Sunday, March 18, 2012

«ውልድብና» እና «ኢውልድብና»


ኢትዮጵያ ካሏት ጥንታዊ፣ ታሪካዊ እና ሃይማኖታዊ ቦታዎች ዋልድባ አንዱ ብቻ ሳይሆን ዋነኛው ነው፡፡ በሰሜን ጎንደር እና በምዕራብ ትግራይ ተንጣልሎ፣ ከሰሜን ተራራዎች ሠንሠለት ግርጌ ተዘርግቶ የሚገኘው ይህ ገዳም፣ በብዙ ወጣ ገባ መልክዐ ምድሮች እና ኮረብታዎች የተሞላ፣ አብዛኛውም በደን የተሸፈነ ነው፡፡ እንደ ኤዶም ገነት አራት ጅረቶች የሚያጠጡት ሲሆን ሴሞ በሰሜን፣ ተከዜ በምሥራቅ፣ ዘወረግ በምዕራብ፣ ዜዋ ደግሞ በደቡብ ያረሰርሱታል፡፡
የዋልድባ ገዳም ታሪክ ሳብ ብሎ ወደ መጀመርያው የክርስትና ዘመናት ይጓዛል፡፡ 5ኛው መክዘ በአካባቢው በተባሕትዎ ይኖሩ የነበሩ መናንያን እንደነበሩበት መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ 485 ዓም ከሰሜን ሸዋ የተነሡ ምእመናን ወደ አካባቢው ተጉዘው መጋቢት 27 ቀን ዋልድባ መግባታቸውን የቦታው ታሪክ ያሳያል፡፡ 574 ደግሞ ሌሎች ከቡልጋ መጥተው ተቀላቅለዋቸዋል፡፡
 በዘመነ ዮዲት ቦታው ከጠፋ በኋላ እንዲሁ ሲኖር አሁንም ለሦስተኛ ጊዜ ከሰሜን ሸዋ ቡልጋ የመጡ ክርስቲያኖች አንሥተውት ነበር፡፡ በኋላ ግን በንጉሥ አግብዐ ጽዮን ዘመን (1278 - 1286 ዓም) ለጊዜው ባልታወቀ በምክንያት ገዳሙ ጠፍ ሆነ፡፡ ዋልድባ እንደገና የቀናው እና በኢትዮጵያ ቤተ ክርስ ቲያን ታሪክ ውስጥ ልዩ ቦታ የያዘው በንጉሥ ዓምደ ጽዮን ዘመነ መንግሥት በተነሡት በአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ነው፡፡
1319 አካባቢ ከደብረ ሊባኖስ የተንቀሳቀሰ አንድ የመነኮሳት ቡድን (አባ ሙሴ፣ አባ እስጢፋኖስ፣ አባ ገብረ መስቀል እና አባ ገብረ ክርስቶስ) ዋልድባ በመግባት ሥርዓተ ገዳሙን አጽንተውታል፡፡ በገዳሙ እህል መመገብ የቀረው ከእነርሱ መምጣት በኋላ መሆኑ ይነገራል፡፡ የዚህ ሃሳብ አመንጭም አባ ሙሴ መሆናቸውን የገዳሙ ታሪክ ያትታል፡፡ እነዚህ መነኮሳትም የእርሳቸውን ሃሳብ በመቀበል የገዳሙ ምግብ ቋርፍ እንዲሆን ወሰኑ፡፡ በገዳሙ እህል የሚበላው ለልደት፣ ለትንሣኤ እና ለካህናተ ሰማይ በዓል ብቻ እንዲሆንም ደነገጉ፡፡
በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት (1426-1440 ዓም) የዋልድባ ገዳም ክልል በአራቱ ወንዞች መካከል እንዲሆን ዐዋጅ ተደንግጎ ነበር፡፡ ዐዋጁ ማንኛውም የሀገር ገዥ እና አራሽ ወደ ክልሉ ገብቶ ምንም ዓይነት ሥራ እንዳይሠራ የሚከለክል ነበር፡፡
የዋልድባ ገዳም እስከ ግራኝ ወረራ ጊዜ ቆይቶ በመከራው ሰዓት ጠፍ ለመሆን ደርሶ ነበር፡፡ በኋላ ግን ከወረራው የተረፉ መነኮሳት ተሰባስበው እንደገና አቀኑት፡፡ በመካከልም እየጠፋ እየቀና ለብዙ ዘመናት ኖረ፡፡ በተለይም በዘመነ መሳፍንት በነበረው የእምነት ክርክር የዋልድባ መነኮሳት ዋነኛ ተሳታፊዎች ነበሩ፡፡
 የዋልድባ ገዳም ቦታ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ       
የዋልድባ ገዳም በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ልዩ ቦታ ካላቸው ገዳማት አንዱ ነው፡፡
 1. በረዥም ታሪኩ፡- የዋልድባ ገዳም ከአንድ ዘመን በላይ የተሻገረ ታሪክ ያለው ገዳም ነው፡፡ በዚህም ከተሰዓቱ ቅዱሳን እና ከደብረ ሊባኖስ ታሪክ ጋር የሚተካከል ታሪክ አለው፡፡ የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን የረዥም ዘመን ታሪክ ለማጥናት ሕያው ከሆኑት ምስክሮች መካከል የዋልድባ ገዳም አንዱ ነው፡፡ በጥንታዊው የክርስትና ዘመን፣ በመካከለኛው ዘመን፣ በዘመነ መሳፍንት እና በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ የታሪክ ምዕራፎች ውስጥ የተሻገረ በመሆኑ ማን ይናገር የሚለውን የሚያሟላ ነው፡፡
 2. እመቤታችን በኪደተ እግሯ ከባረከቻቸው ቦታዎች አንዱ መሆኑ፡ የዋልድባ ገዳም እመቤታችን ወደኢትዮጵያ በስደቷ ጊዜ መጥታ በኪደተ እግሯ ከባረከቻቸው እና ጌታችን በሕፃንነቱ ትንቢት ከተናገረላቸው ቦታዎች አንዱ ነው፡፡
 3. ከሌሎች ቦታዎች አያሌ ቅዱሳን የሚጎበኙት ቦታ ነው፡ የዋልድባ ገዳምን ለመሳለም አያሌ ቅዱሳን ወደ ቦታው ይመጣሉ፡፡ በታሪክ እንኳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስ ሦስት ጊዜ ወደ ቦታው መጥተው ተሳልመውታል፡፡ ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም አባ ጊዮርጊስ ወደ ገዳሙ መምጣቱን ይተርካል፡፡ ኢየሩሳሌምን ለመሳለም የተጓዙ ኢትዮጵያውያን መናንያን እና ቅዱሳን ሁሉ በዋልድባ ገዳም አልፈው፣ ተሳልመው እና ተባርከው፣ በሱዳን በኩል ያልፉ ነበር፡፡
 4. በጥንታዊ ቅርሶቹ፡- የዋልድባ ገዳም ከሺ ዓመታት በላይ ያጠራቀማቸው የሀገሪቱን እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ቅርሶች ጠብቆ እና አቅፎ የያዘ ገዳም ነው፡፡ በተለያዩ ዘመናት ገዳሙ ሲፈታ እንኳን በአካባቢው በሚገኙ የተፈጥሮ መከለያዎች ውስጥ ቅርሶቹን እያስቀመጡ በማትረፍ አቆይተውልናል፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከሚገኙ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገድላት መካከል አንዱ የዋልድባው ገድለ ተክለ ሃይማኖት ነው፡፡
 5. በልዩ የምናኔ አኗኗሩ፡- የዋልዳባ ገዳም ጥንታዊውን የነእንጦንስን የምናኔ ሕይወት ጠብቆ የኖረ፣ከቋርፍ በቀር የላመ የጣመ የማይበላበት፣ መናንያን ከአራዊት ጋር የሚኖሩበት፣ የጽሞና ቦታ ነው፡፡ አንዳንድ መናንያንም ከብቃት ሲደርሱ ማኅበሩን አስፈቅደው የተባሕትዎ ሕይወትን በመያዝ በዱር በገደሉ እንደወደቁ ይቀራሉ፡፡ በገዳሙ ጫካዎች የተዘዋወሩ እንደሚገልጡት በቁም ጸሎት ላይ እንዳሉ ያረፉ አበው ባረፉበት ቦታ ቆመው ለብዙ ዘመናት በመቆየታቸው፣ በአካባቢው ለሚዘዋወሩ ሌሎች መናንያን ያሉ መስለው ይታያሉ፡፡
 6. በቦታው አቀማመጥ፡- የዋልድባ ገዳም በሁለት ክልሎች ውስጥ የሚገኝ ሰፊ ገዳም ነው፡፡ በአራት ወንዞች ተከልሎ በአያሌ አጥቢያዎች የተዋቀረ አንድ አውራጃ የሚያህል ገዳም፡፡
 7. በትምህርት ቤቱ፡- የዋልድባ ገዳም አያሌ ሊቃውንትን ያፈሩ የአብነት /ቤቶች ቦታ ነው፡፡ መናንያኑ ከምናኔያዊ ሕይወት በተጨማሪ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርቶች በገዳሙ ይማራሉ፡፡
 8. ብዙ አበውን ያፈራ ነው፡- የዋልድባ ገዳም ለቤተ ክርስቲያን ታላላቅ አስተዋጽዖ ያደረጉ ብዙ አባቶችን ያፈራ ገዳም ነው፡፡ በየአጥቢያው ከሚገኙ መነኮሳት መካከል ቢያንስ አንድ የዋልድባ መነኩሴ አይጠፋም ይባላል፡፡ የዋልድባ መነኮሳት በግብጽ፣ በኢየሩሳሌም፣ በአውሮፓ­ እና በአሜሪካ ለአገልግሎት ተሠማርተዋል፡፡ ይህም የገዳሙን ሁለገብ አስተዋጽዖ ያመለክታል፡፡
 9. ዋልድባ በኢትዮጵያ ውስጥ ነባር ደኖች ከሚገኙበት የምናኔ ቦታዎች አንዱ ነው፡፡ የዋልድባ ደን አንድ አውራጃ የሚያክል እና በሀገር በቀል ዛፎች የተሞላ፣ የአራዊት እና የአዕዋፍ ማደርያ የሆነ ቦታ ነው፡፡ ዛሬ ለአካባቢ ጥበቃ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ ገበሬውን ሁሉ በአካባቢ ጥበቃ ተግባር በማሳተፍ ላይ ባለበት ጊዜ የዋልድባን ጥብቅ የግዝት ደን ክልል ማረስ የሚጋጭ ተግባር ይሆናል፡፡ ኢትዮጵያ በዓለም ዐቀፍ መድረኮች ድምጽዋን ከፍ አድርጋ እየተከራ ከረችባቸው ከሚገኙ ጉዳዮች አንዱ የአረንጓዴ ልማት ጉዳይ ነው፡፡ ይህ አስተሳሰብ እንኳንስ ነባር ደኖችን መንካት ሊፈቅድ አዳዲስ የዛፍ ቦታዎችንም ጥበቃ እንዲደረግላቸው የሚሟገት ነው፡፡
የዋልድባ ይዞታ ከሥነ ምሕዳር አንፃር ሲታይ የሀገሪቱ አንዱ የመተንፈሻ ሳንባዋ ነው ያሰኛል፡፡
የዋልድባ ሰሞነኛ ነገር
ዋልድባ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰሞነኛ ጉዳይ እንዲሆን ያደረገው በአካባቢው የስኳር እርሻ እና ፋብሪካ ይከፈታል መባሉ ነው፡፡ ይህንን ተከትሎ የገዳሙ መነኮሳት እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የደረሰ አቤቱታ ያሰሙ ሲሆን ሕዝቡም ሁኔታውን መወያያ አድርጎታል፡፡ አካባቢውን በቅርብ ከጎበኙ አካላት እንደ ተገኘው መረጃ ከሆነ በአካባቢው የስኳር ኢንዱስትሪ ለማቋቋም መንግሥት እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡ በዚህ እንቅስቃሴውም እህል አይግባብሽ፣ ዘር አይዘራብሽ ተብሎ ከተከለለው የገዳሙ ክልል 2.5 ኪሎ ሜትር ዘልቆ ለመንገድ የሚሆን ቦታ አርሷል፡፡ ገዳማውያኑ እና የአካባቢው ምእመናን በጋራ የሚጠቀሙባቸው አራት አብያተ ክርስቲያናት ማለትም
