ከወንዝ በላይ እና በታች የሚገኙ ሁለት መንደሮች ነበሩ፡፡ ላይኛው መንደር ወንዙ ከሚመነጭበት ከተራራው ላይ የተመሠረተ ሲሆን ታችኛው መንደር ደግሞ ወንዙ ከሚወርድበት ከገደሉ ሥር የተመሠረተ ነው፡፡ እነዚህ ሁለት መንደሮች እየሰፉ እና ሕዝባቸውም እየበዛ መጣ፡፡ መንደሮቹም ወደ ወንዙ በጣም ተጠጉ፡፡ አልፈውም ከወንዙ እየተሻገሩ ቤት ሠሩ፡፡
በዚህም የተነሣ ዝናብ ዘንቦ ወንዙ በሞላ ቁጥር ከላይኛው መንደርተኞች አያሌዎችን እየጠረገ ወደ ገደሉ ያመጣቸው ነበር፡፡ በመጀመርያው አካባቢ ብዙዎቹ የላይኛው መንደርተኞች በወንዙ እየተወሰዱ ሞቱ፡፡ በኋላ ግን የታችኛው መንደር ነዋሪዎች ዝናብ ዘንቦ ወንዝ በሞላ ቁጥር እየተወሰዱ የሚመጡትን የላይኛውን መንደርተኞች እየዋኙ ያወጧቸው ጀመር፡፡
ይህንን ያዩት ላይኞችም ዘመዶቻቸውን ወንዝ ሲወስድባቸው እየጮኹ ታችኞችን መጣራት ልማድ አደረጉት፡፡ ታችኞቹም እየዘለሉ ወንዝ ውስጥ በመግባት ማውጣቱን ለመዱት፡፡ ላይኞቹ መንደርተኞች በታችኞቹ መንደርተኞች ርዳታ በመደሰት አንድ ነፍስ ባዳኑላቸው ቁጥር አንድ መቶ ብር ይከፍሏቸው ነበር፡፡ ታችኞቹም ይህንን እንደ አንድ የገቢ ማግኛ መንገድ እየቆጠሩት መጡ፡፡
እንዲያውም ታችኞቹ በወንዝ የተወሰዱ ሰዎችን ተጠባብቀው የሚያወጡ ድርጅቶችን መሥርተው፣ ሠራተኞችን ቀጥረው፣ መሣርያዎችን አደራጅተው በኩባንያ ደረጃ ሥራውን ተያያዙት፡፡ የነፍስ አድን ሥራውም የታችኛዋ መንደር ዋና የንግድ ተግባር ሆነ፡፡ አንዳንዶች እንዲያውም በላይኞቹ መንደርተኞች ላይ ዝናብ እንዲወርድ እስከ መጸለይ ይደርሳሉ እየተባሉ ይታሙም ጀመር፡፡ በየጊዜውም የማውጫው ዋጋ እየጨመረ ሄደ፡፡
የነፍስ አድን ድርጅቶችን ተከትለው ወንዙ ያመጣቸውን ሰዎች የሚመልሱ ፈረሰኞች ኩባንያ መሠረቱ፡፡ እነርሱን ተከትለው ወንዙ የጎዳቸውን የሚያክሙ ሐኪም ቤቶች በታችኛው መንደር ተቋቋሙ፡፡ ሐኪም ቤቶቹን ተከትለውም መጠለያ የሚያከራዩ ቤቶች ተሠሩ፡፡
በሁኔታው ያዘነ አንድ ከላይኛው መንደር መጥቶ በታችኛው መንደር የሚኖር ወጣት አንድ ቀን ጓደኞቹን ሰበሰበና እንዲህ አላቸው «ለምን እኛ በላይኞቹ መከራ እናተርፋለን? ለምን ችግሩን ከወንዙ በላይ አንፈታውም?»፡፡ ከጓደኞቹ እንዱ «ምን እያልከን እንደሆነ ገብቶሃል? የናንተ እና የወላጆቻችሁን ጉሮሮ ዝጉ እያልከን ነው፤ በየትኛውም ዓለም አንዱ የሚያተርፈው በሌላው መከራ ነው፡፡ ያንዱ ልቅሶ ለሌላው ሠርግ ነው፤ ያንዱ ርሃብ ለሌላው ጥጋብ ነው፡፡ ያንዱ ሕመም ለሌላው ጤና ነው፡፡» ሌላውም በንዴት መለሰለት «ይህንን ሃሳብ እኛ እንደሰማንህ ማንም አይ ስማህ፡፡ እኛ መሥራት የሚያስፈልገን ልክ የሌለው ዝናብ በላይኛው መንደር የሚወርድበትን መንገድ ነው»፡፡
ጓደኞቹ እንዳሉትም የመንደርዋ ሰዎች የዚህን ወጣት ሃሳብ ሰሙ፡፡ ሁሉም በአንድ እግራቸው ቆሙ፡፡ ይህንን ሲያይ ወጣቱ ጠፍቶ ወደ ላይኛው መንደር ገባ፡፡ እዚያም ገብቶ ያንኑ ሃሳብ ለሽማግሌዎቹ አቀረበላቸው፡፡
«ምን ያስጨንቅሃል ልጃችን፡፡ እኛን ወንዙ ቢወስደን ተሯሩጠው ገብተው የሚያወጡን የታችኞቹን መንደር ሰዎች እግዚአብሔር ሰጥቶናል፡፡ እንጂ ምን ቸገረን ብለህ ነው፡፡ ድሮ ወንዙ ሰውን ይገድል ነበር፡፡ አሁንማ እድሜ ለታችኛዋ መንደርተኞች ቢወስደን ይመልሱናል» አሉት፡፡
«የእናንተ መፍትሔ የታችኛው ወንዝ መፍትሔ ነው፡፡ ችግሩን ከሥሩ የሚፈታ ሳይሆን ችግሩ እድሜ እንዲያገኝ የሚያደርግ ነው፡፡ ሰዎቻችሁ በወንዙ ሲወሰዱ በገደላ ገደሉ ይጎዳሉ፡፡ እናንተም ለነፍስ አድን ሠራተኞች ብዙ ገንዘብ ታወጣላችሁ፡፡ ከዚህም በላይ ወንዙ ችግራችሁ እንጂ መፍትሔያችሁ ሆኖ አይኖርም፡፡» አላቸው፡፡
«ታድያ ምን ይሁን ነው የምትለን?» አሉት መንደርተኞቹ፡፡
«መንደርዋን ከወንዙ የሚለይ፣ ወንዙንም ግራ እና ቀኝ የሚገድብ ግንብ እንሥራ፤ ችግሩን እስከ መጨረሻው እንፍታ» አላቸው፡፡
መንደርተኞቹ የልጁን ሃሳብ ለመቀበል ፈለጉ፡፡ በመካከል ግን አንዳንዶቹ «በቀላሉ ልናልፈው የምንችለውን ነገር ለምን ታወሳስብብናለህ፡፡ መፍትሔው ቀላል ነው፡፡ ሰው በወንዝ ከላይ ይወሰዳል፣ከታች ይተርፋል፡፡ አለቀ በቃ» ሕዝቡ ተበተነ፡፡
