እናት ታምጣለች፡፡
ያለ የሌለ ኃይሏን ሁሉ እያሟጠጠች፡፡
የመንደሯ አዋላጅ እሜቴ ድንበሯ «አይዞሽ ግፊ» ይላሉ እየደጋገሙ፡፡ የመንደሯ ታላላቅ ሴቶችም ዙርያዋን ከብበው «ማርያም ማርያም» እያሉ ይለምናሉ፡፡
አንዳንዶቹ «የመጀመርያዋ ስለሆነ ነው» ይላሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ «ምናልባት ጭንቅላቱ ትልቅ ሆኖ ይሆናል» ይላሉ፡፡ ብቻ ሁሉም በሁላገርሽ ላይ ምጡ የጠናበትን ምክንያት እንደ መሰላቸውን ይተነትናሉ፡፡
ሁላገርሽ መንፈሷም ዐቅሟም እየደከመ መጣ፡፡ ሰውነቷን ላብ አጠመቀው፡፡ ድንገት እንደ ብራቅ እሪ ብላ ስትጮኽ ልጁ ፈትለክ ብሎ ወጣ፡፡ በዚያውም የሁላገርሽ ነፍስም አብራ ወጣች፡፡
እሜቴ ድንበሯ «ኧረ ቀዘቀዘችብኝ፤ ኧረ አንድ በሉኝ» እየተርበተበቱ ጮኹ፡፡ የሚያደርጉት ነገር ግራ ገባቸው፡፡ ሁላገርሽ ቀዝቅዛባቸዋለች፣ ሕፃኑ ደግሞ ብቅ ብሏል፡፡
ይህን ጊዜ ወደዚህች ምድር አዲስ ሆኖ የመጣው ሕፃን አንዳች ፍጡር ከፊት ለፊቱ ቆሞ አየ፡፡ ጥልማሞት የመሰለ አስፈሪ ፍጡር፡፡ ርዝመቱ በመልአክ እንጂ በሰው ክንድ የማይደረስበት፡፡ በዓለም ላይ ያሉ አስቀያሚ ገጽታዎችን ሁሉ ሰብስቦ የያዘ፡፡ በእጁ ደግሞ የሁላገ ርሽን ነፍስ ይዟታል፡፡
ከሁላገርሽ ማኅፀን የወጣው አዲስ ሕፃን ገና የፍርሃት ስሜት አልተፈጠረበትም፡፡ ስለ ጭራቅ እና ስለ ሰይጣን የሚነገሩ እውነቶችንም ተረቶችንም ገና አልሰማም፡፡ ደግነት እና ክፋት፣ መልካም እና ክፉ ገና በማኅበረሰቡ ደንብ ተለይተው አልተሳሉበትም፡፡ እናም ያንን ጥልምያኮስ የመሰለ ፍጡር አልፈራውም፡፡
«አንተ ማነህ? ደግሞስ የእናቴን ነፍስ የትነው የምትወስዳት?» ሲል ጠየቀው፡፡
«እኔማ ሞት ነኝ፡፡ እናትህ አንተን እወልዳለሁ ብላ ሞተች፡፡ ያንተ ሕይወት ሲጀመር የእርሷ አለቀ፤» ሲል አሰቃቂ ጥርሶቹን ብልጭ አደረገበት፡፡
«እንዴት ሕይወት የሚሰጥ ሕይወት ያጣል፡፡ እንዴት ላለው ይጨመርለታል እንጂ ይወሰድበታል፤ እንዴት የሚሰጥ ይራባል፤ እንዴትስ የሚያበራ ይጨልምበታል» ሲል ጠየቀው፡፡
«እርሱን እኔ አልመልስልህም፤ የኔ ድርሻ ነፍሷን መውሰድ ብቻ ነው» አለው ሞት፡፡
«ይህ ከሆነማ እኔም እከተልሃለሁ፡፡ ምንጩን የሚያደርቅ ውኃ፣ ፋኖሱን የሚያጠፋ መብራት፣ ማሳውን የሚገደል እሸት፣ ዛፉን የሚገነድስ ፍሬ፣ ምጣዱን የሚሰብር እንጀራ መሆን የምፈልግ ይመስልሃል?» አለው ሕፃኑ፡፡
«እርሷን እንጂ አንተን ለመውሰድ አልመጣሁም» አለው ሞት ከፊቱ እንደ መራቅ እያለ፡፡