·         ማየ ሕርገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ (የሴቶች ገዳም)
·         ዕጣኖ ቅድስት ማርያም (የገዳሙ እህል ቤት)
·         ደላስ ቆቃ አቡነ አረጋዊ እና
·         ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ናቸው
መንግሥት እንደሚለው እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት መነሣታቸው የማይቀር ሲሆን ለዚህም ካሣ እንደ ሚከፍል ገልጧል፡፡
  የአካባቢው ምእመናን የዋልድባን ቅዱስ አፈር በመሻት ቀብራቸውን በገዳሙ ማድረጋቸው የተለመደ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜም ወደ ክልሉ ሳይደርሱ የዛሬማን እና የአንሽያን ወንዞች ተሻግረው የሚቀብሩ አሉ፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች አካባቢው ሲታረስ 27 ዐጽሞች ተገኝተዋል፡፡ በገዳሙ ክልልም ተቀብረዋል፡፡ ወደፊትም በቀጣይ ሥራ ሌሎች ሊገኙ እንደሚችሉ ይገመታል፡፡
በአካባቢው የሚገኘው ነዋሪ ሲገለገልባቸው የነበሩ 14 የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ይነሣሉ፡፡ የአካባቢው ሕዝብ ወደ ሌላ ቦታ ሄዶ የሚሠፍርበት አሥራ አንድ መንደሮች ተመቻችተዋል፡፡ እነዚህን የተነሡትን የገጠር አብያተ ክርስቲያናት በአዲሶቹ የሠፈራ ቦታዎች እንደሚገነባ መንግሥት ተናግሯል፡፡
እጅግ አከራካሪ የሆነው አባ ነጻ የሚባለው እና በገዳሙ የግዝት ክልል የሚገኘው ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ አቡነ ተስፋ ሐዋርያትን ጨምሮ አያሌ ቅዱሳን ዐጽም ያረፈበት ይህ ቤተ ክርስቲያን በግዝት ክልሉ ውስጥ በመሆኑ አይነሣም፡፡ ነገር ግን የግድቡ ውኃ ወደ አካባቢው ስለሚደርስ የገዳሙን ሕልውና ሊያሠጋው እንደሚችል ገዳማውያኑ ተናግረዋል፡፡ የመንግሥት አካላት የግድቡ ግንባታ ገዳሙን እንዳ ይነካው ተደርጎ ሊሠራ እንደሚችል ቢገልጡም ገዳማውያኑ ግን ሥጋታቸውን የሚቀርፍ ነገር ባለ ማግኘታቸው አልተቀበሉትም፡፡
በአደርቃይ በኩል ያለውን የገዳሙን ክልል ­ርክነት ለመከለል የቀረበው ዕቅድ በገዳማውያኑ ተቀባይነት ባለማግኘቱ መሠረዙን ምንጮች ገልጠውልናል፡፡
የዋልድባ ጉዳይ ለምን ይህንን ያህል መነጋገርያ ሆነ?
ዋልድባ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዓይነተኛ ገዳም ነው፡፡ የዋልድባ ገዳም እንኳን በቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች ቀርቶ በምእመናንም ዘንድ የሚታወቅ እና የሚጠበቅ ገዳም ነው፡፡ «አልፎ አልፎ በዋልድባም ይዘፈናል»«ላወቀባት ገረገራም ዋልድባ ናት» የሚባለው አባባል ዋልድባ ገዳም ለሥነ ቃል የበቃ የሕዝብ ገዳም መሆኑን ያሳያል፡፡ የዋልድባ መነጋገርያ መሆን ገዳሙ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ያለውን ታላቅ ቦታ አመላካች ነው፡፡
የሰሞኑ ትኩሳት መመርያን እንጂ መረጃን መሠረት የማያደርገው አሠራራችን ያመጣውም ችግር ነው፡፡ መቼም አንድ የስኳር ኢንዱስትሪ እንደ ታዴዎስ እርሻ በአንድ ቀን ታስቦ በአንድ ቀን አይጀመርም፡፡ የብዙ ጊዜ ዕቅድ እና ፕሮጀክት ውጤት ነው፡፡ በዚህ ጥናት ውስጥ ሊካተቱ ከሚገባቸው ጉዳዮች አንዱ የፕሮጀክቱ አካባቢያዊ ተቀባይነት ነው፡፡ በዚያ አካባቢ የሚኖሩ ነባር ነዋሪዎች ፕሮጀክቱ በእነርሱ ላይ ስለሚያመጣው ጉዳትም ይሁን ስለሚሰጠው ጥቅም ማወቅ፣መወያየት፣ሃሳብ ማቅረብ እና መሰማትም አለባቸው፡፡
እንኳንና የአካባቢው ሰዎች ሌላውም ግብር ከፋይ ዜጋ ቢሆን በእርሱ ግብር ስለሚሠራው ሥራ በዝርዝር ማወቅ ያስፈልገዋል፡፡
ዋልድባ አካባቢ በሚሠራው ሥራ ይህ የሆነ አይመስለኝም፡፡ መመርያው ተግባራዊ መሆኑን እንጂ መረጃው ሕዝቡ ዘንድ ደርሶ በጎ ምላሽ መግኘት አለማግኘቱን ያየው አካል የለም፡፡ ዋልድባ ገዳም ነው፣ በሀገሪቱ ታሪክ የማይተካ ሚና የነበረው ገዳም ነው፣ አያሌ አባቶችን አፍርቶ ያሠማራ ገዳም ነው፡፡ አብ ሲነካ ወልድ ይነካ እንደሚባለው ዋልድባ ሲነካ አብረው የሚነኩ ብዙ አካላት አሉ፡፡ ይህ እየታወቀ እንዲሁ በድፍረት ወደ ሥራው መገባቱ እስከመቼውም የማያባራ ችግር ለገዳሙም ለሚጀመረው ኢንዱስ ትሪም መፍጠር ነው፡፡
ስኳሩን እንደሚፈልጉት፣ በስኳሩ ኢንዱስትሪ ተቀጥረው እንደሚሠሩት የሀገሪቱ ዜጎች ሁሉ የገዳሙ መናንያንም የዚህች ሀገር ዜጎች ናቸው፡፡ በሀገሪቱ ሂደት የመጠቀም እንጂ ያለ መጎዳት መብት ያላቸው ዜጎች፡፡ የሚጎዱት ጉዳት እንኳን ቢኖር አምነውበት፣ ተቀብለውት፣ መሥዋዕትነት ለመክፈል ወስነውበት፣ ከዚያም በላይ ደግሞ ያሥምረው ብለው አቡነ ዘበሰማያት ደግመውበት መደረግ አለበት፡፡ ይህ አለ መሆኑን በቀላሉ ከሚያሳዩን ነገሮች አንዱ ወደ ግዝቱ የገዳሙ ክልል ሁለት ኪሎ ሜትር ተኩል ከራ ከመንግሥት ዕቅድ እንኳን በተቃራኒው ተገብቶ መታረሱ ነው፡፡
የዋልድባ ገዳም መነጋገርያ ከሆነ በኋላ እንኳን የሚመለከታቸው አካላት (ቤተ ክህነት እና መንግሥት) ለሕዝብ መረጃ ሲሰጡ አልታዩም፡፡ ሁሉም ነገር የሚሰማው በሹክሹክታ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሐሜት እንደ ባህል ለተያዘበት ማኅበረሰብ ያልተገባ ሥጋት እና ጭንቀት መፍጠሩ የማይቀር ነው፡፡ ዛሬ ዛሬ መንግሥታት ማኅበራዊ የመረጃ መረቦችን እየተጠቀሙ የዕለት ተዕለት ጉዳዮችን ለሕዝባቸው መንገር በጀመሩበት ዘመን ብሔራዊ የሚዲያ ተቋማት እንኳን ነገሩን ዝም ማለት አልነበረባቸውም፡፡
ሌላው ችግር ደግሞ ነገሮችን አጣጥሞ ያለ መጓዝ ችግር ነው፡፡ ኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ እና የግብርና ልማት ያስፈልጋታል፡፡ ሌላም ልማት ያስፈልጋታል፡፡ ነገር ግን ዕድገታችን አንዱን ገድሎ በሌላው መቃብር ላይ የሚቆም መሆን የለበትም፡፡ 90 በመቶ የኢትዮጵያ ሕዝብ በላይ ሃይማኖተኛ መሆኑን በሕዝብ ቆጠራዎች ላይ አሳይቷል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ የሃይማኖት ጉዳይ የሀገሪቱ ዋና ጉዳይ ነው ማለት ነው፡፡ የምንጓዘው ጉዞም ይህንን የሀገሪቱን ዋና ጉዳይ ከግምት ያስገባ መሆን አለበት፡፡
የኢትዮጵያ ዕድገት ከታሪኳ፣ ባህልዋ፣ ሃይማኖቷ እና ቅርሷ ጋር የተጣጣመ መሆን አለበት፡፡ አዲስ ሕንፃ ለመሥራት ብለን ላሊበላን ማፍረስ ወይንም አኩስምን መጣል የለብንም፡፡ አዲስ ደን የምንተክለው የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብን የሱጳ ደን ነቅለን በምናገኘው ሜዳ ላይ መሆን የለበትም፡፡ ነባር እሴቶቻችን ከአዳዲስ እሴቶቻችን ጋር የሚጣጣሙበትን ወይንም አብረው የሚጓዙበትን መንገድ መፈለግ ነው ዋናው ሥራችን፡፡
በዋልድባ አካባቢ የልማት ሥራ ለመሥራት መነሣቱ አይደለም ችግሩ፡፡ ከልማት ሥራው በፊት የዋልድባ ገዳም ይቀድማል፡፡ ቢያንስ 1000 ዓመት ይቀድማል፡፡ የልማቱ ሥራ ከዋልድባ ገዳም ጋር መጣጣም አለበት እንጂ፣ የዋልድባ ገዳም ከልማት ሥራው ጋር እንዲጣጣም መጠየቅ የለበትም፡፡ እንዲህ ባለ አካባቢ ምን ዓይነት ልማት መደረግ አለበት? ይህ ሲከናወንስ የገዳሙ እሴቶች፣ መብቶች እና ሀብቶች እንዴት መጠበቅ ይችላሉ? ከሚሠራው ሥራ ገዳሙ የሚጠቀምበት እንጂ የማይጎዳበት መንገድም ቀድሞ መፈለግ አለበት፡፡
እዚህ ላይ ከግምት ውስጥ መግባት የነበረባቸው ቢያንስ ሦስት ጉዳዮች አሉ፡፡
አካባቢያዊ መስተጋብር፡- ይህ አካባቢ የገዳም አካባቢ ነው፡፡ ይህ ገዳምም በዚያ ቦታ ከሺ ዓመታት በላይ ኖሯል፡፡ እናም በአካባቢው የሚደረጉ ሥራዎች የገዳሙን ገዳማዊ እሴቶች የማያጠፉ መሆን አለባቸው፡፡ ገዳሙ ከዓለም ሰዎች እንቅስቃሴ የራቀ፣ ጸጥታ የነገሠበት እና ጥብቅ ክልል ያለው ነው፡፡ በዚህ አካባቢ የገዳሙን ክልል መንካቱ ብቻ አይደለም ነገሩ፡፡ ከገዳሙ ክልል ውጭ የሚሠራ ሥራም ቢሆን እነዚህን የገዳሙን እሴቶች የጠበቁ መሆን አለባቸው፡፡ ለምሳሌ በአሁኑ ጊዜ በገዳሙ አካባቢ ይሠራል የተባለው የስኳር ኢንዱስትሪ ነው፡፡ የስኳር ኢንዱስትሪ ከፍተኛ የሰው ኃይል የሚጠይቅ ኢንዱስትሪ ነው፡፡ በዚህ ከፍተኛ የሰው ኃይል የተነሣም በሀገራችን የስኳር እርሻ እና ፋብሪካ ባሉባቸው አካባቢዎች ሁሉ ከተሞች ተመሥርተዋል፡፡ ወንጂ እና መተሐራን ይጠቅሷል፡፡ ይህ ማለት አካባቢው ከፍተኛ የሰው ኃይል እንቅስቃሴ ይኖርበታል ማለት ነው፡፡
