ማታ በተደረገው ርብርብ እሳቱ ተግ ብሎ አደረ፡፡ ታድያ ምን ያደርጋል፡፡ አበው ሰው በመንገዱ ነው የሚፈተነው ይላሉ፡፡ መነኮሳቱ ለጸሎት ሌሊት እንደሚነሡ የሚያውቅ ሰይጣን እሳቱንም ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ቀሰቀሰው፡፡ እነሆ በገዳሙ የሚገኙ መነኮሳት እና ወጣቶች አሁን በመከላከል ሥራ ላይ ተጠምደው ይገኛሉ፡፡ አሁንም እሳቱ ከአየር ላይ የሚጠፋበትን መንገድ ለመፈለግ ጥረት መደረግ አለበት፡፡
በተለይም ወደ ገዳሙ ለርዳታ የምትጓዙ ምእመናን የውኃ ማመላለሻዎችን፣ መቆፈር ያዎቸን፣ አካፋዎችን እና ሌሎች የርዳታ መሣርያዎችን ይዛችሁ እንድትሄዱ ትጠየቃላችሁ፡፡ እዚያ ቦታ ላይ ሌሊት እና ቀን በድካም ላይ ለሚገኙ ወገኖቻችንም የውኃ እና የምግብ ርዳታ በመውሰድ የበኩላችሁን ድጋፍ ታደርጉ ዘንድ የአደጋ ተከላካዮቹ ጠይቀዋል፡፡
የቸርነት አምላክ የፍጥረታት ሁሉ ጌታ በደላችንን ይቅር ብሎ ይህንን አደጋ ያርቅልን ዘንድ በያለንበት እንፀልይ በቅርብ ያለንም እንዲሁም የቻልን በሁሉም አማራጭ የበኩላችንን እናድርግ፡፡ ወንድማችን ዲያቆን ዳንኤል ለምታደርሰን ወቅታዊ መረጃ እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡
ReplyDeleteተካ ቸርነት፡
dani thank you for all.you are the onliy way to attend the current situation.so dont sleep we wait you.
ReplyDelete