Friday, February 17, 2012

ባለቤት ያቃለለውን አሞሌ ባለ ዕዳ አይቀበለውም


(click here for pdf) 
አብዮቱ ከመፈንዳቱ አምስት ዓመታት ቀደም ብዬ በተባበ መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሥራ ጀምሬ ነበር፡፡ ዋናው ምድቤ ደቡባዊው የአፍሪካ ክፍል ነበር፡፡ በዚህ ቦታ በመመላለስ ለዐሥራ አምስት ዓመታት በማገልገሌ አካባቢው ያደግኩበትን ቦታ ያህል ዐውቀው ነበር፡፡
1976 ዓም በወቅቱ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ የነበሩት ሰው እኔን የደቡባዊ አፍሪካን ጉዳይ በሚከታተለው የመንግሥታቱ ድርጅት አካል ውስጥ ለመሾም ፈለጉ እና አናገሩኝ፡፡ ኃላፊነቱን መቀበሉ ለኔ መልካምም ቀላልም ነበር፡፡ ከባድ የሆነው ነገር የሀገሬን መንግሥት ድጋፍ ማግኘቴ ነበረ፡፡
እኔ ከሀገሬ ወጥቼ መሥራት ከጀመርኩ ያኔ ዐሥራ አምስት ዓመት ሆኖኛል፡፡ ከዚህም በላይ ደግሞ መንግሥትም ሥርዓትም ተለውጧል፡፡ አሁን ያሉትን ባለ ሥልጣናት አላውቃቸውም፡፡ እንደ እነርሱም ኮሚኒስት አይደለሁም፡፡


 ጉዳዩን በመጠኑም ለምቀርባቸው አንድ የወቅቱ ባለ ሥልጣን በስልክ አማከርኳቸው፡፡ ሰዎቹን አናግረው እንደሚደውሉልኝ ነገሩኝ፡፡ ከሳምንት በኋላ ደውለው፡፡ ሃሳቡን እንደ ተቀበሉት ነገር ግን አዲስ የተቋቋ መው የኢሰፓአኮ አባል መሆን እንደሚጠበቅብኝ ነገሩኝ፡፡ እርሳቸውም ለእኔ በማሰብ ምናለ አንተስ ዝም ብለህ ፎርሙን ብትሞላላቸው፡፡ ብለው መከሩኝ፡፡
ከራሴ ጋር ለጥቂት ቀናት ተማከርኩ፡፡ እኔ ለዚህ ቦታ ስታጭ መታየት ያለበት አገልግሎቴ እና ብቃቴ እንጂ የፓርቲ አባልነቴ ነው እንዴ? ብዬ ጠየቅኩ፡፡ በመጨረሻም በራሴ ላይ ወስኜ ለዋና ጸሐፊው ነገርኳቸው፡፡ እያዘኑ ቦታውን ለሌላ ሰጡት፡፡ እኔንም በሌላ የሀገር ድጋፍ በማያስፈልገው ቦታ ሾሙኝ፡፡
ይህንን ታሪክ በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን 1992 ዓም ያወጉኝ አንድ አረጋዊ ኢትዮጵያዊ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያውያን በዓለም ዐቀፍ ተቋማት ለምንድን ነው ጎልተው የማይታዩት? ከሌሎቹ ቀድመን የዓለም ዐቀፍ ተቋማት አባል እንዳልሆንን ለምን ከሌሎቹ አንሠን ታየን? እያልኩ ስጨቀጭቃቸው ነበር ይህንን የራሳቸውን ገጠመኝ ያወጉኝ፡፡
ይህ ሰዎቹን ሁሉ ሀገራዊ በሆነ መሥፈርት ሳይሆን በዘመኑ በተጠለቀው የርእዮተ ዓለም መነጽር የማየት ችግር ኢትዮጵያውያን ጀግኖች በሀገራቸውም ሆነ በዓለም መድረክ ጎልተው እንዳይታዩ ካደረጋቸው ምክንያቶች አንዱ ነው፡፡
ዐፄ ቴዎድሮስን እና ዐፄ ምኒሊክን እያሰቡ ለእኩልነት እና ለዴሞክራሲ፣ ለሰብአዊ መብት እና ለነጻ ምርጫ ምን አስተዋጽዖ አደረጉ? እያሉ ከመጠየቅ የባሰ ዕብደት የለም፡፡ ደገኛን በበቆሎ ቆለኛን በገብስ ማማት ይሉታል ይኼ ነው፡፡ ለመሆኑ አበበ ብቂላን እንደ ጀግና ስናየው በየትኛው መሥፈርት መዝነነው ነው? ታግሎ ሕዝቡን ከፊውዳሊዝም ነጻ ያወጣ፣ ለዴሞክራሲያዊ መብት መሥዋዕትነት የከፈለ፣ ለብሔር ብሔረሰብ እኩልነት ዋጋ የከፈለ፣ ለኢትዮጰያ ነጻነት የተዋደቀ፣ እያልን የምንቀጥል ከሆነ አበበ ብቂላን አንድም ቦታ አናገኘውም፡፡
ይህ ግን የአበበ ብቂላ ስሕተት አይደለም፡፡ ጀግና እና ሸማ በየፈርጁ መሆኑን የረሳነው የኛ የራሳችን እንጂ፡፡ ዐሉላ አባ ነጋን ስናስብ ስለ ኦሎምፒክ እና ስለ ሩጫ፣ ስለ ወርቅ እና ብር ሜዳልያ፣ ስለ ሮም እና ቶኪዮ የምንጠይቃቸው ከሆነ በዚህ ረገድ ጀግና የሚያሰኛቸው አንድም ነገር አናገኝም፡፡ ችግሩ ግን የዐሉላ አባ ነጋ አይደለም፡፡ ለሁሉም ዓይነት እህል ተመሳይ ሙቀጫ የምናቀርበው የኛ እንጂ፡፡
ንጉሥ ኃይለ ሥላሴ የአፍሪካ አነድነት ድርጅትን በመመሥረት፣ አፍሪካውያን ከቅኝ ገዥዎች ተላቅቀው ነጻ እንዲወጡ በመርዳት፣ የአፍሪካንንም ድምጽ በዓለም ዐቀፍ መድረክ በማሰማት ያደረጉትን አስተዋፅዖ እንኳን እኛ ዛሬ ከመቃብር በታች የዋለው አፓርታይድም ዕድል ካገኘ ይመሰክረዋል፡፡
እዚህ ላይ ላመስግናቸውና ራሳቸው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስም ቢሆኑ የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን መቀመጫ ከተማ ከአዲስ አበባ ለማዛወር በተነሣው አጀንዳ ላይ በስሜት እና በቁጭት ሲናገሩ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ በኢትዮጵያ ውስጥ ጨቋኝ ቢሆኑም ለአፍሪካ ነጻነት እና ለድርጅቱ መመሥረት ያደረጉት አስተዋጽዖ ግን ወደር የማይገኝለት መሆኑን ገልጠው ነበር፡፡
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት 1963 ዓም ሲመሠረት የካዛብላንካ እና የሞኖሮቪያ ቡድን ተብላ አፍሪካ በሁለት ጎራ ስትናጥ በወቅቱ ከዐፄ ኃይለ ሥላሴ የተሻለ ተሰሚነት ያለውና አንድነትን ሊያመጣ የሚችል መሪ አልነበራትም፡፡ ልዩ ልዩ መልክተኞቻቸውን ልከው በየሀገሩ ገና በነጻነት ደስታ ተጥለቅልቀው ከፌሽታ ያልወጡትን ነጻ አውጭ መሪዎች እያግባቡ እና እያባበሉ፤ የተጣሉትን እያስማሙ ጉባኤው በአዲስ አበባ እንዲሆን ያደረጉት ንጉሡ ነበሩ፡፡
ከዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ በኋላም ጉባኤው በአዲስ አበባ ሲካሄድ እንየው፣ እንምከርበት፣ ጊዜ እንስጠው እያሉ ብዙዎቹ መሪዎች ነገሩን ሲያዘገዩት «ይህንን የአንድነት ሰነድ ሳንፈርም ከዚህ ጉባኤ አዳራሽ አንወጣም» ብለው በመገዘት ከሌሊቱ በዘጠኝ ሰዓት እንዲፈረም ያደረጉት ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ነበሩ፡፡
ንጉሡን «የአፍሪካ አባት» ብለው የሰየሟቸው ኢትዮጵያውያን አይደሉም፡፡ የአፍሪካ መሪዎች እንጂ፡፡ ይህ ለንጉሡ ብቻ የተሰጠ ይደለም ለሀገራቸውም ጭምር እንጂ፡፡

የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ወደ አፍሪካ ኅብረት ተሸጋግሮ፣ የምሥረታውን በዓል ለማክበርም አንድ ዓመት ያህል ሲቀረው በቀድሞው ከርቸሌ ግቢ ላይ ቻይና አዲሱን የኅብረቱን ሕንፃ አቆመች፡፡
«ለሰጭ ይስጠው ለንፉግ ልብ ይስጠው» ይል ነበር አጎቴ፡፡ በዚህ ታላቅ ሥራ ውስጥ ሰጭም ነፋጊም ተገኘና ደስታችንን ግማሽ አደረገው፡፡ ሴትዮዋ ባልዋ አዳኝ ነበር አሉ፡፡ ወንድ የተባለ የማያገኘውን አውሬ የገባበት ገብቶ የሚያድን፡፡ አንድ ቀን ነብር አድናለሁ ብሎ ወጥቶ እጅግ ብዙ ቀን ቆየ፡፡ ሚስት ተጨነቀች፡፡ ከብዙ ጊዜ በኋላ አያሌ ወታደሮች በሰልፍ ሆነው ወደ መንደርዋ መጡ፡፡ ሰልፉ መቼም ልዩ ነበረ፡፡ የመንደርዋ ሰዎች ግልብጥ ብለው ወጥተው ሰልፉን ተመለከቱ፡፡ የነብር ቆዳ፣ ካባ፣ የደረት ሜዳልያ ይዘዋል ወታደሮቹ፡፡
የአዳኙ ሚስት ተጠራች፡፡ እየፈራች ቀረበች፡፡ «ንጉሡ ይህንን ካባ፣ ይህንን የነብር ቆዳ፣ ይህንንም ሜዳልያ ሸልመውሻል፡፡ ይህንን ያህል ርስት ሰጥተውሻል፡፡ ቤትሽ በግንብ እንዲሠራም አዝዘዋል» አሉና ዐወጁ፡፡ ሕዝቡ እልል ብሎ ተቀበለ፡፡ ሴትዮዋ ግን ጨነቃት፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ባሏሳ፡፡
ወታደሮቹ ይህንን ሲጨርሱ ባልዋ ከንጉሡ ታዝዞ አደን ሲያድን ከነብር መንጋ ሌሎቹ ጓደኞቹን ለማትረፍ ብሎ ሕይወቱን ማሳለፉን አረዷት፡፡ አሁን ግራ ገባት፡፡ ትደሰት ወይስ ትዘን? ታልቅስ ወይስ ትሳቅ? አንዱ ያስተዛዝናታል፡፡ ሌላው እንኳን ደስ ያለሽ ይላታል፡፡ አንዱ ይቀናባታል፡፡ ሌላው ያዝንላታል፡ አንዱ ፈገግ ብሎ ይመጣል፣ ሌላው ተክዞ ይከተላታል፡፡ ሲጨንቃት
ኀዘን እና ደስታ አንድ ላይ ውለው
ላልቅስ ወይስ ልዝፈን የቱ ነው ሞያው
አለች አሉ፡፡
እኛም እንዲህ ነው የሆንነው፡፡
ክዋሜ ንክሩማህ ለአፍሪካ አንድነት መመሥረት አስተዋጽዖ አድረገዋል፡፡ እሙን ነው፡፡ አስተዋጽዖዋቸው ግን የዐፄ ኃይለ ሥላሴን ያህል እንዳልሆነ ራሳቸው ጋናዎች ይመሰክራሉ፡፡ ከጣት ጣት ይበልጣል ይላሉ ሀበሾች፡፡ ታላቁ መጽሐፍም ኮከብ እም ኮከብ ይኼይስ ክብሩ - የአንዱ ኮከብ ክብር ከሌላው ኮከብ ይበልጣል ይላል፡፡ ንክሩማህ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ የነበራቸውን ሥልጣን፣ ዐቅም እና ተቀባይነት አልነበ ራቸውም፡፡ ኢትዮጵያ የነበራትን የነጻነት ተምሳሌትነትም ጋና አልነበራትም፡፡
አሁን መነጋገር ያለብን ስለ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ፊውዳልነት፣ ጨቋኝነት፣ ባላባትነት፣ ባለ ርስትነት አይደለም፡፡ አሁን መመዘኛችን ለፍትሕ፣ ለዴሞክራሲ፣ ለብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት፣ ለምርጫ፣ ለመሬት ላራሹ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ምን አድርገዋል እያልን አይደለም፡፡ አሁን መከራከርያችን ንጉሡ ለአፍሪካውያን ነጻ መውጣት እና ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምን አስተዋጽዖ አድርገዋል? የሚለው ነው፡፡
የክዋሜ ንክሩማህ ሐውልት ሲቆም ሥራቸው ከአፍሪካ ነጻነት እና ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት አንጻር ተመዝኖ እንጂ እርሳቸውምኮ በሀገራቸው እንደ ንጉሡ ይታማሉ፡፡ ያሠሯቸው፣ ያስገደሏቸው፣ ፍትሕ ያዛቡባቸው አሉ፡፡ እርሳቸውምኮ በሀገራቸው የሚቃወማቸው አለ፡፡ መጽሐፉ እንዳለው ነቢይ በሀገሩ አይከበርማ፡፡
ሰውን መመዘን ያለብን በዋለበት መሥመር እንጂ በምልዐት አይደለም፡፡ አንድ ሰው በሂሳብ ትምህርት መቶ ለማምጣት በአማርኛም፣ በእንግሊዝኛም፣ በፊዚክስም መቶ ማምጣት የለበትም፡፡ ወይንም ደግሞ በሌሎች ትምህርቶች መቶ አላመጣህምና የሂሳብን ፈተና ሙሉ በሙሉ ብታልፍም መቶ አልሰጥህም አይባልም፡፡ በሂሳብ ውጤት የሚሸለሙ ሰዎች ሲጠሩ ይህ ተማሪ አንደኛ ተብሎ ሊሸለም፤ ሊጨበ ጨብለት፤ ሐውልት የሚሠራም ከሆነ ሊሠራለት ይገባል፡፡ የፊዚክስ ውጤት ሲመጣ ስሙን አለመጥራት፣ ውጤታማ አለመሆኑን መናገር ይቻላል፡፡
ለዐፄ ቴዎድሮስ መታሰቢያ ስናቆም ለኢትዮጵያ አንድነት ያደረጉትን አስተዋጽዖ በማሰብ እንጂ ፍትሕ፣ እኩልነት፣ ነጻነት፣ ዴሞክራያዊነት፣ ምርጫ፣ የብሔር ብሔረሰቦች መብት፣ ራስን በራስ ማስተዳደር፣ ፓርቲ፣ እያልን አይደለም፡፡
በተለይም የኢትዮጵያ መንግሥት እና ዲፕሎማቶች ሽንጣቸውን ገትረው ሊከራከሩ በተገባቸው ነበር፡፡ ክርክሩ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ለአፍሪካ ነጻነት እና ለአፍሪካ አንድነት ምን ሠርተዋል? በሚለው ነው፡፡ ክርክሩ ሐውልት ይቁም ከተባለ የማን ሐውልት መቆም አለበት በሚለው ነው፡፡ ስለ ንጉሡ በዋነኛነት መከራከር ያለባቸው የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ናቸው፡፡ ያለበለዚያማ ባለቤት ያቃለለውን አሞሌ ባለ ዕዳ እንዴት ይቀበለዋል?
ይህንን አለማድረግ አቶ በረከት ስምዖን «የሁለት ምርጫዎች ወግ» በሚለው መጽሐፋቸው ማጠቃለያ ላይ ያሠፈሩት የታላቁ ፈላስፋ የሲሴሮን ቃል አለመረዳት ይመስለኛል፡፡ ሲሴሮ እንዲህ ይላል «ባለፉት ዘመናት የተሠራው ሁሉ በሚገባ ካልተነገረና ቀደምት ሰዎች ባበረከቱት አስተዋጽዖ በአግባቡ መጠቀም ካልተቻለ፣ ዓለማችን ሁሌም ቢሆን የዕውቀት ብላቴና እንደሆነች ትቀራለች»፡፡
 ዛሬ አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና እንድትሆን፣ ከብራስልስ ቀጥላ ትልቋ የዲፕሎማቲክ ከተማ እንድትሆን፣ ይህ ዛሬ የተሠራው ሕንፃም እዚሁ በከተማችን እንዲሠራ፣ አፍሪካውያን እንዲተባበሩ፣ ከቅኝ ግዛትም ነጻ እንዲሆኑ ታላቅ አስተዋጽዖ ያደረጉትን መሪ መርሳት ኢትዮጵያን «ሁሌም ብላቴና» ማድረግ ነው፡፡ አሁን ንጉሡ የሉም፡፡ አይደሰቱም አይቀየሙምም፡፡ ኢትዮጵያ ግን ቦታዋን አጥታለች፡፡ በገዛ ዳቦዋ ልብ ልቡን አጥታዋለች፡፡
እኔ ተስፋ አለኝ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የተመሠረተበት አምሳኛ ዓመት በዓል ከመከበሩ በፊት የንጉሡ ሐውልት ከነ አስተዋጸዖዋቸው በአፍሪካ ኅብረት ግቢ ውስጥ ይታያል ብዬ፡፡
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ ወጥቷል፤ በተመሳይ ኅትመት ላይ ባታወጡት ይከመራል