ይህንን ዓይነት እንቅስቃሴ የማይጠይቅ ተግባር በአካባቢው ማከናወን አንዱ አማራጭ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ ደግሞ የአካባቢው የሰው እንቅስቃሴ ገዳማዊ ሕይወቱን እንዳይረብሸው በሚያስችል መንገድ የሚከናወንበትን ሥራ መሥራት ነው፡፡ አሁን እንደሚታየው በዚህ ጉዳይ የታሰበ ነገር ስለመኖሩ ምንም ዓይነት ግልጽ መረጃ የለም፡፡
በአንዳንድ ሀገሮች በአንድ ቦታ ላይ የአካባቢውን ነባራዊ መልክዐ ምድር፣ መልክዐ ጠባይ እና መልክዐ እሴት የሚቀይሩ ተግባሮች ከመከናወናቸው በፊት ነባር ነዋሪዎች አስተያየት እንዲሰጡባቸው ይደረጋል፡፡ የነዋሪዎቹን ስምምነት ማግኘትም መሠረታዊ ነገር ይሆናል፡፡ በአሜሪካን ሀገር በአንድ መንደር አካባቢ ቤተ ክርስቲያን ለማቋቋም የአካባቢው ነዋሪ ፈቃድ መገኘቱ ወሳኝ ተግባር ነው፡፡
ከአካላዊ ጉዳት ነጻ መሆን፡- ገዳሙ የሀገሪቱ መንፈሳዊ ሀብትም ቅርስም ነው፡፡ የአኩስም ሐውልትን ወደ አኩስም የመለስነው በሮም አደባባይ መቀመጡ ክብካቤ ስላሳጣው አይደለም፡፡ የአኩስም ሐውልት መንበሩ፣ ክብሩም አኩስም ስለሆነች እንጂ፡፡ ከአኩስም መነቀሉን ስለ ተቃወምን ነው ያስመለስነው፡፡ የዋልድባም እንደዚሁ ነው፡፡ ዋልድባ በሀገሩ ከነ ሙሉ ክብሩ የመኖር ኢትዮጵያዊም ሕጋዊም መብት አለው፡፡ በአካባቢው የሚሠሩ ሥራዎች በገዳሙ ላይ አካላዊ ጉዳት የማያስከትሉ መሆን አለባቸው፡፡ አሁን እንደምናየው ግን የገዳሙ የግዝት ክልል ታርሷል፡፡ የገዳሙ የእህል ቤት ወይንም ሞፈር ቤት የሚባለው ቤተ ክርስቲያን ሊነሣ ነው፡፡ የሴቶቹ ገዳም ሊነሣ ነው፡፡ በአንደኛው የገዳሙ ቤተ ክርስቲያንም ግድቡ አደጋ ሊያደርስ ይችላል የሚል ሥጋት ተፈጥሯል፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ እነዚህን ሁሉ አደጋዎች በሚቀንስ እና የገዳሙን ህልውና በማይነካ መልኩ ፕሮጀክቱን መቅረጽ የገዳማውያኑ ጭንቀት ሳይሆን የአጥኚው እና የአስጠኚው ጭንቀቶች መሆን ነበረባቸው፡፡ ልማቱ ከአካባቢው እሴት ጋር ተጣጥሞ በሚሄድበት መንገድ ላይ ገዳማውያኑ በነጻ መክረው፣ የሃሳቡ ባለቤቶች እና ተሳታፊዎች መደረግም ነበረባቸው፡፡ ወይ በሥጋታቸው መሠረት መሠራት፣ ያለበለዚያም ደግሞ ሥጋቱን በሚያስቀር መንገድ መሠራት ነበረበት፡፡
መንፈሳዊ ጉዳት እንዳይደርስ ማድረግ፡- አስቀድሞ የገዳሙን ማኅበረሰብ ባሳተፈ፣ ችግሮችን በሚፈታ እና ሁለቱም አካላት ሳይጣረሱ በተዐቅቦ ሊኖሩ በሚችሉበት መንገድ ባለመካሄዱ ገዳማውያኑ ምን ሊመጣ ይችላል? በሚለው መንፈስ ተረብሸዋል፡፡ አሁን ክርክሩ የተነሣበት ወቅት በዋልድባ ገዳም ዋናው የሱባኤ ጊዜ ነው፡፡ መነኮሳቱ እና መናንያኑ ከገዳማቸው አይወጡም፡፡ በዚህ ወቅት የነገሩ መነሣት በገዳሙ እና በምእመናኑ ዘንድ መንፈሳዊ ረብሻን ፈጥሯል፡፡ ነገሩ በመገባ ቢታብበት ኖሮ ይህንን ወቅት ማስቀደም ወይንም ማሳለፍ በተገባ ነበር፡፡
ለምሳሌ አሁን እርሻው በሚታረስበት አካባቢ ከጥንት ጀምሮ ቀብር እንደነበረ ይታወቃል፡፡ ዐጽሙ ይፍለስ ከተባለ እንኳን ይህንን ጉዳይ ከገዳሙ ጋር ተነጋግሮ ገዳማዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ ማከናወን ይገባ ነበረ፡፡
አዙረህ አዙረህ ካገሬ መልሰኝ  
በሹም የታዘዘ አፈር አታልብሰኝ
እያለ በሚያንጎራጉር የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ የመቃብር ቦታ ያለውን ዋጋ ዘአስቀድሞ መተንበይ አስቸጋሪ አይመስልም፡፡ ዐጽሞቹ የት የት ይገኛሉ? መፍለስ ካለባቸው በምን ዓይነት ሃይማኖታዊ እና ሰብአዊ ሥርዓት? ማን ያፍልሳቸው? የት ይረፉ? የሚሉት እንደ አንድ ተግባር ሊታሰብባቸው ይገባ ነበር፡፡ ለነገሩ የአዲስ አበባ አጥቢያዎች በግዴለሽነት ያለ በቂ ሃይማኖታዊ፣ ሰብአዊ ሥርዓት እና ክብር ነባር ዐጽሞችን በሚያነሡበት በዚህ ዘመን መንግሥትን በዚህ ረገድ መውቀስ ከባድ ይሆናል፡፡ እነዚህ አበው እና እማት ለሀገር እና ለሕዝብ የሚጸልዩ ናቸው፡፡ ጸሎታቸው እንጂ ኀዘናቸው ማንንም አይጠቅምም፡፡ ይህ የዋልድባ ገዳም ጉዳይ በተገቢው መንገድ ባለመያዙ ከዋልድባ አልፎ ሌሎችን ገዳማውያንም የሚያሳስብ ነገር እየሆነ ነው፡፡
ጉዳዩ እና ቤተ ክህነት
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ነባር ይዞታዎች በውል ለይቶ ማወቅ፣መብታቸውን ማስጠበቅ፣ በሀገሪቱ ውስጥ በሚከናወኑ ተግባራት ተጠቃሚዎች እንጂ ተጎጅዎች እናይሆኑ መጠበቅ፣ ችግሮች ሲፈጠሩ የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥቅም በሚያስከብር፣ የሀገርንም ዕድገት በሚራዳ መልኩ እንዲፈቱ ማድረግ የቤተ ክህነቱ ሥራ ነው፡፡
አሁን በታየው ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ቤተ ክህነቱ ሕዝቡ ተገቢውን መረጃ እንዲያገኝ፣ ችግሮች ቀድመው እንዳይከሰቱ፣ ከተከሰቱም እንዲታረሙ፣ ወሬዎች እንዳይጋነኑ፣ ማድረግ ይገባው ነበር፡፡ ለቅዱስ ሲኖዶስም ከዚህ የሚበልጥ ጉዳይ አልነበረውም፡፡
በመጀመርያ ደረጃ ልዑካንን ልኮ ተገቢውን መረጃ መሰብሰብ፣ በተሰበሰበው መረጃ ላይ የተመሠረተ መግለጫ መስጠት፣ ከሚመለከታቸው ጋር መነጋገር እና የደረሰበትን ማስታወቅ ይገባው ነበር፡፡ ባለቤት ካልጮኸ ጎረቤት አይረዳም እንዲሉ፡፡ አስቀድሞም እንዲህ ሀገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በንቃት በመሳተፍ አሁን የተከሰተውን ችግር በማያ ስከስቱበት መንገድ እንዲከናወኑ የበኩሉን ማድረግ ነበረበት፡፡
ገዳማውያኑ ለአቤቱታ አዲስ አበባ ሲመጡ ተቀብሎ ማስተናገድ፣ ችግራቸውን መስማት፣ ከሚመለከ ታቸው አካላት ጋር ማገናኘት፣ ጉዳያቸውን መከታተል እና የነገሩ ባለ ቤት ሆኖ መሥራት ይገባው ነበር፡፡ እንዲህ ያሉ ችግሮች ግን ችግሮችን የመፍታት ዐቅማችንን ሳይሆን ቤተ ክህነታችን ያለበትን ደረጃ የሚያሳዩን እየሆኑ ነው፡፡
«ኢውልድብና»
አንድን ሃይማኖታዊ፣ ታካሪዊ፣ ባህላዊ እና ጥንታዊ እሴትን ከግምት ውስጥ ሳያስገቡ፣ መብቱን እና ክብሩን ብሎም እሴቶቹን ከግምት ውስጥ ሳያስገቡ ሌላ ጠቃሚ ነው የተባለን ነገር ማከናወን «ኢውል ድብና» ተብሏል፡፡ ሃይማኖታዊ፣ ታሪካዊ፣ ባህላዊ እና ትውፊታዊ እሴቶችን ጠብቆ ለሀገራዊ ተግባራትን ማከናወን ደግሞ «ማወልደብ፣ ውልድብና»፡፡ ዋልድባ ላይ የደረሰውን መሠረት በማድረግ ነው ስሙን የወሰድኩት፡፡
ይኼ ጉዳይ ነገም የሀገሪቱ እና የቤተ ክርስቲያኒቱ መነጋገርያ መሆኑ የማይቀር ነው፡፡ ኢውልድብና መንግሥት እና ሕዝብን የሚቀያይም፣ የሕዝብን ተሳታፊነት የሚቀንስ፣ የሚሠሩ ተግባራት ቅቡል እና ዘላቂ እንዳይሆኑ የሚያደርግ፣ ነገሮችን በአንድ ዓይን ብቻ የሚያሳይ አሠራር ነው፡፡ ባለፈው መንግሥት ጊዜ የገበሬውን ቅቡልነት ሳያገኙ የተሠሩ ተግባራት የደረሰባቸውን ማየቱ ብቻ ትምህርት በሆነን ነበር፡፡ አያሌ ቦታዎች በደን ተሸፈኑ፡፡ ደን አስፈላጊ ነገር ነበር፡፡ ይሁንታ ስላላገኘ ግን ደርግ ሲወድቅ ደኑ ሊቀጥል አልቻለም፡፡ አንድ ነገር ጥሩ እና ጠቃሚ ስለሆነ ብቻ እድሜ አይኖረውም ሕዝባዊ ተቀባይነት ሲኖረውም ጭምር እንጂ፡፡
ኢውልድብና መልካሙ ነገር በመስተጋብር ችግር ምክንያት እንዲጠላ የሚያደርገ አሠራር ነው፡፡ ኢውልድብና አንድ ነገር በሚያስገኘው ቁሳዊ ውጤት ብቻ ከዐውዱ ውጭ እንዲታይ አድርጎ አካባቢያዊ ስሙምነት እንዳይፈጠር የሚያደርግ ነው፡፡
እናም አሁንም አልረፈደምና አሉ የሚባሉ ችግሮችን በቀና መንፈስ እንፍታቸው፡፡ ልማቱም ታሪኩም፣ እምነቱም፣ ቅርሱም ተጣጥመው የሚሄዱበትን መንገድ እንፈልግ፡፡ እንደ ሜዶን እና ፋርስ ሕግ የተቆረጠ የማይቀጠል ከምናደርገው፣ ነገሩን እንደገና ብናየው፡፡ እነዚህ መናንያን በኢንዱስትሪው ላይ ከሚያዝኑበት ቢባርኩት ይሻለናል፡፡
የሀገሬ ሰው «ገብስ እና ፈረስ የሚያጣላ» እንደሚለው የማይጣሉትን ጉዳዮች በኛ ችግር ምክንያት አናጣላቸው፡፡ ያለበለዚያ ግን አካሄዳችን ዋልድባን መተሐራ፣ ስኳሩንም መራራ የሚያደርገው ይሆናል፡፡

