Wednesday, February 15, 2012

የደቡብ አፍሪካውያን ነፃነትና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪካዊ ድርሻ በቀድሞ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት በታቦ እምቤኪ አንደበት

(click here for pdf)
በፍቅር ለይኩን፡፡ ~ fikirbefikir@gmail.com

 የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ ፓርቲ በቅርቡ ዓመቱን የደቡብ አፍሪካዋ Judicial Capital በሆነችው በብሉምፎንቴን በታላቅ ድምቀት ተከብሯል፣ ይህች ውብ ከተማ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ን ታሪክ ከኢየሩሳሌም ቀጥሎ ሁለተኛ የሆነው የቅድስት ሥላሴ ወቅዱስ ያሬድ ገዳምና የካህናት ማሰልጠኛ ተቋም የተቋቋመባትና የተገደመባት ከተማ መሆኗን ልብ ይሏል፡፡ የደቡብ አፍሪካውያኑ ANC ፓርቲ በአፍሪካ ከተቋቋሙ ፓርቲዎች አንጋፋውና ረጅም ዕድሜ ጭምርም ያሰቆጠረ ነው።
የአፍሪካን የሰው ኃይልና የተፈጥሮ ሀብት ለመዝረፍ አፍሪካን በቅኝ ግዛት የተቀራመቱት አውሮፓውያን በዋነኝነት አፍሪካን ምድር የረገጡበት ምክንያታቸው አፍሪካን በወንጌል ቃል ለማቅናት ነው የሚል ቢሆንም በሂደት ግን የአፍሪካውያን የሰው ኃይልና የተፈጥሮ ሀብትን በመዝረፍ ለአፍሪካውያን ታላቅ ስብራትን ጥሎ ያለፈና ይሄ ነው ተብሎ ሊገመት የማይችል ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ታሪካዊ ቀውስንና ክስረትን ሊያተረፍ የቻለ የአፍሪካውያን መራር ጨለማ ዘመን ታሪክ ሆኖ ሊያልፍ በቅቷል፡፡
አፍሪካውያን ወይም በአጠቃላይ ጥቁር ህዝብ ምንም ዓይነት ፖለቲካዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ሰብዕና የለውም ብሎ የሚያምነው የአውሮፓውያን አፍሪካን በቅኝ ግዛት የመቀራመት ዘመቻ፤ ጥቁር ህዝቦችን ከሰውነት ተራ በማውረድ በገዛ መሬታቸው ባይተዋር የሆኑበትንና የተፈጥሮ ሀብታቸው ተዘርፎ ባህላቸው ተንቆ፣ በዘመናት ያፈሩት ስልጣኔያቸው፣ ታሪካቸውና ቅርሳቸው የእነሱ እንዳልሆነና ጥቁር ህዝብ እንዲህ ዓይነት የረቀቀና የመጠቀ ስልጣኔ ባለቤት አይሆንም በሚል እኩይ አስተሳሰብ ቅርሶቻቸውና ታሪካቸው በአውሮፓ ቤተ-መዘክሮችና ዐውድ ርዕዮች ተግዘው ለእነሱ ከፍተኛ የገቢ ማስገኛ ምንጮች በመሆን አፍሪካውያን በገዛ ታሪካቸውና ቅርሳቸው ባይተዋር ሆነው ታሪክና ቅርስ አልባ የሆኑበትን ዘግናኛ የመከራና የሰቆቃ ዘመን በአፍሪካ ታላቅ ታሪክ ጠባሳን ጥሎ አልፏል፡፡
