Friday, March 2, 2012

ጣ'ል


click here for pdf 
አማርኛ እና እንግሊዝኛ እየቀላቀላችሁ ለምን ታወራላችሁ? የሚሉ ሰዎች በጣም ነው የሚያስገርሙኝ፡፡ አሁን እውነት ምክንያቱ ጠፍቷቸው ነው? ለመሆኑ ሊቅነት ምንድን ነው? መቀላቀል ማለት አይደለም እንዴ፡፡ ለመሆኑ ሳይቀላቀል የሚያተርፍ ነገር አለ?
ቆይ ቆይ ግን እነዚህ አጭበርባሪዎች ሙዝ እና ቅቤ፣ ሸክላ እና በርበሬ፣ ስኳር እና የሩዝ ድቃቂ የሚቀላቅሉት ለምን ይመስላችኋል? አንድ ነገር ካልተቀላቀለበት አያተርፍማ፡፡ ወሬ እንኳንኮ ስለ ኢትዮጵያ ብቻ ከተወራ አያተርፍም፡፡ እስኪ ወሬ ሲጀመር እዩ፡፡ ስለ መንደራችሁ፣ ስለ ከተማችሁ፣ ስለ ገጠራችሁ ከአሥር ደቂቃ በላይ ካወራችሁ እንኳን የሚሰማችሁ የሚያያችሁ አታገኙም፡፡ ታድያ በመካከል «አሜሪካን ሀገር» የሚል ' አድርጉበት ወደ እናንተ ያልተቆለመመ አንገት አታገኙም፡፡
እስኪ ጎበዝ ከሆናችሁ ስለ ቡና እና ጊዮርጊስ፣ መከላከያ እና ደደቢት፣ ሲዳማ ቡና እና ሐረር ቢራ ብቻ አውሩ? ራሳቸው ተጫዋቾቹ እንኳን በቅጡ አያዳምጧችሁም፡፡ ያን ጊዜ ታድያ አርሴናል፣ ማንቸስተር፣ ቼልሲ፣ ማድሪድ፣ ባርሴሎና ማለት ትጀምራላችሁ፡፡ መቀላቀል ያለ ነው ጎበዝ፡፡
ለመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ በስሙ ላይ ዴሞክራሲ የሚል ቃል ' ያላደረገ ፓርቲ አይታችሁ ታውቃላችሁ? ድሮ ኮሌጅ ስንማር ዜር ፎር የሚባል ምግብ ነበረን፡፡ በወጡ ውስጥ ከሦስት ፍሬ በላይ ሥጋ የማይገኝበት፡፡ ለስሙ ሥጋ ወጥ ነው፡፡ ሥጋውን ግን ፈልገህ አታገኘውም፡፡ የኛም ዴሞክራሲ እንደ ዜር ፎር ወጥ ' የተደረገ ስለሆነ ፈልጋችሁ አታኙትም፡፡ ' ማድረግ ያለ ነው ጎበዝ፡፡
በኛ ላይ ብቻ ዐቅም አግኝታችሁ የትችት መዓት ታወርዳላችሁ እንጂ እስኪ ሬዲዮውን እና ቴሌቭዥኑን ተከታተሉት፡፡ አዲስ ዐዋጅ ሲታወጅ፣ አዲስ መመሪያ ሲጸድቅ፣ አዲስ መዋቅር ሲሠራ ባለ ሥልጣናቱ፣ «ኤክስፐርቶቹ? ስለ ኢትዮጵያ ብቻ ነው እንዴ የሚያወሩት? ኧረ በጭራሽ፡፡ «ይህ ሕግ» ይሉላችኋል «ከእንግሊዝ የመጣ ነው፣ ከሆላንድ የተወሰደ ነው፣ ከአሜሪካ የተገለበጠ ነው፣ ከጃፓን የተሻለ ነው፣ ከኬንያ የሚመረጥ ነው» አይደል እንዴ የሚሉት፡፡ ካልተቀላቀለ አያዋጣማ፡፡
ፍትሐ ነገሥትን መጠቀም ከጀመረች ሰባት መቶ ዓመት ሊሞላት የደረሰች ሀገር የሕጎቿን ትክክለኛነት ለመግለጥ የእንጀራ አባት ፍለጋ አውሮፓ እና አሜሪካ መንከራተት ነበረባት? ደግሞስ አንድ ሕግ ምርጥ ሕግ ለመባል ከእንግሊዝ እና ከአሜሪካ፣ ከደቡብ አፍሪካ እና ከጋና የተሻለ መሆን አለበት፡፡ እኛኮ እንጀራን የወደድነው ከሕንድ ሩዝ እና ከጣልያን ፓስታ፣ ከኬንያ ኡጋሊ እና ከሜክሲኮ ሾርባ ጋር አወዳድረን አይደለም፡፡ በቃ በራሳችን መመዘኛ መዘንነው ወደድነው፤ አለቀ፡፡
ግን አየህ በዘመኑ ካልተቀላቀለ አያምርም፡፡ ስለዚሀ አትስረቅ የሚል ባህል ቢኖርህም አትስረቅ የሚለውን ሕግ ግን ከጃፓን መውሰድ የግድ ነው፡፡ ' ለማድረግ ፡፡
እንዲያውም ባይገርማችሁ የማይቀላቅሉ የአራዳ ልጆች ብቻ ናቸው፡፡ የራሳቸውን አማርኛ ይፈጥራሉ እንጂ እንግልጣር ከአማርኛ አይቀላቅሉም፡፡ በሀገራቸው ቋንቋ አሟልተው መናገር የሚችሉት አራዶች ብቻ ናቸው፡፡ ምን ዋጋ አለው ታድያ የፋራ ምልክት ሆነ፡፡ እነርሱም ቢጨንቃቸው ፋዘር እና ማዘርን መቀላቀል ጀመሩ፡፡ የሠለጠነ አራዳን ከፋራ አራዳ ለመለየት ያህል ' ያደርጉባታል፡፡
ኧረ ቆይ እንዲያውም ምን እዚያ ድረስ አስኬደኝ፡፡ ባለፈው የጥምቀት በዓል ሲከበር እነማን ነበሩ ከጃንሜዳ በቀጥታ ሥርጭት ቃለ መጠይቅ ሲደረግላቸው የነበሩት እነማን ናቸው? አንድም ፈረንጆች፣ አንድም ከፈረንጅ ጋር ወይ ኖረው ወይ ሠርተው የመጡ፣ አንድም የፈረንጅ ጓደኛ ኖሯቸው እርሱን ተከትለው መድረኩን መጠጋት የቻሉ አይደሉምን?
እኔ ስለ ጥምቀት በዓል ለመናገር ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር በቂ አለመሆኑን፣ የኢትዮጵያን ዕድገት ለመገምገም ለዕድገቱ የሚሆን ግብር መክፈል በቂ አለመሆኑን፣ ስለ ኢትዮጵያን በሚገባ ለመግለጥ ከውጭ ወደ ውስጥ ማየት የግድ መሆኑን ያወቅኩት ያኔ ነው፡፡ በጋዜጠኛው አልፈርድም፤ ወዶ አይደለማ፡፡ ካልተቀላቀለ አያዋጣም ብሎ ነውኮ፡፡ በአማርኛ ላይ እንግሊዝ፣ በሀገርኛ ላይ ዳያስጶራ ' ሲደረግ ያምራል፡፡
እናንተ ልታርፉ አልቻላችሁምንጂ የአራዳ ልጆችኮ ይገባናል፡፡ ለመሆኑ በአማርኛ ወይንም በትግርኛ አለበለዚያም በኦሮምኛ ተናግሮ ሊቅ የተባለ ሰው ታውቃላችሁ፡፡ እርሱንማ ማንም ይናገረዋልኮ፡፡ መወለድ ብቻ በቂ ነው፡፡ ምናልባት እዚች ሀገር በራስህ ቋንቋ መናገርህ ብሔረሰብህን ይገልጥ እንደሆነ እንጂ ዐዋቂነትህን አይገልጥም፡፡ ምን ብሔረሰብህን ብቻ የተወለድክባትን ጎጥ ነው የምታስመሰክረው፡፡
ስለዚህ መሐል መሐል ላይ እንግሊዝኛ ' ታደርጋለህ፡፡ እናቶቻችን ሲናገሩ አልሰማህም፡፡ «ሽሮው ላይ ቅቤ ' አድርጊበት፣ ፍርፍሩ ላይ ሥጋ ጣል አድርጊበት» ይላሉኮ፡፡ አየህ ዋናው ነገር ሽሮው ወይንም ፍርፍሩ ሳይሆን ' የሚደረገው ቅቤው እና ሥጋው ነው ማለት ነው፡፡ ቅቤ እና ሥጋ ውድ ነዋ፡፡ ምግብ ቤት ገብተህ ቅቅል ወይንም ቀይ ወጥ ስታዝ ምንድን ነው የምትለው፡፡ «ማነህ አንተ አጥንት ' አድርግበት» ትል የለም እንዴ፡፡
