በታክሲ እየሄድኩ ነው፡፡ መካከለኛው ወንበር ነው የተቀመጥኩት፡፡ አንዲት ሴትዮ በስልክ በንዴት ያወራሉ፡፡ በጩኸታቸው መጨረሻ «እንዲያውም ካሁን በኋላ ካንተ ጋር መኖር አልችልም፤ በቃ» ብለው ዘጉት፡፡ በታክሲ ውስጥ የነበርነው ሁሉ በድንጋጤ እያየን ነበር ያዳመጥናቸው፡፡
ወዲያው አንዱ ቀልደኛ «እናቴ ይህንን በቃ የሚል ቃል እንኳን ቢተውት፤ ሌላ ትርጉም ያመጣል» ሲል ሁላችንም ከድንጋጤው ወጥተን ሳቅን፡፡
ስልኩን ሲጨርሱ ሁላችንም ወደርሳቸው መዞራችንን ሲያዩ ደንገጥ አሉ፡፡ አጠገባቸው ተቀምጠው የነበሩት አዛውንትም ፈገግ አሉላቸው፡፡
«ልጄ ልበልሽ ወይስ እናቴ?» አሉ አዛውንቱ በነጭ ሪዛቸው ውስጥ ፈገግታቸውን እያሳዩ፡፡
«ኧረ ልጄ ይበሉኝ» አሉ ተናደው የነበሩት ሴትዮ
«በጣም ጥሩ» አሉና አዛውንቱ ከወንበራቸው ላይ ተመቻቹ፡፡
«እይውልሽ በጣም ስትናደጅ እና በጣም ስትደሰች እባክሽ ውሳኔ አትወስኝ» አሏቸው፡፡ የሁላችንም ጆሮ ወደ አዛውንቱ አቀና፡፡
«ቅድም እየተናገርሽ አልነበረምኮ፣ እየጮኽሽ ነበር፡፡ ጩኸት እና ንግግር ይለያያሉ፡፡ መናገር ተረጋግቶ፣ አስቦ፣ ውጤቱን አስልቶ ነው፡፡ መጮኽ ግን አፍ እንዳመጣ ነው፡፡» አሏቸው፡፡
«አሁን ምን እንደተናገርሽ ብጠይቅሽ አታስታውሽውም፤ ምክንያቱም አንደበትሽ ሳይሆን ምላስሽ ብቻ ነበራ የሚናገረው»
«በአንደበት እና በምላስ መካከል ልዩነት አለ እንዴ» አለች አንዲት ወጣት፡፡ሌሎችም ራሳቸውን ነቀነቁ፡፡
«ምላስ እና አንደበትማ ይለያያል፡፡ ምላስ ማለት ይቺ ቅልብልቢቱ ናት፡፡» አሉና ምላሳቸውን አውጥተው አቅለበለቧት፡፡ ሁላችንም ሳቅን፡፡ ሾፌሩ በተለይ ከልቡ ሲስቅ ጊዜ፡፡ «ሾፌር ይኼ ጨዋታ አንተን አይመለከትም ዝም ብለህ ንዳ» አሉት፡፡
«ይቺ እንዳ መጣላት የምትለፈልፈው ናት ምላስ፡፡ አንደበት ግን ልብ አውጥቶ አውርዶ ያቀበለውን ለሰሚው የሚናገረው ነው፡፡ አንደበት ምላስን ይጨምራል፤ ምላስ ግን አንደበትን አይጨምርም» አሉ፡፡ ይኼ እኔ በሥነ ልሳን ከተማርኩት የተለየ ፍልስፍና ነው ብዬ መከታተል ቀጠልኩ፡፡
«ታድያ ሰው ሲናደድ ወይንም ሲደሰት ምንድን ነው ማድረግ ያለበት?» አላቸው አንደኛው፡፡
«ቢቻል ዝም ቢል መልካም ነው፤ »
«ካልቻለስ»
«ካልቻለ ደግሞ ውሳኔ የሌለው ነገር መናገር፡፡»
«ለምሳሌ ምን ዓይነት?»