88 comments:

 1. "አውቆ የተንኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም" ስላም ላንተ ይሁኝ ዻኒ! ሃገር፣ሃይማኖትን ለማጥፋት እና ለማዋረድ የመጣን መንግስት እና የሃይማኖት መሪ ከእግዚሃብሂር ቀጥሎ እያንዳነዱ ግለሰብ እነኝህን ምስጦች በሚችለው አቅምና ቺሎታ መመከት አለበት ምን እየጠበቅን ነው ፡ለመሆኑ< ሃገራችንን ሸጡ ዝም ተባለ፣ በሃይማኖት ቀለዱ ዝም ተባለ ፣ቤተ_ክርስቲያናችንን መነገጃ አደረጉ ተባበርናቸው አሁን ገዳማትን ጀመሩ ምን ቀራቸው መተባበር ቢያቅተን ሀሉም በራሱ የሚችለውን ያርግ እባካቺሁ አንተንም ብርታቱን ይስጥህ ግሪካዊው ዴሞስጠንን ታሰታውሰንኛለህ

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ebakachehu 1 enhun egn mech sekuar felegen.?
   legna enatochchen ena abatochchen yenurule. y egna sekuaroche ensu nachew. esk meche new zemita ?????????????????????????????
   Waldeba tarese
   zequal tekatel
   .........endihu
   negem lela......... . lemin?????????????????????? lemn??????????????
   pls pls

   Delete
 2. benemot men alebet

  ReplyDelete
 3. የሰሞኑ ትኩሳት መመርያን እንጂ መረጃን መሠረት የማያደርገው አሠራራችን ያመጣውም ችግር ነው፡፡

  ReplyDelete
 4. "አውቆ የተንኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም" ስላም ላንተ ይሁኝ ዻኒ! ሃገር፣ሃይማኖትን ለማጥፋት እና ለማዋረድ የመጣን መንግስት እና የሃይማኖት መሪ ከእግዚሃብሂር ቀጥሎ እያንዳነዱ ግለሰብ እነኝህን ምስጦች በሚችለው አቅምና ቺሎታ መመከት አለበት ምን እየጠበቅን ነው ፡ለመሆኑ< ሃገራችንን ሸጡ ዝም ተባለ፣ በሃይማኖት ቀለዱ ዝም ተባለ ፣ቤተ_ክርስቲያናችንን መነገጃ አደረጉ ተባበርናቸው አሁን ገዳማትን ጀመሩ ምን ቀራቸው መተባበር ቢያቅተን ሀሉም በራሱ የሚችለውን ያርግ እባካቺሁ አንተንም ብርታቱን ይስጥህ ግሪካዊው ዴሞስጠንን ታሰታውሰንኛለህ

  ReplyDelete
 5. የሰሞኑ ትኩሳት መመርያን እንጂ መረጃን መሠረት የማያደርገው አሠራራችን ያመጣውም ችግር ነው፡፡ mamush,MN

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሰሞኑ ትኩሳት መመርያን እንጂ መረጃን መሠረት የማያደርገው አሠራራችን ያመጣውም ችግር ነው፡፡ Temesgen

   Delete
 6. kefitegna yehone yeniket tegibar bebete chiristianachin lay menigist ena bete kihinet eyefetsemubin new gobez. ere zimita yibika yihen enkon beminkchilew hulu enkawem yalebelezia sewochu negem kezi yekefa kemamitat aymelesum.

  selam lebete christianachin ena legedamocho.

  ReplyDelete
 7. ታላቅ ወንድሜ ችግሩን በአግባቡ ተገንዝበኸዋል፡፡ ቤተ ክህነትም ችግሩን አይቶ ከመፍታት ይልቅ ብቃቱ የሌላቸውን ሰዎች በመላክ አባቶችን ከማሸማቀቅና በቋሚ ሲኖዶስ ተመልክቶ ውሳኔ በማሳረፍ ልማቱን ደግፎ ገዳሙን ህልውናና ሃይማኖቱን አስቀድሞ መሥራት ይተበቅበታል፡፡ አሁን እየተደረገ ያለው ግን በተቃራኒ መልኩ ትክክለኛ መረጃ የሌላቸውና የግላቸውን ሃሳብ ብቻ የሚያንጸባርቁ ሰዎች ናቸው ከቤተ ክህነቱ ጉዳዩን ሲያበላሹትና እኛንም ተስፋ ሲያስቆርጡን የሚታየው፡፡ ለመሆኑ እነርሱ እነማን ናቸው አባቶችን እየዘለፉ ከላይ የተቀመጡት
  ለማንኛውም መንግስትም ቢሆን ልማቱን ሲያከናውን የማህበረሰቡ ይሁንታ እንደሚያሰፈልግ አውቆ ከገዳማውያኑና ኦርቶዶክሳውያን ጋር መመካከር፣ ይህንንም ፖለቲካዊ በሆነ አካሄድ ሳይሆን ሃይማኖቱ በሚፈቅደው መንገድ በማስኬድ ልማቱም ሳይስተጓጎል ገዳሙም ኦርቶዶክሳዊ ማንነቱ ፈጽሞ ሳይነካ ማስኬድ የሚቻልበትን መንገድ ማመቻቸት ይገባዋል፡፡
  ቤተ ክህነታችንን ግን ምንም እንደማይሠራ ስለማውቀው ምንም አደራ ልሰጠው አልችልም፡፡ ብቃቱም አለው ብየ አላምንም፡፡
  በገዳሙ ያሉ አባቶቻችንም በጸሎት ተግተው ልማቱም መካሄድ እንዳለበት አምነው ግን ሃይማኖታችንን በማይነካ መንገድ እንዲሆን ለመንግስት በማሳሰብ ከዚህ በላይ ደግሞ ለእግዚአብሔር አቤት በማለት መፍትሄ ማምጣት የ,እንደሚችሉ በታናሽነቴ መናገር እወዳለሁ፡፡

  በየቦታው ያላችሁ የመንግስት አካላት ሁኔታውን በአግባቡና ሃገርንና ቤተክርስቲያንን የሚጠቅም ለማድረግ የሚያስችል እይታን እግዚአብሔር እንዲሰጣችሁ ፈቃዱ ይሁን፡፡ አሜን  ያለበለዚያ ግን አካሄዳችን ዋልድባን መተሐራ፣ ስኳሩንም መራራ የሚያደርገው ይሆናል፡፡

  ReplyDelete
 8. May God save our church.we are missing our direction. lemadeg bilen kegeta gar kemetalat yisewuren, libona yisten. I dont have anything to say. it is better to pray.

  ReplyDelete
 9. የነበረን አጥፍተን በአዲስ ካልተካነው ታሪኩ የእኛ አይሆንም፤ ቋሚ ሲኖዶሱም አስቸኳየ ስብሰባ የሚጠራው መቼ ይሆን::

  ደራሲ፣ሰባኪ፣ ጳጳስ እና መሪው ገዳማቶቻቸውን አስጠብቀው፤አለምልመው አረፉ ። የእኛስ ሃውልቱ አለን ዋልድባ ሄዶ ማየት አይችልም እንጅ

  ReplyDelete
 10. Daniel teru tazbehal ene yemigermegn eskemeche yihon yebetkhnet teternet lealemawi mengist yemihonew? Kezeh yebelete lebetekrstian telek ajenda menale?

  ReplyDelete
 11. Min malet endalebigne alawukem betam wuste tekatilowale mengist mine eyesear endehone algebagnem lemin ezheche betekiristian lay endemizemet algebagnem meen aderegineew? yenuuro wudente erasachin lay weeta zime aleen lelam lelam ahun demo be gedamachin ere yibeka enibeleewu.... Egzeabher betekirtiyanachineen yitebek amen.

  ReplyDelete
 12. I think this is very clear we need development but we should protect also our historical places!!!
  FORM MARYLAND

  ReplyDelete
 13. እንዲህ ነው ከሣቴ - ነገር፤ ፈታቴ - ነገር…ሁሉንም ብለኸዋል - Sustainability, EIA (Enviromental Impact Analysis), Ecologically Friendly….‹ዋልድባ መተሐራ፣ ስኳሩም መራራ› እንዳይኾን ለመንግሥታችን ልብ ይስጥልን፤ ለመነኮሳቱ፣ መናንያኑ እስከ መጨረሻው የአፈሩ፣ የእሴቱ ጠባቂ የሚኾኑበትን ጽናት ይስጥልን፡፡ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 14. hayalu egeziabehiere yehen gefena deferet enedihum bedel yakelelin!!!

  lenegeru min yadirigu "gietaw yakelelewin amolie lielaw ayakebirewem" "gietawin kalinaku weshawin ayidefirum" yibal yele. mengisit yedeferew walidiba gedamun bicha sayihon yetekilay bietekihinetin alafiwochin chimir enji.

  ReplyDelete
 15. Dani minew yewerik kufarowin resahew? k 10,000 serategna belay yetesemarabtin Ye Aba Netsahin bota alayehewim? minu yinegeral....kemenaded balefe minim mesrat yalchalin shibawoch honenal....beka ALCHERISEWIM.

  ReplyDelete
 16. ሁላችንም ዋጋ ለመክፈል የተዘጋጀን አይመስለኝም። ነገሮችን በማንኪያ እያንጓለልን ከዚህ ደረስን። ለመሆኑ መቼ ይሆን በቃ የምንለው! ለሕሊና ከሚሰቀጥጡ ብዙ ነገሮች ጋር መታረቅ ለምደን ለምደን ማተባችሁን በጥሱ ብንባል የምናንገራግር አልመስልህ አለኝ።
  የአራዳ ጊዮርጊስ መካነ መቃብር ሲታረስ . . . ዝም
  ጳጳሳት ተደበደቡ . . . ዝም
  ሐውልት ሲቆም . . . ዝም
  ዋልድባ ሲታረስ . . . ዝም
  መቼ ይሆን በቃ የምንለው? ሕሊናችን ከምንም ነገር ጋር መታረቅ መልመዱ አስፈራኝ። ለመሆኑ መንግስት ቤተ ክርስቲያንን እንደተቋም ሊንከባከባት ሲገባ ለምን እንደዚህ ያዳክማታል?

  ReplyDelete
  Replies
  1. Betam yasazinal. Hulachinim yemitebekibinin waga enikfel.

   Delete
 17. I just do not understand from all the places in Ethiopia why they choose Waldeba Gedame?

  ReplyDelete
  Replies
  1. Because they want to destroy EOTC and its Esets.

   Delete
 18. aye bete kihnet?where is mahbere kidusan too ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. What do U expect from Mahbere Kidusan. It doesn't have more power or delegation than bete kihnet

   Delete
  2. ማኅበረ ቅዱሳን ከሚጠበቀው በላይ እያደረገ ይመስለኛል:: ዋናው(ቤተክህነት) ከተኛ ግን ጉዞአችን ወደ ልማት ሳይሆን ወደ ጥፋት ይሆናል:: ለምሳሌ በጥናት በተደገፈ መረጃ መሠረት የገዳማት ችግሮች ተለዩ: መፍትሔያቸውም ተጠቆመ, ባለቤቱ ቤተክህነት ግን ዝም ካለ ተግባራዊነቱን የሚያጠያይቅ ይሆናል:: የባሰም አለ እንጂ ገዳማቱ ይፈርሳሉ: ማኅበረ ቅዱሳን ከሚሰራቸው ውስጥ http://www.eotc-mkidusan.org/site/index.php?option=com_content&view=article&id=892:2012-03-14-21-29-15&catid=1:-&Itemid=18

   እንዲህ አይነቱ ስራ እኮ ነው ዘመኑን የሚያስዋጅ:: ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ኤፌሶን ሰዎች በላከው መልእክቱ እንዳስተማረን:: "ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ።" ኤፌ 5፥16

   አቤቱ አምላካችን ለመሪ አባቶቻችንን ጸጋቸውን አብዛልን::

   Delete
 19. What is the way forward? what is expected from us? Are we expected to sit and observe or act together differently to bring a solution?

  ReplyDelete
 20. +++
  Kalehiwot yasemalin!!!
  The current situation is well described.
  Who is going to listen the voice of the people?!

  ReplyDelete
 21. መንግስት እንደዚህ አይነት ፕሮጄክት ሲያስብ አካባቢያዊ እሴቶችን በማይነካ መልኩ መሆን ነበረበት፡፡ቀደም ሲል በደቡብ ክልል ኦሞ ራቴ አካባቢ ለዚሁ ለስኳር ፋብሪካ ግንባታ ሲባል ብዙ ሃገር በቀል ዛፎችን የያዘ ደን መጨፍጨፉ ሳያንስ አሁን ደግሞ ለዘመናት የኢትዮጵያ ሃብት ሆኖ የኖረዉን ታላቁን የዋልድባን ገዳም ህልውናን መፈታተን ምን ይሉታል? ሃገርን ማልማት ወይስ ለጥፋት መዳረግ?