ይህንን የልጁን ሃሳብ የታችኛዋ መንደር ሰዎች በወሬ ወሬ ሰሙ፡፡ በተለይም ነፍስ በማዳን ሥራ ገንዘብ የሚሰበስቡት ነዋሪዎች አንጀታቸው አረረ፡፡
«ማድረግ ያለብን ሁለት ነገር ነው» አሉ ታችኞቹ፡፡ «ይህንን ልጅ መግደል፣ ወደ ላይኛዋ መንደር ስሚንቶ እና ድንጋይ እንዳይገባ ማገድ፣ የግንባታ ዕውቀት ያላቸውን ሰዎች ወደ ታችኛው መንደር እንዲሰደዱ ማበረታታት፣ ወይንም ይህንን ሞያ ትተው ሌላ ሞያ ውስጥ እንዲገቡ ማድረግ ነው፡፡ ከዚህ በላይ ከሆኑም ርምጃ መውሰድ፡፡»
ወደ ላይኛዋ መንደር ምንም ዓይነት የግንባታ ዕቃ እንዳይገባ ታገደ፡፡ ግንበኛ የተባለ ሁሉ ቀስ በቀስ ከመንደርዋ ይጠፋ ጀመር፡፡ የአንዳንዶችም እጅ ባልታወቁ ሰዎች መቆረጡ ተሰማ፡፡ በወንዝ ዳር ግንብ መሥራት አስቸጋሪ መሆኑን፣ ከዚህ በፊት ለመሥራት የሞከሩ መንደሮች አደጋ እንደደረሰባቸው ይወራ ጀመር፡፡ ግንቡን ለመሥራት ከሚወጣው ወጭ ይልቅ የሰዎቹን ነፍስ ከታችኛው መንደር ለማዳን የሚወጣው ወጭ ቀላል መሆኑን፡፡ ይህንን ግንብ በመገንባት ከፍተኛ ወጭ ከማውጣትም ገንዘቡ ለሌላ ነገር ሊውል እንደሚችል በየጠጅ ቤቱ መከራከርያ ሆነ፡፡
በታችኛዋ መንደር ውስጥ ከላይኛው መንደር በውኃ ለሚወሰዱ ሰዎች ርዳታ የሚያሰባስቡ አያሌ ድርጅቶች ተመሠረቱ፡፡ የላይኛው መንደር ነዋሪዎች በወንዝ ሲወሰዱ፣ ከገደሉ ሲወድቁ፣ ውጭ ነፍስ ግቢ ነፍስ ከወንዙ ጋር ሲታገሉ፣ በነፍስ አድን ሠራተኞች ከወንዝ ሲወጡ፣ ርዳታ ሲደረግላቸው፣ በኋላም ወደ ላይኛው መንደር ሲመለሱ የሚያሳዩ ፊልሞች፣ ፖስተሮች፣ ባነሮች እየተሠሩ ለሕዝቡ ይበተኑ ጀመር፡፡ አንዳንድ ጊዜም ተጎዱ እየተባለ የሚነገረው የላይኛው መንደር ነዋሪዎች ከጠቅላላው የመንደርዋ ነዋሪዎች ቁጥር ይበልጥ ነበር፡፡ አንዳንዶች እንዲያውም «ወንዙ ወደፊት የሚወለዱትንም ይዞ ይመጣል እንዴ?» እያሉ በቁጥሩ ይገረሙ ነበር፡፡
አንድ ቀን የታችኛዋ መንደር ሰዎች ርዳታ ይዘው ወደ ላይኛው መንደር መምጣታቸው ተነገረ፡፡ የከተማው ሕዝብ በደግነታቸው እና በቸርነታቸው ተደንቆ መንገድ ላይ ወጥቶ በጭብጨባ እና በእልልታ ተቀበላቸው፡፡
የልዑካን ቡድኑ መሪ ንግግር አደረጉ፡፡ «በየጊዜው በወንዙ በሚወሰዱ ወገኖቻችን ኀዘን ይሰማናል፡፡ ይህንን ችግር እያየን እና እየሰማን ዝም ለማለት ሰብአዊ ኅሊናችን ስላላስቻለን ይህንን ርዳታ ጭነን መጥተናል፡፡» ብለው ሰዎች በወንዝ ሲወሰዱ ከሩቁ ለመታየት እንዲችሉ የሚያደርግ መብራት ያለው የእጅ አምባር በርዳታ ሰጡ፡፡ «ለወደፊቱም ሦስት ነገሮችን አስበናል፡፡» አሉ የልዑካኑ መሪ
- ወንዙ ሰዎቹን ሲወስድ ለኛ በቀላሉ መልእክት የምታስተላልፉበት ስልክ እናስገባለን
- ሰው በወንዝ ሲወሰድ ከገደል ጋር እንዳይጋጭ ምን ማድረግ እንዳለበት ሥልጠና እንሰጣለን
- ከወንዝ ተርፈው ወደ መንደራቸው ለሚመለሱ ተጎጅዎች የመቋቋሚያ ርዳታ እንሰጣለን
ሕዝቡ አጨበጨበ፡፡
«በመጨረሻ» አሉ መሪው፡፡ «ይህንን ሥራ የሚያስተባብር የርዳታ ደርጅት በዚህ በእናንተ መንደር እናቋቁማለን፡፡»
ሕዝቡ አሁንም አጨበጨበ፡፡ በሚቀጥለው ቀን የልዑካን ቡድኑ የርዳታውን ድርጅት በመንደርዋ ተከለ፡፡ ብዙዎቹ ለከፍተኛው ደመወዝ ሲሉ ተቀላቀሉት፡፡ ወንዙን በእግራቸው ለሚሻገሩ፣ እንስሶቻቸውን ወንዝ ለሚያጠጡ፣ በወንዙ ዳር ቤታቸውን ለሠሩ፣ በወንዙ ውኃ ለሚቀዱ፣ ወንዙ ሲሞላ ወደ መንደራቸው ለሚመጣባቸው ሰዎች ትምህርት የሚሰጥበት ታላቅ ዐውደ ጥናት በቀጣዩ ሳምንት ተዘጋጀ፡፡
ብዙዎቹም ለአበሉ፣ ለካናቴራው እና ለኮፍያው ሲሉ አዳራሹን ሞሉት፡፡ በዚያ ዐውደ ጥናት ላይ ለመሳ ተፍ መንገድ ከጀመሩት መካከል የተወሰኑት በወንዙ መወሰዳቸው እዚያው ዐውደ ጥናቱ ላይ ተነገረ፡፡ ዐውደ ጥናቱን በንግግር የከፈቱት ባለ ሥልጣንም «ትምህርቱን በሚገባ ከተማራችሁ፣ ስልኩም ከተተከለ ጉዳቱን እንቀንሰዋለን፡፡ ወገኖቻችን በወንዝ ቢወሰዱ እንኳን በትምህርቱ መሠረት ሳይጎዱ ታች ይደርሳሉ፤ በሚተከለው ስልክ አማካኝነት ደግሞ በአስቸኳይ ለታችኛው መንደር መልእክቱ ስለሚደርስ በቶሎ ያድኗቸዋል፡፡ ርዳታው ሲጀመርም በአስቸኳይ በቀድሞ ቦታቸው እንዲቋቋሙ ይደረጋል፡፡» አሉ፡፡