እኛም ታድያ በአማርኛ እና በኦሮምኛ መሐል እንግሊዝኛውን ጣል እናደርግበታለን፡፡ ቆይ አንድ ጉድ ላውጋ፡፡ አማርኛ እና ትግርኛ፣ አማርኛ እና ኦሮምኛ፣ አማርኛ እና ሶማልኛ የሚችሉ ብዙ ወገኖች አሉ፡፡ በአማርኛ ቃለ መጠይቅ ሲደረግላቸው ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? ለወደፊቱ እኔ እንደሰማሁት አድርጋችሁ ስሙ፡፡ ቢሞቱ አማርኛን ከትግርኛ፣ አማርኛን ከኦሮምኛ፣ አማርኛን ከሶማልኛ ሲቀላቅሉ አትሰሙም፡፡ ለምን አትሉም? ያስበላላ፡፡ አያተርፍም፡፡ መካከል ላይ እንግሊዝኛ ' ሲያደርጉ ነው የምትሰሙት፡፡ በአማርኛ ላይ ኦሮምኛ፣ በትግርኛ ላይ ሶማልኛ ' ማድረግማ በሽሮ ላይ ድንች ' እንደ ማድረግ ነው፡፡
መቀላቀል ልማድ ቢሆን ኖሮ አማርኛ እና ኦሮምኛ፣ አማርኛ እና ትግርኛ ሳይቀላቀሉ እንዴት ነው አማርኛ ከእንግሊዝኛ ጋር ካልተቀላቀልኩ ብሎ የሚያስቸግረው? የሄ በየትኛውም የቅልቅል ባህል የሌለ ነው፡፡
ፈረንጅ ለዘር እንኳን በሌለበት የገጠር ከተማ የሚደረግ ሠርግ መጥሪያ አይታችኋል? በአማርኛ እና በእንግሊዝኛኮ ነው የሚዘጋጀው፡፡ ታድያ ፈረንጅ ሲጋበዝ ግራ እንዳይገባው መሰላችሁ? ትርጉሙ ሌላ ነው፡፡ ቀላል አይደለንም ነው ነገሩ፡፡
አሁን እናንተ እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ትጠይቁ ይሆናል፡፡ ሁለቱን ቋንቋዎች በየራሳቸው ለምን አትናገሩም ትሉ ይሆናል፡፡ ሀገርኛውንም በሀገርኛ፣ ውጭኛውንም በውጭኛ፡፡ ችግሩ ይህ ጥያቄ የቤት ልጅ ጥያቄ መሆኑ ነው፡፡ ለነገሩ ጥያቄውን በጥያቄ መመለስ ይሻለኛል፡፡
ሽሮው ላይ ሥጋ ጣል ለምን ይደረጋል? ሙዝ ሻጭ ቅቤ አብሮ አይሰጥም፣ ቅቤ ሻጭ ግን ለምን ሙዝ ይቀላቅላል? ሸክላ ሻጨ በበሬ ለምን አብሮ አይሰጥም? እስኪ መልሱልኝ?
ሽሮው እንደ ልብ ይገኛል፡፡ ሙዙንም ማግኘት ቀላል ነው፡፡ ሸክላውም ውድ አይደለም፡፡ በርካሹ ላይ ውድ ' ይደረጋል እንጂ፣ በውድ ላይ ርካሽ ' አይደረግም፡፡ አሁን መልሱ የገባችሁ ይመስለኛል፡፡
እንግሊዝኛው ውድ ሆነብን፡፡ subject + verb + object = sentence እየተባልን ሂሳብ እንጂ ቋንቋ ያልተማርን ሰዎች አሁን ' ከማድረግ በላይ እንግሊዝኛውን ከየት እናምጣው? እኔን ካላመናችሁ እነዚህ እንግሊዝኛን በአማርኛ መካከል እየደነጎሩ መከራ የሚያሳዩዋችሁን ዘመዶቻችሁን እስኪ በእንግሊዝኛ ብቻ ተናገሩ በሏቸው፡፡ መዝገበ ቃላት እያዩ እንኳን አንድ አንቀጽ አያወሯችሁም፡፡
ምን ሩቅ አስኬዳችሁ አወራራቸውን ወይንም በእናንተ ቋንቋ «ፕሮናውንሴናቸውን» አትሰሙልኝም፡፡ ልክ ለእንግሊዝ ፊልም የምንጃር ዜማ «ሳውንድ ትራክ» እንደመጠቀም እኮ ነው፡፡ የሰዎቹ ቃላት እንግሊዝኛ አነጋገሩ አማርኛ ይሆንላችኋል፡፡ ወይንም በቀላሉ በአራዳ ቋንቋ ለመግለጥ ፊልሙ እንግሊዝኛ የማጀቢያ ዜማው አማርኛ ይሏችኋል ይሄ ነው፡፡ ለነገሩ አንዳንዶች ይህ ልምድ ከሕንድ እና ከፓኪስታን የተወሰደ ነው የሚሉ አሉ፡፡
አሁን እኔ አንድ ሃያ የማይሞሉ የእንግሊዝኛ ቃላት አሉኝ፡፡ እነርሱን ሁሉ ለብቻ ከተናገርኳቸውማ ያልቃሉ፡፡ ከዚያ ምን ልሆን ነው፡፡ «ማኑዋል» እያየ አውሮፕላን ሲያበርር የነበረ ጀብደኛ አየር ላይ ሲደርስ "ቀጣዩን በሚቀጥለው መጽሐፍ ይመልከቱ" እንዳለው እኔም ቀጣዩን መቼ ስሙኝ ልል ነው፡፡
ሞኝ አትሁኑ፡፡ ዛሬ አንድ ሦስቷን እንግሊዝኛ ' ታደርጋላችሁ፡፡ ነገ ደግሞ አንድ ሦስቷን ' እያደረጋችሁ ሊቅ እንደመሰላችሁ መኖር ስትችሉ ምን በእንግሊዝኛ አንጣጣችሁ፡፡ ጎበዝ ጥይት በአንድ ዙር መጨረስ ደግ አይደለም፡፡
አንድ ነገር ረስቼው «መሪጌታ ጉግልን» ታውቋቸዋላችሁ? መሪጌታ ጉግል የኛ ሠፈር ሰው ናቸው፡፡ በኛ አጥቢያ ማታ ማታ ያስተምራሉ፡፡ አልፎ አልፎም በየአዳራሹ ገለጣ ይሰጣሉ፡፡ መሪጌታ ጉግል ብለው ስም ያወጡላቸው አንድ የደብራችን ዜማ ዐዋቂ ናቸው፡፡
ነገሩ እንዲህ ነው፡፡
እኒህ ሰው አንድም ቀን ኢትዮጵያዊ የሆነ መጽሐፍ ጠቅሰው፣ ኢትዮጵያዊ የሆነ ሊቅ አድንቀው፣ የኢትዮጵያን ታሪክ አሞግሰው አያውቁም፡፡ የዚህ ምክንያታቸው ደግሞ ከኢትዮጵያ ዓይነተኛ መጻሕፍት፣ ከገድል እና ከስንክሳር፣ ከሊቃውንት እና ከምሁራን መጻሕፍት ይልቅ በኮምፒውተራቸው ጎልጉለው የሚያገኙት ጉግልን ስለሚያምኑት ነው ይባላል፡፡ እና ታድያ የርሳቸው እንግሊዝኛ የጉግል እንግሊዝኛ በመሆኑ አንበውት እንጂ ሰምተውት አያውቁምና ሲናገሩት ስትሰሙ የማታውቁትን ግእዝ የጠቀሱ እንጂ እንግሊዝኛ ያወሩ አይመስላችሁም፡፡
እንግሊዝኛን ' ማድረግ ለኤፍ ኤም ሬድዮ እና ለባለ ሥልጣን ብቻ ማንሰጠው ብለዋል መሪጌታ ጉግል፡፡ እናም በስብከታቸው ሳይቀር ከግእዝ ይልቅ እንግሊዝኛ ' ያደርጉልናል፡፡ እኛም በሊቅነታቸው ተደንቀን አንገታችንን እንነቀንቃለን፡፡ አንዳንድ ሰዎች እንዲያውም ወደፊት በዚሁ ከተጉ በቅዳሴው ውስጥም እንግሊዝኛ ' ሊያደርጉልን እንደሚችሉ በተስፋ እየጠበቋቸው ነው፡፡
መሪጌታ ጉግል እንደ ጉግል የሚያምኑት እና የሚወዱት የለም፡፡ አንድ ጥያቄ ሲጠየቁ «እስኪ ኮምፒውተሬ ላይ አይቼ እነግራችኋለሁ» ይሉናል፡፡ እርሳቸው ኮምፒውተር ላይ የሌለ ነገር ሁሉ በዓለም ላይ እንደሌለ ይቆጥሩታል፡፡ እንዲያውም ከሀገራቸው ይልቅ ውጭውን የሚናፍቁ፣ ከሀገርኛ ሊቃውንት ይልቅ የውጭዎቹን የሚያደንቁ፣ ኢትዮጵያን በውጩ መሣርያ ሊያርሟት የሚፈልጉ አያሌ ደቀ መዛሙርት አውጥተዋል መሪጌታ ጉግል፡፡
እና ' ማድረግ እንኳን በኛ በዓለማውያኑ በነ መሪጌታ ጉግልም እየተለመደ ስለሆነ እኛን ለቀቅ ብታደርጉን፡፡ 30 ወገኖቻችን ካለቁበት የሰማዕታት 75 ዓመት በዓል ይልቅ የቫለንታይን በዓል በሚደምቅበት ሀገር ተቀምጣችሁ እንግሊዝኛ ' አታድርጉ ማለት ነውር ነው፡፡
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ ወጥቷል፤ በተመሳይ ኅትመት ላይ ባታወጡት ይከራል