  ReplyDelete
 22. yasaznal betam lela ingdi min yibalal hooooooooooooooooooo gud lemesmat yetefetern tiwild nen.
  Ingdih Isu rasu yitareken kezim yebase indansema

  ReplyDelete
 23. የማይጣሉ ነገሮች በእኛ ችግር ምክንያት አናጣላቸው አለበለዚያ ግን አካሄዳችን ዋልድባን መተሓራ፣ ስኩሩንም መራራ የሚያደርገው ይሆናል፡፡

  ReplyDelete
 24. Thank you Dani.
  I don't understand what is happening in my country. The government is always acting against the Orthodox church. I don't see any resistive behavior from the believers side when the government distracts our heritages and belief system. I don't blame the church Fathers for this. The problem is how we react. The government can't even think about doing the same thing to other belief systems. You observe how much it is careful about other belief systems on their holidays form what ETV does. But to the contrary our holidays are always celebrated with songs which the belief system doesn't support. To make it worse, ETV says nothing when we die because of luck of justice; when the Government destroys our churches. None of the government bodies respects our belief system but it gets much of tourist attraction from the church. I think we need to do something. I also have fear of other agendas behind the development plans of the government. We have to tell the government that we don't want to see Waldba destroyed(because ultimately if what is happening continues thee is no question that the monastery will not have the silence it has now which is comfortable for prayer and after time we will have non-waldba gedam filled with "diturbing sound and spirit"). Let's do something -oppose the action in a peaceful way.

  ReplyDelete
 25. Hey guys let's be strong and struggle. Let alone Walidiba, peoples have reversed government idea of destructing an old elementary school to build a shopping mall. It was real because peoples were strong.

  ReplyDelete
 26. I think the chief devil is challenging our church in the form of patriarch as the previous devil entered in to heaven in the form of snake.As far as I know, we don't have patriarch but devil leader. I am sorry to say that, but it is 100% real. Please let us pray very hard in order to remove this evil. The devil is playing game on us not a person. Let us confess and ask mercy from GOD, the reason might be our sin. I would like to recommend to organize national prayer, but I don't know how to do it. Let us stop division among us, because that is a big instrument for this devil.
  GOD bless.

  ReplyDelete
 27. መልካም ብለሃል ወንድማችን

  እኔ የማይገባኝ እነዚህ የፖለቲካ ሰዎች ህሊና አላቸው? ደርግ እንኳን ይሄን አላደረገም!

  በጣም የሚያሳዝነው የመነኮሳቱ ተወካዮች ጠቅላይ ሚኒስትሩን እናነጋግር በማለት አዲስ አበባ ላይ ሲጠይቁ…. “ደፋሮች”…ተባሉ አሉ….ህዝብ…እኔ እንጃልኝ መጨረሻውን አለ ሰውየው!

  እኔማ ተስፋ አልቆርጥ ብዬ በኢቲቪም በመንግስትም በየቀኑ እበሳጫለሁ፡፡…ከጓድ….ጋር ወደፊት ብለው ቁርጡን ቢነግሩን እኮ በወጉ እርማችንን እናወጣ ነበር…የዋልድባን ጉዳይ በተመለከተ ለቪኦኤ ቃላቸውን የሰጡ ሰዎችም እየታደኑ ነው አሉ፡፡ የገዳሙ አበምኔት ቤትም እንደ ወንበዴ ቤት ተፈተሸ….በየቦታው የሚናገሩ ሰዎችን ማሰር….የት ያደርሳል…መንግስት የሚዋሽበት አፍ ብቻ ሳይሆን የሚያዳምጥበት ጆሮ ከሌለው…መናገር እኮ አልቻልንም!

  ReplyDelete
 28. ዋልድባን መተሐራ፣ ስኳሩንም መራራ

  ReplyDelete
 29. Dear Daniel,

  It is a very sad story. To my understanding any sort of development projects should be commensurate with the societal value. We must question development for whom. The answer must be to the people. If that is the case, the people in the surroundings must be consulted before any sort of proceedings.Those who religious people should be respected.

  ReplyDelete
 30. Before 18 Churches are demolished, the office building of MK needs to be demolished so that those pseudo Christians stand to fight for the church. Yes if that building is to be demolished for some reason MK will say the world is going to end,bt now it is Churches that are going to be sacrificed for sugar. How on earth the biggest Church organization who claims to be the protector of the church is now silent? No statement or any opposition by MK to this kind of action? Sad!

  ReplyDelete
  Replies
  1. "Yemetechelewun Meta sibal bal mistun debedebe alu"

   Delete
  2. You are so right. I was considering MK to be the loyal protector of the Church. But it doesn't seem now....የቤተ ክርስቲያን ዘብ ነው ማህበሩ ስንል ኖረን ነበር:: አሁን ጥበቃውን; ማስተባበሩን; አልኝታነቱንም አየነው:: አባል ለነበርኩበት ጊዚ አዘንኩ:: መግለጫ መስጠት እንኩዋን ያልደፈረ ማህበር....የትውልድ ማፈሪያዎች ሆንን...ወዮ

   Delete
  3. ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ አለ ያገሬ ሰው ስለ ዋልድባ መፍትሄ አምጣ ምን ይደረግ ስትባል አንተ ማኅበረ ቅዱሳን ምናምን ወዘተ ምን ማለት ነው ለስሙ እውነት ተናጋሪ ብለሃል ወንድ ከሆንክ እውነተኛ ስምህን አትለጥፍም ነበር የነገውን ፍራቻ እውነት ተናጋሪ ብለህ ደግሞ ራስህን ሰያሚ መጀመሪያ አንተ ምን አድርገሀል ከእኔ ምን ይጠበቃል ብለሃል የማኅበሩ ሕንጻ ቢፈርስ ኖሮ ምናምን ብለሃል በመጀመሪያ የዋልድባ ገዳም እና የማኅበሩ ሕንጻ ለመነጻጸር እንኳ አይችሉም ሲቀጥል የማኅበሩ ሕንጻ ከተጀመረ ስንት ዓመት ይመስልሃል ነገር ግን ዛሬ ድረስ አልተጠናቀቀም ምክንያቱን ገለልተኛ ሆነህ ብትመለከተው ሕንጻውን ከመጨረስ ይልቅ የገዳማትና የአድባራት ህልውና መረጋገጥ የአብነት ትምህርት ቤቶች መስፋፋፈተ እና መገንባት ቀዳሚ ስለሆነ ነው
   የማኅበሩ አባል ለነበርኩበት ጊዜ አዘንኩ ላልከው አንተ የማኅበሩ አባል እያለህ የሠራኸው ቁም ነገር አለ ሲጀመር እዛው ውስጥስ ሆነህ ይሄ ለምን አልሆነም ብለህ መጠየቅ አይሻልህም ነበር መጀመሪያውንም የማኅበሩ አላማ ሳይገባህ መናጆ ይመስል ስትከተል ኖረህ ነው የወጣኸው እንጂ አላማው ቢገባህ ኖሮ ዛሬም ድረስ እዛው በቆየህ ነበር ማኅበሩ በድረገጹ ያስነበበውን አንብበሃል ሲጀመር በመጀመሪያ ብዙ ነር እልህ ነበር ግን እንዲሁ በተለምዶ እና በስሜት ለሚጓዝ ሰው ማውራት ጉጭን ማልፋት ይሆንብኛል፡፡ ብትረዳው ዳንኤልስ ቢሆን የማኅበሩ አባል አይደለም ለዚህስ ደረጃ የበቃው በማኅበሩ አይደለም ማስተዋል ቢቀድም ጥሩ ነበር አንተ ቤትህ ተጋድመህ ማኅበሩ መግለጫ ባለመስጠቱ ትናደዳህ ማኅበሩ መግለጫ ለመስጠት ምን ዓይነት ጉዞዎችን መጓዝስ እንዳለበት ታውቃለሀ ለማኅበሩ ጭራ ከመቀጠልህ በፊት ዞር ብለህ የራስህን ጭራ ተመልከት

   Delete
  4. Yes you all are right!MK is fake hodamoch!

   Delete
 31. ዛሬ ለአካባቢ ጥበቃ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ ገበሬውን ሁሉ በአካባቢ ጥበቃ ተግባር በማሳተፍ ላይ ባለበት ጊዜ የዋልድባን ጥብቅ የግዝት ደን ክልል ማረስ የሚጋጭ ተግባር ይሆናል፡፡
  እንኳንና የአካባቢው ሰዎች ሌላውም ግብር ከፋይ ዜጋ ቢሆን በእርሱ ግብር ስለሚሠራው ሥራ በዝርዝር ማወቅ ያስፈልገዋል፡፡
  ስኳሩን እንደሚፈልጉት፣ በስኳሩ ኢንዱስትሪ ተቀጥረው እንደሚሠሩት የሀገሪቱ ዜጎች ሁሉ የገዳሙ መናንያንም የዚህች ሀገር ዜጎች ናቸው፡፡ በሀገሪቱ ሂደት የመጠቀም እንጂ ያለ መጎዳት መብት ያላቸው ዜጎች፡፡ የሚጎዱት ጉዳት እንኳን ቢኖር አምነውበት፣ ተቀብለውት፣ መሥዋዕትነት ለመክፈል ወስነውበት፣ ከዚያም በላይ ደግሞ ያሥምረው ብለው አቡነ ዘበሰማያት ደግመውበት መደረግ አለበት፡፡ ይህ አለ መሆኑን በቀላሉ ከሚያሳዩን ነገሮች አንዱ ወደ ግዝቱ የገዳሙ ክልል ሁለት ኪሎ ሜትር ተኩል ከራ ከመንግሥት ዕቅድ እንኳን በተቃራኒው ተገብቶ መታረሱ ነው፡፡

  ገዳማውያኑ ለአቤቱታ አዲስ አበባ ሲመጡ ተቀብሎ ማስተናገድ፣ ችግራቸውን መስማት፣ ከሚመለከ ታቸው አካላት ጋር ማገናኘት፣ ጉዳያቸውን መከታተል እና የነገሩ ባለ ቤት ሆኖ መሥራት ይገባው ነበር፡፡ እንዲህ ያሉ ችግሮች ግን ችግሮችን የመፍታት ዐቅማችንን ሳይሆን ቤተ ክህነታችን ያለበትን ደረጃ የሚያሳዩን እየሆኑ ነው፡፡

  they try make us history-less
  thank you
  long live

  ReplyDelete
 32. oh! egziabher betibebu yadnen!!! egnama yemetawun eytelamedin aydel yenornew. ene tesfa emderg yeneberew betechristian ezih kemedresua befet endemimot neber. gin ye-egziabhere fekadu honena...

  ReplyDelete
 33. እነዚህ አበው እና እማት ለሀገር እና ለሕዝብ የሚጸልዩ ናቸው፡፡ ጸሎታቸው እንጂ ኀዘናቸው ማንንም አይጠቅምም፡፡


  እግዚአብሔር አምላክ በቸርነቱ እንደ ናቡቴ ርስቴን አልሰጥም የሚሉ አባቶችን ከቤተክህነቱም ከቤተመንግሥቱም ያስነሳልን!
  የአባቶቻችንን ርስት የሚያጠፉትንም እግዚአብሔር ሳይበቀላቸው አይቀርም፡፡

  ReplyDelete
 34. እባካችሁ የታሪክ ተወቃሽ እንዳንሆን በማንገኛውም ነገር እንበርታ አንድ እንሁን!!! አባቶቻችንም እባካችሁ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ለመባል ብቻ አትኑሩ፡፡

  ReplyDelete
 35. ኡኡኡኡኡኡ ኧረ ኡኡኡኡኡ ለማን አቤት እንበል?