«ነገርኩህኮ እኛ ሰዎች እንጂ እፉኝቶች አይደለንም፡፡ የእፉኝት ልጆች ሲፀነሱ አባታቸው፣ ሲወለዱ እናታቸውን ይገድላሉ ይባላል፡፡ እኛ ግን ሰዎች ነን፡፡»
«አንተ ለፈጣሪ የሚጠየቀውን ጥያቄ ነው እኔን የምትጠይቀኝ» አለው ሞት፡፡
«አሁን ገና እውነት ተናገርክ» አለና ሕፃኑ አንገቱን ወደ ሰማይ ቀና አደረገ፡፡ ከዚያም እንዲህ ሲል አሰምቶ ጮኸ፡፡
«ፈጣሪ ሞቷል»
ያን ጊዜ እልፍ አእላፍ መላእክት እንደ እሳት ላንቃ የሚንበለበል ሰይፋቸውን መዝዘው፣ የእሳት ዝናር ታጥቀው በሕፃኑ ዙርያ ቆሙ፡፡
«ምን አልክ?» ሲል አንደኛው መልአክ ጠየቀው፡፡
«ፈጣሪ ሞቷል» አለና ሕፃኑ ላንቃው እስከሚሰነጠቅ ጮኸ፡፡
«ይህ የድፍረት ኃጢአት ነው፤ ከባድ ወንጀልም ነው፡፡ አንተ ገና ዓለምን አላየህም፤ መጻሕፍትን አላነበብክም፣ ከሰዎች ሕይወት አልተማርክም፤ ከራስህም ሕይወት ልምድ አልቀሰምክም፡፡ እንዴት ከጥቂት ሰዓታት በፊት ተወልደህ እንዲህ ያለ ድፍረት ይወጣሃል» ሲል ተናገረው መልአኩ በቁጣ፡፡
«ልክ ነው» አለ ሕፃኑ፡፡ «ልክ ነው የተናገርኩት ድፍረት እንደሆነ፤ እመቀ እመቃት የሚከት ኃጢአት እንደሆነም ዐውቃለሁ» አለ ሕፃኑ በዙርያው የከበቡትን መላእክት በለጋ ዓይኑ እያየ፡፡ «ግን እስኪ ልጠይቃችሁ? ሕይወት የሰጠችኝ እናቴ ከሞተች፣ ለዓለም ሕይወት የሰጠ ፈጣሪ ሞቷል ማለት ነውኮ፡፡ እናቴኮ የፈጣሪን አደራ ተረክባ የፈጣሪን ሥራ ነበር የሠራችው፡፡ ሕይወትን ለሰጠ ዋጋው ሞት ከሆነ ለዓለም ሕይወትን ለሰጠ ፈጣሪ ምን ዋጋ ተከፈለው ታድያ?» ሲል ጠየቃቸው፡፡
በዚህ ጊዜ የብዙዎቹ መላእክት ሰይፎች ቀዘቀዙ፡፡ የአንዳንዶቹም ወደ ሰገባቸው ተመለሱ፡፡ ሌሎች ደግሞ ያንን የሰዓታት ሕፃን በአንክሮ ተመለከቱት፡፡ እንዲህ ያለ ነገር አጋጥሞት የማያውቀው ሞት ግራ ተጋባ፡፡ ጉዳዩ በዚህ እንደማያቆም ገባው መሰል እፍን አድርጎ ይዟት የነበረውን የሁላገርሽን ነፍስ ለቀቅ አደረጋት፡፡
ወዲያው ምድርን ከአፅናፍ እስከ አጽናፍ ያነጋነገ ክስተት ተፈጠረ፡፡
ፀሐይ ጨለመች፡፡ ከዋክብት ረገፉ፡፡ ወንዞች እና ምንጮች ደረቁ፡፡ አየራት ጸጥ አሉ፡፡ ምድር መዞሯን አቋርጣ ቆመች፡፡ በሕፃኑ ዙርያ የቆሙት መላእክት የምጽአት ቀን የመጣ መሰላቸውና ሰይፋቸውን መዘዙ፡፡
ከሰማያት የመጣ ድምጽ ግን ፍጡራንን እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፡፡ «ለምን እንዲህ አደረጋችሁ?»
