us when monastic life has been disrespected by the hierarchy of EOC management through their endorsement of sugar plantation at WALDBA. Patriarch Shinoda said monastic life is beyond comparison and better than being Patriarch.

   Delete
 9. «እንደ አባቶቻችሁ ለእግዚአብሔር ብቻ ስትሉ አገልግሉ፡፡ የናንተ አባቶች ለእግዚአብሔር ብቻ ሲሉ የሚያገለግሉ ነበሩ»
  አዎ የሰዎችን ጫና ችለህና ታግሰህ አደራህን ተወጣ እኛም ሁላችንም ያለብንንን አደራ እንወጣ።
  እንደዚሁም የአባታችን በረከት እና ቃለ ቡራኬ ከእኛ ጋር ይሁንአሜን።

  ReplyDelete
 10. Hello Diakon, I am sure you are already working on this but please include this things in your blog as there is a confusion on Waldiba Gedam situation. There is a confusion and we can't believe what ETV had to say about it and we don't know what the Bete kihinet is agreeing with. If you can it will be very helpful to show a graphical description of the situation using map of the Monastery and the surrounding using tangible references. Please indicate: the area that is called waldiba gedam, all the churches inside the Waldiba gedam, the area known as Welkayit with its churches and the full scale size of the project (putting those in danger of demolition in RED may help describe the situation better.)Also the immediate and the long term consequences of the project on the Monastery. This case could be sensitive to the government and take extra care not to post information with out proof as they could take you to court out of nothing just like M. Zemedikun.

  ReplyDelete
 11. አምላክ ሆይ ለእኛም አባቶች መንፈሳዊ ቅናት አሳድርባቸው:: አሜን::

  ReplyDelete
 12. Dn. Daniel betam enamesegnalen Abune Shinoudan yebelete endiwedachew endakebrachew aderekegn. Yenegeruh gin tilik mele'ekt new ''እንደ አባቶቻችሁ ለእግዚአብሔር ብቻ ስትሉ አገልግሉ፡፡ የናንተ አባቶች ለእግዚአብሔር ብቻ ሲሉ የሚያገለግሉ ነበሩ'' Amlak cher yaseman

  ReplyDelete
 13. ዳን ዳንኢል እግዛብሒር ይባርክህ ለእኛም እንደ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ አይነት አባት ይስጠን

  ReplyDelete
 14. Yeabatachin ye Abune Shenouda bereket yederibin Amen!

  ReplyDelete
 15. Egziabeher Enede Qedusenetachew Yaluten Aluten abatoche Yabezalen

  ReplyDelete
 16. Egziabeher Enede Kidusenetachew Yaluten abatoche Yabezalen

  ReplyDelete
 17. እግዚአብሔር አምላክ ዛሬም በብዙ ዓይነት ውጥረትና ፈትና ውስጥ ላለችው ቅድስት ቤተክርስቲያን ብጹእ ወቅዱስ አባታችን አቡነ ሽኖዳ እንዳሉት ስለእግዚአብሔር ብቻ ሲሉ የሚያገለግሉ የመፍትሔ፣የሰላም አስፋኝ፣የመንጋው አለኝታና አጽናኝ፤ ዕለት ዕለት የቤተክርስቲያን ጉዳይ ብቻ የሚከብድቸው አባቶች በቸርነቱ አያሳጣን።

  ReplyDelete
 18. «እንደ አባቶቻችሁ ለእግዚአብሔር ብቻ ስትሉ አገልግሉ፡፡ የናንተ አባቶች ለእግዚአብሔር ብቻ ሲሉ የሚያገለግሉ ነበሩ» አሉ፡፡
  ድንቅ መልዕክት። አማላክ ሆይ መልዕክቱን ለመፈጸም አብቃኝ።

  ReplyDelete
 19. tselotena berketachew ayeleyen amen
  yonas from dallas

  ReplyDelete
 20. D/n Daniel ke'Abatachin talaq bereketin endihum kebad aderam teqebilehal ...
  -"Ende abatochachihu le'Egziabher bicha sitlu agelgilu, Ye'enante abatoch le'Egziabher bicha silu yemiyagelgilu neberu."
  -"Gbits enihn tibebegna sewu bemitfeligbet wosagn gizie ersachewun matatachin yemiangebegib newu." Egnas ...?
  -"... behyiwotachewum bemotachewum yastemaru abat honewal." Ye'abtachin bereketachew yideribin. Amen !

