Sunday, February 19, 2012

የዲ/ን ዳንኤል ክብረት “ራእየ ዮሐንስ - የዓለም መጨረሻ” መጽሐፍ ተመረቀ(አዲስ አድማስ ጋዜጣ፤)

የዲ/ን ዳንኤል ክብረት “ራእየ ዮሐንስ - የዓለም መጨረሻ” መጽሐፍ ተመረቀ 
(አዲስ አድማስ ጋዜጣ፤)


18ኛ መጽሐፉ ነው ተብሏል

ከመጽሐፍ ቅዱስ(ዐሥራው) መጻሕፍት ሁሉ በስፋት ያልተተረጎመው የዮሐንስ ራእይ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ራእዩ በምሳሌዎች፣ ምልክቶች እና ትንቢቶች በመሞላቱ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ከአንድምታ ትርጓሜው ባሻገር የዮሐንስ ራእይ ከክብደቱ አኳያ ተጨማሪ ማብራሪያዎች እና መረጃዎች እንደሚያስፈልጉ የነገረ ቤተ ክርስቲያንና ታሪክ ተመራማሪው ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ያስረዳል፡፡ በዚህ ረገድ የተሻለ መረጃ ለአንባብያን በማቅረብ ያለውን ክፍተት ለመሙላት ”ራእየ ዮሐንስ - የዓለም መጨረሻ” በሚል ርእስ ያዘጋጀውን መጽሐፍ ባለፈው የካቲት 2 ቀን 2004 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ በሚገኘው ትሪያንግል ሆቴል አስመርቋል፡፡


በመጽሐፉ ዝግጅት ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ምንጮች የተገኙ 78 መጻሕፍት በቀጥታ ማጣቀሻነት ጥቅም ላይ መዋላቸው ተመልክቷል፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ኀያላን ሴቶች እየተባሉ ከሚጠሩት አንዷ የሆኑት የጎንደሯ እቴጌ ምንትዋብ አጽፈውና ዐሥለው ለጎንደር ቁስቋም ማርያም ካበረከቱትና ከራሳቸው ጋ ለዐፄ ኢያሱ ሁለተኛ (1730 - 1755) መታሰቢያ ከሆነው ራእየ ዮሐንስ መጽሐፍ(ብራና) ቅጅ እንዲሁም ደጃዝማች ውቤ አጽፈውና ዐሥለው ለደረስጌ ማርያም ከሰጧቸው ቅጅዎች ላይ የተወሰዱ ሥዕሎችም በአስረጅነት ተካተውበታል፡፡

ለመጽሐፉ ዝግጅት አራት ዓመታትን መውሰዱን ዲያቆን ዳንኤል በምረቃው መርሐ ግብር መክፈቻ ላይ ተናግረዋል፡፡ በአራቱ ዓመታት ውስጥ 5000 የብራና ማይክሮፊልም መጻሕፍት በሚገኙበት አሜሪካ - ሚኒሶታ ቅዱስ ዮሐንስ ኮሌጅ፣ በጎንደር(ቁስቋም ማርያም፣ ደረስጌ ማርያም፣ አዘዞ ተክለ ሃይማኖት)፣ በመንበረ ፓትርያሪክ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሚገኙ የብራና መጻሕፍትን ለመመልከት ተሞክሯል፤ የአርመን፣ ሶርያ፣ ግሪክ እና ግብጽ-ኮፕት ምንጮችን ለመዳሰስ ጥረት ተደርጓል፤ ቅዱስ ዮሐንስ ራእዩን ባየባትና ጥንት በታናሽ እስያ ዛሬ በቱርክ ምዕራባዊ ጠረፍ በኤጅያን ባሕር የምትገኘውን የፍጥሞ(ፓትሞስ) ደሴት ለስድስት ሰዓት በመርከብ ተጓጉዞ በማቋረጥ በአቡቀለምሲስ ዮሐንስ ገዳም ከስምንተኛው መ/ክ/ዘ አንሥቶ በዋሻው ውስጥ የሚገኙ ሥዕሎችና የቃል አስረጅዎች ለመጽሐፉ ዝግጅት ከፍተኛ እገዛ አድርገዋል ተብሏል፡፡ በምረቃው ሥነ ስርዓት ላይ ‹‹The Holy Patmos›› በሚል ርእስ የተዘጋጀውና በደሴቲቱ የሚገኙ 365 አብያተ ክርስቲያናትን የሚያስቃኘው የ30 ደቂቃ ፊልም ለተመልካች ቀርቧል፡፡