ፀሐይም ተነሣች፡፡ እንዲህም አለች «እኔ ለዚህ ዓለም ሌት ተቀን ብርሃንን እሰጣለሁ፡፡ እኔ የምሰጠውን ብርሃን የሚቀበል፣ ነገር ግን ብርሃኑን የምሰጠውን እኔን የማይፈልግ ሕግ ካለ ለምን እኖራለሁ?»
ከዋክብቱ «የኛም ጥያቄ ነው» አሉና ብልጭ፣ብልጭ፣ ብልጭልጭ ብለው አጨበጨቡ፡፡
ወንዞችም እንዲህ አሉ፡ «ውኃ የሚሰጥ ወንዝ እንዲደርቅ ከተደረገ የኛ መኖርስ ለምንድን ነው?»
ምንጮችም «ይህ የኛም ጥያቄ ነው» አሉና ፏፏቴ አሰሙ፡፡
አየራትም አሉ «የኛን አየር እየተነፈሱ እኛን የሚበክሉን ከሆነ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ መኖር አንፈ ልግም»ከአራቱ መዓዝናት የተነሡ ነፋሳትም ዊይይይይው፣ዊይይይይው ብለው አጨበጨቡ፡፡
ምድርም ተናገረች፣ እንዲህም አለች «እኔ እዞራለሁ፣ ቀንና ሌሊትን አፈራርቃለሁ፣ ለኑሮ አስፈላጊ የሆኑትን ሁሉ እሰጣለሁ፤ አገልግሎቴን እንጂ እኔን ካልፈለጉኝ፤ ጥቅሜን ወስደው እኔን በኬሚካል እና በበካይ ጋዝ ከገደሉኝ ለምን እዞራለሁ፤ ዛፎቼን ቆርጠው ሳንባ ከነሱኝ ለምን እንከራተታለሁ?»
የፍጡራን አቤቱታ ሲያበቃ ሕፃኑ ቀጠለ
«እኔ ለፈጣሪ አንድ ጥያቄ አለኝ»
ከሰማይ የመጣውም ድምጽ «ተናገር» አለው፡፡
«አንተ የሕይወት መገኛ ነህ፤ ግን አንተ ትሞታለህ?» አለና ጠየቀ፡፡
በዚህ ጊዜ ሞት ደነገጠ፤ ነገሩ በእርሱ ላይ የተጠመጠመ መሰለውና የሁላገርሽን ነፍስ በሁለት እጁ እንደ ማቀፍ አደረጋት፡፡ ምንም እንኳን የሞት እቅፍ ባይሞቅ፡፡
«ደግሞስ» አለ ሕፃኑ «አባት እና እናታችሁን አክብሩ ብለሃል፤እኔ ስወለድ እናቴ ከሞተች ሕግህ እንዴት አድርጎ ይፈጸማል? እናትነትስ እንዴት ክብር ይሆናል? መውለድኮ በዓለም ላይ ትልቁ ኃላፊነት ነው፡፡ ሰዎች ገንዘብ፣ ወርቅ፣ አልማዝ በኃላፊነት ሊቀበሉ ይችላሉ፡፡ እነዚህን ሁሉ ግን ሰው ይበልጣቸዋል፡፡ ሰውን ያህል ፍጡር በኃላፊነት ተቀብሎ፤ተሸክሞ፤አሳድጎ፤ከሚበሉት አካፍሎ፤ተጠንቅቆ፤የራስን ሕይወት አካፍሎ፤መከራን ተቀብሎ ሰው ማድረግ የፈጣሪን ሥራ መሳተፍ ነው፡፡ ይህንን ኃላፊነት የተወጣች እናት መሸለም ሲገባት እንዴት ሞት ይታዘዝባት?
