Tuesday, March 6, 2012

ሁኔታ ነው ያለው


አንድ የሠፈራችን ሰው ለሥልጠና ወደ አንድ ቦታ ሄደው ሲመለሱ በአንድ ልቅሶ ላይ ተገናኘን፡፡ እኒህ የመንደራችን ሰው ሄደው ስለመጡበት ጉዳይ በዝርዝር እንዲህ አውርተውን ነበር፡፡
«ከእንቶኔ ክልል ልምድ ለመቅሰም ከየቀበሌው አንድ አንድ ሰው የተመረጠበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ እኔም ከተመረጡት መካከል አንዱ የሆንኩበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ለጉዟችንም አንድ ሳምንት ያህል ዝግጅት ያደረግንበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ የሚወስደን መኪና ከመስቀል አደባባይ የተነሣበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡
ወደ ክልሉ ዋና ከተማ ለመድረስ ስድስት ሰዓት ያህል የተጓዝንበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ በመንገዳችን ላይ ስለ ጉዟችን እና ምን መቅሰም እንዳለብን ስንወያይ የነበረበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ከዚህ በፊት የጉብኝት ልምድ ያላቸው አባላት በመካከላችን የተገኙበት ሁኔታ ነበረ፡፡ እኛም ከእነርሱ ጠቃሚ ልምድ ያገኘንበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡
በየደረስንበት ከተማ ደማቅ አቀባበል የተደረገልን ሁኔታ ነው ያለው፡፡ እኛም በአቀባበላቸው በመደሰት አጸፋውን የመለስንበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ የየአካባቢውን ባህል ለማሳደግ እና የገበያ ዕድል ለመፍጠር ስንል ከየአካባቢው ባህላዊ ዕቃዎችን የገዛንበት ሁኔታ ነበረ፡፡ ይህም የአካባቢውን መልካም ገጽታ ለመገንባት አስተዋጽዖ ያደረገበት ሁኔታ ነው ያለው
በክልሉ ዋና ከተማ ስንደርስ ባለ ሥልጣናት የተቀበሉን ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ከዚያም ወደ ማረፊያችን የተጓዝንበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ እኛም ማታ ላይ ወጣ ብለን አካባባቢውን የጎበኘንበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ከጉብኝታችንም ስለ ከተማው የንግድ እንቅስቃሴ በሚገባ የተረዳንበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡
የከተማው ጸጥታም በሚገባ የተጠበቀበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡
በማግሥቱ በወጣልን መርሐ ግብር መሠረት ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን የተመለከትንበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ አካባቢው በልማት አበረታች የሆነ ለውጥ ላይ መሆኑን የተረዳንበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ይህንን ልምድም ወደ የአካባቢያችን ለመውሰድ ቃል የገባንበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡
በየአካባቢው ካሉ ኃላፊዎችም ጋር የተወያየንበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ከኛም መውሰድ ያለባቸውን ልምድ የነገርንበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡
ለሦስት ቀን ያደረግነው ጉዞ በመጨረሻ በተዘጋጀው የእራት ግብዣ የተጠናቀቀበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ በፕሮግራሙም ላይ የአካባቢውን ባህል የሚያንጸባርቅ ስጦታ ለኛ የተሰጠበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡
ስንመለስ ጉዟችን አስደሳች የነበረበት ሀኔታ ነው ያለው፡፡ ቀልድ የሚያወሩ፣ ያገኙትን ልምድ በሚገባ የሚገልጡ፣ ማብራርያ የሚሰጡ የቡድን አባላት የነበሩበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡
በመጨረሻም ትናንት ማታ ቤቴ የገባሁበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ከእናንተ ላለመለየት ስልም ዛሬ በልቅሶ ላይ የተገኘሁበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡» አሉና ጨረሱ፡፡ ብዙዎች እርሳቸው ሲጨርሱ በረዥሙ ተንፍሰዋል፡፡
አንዱ ወዳጃችን ግን «ቆይ እርስዎ ከዚያ ክልል የወሰዱት ልምድ ሁኔታ ነው ያለው የሚለውን ነው እንዴ?» አላቸው፡፡
«አንተ በእኔ ንግግር ተገርመህ ነው ? እንዲያውም እኔ ቀንሼው ነው እንጂ አስጎብኚዎቻችንማ "ሁኔታ ነው ያለው " በሚለው ውስጥ ሌላ "ሁኔታ ነው ያለው " እየጨመሩ ነበር ያስጎበኙን» አሉን አረፉት፡፡