56 comments:

 1. This kind of shame could only happen in present Ethiopia!

  Believe me no nation in the world would allow any regional organizational to undermine its historical contribution to the very existence of not only the organization itself but also the continent.

  I don’t think this has happened without the consent of the incumbent government. Neither they didn’t insist nor recommended the Emperor for the statue to be erected.

  Because none of the contemporary African leaders have the moral fiber to decide in such important issue by there own right.

  My father has always been telling me that the Emperor was known as “Doctor of the world ” for his diplomatic skills.

  Whether we like it or not the king has his owe place in history. Let’s worry to our future history & stand for our past history.

  Let me share Dani’s hope to see the statue of the lat Emperor of Ethiopia in his rightful place in history & in his home too.

  By the way it is a very well written article.

  And God bless historic Ethiopia!

  ReplyDelete
 2. Aye Melese? Is he an Ethiopian, Eritrean, Ghanian? Why don't he stand for fact only? Always He calculated only his personal and Party politics. Where is his struggle for Ethiopia and Ethiopians. Oh God please Do Something...and We will..


  God Bless you Dn. Dani

  ReplyDelete
 3. Dn Daineal

  So many people wrote in this case let us come to some concurent work to do, let us discuss how can we go forward to put the king statue at African Uinted office. Especially the univeristy students can do more....

  ReplyDelete
 4. I was listen Melese speech, It is a shameful speech that I neverd hered before such kind of public speech in my life.Shame on you, Shame on you

  My dear brother whether you like it or not these people are not an Ethiopians.They dont care about Ethiopia.They dont care about their peoples. They only care about their power.They only care about their illigitmate power. The name Ethiopia is more than we know. However,they dont have that the quality to be called them as an Ethiopians. They buried the name, the glory,the prestige and the true identity Ethiopia atleast at this moment. You may be considered me as a fanatic which is full of hate, racism and baise. No, I assure you, am free from that one. I dont want to be a part of the system product of this govenmnent. Look the condtion of Ethiopia which is a good examples. the Ethiopian living condtions,the corrupted systems which is manfested in many ways, like in politics,in economy and in social problems and religion problems and the like that. The status of this country is detorarating from time to time.Thanks to EPRDF, We are landloked country, Dijbouti makes always full us because of this nasty and brutal government. Our govenment is hosting a homosexual conference with out the concent of the Ethiopian peoples. What can I say, I am specless. So, do you think that these people are an Ethiopian. No...

