Friday, March 23, 2012

ከጎላ ወደ ዝቋላ


  
ዓለማየሁ ደንድር ከጎላ ሚካኤል በፌስ ቡክ እንደ ተረከው

የዝቋላ አቡነ /መንፈስ ቅዱስ ገዳም አባታችን አቡነ /መንፈስ ቅዱስ ብዙ ገድላትን የተጋደሉበት ጥንታዊ ገዳም መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሄ ገዳም ዙሪያውን በደን የተሸፈነ ገዳም ነው ፡፡ ሰሞኑን ታዲያ አንድ አስደንጋጭ ዜና ሰማን፡፡ የገዳሙ ደን በእሳት ተያይዞ እየነደደ እንደሆነ እና ይሄንን እሳት ተረባርበን ማስቆም ካልቻልን ብዙ ዘመናት ተጠብቆ የቆየውን ገዳማችንን በጥቂት ሰዓታት ልናጣው እንደምንችል ተነገረን፡፡
እኔ ይሄንን ዜና የሰማሁት ከሚዲያ ሳይሆን ከዲ.ዳንኤል ክብረት ብሎግ «ክተት ወደ ዝቋላ » ብሎ በጻፈልን ጽሑፍ ነው ፡፡ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ የፌስ ቡክ ገጾች በዚህ ዜና ተጥለቀለቁ፡፡
ታዲያ በሕዝበ ክርስቲያኑ ወዲያው ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተጀመረ የተደናገጠው የአዲስ አበባ ወጣት፣ ምዕመናንና የፌዴራል ፖሊስ ጉዟቸውን ወደ ገዳሙ አደረጉ ፡፡ ወደዚያው ያቀኑት ወጣቶችና ምዕመናን እሳቱን ለማጥፋት ደፋ ቀና ማለት ጀመሩ ፡፡ ብዙዎቹ በድንጋጤ ወደ ገዳሙ ይሂዱ እንጂ በቂ መሣሪያና ለራሳቸው የሚሆን ስንቅ እንኳን አልያዙም ፡፡ አሁንም የተለያዩ ብሎጎችና የፌስቡክ ገጾች ይሄንን ዜና ይዘው ወጡ ፡፡ ስንቅና ውሃ አካፋና ዶማ ተይዞ እንዲኬድ ጥሪው ተላለፈ ፡፡

ማክሰኞ መጋቢት 11- ወደ 40 የምንጠጋ የጎላ ሚካኤል አካባቢ ወጣቶችና የፍኖተብርሃን //ቤት አባላት ገዟችን ወደ ዝቋላ ለማድረግ ተነሳን ፡፡ ወደ ገዳሙ መሄድ ብቻ ሳይሆን ቀድመው ለሄዱት ወንድሞች ስንቅ ውሃ እና  እነ አካፋና ዶማ የመሣሠሉትን ይዞ መሄድ አስፋላጊ በመሆኑ ገንዘብ ማሰባሰብ ተጀመረ ፡፡ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ከጠበቅነው በላይ ገንዘብ አገኘን ለዚህም ዋነኛዎቹ በጎ አድራጊዎች ከጥቁር አንበሳ እስከ /ሃይማኖት ያሉት የመኪና መለዋወጫ ሱቆች፣ ካፌዎች እና ግለሰቦች ነበሩ ፡፡

በተገኘው ገንዘብ ምግብ ውሃና አስፈላጊ መሣሪያዎች ተይዞ ፣ከቀኑ 800 ላይ የመኪና ጉዞ ተጀመረ ፡፡ በመኪና  ጉዟችን የአዲስ አበባን ከተማ ጥለን በደብረ ዘይት በኩል ታጥፈን የአካባቢው ሰዎች ድሬ ብለው በሚጠሯት መንደር መኪናችን ሳናስበው ቆመች፡፡ ከፊት ለፊታችን እንደኛው 5 ሚኪናዎች ቆመዋል ፡፡ ከመኪናችን ወርደን ስናጣራ የኦሮሚያ ፖሊስ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ማለፍ እንደማንችል ነገረን፡፡ ከየመኪናችን ሁለት ሁለት ተወካይ ልከን ከኮማንደሩ ጋር እንዲያወሩ ቢደረግም ምንም ለውጥ ሊመጣ አልቻለም ፡፡ ማለፍ የተከለከለው 6 መኪና ወጣት ግብግብ ከመፍጠር ቀድሞ ፈጣሪን መጠየቅ ይሻላል በሚል አርቆ አሳቢነት አካባቢው ላይ በሚገኝ ሜዳ ላይ ጸሎት ተጸለየ ፡፡ ከጸሎት በኋላ አንድ ወሬ ተሰማ የአዳማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ቦታውን ለመቅረጽ ከመጡ ጋዜጠኞች ጋር ጋር እሳቱ ሳይጠፋ ጠፋ ብላችሁ በሚዲያ አስነግራችኋል በማለት በተፈጠረው ውዝግብ ላይ አንድ 4 ዓመት የኢንጅነሪንግ ተማሪ በሚሊሻ ታጣቂዎች በጥይት መመታቱ ተሰማ ፡፡ 