76 comments:

 1. Dn. Daniel.Well come to Hawassa,We are happy that you ,Memhir Zebene & others will be here in Hawassa for three days.

  ReplyDelete
 2. የቻይና መንግስት ለሀገሩ ጋዜጠኞች የሰጠውን ማሳሰቢያ(ማስጠንቀቂያ) መቼም ሳትሰማ የቀረህ አይመስለኝም፡፡ ማንኛውም ጋዜጠኛ አንድ የእንግሊዝኛ ቃል እንዳያስገቡ፤ለቃሉ አቻ ትርጉም እንዲፈልጉ አለበለዚያ ግን ከፍተኛ ቅጣት እንዳለው አስጠንቅቋል፡፡የእኛን መንግስት እጁን ምን አሰረው፤“ቅድሚያ ለልማት ስለሚሰጥ!”

  ReplyDelete
  Replies
  1. That is just foolish. What is the problem with using English words when necessary? What do you feel other local languages apply the same rule over Amharic?

   Delete
  2. Dear Anonymous,

   I don't think you got the point. We have more than enough words. There's no need to mix it with English. When you speak English, speak it by itself. When you speak Amharic or any other Ethiopian language, speak it by itself. It doesn't need a mixture or guramayle!

   Delete
 3. Gosh! Dani endih lik liken nigeregn enji. Ameseginhalehu!

  ReplyDelete
 4. Gosh! Dani endih lik liken nigeregn enji. Ameseginhalehu!

  ReplyDelete
 5. Dani tebarek i really get annoyed when i hear people talking Guramayle.

  ReplyDelete
 6. Tosimo daniel
  Dik iyita new

  ReplyDelete
 7. Egzaibhere Ke'mekera sega Ke'mekra Nefese yetebkeh. This is very nice article, funny but to the point. "Sew ye'libun sengerut yekorkurot yahel yiskal" endmibalew!God Bless. By the way where can we get the new book here in DC area?

  ReplyDelete
 8. በጣም ደስ የሚል ፅሁፍ ነው
  ግን ለምን ጣል ብቻ አንዳንደ ሞዥረቅ ብናደርግስ

  ReplyDelete
 9. ዲ.ዳንኤል የዛሬው እይታህ በ Saturday,April30,2011 ካስነበብከን "ይድረስ ለእንግሊዝ ሠርገኞች" ከሚለው ጋር በተመሳሳይ ዘይቤ የተጻፈ ሆኖ ስላገኘሁት ደስ ብሎኝ አንብቤዋሁ፤ እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡

  አክባሪ እህትህ፡፡

  ReplyDelete
 10. አባግንባርMarch 2, 2012 at 8:08 PM

  እኔም ጣ'ል ላድርግልሃ!

  የሦስተኛ ክፍል ተማሪ ነች ሕጻኗ:: ብዙ ጣ'ል አድርጋ ነው መሰለኝ አንደኛ ወጣች ተብሎ በ"ቴለቪዥን" መስኮት ቀርባ ቃለመጠይቅ ይደረግላታል:: "ሚሚ ውጤትሽ በጣም ጥሩ የሆነው እንዴት ብታጨኚ ነው?" ተብላ ትጠየቃለች:: "ከጓደኞቼ ጋር በማኅበር ተደራጅቼ ስለማጠና ነዋ!"::

  መልዕከቴን ካገኘሄው እንግዲህ ግልጽ ነው:: ጣ'ል አድራጊዎች አስተተምረውን ጣል እያደረግን አደግን:: አሁን ደግሞ ሕጻናቱን ጥቃቅንና አነስተኛ አደራጆች ስለሚያስተምሯቸው በማኅበር መደራጀትን እንደ ትኩረት አቅጣጫ ይዘውልናል::