  ReplyDelete
 5. ልጅ ዳንኤል እጅግ ምክንያታዊ በሆነ አገላለፅ ነው ያቀረብከው፡፡እግዜር ይስጥህ፡፡
  የአቶ መለስ አገዛዝ ከተፈጥሮና ከማህበራዊ ህግና ደንብ ባፈነገጠ አካሄድ ነው የውስጥ ገበናችንን እንደ አንድ ሀገር መሪ ሳይሆን እንደ አንድ በተራ ስሜት እንደሚመራ እንደ ተራ ግለሰብ አስተሳሰብ እያሰበና እንደ ባእድ እያሳጣ አደባባይ እያወጣ ሀገራችንና ህዝባችንን እያዋረደን ያለው፡፡በጠባብ ብሄርተኝነትና ተራ የጥላቻ ስሜት ላይ በተመሰረተ እይታ ይህ በአፄ ኃይለስላሴ ላይ የተፈመው ክህደትና ውርደት በሀገር በህዝብና በታሪክ ላይ እንደተፈፀመ ውርደትና ክህደት ነው የሚቆጠረው፡፡
  አቶ መለስና ወያኔ እንዲያው እስከዚህ ድረስ የውስጥ የዘረኝነትና የጥላቻ ስሜታቸውን ለመቆጣጠር እስኪያቅታቸው ድረስ ይህንን ያህል በአደባባይ እስከመዘርገፍ የደረሱ እየሆኑ መጡ ማለት ነው፡፡እኔ ይህ አይነት ጠባብ ብሄርተኝነትና ዘረኝነት የጤነኝነት አይመስለኝም፡፡ይህ የለየለት እብደት ነው በራሱ፡፡
  አቶ መለስ እኮ 80 ሚሊዬን የኢትዮጵያን ህዝብ ወክለው እንጂ ስልጣን ላይ ያሉት የራሳቸውን ወይንም የወጡበትን 10 ሚሊዬን አካባቢ የሚሆን አንድ ጠባብ የትግሬ ብሄር ስሜትና አመለካከት በመወከል አይደለም፡፡ለምሳሌ አቶ መለስ ባለቤታቸውን ወይንም ልጃቸውን ወይንም አንድ የሆነ የቤተሰባቸውን አባል አስቀየሙ ተብሎ አቶ መለስ ለሀገራቸው የሰሩትን መልካም ስራ ማጣጣል ይቻላል እንዴ?ነው ወይነስ የአቶ መለስ ባለቤት ወይንም ልጅ ወይንም አንድ የሆነ የቤተሰብ አባል መለስ ይህንን መጥፎ ስራ በእኔ ላይ ሰርቶ አስቀይሞኛልና ይህ አይነት የክብር ዶክትሬት አይገባውምና ሊሰጠው አይገባም ይላልን?አቶ መለስና ወያኔ አንድ ሀገርና ህዝብ እንደሚያስተዳድር ሃላፊነት እንደሚሰማው አገዛዝ ማሰብ ያቆሙ ይመስላል፡፡እጅግ የሚገርመው ነገር ደግሞ አቶ መለስና ወያኔ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ የሰሩትን ጥፋት የማመን ተፈጥሮ አልፈጠረባቸውም፡፡ከዚህ በመነጨም አቶ መለስ ስለ ሃውልቱ ሲጠየቁ ስምህ ማነው ሲባል የጨማ ቁጥሬ 42 ነው እንዳለው አይነት ነው መልሳቸው፡፡ኢትዮጵያውያን ለምን የክዋሜ ንክሩማን ሃውልት ቆመ ብለው አንድም አይነት ቅሬታ አላሰሙም፡፡ዋና ቅሬታው ለምን የንጉሳችን ሃውልት አልቆመም ከሚለው ላይ ነው፡፡ነገር ግን አቶ መለስ ያው ለምን እረታለሁ የሚል ተራ ግለሰባዊ አስተሳሰብና ማምታታት ስለለመደባቸው ይህ ለምን ሆነ ለሚለው ወሳኝ ጥያቄ የሰጡት ምላሽ የክዋሜ ንክሩማን ሃውልት በመሰራቱና በዚህም ሀውልት ላይ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች ተብሎ መፃፉ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን በራሱ ክብር ነውና አርፋችሁ ይህንን አሜን ብላችሁ ተቀበሉ ብለው ሲያበቁ በዚህም የተነሳ የክዋሜ ንክሩማን ውለታ እንዳለበን አስገነዘቡን፡፡ከዚህ ንግግራቸው እንደተረዳሁት በአቶ መለስ ዘንድ ኢትዮጵያ የመቶ አመት ታሪክ ያላት ነች የሚለው አስተሳሰብ እንዳለቀቃቸውና ለኢትዮጵያችን አዲስ ታሪክ በራሳቸው ዘይቤና ፍላጎት ለመፃፍ የፈለጉ ይመስላል፡፡ሌላው የገረመኝ ሃውልቱ የተሰራው ከፓን አፍሪካኒዝም ጋር በተያያዘ እንደሆነና ለዚህ ደግሞ ከክዋሜ ንክሩማን በላይ ማንዴላም ሆነ አፄ ሃይለስላሴ ሊገባቸው እንደማይችልና ፓን አፍሪካኒዝም የክዋሜ ንክሩማን ብቸኛ የፈጠራ ስራ ፓተንት እንደሆነ ሊነግሩን ሞከሩ፡፡ነገር ግን አንድን ቲዎሪ የፈጠረውም ሆነ ያንን ቲዎሪ በተጨባጭ ወደ ተግባር የቀየረ ተመጣጣኝ ወጋና ክብር ነው ያላቸው፡፡በዚህ እረገድ ደግሞ ከፓን አፍሪካኒዝም ፅንሰ ሃሳብ ጋር በተያያዘ ክዋሜ ንክሩማን ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም ጥቁር አፍሪካውያን አስቀድሞ ሃሳቡ እንዳላቸው ይነገራል፡፡ነገር ግን ይህንን ራእይ ወደ ተግባር በመቀየር ዋና ሞተር አንቀሳቃሽ በመሆን ፓን አፍሪካኒዝምን ወደ ተግባራዊ አፍሪካ አንድነት ድርጅት በመቀየር አንድ እመርታ በማምጣት ደግሞ ንጉሳችን ከፍተኛውን የአንበሳ ድረሻ ይወስዳሉ፡፡ሌላው ሃውልቱ የተሰራበትን ምክንያት ብቻ መጥቀስ ለሃውለቱ እዚያ ቦታ ላይ መቀመጥ ዋና አግባብነት ሊሆን አይችልም፡፡ለምሳሌ የቻይናውን የማኦን ሃውልት እዚያ ቦታ ለማስቀመጥ ለፅ/ቤቱ የቻይናን የገንዘብ እርዳታ እንደ ምክንያት እኮ ለመጥቀስ ይቻላል፡፡ወይንም አላሙዲን 200 ሚሊዮን ዶላር እረድተው አሰርተውት ከሆነ የአቶ አላሙዲንንም ሃውልት ማቆምስ አይቻልምን፡፡ወይንም የህንፃውን መሀንዲስ ሃውልት እንደዚሁ፡፡በወቅቱ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ሲመሰረት ከነበሩት እንደ ክዋሜ ንክሩማን አይነት ታላላቅ ታሪካዊ ሰዎች ውጪ የማንም ሃውልት ሊሰጥ በሚችለው ማንኛውም ምክንያት ቢቆም ለምን የንጉሱ ሃውልት አልቆመም ለማለት የምደፍር ያን ያህል ሰው አይኖርም፡፡ነገር ግን የክዋሜ ንክሩማን ሃውልት ሲቆም ለምን የንጉሱ አልቆመም ብሎ መጠየቅ እጅግ ጤናማ የሆነና እንኳንስ ታሪኩን በቅጡ የሚያውቅ ሰው አይደለም የዚህ ታሪክ ቅንጫቢ በተደጋጋሚ የሚታይበትን ኢቲቪን የሚያይ ማንም ነፍስ ያላወቀ ህፃን ጭምር የሚያነሳው ጥያቄ ነው፡፡ከዚህ ሃውልት ጀርባ ያለው ትልቅ ድራማና ቁማር ግን ኢትዮጵያ ከማንም ሀገር በላይ ለፀረ-ኮሎኒያሊዝም ትግል ያበረከተችውን ፋና ወጊ አርአያነት ያለው አኩሪ ታሪክ ለመደምሰስ ሆነኝ ተብሎ የተቀነባበረ ሴራ ነው፡፡አቶ መለስና ወያኔ አዲስ የራሳቸውን የታሪክ ድሪቶ ለመፃፍ የፈለጉ ይመስላል፡፡ታሪክንና ተቀባይነትንና ክብርን ማግኘት ደግሞ በቀና ተግባር የሚታደሉት ጭምር እንጂ ያን ያህል የሚታገሉትና በገንዘብና በስልጣን ሃይል ብቻ በብልጣብልጥነትና በሽወዳ የሚቀዳጁት ወይንም የሚቀየር ነገር አይደለም፡፡አንድ ወቅት ላይ ሀይሌ ገብረስላሴ በሩጫ ሲሸነፍ ካሸነፈው አትሌት ጉብዝናና ዝና ይልቅ የሃይሌ መሸነፍ ጉዳይ ነበር ጎልቶ የወጣው፡፡አሁንም የተፈጠረው ነገር በተመሳሳይ መንገድ ከክዋሜ ንክሩማን ሀውልት መሰራት ይልቅ የንጉሱ ሃውልት አለመሰራት ነው ጎልቶ የወጣው፡፡ይህም ታሪክ በምንም መልክ የማይቀየር ነገር መሆኑን ያሳያል፡፡
  እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!!!

  ReplyDelete
 6. ሁሌ አንገታችንን እናዳስደፉን ነው፡፡ መቼ ይሆን ቀና የምንል?

  ReplyDelete
  Replies
  1. አብዮቱ ከመፈንዳቱ አምስት ዓመታት ቀደም ብዬ በተባበሪት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ መሥሪያ
   ቤት ሥራ ጀምሬ ነበር፡፡

   Who is the writer please?

   Delete
  2. read the article again then you will get the answer.

   Delete
 7. በጥላቻ ፖለቲካ ምክንያት አለም ወደ ፊት ሲሄድ እኛ ወደ ኋላ እየሄድን ነው:: እግዚአብሄር መሪዎቻችንን ልቦና ይስጣቸው::

  ReplyDelete
 8. Ayzon ken yimetal. Tesfa sankort . . . ewketachinin eyasadegin entebik. SIMETAWINETIN KALTEKOTATERIN ENWEDKALEN.

  ReplyDelete
 9. We don’t expect anything GOOD from Meles bcs he is BANDA.
  It is now clear that Ethiopia has been ruled by BANDA for the last 20 yrs.
  If really want to know that Meles is BANDA and never Ethiopian,
  Watch these videos. His close former friend has revealed the entire secret.
  http://www.ethiotube.net/video/17657/

  ReplyDelete
 10. ወገኖቼ ትልቁ ልንገነዘበው የሚገባ ቁም ነገር ቢኖር ኰሎኔል መንግሥቱም ሆነ አቶ ለገሠ (መለስ) ዜናዊ ችግራቸው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጥላ ከኋላቸው እየተከታተለ የሚያስደነግጣቸውና የሚያባንናቸው ትናንሽ ፍጡራን መሆናቸውን ነው:: በምንም መለኪያ የእርሳቸው ስምና የነዚህ የታሪክ ውዳቂዎች ስም በአንድ አረፍተ ነገር ውስጥ አብሮ ሊጠራ አይገባውም:: አሁን አቶ ለገሰ (መለስ) የአጼ ኃይለ ሥላሴ ሃውልት እንዳይሰራ በማድረጉ እሳቸውን ያንቋሸሸ መስሎት ይሆናል:: የሚያስበው ከአፍንጫው አያልፍምና አትደነቁ:: ዓለም በታላቅ ሥራቸው ያደነቃቸውን መሪ እሱና ባልደረቦቹ ስላላከበሩአቸው ምንም አይጎድልባቸውም ነገር ግን የርሱን ትንሽነት በጉልህ የሚያሳይ አሳፋሪ ተግባር ነውና መደነቅ አይገባም::

  ReplyDelete
 11. ዲ/ን ዳንኤል በጣም የምስማማበትና መነሳት ያለበት ጉዳይ ነው::ምንም እንኴን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ሀሳቡን ባይስማማበትም የአፍሪካ ህብረት ህንፃም ይሁን የክዋሜ ንክሩማህ ሀውልት የተሰራው በዐፄ ኃይለ ሥላሴ ሀውልት ላይ መሆኑን አይደለም ፖለቲከኛ ነኝ ብሎ የሚያወራ ይቅርና ለሌላም የተሰወረ አይደለም:: እንግዲህ የአብዩታዊ ዴሞክራሲ አንዱ የሀገር ገጽታ መቀየሪያ መንገድ የአንድን ሀገር ታሪክ ለሌላ በመሰጠት ነው እያሉን ከሆነ ድንቄም የሀገር ገጽታ መቀየር,,, አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም ይሉሀል ይሄ ነው::

  ReplyDelete
 12. ሰው ሁሉ ምነው የመለስ ባህሪ አልግባ አለው! 20 አመት ሙሉ እረባካችሁ *አውኮ የተኛን ቢከስክሱት አይሰማም ይባላል* እባካችሁ የምታቁካላቺሁ ማንነች ዲአቢሎስን
  ከመላእክት ጋር ልታስታርክ የሞከረች ታሪኩን ብትነግሩኘ አመሰግናልሁ

  ReplyDelete
 13. There is a Leader who always has self-contradition with him. He bitterly hate Ethiopia, he is against Amhara, he doesn't like to see people of great caliber and prestige; HIS NAME IS ARROGANT MELSES ZENAWI.