በዚህን ጊዜ ወጣቱ ከፍርሃት ይልቅ ምናልባት አቡዬ የጠሩን ለሰማዕትነት ሊሆን ስለሚችል ጉዟችንን በእግር ማድረግ አለብን በማለት ማታ 1200 ላይ  የእግር ጉዞውን ተያያዝነው 3 የድሬ አካባቢ ሕጻናት እንመራችኋለን ብለው ፊት ፊት በመሄድ ተባበሩን ፡፡በእርግጥ ጉዞው በጣም አድካሚና ውጣ ውረድ የበዛበት ቢሆንም የነበረው ፍቅር፣ መተሳሰብ፣ አንድነት የጉዞውን ድካማ አስረስቶናል ፡፡ 1200 ሰዓት  የጀመርነው የእግር መንገድ ከሌሊቱ 830 /830 ተጉዘን / ወደ ገዳሙ ለመድረስ ችለናል ፡፡ በዚህ አድካሚ ጉዞ ውስጥ አስገራሚው ነገር የእኛ የወጣቶች መሄድ ሳይሆን  በሌላ መኪና የነበሩት ሴቶች፣ እናቶችና፣ ማየት የተሳናቸው ጭምር የዚህ ጉዞ ተካፋይ መሆናቸው ነው ፡፡

ምንም እንኳን ሌሊት 830 ወደ ገዳሙ ብንደርስም 8 ሰዓታት በመጓዛችን  የተነሳ እሳቱ ወዳለበት ቦታ ለመሄድ አቅም አጠረን ፡፡ ከኛ ቀድሞ የሄደው ሕዝብ ግን እዛው አድሮ እሳቱን በመጠባበቅ ላይ እንደሆነ ተነገረን ፡፡ 3 ሰዓታት ያክል በገዳሙ ጊቢ በየጥጋጥጉ ተደራርበን ተኛን ፡፡

 ሌሊት 1200 ሰዓት ከእንቅልፍ በመነሳት እሳቱ ወዳለበት ቦታ አመራን፡፡ እሳቱ በደኑ ላይ ብዙ ሊባል የሚችል ጉዳት አድርሷል ፡፡ ምናልባት የሕዝቡ ርብርብና የእግዚአብሔር ረዳትነት ባይኖር ኖሮ ወደ ገዳሙም ሊሻገር ይችል ነበር ፡፡ በቦታው ስንደርስ በጣም ብዙ ወጣቶችና የፌዴራ ፖሊሶች እሳቱን በማጥፋት እና ድጋሚ ቢነሳ እንዳይዛመት የቀድሞ መከላከል ሥራውን  ተያይዘውት አገኘናቸው ፡፡ እኛም በአፋጣኝ ወደ ሥራው ተቀላቀልን እሳት ወዳለበት ቦታ በመሯሯጥ አጥፍተን ቆርጠን ወደ ሌላ ቦታ ማምራት፤ አንድ ቦታ ላይ እሳት ሲታይ  በፉጨት እየተጠራራን ሁሉ ወጣት ይዘምትበታል / ለካ ለእሳትም እሳት አለው / በዚህ ረገድ የፌዴ ፖሊስ አስተዋዕጾ ከመጠን በላይ ሊያስመሰግናቸው ይገባል ፡፡