«አየህ ልጄ እጅግ በጣም በተደሰትክ ጊዜ የምትወስነውን ቀርቶ የምትናገረውን አታውቀውም፡፡ ስሜት መንፈስን ይጫነዋልና፡፡ ስሜት መንፈስን ከተጫነው ደግሞ ልቡና አይሠራም፡፡ በል በል አድርግ አድርግ የሚል ነው የሚመጣብህ፡፡ ስለዚህ ምንም አለመወሰን ነው፡፡ እነዚህ ገንዘብ የሚሰበስቡ ሰዎች ምን እንደሚያደርጉ ታውቃላችሁ?» ብለው ሲጠይቁ አናውቅም በሚል ስሜት ሁላችንም አየናቸው፡፡
«የሚያደርጉትኮ ሁላችንም እንድንደሰት ወይንም እንድናዝን ማድረግ ነው፡፡ ስሜታችንን መቀስቀስ ነው፡፡ ያን ጊዜ እኛ እጅግ በማዘንም ሆነ እጅግ በመደሰት ይህንን ያህል እንሰጣለን ብለን ቃል እንገባለን፡፡ ታድያ አንዳንዱ ሰው ስሜቱ ተረጋግቶ መንፈሱ ሲያንሠራራ ምን ነክቶኝ ነው ይላል፡፡ ለዚህ ነው ስትደሰቱ ወይንም ስታዝኑ አትወስኑ ያልኳችሁ፡፡
«ግዴላችሁም አሳልፉት፡፡ ንዴት ዘላቂ አይደለም፡፡ ደስታም ጊዜያዊ ነው፡፡ ሰው አንድን ነገር ከመናገሩ በፊት አምስት ነገሮች ያስፈልጉታል፡፡»
«ምን ምን» አልናቸው፡፡
«የቀደመ ዕውቀት፣ የቀደመ ልምድ፣ ያለበት ሁኔታ፣ የሚያመጣው ውጤት እና መፍትሔው መናገር ነው ወይ?» የሚሉት ናቸው፡፡
«ይተንተኑ» አለ ሾፌሩ በንግግራቸው ተስቦ፡፡
«ስለምትናገረው ነገር ታውቃለህን? ወይስ እንዳመጣልህ ነው የምትናገረው? ይኼ ወሳኝ ነው፡፡ አንተ ይህንን ለመናገር ዕውቀታዊ ሥልጣን አለህ? ይኼ መመለስ አለበት፡፡ ወዳጄ ስለማያውቁት ነገር መናገርና ስለሚያውቁት ነገር ዝም ማለት አንድ ናቸው፡፡
«በዚያ ጉዳይ ላይ ከዚህ በፊት ልምድ አለህ? እንደዚያ ተናግረህ ነበር ካሁን ቀደም? ታድያ ምን ገጠመህ? በሌሎች ሰዎችስ ምን ተማርክ? በጉዳዩ ላይ ምን ልምድ አለህ? ይህንን መልስ፡፡
«ለመሆኑ አሁን ያለህበት ሁኔታ ይህንን ነገር የሚያናግር ነው? እስኪ አስብበት፡፡ ታክሲ ውስጥ ነህ? አውቶቡስ ውስጥ ነህ? ቢሮ ነህ? ቤተ ክርስቲያን ነህ? ብቻህን ነህ? ከሰዎች ጋር ነህ? ደስ ብሎሃል? ከፍቶሃል? ርቦሃል? ጠግበሃል? ቸኩለሃል? ታምመሃል? ቸግሮሃል? ሁኔታህ ንግግርህን ይወስነዋል፡፡ አሁን ቅድም እኅቴ የተናገረችው ነገር ታክሲ ውስጥ የሚነገር አይደለም፡፡ ከሰውዬው ጋር ለብቻ ማለቅ ያለበት ነው፡፡
«ሁኔታዎቹ ገፋፍተውኝ ነው የሚል ሰው አልሰማችሁም? ሊገፋፉትኮ ይችላሉ፡፡ ጥያቄው ለምን እርሱ በዚያ ሁኔታ ይናገራል? ልቡን የሚገፋው ሲያገኝ ከተናገረማ ጀርባውን የሚገፋው ሲያገኝ ገደል ይገባል ማለት ነው፡፡ የሚገፋፋ ነገር ካለው ማቆም ነው፡፡
«መናገር ለውጤት መሆን አለበት፡፡ እገሌ ተናጋሪ ነው ለመባል፣ የንግግር ችሎታን ለማሳየት፣ እንዴው መለፍለፍ አመል ስለሆነ፣ በሞቅታ ወይንም ተናግሮ አናጋሪ በመኖሩ መሆን የለበትም፡፡