  ReplyDelete
 14. What is new here. They(Woyanes), consider all everything before them of the Amhara. Every single second over the last 20 yrs , they have said and done anything they thought would let the Amhara down.When that day comes....good Lord....

  ReplyDelete
 15. ETV ላይ እየቀረብክ በማያገባህ ነገር እየፖተለክ ስታቃጥለን ነበር ዛሬ ምን ተገኘ? እኔ ETV ላይ ቀርቦ የነበረ ሠው በተአምር አላምንም

  ReplyDelete
 16. Guys,

  Please, shouldn't we do it ourselves? Lets get together and collect signature then apply for AU. I think the Senior known professionals and opposition political parties will join together on this.

  ReplyDelete
 17. የሥነ ጽሑፍ መምህራን ስለ ዘይቤዎች ሲያስተምሩ “ከዘይቤዎች መካከል ሥነፍቻዊ ተቃራኒነት ባላቸው ቃላት የሚመሠረት አያዎ (አይ እና አዎ) የሚባል ዘይቤ አለ፡፡” ይላሉ፡፡ በእኔ አመለካከት የእኛ ኑሮ ኑሯችን ይህን ዘይቤ ይመስላል፡፡ በቃል ትውፊታችን “እንጨት ሁኖ የማይጤስ ሰው ሁኖ የማይበድል የለም፡፡” ወይም “ከሰው ስሕተት ከብረት ዝገት አይጠፋም፡፡” እንላለን፡፡ ፊደል የቆጠርነው ደግሞ እንደ አቶ በረከት ስምዖን ፈላስፎችን ጠቅሰን ከየትኛውም ሰው የሚገኝን ዕውቀት መገብየት እንደሚገባ እንከራከራለን ወይም “አንጋረ ፈላስፋ” የሚል ርእስ ሰጥተነው መጽሐፍ እንጽፋለን፡፡ ሁልጊዜም ነገሮች ጥቁርና ነጭ ብቻ እንዳልሆኑ ይልቁንም ግራጫ መካከለኛ እንዳለ እንናገራለን፡፡ ይህም የዕውቀታችንን ምጥቀት የአእምሯችንን ስፋት ያሳይልናል፡፡ ይህ ልማድም ከጥንት ጀምሮ የያዝነው በመሆኑ ያኮራናል፡፡ ነገር ግን ታሪካችን እንደሚመሰክርብን ድርጅትም ይሁን ሀገር የመምራት ኃላፊነት እጃችን ላይ ሲወድቅ የምንሠራው ፈጽሞ ሌላ ይሆናል፡፡

  ብዙዎቹ መሪዎቻችንም ሆኑ አቆላማጮቻቸው የዛሬ መቶ ዓመት አካባቢ ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ እንዳሉት ዮሐንስን ካልሰደቡ ምኒሊክን ማመስገን የሚቻል አይመስላቸውም፡፡ ምኒሊክን ካልተራገሙ አባጅፋርን ማወደስ፣ ካዎ ጦናን ማሞገስ የሚቻል አይመስላቸውም፡፡ በላይ ዘለቀን ካላዋረድን ጃንሆይ ክብራቸው ሕጸጽ ሲያገኘው ይታያቸዋል፡፡ የኢሕድሪን የትምህርት ፖሊሲና መጻሕፍቱን ሙሉ በሙሉ ደምስሶ አዲስ የማስተማሪያ መጽሐፍ ካልታተመ የኢፌዲሪ ትምህርት ስኬት እውን የሚሆን አይመስላቸውም፡፡ ኢፌዲሪን “በመላእክት የምትመራ ሀገረ ገነት” ብሎ ለመጥራት ኢሕድሪን “በሳጥናኤል የሚተዳደር ገሃነም” ማለት ግድ እንደሆነም የሚቆጥሩት ይመስለኛል፡፡ “በሴኪዩላሩ” መንግሥት የተገኙትን ውጤቶች ለማወደስ ዘውዳዊውን አሠራር አንድም ሥራ ያላከናወነ የአሳሞች ስብስብ አድርጎ መሳል፣ የሠራቸውንም ነገሮች ሙልጭ አድርጎ ጠርጎ መካድ ልማዳችን ነው፡፡ አንዳንድ የታሪኮቻችን ቅንጭብጫቢዎችና ጥግጋት እንደሚጠቁሙት በመግደል እናምናለን፡፡ ሰውየውን ስንጠላ የሠራቸውን ሥራዎች በሙሉ ያለ አንዳች ልዩነት እናርኮሰኩሳለን፡፡ የሰውየውን መልካም ጎን የሚሳዩትን ነገሮች በሙሉ ሽምጥጥ አድርገን እንክዳለን፡፡ መልካሙን ለማየት ዓይኖቻችን እሺ አይሉንም፡፡ የዚህ ክፉ ልማድ ባሮች ስለሆንንም በየዘመኑ በታሪክ መዝገብ ላይ ቀድሞ የነበሩትን ገጾች ቀድደን እንደአዲስ አንድ ብለን ለመጻፍ እንሞክራለን፡፡ ልጆቻችን ብቻ ሳይሆኑ አባቶቻችንም እኛ ሰፍተን የምንሰጣቸውን የታሪክ ልብስ እንዲለብሱ የማንፈነቅለው ደንጊያ የለም፡፡ የትናንቱን ታሪክ ከዛሬ ሕይወት ጋር አዋሕደን የነገን ህላዌ የሚጠቅም ለማድረግ (ወይም በሊቁ እጓለ ገብረ ዮሐንስ አማርኛ “በተዋሕዶ የከበረ” ለማድረግ) የማሰብ ዐቅሙ ያጥጠናል፡፡

  ዘመነኛውን ትምህርት ከፍከፍ ለማድረግ ቤተክህነታዊውን ትምህርት ማውገዝ ዓመል ሆኖብናል፡፡ ከማንበብ፣ ከመፈተሽና ከመመራመር ይልቅ ማድመጥ ስለሚቀናን ወይም ዶ/ር ፈቃደ አዘዘ እንደሚለው “የጆሮ ሀገር ሰዎች” ስለሆንን ብዙዎቻችን የምንራገመው ሌሎች ቀን የሰጣቸው ሲራገሙ ሰምተን እንጂ በራሳችን መርምረን የሚወገዝ ሆኖ አግኝተነው አይደለም፡፡ ከዐዋቂዎች ተርታ ለመሰለፍ ዐዋቂዎች የተጓዙበትን የመሞከር፣ የመሳሳትና የመማር አድካሚ የዕውቀት መንገድ ከመከተል ይልቅ በአቋራጭ በቶሎ ዐዋቂ ለመባል ከአፍ ከአፋቸው እየለቀምን እናስተጋባለን፡፡ እንቸኩላለን፡፡