«እንዲያውም አንድ ሕይወት ለሰጠች ሁለት ይገባት ነበር፡፡ እርሷኮ ሠላሳ፣ ስድሳ፣ መቶ ያፈራች ዛፍ ናት፤ እንዴት ትቆረጣለች? የፍትሕ ሀገሯ የት ነው? የርትዕስ ማደርያዋ ወዴት አለ?
«ከዚህ በላይስ ፍቅር ወዴት ይገኛል? ሕይወት ለመስጠት ሲሉ ከመሞት፣ ራስን ለሌላ ሲሉ ከመሠዋት በላይስ ፍቅር የታለ? የፍቅር ዋጋውስ ይህ ነውን? ራሱ ፈጣሪስ ፍቅር አይደለምን? ታድያ ለዚህ ፍቅሩ ዋጋው ሞት መሆን አለበትን?
እነሆ ከሰማይ ድምፅ መጣ፡፡
«ሕይወት የምትሰጥ እናት ሕይወት እየሰጠች በወሊድ መሞት የለባትም፤ ለሕይወት ሞት፤ ለደግነትም ክፋት፣ ለጣፋጭም መራራ ሊከፈል አይገባም» አለ፡፡
ይህን ጊዜ ሞት የሁላገርሽን ነፍስ ወደ መሬት ለቀቃት፡፡ መላእክትም እልል አሉ፡፡ የመላእክትን ድምፅ ሰምተውም ለልቅሶ ተዘጋጅተው የነበሩ የመንደሯ ሴቶች አብረው እልል አሉ፡፡
«እናት ሕይወት ስትሰጥ ሕይወቷን እንድታጣ ያደረገ ባል፣ መንደርተኛ፣ ሐኪም፣ ሾፌር፣ መድኃኒት ሻጭ፣ርዳታ ሰጭ፣አዋላጅ፣እስከ ሰባት ትውልድ ነፍሱ አትማርም» የሚል አዋጅም ታወጀ፡፡
ይህን ጊዜ በቤቱ የሕፃን ልቅሶ ተሰማ፤ የመንደሩም ልቅሶ በሁለት እልልታ ታጀበ፡፡ በሁላገርሽ ትንሣኤ እና በሕፃኑ መወለድ፡፡
gosh! gosh! gosh! I am surprise for the last news. thanks to God.