በ”ራእየ ዮሐንስ - የዓለም መጨረሻ” መጽሐፍ ምረቃ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት” መጽሐፍ አዘጋጅና የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር ጉባኤ አባል ዲያቆን ዓባይነህ ካሴ፤ “የመጽሐፉ አዘጋጅ ከራሱ ሐሳብ ተቆጥቦ በርካታ የዐሥራው መጻሕፍትን ትርጓሜ ከተለያዩ ድርሳናት ጋ በማመሳከር፣ የቅዱሳት ሥዕላትን ሐሳብ ሳይቀር በአስተርጓሚነት (አስረጅነት) በመጠቀም በብዙዎች ዘንድ ያልተሞከረውን የደፈረ፤ ከባዱንና ረቂቁን ራእየ ዮሐንስን ለመምህራን፣ ጸሐፊያንና አንባብያን በአንድ ደረጃ ያቃረበ ነው፤ አዘገጃጀቱም ለመሰል ጸሐፊዎች ትምህርት  የሚሰጥና ደረጃውን ከፍ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡

ዲያቆን ዓባይነህ በቀጣይ የአዘጋጁ ሥራዎች ከወቅቱ አኳያ መታየትና የበለጠ መብራራት ይገባቸዋል ያሏቸውን ነጥቦችም አመልክተዋል፡፡ ከእኒህም መካከል ቅዱስ ዮሐንስ ራእዩን ላሳየው መልአክ ስላቀረበው ስግደት(ዮሐ. 19 እና 22)፣ የቁጥሮችን ሐሳብ በተለይም ሺሕ ዓመትን እና 144 ሺሕን በተመለከተ ስላለው የአተረጓጎም ልዩነት፣ ከሌሎች የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ራእዩ የተጻፈበት ዘመን ቅድምና፣ ከቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእዚናንዙ ጽሑፍ አንጻር፣ የዮሐንስ ራእይ ቀኖናዊነት ጉዳይ፣ አዘጋጁ በተደጋጋሚ ለምስክርነት የተጠቀሙበት የቪክቶርያነስ ትርጓሜ፣ የተርጓሚው ማንነት የሚሉትና ሌሎችም ነጥቦች ይገኙባቸዋል፡፡

የዲያቆን ዳንኤል ክብረት 18ኛ መጽሐፍ እንደሆነ የተገለጸው “ራእየ ዮሐንስ - የዓለም መጨረሻ” በአግዮስ የኅትመት እና ጠቅላላ ንግድ ሓላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የታተመ ሲሆን በ221 ገጾች የተካተቱና በአምስት ክፍሎች የተከፋፈሉ ማብራሪያዎችን፣ መረጃዎችንና ሥዕላዊ መግለጫዎችን የያዘው መፅሃፉ፤ ዋጋው 80 ብር ነው፡፡

35 comments:

 1. egziabeher yebarekeh

  ReplyDelete
 2. የዓለም መጨረሻ

  ReplyDelete
 3. am proud of that though i haven't attend the ceremony hold on dire.please we need the book it must distributed as soon as possible especially to theb eastern part of Ethiopia
  God bless you your family and your work

  ReplyDelete
 4. enkone dase alahe dn daniel kana batasabeh.plskaETHIOPIA weche lamenenore adaresone

  ReplyDelete
 5. berta geta yetbekh
  yonas abebe

  ReplyDelete
 6. Thank you Dn. Daniel. Where can we get the book out of Ethiopia?
  If possible, can you post the film called "The Holy Patmos". We can get more information about the churches there, who we didn't attend the program.