  ከበደ ሚካኤል ግን እንዲህ ብለውን ነበር፡-
  ፈላስፋው ሲመክር አደራ ብሏል፤
  በምትሠራው ሥራ ቀስ ብለህ ቸኩል፡፡
  የምናደርገውና የምናውቀው የተለያዩ ናቸው፡፡ ስለዚህም የዘለዓለም ብላቴኖች ሆነን እንኖራለን፡፡ ለነገሩ መብታችን ነው! ጨካኝነት ከሃይማኖተኝነት ጋር፣ ዐዋቂነትም ከግብታዊነት ጋር ተምታትተውብናል ወይም አምታትተናቸዋል፤ ወይም ተደበላልቀውብናል ወይም አደበላልቀናቸዋል፡፡
  ከዚህ የአያዎ ኑሮ ለመላቀቅ ምን ማድረግ እንዳለብን ደበበ ሰይፉ “እንደደግ እንደ ዛፍ” በሚለው ግጥሙ በአያዎ ዘይቤ እንዲህ ብሎ ነበር (እሾህን በእሾህ መሆኑ ነው)፡-
  ጥቁር አፈር ዐቅፎን
  ጥቁር ብርሃን ውጦን
  ሥራሥር አንቁለን
  አዝምተን እንደ ሐረግ
  ውስጡን ዕመቃቱን
  ጉራንጉሩን ጠገግ
  ጭረንና አሽትተን
  እንደ ፋኖ ሶለግ
  እንንቀስ አልሚውን
  እንልቀም መልካሙን
  እንደልባም ሰው ወግ፡፡
  ከፍ ብለን እንድናኝ
  አየሩን ልንመላ
  ወደፊት ለመሔድ እንሩጥ ወደኋላ
  እንደ ደግ እንደዛፍ ዋርካ እንሁን ሾላ፡፡

  ይህንን ለማድረግ በቅድሚያ የሰጡትን ሁሉ የሚውጥ ሳይሆን የሚጠይቅ፣ የሚመራመር፣ በዕውቀት አድካሚ ጎዳና ለመጓዝ የተዘጋጀ ሰው መሆን ያስፈልጋል፡፡ ያኔ እንደ መንጋ ከመትመም፣ ለአረንጓዴ ጎርፍነታችን (green የሚለው ቃል ያልበሰለ የሚል ፍቺም እንደሚይዝ ልብ ይሏል፡፡) በተቀየሰልን መሥመር ብቻ ከመሮጥ ወጥተን ለምን ብለን መጠየቅ እንጀምራለን፡፡ እውነትም ነጻ ታወጣናለች!

  ReplyDelete
 18. what can we say, we jest keep on going bcz God in the obove let us to be in this way. May he give as strength to fight this worbela wayane

  ReplyDelete
 19. Dear Daniel,

  What a regretful is this? Emperor Haileselassie was an iconic figure to OAU. Since the establishment of OAU in 1963, no single leader in Africa chaired OAU twice (1963/64 and 1966/67) like him. When the Casablanca and Monrovia groups struggle on different ideas he was the one who pull them together and brought into consensus. Ghana led the Casablanca group, Nigeria led the Monrovia group.

  Some of the governments that were represented in Addis Ababa had different views on what the charter should consist of. Among them, Ethiopia, Ghana, and Nigeria had drawn up charters, which could possibly become the basis for discussion. While the charter of Ghana represented the views of the Casablanca group and the Nigerian charter represented the position of the Monrovia block, the Ethiopian draft charter embodied the views of both groups. As a result, the Ethiopian draft charter was chosen to become the basis for discussion. Ethiopia propose an agenda like:
  1. The establishment of an Organization of African States, with a charter and a permanent secretariat.
  2. Cooperation in areas of economy and social welfare, education and culture, and collective defense.
  3. The final eradication of colonialism.
  4. Means of combating racial discrimination and apartheid.
  5. Possible establishment of regional economic groupings and,
  6. Disarmament.

  For the above reason Emperor Haileselassie was the pioneer icon to the union. Thus, a monument for him like Kwame Nkruhmah is needed.

  «ባለፉት ዘመናት የተሠራው ሁሉ በሚገባ ካልተነገረና ቀደምት ሰዎች ባበረከቱት አስተዋጽዖ በአግባቡ መጠቀም ካልተቻለ፣ ዓለማችን ሁሌም ቢሆን የዕውቀት ብላቴና እንደሆነች ትቀራለች»፡፡

  እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!!!

  ReplyDelete
 20. ንጉሥ ኃይለ ሥላሴ የአፍሪካ አነድነት ድርጅትን በመመሥረት፣ አፍሪካውያን ከቅኝ ገዥዎች ተላቅቀው ነጻ እንዲወጡ በመርዳት፣ የአፍሪካንንም ድምጽ በዓለም ዐቀፍ መድረክ በማሰማት ያደረጉትን አስተዋፅዖ እንኳን እኛ ዛሬ ከመቃብር በታች የዋለው አፓርታይድም ዕድል ካገኘ ይመሰክረዋል፡፡
  this government is shameful and Gotegna newu, world, even America has come with bad history but our kings have done many good things for equality of nations here in the country than America have done;like bad racism.
  eve Arabic world are in the system of monarchical authority till now , Yegnan gin Akefut ;why they preach as our history is more worse than others?
  they(Meles or banda group) are selling the country now and laying but people are in below poverty.
  we can see in evidence even at Addis most people except one Nation that is Tigre who get land, employment for free other all are poor especially Amharas are paying scarification even those kings from AMharas do good thins for the country.
  yeah they come to power by chance but they lost and taken above 11 billion dollar as world financial intelligence report says to their pocket but still they are robbing by transferring many governmental organizations to private especially for their blood relations.

  so why we deny their(Kings) good work for the country ?
  God keep Ethiopia and make their heart to think to Ethiopia

  ReplyDelete
 21. yasazinal Banda emeran.

  ReplyDelete
 22. ይህች ሃገር የእግዚአብሄር ሀገር ናት!..ገድለነዋል ቀብረነዋል ባሉበት ቦታ መቃብርን ፈንቅሎ በድል ትንሳኤ አለሙን ከራሱ ጋር ያስታረቀው አሸናፊ አምላክ የተሰበከባት እና የከበረባት ድንቅ ሃገር ናት ኢትዮጵያችን!!!...አዎ..የከብሩዋ ምንጭ እርሱ ክርስቶስ የሆነላት ቅድስት ምድር!!! የፖለቲካ አይሁዶች ሆይ ታሪኩዋን ቀበርን ብላችሁ ተደስታችሁ ይሆናል!ነገር ግን በገደላችሁባት በዚያው ሕንጻ ውስጥ ትንሳኤዋ እውን የሚሆንበት ግዜ ይመጣል፡፡እሰቡበት ! በእግዚአብሄር መታመናችን የናንተን ክፋት ለህሊናችን የምንሸውድበት ሞኝነት አይደለም!..አይሆንም የተባለውን ሢያረግ አይተነው እንጅ!..ለዚህ የኢትዮጵያ አምላክ ሃያልነት ደግሞ ከጣሊያንና ከናንተ በላይ ምስክር መጥቀስ አያስፈልግም!..ጣሊያን መሸነፉ..በእናንተ ደግሞ ደርግ መውደቁ!..ስለዚህ እንደ ፈርኦን ጥጋበኞች ሳይሆን ዕንደ ዳዊት ቅን እና እግዚአብሄርን የምትፈሩ መሪዎች ሁኑ! ካለዛ ግን ከጫካ እስክ ቤተመንግስት ያደረሳችሁ እግዚአብሄር ይመጣል መቅረዙንም ከናንተ ይወስዳል!!!! ሰው ያርጋችሁ!..ዳኒ እራሴን እያሳመምከኝ ቢሆንም ምስጋናን ልከለክልህ ግን ተሳነኝ!!!..ድንቅ ወቀሳ!!!! ያፄ ሐይለ ስላሴ ሃውልትን እናየው ዘንድ ተስፋ ያደረከው ሁሉ ይባረክ!!!!!!

  ReplyDelete
 23. May be the emperor has done something great to Africa or to the other part of the world, but can anyone here tell me what the emperor did anything good to Ethiopia? He led the country for about 50 years to poverty, darkness and ignorance. He is one of the reasons for many of the negative attributes in the country today. Let me ask you about Nationalism? What kind of leader leaves his land and country to the foreign power during a war? To me those citizens who have paid their precious lives and Golden blood for the peace and democracy of the country are really Ethiopians. God bless Ethiopia and VIVA EPRDF.

  ReplyDelete
  Replies
  1. enante Hoyanewoch degimo mitaworutin atawkum. kemeriyachihu keMeles jemiro. EPRDF yihew le20 amet wodegedel eyemeran ayidel ende? degimo YeHaileselasse guadegna? dinkem alu. koyi zim bel. tarik yiresal meseleh endie? jil atihun wodaje.