ReplyDelete«እናት ሕይወት ስትሰጥ ሕይወቷን እንድታጣ ያደረገ ባል፣ መንደርተኛ፣ ሐኪም፣ ሾፌር፣ መድኃኒት ሻጭ፣ርዳታ ሰጭ፣አዋላጅ፣እስከ ሰባት ትውልድ ነፍሱ አትማርም» የሚል አዋጅም ታወጀ፡፡
ReplyDelete"እናት ሕይወት ስትሰጥ ሕይወቷን እንድታጣ ያደረገ ባል፣ መንደርተኛ፣ ሐኪም፣ ሾፌር፣ መድኃኒት ሻጭ፣ርዳታ ሰጭ፣አዋላጅ፣እስከ ሰባት ትውልድ ነፍሱ አትማርም::"
ReplyDeleteከድንቁርናችን ሕይወትን ሊሰጡን የደከሙልንን ሊቆቻችንን ሁሉ “ከደማችን የተዋሐደው” (የገብረሕይወት ባይከዳኝ ሐረግ ነው፡፡) ድንቁርና በመውጣት በዕውቀት ተወልደን፣ ዕውቀትን እንድንወልድ ሲመክሩን ፈጽሞ ባለመስማትና በማጥላላት ስለገደልናቸው፤ የጥንቶቹን ደግሞ ዕውቀታቸውን “አገር አቆርቋዥ፣ የማይጠቅም፣ ኋላ ቀር የደብተራ ትምህርት” ብለን በመጣል ልፋታቸውን ዋጋ በማሳጣት ሲጥ ስላደረግናቸው ይሆን ዛሬ ያለው “ሁለተኛ ደረጃ ድንቁርና” (አዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ ያገኘሁት የዶ/ር ዳኛቸው ሐረግ ነው፡፡) ላይ የደረስነው? በዕውቀት እንድንወለድ ሲያምጡን ጭንጋፍ ሆነን በንዴት ጨጓራቸውን አቃጥለን፣ በረኀብ ሥጋቸውን ጨርሰን፣ በሐሜት ማኅበራዊ ሕይወታቸውን ገድለን ስለጣልናቸው ይህ እርግማን ደርሶብን ይሆን? እንጃ!
«እናት ሕይወት ስትሰጥ ሕይወቷን እንድታጣ ያደረገ ባል፣ መንደርተኛ፣ ሐኪም፣ ሾፌር፣ መድኃኒት ሻጭ፣ርዳታ ሰጭ፣አዋላጅ፣እስከ ሰባት ትውልድ ነፍሱ አትማርም» የሚል አዋጅም ታወጀ፡፡
ReplyDeleteእግዚአብሔር በነብያቱ አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ ብሎ ተናግሯል
ReplyDeleteእንዲሁም እግዚአብሔር በአንድም በሌላም ያስተምራል ይባል የለ
ስለዘህ አንተም ለማህበረ ክርስትያኑ በተለያየ መልኩ ማቅረብህ ይበል የመያሰኝ ነውና
በርታ ምከረን በተለይ ወጣቱ በቀጥታ ስለሃይማኖት ብትሰብከው አይዋጥለትምና እንደዝህ ባለ መልኩ
ማስተማርህ ደስ ይላል በርታ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር
Hi!De Dani glory to be God!same one that gave life to same one why we judge death?good view.
ReplyDeleteመውለድኮ በዓለም ላይ ትልቁ ኃላፊነት ነው፡፡ ሰዎች ገንዘብ፣ ወርቅ፣ አልማዝ በኃላፊነት ሊቀበሉ ይችላሉ፡፡ እነዚህን ሁሉ ግን ሰው ይበልጣቸዋል፡፡ ሰውን ያህል ፍጡር በኃላፊነት ተቀብሎ፤ተሸክሞ፤አሳድጎ፤ከሚበሉት አካፍሎ፤ተጠንቅቆ፤የራስን ሕይወት አካፍሎ፤መከራን ተቀብሎ ሰው ማድረግ የፈጣሪን ሥራ መሳተፍ ነው፡፡..Egziyabiher Amlak tsegawun abizito Yisitih...Ethiopiyaye.from Italy
ReplyDeleteinteresting! Keep it up danie. GOD BELESS U AND WITH U.
ReplyDeleteDear Daniel,
ReplyDeleteThanks to your touching article.
Mother is the God reason for our existence. One can argue like, "the moment a child is born, the mother is also born. She never existed before. The woman existed, but the mother, never.A mother is something absolutely new.
Like wise the late Abraham Lincoln stated that,"I remember my mother's prayers and they have always followed me. They have clung to me all my life."