52 comments:

 1. mliekitochih ende hager ende Ygil sibenam asitmare nwu lela yemilew Ylegnm

  ReplyDelete
 2. Thanks Dani, it is great

  ReplyDelete
 3. dear.it is not much valuable article.we miss ur well elaborated articles about religion,politics,culture.etc.pls dn say sth more about current issues.ye'anten tshufoch eynafekin yalebet huneta new yalew,ha..huh.May God guide u!

  ReplyDelete
 4. Daniye please tell ETV AND RADIO STATION "JORNALISTS" that this is meant for those limatawi gazetegnoch!!!

  ReplyDelete
 5. እረ በጣም ያስቃል ይሄንን ቃል የበለጠ ጠላሁት ዳኒ

  ReplyDelete
 6. ሁኔታዉ እውነታውን አስጠፋብን እኮ፡፡ ከዓመት በፊት በኤፍ. ኤ. ጨዋታ ላይ ማን. ዩናይትድ ሊቨርፑልን 1 ለ 0 አሸንፎ አንዱ የኢቲቪ ጋዜጠኛ “ማን. ዩናይትድ ሊቨርፑልን 1 ለ 0 ያሸነፈበት ሁኔታ ነው ያለው::” ብሎ ያነበበውን አስታወስከኝ፡፡ የዚያኑ ያህል “በነገራችን ላይ የምትለዋ ሐረግ ከመደጋገሟ የተነሳ ዋናውን ርእስ ስትውጥ በብዙ (ባሉቱ) ሚዲያዎች እያስተዋልን ነው፡፡ ”
  በነገራችን ላይ እ/ር ይባርክህ፡፡ (ቂ. ቂ.ቂ.)
  ይልማ ከሀዋሳ
  ሁኔታዉ እውነታውን አስጠፋብን እኮ፡፡ ከዓመት በፊት በኤፍ. ኤ. ጨዋታ ላይ ማን. ዩናይትድ ሊቨርፑልን 1 ለ 0 አሸንፎ አንዱ የኢቲቪ ጋዜጠኛ “ማን. ዩናይትድ ሊቨርፑልን 1 ለ 0 ያሸነፈበት ሁኔታ ነው ያለው::” ብሎ ያነበበውን አስታወስከኝ፡፡ የዚያኑ ያህል “በነገራችን ላይ የምትለዋ ሐረግ ከመደጋገሟ የተነሳ ዋናውን ርእስ ስትውጥ በብዙ (ባሉቱ) ሚዲያዎች እያስተዋልን ነው፡፡ ”
  በነገራችን ላይ እ/ር ይባርክህ፡፡ (ቂ. ቂ.ቂ.)
  ይልማ ከሀዋሳ

  ReplyDelete
 7. ዲ/ን ዳንኤል የመንግስትን ሚዲያዎች በግልጽ እየተቸህ ያለህበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Asteyayetu ejig betam yasaqegn huneta new yalew!

   Delete
 8. Thanks Dn Daniel

  leloch temesasay limdochim alu. Beteley Ke gazetegnoch.