  ReplyDelete
 36. አውቆ የተንኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም" ስላም ላንተ ይሁኝ ዻኒ! ሃገር፣ሃይማኖትን ለማጥፋት እና ለማዋረድ የመጣን መንግስት እና የሃይማኖት መሪ ከእግዚሃብሂር ቀጥሎ እያንዳነዱ ግለሰብ እነኝህን ምስጦች በሚችለው አቅምና ቺሎታ መመከት አለበት ምን እየጠበቅን ነው ፡ለመሆኑ በሃይማኖት ቀለዱ ዝም ተባለ ፣ቤተ_ክርስቲያናችንን መነገጃ አደረጉ ተባበርናቸው አሁን ገዳማትን ጀመሩ ምን ቀራቸው መተባበር ቢያቅተን ሀሉም በራሱ የሚችለውን ያርግ እባካቺሁ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 37. hayil ye Egizeabiher new ena ersu hayil yihunen egig yemerere negr kemediresu befet gin beyasibubet melikam new Amilakachin bebizu yetagese yimeslegnal ahunise ye Orthodox Tewahido bedel tsewaw yemola yimesilegnal beka ahunim wede Amilakachin enichohalen firedilin .. firedilin ... eyalin enichohalen haylachen ersu newina

  ReplyDelete
 38. ጉዳዩን በጥሩ እይታ አመላክተሃል ምልከታውን በሚገባ አረዳድ መረዳት ፐሮጀክቱን የቀረፀው አካል ነው፡፡

  ReplyDelete
 39. አይ ወንድም እውነት! እንደ ስምህ እውንት ተናገር እንጂ ጎበዝ፡፡አሁን ለዚህ ጉዳይ ማኅበረ ቅዱሳንን ትከስ ነበርን?ለመሆኑ አቢይ ጾምን ትጾም ይሆን? እባክህ በዚህ ጊዜ እንኳን እውነት ተናገር፡፡የሆነ ሆኖ በጽሁፉ እንደተገለጠው ይህ ጉዳይ፤እንደ ተቋም የቤተክርስቲያኗ መሪዎች የሆኑት ከቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ እስከ ገዳሙን በቅርብ የሚመራው የወረዳ ቤተክህነት ጽ/ቤት ስራ ሲሆን እንደ መንፈሳዊነት ደግሞ የሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ጎዳይ ነው ብየ አስባለሁ፤እንደ ሐብት ደግሞ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሐብት ስለሆነ ፤ሁሉም የድርሻውን ቢወጣ መፍትሄ ይኖረዋል ብየ አምናለሁ፡፡ስለዚህ ወዳጄ ሆይ ከነዚህ ውስጥ ከሆንክ በቻልከው አግዝ እንጂ አትክሰስ፡ወንድምህ ሰሎሞን ከደ/ወሎ ኮቻ

  ReplyDelete
 40. EDIGET wyis EBIDET LIMAT wyis TIFAT? HIZBIN banfera ABIZITENM bininik Terarawun bemaikirosekend MEDA Yemeyadrigin Hayalun Enifira LIB YALEW LIB YIBEL

  ReplyDelete
 41. A very thoughtful piece, Dn. Daniel. I cheer my applause. The socioeconomic contribution of the Monastery has not been taken into contribution. The project is really against the purpose of the transformation and growth plan. Emphasis should be given to institutional development, among others to achieve the vision of the country. Ethiopia cannot reach the middle income status by 2025 by demonasterization of the sacred monasteries. Waldiba belongs to the Ethiopian Orthodox Tewahido church, the church belongs to God. The church has all the right to participate in the development efforts of the country without sacrificing her tradition, relics, heritages, and monastic places. The project is against the so called green economy and ecological diversity, which has been the main agenda of the African Union and the Economic Commission of Africa conference. The growth and transformation plan could be realized through the participation of all citizens, institutions,.... If the Holy Synod keep silent, then we know that the end is fast approaching. Or should we go under unfruitful confrontation. What is next. Did the EPRDF members forgot the contribution of
  Waldiba.

  ReplyDelete
 42. ሆሳዕና liyuhosi @ gmailMarch 19, 2012 at 4:45 PM

  ማከያ፣
  በእውነት አንተ ስለምትጥፈውም ሆነ ስለምትናገረው ነገር ማስተካከያ ማበጀት ከባድ የእውቀት ብልጫ ያስፈልጋል፣ ይህንንም አስተያየት ስጥፍ ላንተ ባልፈቅድልህም ይህንን አስተያየት የሚያነቡት ሁሉ ፣ሰው እስኪታዘባቸው ሊስቁ እንደሚችሉ አልጠራጠርም፡፡
  ይህን ሳስብም ተወውተወው ቢለኝም…ጥርሴን ነክሼ እጥፈዋለሁ፡፡
  የህንን ስጥፍ፣ በ ቅን ሃሳብ እንጂ በማቃለል እንዳልሆ እግዜር ያውቃልና፣ አንተም እወቅልኝ…
  ነገሩን አንተ እጅግ አስፍተህ በማሰብ፣ ማንንም ሳታስቀይምም ሆነ ሳትነካ አበክረሃል…በእኔ ጠባብ መነጥር ግን የጣፍከው ሁሉ እንደ ዲያቆን ሳይሆ እንደ ምሁር፣ዶክተር ታሪክ አዋቂ ወይም ዲፕሎማት ጥሁፍ ሆነብኝ፡፡
  ማመናችን ወዴት ሄደ?፣
  ሁሉም ሰው ቦታ ሰጥቶት እንዲያስብበት የሚያስፈልገው፣ነገሩ የቦታና ድንበር፣ የ አናሊስስ ጥናት ጉድለትና የ ህብረተሰብ አመለካከት፣ የታሪክ፣ቅርስና ውርስ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን በዋነኛነት የዕምነት ጉዳይ ስለሆነ እንዲሆን ይገባዋል፡፡
  የሚነገሩትና የተነገሩት ታሪኮች ሁሉ በዲፕሎማሲያዊ ደጅ ጥናት የተገኙ ሳይሆኑ በዕምነት ላይ የተመሰረቱ መሆኑን መዘንጋት የለበትም፡፡
  ለምን አላልክም ብዬ ከምከስህ በራሴ መንገድ ልሞከርና አንተ ጊዜ ካለህ አስተካክለህ ጨምርበት፡፡
  3ነገሮች አሉኝ፣
  1ኛ›› ስለቦታው የዕምነት ቅድስና ስንናገር ፣ በየትኛውም ገድል ሆነ ስንክሳር ሊገኝ በማይችል ታሪክ፣ አባታችን አቡነ ሳሙኤል ዘዋሊድባ ምድሪቱን እንደ ህብስት ቆርሰው እስከሰባተኛ ሰማይ ድረስ አቅርበው አስባርከውና ይችን ቦታ ለረገጠ ኢየሩሳሌምን እንደረገጠ፣ ከዚህች ቦታ የተጠመቀ ከማየ ዮርዳኖስ እኔ በተጠመኩበት ቦታ እንደተጠመቀ አወቆጥረዋለሁ፣ እንደ 40ቀን ሕጣንም አነጻዋለሁ አስብለው፣ ለትውልድ የሚተርፍ ቃልኪዳን የተረከቡበት ስፍራ ነው፡፡
  ዋሊድባ፣በልብሳቸው ጨርቅ ታንኳነት አርድዕቶቻቸውን ወንዝ ያሻገሩባት ቦታ፣ በእጃቸው ፈልቶ የሚገነፍል ንፍሮ እያማሰሉ አርድዕቶቻቸውን የመገቡበት ቦታ፣ጧፋቻ ሳይጠፋ፣ ብራናቸው ሳይርስ ውሃ ውስጥ ጠሎት ያደረሱባት ስፍራ፣ አራዊቱን የሚያነጋግሩበት፣ ጨለማውን በራሳቸው የብርሃንነት ዓምድ ቀን ያደረጉበት ሥፍራ ስትሆን፡፡
  አባታችን በተቀበሉት ቃልኪዳን ትውልድን ሲያስምሩ እንደሚኖሩት ሁሉ እንዲሁ ደግሞ ክፉ በሚያደርግ ላይ፣ መንግሥትን ከመንግሥትነቱ፣ እኛንም ከመንግሥት በተረፈው የመዓት ዝናም ካፊያ እንዲያገኘን ሊጸልዩብን ይችላሉ፡፡
  2ኛ››ለግብፅ አስቄጥስ ገዳም እንዳላት ሁሉ፣ ለሃገራችን ድግሞ ዋልድባ ቦታው ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ እስከ ዘሬዪቱ ዕለት ድረስ ቅዱሳን እንደ ከዋክብት የሚፈልቁባት በአማላጅነታቸው ተራዳኢነት ሲስተሙ ባበላሸው በዘር በሃይማኖት፣በክልል እና በሃብት የተበጣጠሰች ሃገራችንን እንደ ሁቱ እና ቱትሲዎች ከመጨፋጨፍ በጸሎታቸው ይህችን ሃገር የጋረዷት ቅዱሳን ሁሉ ይሰደዳሉ፡፡
  በጥረታችን ግበረሰዶማዊነት ደረጃ የደረስን እኛ የቅዱሳን ጸሎት ሲርቀን እና ከፀጋ ስንራቆት ደግሞ ህብረተሰባችን እና ትውልዳችን ምን ልንሆ እንደምንችል ለመገመት አያዳግትም፡፡ ረድኤተ እግዚአብሔር የምንለውም ነገር በህይወታችን ሳይሆን በወረቀት ብቻ ይቀራል፡፡
  3›› አባቶች በእምነት የሰሩትን በእኛ አለማመን አይናቸን እያየ ሲፈራርስ፣ እንዲሁ፣ ከታሪክና ቅርስነቱ ባሻገር ዕምነታችንም እንዲሁ ይናዳል፡፡ ሥላሴን ማመናችን ትልቅ ጥያቄ ውስጥ ይገባና አሁን ካለንበት ሩቅ መንፈሳዊ ቦታ ጭራሽ እንጠፋለን…ትውልዳችንንም በዕምነት ለማንሳት ደግሞ ከእኛ ቃል ይልቅ የፈረሰውን ቤት ያጠፋነውን ታሪክ ስለሚያዩ፣ ለእምነታችን ባእዳን ይሆናሉ፡፡

  ምን አድርግ ነው የምትለኝ(ን) ከሆነ፣
  እንመን፣ እግዜር ለውጥ ያመጣል፣ አባታችን እና ገዳሙ ያፈራቸው ቅዱሳን አባቶች ላይ አድሮ የሚኖር መንፈስ ቅዱስ በቅን ይፈርዳል፣ ዝምም አይልም፣ እሳት በፊቱ ይነዳል፣ ለትውልድ እንድንመሰክር አድርጎ እነርሱንም ያሳፍርልናል እኛንም በእምነት ያፀናናል! ብለን በልባችን በእውነት እንመን ባይ ነኝ፡፡
  እንዴት ትሉኝ እንደሆነ ፣ የአባታችንን ብቻ ሳይሆን የቅዱሳንን ገድል በቀን አንድ ጊዜ ብናነብና የፈጸሙተን ተጋድሎ ያደረጉትን ገቢረ ተዓምራት የከፈሉትን ሰማዕትነት ብናነብ ከዘመናት በፊት የነበረ የእነርሱ እምነት ከነርሱና ከገድላቸው ተርፎ በእኛ ልቦና ይሞላል የምንጠራጠር ሁሉ ወደማመን እንሄዳለንና ፣ ከዛልንበት እንበርታ፣ ካንቀላፋንበት እንንቃ፣ ለማለት ነው፡፡
  የቅዱሳን አምላክ ቸር እንደሆነ ሁሉ አዳምን አፕል በልተሃልና‹‹ ባለቤቱን ካልናቁ… ብሎ ›› ከገነት እንዳባረረው ለዘመናት በነፍስ በስጋ ስለዛች የድፍረት እርምጃ በስቃይ እንዳስከፈለን መርሳት የለብንም፡፡ እግዜር አሁንም ለነዚህ ደፋሮች እንዲሁ ማድረግ ይችላል፡፡
  አሊያ ሥላሴን ማመናችን ወዴት አለ…ባይ ነኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. እግዚአብሔር ይስጥህ። የአባቶቻችን ልጆች እንሁን!

   Delete
  2. I felt much better reading this reply than reading Daniel Kibreat article. It has truth in it and make us to be very strong in our believe and also make us to pray for God to answer about Waldib. God bless you my brother and Egziabher wagahin besemay bet yikfelih.