ውይይቱ ሲጀመር አንድ ሰው በጉዳዩ በጣም አዝኖ እንዲህ አለ «ይህንን ችግር ለመፍታት ሁለት ዓይነት መንገድ አለው፡፡ የታችኛው መንደር እና የላይኛው መንደር መፍትሔ፡፡ "የታችኛው መንደር መፍትሔ" ያልኩት የችግሩን እድሜ በማስቀጠል የሚኖር መፍትሔ ነው፡፡ ችግሩን ከመፍታት ይልቅ የሚያስታግሥ፡፡ እንድንፈታው ሳይሆን እንድንረሳው የሚያደርግ፡፡ ምክንያቱም ችግሩ እኛን ቢጎዳንም ችግራችን የሚጠቅ ማቸው ሰዎች ግን አሉ፡፡ የታችኛው መንደር ሰዎች ችግራችን ይጠቅማቸዋል፡፡ እኛ በወንዝ ካልተወሰድን እነርሱ ገቢ አያገኙም፡፡ በተዘዋዋሪ መንገድ ደግሞ እኛን መቆጣጠር አይችሉም፡፡ «ካሁን በኋላ ወደ ወንዝ የሚገቡትን አናወጣም» በማለት ብቻ የፈለጉትን ሊያሠሩን ይችላሉ፡፡
«እንዴት እንደምትወድቅ፣ ስትወድቅ ምን ማድረግ እንዳለብህ፣ ከወደቅክ በኋላ ተመልሰህ እንደገና እስክትወድቅ ድረስ እንዴት መኖር እንዳለብህ የሚነግርህ መፍትሔ «የታችኛው መንደር መፍትሔ» ነው፡፡ «የላይኛው መንደር መፍትሔ» ግን ይለያል፡፡ በቃ እንደ ምንም ተሟሙተን ግንቡን እንገንባው፣ መንደርዋን ከውኃ መጥለቅለቅ የሚታደጋትን ግንብ እንሥራው፡፡ ጊዜ ገንዘብ ይጠይቃል፤ ጉልበት ይጠይቃል፤ መሥዋዕትነት ይጠይቃል፡፡ ነገር ግን ያ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ችግሩን ይፈታዋል፡፡» አንድ ሁለት ሰዎች አጨበጨቡለት፡፡ ሌሎች ግን አጉረመረሙበት፡፡
«በወንድሜ ሃሳብ እስማማለሁ» አሉ አንድ ሰው ተነሥተው፡፡ «ግን ጊዜው ገና ነው፡፡ አሁን ግንብ የምንገነባበት ጫንቃ የለንም፡፡ አሁን ዐቅማችን ይህንን አይፈቅድም፡፡ አንደኛ ይህንን ስናደርግ ከታችኛዋ መንደር ወዳጆቻችን ጋር እንጋጫለን፡፡ ሁለተኛ ርዳታቸውን ያቆሙብናል፡፡ ሦስተኛ የምንገነባበት ሲሚንቶ እና ድንጋይ የለንም፡፡ አይዞህ እንደርስበታለን፡፡ አንድ ቀን እንደርስበታለን፣ አትቸኩል» ቤቱ በደስታ እና በጭብጨባ ደመቀ፡፡
«ዛሬ ካልሆነ መቼ?
እኛ ካልሆንን ማን?
እዚህ ካልተጀመረ የት?» የመጀመርያው ሰው ተሟገተ፡፡
«እንደተባለው ነው» አለች አንዲት ወጣት፡፡ «አሁን በብዛት የሚያስፈልጉን የርዳታ ድርጅቶች ናቸው፡፡ ሰዎች እንዴት ነው በወንዝ ውስጥ መሻገር አለባቸው? ለዐቅመ ደካሞች በወንዝ ውስጥ ሲሻገሩ የሚይዙት ምን ዓይነት መቋሚያ መዘጋጀት አለበት? የወንዙ መውረጃ ላይ ያሉ ዐለቶችን ሰው እንዳይጎዱ እንዴት ማስተካከል ይቻላል? ወንዙ ይዟቸው የሚሄዱትን ሰዎች ታችኛው መንደር ላይ ሲጥላቸው እንዳይጎዱ እንዴት ቦታውን በአሸዋ ማስተካከል ይቻላል? እነዚህን ሊመልሱ የሚችሉ የርዳታ ድርጅቶች ያስፈልጉናል፡፡? አለች፡፡
«እኛ እነዚህን ጥያቄዎች ሊመልስ የሚችል ጥናት እንዲደረግ አራት ሚሊዮን ብር መድበናል? ብለው የታችኛዋ መንደር የልዑካን ቡድን መሪ ሳይጨርሱ የብዙዎች ፊታቸው ጥርስ ሆነ፡፡ አንዳንዶቹም እዚያው ተቀምጠው «ፕሮፖዛል» መሥራት ጀመሩ፡፡
መጀመርያ ሃሳብ ሰጥቶ የነበረው ሰው «ይህንን ግንብ ለመሥራትኮ ከዚህ በላይ አያወጣም፡፡ ጥናቱ ቀርቶ ለምን ግንቡ አይሠራም?» አለና ጠየቀ፡፡
«በጀቱ የተፈቀደው ለጥናት እንጂ ለግንብ አይደለም» አሉት መሪው ተናድደው፡፡
በዜና ማሰራጫዎች እንደ ተነገረው ዐውደ ጥናቱ «በተሳካ መንገድ» ሲጠናቀቅ የሚከተለውን መዝሙር እጅ ለእጅ ተያይዘው ተሳታፊዎች ዘመሩት
ወንዙ ጅሉ ጅሉ
አንተ ብትወስደንም እንተርፋለን ቅሉ
ቆሬው እንዳይጎዳን እንጠርገዋለን
ሺ ጊዜ ብትወስደን ሺ ጊዜ እንተርፋለን
እነሆ በዚያች መንደር የርዳታ ድርጅቶች እንደ አሸን ፈሉ፡፡ ወንዙም ሰዎችን እንደ አሸን ይወስዳል፤ እንደ አሸን የፈሉት የነፍስ አድን ድርጅቶችም እንደ አሸን የበዛ ገቢ ያገኛሉ፡፡ እንደ አሸን የበዛ ጥናት ይደረጋል፡፡ እንደ አሸን የበዛ ርዳታ ይመጣል፡፡ እንደ አሸን የበዛ ዐውደ ጥናት አለ፡፡ እንደ አሸን የበዛ ካናቴራ ይታተማል፡፡ እንደ አሸን የበዛ ቢል ቦርድ ይሰቀላል፡፡
የላይኛው መንደር መፍትሔ እስኪሠራ ድረስ ሀገር እንዲህ ትኖራለች፡፡
Hahaha..... You makes me happy. You know why? Because you are singing what am singing. That is the reason my brother. It is a good oversight. Be brave brother.