  ReplyDelete
 9. ቂቂቂቂቂ....... አይ ወጉ! መኮረጁ ነው እንጅ፡፡

  ReplyDelete
 10. ዲ/ን ዳንኤል እኔን የሚገርመኝ ትምህርት ሰጪ ጽሁፎችህ የሚይዙትና የሚያስተላልፉት መልእክት እንዳለ ሆኖ የአንድን አፀያፊ ድርጊት ወይም አባባል ርእስ አግኝተህ ለኛ ማስተላለፍ መቻልህ ችሎታህና ተሰጦህ ከሌላው እንድትለይ ያደርግሃል። እግዚአብሄር የከፈተልህን አዕምሮ ለወደፊቱም ለበጎ ነገር ብቻ እንድትጠቀምበት እየፀለይኩ መጥፎ መጥፎውን በመፀየፍ በጎ በጎውንና የእውነት አምላካችን የሚወደውን እንድታስነብበን የወንድምነት ጥርኝና ኮሳሳ ምክሬን ትቀበለኛለህ በማለት ልኬልሃለሁ።
  ይህ ጽሁፍህ ከመጠን በላይ ሰው በጉያዬ ገብቶ የኮረኮረኝ እስኪመስለኝ ነው ያንፈቀፈቀኝ። ደሞ ዘንግተኽው ይሆናል እንጂ "ዲሞክራሲ ተደርጉዋልስ" የሚል ባለፈው እንዳስነበብከን ዓይነት መጣያስ እንደው ጣ'ል ሳያደርጉ ቀርተዋል ብለህ ነው? እንደሚመስለኝ እነርሱ የሰለጠነ ሰው መለ'ያ ንግግር አርገውት እንደሚሆን እገምታለሁ። ከዚህ ጋር አስታክኬ ለአንባቢዎችህ አስተያየት ሰጪዎች የምለው አለኝ። ለምን የአንተን ጽሁፍ እንደገና እንደአስተያየት ደግመው ያስነብቡናል? ይህም አሳፋሪ እንደሆነ እንዲረዱልኝ አሳስብልኝ። እንዴ ቁምነገሩን አንብቦ አስተያየት አለመጻፍም ጀግንነት እኮ ነው።
  ሌላው ደግሞ የሚገርመኝ አሁን ለዚህ ጽሁፍህ ቃለ ሕይወት ያሰማልን እያሉ የሚያላግጡትን ሳስብ ነው። እንደእኔ እንደእኔ ቃለ ሕይወት ሊሆን የሚችለውና የሚሆነውም የእግዚአብሄር ቃል ሲሆን ብቻ ይመስለኛል። ከተሳሳትኩ ለመማርና ለመታረም ዝግጁ ብቻ ሳልሆን ንቁም ነኝ። ማህበራዊና ፖለቲካዊ ገጽታዎቻችንን ሸረፍ ሸረፍ አድርገህ ስታስነብበን የመንፈስ እርካታ ማግኜት እንችል ይሆናል እንጂ የሕይወት ቃል ሊሆነን አይችልም ብይ ነኝና ወይ እኔው እንድታረም ወይ እነርሱ እንዲያውቁ ዳኝነት ቢታይልኝ ደስተኛ እንደምሆን በመግለጽ ሳልሙዋዘዝ ልሰናበትህ።

  ReplyDelete
 11. ሊተሰመርበት ያለ ጉዳይ ነው ዳ.ዳንኤል..'ወፍ እንደሃገሯ ትጮሃለች ቢባል ምን ይገርማል'
  መሪ ጌታ በወፍ አፍ ቢናገሩ ይገርመኝ ይሆናል:ለጨዋው ግራ ነው ለሊቁ ግን ተርጓሚም አይሻም:..ግን ፊደል ከጥግ እስከ ጥግ ተዘርግቶ ምነው..ጋሼን ያለበት ጉዳይ በላቸው:
  አጉል አባዜ..እንበለው ወይስ ሌላ? ምኝቴ ብዙነህ @ ፍሎሪዳ ጫካ..

  ReplyDelete
 12. bewananet ende atekalay endakitacha singemegimew aberetach huneta new yalew!!!

  ReplyDelete
 13. Afrodayt /KARLSUHEMarch 6, 2012 at 10:11 PM

  ለመደኝና ሳየኝ ይስቃል ነው ያለው ያገሪ ሰው በሁኔታው ላይ ለምጄ ሁኔታው ላይ ነው ያለው ብሎ ሳቀብኝ....ቂቂቂ...

  ReplyDelete
 14. How about " malet new " in between every sentence

  ReplyDelete
 15. Ene Be'ewnetu yetsehufu meleket befitsum algebangim.Melekit yemihone neger sitebik tsihufu aleke

  ReplyDelete
 16. D.n Daniel, minim enquan milketawochih girum bihonum le'ante gin wubtih HAYIMANOT newu. .wub.