  "ቫላንታይንስ ዴይ"ን ነካህ ጭራሽ ብለህ ብለህ? በል በል ይህች ጽሑፍህ እስክትረሳ ድረስ ወደ ኤድና ሞልና ቦሌ ሰፈር እንዳትንቀሳቀስ:: አይ ለነገሩ ግድ የለም መሪጌታ ጎግልም ሆኑ: ሮዝ መጽሔት በ"ቫላንታይንስ ዴይ" አክባሪዎች ዘንድ ትኩረት ስለማይኖራቸው ብዙም አትፍራ::

  ReplyDelete
 11. wow i like the view dani you know what i think most people("ethiopian") think speaking English by it self is a great knowledge ."sorry about my english cus i haven't amharic font"

  ReplyDelete
 12. በጣም ቁም ነገር አዘል እና አዝናኝ ፅሁፍ ነው:: እግዚያብሔር ይስጥልን:: በኮፒ ራይት ማስጠንቀቂያህ ላይ ለውጥ በማየታችን ደስተኛ ነን (እኔ እኔ የሚል መንፈስ መቅረቱ ደስ ይላል):: መጨረሻው ላይ ግን 'ይመከራል' ለማለት ፈልገህ ይመስለኝኣል በስህተት 'ይከመራል' ያልከው::

  እግዚያብሔር በረከቱን ያብዛልህ::

  ወልደ ስላሴ ከፊንላንድ!

  ReplyDelete
 13. Abet Gudachen Mechem Aylkem Eko Ytafal Yetfal Yenegerenal Gen Melewt Alemechalachen New Yerasachenen Teten Yelelawen Senadenk New Yemenegegew Le Hulum Erasen Lemelewt Berase Lekora Wesegalew Enanetes ? Dn Dani EGZIABHER Ahuenm Tegawen Yabezalek Tebarek Egeg Betam Telek Asetemari Nek Endeante Yalewn Aysatan Yabezalen Amen !!!!!!

  ReplyDelete
 14. erasen endiweqis aderekegn, thank you!egiziabher yibarkih

  ReplyDelete
 15. ዲን ዳንኤል ተባረክ ሁል ጊዙ በውስጤ ያለና ያልተመለሰልኝ ጥያቂ ነበር በተለይ በተለይ በጣም የሚገርመኝ በሬዲዮ አና ባለስልጣን ተብለው ከተቀመጡ ይህንን መስማት በጣም ያሳፍራል ። ሁሉ ነገር አያለን አንደሌለን የራሳችንን ነገሮች የጠላን ሆነናል ። ብቻ አራሳችንን የሸጥን ሰዎች ሆነናል ይህ ደግሞ ከቀኝ ግዛትም በላይ የከፋ ነዉ። ልቦና ይስጠን

  ReplyDelete
 16. yabebe24@yahoo.comMarch 3, 2012 at 5:55 AM

  ዳኒ እንዲህ በቀልድ አዋዝተህ እውነታን የምትገልፅበት መንገድ ይደእንቃል በርትአ ያሰብከውን ጌእትአ ያምዋላልህ
  ዮናስ አበበ

  ReplyDelete
 17. Egzer yistih, long live dani. Anjeten new yaraskew. Englizegna tal lemareg yakil "Good job bro".

  ReplyDelete
 18. Well said Dani. But we all have to recognize the fact that in our day to day conversation we have to use some foreign words...words like police, hospital, taxi, television.... I don't think it is wrong to use these words and even there are also inventions, new technologies, ideas, and concepts which are much easier to express in foreign words than our own. For example, to be frank, I don’t know Amharic equivalent words to use for x-ray, computer, algorithm, calculus....I think, it is a negative stereotype against using English words in our society. But the fact of the matter is there are many Italian, Arabic, and French words which we are using in everyday life….don't you think we are "ta'l eyaregen" for that matter. You can correct me if I am wrong, but it is not my problem, your problem or someone's problem...it is all about our broken educational system and how we grown up. Can we minimize using foreign words in our conversation? YES .Can we stop using them at all? NO

  Keep up the good work!

  Addis

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድም/ወይም እኅት!"I don’t know Amharic equivalent words to use for x-ray, computer, algorithm, calculus...." ለሚለው አስተያየት፦ የዲባቶ (ዶክቶር) መስፍን አረጋን ሥራ ልጠቁም። እኒህ ምሁር፣ አሳቡ በቅጡ ተሠራጭቶ ቢስፋፋላቸውና እኛም የራሳችንን በሽታ በራሳችን ዘይቤ የመፍታት ፀጋ ቢታደለን፤ መፍትሔውን ከነ ሕገ ኀልዮቱ (logic)"ሰገላዊ አማርኛ (አማሮምኛ)" በሚል መጽሐፋቸው አስቀምጠውልናል። እንግዲህ የዚህ ሥራ ጽንሰ ሐሳብ ለማናቸውም ዘመን/ሰገል/አፍርንጅ-ፈጠር ቃል ከራሳችን ቋንቋዎች በጥምርም ሆነ በቅይር መተካት እንደምንችልና፤ ታላቁ ኢትዮጵያዊ ሊቅ አለቃ ደስታ ተክለወልድ እንዳስቀመጡት "ያገሩን ቋንቋ ተምሮ ንባብ ከጽፈት ሳያውቅ ያማርኛን ግስ በማቃለል ግእዝን ደግሞ በመናቅ የፈረንጅ ፊደል አጥንቶ ምንም ቢያስተውል፣ ቢራቀቅ፤ የሰው ወርቅ አያደምቅ፣ አያደምቅ የሰው ወርቅ።" የተባለው እየደረሰብን እንደሆነ በሚገባ ያስገነዝባል። እጅግ በጣም የሚያዋርደው (በህሊናም ረገድ ኾነ በተጨባጭ ኅብረተ-ሰብዓዊ ሚዛን)ደግሞ ከላይ ዳንኤል እንዳሰፈረው፦ "... አወራራቸውን ወይንም በእናንተ ቋንቋ «ፕሮናውንሴናቸውን» አትሰሙልኝም፡፡ ልክ ለእንግሊዝ ፊልም የምንጃር ዜማ «ሳውንድ ትራክ» እንደመጠቀም እኮ ነው፡፡ የሰዎቹ ቃላት እንግሊዝኛ አነጋገሩ አማርኛ ይሆንላችኋል፡፡" በነገራችን ላይ ዲባቶ መስፍን ሥራቸውን በአንዳንድ ድረ-ገጾች ላይ "ትምህርት ነክ ቃሎች"፤ " ወታደራዊ ማዕረጎቻችን እንዲህ ቢሆኑስ"፤ "ያይንስታይን የፀራናዊነት ግንገና" ወዘተ በሚሉ አርዕስት ያቀረቧቸው ስለሆነ ቢጎግሉት የበለጠ መረጃ ይሆናል።

   Delete
 19. "ኢትዮጵያዊ የሆነ መጽሐፍ ጠቅሰው፣ ኢትዮጵያዊ የሆነ ሊቅ አድንቀው፣ የኢትዮጵያን ታሪክ አሞግሰው አያውቁም"፡:ቃለሕይወት ያሰማልን፡፡በጣም ግሩም የሆነ ምልከታ ነው ዲን ዳንኤል ለካ'ስ አንዳንድ ሰባኪዎች ከገድል እና ከስንክሳር፣ ከሊቃውንት እና ከምሁራን መጻሕፍት ይልቅ የአርትስቶች እና የሰፈር ወሬ ደግሞም ሥጋዊ ስሜታቸው ማንጸባረቅ የሚያበዙት ጣ'ል የሚል አባዜ ስለያዛቸው ነው፡፡

  ReplyDelete
 20. ይህን ጽሁፍ ያነበብኩት ከሌሊቱ 2፡00AM ነው። ቤተሰብ ተኝቶ ብቻዬን ሳቄ እንዳይረብሽ ተጠንቅቄ ወደውስጤ ከልቤ ሳቅሁ። በእንዲህ ያለ ውድቅት ሌሊት እንደዚህ ስስቅ የመጀመሪያዬ ነው ባልሳሳት። በቃ amazing ታሪክ ነው። “Good Job Dani” እኔም ጣ’ል! ለምን ይቅርብኝ። አያምርማ!