   Delete
  3. እውነት ብለሀል የአባቶቻችን አምላክ የት ሄዶ ከልባችን ከጸለይን አምላክ ሁሉን ማድረግ ይችላል።
   እንመን፣ እግዜር ለውጥ ያመጣል፣ አባታችን እና ገዳሙ ያፈራቸው ቅዱሳን አባቶች ላይ አድሮ የሚኖር መንፈስ ቅዱስ በቅን ይፈርዳል፣ ዝምም አይልም፣ እሳት በፊቱ ይነዳል፣ ለትውልድ እንድንመሰክር አድርጎ እነርሱንም ያሳፍርልናል እኛንም በእምነት ያፀናናል! ብለን በልባችን በእውነት እንመን ባይ ነኝ፡፡

   Delete
 43. ebakachihu abatochachinin tebkew yasrekebun haymanot endekelal animelketew wud yekirstos lijoch mebitochachin entekemibet leselamawi selif eniwuta err eskemech gifu beza beza beza

  ReplyDelete
 44. ዳንኤል እግዚአብሔር እረጅም እድሜ ይስጥልኝ

  እኔ የምለው ሲኖዶስ ምን እየሰራ ነው? አቡነ ጳውሎስ ምን እየሰሩ ነው? ስለሚለብሱት ልብስ እና ስለሚሄዱበት መኪና ነው የሚያስቡት. በጣም ነው የሚያሳዝን ነው. እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን እውነተኛ አባት ይስጠን. ለዚህም ሁሉም ክርስቲያን ስለቤተ ክርስቲያን መጸለይ ያስፈልጋል. እግዚአብሔር የሚፈርድበት ግዜ ስለደረሰ ለሁሉም እንደስራው ይሰጣል. በዚህ ሰአት ሁሉም ክርስቲያን በህብረት መቆም አለበት

  ReplyDelete
 45. Enough with the disappointing tidings and comments.

  A very simple thing we can do to save the monastery is to collect a petition opposing government's plan on ዋልድባ area from all Ethiopians who count ዋልድባ as valuable national treasure than religious site. Submit the petition to concerned government bodies and Bete-Kihnet to pressure them to speak against this outrageous act.

  No offence to anyone, but I thought we are not lead by communists. Are we? Because, government seems to inherit a propensity of communism sometimes.

  ReplyDelete
 46. Where is Mahebere Kidusan? How come they are not condemning this act of evil? or is this ok as long as woyane do not demolish their building?

  Shame on Mahebere Kidusan, shame on Abune Pawlos (Abune Deabelos), shame on dictator Meles whose date is numbered.

  ReplyDelete
 47. ወሬኛ ሁሉ፡፡ ከምታወሩ አንድ ነገር ስሩ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድሜ ለቤተክርቲያን እኮ አንተም ዳንኤልም እኔም እኩል ነን! ይህ ጽሁፍ እግዚአብሄር የህሊናቸውን አይን ካበራላቸው ለመንግስትና ለቤተክህነት ሰዎች ታሳቢ ሁኖ የተጻፈ መሆኑንም ተረዳ! ቁጣ የእግዚአብሄርን ጽድቅ አያሰራውምና ደርሰህ አትጋል!!! ከአቡነዘበሰማያት ጀምሮ ያንተ የሆነውን ሁሉ አበርክት ! ቆይ እኛ በሰላም ሀገር ተቀምጠን በል በል እያልን ለዝች ዘመን የተሰጡንን መምህራን ለጭራቅ መንግስት የማስበላቱ ትርፍ ምንድን ነው;;;ስውኮ ከድንጋይ ጋር ሲጋጭ መንገድ ቀይሮ ካልሄደ በቀር ትርፉ መድማት ነው! ይልቅ ድንጋዮቹን እንዲፈረካክስላቸው መምህራኖቻችንን በጸሎት እንገዝ! ትርፉን አስልተን መንቀሳቀሱ ከዚህ ጭራቅ መንግስት የምንድንበት ጥበብ ነው!!!

   Delete
  2. ye Ethiopia hizib be alem akef dereja yetekebere enji weregna ayedelem weregnoch sanhon tagashoch selehonen new

   Delete
 48. በመጀመሪያ አንድን ልማትን ሊያመጣ የሚችል ፕሮጄክት ከእቅድ ወደ ተግባር ስናሸጋግር በእቅዱ ውስጥ ሊካተቱ የሚገባቸው ሊኖሩ የሚችሉትን ተግዳሮቶቸን ማካተት ነበረበት፡፡ከነዛ ተግዳሮቶች ውስጥ ደግሞ አንዱ አሁን እየታየ ያለው የግልጸኝነተ ችግር ይመስለኛል ፡፡

  ሌላው መንግስት ያላሰበው የሚመሰለኝ ምንም አይነት ልማቶችን ልክ እንደ አባይ ግድብ የልማት ተሳትፎ አይነት የህዝብ ይሁንታና ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማደረግን እና ልማቶችን(ፕሮጄክቶችን) ሁሉ የዋልድባንም አካባቢ ልማትን ጨምሮ እንደ አባይ ግድብ አይት የኔነት ስሜት እንዲኖራቸው ማደረግ ነበረበት፡፡

  ሌላው ዳንኤል እንደገለጽከውም ሆነ መንግስትም እንደሚያውቀው የሀገራችን ህዝብ ከ95 በመቶ በላይ ሀይማኖተኛ እንደሆነ ይታወቃል ፡፡ግን አንዳንድ ግዜ ሀይማኖተኝነቱን በስም ብቻ የያዝነው ይመሰለኛል፡፡ምክንያቱም በሀገራችን ውስጥ ብዙ ግዜ ከልማት ጋርም ጋር ተያይዞ ይሁን ከመለካም አሰተዳደር ጋር የሚከሰቱት አለመግባባቶች እና ቅሬታዎች ሀይማኖተኝነታችንን የዘነጋነው ያስመስላል፡፡መቼም በቅርቡ በሀገራችን የሚታዩት ትላልቅ የልማት እንቅስቃሴዎች ከኛው የሀገራችን ልጆች ሀሳብ እና እውቀት የፈለቀ ነው፡፡ግን ታድያ በኛው ልጆች ሀሰቡ ተመንጭቶ ፣ተጠንቶ ሊተገበር ሲል የሚነሱት ቅሬታዎች መጀመሪያወኑ ጥናቱን ያጠናው የባእድ ሀገር ሰው ይመስላል፡፡ምንም አይነት ልማት ይምጣ የግንዮሽ ችግር ሊኖረው ይችላል፡፡ይህ የግንዮሽ ችግሩ ግን በተለይ ከሀይማቶቹ ባለቤቶች ጋር የማያጋጭና የማያነካካ ቢሆን ጥሩ ይመስለኛል፡፡

  ሃይማኖተኞች የሀገሬ ልጆች እና ህዝቦች ሆይ ስራዎቻችሁና ሃሳቦቻችሁ ለወገናችሁ እንደሚጠቀም አድርጋች እየሰራችሁ እና እየለፋችሁ እንደሆነ አምናለሁ፡፡የናንተም ሃይማኖተኝነታችሁ የሚለካው ደግሞ በታማኝነታችሁ ነውና ታመኑ አዎ ለህዝብም ለመንግስትም ታመኑ፡፡

  ዳንኤል ክብረት የዮሐንስ ራእይ በሚለው መጽሐፍ ገጽ 22 ላይ እንዲህ ይላል፡፡‘’ሰው ግን የሚመዘነው በስኬቱ መጥን ሳይሆን በታማኝነቱ መጥን ነው፡፡ታማኝነት የሃይማኖት መለኪያ ነው፡፡ስኬት ግን ሁል ግዜ ላይገኝ ይችላል ፡፡ክርስትያኖች የበለጠ ጸጋ ለማግኝት መገዳል አለባቸው፡፡ሁሉም ግን በተመሳሳይ መዕረግ እና ክብር አይደርሱም ኮከብ ከኮኮብ ክብሩ ይበልጣል ፡፡’’

  እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሀገራችንን እና መሪዎቻችንን ይባርክልን፡፡

  ተስፋዬ ለማ

  ReplyDelete
 49. በመጀመሪያ አንድን ልማትን ሊያመጣ የሚችል ፕሮጄክት ከእቅድ ወደ ተግባር ስናሸጋግር በእቅዱ ውስጥ ሊካተቱ የሚገባቸው ሊኖሩ የሚችሉትን ተግዳሮቶቸን ማካተት ነበረበት፡፡ከነዛ ተግዳሮቶች ውስጥ ደግሞ አንዱ አሁን እየታየ ያለው የግልጸኝነተ ችግር ይመስለኛል ፡፡

  ሌላው መንግስት ያላሰበው የሚመሰለኝ ምንም አይነት ልማቶችን ልክ እንደ አባይ ግድብ የልማት ተሳትፎ አይነት የህዝብ ይሁንታና ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማደረግን እና ልማቶችን(ፕሮጄክቶችን) ሁሉ የዋልድባንም አካባቢ ልማትን ጨምሮ እንደ አባይ ግድብ አይት የኔነት ስሜት እንዲኖራቸው ማደረግ ነበረበት፡፡

  ሌላው ዳንኤል እንደገለጽከውም ሆነ መንግስትም እንደሚያውቀው የሀገራችን ህዝብ ከ95 በመቶ በላይ ሀይማኖተኛ እንደሆነ ይታወቃል ፡፡ግን አንዳንድ ግዜ ሀይማኖተኝነቱን በስም ብቻ የያዝነው ይመሰለኛል፡፡ምክንያቱም በሀገራችን ውስጥ ብዙ ግዜ ከልማት ጋርም ጋር ተያይዞ ይሁን ከመለካም አሰተዳደር ጋር የሚከሰቱት አለመግባባቶች እና ቅሬታዎች ሀይማኖተኝነታችንን የዘነጋነው ያስመስላል፡፡መቼም በቅርቡ በሀገራችን የሚታዩት ትላልቅ የልማት እንቅስቃሴዎች ከኛው የሀገራችን ልጆች ሀሳብ እና እውቀት የፈለቀ ነው፡፡ግን ታድያ በኛው ልጆች ሀሰቡ ተመንጭቶ ፣ተጠንቶ ሊተገበር ሲል የሚነሱት ቅሬታዎች መጀመሪያወኑ ጥናቱን ያጠናው የባእድ ሀገር ሰው ይመስላል፡፡ምንም አይነት ልማት ይምጣ የግንዮሽ ችግር ሊኖረው ይችላል፡፡ይህ የግንዮሽ ችግሩ ግን በተለይ ከሀይማቶቹ ባለቤቶች ጋር የማያጋጭና የማያነካካ ቢሆን ጥሩ ይመስለኛል፡፡

  ሃይማኖተኞች የሀገሬ ልጆች እና ህዝቦች ሆይ ስራዎቻችሁና ሃሳቦቻችሁ ለወገናችሁ እንደሚጠቀም አድርጋች እየሰራችሁ እና እየለፋችሁ እንደሆነ አምናለሁ፡፡የናንተም ሃይማኖተኝነታችሁ የሚለካው ደግሞ በታማኝነታችሁ ነውና ታመኑ አዎ ለህዝብም ለመንግስትም ታመኑ፡፡

  ዳንኤል ክብረት የዮሐንስ ራእይ በሚለው መጽሐፍ ገጽ 22 ላይ እንዲህ ይላል፡፡‘’ሰው ግን የሚመዘነው በስኬቱ መጥን ሳይሆን በታማኝነቱ መጥን ነው፡፡ታማኝነት የሃይማኖት መለኪያ ነው፡፡ስኬት ግን ሁል ግዜ ላይገኝ ይችላል ፡፡ክርስትያኖች የበለጠ ጸጋ ለማግኝት መገዳል አለባቸው፡፡ሁሉም ግን በተመሳሳይ መዕረግ እና ክብር አይደርሱም ኮከብ ከኮኮብ ክብሩ ይበልጣል ፡፡’’

  እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሀገራችንን እና መሪዎቻችንን ይባርክልን፡፡
  ተስፋዬ ለማ

  ReplyDelete
 50. YeKIDUSAN abatochachin amlak selamun yawuridilin!
  Ignam e-sebiawi hilina tetekimen yetarik tewekashina ye bereket dihoch indanihon yirdan.
  INDENE CHIGIRU KELAY NEW INJI MAHIBER KIDUSAN YETECHALEWUN IYADEREGENA IYETARE YALE YIMESILEGNAL; LIBONAN LE-ABATOCHACHIN . . . .
  Rejim idimena biruk agelgilot le-ante!

  ReplyDelete
 51. yih hulu mekera eyemeta menale mekases akumen min enaderg binil. Ebakih daniel kechalk astebabrenina meftihe enfelig.

  Kehulum belay degmo yesewin hatiyat kemekuter hulachinim silerasachin hatiyat niseha enegba,"hulum akababiwin biyatseda...". betechemari entseliye.

  Amlak yirdan, emamlak ateleyen.

  ReplyDelete
 52. እባካችሁ የታሪክ ተወቃሽ እንዳንሆን በማንገኛውም ነገር እንበርታ አንድ እንሁን!!!