«አስበን እንናገር፤ ወይንም ካላሰብን አንናገር፡፡ ምንም ሃሳብ ከሌለን ዝምታ ከንግግር በላይ ነው፡፡ በእያንዳንዱ ንግግር መካከል የዝምታ ጊዜ ያስፈልጋል፡፡ የዝምታ ጊዜ ማለት የማሰቢያ ጊዜ ማለት ነው፡፡ የታደሉት በአንደበታቸው ሲናገሩ በውስጣቸው ታላቅ ዝምታ አለ፡፡ ለማሰቢያ የሚሆን ዝምታ፡፡
«ከበሮ በሚገባ ለምን ይጮኻል፡፡ የሚጮኽ እና የማይጮኽ ነገር ስላለው ነው፡፡ በከበሮው ግራ ቀኝ የተወጠረው ቆዳ ይጮኻል፡፡ በከበሮው ዙርያ የተገጠመው እንጨት ደግሞ ዝም ይላል፡፡ የከበሮው ድምጽ ከዝምታው መካከል ስለሚመነጭ ልዩ ነው፡፡ ሰውም ዝምታ እና ንግግር በአንድነት ያስፈልጉታል፡፡
አረጋዊው ዝም አሉ፡፡ ምናልባትም እርሳቸው ራሳቸው ዝምታን ሊያሳዩን ይሆናል ብዬ አሰብኩ፡፡
«አምስተኛው ነጥብ ይቀራል» አለ ከጎናቸው የነበረ ተሳፋሪ
«ሞት ይርሳኝና ረሳሁት» አሉና ቀጠሉ፡፡ «አንዳንዱ ነገር በመናገር የማይፈታ አለ፡፡ ወይንም መፍትሔው መናገር ያልሆነ፡፡ ምናልባትም መፍትሔው ዝምታ ሊሆን ይችላል፡፡ ጸሎት ሊሆን ይችላል፡፡ ወደ ሕግ መሄድ ሊሆን ይችላል፡፡ ለሚመለከተው ማመልከት ሊሆን ይችላል፡፡ ተግባር ሊሆን ይችላል፡፡ ታድያ በመናገር ለማትፈታው ነገር ለምን በመናገር ትደክማለህ?»
«በሉ አንድ ታሪክ ነግሬያችሁ ልውረድ፤ እዚሁ ልታስቀሩኝኮ ነው፡፡» ፈገግ አሉ በነጩ ሪዛቸው መካከል፡፡
«በድሮ ጊዜ አንድ ሰው ጥፋት ያጠፋና ዳኛ ፊት ይቀርባል» ሁላችንም የተመካከርን ይመስል በአንድ ላይ «እሺ» አልናቸው፡፡
«ታድያ ዳኛው ሦስት ዓይነት የቅጣት ምርጫ አቀረቡለት፡፡ አንድ ኪሎ ሽንኩርት እየላጠ መብላት፣ አንድ መቶ ጅራፍ መገረፍ፣ ወይንም አምስት መቶ ብር መክፈል፡፡ ሰውዬው ለማሰብ የሚሆን ልቡና የሌለው ነበርና የመጀመርያ ምርጫ ሆኖ ስላየው ብቻ «ሽንኩርቱን እበላለሁ» አላቸው፡፡
«ቀረበለት አንድ ኪሎ ሽንኩርት፡፡ ገና አንድ ሁለት መብላት ሲጀምር ዓይኑ ማልቀስ ለሐጩም መዝረብረብ ጀመረ፡፡ አልቻለም፡፡ ከመቀመጫው ተስፈንጥሮ ተነሣና፡፡
«መቶ ጅራፍ መገረፍ ይሻለኛል» አላቸው፡፡ ወዲያው ኃይለኛ ገራፊዎች ተጠሩና እየተፈራረቁ ይለበልቡት ጀመር፡፡ ግማሽ እንደደረሰ አልቻለም፡፡ እጁን ወደ ላይ አነሣ፡፡
«እህሳ» አሉት ዳኛው፡፡
«አልቻልኩም» አላቸው፡፡
«ታድያ ምን ይሻላል» አሉት እየሳቁ፡፡
«በቃ አምስት መቶ ብሩን እከፍላለሁ» አለ ከተኛበት እየተነሣ፡፡
«ያንተ ትልቁ ጥፋት መጀመርያ ወንጀል መሥራትህ ብቻ አይደለም፡፡ ማሰብ አለመቻልህ እንጂ፡፡ ምናለ አስበህ ከሦስቱ አንዱን ብትመርጥ ኖሮ፡፡ እኔ ከሦስቱ አንዱን እንድትቀጣ ነበር የወሰንኩት፡፡ አንተ ግን መናገር እንጂ ማሰብ ባለመቻልህ ሦስቱንም ተቀጣህ፡፡» አሉት፡፡
«ወዳጆቼ ሳያስቡ እንዳመጣ መናገር አንዱን ችግር ሦስት እጥፍ ያደርገዋል፡፡»
አሉና ወረዱ፡፡ አንዳንዶቻችን ወረድን፡፡ ሌሎች በታክሲው ቀጠሉ፡፡ አንዳንዶችም ከአረጋዊው ጋር ከታክሲው በኋላም ጨዋታ ሳይቀጥሉ አይቀሩም፡፡ እኔ ግን የተናገሩትን ነበር የማመላልሰው፡፡