4 ቀን ሙሉ ምግብ ሳይመገቡ  /በዛ ላይ ብዙዎቹ ጿሚዎች ናቸው / ከወጣቱ ጋር በፍቅርና በመተሳሰብ ሲሰሩ ተስተውሏ፡፡ እንደውም ከተማ ላይ ለነሱ የነበረንን የተሳሳተ አመለካከት አስቀይረውናል፡፡ እንዲህ እንዲህ እያልን እሳቱ ጠፍቷል የሚባልበት ደረጃ ላይ ደረስን ፡፡ ጠፍቷል ስንል አይነሳም ማለታችን ግን አልነበረም ሰው ላይደርስበት የሚችሉ ገደሎች ነበሩ ምናልባት ድጋሚ እንዳያስነሳ ስጋት አሳድሯል ፡፡ ምናልባት አንድ ጊዜ በሄሊኮፕተር ርምጃ ቢወሰድበት ስጋቱን ሊቀንሰው ይችላል፡፡ የእሳቱን መጥፋት ካረጋገጥን በኋላ ከፌዴራል ፖሊሶች ጋር በመሆን ወደ ገዳሙ አመራን ፡፡ በገዳሙ አዳራሽ የሚቀመሰውን ቀማምሰን ከፖሊሶቹ ጋር አዲስ አበባ ላይ ለመገናኘት ተቃጥረን  የመልስ ጉዟችንን ጀመርን ፡፡

እኛ ስንመለስ እኛን የሚተኩ ብዙ መኪኖች በመምጣት ላይ ነበሩ ፡፡ መኪናችን በባዶው እንዲመጣ  ስለተፈቀደለት ሐሙሲት ጋር ጠብቆን ወደ አዲስ አበባ ገሰገስን ስንሄድ በድንጋጤና በጭንቀት የነበረው ወጣት አሁን ፊቱ ፈክቶ መቀላለድ ጀምሯል ፡፡ ቀልድ ሲባል ደግሞ ቀልድ እንዳይመስላችሁ /ድሮስ የጎላ ልጅ አይደልን/ ፡፡ ለኔና ለአንድ ጓደኛችን በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ የሚል ስም ወጣልን /ስልካችን እንዴት እንደወደቀ ሳናውቀው ስለጠፋብን በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ - እሳቱንም ስልካችንንም አጥፍተን መምጣታችን መሆኑ ነው/፡፡

ለኛ ግን ደስታው ወደር አልነበረውም ፡፡ አንድ አካባቢ ሆነን የማንግባባ፣ የማንነጋገር ሁሉ የሚገርም ፍቅር ሸምተን መጣን ፡፡ እንደውም አንድ ጓደኛችን ሲናገር « አቡዬ   በዚህ እሳት አመካኝተው እኛን ሰብስበውናል የሌለ የሚመስለውን ፍቅር፣ የተከፋፈለ የሚመስለውን አንድነት እና ሕዝበ ክርስትያኑ ምን ያህል ለሃይማኖት እንደሚቆም ለማሳየት ፈልገው ነው » ያለውን ንግግር አልረሳውም ፡፡፣

እግዚአብሔር አምላክ ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን ፡፡ አሜን ፡፡
 

የአክብሮት ምስጋና - ለዲ.ዳንኤል ክብረት / ከሰባኪነት ወደ ጋዜጠኝነት / የአካባቢያችንን ወጣቶች እንድንነሳሳ ትልቁን ማስተባበር በብቃት ለተዋጣው ለዳዊት ለአካባቢያችን ስፔርፓርቶች፣ ለፌዴራል ፖሊሶች፣ ምንም እንኳን ክርስቲያናዊ ግዴታቸው ቢሆንም ከነሱ አልፎ ሌላውን በማነሳሳታቸው ሊበረታቱ ይገባል ፡፡ 

54 comments:

 1. እመብረሃን በአማላጅነቷ ስራችሁን ለበረከት ታድርግላችሁ፡፡

  ReplyDelete
 2. May God bless you all! I am proud of you.

  ReplyDelete
 3. ያሬድ ደበበMarch 23, 2012 at 12:04 PM

  እግዚአብሔር ለሁሉም ምክንያት አለው ፡፡ የጎላ ልጆች ያደረጋችሁትን ተጋድሎ ሳነብ እንባ እየተናነቀኝ ነው ለቤተክርስቲያናችሁ ለሃይማኖታችሁ ያላችሁን ቅንዓት በአርአያነት በመወጣታችሁ ቤተክርስቲያናችን ተቆርቋሪ ተተኪ እንዳላት መስገንዘባችሁን ቀጥሉበት እግዚአብሔር በእሳት መልክ የመጣውን ዲያብሎስ እናሸንፈው ዘንድ ብርታቱን ይስጠን፡፡

  ReplyDelete
 4. This is Christianity mean: Winning with Love & pray! enables Crossing the polices.