  ReplyDelete
 21. የታላቁ የአልአዝሐር መስጊድ ኢማም የፖፕ ሺኖዳን ሞት ተከትሎ «ግብጽ እኒህን ጥበበኛ ሰው በምትፈልግበት ወሳኝ ጊዜ እርሳቸውን ማጣታችን የሚያንገበግብ ነው» ነበር ያሉት፡ I wish Ethiopia has ..............

  ReplyDelete
 22. የታላቁ የአልአዝሐር መስጊድ ኢማም የፖፕ ሺኖዳን ሞት ተከትሎ «ግብጽ እኒህን ጥበበኛ ሰው በምትፈልግበት ወሳኝ ጊዜ እርሳቸውን ማጣታችን የሚያንገበግብ ነው» ነበር ያሉት፡ I wish Ethiopia has ..............

  ReplyDelete
 23. ቅዱስ አባታችን እዚህ ኢትዮጵያ የመጡ ጊዜ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተደረገላቸው አቀባበል ላይ ሲያስተምሩ "እኛ ካህናት ልናገለግል ተመረጥን እንጂ ልንገለገል አልተመረጥንም" ያሉትን ትምህርታቸውን በኑሯቸው ያሳዩ ቅዱስ አባት ናቸው በረከታቸው ይደርብን።

  ReplyDelete
 24. may his soul rest in peace.

  ReplyDelete
 25. «እንደ አባቶቻችሁ ለእግዚአብሔር ብቻ ስትሉ አገልግሉ፡፡ የናንተ አባቶች ለእግዚአብሔር ብቻ ሲሉ የሚያገለግሉ ነበሩ» አሉ፡፡

  ReplyDelete
 26. \yegnawochu Hager Yikefafilalu, emmm----
  thank you Dn.Dani

  ReplyDelete
  Replies
  1. may GOD make their hurt to become generous and not be racist.

   Delete
 27. እንደ አባቶቻችሁ ለእግዚአብሔር ብቻ ስትሉ አገልግሉ፡፡ የናንተ አባቶች ለእግዚአብሔር ብቻ ሲሉ የሚያገለግሉ ነበሩ» thank you pope shenueda this is your world about my country. Dani you are lackey gay i swear to God I am Jealousy about you.

  Maki
  Juba

  ReplyDelete
 28. KALEHIWOT YASEMALEN DAN.....ወዳጄ ሆይ እውነተኛው ቅድስና ሲመት ሳይሆን ልብን ቤተ መቅደስ አድርጎ ለክርስቶስ መቀደስ ነው፡፡ ክርስቶስ በመጨረሻው ቀን የልባችንን ንጽሕና እንጂ የክህነታችንን መዓርግ አይጠይቀንም፡፡ ይህንን ደብዳቤ የምጽፍልህ በምወድዳት ዋሻዬ፣ በባሕር አል ፋሬግ፣ በዋዲ ኤል ናትሩን ውስጥ ሆኜ ነው....OUR REAL FATHER

  ReplyDelete
 29. anten yeseten yabatochachen amlak yekeber yemesegen

  ReplyDelete
 30. ዲ.ን ዳኒ ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡ እውነቴን ነው የምልህ በአቡነ ሺኖዳ ዕረፍት ሁሉም ሰው ደንግጧል፡፡ ሁሌ ስለ እሳቸው በጸሎት እግዚአብሔርን እንለምን፡፡ ነፍሳቸውን በገነት ያሳርፍልን፡፡

  ReplyDelete
 31. Enmar,egziabher yemiserabin ende Abune Shenouda yetegan yadrgen.yersachewun nefs yimarlin.amen.