  ReplyDelete
 17. ጨዋ በሆነ መልኩ የገሰፅክበት ሁኔታ ነዉ ያለዉ ዳኒ
  "ሁኔታ ነዉ ያለዉ"ን ለመጨረሻ ጊዜ መጠቀሜን ልብ ይሉአል!!!

  ReplyDelete
 18. Dear Daniel,

  This is really nice intervention. I do recall that at one point of time every government officials put the term like " it is one and one. They imitate the term from H.E. PM Melese.

  ReplyDelete
 19. ዳኒ እውነት ነው የምልህ ንባቡ አልገፋልህ አለኝ! ያቅለሸልሻል፡፡ ግን ምን አስታዎሰኝ መሰለህ ከዛሬ 16 አመት በፊት ዕለቱን እረሳሁት ከባልንጀራዬ ጋር 5 ኪሎ በሚገኘው ዶን ዶር ሻሂ ቤት ሻሂ እየጠጣን እያለ በዓይን የምናውቃቸው ሁለት ጓደኛሞች አጠገባችን ቀጭ ብለው ያዎጉ ነበር፡፡ በወጋቸው መሃል አንደኛው ሌላውን ለመሆኑ እገሌን አግኝተኸው ታውቃለህ? ብሎ ሲጠይቀው አዎ በቀደም አግኝቸው እዚህ ሻሂ እየጠጣን ነበርና ይገርምሀል አንድ ቃል ተናግሮ you see ሲለኝ እኔም I see ስለው ቆይተን ምን እንዳዎራን ሳላውቀው ተለያየን ሲለው እኔና ጓደኛዬ ከት ብለን ሳቅን እነሱም ደንገጥ ብለው ፈገግ አሉ፡፡ ጨዋታቸውን እኛ የምንሰማ አልመሰላቸውም ነበርና፡፡ እናም እንደዚህ አይነት ቃላቶችን የመደጋገም ብቻ ሳይሆን በሽታ ሆኖብን እያየን ነውና ስንናገር በዎግ በዎጉ ቢሆን መልካም ነው፡፡ ዲምፕል

  ReplyDelete
 20. yea, I hate this word, AND NOW I HATE IT MORE! this kind of words make etv the most boring channel on earth ever! besides their lies
  THANKS Dn Dani, bless u!

  ReplyDelete
 21. ke hulet kene befite be ETV kalemeteyek yetederegelat weyezero betedegagami "yalebet huneyta newe" yemile hareg beyedekikawe setasegeba ayeche sasebewe yeneberewen neger ezihe tetsefo bemayete dese belognale, mekeneyatume endene yetazebe sewe endale bemegenezebe. Betechemari degemo yehe werereshign behulachenm endemizamet sasebewe degemo le amharic sewasew azenalehu.....mekeneyatume negere sidegageme sanasebew yewahadenena yekeral.!!!

  ReplyDelete
 22. Egame bdnebe yenebebenebet huneta new yalewe!

  ReplyDelete
 23. እኔ ልማታዊ የኢትዮጵያ ጋዜጠኛ ብሆን ኖሮ ስለዚህ ጽሑፍ እንዲህ ዓይነት ዜና መሰል ነገር እሠራ ነበር፡፡