  ReplyDelete
 21. YOU toched the point.May the ALMIGHTY help U.

  ReplyDelete
 22. Tiru eyita new Dn. Daniel. Erasen tazebkubet.

  ReplyDelete
 23. Dani, wow amazing viwe!

  ReplyDelete
 24. ሳሚ (ወ/ሚካኤል)March 3, 2012 at 1:02 PM

  አሃሃሃሃሃ..(ሳቅ) የልቡዋን ሲነግሩዋት የኮለኮሉዋት ያክል ትስቃለች አሉ!..ሌላም ተረት ነበረ....ማሽላ እያረረ ይስቃል ነው የሚባለው??!! አዎዎዎ ሁለቱም እኔን ይገልጹኛል!!! (በወሎኛ ቁልምጫ)ዳኒየዋዋዋዋዋ ......አቤቱ አምላክህ እንዴት ድንቅ ነው?!! ህዝቡን የሚመክርበት ምርጥ ማይክራ.... (እየው የኔ ነገር ቂቂቂ) ማለቴ.. ምርጥ የሆነ ቃሉን ማጉያ ለኛ ሰጥቶናልና!!! "ትንሳኤሽን ያሰየን ያሳየን" ብሎ ዘማሪው የዘመረበት ትርጉም አሁን ገባኝ! ለካ ለህግም ትንሳኤ አለው፡፡ እንጀራችን ”ሳር ነው” : ”ፈርስ ነው” የሚለውን የነጮች ልፈፋ ሰምቶ አዳሜ ሁሉ ወደ ፓስታና ዳቦ ሲባዝን እንዳልኖረ ..ዛሬ የጤፍ ትንሰኤዋ ሆነና ከፍተኛ ፕሮቲን እና ግሎቲን (መሰለኝ) የተባለ ጸረ-አለርጅክ ንጥረ ነገር ተገኘባት ተብላ እኛን እንደ ሳር በሊታ ከብት ሲያዩን የነበሩ ነጮች ሁሉ ነጩን ጤፋችንን በገፍ መሸመት ጀመሩ! እግዚአብሄር ይመስገን!..ነገም የፍትሃ ነገስታችን በጎ እጣ ፈንታ የሄው ነው! ”ሕግስ የኢትዮጵያ” ተብሎ የናቁዋት ፖለቲከኞች ሁሉ በህገ መንግስቱዋ ስር ወድቀው የምክር ቤቱዋን ትቢያ የሚልሱበት ቀን ይመጣል! ስለዚህ በዳኒ አምላክ !!!....ከውጭ መጣ ለተባለው ሁሉ ልባችንን ስንከፍት ከውጭ ያሉት በክፍተታችን እየገቡ የኛኑ ሀብት እንቁልልጭ የማለታቸውን ድብብቆሽ እንንቃበት! አባቶች በመንፈስ ቅዱስ ተመርተውና ነገን ማእከል ባደረገ ትንቢት ያኖሩልንን የስልጣኔ ቅኔ ሰሙን ብቻ እያየን በነገር በጎሸሙን ቁጥር አንበርግግ ፡፡ቅኔው ሲገባቸው የኛኑ ጤፍ አምርተው ግዙን ሳይሉን በፊት እግዚአብሄር በግዜው ጊዜ ”ኢትዮጵያ” ብሎ የሰየማትን ”ቅኔ” ."ወርቁን” ይፈታልና በመጠበቂያው ግንብ ላይ ሁነን በጸሎት ዝምታ የሚደርገውን እንይ!!! ዳኒ እግዚአብሄር ቢፈቅድ አንተን በኔ ስራ የምገልጥብህ ቀን ይኖር ዘንድ ስለክርስቶስ እርግጠኛ ነኝ!!! እያንዳንዱ ምልከታህ ለኔ ግብአቴ ነው!!!! ልጆችህ ላንተ ያላቸውን ፍቅር የሚገልጹበትን ማንኛውንም ድርጊት እጅ መንሻ አድርጌ አቅርቤልሃለሁ!!! የጉርሻህን ጥፍጥና የማውቅ ልጅህ ነኝና!!!..እግዚአብሄር ለኛ ያለ’ውን ፍቅር የዳኒን አይምሮና እድሜ በመባረክ ይፈጽምልን!!! አሜንንንን! thank you!!! አሃሃሃሃሃ..(ሳቅ)ሳሚ ዘሰመራ

  ReplyDelete
 25. ብላቴናዋ ከጀርመንMarch 3, 2012 at 1:57 PM

  እህ እንደው ምን ልበልህ ? ሰላም ጤናይስጥልኝ ዳኒ እንደምን ከረምክ እንደው ደስበሚል አሽሙር እንዲህ ባዶነታችንን ማን ይነግረን ነበር አይምሮህን ብሩህ ላደረገ አምላክ ምስጋናይድረሰው ለኛም በማንነታችን ይምንኮራ ህዝቦች ያድርገን ለሁላችንም ማስተዋልን ይስጠን አሜን !

  ReplyDelete
 26. ከአሁን በኋላ እንግሊዘኛ አልቀላቅልም፡፡ ሙሉ እንግሊዘኛ ወይም አማረኛ እናገራለሁ እነጂ፡፡ ዳኒኤል አመሰግንሀለሁ፡፡

  ReplyDelete
 27. Girum eyita new! eskahun dires be edgetachin lay be hagerachin lemejemeria gize yesiltane berhan kefenetekebet gize (be ethiopiawuyan abatochina enatoch zemen) jemkiro eskahu dires lalew yezemen rizimane temetatagn EDGET'CIVILIZATION' yalametanew lemin honene!!!??? Eyitachin,ekidachin,sirachin ,hasabachin ,nuroachin,...HAGERAWI meseret yelelew silehone ayidelem? sinikeda enkuan melkamun bicha ayidelem 'kene merzu chimir new enji!',lik ende mognuna senefu temari(yefetenaw yemejemeriya tiyake mulu simihin be ENGLIZIGNA tsaf neber! tadiya ajirew yegobezun temari sim kene ayatu sim chimir sile tsafe MEKOREJU tenekabet!)

  ReplyDelete
 28. Dear Daniel,

  I am not in agreement with this intervention. Our language have a power to explain whatever we want to say. Actually, it is an attidunal problem in considering someone consider to be as a wiseman when he/she talking a mixture of English and Amharic togetehr. If we recall the late Sibehat Geberaegziabher interview, he never mixed English and Amharic. This means he can expalin whatever he wants in Amharic in a very expressive and simple manner. To my observation, mixing languages while talking is simply defusion of self rather than having wisdom. I strongly insist, the perception and the mind set up should be changed.

  ReplyDelete
 29. Kal hiwot yasemalin

  ReplyDelete
 30. Enem englizigna tal endaladerg be Amarigna litsaf. Konjo tshihuf new. Ta'l madreg alu.

  And asteyatet - mecheresha lay yalew yebalebtnet milikt yemiyasayew milikit ye Ethiopiawi temetatagn yelewm ende. Benegrachin lay yikemral yemilew yimekeral teblo bistekakel tiru new. Eskezare endet manim endalayew yigermal. Mechem limad honobign tinignin mawtat ewedalehu.