nice article Dn.Dni.Igiziabher yibarkih
ReplyDelete«እይውልሽ በጣም ስትናደጅ እና በጣም ስትደሰች እባክሽ ውሳኔ አትወስኝ» አሏቸው፡፡ የሁላችንም ጆሮ ወደ አዛውንቱ አቀና፡፡
ReplyDeletethank you bro
Dear Daniel,
ReplyDeleteThis is really a very wonderful intervention. Since my childhood I do remember a couple of sayings like think before you speak, measure twice and cut once, and others. Actually, it would be better to shut our mouth and open our mind. Our silence make others silent too. Besides, it is true, "If you keep your mouth shut, the flies won't get in."
What I am impressed by your intervention is that:
ስትደሰቱ ወይንም ስታዝኑ አትወስኑ፡፡ «ግዴላችሁም አሳልፉት፡፡ ንዴት ዘላቂ አይደለም፡፡ ደስታም ጊዜያዊ ነው፡፡ ሰው አንድን ነገር ከመናገሩ በፊት አምስት ነገሮች ያስፈልጉታል፡፡» «የቀደመ ዕውቀት፣ የቀደመ ልምድ፣ ያለበት ሁኔታ፣ የሚያመጣው ውጤት እና መፍትሔው መናገር ነው ወይ?» የሚሉት ናቸው፡፡
«ያንተ ትልቁ ጥፋት መጀመርያ ወንጀል መሥራትህ ብቻ አይደለም፡፡ ማሰብ አለመቻልህ እንጂ፡፡ ምናለ አስበህ ከሦስቱ አንዱን ብትመርጥ ኖሮ፡፡ እኔ ከሦስቱ አንዱን እንድትቀጣ ነበር የወሰንኩት፡፡ አንተ ግን መናገር እንጂ ማሰብ ባለመቻልህ ሦስቱንም ተቀጣህ፡፡» አሉት፡፡ «ወዳጆቼ ሳያስቡ እንዳመጣ መናገር አንዱን ችግር ሦስት እጥፍ ያደርገዋል፡፡»
ልቡን የሚገፋዉ ሲያገኝ ከተናገረ ጀርባዉን የሚገፋዉ ሲያገኝ ገደል ሊገባ ነዉ ::ድንቅ አባባል ነዉ እግዚአብሄር ያበርታህ ዳኒ በታም አስተማሪ ነዉ ::
ReplyDeleteሶፎኒያን
it is a nice article Dane K/w yasmalen
ReplyDeleteKidanmariam
እኔ ግን የተናገሩትን ነበር የማመላልሰው፡፡
ReplyDeleteAstmary new Egizabher yebarkih
ReplyDeleteወዳጆቼ ሳያስቡ እንዳመጣ መናገር አንዱን ችግር ሦስት እጥፍ ያደርገዋል፡፡»
ReplyDeleteወዳጆቼ ሳያስቡ እንዳመጣ መናገር አንዱን ችግር ሦስት እጥፍ ያደርገዋል፡፡» thank you dani
ReplyDeletethanks! KHY
ReplyDeleteአሪፍ ምክር ነው:: ትእግስትን የሚያክል ትልቅ ነገር ምን አለ? ንዴትም ማለፉ ላይቀር ከመተዛዘብ ትንሽ ታጋሽ መሆን ይጠቅማል::
ReplyDeleteI found the following English proverb too.