ReplyDeleteHaileyesus, from Debremarkos
Dani, አንተ በርክትልን!
ReplyDeleteMamush,MN
ሀገር እንዲህ ትኖራለች!! ልክ ነህ መፍትሄው ከላይ ነው፡፡
ReplyDeleteየላይኛው መንደር መፍትሔ እስኪሠራ ድረስ ሀገር እንዲህ ትኖራለች፡፡
ReplyDeleteድንቅ ነው ከዚህ በላይ ማለት አልችልም:: ደጋግሜ ደጋግሜ ላነበው የሚገባኝ መልእክት:: ከድህነት ለመውጣት የላይኛው መንደር መፍትሔ ያስፈልጋል::
ReplyDelete"መጀመርያ ሃሳብ ሰጥቶ የነበረው ሰው «ይህንን ግንብ ለመሥራትኮ ከዚህ በላይ አያወጣም፡፡ ጥናቱ ቀርቶ ለምን ግንቡ አይሠራም?» አለና ጠየቀ፡፡"
ዳኒ ምን ላድርግህ: ከሥራ ጫና ብዛት ይሄንን ሳምንት ብሎግህን ላለመክፈት ፈልጌ ነበር ግን አልቻልኩም: ከፍቼ ሳነብ ይህንን አይነት አሪፍ ጽሑፍ አስነበብከኝ:: በቃ አሁን አታዘናጋኝ ላጥናበት::
አድናቂህ ነኝ!!!!!!!! እግዚአብሔር እንደ በፊቱ ሁሉ ካንተ ጋር ይሁን::
እጅግ በጣም ግሩም ፅሑፍ ነው! የዛሬዋ ኣፍሪካ ችግር ነው! የዛሬዋ ኢትዮጵያ ጉድ ነው!!
ReplyDeleteበእውነት ነገሮችን በጥንቃቄ የሚመለከት ብሩህ ህሊና ነው ያለህ!!
እጅግ በጣም እናመሰግናለን!! እግዚኣቢሔር ይስጥልን።
ስኮት ፔክ የሚባል ሳይኮቴራፒስት “የሰው ልጅ ያለበት ጥንተ አብሶ ወይም አዳማዊ ኃጢኣት (Original Sin) ስንፍና ነው፡፡” ይላል፡፡ ስንፍና ብዙ መልኮች እንዳሉትና አንዱና ትልቁ ከአዳም የወረስነው ኃጢኣት መገለጫው ለለውጥ ያለን ስንፍና እንደሆነ ያስረዳል፡፡ ሁላችን የምቾት ዞናችንን የሚነካብንን ሰው ፈጽሞ አንወድም፡፡ የምቾት ዞናችንን ለማስጠበቅ ከኩርፊያ እስከ ሐሜት፣ ከዛቻ እስከ ግድያ ያሉ ቴክኒኮችን ስንጠቀም ኖረናል፡፡ የኢንኲዚሽን ፍርድቤቶች፣ ቋንጃና አፍንጫ ቆረጣዎች፣ ጀሀድ ጦርነቶች ሁሉ የምቾት ዞናችንን ለማስጠበቅ ከተፋለምንባቸውና እየተፋለምንባቸው ካሉ ግንባሮች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
ReplyDeleteበስኮት ፔክ አስተሳሰብ፣ አዳምና ሔዋን የመጀመሪያው ጥፋታቸው የተከለከሉትን ፍሬ መብላታቸው አይደለም፡፡ እባብ ፍሬዋን እንዲበሉ ሲሰብካቸው እባብን ብቻ ከማመን ይልቅ በግልጽ ያናግሩት የነበረው አምላካቸውን “ለምን ከለከልኸን?” ብለው ጠይቀው ለመረዳት አለመሞከራቸው እንጂ፡፡ የዚህም ምክንያቱ ስንፍና ነው፡፡ ስንፍና ከሚደበቅባቸው ወይም ራሱን ከሚገልጥባቸው መንገዶች አንዱ ደግሞ ያልተገባ ፍርኃት ነው፡፡ አምላክን ምን ብለን እንጠይቀዋለን ብለው ፈሩ፡፡ ፍርኃታቸው ግን ስንፍና እንጂ ተገቢ ፍርኃት አለመሆኑ የሚታወቀው አታድርጉ የተባሉትን በማድረጋቸው ነው፡፡ አታድርጉ የተባሉትን ለምን አታድርጉ እንደተባሉ ለመረዳት “አታድርጉ!” ያላቸውን ፈጣሪያቸውን ከመጠየቅ ይልቅ የእባብን ምክር እንዲሁ መቀበልን መረጡ፡፡ ለመጠየቅ ሰነፉ፡፡
ስለሆነም የላይኛው መንደር ሰውዬ
“አሁን ግንብ የምንገነባበት ጫንቃ የለንም፡፡ አሁን ዐቅማችን ይህንን አይፈቅድም፡፡” የሚሉትን ከስኮት ፔክ የተማርሁትን ትምህርት ተገን አድርጌ ስረዳው ሰውየው “ጫንቃ” የሚሉት ተራ ጫንቃ አይደለም፡፡ ጫንቃ ጭንቅላት ነው፡፡ “ጫንቃ የለንም፡፡” ማለት “አንተ የምትሰብከውን ለውጥ የምናስብበት ጭንቅላት የለንም፡፡” ማለት ነው፡፡ አንድም ለውጥ የምትጠይቀውን ውጣ ውረድ “የምንጋፈጥበት የወኔ እንጥፍጣፊ አልቋጠርንም፡፡” ማለት ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ አዲሱን ዓለም የመገንባትን ውጣውረድ በድፍረት ከመጋፈጥ ይልቅ በስንፍናችን ውስጥ መተኛት ይመቸናል ነው፡፡ ስንፍና አዳማዊ ኃጢኣት!