«አባት እና እናታችሁን አክብሩ ብለሃል፤እኔ ስወለድ እናቴ ከሞተች ሕግህ እንዴት አድርጎ ይፈጸማል? እናትነትስ እንዴት ክብር ይሆናል? መውለድኮ በዓለም ላይ ትልቁ ኃላፊነት ነው፡፡ ሰዎች ገንዘብ፣ ወርቅ፣ አልማዝ በኃላፊነት ሊቀበሉ ይችላሉ፡፡ እነዚህን ሁሉ ግን ሰው ይበልጣቸዋል፡፡ ሰውን ያህል ፍጡር በኃላፊነት ተቀብሎ፤ተሸክሞ፤አሳድጎ፤ከሚበሉት አካፍሎ፤ተጠንቅቆ፤የራስን ሕይወት አካፍሎ፤መከራን ተቀብሎ ሰው ማድረግ የፈጣሪን ሥራ መሳተፍ ነው፡፡ ይህንን ኃላፊነት የተወጣች እናት መሸለም ሲገባት እንዴት ሞት ይታዘዝባት?
«እንዲያውም አንድ ሕይወት ለሰጠች ሁለት ይገባት ነበር፡፡ እርሷኮ ሠላሳ፣ ስድሳ፣ መቶ ያፈራች ዛፍ ናት፤ እንዴት ትቆረጣለች? የፍትሕ ሀገሯ የት ነው? የርትዕስ ማደርያዋ ወዴት አለ?
«ከዚህ በላይስ ፍቅር ወዴት ይገኛል? ሕይወት ለመስጠት ሲሉ ከመሞት፣ ራስን ለሌላ ሲሉ ከመሠዋት በላይስ ፍቅር የታለ? የፍቅር ዋጋውስ ይህ ነውን? ራሱ ፈጣሪስ ፍቅር አይደለምን? ታድያ ለዚህ ፍቅሩ ዋጋው ሞት መሆን አለበትን?
ዳኒ እግዚአብሔር ይስጥህ፡፡ ጨምሮ ጨምሮ ይስጥህ፡፡
ReplyDeletewendem daniel hulem yemetawetachew tsehufoch astemariwoch nachew. EGEZIABEHER TEBEBUN YABEZALEH. hiwoten yemeteset andit enat be welid mekeneyat hiwetwan matat yelebatem.
ReplyDeleteOH GOD.......DANI EJIG YGERMAL ,BEWNET HULUM YETENA BALEMUYA ENA HAGER ALEMALEHU YEMIL LYANEBEW YEMIGEBA !!!!!!
ReplyDeleteእናቶቻችን እኛን ወደዚች ዓለም ለማምጣት ከእግዚአብሔር አደራ የተቀበሉ ታማኝና የፍቅር ተምሳሌት ናቸው፡፡ ስለዚህ በወሊድ ምክንያት አይሙቱብን፤ እነርሱ ከሞቱ ፍቅርን ማን ያስለምደናል? አናትኮ… ምድርም በበካይ ነገሮችና ሰው ሰራሽ ምክንያቶች ከመጥፋት ልትድን ይገባታልና ሁሉም የራሱን ድርሻ መወጣት ይገባዋል፡፡ ገዳማቶቻችን የቆዩልንን የደን ሃብት ባለማቃጠል አደራችንን ለትውልድ ማስተላለፍም ይጠበቅብናል፡፡ ዳኒ በምሳሌ ማስተማርህን ቀጥልበት ከጌታህ የተማርከው ነውና፡፡
ReplyDeleteIt is true why the mother died when they born?