  Be Amarigna computeru lay metsaf bichil degmo endet yikelegn neber. Esum eko andande saywedu englizgna ta'l endiaydergu yigefafal.

  ReplyDelete
 31. ውድ ዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሄር ይባርክህ:ያሳድግህም።
  ከዚህ ጡመራ መድረክ ብዙ ተምሬአለሁ።
  ያነሳሀው ጉዳይ እጅግ ስር የሰደደ ሆኗል። በቴሌቪዥንና በራዲዮ ዜናዋች፣ ውይይቶችና ዕቅዶች በሚተላለፉበት ወቅት ሳይቀር አልፎ አልፎ የእንግሊዝኛ ቃላቶችን እየሰነቀሩ፥ የሀሳቡ ፍሰት ወደ አብዛኛው ያልተማረው የህብረተሰብ ክፍል በሚገባ እንዳይደርስ ከማድረጋቸውም በተጨማሪ ሌሎቹ ላይ ደግሞ ለእንግሊዝኛ ከፍ ያለ፥ ለአገራችን ቋንቋዎች ዝቅ ያለ አመለካከት እንዲኖራቸው በር እየከፈተ ነው። ዛሬ እንግሊዝኛን እንደ አንድ የመግባቢያ ቋንቋ ሳይሆን እንደ ዕውቀት የሚቆጥሩት ብዙዎች ሁነዋል። አንድ ሰው የቋንቋ ምሁር ከሆነና በዚያ ቋንቋም ጥልቅ እውቀት ካለው እሱ ስለዚያ ቋንቋ አዋቂም ሊቅም ነው። በሌላ ነገር ግን አዋቂ ላይሆን ይችላል።ቋንቋ ሀሳብን ያለ ችግር ለማስተላለፍ ወሳኝ ስለሆነ በሌላ የትምህርት መስክ ያለ ሁሉ ይማረዋል ይጠቀምበታልም። እንግዲህ እኛ አገርም ቀስ በቀስ እየታየ ያለው ችግር ይህንን በውል ያለማስተዋል ይመስለኛል። ልጃቸው እንግሊዝኛ አቀላጥፎ ከተናገረላቸው ብዙ ያወቀ የሚመስላቸው ወላጆች አሉ። ለዚያም ነው ዛሬ ልጆች የአገራችንን ቋንቋዎች እየተጠየፉ እንግሊዝኛ ላይ ትኩረት የሚያደርጉት። ስለዚህ ልጆቻችን ቋንቋችንን ካልቻሉ እውቀት ቢኖራቸውም እንኳ የውጭ ናፋቂ ይሆናሉ እንጅ በኢትዮጵያችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳይ ላይ ሚና አይኖራቸውም ማለት ነው።
  እኔ ባለሁበት ሩስያ ፡ለአገራቸው ትላልቅ ስራዎችን የሰሩና ያሰሩ በዓለም አቀፍ ደረጃም ለሽልማት የበቁ ፕሮፌሰሮች ስማቸውን እንኳ በእንግሊዝኛ መጻፍ አይችሉም፥ አይፈልጉምም። ምክንያቱም ሊቅ ለመሆን የእንግሊዝኛ እውቀት የግድ አይደለምና።

  ReplyDelete
 32. ውድ ዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሄር ይባርክህ:ያሳድግህም።
  ከዚህ ጡመራ መድረክ ብዙ ተምሬአለሁ።
  ያነሳሀው ጉዳይ እጅግ ስር የሰደደ ሆኗል። በቴሌቪዥንና በራዲዮ ዜናዋች፣ ውይይቶችና ዕቅዶች በሚተላለፉበት ወቅት ሳይቀር አልፎ አልፎ የእንግሊዝኛ ቃላቶችን እየሰነቀሩ፥ የሀሳቡ ፍሰት ወደ አብዛኛው ያልተማረው የህብረተሰብ ክፍል በሚገባ እንዳይደርስ ከማድረጋቸውም በተጨማሪ ሌሎቹ ላይ ደግሞ ለእንግሊዝኛ ከፍ ያለ፥ ለአገራችን ቋንቋዎች ዝቅ ያለ አመለካከት እንዲኖራቸው በር እየከፈተ ነው። ዛሬ እንግሊዝኛን እንደ አንድ የመግባቢያ ቋንቋ ሳይሆን እንደ ዕውቀት የሚቆጥሩት ብዙዎች ሁነዋል። አንድ ሰው የቋንቋ ምሁር ከሆነና በዚያ ቋንቋም ጥልቅ እውቀት ካለው እሱ ስለዚያ ቋንቋ አዋቂም ሊቅም ነው። በሌላ ነገር ግን አዋቂ ላይሆን ይችላል።ቋንቋ ሀሳብን ያለ ችግር ለማስተላለፍ ወሳኝ ስለሆነ በሌላ የትምህርት መስክ ያለ ሁሉ ይማረዋል ይጠቀምበታልም። እንግዲህ እኛ አገርም ቀስ በቀስ እየታየ ያለው ችግር ይህንን በውል ያለማስተዋል ይመስለኛል። ልጃቸው እንግሊዝኛ አቀላጥፎ ከተናገረላቸው ብዙ ያወቀ የሚመስላቸው ወላጆች አሉ። ለዚያም ነው ዛሬ ልጆች የአገራችንን ቋንቋዎች እየተጠየፉ እንግሊዝኛ ላይ ትኩረት የሚያደርጉት። ስለዚህ ልጆቻችን ቋንቋችንን ካልቻሉ እውቀት ቢኖራቸውም እንኳ የውጭ ናፋቂ ይሆናሉ እንጅ በኢትዮጵያችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳይ ላይ ሚና አይኖራቸውም ማለት ነው።
  እኔ ባለሁበት ሩስያ ፡ለአገራቸው ትላልቅ ስራዎችን የሰሩና ያሰሩ በዓለም አቀፍ ደረጃም ለሽልማት የበቁ ፕሮፌሰሮች ስማቸውን እንኳ በእንግሊዝኛ መጻፍ አይችሉም፥ አይፈልጉምም። ምክንያቱም ሊቅ ለመሆን የእንግሊዝኛ እውቀት የግድ አይደለምና።

  ReplyDelete
 33. Dear Daneil,

  Tsuhfih hulem mar new! Ketlbet! Egziabher edmehin yarzemew!!!

  ReplyDelete
 34. ግሩም ድንቅ ብቻ ነው!!!

  ReplyDelete
 35. Well said,I agree with you. Thanks.