  ዳንኤል ክብረትና ግብረጦማሪዎቹ የኢትዮጵያ ልማታዊ ጋዜጠኞችን ቋንቋ አጠቃቀም የሚተቹበት ሁኔታ ተፈጠረ፡፡

  በእውነቱ በአሁኑ ጊዜ ዲያቆን ዳንኤል ክብረትና የጡመራ ተባባሪዎቹ የኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞችን አማርኛ ክሪቲሳይዝ እያደረጉ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ይህ ሁኔታም በብዙኃኑ ዕውቀት አጠር ጋዜጠኛ ዘንድ አንዳችም የመነቃቃትም ሆነ ራስን የመገምገም ሁኔታ ሲፈጥር የማይታይበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ በዚህ ላይ መንግሥትም ሆነ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ይህንን በዕውቀት አጠር ጋዜጠኞቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን ማሸማቀቅ ለመቀልበስ ምንም ዓይነት ጥረት ሲያደርጉ የማይታይበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ በዚህም ሁኔታ “ጋዜጠኞቹ እኛስ ግብር ከፋይ የሆንንበት ሁኔታ አይታሰብልንምን መንግሥትስ ስለምን የግብር ከፋይነታችንን ሁኔታ የሚያይበት ሁኔታ ፈጥሮ ይህንን ከእጅ እጅ አልፎ እግር እግር የሚል የዘቀጠ የቋንቋ ክሂላችንን ባሻን መንገድ የመጠቀም መብታችንን የሚያስከብርበት ሁኔታ ስለምን አያመቻችም?” በማለት የሚጠይቁበት አጋጣሚ ተፈጥሯል፡፡ ይህን አጋጣሚም በመጠቀም ሕዝቡ በጋዜጠኞች ላይ የሚሳለቅበት ሁኔታ እየተፈጠረ መሆኑን መመልከት ተችሏል፡፡ አንዳንድ መረጃዎችም በርካታ ቁጥሮች ያሏቸው ጋዜጠኞች መሳቂያ መሳለቂያ የሆኑበት ሁኔታ እንደተፈጠረ እያመላከቱ ናቸው፡፡ አንዳንድ ምሁራንም የቋንቋ ክሂል ዝቅጠት በሀገሪቱ ያለውን ታላቅ የሆነ አጠቃላይ የትምህርት ዝቅጠት ያመላክታል የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል፡፡ ዳንኤል ክብረት ጸዳ ያለ ቋንቋ ከሚጠቀሙ የሚዲያ ሰዎች አንዱ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ጉዳዩን በሚገባ የተረዱ አስተያየት ሰጪዎች ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው

   Delete
 24. Yihe eko besew saniba Yemetenfes wutet enji lela ayimesilegnim. Andu Amarign ende kumta yaterew betenagariwoch zenid talak sew siyawora tesemito "copy and Paste" yideregal. Beka bezaw yizametal malet new. Gin Siyastell lesemiw ayitl new tuf tuf tuf ....

  ReplyDelete
 25. ይቺ አባባል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በመንጨት የኢ.ቲ.ቪ ጋዜጠኞች ጋር እየደረሰ ያለበት “ሁኔታ ነው ያለው”

  ReplyDelete
 26. hulachenem endezihu eyehone yalenebete huneta new yalew!!!
  Dani good looking!
  thanks!

  ReplyDelete
 27. I heard this phrase also from ETV Yemedia Dasesa program azegajoch...always things are in some circumstance (ሁኔታ ነዉ ያለዉ )in Ethiopia....keep on writing
  God bless you

  ReplyDelete
  Replies
  1. Now a days so many words are transmitted from door to door like a disease for example, (huneta new yalew, bezhi aktacha new yayenew, andandi yadisabeba newariwoch, ……………… etc.,

   Any ways it is good view , thanks Dani.

   Delete
 28. የመስራት ስራ እንስራም እጅግ እየተለመደ የመጣ ቃል ነዉ። ሕዝቡን የማንቃት ሥራ እንሥራ፣ የማሥተማር ሥራ እንሥራ፣ የማደራጀት ሥራ ተሠራ፣ የማብቃት ሥራ መሥራት ያስፈልጋል፣ ወዘተ። አንድ ጓደኛዬ ቃሉ እጅግ ስለሰለቸዉ ዉሃ ልጠጣ ክማለት ይልቅ፤ ውሃ የመጠጣት ሥራ እንሥራ፣ ምግብ የመብላት ሥራ እንሥራ፣ ሰዉነት የመታጠብ ሥራ እንሥራ ወዘተ ይለኛል። አይ ዝቅጠት!

  ReplyDelete
 29. ይመችህ ዳኒ!

  ReplyDelete
 30. oh thank you bro. This is the phrase used by government bodies (if you don't believe me open ETV now and you will hear a lot of and )even our medias are encountering a problem of language.their is also one word which is used as a joker for everything . oh my GOD you don't know how much i hate this word pleas write on it .such kinds of phrases and words shows that how much we are poor in reading,speaking experience and language knowledge.