ReplyDeletemaki
“ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ!?” እነ ላሊበላስ፣አክሱምስ … ላለመፍረሳቸው ምን ዋስትና አለ? አንድ ቀን ግን ፈጣሪ ፊቱን ያዞራል፤ግን መቼ ይሆን? ነጋሪ አያሳጣን::
ReplyDeleteእናት ለምን ትሙት ትሂድ አጎንብሳ ታበላ የለም ወይ በጨለማ ዳብሳ
ReplyDelete«ግን እስኪ ልጠይቃችሁ? ሕይወት
ReplyDeleteየሰጠችኝ እናቴ ከሞተች፣ ለዓለም
ሕይወት የሰጠ ፈጣሪ ሞቷል ማለት
ነውኮ፡፡ እናቴኮ የፈጣሪን አደራ ተረክባ
የፈጣሪን ሥራ ነበር የሠራችው፡፡
ሕይወትን ለሰጠ ዋጋው ሞት ከሆነ
ለዓለም ሕይወትን ለሰጠ ፈጣሪ ምን
ዋጋ ተከፈለው ታድያ?» Nice view!
Please don't kill our true mother for the sake of unknown future. she will give more life than you who the killers are thinking. if you are going to kill her cruelly,"እናት ሕይወት ስትሰጥ ሕይወቷን እንድታጣ ያደረገ ባል፣ መንደርተኛ፣ ሐኪም፣ ሾፌር፣ መድኃኒት ሻጭ፣ርዳታ ሰጭ፣አዋላጅ፣እስከ ሰባት ትውልድ ነፍሱ አትማርም::" will come even if it seems too late.
ReplyDeleteThank you Daniel!
always amazing and fantastic post. May GOD bless you. I am happy when i read your smart post.
ReplyDeleteየእማማዬ ሁላገርሽ (ሁሉሃገርሽ) አምላክ አሁንም እሱ የፈጠራት መድሐኒተ አለም!!! ፊቱን አይስውርባት ይጠብቃት አሚን፣፣ ውንድማችን ዲያቆን ዳንኤል እድሜ ጤና ይስጥልን በርታልን፣፣
ReplyDeletetanx so much, it is a great of all...
ReplyDeletedn.dani የፍትሕ ሀገሯ የት ነው? የርትዕስ ማደርያዋ ወዴት አለ? I need to know!
ReplyDeleteTenaye Araya
Thank You Danie
ReplyDeleteAmilak lante yihinin tsega sileseteh Yetemesegene yihun, I love it man!!!!! Thanks.
ReplyDeleteWhat amazing article; God Bless You. Many mothers are suffering in our country by moving around from one hospital to another to find a place they can be accepted to deliver there babys. In the mean time the baby born in the taxi on hospital floors many many things happen . Sometime tha baby died or most of the time the mother bleed to death it is not fair and the person who is in charge they need to have humanity and help that mother to avoid accident like that. At least
ReplyDeletecheck the mother how far she is before telling her you don't have any bed available to deliver the baby and send her another hosopital. If you know she can't make it to go another hospital do everything you can on your power with God to help and deliver the baby then you couled refer her for the next steep. By doing this you save one generation & you make history. The mother with the labor is in a lots of pain more than we can imagine.please help help help !!! around you . God Bless You Danie to bring this important issue . I hope we all learn something from it .
amazing, blessed to your brain and to your fingers.
ReplyDeleteዲ/ን ዳንኤል እንደምን አለህ? አንድ ነገር ሰምቼ በሃሜት እንዳልጎዳ ከአንተው ማረጋገጥ ፈለግሁ። እባክህን እውነቱን ንገረኝ። በቅርቡ ገብርሔር በተሰኘው ብሎግ ላይ የዋልድባ ገዳምን አስመልክቶ ያለውን “ሁለተኛ መረጃ'' (የሰከነ ልቡና የሚሻው የዋልድባ ገዳማት ህልውና እና የመንግስት የልማት እንቅስቃሴ!!!!