Anonymous
Deleteit is an eagle eye watching, keep in touch
U r right.... nice interpretation.
DeleteThis is your best articel in 2004EC. I love it, you nailed it. This article very differnt from the others, it strart with history, it finished with that. Thank you Dani
ReplyDeleteDear Daniel,
ReplyDeleteThis is really a very wonderful expemplery message. In most part of the world people are living lexuriosly with conference tourisim. Somalia had more than 16 reconcilation fora and none of them are workable. Fire exthingushing could not be a solution.
Switzerland,
This is a well written article. Thanks for your hard work and sharing with us.
ReplyDeleteOMG amazing article how powerful is the message in it. This is how we really are ( kewenzu belay).
ReplyDeleteThxs So much D/Danel
Thank you for your article. This article look like "Animal Farm" book style.You show us a number of points in this article.
ReplyDeleteBrile
nice articlegood job dani
ReplyDeleteታሪክና ተረት የመፈልሰፍ ችሎታህን አደንቃለሁ
ReplyDeleteThanks Dn. Daniel. This is our situation in Ethiopian Today. Nobody cares about long-term solution, some people make money with others' problems. Some of them think about the perdiem and the T-shirt, and others think about how they can get money for themselves. Some local NGOs do not care about the real poverty problem. They take street children's picture to get donation, but they do not help the poor children. They make Ethiopia as an example of poverty. I feel bad with images coming when I put the word "Ethiopia" in gooogle search.
ReplyDeleteWelete-Amanuel
God bless you! የላይኛው መንደር መፍትሔ እስኪሠራ ድረስ ሀገር እንዲህ ትኖራለች፡፡!!!!
ReplyDeleteበየትኛውም ዓለም አንዱ የሚያተርፈው በሌላው መከራ ነው፡፡ ያንዱ ልቅሶ ለሌላው ሠርግ ነው፤ ያንዱ ርሃብ ለሌላው ጥጋብ ነው፡፡ ያንዱ ሕመም ለሌላው ጤና ነው፡፡
Deleteበጣም አስተማሪ ነዉ
ReplyDeleteD/n Daniel, Negerochin endet endemitayachew sasib betam yigermegnal.
ReplyDeleteEgziabher Tibebun abzito yadilih!,
Edmena Tena yistih. Kefetenam yitebikih. kemalet beker min afalegn.
Nice Perespective
ReplyDeleteit is a very nice written
ReplyDeleteit is very nice written d.daniel.
ReplyDeleteበጣም የሚገርም እይታ ነው በእውነት ይኼ ነገር በአሁኑ ጊዜ ቁልጭ ብሎ የሚታይ አስተሳሰብ ነው ዘላቂ መፍትሔ ከማምጣት ይልቅ ለጊዚያዊ ምላሽ በሚል ለጥናት ለሲፖዚየም ለውይይት ለስብሰባ እየተባለ የሚወጣው ገንዘብ ጊዜና ጉልበት በቀጥታ ለችግሩ ቢውል ምን አይነት ለውጥ እንደሚመጣ እስቲ አስቡት፡፡አሁን በዚህ ሰዓት እንኳን የራስን ኪስ በአበል ለመሙላት የይምሰል አውደጥናቶች ምን ያህል እየተካሄደ እንደሆነ ሳስበው በጣም ያመኛል፡፡ግን እስከመቼ ለራሳችን እንጂ ለሀገር የሚጠቅም ዘላቂ መፍትሔ ሳናመጣ ሆዳሞች ሆነን እንቀጥላለን፡፡እስኪ እስከዛሬ ለጥናት ተብሎ የወጣው ገንዘብ ምን ያህል እንደነበር እናስብ፡፡ፈረንጆቹ ከረዱን ይልቅ የወሰዱት ምን ያህል ይሆን ፤ከወገናችን ውስጥስ የእርዳታ ድርጅት ካቋቋሙት ምን ያህሉ ለተቋቋሙት አላማ ከመስራት ይልቅ ስንቶቹ ናቸው ኪሳቸውን ከማደለብ አልፈው ችግሩ እንዳይቀረፍ እንቅፋት የሚሆኑት፡ለአንድ ችግር መፍትሔ ስብሰባ ተብሎ ላንጋኖና አዋሳ ናዝሬት ወይም ሌላ ቦታ ካልሆነ የማይዋጥላቸው ስንቶቹ ናቸው፡ ስለዚህ አዎ መፍትሔው ከላይ ነው ከአምላካችን እርሱ ይርዳን አሜንበጣም የሚገርም እይታ ነው በእውነት ይኼ ነገር በአሁኑ ጊዜ ቁልጭ ብሎ የሚታይ አስተሳሰብ ነው ዘላቂ መፍትሔ ከማምጣት ይልቅ ለጊዚያዊ ምላሽ በሚል ለጥናት ለሲፖዚየም ለውይይት ለስብሰባ እየተባለ የሚወጣው ገንዘብ ጊዜና ጉልበት በቀጥታ ለችግሩ ቢውል ምን አይነት ለውጥ እንደሚመጣ እስቲ አስቡት፡፡አሁን በዚህ ሰዓት እንኳን የራስን ኪስ በአበል ለመሙላት የይምሰል አውደጥናቶች ምን ያህል እየተካሄደ እንደሆነ ሳስበው በጣም ያመኛል፡፡ግን እስከመቼ ለራሳችን እንጂ ለሀገር የሚጠቅም ዘላቂ መፍትሔ ሳናመጣ ሆዳሞች ሆነን እንቀጥላለን፡፡እስኪ እስከዛሬ ለጥናት ተብሎ የወጣው ገንዘብ ምን ያህል እንደነበር እናስብ፡፡ፈረንጆቹ ከረዱን ይልቅ የወሰዱት ምን ያህል ይሆን ፤ከወገናችን ውስጥስ የእርዳታ ድርጅት ካቋቋሙት ምን ያህሉ ለተቋቋሙት አላማ ከመስራት ይልቅ ስንቶቹ ናቸው ኪሳቸውን ከማደለብ አልፈው ችግሩ እንዳይቀረፍ እንቅፋት የሚሆኑት፡ለአንድ ችግር መፍትሔ ስብሰባ ተብሎ ላንጋኖና አዋሳ ናዝሬት ወይም ሌላ ቦታ ካልሆነ የማይዋጥላቸው ስንቶቹ ናቸው፡ ስለዚህ አዎ መፍትሔው ከላይ ነው ከአምላካችን እርሱ ይርዳን አሜን
ReplyDeleteFirst time visiting your blog. Good story and moral... keep it up
ReplyDeleteWell written.