  ReplyDelete
 31. አሁንም አንተ በግሩም ሁኔታ እየተቸህ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው አይ አማርኛ በጨወዎች አይን ሲታይ እንዲሁም በድንቁርና አስተሳሰብ ሲታይ መገለጫው ይህን ይመስላል ጥሩ ተመልክተሃል እንደ ንስር አሞራ:: እግዚአብሔር እድሜህን ያርዝመው ከመልካም አስተሳሰብህ ጋር
  ያንተው ዘጠበሉ ዮርዳኖስ

  ReplyDelete
 32. ዳኒ በጥሩ ሁኔታ ያየህበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ለኔም እያቃጠሉኝ ያሉትን የ…ጋዜጠኞችን አካሄድ የታዘብኩበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ እንደ አንባቢ ሆኜ ስመለከተው ያንተን አስተዋይነት ያየሁበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ እንደ ጋዜጠኞቹ ከሆነ ግን እንደ …ቆጥሬ ዘብጥያ የምትወርድበትን ሁኔታ የምፈጥርበት ሁኔታ ነበር ያለው፡፡ ይሁንና ይህችን “እንደ”ን ደግሞ ብታይልኝ ደስ የሚል ሁኔታ የሚኖርበት ሁኔታ ያለ ይምስለኛል፡፡ እንደ ወጣት፤እንደ አገር ሽማግሌ፤እንደ ጋዜጠኛ፤እንደ ስፖርት ባለሞያ ወዘተርፈ…ትንሽ በለን እስኪ

  ReplyDelete
 33. ዳኒ በጥሩ ሁኔታ ያየህበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ለኔም እያቃጠሉኝ ያሉትን የ…ጋዜጠኞችን አካሄድ የታዘብኩበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ እንደ አንባቢ ሆኜ ስመለከተው ያንተን አስተዋይነት ያየሁበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ እንደ ጋዜጠኞቹ ከሆነ ግን እንደ …ቆጥሬ ዘብጥያ የምትወርድበትን ሁኔታ የምፈጥርበት ሁኔታ ነበር ያለው፡፡ ይሁንና ይህችን “እንደ”ን ደግሞ ብታይልኝ ደስ የሚል ሁኔታ የሚኖርበት ሁኔታ ያለ ይምስለኛል፡፡ እንደ ወጣት፤እንደ አገር ሽማግሌ፤እንደ ጋዜጠኛ፤እንደ ስፖርት ባለሞያ ወዘተርፈ…ትንሽ በለን እስኪ

  ReplyDelete
 34. Dear DK Daniel Kibret.
  I am addict to read your articles about different religious,social, cultural,humanitarian etc etc issues.most of them are what is in my mind and relay nice.I always admire those wonderful thoughts and ideas.But this one is, though it is true you are much much better than this kind of article.Please focus on big issues and let the so called journalist do such small things.
  I want to read kind of YEZEMED KES,KEWENZU BELAY,etc
  Thanks

  ReplyDelete
 35. In addition "አካባቢ" እና "የሚጠጉ" የሚባሉ ሌሎች ሁለት ቃላት ደግሞ ያሉበት ሁኔታም አለ ፡፡ ለምሳሌ "....የወረዳው አስተዳደር ወደ ሁለት የሚጠጉ ሕንጻዎችን ያስገነባበት ሁኔታ ነው ያለው...."
  How much a building is a building more than one but less than two?

  :)

  ReplyDelete
 36. ሁኔታ ነው ያለው የሚለውን ቃል እየነቀፍን ያለንበት ሁኔታ ነው ያለው!!

  ReplyDelete
 37. ሁኔታ ነው ያለው የሚለውን አባባል ያወገዝንበት ሁኔታ ነው ያለው!!

  ReplyDelete
 38. i really thank and appreciate your pinpoint.
  i think the originator of this phrase is due to the originale lingual syntax and the linguistic determinism. the sickness, however, is 'why do others imitate as if it is a natural language syntax in the amharic syntax?'