Don’t promise when you’re happy, Don’t reply when you’re angry, & Don’t decide when you’re sad.
Tnxs Daniel!
greate
Deleteየታደሉት በአንደበታቸው ሲናገሩ በውስጣቸው ታላቅ ዝምታ አለ፡፡ ለማሰቢያ የሚሆን ዝምታ፡፡
ReplyDeleteit is very nice thank you our brother d.daniel
ReplyDeletedersobeghal
ReplyDeleteአኔ በራሴ ላይ ያለ ችግር ነው አስቦ አለመናገር
ReplyDeleteዲነን እግዚያብሄር ይባርክሀ..
"ልቡን የሚገፋው ሲያገኝ ከተናገረማ ጀርባውን የሚገፋው ሲያገኝ ገደል ይገባል ማለት ነው፡፡ የሚገፋፋ ነገር ካለው ማቆም ነው፡፡....አስበን እንናገር፤ ወይንም ካላሰብን አንናገር፡፡ ምንም ሃሳብ ከሌለን ዝምታ ከንግግር በላይ ነው፡፡ በእያንዳንዱ ንግግር መካከል የዝምታ ጊዜ ያስፈልጋል፡፡ የዝምታ ጊዜ ማለት የማሰቢያ ጊዜ ማለት ነው፡፡" mekari abat ayasatan dani tiru tsehuf new berta dingel tetbekeh
ReplyDeletewow thx very nice article god bless u
ReplyDeleteeminager mlas bicha sayhon emiyastewl lbona yadlen .thank you wendmachin !!!
ReplyDeleteWoW, It is good analysis.
ReplyDeleteIt is really touched. And It will be a lesson for our life. The premature decision because of our sadness or anger and unlimited happiness will expose for unnecessary commitment or full of risk to our life.We should learn about anger management and the over control of our happiness. Unless we can proceed this things, we played the lose game.
Haileyesus, Debremarkos University
dn.Daniel!! berta bezu gize ye MESEHAF QEDUS temehrtehen ektatlalhung aderahen berta.bterefe betaaam temehert,astesaseb,tegestena,maseben yemiyastemer sehof new. bahunu zemen lemnenor sewoch betely lenga ETHIOPIAN ytefaben endenzih abatoch masebena mastawel zeg belo menoren weyem be hywet gudan eyzgemo mehidu new. ahunem yenezihen abatoch aynet be ETHIOPIAM meder ketina,edmi gar HYALU AMLAKACHEN yabzalen. engam ye ETHIOPIA lijoch ye hywet tebeb mengedun FETARYACHEN yadelen:: ETHIOPIA LEZELALEM TENUR!!
ReplyDelete«ወዳጆቼ ሳያስቡ እንዳመጣ መናገር አንዱን ችግር ሦስት እጥፍ ያደርገዋል፡፡» people including me need this so badly
ReplyDeletenigigir eko kal new KAL degmo ayimotim Yitebikula enji. Libetu tefach enji yetemare molto nebere.
ReplyDeleteልቡን የሚገፋው ሲያገኝ ከተናገረማ ጀርባውን የሚገፋው ሲያገኝ ገደል ይገባል ማለት ነው፡፡
ReplyDeleteI really thank you dani. I love this post
ReplyDeleteትልቅ ትምህርት ነው፤፤ላነበበው ሳይሆን ላስተዋለው
ReplyDeleteልብ ያለው ልብ ይበል፤ ጆሮ ያለው ይስማ.....በጣም ግሩም ድንቅ ምክር ነው። እግዚአብሔር ይስጥልን!
ReplyDeleteዲ ዳኒ እንደዚህ አይነት ጽሑፎችህ በጣም አዝናኝና አስተማሪ ናቸው እና እግዚአብሔር ፍጻሜህን ያሳምርልህ። ከነ ቤተሰብህ ከክፉ እምአምላክ ትጠብቅህ።አሜን!