  I fell that this & other websites are additional guards of our Churches and Christianity; Do U think what will happen these websites do not exist/functional. Hence, Dn dani keep updating us frequently like what is happening now and we also visit yours & other websites frequently. If U take me I visit it more than five times per day,even I visit it before I slept.

  From
  Awassa

  ReplyDelete
 5. Golawoch betam kenahubachu! ezih kehager riko lale sew ejig betam kebad himemina kichit yasadiral Abuye min leyastemirun endehone giltsi new Egiziabiher And yadirigen AMEN!

  Ruth
  Siouxfalls

  ReplyDelete
 6. Hi!Daniel,ende Amlk fekad yibel yemiyasegn mima new blogs,people,...yetechawotut.AMLAKE KIDUSAN yirdan.

  ReplyDelete
 7. ዲን ዳን እግዚአብሔር ይጠብቅልን

  ReplyDelete
 8. Yegola lijoch kiristianawi andinetachiu lelelawim timihrt new EGZIABHER ayeleyachiu

  ReplyDelete
 9. You the children of Golla! thousands of others like you have participated and have succeeded in controlling the fire. Let Our God keep this love forever and make us flourish in other ways too. Let us pray for the Adama students who are shot by the police. Don't you think that we have to help those students till they become totally healthy?

  ReplyDelete
 10. Very proud of you all Alex and all of your friends.
  Yared L.

  ReplyDelete
 11. ADDISU
  GOOD JOB ALL OF YOU SPECIALLY Dn. DANIEL, I READ WITH FULL OF TEARS ON MY EYES.

  ReplyDelete
 12. DROM YEGOLA LIGOCH Egzyabhier yibarkachhu!


  Lemma Hailu

  KE GOLA

  ReplyDelete
 13. emberhan wagachune besemay tekfelachu

  ReplyDelete
 14. Yegola ligoch lebetekristian alentanetachiu betam yemiaskena ena belela akababi lalen hizbe kristianochim bihon kefitegna ar'aya lihon yemichil sira new yeserachihut! Le D.Daniel,le Federal police ena estun lematifat yebekulachihun astewatsiwo le aderegachihu hulu Egziabheramlak bedratachihun besemay yikfelachihu amen!

  ReplyDelete
 15. I have no words!!!!!!!!!!!!!!!My eyes feel on tears.Medhanialem ebakih hulema sanikefafel tewaden betekristyanachinin endintebik eredan!!

  ReplyDelete
 16. God Bless You Daniel. It is because of you we are able to read this lovely story of Golla people.God Bless Ethiopia. Together we can make the impossible possible!

  ReplyDelete
 17. MAY GOD BLESS YOU ALL !!!!!! LET OUR GOD KEEP THIS LOVE FOREVER!!!!!!

  ReplyDelete
 18. በጣም ደስ ይላል፡፡ በአባቶችሽ ቦታ ልጆች ተተኩልሽ ማለት ይህ ነው፡፡ የደስታ ሲቃ እየተናነቀኝ አነበብኩት፡፡ አምላከ ቅዱሳን ለዚህ ወጣትና ምእመን ደግ መሪ(አባት) ይስጥልን፡፡ አሜን፡፡