  ReplyDelete
 39. Dear, Daniel and dear readers, how have you been? It’s a pleasure to have access to read and post our reflection. I’d like to thank those who have made this happen.
  I think you've read "Animal Farm" by Jorge Orwell. Whenever I watch ETV, the Parlama(parliament),I recall such allegorical novel, for the members of the parlama are fairly represented by the characters of the novel. So are the themes in the parlama.

  More to the point, these people have divorced with their own original identity. Losing one's identity and being cloned seems to be one of the criteria to get into and to "survive" in the parlama. The similarity in their language is one of the manifestations of this fact. This is like playing the same CD with different CD players. Man is "man", man is not a inanimate object (CD) that plays the software/CD given to him.

  What makes such act of self-denying the most surprising and paradoxical is the "place" and the purpose as to why they gather. That should have been where different ideas need to be freely and peacefully raised. Instead, it has become a place where the roar of a "lion" is destructively echoing. It won't be long to see all those people become "bald” as the result of the strategy of cloning a nation.

  It is true; imitation is one way of learning. It is natural and unavoidable. However, hewing others' identity on ours, by any measurement, cannot be an exemplary deed. It is rather a sign of deep identity crises which needs proper medical treatment. So those trainees are not the only victims. We have a lot in and outside.

  Preserve your value and identity. If it has to be changed, let it be changed for the better, but shouldn't be in your expense and in the expense of a nation.

  Peace be upon you and upon those you love!

  ReplyDelete
 40. አስተያየት ሰጭዎችና አንባቢዎችህ ሁሉ ያንተ ግርፍ ሆነው የለምእንዴ የሚያዝናናኝና የሚያስተምረኝ የአንተ ጽሑፍ ብቻ ሳይሆን የአስተያየት ሰጭዎችም ሆኗል፡፡

  ReplyDelete
 41. አንዱ “ባለስልጣን” ቀየር ያሉ ቃላት ከተናገረ የበታቾቹ ጫጩቶች ይሄንኑ ሲያንቆለጳጵሱት ከአንድ ወንዝ የወጡ ለመሆናቸው ምንም የሚያከራክር ነገር የለውም፤የሚገርመኝ ቃላቱን እነሱም ካልደገሙት የሆነ ነገር የጎደላቸው ወይም የሚቀጡ ይመስላቸዋል፡፡ምን ይባላሉ ከንቱ!

  ReplyDelete
 42. huneta new yalw.lelam ale eku.

  mesrt tilenal=ysedimocracy mesret, yeidiket mesert....
  hidase-hidaye dildiy, hidase ethiopia....
  limatawi=limatawi balehabt,limatawi gazetegna, limatawi,arsoader, limatawi,astedader...
  wozet yilunal geziwochachin!!!

  ReplyDelete
 43. A very terrible situation is just happening right now while I writing this blog comments at Ziqual Monastery being getting into fire Every one of us please do your best so as to stop it and not to bring about a lot of damage to the Monastery. Specially those of you who have got the capacity including vehicles.Even the government has to give due attention so as extinguish it by means of any equipments including some Air crafts other wise it is a great damage the county as a whole.The primary responsibility relies on the Ethiopian Orthodox Church Personnel s. They have to deal with any concerned body including inside and outside the country. Otherwise they are the ones to blamed for the destruction.

  ReplyDelete
 44. Dear Daniel....As always you proved to be the only one to see things fromd different angles and we are proud to have you here.as for the ETV journalists Please do your best to read this kind of articles so that you can update yourself.keep up the good work DANI

  ReplyDelete
 45. አንዳንድ ቀልዳቀልድ መፃፍህ ጥሩ ነው ነገር ግን ትኩረት ለመንፈሳዊ ነገር ብትሰጥ ይሻላል::from adama university

  ReplyDelete
 46. ''ke musina yesteda ye sira zerf binor ye taxi sira tetekash new''by Biruk

  ReplyDelete
 47. Ewineten new yemilihi yenadenkewin talaki sew tsihufi anibibe endecheresiku kesiri baluti asiteyayetochiy beahunu seati zena eyaliku yemigegnibeti huneta new yalew kkkk

  ReplyDelete