ReplyDelete-ልቡን የሚገፋው ሲያገኝ ከተናገረማ ጀርባውን የሚገፋው ሲያገኝ ገደል ይገባል ማለት ነው፡፡
ReplyDelete-ስትደሰቱ ወይንም ስታዝኑ አትወስኑ፡፡
-ወዳጆቼ ሳያስቡ እንዳመጣ መናገር አንዱን ችግር ሦስት እጥፍ ያደርገዋል፡፡
02/14/2012 @1:09PM
dn yezare meseganaye lajorohe nawe
ReplyDeleteዝምታ..... በደህናው ጊዜ ብቻ ሳይሆን በመከራ ጊዜ ሳይቀር ክርስቶስ ዝም ማለትን አስተምሮናል:: ቅዱሳን አባቶቻችን ደግሞ ከአባታቸው የተማሩትን አርምሞን ገንዘብ አድርገው ለቅድስና በቁ የእግዚአብሔርንም መንግሥት ወረሱ:: ትዕግሥት....የመንግስተ ሰማያት መክፈቻ ቁልፍ...የማህበራዊ ሕይወት ዋስትና ...የትዳር መሠረት...የሕይወት ጣዕም.....ሁሉም ነገራችን...
ReplyDeleteDaniye...Minim alilihim endew egziyabiher edime ena tenawun yisitih...Aderahin enezihin yimitisifachewun wegoch mechem endatakuarit...Erasen wekiye new yeminagerew...Behiwete lay liyu tirigum eyametulign new.....Abet lee ende ene aynetu besidet lay lalew wegene ema....
ReplyDeleteEthiopiyaye Lezelalem nuri...
From Italy
Kale hiwot yasemalen...Egziabher yagelegelot zemenehen yebarkew
ReplyDeletegita edmi ena tina ysth
ReplyDeleteyes, kemenegerik befit soste asib ybalal.
ReplyDeletemelkam timihirt eyetemarku new.
thanks, dani.
Aychew.
ዉድ ወንድማችን ዳኒ እጅግ በጣም አስተማሪ መልእክት ነዉ ፡፡ እግዚአብሐር ይባርክህ፡፡
ReplyDeleteአምላክ ኢትዮጵያን ይባርክ፡፡
ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡
ReplyDeleteበእውነት እኔም ብሆን ሽንኩርት እየላጥኩ መብላቱን ነበር የምመርጠው፡፡
ትልቅ ትምህርት !
ከበሮ በሚገባ ለምን ይጮኻል፡፡ የሚጮኽ እና የማይጮኽ ነገር ስላለው ነው፡፡ በከበሮው ግራ ቀኝ የተወጠረው ቆዳ ይጮኻል፡፡ በከበሮው ዙርያ የተገጠመው እንጨት ደግሞ ዝም ይላል፡፡ የከበሮው ድምጽ ከዝምታው መካከል ስለሚመነጭ ልዩ ነው፡፡ ሰውም ዝምታ እና ንግግር በአንድነት ያስፈልጉታል፡፡
ReplyDeleteMamush,mn
ቃለ ህይወት ያሰማልን!
ReplyDeleteThanks .GOD weth you
ReplyDeleteI like the KEBERO analogy
ReplyDelete«አስበን እንናገር፤ ወይንም ካላሰብን አንናገር፡፡ ምንም ሃሳብ ከሌለን ዝምታ ከንግግር በላይ ነው፡፡ በእያንዳንዱ ንግግር መካከል የዝምታ ጊዜ ያስፈልጋል፡፡ >> ዳንኤል ክብረት
ReplyDeleteተባረክ ዳኒ!