  ReplyDelete
 32. ወዳጄ ሆይ እውነተኛው ቅድስና ሲመት ሳይሆን ልብን ቤተ መቅደስ አድርጎ ለክርስቶስ መቀደስ ነው፡፡ ክርስቶስ በመጨረሻው ቀን የልባችንን ንጽሕና እንጂ የክህነታችንን መዓርግ አይጠይቀንም፡፡
  ይህንን ቃል በያንዳንዱ አባቶቻችን ልቦና ውስጥ ያኑርልን፡፡
  አሜንንንንንንንንን.......

  ReplyDelete
  Replies
  1. አባት ሽኖዳ ለኛ መጽናናትና የመንፈስ እረፍት የሚሰጡን አባት፤ የእምነት ተምሳሌትም ነበሩ፡፡ አሁንም የአባታችን መንፈስ በኛ ላይ ይሁን፡፡ የአባቶቻችን አምላክም በሳቸዉ መንገድ የሚህድን ደግ አረኛ ይላክልን፡፡ ከምንግዤዉም በላይ ሱባኤ የሚያስፈልገን ጊዜ ላይ እንዳለንም የተገለጠ ስለሆነ እንበርታ፡፡ ዲ/ን ዳንኤል አንተንም እግዚአብሔር በመንገድ ሁሉ ያበርታህ፡፡

   Delete
 33. egziabhar yebarkhe btam ymewdachwne abat tarik ngerkegn berktachw yederben amen

  ReplyDelete
 34. አባት ሽኖዳ ለኛ መጽናናትና የመንፈስ እረፍት የሚሰጡን አባት፤ የእምነት ተምሳሌትም ነበሩ፡፡ አሁንም የአባታችን መንፈስ በኛ ላይ ይሁን፡፡ የአባቶቻችን አምላክም በሳቸዉ መንገድ የሚህድን ደግ አረኛ ይላክልን፡፡ ከምንግዤዉም በላይ ሱባኤ የሚያስፈልገን ጊዜ ላይ እንዳለንም የተገለጠ ስለሆነ እንበርታ፡፡ ዲ/ን ዳንኤል አንተንም እግዚአብሔር በመንገድ ሁሉ ያበርታህ፡፡

  ReplyDelete
 35. አባት ሽኖዳ ለኛ መጽናናትና የመንፈስ እረፍት የሚሰጡን አባት፤ የእምነት ተምሳሌትም ነበሩ፡፡ አሁንም የአባታችን መንፈስ በኛ ላይ ይሁን፡፡ የአባቶቻችን አምላክም በሳቸዉ መንገድ የሚህድን ደግ አረኛ ይላክልን፡፡ ከምንግዤዉም በላይ ሱባኤ የሚያስፈልገን ጊዜ ላይ እንዳለንም የተገለጠ ስለሆነ እንበርታ፡፡ ዲ/ን ዳንኤል አንተንም እግዚአብሔር በመንገድ ሁሉ ያበርታህ፡፡

  ReplyDelete
 36. As Dn. Abibi and then Abune Shenoda Changed into coptic church into high rank;Ethiopian preachers,theologians and by large Mahibere Kidusan(including you) Movement will resume church's honour in the near future.

  ReplyDelete
 37. YEMOTE SAYIHON YENORE TEGODA.....

  ReplyDelete
 38. Dear Daniel,

  Thank you for your feed back in all aspects in relation to our church & fathers. You are doing a very good job since your blog is on the PCs.
  God Bless Ethiopia and its people
  God Bless Daniel too
  I thank you

  ReplyDelete
 39. i donot know,i can not say something,i can cry

  ReplyDelete
 40. how many books are written by our partiarch?

  ReplyDelete
 41. ክርስቶስ በመጨረሻው ቀን የልባችንን ንጽሕና እንጂ የክህነታችንን መዓርግ አይጠይቀንም፡፡

  ReplyDelete
 42. አምላክ ሆይ ለእኛም እንደ አቡነ ሺኖዳ III አይነት አባት ስጠን:: አሜን::

  ReplyDelete
 43. Selam, Dn. Daniel,

  You deserve the fullest appreciation for your condolences and detailed presentation about the passing away of a highly respected leader of a sister church, Abune Shinoda.