በዚህ ግፍና መከራ ኅሊናቸው የቆሰሉ አፍሪካውያን ይሄን ግፈኛ ስርዓት ከጫንቃቸው አሽቀንጥሮ ለመጣል ሲሉ ነበር በኛው መቶ ክ/ዘመን መባቻ የጸረ-ኮሎኒያሊስት እንቅስቃሴ በአፍሪካ መቀጣጠል የጀመረው፣ በተለይም ደግሞ በደቡብ አፍሪካ በነበረው የአፓርታይድ ዘረኛና ከፋፋይ ሥርዓት ክፉኛ የተቆጡና የህዝባቸው ውርደትና ሰቆቃ በእጅጉ እንቅልፍ የነሳቸው አፍሪካውያን ይህን ሥርዓት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ታሪክ ሊያደርጉት ከዛሬ መቶ ኣመት በፊት  የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ ፓርቲ African National Congress Party (ANC) አቋቋሙ፡፡ የዚህ አንጋፋ ፓርቲ ጽንሰትና ልደትም ምክንያቶቹ የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሚከተሉ ደቡብ አፍሪካውያን የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮችና የነፃነት ፋኖዎች ነበሩ፡፡
ለሰው ልጆች ሁሉ ከፈጣሪ ዘንድ ስለተሰጠ ነፃነትና ክብር በግልጽ የምታሰተምረው ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን፡- ነፃነት የሰው ልጅ ከአምላኩ የተሰጠው ክብሩ መሆኑን ቅዱሳት መጻህፍትንም ዋቢ በማድረግ፣ የሰው ልጅ በታሪኩ ዘመን ለነፃነቱ የከፈለውን ክቡርና ውድ ዋጋ የእግዚአብሔርን ህዝበ ታሪክ በመጥቀስ በዘመኗ ሁሉ ስታስተምር ቆይታለች፤ አሁንም በማስተማር ላይ ነች፣ ወደፊትም እንዲሁ፡፡ ለዘመናት ሀገራችን በነፃነት ኮርታ የመቆየቷ፣ የህዝቦቿም አይበገሬነት ምስጢሩ ይኽው ቤተክርስቲያን ለሰው ልጆች ነፃነትና ክብር ካላት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ከሆነ አስተምህሮ የተነሳ ነው፡፡ ለጥቁር ህዝቦች ሁሉ ትልቅ ድልን ያጎናጸፈው የአድዋው ድል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ መንፈሳዊ ተጋድሎ፣ ጸሎትና ትልቅ የሆነ ታሪካዊ አሻራ ያለበት እንደሆነ በተለያዩ የውጭ ሀገርና የሀገራችን የታሪክ ምሁራንና ተመራማሪዎች ዘንድ ብዙ የተነገረለትና የተፃፈለት ነው፡፡
ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መባቻ ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን መሰረት በማድረግ በሰሜን በአሜሪካ፣ በካረቢያንና በጃሜይካ እና በመላው አፍሪካ እንዲሁም በተለይ ደግሞ በደቡብ አፍሪካ በስፋት የተነሱ የነፃነት እንቅስቃሴዎች በዋነኝነት መነሻ ያደረጉት የኢትዮጵያን የረጅም ዘመን ስልጣኔ እና ታሪክ፣ የህዝባችንን አኩሪ የነፃነት ተጋድሎን፣ ክርስትናን በቀደምትነት ሰላማዊ በሆነ መንገድ የተቀበለችና በአፍሪካ በቀዳሚነት የክርስትና ማዕከል መሆኗን፣ ከዚህም የተነሳ በተደጋጋሚ በቅዱሳን መጻህፍትና በተደጋጋሚ መጠቀሷ፣ በጥንት ጸሀፍትና ታሪክ ተመራማሪዎች ዘንድ ብዙ የተነገረላትና የተፃፈላት መሆኑ ነው፡፡