  ReplyDelete
 36. ዲ/ን ዳንኤል፦ የዛሬውስ ጽሑፍህ ማር እና ሬት ሆነብኝ። ይኸውልህ! እኔ ከኢትዮጵያ ከወጣሁ አርባኛ ዓመቴን ያዝኩ። ታዲያ ከወገኖች ጋር በአማርኛ ስነጋገር አንዳንዴ ቃላቶቹ ይረሱኝና የግድ በእንግሊዝኛ ቃላት መተካት ባስፈለገኝ ቁጥር፤ እራሴን ከመታዘብም አልፌ ያደግኩበትን የአገሬን፤ የወገኔን ቋንቋ በመርሳቴ እራሴን እወቅሳለሁ፤ እቆጣለሁ። አንዳንዶች ወዳጆቼ "አይዞህ፣ ከአርባ ዓመታት በኋላ አይፈረድብህም ..." ቢሉኝም እንኳ ምንም የሚያረካ ጽናዓት አይሰጠኝም። ታዲያ በዚህ መልዕክትህ የተጠቀምክበት ምፀታዊ (saracastic) ስልት ጽሑፉ ያዘለውን ቁም ነገር እንደማር ሲያስልሰኝ የተደስትኩትን ያህል፤ ያስቀመጥካቸው ማስረጃዎችና ሌሎችም የኔ ብጤውን በሀገር ቋንቋ አሟልቶ ለመናገር የሚጥረውን፤ የሀገር ሊቃውንትን ሥራ ቀደምትነትም ሆነ ብቃት የሚያምንና የሚኮራበት ወገን ልክ እንደአራዶች ልፋት ከፋራነት ምልክትነት አለመውጣቱ እንደሬት መረረኝ፡፡ "30 ሺ ወገኖቻችን ካለቁበት የሰማዕታት 75ኛ ዓመት በዓል ይልቅ የቫለንታይን በዓል በሚደምቅበት ሀገር ተቀምጣችሁ እንግሊዝኛ ጣ'ል አታድርጉ ማለት ነውር ነው፡፡" ያልከውማ ጥርሹን ዕንባዬን አስጠረገኝ

  ReplyDelete
 37. selam lante yihun dn daniel. yelib yeliben tenagrehilignal.beteley "ባለፈው የጥምቀት በዓል ሲከበር እነማን ነበሩ ከጃንሜዳ በቀጥታ ሥርጭት ቃለ መጠይቅ ሲደረግላቸው የነበሩት እነማን ናቸው? አንድም ፈረንጆች፣ አንድም ከፈረንጅ ጋር ወይ ኖረው ወይ ሠርተው የመጡ፣ አንድም የፈረንጅ ጓደኛ ኖሯቸው እርሱን ተከትለው መድረኩን መጠጋት የቻሉ አይደሉምን? እኔ ስለ ጥምቀት በዓል ለመናገር ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር በቂ አለመሆኑን፣ የኢትዮጵያን ዕድገት ለመገምገም ለዕድገቱ የሚሆን ግብር መክፈል በቂ አለመሆኑን፣ ስለ ኢትዮጵያን በሚገባ ለመግለጥ ከውጭ ወደ ውስጥ ማየት የግድ መሆኑን ያወቅኩት ያኔ ነው፡፡ በጋዜጠኛው አልፈርድም፤ ወዶ አይደለማ፡፡ ካልተቀላቀለ አያዋጣም ብሎ ነውኮ፡፡ በአማርኛ ላይ እንግሊዝ፣ በሀገርኛ ላይ ዳያስጶራ ጣ'ል ሲደረግ ያምራል፡፡" bileh yeliben neaw yetenagerkew. yemeskel ena yetimket bealin be ETV bayhu qutir yemiyaqatilegn neger neaw. ebakachihu beteley media akababi yemitiseru sewoch lelelochachin araya lithonu yigebal.

  ReplyDelete
 38. ውድ ዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሄር ይባርክህ:ያሳድግህም።
  ከዚህ ጡመራ መድረክ ብዙ ተምሬአለሁ።
  ያነሳሀው ጉዳይ እጅግ ስር የሰደደ ሆኗል። በቴሌቪዥንና በራዲዮ ዜናዋች፣ ውይይቶችና ዕቅዶች በሚተላለፉበት ወቅት ሳይቀር አልፎ አልፎ የእንግሊዝኛ ቃላቶችን እየሰነቀሩ፥ የሀሳቡ ፍሰት ወደ አብዛኛው ያልተማረው የህብረተሰብ ክፍል በሚገባ እንዳይደርስ ከማድረጋቸውም በተጨማሪ ሌሎቹ ላይ ደግሞ ለእንግሊዝኛ ከፍ ያለ፥ ለአገራችን ቋንቋዎች ዝቅ ያለ አመለካከት እንዲኖራቸው በር እየከፈተ ነው። ዛሬ እንግሊዝኛን እንደ አንድ የመግባቢያ ቋንቋ ሳይሆን እንደ ዕውቀት የሚቆጥሩት ብዙዎች ሁነዋል። አንድ ሰው የቋንቋ ምሁር ከሆነና በዚያ ቋንቋም ጥልቅ እውቀት ካለው እሱ ስለዚያ ቋንቋ አዋቂም ሊቅም ነው። በሌላ ነገር ግን አዋቂ ላይሆን ይችላል።ቋንቋ ሀሳብን ያለ ችግር ለማስተላለፍ ወሳኝ ስለሆነ በሌላ የትምህርት መስክ ያለ ሁሉ ይማረዋል ይጠቀምበታልም። እንግዲህ እኛ አገርም ቀስ በቀስ እየታየ ያለው ችግር ይህንን በውል ያለማስተዋል ይመስለኛል። ልጃቸው እንግሊዝኛ አቀላጥፎ ከተናገረላቸው ብዙ ያወቀ የሚመስላቸው ወላጆች አሉ። ለዚያም ነው ዛሬ ልጆች የአገራችንን ቋንቋዎች እየተጠየፉ እንግሊዝኛ ላይ ትኩረት የሚያደርጉት። ስለዚህ ልጆቻችን ቋንቋችንን ካልቻሉ እውቀት ቢኖራቸውም እንኳ የውጭ ናፋቂ ይሆናሉ እንጅ በኢትዮጵያችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳይ ላይ ሚና አይኖራቸውም ማለት ነው።
  እኔ ባለሁበት ሩስያ ፡ለአገራቸው ትላልቅ ስራዎችን የሰሩና ያሰሩ በዓለም አቀፍ ደረጃም ለሽልማት የበቁ ፕሮፌሰሮች ስማቸውን እንኳ በእንግሊዝኛ መጻፍ አይችሉም፥ አይፈልጉምም። ምክንያቱም ሊቅ ለመሆን የእንግሊዝኛ እውቀት የግድ አይደለምና።

  ReplyDelete
 39. ደስ የሚል ፅሁፍ ነው

  ReplyDelete
 40. እውነቱን ልንገርህ በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮችህ ብዙ ጊዜ አልደሰትባቸውም። በእርግጥ ሁሉም የሰሙቱ ይደሰቱ ዘንድ አይጠበቅም። መስማትና ማመስገን፣ የሰሙትን መመዘንና ማመስገን ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸውና አትፈርድብኝም አይደል? ይሁን እንጂ የማልክደውን መዝኜ በማመስገን የምነግርህ ደግሞ ይህን ነው።
  ወግ ቀመስ ጽሑፎችህ ወዝ አላቸው። ቁም ነገራምና ገሳጭ አስተማሪዎች ናቸው።
  የሃሳብ ወንዝ አፈሳሰሱ፣ የቋንቋ ስልት አሰካኩና የመልእክት ሥረ ነገር ጭብጡን አስማምተህ ስታቀርብ በእውነት እንደበሰለ ፍሬ እንበላ ዘንድ እንገደዳለን። እኔ እገደዳለሁ።
  በርታ፣ቀጥል። እግዚአብሔር ያበርታህ!!

  ReplyDelete
 41. quanqua yeweledal yadgal.ene english lehasabe gelach kehone eteqemibetalew.hizb define medereg yalebet bequanquaw sayhone letewled beseraw sera new.endene tsehufeh semeat yenekal gin i think it lacks detailed analysis of z matter.

  ReplyDelete
 42. Qale Hiwoten yasemalin Ye Agelgelot Zemenhin Yarzimlih D.Dani Hulachinm Manentachenin Yemifetshibet Shega tshuf Nat ""Ene Man Negn""????

  ReplyDelete
  Replies
  1. Bakela zerto meser yachede yenor yehone ?

   HL.