  However, it is regrettable that you deliberately omit to mention his highly negative policy to our beloved church, EOTC, concerning our historic monastery, "Deir el Sultan", in Jerusalem.

  For more details, please check: www.eotcipc.org where an international petition addressed to the Israeli Prime Minister is being signed calling for his approval to allow us to repair the monastery.

  As one of the renowned deacons of our beloved church, it would be normal to expect you present a more balanced and fair picture concerning Pope Shenoda's policy with regard to our church, especially the monastery in Jerusalem.

  ReplyDelete
 44. Dani medihanealem yeageligilote zemenihine yabizalih. yeabatochi bereket ayileyihe.
  selame egzeabher kante ga yihune.

  ReplyDelete
 45. Dani Egziabhere yetebkhe lebetachen ewentenga Abate Geta yesten yeAba Shenouda nifse yimarline

  ReplyDelete
 46. Dn.Dani let me give you one assignment for you. that is pleas arrange one program remember abune shinoda and discus our " ".

  «እንደ አባቶቻችሁ ለእግዚአብሔር ብቻ ስትሉ አገልግሉ፡፡ የናንተ አባቶች ለእግዚአብሔር ብቻ ሲሉ የሚያገለግሉ ነበሩ»

  ReplyDelete
 47. ዲ/ን ዳንኤል ቃለ ህይወት ያሰማልን፡፡ የኛ የቀድሞ አባቶች እንደ አቡነ ሺኖዳ ነበሩ እነ አቡነ ተ/ ሃይማኖት እነ አቡነ ጴጥሮስ … የአሁኖቹ ግን ስንፈልጋቸው የማናገኛቸዉ ናቸዉ፡፡ ገዳሞቻችን ሲወድሙ አልወደሙም ብለው የሚዋሹ፤ ሲቃጠሉ በቦታው ተገኝተዉ ምእመናኑን የማያበረቱ፡፡ ህዝቡ እነሱን የሚመራቸዉ ፡፡ አምላካችን ስለ እናቱ ስለ ቅድሰት ድንግል ማርያም ሲል ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን፡፡ ለሁላችንም ብርታት ይሁነን፡፡

  ReplyDelete
 48. ዘውዱ መንገሻMarch 28, 2012 at 6:11 PM

  እውነተኛ አባት ቤተክርስትያናችን አጥታለች ግን ወደ ዘላለማዊው ቤታችን ነው የሄዱትና አንከፋም!!
  የአባቶቻችን አምላክም በሳቸዉ መንገድ የሚህድን ደግ አረኛ ይላክልን፡፡ አሜን!
  «እንደ አባቶቻችሁ ለእግዚአብሔር ብቻ ስትሉ አገልግሉ፡፡ የናንተ አባቶች ለእግዚአብሔር ብቻ ሲሉ የሚያገለግሉ ነበሩ»
  አምላካችን ስለ እናቱ ስለ ቅድሰት ድንግል ማርያም ሲል ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን፡ አሜን!!!

  ReplyDelete
 49. «እንደ አባቶቻችሁ ለእግዚአብሔር ብቻ ስትሉ አገልግሉ፡፡ የናንተ አባቶች ለእግዚአብሔር ብቻ ሲሉ የሚያገለግሉ ነበሩ» አሉ፡፡

  nefsachewun ymarln yegnam abat lbona yistln

  ReplyDelete
 50. «በልባችን ውስጥ ያለችው ግብጽ ከምናያት ግብጽ ትበልጣለች»

  «እንደ አባቶቻችሁ ለእግዚአብሔር ብቻ ስትሉ አገልግሉ፡፡ የናንተ አባቶች ለእግዚአብሔር ብቻ ሲሉ የሚያገለግሉ ነበሩ» አሉ፡፡

  ተወዶ የሚኖርና ተለቅሶለት የሚቀበር የሃይማኖት መሪ በዓለም ላይ እየጠፋ ባለበት በዚህ ጊዜ ሺኖዳ በሕይወታቸውም በሞታቸውም ያስተማሩ አባት ሆነዋል፡፡
  Thanks Dn. Dani!Bereketachew yidrbn!Amin