ReplyDeleteNo comment Dani
God bless you! የላይኛው መንደር መፍትሔ እስኪሠራ ድረስ ሀገር እንዲህ ትኖራለች፡፡!!!!Nice Perespective Dani, አንተ በርክትልን!...
ReplyDeletegelets aderegeh bemigba yagerachinen gude kNail gare aberartehelenal Egziabeher dgemo beruh aemero yadeleh kaleheiwot yasemalen
ReplyDeleteDear Daniel
ReplyDeleteThis is the real problem of our country ETHIOPIA
I was laughing through the roof the way u wrote I love it, and also i was angry too because we have got plenty selfish people. only for them selves. Don't care about the rest. as long as they have got ብዙዎቹም ለአበሉ፣ ለካናቴራው እና ለኮፍያው ሲሉ አዳራሹን ሞሉት፡፡
May GOD bless u long live for u
በእውነት ነገሮችን በጥንቃቄ የሚመለከት ብሩህ ህሊና ነው ያለህ!!
እጅግ በጣም እናመሰግናለን!! እግዚኣቢሔር ይስጥልን።
“ለሞኝ ጉድጓድ አያሳዩትም ቤት ነው ብሎ ይገባበታል” አለች እህቴ እውነቷን እኮ ነው፤ “ለእባብ እግር የለው ለሞኝ ብልሃት የለው” እንዲል መፅሐፉ ወንዝ የወሰዳቸው ሰዎች መትረፍ እንደሚችሉ ሲያውቁ ልክ እንደ ሞኙ ቤቴ ብለው ተቀመጡ! ይህን አጋጣሚ እንደ ገቢያቸው የቆጠሩ ሰዎች ያወሩት የሐሰት ወሬም ሐሰቱን ዋዛ አደረገው፤ የሀገሬ ሰው “ሐሰቱ ሲበዛ እውነት ሆነ ዋዛ” ይል የለ።
ReplyDelete“ለማየት የፈለገ ዓይኑን ይከፍታል”
ለሚያጋጥመው ችግርም ዘላቂ መፍትሄ ይፈልጋል።
እናንተዬዋ ኧረ ለመሆኑ ዳንኤል የተባለው ወንድማችን የሚያነበው መፅሐፍ የት ይሆን የሚታተመው? መልካም ላባ ከመልካም እርግብ ይገኛል እንዲል ይህን ሰው ለሀገሪቱ ያበረከቱ ወላጆቹን አመሰግናለሁ! በእውነት ያለሐሰት የተከበሩ እናቱንና ባለቤቱን እናመሰግናለን። ለእያንዳንዱ ታላቅ ሰው ከጀርባው ታላቅ ሴት አለችና ይህ ምስጋና ይገባል!
እኔ በምኖርበት በለንደን ከተማ በቅርቡ ለሀገሪቱ ታላቅ ስራ ያበረከቱ ሰዎች ሽልማት ተሸልመዋል፤ ይህ በሀገራችን ቢለመድ እንዴት መልካም ነበር።
OMG! anjetaen kibe atetahw. I taught I was reading my own taughts displayed on the screen...
ReplyDeleteGod Bless!!!!!!
thumps up dani. What a nice perspective.
ReplyDeletethe style looks pretty much that of "Animal Farm", did u read that book?
long live
I visualized this piece of writing for ABYE(BLU NILE) I mean think about it Dn Dani is (was)??a supporter the new ABYE DILIDYE thing. I think I got what he wanted to communicate.....readers let us see it that way too but I do not mean you(readers) are not correct!
ReplyDeleteAs long as any piece of information has some impact or likable with the readers, I think it is OK to be appreciated. Daniel is sending the right message to his audiences. Wherever he brought the materials and as long as he doesn't copy them word by word, I really read them and learn from every article he can come up with. After all it is all about the messages.
DeleteNice article in our native way so that a lot of people can understand whatever the writer trying to convey.
Good job!
It is not about the River Abay. It is about NGOs in Ethiopia. I know what this NGOs (both foreing & local) are doing. I am their employ for the sake of transient money although I know I am not accomplishing things for long lasting benefits of the country & its people. I have had the emotion to produce the fact as book but afraid because I could lose my salary. Thanks Dani!!
DeleteDani, many of us agreed z article is perfect. U know what this is 1. We r so suppressed to make a huge step forward 2. Z problem is at z head, not at z extremities! Almighty God multiply our good brothers and sisters. Amen.