   Delete
  2. For what you said "What kind of leader leaves his land and country to the foreign power during a war?" The answer is the grand father and all the relatives of Meles who are named Agamey in north Tigray has collaborated with the Fascist Italy during the Wars of Ethiopia with Italian Colonial Powers in 1928 E.C. They are also here to collaborate with our enemies. The ancestors of Meles and he himself tends to be collaborator by their nature. They have had no reason even to make wars against Durg simply they collaborated with ELF at the very begining without evaluating the Durg Regime. So they tend to collaborate to vanish Ethiopia to divide Ethiopia not construct Ethiopia.

   Delete
 24. I think we can do one thing. We can show our anger through petition send to memebers of AU. Ignore Meles.He dont sleep until he down our country.Shame on you.We dont expect anything from him,but we do the best for our country.
  Brile

  ReplyDelete
 25. please my brothers and sisters we have to know what we saying. "think twice before speaking once" any ways good writing dn.daniel but we have to look things in differenet prespective. thank you

  ReplyDelete
  Replies
  1. Please tell us that prespective?

   Delete
 26. we or our son will erect z king statue next to Nkrumah. history never dies

  ReplyDelete
  Replies
  1. ዲን ዳንኤል እግዚአብኄር ጩዀትህን ከንቱ አያድርግብህ ምኞትህ እዉን ያድርግልህ፡፡ ጩዀትህ ጩዀታችን ምኞትህ ምኞታችን ነውና፡፡ለመሪዎቻችንም በቃኝ ማለትና የራስን የማክበር አእምሮ ይስጥልን፡፡የተከበረውን አዋርደዋልና እነሱም ነጌ እንደምዋረዱ የሚያስብ አእምሮ ይስጥልን፡፡

   Delete
 27. To Noah &some others: ያልተረዳህው ታሪክ ያለ ይመስለኛል:: ዘመናዊ ትምህርትን በዩኒቨርሲቲ ደረጃ እንዲዋቀር ያደረጉት አጼ ዮሃንስ ናቸው እንደማትል ተስፋ አለኝ:: ንጉሱ ምንም እንኩዋን ለባላባት ልጆች ቢያደሉም ውጭ ሃገር እየላኩ ያስተምሩ ነበር ምንም እንኩዋን ደርግ ቢገላቸውም ምሁራኑን:: ንጉሱ ለአፍሪካም ሆነ ለኢትዮጵያ ብዙ ሰርተዋል እኛ የበላንበትን ወጭት ሰባሪ ሆነን ነው እንጅ:: ያን ዘመን ከዚህ ዘመን ጋር የማወዳደር አባዚ ከመለስ እየወርስን መንገዳችንን እየሳትን ነው:: ያ ዘመን ከዚህ ዘመን ጋር ፈጽሞ መወዳደር የለበትም:: በዚያ ዘመን አለም አልበለጸገችም ሃብትም እንዳሁኑ አልነበረም:: በዛን ዘመን አንድ ት/ት ቤት መክፈት ዛሬ አስር ዩኒቨርሲቲም አይወዳደረውም:: የባላባት ጉዳይም ቢሆን በሌላው አለም የለም ነበር? በአውሮፓ አልነበረም? ችግራችን ቁንጽል ሃሳብ ይዘን ማነከሳችን ነው:: የንጉሱ ስህተት ስልጣን ለልጃቸው አለመስጠታቸው ብቻ ነው:: በዚያን ጊዚ ለልጃቸው ሰጥተው ቢሆን ኖሮ ደርግም ኢሃዲግም አይኖሩም ነበር:: በተሻለ መንገድ የመጉዋዝ እድሉ ነበረን:: ከዚያ ዉጭ ግን ከመለስ የበለጠ ጥፋት አልሰሩም:: ድርቅ ነበር በዚያ ዘመን; አዎ ነበር በደርግም በዒሃዲግም አለ:: ለዛውም ዘመናዊ ድርቅና ርሃብ:: ታሪክ ይመሰክረዋል ቆይቶ:: ማንም ከሱ አያመልጥምና:: ሌላው ደሞ: ንክሩማህ ለጋና ባደረጉት ነው ወይስ ለOAU ባደረጉት አስተዋጾ? የመለስም ስህተት ይህ ነው:: አለም የመሰከረው አስተዋጾ እርሱ ካደው:: ከድንጋይ ይልቅ ታሪክ ትልቅ ቦታ አለው:: እርሳቸውን የጎዳ መስሎት የራሱን ታሪክ አፈር አስጋጠው:: ለማንኛውም ማስተዋሉን ይስጠን:: ከፉ የሰይጣን ዘመን::

  ReplyDelete
 28. Let me tell you one thing you amhara donkey haters, Meles will still continue to make history while you keep braying. Let me tell you the truth, All ahiya lingo, culture, religion is taken from Tigray. So U better watch your mouth.

  ReplyDelete
 29. thank u Dani and all who wrote comments,
  Long live for ethiopia

  ReplyDelete
 30. Anonymous Feb 19, 2012, 11:07 AM: which culture is taken from Tigray? Which religion is taken from Tigray? Do you think that Gojames have a similar culture with Tigres? Gonderes with Tigray? Shewes with Tigray? Religion?, Christianity has not originated from Tigray (ማን ያውቃል ክርስቶስ ትግሬ ነው ትል ይሆናል ቆይተህ). If you don't know please go to school. At least you will get these histories from elementary school. Please just read before you speak to people. ኢሃዴግ እንዲጠላ የምታደርጉትና ያደረጋችሁት አንተና መሳዮችህ ናችሁ:: ይሄ አመለካከት ደሞ ገደል ይጨምር ካልሆነ በቀር የትም አያደርስም:: ቆይተህም ታየዋለህ ውጤቱን:: Historyም ስለ መለስ ምን ብሎ እንደሚያወሳ አብረን እናያለን:: የዚያ ሰው ይበለን::መለስ እና በረከት የጻፉት መጻፍ ታሪክ ከመሰለህ ተሳስተሃል:: የውጭ የታሪክ ተመራማሪዎች ከአድልዎ ነጻ ሆነው ይጽፉታል::

  ReplyDelete
 31. Thank you Dani, God be with you all the time!

  ReplyDelete
 32. "ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፣ በህያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ፡፡"1ኛ ጴጥሮስ1፡23

  ReplyDelete
 33. Anonymous Feb 20, 2012 10:11 AM just you need to accept the truth. Anonymous Feb 19, 2012, 11:07 AM: is right about the fact that roots of culture, religion, language, and every civilization this country has all roots from Tigre. I don't think the cultures of amara and tigre are that much differnt. Look at the holidays and the foods we eat and the languags we speak, the alphabets we write, the calendars we use.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Hey! Stop your squabbling with who is the originator. Both of you are wrong and both of you are right. The answer for whatsoever this country has should be answered in a way of paradox. No one is the originator and everyone is the originator. Each and every clan has the share to whatsoever this country of yours has.

   To your surprise neither the alphabets nor the holidays were invented in Ethiopia. They were adapted from somewhere else. Talking about the alphabets, have you ever tried to look the similarity between Hebrew and Greek alphabets to the Ethiopic ones? Your fathers were not victims of confined mind with parochialism. They were amazingly eclectic. They were open to the world as much as they could. Everything is connected to everything. Get out of your boxes!

   Delete
  2. Ancient axumites were amharas.