የኢትዮጵያ የሺ ዘመን አኩሪ ታሪክ የብዙዎችን ቀልብ በመሳቡ በተጨማሪም በ ፲፱ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ጀግንነትና ኢትዮጵያውያን አንድነት በዘመናዊ መልኩ ተደራጅቶ የመጣውን የኢጣሊያ ወራሪ ጦር በማንበርከክ በመላው አውሮፓውያን ቀኝ ገዢዎች ዘንድ መደናገጥንና ለመላው ጥቁር ህዝቦች ደግሞ አዲስ የሆነ የነፃነት ፋና የለኮሰውን ኢትዮጵያውያን በአድዋው ጦርነት የተጎናጸፉት ታላቅ ድል በአፍሪካ፣ በአፍሪካ አሜሪካውያን፣ በካረቢያና በጃሜይካ ጥቁር ህዝቦች ዘንድ ትልቅ የነፃነት ጥያቄ ማስነሳቱና ለዚህም የነፃነት ጥያቄ ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የነፃነት ትግሉ ዋና ማዕከልና መነሻ በመሆን ትልቅ ድርሻ የወሰዱበት ታላቅ የታሪክ ምዕራፍ ሊከፈት ችሏል፡፡
በደቡብ አፍሪካውያን፣ በአፍሪካ አሜሪካውያን፣ በካረቢያንና በጃሜይካውያን ህዝቦች ዘንድ በእጅጉ ተስፋ ትደረግ የነበረችው ቤተክርስቲያናችን ለሰው ልጆች ነፃነትና በተለይም ደግሞ ለአፍሪካዊ ወንድማማችነት መንፈስ (Pan Africanism) ትልቅ የሆነ ታሪካዊ ድርሻን አበርክታለች፡፡ የዚህን ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን ለነፃነት የከፈለችውን ክቡርና ውድ ዋጋ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት፣ በላቲን አሜሪካ እንዲሁም በአፍሪካ አሜሪካውያን ዘንድ ያሳደረውን ትልቅ መነሳሳትና ወኔ እንዲሁም ታሪካዊ ፋይዳ በጉልህ የሚያስገነዝብ እውነታ በዚህ በደቡብ አፍሪካ ህያው የሆነ የታሪክ ትስስሩን ጠብቆ ቆይቷል፡፡
የዛሬው አንጋፋው የአፍሪካን ናሽናል ኮንግረስ ፓርቲ (African National Congress Party-ANC) መጸነስና መወለድ ምክንያት የሆነችው ሀገራችን ኢትዮጵያና፣ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካውያን የነፃነት ተጋድሎ ታሪክ ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የነበራትን ታሪካዊ ፋይዳና ጉልህ ድርሻ የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩት ታቦ እምቤኪ እ.ኤ.አ በ2010 ዓ.ም የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሴኔት በወሰነው መሰረት በሕግ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ በተሰጣቸው ጊዜ በዳረጉት ንግግር ቤተክርስቲያናችን በደቡብ አፍሪካውያን የነፃነት ተጋድሎ ታሪክ ውስጥ የነበራትን ጉልህ ድርሻ እንዲህ ነበር የገለጹት፡-