  ReplyDelete
 51. ጥጋብና እርሃብ ምን እንደሆኑ ለመረዳት እሩቅ መሄድ አይጠበቅብንም፡፡ኢትዮጵያ እንደሆነች የጥቂቶች ገነት የብዙሃኖች ገሀነም ከሆነች ሰነባብታለች፡፡ይሳካላቸውም አይሳካላቸውም ሌላ ነገር ሆኖ አዎ ጥቂቶችም በብዙሀኖች መቃብር ላይ ቤተ-መንግስት ለመስራትና አዲስ ታሪክ ለመፃፍ ሽርጉድ እያሉና እየተጣደፉባት ነው፡፡የእብሪት የንቀት የዘረኝነትና የዝርፊያ የመጨረሻ ደረጃም በአለም ላይ እጅግ በተሻለ ኢትዮጵያ ውስጥ ተግራባዊ እሆነ ያለ ስለሆነ ኢትዮጵያ እራሷ የነገሮች ሁሉ ቤተ-ሙከራ እየሆነች ነው፡፡ጥጋብና በተቃራኒው ያለው ርሃብ ምን እንደሚያደርግ እንደ ቤተ-ሙከራ እዚሁ ሀገራችን ውስጥ በደንብ እያየነው ነው፡፡ዲያቆን ዳንኤል ነገሮች አንተ በነገሮችህ እያስተማርክ ልታስተካክላቸው ከምትችለው አቅም በላይ እየተወሳሰቡ ነው፡፡በዘመነ ወያኔ በአጭሩ ኢትዮጵያና ህዝቦቿ ዘመናዊ የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ውስጥ ገብተዋል፡፡ዛሬ ጥቂት ዶላር በሳምሶናይት ይዘው ለመጡ ለባእዳን ሀገራት ኢንቨስተር ተብዬዎች ወያኔ የሀገሪቱን ሰፊ ለም መሬት በርካሽ እየቸበቸበ ባለበት ሰዓት በቅርቡ እስከ 22 000 ደረጃ የሚደርሱ የብሄረ አማራ ተወላጆች ገበሬዎች ከነቤተሰቦቻቸው ነፍስ ያላወቁ ህፃናትን ጨምሮ ከደቡብ አታስፈልጉም ተብለው በጥጋብ በግፍና በእብሪት ስልጣን ላይ ባለው የወያኔ አገዛዝ ተባረው ዛሬ በአዲስ አበባና በሌሎችም ቦታዎች ሀገር እንደሌለው አውላላ ሜዳ ላይ እንዲፈሱ እየተደረገ ነው፡፡እሺ አታስፈልጉም ተብለው ይባረሩ ሌላውም ጋምቤላውም ከገዛ ቀዬው እየተፈናቀለ ነውና ነገር ግን እንዴት ለብዙ አመታት ያፈሩት አንጡራ ሀብታቸውና ንብረታቸውን እንደ ወንጀለኛ ያለምንም ተገቢ ዝግጅትና ሂደት ተነጥቀው በዶ እጃቸውን ይባረራሉ?ትናንት በኤርትራ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ላይ የደረሰው የወርቅ ጥርስ ማውለቅ ሳይበቃ ዛሬ ደግሞ በገዛ ሀገራቸው እንዴት ተመሳሳይ ነገር ይከሰታል፡፡እረ ጎበዝ ኢትዮጵያ አሁን እየተመራች ያለቸው እውን ርህራሄና ቀና ልብ ባለው በኢትዮጵያዊ ነው ወይንስ በባእድ አረመኔ ነው?አዎ ዛሬ እኛ ኢትዮጵያውያን አፋችንን ሞልተን ደረታቸውን ነፍተን ሀገር አለን ለማለት የማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡በተቃራኒው ወያኔና ጥቂት የወያኔ ጀሌዎች ከባእዳን ሃይሎች ጋር ተባብረው ሀገሪቱን በራሳቸው ቁጥጥር ስር አድርገው እንደፈለጉት እየፈነጩባትና ዝርፊያ ግፍና በደል እየፈፀሙ ነው፡፡በቃ የኢትዮጵያ ህዳሴ ይህ ነው ማለት ነው?የህዳሴ ግድባችንም ይህ አይነት ግፍና በደል እየተፈፀመ ነው የሚገነባው ማለት ነው? እረ ንቀትና እብሪት ጫፍ ላይ ደረሰ፡፡አንዱ ከገዛ ሀገሩ የእንጀራ ልጅም በላይ የእንጀራ ባሪያና ከሁለተኛ ዜጋ በታች ሆኖ ጥሪት ሀብቱ እየተዘረፈ ሲባረር ሌላው ደግሞ የሀገሪቱ ምርጥ ዘር አንደኛ ዜጋ ሆኖ አባራሪና ፈላጭ ቆራጭ ሲሆን