ReplyDeleteOhh!!dn Daniel you are so gifted for this! i am so impresed .this is the real problem of aid dependent 3rd world counties like ethiopia!!that is why" AIDS kegedelwu AIDS yakeberew yibeltal" eyetebale yemikledewu!!semi yalew joro yisma !!for you may GOD bless your work & family
ReplyDeleteወንዙ ጅሉ ጅሉ
ReplyDeleteአንተ ብትወስደንም እንተርፋለን ቅሉ
ቆሬው እንዳይጎዳን እንጠርገዋለን
ሺ ጊዜ ብትወስደን ሺ ጊዜ እንተርፋለን
yegaremale
ReplyDeletegerum nwe yelayegnochu meder sewoch yemenewekelewe yezarewa tewelede ethiopian ena ethiopian nen......ewenetaw beagebabunwe yetekemetewe....betam astemarinwe bereta
ReplyDeleteያንተው ፅሁፍ ዘካሪ መካሪ ነው እጅህን ያለምልመው፤የተባ ብዕር ነው፤ልቦናን ይነካል፤ወዘተ….ዘክእሌ ልቡ
ReplyDeleteጥሩ የቀለም ቀንዲል ነህ በዕርህ ሁልጊዜ እንደ ፀሐይ ብርሃን ለሁሉም ይዳረስ መልካም ጤና ከቤተሰብህ ጋር ያንተው
ReplyDeleteዘጠበሉ ዮሐንስ
ወንድም ዲያቆን ዳንኤል መቼም እንደዚህ አይነት ጥልቀትና ስፋት ያለው ነገር ስትፅፍ መላእክት ሹክ እያሉህ ይመስላል፡፡እጅግ ድንቅ ፅሁፍ ነው፡፡የዘመናችንን አለም አቀፍ የካፒታሊስት ስርዓት ምንነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነገር ነው፡፡እንደዚህ አይነቱን አጠቃላይ ክስተትና ሂደት ፈረንጆች የዜሮ ድምር ውጤት(Zero-Sum-Game)ይሉታል፡፡አንዱ የሚያገኘው መልካም ጠቃሚ ነገር በሌሎች መጥፎ ክስረትና ጥፋት እየሆነ መምጣቱ የሀገራችንና የዓለማችንን አጠቃላይ ሁኔታ እጅግ ውስብስብና አሳሳቢ እያደረገው ነው፡፡በእርግጥ ጉዳዩ በዚህ አይነት ሁኔታ ከቀጠለ ከዜሮ ድምር ውጤት(Zero-Sum-Game) ወደ ኔጌቲቭ ድምር ውጤት(Negative-sum-game) የሚሸጋገርበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም፡፡
ReplyDeleteማንኛውም ነገር እንደ ሸቀጥ (Commodity) ለገንዘብ ልውውጥና ክምችት (money capital accumulation through the perpetual cycle of money sequencing) ሂደት መዋል ይችላል ወይንም አለበት የሚለው የካፒታሊዝም ስርዓት ስር የሰደደ የተሳሳተ አስተሳብ የፈጠረው ነገር ዛሬ ነሮችን ወደ ውስብስብ ሁኔታዎች ውስጥ እየከተተን ነው፡፡ድሮ ድሮ በየዋሁ ዘመን ታላላቆቻችን ሰዎች ሲልኩን ወይንም አንድ ነገር እንድናደርግላቸው ሲያዙን ይህንን በትህትና እንታዘዝ ነበር፡፡ዛሬ ግን ይህ አይነት የተለመደ የማህበራዊ ህይወት የእርዳታ ጥያቄ ሲቀርብ ስንት ብር ወይንም ሳንቲም ትሰጠኛለህ ብሎ መጠየቅ የተለመደ ነገር እየሆነ መጥቷል፡፡አንድ የተበላሸን ነገር የሚጠግን ሰው በአስተማማኝ ከመጠገን ይልቅ ዳግም እንዲበላሽና ተመሳሳይ የጥገና ገንዘብ ለማግኘት ሲባል እንደነገሩ አድርጎ መስራት የተለመደ ነገር እየሆነ መጥቷል፡፡በእለት ተእለት ህይወታችን የምንጠቀምባቸው ቁሳቁሶችና ሸቀጦችም ተገቢውን ጥራታቸውን ያልጠበቁ እየሆኑና ለትርፍ ሲባል ብቻ ተገቢውን አገልግሎት ሳይሰጡ ወዲያውኑ የሚበላሹ እየሆኑ ነው፡፡ይህም የሚደረገው አንድም ከገዥው አቅም ማነስ የመነጨ ቢሆንም በዋናነት ግን ምክንያቱ የምርት ሂደትን ላለማስተጓጎልና ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ ሲባል ነው፡፡ታዲያ ይህ አይነቱ አካሄድ የአካባቢ ብክለትንና እንዲሁም ተፈጥሮን ያለአግባብ የመመዝበርና የማራቆት ክስተትን እያስከተለ ነው፡፡ስለዚህም ይህ አይነት አካሄድ የአለም የተፈጥሮ ሀብት ውስን መሆንን ግምት ውስጥ ያላስገባና እንደዚሁም አላስፈላጊና አደገኛ የሆነ የተፈጥሮ ሀብት ብክነትንና መራቆትን ያስከትላል፡፡ይህ አይነቱ አንተ በደንብ አድርገህ የገለፅከው ነገር አንድም የሚመነጨው ከስግብግብነት ራስ ወዳድነትና እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አይነት ለራስ ብቻ ማሰብና ስለሌሎች የወደፊት ህይወት እጣ ፈንታ ምንም ካለመጨነቅ የሚመነጭ ነው፡፡መቼም ትዝ ይልሃል አንድ ወቅት ላይ ስለ ጫካና ስለ አራዊት አንድ እጅግ ጠቃሚ ነገር ፅፈህ ነበር፡፡አዎ አራዊቶቹ እንዴት አድርገው ጨካውን እንደሚጠብቁትና ጫካውም እንዴት አድርጎ ኣራዊቶቹን እንደሚያኖራቸው የሚያስረዳ ነበር፡፡ችግሩ ዛሬ የሰው ልጅ የፈጣሪንና የተፈጥሮን ህግ እየሻረ ለራሱ ጠባብና ስግብግብ ፍላጎትና እርካታ ሲል ከፍተኛ የሆነ አጠቃላይ ቀውስ እየፈጠረ መሆኑ ነው፡፡እያንዳንዱ ስነ-ፍጥረት እርስ በርሱ እጅግ በረቀቀና በተወሳሰበ መንገድ እርስ በርሱ እንደ ድር የተሳሰረ መሆኑን አብዛኞቻችን የተረዳን አይመስለኝም፡፡ዛሬ ብዙዎቻችን ሁሉም ነገር ላይ ቢዝነስ መስራትና ከዚያም ብዙ ገንዘብ በአንድ ጊዜ ዘርፎ ወይንም አትርፎ መርጥ መኪና እያሽከረከሩ በምርጥ ቪላዎችና ፎቆች እየኖሩ የራስን የቅንጦት ህይወት መምራት ይቻላል ብለን እናስባለን፡፡ነገር ግን ይህ አይነት “I do not care about others but first only me and me” አይነት ግለሰባዊ ፍላጎትንና እርካታን በመከተል እየተደረገ ያለ አደገኛ የእብደት አካሄድ ወደ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ እያመራን መሆኑን አብዛኞቻችን የተረዳን አይመስለኝም፡፡ለዚህም ነው ዛሬ ጫት አደንዛዥ እፅና እንዲሁም ሌላው መጥፎ ነገር ሁሉ ጥቂቶችን ሚሊዬነር ወይንም ቢሊዬነር ሲያደርገን የዚያኑ ያህል ደግሞ ሌሎችን ሚሊዮኖችን ወይንም ቢሊዮኖችን ከሰውነት ጎዳና እያስወጣን ያለው፡፡ትልቁ ችግር ያለው አጠቃላዩን የሰውን ልጅና ስነ-ፍጥረትን እንደ አንድ ወጥ ስብስብ በአንድ እይታ ባለ holistic view and approach ለማየት አለመቻሉ ነው፡፡እያንዳንዳችን የተለያዩ የሰውነት ብልቶች አሉን፡፡ከሰውነት ብልቶቻችን አንዱ ሲታመም በተዘዋዋሪም ሆነ በቀጥታ ሌላው ሰውነታችን ችግር ውስጥ ይወድቃል፡፡አይናችን ሲታወር እንቅፋት ይመታናል ከዚያም እግራችን ሊሰበር ይችላል፡፡ጆሯችንም ቢታመም እንደዚሁ፡፡ስለዚህም በሌላው ኪሳራ አንዱ ለጊዜው ያተረፈ ቢመስለውም የኋላ ኋላ ይዋል ይደር እንጂ ጉዳቱ ግን ለሁሉም ነው የሚሆነው፡፡በአንድ በኩል ስልጣኔና ይህ ስልጣኔ ያመጣብን አዲስ አይነት የኑሮ ዘይቤ ያመጣብን ጣጣ ህይወታችንን የብክነትና የውጥረት እንዲሆንና እያደረገው ነው፡፡ከዚያም የጤንነት ቀውስ ሲመጣብንና ልባችን ወይንም ኩላሊታችን ሲታመም ይኸው ስልጣኔ መልሶ አይዞን ምን ነካችሁ ልጆቼ እያለንና ከዚያም አይዟችሁ እያከምኩላችሁ ነው እያለን ነው፡፡ከሚያስፈልገን በላይ ገንዘብ ለመሰብሰብ ስንል የኋላ ኋላ ጤንነታችንን እናጣለን ጤንነታችንንም ለመመለስ ስንል መልሰን ገንዘባችንን እንገፈግፋለን፡፡ለገንዘብ ሲባል በጦርነት ደካማ ሀገራት ይፈራርሳሉ መልሰው ደግሞ ለገንዘብ ሲባል ይገነባሉ፡፡ይህ አይነት ጤናማ ያልሆነ የገንዘብ ዝውውር ኡደት ያለበት ስርዓት በቅጡ ሊመረመር ይገባል፡፡ያለበለዚያ ግን መላው የሰው ልጅና ስልጣኔም በራሱ አደጋ ውስጥ እንደሆኑ ይኖራሉ፡፡