ዘመናዊው የአፍሪካ የነፃነት ንቅናቄ የመነጨው ወደ ፲፱ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ አካባቢ በደቡብ አፍሪካ ነበር፣ የዚህ ንቅናቄ የቀድሞ መስራቾች የሀገራችን የመጀመሪያዎቹ ዘመናዊ አፍሪካውያ ልሂቃን ናቸው፡፡ የተነሱትም ከአብያተክርስቲያናት ትምህርት ቤቶች ሲሆን፣ የመጀመሪያዎቹ አፍሪካውያን የቤተክርስቲያን አገልጋዮችም ነበሩ፡፡ እነዚህ ዘመናዊ የአፍሪካ ልሂቃን ከአውሮፓውያን ሚስዮኖች እራሳቸውን አላቀው በቤተክርስቲያናቱ ላይ ባለቤትነታቸውን ሲያውጁ፣ እነደመነሻ የተጠቀሙት የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በመዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፷፰ ላይ ይገኛል፤ ይህም፡- ‹‹መኳንት ከግብጽ ይመጣሉ፣ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች፡፡›› የሚለው ነው፡፡

እንደ ቅኝ ገዢዎች አፍሪካ የአውሮፓውያን የቅኝ ግዛት እሽቀድድም ሰለባ ሆና በኖረችበት ወቅት ኢትዮጵያ ነፃነቷን እንደያዘች መቀጠሏ መነሳሳትን ይሰጣቸው ነበር፣ እናም በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተተነበየው ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ስትዘረጋ ቤተክርስቲያናችን በአፍሪካዊ ስነ ምግባር ትሞላለች ብለው ያምኑ ነበር፡፡ ይህች እውነተኛ የአፍሪካ ቤተክርስቲን ደግሞ አፍሪካያን በሙሉ ለነፃነት፣ ለባህላቸው፣ ለልዑላዊነታቸው፣ ለማንነታቸውና ለሰብአዊነታቸው እንዲከበር ላላቸው ህልም እንደማከማቻ ቦታ ሆና ታገለግላለች ብለው ያምኑ ነበር፡፡ ታዲያ በዚህ እውነታ እና ታሪካዊ ሀቅ ላይ ተመስርተው ነበር እነዚህ የጠቀስናቸው ቤተ ክርስቲያናት እራሳቸውን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብለው የሰየሙት፡፡ በአህጉራችን ላይ የመጀመሪያው ዘመናዊ የብሔራዊ ንቅናቄ የሆነው የደቡብ አፍሪካው አፍሪካን ናሽናል ኮንግረስ ፓርቲ (ANC) የተወለደውም ከነዚሁ ከሀገራችን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ነው. . . የፓርቲያችን የመጀመሪያ ፕሬዝዳንት የነበሩት ቄስ ጆን ዱቤም የዚሁ የደቡብ አፍሪካ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መሪ ነበሩ… ፡፡[1]   

የመቶ ዓመቱ ባለዕድሜ የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ ፓርቲ (ANC) የነፃነት እንቅስቃሴ እና የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ፕሬዝዳንት የታቦ እምቤኪ ታሪካዊ ንግግር የሚነግረን ሐቅ ቢኖር ለሰው ልጆች ከፈጣሪ ለተቸረው ነፃነትና ክብር ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የነበራትን ጽናትና መንፈሳዊ ተጋድሎዋን ነው፡፡ ይሄ የቤተክርስቲያናችን መንፈሳዊ ተጋድሎና መልካም ስም ተጠብቆ እንዲቆይ እንዲሁም የቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልእኮዋ የሆነውን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቅዱስ ወንጌል ለሰዎች ሁሉ በቋንቋቸው ለማዳረስ ዛሬስ በዚህ ዘመን የምንገኝ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ኃላፊነት ምን ድረስ ሊሆን ይገባዋል የሚለውን ጥያቄ የመመለስ የሁሉም የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮችና ልጆች ኃላፊነት ነው፡፡

[1] www.unisa.com the speech of Tambo Mbeki at Addis Ababa University, 2010 and interview conducted with Father Diliza Valisa a Senior Priest and Oral Historian in the Ethiopian Orthodox Tewahido Holy Savior Cathedral (Johannesburg).

21 comments:

 1. ያቺ ቤተክርስቲያን አሁን አለች (Autocrat) ክፍሉ ማለቴ ነው

  ReplyDelete
 2. How nice is this? our religion contributed, contribute, and contributing to human freedom.