   Delete
 43. tew enji D/n Dikala bedikala litadergen new ende?

  ReplyDelete
 44. በጣም አሪፍ ፅሁፍ ነው ፡፡
  በተረፈ የመጨረሻዋ አረፍተ ነገር ላይ ማስተካከያ ቢደረግ፡፡

  © ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ ወጥቷል፤ በተመሳይ ኅትመት ላይ ባታወጡት ይከመራል=(ይመከራል)

  ReplyDelete
 45. Qale hiwot yasemalin , tiru eyita newu

  ReplyDelete
 46. "30 ሺ ወገኖቻችን ካለቁበት የሰማዕታት 75ኛ ዓመት በዓል ይልቅ የቫለንታይን በዓል በሚደምቅበት ሀገር ተቀምጣችሁ እንግሊዝኛ ጣ'ል አታድርጉ ማለት ነውር ነው፡፡ግሩም አባባል" ግሩም አባባል፡፡
  AA ke Addis Ababa

  ReplyDelete
 47. አስተያየት ለመስጠት የሚያስቸግር ጽሑፍ ነው፡፡ ጽንፈኝነትም ይመስላል ደግሞም ትላለቅ ቁም ነገሮች አሉት፡፡ ለማንኛውም ስለ ፕሮናውንሲዬሽን ያነሳኸው የአፍ መፍቻ ቋንቋህ ይወስነዋል፡፡ አፍ የፈታኸው ከእንግሊዝኛ ው ጪ ከሆነ እንግሊዝኛ ስትናገር አፍ የፈታህበትን ቋንቋ ማወቅ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ሕንዶች

  ReplyDelete
 48. የሚቀላቀለውን ቃል ሰዎች የሚረዱት ከሆነ ምንም ችግር የለውም ፡፡ የቋንቋ ጥቅሙ መልዕክትንና ሃሳብን ለማስተላለፍና ለመለዋወጥ ስለሆነ ድክመት ሆኖ አይታየኝም ፡፡ ችግሩ ጣል የተደረገውን ቃል የሚረዳው ሰው ካልተገኘ ነው ፡፡ አንተ በእንግሊዝኛው ጣል ጣል ትደነቃለህ ፤ ዛሬ ዛሬ አማርኛ ብቻ ለሚረዳው ህዝብ ግዕዝ እየቀላቀሉ ስለ መንግሥተ ሰማያት ሊያስተምሩ የሚታገሉትን ነው መረዳት ያቃተኝ ፡፡ ግዕዝን ስላልተማርኩት በመሃል የሚያስተላልፉት ያ በልሳን ተናገርን የሚሉትን ሰዎች ቋንቋ እየመሰለኝ ፣ ልሳናቸውን ቀየሩ ብዬ ስተክዝ አማርኛው ይመጣል ፡፡ ስለዚህ ጣል ጣል ማድረጉ አድማጭን በአገናዘበ መልኩ ከሆነ ምንም እንከን አይሆንም ፡፡ ጥሩ ምልከታ ነው ፡፡

  ReplyDelete
 49. Dani betam ameseginalehu, hulgize lerasie yemigermegnin ena enem lalemadreg zewetir yemitrewn new yenegerkegn. Sewoch gin yaw mehayim.......adirigew yasbuhal...bihonm eskahun balehubet alew.

  kezih beterefe gin ene ketsihufih mecheresha lay yayehutin degmo lasayih...hahahahah
  "ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ ወጥቷል፤ በተመሳይ ኅትመት ላይ ባታወጡት ይከመራል"

  min endalik awikehal "yimekeral" sayihon "Yikemeral" new:: tadia min lemalet feligeh new?

  Tesfahun Phoenix, AZ

  ReplyDelete
 50. I just read all what I am saying to the people who speak mix(Amharic with English) with a good dryly explanation.let God bless us to be proud by our own stuffs. Some how we just lost it. I wish every Ethiopian understand what modernization means, which will help us to recognize our beauty .
  Thanks Dani
  God bless Ethiopia

  ReplyDelete
 51. tiru tshufe new berta wendeme!

  ReplyDelete
 52. Great Observation!

  ReplyDelete
 53. God bless you & your family, you are the one out of few matured people in Ethiopia, thanks God for giving us a good person like Dani.

  ReplyDelete
 54. ውይ ዳኒ በጣም ያስቃል ተባረክ

  ReplyDelete
 55. I don't agree with you at all. Whether I speak English or Amharic or mixed, it is just a language for me. I don't care to speak pure Amharic (if it is possible actually b/c all languages use words from other languages, for example English uses too much Latin words).

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dear anonymous, Why are you so mad anyway? do not take it personal this is written for ehtiopian people not for individual. I think you are the one who is Portrayed by "merigeta google."
   stay positive!!!!!!!!!!!!!!!!!

   Delete
  2. ውድ AnonymousMar 6, 2012 06:42 AM
   የጽሁፉን ሐሳብ ሳትረዳው ለምን አስተያየት ትሰጣለህ;

   Delete
  3. geez tenagari amaregna tenagariwen menaq neberebet dero ende dani ababal

   Delete
 56. i read an article on reporte that Amharic is so popular due to the pervious government's effort so now we have to add additional language as offcial language.so at that time we are even losing all our history...every thing is gone..

  ReplyDelete
 57. betam desse yemele nwe

  ReplyDelete
 58. Dear Dani,
  You really touch our problem. I don't know what we should do as a way out.
  You remind me one photo posted on a face book by one of my friends. It is a billboard of Kindergarten, saying the Vision and Mission .... of the " XXXX Mewale Hitsanat". I was really amazed to get the words of Mission and Vision to the kindergartens. The content of this billboard is worsen, it says the vision of the kindergarten is to develop kids who are democratic, etc... I am afraid this word (democracy) will be preached in the mother's womb.
  Democracy Yemilew Kal Tal Kaltedrege Ayhonm Meselegn.
  TY

  ReplyDelete
 59. ፈረንጅ ለዘር እንኳን በሌለበት የገጠር ከተማ የሚደረግ ሠርግ መጥሪያ አይታችኋል? በአማርኛ እና በእንግሊዝኛኮ ነው የሚዘጋጀው፡፡ ታድያ ፈረንጅ ሲጋበዝ ግራ እንዳይገባው መሰላችሁ? ትርጉሙ ሌላ ነው፡፡ ቀላል አይደለንም ነው ነገሩ፡፡
  Mamush,MN

  ReplyDelete
 60. ዳኒ በጣም ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ነገር ነው የነገርከን ሁሉም ሀገሮች ማንነታቸውን ይዘው ነው ይደጉት......
  30 ሺ ወገኖቻችን ካለቁበት የሰማዕታት 75ኛ ዓመት በዓል ይልቅ የቫለንታይን በዓል በሚደምቅበት ሀገር ተቀምጣችሁ እንግሊዝኛ ጣ'ል አታድርጉ ማለት ነውር ነው፡፡

  ReplyDelete
 61. hasabu tiru new yasmamal, neger gin be amaregna mehal giez tal madregn tsehafiw endet yayewal? new tilu k wech kuwanka gar bicha new?

  ReplyDelete
 62. tnsh asakegn! "Yelbn sinegrut ye korekorut yahl yiskal" ybal aydel.Ewnet endih des ylal.be Ewnet des ybelena... Mndn new zm blo kenfer mezergat...?

  ReplyDelete
  Replies
  1. በአማርኛ ላይ ኦሮምኛ፣ በትግርኛ ላይ ሶማልኛ ጣ'ል ማድረግማ በሽሮ ላይ ድንች ጣ'ል እንደ ማድረግ ነው፡፡

   Delete