  ReplyDelete
 7. May you live long for your efforts that you have been putting on digging out our lost and hidden churches' history and tradition. you are making this lost generation to know his/her history and identity. God bless you.

  ReplyDelete
 8. I am very glad to hear this news-waiting for it so long! Is there any way to get the book outside Ethiopia?
  Wish u all the best Dn. Daniel!

  ReplyDelete
 9. Egiabher yibarkih Deacon Dani!!!!

  ReplyDelete
 10. Enkuan des yaleh dn.Dani Egziabher amilak ahunem tsegawun yabezalh metshafun betam begugut eytebkut neber .Agerihen ena betkirstiyanhen yemitagelgelibet rejim edime ketena gar Amilake kidusan yadelh .

  ReplyDelete
 11. Dn. Daniel Egziabiher Yitebikilin. Tsegawun abizto abizto Yadilih. Endih Yalu sewoch Lekidist Tewahido Betekrstianachin Yasfeliguatalna Egziabiher be-edime, Betsega ena bemulu teninet Yitebiklin.

  ReplyDelete
 12. ዲ/ን እደግ ተመንደግ ደስ የሚያሰኝ ሥራ ነው

  ReplyDelete
 13. My God bless your hard work including your family!!!

  ReplyDelete
 14. ዲ/ን እደግ ተመንደግ ደስ የሚያሰኝ ሥራ ነው
  CONGRA

  ReplyDelete
 15. why then don't u produce commentaries as esdros of ethiopia,st.chrysostom,St.Jerome,st.Cyril.Why don't u for example involve in the study of canonization of the number of books in bible as Dn Abib Georgis for Egypt? May God bless u and ur work.

  ReplyDelete
 16. ጌታ እግዚአብሔር አምላክ የወንድማችንን የአገልግሎት ጊዜ ያርዝምለት

  ReplyDelete
 17. Dear D.n Daniel Kibret

  You are our Ethiopians Dn Abib Georgis. Keep doing ur marvelous job.

  GOD BLESS U AND UR FAMILY

  ReplyDelete
 18. God bless you Danny.

  ReplyDelete
 19. EGZEABHER TSEGAWUN YABZALIH YIHIN LADEGEGLIH LAMILAKACHIN KIBIR MISIGANA YIHUN GENA BIZU BIZU YALITBERZU YALITEKLESU SIRAWOCHIHIN ENTEBKALEN TADYA YIHIN YAYE TELAT DEYABILOS TORUN YISEBQALINA YIHIN YADEREG EGZIABEHER ENJE
  ENE AYIDLEHUM BILEH ZEWETRI BTIHITNA ASAFIREW

  ReplyDelete
 20. WHAT ABOUT HISKE'EL AND GEDLE TEKLHAYMANO? GO AHEAD.

  ReplyDelete
 21. ተሻለ ጥላሁን ለአዲስ አበባFebruary 22, 2012 at 3:32 PM

  እግዚአብሔር ከዚህ የበለጠ የምትሰራበት ብርታቱን ያድልህ!

  ReplyDelete
 22. Dear Dn Daniel
  Your using your time!
  God bless you

  ReplyDelete
 23. እግዚአብሔር ፀጋውን ያድልህ። ግን አንዲት እህት እንዳለችው ይህ ሥራ የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ነው እና ትዕቢት የሚባል ሐጥያት እንዳያጠቃህ ተጠንቀቅ።
  ንጉሴ ከመቀሌ

  ReplyDelete
  Replies
  1. Diacon Daniel God bless you and your useful works.

   Delete
 24. How can we get this book in USA?

  ReplyDelete
 25. Thanks Jesus Christ for giving us Dn. Daniel Kibret for my spiritual life.

  ReplyDelete
 26. ግሩም ዜና : እግዚአብሔር ከዚህ የበለጠ የምትሰራበት ብርታቱን ያድልህ! አሜን!