  ለሰው ልጆች ሁሉ ከፈጣሪ ዘንድ ስለተሰጠ ነፃነትና ክብር በግልጽ የምታሰተምረው ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን፡- ነፃነት የሰው ልጅ ከአምላኩ የተሰጠው ክብሩ መሆኑን ቅዱሳት መጻህፍትንም ዋቢ በማድረግ፣ የሰው ልጅ በታሪኩ ዘመን ለነፃነቱ የከፈለውን ክቡርና ውድ ዋጋ የእግዚአብሔርን ህዝበ ታሪክ በመጥቀስ በዘመኗ ሁሉ ስታስተምር ቆይታለች፤ አሁንም በማስተማር ላይ ነች፣ ወደፊትም እንዲሁ፡፡ ለዘመናት ሀገራችን በነፃነት ኮርታ የመቆየቷ፣ የህዝቦቿም አይበገሬነት ምስጢሩ ይኽው ቤተክርስቲያን ለሰው ልጆች ነፃነትና ክብር ካላት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ከሆነ አስተምህሮ የተነሳ ነው፡፡ ለጥቁር ህዝቦች ሁሉ ትልቅ ድልን ያጎናጸፈው የአድዋው ድል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ መንፈሳዊ ተጋድሎ፣ ጸሎትና ትልቅ የሆነ ታሪካዊ አሻራ ያለበት እንደሆነ በተለያዩ የውጭ ሀገርና የሀገራችን የታሪክ ምሁራንና ተመራማሪዎች ዘንድ ብዙ የተነገረለትና የተፃፈለት ነው፡:

  ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች

  ReplyDelete
 3. Thanks, Danie
  I was On the graduation ceremony and herd the president speech.

  ReplyDelete
 4. ?????????????????????

  ReplyDelete
 5. Thanks for sharing but the site seems broken. It directed me to a different site.Please put the exact link for the speech of Tambo Mbeki at Addis Ababa University, 2010. Thanks in advance.

  ReplyDelete
 6. በአህጉራችን ላይ የመጀመሪያው ዘመናዊ የብሔራዊ ንቅናቄ የሆነው የደቡብ አፍሪካው አፍሪካን ናሽናል ኮንግረስ ፓርቲ (ANC) የተወለደውም ከነዚሁ ከሀገራችን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ነው. . . የፓርቲያችን የመጀመሪያ ፕሬዝዳንት የነበሩት ቄስ ጆን ዱቤም የዚሁ የደቡብ አፍሪካ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መሪ ነበሩ… ፡፡[1]
  Mamush,MN

  ReplyDelete
 7. This is just 1+1=2
  but nowadays people do not believe this answer.

  For the this and coming generation this question means

  1+1=..... no answer ,

  People are unable accept the bold truth answer=2

  Thanks Dn Daniel.

  ReplyDelete
 8. yegaremale ewenate yamenagare ayasatane.ejachohe yebarake

  ReplyDelete
 9. Dn.Daniel Yetsafekew neger Yemayitabel haq bihonim qilu Bemetsehafe kidus lay "YOSEFIN YEMAYAWUKEW NIGUS TENESA HIZIBUNIM BEMEKERANA BECHINIK YIGEZACHEW JEMER" Endetebale zare bezemenachin Ye"EOTC"n Yemayawuk teweled ena mengist menesatun betekeresetiyanachininim bechibnik ena bemekera eyegefat mehonun lib yemil Yetefa Yimesilegnal. Enkuanis lewuchiw alem Yewuset mekidesochachinin mastedader eyakaten bebeg lemid lebash tekulawoch eyetebelan balenibet wokete ante kelay yetsafekewun sanebibi hazenina enba yekedimegnal. Kidusan yimetubat yeneberechiwu hagerachin aganinite Menafikan siworuat minun tesfa honech tilaleh? Egna Eyetefan leleloch endet enderisilachewalen tebilo yitasebal? Bicha Esu Amlak Kidusan hagerachinin ena betekeresetiyanachinin Yitebikilin Amen!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. the speech of Tambo Mbeki at Addis Ababa University


   http://www.diretube.com/full-speech/thabo-mbeki-received-an-honorary-doctorate-degree-from-aau-video_4b1cc50df.html

   Delete
  2. Ethiopia will govern the world.The time will come after the down fall of this government.

   Delete
 10. thank you, God please make our popes to be wise and think er to our church

  ReplyDelete
 11. ዳኔ በአለህበት ቦታ ሰላም ላንተ ይሁን::
  ስለ አኩስም ጽዩን መእመኑ ያለውን ስጋት በቅድሜያ በመገንዘብ ይመስላል ማጽናኛ ይሆነን ዘንድ የጻፍከው የቅርብ ግዚ ትውስታ ሲሆን:ይህ ደግሞ ይበልጥ አንገት ቀና የሚያስብል ነው:: የዋልድባ ገዳምስ ጉዳይ እንዲት ታየው አለህ ?