ReplyDeleteየጻፍከው አንተ ነህ የሚል መረጃ አግኝቻለሁ። መረጃውን ለማመን/ላለማመን ከአንተ እውነቱን መስማት ይቻላል የሚን እምነት አለኝ። አሁን የምጠይቅህ ጽሑፉ ያንተ መሆኑን /ያለመሆኑን እንድታረጋግጥልኝ ሳይሆን ሰለዋልድባ ገዳምና ስለታቀደው የልማት ሥራ ያለህን ግንዛቤ በብሎግህ ላይ በማውጣት አቋምህን እንድትገልጽ ነው። በእኔ እምነት የታቀደው ልማት የገዳሙን ህልውና የማይነካ ከሆነ ልማቱን በማደናቀፍ የሚገኝ ጽድቅም ሆነ ምድራዊ ጥቅም ያለ አይመስለኝም። ስለሆነም ትክክለኛውን መረጃ መስጠት አንተንም ሆነ ሌሎች የቤተክርስቲያን መምህራንን ሊያሰፈራችሁ አይገባም ። ለማንኛውም የምታምነውን ለመናገር ሞክር።
I am sure Dn.Daniel didnot write that, if it was why not he post it on his blog rather than the other.ferto? it couldn't be. Now adays when some kind of good writing is posted, it is said to be of Dn.Daniel. I agree that Dn. is a matured writer, but it doesn't mean that no other person couldn't think, write like him.Esun yemeselu sewoch endibezulin degmo enfelgalen.
DeleteEnat yetebalech Ethiopia nat,lij yetebalew degimo Ethiopian yemitadeg meri new. Kenun yaqirbew.
ReplyDeleteሠናይ
ReplyDeleteEndante aynetun yabzalin. Egziabher Yitebekeh.
ReplyDeleteTena Yistilign, Dn Daniel.
ReplyDeleteWhen I read this article, I was trying to see the real message that you wanted to convey. I was sure that you were not just talking about a God-mother-son relationship, which was too obvious and would make your story silly. For me, the life of the article was its strong sentiment and great wish for Ethiopia, our country which is being tormented after giving birth to the current never-seen-before serpents. I especially liked the last couple of paragraphs which reflected the wish of most Ethiopians today - to see those who are destroying Ethiopia, its people and religion be held accountable and receive the punishment they deserve both in this and the coming world.
P.S. Dn Daniel, I can't help noticing that most of your readers are just your loyal followers who clap their hands to whatever you write without trying to see a little bit deeper into what is written.
'Tike Senay',touching article,it send a great msg into z minds of ppls in d/t hierarchy.
ReplyDeleteTike Senay touching article,it send a great msg into z minds of ppls in d/t hierarchy.
ReplyDeletenoting else like mother in our universe thank u diakon danny always u posted amazing thing and the very interested for the people .thank u god bless u
ReplyDeleteDani please say something about the rapes going on in the universities. A lot of our sisters are hurting
ReplyDelete«አባት እና እናታችሁን አክብሩ ብለሃል፤እኔ ስወለድ እናቴ ከሞተች ሕግህ እንዴት አድርጎ ይፈጸማል? እናትነትስ እንዴት ክብር ይሆናል?«ይህ ከሆነማ እኔም እከተልሃለሁ፡፡ ምጣዱን የሚሰብር እንጀራ መሆን የምፈልግ ይመስልሃል?» አልሁ እኔ ሕፃኑ፡፡b/s the death of my country is the death of me!!!!Please My God, do me a fever,Give back a honer to my mother ! or give me your permission to follow her!!!! Thanks daniye!!!!what is our benefit with out our motherhood??? Bless you! You touch me deep!!!
ReplyDeletei agree with Kinfe-Michael.... Mr. Daniel most followers of your do not bother about what you exactly want to transmit via the message. they just see the literal meaning. they don't get the real message. that is why they support and appreciate you. i also appreciate your writing skill and it is very good.
ReplyDeleteThe hidden analogy that you have tried to create in our mind and the real mother and son relationship doesn't match......i wish you explicitly tell us who the mother and the son stands for.....
those of you who write comments like wow , pa pa pa .... please read it again and again express your feeling with full consciousness......
Besentu enekatel bakachuhe