  አየናቸው
  ከደቡብ ኢትዮጵያ

  ReplyDelete
 19. የጎላ፡ሚካኤል፡ልጆችን፡ከልብ፡ኮራንባችሁ!እንዲህ፡ነው፡ለሃይማኖት፡
  መቆም!እንዲህ፡ነው፡ለአቡዬ፡ጻድቁ፡ገብረ፡መንፈስ፡ቅዱስ፡ገዳም፡መድረስና፡ግልጋሎት፡መስጠት!የመጣውን፡እሳት፡በመልኮታዊ፡እሳት፡መመከትና፡ፍቅርንና፡አንድነትንም፡ማቀጣጠል፡እንዲህ፡ነው!ጥንትም፡እንደኔ፡ባሉ፡አዛውንቶች፡ዘመን፡የጎላና፡የተክልዬ፡ልጆች፡የቤተ፡ክርስቲያን፡ፈጥኖ፡ደራሾች፡ነበሩ!ይህ፡ታላቅ፡ታሪካችን፡በመደገሙ፡ደስታዬን፡በእንባ፡ነው፡የምገልጸው።በርትተን፡ዋልድባን፣ደብረ፡ወገግን፡ዝቋላንና፡ሌሎቹንም፡ለጥቃት፡የተጋለጡ፡ገዳሞቻችንን፡በመጠበቅ፡በታላቁ፡የጌታ፡ፍርድ፡ቀን፡ለአባቶቻችንና፡ለአባታችን፡ለመድኃኔ፡ዓለም፡ክርስቶስ፡ማስረከብ፡አለብን!እግዚኦ፡መሐረነ፡ክርስቶስ!በእንተ፡እግዚእትነ፡ምርያም፡እግዚኦ፡መሐረነ፡ክርስቶስ!በእንተ፡ቅዱስ፡ሚካኤል፡ሊቀ፡መላእክት፡እግዚኦ፡መሐረነ፡ክርስቶስ!አሜን።

  አውሬው፡ስራውን፡መሥራት፡ጀምሯል!
  ለጥፋት፡እንዲናገርም፡የተሰጠውን፡አፍ፡ከፍቷል
  ለታላቅ፡ክርስቲያናዊ፡መስዋዕትነት፡እንዘጋጅ!

  ከጥንት፡የጎላ፡ሚካኤል፡ተማሪዎች፡አንዱ፡ነኝ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. HOW CAN WE DO THAT? I AM AND MAY BE MANY HAVE THE SAME IDEA.

   Delete
 20. Dirom Yegola lijoch yihew new. You are the first if there is a group fight or a group work. I am proud to be from Gola. I love you all. You remind me the time I spent in Finote Birhan. God Bless You all for the good work you did.

  ReplyDelete
 21. Hi Alex,
  All what u and ur friends did makes me cry. i am really proud of u guys , i wish if i were there to share the bless. plz keep use uthis amazing teamwork for some other things too, and i promiss I am in it. God bless Ethiopia
  Thxs

  ReplyDelete
 22. Egziabiher Yibarkacihu. TEBAREKU!!!!!!!!!

  Sara

  ReplyDelete
 23. i can stop my tear wow amelak kenanet gar yehun . amen

  ReplyDelete
 24. Daniel, this behavior of yours is really annoying me. You like celebrity, glorifying your work, glorifying yourself...Or is that just how you do business. This blog is not to sell yourself. Neither to promote yourself. This blog is not yours, you are just an admin. I am not here to read people's opinion about you. I am not here to follow you. I am here hoping God will teach me something to my life through you. So please, stop it.

  ke Helsinki

  ReplyDelete
  Replies
  1. @Anonymous from Helsinki
   yemitnagerewun atakim ena egziabher yikir yibelih. try to build unity and strength than saying what u fill. Negative thinkers search for fault in Heaven.

   Delete
  2. what are you trying to say?
   DN DANIEL is trying to tell us the story about what going on in ZEKUALA ABO!! ebakachehu selemedaneyalem belachu melakam neger enaseb???God help us!!

   Delete
 25. yewuseten fikir yemegeletsibet kalat binoregn benegerkuwachu!Kidus Egeziyabeher Talak yaregachu! betekerstiyanene kesat endetadegachu ke gehaneb esat yetadegachu!!
  !

  ReplyDelete
 26. እግዚአብሔር አምላክ ለሃገራችን ፍቅርና ሰላም ያምጣልን
  ይህንን እንዳናገኝ በዙሪያችን ዲያቢሎስ እያደባ ነው እሱንም
  እንድናሸንፍ እግዚአብሔር ይረዳን የአቡዬ በረከታቸው ይድረሳችሁ
  ውስጤ ከነዚህ ወጣቶች ጋር አብሬ ብሆን የሚል ቁጭት አደረብኝ

  ReplyDelete
 27. እግዚአብሔር አምላክ ለሃገራችን ፍቅርና ሰላም ያምጣልን
  ይህንን እንዳናገኝ በዙሪያችን ዲያቢሎስ እያደባ ነው እሱንም
  እንድናሸንፍ እግዚአብሔር ይረዳን የአቡዬ በረከታቸው ይድረሳችሁ
  ውስጤ ከነዚህ ወጣቶች ጋር አብሬ ብሆን የሚል ቁጭት አደረብኝ