  ReplyDelete
 53. Amilak mechereshawun yasamirilin

  ReplyDelete
 54. አንድን ሃይማኖታዊ፣ ታካሪዊ፣ ባህላዊ እና ጥንታዊ እሴትን ከግምት ውስጥ ሳያስገቡ፣ መብቱን እና ክብሩን ብሎም እሴቶቹን ከግምት ውስጥ ሳያስገቡ ሌላ ጠቃሚ ነው የተባለን ነገር ማከናወን «ኢውል ድብና» ተብሏል፡፡ ሃይማኖታዊ፣ ታሪካዊ፣ ባህላዊ እና ትውፊታዊ እሴቶችን ጠብቆ ለሀገራዊ ተግባራትን ማከናወን ደግሞ «ማወልደብ፣ ውልድብና»፡፡ ዋልድባ ላይ የደረሰውን መሠረት በማድረግ ነው ስሙን የወሰድኩት፡፡
  ይኼ ጉዳይ ነገም የሀገሪቱ እና የቤተ ክርስቲያኒቱ መነጋገርያ መሆኑ የማይቀር ነው፡፡ ኢውልድብና መንግሥት እና ሕዝብን የሚቀያይም፣ የሕዝብን ተሳታፊነት የሚቀንስ፣ የሚሠሩ ተግባራት ቅቡል እና ዘላቂ እንዳይሆኑ የሚያደርግ፣ ነገሮችን በአንድ ዓይን ብቻ የሚያሳይ አሠራር ነው፡፡ ባለፈው መንግሥት ጊዜ የገበሬውን ቅቡልነት ሳያገኙ የተሠሩ ተግባራት የደረሰባቸውን ማየቱ ብቻ ትምህርት በሆነን ነበር፡፡ አያሌ ቦታዎች በደን ተሸፈኑ፡፡ ደን አስፈላጊ ነገር ነበር፡፡ ይሁንታ ስላላገኘ ግን ደርግ ሲወድቅ ደኑ ሊቀጥል አልቻለም፡፡ አንድ ነገር ጥሩ እና ጠቃሚ ስለሆነ ብቻ እድሜ አይኖረውም ሕዝባዊ ተቀባይነት ሲኖረውም ጭምር እንጂ፡፡
  ኢውልድብና መልካሙ ነገር በመስተጋብር ችግር ምክንያት እንዲጠላ የሚያደርገ አሠራር ነው፡፡ ኢውልድብና አንድ ነገር በሚያስገኘው ቁሳዊ ውጤት ብቻ ከዐውዱ ውጭ እንዲታይ አድርጎ አካባቢያዊ ስሙምነት እንዳይፈጠር የሚያደርግ ነው፡፡
  እናም አሁንም አልረፈደምና አሉ የሚባሉ ችግሮችን በቀና መንፈስ እንፍታቸው፡፡ ልማቱም ታሪኩም፣ እምነቱም፣ ቅርሱም ተጣጥመው የሚሄዱበትን መንገድ እንፈልግ፡፡ እንደ ሜዶን እና ፋርስ ሕግ የተቆረጠ የማይቀጠል ከምናደርገው፣ ነገሩን እንደገና ብናየው፡፡ እነዚህ መናንያን በኢንዱስትሪው ላይ ከሚያዝኑበት ቢባርኩት ይሻለናል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. እንዲህ ያሉ ችግሮች ግን ችግሮችን የመፍታት ዐቅማችንን ሳይሆን ቤተ ክህነታችን ያለበትን ደረጃ የሚያሳዩን እየሆኑ ነው፡፡

   Delete
 55. weineshet zamdehimanotMarch 22, 2012 at 12:10 PM

  ይኼ ጉዳይ ነገም የሀገሪቱ እና የቤተ ክርስቲያኒቱ መነጋገርያ መሆኑ የማይቀር ነው፡፡ ኢውልድብና መንግሥት እና ሕዝብን የሚቀያይም፣ የሕዝብን ተሳታፊነት የሚቀንስ፣ የሚሠሩ ተግባራት ቅቡል እና ዘላቂ እንዳይሆኑ የሚያደርግ፣ ነገሮችን በአንድ ዓይን ብቻ የሚያሳይ አሠራር ነው፡፡ ባለፈው መንግሥት ጊዜ የገበሬውን ቅቡልነት ሳያገኙ የተሠሩ ተግባራት የደረሰባቸውን ማየቱ ብቻ ትምህርት በሆነን ነበር፡፡ አያሌ ቦታዎች በደን ተሸፈኑ፡፡ ደን አስፈላጊ ነገር ነበር፡፡ ይሁንታ ስላላገኘ ግን ደርግ ሲወድቅ ደኑ ሊቀጥል አልቻለም፡፡ አንድ ነገር ጥሩ እና ጠቃሚ ስለሆነ ብቻ እድሜ አይኖረውም ሕዝባዊ ተቀባይነት ሲኖረውም ጭምር እንጂ፡፡ኡኡኡኡኡኡ ኧረ ኡኡኡኡኡ ለማን አቤት እንበል?ዋልድባን መተሓራ፣ ስኩሩንም መራራ የሚያደርገው ይሆናል፡፡ዳንኤል እግዚአብሔር እረጅም እድሜ ይስጥልኝ

  ReplyDelete
 56. ዝም ብለን በስሜት መንቀሳቀስ ጥሩ አይደለም:: መጀመሪያ ነገሩን ምን እንደ ሆነ በደንብ ጠይቆ መረዳት ያስፈልጋል:: ካሉባልታ እና ከወሬኛ ይጠብቃቹ::

  ReplyDelete
 57. የሰሞኑ ትኩሳት መመርያን እንጂ መረጃን መሠረት የማያደርገው አሠራራችን ያመጣውም ችግር ነው፡፡ መቼም አንድ የስኳር ኢንዱስትሪ እንደ ታዴዎስ እርሻ በአንድ ቀን ታስቦ በአንድ ቀን አይጀመርም፡፡ የብዙ ጊዜ ዕቅድ እና ፕሮጀክት ውጤት ነው፡፡ በዚህ ጥናት ውስጥ ሊካተቱ ከሚገባቸው ጉዳዮች አንዱ የፕሮጀክቱ አካባቢያዊ ተቀባይነት ነው፡፡

  ReplyDelete
 58. weineshet zamdehimanotMarch 23, 2012 at 2:08 PM

  engdih ylbunachen wegeb tatken wde Amlakachen Medhanealem enchuh meknyatum ahun endih aynachwn chefn adrgew menm chegr altefterm eyalu bete kehnet ena bete mengist kedwal bsraw hulu ytamene Egziabher hizkiasn ksenakrem endtadege kegna gar yale kenrsu ybeltalna tarkachen ende merdokios ylwtal becha egna bfsum nisha wde Egziabher ybhriachen memekia yhonech WoladiteAmlaken yzen enkerb yasrat hagran zem atlem
  Amlake kedusan Egziabher brtatun tnatn ysten Amen

  ReplyDelete
 59. Semachihu Wondimoche, yehaimanot abotochachin sle betkirstian ena slemimerut miemen kaltechenkuna kalasebu mengist min agebaw! Orthodoxn behualakernetna adharinet yefereje mengist slekirsuwana sratuwa min yigedewal.

  ABET!!!!!!!!!! Ebakih EGZIABHER HOY YEHENIN JORO CHEW YEMIADERG WORENA DIRGIT KEMTASEMAN BITGELAGLEN LETELATOCHACHIN MEZEBABECHA KEMINHON......................

  ReplyDelete
 60. Dani Yih kezih Tsihuf behuwala Ye Ziquwala guday silemeta lezih tikuret sayiset yetalefe yimeslegnal ena ebkih "Kitet wede Ziquwala" bileh endanesahen ahunm yemianesa adirigeh tsafilin weyinim bians digemew yasifeligal kalih.

  Tesfahun, Phx, Az

  ReplyDelete
 61. enye min endemle alawkim,eskemechenew yegna haymanot endehaymanot ,amagnochua endezega tekotrew mebtacew yemikeberew?????????????????????????? .lenegeru balesltanochachin enema nachew yenesus swur alama min endehone,yenesu emnet yemisetachew telko min endehone atawukumn.enye yemigermegn yegna frat .lelaw haymanot teketayma gelo ,betekristian akatlo mebtu ykeberal.yehe bihon aydenqenm egna yealem slalhon alem aywodenm.wud ehtochna wondmoch ebakachihu tegten entsely.egnan lyu yemiyadergen midrawi tebakiwochachin lmdrawi zina enji semayawi aderachewun yeresu mehonachew new. ebakachihu betekrstianen enasbat.egziabher tsenatun yiten yemetabnen yesetan fetena egziabher yarklin emebetachin trdan.AMEN

  ReplyDelete
 62. ጳጳሱ እና ሲኖዶሱ ቢያንስ በህይወታቸው ላንድ ግዚ እንኳን ለሐይማኖታቸው ሲሉ እውነትን አሳውቀው ለዘላለም እንደ አቡነ ጰጥሮስ ሲታወሱ ቢኖር ይሻል ነበር፤ የነመለስ ዚናዊ አሽከር ከመሆን እነሱ እንደሆን ገንዘብ ያስገኛል የተባለውን ሁሉ ከመሸጥ አይመልሱም የሆነ ሆኖ ቢተክርስቲያንን በማፍረስ ያገር ልማት አይገኝም ምናልባት የኛ የራሳችን የኦርቶዶክስ አለመፋቀር ያመጣው ችግር ካልሆነ በስተቀር።
  ዳኒ በጣም ነው የማመስግንሀ ይሀን ሃስብ ስላካፈልከን

  ReplyDelete
 63. aydelem wendmoche hulunem neger lemen lebatekehnet ensetalen,beka ensu hulunem tetwetal,eghnas?????

  ReplyDelete
 64. ዲ.ዳ
  እግዚአብሔር በሰጠህ ጸጋ በጣም ገልጸኸዋል፡፡ እግዚአብሔር አሁንም ጸጋውን ያብዛልህ፡፡ እኔ ምንም መናገርም መጻፍም ችሎታው ስለሌለኝ ተቃጥዬ መሞቴ ነው ፡፡ በአንተ እንኳን እንተንፍስ እንጂ በተክህነትን መዝጋት ቢቻል መዝጋት ነበር፡፡
  እግዚአብሔር ከአንተ ጋ ይሁን፡፡

  ReplyDelete
 65. Hi guys,Daniel's and other broad minded writers thought is very important for Peace and development of the country. firstly, Government has a responsibility for those all questions of today because if participation of the society and Religious leaders were incorporated on the preparation of the project these questions were solved simply however, If We think rationally this project is for the well-being of the society as well as the religion, ignoring all the mistake of the gov't Waldba can not exist if peace and development of the country decelerated. Hence,
  by forwarding constructive ideas please help the project and but it should not harm the existence of the holly area. it is our religious and historical place. keeping this is keeping our all.

  ReplyDelete
  Replies
  1. I do not understand what you are saying. Are you supporting the sugar factory?

   Delete
 66. I believe that I give my life to protect Waldiba Monastery from destruction. But I don't know how.

  ReplyDelete
 67. let us unite to defend ourselves and our religion from this regime and the so called the patriarch.Enough is enough!!!!

  ReplyDelete
 68. የአኩስም ሐውልትን ወደ አኩስም የመለስነው በሮም አደባባይ መቀመጡ ክብካቤ ስላሳጣው አይደለም፡፡ የአኩስም ሐውልት መንበሩ፣ ክብሩም አኩስም ስለሆነች እንጂ፡፡ ከአኩስም መነቀሉን ስለ ተቃወምን ነው ያስመለስነው፡፡ የዋልድባም እንደዚሁ ነው፡፡ ዋልድባ በሀገሩ ከነ ሙሉ ክብሩ የመኖር ኢትዮጵያዊም ሕጋዊም መብት አለው፡፡ ወንድም ዲያቆን ዳንኤል ቃለ ህይወትን ያሰማልን!

  ReplyDelete
 69. in ethiopia the separation of religion and state is untill now its unreal.who is propose those idea ? there are many free space that sugar fabrics will be done.
  These is propaganda arise from government.
  even if what we shall do?
  please every one don't mix the issues of heaven life and earths life if you have power in government structure think this all things,is sugar will stand for our soul? no!

  ReplyDelete
 70. in ethiopia the separation of religion and state is untill now its unreal.who is propose those idea ? there are many free space that sugar fabrics will be done.
  These is propaganda arise from government.
  even if what we shall do?
  please every one don't mix the issues of heaven life and earths life if you have power in government structure think this all things,is sugar will stand for our soul? no!

  ReplyDelete