ይጠቅመናል ብለን ያለ አግባብ እያግበሰበስን ያለነው የማያስፈልግ ብልጭልጭ አርቲ ቡርቲ ሸቀጥ ነገር ሁሉ የሚጠቅመንና የመኖር የህልውና መሰረታችን የሆነውን የሚያስፈልገንን ነገር ሁሉ መሰረት እየናድን እንደሆነ በቅጡ የተረዳን አይመስለኝም፡፡
በድጋሚ ለዳንኤል አድናቆቴን እገልፃለሁኝ፡፡
እግዚአብሄር ይስጥህ፡፡
Mehari Feb 22, 2012 07:13 AM
ReplyDeleteYou are also so genius and i respect you for this unique marvelous comment.Because it concerns me greatly.Yes chronic Laziness is our number one enemy and sin.
God bless you Mehari
ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ
ReplyDeleteታሪክና ተረት( የመፈልሰፍ የሚለው ቃል የማወቅ: የማንበብ :የማስተዋል ተብሎ ይነበብና ) ችሎታውን : ታታሪነቱን: መንፈሳዊ ጔዞውን ለሱም ሆነ መሰል ጓደኞቹ ታላቅ አክብሮትና ምስጋና አለኝ::ጌታም በመንገዳቸው ሁሉ አብሮ እንዲሆን የዘወተር ጾለቲ ነው::ለኛም የቀና ልቦና አስተዋይ አእምሮ ይስጠን:: ማድነቅን ከልብ እንድናውቀው::ዳኒ በርታ !
ReplyDeletereally interesting article.also i am getting knowledge from commentors.all laziness come from on thinking of i can't do things.without money,etc.
ReplyDeletethe article well defines the current NGOs in Ethiopia which are creating dependency to the peoples.
the current Chinese road building,railway building also creates huge fear on our local ability to do things ourself.example,if you see the railway rail Ethiopia got it before 100 years ago but still the governments are saying skill transfer like that but it is not like that,we are fearing to do things by our self.
መኖር ከተባለ ........
ReplyDeleteእጅግ በጣም ግሩም ፅሑፍ!!!!! God bless you!
ReplyDeleteNo words to thank you Dn Dani. Thanks!!!
ReplyDeleteI was thinking of the solutions for the problems [NGOs bad influence, losing committment to make difference by ourselves] many times. I also tried to discuss with people. But most prefers the per diem instead of facing the ups & downs for sometime & leting it go forever throgh committments to make a real difference. It has I think moral component. And I also believe that leaders (be it religious, political, family heads,....) must take the lions share to change the attitude of the mass. Guys what do you think?
ስንት እኮ የወገብ ቅማል አለ መሰለህ፤በሰው ሀዘን፣መከራ፣ሞኝነት… እሱ የሚደሰት፣የሚፈነድቅ፣የሚፈነጥዝ … ብቻ ሆድ ይፍጀው!
ReplyDeleteJust lords of poverty
ReplyDeletevery interesting message that has a lot of idea on it... I have got a chance to use websites after long time... as I choose this title I got many things on it... Thank you really Dn. Daniel...
ReplyDeleteas far as I understood people from any country are part of the river. chianis, Americans, Europe, Africans and the middle east people are all responsible for what happen in our country as they are for the Globes normal life...But still the lions share of the problem lies on all Ethiopians whether they are from any politics or religion...those who count themselves as religious person among Ethiopian orthodox church are among the great are not from the list solution finder mainly because they I can say we are from the earlist and the truth who have exact relation with almighty God more than any one almost
THE IDEA OF THIS ARTICLE IS VERY STRONG... EVERY ONE MUST BE OR TRY TO BE ON THE SIDE OF THE SOLUTION RATHER THAN PUTTING, OR SIMPLY LOOKING MILLIONS OF INNOCENT ETHIOPIANS WHILE THEY ENTER IN A VERY DANGEROUS LIFE, AND LIFE STYLE WHICH IS SHAME FOR THE READERS, THE RELIGION, THE COUNTRY, THE POLETICS, THE PHILOSOPHY WE FOLLOW, AND THE GIFT AND POWER WE HAVE...
I SAID MORE SORRY ...BUT THANKYOU AGAIN FOR SUCH WONDERFUL MESSAGE THAT I MISSED FOR LONG