  ReplyDelete
 28. እግዚአብሔር አምላክ ለሃገራችን ፍቅርና ሰላም ያምጣልን
  ይህንን እንዳናገኝ በዙሪያችን ዲያቢሎስ እያደባ ነው እሱንም
  እንድናሸንፍ እግዚአብሔር ይረዳን የአቡዬ በረከታቸው ይድረሳችሁ
  ውስጤ ከነዚህ ወጣቶች ጋር አብሬ ብሆን የሚል ቁጭት አደረብኝ

  ReplyDelete
 29. ቅዱስ ሚካኤል እሳቱን አጠፋው፡፡

  ReplyDelete
 30. ደስ ይላል በቦታው ብኖርም የጎላ ልጆች እንዳላችሁ አላወቁም ነበር። ጎላዎች ደስ ይበላችሁ እናንተ ከመምጣታችሁ በፊት የዑራኤል ፡ የገርጂ ፡ የአዳማ ፡ የደብረ ዘይት የደጆችሽ አይዘጉ ፡ የማኅበረ ቅዱሳን ሌሎችም ወጣቶች ወንድሞች በጋራ የሚያደርጉትን ርብርብ ሳይ አልቅስ አልቅስ ነው ያለኝ (የደስታ)። እንዲሁም በግጭቱ ሰዓት በቦታው ነበርኩ። በጣም አዝኛለሁ፡ ዓይኔ አያየ ጥይቶች ወደ ሰማይ ተተኩሰዋል(በፖሊሶች) ወጣቶች ጥይት ሲተኮስ መተኛት ሲገባቸው ልበሳቸውን እያወለቁ መሕተማቸውን ወደላይ ይዘው ግማሹ እያለቀሰ (ወይኔ ቤተክርስቲያን አያል)ወደጥይቱ ሲሄዱ ሳይ የማየው ነገር ህልም እንጂ እውን አለመሰለኝም ነበር። እግዚአብሔር ግን ክፉ እንዲፈጸም አልፈለገም ያለምንም ገላጋይ ሁኔታው ቆመ። የሚገርመው የወንደማችን መመታት የተሰማው ከ1 ወይም ከ2 ደቂቃ በኋላ ነው(የእግዚአብሔርን ድንቅ ስራ እዩ በወቅቱ ፖሊሶቹም ሆነ ታጣቂዎቹ አልነበሩም የባሰ ችግር ይፈጠር ነበርና)። በጣም የገረመኝ የተመታው ወንድማችን ደሙ እየፈሰሰ ሰዉ ሲያለቅስ ደህና ነኝ በማለት ያጽናና ነበር። ቀልጣፋ ወንድሞች ተረባርበው ቁስሉን በጨርቅ አስረው ይዘውት ሄደዋል። የቀረነውንም በጣም ጠንካራ የሆኑ ወንድሞች አበረታተው፡ በዚህ ምክንያት ዓላማችን መገታት የለበትም በማለት ወደ ስራችን እንድንመለስ አድርገውናል። ይሄም ነበር ልበላችሁ ብዬ ነው።

  ከእርሱ ጋር ሲሆኑ የማይታለፍ የለም! ቅዱሳንስ ይሄን አይደል በሕይወታቸው የሰበኩን!

  ዲ.ዳንኤል በጣም አመሰግናለሁ(ስለ መረጃው)!

  ReplyDelete
 31. I have on words, just only Thanks be to the Almighty.

  ReplyDelete
 32. Wow! it is just unthinkable. You young Gola boys we are proud of you. We didn't now Gods call, this maigt be the time for unity Please let us pray not only for the fire, in which by you we able to extingush but also for all the wrond deeds that are don by those who are playing at the province of our wholly church. "MAY GOD BLESS ETHIOPIA AND ITS PEOPLE FOREVER. AMEN!"