  ReplyDelete
 12. የሰበኩን ክርስትና አጥፊና ጎጂ ሆኖ ይመስልሻል የማታ ማታ ለባርነት የተዳረግን? አይደለም ክርስትና ማወናበጃ ክርስትና ማታለያ ሆኖ አልነበረም እዉነቱ ግን ነጮቹ ክርስትናን ወንጌልን መሣርያ አድርገዉ መሸፋፈኛ አድርገዉ ሊያዘናጉን መቻላቸዉ ነዉ ወንጌልን እንስበክ ብለዉ ገብተዉ ዉስጥ ገመናችንን ሊሰልሉ ሊያዉቁን ሊያጠኑንና ሊለያዩን በመቻላቸዉ ነዉ ርብቃ ዛሬም ዲሞክራሲማታለያ አጥፊና ጎጂ ሆኖ አይደለም ሚሥጥሩ ግን በዲሞክራሲ ሰበብ እርስ በርሳችን እየለያዩ እያጋጩ ማፋጀታቸዉ ነዉ ጆሞ ጆሞ ኬንያታ ከተፈሪ መክሮ ከቆንጆዎቹ መፅሀፍ የተወሰደ

  ReplyDelete
 13. www.aweineshet@yahoo.comFebruary 21, 2012 at 5:18 PM

  D. Danel betam lebn yminka neger new ynegrken EGZIABHER yseytanen fetna kegrh betach rasun ketkto ytalleh wondmachen fsamehn ysamrlh.

  ReplyDelete
 14. It's my first time to post my comment. Daniel, you know you're doing a great job.nothing is as worthy as giving access to information especially for those who are denied off.Africa is where this is true. Though Africa had become "free" of the 300yrs colony in the late 60s, the agonizing experience is as fresh as today's wound.we are paying the cost and we will continue to pay as long as we are not free from our own colonizers. these are the post colonization leaders who i think are the replicas of their godfathers(western colonizers)the brutality of these leaders is not ,by any measurement, less than from their godfather's, for they are hatched by the western colonizers' incubator.thus currently, Africa has faced two battles external and internal.TRUE FREEDOM can never be guaranteed with out TRUE,AIM FULL,TIMELY and SUSTAINABLE COMMITMENT. PEACE be upon you and upon those you love!

  ReplyDelete
 15. Thanks Dani for shairing this.yes while we remember the dids of fourfathes ,we must strive to maintain and increase teaching of our church in ever aspects of our society.

  ReplyDelete
 16. I doubt i mean the contribution of the Ethiopian Orthodox church to educate about freedom.I don't think so.

  ReplyDelete
 17. hello, dear Daniel and dear readers, i have never have any doubt about the contribution of Ethiopian Orthodox Church on the democratization of the country.indeed, weighing the contribution depends on our understanding of democracy.for some one who is curious , i personally suggest him/her to read history. at least he/she will find a paragraph that attests what the church has been doing. our forefathers who had not been as prejudice and factional as we, their children are, made use of the church/religion to mobilize and teach the public to fight for freedom.i would also suggest he/she to stop and have a glance at Abon Petros's statue erected around Georgis.as he/she is doing this, he/she faces undeniable fact. besides, the works of Ethiopian philosopher, Zeryako had been a landmark ,on the history of Ethiopian philosophy ,not only for the church but for the country.but it is a pity to learn that only few Ethiopians know about his work, especially none-orthodoxes Ofcours, i believe the church could have done much better. in this respect, enough has not been done as compare to the power the church has had especially now due to various things.however, what is good for all of us is to put off our glasses of prejudice and give the due credit for everything regardless of our idealogical and other differences.that is a great lesson we failed to learn from our forefathers.
  Peace be upon you and upon those you love

  ReplyDelete