  ReplyDelete
 27. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

  ወድ ወንድማችን/መምህሬ/ ዲ. ዳንኤል ክብረት እንኳን እግዚአብሔር አምላካችን ይህንን መጽሐፍ እንድታዘጋጅ እረዳህ። ከታች የተገለጹት ቢደረጉ በቻሉ መልካም ይመስለኛል።
  1. ከሊቃውነተ ቤተ ክርስትያን ስለ መጽሐፉ የተሰጡትን አስተያየት መስማት ማንበብ የምንችልበት ሁኔታ ቢኖር/በጡመራ መድክህ/ ዲ. ዓባይነህ የተናገረው እንዳለ ሆኖ።
  2. መጽሐፉን ገዝቼ እያነበብኩት ነው። እጅት በጣም ጥሩ ነው። መጽሐፍ አዟሪዎች ግን መጽሐፉ ትንሽ እትም ነው ብለው ይሁን አላውቅም ከዋጋው በላይ እየተሸጠ ነው። ማድረግ የምትችለው ካለ።
  3. በቀጣይ ስራዎችህ ለሰንበት ትምህርተ ቤት ማስተማሪያ/ የሚሆን ልክ አንደ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ብታዘጋጅ መልካም ይመስለኛል።

  ሊቃውንቱን ወደ ጉባኤ፣ ጻድቃንን ወደ ገዳም፣ ሰማዕታትን ወደ እሳት የላከ መንፈስ ቅዱስ አንተንም ወደ ጸሐፊነት አምጥቶሀል መምህር ትልቅ ስራ አንደሰራት ምንም ጥያቄ የለውም ነገር ግን አባቶቻችን እንደሚሉት ጭንጋፍ ነኝ /14 መጽሐፍ ጽፈው/ ብለዋል አንተም ይህንን እያልክ ቀጣይ ስራዎችን እንድትሰራ ይህንን ስራ የረዳህ ልዑለ ባህሪ እግዚአብሔር አምላካችን ከናታችን ከድንግል ማርይም እና ከወዳጆቹ ጋር ይርዳህ። ተማሪ መምህሩን ባይናገርም ደፍሬአለሁ ይቅርታ ይደረግልኝ።

  ኪዳነማርያም ዘደብረ ይድራስ

  ReplyDelete
 28. መንፈስ ቅዱስ አይለይህ። የበለጠ ብርታት ያድልህ።

  ReplyDelete
 29. ጥሩ አገልግሎት ነው

  ReplyDelete
 30. Thank you for your hard work,but where we can find the book ourside Ethiopia.

  ReplyDelete
 31. dani its good view!

  ReplyDelete
 32. Christ peace and love be up on u, how do we get the book in US?

  ReplyDelete
 33. Selam leante yihun Dn. Daniel endet des yemil zena new ebakih minim fetenaw yebeza bihonim sirahin eyeserah bemehonu telat yafralina berta Amlake Kidusan sirahin betesebihin hulu beselam yitebikilih.

  ReplyDelete
 34. "በ”ራእየ ዮሐንስ - የዓለም መጨረሻ” መጽሐፍ ምረቃ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት” መጽሐፍ አዘጋጅና የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር ጉባኤ አባል ዲያቆን ዓባይነህ ካሴ፤ “የመጽሐፉ አዘጋጅ ከራሱ ሐሳብ ተቆጥቦ በርካታ የዐሥራው መጻሕፍትን ትርጓሜ ከተለያዩ ድርሳናት ጋ በማመሳከር፣ የቅዱሳት ሥዕላትን ሐሳብ ሳይቀር በአስተርጓሚነት (አስረጅነት) በመጠቀም በብዙዎች ዘንድ ያልተሞከረውን የደፈረ፤ ከባዱንና ረቂቁን ራእየ ዮሐንስን ለመምህራን፣ ጸሐፊያንና አንባብያን በአንድ ደረጃ ያቃረበ ነው፤ አዘገጃጀቱም ለመሰል ጸሐፊዎች ትምህርት የሚሰጥና ደረጃውን ከፍ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡"

  Dn. Daniel, Egziabiher Edime ena mulu tena yadilih. Egziabiher Yitebikih.

  ReplyDelete