  ReplyDelete
 33. ምግባር ከሃይማኖት ጋር ማለት ይሄ ነው፡፡ ይህ እሳት እግዚአብሄር እንድንፀድቅበት ያዘጋጀልን ፈተና ይሆን አንዴ? ከሆነም ፈተናውን አልፈናል፡፡ እግዚአብሄር ይመስገን! ይህን ጥንካሬያችንንና አንድነታችንን አያሳጣን

  ReplyDelete
 34. our church get incredible Sons thanks almayete God
  maki

  ReplyDelete
 35. ምንም እንኳን የቦታ ርቀት ገድቦኝ ለዚህ በረከት ባልታደልም እንዲህ ያለውን ክርስቲያናዊ ፍቅር ሲገለጥ በማየቴ መድኃኔዓለም ክብር ምስጋና ይግባው።

  ReplyDelete
 36. በ 1970ዎቹ በየዩኒቨርሰቲዉ የክህደት እሳት ተስፋፍቶ በነበረበት ወቅት እግዚኣብሔር ባወቀ የዉትድርና እንቅስቃሴ በማስነሳት ወጣቶቹን (በኣሁኑ ወቅት ታላላቅ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችንን)በቤተክርስቲያን ዙርያ እንዲሰባበሱ እነዲሁም የቁርጥ ቀን ሆነዉ እንዲንቀሳቀሱ ኣድርጓል። ወዳጆቼ ይህ ኣጋጣሚስ ኣንድነታችን ፍቅራችን እዉነተኛ ኣላማችን የገለፅንበት ኣጋጣሚ ኣይደለም ትላላችሁ? የወጣቱ መሰባሰብ ከ እዉነተኛ ቀናኢነት፤ ሃይማኖተኛነት እና አገር ወዳድነት የመነጨ እንጂ ኣደናጋሪዎች እነደሚሉት ሌላ ዓላማ የሌለን መሆኑን ለሁሉም ወገኖች ግልፅ ኣድርጋችኋል እና እግዚኣብሔር ይባርካችሁ።
  ገብረሂወት ከሰሜን ኢትዮጵያ

  ReplyDelete
 37. በሥራ አጥነት የሚሰቃዩት እንደዚህ ለአገራቸውና ለወገናቸው ብዙ ማድረግ የሚችሉ ብሩኅ አእምሮ ያላቸው ወጣቶች መሆናቸውን ሳስብ እጅጉን አዝናለሁ። የዘገዬ ቢመስልም ሁኔታውንም የሚቀይሩት በእግዚአብሔር ፈቃድ እነሱው ናቸው።

  ReplyDelete
 38. yes yegolye lijoch I'm PROUD OF YOU !!!BETAM
  EWEDACHEHUALEW WEDEDEDEDEDDDDDD BEKA!!!!!!!

  ASRAT EYOB FROM MARYLAND

  ReplyDelete
 39. take me back to my curch GOLA MICHAEL..so many
  memory so many God bless our curch!! good job!
  EPH. USA

  ReplyDelete
 40. I have no word to say about GOLA MICHeil .since I was a kid I start going to curch and sundy school, which calls FINOTE-BEREHAN and I used to be {TADAGI KIFEL}
  I can say so many things about this curch but... you did good job and God bless you
  more and more!!
  YEBERAL BE KINFU MELJAWEM FETAN NEW
  YAMELAK SEM YALEBET SEMU MICHAEL NEW
  YASADEGEN MELAK ZAREM KENA GARE NEW ...
  JUST CRYING..SOORY
  USA

  ReplyDelete
 41. Egziabher yewtatenet zemnachun yebark

  ReplyDelete
 42. መልካም ዜና የሚናገሩ እግሮቻቸው እንደ ከዋክብት ያበራሉ፡፡ አሌክስዬ ያሳድግህ በትህትናና በታዛዥነት ያኑርህ፡፡አሜን፡፡