ReplyDeleteአይሁዳውያን በናዚ የደረሰባቸውን ጭፍጨፋ ዓለም Holocaust ብሎ ይጠራዋል፡፡ የቃሉ መነሻ ጽርዕ (ግሪክ) ሲሆን የሚቃጠል መሥዋዕት (burnt offering) የሚል ትርጉም ይይዛል፡፡ የሚያመለክተውም በብሉይ ኪዳን የነበረውን ከመሥዋዕቱ አንዳችም ሳይተርፍ ሙሉ በሙሉ ለአዶናይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ነው፡፡ ልክ እንደዚሁ የናዚዎች ጥረት አይሁዳውያን አንድም ዘር ሳይተርፋቸው እንዲጠፉ የማድረግ ስለነበር ዓለም ይህንን ጭፍጨፋ Holocaust ብሎ ጠራው፡፡ አይሁዳውያን ግን ይህንን ቃል አልተቀበሉትም፡፡ ምክንያታቸውም “መሥዋዕት ስለአንዳች ጉዳይ ለአምላክ የሚቀርብ ነገር ነው፡፡ በእኛ ላይ የደረሰው ግን የትኛውም ምክንያታዊ አእምሮ ምንም ዓይነት ምክንያት ሊያቀርብለት የሚችል አይደለም፡፡ እንደዚያ ዓይነት መሥዋዕት የሚቀበል አምላክም የለም፡፡” የሚል ነው፡፡ ነገር ግን የደረሰባቸውን ነገር ሁሉ ጠቅልለው የሚጠሩበት አንድ ቃል አላቸው፡- “ሸቫ” ወይም “ሸዋ” ይሉታል፡፡ ትርጉሙም “ዝምታ” ማለት ነው፡፡ ዝምታም ይናገራል- ያውም ከንግግር ባይበልጥ፡፡
«ግዴላችሁም አሳልፉት፡፡ ንዴት ዘላቂ አይደለም፡፡ ደስታም ጊዜያዊ ነው፡፡ ሰው አንድን ነገር ከመናገሩ በፊት አምስት ነገሮች ያስፈልጉታል፡፡»
ReplyDelete«ምን ምን» አልናቸው፡፡
«የቀደመ ዕውቀት፣ የቀደመ ልምድ፣ ያለበት ሁኔታ፣ የሚያመጣው ውጤት እና መፍትሔው መናገር ነው ወይ?» የሚሉት ናቸው፡፡
"ዝምታ ጸሎት ሊሆን ይችላል..."!!! እርግጥም ትልቁ ዝምታ ጸሎት ነው!!! እኔም በዚህ ዝምታ ወስጥ ሁኘ ለዚህ ገራሚ ጦማሪ እድሜ..ጤና እና ጥበብን ይሰጠው ዘንድ እተጋለሁ!!! ዳኒ ከሚጮሁብህ ሰውሮ የሚናገሩህን ያኑርልህ! ኡህህህህህህ እረክቻለሁ!
ReplyDeleteThank you. I found my self very talkative lately. And the other day i was asking my self what did i get from all those talks ? But it is very hard to get back to old me. I was very quite. and i say from my experience a person who knows where to talk and what to talk is a very wise person. Unlike of me!!! Thank you again and please pray for me to get my sense back! Please!!!
ReplyDeleteWhat an article, God bless U
ReplyDeleteእናመሰግናለን ዲያቆን.ቃለ ህይወት ያሰማልን
ReplyDelete"ትናንንሽ ጆሮዎችና ትልቅ አፍ ያለበት.."..ያልከውን አስታወሰኝ : እንደባለ አእምሮ የሚያስብ ትውልድ አዛውንቱ ተጠምተዋልና እርሱን አይንፈገን:..ቀሪው ሂሳቡን እኛ እንከፍላልን:መልካም ጉዞ ዲ.ዳንኤል::W.E.B. DuBois@florida.
ReplyDeleteThank u sooooo much
ReplyDeleteDan Really what a wonderful view? I want to quote some of the most expressible & powerful parts(statements) to rehearse and use them in building my ethical personality as usual. However, I can’t. Since each and every word, at least sentences have inexpressible meaningful message. It is so difficult to distinguish one from another, as each constitute wonderful truth. So I used to read it time after time like Wudassie Mariam. መጽሐፉ ግን “አንደበት እሳት ነው” ብሏል… እዚህ ግን የአንደበት ቦታ ለምላስ ተሰጥቷልና..
Deleteit's a novel not real story but,a worth a worth to learn from keep up Danny!
ReplyDeleteThank you for this fruitful article... I have personally learned a great deal from it.
ReplyDeletePlease keep it up.
Personally I have this problem keweseniku behuwala metsetseti leka yihi yemihonew benezihi hulet mikinayetochi new medesetina mazeni ewineti New bekiribu me shegeri radio endetikis yewesedikuti tikisi neberi kemekuretihi befiti 9 gize leka leka yemili neberi salakew bedingeti leka yihe gudaye biye bewisite yizew yebeberewina zare gin bekagn biye yasenabetikuti zaremi adis hono bewisiti yimelalesali leka mikunayetu siwesin betami azigne sileneberi endihum 9 gize salekaw keriche neberi leka
ReplyDeleteAmeseginalehu dear Dakon Daniel
I really admire ur point of
ReplyDeleteView Daniel pleas keep it up
God bless you & yours
I really admire ur point of
ReplyDeleteView Daniel pleas keep it up
God bless you & yours