  ጥጋብና እርሃብ ማለት ይህ አይደለም እንዴ ታዲያ?እንዴት ነው ነገሩ ዳግም ምፅዓት መጣ ተባለ እንዴ?በዚህ ጉዳይ ላይ ገዢዎቻችንና የሃይማኖት መሪዎቻችን እኛ ያላወቅነው በሚስጥር የሰሙት ነገር ካለ ይንገሩንና እኛም እንወቀው፡፡ችግር የለም ዳግም ምፅአት እየመጣ ከሆነና በዚህም አንዳንዶች የዓለም ፍፃሜ ነውና ደስ ያለንን ነገር ሁሉ ክፉውንም ደጉንም የመሰለንን አድርገን ዘርፈን ብልተን ጠጥተን ጮቤ እረግጥን እንሙት ብለው ካሰቡ እኛ ደግሞ ይህ አይነት እብደት ፈፅሞ ምርጫችን አይደለምና የሚርበንም ቢሆን እንኳን ያለንንም ቢሆን እንሰጣቸዋለን እኛ በዚህ ችግር የለብንም ተርበንም ቢሆን ከህሊናችን ጋር ሰላም ሆነን እንሙት፡፡ነገሮች የመጨረሻው ጫፍ ላይ እየደረሱ ያለ ይመስላል፡፡ማለትም የእብሪትና የጥጋብ ጫፍ፡፡ይህ ደግሞ የጤና አይደለም ምክንያቱም አንተም እንዳልከው ከራበው ለጠገበው አዝናለሁ ምነው ቢሉ ሲዘል ይሰበራል ብዬ እንደተባለው አይነት ብቻም አይወሰንም፡፡የጠገበና የሰከረ ሰው መጠጥ ቤት ውስጥ እንዳለ ጠብ ያለሽ በዳቦ ስለሆነ ያየውን ሁሉ ነገር እየፈለገ ጭምር ያጠቃል ይጎዳል፡፡ስለዚህም የጠገበ ሰው ጉዳት በራሱ ብቻ አያቆምም፡፡በእርግጥ የራበውም በርሃብ ጠኔ ከሚሞት ከጠገበው ዘርፎ መሞትን ሊመርጥ ይችላልና፡፡ስልጣንና ገንዘብ አገዛዞችን ይህንን ያህል ይይዙት ይጨብጡት አቅል ሲያሳጣና እብደት እብሪትና ንቀት ውስጥ ሲከት በታሪክ ታይቶ አይታወቅም፡፡እንዲያው ለነገ በፈጣሪ ስም ይቅር መባባል እንጭፍጫፊም እንዳይቀር እንዲሆን ነው እንዴ የተፈለገው ማለት ነው?መልካም ታሪክን ለመስራትና ለመፃፍ ያልታደለው ያልቻለውና በዚህም ያልፈለገው ስልጣን ላይ ያለው የወያኔ አገዛዝ በተቃራኒው ያለውን የክፋት የእብሪት የጥጋብና የዝርፊያ የዘረኝነት ጫፍ ሪከርድ በመስበር በጊነስ ቡክ ለመመዝገብ ያሰበ ነው የሚመስልበት፡፡መውደቅ አይቀሬ ሲሆን እኮ እረ አወዳደቅንም ማሳመርና ለቀሪው ቀጣይ ትውልድ ማሰብም ጥሩ ነው፡፡ነገሩ ሁሉ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል እንዳለቸው አህያ በእኩይነት መንፈስ ጭምር የሚመራ ይመስላል፡፡ዳንኤል አሁን በኢትዮጵያና ኢትዮጵውያን ላይ እየመጣ ያለውን አጠቃላይ ጥፋት በቅጡ መረዳት አለብህ፡፡ዛሬ 22 ሺህ ኢትዮጵውያን በዘር ሀረጋቸው ብቻ ተመርጠው ያለምንም ቅድመ ዝግጅትና ሂደት ንብረታቸው እየተቀማ ከነበሩበት መኖሪያ ቀያቸው ሲባረኑ እና በተቃራኒው የኢትዮጵያ ለም መሬት በርካሽ ዋጋ ለባእዳን ሃይሎች ሲቸበቸብ የዚህ የመጨረሻ ትርጉም ምን ማለት ነው?አንተስ እስከዛሬ ባህልን ታሪክን ሃይማኖትን ፖለቲካን ኢኮኖሚን በሚመለከት እውቀትን ለማስተላለፍ ብለኽ በቀናነት የሰራኸው እውቀትን የመዝራት ስራ እውን ተስፋ ሰጪ እየሆነ ነውን?ሰዎች ይህንን አይነት አሳፋሪና አሳዛኝ የሆነ እኩይ ሰይጣናዊ የእብሪት የጥጋብ የንቀት የዝርፊያ ስራ እየሰሩ ያሉት እውን ብዙዎቻችን የምናስበውን ያህል ባለ እውቀትና ማስተዋል ስላነሳቸው ነውን?
  ነው ወይንስ ያንተም ‘ተረት-ተረት’ በራሱ ‘ተረት-ተረት’ ሆኖ እንደሞኝነት ተደርጎ ተቆጥሮ ተንቆ ይቀር ይሆንን?ለማንኛውም እድሜ ከሰጠን ጊዜ ሁሉንም ያሳየናል፡፡እግዚአብሄር በእንደዚህ አይነት ባለ ጥጋብና እብሪት ባለ ከሚመጣ መጥፎ የአጥፍቶ ጠፊ አይነት አወዳደቅና ጥፋት ይሰውረን፡፡