  ReplyDelete
 43. ሳሚ (ወ/ሚካኤል)March 26, 2012 at 6:23 PM

  ገዳማችንን በጥቂት ሰዓታት ልናጣው እንደምንችል ተነገረን፡፡
  እኔ ይሄንን ዜና የሰማሁት ከሚዲያ ሳይሆን ከዲ.ዳንኤል ክብረት ብሎግ «ክተት ወደ ዝቋላ » ብሎ በጻፈልን ጽሑፍ ነው ፡፡
  ህህህህህህ.....እኔም ይህንን የጀግና ልጅ ትረካ ከዲ.ዳንኤል ክብረት ብሎግ ለመጀመሪ ጊዜ አነበብኩት!.....ከትረካወ ገራሚ እይታዎች.......
  1 ለካ ለእሳትም እሳት አለው (ልክ ነው! እሾህን በሾህ ይባል የለ)
  2በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ፡- እሳቱንም ስልካችንንም አጥፍተን በመምጣታችን
  3አቡዬ በዚህ እሳት አመካኝተው እኛን ሰብስበውናል ፤ የሌለ የሚመስለውን ፍቅር፣ የተከፋፈለ የሚመስለውን አንድነት እና ሕዝበ ክርስትያኑ ምን ያህል ለሃይማኖት እንደሚቆም ለማሳየት ፈልገው ነው
  4በዚህ ረገድ የፌዴራል ፖሊስ አስተዋዕጾ ከመጠን በላይ ሊያስመሰግናቸው ይገባል ፡፡
  ቀን ሙሉ ምግብ ሳይመገቡ /በዛ ላይ ብዙዎቹ ጿሚዎች ናቸው / ከወጣቱ ጋር በፍቅርና በመተሳሰብ ሲሰሩ ተስተውሏ፡፡ እንደውም ከተማ ላይ ለነሱ የነበረንን የተሳሳተ አመለካከት አስቀይረውናል፡
  በእለቱ በጻድቁ አባት የምለጃ መዝገብ ስለ እግዚአብሄር በረከት ከተጻፉት(ተራኪወ የአክብሮት ምስጋና ሲል ካከበራቸው) በጥቂቱ...
  ለዲ.ዳንኤል ክብረት / ከሰባኪነት ወደ ጋዜጠኝነት /፣ የአካባቢያችንን ወጣቶች እንድንነሳሳ ትልቁን ማስተባበር በብቃት ለተዋጣው ለዳዊት ፣ ለአካባቢያችን ስፔርፓርቶች፣ ለፌዴራል ፖሊሶች፣
  ይትባረክ እግዚአብሄር አምላክ አበዊነ !!!! እረኛው የረሳውን በረት በመንጋዎቹ የማስጠበቅ ጥበብ ከእግዚአብሄር ብቻ ነው!!! ዕንኩዋን ወንድሞቸ የሆናችሁ! ይቅርታ የተጻፈን የሚደግሙትን የምቃወም ብሆንም ይህን ላለምድገም ግን ምክንያትና ወኔ አጥቸ ነው!!!!

  ReplyDelete
 44. I have a lot to say about Yegola lijoch. But I will leave it for now. I wish people from Gola Sunday school can meet in US. I was in tadagi kifil. I know most of "Tadagi kifil" came to US and "wetatoch kifil" went to become a police officers. Isn't it? So many memories come to my mind. God bless you all. I am happy you did your part in protecting our church. Thank you.

  ReplyDelete
 45. ተመስገን፡፡ ተመስገን፡፡ ተመስገን፡፡ እኔም በቦታው መሄድ ባልችልም ቅዱስ ሚካኤል እስራኤልን ከጸሀይ ቃጠሎ በደመና እንደጋረድካቸው እኛንም ተራዳን፤ እሳቱን አጥፋልን ብይ ተስዪ ነበር፡፡ ስለቴን ሰምቶኛል፡፡ ደስ ብሎኛል፡፡ ለበጎ ነው፡፡ እኔን ስለቤተክርስቲያን ደህንነት መጸለይ እንዳለብኝ አስተምሮኛል፡፡ ያላሳፈረን እግዚአብሔር፤ ቅድስት ድንግል እናታችን ወላዲተ አምላክ ምስጋና ይድረሳት፡፡ አሜን

  ReplyDelete
 46. G/Eyesus Ke ChicagoMarch 27, 2012 at 7:59 AM

  Golawoch Bereketachihu yideresen!!!
  Endih new hayimanot kesira gar sitebaber...
  Bertu ketelubet seyitanum yifer,,,

  ReplyDelete
 47. yegolye lijoch yeregetubet
  enkuan beremetad yetefal esat!!

  ReplyDelete
 48. I AM HAPPY TO READ ABOUT THE GOLA MICHAEL GROUP TRAVEL TO ZIQUALA. WE NEED SUCH A TROOP WHICH SHOULD BE FINANCED TO MAKE SUCH A TRIP WHEN EVER NECESSARY. SOMETIMES THE OBSTACLE ON THE WAY MAY BE SO POWERFUL; HOWEVER, IT SHOULD BE CHALLENGED WHEN IT IS A MUST TO DO SO.

  ReplyDelete