   Delete
 34. ነግ በኔ የሚለው ተረሳ

  ReplyDelete
 35. ስለወያኔና ትግሬ ያወራሃው Anonymous አንተም ወያኔም ከዚህች ሃገር ብቻ ሳይሆን ከምድራችንም ያጥፋችሁ፤ ድሮሰ እንደአንተ አይነት ጠባብ ዘረኛና የወያኔን አይነት ጨቋኝና ታሪክ ደምሳሽ ከሀዲ ባለበት ሀገር እንዴት ስለታሪካዊ ሰዎቻችን ማውራት እንችላለን? ብቻ እግዚአብሄር ሀገራችንን መከራውን ያሳጥርላት አሜን።

  ReplyDelete
 36. ምን ነካው ሰው የው አነጋገሩ ሃገርን ወክሎ ሳይሆን እራሱን ወክሎ እንኳን እየተነገረ ለመሆኑ ስጋት ገባኝ፡፡
  ምናአልባት ራት አግባዎቹ የሚነገርለት ሙገሳ እና ውዳሴ እውነታውን አስረስቶት ለእርሳቸው ሃውልት መሰራቱ እሱን የሚያሳንሰው መስሎት ይሆን እንጃ
  ለማንኛውም ግን ራሱን እና ታሪኩን ጥላሸት ቀባ

  ReplyDelete
 37. ዳኒ እድሜና ጤና ይስጥህ: ይኋው ነው ሃቁ ሌላ የለም:: ለመሬዎቻችን የሕዝቡን ቅሪታ የሜሰሙበት ዕእምሮ ጌት ይስጥልን::

  ReplyDelete
 38. ዳንኤል ያነሳኸው ርዕስ ትክክለኛና ወቅታዊም ሲሆን ሳላመሰግንህ
  አላልፍም።ሆኖም ግን በረከት ስምዖንን(ዮሴፍ ጎብልስ) መፅሀፍ ማጣቀሻ ማድረግህ አሳዝኖኛል!በረከት በዐይናችን ያየነውን የ1997 ምርጫ ውጤት፣ግድያ፣ክህደት እያወቅክ ከበረከት ሀሳብ መውሰድህ
  ትዝብት ላይ ይጥልሀል።ከወያኔ ጋር የተነካካህ ይመስለኛል ሳስብህ።መደምደሚያ ላይ የፃፍከው ማሳሰቢያ ይህን ፅሁፍ ሌሎች
  መጠቀም የለባቸውም ማለትህ ለምንድን ነው? በአሸባሪነት ላለመከሰስ? ወይስ በረከት እዳይቀየምህ? ፈሪ ፀሀፊ አትሁን ከተመስጌን(ፍትህ)ተማር በበዐሉ ግርማ አባባል ልሰናበትህ
  ከአድርባይ ደራሲ ባዶ ወረቀት ይሻላል።የሚያምን አይፈራም ይላል
  መፅሀፍ ልመርቅልህ!!!

  ReplyDelete
 39. ዳንኤል ያነሳኸው ርዕስ ትክክለኛና ወቅታዊም ሲሆን ሳላመሰግንህ
  አላልፍም።ሆኖም ግን በረከት ስምዖንን(ዮሴፍ ጎብልስ) መፅሀፍ ማጣቀሻ ማድረግህ አሳዝኖኛል፣በረከት በዐይናችን ያየነውን የ ምርጫ ውጤት፣ግድያ፣ክህደት እያወቅክ ከበረከት ሀሳብ መውሰድህ
  ት ዝብት ላይ ይጥልሀል።ከወያኔ ጋር የተነካካህ ይመስለኛል ሳስብህ።መደምደሚያ ላይ የፃፍከው ማሳሰቢያ ይህን ፅሁፍ ሌሎች
  መጠቀም የለባቸውም ማለት ህ ለምንድን ነው በአሸባሪነት ላለመከሰስ ወይስ በረከት እዳይቀየምህ ፈሪ ፀሀፊ አት ሁን ከተመስጌን(ፍት ህ)ተማር በ በዐሉ ግርማ አባባል ልሰናበት ህ
  ከ አድርባይ ደራሲ ባዶ ወረቀት ይሻላል።የሚያምን አይፈራም ይላል
  መፅሀፍ ልመርቅልህ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምጸት (irony) ያውቃሉ?
   You want Daniel to be courageous than what he is but you yourself are writing as anonymous. Daniel has showed us how our intellect and our deeds are quite far apart through quoting. We do what we do not because we don't know but because we don't want. Our hardware and our software are not matching. We don't do what we know we should do. That is our living (or dying if you want) principle.

   Delete
 40. gena legena berket tsafew tebelo....

  ReplyDelete
 41. አይ የሀገሬ ሰዎች፡፡ ሁሉንም አነበብኩ እጅግም አዘንኩ፡፡ እኔ ትግሬ እና ወያኔ ከሀገር ይጥፉ አልልም፡፡ እነሱም እጅግ የምወዳቸው ወገኖቼ ናቸውና፡፡ ኢትዮጵያ የምትባለው ሀገር እንድትኖር ትግሬዎችም አማራዎችም፣ ኦሮሞዎችም ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦችም መኖር አለባቸው፡፡ ይሀንን የምታነብ ወገኔ መፈረጅ ትወዳለህና ይሄ የወያኔን ጠጅ የጠጣ ትለኝ ይሆናል፡፡ ግን አልጠጣሁም፡፡ እኔ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ከችግርና ከረሀብ ተላቀው ማየት፣ የምንበላው የምንጠጣው ኖሮን ማየት፣ የምነጠለልበት ኖሮን ማየት ነው የምፈልገው፡፡ ይሄንን ለማምጣት የሚተጋ መሪ ከኦሮሞ ይሁን ከትግሬ፣ ከጎጃም ይሁን ከጎንደር፣ ከሸዋ ይሁን ከሀረር፣ ከጉራጌ ይሁን ከወላይታም ግድ የለኘኝም፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው ብዬ ስለማምን፡፡ አቶ መለስንም ባንዳ አልልም፡፡ እጅግ ብዙ ነገር ሰርተው በአይኔ አይቼአለሁና፡፡ ጭፍን ፖለቲካ አልወድመም፡፡ ነገር ግን ዳንኤል ክብረትን እንኳን በኢቴቪ ቀርበህ ስለአባይ ግድብ እና ኢትዮጵያ ተናግረሃል ብሎ መፈረጅ፣ ሀሳቡን ሳይሆን እከሌ ከጠላቴ ጎን ለምን ቆመ፣ የበረከትን መፅሀፍ ለምን አነበብክ የምንባባል ከሆነ እኛም መሪ ሆነን ተራ ቢደርሰን ምናልባት ጥፋታችን የትየለሌ ይሆናል፡፡ አቶ መለስ የአፄ ኃይለ ሥላሴ ሃውልት ለምን እንዳልተሰራ የመለሱበት መንገድ አልተመቸኝም፡፡ ንጉሳችን በአፍሪካ ህብረት የነበራቸው ሚና የትየለሌ ነው፡፡ ለመሆኑ እርስዎ ንጉሱን ወግነው ካልተከራከሩ ማን መጥቶ ይናገር፡፡ ኢትዮጵያ ያላት ወንበር አንድ ነው፡፡ እርሱንም ይዘውታል፡፡ ታዲያ ማን ይናገር፡፡ ሀገሬ ኢትዮጵያን ስለምወድ እርስዎም በታሪክ አጋጣሚ ሀገሬን ስለሚመሩ አከብርዎታለሁ፡፡ ግን ንኩሩማህ ከአፄ ኃይለሥላሴ የበለጠ ታሪክ አላቸው ያሉት እጅግ የወረደ ነው፡፡ ሌሎችም ውድ ወገኖቼ እባካችሁ የአንድን ሰው ሃሳብ ጨፈላልቃችሁ የኔን ተቀበሉ አትበሉን፡፡ የኔንም ሃሳብ አለመቀበል መብታችሁ ነው፡፡ እንዲህም አይነት አመለካከት ያለው ኢትዮጵያዊ ወገናችሁ ግን አለ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. I would like to say "Tebarek" to AnonymousMar 3, 2012 08:17

   Delete
 42. አቶ መለስ እኮ 80 ሚሊዬን የኢትዮጵያን ህዝብ ወክለው እንጂ ስልጣን ላይ ያሉት የራሳቸውን ወይንም የወጡበትን 10 ሚሊዬን አካባቢ የሚሆን አንድ ጠባብ የትግሬ ብሄር ስሜትና አመለካከት በመወከል አይደለም፡፡Shame on you. No one is the originator and everyone is the originator. Each and every clan has the share to whatsoever this country of yours has.This shows the way u think & who u r.Balege

  ReplyDelete
 43. please be active to differentiate on what is woyane( meles and bereket) and who is Tigrian people being we people will live together for ever.

  ReplyDelete
 44. yemecheresha bikat aleh kante lela ethiopia sew yelem u are really wonderful
  እኔ ተስፋ አለኝ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የተመሠረተበት አምሳኛ ዓመት በዓል ከመከበሩ በፊት የንጉሡ ሐውልት ከነ አስተዋጸዖዋቸው በአፍሪካ ኅብረት ግቢ ውስጥ ይታያል ብዬ፡፡

  ReplyDelete