  ReplyDelete
 52. SELAME D/N please d/n danial right about pop shonuda book

  ReplyDelete
 53. እያለ የሚመሰገን ሲያልፍ የሚለቀስለት እንደ አቡነ ሺኖዳ ያለ የሀይማኖት መሪ ይገኝ ይሆን? ደ/ዳንኤል ቃለህይወት ያሰማልን፡፡ እግዚአብሄር እድሜና ጤና ይስጥህ::

  ReplyDelete
 54. thank you Dani. God Bless U

  ReplyDelete
 55. Thank you for sharing Dn. Daniel. His holiness was hero of Orthodox Church for this century. Yes I definitely learned a lot from his books and teachings more over by just seeing him the way he speaks, the way he act and the way he silent also.
  I deeply sad by his departure I was so sensitive when I noticed. Now he went to heaven to God; in the other hand I am happy he went to God that he will receive his crown before God; he accomplished and keeps God's words and thought and lead his sheep to the right path.
  Now, I'm thirsty to see a good shepherd for our church just like H.H Pope Shenouda.
  Don’t we deserve a good leader for Tewahedo? I am wondering why is not happening for us?

  ReplyDelete
 56. wow! what a big loss for our Orthodox church and our world. pope Shenouda is loved,needed,respected,and missed forever. I had a dream one day to go to egypt visit churches, monestries and his holiness if God is willing. I can see I missed to see his holiness though.

  ReplyDelete
 57. Egziabehare yistlin daniye, tebarek!! des yemil tarik new!!

  ReplyDelete